fidelmeznagna | Unsorted

Telegram-канал fidelmeznagna - ብርሀን Revelation

-

የመዝናኛ እና የመረጃ ገጽ

Subscribe to a channel

ብርሀን Revelation

ሙሶሊኒ ኢትዮጵያ በኢጣልያ የጦር ኃይል በመያዝዋ ሁለተኛው የሮም የንጉሠ ነገሥት መንግሥት (የሮማን ኤምፓየር) መመሥረቱን እ.አ.አ. ግንቦት 5 ቀን 1935 ዓ.ም ለዓለም አስታውቆ አዲሱን መንግሥት የሚያናውጥ ኃይል በምድር ላይ ሊኖር አይችልም ብሎ በታላቅ ትዕቢት ተናገረ:

የምሳ ማስታወሻ !! ከመጻሕፍት የተወሰደ ነው

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ገንዘብ ያለውና


ውሸታም ተዋደዋል ወዳጄ !!!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ተመልሰናል። ወዳጆቻችን እንደምን አላችሁልን።
እንደተለመደው በተለያየ መዝናኛ እና መረጃ ክእናንተ ጋር በአዲስ መልኩ እንቀጥላለን ።

እንወዳችሁአለን። ሰላም ለሀገራችን ።

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ከበዓላት እስከ በዓላት ድረስ ዘመናችን ሁሉ የተባረከ እና የሰላም ይሁንልን !!!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ቸር አይለፈን

ክፉ አይግጠመን

መልካሙን ሁሉ ይስጠን

!!!!!!❤️❤️❤️❤️!!!!!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ክፍል ሦስት

በመምህር ኤፍሬም ብርሃኑ


አባትየው ግራ በተጋባ ስሜት ውስጥ ሆኖ የሚሆነውን ይመለከታል። ወይዘሮ ተስፋነሽ ተንቀሳቃሽ ስልኳን በማንሳት ወደ ጎረቤት ደወለች። 'እባካችሁ ድረሱልኝ' ብላም ተጣራች። ጩኸቷን የሰሙ ጎረቤቶቿም ቤት ውስጥ ተገኝተዋል። ደግ የሆነው ጐረቤቷ አቶ እንዳለው ሁኔታውን ከተመለከቱ በሁዋላ ሮጠው በመሄድ መኪናቸውን ይዘው ከተመለሱ በሁዋላ ዮሴፍን ከእናቱ እና ከሁለት ጎረቤቶች ጋር በማድረግ በፍጥነት ከአካባቢያቸው ወደሚገኘው የግል ክሊኒክ አደረሱት።
የ ክሊኒኩ ነርሶች ዮሴፍን በፍጥነት እያገዙት ነው ። የራሳቸውን ህክምናዊ አስተያየትም እየሰጡ ነው .....

አባትየው ቤት ውስጥ ከ ዮሴፍ እጅ ላይ ውድቆ መሬት ላይ የነበረውን በ ፖስታ የታሸገ ወረቀት አነሱት። ፖስታውን በዝግታ ከፍተው ከውስጥ የነበረ ሌላ ወረቀት አወጡና ተመለከቱ። ያዩትን ነገር ማመን ስላልቻሉ በብስጭት ወደ መኝታ ቤት በመግባት ቁምሳጥን ውስጥ ያስቀመጡትን ሽጉጥ በማንሳት ጭንቅላታቸው ላይ ደገኑ። የዮሴፍ እህት እዬሮጠች ሽጉጡን ለመቀማት ሞከረች ግን አልቻለችም። አባት ራሳቸው ላይ ተኮሱና መኝታ ቤት ውስጥ ወደቁ። ተኩሱን የሰሙ ጎረቤቶች አሁንም በተፈጠረው ነገር በመደናገጥ አባትየውን በሌላ መኪና ዮሴፍ ወዳለበት ክሊኒክ ወሰዱ። ክሊኒክ እንደደረሱ ያልተጠበቀ ክስተት ተመለከቱ።........

