fidelmeznagna | Unsorted

Telegram-канал fidelmeznagna - ብርሀን Revelation

-

የመዝናኛ እና የመረጃ ገጽ

Subscribe to a channel

ብርሀን Revelation

ምን ያህል ቀናት እንዲያልፉ ተመኝቼ ነበር: የራሴው እድሜ መሆኑን ዘንግቼ...
ራማድ አብዱ

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ስኬታማ ሰወች የሚሰሩትን ያቅዳሉ ያቀዱትን ደግሞ በአግባቡ ይተገብራሉ።

Successful people plan their work and implement their plans properly

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ውይይት ለመጀመር መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች
1. አእምሯችሁን አስፉት
2. ጭቅጭቅ ውስጥ አትግቡ
3. ጣልቃ አትግቡ
4. አመለካከታችሁን ከመግለፃችሁ በፊት የሌላውን ሀሳብ አድምጡ
5. ያልገባችሁን ነገር እንዲብራራላችሁ ጠይቁ
6. አታጋንኑ
7. የማሳመን ጉጉት ይኑራችሁ፣ ሀይለኛ አትሁኑ
8. መረታት ካለባችሁ እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ ሁኑ
9. በተራ ነገሮች ላይ ለዘብተኛ ሁኑ፣ በመርሆች ላይ ግን የፀና እቋም ይኑራችሁ
10. ክብርን የሚነካ ጉዳይ አታንሱ
11. ተቀናቃኛችሁ ክብሩ ሳይጐዳ ገለል የሚልበት ደስ የሚያሰኘው መንገድ ጥረጉለት፡፡
12. ከጠጣር ቃላትና ለስላሳ የመከራከሪያ ነጥቦች ይልቅ ለስላሳ ቃላትና ጠጣር የመከራከሪያ ነጥቦችን ተጠቀሙ
አንድን አላዋቂ በጭቅጭቅ ድል መንሳት አይቻልም፡፡ ጠንካራ እና መራራ ቃላቱ ደካማ ጐኑን ያመላክታሉ።

ካነበብኩት

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

አንድን ሀሳብ መንቻካና የማይፈታ ሀሳብ የሚያደርገው የአንተ
ከአዕምሮህ ጋር መቆራኘት ነው፡ አንድ ሀሳብ በአዕምሯችን እየተንከላወስ ምንችክ ሲልብንና እርሡን ለማስቆም አለመቻል ስቃዩ መራር ነው፡ እኛ ግን ይህን ኣንረዳውም፤ ምክንያቱም ሁሉም ሰው ማለት ይቻላል የዚሁ ነገር ሠለባ
ነውና፡ ስለሆነም በሀሳብ መዋጥ እንደ ኖርማል(ልከኛ) ተቆጥሯል፡ ይህ የማያባራ የአዕምሮ ሁከት ከሰዋዊ ማንነት መነጠል የማይችለውን ለሰዋዊ ማንነት ገፀ በረከት የሆነውን ውስጣዊ ስክነትና እርጋታን እንዳታገኝ ከልክሎሀል በተጨማሪም የፍርሀትንና የስቃይን ድባብ የሚያጭር አዕምሮ ሠራሽ የውሸት ማንነትን ይፈጥራል፡

ካነበብኩት

መልካም ቀን

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

አልፎ አልፎ መጠኑ ይለያይ እንጂ ሁላችንም በኑሮአችንና
በዕለታዊ ሥራችን ጣዕም የምናጣበትና ስልችት የሚለን ጊዜ አለ። ከዚህ ስሜት ነጻ የሆነ ሰው ማንም የለም: አንዳንድ ሰዎች ከዚህ ስልችት ከሚል ሕይወት ነጻ ለመውጣት ሲሉ በመጠጥ፣ በሀሺሽ፣ በቴሌቭዥን፣በሲኒማና እነዚህን በመለሳሰሉት ነገሮች ላይ ሰፊ ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ፤ እንዲሁም ብዙ ገንዘባቸውን ያጠፋሉ። ይሄ ስሜት
እየቀጠለና እያደገ ሲሄድ፣ ቀስ በቀስ ካሉበት ሕብረተሰብና ከእውነት እየሸሹ እንዲሄዱ ስለሚያረጋቸው የአዕምሮ ጭንቀት ይደርስባቸዋል።
የአዕምሮ ጭንቀት የስሜት መለዋወጥ ብቻ ሳይሆን፣ የእዕምሮ፣
የስጋና እንዲሁም የስሜት ድክመት በአንድ ላይ ሲደማመር ነው።
ራሰችንን « ዋጋ የለኝም» ብለን እሰከአልጣልንና ተስፋ እስከልቆረጥን ድረስ የተለያዩ ችግሮችንና ፈተናዎችን በትዕግሥት ማለፍ እንችላለን በራሳችን ተሰፋ ከቆረጥን ግን አቋማችን የታሰረ ይሆናል።
የዕምሮ ጭንቀት የጥንት ሰዎች እንደሚያምኑት በአማልክት
ወይንም እርኩስ መናፍስት በሰው ላይ የሚያመጡት በሽታ ብቻ
አይደለም። በሰው ላይ ሊደርሱ እንደሚችሉት በሽታዎች፣ ማለትም እንደ እንጀት፣ ኩላሊት፣ የልብ ወይንም ሌሎች ዓይነት በሽታዎች የተለየ አይደለም። የሚያሳዝነው ይኼኛው በሽታ መድኃ ኒት ቢኖረውም መድኃ ኒት እንደማይገኝለት መምሰሉ ብቻ ነው፡ ይሁን እንጂ በአዕምሮ ጭንቀት ውስጥ የተያዙ ሰዎች አስፈላጊውን ዕርዳታና ህከምና ካገኙ መዳን ይችላሉ።

