ኢትዮጵያ አረቄ ነች ወዳጄ
ያለልምድ ያለአቅም ያለ ጥንቃቄ ከነኳት ጭንቅላት የምታዞር የምታደነባብር ጀግና የጀግና ሀገር ነች።
ግብጽ እና ሱዳንን ይመለከቷል!!!
ገና አሜሪካም ጭንቅላቷ ዞሮ ዧ ብላ ትወድቃለች።
እናም ኢትዮጵያ ከባድ አረቄ ነች እልሀለሁ
ፊደል አስር ነኝ
መልካም አዳር!!
ምንጭ ማህበራዊ ድህረገጽ ነው ።
ይሄ ትልቅ በጣም ትልቅ ሀይለ ቃል ነው ። የሁላችንም መፈክር ሊሆን ይገባዋል።
ታዲያ ከኛ ውጭ ለእኛ ማን አለን ????????
ለዚህ ንግግር ባለቤት የ ጦር ሃይል አዛዥ ክብሬ ከፍ ያለ ነው ። መልካም አዳር!!!❤️❤️❤️❤️💋💋💋💋💋
ፊደል አስር
ለዚህ ፖስት ትልቅ ይቅርታ አድርጉልኝ ፖለቲካ ውስጥ ባልገባ ደስ ይለኝ ነበር ።
የ ኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ ሰሞኑን 11000 ( አስራ አንድ ሺህ ) ፕሮጀክቶችን እናስመርቃለን ብለው በተናገሩ በማግስቱ
ይህ ፎቶው ላይ የምታዩት የሆነ ነገር ደግሞ በአማራ ክልል የሆነ ቦታ ላይ እየተመረቀ ይታያል።
ነገርየው ምንድንነው ። ምናልባት ከ ፕሮጀክቱ ይልቅ ፕሮጀክቱን ለማስመረቅ ከመጡት ሰዎች መሃል ለአንደኛው ሰውዬ ለትራንስፖርት የሚወጣው ውጭ ብቻውን ይበልጣል ይመስለኛል።
ምንድንነው እንደዚህ ሞራላችንን የነጠቀን??? ምንድንነው እንደዚህ ያደከመን ነገር???
ምናልባት ፎቶው የሆነ ቦታ ላይ የተቆረጠ ከሆነ እና ሰውን ለማናደድ ታስቦም ከሆነ የሚመለከተው ስለ ሙሉ ፕሮጀክቱ በዜና መልክ መግለጽ አለበት።
ካልሆነ ግን አይነፋም።
ለማንኛውም መልካም ቀን ይሁንላችሁ።
ፊደል አስር ነኝ!!!!
ሰው ህመም ሰው መድህን!!!
ለሰው ህመሙም መድሀኒቱም ራሱ ሰው ነው !!!!!
ታዲያ ለማን ምን እየሆንን ነው ??? የታለ አብሮነታችን?? የታለ ርህራሄአችን??????? የታለ ደግነታችን??
እንዴትስ ሆኖ ነው ይሄ ሁሉ ከእኛ የራቀው???
ደግ ነን ብለን የምናስብ ሰዎች እስኪ የታለን!!??
"አቤቱ በአንተው እስትንፋስ በአምሳልህ ተፈጥረን
ግፋችን ልክ አልፏልና በይቅርታህ ማረን"
እንዳለችው ድምፃዊቷ ይልቁንስ ወደ ልባችን እንመለስ እና ሁላችንም
አቤቱ ማረን እንበል!!!!!!!!!!!!!!!!!!
የቀደመው ደግነት ርህራሄአችን የቀደመው አብሮነታችን አሁኑኑ ይመለስልን!!!
ፊደል አስር!!!!!❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ኮሚክ እኮ ነው፡፡ ምን ይመስለኛል መሰላችሁ…ከእለታት አንድ ቀን… አለ አይደል… “በቃ በሞባይል ድምጽ ሳይቆራረጥ ማውራት ላንችል ነው!” ሲባል መልሱ ምን ሊሆን ይችላል መሰላችሁ፣ “ምን እናድርግ! የአጼዎቹ ስርአት ጥሎብን የሄደ ችግር ነው፡፡”
እንዴት ሰነበታችሁሳ! በመኪና አሽከርካሪዎች ባህሪይ ከአፍሪካም፣ ከዓለምም ስንተኛ እንደሆንን ይጣራልን፡፡ ግራ ገባና...የከተማችን ባለመኪኖች፣ ያውም የሆሊዉድ ሰዎችን አይነት ሊመስሉ ምንም የማይቀራቸውን መኪና እየነዱ የሚያሳዩት ባህሪይ...አለ አይደል... “ጧት ቁርስ ሆት ዶግ፣ እንቁላል ቁጭ ቁጭና ብላክ ሌብል፣ ቀን ምሳ ቢፍ ስቴክና ብሉ ሌብል፣ ማታ እራት ቺክን ሮስትና ጎልድ ሌብል የሆነ ‘ዳየት’ በአፍንጫችን ይውጣ!” ብንል አይፈረድብንም፡፡ (“በቃ ነፍስ ካላቸው ምግቦች እነኚህን ብቻ ነው የማውቀው ለምትሉና ‘አኒማል ፕሮጀክት’ ስልችት ላላችሁ እስቲ “ቁርሴን እርጥብ ነው የበላሁት፣ እርጥብ ምን እንደሆነ ንገሩኝ፣” ብላችሁስ! ስሙኝማ...