fkeradis | Unsorted

Telegram-канал fkeradis - 😍ፍቅር አዲስ💖

1151

WELLCOME.TO. @fkeradis አላማችን እናንተን ፈታ እያረግን ቁም ነገር ማስጭበጥ ነዉ። አልቃሻን ማሳቅ ለኛ በጣም ቀላል ነዉ!! #የተለያዩ ቀልዶች #አስቂኝ ፎቶዎችን #የፍቅር ታሪኮች #ገራሚ እና አስደናቂ እዉነታዎች $.ሰለቸኝ ደገመኝ በማለይዉ እዬብ አማካኝነት ይቀርባሉ። le fkr mekri for any 👇conment 📩 @eyobreta 📩

Subscribe to a channel

😍ፍቅር አዲስ💖

[Forwarded from 💕 ፍቅሬን በ ግጥም 🌷✏️ (🌻 መልካም አዲስ አመት ይሁንልን 🌻)]
~~~~~~ መልካምነት ~~~

🙏 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ 🙏

➲ ‹‹አመድ አፋሽ ሆንኩኝ›› ➲

አንድ ሰው በበረሃ እየተጓዘ እያለ የያዘው ውሃ አልቆበት በውሃ ጥም ይያዛል፡፡ ቀስ በቀስ ውሃ ጥሙ ሰውዬውን እያደከመው ይመጣል በስተመጨረሻ ከአንድ የውሃ ጉርጓድ ጋር ይደርሳል ጉርጓዱ በጣም ጥልቅ ነበረ፤ ውሃ ይኑረው አይኑረው አይታይም፡፡ ከዚያም ከጉርጓዱ ጎን አንድ አሮጌ የውሃ መሳቢያ ሞተር አለ ሞተሩ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ ሰፍሯል፡፡

‹‹ይህ የውሃ መሳቢያ ሞተር የሚሰራው በውሃ ነው›› ይላል፡፡ ከሞተሩ ጎን አንድ ጆግ ሙሉ ውሃ ተቀምጧል ጆጉ ላይ እንዲሁ አንድ ፅሁፍ ሰፍሯል ‹‹ወዳጄ ሆይ ይህንን ጆግ ውሃ ሞተሩ ውስጥ ጨምረው ሞተሩ ብዙ ውሃ ያወጣልሃል፤ ታዲያ አደራ አንተም እንዳንተ ላለ ሌላ መንገደኛ ይጠቅማልና ውሃው ከጉርጓዱ ሲወጣልህ ጆጉን ሞልተህ ማስቀመጥን አትርሳ›› ይላል፡፡

በጆግ ያለውን ውሃ ሞተሩ ውስጥ ይጨምረው ወይስ ይጠጣው? እዚ ጋር ሰውዬው በሁለት ሃሳብ ተወጠረ ‹‹አንደኛ ይህ ሞተር አርጅቷል ጨምሬው ባይሰራ ይህንንም ውሃ አጣሁ ማለት ነው ሞትኩ ማለት ነው ስለዚህ ልጠጣውና ህይወቴን ላድን፤ ደሞ ማሳሰቢያውስ ውሃው ያለሞተር አይሰራም እንደኔ ውሃ የተጠማ ሰው ቢመጣ ይህንን ማንቀሳቀሻ ከጠጣሁት ይሞታሉ›› ብሎ ለራሱም ለሌሎቹም አሰበና በሃሳብ ተወጠረ።

በስተመጨረሻ በብዙ ጭንቀት ተወጥሮ ትልቅ ውሳኔ ወሰነ እንዲህ አለ ‹‹ውሃውን ወደሞተሩ ብጨምረው ይሻላል ከሰራ ጥሩ ካልሰራ ግን እሞታለሁ እንጂ በፍፁም ይህንን ጆግ ውሃ ጠጥቼ ሄጄ ዛላለሜን ስለዚህ ጉርጓድና ይህንን ውሃ አተው ስለሚሞቱ ሰዎች እያብኩ መኖር አልፈልግም›› አለ፡፡ ከዚያም የጆጉን ውሃ ወደ አሮጌው ውስጥ ጨመረውና የሞተሩን ማስነሻ ተጫነው፡፡ ሞተሩም ድምፅ እያሰማ ውሃ የማውጣት ስራውን ጀመረ፡፡ ሰውዬው ተደነቀ የሚፈልገውን ያህል ጠጣ አካባቢው በሙሉ በውሃ እራሰ ከጠበቀው በላይ አካባቢው ሁሉ ውሃ በውሃ ሆነ ከዚያም በተባለው መሰረት እሱም ጆጉን በውሃ ከሞላው ቦሃላ ጆጉ ላይ ፅሁፍ ጨመረበት ‹‹እመኑኝ በትክክል ይሰራል›› አለ፡፡

እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው ለራስ ማሰብ በህይወት መኖር ነው ለሌላው ማሰብ ግን ሰው መሆን ነው፡፡ ያለህን በሙሉ ሳትሰስት ከሰጠህ በእጥፍ ድርቡ ፈጣሪ ይሰጥሃል፡፡ ሰውዬው ጆግ ውሃ ሰቶ አካባቢን የሚያርስ ውሃ እንደተቸረው አንተም የምትሰጣት ጠብታ ከልብህ ከሆነ በእጥፉ ይሰጥሃል፡፡ በምትሰፍረው መስፈሪያ ይሰፈርልሃል በሰጠኸው ልክ ይሰጥሃል ስለዚህ ‹‹አመድ አፋሽ ሆንኩ›› ከማለትህ በፊት አመድ ሰተህ ከሆነስ፡፡ መስጠትን ብቻ ሳይሆን አሰጣጥህ ወሳኝነት አለው፡፡ አንዳንዴ ከመንጠቅ የማይተናነስ መስጠትም አለ፡፡

✍️ያለንን ሁሉ ያለስስት የምንሰጥበት መልካም ምሽት ይሁንልን!!!


ሼር በማድረግ ለሌሎች አድርሱ 🙏

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

ለጊዜው ቢመስልም፤
ለኔ የተለኮሰች እሳት ላንቺ አትመለስም፡፡
--------------------------------------
በአንድ ገበሬ ቤት የምትኖር አንዲት አይጥ ነበረች። ታዲያ ከለታት አንድ ቀን ይቺው አይጥ
ገበሬው እና ባለቤቱ እቃ ሸምተው ወደ ቤታቸው ሲገቡ ትመለከትና ለእኔ የሚሆን ምን
ገዝተው ይሆን? ብላ በቀዳዳ አጮልቃ ስታይ ፍፁም ያልጠበቀችው ነገር፡፡ የተገዛው
የሚበላ ነገር ሳይሆን የአይጥ ወጥመድ ሆኖ እርፍ! ያዝ እንግዲህ!!
እሜቴ አይጥ በድንጋጤ ውስጥ ሆና ከጉድጓዷ ወጥታ እየሮጠች በግቢው ውስጥ ወዳሉት
የቤት እንስሳት ሄደች፡፡ መጀመሪያ ያገኘችው ዶሮን ነበር፤ ጫር ጫር እያደረገች
ጥራጥሬዋን ትለቅማለች፡፡
“ማነሽ አንቺ ዶሮ፣ ኧረ ጉድ አልሰማሽ! ቤት ውስጥ ወጥመድ ተገዝቷል!!” አለቻት እሜቴ
አይጥ ካሁን ካሁን ዶሮዋ ደንግጣ “እስኪ ሙች በይኝ! እውነትሽን ነው?”እስክትላት
እየጠበቀች፡፡
ዶሮዋ እቴ እንኳን ልትደነግጥ ጭራሽ እየተቆናጠረች “እና ምን ይጠበስ! አንቺ ተጨነቂበት
እንጂ እኔን ምን ያሳስበኛል!?” አለቻት፡፡
አይጧ እየተበሳጨች ስትሮጥ ወደ በግ ሄደችና “ስማኝማ አቶ በግ፣ ቤት ውስጥ የአይጥ
ወጥመድ ተገዝቷል፤ እባክህ አንድ ነገር እናድርግ!!” ስትል በተማፅኖ ጠየቀችው፡፡ አቶ በግ
ካቀረቀረበት ሳር ላይ ቀና ሳይል “በጣም ያሳዝናል! ግን ልረዳሽ አልችልም፤ ራስሽ
ተወጪው” አላት፡፡
አሁንም አይጥ ቁና ቁና እየተነፈሰች፣ ወደ በሬ ዘንድ ሄደችና ቤት ውስጥ ስለተገዛው
ወጥመድ ነገረችው፡፡ በሬውም ምንም ሳይመስለው “እንዴው ምን ይሻልሻል? ባይሆን
በግና ዶሮ ይርዱሽና አንድ ነገር አድርጊ፤ እኔን እንኳን ተይኝ፡፡” አላት፡፡
አይጧ ሚጢጢ አናቷ በብስጭት እየዞረባት “ኧረ ተው አንድ ነገር ብናደርግ ይሻላል…
ለጊዜው ቢመስላችሁም ችግሩ የጋራችን ነው!!” ስትል ተማጸነች፡፡
ሁሉም ተያይተው ተሳሳቁ፡፡ “ቀልደኛ ነሽ!” እየተባባሉ፡፡ “አይታያችሁም አንድ የአይጥ
ወጥመድ የጋራ ችግራችን ሲሆን?” እያሉ፡፡
አይጥም ተስፋ ቆርጣ ሄደች ወደ ጉድጓዷ፡፡ የዚያን እለት ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ በአይኗ
ሳይዞር አደረች፡፡
ማታ ወጥመዱ ተጠምዶ እያለ ቀጭ የሚል ድምፅ ሲሰማ የገበሬው ሚስት ተስፈንጥራ
ተነሳች. . . ወጥመዱ የያዛትን አይጥ ለማየት፡፡ ጭለማ ስለነበረ በዳበሳ ወደ ወጥመዱ ሄዳ
ወጥመዱን ስትነካው በአይጥ ፋንታ የተያዘው መርዘኛ እባብ ኖሮ ነደፋት፡፡ በነጋታው
የገበሬው ሚስት ከሀኪም ቤት ስትመለስ ራስ ምታት እንዳያስቸግራት ተብሎ ዶሮዋ
ታረደችና ሾርባ ተዘጋጀላት፡፡ የገበሬው ሚስት ህመሙ እየጠናባት ሲሄድ በቶሎ
እንድታገግም ተብሎ በግ ታረደላት፡፡ ሆኖም ግን ሴትዮዋ ማገገሟ ቀርቶ ሞተች፡፡ ይህንን
ተከትሎ ዘመድ አዝማድ ለለቅሶ ሲመጣ ለተስካር በሚል በሬውም ታረደ፡፡