ይቀጥላል

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ክፍል ሁለት እነሆ

በመምህር ኤፍሬም ብርሃኑ

አባት በብስጭት 'ምናባህ ፈልገህ ነው የምትጠራኝ በማለት ከፊት ለፊቱ ከተቀመጠው ጠረጴዛ ላይ የተቀመጠውን የ ውሃ ብርጭቆ በማንሳት ወደ ዮሴፍ በሀይል ወረወረ። ብርጭቆው ከዮሴፍ ጭንቅላት ላይ  በጎን በኩል በሀይል ከመታው በሁዋላ መሬት ላይ ወድቆ ተከሰከሰ።
ዮሴፍ በጣም ስለተመታ ተዝለፍልፎ መሬት ላይ ወደቀ ። በእጁ ይዞት የነበረው ነገር መሬት ላይ ወድቋል። ልብ ብሎ የተመለከተው ግን አልነበረም።
እናቱ ወይዘሮ ተስፋነሽ ጩኸቷን አቀለጠችው። እህቱ ደግሞ ከ ዮሴፍ ላይ ውሀ እየደፋች ነው ። ዮሴፍ መንቃት አልቻለም.......
ይቀጥላል

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ችግሮቻችን እንደ ቋጥኝ ገዝፈው ድንገት የሚፈነዱት እለት ከእለት እያስታመምንና እየሸነገልን ያዳፈንናቸው ጥቃቅን እክሎች
ዳብረው ነው፡: በየጊዜው እያወቅን የምናልፋቸው ጥቃቅን የማንነት እክሎች ተጠራቅመው በድንገት ማህበራዊ ህይወታችንን ያናጉታል፡፡
ስለዚህ ማንነታችንን በጥልቀት መርምረን በትክክለኛ ማንነት ላይ የተመሰረተ ትክክለኛ ማህበራዊ ግንኙነት መፍጠር እስክንችል ድረስ
ከችግሩ መፍትሄ ጋር እንጠፋፋለን፡፡ ጥቃቅን እክሎችን ማስታመሙን
ትተን ችግሩን ከስረ-መሰረቱ ለመመንገል ካልሞከርን ልፋታችን ችግሩን
ከማዳፈን ወይም ከማባባስ የተሻለ ፋይዳ አይኖረውም:፡

መልካም ጊዜ

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

የማይመለከቱንን ነገሮች ትተን በሚመለከቱን ላይ
ስናተኩር ተጽእኖ የመፍጠር አቅማችን መስፋት ይጀምራል፡: ማድረግ የማንችለውን ትተን ማድረግ የምንችለውን በሙሉ ሀይልና ተነሳሽነት
ስናደርግ ከቁጥጥራችን ውጪ የሆኑ ነገሮችን የመለወጥ አቅማችን
ይጨምራል::


አዲሱ ዓመት በሁሉም መስክ ከሰው በላይ የምንሆንበት ይሁንልን

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ለተወሰነ ቅጽበት እራስህን ለማንበብ ሞክር:: ህይወትና አኗኗርህይመስላል?
በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለኸው?
ምን አይነት ስሜት እየተሰማህ ነው? በጭንቅላትህ ውስጥ የሚተራመሰው የሀሳብ
ግርግር ምንድን ነው?
እናም በዚህ ቅጽበት አእምሮህ በምን አይነት መንገድ እንደሚሰራ ተመልከት:: አእምሮህ ነገራትን ሲተነትን፣ ሲጠቀልል፣ ሀሳቦችን
ሲያመነዥግ፣ ሲመረምር ትኩረት ሰጥተህ ለመከታተል ሞክር፡፡ ይህን
የማድረግ ተሰጥኦ ለሰውና ለሰው ብቻ የተሰጠ ሰብአዊ ጸጋ ነው፡: ከሰው
በስተቀር ይህን የማሰብ የማሰላሰልና እራስን የመመርመር ተሰጥኦ
የሚያውቅ ምድራዊ ፍጡር የለም::

እንኩዋን ደስ አለህ !!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ጓደኛችሁ በፍቅር ዘርታችሁ
በምስጋና የምታጭዱበት ማሳችሁ ነው

