በአሁኑ ጊዜ አራት ዓይነት ኢትዮጵያውያን አለን፡፡
1. ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ፤ ኢትዮጵያም በእነርሱ ውስጥ ያለች
እነዚህ ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ያለችው ኢትዮጵያ ልዩ ናት፡፡ በሀገራቸው ውስጥ ሆነው፣ ችግሯን እና
መከራዋን ሁሉ አብረው ተቀብለው፤ ቢያዝኑም ሳይማረሩባት የሚኖሩ ናቸው፡፡ አቡነ ሺኖዳ «በአካል
ካለችው ልብ በልባችን ውስጥ ያለችው ልብ ትበልጣለች» እንዳሉት በእነዚህ ኢትዮጵያውያን ውስጥ
ያለችው ኢትዮጵያም ታላቅ ናት፡፡ በቀበሌው፣ በአስተዳደሩ፣ በአመራሩ፣ በአሠራሩ፣ በኢኮኖሚው፣ በኋላ
ቀርነቱ ወዘተ ምክንያት በሚደርሰው ነገር አይለኳትም፡፡ እዚህ በዓይናቸው የሚያዩት ገጽታ በውስጣቸው
ያለችውን ኢትዮጵያ ገጽታ አይቀይርባቸውም፡፡ የእነርሱ ኢትዮጵያ ታላቅ ናት፤ ኩሩ ናት፤ ጀግና ናት፤ ነጻ
ናት፤ ውብ ናት፤ ፍቅር ናት፤ ሥልጡን ናት፡፡ ሲሠሩ፣ ሲደክሙ፣ ሲያለሙ፣ ሲሠው፣ ሲከፍሉ፣ በልባቸው
ላለቺው ኢትዮጵያ ነው፡፡ በሚያዩዋት ኢትዮጵያ እንጂ በልባቸው ባለቺው ኢትዮጵያ አይማረሩም፡፡
2. ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ፣ ኢትዮጵያ ግን በእነርሱ ውስጥ የሌለች
እነዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ አሉ፡፡ አንዳችም የኢትዮጵያ ጠባይ፣ ባህል፣ ፍቅር፣ ክብር፣ አመል፣ ስሜት፣
ወኔ፣ ቅንዐት በልባቸው ውስጥ የለም፡፡ ለእነርሱ ኢትዮጵያ መልክዐ ምድር ብቻ ናት፡፡ ቦታ ብቻ ናት፡፡
በሰሜን ኤርትራ፣ በደቡብ ኬንያ፣ በምዕራብ ሱዳን፣ በምሥራቅ ሶማልያ እና ጂቡቲ የሚያዋስኗት ሀገር
ብቻ ናት፡፡ አለቀ በቃ፡፡ ኢትዮጵያ ብትወድቅ ብትነሣ፣ ብትሞት ብትድን፤ ቢያልፍላት ባያልፍላት፣
ብታድግ ብትደኸይ አይገዳቸውም፡፡ ሊጠቅሟት ሳይሆን ሊጠቀሙባት ብቻ ይፈልጓታል፡፡ ስለ እነርሱ
እንድትኖር እንጂ ስለ እርሷ እንዲኖሩ አይፈልጉም፡፡ ለእርሷ አይሠውም፤ ለእነርሱ ግን ይሠውዋታል፡፡
3. ከኢትዮጵያ የወጡ፣ ኢትዮጵያ ግን ከእነርሱ ልብ ያልወጣች፣
እነዚህ ደግሞ ወደውም ሆነ ሳይወዱ ከሀገር የወጡ ናቸው፡፡ በአካል ከሀገር ርቀዋል፡፡ በልባቸው ግን
ኢትዮጵያን ፀንሰዋል፡፡ ደማቸው፣ ጠባያቸው፣ እምነታቸው፣ ዐመላቸው፣ ባህላቸው፣ ስሜታቸው ኢትዮጵያ
ውስጥ ነው፡፡ ስሟን ሲሰሙ አንዳች ነገር እንደ ኤሌክትሪክ ይነዝራቸዋል፡፡ ልጆቻቸውን፣ ቤታቸውን፣
አቆጣጠ ራቸውን፣ ሃሳባቸውን፣ ምኞታቸውን፣ ጸሎታቸውን ሁሉ ኢትዮጵያኛ አድርገውታል፡፡ ለእነርሱ የጊዜ
ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ቀን ነፍሳቸውም ሥጋቸውም እዚያው ኢትዮጵያ ትኖራለች፡፡ ቢሞቱ እንኳን ሥጋቸው
እንዲመለስ ይፈልጋሉ፡፡
4. ከኢትዮጵያ የወጡ፤ ኢትዮጵያም ከእነርሱ ልብ የወጣች
እነዚህ ደግሞ የሚኖሩትም ውጭ ነው፤ ኢትዮጵያም ከእነርሱ ወጥታለች፡፡ ምናልባትም መልካቸው ብቻ
ካልሆነ በቀር አንዳችም ከሀገራቸው ጋር የሚያመሳስላቸው ነገር በዲኤን ኤ እንኳን ላይገኝ ይችላል፡፡
ለእነርሱ ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ የምትገኝ አንዲት ሀገር ናት፡፡ በቃ፡፡ ብትኖር ብትሞት ስሜት አይሰጣቸውም፡፡ አይኖሩባትም፤ አትኖርባቸውም፡፡ «ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ፣ ባላስብሽ ምላሴ ከትናጋዬ
ትጣበቅ» የሚል ምሕላ የላቸውም፡፡ ኢትዮጵያን ከልባቸው ማውጣት ብቻ ሳይሆን ከልጆቻቸው ልብ
አንዳትገባም አድርገዋታል፡፡
በዓለም ባሉ ቋንቋዎች ሁሉ ሁለት ቃላትን መተርጎም ከባድ ነው ይባላል፡፡ «ፍቅር እና ሀገር»፡፡ ልብ
እንጂ ቃል አይተረጉማቸውምና፡፡
እኛስ ከየትኞቹ ወገን ነን?