እሜቴ አይጥም ቁጭ ብላ እያለቀሰች ሦስቱም ሲታረዱ አየች።
አንዳንዴ ችግር ሲመጣ ለጊዜው አንድ ሰውን ብቻ የሚጎዳ ይመስላል፡፡ ያኔ ሁሉም
አያገባኝም ይላል፡፡ ቆይቶ ግን ይጎዳል የተባለው በህይወት እያለ ያላገጡ ሰዎችን ማዕበሉ
ጠራርጎ ሲወስዳቸው ለመታዘብ ይበቃል፡፡ የተለኮሰ እሳት ባለበት ቦታ ይቀር ይመስል
እጃቸውን አጣጥፈው የሚጠብቁትን አመድ አድርጓቸው ይሄዳል፡

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

‹‹አመድ አፋሽ ሆንኩኝ››


አንድ ሰው በበረሃ እየተጓዘ እያለ የያዘው ውሃ አልቆበት በውሃ ጥም ይያዛል፡፡ ቀስ በቀስ ውሃ ጥሙ ሰውዬውን እያደከመው ይመጣል በስተመጨረሻ ከአንድ የውሃ ጉርጓድ ጋር ይደርሳል ጉርጓዱ በጣም ጥልቅ ነበረ፤ ውሃ ይኑረው አይኑረው አይታይም፡፡ ከዚያም ከጉርጓዱ ጎን አንድ አሮጌ የውሃ መሳቢያ ሞተር አለ ሞተሩ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ ሰፍሯል፡፡

‹‹ይህ የውሃ መሳቢያ ሞተር የሚሰራው በውሃ ነው›› ይላል፡፡ ከሞተሩ ጎን አንድ ጆግ ሙሉ ውሃ ተቀምጧል ጆጉ ላይ እንዲሁ አንድ ፅሁፍ ሰፍሯል ‹‹ወዳጄ ሆይ ይህንን ጆግ ውሃ ሞተሩ ውስጥ ጨምረው ሞተሩ ብዙ ውሃ ያወጣልሃል፤ ታዲያ አደራ አንተም እንዳንተ ላለ ሌላ መንገደኛ ይጠቅማልና ውሃው ከጉርጓዱ ሲወጣልህ ጆጉን ሞልተህ ማስቀመጥን አትርሳ›› ይላል፡፡

በጆግ ያለውን ውሃ ሞተሩ ውስጥ ይጨምረው ወይስ ይጠጣው? እዚ ጋር ሰውዬው በሁለት ሃሳብ ተወጠረ ‹‹አንደኛ ይህ ሞተር አርጅቷል ጨምሬው ባይሰራ ይህንንም ውሃ አጣሁ ማለት ነው ሞትኩ ማለት ነው ስለዚህ ልጠጣውና ህይወቴን ላድን፤ ደሞ ማሳሰቢያውስ ውሃው ያለሞተር አይሰራም እንደኔ ውሃ የተጠማ ሰው ቢመጣ ይህንን ማንቀሳቀሻ ከጠጣሁት ይሞታሉ›› ብሎ ለራሱም ለሌሎቹም አሰበና በሃሳብ ተወጠረ።

በስተመጨረሻ በብዙ ጭንቀት ተወጥሮ ትልቅ ውሳኔ ወሰነ እንዲህ አለ ‹‹ውሃውን ወደሞተሩ ብጨምረው ይሻላል ከሰራ ጥሩ ካልሰራ ግን እሞታለሁ እንጂ በፍፁም ይህንን ጆግ ውሃ ጠጥቼ ሄጄ ዛላለሜን ስለዚህ ጉርጓድና ይህንን ውሃ አተው ስለሚሞቱ ሰዎች እያብኩ መኖር አልፈልግም›› አለ፡፡ ከዚያም የጆጉን ውሃ ወደ አሮጌው ውስጥ ጨመረውና የሞተሩን ማስነሻ ተጫነው፡፡ ሞተሩም ድምፅ እያሰማ ውሃ የማውጣት ስራውን ጀመረ፡፡ ሰውዬው ተደነቀ የሚፈልገውን ያህል ጠጣ አካባቢው በሙሉ በውሃ እራሰ ከጠበቀው በላይ አካባቢው ሁሉ ውሃ በውሃ ሆነ ከዚያም በተባለው መሰረት እሱም ጆጉን በውሃ ከሞላው ቦሃላ ጆጉ ላይ ፅሁፍ ጨመረበት ‹‹እመኑኝ በትክክል ይሰራል›› አለ፡፡

እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው ለራስ ማሰብ በህይወት መኖር ነው ለሌላው ማሰብ ግን ሰው መሆን ነው፡፡ ያለህን በሙሉ ሳትሰስት ከሰጠህ በእጥፍ ድርቡ ፈጣሪ ይሰጥሃል፡፡ ሰውዬው ጆግ ውሃ ሰቶ አካባቢን የሚያርስ ውሃ እንደተቸረው አንተም የምትሰጣት ጠብታ ከልብህ ከሆነ በእጥፉ ይሰጥሃል፡፡ በምትሰፍረው መስፈሪያ ይሰፈርልሃል በሰጠኸው ልክ ይሰጥሃል ስለዚህ ‹‹አመድ አፋሽ ሆንኩ›› ከማለትህ በፊት አመድ ሰተህ ከሆነስ፡፡ መስጠትን ብቻ ሳይሆን አሰጣጥህ ወሳኝነት አለው፡፡ አንዳንዴ ከመንጠቅ የማይተናነስ መስጠትም አለ፡፡

✍️ያለንን ሁሉ ያለስስት የምንሰጥበት መልካም ቀን ይሁንልን!!!

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

♥️♡+:。.。 ... አሳዛኝ ታሪክ . 。.。:+♡♥️


🙏🏾ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏🏾

ድፍን ኬንያውያንን በእንባ ያራጨው ምስኪን ጎዳና ተዳዳሪ የፈፀመው ድንቅ
ተግባር፡፡

እንዲህ ሆነላችሁ ኬንያዊው ከታች በፎቶ የምታዩት ጆን የተሰኘው ህፃን የጎዳና
ተዳዳሪ የእለት ጉርሱን ለምኖ በረንዳ የሚያድር ምስኪን ህፃን ነው። ታዲያ
ጆን እንደለመደው ትራፊክ መብራት ላይ መኪኖች ሲቆሙ በመስኮት ሄዶ
መለመኑን ተያያዘው። ከበርካታ መኪኖች ገንዘብ ተቀብሎ ወደ አንዱ መኪና
በመስኮት እጁን ይዘረጋል። እጁን ሲዘረጋ የመኪናው መስኮት ሲከፈት #ግላዲ_ካማዳ ከተባለች ሴት ጋር ፊት ለፊት ይተያያል፡፡

ግላዲ ካማዳ ያረገችውን የኦክስጅን መተንፈሻ ምንድነው ብሎ
ይጠይቃታል። እሷም በሰው ሰራሽ መተንፈሻ ኦክስጅን የምትተነፍስ፤ አይኗም በቅጡ የማያይ፤ በእግሯ መንቀሳቀስ የማትችል፤ በየእለቱ ጤና ፍለጋ ሆስፒታል የምትንከራተት፤ መታከሚያ ገንዘብ ያጣች፤ 7 ዓመት ሙሉ በዚህ በሽታ የምትሰቃይ ምስኪን ሴት መሆኗን ትነግረዋለች፡፡

ይህንን ያየው የጎዳናው ህፃን ጆን እንባውን መቆጣጠር አቅቶት ለልመና
የዘረጋውን እጁን ሰብስቦ የለመናትን ጥቂት ገንዘብ ታከሚበት ብሎ
ይሰጣታል፡፡ እንባውና ሁኔታው የገረማቸው መንገደኞችም በሁኔታው
ተደንቀው የልጁን የሃዘን ገፅታ እንዲህ በምስል አስቀሩት፡፡

ታዲያ ይህንን ምስል በፌስ ቡክ ይለቁታል፤ ድፍን ኬንያ ይህንን ምስል ተቀባበለው። ሁሉም የልጁ ሃዘን አሳዘነው፤ ኢሄ ልጅ ምንም ሳይኖረው የዳቦ መግዣውን ከሰጠ እኛስ ብለው ለህክምና የተጠየቀችውን 4 ሚሊዮን
ሽልንግ እንዲሞላ ያቅማቸውን አደረጉላት፡፡

ዛሬ ግላዲ በዚህ በጎዳና ህፃኑ ጆን ተግባር ለህክምና የሚሆናት ገንዘብ
በህዝብ መዋጮ ተሟልቶ ወደ ህንድ ተጉዛ ታክማ ኦክስጅኗን ጥላ ዛሬ
በነፃነት ትተነፍሳለች፤ ትንቀሳቀሳለች፡፡

እንግዲህ አንዲህ ነው ለመስጠት የግድ ሃብታም መሆን አይጠበቅብህም፡፡ ደግሞ ማንም ሰው ልስጥ ካለ የሚሰጠው አያጣም፡፡


አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ 🙏

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

━━━━━✦ አስተማሪ ታሪክ ✦━━━━━


💡 እማትጨርሱት ከሆነ አትጀምሩት 👍


አንድ ኩራተኛ የሆነ ሰው ጥሩ ልብስ ለብሶ በኩራት ታጅቦ እራሱን እየቆለለ፤ በአንድ ገበያ ይዘዋወር ነበር። ታድያ ፈሳሽ ጁስ የምትሸጥ ሴትዬ በአጠገቡ ስታልፍ ይመለከታል። ጠራትና

"ምንድነው የምትሸጭው አላት?"

እሷም: "ፈሳሽ ጁስ ነው ጌታዬ" አለችው

እሱም፡ አሳይኝ

በእንስራ የያዘችውን ፈሳሽ ከጀርባዋ ላይ ለማውረድ ስትሞክር ድንገት የሰውየው ልብስ ላይ ይህ ፈሳሽ ይደፋበታል። ሰውየው ከባድን ቁጣ ተቆጣ። እንዲህም አላት

"የዚህን ልብስ ዋጋ እስከምትከፍይኝ ከዚህ ቦታ የትም አልሄድም" ሲል ዛተ። ሴትየዋም እያለሳለሰች ትለማመጠው ጀመር።

"እባክህ ተወኝ ጌታዬ ምክንያቱም እኔ ምስኪን ነኝ" አለችው። ሰውየውም

" እስክትከፍይኝ የትም አልሄድም" አላት። እሷም ዋጋውን

"ስንት ነው?" ስትል ጠየቀችው። እሱም

"1000ብር" ሲል መለሰላት። እሷም...