እንግዲህ ጨዋታም አይደል... አብዛኞቹ የአዲስ አበባ አሽከርካሪዎች ‘እየነዱ’ ነው ‘እያበረሩ’ የሚባሉት! የሆነ ሰው መጥቶ... “እመንም፣ አትምንም አራቱም ጎማዎች ከመሬት ለቅቀው ለአንድ አስር ሜትር ያህል በአየር ላይ የሚበር መኪና ቦሌ መንገድ አየሁ፣” ቢለኝ በችኮላ “የጠጣኸው ጠጅ ሙሉ ለሙሉ በግራዋ ብቻ ነው የተጠመቀው?” ከማለቴ በፊት “ምናልባትም አይቶ እንደሆንስ!” ልል እንደምችል ለማስመዝገብ ያህል ነው፡፡ ተቸገርን እኮ! የምር አንዳንዶቹ መኪኖች አጠገባችን ሳይደርሱ እንኳን ‘ሽው’ ብለው ሲያልፉ የሚፈጥሩት ነፋስ “እንዳሞራ ክንፍ አውጥቼ ልብረራ...” ሊያሰኙን ምንም አይቀራቸው፡፡ እኔ የምለው... የባህሪይ ነገር ካነሳን የሆነ የከተማችን ክፍል ነው፣ መአት መኪኖች ተጠጋግተው ቆመዋል፡፡ የምር እኮ... “አነኚህ መሀል፣ መሀል ያሉት እንዴት ብለው ነው የሚወጡት!” የሚያሰኝ ነው፡፡ (መኪኖች መንገድ ዳር ምናምን ሲቆሙ በመሀላቸው ሊኖር ስለሚገባው እርቀት የሆነ ህግ ምናምን ነገር የለም እንዴ! ) እናላችሁ...የሆነች እንደ ዘመናዊዎቹ ከሩቅ የምትጣራ ባትሆንም ከማን አንሼ አይነት መኪና ውስጥ ሞተር አጥፍቶ የተቀመጠ ሰው አለ፡፡ በሞባይል እያወራ ነበር፡፡ ከእሱ ፊት የነበረው መኪና ባለቤት ይገባና አስነስቶ ሲያንቀሳቅስ ሸርተት ብሎ ኋላ የነበረውን ይገጨዋል፡፡ ከዛ ገጪው ራሱ አንበሳ ሆኖ ይወጣላችሁና በሰላም መኪና ውስጥ የነበረው ሰውዬ ላይ ይጮህበታል፡፡ “ለምንድነው መኪናህን ወደ ኋላ የማታደርግልኝ! መኪናዬን ያደረግኸው ይታይሀል!” የሚገርም እኮ ነው፡፡ የ‘ምኒታ ተቆጢታ’ የሚሉት ነገር አይነት ነው፡፡ ታዲያላችሁ...በእርጋታ ተቀምጦ የነበረው ሰውዬ ተፈናጥሮ ሲወጣ...አለ አይደል... “አንዳንድ ሰው በጣም ሲናደድ ክብደቱ በምን ያህል ኪሎ ነው የሚጨምረው?” ያሰኛል፡፡ አልተናገረ፣ እልጮኸ...ብቻ ሰውየውን ተጠግቶ አፈጠጠበት፡፡ የተፈጥሮ ተአምር የሚባለውን ነገር ይሄኔ ነው የምታደንቁት፡፡ በሦስት ስከንድ ውስጥ ከአንበስነት ወደ‘ሚያውነት’ መውረድ ይቻላል! (ቂ...ቂ...ቂ...) ደግነቱ ወዲያው እግር የጣለው አይነት ትራፊክ ከች አለ፡፡ በቀደሙት ዘመናት እንደ ጨዋታ አይነትም የምትባል ነገር ነበረች... ኩኩ መለኮቴ እሷ በበላችው በእኔ ላከከችው፡፡ ኋላ የነበረው ሰውዬ እኮ መኪናውን ላንቀሳቅስ ቢል እንኳን መፈናፈኛ አልነበረውም፡፡ እናላችሁ የፊተኛው ሰውዬ በስነስርአቱ መኪናውን ማንቀሳቀስ ስላቃተው ሀገር ሰላም ብሎ የነበረው ሰውዬ ላይ ማሳበብ አለበት! ግን ምን መሰላችሁ...የሆነ ባህል ሊሆን ምንም የቀረው የማይመስል ነገር ነው... በሁሉም ነገር ላይ ሌላ ጣት የምንቀስርበት መፈለግ፡፡ እናላችሁ…እንግዲህ ጨዋታም አይደል...በምኑም በምናምኑም ‘ሰበብ’ ፍለጋ... ‘ናሽናል አይዴንቲቲ’ ነገር ሊሆን ምንም አልቀረው፡፡ በፊት ጊዜ የብሄራዊ ቡድናችን ሌላ ሀገር ሄዶ ሦስትም፣ ምናምንም ጠጥቶ መምጣት ለምዶበት ነበር፡፡ (አንድ ጊዜ የአልሲሲ ሀገር ተጫዋቾች ስምንት ነው ምናምን ነገር አጠጥተውን ነበር፡፡ (አይ... ‘ድፍረቱ’ ዛሬ የተጀመረ አይደለም ለማለት ያህል ነው፡፡ ቂ...ቂ...ቂ...) ታዲያ...ቡድናችን በተሸነፈ ቁጥር ሁልጊዜ የሚሳበበው በምን ነበር መሰላችሁ...በአየሩ፡፡ “አየሩ ከብዶን ነው፣” ይባል ነበር፡፡ በቦተሊካው የሆነች አሁን፣ አሁን ከመሰልቸቷ የተነሳ ለ‘ጆክነት’ እንኳን የማትመች ሰበብ አለች፡፡ ቦተሊከኛውም፣ አክቲቪስቱም፣ ተንታኙም፣ አንዳንድ የከተማችን ነዋሪዎችም--- ሁላችንም በ‘ትናንት’ ላይ ማሳበብ ይቀናናል፡፡ ኩኩ መለኮቴ እሷ በበላችው በእኔ ላከከችው፡፡ “ይሄ ነገር እንዴት ነው እንዲህ ሊሆን የቻለው?” “ያለፉት ስርአቶች ጥለውብን የሄዱት ነው፡፡” ኮሚክ እኮ ነው፡፡
ምንጭ ማህበራዊ ድህረገጽ
ከዋናው ጽሑፍ ላይ ተቆርጦ የቀረበ
መልካም ቀን
😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂
ሮጠን ቀደምናቸው
ቆመን ጠበቅናቸው
ጥለውን አለፉ
አለች እማማ ዝናብነሽ !!!!!!!!!
ለካ እየቆምን ነው ጥለውን ያለፉ
በሉ ቁጭ በሉ አሁን !!! 😂😂😂😂👍👍
የተባረከ ቀን ይሁንልን!!