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
በፊደል አስር
የዛሬው የሽልማት ጥያቄ
በመጀመሪያ የተኮሳት ጥይት ኢላማውን ሳተች።ሁለተኛይቱ የቀኝ ክንድ መታች ሦስተኛዋም ባከነች አራተኛዋም ተሰለሰች አምስተኛዋ የግራ ክንድ መታች።የተሰጡት ጥይቶች አለቁ ።ወጣቱ በንዴት እየጤሰ ስናድሩን ከድግኑ ቀና አደረገናበትልቅ ደጎራ ስር ተተክሎ የነበረውን የከብት ግንባር አጥንት በጥላቻ ተመለከተው............
ይህ ጽሑፍ ከየትኛው መጽሐፍ የተወሰደ ነው ?? ደራሲው ማን ይባላል???
በተሰጠው አንቀጽ ውስጥ 'ደጎራ' የሚለው ቃል ምን ማለት ነው ??
አስር ደቂቃ ብቻ !!
ዛሬ የምንሸልም ሁለት ሰው ብቻ ይሆናል መልካም ዕድል ።
የመልስ መስጫ ሊንክ ይሄው ተጭነው መልስ ይስጡ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@Fogremover
እናንብብ እንወቅ ከዓለም ጋር እንተዋወቅ።
ፊደል አስር
የግድ መነበብ ያለበት ምርጫ እና በጣም አጭር ጽሑፍ
ምንጭ ማህበራዊ ድህረገጽ
'ሸክም'
መዝገቡ እንቅልፍ በዐይኑ አልዞር ብሎ ጣሪያ ይቆጥራል፡፡ አሁንም አሁንም ይገላበጣል፡፡ ከራስጌው ያለውን መብራት አበራና ከጠረጴዛ ላይ ከደረደራቸው መጻሕፍት መካከል፣ አንዱን አፈፍ አደረገ፡፡መጽሐፍ የሚገልጠው በተካልቦ አይደለም። በእያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅጠል ላይ፣ እንደ ኒሻን የተደረደሩትን የቃላት መንጋ፣ በጥሞና ይመረምራል፡፡ አርበ ጠባቧ ክፍል ጅምር ንባብ በዳበሳቸው መጻሕፍት ተሞልታለች፡፡ እንዲያም ሆና ብዙም የከፋ ገጽታ የላትም፡፡ ከእጁ የገባው ድርሳን፣ የሌሊቱን ሸክም የሚያስረሳ መስሎ ስለታየ፤ለማንበብ ተበራታ፡፡ ድርሳኗን የከተበው ጥበበኛ በጨዋታ እያዋዛ፣ ቋጥኝ ቁም ነገርን ማቀበልን ያውቅበታል፡፡ ጥቃቅን ገጠመኞችን እያስታከከ፣ ንቃትን የሚያበራ ስንቅ እንካችሁ ይላል፡፡ ሲጠበብ ድንቅፍቅፍ አያደርገውም፡፡ መስመር በመስመር የደረደራቸው ውብ ሽንጣም የምናብ ፍሬዎች፣ እየተስለመለሙ ይጠራሉ። አንዴ ማንበብ ከጀመሩ፣ ለማቆም ሐሞት ይጠይቃል፡፡ የመጽሐፉን ገጽ እንደገለጠ፣ እጅ ነስቶ የተቀበለው፣ የአንድ ሸክም አልባ ትሁት ሰው ገጠመኝ ነው፡፡ አብርሀም ሊንከን የአገሪቱ ቁንጮ በሆነ ማግሥት፣ የመክፈቻ ንግግር ለማድረግ ወደ ሰገነቱ ወጣ፤በዚህ ጊዜ አንድ ግርማ ሞገስ የራቀው አድሃሪ፣ ጉባኤውን በቃጭል ድምጹ ያውከው ጀመረ፡፡ “ስማ፣ በለስ ቀንቶህ መሪ ሆንክ ማለት፣ ድህነትህ ይፋቃል ማለት አይደለም። አባትህ ጫማ ጠጋኝ እንደነበረ፣ ሀገር ያውቃል። እንደውም፤ በዚህ ጉባኤ የታደምነው የምክር ቤት አባላት የተጫማናቸው ጫማዎች፣ በአንተ አባት እጅ የተበጃጁ ናቸው። እናም፤ትላንትህን አትርሳ” አለ እያፌዘ፡፡ አብርሀም ሊንከንም ይህንን ጎርባጭ ፌዝ፣ በሚገርም ሁኔታ ወደ ቁምነገር እንዲህ ለወጠው፤ “ወዳጄ፤ የአባቴን ስራ ስላስታወስከኝ በእጅጉ አመሰግንሃለሁ። እርግጥ ነው፣ አባቴ ጫማ ሰፊ ነበር። ሲበዛ ፈጠራን የታደለ፣ ቢፈጥር ቢፈጥር የማያልቅበት፤ እኔ እንኳን እዚህ ደረጃ ላይ ደርሼ፣ የእርሱን አንድ እጅ ችሎታ ልተካከል አልችልም። በእውነት