"እኔ እኮ ደሃ ሴት ነኝ ከየት አመጣለሁ" አለችው። እሱም..

"ምን አገባኝ" በማለት ፍፁም ጭካኔውን አበረታባት። እያስፈራራትና እየዛጠባት ሳለ፤ አንድ ወጣት በመንገድ ሲያልፍ ይመለከትና

"ምን ሆነሽ ነው?" ሲል ጠየቃት። እሷም የተከሰተውን በደንብ አስረዳችው። ወጣቱም እንዲህ አለ...

"ብሩን እኔ ሰጥሃለው" ብሎ አንድ ሺህ ብር በማውጣት ለሰውየው ከፈለው። ኩራተኛው ሰውየም ብሩን ቆጥሮ ተረክቦ ሊጓዝ ሲል፤ ወጣቱ ልጅ...

"ተረጋጋ እንጂ ወደየት ነው!?" አለው። ሰውየውም..

"ምን ፈለግክ!?" አለው። ወጣቱም...

"የልብስህን ዋጋ ወስደሃል አይደል!!" አለው። ሰውየውም..

"በሚገባ እንጂ!!" አለ። ወጣቱም...

"ታድያ ልብሱ የታለ?" ሲል ጠየቀው። ሰውየም

"ለምን!?" አለው። ወጣቱም...

"የልብስህን ዋጋ ሰጥተንሃል፤ ስለዚህ ልብሱን ስጠን አለው። ሰውዬውም..

"ራቁቴን ልሄድ ነው!?" አለው። ወጣቱም...

"አይመለከትኝም! ምን አገባኝ!!" አለው። ሰውዬውም..

"ልብሱን ካልሰጠውህስ?" ሲለው ወጣቱ..

"ገንዘብ ትከፍለናለህ አለው" ሰውዬውም

"አንድ ሺ ብሩን ነው አለ?" ወጣቱም...

"አይይ አይደለም። እኛ የምንልህን ነው" ሲል መለሰለት። ኩራተኛውም ሰው እንዲህ አለ...

"እንዴ የከፈልከኝ እኮ አንድ ሺ ነው" ወጣቱም..

"ስለከፈልኩት አያገባኝም አለው" ሰውዬውም...

"ስንት ነው ምትፈልገው?" አለው። ወጣቱም...

"ሁለት ሺህ ብር" አለው። ሰውዬውም...

"ይህ ብዙ ነው!!" ሲል ተናገረ። ወጣቱም...

"እንግዲህ ልብሱን ስጠና!!" አለው። ሰውዬውም...

"ልታዋርደኝ ፈልገህ ነው ራቁቴን" አለው። ወጣቱም....

"ሴትየዋን ልታዋርድ እንደፈለግከው አዎ!!" አለው። ሰውየውም ..

"ይህ በደል ነው!!" አለ። ወጣቱም....

"እንዴ አሁን ስለ በደል ታወራለህ!! ድንቅ ነህ" አለው። ሰውየውም በማፈር የተባለውን ብር ለወጣቱ ከፈለው።

ወጣቱም ይህ ሁለት ሺህ ብር ለምስኪኗ ሴት ስጦታ መሆኑን አውጆ በደስታ ሸኛት።

የእለቱ መልዕክት ከታሪኩ....

ክርክሮችን ለመፍታት #ጥበብ ሁነኛ መፍትሄ ናት!! ህይወትም ኩራትና እኔ የበላይ ነኝ የምንልባት የፋከራ መድረክ አይደለችም።


━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━
➲ ••●◉Join us share◉●••

T.me/fkeradis

➲ሼር ማድረግ አትርሱ 💡

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

➲ ለፍርድ አንቸኩል


አንድ አባት እና ሴት ልጁ በፓርኩ ውስጥ እየተጫወቱ ነበር ፡፡ ትነሿ ልጁ አንድ የፖም (አፕል) ሻጭ አየች ፡፡ ወዲያም አባቷን ፖም እንዲገዛላት ጠየቀችው ፡፡ አባት ብዙ ገንዘብ አልያዘም ነበር ፣ ነገር ግን ሁለት ፖም ለመግዛት የሚያስችል በቂ ገንዘብ ነበረው ፡፡ ስለዚህ ሁለት ፖም ገዝቶ ለልጁ ሰጣት ፡፡

ልጁም ሁለትን ፖም በሁለት እጆ እንድ አንድ ያዘች ፡፡ አባትም አንድ ፖም ልታካፍለው ትችል እንደሆነ ጠየቃት ፡፡ ሴት ልጁ ይህን ስትሰማ በፍጥነት አንደኛውን ፖም በትንሹ ግምጥ አደረገቸው ፡፡ እናም አባቷ ተናግሮ ከመጨረሱ በፊት ከሁለተኛው ፖምም በትንሹ ግምጥ አደረገቸ ፡፡

አባት በሁኔታው ተገረመ እንዲሁም አዘነ ፡፡ ‘ምን ዓይነት ስግብግብ እና እራስ ወዳድ ልጅ ነው ያሳደኩት? እንደወላጅ የቱ ጋር ነው ያጠፋሁት እሰዋን ሳሳድግ?’ እያለ ማሰብ ጀመረ ፡፡ አዕምሮው በብዙ በሀሳቦች ተወጥሮ ነበር ፡፡ እንዴት ብሎ ሴት ልጁን ስለ መጋራት እና ስለመስጠት ማስተማር እንዳለበት በማሰብ ፈገግታው ከፊቱ ላይ ጠፋ ፡፡

እናም በድንገት ሴት ልጁ በአንድ እጇ ላይ አንድ ፖም ይዛ “አባዬ ይህን ውሰድ ፣ ይህኛው በጣም ለስላሳና እና ጣፋጭ ነው” ብላ እጇን ዘረጋችለት ፡፡ አባቷም በሆነው ነገር ተገርሞ ቃላት ስላጣ ዝም አለ ፡፡ ስለ አንድ ትንሽ ልጅ በፍጥነት ወደ ድምዳሜ በማምራቱ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማው ፡፡ ልጁ በፍጥነት አፕሎቸን የገመጠችበት ምክንያት ምን እንደሆነ ሲገባው ተደሰተም ተገረመም ፡፡ አሁን ፈገግታው ተመልሷል ፡፡


በፍጥነት ማንኛውንም ነገር አይፍረዱ ወይም መደምደሚያ ላይ አይደርሱም። ነገሮችን በተሻለ ለመረዳት ይሞክሩ ከመፍረዶ በፊት።



Join ➲ T.me/fkeradis

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

🚺 ሚስት ስጦታ እንጂ ምርጫ አይደለችም 🚺


🔵 አንድ ምሽት በጎልማሶች የትምህርት ክፍለ ግዜ የሳይኮሎጂ መምህሩ ወደ ክፍል ገባና "ዛሬ አንድ Game እንጫወታለን" አለ፡፡
ተማሪዎቹም "ምን አይነት Game?" በማለት በህብረት ጠየቁ፡፡ መምህሩ ቀጥሎ "ፈቃደኛ የሆነ አንድ ሰው?" አለ፡፡ አንድ ፈቃደኛ ወንድ ተማሪ እጁን አወጣ፡፡

መምህሩም ተማሪውን በህይወቱ ትልቅ ቦታ ያላቸውን 30 ሰዎች ስም ጥቁር ሰሌዳው ላይ እንዲፅፍ ጠየቀው፡፡ ተማሪውም ከቤተሰቦቹ ጀመሮ የጎረቤቶቹን፣ የዘመዶቹንና የጓደኞቹን ስም ፃፈ፡፡

መምህሩ በመቀጠል በጣም ጠቃሚ ያልሆኑ 3 ስሞችን እንዲሰርዝ አዘዘው፡፡ እሱም የጎረቤቶቹን ስም ሰረዘ፡፡ አሁንም ሌላ 5 ስሞችን እንዲሰርዝ ነገረው፡፡ተማሪውም የሩቅ የምላቸውን ዘመዶቹን ስም ሰረዘ።

በዚህ መልኩ የአራት ሰዎች ስም ብቻ (የእናቱ፣ የአባቱ፣ የሚስቱና የብቸኛው ልጁ) እስኪቀር ብዙ ስሞችን ሰረ። ሙሉ የክፍሉ ተማሪዎች Gamu ለዚህ ተማሪ ብቻ እንዳልሆነ ተረድተው በተመስጦ ይከታተላሉ፡፡

አሁንም መምሩ ከቀሩት አራት ስሞች 2 እንዲሰርዝ አዘዘው፡፡ ተማሪውም በጣም ከባድ ምርጫ ነበር፡፡እያመነታና እንዳልተቀበለው በሚያስታውቅ መልኩ የወላጆቹን ስም ሰረዘ።

መምህሩ በስተመጨረሻ ከቀሩት ሁለት ስሞች 1 እንዲሰርዝ ነገረው፡፡ ተማሪውም ሙሉ በሙሉ አእምሮው ተረበሸ፡፡

በአይኖቹ እያነባ በሚንቀጠቀጡ ጣቶቹ የልጁን ስም ሰረዘ፡፡ መምህሩም ተማሪውን ወደ መቀመጫው እንዲመለስ ነገረው። ከደቂቆች በኀላ መምህሩ "ለምን ሚስትህን አስቀረህ?

