ወዳጄ ልቤና ሌሎችም
ነገር ግን ፍሬው አጅግ መራራ ነውና ከርሱም ፍሬ የቀመሰ ሰው የዘላለም ሕይወት አያገኝም።ከዛፉም ሥር ተነሥቸ ብዙ መንገድ ከሔድሁ በኋላ፤በስተምሥራቅ ቆሜ ዘወር ብዬ በመስኮት ያየሁት ዛፍ ሦስት መስሎ ታየኝ፡፡ ማቴ፲ ፳፰ቶ ፲፱፡፡ ቶሎ ብዬም ወደ ምዕራብ ዞርሁ፡፺ በዚያም ቆሜ ብመለከት ፍጹም አንድ መስሎ ይታያል፡፡ መነጽሬን አውጥቼ ብመለከት ግን ጥቂት ጥቂት ሦስት መስሎ ይታያል፡፡ ዘፍጥ፮፩፥ ፳፮፯ኔ ከዚያም ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ዞርሁ፡፡ በዚያ ቆሜ ብመለከት ግን አንድ ጊዜ ሦስት አንድ ጊዜ አንድ እየሆነ ታየኝ፡፡ በዚህም አጅግ ተደነቅሁ፡፡ከዚያም ካለፍሁ በኋላ ዮሐንስ ታዓቃቢ የሚባል ሰው አገኘሁ።የዛፉንም ነገር ያውቀሙሸው እንደ ሆነ ብዬ ጠየቅሁት፡፡ በጥላው አርፈህ ስትነሣ ምድርና ሰማይ ቢዞርብህ ነው እንጂ ዛፉስ ዘጠኝ ነው፤ አለኝ።እኔ ግን ስቄበት መንገዴን ሔድሁ ጤ ጥቂትም መንገድ ከሔድሁ በኋላ፤ ሰባልዮስንና መሐመድን አገኘኋቸው፡፡ የዛፉንም ነገር ያውቁት እንደ ሆነ ብዬ ጠየቅኋቸው ዓይንህን አሞህ እንደ ሆነ ብዥ ብዥ እያለብህ ነው አንጂ ዛፉስ አንድ ነው፡፡ በዚህ ነገር ምንም ጥርጣሬ አይግባህ አሉኝ እኔ ግን ስቄባቸው መንገዴን ሔድሁ።ከዚህም በኋላ ከስሜን ሀገር የመጡ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ቁርሎስ አትናቴዎስ ጎርጎርዮስ የሚባሉ ሰዎች አገኘሁ። ስለ ዛፉም ጠየኳቸው፡፡ እነርሱም ቶሎ ብለው ማስረዳት ወደምትባል እልፍኛቸው ይዘውኝ ገብተው ብዙ ጨዋታ ተጫወትን በመጨረሻውም የዚህን የዛፍነገር መርምሮ ያወቀ የለም፡፡ አንተም መርምሬ አውቃለሁ ብለህ አትድከም፡፡ እኛም የዚህን የዛፍ ነገር አንመረምራሰን ብለን ብዙ ደክመን ነበር፡፡ ግን እንዲሁ አንተ አንዳየኸው አየን እንጂ ሌላ ነገር ምንም አሳየንም አለኝ፡፡ ጌቶቹ ሆይ፤ ይህን ስለ መከራችሁኝ ዋጋችሁ በሰማይ ይሁን፡፡ አሁንም ወደ ምሥራቅ ሀገር እሔዳለሁና መንገዱን አመልክቱኝ በዘወርዋራ መንገድ አንዳልሔድ አልኋቸው፡፡
ክፉ ምርምር የምትባለውን ከተማ ወደ ግራ እየተውህ ቀኝቀኙን ሒድ አሉኝ፡፡
መልካም ቀን ይሁንላችሁ!! ❤️❤️❤️❤️
ፊደል አስር ነኝ ❤️❤️❤️❤️❤️😡
አስቴር አወቀ 1
እጅጋየሁ ሽባባው 2
ማን የበለጠ ይመቻችኋል። ከተለያየ አቅጣጫ ተመልከቱ መዝኑ እና ምረጡ።
አስቴር የምትሉ አንድ ቁጥርን ይጫኑ
እጅጋየሁ ያላችሁ ደግሞ ሁለት ቁጥርን ተጫኑ
በብዛት የተመረጠ አርቲስት ምርጥ ጽሑፍ ተመርጦ ጽሑፋ በተመረጠው አርቲስት ሙዚቃ ተቀናብሮ ይቀርብላችሁአል።
ይመቻችሁ።
እናከብራችሁአለን!!
ይህን አንብቡልኝ!!! ግዴታ ነው !!
ከዘር ከሃይማኖት ከጐሰኝነት ከጎጠኝነት ከመንደርተኛነት አስተሳሰብ እና ይዘት የራቁ በይዘታቸው አዳዲስ እና ያልተደጋገሙ ምርጥ ምርጥ መረጃዎችን በተለይ የአሁኑ የፖለቲካ ትኩሳት ስለሆነው የአባይ ጉዳይ ገራሚ ገራሚ መረጃዎችን በቅንነት የሚያደርሰን የ ጋዜጠኝነት ውሃ ልክ ማነው ብትሉኝ እስሌይማን አባይ እዚያው ፌስቡክ ላይ በሚጠቀምበት ስሙ ነው የነገርኳችሁ።
እስሌይማን አባይን በአካልም ሆነ በስልክ አላውቀውም። ፌስቡክ ላይ በሚለቃቸው መረጃዎቹ ብቻ ነው የማውቀው ። እጅግ ምርጥ ጋዜጠኛ ብየ መርጨዋለሁ ።
ከዚህ በፊት አንድ ጎንደር የሚኖር ምርጥ የሃሳብ ባለቤት የግል የሬዲዮ ፕሮግራም(ጃን ዜማ) አዘጋጅ እና ባለቤት የሆነውን ዋሴ ነጋሽን ለእናንተ ማስተዋወቄ የሚታወስ ነው ።
ሌሎችንም እየፈለፈልኩ ይዤ እመጣለሁ !!
