............
ከእውነት አልዋሸሁም በጣም ናፍቀሽኛል
ብዙ እንዳስቀየምኩሽ ከልብ ይገባኛል
ምክንያቴ ብዙ ነው ከሰው ነጥሎኛል
ነጥሎም አልቀረ ደግሞ ያስናፍቀኛል
ይቅርታ እንድጠይቅ ውስጤ ገፋፍቶኛል
'ይቅርታ' አልኩሽ ይሄው ይድረስሽ ከፍቶኛል
ባዶነቴ ቢያሸንፍም
ሰው ነኝና ብሳሳትም
ይቅርታሽን ብፈልግም
ምክንያቱ አንሶሽ ቅር ቢልሽም
ኩራት ይዞሽ ባትመልሽም
ለፈለፍኩኝ ለማስረዳት ባይገባሽም
ውስጥ አምቄው እንዲበላኝ አልፈለኩም
✍ሀብታሙ
ከተላኩልን መካከል ለእናንተ የተመረጠ
እርስዎም @fogremover ላይ ይላኩልን እናስተናግዳለን!!
👉👉👉👉👉👈👈👈👈👈👈👈
አዲስ ነገር ፍለጋ ወዲያ ወዲህ ሲሉ ዘመናቸውን የሚጨርሱ ጥቂት አይደሉም፡፡ ግን አዲስ የሚመሰለው ሁሉ አዲስ አይደለም። ወይም ሲጨበጥ ባዶ ሊሆን ይችላል። በርግጥም ዐዋቂዎቹ እንደሚሉት የሚያብለጨልጨው ሁሉ ወርቅ አይደለም። በተለይ የሚያምን ሰው ረግቶ መጭውን ነገር ከፈጣሪው መቀበል አለበት፡፡ ያለበለዚያ በግሣንግሥ ይረታና ሕይወቱን ይጥላል። በዴማስ ሕይወት የሆነው ይህ ነው። “ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና፥ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል” 2 ጢሞ. 4:10፡
ከመፅሀፍት ጓዳ
በዚህ የ ቴሌግራም ቻናል ላይ እንዲለጠፍላቺሁ የምትፈልጉት መልእክት ካለ ይህን ሊንክ በመጫን
👉👉 @fogremover👈👈👈 ይላኩልን በእርስዎ ስም እንለጥፋለን።
ስምወትን መጥቀስ እንዳይረሱ !! እንማማር !!
እናመሠግናለን!!
ሕልምን ለአላጋጮች መንገር ከጥቅሙ ጉዳቱ
ያመዝናል። የዮሴፍ ወንድሞች
የዮሴፍ ወንድሞች “ሕልመኛው መጣ" የተባባሉት ስለሕልም ስለማያውቁ ሳይሆን ታላቆቹ እያሉ እርሱ የሚያልምበት እውነት ስላልተዋጠላቸው ነው። ዛሬም
እነርሱን የሚመስሉ ሰዎች በዙሪያችን ተኮልኩለዋል፡
በምክር ሰበብ ራዕይን ከሚገድሉ ሰዎች መራቅ የማንም ሳይሆን የባለራዕዩ ኃላፊነት ነው። ይልቁንም እኛ ከማያምኑት ጋር የሚኖረን ሕብረት ብዙ ማስተዋልና
ጥንቃቄ የሚያሻው ነው። “ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ
አትጠመዱ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት እለውና?
ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን
ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? ለእግዚእብሔር ቤተ
መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው?
ከመፅሀፍት ጓዳ
ብዙ ሰባኪዎች ምዕመኑን ማሳተፍ ይወዳሉ።
ለዚህም ይመስላል "አጠገብህ ላለው አንዲህ በለው፤ አሜን በሉ እንጂ” ወዘተ…የሚሉት።
ታዲያ አንድ ቀን አንዱ መጋቢ መዝሙር ሃያ
አራትን በቃሉ የሚያውቅ ሰው ካለ ተነሥቶ በቃሉ
እንዲወርደው ይጠይቃል። ለዚህም አንድ ወጣትና አንድ ሽማግሌ እጃቸውን ያነሣሉ። መጀመሪያ ዕድሉን ያገኘው ወጣት "እግዚእብሔር እረኛዬ ነው፤ የሚያሳጣኝም የለም ብሎ ይጀምርና እንደ ጥይት በመወንጨፍ ላስ ያደርጋታል።በዚህም ጉባዔው በብዙ አድናቆት ተሞላ። ሽማግሌው ግን እየተደናቀፉና አንዳንዴም እየደገሙ በቀሰሰተኛ ድምፅ ነበር
መዝሙሩን የወጡት። ሲጨርሱ ጉባኤተኞቹ በሙሉ እንባ አቅርረው ነበር። እናም መጋቢው ወደ ስብከቱ ከመመለሱ በፊት የተፈጠረውን ነገር እንዲህ ሲል ገምግሞታል። "ወጣቱ መዝሙሩን ጠንቅቆ ያውቀዋል፤ እሳቸው ግን ራሱን እረኛውን ያውቁታል!