አንድ ወጣትም አለው:- «ስለ ጓደኝነት ንገረን?»
እሱም እንዲህ በማለት መለሰለት:-
«ጓደኞቻችሁ ለፍላጐቶቻችሁ ምላሽ ናቸው:: ጓደኛችሁ በፍቅር ዘርታችሁ በምስጋና የምታጭዱበት ማሳችሁ ነው: ገበታችሁና የምትሞቁት እሳታችሁም ነው. .
«በራባችሁ ጊዜ ወደ እሱ የምትሄዱትን ያህል በሰላም ጊዜስ አትፈልጉትምን?. . .
«ጓደኛችሁ ከአእምሮው ጋር ሲነጋገር በገዛ አእምሯችሁ ውስጥ ስላለው <አሉታ> አትሰጉም:: <አዎንታ>ንም አትነፍጉትም:: ዝም ባለም ጊዜ ልባችሁ የእሱን ልብ ማዳመጡን አያቆምም: በጓደኝነት ውስጥ ሀሳቦች፣
ምኞቶችና ተስፋዎች ሁሉ ቃላትን መጠቀም ሳያስፈልግ፣ ያለ ሆታና ጭብጨባ ተወልደው በወዳጅነት የሚጋሩ ነገሮች ናቸውና. . .
«ከጓደኛችሁ ስትለያዩ አትዘኑ፡፡ ለተራራ ወጪ ሰው ተራራው በግልፅ የሚታየው ከሜዳው ላይ ሆኖ እንደሆነው ሁሉ፣ ከሁሉ አስበልጣችሁ
በምትወዱት ሰው ውስጥ ያለውም ብዙው ተወዳጅ ነገር የበለጠ ግልፅ ሆኖ
የሚታያችሁ እሱ በሌለበት አይደለምን?. .
«እናም በጓደኝነት ውስጥ ከመንፈስ ጽናት በስተቀር ሌላ ምንም
አላማ አይኑራችሁ. ..

«የገዛ ራሱን ምስጢር (ምኞት) ለመፍታት ከመሻት በቀር ሌላ የማይፈልግ ፍቅርስ፣ ዋጋ ቢስ ነገሮችን ብቻ ለማጥመድ
የተወረወረ መረብ እንጂ ፍቅር ሊሆን ይችላልን? ..
«ደግሞም
ለጓደኛችሁ የተቻላችሁን ያህል መልካም ሁኑለት
የልባችሁን ባህር ማዕበል ሞገድ
ጭምር ይወቅ. ..

ማወቅ ካለበት የውሀ ሙላቱን (ጎርፉንም ቢሆን ይወቅ)
«በጣዕረ ሞት (በመቀበሪያ) ጊዜያት ልትፈልጉ የሚገችሁ የቱን ጓደኛችሁን ነው? ሁልጊዜም በፍስሃ (በህይወት) ጊያት ፈልጉት፡ባዶነታችሁን ሳይሆን ፍላጐታችሁን መሙላት የሚገባው እሱ አይደለምን?…
«በጓደኝነት ጣፋጭ ጊዜያት ውስጥም ሳቅና ደስታን መጋራት ይኑር፡ ልብ ንጋቱን (ብርሃኑን) አግኝቶ የሚታደሰውስ በጥቃቅን ነገሮች ጤዛ ውስጥ አይደለምን?»