በሁሉም መስክ አሸናፊዎች ያድርገን
ፊደል አስር ነኝ።
መርካቶ መሀል ዕቃ ለመግዛት እያዘገምኩ ነው። ድንገት ሰው ተሰብስቦ ሲያዳምጥ አየሁ። አንድ “ንክ” ቢጤ እየተንጎራደደ ይለፈልፋል። ‹‹እንዲያው ሰው ሥራ ፈት ነው፣ አሁን ይኼ ምኑ ይታያል?›› ብዬ ላልፍ ስል ወሬው ጆሮ ገብ ሆነብኝ። ‹‹ጅምላን ማን ይወዳል? ቢሉ፣ መልሱ ነጋዴ ብቻ ነው፤›› ሲል ሰማሁት። ‹‹በጅምላ የሚሸጠውም በጅምላ የሚገዛውም ነጋዴ ነው።››
አሃ! ሰውዬው ነጋዴ ወይም የቢዝነስ ተማሪ ነበር ማለት ነው ብዬ ላልፍ ስል ሰውየው ቀጠለ። ‹‹ጅምላ ብሎ ነገር የለም፣ ለንግድ ካልሆነ በቀር። እያንዳንዱ የግሉ ምርጫ አለው፣ የብቻ ተመን አለው፣ ልዩ ሚዛን አለው፣ የራሱ ክብር አለው። እንዴት ሁሉን በአንድ መለኪያ በጅምላ እንለካ ትላላችሁ። ቁመትን በሜትር፣ ክብደትን በኪሎ፣ ፈሳሽን በሊትር እንደምትለኩት ሁሉ፣ የእያንዳንዱን ውበት፣ አስተሳሰብ፣ ጥንካሬ፣ እውነትና ፍላጎት የምትለኩት በየራሱ መለኪያ ሊሆን አይገባም? ዳሩ አይገባችሁም! ቢገባችሁም የሚታያችሁ ትርፍ ብቻ ነው። አጭበርባሪዎች! ግን ልክ እንደ ቀድሞው ከስራችኋል፣ ስታሳዝኑ!›› አለና ወደኋላና ወደፊት ተንጎራደደ ሰውየው።
አንዱን አጠገቡ ያለውን ተጠግቶ "ስማ! አንድ ዓይነት ፋሽን፣ ተመሳሳይ ሐሳብ፣ አንድ ዓይነት የፀጉር ቁርጥ፣ ታይት ሱሪ፣ ፒኪኒ ፓንት፣ ስኪኒ ሱሪ፣ ጆርዳን ጫማ፣ ምናምን እያልክ በጅምላ ውስጥ እስከ መቼ ትደበቃለህ? ልዩነትን መፍራት አይደብርህም እንዴ?" አለው።
ባለፍሪዙ ወጣት ዝም ብሎ ፈገግ አለ። ‹‹አይገርምም? ሙዚቃው እንኳ አንድ ዓይነት ካልሆነ አትጫወቱም? ዝም ብላችሁ ከጠዋት እስከ ማታ ‘የእኔ ማር!' ብላችሁ ትጮሃላችሁ። ውሸት! ውሸታችሁን እኮ ነው። እንደ ችቦ በጅምላ ታስራችሁ ነፃ ነን ትላላችሁ! ዳሩ መቼ ይገባችኋል? ሁሉ የሚወደውን ትሸጣላችሁ፣ ሁሉ የሚወደውን ለመግዛት ትሻማላችሁ! ከዚያ ደግሞ ዋጋ በዛ ትላላችሁ። መፅዳቆች! በፎቶ ኮፒ የተባዛችሁ እኮ ነው የሚመስለው፣ ጅምላ ነጋዴ ሁላ!›› ሲል ሰው ሁሉ ሳቀ።
ተገርሜ ቆሜ ማዳመጤን ቀጠልኩ። ንግግሩ ጠጠር ያለ ነው።
‹‹ጅምላ ስድብና ጅምላ ፍረጃ ጅምላ ጠላትን ይፈጥራል። ይህ እንኳን አይገባችሁም። ይኸው አሁን አንድ አስተባባሪ ብታገኙ እኔ ላይ በጅምላ ልትቧደኑ ያምራችኋል። በጅምላ ስም አውጥታችሁ፣ አጥር ውስጥ ከትታችሁ ሰው ትሰድባላችሁ፣ ታጠቃላችሁ። በጅምላ ስትሰደቡም በጅምላ ትሟገታላችሁ፣ በጅምላ ትጣላላችሁ። ለብቻ መሆን ትፈራላችሁ። በመንጋ ውስጥ ደኅንነታችሁ የተጠበቀ ይመስላችኋል። ለብቻው ከሚሄድ አንበሳ ይልቅ የአጋዘን መንጋ አደጋ ላይ ያለ መሆኑ አይታያችሁም። በጅምላ ሲነዷችሁ እሺ ነው። በአንዱ ጥፋት ሳይገባችሁና ሳታምኑበት በፍርኃት ተሸብባችሁ ትስማማላችሁ። በዚያም የተነሳ ሌሎች ገደል ሲገቡ እያያችሁ፣ እናንተም የዛሬን ተስማምቶ ለማለፍ ከእነ ልዩነታችሁ ትቧደናላችሁ። ይህ ሁሉ ግፋችሁን ለማብዛት ነው። ጊዜው ሲደርስም ያው እንደተለመደው የእጃችሁን ለማግኘት ነው። ኧረ ሳይረፍድ ንቁ! አሁንስ ፋሲካ የመጣባችሁ በጎች መሰላችሁኝ። እረኛና አራጅ እንኳ መለየት ይሳናችሁ?›› አለ። ሰው ሁሉ እያንሾካሾከ ተገለማመጠ።
ሰውየው ጎንበስ ብሎ ወረቀት አነሳና ወሬውን ቀጠለ። ፈገግ ብሎ ከወረቀቱ ላይ የሚያነብ ይመስላል። ‹‹ሰውን በአንድ አስተሳሰብ ደምሮ አስማምምቶ ሆነም አስገድዶ የሚያቀርብ በሰው ፍላጎት የሚነግድ ነጋዴ ነው። ምክንያቱም አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ብሎ ነገር የለማ! በሰው ፍላጎት የሚነግድ ደግሞ በችርቻሮ ሲሆን አታላይ፣ ሰውን አጃምሎ ሲያቀርብ ደግሞ ፖለቲከኛ ነው። የሰው ፍላጎት ሲጀመል ነው ፖለቲካ ብቅ የምትለው። ፖለቲካ ፈሪ ናት። ፖለቲካ ብቻዋን አትቆምም፣ ነፍስ የላትም፡፡ ነፍስ የምትዘራውም ጥንካሬና ውበቷ የሚጨምረውም ጅምላነት ሲበዛ ነው። አለበለዚያ ኮስሳ ኮስሳ ትሞታለች። አይደለም እንዴ?›› ብሎ አፈጠጠብኝ። አንድ አዛውንት "ጎመን በጤና!" አሉ።
‹‹አሁን ሌባ አልበዛም?፣ ወሬ አልበዛም? በዝቷል። ምን ዝም ትላለህ? ማናለብኝነት ነግሷል፣ ኃላፊነትን መሸሽ ተንሰራፍቷል። ፖሊስ ከሸሸ የማን ያለህ ይባላል? ምናገባኝ ከበዛ ማን ሊያገባው ነው? እንዴት አለሁ ባይ ይጠፋል? የጎበዝ አለቃ እንፈልግ እንዴ? ተው! ዋ! ዋ! ብቻ ተጠንቀቁ፣ በጅምላ ውስጥ አትደበቁ።››
ድንገት "የምፅዓት ቀን ቀርባለችና ንስሐ ግቡ!" የሚል ሰባኪ መሰለኝ። "እውነትም ንስሐ ያሻናል!" አልኩ ለራሴ። "አሁን በቀደም ለት…" ሰውየው እያየኝ ቀጠለ። ንግግሩን ተከትዬ ድንገት ፈሪዎች ተቧድነው አንድ ሰው ሲያጠቁ ያየሁት ትዕይንት በዓይነ ህሊናዬ ታየኝ። ንድድ አለኝና "ክላ!" ብዬ እኔም መንገዴን ወደ ጉዳዬ ቀጠልኩ... ተናጋሪውን የእውነት “ንክ” ነው ማለት ከበደኝ። ግርም ብሎኝ ሰማሁት፣ ውስጤ የቀረውን ለእናንተ ላካፍል ወደድኩ። “Thumbs Up!” ሳልለው ቀረሁ እንዴ? እንጃ። አይ መርካቶ!