የእስሌይማን አባይ የ ፌስቡክ ሊንክ ይሄው ።
https://www.facebook.com/100003626461788/posts/2297306313733562/?app=fbl
የዩቱይብ ሊንኩም ይሄው
የ አባይ ልጅ ዳዊት ቸርነት
ከአለመማራችንም ቢሆን እንማር
አንድ ሰባ ሰማኒያ ዘመን የሆናቸው ሽማግሌ፤ ተማሪ ቤት ገብተው ሲማሩ አንድ ተማሪ፤ “አባቴ ፤ ዛሬ ተምረው ከእንግዲህ ወዲህ ሊሾሙበት ነው? ወይስ ሊከብሩበትና ሊታዩበት?” ቢላቸው፤ ሽማግሌው፡- “ልጄ ልሾምበት፣ ልከብርበትና ልታይበትስ ብዬ አይደለም። ነገር ግን የማይቀረው ሞት ሲመጣ፣ መልአክ-ሞቱ ይዞኝ ወደ ፈጣሪ ሲቀርብ ወዴት አገኘኸው?” ሲለው “ከአትሮኑሱ (መጽሐፍ ማስቀመጫና መግለጫ ገበታ) እግር አገኘሁት” ብሎ እንዲመሰክርልኝ ብዬ ነው” አሉት። ሽማግሌው “በየትኛውም እድሜ መማር ራሱ ጽድቅ ነው”፤ ነው የሚሉት። እውነት ነው። የድንቁርና ዳር ድንበር በየትኛውም እድሜ አለመማር ነው። መማር ግን ፊደል መፈደል ፣ ቀለም መቅለም ብቻ አይደለም። ከመከራችን መከር፣ ከአሳራችንም ሳር ለማብቀል ይቻላል። ደንቆሮ አእምሮዬን ይዤ ሰማይ ቤት አልገባም። እጌታም ፊት አልቀርብም ያሉት አዛውንት፤ ይህ ገብቷቸዋል።
ምንጭ ማህበራዊ ድህረ ገጽ
በመጠኑ ከዋናው ጽሑፍ ላይ የተቆረጠ
እስኪ ይህንን የዩቱይብ ቻናል ደግሞ ሰብስክራይብ ያድርጉ። የምትፈልጉትን ሁሉ ታገኛላችሁ። የ ጎንደርዋ ሰሎሜ በቃ እጹብ ምርጥ ቻናል ነው ።
https://youtu.be/2AC1iH08aho
ወዳጄ ሆድህ እና ልጅህ አይጣሉህ።
እሱ ነው ከባዱ ነገር !!!
ካልወለድክ ደግሞ አሁኑኑ አግባና ውለድ። ዝም ብል አትመዣለጥ!!
የዛሬው ስብሰባችን በዚህ ተጠናቋል። መልካም ሰንበት!!!
ባይፈትኑኝ
ቋንቋዬ - ላይሆን ቋንቋቸው
ዕውነቴ - ላይሆን ሸፍጣቸው
ብራብ - እንጂ ላይራቡ
ጥማቴንም ላይጠሙ
የሚታየኝ - ላይታያቸው
የሚሰማኝን ላይሰሙ
የቸገረኝ - ላይቸግራቸው
የቸገራቸው ላይቸግረኝ
ቅዠታቸው - ላያቃዠኝ
ምሬታቸው ላይበግረኝ
ምናለ - አቦ ቢተውኝ?
በነገር - ስለት ባይፈልጡኝ?
በዕልህ - እሳት ባያቀልጡኝ
ጽናቴን - ከቶም ላይንዱት
ዕውነቴን - ከቶም ላይረቱት
ቢያደሙኝ - እንጂ - ቢገድሉኝ
ኢትዮጵያ!
ከክብርሽ - ሞት!
ከፍቅርሽ መቼም ላይለዩኝ
አቦ - ምናለ ቢተውኝ
በመከራ ጽልመታቸው
በማልወድቀው ባይፈትኑኝ
ምንጭ ከመጽሀፍት
ገራሚ ነው
ተረብ
ምን ተሸክመሃል?
የስንደዶ ፍልጥ
በምን አስረህ?
በወይራ ልጥ
ማን አሸከመህ?
ዝሆን ተካቦ
እንዴት ልታወርድ?
በትንኝ ደቦ
ስምህ ማን ይባል?
ላገር አይመች
ማን አወጣልህ?
ጐረቤቶች
እናትህ ማን ነች?
ሳትወልደኝ ሞተች።
ምንጭ ካነበብኩት
ነገ ተወዳጁ የ አሌክስ አብርሃም 'ከእለታት ግማሽ ቀን ' ትረካ ሁለት ክፍሎች በአንድ ላይ ወደ እናንተ ይደርሳሉ። በፊደል አስር ብቻ !!!!