►ቤተሰቦችህ ላንተ ብቸኞች ናቸው፤

►ልጅህን የወለድከው ( ወደ ህይወት ያመጣኸው) አንተ ነህ፤

►ሚስት ግን ሌላ ማግባት ትችላለህ፤

►ለምን ከእነሱ እሷን አስቀደምክ?" በማለት ተማሪውን ጠየቀው፡፡

►ሁሉም ተማሪውን ምላሽ ለመስማት ጓግቷል፡፡

ተማሪውም በተረጋጋ መንፈስ እንዲሁም በቀስታ እንዲህ ስል መለሰ፦

አንድ ቀን ቤተሰቦቼ ምናልባት ከእኔ ቀድመው ያልፋሉ፤ ልጄም ሲያድግ ለትምርት፣ ለስራ ወይም በማንኛውም ምክንያት ጥሎኝ ይሄዳል፡፡
ሙሉ ህይወቴን ሁሉን አብራ የሚትጋራኝ ብቸኛ ሰው ቢኖር ባለቤቴ /ሚስቴ/ ናት፡፡" አለ።
ሁሉም ተማሪ ከመቀመጫቸው ተነስተው እውነተኛውን የህይወት ገፅታ ስላካፈላቸው አጨበጨቡለት 👏👏👏

✅ #እውነት_ነው፡፡✅

✴️ ሁላችንም ቤተሰቦቻችንን ምንም ያህል ብንወዳቸው ጥለናቸው እንሄዳለን፡፡
ለማን ስንል? ለባል ወይም ሚስት፡፡

✴️ ልጆቻችንን ምንም ያህል ብንወዳቸው ጥለውን ይሄዳሉ፡፡ ለማን ሲሉ ለሚስታቸው ወይም ለባላቸው ሲሉ፡፡

✴️ በስተመጨረሻ አብረው የሚዘልቁት ፈጣሪ ያጣመራቸው ሁለት ነፍሶች ብቻ ናቸው፡፡

ባልና ሚስት፤ ወይም ፍቅረኞች።

✴️ ስለዚህ ወዳጄ የህይወት አጋሬ ናት የምትላትን ሴት ከምንም በላይ አክብራት፤ ቅድሚያም ስጣት፡፡ አንቺም እንደዛው እህቴ፡፡

🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿

#አዎን_ወዳጄ ፦

🚺 ሚስት ስጦታ እንጂ ምርጫ እንዳልሆነች ልብ በል።

🚺 ሚስት ማግባት ትዝ የሚልህ ሲመሽ ከሆነ ትዳር ሳይሆን አዳር ፈላጊ ነህ ማለት ነው።

🚺 ሚስት ማግባት ትዝ የሚልህ ቤትህና ልብስህ ሲቆሽሽ ከሆነ ሚስት ሳይሆን ሰራተኛ ነው የሚያስፈልግህ።

🚺 ሚስት ማግባት ትዝ የሚልህ ልጆችን ስታይ ከሆነ ሚስትህን የምትፈልጋት ለርቢ ነው ማለት ነው።

🚺 ሚስት ማግባት ትዝ የሚልህ ተኝተህ ሲበርድህ ከሆነ ሚስት ሳይሆን ወፍራም ብርድልብስ ነው ።

Join us ➲ T.me/fkeradis

••✦✿✦••┈┈┈┈┈┈┈┈••✦✿✦

♻️ የተመቸው ሼር ያድርገው ♻️ t.me/fkeradis

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

https://t.me/joinchat/k3wOMOhZJPEyNmU0

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

💕 ፍቅሬን በ ግጥም 🌷✏️ (👉 ፍቅሬን በግጥM ✍️)]
💌─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─💌



❤️ _እውነተኛ ፍቅር በዚህ ታሪክ ልቤ ተነክቷል _❤️

🚻 ሁልጊዜ ማወቅ ያለብን ፣ ሁሉም ሁኔታዎች ቋሚ አይደሉም !



🤦‍♂️ ምንም ሥራ የሌለው አንድ ወንድ፡- የባንክ ሰራተኛ የሆነችን ሴት ለማግባት ይፈልጋል፡፡ ፍራቻ ቢኖርበትም ብዙ ሰዎች ስራ ሳይኖረው ስራ ያላትን የባንክ ሰራተኛ ማግባት እንደሌለበት ይነግሩታል ፤ የሆኖ ሆኖ ግን ይጋባሉ ልጅቱም የደሞዟን 10% ለቤተክርስትያን የሚሰጠውን አስራት እየቀነሰች የቀረውን 10,000.00 ብር እነዳለ ለባሏ ትሰጠው ነበር ፡፡

በየወሩ ይህን በማድረግ ትቀጥላለች እርሱም ከተቀበለው ገንዘብ ለሚስቱ 2,000.00 ብር ለግል ጉዳዋ ይሰጣታል ከዚያም በቀረው ገንዘብ ምን ማድረግ እንዳለበት ይወስናል፡፡ በዚህ አይነት ሁኔታ ላለፉት 3 አመታት ያህል ይቆያሉ በነዚያ አመታት ያለምንም ችግር በደስታ ሚስትም ተቃውሞ ሳታሰማ ይኖሩ ነበር፡፡ ተቀዳሚ የቤቱን ስራም አሻፈረኝ ሳትል ለ3 አመታት ትሰራ ነበር ሆኖም ጓደኞቿ የቤቱን ሁሉንም ስራ መስራት ይቅርብሽ ላንቺ ማሰብ አለበት እያሉ የተሳሳተ
ምክር ቢሰጧትም ለተለያዩ ቃለመጠይቆች እና ስራ ፍለጋ ከአንዱ ወደ ሌላው አካባቢ ለመጓዝ በወር 2,000 ብር ጥቅም ላይ ያውል ነበር፡፡

በመጨረሻም በጥሩ ኩባንያ ተቀጠረ ደመወዝም ለመነሻ የሚሆን በየወሩ 25,000 ነበር፡፡ ከጥቂት አመታት በኋላ አዲስ ምርት ቆንጆ መኪና በሚሰራበት ድርጅት በኩል በማስመጣት ይገዛና ለባለቤቱ የመኪናውን ቁልፍ ሰጠ እናም ለ 3 ዓመታት ያህል በሕዝብ መጓጓዣ መጓዝ ቀጠለ::ከዚያም የመጀመርያውን መኪና ክፍያ በመጨረሱ እንደገና ከመጀመርያው የሚሻል ሁለተኛውን መኪና ገዝቶ የመጀመሪያውን የመኪና ቁልፍ ከርሷ ተቀብሎ የአዲሱን መኪና ቁልፍ ለሚስቱ ሰጣት፡፡ ከዚያም ከጥቂት ዓመታት በኋላ በራሳቸው ቤት ውስጥ መኖር ይጀምራሉ፡፡

አንድ ቀን ሚስትየው ጥቂት ሰነዶችን እንዳጋጣሚ ታገኛለች እሷበጥንቃቄ የተቀመጠውን ፋይል ስትመለከት ትኩረቷን ሳበው እርስዋም ስትከፍት የሰርግ ፎቶዋን ተመለከተች በፋይሉ የመጀመሪያ ገጽ ላይ በጣምቀጭን እና በጣም ትንሽ ነበረች፡፡እዚያም ሰነዶቹን በሙሉ ተመለከተች የመሬት ግዢ ፣ እና በቤት ውስጥ ያሉ
ማንኛውንም ሌሎች ነገሮች በሙሉ ሁሉም በስሟ የተፃፉ ደረሰኞች ነበሩ፡፡

በመጨረሻው ገጽ ላይ ግን የእርሷ የጋብቻ ፎቶ እና በእርሱ የተጻፈ ማስታወሻ አየች እንዲህ ይላል

ሚስቴ የእኔ ሁሉም ነገር ናት የዚህ ቤት ዋጋ እንኳን አይተካከላትም እርሷን በ 100 ሚሊዮን ብር አላገኛትም ይላል፡፡

እንባ ከአይቿ መንከባለል ጀምረዋል ፡፡ እነዚህ ባልና ሚስት በ 1997 ተጋቡ ፡፡ ባለፈው እሁድ የጋብቻ 17 ተኛ አመታቸው ሲሆን በ 3 ልጆች ተባርከዋል እውነተኛ ፍቅር እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራል፡፡ለትዳር ጓደኛዎ ያሎት ፍቅር አሁን ከማነበቡት ጋር ሊወዳደር ይችላልን?አንዳችሁ ሌላውን የመረጣችሁበት ሁኔታ እንዴትም ቢሆን እንኳን የቤቱን ምግብ ሰርቶ ቢያበልሽም /ብታበይው ወይም የመብራት/የውሃ የስልክ እና ሌሎች ክፍያዎችን የሚከፍለው ማንም ቢሆን ችግር የለውም,ሁልጊዜ ማወቅ ያለብን ፣ ሁሉም ሁኔታዎች ቋሚ አይደሉም።

ከተመቻችሁ #ሼር አድርጉት

*Join us* ➲ T.me/fkeradis

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

" ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማለፋችንን ካረጋገጥን በኋላ በመልበሻ ክፍል የነበረው የደስታ ድባብ" @fkeradis @fkeradis @fkeradis

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

አንዳንዴ በፍጥነት ለመሄድ ዝግ ማለት ያስፈልጋል፡፡ በብዙ የህይወታችን እንቅስቃሴዎች ዉስጥ በብልሃት የተደረገ ነገር በችኩልነት ከተደረገዉ በላይ ዉጤታማ ነዉ፡፡

ነገሮች ቶሎ ሲደረጉ እንደ "በረከት" በሚቆጠርበት ማህበረሰብ ዉስጥ ሆነን ዉጤቱን ካየን እርግማን ይዘዉብን ይመጣሉ፡፡

በልጅነታቸዉ ታዋቂ የነበሩ የፊልም አክተሮች፣ አርቲስቶች፣ ሀብታሞች ወዘተ...አሁን የት ናቸዉ?

ብዙ አለም አቀፍ ጥናቶችና ሃገራዊ ምሳሌዎች እንደሚያሳዩት ብዙ ጊዜ ሰዎች የተሻለና ዉጤታማ መንገድ ዉስጥ የሚገቡት በእድሜያቸዉ የመጨረሻ ክፍል ነዉ፡፡

የጀመሩትን ቢዝነስ ሲወድቁ ሲነሱ፡፡ በጎልማሳነታቸዉ ወራት ቀስ በቀስ ጠንካራና በቀላሉ የማይናድ ግንብ አድርገዉ ይገነቡታል፡፡

በ 50ዎቹ፣በ 60ዎቹና ከዚያ በላይ ያሉ የተሳካላቸዉ ሰዎች በወጣትነታቸዉ ከተሳካላቸዉ ሰዎች ይበዛሉ፡፡

ስለዚህ "ሁሉ ነገር አሁን ካልተደረገ ሞቼ እገኛለሁ!" ማለትን ትተን ዘመን የሚሻገር ራእይ ይዘን መሄድ እንጂ በችኩልነት ስሜታችን በተለዋወጠ ቁጥር ሳንለዋወጥ ወደፊት መገስገሱ ይበጀናል እላለሁ፡፡

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያውለን፤ ቸር ያሰማን🙌

@eyobreta

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏

ወደ መኝታ ከማምራቴ በፊት ይቺን ፅሁፍ አንድ ወዳጄ የፌስቡክ ግድግዳ ላይ ተለጥፋ አነበብኳትና ላጋራችሁ ወደድኩ፤ ሳትሰለቹ ተከተሉኝ።

እስከሞት የሚያደርስ “ቢዚነት”!