እረኛውን ማወቅ
ከመፅሀፍት ጓዳ
ሌሎች. . .
1- ሌሎች ሲተኙ- አጥና
2- ሌሎች ሲያመነቱ- ወስን
3- ሌሎች ሲያልሙ- ተዘጋጅ
4- ሌሎች ዛሬ ነገ ሲሉ- ጀምር
5- ሌሎች ሲመኙ- ስራ
6- ሌሎች ሲያባክኑ- ቆጥብ
7- ሌሎች ሲያወሩ- ስማ
8- ሌሎች ሲያኮርፉ- ፈገግ በል
9- ሌሎች ሲያቋርጡ- ጽና
ይህ ነው ቢዝነስ ጥበብ!
ምንጪ ፌስቡክ
##### ል ብ ስ #####
ልብስን የፈጠረ ይሰበር እጅ እግሩ
የሰው ልጅ በራቁት ነበረ ማማሩ
ለምጣሙ እከካሙ በልብስ ተሽፍኖ
እስከ ጉዳጉዱ ሲተራመስ አብሮ
ሰው መሳይ በሸንጎ በልብስ ተደራርቦ
ጎቢጥ ከመለሰው ይቀመጣል አብሮ
ልብስ ባይለብስ ሰው እርቃኑን ቢወጣ
አደባባዮች ላይ ፀሀይ እንዴት በወጣ
ልብስን የሰራ ሰው እጅ እግሩ ቢሰበር
ትምክህትና ጉራ ዛሬ አይኖሩም ነበር።
ምንጭ መፅሀፍ
የሰው፡ ሙያ: ሦስት፡ ዐይነት፡ ነው፡፡
አንደኛው፡ ማሰብን፡ማወቅ፤
ሁለተኛው፡ መናገርን፡ ማወቅ፤
ሦስተኛው፡ መሥራትን፡ማወቅ፤
አብዛኞቹ፡ ብልኆች: የሚባሉ፡ ሰዎች፡ ከእነዚህ፡ ከሦስቱ፡ አንደኛውን፡ ብቻ፡ ነው፡ የሚይዙ፡ ወይም፡ መሥራት፡ ያውቁና፡ ትክክል፡
ማሰብ፡ አይችሉም፡ ይሆናል፡፡ ስለዚህ፡ ትክክል፡ ካለማስባቸው፡ የተነሣ፡ ደክመው፡ የሠሩት፡ ሥራ፡ ሁሉ፡ ይፈርሳል። ወይም ደግሞ፡
ንግግር፡ አሳማሪዎች፡ ዐሳባቸውና፡ ሥራቸው፡ ብላሽ፡ ይሆናል። ትክክል፡ ዐስቦ፡ ያሰበውን፡ ትክክል፡ አድርጎ፡ በቃል፤ ወይም፡ በጽሕፈት፡
አስረድቶ፡ እንዳሰበውና፡ እንደተናገረውም፡ አድርጎ፡ ትክክል፡ የሚሠራ፡ ሰው፡ እውነት፡ ትልቅ፡ ዐዋቂ፡ ነው፡ ሊባል፡ ይቻላል፡፡
አይደለም እንዴ???!