ክፍል 5 እና 6
አስተያየት ካለዎት ይህን ሊንክ ይጫኑ
@Fogremover
እንዴት ሰነበታችሁሳ! ስሙኝማ...‘የእሱና የእሷ’ ነገር ከትላንት እስከ ዛሬ እንዴት አሪፍ ‘ጎን ዊዝ ዘ ዊንድ’ ምናምን አይነት ነገር ይወጣው መሰላችሁ! ያኔ...መጀመሪያ ምን አለ መሰላችሁ... ‘እሺ’ ማሰኘት፡፡ እንደ ዛሬው ‘የፋስት ፉድ’ ሽያጭ ስትራቴጂ ወደ ‘ፋስት ፍቅር’ የሚባል ‘ሾርትከት’ ነገር አልነበረም፡፡ ሁሏም ነገር የምትገኘው በላብና በጥረት ነው፡፡ ልክ ነዋ...እስከሚሳካ ድረስ ስንትና ስንት መሳቀቅ አለ፡፡ እኛ እንኳን ትንሽ ጫፍ አግኝተው ሳያገኙ እንኳን መግቢያ፣ መቅድም፣ ቅድመ ታሪክ፣ ድህረ ታሪክ፣ ምናምን ጨማምረው የሚያወሩት እትዬ እንትና ዓይን ከተገባ...ፕሮጀክት ተበላሸ ማለት ነው፡፡ (አዎ፣ በዛ ጊዜ ነገርዬው ሁሉንም የፕሮጀክት መመዘኛዎች የሚያሟላ ነገር ነበር፡፡ ፒያሳ ተጀምሮ አራት ኪሎ ላይ “ሁሉም ነገር ዓለምን ሊያስደንቅ በሚችል ፍጥነት ተሳክቷል፣” ብሎ ነገር የለም፡፡ የምር እኮ...ዘንድሮ ሁሉም ነገር እጅ በእጅ ሆነና፣ እሷዬዋን ለማግኘት ከጎጃም በረንዳ ቅምብቢት በእግሩ ይኳትን የነበረ... “ምን ጊዜ ተጩሆ፣ ምን ጊዜ ደረሱ” የሚባልለት ሁሉ ከጨዋታ ውጪ ሆነ! “ኸረ ተሳታፊነቱ ቢቀርብን እንኳን ድምጽ የመስጠት መብት የሌለው የተመልካችነት ወንበር ስጡን!” የሚል አይጠፋም ለማለት ያህል ነው፡፡ (በአንዳንድ ሀገራት በእነሆ በረከት ጉዳይ ...አለ አይደለ...ዝም ብሎ ‘የሚፈጠጥበት’ እንደ ‘ዊንዶው ሾፒንግ’ አይነት ነገር አለ ሲባል ስለምንሰማ ነው፡፡) እናማ... እኛ የሰፈር እትየ እንትና እንዳያዩ በምናምን ቁጥር አንበሳ አውቶብስ አገር አቆራርጦ መሄድ ነው፡፡ በነገራችን ላይ... እንደው የፈለገ ነገር ቢረሳ፣ የፈለገ ነገር ቢዘነጋ፣ እንደፈለገ ‘ዘመናዊ’ ለመሆን ቢሞከር የ‘ነጠላ’ን ውለታ መርሳት ግን ‘ፌይር’ ነው! “ማነሽ አንቺ! አንቺን እኮ ነው የምጠራው!” “እመት እማዬ...” “ስጠራሽ ጆሮሽ ላይ ተቀምጠሽበታል እንዴ!” “ሥራ ላይ ሆኜ እኮ ነው...” "ሰረሰርሽ ይውለቅ! ባለሰማያዊ ጥለት ነጠላዬን ማን ወሰደው?” “ማሚቱ ነች፡፡” በአምስት ዓመትም፣ በሀያ አምስት ዓመትም ማሚቱ ማለት ይቻል ነበር፡፡ “ከመቼ ወዲህ ነው ደግሞ እሷ ነጠላ መልበስ የጀመረችው?” “የጓደኛዋ አክስት አርፈው ለቅሶ ልድረስ ብላ ነው፡፡” “ጎሽ!” ማዘር ደስ አላቸው፡፡ “አሁን ገና ለቁም ነገር በቃች፡፡” በትክከል ተመልሷል! አሀ...ነጠላ እንደሁ አያሳብቅ...እሱዬው ቅበጥ ብሎት ‘ሊፕስቲክ’ ካልተለቀለቀ በስተቀር! ቂ...ቂ...ቂ... እኔ የምለው... እንግዲህ ጨዋታም አይደል... ግን የዘንድሮ ‘ሊፕስቲክ’ እንትናዬዎቹ ላይ ቦግ ብሎ፣ ወደ እንትናዎቹ ሸሚዝ ሲሸጋገር ‘ኢንቪዝብል ይሆናል እንዴ! ግራ ስለገባን እኮ ነው፡፡ የ‘ኪሶሎጂ አርት’ እንዲህ በተስፋፋበት እንዴት የሚጣበቅ የሊፕስቲክ ዓይነት ጠፋ ብለን ነው፡፡ እናላችሁ... አሁን በ‘ፕሮፋይል ፒክቸር’ ብቻ አነጣጥሮ የሚጣልበት ዘመን አልነበረም፡፡ ስሙኝማ... እንግዲህ ጨዋታም አይደል፣ የ‘ፕሮፋይል ፒክቸር’ ነገርማ ራሱን የቻለ ሲዝን ፋይቭ ድረስ የሚሄድ ተከታታይ ድራማ ሊሠራለት ይገባል፡፡ አሀ... ከትናንት ወዲያ የእኛ ቢጤ ከወጪ ቀሪ፣ ማለትም እንደው ሁሉም ነገር ድንገት የጠፋ እንደሆነ ተብሎ ለ‘ምናልባቱ’ ብቻ የተቀመጠ የሚመስለው ሁሉ ‘አፕዴት’ የተደረገ ፕሮፋይል ፒክቸሩ ላይ... አለ አይደል...“አንጀሊና ጆሊ ብራድ ፒትን የፈነገለችው በዚህ ሰውዬ የተነሳ ነው እንዴ!” ሊያሰኝ ምንም አይቀረው፡፡ ከ‘ፕሮፋይል ፒክቸር’ በፊት አሪፍ የሚባለው ሩስያ ተልኮ በእጅ ይሁን በምናምን ነካ፣ ነካ ተደርጎ ‘ባለ ቀለም ስእል’ ሆኖ የሚመጣው ነበር፡፡ (እናላችሁ...ለጥቆማ ያህል፣ “እኔ እኮ ሲያዩኝ ትልቅ ሰው እየመሰልኩ ነው እንጂ ገና አንዲት ፍሬ ልጅ ነኝ፣” የምትለዋን ሁሉ በማስረጃ ለመሞገት ቢፌው ላይ ያለው ፎቶ፣ የእጅ ሥራ መሆን አለመሆኑን ማየት ይበቃል፡፡ ስሙኝማ...