በትምህርት አለም ሁሌም ጀግና የነበረ ሰው ሁሉ ከትምህርት አለም በሁዋላ ጀግና እንደሆነ ይቀጥላል ማለት አይቻልም። ሁሉም ነገር ሊጣፋበት ይችላል።
ስለዚህ ከትምህርት ጎን ለጎን ሌሎች የህይወት ልምዶችን ማዳበር የምንችልበት እድል ሊፈጠር ይገባል።
ካነበብኩት የተወሰደ ሀሳብ ነው
#እሁድ_ቁርስ
ለእራስህ_ነው!
፨፨፨/////፨፨፨
ቅዱስ መፅሐፍ የአክብሮትን አስፈላጊነት " ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።" በማለት ያስተምራል። ሰውነት ደግሞ ክቡር ነው፤ ማንም ይሁን ማን በሰውነቱ ብቻ የሚገባው ክብር አለ። ብዙ በደል የፈፀመ፣ እጆቹን ለእርዳታ የሚዘረጋ፣ ጎስቋላ ደሃ እንደሆነ የሚሰማው፣ በሰዎች ፊት ምስኪንና ምንም እንደሌለው ተደርጎ የሚታሰብ፣ ካለው አቅም አንፃር ደካማ፣ ካለው እውቀት አንፃርም አላዋዊ የተባለ ሁሉ ከሚለካበት መስፈርት በላይ ሰውነቱ ይበልጣልና እንደማንኛውም ሰው ክብር ይገባዋል። ካንተ እንዲወሰድ የማትፈልገውን የሰውነት ክብር፣ የታላቅነት ክብር፣ የወላጅነት ክብር ከሰው ላይ አትውሰድ። ሁሌም ልጅነት የለም፣ ሁሌም ህፃንነት አይኖርም፣ ዘወትር በተረጂነት አትቀጥልም። በሂደት ነገሮች ሲቀየሩ ታያለህ፤ እያደረ እድገትህን፣ ብስለትህን ትመለከታለህ። ዛሬ የምታደርገው ድርጊት ነገ እንዳያስቆጭህና ዋጋ እንዳያስከፍልህ ተጠንቀቅ።
አዎ! ጀግናዬ..! ለሰዎች መስሎህ እንጂ የምታደርገው እያንዳንዱ ነገር #ለእራስህ_ነው። ታላላቆችህን ብታከብር የምትከበረው እራስህ ነህ፤ ለቤተሰብህ ትኩረት ብትሰጥ የምትጠቀመው አንተው ነህ፤ የያዝከውን ትምህርት በሚገባ ብታነብ ውጤቱ የእራስህ ነው። ማንንም ለመጥቀም ሳይሆን ለእራስህ ብለህ ግብረገብ ሁን፤ ማንንም ለማስደሰት ሳይሆን ለእራስህ ደስታና እርካታ ብለህ ከሰዎች ጋር በፍቅር ኑር። ያንተ ህይወት ባለቤት እግዚአብሔር ነው፤ ነገር ግን እራስህን ታስተዳድር ዘንድ ባንተ ለይ የሾመው ደግሞ አንተ እራስህን ነው። ጥሩ ሰው መሆን የምርጫ ጉዳይ ነው፤ መጥፎና ክብር የሌለው ሰው መሆንም እንደዛው። ውጫዊ ጫናዎችህ እራስህን እንዳትቆጣጠር ሊያደርጉህ ይችላሉ፤ የእድሜህ ጉዳይ ለስሜታዊነት ሊያጋልጥህ ይችላል፤ በአቋራጭ ውጤት ለማምጣት መፈለግህ ከባዶቹን መንገዶች እንዳትከተል ሊያደርግህ ይችላል። ነገር ግን በዚህም ሁኔታ ውስጥ ሆነህ ያንተ ጉዳይ አንድና አንድ ነው። ለእራስህ ብቁ ሆነህ እራስህን ማስከበር።
አዎ! "ህይወት አዙሪት ናት" ይላል የዶ/ር አለማየሁ ዋሴ መፅሃፍ መርበብት። ዞረህ ዞረህ፣ ኳትነህ ኳትነህ መጨረሻህ እዛው የጀመርክበት ስፍራ ነው። ለቤትህ አስቸጋሪ፣ ለሰዎች ክብር የሌለህ፣ ስረዓት የጎደለህ፣ ታላቅህን በንቀት የምታይ፣ የወገንህ ችግር የማይገባህ፣ የማንም ህመም ግድ የማይሰጥህ፣ የስሜትህ ባሪያ ሆነህ የምትቀጥል ከሆነ በአንድም በሌላም እንዲህ አይነት ሰው ማግኘትህ አይቀርም። በሰፈርከው ቁና ይሰፈርብህ ዘንድ፣ በፈረድክበት ልክ ይፈረድብህ ዘንድ የግድ ነው። የተፈጥሮ ህግ ላንተ ሲባል የሚቀየርበት ምክንያት አይኖርም። ቅንነትህ ለእራስህ እንደሆነ አስብ፤ መታዘዝህ፣ አክብሮትህ፣ አጋዥና ደጋፊነትህ ሁሉ ለእራስህ እንደሆነ አስታውስ። ለማንም መልካም ብታደርግ ካረክለት በላይ አንተ ያደረከው የእግዚአብሔርን በረከት፣ የአምላክህን ስጦታ ትቀበላለህ፤ ካሰብከው በላይም በሲሳዩ ትሞላለህ።
#እሁድ_ጉሩም_ድንቅ_ቀን_ይሁንልን!
