አትዋሹ ሀብታም ናችሁ
አንድ ድሀ ወደ አንድ ገዳም ሄዶ በዚያ ያገኛቸውን መነኩሴ አባት፡- “አባቴ ለምን በጣም ደሀ ሆንኩ ?” ብሎ ጠየቃቸው ። እርሳቸውም፡- “የምትሰጠው ብዙ አለህ እኮ ግን አላወቅከውምን ?” ብለው በጥያቄ መለሱለት ። ድሀውም፡- “የምሰጠው ምንም ነገር የለኝም” አላቸው ። እኒህ አባትም እንዲህ አሉት፡- ከማንም የማያንስ የምትሰጠው ብዙ ነገር አለህ ተመልከት፦
• ፊትህ፦ ይስቃል ፥ ይደሰታል ፣ ለኀዘነተኞች ፈገግታህን ያካፍላል !
• አንደበትህ፦ ውብ የሆኑ ቃላትን ትናገርበታለህ ፥ ታመሰግንበታለህ ፥ ሰዎችን ታበረታታበታለህ ፥ ትመክርበታለህ ፥ ታጽናናበታለህ !!
• ልብህ፦ ለመልካምነት ፥ ለእውነትና ለትሕትናን ክፍት ነው !
• ዓይንህ፦ ጎስቋሎችንና ችግረኞችን በፍቅርና በደግነት ትመለከታለች !! በኀዘን ለተዋጠው እንባን ትሰጣለች !
• እጆችህ፦ አቅመ ደካሞችን ያግዛሉ ።
ተመልከት ይህን ሁሉ መስጠት ከቻልህ አንተ ደሀ አይደለህም !!
በዚህ ዓለም ላይ ከሌላቸው ሰዎች ይልቅ ያላቸውን ያላወቁ ሰዎች ይበዛሉ ። ያለንን ካላወቅነው ያው ድሀ ነን ። ድህነት ያለው እጅ ላይ ሳይሆን አእምሮ ላይ ነው ። ሁሉም ነገር ያላቸውና ምንም ነገር የሌላቸው ሰዎች በዓለም ላይ የሉም ። ጉድለቱን ያው ባለቤቱ ብቻ ያውቀዋል ፣ ሙላቱንም ሰዎች ብቻ ያውቁታል ። የጎደልንን እኛ ስናውቀው ፣ ያለንን ግን ሌሎች ያውቁታል ። ላወቀበት ፈገግታም ሀብት ነው ። አንድ ትልቅ ባለጠጋ ናቸው ፣ ስማቸውን ብጠራ ታውቋቸዋላችሁ ። ግን ስም አይጠሬ ናቸው ። በጣም ደስተኛና ሳቂታ የሆነ ወጣት ሁልጊዜ ማኪያቶ ይሠራላቸዋል ። አንድ ቀንም ከመቀመጫቸው ተነሥተው ወደዚህ ወጣት ሄዱና፡- “ልጄ ሁልጊዜ ሳይህ ፈገግታ ሞልቶብሃል ። ያንተን ደስታ እኔ ለአንድ ቀን አግኝቼው አላውቅም ፤ እንደ ተደሰትክ ፣ እንደ ሳቅህ ኑር” ብለው ስቅስቅ ብለው አለቀሱ ። አዎ ፈገግታ ሀብትና ከሀብትም በላይ መሆኑን እኒህ ቢሊየነር መስክረዋል ።
ዝነኛ የነበሩት ፖፕ ዮሐንስ ዳግማዊ፡-። “አንድ ሰው የመጨረሻ ድሀ ቢሆንም እንኳ ለሌላው ሊሰጥ የሚችለው ነገር አለው ፤ እንዲሁም ሌላውም በጣም የተረፈው ሀብታም ቢሆንም ከሌላ ሰው መቀበል የሚያስፈልገው ነገር አለ” ብለዋል ። ይህ ዓለም ሙሉ ድሀ ነኝ ፣ ሙሉ ባለጠጋ ነኝ የማይባልበት ዓለም ነው ። እንዳንሳቀቅ የምንሰጠው አለን ፣ እንዳንኮራ የምንቀበለው አለን ። እግዚአብሔር ቅዱስ ሙላትን ፣ እንዲሁም ቅዱስ ጉድለትን በእኛ ውስጥ በማስቀመጡ ሕይወትን ውብ አድርጓታል ።
በዓለም ላይ ፈግታን የመሰለ ሀብትና ምግብ የለም ። ፈገግ ያሉልን ሰዎች ፀሐይ እንዳበሩልን ናቸው ። ፀሐይ በርቶም የጨለመባቸው ፈገግታን ሲያዩ ይደሰታሉ ። ልባቸው ኀዘን አርግዞ የሚኖሩ ፈገግታ ሲያዩ ይፈወሳሉ ። ዋጋ የለኝም የሚሉ ፈገግታ ሲያዩ ለካ አስደሳች ሰው ነኝ ብለው በራሳቸው ይኮራሉ ። ፈገግታ ከማንኛውም ስጦታ በፊት ከቀደመ ስጦታውን አስደሳች ያደርገዋል ። እውነተኛ ፈገግታ ያሳዩን ሰዎች በዘመናችን ሁሉ አንረሳቸውም ። በፈገግታ እንኳን ሰው