ከመፅሀፍ ላይ የተወሰደ ሀሳብ ነው
መልካሙን ሁሉ ያምጣልን መልካም አዳር !!!;;
በዓለም፡ ላይ፡ ትልቅ፡ ሥራ፡ ለመሥራት፡ የሚቻለው: ሠሪው፡ ሰውና: ለመሥራት፡ የተመቸበት፡ ጊዜ፡ እነዚህ፡ ሁለቱ፡ ሲገናኙ፡ነው፡፡ ትልቁን፡ ሥራ፡ ለመሥራት፡ የሚችለው፡ ሰው፡ ባልተመቸ፡
ጊዜ፡ ሲፈጠር፡ ሊሠራው፡ የሚችለውን፡ ሥራ፡ ሳይሠራው፡ መቅረት፡ግድ፡ ይሆንበታል። ልሥራም፡ ቢል፡ ጊዜው፡ እይደለምና፡ አይሆንለትም፡፡ ትልቅ፡ ሥራ፡ ለመሥራት፡ የተመቸ፡ በሆነበት፡ ጊዜ፡ ደግሞ፡
ሊሠራው፡ የሚችል፡ ሰው፡ ባለመፈጠሩ፡ መልካሙ፡ ጊዜ፡ በከንቱ፡ያልፋል፡፡ እነዚህም፡ ሁለቱ፡ ተፈላላጊ፡ ነገሮች፡ የሚገናኙት፡ በብዙ፡
ዘመን፡ ወስጥ፡ ጥቂት፡ ጊዜ፡ ነው፡፡
ታሪክ እና ምሳሌ
አብራቺሁን ቆዩ
ሻርኮች ውስጥ ኮኬይን ሲገኝ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ሻርኮቹ ውስጥ የተገኘው የኮኬይን መጠን ከሌሎች የውቅያኖስ እንስሳት ሲነፃፀር በ100 እጥፍ ከፍ የሚል ነው። ይህ እንዴት ሊሆን እንደቻለ አነጋጋሪ ከመሆኑም በላይ ጥናት እየተደረገ ነው።
ምንጭ bbc Amharic
የ ቁስቆሳ ጥያቄ
☺️☺️☺️☺️☺️☺️☺️☺️☺️
😜😜😜😜😜
ከሰውነታችን ውስጥ በጣም ጠንካራው እና ረጅሙ አጥንት የትኛው ነው ??
ሀ የ ክንድ
ለ የጀርባ
ሐ የትከሻ
መ የአከርካሪ
ሰ መልስ አልተሰጠም
የሽልማት ጥያቄ
ባህልና ቱሪዝም
ሽልማቱ የወንዶች የፀጉር ማሽን
የአጼ ፋሲል አብያተ መንግሥታት 12 በሮች አሉት
ከእነዚህ ወሰጠ በቀጥታ ከአደባባይ ተክለሀይማኖት ጋር የሚያገናኝ
ድልድይ ያለው ሆኖ አስቸጋሪ ነገር ሲፈጠር ነገሥታቱ በድብቅ ለመውጣት
እንዲያመቻቸው ታስቦ የተሠራ በር ነው፡፡
የበሩ ስም ማን ይባላል ????
እስከምሽቱ 3:30 ብቻ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን መልስ ይጻፉልን ።
ሊንክ
@fogremover
አንድ ወጣት የሚኖርበት ቤት እጅጉን የተዝረከረከ ነው።ክፍሉ ውስጥ የሚቀይራቸው ልብሶች: መመገቢያ እቃዎች:መፅሐፍቶች:ጫማዎች በየቦታው ተዘበራርቀው ያሉ ናቸው።በየጊዜው ይህ ወጣትአንድ ቀን አፀዳዋለሁ ብሎ ያልማል።ከዕለታት በአንዱ ቀን ክፍሉን በሚስብ መልኩ አፀዳው እና ደስ አለው።በሳምንት ውስጥ ግን ክፍሉ ወደነበረበት ወደዛው ዝብርቅርቅ ሁኔታ ተመለሰ።ወጣቱ የማፅዳት ግብ አለው ልማድ ግን በተቃራኒው።
አዎን ሁሌም ብዙ ግቦች ይኖረናል።ከዚህ በኋላ በደምብ ትምህርቴን አጠናለሁ የሚል ግብ ያለው ተማሪ የማጥናት ልምድን ሊያዳብር ግድ ይለዋል።ሰውነቴን በአካል ብቃት እገነባለሁ ብሎ ግብ ያነገበ ሰው የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ልምዱ ካላደረገ ግቡ መና እንደሚሆን አያጠያይቅም።
እርግጥ ግብ ማስቀመጥ ዋጋ ይኖረዋል ይሁን እንጂ ግቦቻችን በልማድ ወደ ተግባር ሊወርዱ ግድ ይለናል የምንፈልገውን ውጤት ለማግኘት።
ግብን በልማድ እንደግፍ የዛሬው መልዕክቴ ነው።
ቸር ውሎን ተመኘሁ።
የእናንተው Isam
📓ርዕስ :- ትዝታሽን ለእኔ ትዝታዬን ለአንቺ
📝ደራሲ :- እሱባለው አበራ
📅ዓ.ም :- 2012
📖የገፅ ብዛት :- 180
👩🦰አዘጋጅ :- ✨️...✨️
✍️አቅራቢ:- @ETHIO_PDF_BOOKS1
📌ማጋራት አይዘንጋ!