ከዚህ በፊት እንዳወራነው እዚህ ሀገር ሊዘመርለት ሲገባ ‘ኢግኖር’ የተደረገ ማን አለ መሰላችሁ...ታላቅ ወንድም፡፡ እናማ...አለ አይደል... በታላቅ ወንድም ‘ታሪካዊ ሚና’ ላይ የሚሰጠው ድምጽ እኩል ለእኩል ሳይሆን አይቀርም። ልጄ... “ተው ይቅርብህ፣ ታላቅ ወንድሟ የሰማ እንደሆነ አንስቶ እንዳያፈርጥህ (ያኔ ‘አፐርከት’ ‘ሌፍት ሁክ’ ምናምን ብሎ ነገር ሳይሆን ዳኛው የ‘ኖክአውት’ ውሳኔ የሚሰጠው “ማን አንስቶ አፈረጠ!” በሚለው ነበር። የእንትናዬዎቹ ‘የምንጊዜም አንስቶ አፍራጮች’ ታላቅ ወንድሞች እንደነበሩ ታሪክ ይመዝግበው ለማለት ያህል ነው። (ቂ...ቂ..ቂ..) “ምን እንዳያመጣ ነው!” እያለ ሲያስቸግር መንጋጭላው ሱናሚ ያናጋው ይመስል ቦታውን የለቀቀ ሁሉ “ታላቅ ወንድሞች ለዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ይቅረቡ!” ባይ ነው። ራሳቸው ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ይገባቸው የነበሩና ስንት መንጋጭላዎች የተፈጥሮ ስፍራቸውን ከመልቀቅ ጀርባ ያሉ እንትናዬዎች ደግሞ ለታላቅ ወንድሞች “የሆነ የተባበሩት መንግሥታት ሽልማት ይገባቸዋል፣” የሚሉ ይመስለናል፡፡ ስሙኝማ... ሌላ ደግሞ እዚህ ሀገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገው ያልተዘመረላቸው እነማን መሰሏችሁ...በእሱና በእሷ መሀል የፍቅር ደብዳቤዎች ሲያመላልሱ የኖሩ የየሰፈሩ ህጻናት፡፡ (ታሪክ ለባለታሪኮች ይመለሳ! የምን ማዳላት ነው! (ቂ...ቂ...ቂ...) ድሮ... ድሮ ነው፡፡ (ሂሳቡን አስሉትና... ሁሉም ሰው ልክ ነው፡፡) እሱዬው እንትን ሀይ ስኩል ተማሪ ነው፡፡ (ስሙ አስፈላጊ ስላልሆነ ነው፡፡) እናላችሁ... አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ሲመለስ እንደ ጉድ ተናዶ ነበር፡፡ እና የሰፈር ልጆች ደግሞ የአንዱ ንዴትም፣ ሳቅም የጋራ ጉዳይ ስለሆነ ሰብሰብ ብለው ይከቡታል፡፡ “ምን ሆነህ ነው?” ይባላል፡፡ ተቧቅሶ መጣ እንዳይባል ፊቱ ላይ የተጫረ ነገር፣ ወይም የጎደለ የጃኬት ቁልፍ የለም፡፡ እሱዬው መልስ ሳይሰጥ እንዲሁ ብቻ ይንተከተካል፡፡ “ምን ሆነህ ነው?” ምን ሆኖ መሰላችሁ...ለካስ አንዱ ጎረምሳ ‘ገርልዬውን’ ነጥቆት ነው፤፡ (ያን ጊዜ ‘ገርል’ ሲባል ‘ከእነሙሉ ትርጉሙ’ ነበር፡፡ ታሪክ መመዝገብ አለበታ!) እናላችሁ... ነጠቃው ደግሞ ዝም ብሎ...አለ አይደል... ‘አካሄድ አይቶ ጭብጦ እንደ መቀማት’ አይነት አልነበረም፡፡ ...ነጣቂው የእንትን ሰፈር ልጅ ነው፡፡ ይኸው ‘እንትን ሰፈር’ ደግሞ ከዚህኛው ልጅ ሰፈር ጋር “ታሪካዊ ለመባል ምን ይጎድለዋል!” የሚባልለት አይነት ባላንጣነት ነበር፡፡ እናማ ነገርዬው “የተረት ሰፈሯ ብትሄድ የገዳም ሰፈሯ ትመጣለች” ተብሎ የሚታለፍ አልነበረም፡፡ (እነኚህ ሰፈሮች የተጠቀሱት የ‘ኖስታልጂያ ምናምን ነገር ሳይሆን አፍ ላይ ስለመጡ ብቻ እንደሆነ ይመዝገብልንማ!) እናላችሁ... የልጁ ሳይሆን የሰፈሩ ‘ክብር’ ነበር የተዋረደው! ምን ቢሆን ጥሩ ነው... ንዴቱ ሁሉም የሰፈር ልጆች ላይ ተዛመተ። ክብር ተነካ! እናላችሁ መፈክሩ...“የእንትን ሰፈር ልጅ የሰፈራችንን ልጅ ነጥቆ፣ እጃችንን አጣጥፈን ልንቀመጥ! ሞተናላ!” አይነት ነበር! በማግስቱ የዚህ ሰፈር ልጆች ለአጸፋዊ ምላሽ ወደዛ ትምህርት ቤት ዘመቱላችኋ! እናማ... ምድር ቀውጢ ሆነች። እንዲህ ነበር ያኔ፡፡ የዛን ዘመን የከተማ ጀግንነት እንትናዬዋን የነጠቁ፣ ያስነጠቁና ስትነጠቅ ዝም ብለው ያዩ፣ እንዲሁም በነጠቃው አሳበው የ‘ሰፈርን ክብር’ ያዋረዱ ላይ ‘ተገቢውን’ ምላሽ መስጠት ነው። (‘ተመጣጣኝ’ ቅብጥርስዮ ብሎ ነገር የለም!) ስሙኝማ...
Читать полностью…ቁመቱ ስለረዘመ ነገን ማየት የሚችል እየመሰለው የሚንጠራራ ብዙ ቀውላላ አለ አሉኝ ?? እውነት ነው እንዴ !??