በአለም በትልቅነቱና በዝናው ተወዳዳሪ ያልተገኘለት መርከብ - ታይታኒክ! ይህ መርከብ እጅግ ትልቅና በፍጹም ምንም ነገር ሊያሰጥመው አይችልም የተባለለት መርከብ ነበር፡፡ ቅጽል ስሙ “የማይሰጥመው መርከብ” ነው፡፡ እንደውም ይህንን መርከብ የሰሩት ሰዎች “አምላክ እንኳ ሊያሰጥመው አይችልም” በማለት አጋንነው በድፍረት ይናገሩለት ነበር፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1912 ዓ/ም ግነ አንድ ነገር ተከሰተ፡፡

መርከቡ በጉዞ ላይ እንዳለ፣ በፊቱ የበረዶ ክምር እንዳለ ማስጠንቀቂያ ለካፒቴኑ ይደርሰዋል፡፡ካፒቴኑ ማስጠንቀቂያውን ከቁጥርም አልከተተው፡፡

በባህር ላይ የሚገኙ የበረዶ ክምሮች (Iceberg) ጫፋቸው ትንሽ፣ ከታች በውኃው የተሸፈነው አካላቸው ግን ግዙፍ በመሆናቸው ይታወቃሉ፡፡ ይህ ካፒቴን ለስድስተኛ ጊዜ ማስጠንቀቂያው ሲመጣለት የሰጣቸው ምላሽ “ቢዚ ነኝ ተውኝ” የሚል ነበር፡፡ ይህ ቃል የካፒቴኑ የመጨረሻው ቃል እንደ ነበረ ይነገራል፡፡ ብዙም ሳይቆይ ታይታኒክ በደረሰበት የግጭት አደጋ ለመስጠም በቃ፡፡ የብዙ ሰዎች ሕይወት አለፈ፤ ብዙ ክስረትና ሃፍረት ደረሰ፤ በአንድ ሰው እስከሞት በሆነ
ቢዚነት!

ቀናችንን የምናሳልፈው በምን ላይ ነው? በአስፈላጊው ወይስ በአጣዳፊው? ቀኑ
አልቆ ማታ ወደ ቤታችን ስንገባ መለስ ብለን ውሎአችንን ስናስበው ብዙውን ጊዜአችንን የወሰደው ነገር ምን ያህል ቁም ነገር ያለው ጉዳይ ነው? ከአስፈላጊው ጉዳይ ላይ ትኩረታችንን የወሰደው አጣዳፊውና አንገብጋቢው ነገር
ምንድን ነው?

የተግባር “ቆጠራ” እና “ቁጥጥር” ካላደረግን ያልታሰበና የቀስ በቀስ ሞት መሞታችን አይቀርም። ለሕይወትና ለእድገት የሚሆኑትን ትተን ለጊዜአዊ ስሜት ግለት በሆነው እንወሰዳለንና፡፡ ብዙ ሰዎች “ቢዚ” ናቸው፤ እስከሞት ድረስ “ቢዚ”!

ምንም “ቢዚ” ብትሆን . . .
• ለቤተሰብህ ጊዜ እስከምታጣ ድረስ “ቢዚ” አትሁን!
• ለትዳር አጋርህ ጊዜ እስከምታጣ ድረስ “ቢዚ” አትሁን!
• ጤንነትህን ለመንከባከብ ጊዜ እስከምታጣ ድረስ “ቢዚ” አትሁን!
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድግ ጊዜ እስከምታጣ ድረስ “ቢዚ” አትሁን!
• ለማንበብና አእምሮህን ለመመገብ ጊዜ እስከምታጣ ድረስ “ቢዚ” አትሁን!
• ለብቻህ ሆነህ ሩጫህን ለመገምገም ጊዜ እስከምታጣ ድረስ “ቢዚ” አትሁን!
• ከአንተ የተሸሉ ሰዎች የሚሰጡህን ምክር ለመስማት ጊዜ እስከምታጣ ድረስ
“ቢዚ” አትሁን!

by Dr.Eyob Mamo

🙌መልካም ምሽት ይሁንልን🙌

🔵Share and join

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

[ Photo ]
🌀🌻 አስገራሚ የእንሰሳት እውነታዎች! 🌻🌀

1. ቀበሮ በሂወት ዘመኑ አንዴ ብቻ ነው ፍቅረኛ ሚኖረው። ምን አልባት ሚስቱ ከሞተች ቀሪ ሂወቱን ብቻውን ነው የሚያሳልፈው! ምስኪን ታማኝ!!
2. የጂብ እድሜ ጣራ 80 ዓመት ነው!
3. አይጦች የራሳቸውን ያልሆነ ልጅ አጥብተው ያሳድጋሉ!
4. የወባ ትንኝ 47 ጥርሶች አላት!!!!
5. ፍየሎች ሴቷን ፋየል ለማማለል ሲሉ እርስበእርስ ይዋጋሉ!!!!!
6. ድመት በሂወት ዘመኗ እስከ 100 ግልገሎች መውለድ ትችላለች!!!!
7. እንደ ሰው ህልም ማየት ሚችለው እንስሳ ፈረስ ብቻ ነው!!!!
8. ዳክየ እንቁላል የምትጥለው ጧት ጧት ብቻ ነው!!!
9. የሌሊት ወፍ ጆረዋ ከተደፈነ መብረር አትችልም!!!!
10. ጊንጥ 12 አይኖች አላት!!!!
11. አዞ ምላሱን ወደውጭ ማውጣት አይችልም!!!
12. ሴት ካንጋሮ ከወንዱ ምትለየው በደረቷ ባለው ከረጢት ነው!!!
13. አይጥ ያለምግብ 14 ቀን መቆየት ትችላለች!!
14. አለም ላይ የመጀመሪያው ለማዳ እንስሳ ውሻ ነው!!
15 .የጊንጥ መርዝ ጊንጥን ሲገድል የእባብ መርዝ ግን እባብን አይገድልም!!!
16. በአንድ ጉንዳን መንጋ ውስጥ እስከ ግማሽ ሚሊየን ጉንዳኖች ሊኖሩ ይችላሉ!!!
17. ማንኛውም ስጋ በል እንስሳ በመብረቅ ተመትቶ የሞተን እንሰሳ አይበላም!!!
18. ቢራቢሮ 12, 000 አይኖች አሏት!!!
19. የመሬት ትል 5 ልቦች አሏት!!!

የትኛው ግርምት ፈጠረባቹህ?
ንባብ ለህይወት!!!!!!!!!
ሟርርርር @fkeradis @fkeradis

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

መታመንስ እንደ ሀቺኮ! ፅናትስ እንደ ሀቺኮ!!

ድንገት እግር ጥሏችሁ በጃፓኗ ቶኪዮ ሽቡያ ባቡር ጣቢያ ብትከሰቱ አንድ የውሻ ሀውልት ታያላችሁ!
ታሪኩ እንዲህ ነው፣በጃፓን ቶኪዮ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ሳይንስ ፕሮፌሰር የሆኑት ኢዛቡሮ ኡኖ የአኪታ ዝርያ የሆነ ውሻ እንዲኖራቸው የረጅም ጊዜ ፍላጎት ነበራቸው። ታዲያ ይህን ያወቀ አንድ ተማሪያቸው አንድ ሀቺኮ የሚባል ውሻ አምጥቶ ሰጣቸው።
አዲሱ ባለቤቱና ሀቺኮ ብዙም ሳይቆዩ የቅርብ ጓደኛሞች ሆኑ ፡፡ ሀቺኮ እያደገ ሲሄድም ማለዳ ላይ ፕሮፌሰሩ ወደ ስራ ሲሄዱ የሽቡያ ባቡር ጣቢያ ድረስ አብሮ እየሄደ ሸኝቷቸው ይመለሳል፣ማታ 11 ሰዓት ላይም ባቡር ጣቢያ ሄዶ ይቀበላቸውና ቤት ድረስ አብሯቸው ይመጣል።
ታዲያ ከእለታት በአንዷ ክፉ ቀን (እ.ኤ.አ. ግንቦት 21 ቀን 1925) ሀቺኮ ፕሮፌሰሩን ሸኝቶ ውሎውን ቤቱ አድርጎ ማታ እንደልማዱ ሊቀበላቸው ባቡር ጣቢያ ተገኝቶ ቢጠብቃቸው ቢጠብቃቸው የውሃ ሽታ ሆነው ቀሩበት።ለካ ሰውየው በስራ ገበታቸው ላይ ሳሉ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ገጥሟቸው ሞተው ኖሯል።
ሀቺኮ ግን ይመጣሉ እያለ ተስፋ ባለመቁረጥ በየቀኑ ባቡር ጣቢያው ድረስ እየሄደ ይጠብቃቸዋል። ይህን ያደረገው 1 ቀን ብቻ አይደለም ጥቂት ወራትም አይደለም ድፍን 10 አመት አንዲትም ቀን ሳያዛንፍ እንጂ! በመጨረሻም እሳቸውን በሚጠብቅባት ባቡር ጣቢያ ሞተ፡፡
ሀቺኮ ለ10 አመታት ፍቅርና ታማኝነት ተምሳሌት በመሆኑ ጃፓናውያን ይኮሩበታል
ይወዱታልም።ያ እግር ጥሏችሁ ካያችሁት ያልኳችሁ ሀውልትም ለሀቺኮ መታሰቢያነት ያሰሩለት ነው፡፡
በነገራችን ላይ የዚህ ውሻ ታሪክ ፊልም ሆኖ ተሰርቷል፡፡

አስደናቂ ነው!!

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

✍️ታላቅ ምክር

✿ ስለ ገንዘብህ ከድሃ ፊት ለፊት አትናገር!

✿ ስለ ጤንነትህ ከበሽተኛ ሰው ፊት ለፊት አትናገር!

✿ ስለ አቅምህ(ጥንካሬህ) ከደካማ ሰዎች ፊት ለፊት አትናገር!

✿ ስለ ደስታህ ከተከፋ ሰው ፊት ለፊት አትናገር!

✿ ስለ ነፃነትህ ከእስረኛ ሰው ፊት ለፊት አትናገር!

✿ ስለ ልጆችህ ከመሀን ሰው ፊት ለፊት አትናገር!

✿ ስለ እናትና አባትህ ከወላጅ አልባ ፊት ለፊት አትናገር!

ምክንያቱም ቁስሎቻቸው ይበልጥ ይጎዳቸዋልና፡፡

🙌መልካም አሁድ! ቸር ያውለን

ይቀላቀሉን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@fkeradis @fkeradis @fkeradis

ለ አስተያየትዎ 👉👉 @eyobreta

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

[Forwarded from ንባብ ለ ሕይወት (𝐓𝐞𝐬𝐡𝐞 ......) via @like]
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏

ወደ መኝታ ከማምራቴ በፊት ይቺን ፅሁፍ አንድ ወዳጄ የፌስቡክ ግድግዳ ላይ ተለጥፋ አነበብኳትና ላጋራችሁ ወደድኩ፤ ሳትሰለቹ ተከተሉኝ።

እስከሞት የሚያደርስ “ቢዚነት”!