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

እዉነት እልሻለሁ እናት ኢትዮጵያ ፍቅርሽን እና እናትነትሽን ጠጋ ብሎ ላየዉ ልብን የሚያርድ እና የሚያንሰፈስፍ
ነዉ ፤ ላንቺ ዉለታሽን መመለስ ከቶ አይታሰብም፡፡ ልጆችሽ ሳናዉቅበት አንቺንም ሳናዉቅሽ እየኖርን ነዉ እንጂ ፈጣሪ በስስት
የሚያይሽ የአይኑ ብሌን የምድር ገነት ፤ ነፍስ የዘራብሽ የበኩር ልጁ ነሽ፡፡ ተፈጥሮ ያደለችሽ ያለምንም የአየር ማቀዝቀዣ እና
ማሞቂያ የተመቻቸ አየር ያለሽ ፤ የዉሀ ጋን የምትባል የአባይ ምንጭ ፤ የሰዉ ዘር መነሻ የእነ አርዲ እና ድንቅነሽ መገኛ ፤
የኤርታሌ እሳተ ገሞራ መናሀሪያ ፤ የዘሩትን የሚያፈራ አፈር ባለቤት ፤ በአጭሩ ፈጣሪ አለምን ሲፈጥር አዳልቷል ቢባል
በመጀመሪያ ደረጃ ላይ የምትቀመጪዉ የኛዋ እንቁ ነሽ፡፡
ኢትዮጵያችን በተፈጥሮ ብቻ አይደለም ህዝቦችሽም የሚያኮራ ባህል ፤ እምነት እና ታሪክ ያላቸዉ ፅኑዎች ናቸዉ፡፡
አንቺ ዉብ ሀገር ሆይ እስላም ከክርስቲያን ተዋዶ እና ተዋልዶ የሚኖርብሽ ምድራዊ ገነት ፤ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች
ለዘመናት ተከባብረዉ ፣ ተጋብተዉ በመቻቻል እና በፍቅር ሲኖሩብሽ የቆዩ ልዩ ቅድስት ሀገር ፤ ለጥቁሮች የነፃነት ፋና ወጊ
እና ጎህ ቀዳጅ የሆኑ ዜጎች ባለቤት ነሽ።

ከመፅሀፍት አለም

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ጠየም አድርጉት፤ እንደ ባለጌ ጥፊ ድርግም አይደረግም›› አሉ ሌላ አስተያየት ሰጭ፡፡
‹እኮ ምን እንባል?, አሉ ሰበሳቢው፡፡
‹‹ሌሎቹ ሠርቶ አደር፣ አርብቶ አደር፣ ወቶ አደር፣ አርሶ አደር ከተባሉ እኛም ነጥቆ አደር ነው መባል ያለብን
ይኼው ጸደቀ፡፡
‹‹የሕዝቡ ምሬት ጨምሯል፡፡ ሕዝቡ በሌቦች መማረሩን በተደጋጋሚ እየገለጠ ነው፡፡ አንድ ቀን መሣሪያ ቢያጣ እንኳን አካፋና ዶማ ይዞ መነሣቱ አይቀርም፡፡

ከተንተከተከ እሳቱ ጨምሮ
ክዳኑን ይገፋል የፈላበት ሽሮ

ሲባል አልሰማችሁም፡፡ ያን ጊዜ ደግሞ ለሁላችን መግቢያ ቀዳዳው ጠባብ ነው የሚሆነው፡፡ ለዚህ ጉዳይ እኛው ራሳችን መፍትሔ ማምጣት አለብን›› አሉ ሰብሳቢው፡፡
‹ስንናገር ለይተን መናገር አለብን፡፡ ሌባ ሁሉ አንድ ዓይነት አይደለም፡፡
ኩሩ ሌባና ልክስከስ ሌባ፤ ጨዋ ሌባና ባለጌ ሌባ፤ ሸቃጭ ሌባና ኢንቨስተር ሌባ፤ ነጥቆ ሂያጅና ነጥቆ ገንቢ፤ ገፋፊ ሌባና ለካፊ ሌባ፣እየተባለ የሚዘረዘር ብዙ ዓይነት ሌባ ነው ያለው፡፡ በስመ ሌባ ሁላችንም መሰደብ የለብንም» አሉ አንድ የታወቁ ሌባ፡፡