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ታላቁ ባህር

እኔና ነፍሴ ገላችንን ልንታጠብ ወደ ታላቁ ባህር ሄድን፡፡ ከባህሩ ዳርቻ እንደደረስን አንድ የተደበቀና ጭር ያለ ስፍራ ፈለግን፡፡ስፍራውን ፍለጋ እየተራመድን ሳለ አንድ ሰው በአንድ ግራጫማ ድንጋይ ላይ ተቀምጦ ከከረጢቱ ውስጥ ጨው ቆንጥሮ እያወጣ ወደ ባህሩ ሲጨምር ተመለከትን::
«ይህ መጥፎ አሳቢ ነው» አለች ነፍሴ፡፡ «ከዚህ ቦታ እንሂድ፡፡ እዚህ መታጠብ አንችልም::»
አንድ መግቢያ እስክናገኝ ድረስ ተራመድን፡፡ እዚያ እንደደረስን አንድ ሰው አንድ ነጭ ድንጋይ ላይ ቆሞ ከወርቃማ ሳጥኑ ውስጥ ስኳር
እያወጣ ወደ ባህሩ ሲበትን ተመለከትን:፡
«ይህ ቀና አሳቢ ነው» አለች ነፍሴ፡፡ «ይህ ሰውዬ ራቁት ገላችንን ሊያይ አይገባም::»
መንገዳችንን ቀጠልን፡፡ ከባህሩ ዳርቻ ላይ አንድ ሰው የሞቱ ዓሳዎችን እያነሳ ወደ ባህሩ እየጨመራቸው ነው፡፡
«ከዚህ ሰውዬ ፊት ሆነን አንታጠብም» አለች ነፍሴ፡፡ «ይህ ሰውዬ በጐ አድራጊ ነው::
እናም አልፈነው ሄድን:፡
ጥቂት እንደተጓዝን የገዛ ጥላውን በአሸዋው ላይ የሚፈልግ ሰው አገኘን:: ትልቅ ማዕበል ተነሳና ጥላውን አጠፋው: ሰውየው ግን ደጋግሞ
ይፈልገዋል
«ይሄ ደግሞ ሚስጥር የሆነ ሰው ነው» አለች ነፍሴ፡፡ «ጥለነው እንሂድ፡፡»
ጉዞአችን ከአንድ ሰርጥ አቅራቢያ አደረሰን፡፡ እዚህ አንድ ሰው አረፋውን እየዘገነ በአንድ ጌጥማ ጐድጓዳ ሰሃን ውስጥ ሲጨምር ተመለከትን:
«ይህ ሰው ሃሳባዊ ነው» አለች ነፍሴ፡፡ «ለዚህ ሰው እርቃናችንን ማሳየት የለብንም:
እናም ጉዟችንን ቀጠልን፡፡ በድንገት «ይህ ነው ባህሩ፡፡ ጥልቁ ባህር ይህ ነው: ሰፊውና ግዙፉ ባህር ይህ ነው» የሚል ድምፅ ሰማን፡፡ ድምፁ
ካለበት ስፍራ ስንደርስ አንድ ሰው ጀርባውን ለባህሩ ሰጥቶ አንድ የባህር ዛጐል ወደ ጆሮው አስጠግቶ ሹክሹክታውን ሲያዳምጥ ተመለከትን፡፡«እንለፈው» አለች ነፍሴ፡፡ «መጨበጥ ለማይችለው ነገር ጀርባውን
ሰጥቶ መያዝ ወደሚችለው ነገር ፊቱን አዙሮ የቆመ በተጨባጭ ነገር የሚያምን ሰው ነው፡፡»
እናም አለፍነው፡፡ በቋጥኞቹ መሃል አረም በበዛበት አንድ አካባቢ አንድ ሰው ጭንቅላቱን አሸዋ ውስጥ ቀብሮ ተመለከትን፡፡ «ሰውየው ሊያየን ስለማይችል ከዚህ መታጠብ እንችላለን» አልኳት ነፍሴን፡፡«በፍፁም» አለች ነፍሴ፡፡ «እስካሁን ካየናቸው ሁሉ ይህ የሞተ
ነው:: አክራሪ ሰው ሳይሆን አይቀርም፡፡»
በነፍሴ ፊትና ድምፅ ላይ ታላቅ ሃዘን ታየ፡
«ስለዚህ እንቀጥል» አለች: «ጭር ያለና የተሸሸገ ስፍራ እዚህ አካባቢ የለም፡፡ ወርቃማ ፀጉሬ በነፋሱ እንዲነሳ፣ ራቁት ነጭ ደረቴ ለአየር
እንዲጋለጥ ወይም ብርሃኑ እርቃኔን እንዲያጋልጥብኝ አልፈልግም፡፡»

ከዚያ ታላቁን ባህር ፍለጋ ይህን ባህር ትተን ሄድን፡፡

የቀኑ ትልቅ መልዕክት ነው

ከመጻሕፍት አለም !!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

የማትታገል ከሆነ መወለድ አልነበረብህም!!