ደግሞ ይህን ጽሑፍ የፃፈው ሰው ቁመቱ አጭር ነው በሉኝ። አይደለሁም መካከለኛ ነኝ ።
ረጃጅሞችን ወደ ላይ አንጋጥጨ ለማየት አጫጭሮችን ደግሞ ጎንበስ ብየ ለማየት መሃል ላይ የተፈጠርኩ😂😂😂😂😂
እና ምን ለማለት ፈልጌ ነገን ማየት የሚችል የፈጠረህ ብቻ ነው ።
አያለሁ ብለህ ከተንጠራራህ ግን እየተበትክ ነው ማለት ነው 😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂
መልካም ጊዜ ። ፊደል አስር ነኝ በጉዞ ላይ ሆኜ
ለሆነ ጉዳይ ለመድረስ ትራንስፖርት ጠፍቶ በጣም ተቸግሮ በሆነ አጋጣሚ ባገኘው የሕዝብ ማመላለሻ ትርፍ ሆኖ ተጭኖ ሄዶ ለዚያውም ለምኖ ማለት ነው ፈጣሪውን፣ ሾፌሩን እና ረዳቱን ያመሰገነ ሰው ሌላ ጊዜ ደግሞ እሱ ራሱ መደበኛ ተሳፋሪ ሆኖ እሱ የተጫነበት የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ሾፌር ትርፍ ሲጭን ለምን ትርፍ ትጭናለህ ብሎ ቡራ ከረዩ ቡራ ከረዩ ይልና ደግሞ ለትራፊክ እከሳለሁ ብሎ ይገለገላል። ይገርማል ።
የዚህ አይነት ሰዎች በጣም ያናዱኛል። ራሳቸውን ብቻ የሚመለከቱ !! ሆዳሞች ናቸው !!
መልካም ምሽት
ፊደል አስር ነኝ ከታዘብኩት ነው ያካፈልኳችሁ
❤️💋❤️💋❤️💋👍👍👍👍
አልወጣችም ፀሀይ ጋርዷታል ደመና
ጉሙም አለቀቀ
አላለፈች ጤዛ
ቀኑም ተገባዷል ወርሶታል ጨለማው
ጨረቃም ፈዛለች
ኮኮቦችም ቀርተው
ተዛምዷል ከኔውጋ ሀሳቤም ከንፋስ
ይወስደኛል ማዶ
ይዞኝ ላይመለስ
ምንጭ ማህበራዊ ድህረገጽ
ያው እድለኛም አይደለሁ... ታዋራኛለች! ደፍሬ ስልኳን የጠየኩበት ቀን ትዝ ይለኛል። ልዩ መሆኗ ግልፅ ነው... ድፍረቴ ቀርቶ! “ይሄን ነገሬን ባትወደውስ?” ብዬ መስጋቴ ሌላ ታሪክ ነው! ሰው እንዴት “ድምፄን ባትወደውስ?” ብሎ ይሳቀቃል? እንደው ስንት አይነት ድምፅ ቢኖር ነው? ብቻ እንዳልኩት እድለኛ ነገር ነኝ! የመጀመርያ ቀን ደውዬላት፣ ቆንጆ ድምፅ እየሰማሁ ስቁነጠነጥ... “ወይኔ መስዬ... ድምፅህ እንደዚህ የምስኪን ነው? እዛ ‘ፌስቡክ’ ላይ ስትፅፍ እኮ የሆነ አስፈሪ ኮስታራ ድምፅ ያለህ ነው የምትመስለው! “ አለቺኝ... ኮስታራ ድምፅ እንዴት ያለው ነው? Is ምስኪን ድምፅ a compliment? ብቻ ከእነ ውዝግቤ የተጨመረልኝም የድምጿን በረከት እየባረክሁ ጥቂት ጊዜ አለፈ... “አግኚኝ” ለማለት እስክደፍር... በዚህ ጥቂት ጊዜ በስሟ እልፍ ግጥም ፃፍኩ... ከእልፍ ቆነጃጂት ተኳረፍኩ... እልፍ የፍቅር ዘፈን ተረጎምኩ... ፍቅር፤ ፀሀፊ የሚያደርገው ነገር ሳይኖር አይቀርም! ‘ከፖስቶቼ’ ስር አስቀምጣ በምታልፈው ቀይ የልብ ቅርፅ፣ የልብ ልብ ተሰምቶኝ፣ እንድታገኘኝ መወትወት የጀመርኩበት ደፋር ሰሞን... “የምትወደኝ መስሎኝ እኮ ነው...” ብላ አስደነገጠችኝ! ለምን አልወዳትም? አጭር እንደሆነች የማላውቅ መስሏት ይሆን? ስንት ሰው ጠይቄ ስታወራ nervous እንደሆነችና እጆቿ እንደማያርፉ ያልሰማሁ መስሏት ይሆን? “እንዴ... እወድሻለሁ እንጂ! ለምንድነው እማልወድሽ?” አልኳት ኮስተር ብዬ... “ባክህ የመሰልኩህን ሴት ነው የምትወዳት፤ እኔን አይደለም! አታውቀኝም! ብታውቀኝ Lewis Capaldiን... Joel Corryን... አትጋብዘኝም... እየተረጎምክ በስሜ አትለጥፍልኝም ነበር! አብነት አጎናፍር ምን አለህ...?” አለቺኝ እንደማምረር እያደረጋት... ጀንጃኝ ጎኔ አፍሮ ሲሽኮረመም egoዬ ምላሴን ተረክቦ... “እንዴ... እንዴ... ይኸው ልደታን! እሁድ እንደውም... Palmy የሚባል ቤት አብነትን ካላየን... ብዬ ልነዘንዝሽ ስል...” አላት! “ውይ ደስ ይለኛል ጌታን!” አለቺኝ፤ ደስ በሚል ድምፅ! ያው አርብና ቅዳሜ ሾፌሬን ይዤ፣ እሁድ የምለብሰውን ልብስ ፍለጋ ባከንኩ... እድለኛም አይደለሁ... እሁድ ደረሰና አጭሯን ሱሴን አትላስ አገኘኋት... እና ምን ለማለት ነው... አብነት አጎናፍር ጥሩ ሰው አይደለም! መጀመርያ ወደ መድረኩ ሲወጣ he is not