(ቱጌ ጂ. ከበደ፣ በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው)
ፊደል አስር ደግሞ ወደ እናንተ አመጣው
'ረሃብ ትችላለህን'?? ቢሉት
' ኧረ ጥጋብም እችላለሁ ' አለ አሉ!!!!!
ከ ፊደል አስር ጋር በመሆንዋ ብቻ ከተለያየ አቅጣጫ መዝናኛ እና ዕውቀት ያለማቋረጥ ይደርስወታል።
መልካም ቀን
ለአስተያዬትዎ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ
@Fogremover
ከዊንጌት የያዝኩት ሚኒባስ ታክሲ ወደ ፒያሳ እያመራ ነው፡፡ የኮሮና ወረርሽኝ ብዙዎችን እያሳጣን ባለበት በዚህ አስፈሪ ጊዜ፣ ታክሲውን እጭቅ አድርገው የሞሉት ወያላና ሾፌር በዕድሜ ተቀራራቢ በመሆናቸው በማይገባን የንግግር ዘዬ እየተቀላለዱ ይሳሳቃሉ፡፡ በዚህ መሀል አንድ ትልቅ ሰው፣ ‹‹እናንተ ምናለባችሁ ሕግ እየጣሳችሁ እኛን እንደ ጌሾ ጠቅጥቃችሁ ተጫወቱብን እንጂ…›› እያሉ በምሬት ተናገሩ፡፡ ወያላው ተንጠራርቶ እያያቸው፣ ‹‹ፋዘር ታክሲና ኑሮ መቼ ሞልተው ያውቃሉ? ካልተመቸዎት እኮ ቢፈልጉ ራይድ፣ ፈረስ፣ ሄሎ ታክሲ ሞልቷል…›› እያለ ሲያሾፍ አነጋገሩ አናደደኝ፡፡ ታክሲው በትርፍ ከያዛቸው ሰዎች በተጨማሪ በዕቃ ተጨናንቋል፡፡ በስጨት ብዬ፣ ‹‹አባትህ አይሆኑም? እንዴት በእሳቸው ትቀልዳለህ? ሕግ እየጣሳችሁ መተንፈሻ አጥተን ተጣበን አንተ ታሾፋለህ?›› ስለው እየሳቀብኝ፣ ‹‹ፍሬንድ አትበሳጭ፣ ንዴት የድመትን ጀርባ ከማጉበጡ በቀር የሚፈይደው የለም…›› ሲለኝ ታክሲው በተሳፋሪዎች ሳቅ ተሞላ፡፡
ይህ ቀልደኛና ተረበኛ ወያላ እኔና አዛውንቱን ሲያሾፍብን የሌሎቹ ተደርቦ መሳቅ አናዶኝ ስለነበር፣ ‹‹ግድ የለም ቀልድ፣ ቁምነገር በተዘነጋበት በዚህ ዘመን ቀልድ በዝቶ ነው አገር መላ ያጣችው…›› አልኩኝ፡፡ በዚህ መነሻ አንዷ ዘመናይ፣ ‹‹የእኔ ወንድም አገሩ በሙሉ በኮሜዲ ፊልም ተጥለቅልቆ መሳቅ እንጂ መናደድ ዋጋ የለውም…›› እያለች ስትንጣጣ ገረመኝ፡፡ ቀልድና ቀልደኞች በዝተው ምን መናገር ያስፈልጋል ብዬ የታክሲውን ዙሪያ ገባ ስቃኝ የተለያዩ ጥቅሶች ተለጥፈዋል፡፡ ‹‹መጨቃጨቅ ከአሸባሪነት አይተናነስም››፣ ‹‹ኮሮናንና የጫማ ሽታን በጋራ እንከላከል››፣ ‹‹ሾፌሩን በፍቅር እንጂ በነገር መጥበስ ክልክል ነው››፣ ‹‹መብትዎ ታክሲ ውስጥ ብቻ ትዝ አይበለዎት››፣ ‹‹ታክሲያችን የፍቅር እንጂ የጭቅጭቅ መድረክ አይደለም››፣ ወዘተ የሚሉ ጥቅሶች ተለጥፈዋል፡፡ ከሆሊውድ እስከ ቦሊውድ አክተሮች በየዓይነቱ ምሥላቸው በብዛት ይታያል፡፡
በዓይኔ ያደረግኩትን አሰሳ ስጨርስ ከወያላው ጋር ዓይን ለዓይን ተጋጠምን፡፡ ‹‹ፍሬንድ ተመቸህ?›› ሲለኝ ‹‹ምኑ?›› በማለት ጠየቅኩት፡፡ ‹‹የታክሲያችንን ሙዚየም ማለቴ ነው…›› አለኝ፡፡ ‹‹እንቶ ፈንቶውን አይቼልሃለሁ፣ የደረደርከው ሁሉ ለማንም አይጠቅምም…›› አልኩት፡፡ ወያላው የኮሜዲ ፊልም ወይም ድራማ የሚያይ ይመስል ተንከትክቶ ሳቀ፡፡ ሳቁን ሲጨርስ፣ ‹‹ፍሬንድ የአንተ ችግር ምን እንደሆነ ደረስኩበት…›› አለ፡፡ በጣም ከመገረሜና ከመደንገጤ የተነሳ፣ ‹‹የእኔ ችግር ምንድነው?›› ማለት፡፡ ወያላው አሁንም እየሳቀ፣ ‹‹የአንተ ችግር በምታየው ነገር አለመዝናናት ነው፣ በምታየውና በምትሰማው ካልተዝናናህ ድብርት አለብህ ወይም ሕመም ይኖርብሃል…›› ሲለኝ ወይ ድፍረት እያልኩ መናደድ ጀመርኩ፡፡
ያቺው ሴት፣ ‹‹ትክክል ነው፣ አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን ዘና የሚያደርግ ነገር የማይፈልጉት ወይም የሚሸሹት ውስጣዊ ችግር ስላለባቸው ነው…›› ብላ ራሷን እንደ የሥነ ልቦና ባለሙያ አቀረበች፡፡ እኔና አጠገቤ የተቀመጡት አዛውንት ስንቀር ሌሎቹ ይስቃሉ፡፡ በዚህ መሀል ሾፌሩ፣ ‹‹ለዚህች ለማትሞላ ዓለም እየተጨነቅን ራሳችንን ድብርት ውስጥ ለምን እንደምንከት ይገርመኛል፡፡ ጥለነው ለምንሄድ የታክሲ መቀመጫና ለማይሞላው ዓለም እየተንገበገብን ራሳችንን እናቆራምዳለን፡፡ ለዚህች ከንቱ ዓለም መድኃኒቱ ፊት ሳይሰጡ ባገኙት ነገር መዝናናት ነው…›› ሲል ሌሎቹ ‹ልክ ነህ› በሚል ስሜት ሳቁለት፡፡ ዛሬ ደግሞ ሰው ምን ነክቶት ነው የሚፈላሰፈው እያልኩ ተገርሜያለሁ፡፡
የታክሲው ሾፌር፣ ወያላውና ሌሎቹ ተሳፋሪዎች ዓለምን ንቀው ሲደሰኩሩ አዛውንቱ ወደኔ ጠጋ ብለው፣ ‹‹ልጄ አትበሳጭ፣ ይኼ ሁሉ ወፈ ሰማይ እኮ የውስጡን ጭንቀት ለማስተንፈስ ሲል ዝባዝንኬውን ቢለፈልፍ እውነት እንዳይመስልህ…›› እያሉኝ ሳለ አንዱ የተደወለለትን ስልክ አንስቶ፣ ‹‹ኧረ እባክህ? መቼ? አሁን?...›› እያለ በድንጋጤ ይርበተበት ጀመር፡፡ ስልኩን ዘግቶ፣ ‹‹ሾፌር እስቲ ሬዲዮ ክፈት…›› እያለ ሲጮህ ሁላችንም በድንጋጤ ምን ተፈጠረ ብለን ዓይናችን ፈጠጠ፡፡ ሾፌሩ በፍጥነት የኤፍኤም ጣቢያዎችን ሲጎረጉር ዘፈን ብቻ ነው የሚደመጠው፡፡ በመጨረሻ አንደኛው ጣቢያ ሙዚቃውን አቁሞ አንዲት ታዋቂ ኢትዮጵያዊት በኮሮና ሳቢያ ሕይወታቸው ማለፉን ተናገረ፡፡ ድንጋጤ ነው መሰል ታክሲያችን በፀጥታ ተሞላ፡፡ ነፍሳቸውን ይማረውና እኚህ ሴት በተለይ የኦቲዝም ተጠቂ የሆኑ ልጆችን ሕይወት የቀየሩ መሆናቸው ስለሚታወቅ፣ ሁላችንም በድንጋጤ ነበር ዜናውን የሰማነው፡፡ እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነገር ሲገጥም ማዘን ያለ በመሆኑ አንገቴን ደፍቼ ተከዝኩ፡፡