በአለም በትልቅነቱና በዝናው ተወዳዳሪ ያልተገኘለት መርከብ - ታይታኒክ! ይህ መርከብ እጅግ ትልቅና በፍጹም ምንም ነገር ሊያሰጥመው አይችልም የተባለለት መርከብ ነበር፡፡ ቅጽል ስሙ “የማይሰጥመው መርከብ” ነው፡፡ እንደውም ይህንን መርከብ የሰሩት ሰዎች “አምላክ እንኳ ሊያሰጥመው አይችልም” በማለት አጋንነው በድፍረት ይናገሩለት ነበር፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1912 ዓ/ም ግነ አንድ ነገር ተከሰተ፡፡

መርከቡ በጉዞ ላይ እንዳለ፣ በፊቱ የበረዶ ክምር እንዳለ ማስጠንቀቂያ ለካፒቴኑ ይደርሰዋል፡፡ካፒቴኑ ማስጠንቀቂያውን ከቁጥርም አልከተተው፡፡

በባህር ላይ የሚገኙ የበረዶ ክምሮች (Iceberg) ጫፋቸው ትንሽ፣ ከታች በውኃው የተሸፈነው አካላቸው ግን ግዙፍ በመሆናቸው ይታወቃሉ፡፡ ይህ ካፒቴን ለስድስተኛ ጊዜ ማስጠንቀቂያው ሲመጣለት የሰጣቸው ምላሽ “ቢዚ ነኝ ተውኝ” የሚል ነበር፡፡ ይህ ቃል የካፒቴኑ የመጨረሻው ቃል እንደ ነበረ ይነገራል፡፡ ብዙም ሳይቆይ ታይታኒክ በደረሰበት የግጭት አደጋ ለመስጠም በቃ፡፡ የብዙ ሰዎች ሕይወት አለፈ፤ ብዙ ክስረትና ሃፍረት ደረሰ፤ በአንድ ሰው እስከሞት በሆነ
ቢዚነት!

ቀናችንን የምናሳልፈው በምን ላይ ነው? በአስፈላጊው ወይስ በአጣዳፊው? ቀኑ
አልቆ ማታ ወደ ቤታችን ስንገባ መለስ ብለን ውሎአችንን ስናስበው ብዙውን ጊዜአችንን የወሰደው ነገር ምን ያህል ቁም ነገር ያለው ጉዳይ ነው? ከአስፈላጊው ጉዳይ ላይ ትኩረታችንን የወሰደው አጣዳፊውና አንገብጋቢው ነገር
ምንድን ነው?

የተግባር “ቆጠራ” እና “ቁጥጥር” ካላደረግን ያልታሰበና የቀስ በቀስ ሞት መሞታችን አይቀርም። ለሕይወትና ለእድገት የሚሆኑትን ትተን ለጊዜአዊ ስሜት ግለት በሆነው እንወሰዳለንና፡፡ ብዙ ሰዎች “ቢዚ” ናቸው፤ እስከሞት ድረስ “ቢዚ”!

ምንም “ቢዚ” ብትሆን . . .
• ለቤተሰብህ ጊዜ እስከምታጣ ድረስ “ቢዚ” አትሁን!
• ለትዳር አጋርህ ጊዜ እስከምታጣ ድረስ “ቢዚ” አትሁን!
• ጤንነትህን ለመንከባከብ ጊዜ እስከምታጣ ድረስ “ቢዚ” አትሁን!
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድግ ጊዜ እስከምታጣ ድረስ “ቢዚ” አትሁን!
• ለማንበብና አእምሮህን ለመመገብ ጊዜ እስከምታጣ ድረስ “ቢዚ” አትሁን!
• ለብቻህ ሆነህ ሩጫህን ለመገምገም ጊዜ እስከምታጣ ድረስ “ቢዚ” አትሁን!
• ከአንተ የተሸሉ ሰዎች የሚሰጡህን ምክር ለመስማት ጊዜ እስከምታጣ ድረስ
“ቢዚ” አትሁን!

by Dr.Eyob Mamo

🙌መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን🙌

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

👉ጥቂት መረጃ ስለ ሴቶች

1️⃣ አንዳንድ ሴቶች አስመሳይ ናቸው በዚህ ግራ አይግባህ ተጠንቀቅ
2️⃣ ሴቶች አብዛኛውን ጊዜ ቁመና ባላቸው ወንዶች ይሳባሉ ምንም ቆንጆ ባይሆንም
3️⃣ ሴቶች ሲደነቁ ይወዳሉ እናም የሚያምረውን ክፍሉአን አድንቅላት
4️⃣ ሰቶች ንዴታቸውን በስርት ከገልፁልህ ይወዱሃል
5️⃣ ሴቶች የሚወዱት ወንድ ሳያያቸው ያዩታል
6️⃣ ሴቶች ጥፍት የሚሉት ወንዶች የሆነ ነገር ከሴቶች ሲፈልጉ ነው
7️⃣ ሴቶች የሚወዱትን ወንድ ማታ ሁሌ ከመተኛታቸው በፊት ያስቡታል ምንም አንኩዋ ከሌላ ወንድ ጋር ቢዉሉም
8️⃣ ሴቶች በወንድ ልጅ በቀላሉ በፍቅር ይያዛሉ
9️⃣ ሴቶች የሚወዱት ወንድ ከሌላ ሴት ሲሆን ያብሰልስላቸዋል
1️⃣0️⃣ ሴቶች የሚወዱት ወንድ በአጠገባቸው ሲያልፍ ይደሰታሉ
1️⃣1️⃣ ሴቶች ሌላ ሰው ለመምሰል የሚሞክር ወንድን ይጠላሉ
1️⃣2️⃣ ሴት አንደወደድካት ታውቅባሃነች ነገር ግን ካልነገርካት አርግጠኛ አትሆንም
1️⃣3️⃣ ሴቶች የሚወዱት ወንድ ሲቀልድ ባያስቅም ምን አልባት ውሃ ፈላ ቢላት ት ስቃለች
1️⃣4️⃣ ሴት ፍቅረኛህ ከወንድ ጉዋደኛህ ፍቅር አንዳይዛት ትጠነቀቃለች
1️⃣5️⃣ ሴት ስለ ውንድ ትጉአጉአለች ለምን በትል ወንዶች ለሴቶች አስፈላጊ ናቸው
1️⃣6️⃣ ስለሷ ማወቅ ከፈለክ ጓደኛዋን ጠይቃት እሷ እራሱዋ የማታቀውን ሁላ ትነግርሃለች

አረ ላይክ እያነሰ ነው 👍 በማረግ ያበረታቱን

🌹━━━✦◉●••┈❀┈┈••●◉✦━━ 🌹




❣️ @fkeradis ❣️

💞in box @fkeradis❤️

┈┈••◉❖◉●••┈❀┈┈••◉❖◉●••┈┈

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

❂✿❂✿❂ ጣፋጭ አስተማሪ ታሪክ ✿❂✿❂


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን🙏



✍️ አንድ ሠው ወደ አንድ ታላቅ ጠቢብ ሠው ይሄድና ትምሕርት መማር ይጀምራል። በትምህርቱም መሐል ሥለ እናት ማስተማር ይጀምራሉ። ሲያስተምሩም "እናት ማለት ከፈጣሪ በታች በዚህ ምድር ባለው ሕይወታችን ታላቅ ሥፍራ ያላት ናት። ለምሣሌ እናትህ አንተን 9 ወር አርግዛ በስቃይና በምጥ ወልዳ ጡቷን አጥብታ አዝላ ስትወድቅ እየወደቀች፣ ስትነሳ እየተነሳች ሙሉ ሠው እስክትሆን ድረስ ደክማና ለፍታ ያሳደገችህ ውለታዋን በምንም የማትከፍላት ታላቅ ፍጥረት ናት።" ሲሉ ይናገሩታል።

ልጁም እንዲህ ሲል ጠቢቡን ሰው ይጠይቃቸዋል" እሺ ቆይ እኔም እናቴ እንዳደረገችልኝ እሷን ባበላት ባጠጣት እግሯን ገላዋን እያጠብኩ ሲደክማት እያዘልኩ ቤተ- መንግስት የመሰለ መኖሪያ ቤት ሰርቼ ባኖራት ባጠቃላይ በዚህ አለም ለእናት የሚደረገውን ሁሉ እያደረግኩ ባኖራት ብድሬን ውለታየን መመለስ አልችልም ወይ?" ሲል ይጠይቃቸዋል።

ጠቢቡ ሰውም " አትችልም። ምክንያቱም እናትህ አንተን 9 ወር አርግዛ ወልዳ ጡቷን እያጠባች እያበላች እያጠጣች ስታሳድግህ የምታመጣህ ወደ ሕይወት ነው። አንተ ግን የፈለገ ብትንከባከባት ለእናት መሆን ከሚገባው በላይ ብታደርግላት እየተንከባከብካት የምትወስዳት ወደ ሞት ነው። አየህ ልዪነታችሁ ይህ ነው! ለዚህ ነው ውለታዋን በምንም አትመልሰውም ያልኩህ"

🙌መልካም አዳር

#ሟር

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

⊶⊷⊶⊷❍ ➲➲✍️➲➲ ❍⊶⊷⊶⊷



🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

"እንደኔ ግን መሄድ ከመቆም ይሻላል። መቆም ቢያንስ ለጠላቶችህ የታወቀ አድራሻ ይሰጣል። መሄድ ግን ቢያገኙህ እንኳን ለፍተው እንዲያገኙህ ያደርጋል።
መቆም በቆምክበት ቦታ ብቻ ያለውን እድል እንድትጠቀም ያደርግሃል፤ መሄድ ግን የማታውቀውንም ዕድል እንድትሞክር ይረዳሃል።

ስትቆም መጀመሪያ ታረጃለህ፣ ቆይቶም ትበሰብሳለህ። ስትሄድ ግን መጀመሪያ ትደክማለህ፣ ቀጥሎ ግን ትጠነክራለህ።
ባለቀ ትናንት አትታሰር፣ በተበላ ዛሬ አትወሰን፤ ይልቅ ወደማይታወቀው ነገ ሂድ። ነገ ወዳንተ ሳይመጣብህ አንተ ወደ ነገ ሂድ።

አንድ ቦታ ላይ የግድ እንድንቆም ቢፈለግ ኖሮ እግር ሳይሆን እንደ ዛፍ ሥር ይሰጠን ነበር። የመሄዳችን ዋናው ምክንያቱ የምንቆይበት ምክንያት አለመኖሩ ነው።"
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
"የአዲስ አበባ ውሾች"
✍️በዳንኤል ክብረት
📗 ሐምሌ 2010 ዓ.ም.