.... 🙏🙏🙏
ምንጭ :- ካነበብኩት
ሙሉጌታ ዋሴን እናመሰግናለን
ብለህ ፃፍበት ታሪክ ተሰራ
ታምራት ቶላ የ ፓሪስ ማራቶንን አሸነፈ!!!!!!!🍓🍓🍷🍷🍷❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
የአለማችን ትልቅ የማራቶን ታሪክ ዛሬ ተፈፀመ!!!!!!
እንኳን ደስስስስስስስ አለን !!!!❤❤❤❤❤❤
ሊመጣ ነው! ሲሉኝ
የሰላም የደስታ - የጥጋብ ዘመን
የት ደርሷል ስላቸው ? ተቃርቧል እያሉኝ
መች ይመጣል'ም? ስል ተዳርሷል እያሉኝ
ይሄው አርባ አመቴ በናፍቆት አለሁኝ
ወይ ዘመኑ መጥቶ በደስታ አላሻረኝ
ናፍቆቱ ናፍቆቱ ናፍቆቱ ገደለኝ !
ፌስቡክ ላይ የተወሰ
ማሣሠቢያ:
😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊
ከዛሬ ጀምሮ
1.. ተስፋ የማይቆርጡ ሰወችን ፈልገው እንደምንም ጓደኛ ያድርጓቸው። የህይወት ተሞክሮአቸውንም ጠይቀው ይረዱ
2.. ሌሎች ሰዎች ሲጨነቁ ጭንቀታቸውን እንዲያስወግዱ በሀሳብም ጭምር በቅንነት ይርዱ
3..በተቻለወት መጠን ' ሲያስጠላ ' የሚልን ቃል አይጠቀሙበት። የፊትዎ ቅርፅ ይበላሻል
4... መጥፎ ባህርይ ካለብዎት አሁኑኑ ለማስተካከል አንድ እርምጃ ይጀምሩ
5... የሰው ገንዘብ በፍፁም አይንኩ
6... በፍጹም አያስመስሉ
ይቀጥላል
ብዙ መጥፎ ልምዶቻችን በቀላሉ የማይለቁን ቢሆንም ለህይወታችን አደገኛ ሊሆኑ ስለሚችሉ አሁኑኑ ልንታገላቸው እና ከእኛ ህይወት ውስጥ ጨርሶ ልናስወግዳቸው ይገባል !! ቀጠሮ አያስፈልግም!!
Читать полностью…አለማወቋን እውቅና ሰጡት !