በፀጥታው መሀል ያቺ ሴት፣ ‹‹ፊጣሪዬ ይቅር በለን፣ ስናውቅ በድፍረት ሳናውቅ በስህተት ለምንሠራው ሥራ ሁሉ ይቅርታህ አይለየን..›› እያለች ስትማፀን፣ ወያላው በበኩሉ፣ ‹‹ምን ዓይነት ዘመን ውስጥ ነው ያለነው እባካችሁ?›› ማለት ጀመረ፡፡ ሾፌሩ፣ ‹‹በጣም ከመደንገጤ የተነሳ ምን እንደምል ግራ ይገባኛል…›› እያለ ሲናገር ሌሎቹ ከንፈራቸውን እየመጠጡ ተክዘዋል፡፡ ፒያሳ ደርሰን ታክሲው ሲቆም አዛውንቱ፣ ‹‹ልጄ አየህ አይደል? የብዙዎች ፉከራ ከአንገት እንጂ ከአንጀት ባለመሆኑ ብዙም አትገረም…›› ብለውኝ ሲሰናበቱኝ፣ ‹‹እኛ እኮ የአንድ አገር ሰዎች ብንሆንም እንደ አንድ ቤተሰብ ስለሆንን ቀልዳችንን፣ ቁጣችንንና የተለያዩ ፍላጎቶቻችንን በልክ ብናደርግ የሚያስቸግረን ነገር የለም፡፡ የሚያምርብን አንተ ትብስ አንቺ ስንባባል ነው…›› ካሉ በኋላ አቅፈው ስመውኝ ተለያየን፡፡ እንዲህ ነው አባትነት፣ ወገንነት፣ ትልቅ ሰውነት፡፡
(መሳፍንት በዛብህ፣ ከዊንጌት)
ምንጭ ማህበራዊ ድህረ ገጽ ኢትዮጵያን ሪፖርተር በሳምንቱ ገጠመኝ አምዱ ካሰፈራቸው)
ፊደል አስር ደግሞ ትዝናኑበት እና ትማሩበት ዘንድ ወደ እናንተ አደረሰ
ፊደል አስር ቻናልን በሚመለከት ማንኛውንም አስተያየት ለመስጠት ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ
@Fogremover
'ከሯጭ ፈረስ ይልቅ መንገድ የምታውቅ አይጥ ትሻላለች'!!!
ከእለታት አንድ ቀን የዱር አራዊት ተሰብስበው ድግስ ለመደገስ ያስቡና የድግሱን እቃ ግዥ የሚያሳኩ እጩዎችን ለመምረጥ ይወያያሉ። በመጀመሪያ በአያ አንበሶ ጥያቄ ሰጎን ስሟ ተጠቀሰ። እመት ጦጢት ሃሳብ ሰጠች፡- “ሰጎን ለሩጫና ለሽቅድምድም ትመቻለች፤ ነገር ግን የእቃ ግዥነት ልምድ የላትም፤ ስለዚህ ሌላ ተመራጭ እንጠቁም” አለች። ቀጥሎ ዝሆን ሀሳብ ሰጠ፡- “እንደ እኔ እንደ እኔ ጦጢት የምትሻል ይመስለኛል፤ ምክንያቱም ገበያውን ስለምታውቅ የተሻለ እቃ ግዥ ትሆነናለች” ቀጥሎ ዝንጀሮ ተነሳና:- “ጦጢት ብልጥ ናት እንጂ የምግብ ዓይነት ምርጫዋ ውስን ነው፤ ስለዚህ ነብርን ብንልከው ያዋጣናል” አያ ጅቦ ቀጥሎ ሃሳቡን ገለጠ:- “አያ ነብሮ ጥሩ ምርጫ አይመስለኝም፤ እሱ ስጋ በል ስለሆነ ስጋ ያሳሳዋል። ስለዚህ ስጋ በሎቹንና ቅጠል በሎቹን ያምታታቸዋል። በእኔ እምነት ዔሊ ሄዳ ገዝታ ብትመጣ ያዋጣናል እላለሁ” በአያ ጅቦ ሃሳብ አብዛኛዎቹ እንስሳት ተስማሙና ዔሊ ወደ ገበያ ተላከች። ጥቂት ሰዓታት እንዳለፈ አውሬዎቹ ማጉረምረም ጀመሩ። ረሃቡ ጠንቶባቸዋል። “ድሮም ዔሊን መላካችንና ይቺን ቀርፋፋ መልዕክተኛ ማድረጋችን ትልቅ ስህተት ነው። ገና እየተንቀረፈፈች ደርሳ እስክትመለስ ድረስ ሁሉም በርሃብ ሊሞት ይችላል; አሉ። ለካ ዔሊ ገና አልተንቀሳቀሰችም ኖሯል። አንገቷን በበሩ ብቅ አድርጋ፡- “እንደዚህ የማታምኑኝ ከሆነ እንደውም ከነጭራሹ አልሄድም” አለች፡፡ የሀገራችን የሰው ሃይል ምጣኔና ምርታማነት መለኪያ ከሆኑት መስፈርቶች አንዱ ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛው ቦታ ማስቀመጥ ነው። (The right man at the right place) የሚባለው ነው። የተማረ የሰው ሃይልን በወጉ አለመጠቀም ትልቅ በደል ነው። በአንጻሩም የተማረው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ እውን በአግባቡ ተምሯል ወይ ብሎ መጠየቅም ያባት ነው። የተማረው ክፍል አገሬን እወዳለሁ እንዲልና ምን ጎድሎባታል? ምንስ ሞልቶላታል? እኔ ምን አስተዋጽኦ ላድርግ? ብሎ እንዲጠይቅ ማድረግ ተገቢ ነው። የቀድሞው ንጉስ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ “ሀገሬ ምን ታደርግልኛለች ከምትል እኔ ለሀገሬ ምን ላድርግላት በል” ብለው ነበር። የህዝቡን የትምህርት ስርዓቱን መመርመር፣ ከተቻለም በየጊዜው መፈተሽ ዋና ነገር ነው። ምንግዴነትን ማስወገድ ያሻል። አንድ የሀገራችን ገጣሚ እንዳለው እኔ ምን አገባኝ የምትሉት ሐረግ እሱ ነው ያረዳት ሀገሬን እንደ በግ ብዬ ግጥም ልጽፍ ተነሳሁኝና ምናገባኝ ብዬ ቁጭ አልኩ እንደገና” እንዳይሆንብን እንጠንቀቅ። አንድም የምርጫ ዘመን እየመጣ ነውና ትክክለኛውን ተመራጭ አንጥሮ በአግባቡ መምረጥ ለሀገርና ለህዝብ ሁነኛ እርምጃ እንደሚሆን ከወዲሁ እንገንዘብ።
ምንጭ ማህበራዊ ድህረገጽ ላይ ካነበብኩት የተወሰደ
ፊደል አስር ነኝ መልካም ቀን !!!!!