ዛሬ የምክር ቤቱ አባላት በሙሉ የተጫሙት ጫማ፣በአባቴ ታታሪ እጆች የተበጃጁ እንደሆኑ በመበሰሬ፣ ልዩ ስሜት ነው የተሰማኝ፤ ደስታዬን እጥፍ ድርብ ላደረገልኝ ለዚህ ቀናኢ ወዳጄ፣ ደግሜ እጅ እነሳለሁ፤” አለ፡፡ ጠቢቡ ታሪኳን ተንተርሶ ያኖረውን ምልከታ ለመቃረም፤ መዝገቡ በመጣደፍ ስሜት ገጣዩን ገጽ ገለጠና በምናብ ማነብነብ ጀመረ ፤ “ሸክምህን እንደ አብርሃም ሊንከን ማቅለልም ሆነ ማክበድ የምትችለው አንተ ብቻ ነህ፡፡ በትላንት ማንነትህ የምትታሰር፣ በነገ ሕልምህ የምትታበይ ከሆነ፤ ሸክምህን ለመቋቋም ጫንቃህን ከወዲሁ ማወፈር ይጠበቅብሃል፡፡ ሰዎች ሸክምህን በጎነተሉት ቁጥር፣ ስሜትህ ይጎፈንናል፡፡ እላይህ ላይ በየአፍታው የሚቀያየር የአየር ጠባይ፣ እንደ መርግ ይጫንሃል፡፡ በሰዎች ተግሳጽ ቆፈን ውስጥ ትገባለህ፡፡ በሰዎች ጭብጨባ ወበቅ ትቸገራለህ፡፡ ምርጫው የአንተ ነው፡፡ ወደ እሳት ወይም ወደ ውሃ፡፡” መዝገቡ በውድቅት ቀስቅሶ ንቃት የሚያባራ ቁምነገርን ላቀበለው ጠቢብ እጅ ነሳ፡፡ ምልከታው በውስጡ ያደፈጠውን ጨለማ ሰብእናን፣ እንደ ባትሪ ወለል አድርጎ ሲያሳየው ይሰማዋል፡፡ ጣቱን ከመጽሐፉ መሀል እንደወሸቀ፣ የወየበው ግድግዳ ላይ ዓይኑን ማንከራተት ጀመረ፡፡ ጥቂት ጥሞና ውስጥ እንደገባ በሞት ታናሽ ወንድም ተቸነፈ፡፡ በማግሥቱ በሩ በኃይል ሲደቃ ይሰማዋል፡፡ መዝገቡ ድብልቅልቅ ባለ ስሜት እየተጨናበሰ መዝጊያውን እንደከፈተ፣ የሰማይ ስባሪ የሚያህል መለዮ ለባሽ ሰደፉን እላዩ ላይ አሳረፈበት፡፡ “አንተ ብሎ ተራማጅ፣ ቀጥል!” አለ ጉርድ በርሜል የመሰለው ሌላኛው ባለመለዮ፡፡ የሥጋ ጨርቅ አድርገው ከጭነት መኪናው ላይ አሰጡት፡፡ መለዮ ለበሾቹ እያዳፉ ከአስፈሪው ወህኒ ቤት ለምን እንደጣሉት ቢያወጣ ቢያወርድ፣ ወደ አእምሮው ሊመጣለት አልቻለም፡፡ ጊዜው "የአይንህ ቀለም አላማረኝም" ተብሎ የጥይት ራት የሚኮንበት ዘመን ስለሆነ፤ በእርሱ ላይ የደረሰው አልደነቀውም፡፡ በወህኒ ቤቷ የታሸገው እስረኛ ለዐይን ያስፈራል፡፡ የሚያቃስት ድምጽ እዚህም እዚያም ይሰማል፡፡ የወህኒ ቤቷ ብቸኛ መጽናኛ የኳሏት ጥቅሶች ናቸው፡፡ “አለም ሰፊ እስር ቤት ናት፤” “እንኳን ከእስር ወደ እስር በደህና መጣችሁ፡፡” ጥቅሶቹ በቁጥር አይገፉም፡፡ ከጥቅሶቹ መሀል መዝገቡን የሳበው፣ “ሸክምህ እንዲቀልህ ከፈለግህ፤ሞትን እንደ ሶቅራጠስ ቅደመው” የሚለው ነው:: ከውድቅት ጀምሮ እንደ ጥላ እየተከተለው ያለው ሸክም፣ ለራሱ ገርሞታል፡፡ እግር የጣለው አውጠንጣኝ ወህኒ ቤቷን እንደተወዳጃት ገመተ፡፡ አስፈሪዋን ወህኒ ቤት በዐይኑ ከእግር እስከ ራሷ ዳበሳት፡፡ አንድ ሪዛም አዛውንት ከጥቅሱ ጋር በአይን ይነጋገራሉ፡፡ የጥቅሱ ቅኔ በብቸኝነት የገባቸው ይመስላሉ፡፡ እንደ መቃብር በሚደብት ፅልመት ውስጥ ፊታቸው እንደ ፀሐይ ያበራል፡፡ የፊታቸው ጸዳል ሲጋባበት ይሰማዋል፤ በአዛውንቱ ሰበብ እርሱም በተራው ሸክሙን ለመመርመር ተነሳሳ፡፡ “ገላዬን እንደ አውሬ ትቦጫጭቁት ይሆናል፤ነፍሴ ግን ከእናንተ አይን የራቀ ነው፡፡ እኔም እንደ ፈላስፋው ከዚህ ግኡዝ በድኔ ጋር ሰማኒያዬን ቀድጃለሁ፤” እንዳለ እንደ መርግ የተጫነው ሸክም ከላዩ ላይ ሲራገፍ ተሰማው፡፡
እንዴት አመሻችሁ!!