( ካሊድ አቅሉ)
ድንኳን ተጥልዋል ሰው ጢም ብሎ እያጨበጨበ ትልቅ መድረክ ላይ በባለዙፋን ወንበር ተቀምጣ ጋውንና ኮፍያ ይዛ እጇን ምታንቀሳቅሰውን ተመራቂ ተማሪ ይመለከታል ። አብሮ አደጎች ነን ቤታችን ጎን ለጎን እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል አንድ ትምህርት ቤትና አንድ ክፍል ነው የተማርነው እኔ ጤናን መርጬ ፓውሎስ ስገባ እሷ ሶሻል ሳይንስ መርጣ በእካውንቲንግ ተምራ ዛሬ ነው ምርቃትዋ ። በስርዓት ገብታ ከተማረችበት ቀን በላይ ትምህርቱን ወድቃ የደገመችባቸው (Add class) ይበልጥኑ ይበዛሉ ።
የምርቃትዋ ቀን ስለምትለብሰው ጋውን ቁመት ስለምትነሳቸው ፎቶ አነሳሶች ነበር ጭንቀትዋ ግን ዛሬ ተማረች በቃች ብሎ ቤተሰብ ውሮ ወሸባዬውን ያደምቃል ። " እንዴ የተማረ ሰው አይደለሽ እንዴ " የመባልን ጎራ ህዝብ ገፍቶ በሷም የመብት ፍላጎት ተቀላቅላለች ።
ስጦታው ለጉድ ይዘንባል በስጦታ ወረቀት ታሽጎ ። እናት ትመርቃለች አባት ምኞቱን ደስታ ባፈነው ድምፅ ያስተጋባል ፤ እኔ ባለችኝ መሰረት ወደነሱ ቀርቤ በስልኬ ቪድዮ እና ፎቶ አስቀራለው ድንገት አንድ ሀሳብ ብልጭ አለብኝ ስንቱ ይሆን በጋውን ካባ በኩል አለማወቁን ሸፍኖ ያሳለፈ ፤ስንቶች ይሆን ካባ አታሉዋቸው የስንቶችን አለማወቅ እውቅና የሰጡት ፤ መንገድ በሳተ ብሄል ተገፍተን ማወቅ ማለት መመረቅ ነው ብለን እውቀትን ከዩንቨርስቲ ቅጥር ግቢ ብቻ የፈለግን ...
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
@kalidakelu
ሙጃ ትውልድ........
.......
.......
.........
........
በነዱት የሚነዳ ምክንያቱን ሳይረዳ ሲለቀስ የሚያለቅስ ከሞቀው የሚዘፍን መውደዱ ጭፍናዊ
ሌሊት ያየውን ህልም ጥዋት የማያስታውስ ራሱን የማይገስጽ ሥልጣኔንና ሁዋላ ቀርነት ለይቶ የማያውቅ
ተዝካር በልቶ አመት ድገሙ የሚል ውል የጠፋበት ትውልድ ፤ ሙጃ ዝም ብሎ ሙጃ ራስ ወዳድ
በግምት የሚኖር አ
እንደጎርፍ አንድ ላይ ተያይዞ የሚነጉድ ሲጮሁ ያንኑ ደግሞ የሚጮሁ ገደል
ማሚቶ : የሰው አድናቂና ተመልካች የሚጠቅመውን እና የሚጎዳውን ለይቶ የማያውቅ ኮሽ ባለ
ቁጥር የሚደነብር ደንባራ ባልሰራው ስራ የሚኮራ ሳይኖረው የሰው ብር የሚቆጥር ያልጠየቁትን
የሚጃፍት ጃፋታም ትውልድ.... ምን ይባላል?
?????????
ዓሊ ዓለሙ ሃሰን
ከመፅሀፍ ላይ የተወሰደ
የመኖር ትርጉሙ
የመኖር ትርጉሙ
የንባ ቅብብል ነው፥ በትውልዶች ማሀል
አባትህ ያነባው፥ ላንተም ይደርስሃል፤
ስው የሆንሁ ለታ፥ ደርሶኛል ይህ አጣ
አልቅሼ አንደገባሁ
አስለቅሼ ልውጣ።
ከመፅሀፍት
መነበብ ያለበት !!!!!!😊😊😊😊😊😊😊
ምስጋና
ሠላም ያዋልከኝ ... ሠላም አሳድረኝ ለነገው አንተ ታውቃለህ፡፡ ከፉውን አርቅልኝ .. መልካሙን
ሁሉ አቅርብልኝ፡፡ ከሀጢያቴ ይቅር በለኝ፡፡ እፈራለሁ. ስለምፈራህ ሳልወድ በግድ ማረኝ አላለሁ፡፡
የሚያቃጥል እሣት ባይኖርህ ፣ ባትቆጣ፣ ባትቀጣ ኖሮ እንዲህ አልለማመጥህም ነበር፡፡ መቸም ሁለት
ትልልቅ አይኖች አሉህ፡፡ ሠማይና ምድር... ከሁለቱ የሚሠወር አንዳች ነገር የለም፡፡ ፈጣሪ አምላኬ
የማደርገውን ሁሉ ታያለህ፡፡ ከምታየው ሁሉ የእኔዋ ኢምንት ናት፡፡ ለቅጣትም አታበቃኝ፡፡ እኔ ያንተው
ደካማ ፍጡር ለፍቼ ፣ ቆፍሬ ፣አንተን አምኜ ባንተ በረከት የምኖር ጥርንቁስ ነኝ፡፡ እነዛን እነዛን ባየህበት
አይን እንደማታየኝ እርግጠኛ ባልሆንም እንደሰው መንግሥት ያንተም መንግሥት በጭቁናን ላይ የግፍ
ፍርድ ትፈርዳለህ ብዬ አልገምትም፡፡ ከሆነ ግን እኔና መሰሎቼ የት አባታችንስ እንደርሳለን፡፡ የበሰበሰ
ዝናብ አይፈራምና የገሃነቡን ኑሮ እዚሁ አሁን ላይ በመጠኑ ስለምናውቀው እንደፍቃድህ ይሁን ብለን ዝም
እንላለን፡፡ ዝም ካልን .. ከዚህም እንቀምሳለን፡፡ አንተም አትለቀንም፡፡ አንተና ሃያላን መንግሥታት
የሚሳናችሁ ነገር የለም፡፡ ጀግኖች፣ ሰጭና ነጣቂ ናችሁ፡፡ ከሃያሎቹ አልፈው አቤቱታ ወዳንተ
የሚያመጡትን ልጓማቸውን ብታጠብቀው እንጅ አታላላቸወዏ፡፡ ገንዘብን አብዝተህ ከደሀ ነጥቀህ..