እምቢ አልወለድም ማለት ነበረብህ !!!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ግጥሙን ሙሉውን ያድምጡት። ምናልባት ከዚህ በፊት ሰምተወት ሊሆን ይችላል ። ግን አሁንም ደግመው ይስሙት አንዳች ወኔን የሚሰንቅ መንፈስን ያላብሳል። የግጥሙ ባለቤት ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ናቸው
ግጥሙን አንብቦ አቀናብሮ ላደረሰን መምህር ኤፍሬም ብርሃኑ ደግሞ  ምስጋናችን ይድረስ።

ከተመቸወት በላይክ ይግለፁልን። መልካም ምሽት

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ለጆሮ የሚስማማ ወቅቱን የጠበቀ ምርጥ ግጥም ጋበዝናችሁ። ንባብ እና ቅንብር በፊደል አስር ኤፍሬም ብርሃኑ

መልካም ጊዜ

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ሰዎች አንድን ነገር የሚያደርጉት ለራሳቸው ሲሉ እንጂ ለሌላ ሰው ብለው አይደለም፡፡› ይህ አባባል ከራልፍ ዋልዶ ኤመርሰን ታሪክ ጋር
ይዛመዳል፡፡ ባንድ ወቅት ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰን ከልጁ ጋር በመሆን
አንዲትን ጥጃ ወደ በረት ውስጥ ለማስገባት ትግል ጀመሩ፡፡ ጥጃዋ የፊት
እግሮቿን ተክላ ንቅንቅ አልል በማለቷ ሁለቱም አባትና ልጅ ከድካም
በቀር ውጤት ላይ መድረስ አቃታቸው፡፡ ይኸኔ ባጠገባቸው ስታልፍ የነበረች
አንዲት ህፃን ልጅ ልትረዳቸው ጠጋ አለችና ጣቷን ጥጃዋ አፍ ውስጥ
ከተተችው፡፡ ጥጃዋ ጣቷን መጥባት ስትጀምር ልጅቷ በዝግታ ወደበረቱ
ማቅናት ጀመረች፡፡ ጥጃዋም ተከትላት ገባች፡፡

ከመጻሕፍት ዓለም

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ፍቅር እውር ነው?

ለእኔ ግን ፍቅር እውር ሳይሆን ጠንጋራ ሽውራራ ከውካዋ ውቃቤ ቢስ ነው። ክብር ይነሳል፡
ከሰው በታች ያደርጋል፡ አገር ጉድ ያሰኛል፡ አመድ ያለብሳል፡ ኮሶ ያስቆረጥማል፡ ያልሆኑትን ያደርጋል።
ታዲያ የምን እውር ያያል እንጅ አሳምሮ አጠናግሮ ያያል።አይገቡ ጉድጓድ ያስገባል።
በተለይ በአሁኑ ጊዜ ጠንጋሬ በነፃ ገበያው አለም ገብቶ እየነገደ ነው። ስንቱን አከሰረው እኮ
አግሰበሰው በኮንትሮባንድ ቱባ ሃብታም ሆነ እኮ ነብራሬ
በአሁኑ ጊዜ ፍቅር ብሎ የሚሟዘዝ በእጁ ያለችውን ያጣል። ገንዘብ ሆነ ጨዋታው። ከሌለህ
የለህም ሆነ ዘፈኑ
ሁሉም ነጥቆ ሯጭ ቀማኛ መነገጃ አድርጎታል
ፍቅረኛ አገኝሁ ብሎ ከፍቅረኛ
ጋC መዋል በሬ ካራጁ ጋር ነው። የእርድን ቀን መጠበቅ እና መሰዋት ነው። ከዛ በሁዋላ ማን ዞሮ ሊያይህ: ማነህ ባለ ሣምንት ቸር ያድርስህ ነው። ወጥመድ ውስጥ ገብቶ አንገት አስይዞ መንደፋደፍ
ነው። ስንቱ ቀምሷል ???? ቤት ይቁጠረው !!!