ሰብሳቢው የተገረሙ ይመስላል፡፡የጫቸውን በጃቸው ይዘው ‹‹እኔም የእናንተን ያህል ባይሆንም መቼም በዚሁ ስም ተጠርቼበታለሁ፡፡ አሁን የዘረዘርከው ግን ምንድን ነው አሉት:
ሰወዬው ዕውቀት በጠየቁ ወንበሩ ላይ ተገላብጦ ተቀመጠና
ጉሮሮውን ጠራርጎ፤ መቼም ዕውቀት ማካፈል ደስ ይለኛል፡፡ ኩሩ ሌባ ማለት ከሚሊዮን በታች የማይነካ፤ ዝም ብሎ በመቶውም በሺውም የማይልከሰከስ ነው፡፡ ልከስክስ ሌባ ደግሞ የዚሀ ተቃራኒ ነው፡፡ ጨዋ ሌባ ማለት ደግሞ ሲሰርቅ በሕጉ መሠረት የሚሰርቅ ማለት ነው፡፡ ሰነድ አዘጋጅቶ፣ ጨረታ አጣርቶ፣ ማስታውቂያ አሠርቶ፣ ቃለ ጉባኤ ያይዞ፣ ዕቃ ገቢ አድርጎ የሚሰርቅ ማለት ነው፡፡ ባለጌ ሌባ ደግሞ የዚህ ተቃራኒ ነው፡፡ ኢንቨስተር ሌባ ገንዘብ የሚቦጭቀው ከትላልቅ ኢንቨስትመንቶች
ብቻ ነው፡፡ መጉመድ እንጂ መጉረስ የማያውቅ ቆፍጣና፡፡ መጉረድ እንጂ መቁረጥ ያለመደ ጀግና፤ መቦጨቅ እንጂ መንጨት የማያውቅ ሆደ ሰፊ ማለት ነው፡፡ ሸቃጭ ሌባ ግን ከገቢውም፣ ከወጭውም
ከሱቁም፣ ከኅብረት ሱቁም የሚቀነጣጥብ ቀነጣጣቢ ነው፡፡ ነጥቆ ሂያጅና ነጥቆ ገንቢ ስለሚባሉት የሌባ ዓይነቶች በደንብ መግለጥ አለብኝ፡፡ ‹‹ነጥቆ ሂያጅ ሌባ ማለት ካገኘ በኋላ እዚህ ሀገር የማይቀመጥ
ሌባ ነው፡፡ ይኼ ዓይነቱ ሌባ ለሀገሪቱ ዕድገት ዕንቅፋት ነው፡፡ የሀገሪቱን ገቢ ወደ ባዕድ ሀገር የሚያሸሸ ከሐዲ ሌባ ነው፡፡ የሀገር ፍቅር ስሜት ፈጽሞ የሌለው ሌባ ነው፡፡ እዚሁ ነጥቆ እዚሁ መብላት ሲባል ሀገሩን............ በ ዳንኤል ክብረት

ክፍል ሶስት እና የመጨረሻው ይቀጥላል

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ለተወሰነ ቅጽበት እራስህን ለማንበብ ሞክር:: ህይወትና አኗኗርህይመስላል?
በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለኸው?
ምን አይነት ስሜት እየተሰማህ ነው? በጭንቅላትህ ውስጥ የሚተራመሰው የሀሳብ
ግርግር ምንድን ነው?
እናም በዚህ ቅጽበት አእምሮህ በምን አይነት መንገድ እንደሚሰራ ተመልከት:: አእምሮህ ነገራትን ሲተነትን፣ ሲጠቀልል፣ ሀሳቦችን
ሲያመነዥግ፣ ሲመረምር ትኩረት ሰጥተህ ለመከታተል ሞክር፡፡ ይህን
የማድረግ ተሰጥኦ ለሰውና ለሰው ብቻ የተሰጠ ሰብአዊ ጸጋ ነው፡: ከሰው
በስተቀር ይህን የማሰብ የማሰላሰልና እራስን የመመርመር ተሰጥኦ
የሚያውቅ ምድራዊ ፍጡር የለም::

እንኩዋን ደስ አለህ !!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

የቀኑ ጥያቄ መልስ   መ    ኔዘርላንድ የሚለው ነው

ቀጣይ ማምሻ ጥያቄ

White house  የአሜሪካ ነው

Blue house is for.......

A/ Germany

B/ north Korea

C/ vietnam

D/ south korea

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

የቀኑ ጥያቄ መልስ C congo የሚለው ነው። ስለተሳተፉ እናመሠግናለን።

መማማራችን ይቀጥላል።

የምሽቱ ጥያቄ👇👇👇👇👇👇👇


በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ሀይቆች መካከል አንዱ የ ጣና ሀይቅ መሆኑ ይታወቃል።

ጥያቄ

ጣና የሚለው ቃል ትርጉም የትኛው ነው?

A/ ሰፊ

B/ ብዙ ውሀ ያለው

C/ ጥልቅ

D/ ቅርብ

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

አስቸኳይ በጣም ቀላል የሽልማት ጥያቄ አሁን ኦንላይን ላላችሁ ብቻ

መልስ መስጫ ሊንክ ከታች ያለውን ይጠቀሙ

@fogremover

የሚሸለሙ ሰወች ሶስት

የተሰጠ ደቂቃ አምስት

ጥያቄ

በረሀ የማይገኝበት ብቸኛ የአለማችን አህጉር ማነው??

ይፍጠኑ

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ፍልስፍና የሚለው ቃል ከግሪኩ Philos»/ፊሎስ/ማለትም ፍቅር እና፣
«sophos»/ሶፎስ/(ጥበብ)የተገኘ ውሁድ ነው።በቀጥታው የጥበብ ፍቅር
ወይም ፍቅረ ጥበብ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
በመሆኑም ጥበብ እና ፍቅርን መውደድ የፍልስፍና መሰረታዊ ትርጉም ነው።
ፍልስፍና በአንዳንድ ሰዎች አገላለፅ ፍልስፍና የአንድን ነገር ምንነት ለመረዳት
በጥያቄ የሚጀምርና በማሰላሰል ውስጥ ትክክለኛ መረዳትን ለማግኘት የሚደረግ
የሀሳብ መመላለስ ነው።
በመሆኑም ፍልስፍና
እውቀትን፣እውነትን፣ጥበብን መውደድ፣መሻት፣መመርመር ተብሎ ሊተረጎም
ይችላል።ባንድ በኩል ወደ ጥበብ የተሳበ፣ጥበብን የወደደ እንደዚሁም
የጥበብ ባለሟልን የሚያመለክት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ጥበብን ወዶ
ሌላውም እንዲወድ ምክንያት የሚሆን ለማለት
ይውላል።