@ETHIO_PDF_BOOKS1
@ETHIO_PDF_BOOKS
@YETMHRTPDF
@BHERE_TREKA
😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊
አኑረን እንዳንል ኑረን ምን አፈራን ?
ግደለን እንዳንል እሳትህን ፈራን!
ፀሎቱ ጠፍቶናል በፈለከው ምራን ።
ገጣምያን የላኩልን ነው
ወዳጄ !!!!!!
😍😍
😍😍😍😍
😘😍😍😍
ከእኛ የሚያንሱትን እያየን እነርሱን ከማብጠልጠል ይልቅ የሚበልጡንን ለመፎካከር ነው መዘጋጀት ያለብን፡፡፡ በመንፈሳዊው ጉዞም ቢሆን የወደቁትን እንድናነሣ፣ ለደከሙት እንድንማልድና ያዘኑትንም እንድናጽናና ነው ጥሪአችን። " የደከሙትን እጆች አበርቱ፥ የላሉትንም ጉልበቶች አጽኑ ይላልና መፅሀፉ
ከመፅሀፍት ጓዳ
መልካም ጊዜ እንወዳችሁአለን
በዚህ የ ቴሌግራም ቻናል ላይ እንዲለጠፍላቺሁ የምትፈልጉት መልእክት ካለ ይህን ሊንክ በመጫን
👉👉@Fogremover👈👈👈 ይላኩልን በእርስዎ ስም እንለጥፋለን።
ስምወትን መጥቀስ እንዳይረሱ !! እንማማር !!
እናመሠግናለን!!
አዎን እጥራለሁ
. . .
ችግር አደናቅፎኝ
ልደርስ ካሰብኩበት ብቀር ወደ ኋላ
.
ለምን ተስፋ ልቁረጥ
ነገዬን እያሰብኩ እሞክራለሁ ሌላ
. . .
አዎን እጥራለሁ
ጎልያድን ቢያክል መከራው ቢገዝፍም
የተስፋ ጠጠሬን ሁሌም ከመወርወር
ለአፍታ አንኳ አልሰንፍም💪
29/12/16 2:21
✍️ እስማኤል አሰለፍ አየለ
አፈር ስሆን ተይኝ ፡ ባላውቅሽ ነው ጥሩ
ምን ብዬ ልንገርሽ ፡ ብዙ ነው ሚስጥሩ
ልቤ ዩናይትድ ነው : ለፍቅር አይመችም
ቶሎ ይሸነፋል ፡ ለዚችም ለዛችም
እንዴት እሆናለሁ ፡ ስትቀርቢኝ ብወድሽ
እድሌ አርሰናል ነው......
.
.
.