'ከህይወት እና ከሞት የቱ ይሻልሀል' ተብሎ ሲጠየቅ ፤ ሲያስብ ዘገየ አሉ
😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂
አይ ጋሼ ዘገየ!!
ማነህ ዘገየ የሚባል ስም ያለህ ሰውየ አደራ ጽሑፉ በቀጥታ ለአንተ አይደለም ሳነብ አግኝቸው ነው ያካፈልኩህ።
' ጓ ' አትበሉ ከኛ ጋር ብቻ ሁኑ ትደሰታላችሁ!!!!!!!!!
እናንብብ ካነበብነው ውስጥ ለጉዋደኞቻችን በተለየየ መልኩ እናካፍል።
ፊደል አስር ነኝ ሥራ ውየ ቤት ውስጥ ገብቼ እግሬን ታጥቤ እስኪደርቅልኝ ድረስ ቁጭ ብየ😂😂😂
ደፋሮች የተናገርከውን ሰምተው ለጠብ ይዘጋጃሉ !!!
አዋቂዎች ግን የተናገርከውን ብቻ ሳይሆን ልትናገር የፈለከውን ተረድተው ያስተምሩሀል።
ተስፋሁን ከበደ ( ፍራሽ አዳሽ )
እንዲያው በፈጠራችሁ ተስፋሁን ከበደን የምትወዱት ላይክ እያደረጋችሁ እለፉ።
እዚህ ግሩፕ ውስጥ ራሱ ተስፋሁን ከበደ አለ
🤫🤫🤫🤫🤭🤭🤭❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
አሁን እኮ የቸገረን
አብዛኛው ሰው
ድህነትንና
ድሀን
መለየት አልችል ብሎ ነው !!!!!
ሰው ወዶ አይደኸይም እኮ ማነህ ጉዋደኛዬ !!! ሃብት ደግሞ ነገ ጥሎህ ነው የሚጠፋው !! ዛሬ ላይ ሰው ወገን ዘመድ አፍራበት። ሀብትህ ጥሎህ ቢጠፋ ቢያንስ ሰው ከጎንህ ይኖርሀል !!!
ሰምተሀል!!!
ዕድል የሰጠችህን ሃብት ተጠቀም፤ሰርተህ ያፈራኸው ሃብት ከሆነ ደግሞ የበለጠ ደስ ብሎህ ተጠቀም። ነገር ግን በሁለቱ መሃል አንድ ነገር አትርሳ
ሌሎች ሰዎችን በፍጹም ፤ተሳስተህ እንኩዋን አትበድል። በፍጹም !!!!!!!!!
መልካም ቀን
ፊደል አስር።
የሗላ ማርሽ ብቻ እንደተገጠመበት ተሽከርካሪ ወደ ሗላ ብቻ የሚጓዝ እና የሚያስብ ያለፈ ነገር ብቻ እያነሳ የሚጨቃጨቅ ሰው ግን እንዴት ነው የሚያናድድ ባካችሁን ።
💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪
ብዙ ጊዜ ሚኒባስ ታክሲ ውስጥ ስሳፈር አስገራሚ ነገሮች ይገጥሙኛል፡፡ በተለይ አራዳ ሾፌሮችና ወያላዎች የሚሠሩባቸው ታክሲዎች ከሆኑማ አንዳች ደስ የሚል ስሜት ይሰማኛል፡፡ ከወር በፊት ነው ከሲኤምሲ ወደ መገናኛ ስመጣ ሾፌርና ወያላው ያወራሉ፡፡ የወሬያቸው ጭብጥ ደግሞ ምሳ የትና ምን እንደሚበሉ ነው፡፡ ወያላው፣ ‹‹እዚያ ምግብ ቤት እንሂድ ከምትለኝ ፆሜን ብውል ይሻለኛል…›› ሲል፣ ‹‹እኔ ደግሞ አንተ የምታደንቀው ቤት ከምሄድ በእግሬ ወክ እያደረግኩ አስፋልት ለብለብ ብበላ ይሻለኛል…›› ብሎ ይመልስለታል፡፡ እንዲህ እየተባባሉ መገናኛ ስንቃረብ የምሳው መብያ ቦታ መወሰን ስላለበት ሾፌሩ፣ ‹‹አሁን ማማረጡን ለጊዜው እንተውና የት እንሂድ ወስን…›› ብሎ ለወያላው ውሳኔውን ሲተውለት፣ ‹‹አንተም እንዳትከፋ እኔም እንዳይደብረኝ ቦጌ ቤት እንብላ…›› ከማለቱ ሾፌሩ ሳቅ እያለ፣ ‹‹እባክህ ነቅቼብሃለሁ የዚያች ልጅ ፍቅር ገብቶልህ ነው ዙሪያውን ስትዞር የነበረው… በቃ ይመችህ…›› ሲለው ሁላችንም ተሳፋሪዎች ማለት ይቻላል በሳቅ አጀብናቸው፡፡ በወንድማማችነት መንፈስ ላደረጉት አዝናኝ ቆይታ ሁለቱንም ይመቻቸው፡፡
በቀደም ደግሞ የተሳፈርንባት ታክሲ አዲስ ናት፣ በዚያ ላይ በማስታወቂያዎች ደምቃለች፡፡ ከአሮጌ ዕቃዎች እስከ ኮምፒውተር የምንፈልጋቸውን ነገሮች የሚጠቁሙ ማስታወቂያዎች ዙሪያዋን ከበዋታል፡፡ ሃይማኖታዊና ዓለማዊ ጥቅሶችም በየፈርጃቸው ተሰድረዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ፣ የኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም፣ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ የአፄ ምኒልክ፣ የኔልሰን ማንዴላና የባራክ ኦባማ ፎቶግራፎች ተገጥግጠውባታል፡፡ የታክሲዋ ሾፌር ፀጉሩ የተቆጣጠረ ቀላ ያለ ለግላጋ ወጣት ነው፡፡ በእንክብካቤ የተያዙት ታክሲዋና ሾፌሯ ብቻ ሳይሆኑ ወያላውም ጭምር ነው፡፡ ፅድት ያለና የዘናነጠ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ታክሲዋን በፈረቃ እየተቀያየሩ ሳይሾፍሯት አይቀርም፣ ሲነጋገሩም በጣም ተከባብረው ነው፡፡