ከመጻሕፍት አለም

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ  ነብስህ በሰላም ትረፍ !!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ይሄ ደግሞ ግብዣችን ነው ። በአጭር ጊዜ ተወዳጅነትን ያተረፈ ምርጥ የዩቱይብ ቻናል ነው ። ይማሩበታል  ይዝናኑበታል👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/JMjc1BNlRtM

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ክፍል አራት እና የመጨረሻው ይሄው

በመምህር ኤፍሬም ብርሃኑ

ከወደዳችሁት በላይክ ግለፁልኝ




ዮሴፍ የተመታበት ቦታ ላይ በተደረገለት ሕክምና ወዲያውኑ ነበር ያገገመው ። የክሊኒኩ ነርሶችም የደረሰበት አደጋ እጅግ በጣም ቀላል እንደሆነ እና ወደ ቤት መሄድ እንደሚችል ተናግሮ ወደ እየሄዱ ነበር አባትየውን የያዘችው መኪና ክሊኒክ የደረሰችው።

ዮሴፍ እና እናቱ መኪናዋን ልብ ብለው አልተመለከቱም ። በነበረው ሁኔታ እየተወያዩ ከግቢ ወጡ። ወዲያው የ ወይዘሮ ተስፋነሽ የ እጅ ስልክ አቃጨለ። አነሳችው ቶሎ በይ ወደ ክሊኒክ ተመለሽ ተባለች።
ተመለሰች ። የተፈጠረውን ሁኔታ በሙሉ  ጎረቤቶቿ  ሲያስረዷት እጅግ ደነገጠች ። ባለቤትዋ ወደሚገኝበት የ ክሊኒኩ ክፍል አመራች። የዮሴፍ አባት ቁጭ ብለው ጭንቅላታቸው በትንሹ የደረሰባቸውን አደጋ እየታከሙ ነበር ። ሽጉጡ በትንሹ ነበር የመታቸው። የዮሴፍ እህት ሽጉጥ ለማስጣል ስትሞክር ነበር ጥይቷ በጭፍ በኩል ጨርፋቸው ያለፈች እንጂ አደጋው የከፋ ይሆን ነበር ።

ከ ወይዘሮ ተስፋነሽ ጋር ፊት ለፊት ተፋጠጡ። የዮሴፍ አባት ከተቀመጡበት በመነሳት ከሚስታቸው እግር ላይ ወድቀው ለሁሉም ነገር ይቅርታ ጠየቁ።

ሁሉም ቤተሰብ እና ጎረቤት በሙሉ በአንድ መኪና ወደየቤታቸው ተመለሱ።

ፖስታው ውስጥ የነበረው ወረቀት በዮሴፍ እጅ የተዘጋጀ እና   የዮሴፍ አባት ምስል  ያረፈበት ወረቀት ሆኖ  'አባየ ቤተሰቦችህ በሙሉ እንወድሃለን 'የሚል  ጽሑፍ ከስዕሉ ስር የተፃፈበት ወረቀት ነበር ። አባት እንባውን መቆጣጠር አልቻለም ። ቤተሰቡን በሙሉ ይቅርታ ጠየቀ።

በቤት ውስጥ ይቅርታ  ሰላም እና ፍቅር ነገሰ።

2015 በሕይወታችን ውስጥ ሰላም እና ፍቅር የሚነግስበት ዓመት ይሁንልን!!!!!!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

እጅግ አስደንጋጭ ፤






ጥብቅ ማሳሰቢያ ፤

ገና ለገና ገንዘብ ሞልቶናል ብላችሁ የምታስቡ ሰወች ፤ ገበያ ውስጥ አንድን ዕቃ ከሚገባው ዋጋ በላይ የተጠየቃችሁትን ሁሉ እየከፈላችሁ እየገዛችሁ የኛን ኑሮ አትፈታተኑብን።

እንኑርበት እባካችሁ ። አመሰግናለሁ ጨርሻለሁ !!