ለፍቼ ደክሜ ሌላ ነው ሚወስድሽ
ገጣሚ እንደልቡ
ያለፈ ታሪካችንን ምንም ልናደርገው አንችልም።😡
ነገር ግን ካለፈ ታሪካችን ጋር ተደብቀው የመጡ ጥቃቅን እና አደገኛ ልምዶቻችንን ግን ልናስወግዳቸው ይገባናል👍
ካነበብኩት የተወሰደ
ይድረስ
ይደርስ ለምወድሽ ይድረስ ለማከብርሽ
ስለ እኔ መባዘን ላፍታ ለማያምርሽ
መሠብሠብ ለማያውቅ የደግነት እጅሽ
ፍቅርን ለሚመግብ ቅን አሳቢ ልብሽ
ሀሴት ለሚያለብሠው ቆንጅዬ ፈገግታሽ
በጎ ብቻ አሳቢ ለሆነው ህሊናሽ
ከማር ለሚበልጠው ውቡ አንደበትሽ
ይህ ነው ለማልለው ህያው ስብዕናሽ
ይድረስ ብዬ የምለው አንድ መልክት አለ
በልቦናዬ ውስጥ ሠርፆ የበቀለ
እማ እናቴ
አንቺን ለማመስገን አንቺን ለማወደስ
ከቃላት መሀከል ውሎው የማይጠፋ
ከቁጥር ታዛ ስር ዘውትር የሚለፋ
ድንቅ አዋቂ ነኝ ባይ በአለም ቢታሰስ
ማን ይሆን ስለአንቺ አውርቶ የሚጠግብ
ወለታሽ አስክሮት በፍቅርሽ ታውሮ
ከልቡ የሚወጣን ግዙፍ ስንኝ ቋጥሮ
የመውደድሽን ጣም በልሳኑ የሚያረግብ
እማ እናቴ
ግጥሜን ስጀምረው ላንቺ ይድረስ ብዬ
ፍቅርሽ ያስተማረው የገዛ አይምሮዬ
እንዲህ ሲል መከረኝ
"ወዳጄ ሆይ ስማኝ አድምጠኝ ከልብህ
በእርግጥ መልካም ነው ይህንን ማሠብህ
ዳሩ ግን
ይቺን የሠውን ልክ አለም ባፈለቀው
እጅግ በዘመነው እጅግ በረቀቀው
በሺ ቃል ሺ ጊዜ ብታወዳድሳት
እውነት እልሀለሁ አትችልም ልትገልፃት
ስለዚህ
እሷን ለሸለመህ ለፈጠራት አምላክ
እንደዚህ በማለት ቃላቶችህን ላክ
"አምላኬ ሆይ አንተ እባክህን ስማኝ
ለንተ የማዋየው ጥብቅ ጉዳይ አለኝ
ከራሷ በማነሥ ሰው ያረገችኝን
ያላትን በሞላ የምታካፍለኝን
አንዲቷን እናቴን አንተ ጠብቅልኝ
የእድሜ ጤናን ካባ ዘውትር አልብስልኝ" "
መታሠቢያነቱ ለሁሉም እናቶች ይሁንልኝ።
📝 እስማኤል አሰለፍ አየለ
3/02/14 3:32pm
ደሰታ፡ ምንድን፡ ነው፡ ብለው፡ ቢጠይቁት፡ እንዱን፡ ሊቅ፡
ደስታ ማለት፡ ጤንነት፡ ነው፡ ብሎ ተናገረ፡፡ ጤንነትሳ፡ ደግሞ፡ ምንድን፡ነው፡ ብለው፡ መልሰው፡ ቢጠይቁት፤ ጤንነት፡ ማለት፡ ሁሉም፡ ነው፡ብሎ መለሰ፡፡
እውነት፡ ነው፡ ጤንነት: ከሌለስ?፡ ሁሉ፡ ነገር፡ ከንቱ፡ነው፡፡ ጤንነት፡ ካለ ፡ ግን፡ ሁሉም፡ ነገር፡ መገኘቱ፡ አይቀርም፡፡
አይደለም እንዴ???????????????
ከመፅሀፍ የተወሰደ ሀሳብ ነው
የጤና ቀን ይሁንልን !!!!!
አትውረድ ልጄ፣ ዕውቀት ዋጋ ወደማታገኝበት፣ ሃሳብ ልዕልት ወደማትሆንበት፣ ችሎታ
የሚያስቀጣበት አለማወቅ ወደሚያስከብርበት፣ ማይም አለቃ ወደሆነበት፣ ክርክር ተረብ ወደሆነበት፣ ውይይት እንደ ኮካ ኮላ
ጠርሙስ አንድ ዓይነት ወደሆነበት፣ አላዋቂዎች ወደሠለጠኑበት፣ ከብት ካለው ይልቅ አፍ ያለው ወደተሾመበት ሜዳ አትውረድ፡፡
ከወረድክ ግን በማታውቀው ሜዳ፣ በማታውቀው ስልት፣ በወረደ ትግል ይደበድቡሃል፡፡
አትውረድ ልጄ፡፡ አትውረድ፡፡
ከመፅሀፍት አካባቢ
ከተመቸዎት ይመችወት በቃ !! ሰላሙን ያብዛልወት !!!