intimidating at all... ጅንስ ሱሪው ውስጥ ሸሚዙን የሰገሰገ... የሚያብለጨልጭ ጫማ የለበሰ ጎልማሳ ምኑ intimidate ያደርጋል? ደግሞ ከፈረንሳይኛ እስከ እንግሊዝኛ የፍቅር ዘፈኖች ተርጉሞና አስተርጉሞ ለጀነጀነ ሰው... አብነትዬ መዝፈን ጀመረ... “አንቺን ብሎ... ልቤ አልረጋ አለ... ባሳብ ካንቺ ጋር... ሄዶ እየዋለ... አስቻለሽ ወይ... ካለኔ ኑሮ... ከበደኝ እኔን... እንጃ ዘንድሮ... ለኔ ካለሽ... መቼም አይቀርም... ውደጂኝ ብዬ... ሙጢኝ አልልም... ለኔ ካለሽ... መቼም አይቀርም... ውደጂኝ ብዬ... ሙጢኝ አልልም!” እሷ በሳቀ ፊት ጮክ ብላ አብራው ትዘፍናለች... ቁመቷን ናቅ አድርገው እንዳሻቸው ደረቷ ላይ የነገሱ ጡቶቿን 6-8 ምናምን እየጠበቀች nude ጥፍር ቀለም በቀባቻቸው ቆንጆ ትንንሽ ጣቶቿ ነካ ታደርጋቸዋለች... አብነት ግን ምን ኾኖ ነው? “ዞራ ዞራ የኔው ናት ዞራ ዞራ...” ምናምን በሚዘፈንበት ሀገር፣ እንዲህ መፈላሰፍ ምን የሚሉት ነገር ነው? “... አለሁ... ይግባኝ አልጠየኩም... ክፉም ነሽ አላልኩም... ደግም ነሽ ሳልልም... ብቻ ግን አለሁ... እራሴን ባልጥልም... አለሁ እንዳለሁ...” ቱ... እኔን ብሎ ገጣሚ! እኔን ብሎ ተርጓሚ... በጌታ ስም... እሸማቀቃለሁ... “... ዘንድሮስ ቸገረኝ... እምባዬ አልደርቅ አለኝ... ሆዴም አልቆርጥ አለኝ... ድካሜ አሳዘነኝ... ፍቅር አልቆይም አለኝ... እየወሰወሰኝ... ከማጥ ወስጥ ዘፈቀኝ...” እሷ እርክት እያለች ከአፍ ከአፉ ትቀበላለች... እኔ እስከዛሬ “እንደዚህ ነው የምወድሽ...” ባልኩት እየተሳቀቅሁ አፈጣለሁ... አብነት ሆዬ ይቀጥላል... “...በርግጥ አታምኚም... አንቺን ማሰቤን... ርቀሺኝ ስትሄጅ... ገፍተሺኝ እኔን... አልጠላሽም... ስላልወደድሺኝ... ካሳብ እንድድን... ብቻ ጠይቂኝ...” እንዳልኩትም እድለኛ ነኝ... ቆንጆ ብቻ ሳትሆን ልክም የሆነች ምትሀት ነው የወደድኩት! ልክማ ነች... የምወዳትን ያክል አልወደድኳትም... አብነት ይሙት!
ምንጭ ማህበራዊ ድህረገጽ
ብዙዎቻችን የውክቢያ ሕይወት ነው እየገፋን ያለነው፡፡ እንጣደፋለን! እንዋከባለን! ድካማችን ብዙ ዕረፍታችን ጥቂት ነው። እንቸኩላለን! መድረሻችን የት እንደሆነ ግን አናውቀውም፡፡ የኑሯችንን ጎዶሎ ለመሙላት እንሯሯጣለን፡፡ የኑሮ ጣጣ ፈንጣጣው አላላውስ ብሎናል፡፡ የሆዳችንን ጥያቄ ለመመለስ፣ ማጀታችንን ለመሙላት፤ ሳሎናችንን ለማሳመር የማንወጣው ዳገት፤ የማንወርደው ቁልቁለት የለም፡፡ አስቤዛችን እንዳይጎድል እንታትራለን፡፡ የሩጫ ሕይወት! የጥድፊያ ኑሮ! የትርምስ ዓለም! የግፊያ ጊዜ! አዎ ለራሳችን ጊዜ የለንም፡፡ ለሆዳችን መሮጡ ጥሩ ሆኖ ሳለ የነፍሳችንን ርሃብ ለማስታገስ፣ አዕምሯችንን ለመመገብ አንዲት እርምጃ ግን እየተራመድን አይደለም፡፡ ራሳችንን ያን ያህል አልተገነዘብነውም፡፡ የሆዳችንን ጩኸት እንጂ የሕሊናችንን ድምፀት አንሰማም፡፡ የኑሮ ውድነቱ ትኩረታችንን ጠልፎታል። አስተሳሰባችን ተሰርቋል፤ እኛነታችን በዘመን አመጣሹ የውክቢያ ኑሮ ተነጥቋል። እናውቃለን የምንለውን ማንነታችንን በደንብ አናውቀውም፡፡ ሰውነታችንን በቅጡ አልተረዳነውም፡፡ የምናየውን ዓለም አናስተውልም፤ የምንሰማውን ውስጣዊ ሮሮ አናዳምጥም፡፡ ለራሳችን ትኩረት አልሰጠንም፡፡ ውበታችንን ለመጠበቅ፣ ሳሎናችንን ለማሳመር፤ ኑሯችንን ለመሙላት እንደምንፍጨረጨረው ሁሉ ሰውነታችንን ፈልገን ለማግኘት፣ የሕሊናችንን ውበት ለመጠበቅ፣ ስነ ምግባራችንን ለማሽሞንሞን፣ ውስጣችንን ለማሳመር፣ መንፈሳችንን ለማስዋብ፣ አዕምሯችንን በፍቅር፣ በዕውቀትና በጥበብ ለመሙላት፣ ነፍሳችንን ለማስደሰት ስንፍጨረጨር አንታይም፡፡ ራሳችንን የዘነጋን ከንቱዎች ሆነናል፡፡ በራሳችን ላይ ለጥ ብለን ተኝተናል፡፡ ማን ያነቃን ይሆን? ወዳጄ ሆይ.... ለራስ የማርያም መንገድ እንደ መስጠት ያለ ብልህነት የለም። ከራስ ደካማ አስተሳሰብና ዓለሙ ካዘጋጀልን የእንቁልልጭ ወጥመድ መውጫ የወንድ በር ማዘጋጀት ያስፈልገናል፡፡ ፈረንጆቹ “Exit door” እንደሚሉት ዓይነት። ከራስ ጋር መነጋገርን የመሰለ ከወጥመድ ማምለጫ መድሐኒት ሌላ ምንም የለም፡፡ ሕይወት እንዳይሰለችህ፣ ኑሮ እንዳይመርህ አዕምሮህን አዲስ ሃሳብ አስተምረው። ከራስ ጋር መነጋገርን አለማምደው፡፡ ሕሊናህን በአዲስ ሃሳብ አሰልጥነው፡፡ ከራስ ጋር ከመደንቆር ይልቅ ከራስ ጋር ለመግባባት ለራስህ ጊዜ ስጠው፡፡