አብዝተህ ለሐብታም ትሰጣለህ፡፡ ሃብታም አይፀድቅም፡፡ እናንተ ግን ገነት ናችሁ እያልክ ታሞኘናለህ፡፡
እባክህን ለነገው አንተ ስለምታውቅ በመርፌ ቀዳዳ ባላልፍም እስከዛው ግን ቆንጠር አድርገህ ስጠኝ፡፡
በግድ እንድወድህ ፈርቼ እንድለምንህ ያደረከኝን በውዴ ወድጀህ ተረጋግቼ እንዳመሰግንህ ታደርግልኝ
ዘንድ እለምንሀለሁ፡፡
ከመፅሀፍት ጓዳ
እንደዚህም ይባላል ¡¡¡¡¡¡¡
ሴቶች ባይኖሩ ኖሮ እኛ ወንዶች የሙሉ ጊዜ ሥራችን ጦርነት
ብቻ ይሆን ነበር፡፡ ዓለማችንም የጦርነት አውድማ ትሆን
ነበር፡፡ የሮማው ንጉስ ክላውዲዮስ ሁለተኛ የአገሩ ወንዶች ወደ
ጦርነት አንዘምትም ሲሉት አስቦ አሰላስሎ የደረሰበት መፍትሄ
ወንዶች ከሴቶች ጋር የፍቅርና የትዳር ህይወት እንዳይኖራቸው
መከልከል ነበር፡፡ ንጉስ ክላውዲዮስ ፍቅርና ትዳርን የሚከለክል
ህግ ያወጣበት ምክንያት ወንዶች ወደ ጦርነት እንዳይዘምቱ
የሚያደርጋቸው የሴቶች ፍቅር ነው በሚል ነበር፡፡ ትክክል ነው፡፡
ህይወት ጣፋጭና አጓጊ እንድትሆን ወሳኝ ሚና የሚጫወቱት
´´ሴቶች ናቸው፡፡ ወንዶች በሴቶችና በልጆች ፍቅር ይንበረከካሉ፡፡
ንጉስ ክላውዲዮስ ፍቅርና ጋብቻን በሞት ቅጣት ደንግጎ
ቢከለክልም ወንዶች ሴቶችን ከማፍቀርና በድብቅ ከማግባት
አልተቆጠቡም፡፡ ቄስ ቫሌንታይን ለፍቅረኛሞች ቀን(ቫሌንታይንስ
ዴይ)መታሰቢያ ሊሆኑ የቻሉትም በዚህ ንጉስ ዘመን በድብቅ
ፍቅረኛሞችን ሲያጋቡ ተይዘው በመገደላቸው ነው፡፡
በአጠቃላይ ሴት ልጅ ውበት ነች... ፍቅር ነች… ስኬት ነች
ጣፋጭ ነች. ህይወት ነች... ለኑሮህ እጅግ እጅግ በጣም
ታስፈልግሃለች፡፡
ጥያቄው ለስኬትህና ለደስተኛ ኑሮህ ምክንያት
የምትሆን ሴት እንዴት ታገኛለህ? ነው።
👉👉👉ንዴቴን ፈራሁት👈👈👈👈👈
በዳይ በአማን ሲኖር - ዕድሉ እንዳማረ
የተበደለ ሰው - አንጀቱ እንዳረረ
በስኳር ደም ብዛት - ሲሞት እያየሁት
ካናደደኝ ይልቅ - ንዴቴን ፈራሁት ...