ይመቻችሁ  !  ብርሃን ለሁሉም  !!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

የ እውነት ከሆነ እጅግ አስገራሚ ነው ። ተከታይ ለማፍራት ተብሎም ከሆነ እጅግ ያሳዝናል !!! እስኪ ተመልከቱት

ለማንኛውም





ክፋትን የመሥራት ዕድል በቀን መቶ ጊዜ ነው፣ ነገር ግን በዓመት ኣንድ ጊዜ መልካም ነገርን የማድረግ ዕድል አለን፡፡ የጋራ አስተሳሰብ ውስጥ ብልህነት ብቃት ነው።''

በጋራ እንለወጣለን !! በአዲስ አስተሳሰብ እንሞሸራለን !!!!!!!!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

"ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ይባላል"
እኔም እላለሁ የሚያነብ ሰው 2(ሁለት) ዘመን ይኖራል ።
1,የራሡን ዘመን አሁንን ይኖራል።
2,ከሚያነባቸው መፅሐፍት ደራሲያን (ሊቃውንት) ጋር ደሞ ያለፉ ዘመናትን ይኖራል።
ደራሲያን ደሞ 3 ዘመንን ይኖራሉ።
ዛሬን ፣ ነገንና ያለፈውን ይኖራሉ።
አላማ የሌለው ንባብ የለም ንባብ አላማ አለው፦
#ለመረዳት
#ለማወቅ
#ለማገናዘብ እና ለመለወጥ ይጠቅማል።እጅ የደራሲ ስም እየሸመደዱ ለጉራ መሆን የለበትም።
እየመረጥን እናንብ።


ደራሲ ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ።

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ሕዝብን የሚያዳምጥ መንግሥት፤
መንግሥትን የሚያዳምጥ ሕዝብ
Uገር ሰላም እንድትሆን፤ ሰላም ሆና በብልጽግና ጎዳና እንድመትራ
ከተፈለገ ሁለት ነገሮች ያስፈልጓታል፡፡ ሕዝብን የሚያዳምጥ መንግሥትና መንግሥትን የሚያዳምጥ ሕዝብ፡፡ ማዳመጥ ከመስማት
ይለያል፡፡ መስማት ጆሮ ለተፈጠረለት ሁሉ የሚቻል ነወ፡፡ ይህን ጽሑፍ ስናነብ እንኳን ስንትና ስንት ድምፆችን ፈልገንም ሳንፈልግም
እንሰማለን፡፡
ማዳመጥ ግን ሦስት ነሮችን ይፈልጋል፡፡
ይሁነኝ ብሎ መስማት፣ ሰምቶ ማስተዋል፣ እና አስተውሎም መመለስን፡፡

ከመጽሐፍ የተወሰደ

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ሰላም ለሁላችን !! የጥይት ድምጽ የማይሰማባት ሀገር ምንኛ የታደለች ነች??!!!!!!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ዝንብ


ዝንብ እንደ ንብ ሆና ማር እሰራ ብላ
ከቆሻሻ ርቃ ጣፋጩን ልትበላ
አበባ ፍለጋ ሜዳ ወጣችና
አልጥም አላት ማዕዛው ያበቦቹ ቃና
ዝንብም እንዲህ አለች በንቦች ተገርማ
አቤት ሽታ አየን አበባ ሲገማ
እግር ቢጥላቸው ወደ እኛው ከተማ
ይቀስሙ ነበረ ከሽታው አውድማ
ከቆሻሻ ጠረን ከሚሰነፍጠው
አንድ ቀን ቢቀምሱት ንቦች ሁሉ ዘልቀው
ሰክረው ያብዱ ነበር ቀፏቸወን ለቀው

ከመፅሀፍ የተወሰደ

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

በዚህ አለም ላይ ከብዙ ሰዎች የተሰወረ አንድ አስገራሚ ስሌት አለ፡፡ አንድን ጤና-ቢስ ነገር የማሸነፊያው መንገድ ያንኑ ወይም ተመሳሳይ ጤና-ቢስ ነገር በማድረግ አይደለም፡፡
ለምሳሌ፣ ጨለማን በሌላ ጨለማ ማሸነፍ አይቻልም፡፡ ጨለማን የምናሸንፈው ተቃራኒው በሆነው በብርሃን ነው: ቁጡን ሰው በትእግስት እንጂ በቁጣ
አታሸንፈውም፡፡ ወሬኛን ሰው በዝምታ እንጂ በወሬኛነት አታሸንፈውም፡፡ ከሰዎች ጋር ባለንም የግልጽነት ጎዳና ሂሳቡ እንዲሁ ነው:፡ ሰዎች የሚያሳዩህን “ቆሻሻ” ባህሪይ
የሚያስንቅ “ንጹህ ባህሪ በማሳየት አሸንፍ እንጂ የእነሱ ጤና-ቢስ አካሄድ አንተንም ወደ ጤና-ቢስ ምላሽ ውስጥ እንዲከትህ አትፍቀድለት፡፡