የኢትዮጵያ ትምህርት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተምረን ከተመረቅን በሁዋላ የሚገጥመንን የህይወት ፈተና መጋፈጥ የምንችልበትን አቅም የሚገነባልን አይደለም። ግብረገብ ወይም ስነምግባር ምን እንደሆነም ለመናገር የሚያዳግተው ትምህርት ነው የምንማረው።ለዚያ ነው ተመርቀን ከትምህርት አለም ከወጣን በሁዋላ ሁሉም ነገር አዲስ የሚሆንብን ጨካኞች ራስ ወዳዶች የምንሆነው እና ግራ የሚገባን !! ሁሉም ነገር ብላሺ !!!! አሁንም ያው ነው ።
Читать полностью…በዚህች ሕፃን ላይ የተፈፀመውን ድርጊት በምንም አይነት ቃላቶች መግለጽ አይቻልም። በርግጥ የዚህ አይነት ዘግናኝ ድርጊቶች እጅግ በጣም ተበራክተዋል። እሱ ፈጣሪ ደጉን ዘመን ያምጣልን። ያስፈራል !!!!!!
Читать полностью…የዛሬው ጥያቄ መልስ " አደናግር በር " ነው ። መጀመሪያ ላይ መልስ የሰጠንን ሰው ስም ይዘናል። እናመሰግናለን ። ሽልማቱን በአድራሻው እንልካለን ።
ጠቅላላ መልስ የላከልን ሰው ብዛት 123
መልሱን በትክክል ያገኘ 116
የነገ ሰው ይበለን።
የዚህ ዘመን አሁናዊ ሁኔታ ይሄ ነው። ብዙወቻችን የሆነ ነገር ለማከናወን አቅም አንሶን አይደለም። ነገር ግን ከእኛ ጥረት እና ውጣ ውረድ በስተጀርባ የማንረዳቸው ብዙ ሴራወች ስለሚተበትቡን ነው።
ደጉን ዘመን ያምጣልን !! መልካም ቀን ይሁንልን !!
በህመምና በስቃይ ውስጥ እናልፋለን።እኔም ያመመኝ ጊዜ ለአንድ ወዳጄ ደውዬለት ነበር።ያን ምሽት ለረጅም ሰአታት አወራን።ስለ ጠባሳዎቼ አንስቼ ስቃይ ምን ያህል እንደሰለቸኝ ነገርኩት።በድምፄ ውስጥ የመከራዬን ክብደት አሳየሁት።በትዕግስት አድምጦኝ ከጨረሰ በኋላ ዛሬም ድረስ የማልረሳውን አንድ ጥያቄ ጠየቀኝ።"ካለጠባሳዎችህ ምንድን ነህ?" ብሎ።ካለጠባሳዎቼ ምንም አልነበርኩም።ጠባሳዎቼ ቢጠፉ የምናገረው ታሪክ የሌለኝ ሰው ነኝ።
ህይወት አልጋ በአልጋ አይደለችም።የተወለድነው በጣዕርና በስቃይ ውስጥ ነው።እናቶቻችን ሲወልዱ "ምጡን እርሺው ልጁን አንሺው" የተባሉ ናቸው።ተፅፈው ያነበብናቸው:የወደድናቸው መፅሐፍትና ገፀ ባህሪያን ሳይቀሩ በጽኑ መከራ ውስጥ ተፈትነው ያለፉ ናቸው።ምናልባት እያንዳንዳችን በእየርምጃዎቻችን እና በየውሳኔዎቻችን እየተፃፉ ያሉ ጅምር መፅሐፍቶች ነን።እያዘጋጀን ላለነው ግለ ታሪክ ፀሐፊውም ገፀ ባህሪውም እኛ ነን።በምን መልኩ ታሪካችንን መዝጋት እንፈልጋለን?
ትዝታሽን ለእኔ ትዝታዬን ላንቺ
ከእሱባለው አበራ ንጉሴ
መፅሐፉን በ "soft copy" ካገኘሁ እንደምልክላችሁ ቃሌን እሰጣለሁ።
ቸር ውሎን ተመኘሁ። Isam