ከመፅሀፍት አለም
መውደድ አለመውደድ ደግሞ በእጅወ ነው!!
👉👉👉👉ሰሞነኛ👈👈👈👈👈
በሌለ ቅዳሴ ሰሞነኛ በዝቶ ስንዴ እንዲወረዛ
እንደ ዘኬ ቆሎ ዝና እየተነዛ
ትናንት የጉድ ተብሎ ለዛሬ ጠነዛ
ማታ ተድመንምኖ ጧት ሆነብን ጤዛ፡፡
ፅዋ እንደሚረከብ ያቦ ባለተራ
እንዳፈረሰ ቄስ የፅጌ ደብተራ
ስም ሰሞነኛ ነው ገኖ 'ሚሆን ተራ፡፡
ከመፅሀፍት ጓዳ
በነገራችን ላይ በባህላችን ከወርቅ በላይ የተከበረው ማእድን ብር ነው፤ ገንዘባችንን ብር ብለን የጠራነው ለዚህ ነው፤ በሰርግ ወቅት “ ወርቅ አምባር ሰበረልዎ “ ተብሎ ሳይሆን “ ብር አምባር ሰበረልዎ” ተብሎ እንደሚዘፈን አንርሳ፤ ትልቅ ዋጋ ያላቸው ነገሮች ውስጥ “ብር “ እሚል ቃል አይጠፋም፤
ለምሳሌ-
ክብር
ደብር
ነብር
ወዘተረፈ
እንዲህ ብየ በመጽናናት እሁዴን ቅደሜ ላድርገው ፤
በውቀቱ ሰዮም
እሰይ....እሰይ....እሰይ....እ'ሰየው ደስአለኝ
ፍንድቅድቅ አልኩ ይቺ ምድር ጠበበችኝ
የኔ የምላት የልቤ ሰው ቀና ብላ ባይኗ አየችኝ
ደስ አይልም????
እስማኤል አሰለፍ አየለ
ሀገሬ ኢትዮጵያ እዘኝ በዕድልሽ
አሸብር ተብትቦ ይኸው ገደለሽ!!
-----
በጣም ነው የተሰማኝ በእውነት! ይህ ነው የጥሩዬ ሌጋሲ? የደራርቱ ሌጋሲ እንዲህ ነው?የነሐስ ሜዳሊያ እንኳ ብርቅ ይሁንብን? የሴቶች 10,000 ሜትር ውድድር የኢትዮጵያ ክብር መለኪያ ነበር። ነገር ግን ስለስፖርት ምንም በማያውቁ አመራሮች ሳቢያ ሁሉም ነገር እየጠፋ ነው።
ያሳዝናል በእውነት!!
አፈንዲ ሙተቂ
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ #በሕግ መጠየቅ አለበት!
#Ethiopia | “የፓሪስ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያን አንገት ያስደፋ ነው፤ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ #በሕግ መጠየቅ አለበት”
- ሻለቃ አትሌት ሐይሌ ገ/ሥላሴ
በመናኸሪያ #ምልከታ
አርብ ነሐሴ 03 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋድ 4፡00-6፡00 ይጠብቁን
ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን
የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ቀጥት ከ ፌስቡክ ላይ የተወሰደ
ያለምንም የስፖርት እውቀት በእጅ ብልጫ ብቻ በተደራጀ 49 የማይረባ የ ካቢኔ ስብስብ የ ዚህ አመት የ ኦሎምፒክ ውድድራችንን አደብዝዞታል። አሁን ባለኝ መረጃ መሠረት ኢትዮጵያ በዚሁ አመት በፓሪስ ኦሎምፒክ የደረጃ ሰንጠረዥ 49 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።😏😏😏😏😏😏😏😏
Читать полностью…እማማ አፀደ የሚባሉ ጎረቤት አሉን የእናቴ ጓደኛ ናቸው። እማማ አፀደ አመም አድርጓቸው ህመማቸው በባሰ ቁጥር እናቴን ጠሏት።
ይሰድቧታል ሌባ ናት ይላሉ።
መሰሪ ናት ይላሉ።
ልትገለኝ ትፈልጋለች ይላሉ።
መርዝ አበላቺኝ ይላሉ ። አትምጣብኝ ብለው ስሞታ ይናገራሉ ሌሊት እቤቴ ልትገባ ነበር ይላሉ ።
ሰው እንዳትመስላችሁ ይላሉ ። እናቴ ቤታቸው መሄድ አቆመች ።
ከቤት መውጣት እያቆሙ ግቢያቸው መዋል ጀመሩ ....