ከመፅሀፍ ላይ የተወሰደ

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

እንደ መግቢያ

እጦቴንም ሙላቴንም የትም መፍጨቴን እንጂ ዱቄት ማምጣቴን› እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ብቻ ስልቻዬን ይዤ መጣሁ፡ስፈጭ ስከካ ነው የኖርኩት። የለዘዘውንም…ቃ! ያለውንም... ብቻ ከላዬ ፈስሶ ያገኘሁትን ስሜት
ሰንበት አዘቦት ሳልል ስፈጭ ነበር- መጅ በላዬ ላይ ሳመላልስ፡፡
ይሄው ከቋቴ ስር የለገትኳትን፤ ስልቻዬን ይዤ መጣሁ፡
ንፋስ የበላው ስሜት አይታጣም ቋቱን ትቶ የተበተነ፡፡
ሌላ ስሜትም ይኖራል- የወፍጮው ዓይኖች ውስጥ ተቀብሮ የቀረ።ጥሬ ስሜት ይኖራል- መጅ አምልጦ የወደቀ፡፡ ልዝ ስሜትም
አይጠፋም- ሾልኮ ዱቄቱን የተቀላቀለ፡፡።።።❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

የአንድ መፅሀፍ ጥፍጥ ያለች መግቢያ ነች። ከተረዳነው ብዙ መልእክት ያለው ምርጥ መግቢያ ነው።

መልካም ቀን

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ተነሳሽነትን የሚገድሉ ምክንያቶች
❖ ተገቢ ያልሆነ ወቀሳ
❖ ገንቢ ያልሆነ ትችት
❖ በህዝብ ፊት መዋረድ

ሌሎችን ለማነሳሳት የሚረዱ አንዳንድ ነጥቦች
❖ ዕውቅና መስጠት
❖ አክብሮት ማሳየት
❖ በውዴታ እንዲሰሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
❖ ጥሩ አድማጭ መሆን
❖ ግቦቻቸውን ለይተው አንዲያውቁ ማበረታታት
❖ የዕድገት ዕድሎችን መፍጠር
❖ማሰልጠን
❖ የውድድር ስሜትን ማሳደር
❖ ሰዎችን መርዳት

ከመፅሀፍ ላይ የተወሰደ

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

የመጨረሻ ክፍል ይሄው




ከድቶ ወጥቶ የሚበላ፡፡ እኛ ወጥቶ በል ሌባ›› ብለነዋል፡፡ ነጥቆ ገንቢ ሌባ ግን አገር ወዳድ ሌባ ነው፡፡ እዚሁ ነጥቆ እዚሁ ፎቁንም ፋብሪካውንም፣ ሆቴሉንም፣ እርሻውንም ይገነባል፡፡ ለሀገሩም አጥብቆ
ያስባል፡፡ እዚሁ ነጥቆ እዚሁ የሚሊዮን ብሩን መኪና ያሽቃብጠዋል። እዚሁ የመቶ ሺ ብር ውስኪ ያወርዳል፡፡
ነጥቆ ገንቢ ሌባ ደግ ሰው ነው፡፡ ሃይማኖተኛ ከሆነ ከነጠቀው ገንዘብ ወይ ለቸርች ወይ ለገዳም ይሰጣል፡፡ ነዳያንን ያበላል፡፡ ድሃ ይረዳል፡ሃይማኖተኛ ካልሆነ ደግሞ ለወጣት ማኅበራት ይለግሳል፤ለቀበሌ ቲሸርት ያሠራል፤ በዓል ስፖንሰር ያደርጋል፤ እንዲህ ያለው ነጥቆ ገንቢ ሌባ ሊበረታታ ይገባዋል፡፡ ግን ምን ያደርጋል የሀገራችን የኢንቨስትመንት ዐዋጁ በቂ ማበረታቻ ለዚህ ሀገር ወዳድ ሌባ አይሰጥም፡፡
በመጨረሻ የማብራራላችሁ ገፋፊ ሌባና ለካፊ ሌባ» ስሰሚባሉት
ነው፡፡ ገፋፊ ሌባ ማለት ሥጋ ሲበላ አጥንት የማያስቀር፤ እንጀራ ሲበላ
ሞሰብ የማይተርፈው፤ ሻይ ሲወስድ ከነ ብርጭቆው፤ የደራሲውን
ድርሰት ወስዶ የደራሲውን ስም የሚያጠፋ፤ ሚስቱን መንጠቁ ሳያንሰው
ባሏን የሚገድል፤ መሬትህ ላይ ባለ ዘጠኝ ፎቅ ሊሠራ አንተን
በዘጠነኛው የኮንዶሚኒየም ፎቅ ላይ የሚወረውርህ፣ሃምሳ ዓመት
የኖርክበትን ቤት ወስዶ ከከተማው ሃምሳ ኪሎ ሜትር አውጥቶ
የሚጥልህ ማለት ነው
ለካፊዎቹ ሌቦች ዝም ብለው ነው፡፡ እዚህምእዚያም ለኮፍ ለኮፍ ነው የሚያደርጉት፡፡›
ሰውዬው ማብራሪያውን ሲጨርስ አድናቂዎቹ እየሳቁ አጨበጨቡ፡፡
ሰው የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩት ያህል ይስቃል ይባል የለ፡፡
ታድያ አሁን መፍትሔው ምንድን ነው?»  አሉ ሰብሳቢው ነገሩ
ውስብስብ ብሎባቸው፡፡ አንዱ እጁን ኣወጣ፡፡
ለችግሩ መባባስ ዋነኞቹ ተጠያቂዎች ከመሐልና ከታች ያሉት ሌቦች ናቸው፡፡ አሁን እኔ ኩሩ ሌባ ነኝ፡፡ ልስረቅ አልስረቅ ሰፊው ሕዝብ አያወቅም፡፡ እይውልዎት፣ መንደር መንገድ ላይ ያለችውን ዛፍ የሚቆርጠውን እንጂ ደን ውስጥ ያለውን ዛፍ የሚቆርጠውን ማንም አያየውም፡፡ አሁን ለኛ ችግር የሆኑብን የመንደር ዛፍ ቆራጮች ናቸው፡፡ ለካፊ ሌቦች ከስኳሩም፣ ከጨውም፣ ከድንቹም፣ ከሸማቾቹም
ይቀነጣጥቡና ሕዝሱን ያነሣሡታል፡፡ ሕዝቡኮ ስኳሩ ወደ ሸማቾች ከገባ በኋላ አለቀ ሲሉት እንጂ መጀመሪያውኑ ወደ ሸማቾች ባልመጣው ስኳር ላይ አይበሳጭም፡፡ ሃምሳ ኩንታሉን ወስደን ሃምሳውን ኩንታል ሩብ ሩብ ኪሎ ብናከፋፍለው ተመስገን ብሎ _ ነው ወደ ቤቱ የሚሄደው፡፡ ሥራው ግልጽነት ያለው እንዲመስል ደግሞ የመጣውን ሃምሳ ኩንታል ከሴቶች፣ ከወጣቶችና ከአዛውንት ኮሚቴዎችን አሰልፎ እኩል እንዲያካፍሉ ማድረግ ነው፡፡