📯ገ ፅ 171

◈━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM ⸙━━━━◈

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

ልወጋሽ ነው😡
👏👏👏👏👏

in box commet
@eyobreta


➡️ #MØØD✔️☑️

ለሚወጓቸው ብቻ ጋብዙልኝ ግሩፑ ውስጥ ሰው 🤣t.me/fkeradis

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

https://t.me/joinchat/9upz4-CuTYQ4ZGFk

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

በጣም አስገራሚ ቻናል መጣለቹ
👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌
የተሰረቀ ፊልም የሚገኝበት

channle new goin በሉ ቶሎ
በሉ

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

💕 ፍቅሬን በ ግጥም 🌷✏️ (👉 ፍቅሬን በግጥM ✍️)]
💌─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─💌

...... ደሃ ፍለጋ .......

አንድ ጠቢብ በአንድ ታዋቂ ንጉስ ግዛት ስር ባለች ዋና ከተማ ውስጥ እያለፈ ነበር ፡፡ እየተጓዘ ሳለ በመንገድ ላይ ዋጋው ከፍ ያለ የወደቀ ሳንቲም አገኘና አነሳው ፡፡ ሕይወት የሞላለት ሰው ስለነበር ይህ ሳንቲም ለሱ ጥቅም አልነበረውም ፡፡ ስለዚህ ለሚያስፈልገው ለመለገስ ወሰነ ፡፡ ቀኑን ሙሉ በጎዳናዎች ሲዞር ዋለ ነገር ግን እርዳታ የሚያስፈልገው ሰው አላገኘም ፡፡ በመጨረሻም ወደ ማረፊያ ቦታው ደርሶ እዚያ አደረ ፡፡
በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ለዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ከእንቅልፉ ሲነቃ አንድ ንጉስ ለጦርነት ከተዘጋጀው ጦር ጋር ሌላ ግዛት ለመውረር ሲሄድ መንገድ ላይ ተገናኙ ፡፡ ንጉሡም ጠቢቡን ቆሞ ባየ ጊዜ ጦሩን ወደሱ እንዲያመጡት አዘዘ ፡፡ ወደሱ እንዳደረሱትም “ኦ ታላቁ ሊቅ ፣ ግዛቴ እንዲስፋፋ ሌላ ክልል ለማሸነፍ ወደ ጦርነት እገባለሁ ፡፡ ስለዚህ አሸናፊ እሆን ዘንደ ቡራኬክን ስጠኝ! ”፡፡
ጠቢቡም ካሰበ በኋላ ለንጉሡ ቀደን ብሎ ያገኛትን ሳንቲም ሰጠ! ንጉሡም በዚህ ግራ ተጋባ እንዲሁም ተበሳጨ፡፡ ምክንያቱም እሱ ቀድሞውኑ ከበለፀጉ ነገሥታት አንዱ ሆኖ ሣለ አንድ ሳንቲም ለሱ ምን ይጠቅማል! ንጉሡም ጠየቀ “የዚህ አንድ ሳንቲም ትርጉም ምንድን ነው?” ፡፡
ጠቢብም ሲያስረዳ “የተከበሩ ታላቅ ንጉስ! ትናንት ይህንን ሳንቲም ያገኘሁት በዋና ከተማዎ ጎዳናዎች ዙሪያ እየተዘዋወርኩ ነው ፡፡ ለእኔ ምንም ጥቅም የለውም ነበርና ለችግረኛ ለመለገስ ወሰንኩኝ ፡፡ በዋና ከተማዎ ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ተዘዋወርኩኝ ፣ ነገር ግን እርዳታ የሚያስፈልገው አላገኘሁም ፡፡ ሁሉም ሰው ደስተኛ ኑሮ እየኖረ እንደሆነ አስተዋልኩኝ ፡፡ ባገኙት ነገር ረክተው እንደሚኖሩ ያስታውቃል ፡፡ ስለዚህ ይህንን ሳንቲም የምሰጥ ሰው አላገኘሁም ፡፡ ግን ዛሬ የዚህ ግዛት ንጉስ አሁንም የበለጠ የማግኘት ፍላጎት እንዳአለው እያየው ነው፡፡ ያሎት ነገር አልረካዎትም እና ተጨመሪ እየፈለጉ ነው ፣ ስለዚህ ይህ ሳንቲም ለእርሶ እንደሚገባዎት ተሰማኝ ንጉስ ሆይ ሺ አመት ይንገሱ፡፡ ” በማለት በትህትና እጅ ነሳ ጠቢቡ ፡፡

ንጉሱም ስህተቱን በግልፅ ስላሳያቸው የታቀደውን ጦርነት አስቀርተው ባላቸው ነገር ተደስተው በሰላም መኖር ጀመሩ ፡፡

ሁላችንም ባለን ተደስተን አመስጋኝ መሆንን መማር አለብን ፡፡ ብዙ ሁላችንም ከያዝነው የበለጠ ወይም የተሻለ እንመኛለን ፣ ግን ቀድሞውኑ ባለው የመደሰት ልማዱ የለንም ፡፡ እርሶ ያለዎት ነገር ምናልባት ሎሎች ላይኖራቸው ይችላል ፣ በተቃራኒው ደግሞ ከእርስዎ የበለጠ ብዙ ያላቸውም ይኖራሉ ፡፡ የተሻለው ነገር አላስፈላጊ ውድድርን በመተው ደስተኛ ይሁኑ እና ጤናማ ሕይወት አይመሩ ፡፡

#ሼር በማድረግ ለሌሎች አድርሱ

Join us ➲ T.me/fkeradis

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

➲ ቁርጥራጭ አሉባልታ


በአንድ ወቅት አንድ ሽማግሌ ጎረቤቱ ሌባ ነው ብለው ወሬ ያሰራጩ ነበር ፡፡ በዚህ ምክንያት ወጣቱ ተያዘ ፡፡ ከቀናት በኋላ ወጣቱ ንፁህ መሆኑ ተረጋገጠና ከስር ተፈታ ፡፡ ከእስር ከተለቀቀ በኋላ ወጣቱ ወደ ቤቱ ሲሄድ የውርደት ስሜት ተሰማው ፡፡ ሽማግሌውን በተሳሳተ መንገድ ስሙን ስላጎደፉት በተራው ክስ መሰረተ ፡፡

ፍርድ ቤት ውስጥም አዛውንቱ ለዳኛው “ክቡር ዳኛ ቀለል ያሉ አስተያየቶች እና ወሬ ነበር ያውራሁት እንጂ እንዲህ እንደሚሆን አልጠበኩም ነበር ...” ሲሉ ዳኛው በጉዳዩ ላይ የቅጣት ውሳኔ ከማስተላለፋቸው በፊት ለአዛውንቱ “ስለ እሱ የተናገሩትን ሁሉ በወረቀት ቁራጭ ይፃፉዋቸው ከዛም እነሱን ይቁረጡ እና ወደ ቤት ሲመለሱ ፣ የወረቀቱን ቁርጥራጮቹን በየመንገዱ ይጣሉ ፡፡ ነገ ብይኑን ለመስማት ተመለሱ፡፡ ”ብሎ አዘዘ ፡፡

በቀጣዩ ቀን ዳኛው ለአዛውንቱ “ፍርዱን ከመቀበልዎ በፊት ትናንት የጣሉትን ወረቀት ሁሉ መሰብሰብ ይኖርብዎታል” አሏቸው ፡፡ ሽማግሌውም “ክቡር ዳኛ እኔ እንዲህ ማድረግ አልችልም! ባዘዙኝ መሰረት ወረቀቶችን መተን እንደጀመርኩኝ ነፋሱ እያንሳፈፍፈ ወስዷቸዋል፡፡ መልሼ ለማግኘት እቸገራለው›› አሉ፡፡

ከዚያም ዳኛውም መለሱ ፣ “በተመሳሳይ መንገድ ቀላል አስተያየቶች እና አሉባልታ የአንድን ሰው ሕይት መልሰን ማስተካከል እስከሚቸግረን ድረስ ያበላሻል፡፡ የሰውን ክቡር ሕይወት ሊያጠፋ ይችላል ፡፡ ” ሽማግሌው ስህተታቸውን ተገንዝበው ከልብ ይቅርታ ጠየቁ ፡፡


እውነት ወይም ውሸት ነገሩ ሳታውቅ ማንንም በክፉ አትወቅስ ወይም አትወቅሽ ፡፡ በቃላቶችዎ ያለ አንዳች ጥፋታቸው የአንድን ሰው ሕይወት ሊያበላሹ ይችላሉ።




Join ➲ T.me/fkeradis

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

" መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በተገኘው ድል እንኳን ደስ ያለን " እንኳን ደስ ያለን
ኢትዮጵያ🇪🇹 ወደ አፍሪካ ዋንጫ አልፋለች
#ደስ_ያለው_ብቻ 👍

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

አንድ ቀን ሁሉም ሰራተኞች ወደ ቢሮ ሲደርሱ እንድ ጎላ ተደርጎ የተፃፈ ማስታወቂያ ተለጥፎ አዩ ፡፡ “በዚህ ኩባንያ ውስጥ እድገትዎን የሚያደናቅፈው ሰው በትላንትናው ዕለት ከዚህ አለም በሞት ስለተለየ በመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ተዘጋጅቷልና መጥተው ይሰናበቱት ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን" የሚል

መጀመሪያ ላይ ሁሉም በሞተው የሥራ ባልደረባ ሐዘን ገብቷቸው ነበር ፣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን የባልደረቦቹን እና የድርጅቱን እድገት የሚያደናቅፍ ያ ሰው ማን እንደሆነ ለማወቅ መጓጓት ጀመሩ፡፡
በአዳራሹ ውስጥ በርካታ ሰው ስለነበር ደንብ አስከባሪ ጥበቃ በክፍሉ ውስጥ ያለውን ሕዝብ እንዲቆጣጠሩ ትእዛዝ ተሰጣቸው። አዳራሽ ውስጥ ያለው ሰው እየጨመረ በመጣ ቁጥር የሟቹን ነገር ተረስቶ እድገታቸውን ያስተጓጎለው ሰው በሞሞቱ ደስታ ይሰማቸው ነበር፡፡ ብዙዎቹም እያጉረመሩሙ መደሰታቸውን ይገልጻሉ፡፡ ሰዎች ወደ ሬሳ ሳጥኑ በቀረቡ ቁጥር ደስታቸው እየጨመረ መጣ፡፡ በዛው መጠን ማን እንደሆነ የማወቅ ጉጉታቸው አየለ፡፡ “እድገቴን የሚያደናቅፈው ይህ ሰው ማነው? እንኳንም ሞተ! አሁን ቶሎ አድጋለው” ብለው የሚያስቡ በርካቶች ነበሩ፡፡ አስተናባሪዎች፤ ሰራተኞች አንድ በአንድ ወደ የሬሳ ሳጥኑ እንዲጠጉ እና ወደ ውስጥ እንዲያዩ አደረጉ፡፡ ሳጥኑ ውስ ያለውን ነገር ሲመለከቱ ግን በሙሉ ድንገት ዝም አሉ። በሬሳ ሳጥኑ ውስጥ የጠበቁት ሬሳ አልነበረም። በምትኩ የራሳቸውን ምስል መልሶ የሚያሳያቸው መስታዎት ነበር የተቀመጠው።
ከመስተዋቱ አጠገብ “በእድገትዎ ላይ ገደብ የማድረግ ችሎታ ያለው አንድ ሰው ብቻ ነው ፡፡ እርሱም ራስዎ ነዎት” የሚል መልእክትም በጉልህ ይታያል። ያኔ ሁሉም ሰው ወደ ልቡ ተመልሶ ስራውን በአግባቡ ይሰራል ጀመር...