እናቴ እሷ መሆኗን አትንገሩ ብላ ፤ ምግብ ትልክላቸዋለች ። በእህታቸውን ልጅ ፤ ምን ጎደለ ጤናቸው እንዴት ነው እያለች ትሰልላቸዋለች...
ንዴት ሊገድለኝ ይደርሳል ። እቆጣታለሁ << ስምሽን እያጠፉሽ እየሰደቡሽ እየጠሉሽ አትተያቸውም ወይ?>> እላታለሁ!!
<<ጭንቅላታቸው እጢ ወጥቶባቸዋል እሱ ነው ትንሽ ቀየር ያደረጋቸው እንጂ ፤ እሳቸው እንኳን ሳልበድል ብበድላቸው እንኳን በክፉ አያነሱኝም>> ትለኛለች።
ምግብ ትልክላቸዋለች ። በእህታቸው ልጅ በኩል የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒት መግዣ ከኛ ወስዳ ... ተበድራም ቢሆን ትገዛላቸዋለች ። እሳቸው ያቺ ምናምንቴ ፣ ድግምታም ያቺ ነጠላ እያሉ ጮክ ብለው እናቴን ሲሰድቧት ይውላሉ ።
ጠላኋቸው !!
አንድ ቀን ለምን ግን እንዲ ስምሽን እያጠፉ እየጠሉሽ እያልፈለጉሽ አልጠላሻቸውም? ብዬ እናቴን ጠየቅኋት።
<<ጓደኛዬ ናቸው! እዚህ ሰፈር ስመጣ እሳቸው ናቸው ያለመዱኝ ። እድር ያስገቡኝ ፥ የሌለኝን እቃ ያዋሱኝ ፥ የተቆረቆሩልኝ ፥ የአረሱኝ ፣የመከሩኝ...
እንዲህ አይባልም እያሉ መንገድ ያሳዩኝ እርሳቸው ናቸው ። ድንገት ታመው ነው የተቀየሩት ።ከሁሉም ጋር ነው መጣላት የጀመሩት እኔ ላይ ትንሽ ጠንከር አሉ እንጂ ...
በክፉ ግዜ እንኳን ወዳጅ ላይ ጠላት ላይ አይጨከንም!!
የጨዋ ሰው ልክ የሚታየው ሲጣሉት ነው ። በፍቅር ግዜ ሰው አይመዘንም ክፉ ግዜ ነው ሰው የሚያጠለው ....
አፀዱ እንዴት አይነት ጥሩ ሰው መሰሉህ ዛሬ ህመም ተጣብቷቸው እን'ጂ ። ስንት ቀን መሰለህ እጦት በሳቸው ሳብያ ከቤታችን የተባረረው ።
አፀደ ደግ 'ሩህሩህ ናቸው...
እናንተ ሳትወለዱ ማንም ሳይኖረኝ ነው ከኔ ጋር የነበሩት...
የአፀደ ውለታ አለብኝ !>>
© Adhanom Mitiku
@WAS143
@WAS143
መረጃው ላመለጣችሁ እና ምናልባት የሚጠቅማቺሁ ከሆነ
........
..........
..........
እንኳን ደስ ያላችሁ
ኢምሬትስ ዛሬ ጥዋት ለ2 ወር የሚቆይ
የምህረት አዋጅ አውጥታለች
የምህረት አዋጅ ከ September 1 ጀምሮ
ለሁለት ወር የሚቆይ ሲሆን
ቪዛችሁ የተበላሸባችሁ ኢትዮጵያውያን ያለ ምንም ክፍያ ስፖንሰር ፈልጋችሁ
ቪዛ ማስራት ወይንም
ወደ ሀገር መሳፈር ትችላላችሁ
የኢምሬትስ መንግስት ይሄን እድል ያመቻቸነው ለሰዎች ባለን ሰብአዊነት ነውም ሲል ገልፆል
ስለዚህ የዚህ እድል ተጠቃሚ እንደትሆኑ ጉርሻዎች ጥሪያችንን እናስተላልፋፈለን
እዚህ ጋር
እንዴት ነው ?
የት ነው የምንሄደው ?
የሚለውም በሂደት መንግስት ራሱ ሲያሳውቅ የምናሳውቅ ሲሆን
በውሸት ቪዛ እንሰራለን ከሚሉ ሰዎች እንድትጥነቀቁ ከወዲሁ እያሳሰብን::
እንኳን ደስ ያላችሁ ግን ረጋ በሉ ማለት እንወዳለን
እንዲሁም ቪዛ እንደ ድሮ ብዙ ቀኖች ስላማይወስድ እስከዛ ድረስ በተረጋጋ መንፈስ ቪዛ የሚስራላችሁንን ጥሩ ሰው ነው የምትሉትን ሰው ጠይቁ::
እድሉን ከብዙ ዓመት ቆይታ በኃላ የመጣ እድል ስለሆነ ተጠቀሙበት
ለጏደኞቻችሁ ሼር በማድረገ አሰሙ::
ጉርሻ
🙏🙏🙏
🌴🌴🌴
አስታራቂ የለም
ጠብ ምድርን ባይሞላት
አቤል ባይፈጠር
አቤል ያቤል ጠላት
አቤል የራሱ ጠር
አንድ ሰው ከሁለት፥ ተከፍሎ ሲፋለም
ሸምጋይ
ወይ ገላጋይ
አሰታራቂ የለም።
ከመፅሀፍት ጓዳ
ለምሳሌ፡ እንደ ሀገራችን አነጋገር አንድ ልጅ ሲላክ እንቢ ካለ
ትርጉሙ አልሄድም ማለት ይሆናል፡፡ ነገር ግን በጦርነት ጊዜ
እንቢ ለሀገሬ ቢል ትርጉሙ እሄዳለሁ ይሆናል፡፡
ደግሞም አንድ ሰው ፍሬ ከርስኪ ቢባል የማይረባ የማይጠቅም
ለማለት ነው፡፡ ነገር ግን በግዕዙ ወቡሩክ ፍሬ ከርስኪ ሲል
የማህፀንሽ ፍሬ ቡሩክ ነው ማለት ይሆናል፡
ካነበብኩት
መልካም ውሎ ይሁንልን
ወዳኝ ነበር
ወዳኝ ነበር ያቺ ቆንጆ
ወዳኝ ነበር ያቺ እንስት
ልቧን ሳታጥፍ ያለ ስስት
እኔ ሞኙ ችላ ብላት
መች ከሀሳቧ አወጣችኝ
ፍቅርን ብላ ከልቧ ላይ ከዙፋኗ ሰየመችኝ
አዎን
ወዳኝ ነበር ያቺ የዋህ
የኔ ምስኪን የኔ እርግብ
እኔ ከንቱው መች ሰማኋት
የማትገኝ ሌላን ሳስብ
ነፍሷ ...ንጉስ አርጋኝ
ወደ እኔ ስትጓዝ እሷ አትከለክላት
እርባና ቢሡ እኔ
ይሄን ሁሉ እያየሁ መች ከቁብ ቆጠርኳት
ስትዘምረው ፍቅሯን እኔን ብቻ እያለች
ሁልጊዜ ስትጠራኝ አንደበቷ አይሰለች
የሴትነት ወጓን ከነምኑ ትታ
እወድሃለሁ አለች ልቤን ተመኝታ
እኔ ግን..............እኔ ግን
ጆሮዬን ነፈግኳት ዝም አልኩኝ እንደ ቀልድ
እሾህ ነሰነስኩኝ በእሷ የፍቅር መንገድ
ጎዳኋት በጣሙን ልቧን ሰባበርኩት
ፍቅርን ያህል ነገር እቃቃ አደረኩት
አሁን...........................
አሁን ግን እላለሁ ምነው ባደመጥኳት
እሺ ወይ አይሆንም ግልፁን በነገርኳት
ምን ያህል ጎዳኋት እያልኩኝ ማስታወስ
የእሷን ቁስል አይሽር እንባዋን አያብስ
አዎ አሁንም እላለሁ
ምነው እህ ብዬ አንዴ ባደምጥኳት
ያቺን የፍቅር እርግብ ቀርቤ ባቀፍኳት
ጊዜ ሀያል ነገር አይመልስ ትናንትን
ባይሆን ራሴን ልውቀስ ፍቅር የገፋሁትን
ፀፀትን መሸከም እንዲህ ካሳመመኝ
ያኔ ያሳመምኳትን መታመም ነው የምመኝ
ወዳኝ ነበር.........ወዳኝ ነበር
✍️እስማኤል አሰለፍ አየለ
😷😷😷😷😷😷😷
ሞቴ ሰው ላክብኝ
እንዳታጣኝ
ሞቴ ሰው ላክብኝ
መቼ እንደምትመጣ
እንድጠባበቅህ
ከቤቴ ሳልወጣ
ሰው ብታጣም እንኳ
ሌላው እስኪመጣ
ኣንተ ስራ ፈተህ
ወደ እኔ እንዳትመጣ፡፡
ናፋቂ ዜማወች
Like dislike በእጅዎ ነው😕 ነፃነት እንደልብ ነው በቤታችን
👉👉👉👉ሰይጣን የታደለው👈👈👈👈👈
ሰይጣን የታደለው
ሱሪው አያልቅበት፤ እህል አይቸግረው፡፡
-አይበርደው፤ አይሞቀው፡፡
---
ሰይጣን የታደለው!