በቃላችን መሠረት የካርድ ሽልማት የሚያስገኘውን ጥያቄ ይዘን መጥተናል።
ሕግ ጥያቄው በተለቀቀ በአስር ደቂቃ ውስጥ የምናስቀምጠውን ሊንክ ተጠቅመው ትክክለኛ መልስ ለሰጡን ሦስት ሰዎች ብቻ ካርድ እንሞላለን።
እርግጠኛ ይሁኑ በቂ አባል ስላለን አባል ለማፍራት ብለን አንድም ቀን ዋሽተን አናውቅም!!!!!!
የመልስ መስጫ ሊንክ ይሄው።
@Fogremover
ጥያቄ
"መታ ያለ" እደግመዋለሁ
"መታ ያለ"
የሚለው የአማርኛ ቃል ምን ማለት ነው ???????
መልካም ዕድል
ፊደል አስር
ምን ማለት ነው !!!!!!
'ተረት ለነገር ይሆናል መሰረት ' አለች አክስቴ
ስንቱን አየነው!!!!!!!!!
በነገራችን ላይ ነገ ለ ፊደል አስር አባላት በፊደል አስር ቻናል ብቻ የተዘጋጀ የ ሞባይል ካርድ ሽልማት አለን። ጥያቄው ተዘጋጅቷል ። በምናስቀምጠው የመልስ መስጫ ሊንክ ወዲያው መልስ ለሚሰጡ ሦስት መላሾች ካርድ እንሞላለን ። እነሱንም እናሳውቃለን!!!!! ይህን ስንል አባል ለማፍራት በማሰብ እንዳልሆነ ልብ ያድርጉልን። ዓላማችን መማማር ብቻ ነው ። ፊደል አስር ላይ ይግቡና join ይበሉ።
ሊንካችን ደግሞ ይሄው 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/fidelMeznagna
አባል መሆን ይችላሉ በራችን ክፍት ነው
ልብ ይበሉ ታላቁ ቻናላችንን ' የግጥም ማዕበልን ' ለቆ መውጣት ዋጋ ያስከፍላል። በአዲስ መልኩ በርካታ ነገሮችን ይዞ እየመጣ ነው !!!!!!!!!!!!
ፊደል አስር
ብዙ ሰዎች የነሱ ሆድ ከሞላ የሌላውም ሰው ሆድ የሞላ ይመስላቸዋል። እና የሆነ ሰው ቸግሮት ትንሽ ትብብር ከጠየቃቸው
ሰርተህ አትበላም እንዴ ሲያዩህ እኮ ጠንካራ ነው የምትመስለው ይሉና ሊያሸማቅቁት ይሞክራሉ የነሱ ጉራ ምግብ ይሆን ይመስል!!!
ዘወር ይሉና ደግሞ የሆነ ሻይ ቤት ውስጥ ለተመቻቸው አስተናጋጅ ሦስት ብር ስጦታ ጥለው ይወጣሉ።
ለእነዚህ አይነት ሰዎች የሚገባቸው ቦክስ ብቻ ነው 👊👊👊👊👊
አስመሳይነት ተጠናውቶናል ወዳጄ !!!
ካፌ ላይ ተቀምጬ የታዘብኩትን ነው ያካፈልኳችሁ!! መልካም ምሳ
ፊደል አስር ነኝ
እና ይሄው ቦክስ ተቀምጦላችኋል ይህን የታዘባችሁን የተበሳጫችሁ ቦክሷን በመጫን አቅምሷቸው።
ይህንን ሁሉ ስለምታደርግልን እናመሰግንሀለን ። ክቡር እግዚአብሔር ሆይ ነገንም እንዲሁ ታደርግልን ዘንድ እንለምንሀለን!!!
👍❤️👍❤️👍❤️👍❤️👍❤️👍😂
አሁን ያለችውን ሰላማችንን ለነገም አድርግልን
ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ይህንን እንሞክረው
'ተረትተረት' ስንባል 'የመሰረት' ከምንል ይህንን እንበል
'መሰረቱ የታለ'??
'መሠረት ምንድንነው' ??
'ማነው የመሠረተው '??
'የት ነው የተመሠረተው' ??
ተረት ተረት ስንባል ' የላም በረት'ከምንል
በረቱ የታለ??
ላሞች የታሉ??
ብለን እጠይቅ እንደነዱን አንነዳ!!
'አፌን በዳቦ አብሱ' ከምንልም!
'ዳቦው የታለ' ብለን እንጠይቅ ነው የምላችሁ ወዳጆቼ !!