***
በህይወታችን ውስጥ ለውጥ ሊያመጡ የምንችለው ራሳችን ብቻ ነን፡፡ በደስታ እና በስኬታችንም ላይ ተጽዕኖ ልናሳርፍ የምንችለው እኛው ነን። ለእኛ ከእኛ በቀር ረዳት ከየት ሊመጣል ይችላል።

አለቃችን ስለተቀየረ ፣ ጓደኞች ስለለወጥን፣ መስሪያ ቤት ስለቀየርን፣ ሕይወታችን ላይ ለውጥ አይመጣም። ራሳችንን በለወጥን ጊዜ ግን ሁሉም ለውጥ ያሳያል፡፡ ለራሳችን ላይ ምቀኛ አንሁን።

እናንብብ፣ እንወያይ ነጻ እንውጣ
#ፍቅር_አዲስ

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

• በተለያዩ ጊዜያት ሃላፊነት ይሰጠናል፡፡ በእዉነቱ ከሆነ 'የማደጎ ራእይ' በራሱ መጥፎ ባይሆንም ከሰዉ ተቀብሎ ለማሳደግ ግን በሳል መሆንን የሚጠይቅ ይመስለኛል፡፡ የሰዉ ልጅ ለሌላ ሰዉ በማደጎነት ይሰጣል...'ይህንን ልጅ አሳድገዉ' ተብሎ

• ሃሳብና ራእይም እንዲሁ ነዉ፤ አባቶቻችን በትንሹም ቢሆን ሲመግቡት የነበረዉን 'የሃሳብ ማደጎ' ለኛ አስረክበዋል፡፡ ጥሩም መጥፎም ሊሆን ይችላል...ቁም ነገሩ የተቀበልነዉ ሃሳብ ጥሩ ከነበረ የበለጠ እንዴት እናፋፋዋለን? እናሳድገዋለን? መጥፎ ከነበረ ደግሞ እንዴት ወደትክክለኛዉ መንገድ ሊመጣ ይችላል ብለን ማሰቡ አይከፋም፡፡

• የሃሳብ ማደጎ ከትዉልድ ትዉልድ ይተላለፋል፡፡ ካለበት ቦታ ሆኜ የተሻለ አሻራ አኑሮ ማለፍ የሚፈልግን ሃሳብ የበለጠ መለወጥ፣ ማስፋት ያስፈልጋል፡፡ በኛ ሀገር የህይወት ሩጫ ዉስጥ ግን ለምን እንደሆነ ባላዉቅም ይህንን ነገር አናገኘዉም፡፡

የሆነ ሃሳብ ወይም ራእይ ከሰዎች በሚሰነዘርብን ሰአት ቶሎ ብለን መጥፎዉን ጎን ማጉላት ይቀለናል፡፡'ይሄማ ፈፅሞ የማይሆን ቅዠት ነዉ...የማይመስል ሃሳብ' ምናምን እያልን እናጣጥላለን፡፡

• ሁላችንም በጊዜና በቦታ ዉስንነት የተገደብን ነን፡፡ ዛሬ ወጣት 'የነብር ጣት' የተባልነዉ ነገ ጉልበታችን ዝሎ ለሚቀጥለዉ ትዉልድ ምንም ነገር ሳናስተላልፍ 'የሃሳብ ቃሪያ የተጠቀጠቀበትን ጉርሻ' አጉርሰን ከምንሄድ ዛሬን ማስተዋሉ መፍትሄ ነዉ፡፡

አለበለዚያ 'እንቆቅልሹን ያልፈታ የትናንሽ ራእዬች ባሪያ' የሆነን ትዉልድ ደጓሚ ሆነን እንቀራለን፡፡

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን🙌

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

አይ ዕድሌ
ወግ፤ ከበእውቀቱ ስዩም

ትናንት የኮቪድ 19 ምርመራ ቀጠሮ ነበረኝ፤ ምርመራው ከባድ እንደሆነ የገመትኩት ሁለት ነርሶች እንደሚገረዝ ጎረምሳ እግሬና እጄን ጠፍንገው ሲይዙኝ ነው! ዶክተሩ አፍንጫየ ውስጥ ያንሙቴን ዋሽንት የሚያክል ነገር መሰገብኝ!( አይ ፈረንጆች አንጎላችንን በስትሮው ይመጡና አይኪዋችሁ ትንሽ ነው ይሉናል)
ተምርመራው በሁዋላ፤

“ለምርመራ ያነሳሳህ ምንድነው?" ሲል ጠየቀኝ!

“ ምልክት አይቼ ነው” አልኩት!

“ምን ዓይነት ምልክት ?”

“ እእእ አፍንጫየ አያሸትም! “

“ሌላ?"

“ሌላ የለም”

“አፍንጫህ እንደማያሸት በምን አወቅህ?”

"ትናንት ሉባንጃ አጭሼ ነበር! የጭሱ መልክ እንጂ መአዛው አልደረሰኝም"

ዶክተሩ ማስታወሻው ላይ ሞነጫጭሮ ሲያበቃ፤
“ይሄ ባንተ ዕድሜ ላይ የሚያጋጥም ነገር ነው፤ ባፍንጫ ውስጥ የሚገኘው ታህታይ - ሰርን የተባለው ክፍል ይመለጣል”

“እና ከዚህ በሁዋላ ማሽተት አልችልም ማለት ነው?”

“አይ ! የጎማ ጭስ ! የፈነዳ ሽንት ቤት ፤ የሾቀ ካልሲ፤ የሞተ አይጥ፤ እና የመሳሰለው ነገር ማሽተት ችሎታህ እስከ ዕለተ ሞትህ ድርስ ይቀጥላል ! የአበባ የዕጣንና የሽቶ መዓዛ ግን አፍንጫህ ላይ ነጥሮ ይመለሳል “

“ያፈር ሽታስ?"

“የመቃብር አፈር ከሆነ ይሸትሀል”

ትንሽ ከተካከዝኩ በሁዋላ፤

“ ችግሩ በህክምና አይስተካከልም?” የሚል ጥያቄ አስከተልኩ፤

“ ከሁለት ወር በሁዋላ ከመጣህ እንደመነጽር ያለ ነገር እንገጥምልሀለን”

“አስተማማኝ ነው?"

“ስታስነጥስ ይወልቃል! ቢሆንም ከባዶ ይሻላል”

ተሰናብቼ ልወጣ ስል፤
“ቤት ውስጥ እጣን በምን አይነት እቃ ነው የምታጨሰው?” ሲል ጠየቀኝ፤

እንዴት ያለ ጥያቄ ነው? በፒፓ እንድለው ፈልጎ ነው?

“ካገር ቤት ያመጣሁት ቆንጆ ገል አለኝ ዶክተር”( በነገራችን ላይ “ገል” የሚለውን ቃል ለመግለፅ a piece of broken vase የሚል ቃል ነው የተጠቀምኩት)

ዶክተሩ የተገረመ መሰለ፤ ከዚያ አድራሻየና ስልኬን እንደገና አረጋግጦ ሲያበቃ እንዲህ አለ፡

“አንተንና ጎረቤትህን ከኮረና በላይ የሚያሰጋችሁ የእሳት አደጋ ነው! ለማንኛውም ሰሞኑን ፖሊስ መጥቶ ቤትህን ቢያንኳኳ እንዳትደነግጥ”

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

1 "ከምንፈልገው ይልቅ የተሰጠነው ይበልጣል "

2 "ሴት ብር ትወዳለች ብሎ ሴትን ሁሉ በገንዘብ ለመግዛት የሚሞክር እሱ ጭንቅላቱ ኪስ ነው ማለት ነው"

3 " ጥበበኛ ሰው ማለት የተወረወረውን ድንጋይ መልሶ የሚወረውር ሳይሆን በተወረወረበት ድንጋይ ቤት የሚሰራ ነው "

4 " ህመም ይሁን ጤና እኔ ምን አውቄ እኔን የገረመኝ ሲከፍኝ መሳቄ"
:
5 " ፈልጌ ባጣሁት ነገር አልናደድም ፈጣሪ ከሱ የተሻለዉን እንደሚሰጠን አልጠራጠርምና"
:
6 "የሰው ቁንጅናው መልካም ባህሪው እንጅ መልኩ አይደለም"

7 "በምድር ላይ ለሚፈጠረው ችግርሁሉ መውጫ በር አለው አንዱና ዋነኛው ትግስት ነው
"

የትኛው አባባል የበለጠ ተመቻቹ?👇

👉 Comment-- @eyobreta

Читать полностью…

😍ፍቅር አዲስ💖

[ Photo ]
የተለያዩ ስራወችን ጀማሪ ተዎንያን በየጊዜው እያሰራ ይገኛል
እርሶም በዚህ ካስት ኤጀንት ላይ የሚለቀቁ ስራዎችን በማየት ከራሶ አርፎ ለወዳጆ ያጋሩ
በቅርቡ የራሱ የሆነን ፊልም ለመስራት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል
እርሶም አብረውን ለመስራት ከፈለጉ
Inbox 📩
@filacast
Join
👇

Читать полностью…
Subscribe to a channel