--
---
ቀድሞ ቁርጥ ያወቀው
እፀድቅ - እኮነን ሲል የማይጨነቀው
ሰይጣን የታደለው!
ልጁ አያለቅስበት፤ ሚስቱ ልፍታ አትለው
ሰይጣን የታደለው!
ሱሱ 'ማይደቁሰው
· ጎጆ ማይቀልሰው
አፈቀርኩ
ብሎ
- አንገት ማይደፋው
--- ወሲብ ቅንዝርና ቂም ማያዳፋው
- የማያርስ የማይጎርስ የማይጎለጉለው
ሰይጣን የታደለው!
የስልጣኔ አባት
- መፈንቅለ መንግሥት
- ቀድሞ ያካሄደው
ከሰው ልጅም በላይ፣ ፈጣሪን የሚያውቀው
የፈጣሪን ምስጢር፣ አክስሎ የሞቀው
ባለውለታችን፤ ሊቁ መልአክ ሰይጣን፣ ከበለስ ጀምሮ
የተፈጥሮን ምስጢር ያምላክን ቋጠሮ
ለሰው አቀብሎ፤ ለሰው አንቆርቁሮ
ፈትኖ ፈታትኖ፣
ቀድሞ ተፈታትኖ፣
ሰውን ሰው ያረገው
ግልፁ ደግ መልአክ ሰይጣን የታደለው!
ጥርቅምቅሞሽ እምነት ተደፋ! ተወጋ ወደ ጥልቁ ውረድ! ሲለው የማይፈራዉ
እኔ ላይ ተባሮ እሷ ላይ 'ሚሰፍረው
ሙስሊም ክርስቲያኑ - ጴንጤ ኦርቶዶክሱ
ካቶሊክ - - -ዊትነሱ - ምዕመን መናፍቁ
--- ባለዛር ጠንቋዩ -- ድፍን ቅሉ ሊቁ
አስወጣሁት ሲለው ምንም የማይመስለው
ሳጥናኤል ታጋሹ ሰይጣን የታደለው
ሳጥናኤል ሉሲፈር ፀሎት አያደቀው ውዳሴ አያደምቀው
ጨለማ አይዘፍቀው ገነት አትናፍቀው፡፡
ሳጥናኤል ሉሲፈር ፍቅር የራበውን
ከልቤ ጠሊቅ ሥር ምናለ ብወደዉ
ጠላቴ ከሆነ - - ሰይጣን ወዳጄ ነው፡፡
እስኪ በዚህች እንኳ ታላቁን ልብለጠው
ልጁ ሲያስተምረን - ጠላቶቻችሁን ውደዱ ብሎ ነው፡፡
ምነዋ ይህች ቃል ለሱም የማትሰራው?
መቂያቂያም በቂም ልክ ቂሙን ቢደብቀው
ምነው የእሱን ሥራ የማይታረቀው?
ለሰው ልጅ ተሰቅሎ እጥፍ ለበደለው
ምነዋ ወዳጁን ይቅር ይብቃ ቢለው!?
(ለክርስቶስ ሰምራ፣ ወለዘይገርም ፍልስፍና ዘፎገራ)
አንቺዬ
እመጣለሁ ብትይ መሬት ምህዋር ሳተች
ፀሀይ ሞቃ ደምቃ የሰው ደም መሰለች
አዋፍት ዘመሩ ተቀኙት እንደ ጉድ
የዱር አራዊቶች ጀመሩ ጉድ ጉድ
እናም አንቺዬዋ
ይህ ሁላ ህላዌ አንቺን ብቻ እያለ
የተፈጥሮአችን ህግ ባንቺ ከጎደለ
የነበረ ሁሉ እንዳልነበር ሲሆን
ምናለ መምጣትሽ መዳኛችን ቢሆን
ስትመጪ ከሻርኩኝ ከከበበኝ ህመም
ነይ አድባሬ ሁኚ ሁሌ አንቺን ልሳለም
✍️እስማኤል አሰለፍ አየለ