ምንጭ ማህበራዊ ድህረገጽ
አንዳንድ ተረት ተደጋግሞ ካልተነገረን አንጀት አይደርስም። የሚከተለውን ተረት ከአመታት በፊት ተርከነዋል። ዛሬም ይሄው እንተርከዋለን። ትምህርታዊነቱ ደግ ነው ብለን ነው። እነሆ! ከእለታት አንድ ቀን ሌሊት በጠፍ ጨረቃ ሶስት አህዮች ሳር ይግጣሉ። እንዳጋጣሚ የተራቡ ጅቦች በዚያው ገደማ ያልፉ ኖሮ አህዮቹን አዩአቸው። ከበቧቸውና “ለመሆኑ ማንን ተማምነው ነው በጠፍ ጨረቃ በኛ ግዛት እንዲህ እየፈነጩ ሳር የሚግጡት? ችሎት ተቀምጠን እንጠይቃቸው” ብለው ጅቦቹ ለዳኝነት ተሰየሙ። የመጀመሪያዋ አህያ ቃል ልትሰጥ መጣች። የመሃል ዳኛው፤ “እሜቴ አህያ፣ ለመሆኑ ማንን ተማምነሽ ነው በኛ ግዛት በጠፍ ጨረቃ ሳር የምትግጭው?” አህያይቱም፡- “ፈጣሪዬን አምላኬን ተማምኜ ነው፤በእኔ ላይ ጉዳት የሚያደርሱን ሁሉ ፈጣሪዬ ይበቀልልኛል” ስትል መለሰች። ሁለተኛዋ አህያ ቀረበች፡፡ መሃል ዳኛው፡- #አንችስ ማንን ተማምነሽ ነው በጠፍ ጨረቃ በእኛ ግዛት የምትግጭው?; ብሎ ጠየቃት። አህያይቱም፡- “ጌታዬን፤ ሀብት የሆንኩትን ባለቤት፤ ለእኔ ክፉ የሰራን ሁሉ የገባበት ገብቶ ይበቀለዋል” አለች። በመጨረሻም ሶስተኛዋ አህያ ቀረበችና አስረጅ ተባለች። ሶስተኛዋ አህይትም፡- “እኔ በጠፍ ጨረቃ የወጣሁት እናንተኑ ጌቶቼን ተማምኜ ነው” ስትል መለሰች። ዳኞቹም መከሩና “የመጀመሪያዎቹን ሁለቱን ብንበላ እውነትም አደጋ አለው። ይህቺን እኛን የተማመነችውን ብንበላት ግን ማን ይጠይቀናል!” አሉና ከመቅጽበት ወረዱባት ይባላል። እነሆ መተማመኛችንን አጥርተን ሳናውቅ መጓዝ ለአደጋ ሊያጋልጠን ይችላል። ሁሉ ነገር ከየጀርባው የስጋት ባለቤት አለው። ያም ሆኖ እጅግ ከባዱን አደጋ ከመካከለኛው አደጋ አመዛዝነን ማጤን ይገባናል። መካከለኛውንም ከትንሹ ማመዛዘን አለብን። ጉዳዮቻችንን በእውቀትና በብልሃት መከወን ይጠበቅብናል። ነገር ግን የእነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ እንዳይሆን በጥንቃቄ መራመድን ግድ ይለናል።
ምንጭ ማህበራዊ ድህረ ገጽ
በመጠኑ ከዋናው ሃሳብ ላይ ተቆርጦ የቀረበ
ድህነት፣ ሰላም አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ?!
#Ethiopia | ዳንኤል ክብረት አንድ ቃለ መጠየቁ ላይ እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ
" አድናቂዎችህ በሚሰጡህ አስተያየት እና ደግሞ በተቀራኒዉ የማይደግፉህ ሰዎች በጣም በሚዲያ ሲያብጠለጥሉህ ምንድነዉ ምላሽ!" ተብሎ ለተጠየቀዉ ጥያቄ ይቺን ምሳሌ አስቀሞጥዋል
ከእለታት አንድ አንድ ወጣት ወደ መርቆሪዮስ የሚባል አባት በኣት(መገኛ) ሄደና፡፡
"አባቴ ሆይ!... ድህነት፣ ሰላም አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ?!ሲል ጥያቄ አቀረበ
መቃርዮስም ፦ ወደ መቃብር ሂድና ሰድባቸው ና
ይህም ወጣት የተባለው አድርጎ ተመለሰ፡፡
መቃርዮስም ፦ ምን አሉህ?
ወጣቱም ፦ "ምንም አልመለሱልኝም!" ሲል
መለሰ፡፡
አባ መቃርዮስም ፦ "አሁን ደግሞ ሙታንን
አመስግናቸው ና" - አሉት
ሄዶም አመሰገናቸው ፡፡
"አሁንስ ምን አሉህ ?" ሲሉ በድጋሚ ጠየቁት
ወጣቱም ፦ "ኧረ አንዳች አልመለሱልኝም!' ሲል
መለሰ፡፡
አባ መቃርዮስም ፦ ስትሰድባቸውን
ስታመሰግናቸውም ሆነ ስታወድሳቸው
ምንም አልመለሱልህም፡፡ አንተም ለነፍስህ ድህነት ከፈለክ እንደሞተ ሰው ሆነክ ኑር!