ካነበብኩት በመነሳት የተጻፈ
በሉ መልካም ጊዜ
ፊደል አስር 👍👍👍👍
አዛውንቶችን አትናቅ
👉 የናቁት ያደርጋል ራቁት ነውና
➡️ አንዳንድ አዛውንቶችም ሽምግልናን አታቅሉ
⏩ ለጋ ነው ብለህ የናከው አቅም ሲያገኝ ያላጋሀል። እምቡጥ ነው ብለህ የተወከዉ አቅም ሲያገኝ አንተ በእርጅና ምክንያት ወንበር ስትይዝ መሮጥ በማትችልበት ጊዜ ያሯሩጥህና በገዛ ልጅህ ክብርህንም ዕድሜህንም ትነጠቃለህ።
➡️ የተጎዳ ፍራሽ አዳሽ
ፊደል አስር
መምሰል ክፉ በሽታ ነው፡፡ ለጥቅምም ሆነ ለአንዳች ግላዊ አላማ ብሎ ሌሎችን መስሎ፣ የሌሎችን ማሊያ ለብሶ፣ የሌሎችን ዜማ አጥንቶ፤ እንደሌሎች እሆናለሁ ብሎ ማሰብ፤ “የባዳ ሞኝ ከልጅህ እኩል አርገኝ” አለ፤ እንደሚባለው ነው፡፡ የተቀቡት ቀለም መደብዘዙ፣ ያጠኑት ዜማ መፍዘዙ እና የራስ ማንነት የማታ ማታ በዚህም ቢሉት በዚያ ብቅ ማለቱ አይቀሬ ነው፡፡
የሥነ - አዕምሮ ጠበብቶች እስስታዊ ባህሪ የሚሉት ማለት ነው፡፡
ፖለቲከኞች አድር - ባይነት ይሉታል፡፡
ገጣሚዎች ደሞ፤ “ያካባቢ ቀለም ብትለብስም፣ እስስት የኖረች መስሏት የማይወላውል ባላንጣ፣ አድብቶ ለቀም አደረጋት! ቀን የተመቸን መስሎን፣ የኛ ካልሆነ መጠጋት የጅሎች አጉል ብልጠት ለ”አስብቶ - አራጅ” እጅን መስጠት የሰው ቀለም ፍለጋ፣ የራስን ቀለም ማጣት! የዛም የዚህም ሳይሆኑ፣ ምላስ አርዝሞ መቅረት!!!
ምንጭ ማህበራዊ ድህረገጽ
ከዋናው ጽሑፍ ውስጥ ተቆርጦ የወጣ
ፊደል አስር
ኩሉ አመክሩ ወዘሰናየ አጽን
(ሁሉንም ሞክሩ የተሻለውን አጽኑ)
ነገር ግን ዝም ብላችሁ አትቀመጡ። በሉ የተቀመጣችሁ ተነሱ
ይቅርታ ተቀመጡ በቃ እንደፈለጋችሁ ሁኑ !!❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
አስደሳች !!!!!!!!
ከዚህ በፊት አንድ ምርጥ ጋዜጠኛ አስተዋውቄአችሁ ነበር ። እስሌይማን አባይ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ውስጥ ያገለግላል ። የ ኢትዮጵያ ዋስ ጠበቃ ነው ።በአባይ ላይ የሚገነባውን የታላቁን የ ህዳሴ ግድብ በሚመለከት የ ግብጽ እና የ ሱዳን የጎን ውጋት ነው እስሌይማን አባይ ። በሚፅፋቸው እና በሚያቀርባቸው ምንም ያልተነካኩ ያልተበረዙ አዳዲስ ጽሁፎቹ ይታወቃል። ግብጽ እና ሱዳን የሀገር ያህል ይፈሩታል። የ አባይ ጠበቃ እስሌይማን አባይ ።
በፊደል አስር ብቻ የ እስለይማን አባይ የተመረጡ ጽሑፎች ከእስለይማን አባይ በወሰድነው ፈቃድ መሰረት በድምፅ ይተረካሉ።
እንዳይመልጥወት። ከቅርብ ቀን ጀምሮ
ይህንን ሊንክ በመጠቀም አባል ሆነው ትረካዎችን ማድመጥ ይችላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/fidelMeznagna
ሪፖርት የዛሬውን ጥያቄ የሞከሩ ሰዎች ብዛት 87 ሲሆን መልሱን በትክክል የመለሰ አንድም ሰው ባለመኖሩ ሽልማቱ ለቀጣዩ ቀን ለቀጣዩ ጥያቄ ተሸጋግሯል
የዛሬው ጥያቄ መልስ ይሄው
አሉላ አባ ነጋ
ታሪካዊ ልብወለድ
በማሞ ውድነህ
ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት
መልካም አዳር እናከብራችሁአለን!!!
የቴክኖሎጂ የፍቅር የታሪክ የፍልስፍና የቋንቋ ጥያቄዎች እና ሽልማቶቻቸው ተዘጋጅተዋል። ምርጥ ምርጥ ጽሑፎች ይተረካሉ።
በፊደል አስር ብቻ ከ ግጥም ማዕበል ቻናል ጋር በጥምረት !!!!
ማታ አንድ ሰዓት ተኩል ላይ በሌላ ሽልማት እንገናኝ በፊደል አስር ብቻ !!
ልብ ይበሉ በትናንትናው ዕለት ሁለት መላሾችን ለእያንዳንዳቸው ባለ 150 ብር የሞባይል ካርድ ሸልመናል። ጠቅላላ 300 ብር እንደማለት ነው !!!