‹ልክ ነው፡፡» አለ አንዱ ሰርቆ አደር ኢንቨስተር ‹‹ሕዝቡ መብራት
ተቆራረጠብን አለ እንጂ የመብራቱን ኬብል እነማን ናቸው ከውጭ
የሚያስገቡት ብሎ ጠየቀ? ዱቄቱ ወደ ሸማቾች በብዛት አልመጣም አለ
እንጂ፤ ዱቄቱን እነ እገሌ ብቻ ለምን ከውጭ ያስመጣሉ? ብሎ ጠየቀ?
አልጠየቀም፡፡ ኮንዶሚኒየም በትክክል አልደረሰኝም አለ እንጂ፤ እነ እገሌ
የከተማ ቦታ በካሬ 300 ሺሕ ብር የሚጫረቱት ብሩን ከየት ቢያመጡት
ነው ብሎ ጠየቀ አልጠየቀም፡፡ እገሌና እገሌ የተባሉ ዋና አከፋፋዮች
ለምን አስወደዱብን ?ለምን አሳነሱን? አለ እንጂ ግን እነርሱ የውጭ
ምንዛሪ ከየት እያገኙ ነው ዕቃውን ከውጭ የሚያመጡት? ብሎ መች
ጠየቀ፡፡ ስለዚህ ችግሩ ከታች ያሉት አቀባባይ ሌቦች አሠራሩን
ስላላወቁበት ነው ማለት ነው፡፡ አያችሁ ሕዝቡ የዋሕ ነው፡፡ በጥፍርህስትቧጭረው ጥፍሩን ቁረጡልኝ ነው የሚለው፡፡
ሰውዬውኮ የቧጨረው ጥፍር ስላለው አይደለም፡፡ በጥፍሩ እንዲቧጭር የሚያዝ ጭንቅላት ስላለው ነው፡፡ ሕዝቡ የቧጫሪውን ጥፍር አስቆርጦ ወደ
ቤቱ ይገባል፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ቧጫሪው ዝም ይላል፡፡ ቆይቶ ግን ጥፍሩ
ሲያድግ መቧጨሩን _ ይቀጥላል፡፡ መጀመሪያ ጥፍሩን ያሳደገው
ተቧጨር ብሎ መብት የሰጠው ማን ሆነና፡፡ አሁንም ያስቸገሩን ራሶቹ
አይደሉም፡፡ ጥፍሮቹ ናቸው፡፡» አንደ ድጓ አድራሽ በሊቃውንት ፊት
ዕውቀቱን ያስመሰከረ መስሎት ትከሻውን ሰበቀ፡፡


ሰብሳቢው ግራ እየገባቸውም ቢሆን ሐሳቡን እንጠቅልለው፤ መቋጫ
ሐሳበ አምጡ አሉ፡
ሁለት ሰዎች ተረዳድተው ያዘጋጁትን የአቋም መለጫ ይዘው ወጡ፡፡
እነርሱ የአቋም መግለውን ሲያቀርቡ ተሰበሳቢዎቹ ወረቀትና
እስክርቢቶ አዘጋጁ፡፡
አንደኛ፡- ኅብረተሰቡ ስርቆትን እንዲጠየፍ ስለ ስርቆት በመገናኛ ብዘኃን
ትምህርት ይሰጥ፤ (ይኼ ሲነበብ አንድ _ አምስቱ በቲቪና ሬዲዮ
የሚቀርበውን ማስታወቂያ ለመሥራት እንዴት ከባለ ሥልጣናቱ ጋር
እንደሚሠሩ ተንሾካሾኩ፤ አንድ ሁለቱ ደግሞ በእነርሱ ሬዲዮ ጣቢያ
ይህን ፕሮግራም ለመሥራት የስፖንሰር ገንዘብ ሲቦጭቁ ታያቸው፡፡)
ሁለተኛ፡- በየቀበሌውና በየደረጃው ሕዝቡ ሌቦችን እንዲያጋልጥ
ይደረግና ርምጃ ይወሰድ፤ (የተወሰኑት ተሰብሳቢዎች ለቀበሌ ተሰብሳቢዎች
ሞንታርቦ፣ ውኃና ኮፍያ ያለ ጨረታ ለማቅረብ ተጠቃቀሱ፡፡)
ሦስተኛ፡- ሌብነትን የተመለከተ ዜማ በታዋቂ አርቲስቶች እንዲዘጋጅ
ይደረግ፤ (አርት ነክቶናል የሚሉ ነጥቆ አደር አርቲስቶች የሚዘጋጀውን
የፀረ ስርቆት ቅስቀሳ ከእነርሱ እንዳይወጣ መላ ዘየዱ፡፡)
አራተኛ፡- ስለ ስርቆት አሰከፊነት የሚያስተምር ቢል ቦርድ በመላ ሀሪቱ
ይተከል፤ (የማስታወቂያ ድርጅት ያላቸው ተሰብሳቢዎች ይቺ ፕሮጀክት
ከኛ አታልፍም ብለው ማሉ፡፡)