ሲሰድቡህም ሲያመሰግኑህም ምንም
አይምሰልህ፡፡
ምንጭ ማህበራዊ ድህረገጽ
የአንዳንድ - ሰው
ከነጮቹ
ከጥቁሮቹ
ከሰው ልጆች የአንዳንዶቹ
«ዕጣ» ሆኖ የ«ዕድል» ክፋይ
ከዕልፍ አዕላፍ የአንዱ ሲታይ
እንደ «ቡሬ» ሞፈር ቢስብ
አፈር - ምሶ፤ አፈር ቢክብ
እሳት - ሆኖ፤ እሳት - ቢያምጥ
ጋራ - ንዶ፤ ቋጥኝ - ቢያቀልጥ
ለግንባሩ «ግንባር» የለው
ቅን ምግባሩ «ጐሽ!» አያየው።
ጥሞም - አይጥም የእርሱ አንደበት
«ዕውን» አይሆን የእርሱ ዕውነት
የአንዳንድ ሰው የ«ጐህ» መዳፍ
ቋትሞ የለው ቀሪ ምዕራፍ።
አዬ!
የአንዳንድ ሰው ጥምር ትግል
የባካኝ ሰውነት «ሽፍን» ገድል!።
ምንጭ ከመጽሐፍት
ለ - ፍቅር
ዓይንሽን - ዓይና
ጥርስሽን - አይና
ክዳው ክዳው አለኝ
ያባትሽን - ዝምድና
እራሷን - ሹሩባ
ተሠርታው ብትመታ
ዓይኗን - በቀጭኑ
ተኩላው ብትመጣ
ጥርሷን - ጉራማይሌ
ተነቅሳው ብትመጣ
ሣልታመም ታመምኩ
ሣልሞት ነፍሴ ወጣ
ምንጭ ከመጽሐፍት !!
ለ - ጅገና
ተው! ተመለስ በሉት
ተው! ተመለስ በሉት!
ያንን መጥፎ በሬ
ከጠመደ አይፈታም ያገሬ ገበሬ።
ያባቴ ነው ብሎ፤
የናቴ ነው ብሎ፤
ይፋጃል በርበሬ
አባት የሌለው ልጅ፤
እናት የሌለው ልጅ፤
አይሆንም ወይ አውሬ።
ምንጭ ከመጽሐፍት
ኮሚክ አይደል...ድሮ ጊዜ እንትናዬዎች ሰውና ሰውን ሳይሆን ሰፈርና ሰፈርን ያደባድቡ ነበር... (እንደውም ሼክስፒር የሮሚዮና የጁሊየት ቤተሰቦችን ያፋለመው ከድሮ ጊዜ የሰፈር ልጆች ሀሳቡን አግኝቶ መሆን አለበት! በፕሪሚየር ሊግ አባብለው የባለቤትነት መብት ጥያቄ እንዳናነሳ አደረጉን እንጂ!) እናላችሁ... ያኔ ስንትና ስንት ‘ፍስፍስ’ (እንዲህ የሚባል ቃል አለ አይደል!) ነበር ለማለት ነው፡፡ ነገሩ ሁሉ እንዲህ ‘ፍሪ ላንች’ ዘመን ሊደረስ! ቂ...ቂ...ቂ... ዘንድሮ ደግሞ ራሳቸው በኩንግ ፉ ጸጥ ሊያደርጉ ይችላሉ የሚል ሀሜታ አለ። “ሲሱ...” “ምን ሆንክ! እንተዋወቃለን?” “አይ እንደው ሳይሽ ደስ አልሽኛና...” “ደስ አልኩህ! ሂድና የለመድከበት ተለፋደድ!” “እንዲህ ነች ቀዮ! ምን ታካብጂያለሽ... አናውቅሽምና ነው...” ክንድ ለመያዝ ይሞከራል፡፡ ምን መብረቅ እንደወረደበት ሳያውቅ ምንጣፍ ይሆናል፡፡ (ከወራት በፊት ፒያሳ መሀል ሞባይሏን ነጥቆ ሊያመልጥ የሞከረውን ጎረምሳ፣ አንድ እህታችን፣ ምን መብረቅ እንደወረደበት ሳያውቅ አንጥፋው ነበር፡፡) (የዚችን አይነት እህቶች ያብዛልንማ!) እናማ... ከታላቅ ወንድም እስከ ‘ፍሪ ላንች’ የተጓዘው ባቡር መንገዱን ቀጥሏል ለማለት ያህል ነው፡፡ ደህና ሰንብቱልኝማ!
Читать полностью…ዛሬ ማታ ተወዳጁ የአሌክስ አብርሃም ከዕለታት ግማሽ ቀን መጽሐፍ ላይ ራሱ ከዕለታት ግማሽ ቀን ክፍል አንድ ተሰርቶ ይቀርብላችኋል። በፊደል አስር ብቻ !!!!! ብዙዎቻችሁ እየጠበቃችሁ እንደሆነ በአስተያየት ስለነገራችሁን ከመጽሐፍ ባለቤት የይለቀቅ ፈቃድ ስላገኘን( መጽሃፉ አዲስ ስለሆነ ነው ፈቃድ መጠየቃችን) ማታ ለእናንተ ለምንወዳችሁ ይደርሳል ማለት ነው ። ክፍል አንድ 5 mb ብቻ ነች። ዳውንሎድ ለማድረግ እንዳትቸገሩ ከ 21 mb ላይ ነው ወደ 5mb የቀነስነው ሆኖም ግን ጥራቱ ቆንጆ ነው ። ወደ ቻናላችን የምትገቡትን እና አስተያየታችሁን መሠረት በማድረግ ክፍል ሁለት በፍጥነት ይለቀቃል። ወደ ቻናላችን ለገባችሁት ደግሞ ምስጋናችን እጅግ በጣም ከፍ ያለ ነው !!!!!!!! ማታ ይጠብቁን!!
Читать полностью…