የዛሬው ለየት ይላል ። ጥያቄያውም ለየት ይላል።💪💪💪💪💪💪💪
በፊደል አስር ብቻ
ሪፖርት
ቀደም ብሎ በተጠየቀው ጥያቄ መሠረት
በነበሩት አስር ተከታታይ ደቂቃዎች ውስጥ 18 ሰዎች የመለሱ ሲሆን ከ 18 ቱ መካከል ሁለት ሰዎች ብቻ መልሰውታል።
ከአስር ደቂቃዎች በሁዋላ ግን በጠቅላላው 288 ( ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት) ሰዎች የሞከሩ ሲሆን ከነሱ ውስጥ በርካታ ሰዎች መልሱን አግኝተውታል።
ስለዚህ መጀመሪያ ላይ ለመለሱ ሁለት ሰዎች አንዱ ስልክ ቁጥሩን ስለላከልን በቁጥሩ በኩል ለሌላኛው ደግሞ በ ቴሌግራም የመልዕክት መስጫ በኩል እንዲደርሰው ስለፈለገ ተልኮላቸዋል ማለት ነው ።
ለሦስት ሰው ስፖንሰር የተደረገልንን የሞባይል ካርድ ለሁለት ሰዎች 150 ብር ለእያንዳንዳቸው በጠቅላላ የ ሦስት መቶ ብር ካርድ ሞልተናል ማለት ነው ።
የዛሬው ጥያቄ መልስ
' መታ ያለ ' ማለት አጠር ብሎ በመጠኑ የወፈረ ሰው ማለት ነው
እናመሰግናለን ። ለቀጣይ ውድድር ይዘጋጁ አብረውን ይሁኑ።
መልካም አዳር
ፊደል አስር
ትናንትና ቃል በገባነው መሠረት የመጀመሪያውን የ ሞባይል ካርድ የሚያሸልመውን ጥያቄ ማታ አንድ ሰዓት ተኩል ላይ ይጠብቁን ! መልካም ቀን
በፊደል አስር ብቻ
'ሹመት ሺህ ሞት' አሉ እማማ ብርጣሉ!!
በዚህ ዘመን ከመሾም ቢቀር ይሻላል !!!! የተሾማችሁ አይዟችሁ ቻሉት!!!! ብስል ለመሆን ሞክሩ። ፈጣሪአችሁን አድምጡ
የፊደል አስር መልዕክት
"አምላክ ሆይ ከተሰወረ ሀጥያት አንፃን"
አሜን የምትለዋን ጠቅ በማድረግ አብራችሁኝ እንደሆናችሁ ንገሩኝ
መልካም ሰንበት !!
ፊደል አስር
ትውስታ አድማስ
“--ዝምታ የተወጠረን ገመድ እንደ ማርገብ ነው፥ ዝምታ ከሩጫና ከውክቢያ ጋብ ብሎ ፋታ እንደ መውሰድ ነው፥ ፋታ ወስደን ስናበቃ ትላንት እንዴትና ምን እንደነበርን፥ ዛሬ የትና ምን ላይ እንዳለን ፥ ነገ ወዴትና እንዴት እንደምንጓዝ እናውጠነጥናለን።--”
ስለ ኑሮው፣ ስለ ፖለቲካው፣ ስለ እምነቱ፣ ስለ መዝናኛው፣ ስለ ሀዘኑ፣ ስለ ደስታው፣ በዙሪያችን ስላሉ አጠቃላይ ተፈጥሮአዊም ሆኑ ሰው ሰራሽ ነገሮች በትክክል አስበን፣ ትክክለኛ መፍትሄ ማምጣት ይጠበቅብን ከሆነ፣ ለዚያ ትክክለኛው የህይወት ቁልፍ፣ ለራስ ጊዜ ሰጥቶ፣ በዝምታ ከራስ ጋር መነጋገር መቻል ነው:: በአዕምሯችን ላይ ተዘበራርቆ የተቀመጠው አለማችን፣ በልባችን ላይ ግን ሰላምና ፍቅርን ያገኛል፡፡ አዕምሮ የተቀነባበረና የተሰላ እውቀትን ሲሻ፣ ልብ ግን ህያው የእስትንፋስ ስሜትንና ፍቅርን ያቀዳጃል፡፡ እነዚህን ሁለት የአካለ ስጋ ሞተሮች ግብርና አካሄድ በውል አሰላስሎ ለማጥናት ዝም መሰኘት፣ ከራስ ጋር ስብሰባ መቀመጥ፣ የራስን ቃለ ጉባኤ በገዛ እግረ ህሊናችን ተጉዘን፣ በገዛ ነፍሳችን እጆች መፃፍ ያስፈልጋል፡፡ በፀጥታ ዝም፣ ቀስ ብሎ ምንም ሳያንሾካሹኩ፣ ዝም እንዳሉ እቃ ሳያጋጩ፣ ብረት ወይም ቆርቆሮ ነገር ሳይረግጡ፣ ሳልም ሳያስሉ፣ እሚያንሸራትት ነገር እረግጠው ድንገት ጧ ብለው ወድቀው ሰው ሳይረብሹ፣ ፀጥታ ሳያደፈርሱ፣ ፊሽካ ነገርም ሳያጮሁ ወይም እሚያለቅስ ልጅ ሳያዝሉ፣ መኪና ሳያንጋጉ፣ እሚነዳ መንጋም ሳያግተለትሉ፣ ታኮ ጫማም ሳይጫሙ ወይም እሚጮህ ከስክስ፣ እሚላመጥ ማስቲካም ቢሆን ወይም ከንፈር መምጠጥ --- ምንም ነገር ሳያደርጉ ዝም እንዳሉ ዝም ማለት፣ የሌላውንም ሆነ የራስን ሰላምና ፀጥታ ላለመበረዝ ወይም ላለማበላሸት ፀጥ ብሎ በዝምታ ቀስ እንዳሉ ዝም ማለት፤ ለዝምታ በዝምታ ከራስ ጋር ዝም እንዳሉ ተማክሮ፣ በፀጥታ ቀስ ብሎ ዝም ማለት፤ ሌላው ከገባበት አለምና ምሳጤ ነቅቶ በኛ ከንቱ ጩኸት እንዳይረበሽና ከነበረበት አውድ እንዳይሰናከል፣ በጥንቃቄ ዝም መሰኘትን መልመድ፡፡ በኛ በአንዳንዶች ዝም ማለት ምህኛት ብዙ ጩኸቶች እራሳቸውን ታዝበው ዝም ሲሰኙ መመልከት፣ ጩኸት እሚበረታው የበለጠ አጯጯሂ ሲያገኝ ነውና በዝምታ መበርታት፣ አጃቢ አልባ ብቸኛ ጩኸት የእብደት እንኳ ቢሆን ብቻውን መሆኑን ሲያውቅ ደንግጦ ዝም ወደ ማለት ይመጣል፡፡ ኳኳታን በመጥላት ብቻ ሳይሆን የውስጥን ሰላም ለመፈለግ ብሎም የከባቢውን አየር ላለመበረዝ ስንል ዝም ማለት፡፡ ዝም እንዳልን የአለምን ዝምታና ጩኸት ማሰስ፣ የዝምታን ዜማና ግጥም ዝም እንዳልን ማንጎራጎር፤ የውስጥን ዝምታ አውጥቶ በዝምታ የዘፈነ ከያኒም ያለ እንደሆነ፣ ያንን ዝም እንዳልን በዝምታ ውስጥ አብረን መዝፈን፡፡ የሸንበቆውና የዛፉ እንቅስቃሴ፣ የባህሩና የውቅያኖሱ ውዝዋዜ፣ የነፋሱ ሽውታና የበጋው ፀሐይ ሙቀት፣ የክረምት የጉም ጉዞና የደራሽ ጎርፍ ነገረ ስራ፣ የሰማዩ ጉርምርምታና የአካባቢው ቅዝቃዜ፣ የቀዬው ልምላሜና የከብቱ ፌሽታ ድንፋታ፣ የእረኞች ከብት የማገድ ተግባር፣ የገበሬው ባተሌነት፡፡ ወዲህ የከተሜው ዘናጭነት፣ ጎፈሬው፣ ቁንዳላው፣ ፍሪዙ፣ ባላቶሊው፣ መላጣው፣ ክብ ፂሙ፣ ባለ ከራባቱ፣ ባለ ጉልበት ቅድ ሱሪው፣ ባለ ሂውማን ሄሯ፣ ባለ ቦርሳው፣ ባለ ላፕቶፑ፣ ባለ መኪናው፣ ባለ ፎቁ፣ ነጋዴና ወዛደሩ፣ አስተማሪና አስተዳደሩ፣ ስፖርተኛውና አርቲስቱ፣ ፖለቲከኛውና የቤተ-እምነት ሰው ሁሉ፡፡ እንደ ሰው ሁሉ የቤት እንስሳት ይዞታና አኗኗር….ደግሞም የዱር እንስሳትና የሃገር ታሪካዊ ቦታዎች…. እነዚህ እና መሰል የህይወት አካሎች በሙሉ የጠቀስናቸውን ጎብኝተን ስናበቃ፣ የጉብኝታችንንና የእይታችንን ብሎም የመደመም የመናደዳችንን ስሜት የምናስቀምጠው በልቦናችን ጓዳ ውስጥ ነው:: ከልቦናችን አውጥተን በአዕምሯችን ሸምነንና አስልተን ስናበቃ መልካም ወደሆነው የጋራ የልብና የአዕምሮ ውሳኔ እናቀናለን፡፡ ይህንን ድርጊያ ለማሳመርና የእኛነት ስሪት ዛሬ ላይ ለተፈጠረውና ላፈጠጠው ገሃዳዊ እውነት ችግር መፍትሄ መሆኑን በውል ለማወቅ ስንል የዝምታ መረብ ውስጥ፣ የራስ አለም ምሳጤና ንጉደት ውስጥ መጥለቅ ያስፈልጋል፡፡ ከተሰለፍንበት ታክሲ ተራ፣ ከመርካቶ ገበያ ጫጫታ፣ ከዳንኪራ ቤት የወል ደስታ፣ ከስታዲዬም ሆይሆይታ፣ ከግርግርና ከስብሰባ ቦታ አንድምታ ተገልለን በየራሳችን ቤት፣ በየራሳችን የአዕምሮ ወለል፣ በየነፍሳችን ኮሪደር ላይ ብንሰበሰብ፤ አለምም እኛም በእፎይታና በሰላም አየር እንከበባለን፡፡ ደግሞስ በጫጫታ ውስጥ ልክ የኦዞን መስመር በተቃጠለ አየር እንደሚሸነቆረው ሁሉ ጩኸታችን የአሰተሳሰብን አየር ቢሸነቁር እንጂ ሌላ ምን ሊያተርፈን? የሙዚቃው ልሂቃን እነ ሞዛርት ሲናገሩ፤ Silence is the core part of Music ይላሉ። በእያንዳንዱ ሙዚቃ ውስጥ የሚያስፈልግ እረፍት አለ …ያ እረፍት ነው በሙዚቃ ውስጥ እንደ ዝምታ የሚቆጠረው። ይህ የሚያሳየን እንግዲህ በጥድፊያው አለማችን መካከል፥ በነገሮቻችን መካከል እረፍት ወይም አንዳች ዝምታ እንደሚያስፈልገን ነው። ዝምታ የተወጠረን ገመድ እንደ ማርገብ ነው፥ ዝምታ ከሩጫና ከውክቢያ ጋብ ብሎ ፋታ እንደ መውሰድ ነው፥ ፋታ ወስደን ስናበቃ ትላንት እንዴትና ምን እንደነበርን፥ ዛሬ የትና ምን ላይ እንዳለን፥ ነገ ወዴትና እንዴት እንደምንጓዝ እናውጠነጥናለን። ስለዚህ ይህንን ለማድረግ በሎሬቱ አንደበት እንዲህ እንበል…… ከሰው መንጋ እንገንጠል ላንድ አፍታ እንኳን እንገለል ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል እያልን በዝምታ ዝምተኛ ግለሰብ አባዝተን፣ ዝም የሚል ከጩኸት የራቀ ማህበረሰብ ወልደን፣ ዝም ጸጥ ረጭ ርግት ያለ፣ የራሱን ችግር በራሱ መፍትሄ የሚፈታ ሰላማዊ ሀገር እንፈጥራለን ብዬ አስባለሁ:: ቸር እንሰንብት! ( ምንጭ:-አዲስ አድማስ ድረ ገጽ ፤ሜይ 28, 2019)
በጣም የሚያሳዝነኝ በጣም ብዙ ሰው ዛሬ የሌላ ሰው ቤት ሲንኳኳ ነገ የሱም ቤት በተራው ሊንኳኳ እንደሚችል የተረዳ አይመስልም።
💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪
የብዙኋን እናት
መጠጊያ የምንላት
እማማ ናትና
ሀገሬን አትንኳት!!!!