ለማንኛውም ዮሴፍ ክፍል ሦስት አጭር ልብወለድ ማታ በተለመደው ሁለት ሰዓት ላይ ወደ እናንተ ይደርሳል !!!!!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ክፍል አንድ
ከበዓሉ ጋር የተያያዘች እጅግ ምርጥ አጭር ልብ ወለድ
በ ኤፍሬም ብርሃኑ


የ 13 ዓመቱ ሕፃን ዮሴፍ ከነበረበት መኝታ ቤት ውስጥ ሩጫ በሚመስል ፍጥነት በእጁ የሆነ ነገር ይዞ   እናት እና አባቱ እንዲሁም እህቱ ወደሚገኙበት ሳሎን ቤት ሄደ ። ወዲያውም 'አባየ'  'አባየ'  እያለ ከአባቱ ፊት ቆሞ  በደስታ ስሜት አባቱን በተደጋጋሚ ይጠራዋል።
አባት ድሮውንም ከፍተኛ የባህርይ ችግር ስለነበረበት እየሰማ ዝም ብሏል። ከሚስቱ ጋርም ጭቅጭቅ ላይ ነበሩ።

የ 13 አመቱ ዮሴፍ አሁንም በደስታ ስሜት እንደሆነ አባቱን መጣራቱን ቀጥሏል ። ድንገት ግን አንድ አስደንጋጭ ነገር ተከሰተ.......

ይቀጥላል !!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

እየደሙ መዋብ !?!


እንዲህ ናት ሀገሬ ...
ገነት ሆና ሳለ፣
የሲኦል አበጋዝ፣ ሚፈራረቅባት፤
የበቀል ቁርሾና፣
የተስፋ አበባ፣ አብሮ ሚፈካባት!
በጥላቻ ጦሮች፣
ልቧ እየተወጋ፣ በዓይኗ ስታነባ፤
ደስታዋን ሊመልስ፣
ምድሯ ያበቅላል፣ የተስፋ አበባ!
ደም እየፈሰሰ፣
ሀገር ተተብትባ፣ በሰማንያ ጣጣ፤
ይኸውና ደግሞ፣
አደይ ፍንድት ብሎ፣ አዲስ ዓመት መጣ !
ግሩም፣ አስደማሚ፣
የማትመረመር፣ ቅኔ ናት ምድሪቷ፤
አካሏ እየደማ፣
ለአልቃሽ ዓይኗ ደስታ፣ አበባ ነው ቤቷ።
(አዲሱን ዓመት ሀገር ከመከራ የምታርፍበትና እኛም የሰላም አየር
የምንተነፍስበት ያድርግልን!)


ገጣሚ መላኩ አላምረው

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ህይወቱን የመለወጥ ፍላጎት ያለው ማንኛውም ሰው ከሁሉ ነገር አስቀድሞ ለበፊቱም፣ ለአሁኑም ሆነ ለወደፊቱ ህይወቱ መንሰኤ እራሱ
መሆኑን ማመን አለበት ማንኛውም ለውጥ ሀላፊነትን ከመውሰድ ይጀምራል ከሁሉ ነገር አስቀድመን አሁን ለምንኖረው ህይወትና
ላለንበት ደረጃ መንስኤው የራሳችን ምርጫ፣ ውሳኔና ድርጊት መሆኑን መቀበል አለብን አሁን ባለንበት ደረጃ የተገኘነው በሰዎች ወይም
በሁኔቶች አስገዳጅነት አይደለም:: አሁን የተላበስነውን ባህሪና ማንነት የያዝነው መርጠን እንጂ በወላጅ በአካባቢ ወይም በዘር ማንዘር ተገደን አይደለም፡፡ ፍላጎቱና ቁርጠኝነቱ እስካለ ከቁጥጥራችን ውጪ የሚሆኑ
አስገዳጅ ተጽእኖዎች በእጅጉ ውሱን ናቸው::