አምስተኛ፡- የፀረ ስርቆት ቀን በየዓመቱ ይከበር፡፡ (ቲሸርት ኮፍያ
መድረክና መስተንግዶ የሚያቀርቡ ተሰብሳቢዎች ዓመታዊ ገቢ ተገኘ
ብለው ጮቤ ረገጡ)
ተሰብሳቢዎቹ ሲወጡ የአዳራሹ ዘበኛ በሐዘን ለጓደኛቸው ‹‹በሬ ሞተና ፍትሐት ሲፈታ ከበሮው ድምፁ እንዳይይማ ትሽ፣ ትሽ፣ ትሽ ይል ጀመር፡፡ ከዚያ በፊት እድም! እድም! እድም ሲል ይሰሙት የነበሩት
ጽናጽንና መቋሚያ ምነው ዛሬ ያለወትሮህ ድምፅ እንዳይሰማ ትሽ
ትሽ፣ ትሽ ትል ጀመር? ብለው ቢጠይቁት የሞተው በሬ፤ የሚመታው
የበሬ ቆዳ ሆኖበኝኮ ነው፡፡ እንዴት ከበሬ ቆዳ ተሠርቼ በሬ ሞተ ብዬ
ከበሮ ልምታ አላቸው ይባላል ብለው ተረቱ፡፡

በ ዳንኤል ክብረት

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ሰሞኑን በአዲስ አበባ አንድ ትልቅ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ የአዲስ አበባ
ደረጃ አንድ ሌቦች ስብሰባ ድርገው ነበር፡፡ የስብሰባው መሪ ቃል
‹‹የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ሌቦች ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?›› የሚል ነው፡፡ ስብሰባው እንደተጀመረ አንደኛው የታወቀ ሌባ እጁን አወጣና
‹‹መፈክሩ ላይ የተጠቀስንበት ስም ትክክል አይደለም፡፡ ገጽታችንን የሚያበላሸ ነው» ሲል አስተያየት ሰጠ፡፡ ጭብጨባ አዳራሹን ሞላው::
«ታድያ ምን ይሁን፤ መቼም ሌባ መሆናችን ርግጥ ነው አሉ ሰብሳቢው፡......... በዲያቆን ዳንኤል ክብረት

ክፍል ሁለት ይቀጥላል።

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

በብርሀን ቲዮብ ምን እንድንሰራ ይመክሩናል ??

A/ አጫጭር ልብወለድ

B/ ተከታታይ ትረካዎች

C/ ወቅታዊ መረጃወች

D/የስነ ልቦና መፅሀፍት

E/ የፍቅር መፅሀፍት

F/ criticism ( ትችቶች)


ሌላ የሚመክሩን ካለ ደግሞ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ቢፅፉልኝ ከታላቅ ምስጋና ጋር እቀበላለሁ

@fogremover

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

የምሽቱ ጥያቄ መልስ C ጥልቅ የሚለው ነው


ቀጣይ ጥያቄ

በአውሮፓ ለመጀመሪያ ጊዜ ቡናን ያስተዋወቀች ሀገር ማን ትባላለች

ሀ/ ኢትዮጵያ

ለ/ ብራዚል

ሐ/ አሜሪካ

መ/ ኔዘርላንድ

ሰ/ መልስ አልተሰጠም

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ሞባይልን ለመጀመርያ ጊዜ የተጠቀመች አፍሪካዉት ሀገር ማነች?
A. ኬንያ
B.ደቡብ አፍሪካ
C.ኮንጎ
D.ሞሮኮ

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ሰሎሜ በቃ እጹብ ትባላለች ። አለማችን የጎደለባትን ለመሙላት እንቅልፍ ካጡ ጥቂት ነፍሳት መካከል አንዷ ነች። የ ጎንደርዋ ቸር !! ገዳማትን ታግዛለች። አብያተ ክርስቲያናትን ትደግፋለች። ሃይማኖት ሳትለይ የተቸገሩ ወገኖቻችንን ታግዛለች። ደግ ተጫዋች ጥበብ አዋቂ ነች። ግጥሞቿ ደስስስ ይላሉ። ጎንደር ከተማ ላይ በርካታ የጥበብ መድረኮችን አዘጋጅታለች። ከ ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ጀምሮ እነ አለማየሁ ገላጋይ   አበበ ባልቻ     ዶክተር ወዳጄነህ መሀረነ   እና ሌሎች በርካታ ታዋቂ ሰዎች ጋር በጋራ ብዙ መድረኮችን ፈጥራለች።የብዙ ታወቂ ሰዎች ቁልፍ አጋርም ነች። ለስራ በተለይ ሰዎችን ለመርዳት ጊዜ አይወስድባትም። የጠየካትን ለመመለስ ፈጣን ነች። ቅኔም አዋቂ ነች።  ካለን ብናካፍል የአረጋውያን እና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ላይ ትልቅ ስራን እየሰራችም ትገኛለች።
ስለ ሶሎሜ ብዙ አልተባለም። ብዙም አልተነገረም። እኛም ሶሎሜን ለመዘከር የላከችልንን ወቅታዊ ግጥም እንዲህ አንብበን አዘጋጅተን ወደ እናንተ አድርሰናል።