ኢትዮጵያዬ ሀገሬ ክብሬ ከአምላክ በታች የሚሆንሽን ራስ መርጠሽ ትንሳኤሽ ሊበሰር ቀኑ ደረሰ መሰለኝ!!
ኦ አምላኬ ሁሉን ነገር ሰላም አድርግልን!!!!!!❤️❤️❤️❤️👍
'እንደእኔ አጠባለሁ ብለሽ ጥጃሽን አትግደይ' አሉ እማማ አስካሉ እውነታቸውን ነው እኮ
ማነህ እንትናየ ይሰማል?? ባክህ ሰምተሀል!!😭😂😂😂❤️
መልካም ረፋድ
ፊደል አስር
አንዳንድ ተረት ተደጋግሞ ካልተነገረን አንጀት አይደርስም። የሚከተለውን ተረት ከአመታት በፊት ተርከነዋል። ዛሬም ይሄው እንተርከዋለን። ትምህርታዊነቱ ደግ ነው ብለን ነው። እነሆ! ከእለታት አንድ ቀን ሌሊት በጠፍ ጨረቃ ሶስት አህዮች ሳር ይግጣሉ። እንዳጋጣሚ የተራቡ ጅቦች በዚያው ገደማ ያልፉ ኖሮ አህዮቹን አዩአቸው። ከበቧቸውና “ለመሆኑ ማንን ተማምነው ነው በጠፍ ጨረቃ በኛ ግዛት እንዲህ እየፈነጩ ሳር የሚግጡት? ችሎት ተቀምጠን እንጠይቃቸው” ብለው ጅቦቹ ለዳኝነት ተሰየሙ። የመጀመሪያዋ አህያ ቃል ልትሰጥ መጣች። የመሃል ዳኛው፤ “እሜቴ አህያ፣ ለመሆኑ ማንን ተማምነሽ ነው በኛ ግዛት በጠፍ ጨረቃ ሳር የምትግጭው?” አህያይቱም፡- “ፈጣሪዬን አምላኬን ተማምኜ ነው፤በእኔ ላይ ጉዳት የሚያደርሱን ሁሉ ፈጣሪዬ ይበቀልልኛል” ስትል መለሰች። ሁለተኛዋ አህያ ቀረበች፡፡ መሃል ዳኛው፡- #አንችስ ማንን ተማምነሽ ነው በጠፍ ጨረቃ በእኛ ግዛት የምትግጭው?; ብሎ ጠየቃት። አህያይቱም፡- “ጌታዬን፤ ሀብት የሆንኩትን ባለቤት፤ ለእኔ ክፉ የሰራን ሁሉ የገባበት ገብቶ ይበቀለዋል” አለች። በመጨረሻም ሶስተኛዋ አህያ ቀረበችና አስረጅ ተባለች። ሶስተኛዋ አህይትም፡- “እኔ በጠፍ ጨረቃ የወጣሁት እናንተኑ ጌቶቼን ተማምኜ ነው” ስትል መለሰች። ዳኞቹም መከሩና “የመጀመሪያዎቹን ሁለቱን ብንበላ እውነትም አደጋ አለው። ይህቺን እኛን የተማመነችውን ብንበላት ግን ማን ይጠይቀናል!” አሉና ከመቅጽበት ወረዱባት ይባላል። እነሆ መተማመኛችንን አጥርተን ሳናውቅ መጓዝ ለአደጋ ሊያጋልጠን ይችላል። ሁሉ ነገር ከየጀርባው የስጋት ባለቤት አለው። ያም ሆኖ እጅግ ከባዱን አደጋ ከመካከለኛው አደጋ አመዛዝነን ማጤን ይገባናል። መካከለኛውንም ከትንሹ ማመዛዘን አለብን። ጉዳዮቻችንን በእውቀትና በብልሃት መከወን ይጠበቅብናል። ነገር ግን የእነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ እንዳይሆን በጥንቃቄ መራመድን ግድ ይለናል።
ምንጭ ማህበራዊ ድህረገጽ
ከዋናው ጽሑፍ ላይ ተቆርጦ የቀረበ
መልካም ሰንበት