መጪው አዲስ ዓመት የትኛውንም ሃላፊነት መቀበል የሚያስችል አቅም የምናገኝበት ዓመት እንዲሆንልን እመኛለሁ

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ለአንዳንድ ደስታዎች ያለን ከልክ ያለፈ ፍላጎት የ ሕመማችን መንስኤ ነው !!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ሁለቱ የተማሩ ሰዎች


በአንድ ወቅት በጥንታዊቷ አፍቃር ከተማ አንዳቸው የሌላኛቸውን
ትምህርት የሚነቅፉና የሚያጥላሉ ሁለት የተማሩ ሰዎች ይኖሩ ነበር:
አንደኛው የጣዖታትን መኖር ሲክድ ሌላኛው በበኩሉ ያምናል
አንድ ዕለት በገበያ መሃል ይገናኙና ስለ ጣዖታቱ መኖርና አለመኖር
መከራከር ይጀምራሉ፡፡ ለሰዓታት ያህል ከተጨቃጨቁ በኋላ ይለያያሉ፡፡ የዛኑ
ዕለት ምሽት አላማኙ ወደ መቅደስ ሄዶ ከመሰዊያው ፊት በመቆም እስከዛሬ
ላጠፋው ጥፋት ይቅርታን ለመነ፡፡
በዚያው ሰዓት በአምላካቱ የሚያምነው ሌላኛው ሰው ቅዱስ መፃህፍቱን አቃጠላቸው::

ለካ ወደ አላማኝነት ተለውጦ ኖሯል፡

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

እንደ ንብ ማር ማምረት ካልቻልክ  እንደ ዝንብ አር ላይ ትውላለህ!!!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

እርስ በእርሳችን የማንግባባ  የማንዋደድ የማንደጋገፍ ከሆነ  ከማን ጋር እና መቸ መግጠም እንዳለብን በትክክል ካላወቅን አደጋ ነው !!

✋✋✋✋✋✋✋✋✋✋✋✋✋

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

የ ሰላም ንጉሥ ሆይ

ሰላምን ስጠን

ሰላምን አፅናልን


'ኦ ንጉሰ ሰላም

ሰላምከ ሀበነ

ወአፅንዐ ለነ ሰላምከ'


አሜን !!!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ስለአንተ እንባ ኢትዮጵያ በቅርቡ ወደ ነበረችበት ከፍታ ትደርሳለች። በየመድረኩ ስለ ኢትዮጵያ ሰላም ስለ ኢትዮጵያ ሕዝቦቹ አንድነት እና ፍቅር ከልብህ አልቅሰሀል። መንግሥትን በግልፅ ስለ ሰላም ስትል እያለቀስክ ሞግተሀል። ብዙ ጊዜም አልቅሰህ አስለቅሰኸኛል። እንባህ ከልብህ እንደሆነ ሁኔታህን አይቼ ተረድቻለሁ። የፍቅር የሰላም አባት እግዚአብሔር እንባህን ተመልክቶ ሀገራችንን ሰላም ያደርጋል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ። እንባህ ተቆጥሮልህ በከንቱ ደማቸው የፈሰሰ ንጹሀን የ ኢትዮጵያ ሕዝቦች በተለይ የአማራ ሕዝብ ሰላሙ  ፍቅሩ አንድነቱ ይመለሳል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ ። መላው ኢትዮጵያ ከዳር ዳር በ 2015 አንድ ሆኖ በፍቅር በሰላም ይኖራል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ። ከልብህ ስለምታለቅስልን እግዚአብሔር የጠየከውን ጥያቄ ሁሉ መልሶልህ በደስታ ረጅም ዕድሜ ያኖርህ ዘንድ እመኛለሁ ።

ተፃፈ ከመምህር ኤፍሬም ብርሃኑ   ለአርቲስት ደሳለኝ ሀይሉ

ነሐሴ 15 / 2014 ዓ.ም

Читать полностью…
Subscribe to a channel