ቪዲዮው ላይ በርካታ የ ሶሎሜ ፎቶወች ተካተውበታል። ግጥሙን እያደመጡ ፎቶወችን ይመልከቱ


ማንኛውንም አስተያየት ከታች ባለው ሊንክ መጻፍ ይችላሉ ።
👇👇👇👇👇👇👇

@fogremover

መልካም ሰንበት

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

እጅጉን ጎበዝ የሆኑ፣
እስከ ጥግ የተማሩ ነገር ግን ደግም ፈፅሞ ንቃተ ህሊና የሌላቸውን በርካታ
ሰዎች አውቃለሁ፡ ማለትም ሙሉ በሙሉ ከአዕምሯቸው ጋር የተቆራኙ
ማለት ነው፡ የአዕምሮ ግስጋሴና እንዲሁም የትየለሌ እውቀት መሳ ለመሳ
ከንቃተ ህሊና እድገት ጋር ካልተጣጣመና ሚዛኑን ካልጠበቀ እርግጥ ነው፣
ደስታ ቢስ የመሆኑ አዝማሚያ ፣ እንዲሁም ጥፋቱ እጅጉን የትየለሌ ነው፡

Many who are educated to the core but are not conscious at all
I know people, that is, they are completely connected to their minds
It means: the progress of the mind and also the knowledge of more
If it is not in harmony with the development of consciousness, if it is not balanced, of course,
It tends to be lazy, and the fault is very small.

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

አደገኛ !!
















አንድ ስለ ራሱ ዝቅተኛ አመለካከት ያለው ሥራ አስኪያጅ የደረጃ
ዕድገት አግኝቶ ወደሌላ የተሻለ ቢሮ ቢዛወርም አዲሱን ቢሮውን ሊላመደው
አልቻለም፡፡ ቢሮው ተቀምጦ ሳለ በሩ ተንኳኳ፡ ይህን ጊዜ በሥራ
የተጠመደ ለመምሰል ስልኩን አንስቶ መቀበጣጠር ጀመረ፡፡ የእንግዳውን
መቆም ምንም ሳይመስለውም የስልኩን እጄታ ከጆሮው እንደለጠፈ
ሲል ቆየና በመጨረሻ
በተደጋጋሚ “ምንም ችግር የለም! በአኔ ይተማመኑ”
“ደህና ይሁኑ!” በማለት የስንብት ቃል አሰምቶ ስልኩን ከዘጋ በኋላ
እንግዳውን “ምን ልታዘዝ?” አለው፡ እንግዳውም “እኔ እንኳን የመጣሁት
ስልኩን ለመስራት ነው” ብሎት ቀጥታ ወደ ስራው ገባ፡፡
ከዚህ ምን እንማራለን? ማስመሰሉ ለምን አስፈለገ? ምን ለማሳየት
ወይም ምን ለማግኘት ብለን ነው እንዲህ የምንሆነው? መዋሸት ምን
ይጠቅመናል? በሀሰት ጠቃሚ ሰው ብንመስል ምን እናተርፋለን? ሁሉም
እንደዚህ ዓይነት ስሜቶች የሚመነጩት ራስን ዝቅ አድርጐ ከመመልከት ነው ።

መጽሐፍ


በፍጹም ራስህን ዝቅ አድርገህ እንዳትመለከት !! በፍጹም !!

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

በቅንነት እና በፍቅር ክፋት ምቀኝነት እና ተንኮልን ከእኛ እናርቃለን። ብርሀን እና አዲስ መገለጥ በሕይወታችን ውስጥ አስፈላጊ ነገሮች ናቸው ። አሮጌ አስተሳሰብን ከእኛ ላይ እናራግፍ።

አዲስ ተስፋ አዲስ መንገድ አዲስ አስተሳሰብ ያስፈልገናል።

ከእናንተ ወደ እኛ ከእኛ ደግሞ ወደ እናንተ ሃሳቦችን እንቀያየራለን። መጻሕፍትን በብዛት እንዳስሳለን።

ሰላም ለኢትዮጵያ ።

ብርሀን    መገለጥ   


ለሁላችንም ሰላም ይሁንልን

Читать полностью…

ብርሀን Revelation

ስለዚህም ‹ይህንን ወይም ያንን ሐሳብ ለምን ትሰጣላችሁ፤ እኛ የምንላችሁን ብቻ አራምዱ የሚሉ አካላትም ወደ
በአታቸው ሊመለሱ ይገባቸዋል፡፡
‹ጴጥሮስ ሆይ ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ› ሊባሉም ይገባል፡፡ የተለየ ሐሳብ
ያለውን ሁሉ ማውገዝ ፍቅርን ከማሻከርና የቤት ሥራ ከመጨመር በላይ ጥቅም እንደሌለው በቅርብ ጊዜ ታሪካችን
የተማርን ይመስለኛል፡፡
እናም ‹ሁሉም ወደየበኣቱ ይመለስ›

ከዳንኤል ክብረት መጽሐፎች ውስጥ ከአንዱ

Читать полностью…
Subscribe to a channel