ከሜክሲኮ ቦሌ የምትሠራው ታክሲ መቀመጫዋ ይደላል፡፡ ውስጧም ፀዳ ያለና ዘና በሚያደርጉ ለስላሳ ሙዚቃዎቿ ተሳፋሪዎቿን ታዝናናለች፡፡ ጉዞ ተጀምሯል፡፡ አሪፉ ወያላ ሒሳብ መቀበል እንደ ጀመረ አንዲት ኮረዳ ሳቋን ለቀቀችው፡፡ ከዚያ ዝግ ተደርጎ ከተለቀቀው ለስላሳ ሙዚቃ ውጪ ፀጥታ በሠፈነበት ሁኔታ ውስጥ የእዚህች ቆንጂዬ ልጅ ሳቅ ምን ይሉታል? አልኩኝ ለራሴ፡፡ ወያላው ፈገግ እያለ፣ ‹‹በሰላም ነው? ምን ገጠመሽ?›› አላት፡፡ በዓይኑም ጠቀስ አደረጋት፡፡ በሾፌሩ ትይዩ ባለው ጥቅስ ላይ እንዳፈጠጠች፣ ‹‹ያንን ጥቅስ አላነበብከውም?›› አለችው፡፡ ሁላችንም ወደ ሾፌሩ አቅጣጫ አንጋጠጥን፡፡ ‹‹በርትተህ ከተማርክ የአለቆችህን ቁጥር ትቀንሳለህ›› ይላል የዚያ የጉደኛ የታክሲ ጥቅሶች ጸሐፊ ጥቅስ፡፡
ሁላችንም ማለት ይቻላል በሳቅ ሆነን ተያየን፡፡ አንዲት በመካከለኛ ዕድሜ ያሉ ወይዘሮ፣ ‹‹እጅግ በጣም የሚደንቅ ጸሐፊ ነው፡፡ ካሁን ቀደም ‹መብታችሁ ትዝ የሚላችሁ ታክሲ ውስጥ ነው? መጨቃጨቅ ከአሸባሪነት አይተናነስም› አሁን ደግሞ ይኼንን በመጻፉ አደንቀዋለሁ…›› አሉ፡፡ ወይዘሮዋ ወቅታዊ ጉዳዮችን እየተከተለ የሚያስተላልፋቸው መልዕክቶች የባለ ጥቅሱን የግንዛቤ ምጥቀት የሚያሳይ ነው ሲሉ አከሉበት፡፡ እንዲህ ዓይነት በሳል አስተያየት የሚሰጡ እንስቶችን ሳይ እጅግ በጣም ደስ ስለሚለኝ እኔም ለእሳቸው አድናቆቴን ገለጽኩላቸው፡፡ ‹‹እንደ እርስዎ ዓይነት አርቆ ተመልካች ባይኖር ኖሮ የሰው ልፋት ሁሉ ገደል ይገባ ነበር፡፡ እርስዎ ለእንዲህ ዓይነቱ የፈጠራ ችሎታ ትኩረት ሰጥተው በአደባባይ የተሰማዎትን መናገር በመቻልዎ ሊመሠገኑ ይገባል…›› በማለት አወደስኳቸው፡፡ እሳቸው የእኔን ምሥጋና ተቀብለው ፍላሚንጎ ወረዱ፡፡
ያቺ የመወያያ አጀንዳችንን የቆሰቆሰችው ልጅ ወያላውን በፍቅር እያየችው ጎሸም አደረገችው፡፡ እየሳቀ እያያት፣ ‹‹ምነው እቱ?›› አላት፡፡ ‹‹ሰዎች እንዲህ ሲመሠጋገኑ ደስ አይልም?›› ስትለው እሱም የዋዛ አልነበረምና፣ ‹‹እኔም አንቺን በጣም ነው ያደነቅኩሽ፣ ስሜትሽን ሳትቆጣጠሪ በመሳቅሽ የመወያያ ርዕስ ከፈትሽልን፣ አድናቂዎችሽ ነን…›› አላት፡፡ ልጅቷ በወያላው ምሥጋና ፍንድቅድቅ ብላለች፡፡ አጠገቤ ያለው ሰውዬ ግን ልጅቷን ደስ በማይል ስሜት ይመለከታታል፡፡ የእኔ እሱን አትኩሮ ማየት የገባው ሰውዬ፣ ‹‹ይህች ልጅ ሞልቀቅ ያለች አትመስልም?›› አለኝ፡፡ በጣም ገርሞኝ፣ ‹‹መብቷ መሰለኝ…›› አልኩት፡፡ ‹‹መብቷ ሊሆን ይችላል፣ ሴት ልጅ እንዲህ ስትሆን ማየት ያስጠላል…›› ሲለኝ ደብሮኝ ዘጋሁት፡፡ እንዲህ ዓይነቶቹ ናቸው እኮ በየቦታው የሰውን ልጅ መብት እየደፈጠጡ አገሪቱን የሚያምሱ፡፡
ወያላውና ልጅቷ በመግባባት ጨዋታቸውን ቀጠሉ፡፡ ሹፌሩ አልፎ አልፎ ሳቅ እያለ ያያቸዋል፡፡ ኦሎምፒያ መብራቱን አልፈን የጎደለ ወንበር ሞልተው ጉዞ ወደ ቦሌ ቀጠለ፡፡ የአዳዲስ ገቢዎችን ሒሳብ ከተቀበለ በኋላ ልጅቷና ወያላው እንደገና ወሬያቸውን ጀመሩ፡፡ ወዲያው፣ ‹‹ፈተና ስለደረሰ የጥናት ፕሮግራም ይውጣና እንዘጋጅ እንጂ?›› አለች ልጅቷ፡፡ ሾፌሩ ፕሮግራም መውጣቱን ነግሯት ማታ የተዘጋጀውን ፕሮግራም እንደሚወያዩበት ሲነግራት ተሳፋሪዎች ጆሮዎቻችን ቀጥ አለ፡፡ ልጅት ወሎ ሠፈር ወርዳ ተሰናብታቸው ሄደች፡፡ ወያላውና ሾፌሩ በኋላ የጥናት ፕሮግራሙን ፎቶ ኮፒ አስደርገው ለጓደኞቻቸው ይዘው እንደሚሄዱ ተነጋግረው ተስማሙ፡፡ ወያላውን ጠጋ ብዬ ‹‹ትማራላችሁ እንዴ?›› አልኩት፡፡ ‹‹ወንድማማቾች ነን፣ አባትና እናታችን በሞት ተለይተውናል፡፡ ታናናሾቻችንን እያሳደግን እኛ ደግሞ ማታ ዩኒቨርሲቲ እንማራለን፤›› ሲለኝ፣ ‹‹እግዚአብሔር ያሰባችሁትን ይሙላላችሁ…›› ብያቸው ወረድኩ፡፡
ወጣቶች እንዲህ ለራሳቸው ሥራ ፈጥረው በዚህ ላይ ሲማሩ ደስ ይላል፡፡
ምንጭ ማህበራዊ ድህረ ገጽ
ከዋናው ጽሑፍ ላይ መዝናኛው ክፍል ብቻ ተቆርጦ የቀረበ
ከክብና ከአጽም ጋር የመቆዘም ጣጣ (ገብረክርስቶስ ገጣሚውና ሰዓሊው)
ለእኔ ኢትዮጵያዊ እንደ ኢትዮጵያዊ ነው መኖር የሚችለው፡፡ ቀላል ምሳሌ ልስጥህ… ብሔራዊ ባንክን ሲሰራ አርክቴክቱ ከመስራቱ በፊት በየክፍለ ሀገሩ እየተዘዋወረ አጥንቶ ነበረ፡፡ ከዚያ ውስጥ የተረዳው ነገር ቢኖር ክብ ሰርተን የምንኖር ህዝቦች መሆናችንን ነው፡፡ ክብ ሰርተን እሳት እንሞቃለን፡፡ ክብ እንጀራ እንበላለን፡፡ ክብ ምጣድ አለን፡፡ ክብ ምድጃ አለን፡፡ አምባሻችን ክብ ነው፡፡--"
ምንጭ ማህበራዊ ድህረ ገጽ
ከዋናው ጽሑፍ ላይ ተቆርጦ የቀረበ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ለአስተያዬትዎ ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ
👎👎👎👎👎👎👎👎👎👎👎👎
@Fogremover
ለ'ፍቅር ቢዘመር ስለ'ፍቅር ቢቀኝ
ድርቡሽ አንጀት ራርቶ ምንም ልብ ቢመታ፣
እናትን ሲፈጥር፤
ሀያል ነው እግዚአብሔር ኤልሻዳይ ነው ጌታ።
እናም...!
በሰዉ ልክ ቁመና፤
የመዉደድ መስፈርቱ በግብር ቢለካ፣
እናትነት ማለት
'የፍቅር ማብቂያ ጥግ' ሰው የመሆን ዲካ።
እናት.....እናቴ.....እናትነት
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ገጣሚ ልዑልሰገድ መላክ
ማስመሰል! ማስመሰል! ማስመሰል! እናላችሁ...አለ አይደል...ፎርጅድ ሰው መኖሩን እስካሁን ‘በማስረጃና በመረጃ’ እንደሚባለው አይነት በማሳያነት የምናቀርበው ባይኖረንም፣ ፎርጅድ ባህሪ ግን መኖር ብቻ ሳይሆን የዘመናችን ዋናው መለያ ሆኗል፡፡-"
አላጋጠማችሁም???????? እኔ ግን ብዙ ሰው ነው ያጋጠመኝ።
መልካም ቀን ፊደል አስር ነኝ
ወዳጄ 'ትናንትናን ያለፍነው እኮ ተጎራርሰን እንጂ ተገፋፍተን አይደለም'
አይደለም እንዴ
ፍራሽ አዳሽ ወይም ተስፋሁን ከበደ ይህንን ተውኔት መድረክ ላይ ሲያቀርብ እያለቀሰ ነበር
ሕይወትን ደስ ባለህ ጊዜ እና በፀደይ ወራት ብቻ አትተርጉማት ወዳጄ !!!!!!!
ደህና ዋሉ!!!
ፊደል አስር ነኝ
ቁጭ ብየ ስለ እናንተ እያሰብኩ
ለውሏችሁ ደግሞ ይህችን አልኩኝ ምርጥ ጽሑፍ ነች አንብቡልኝ እስኪ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
አሁን የት ይገኛል ቢፈልጉ ዞሮ
መስማት ከማይፈልግ የባሰ ደንቆሮ”
- ከበደ ሚካኤል
ስራዬ ብሎ የማዳመጥን አጀንዳ ማድመጥ ብልህነት ነው። የማዳመጥ፤ ክህሎት ቀዳሚ ጥበብ ነው። ተናጋሪነት ህፀፅ አያጣውም። ማዳመጥ ግን ምሉዕ በኩላሄ ነው። ወደ መመራመር ካልመራ መላ የለውም” እንዳሉት ነው፤ አለቃ ስርግው፡፡ ማየት የተሳነው መሆን ተፈጥሯዊ ነው። መስማት የተሳነው መሆንም ተፈጥሯዊ ነው። ማሽተት የተሳነው መሆንም አካላዊ ክስተት ነው። ማሰብ የተሳነው መሆን ግን ክፉ መርገምት ነው። መላም መድሃኒትም የለውም። ምናልባትም ዘመናችን እንደ ፈጠራቸው ፈውስ አልባ በሽታዎች ተርታ የሚቆጠር ነው። ከሀሳብ ማጣት የከፋ መርገም የለም። ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን እንዳለው፤ “ከመርገምት ሁሉ የከፋ መርገምት ቋንቋ ለቋንቋ መጠፋፋት” ይለናል። ሀሳብ ለሃሳብ አንጠፋፋ፣ ልብ ለልብ አንራራቅ፣ መንፈስ ለመንፈስ እንተቃቀፍ፣ ልዩነታችንን አውቀን ነቅተን Vive La Diference (ልዩነት ለዘለዓለም ይኑር!) እንባባል። ወደን እንማማር፣ አውቀን እንዋደድ፣ የማንንም ጣልቃ ገብነት አንፍቀድ፣ ኢትዮጵያዊነትን ማንም አልሰጠንም፤ እኛው እራሳችን እንጂ! ዛሬም ከሮበርት ብራውን ጋር በገ/ክርስቶስ ትርጓሜ “ከውጪ ያለውን ሄዶ ከመፈለግ ከውስጥ የበራውን እንዲወጣ ማድረግ”
ካነበብኳቸው ላይ የወሰድኩት ነው !!!
ፊደል አስር ነኝ ቁርስ እንዲሰራልኝ አዝዤ እየጠበኩ😂😂😂😂❤️❤️❤️❤️❤️