እንስሳትም ይፈነድቃሉ ። በፈገግታ ውኃና ዛፍ ሳይቀር ይስቃሉ ። ፈገግ ስንል ቤቱ ይበራል ። የሥራው ቦታ ተወዳጅ ይሆናል ። ፈገግ ስንል ሰዎች ፈገግ ይላሉ ። የዘራነውን ወዲያው የምናጭደው በፈገግታ ብቻ ነው ። በፈገግታ ጠላትን መማረክ ይቻላል ። ላለመደሰት የቆረጠውን ኪዳኑን እንዲያፈርስ ማድረግ ቀላል ነው ። ፈገግታ መንፈሳዊነትን የሚነካ አይደለም ። መኮማተርና መኮሳተር መንፈሳዊነት ከመሰለን ተሳስተናል ። አዎ ምንም ድሀ ብንሆን ፈገግታን መስጠት እንችላለን ። በፈገግታችን የምንቀጥለው ዕድሜ አለና አበርትተን እንያዘው
።
ብዙ ኀዘን ፣ የልብም ስብራት ያለብን ፣ ቀንበር እንደ ተሸከመ የጎበጥነው ሰዎች ክፉ ተናገሩኝ ብለን ነው ። አንደበት ኃይል አለውና ይጎዳል ። ለመልካም ከተጠቀምንበት በአንደበታችን ማስደሰት ፣ መጠገንና ሰዎችን ነጻ ማውጣት እንችላለን ። በአንደበታችን እግዚአብሔርን ስናመሰግን አካባቢውን መለወጥ እንችላለን ። እኛ ስናመሰግን ሰዎች ራሳቸውን ማየት ይጀምራሉ ። ስናደንቃቸው ኃይልን ይሞላሉ ። ጥሩ ፣ ጥሩ ስንናገርላቸው በደስታ ይሰክራሉ ። በዓለም ላይ በበጎ ጎኑ ያልተጠቀምንበት ነገር ቢኖር አንደበት ነው ። አንደበት የኒውክለርን ያህል ጎጂ ነው ። አንደበት ከተጠቀሙበት ነቢይና ሐዋርያ ፣ ሰማዕት የሚያሰኝ ነው ። በአንደበታችን መልካም መናገር ተገቢ ነው ። ቀድሞ የሚዘጋው እርሱ ነውና ። ዘግይቶ ተከፍቶ ቀድሞ የሚዘጋ አንደበት ነውና መልካም ልንናገርበት ይገባል ። ምንም የምሰጠው የለኝም ማለት ስንፍና ነው ። መልካም ቃል የወርቅ ሳንቲም ነው ።
ምስኪኖችን በሙሉ ዓይናችን ስናያቸው ችግሬን አወቀልኝ ብለው ይደሰታሉ
። በአንድ የሕፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ስጎበኝ፡- “ሕፃናቱ ምን ያስፈልጋቸዋል?” ስል፡- “የሚፈልጉት የሚያያቸውና የሚያቅፋቸው ሰው ነው ። ምግብ እዚህ ይሟላል ፣ የእናት ፍቅር ግን ልንሰጣቸው አልቻልንም ። እባካችሁ መጥታችሁ እቀፏቸው” አሉኝ ። እስካሁን ይህ ድምፅ ውስጤን ያጠቀጥቀዋል ። ለማቀፍ ባለጠጋ መሆን አያስፈልግም ። ሰውን በፍቅር ዓይን ስናየው ይበረታታል ። ዓይንም ፍቅርን ያሳብቃል ። ዓይንም ይናገራል ። በዓለም ላይ በቃላት የሚገለጡ ነገሮች ጥቂት ናቸው ። ቃላት የማይችሉትን ዓይን ይገልጠዋል ። ዓይን ከተጎዱት ጋር አብራ ስታለቅስ የተጎዳው ሰው ኀዘኑን ይተዋል ። መቼም ላይረሳን በልቡ ይጽፈናል ። ከሚያዝኑት ጋር ማዘን ትልቅ ዋጋ አለው ። ለዚህ ባለጠጋ መሆን አያስፈልግም ።
በጉልበት የምናግዛቸው ብዙ ደካሞች አሉ ። መንገድ የምናሻግራቸው ዓይነ ሥውራን ፣ ገላቸውን የምናጥባቸው የአእምሮ ሕሙማን ፣ ቤታቸውን የምናጸዳላቸው ባልቴት አረጋውያን ብዙ ናቸው ። ገንዘብ መስጠት ባንችል ጉልበት ገንዘብ ነውና ያንን መስጠት እንችላለን ። ለመስጠት ፈቃዱ ካለን መስጠት እንችላለን ። እግዚአብሔር ተቀባይ ብቻ አድርጎ አልፈጠረንም ፣ መስጠት የምንችል አድርጎም ፈጥሮናል ። እባካችሁ ስጡ ።
ቀኑን ዕለተ ወርቅ ያድርግላችሁ !
/ ከሀሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰሯት በአንዲት ክብርት ቅድስት ቤተክስቲያን እናምናለን //
👇👇👇👇👇
@fkl26
@fkl00
>>>>> የድኅነታችን ምክንያት <<<<<
(ምክንያተ ድኂን)
ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምን የድኅነታችን ምክንያት ( ምክንያተ ድኂን) ማለት ይቻላል ወይ? አዎን!ይቻላል ብቻ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን፥ አዳም በኃጢአት በወደቀበት ወቅት፥ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም ከሰጠው ተስፋ አንዱ፥ የሴቲቱ ዘር የእባቡን ራስ እንደሚቀጠቅጥ ነው። ከሴት የተወለደው ( ገላ ፬፥፬) ከድንግል ማርያም የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ድኅነታችን ነው። መዳን በሌላ በማንም የለምና። ይህን አዳኝ የወለደችልን ደግሞ ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ስለሆነች፥ ምክንያተ ድኂን ትባላለች። ከእርሷ ሥጋን ነሥቶ ነውና ያዳነን። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ እንዳለው፥ «For that which He has not assumed He has not healed ጌታ ያልተዋሃደውን አላዳነውም፤» ከዚህ ጠለቅ ብለን ከሄድን ደግሞ፥ ምንም እንኳን ሰው በኃጢአት ቢወድቅም እግዚአብሔር የፈጠረው ከነጻ ፈቃድ ጋር
ነው። ይህም የሆነው እውነተኛ ኅብረት ከእርሱ ጋር እንዲኖረው ነው። በመሆኑም እግዚአብሔር እኛን ለማዳን የእኛን ፈቃድ ይጠይቃል። በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ ጣልቃ ለመግባትም የእኛን ፈቃድ ይጠይቃል። ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት እንደሚናገሩት፥ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ራሷን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ማስገዛቷና «ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ» ማለቷ፥ አካላዊ ቃል በማኅፀኗ እንዲያድር አድርጎታል። ይህ ይኩነኒ (fiat) ይህ አዎንታ፥ የአዳምን ዘር ሁሉ የወከለ አዎንታ ነው። በዚህ ምክንያት ምክንያተ ድኅኒ ( የደኅንነታችን ምክንያት) ብቻ ሳይሆን፥ ትምክህተ ዘመድነ (የባሕርያችን ( የሰውነታችን) መመኪያ) እንላታለን!!
Join 👇
@fkl26🌸
@fkl00
..........የእግዚአብሔር ታቦት........
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
እንኳን ለህዳር ጽዮን ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሠን
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
በዚህችም ቀን በፍልስጤም ሀገር የእግዚአብሔር ታቦት ድል ተቀዳጀች።
ታሪኩም እንዲህ ነው............
ታላቁ ካህን ኤሊ ክህነትን ከምስፍና አስተባብሮ በሚገኝበት ዓመት ሁለቱ የካህኑ ልጆች የማይገባ ሥራ ሠሩ።ቤተመቅደሱንም አረከሱ።በቤተመቅደሱ ያመነዝሩ ነበር።እንዲሁም ለቤተመቅደሱ የሚመጣውን መባዕ ለራሳቸው ይወስዱ ነበር።በቤተመቅደሱ የሚበራውን ሻማ ማብራት አይገባም እያሉ ያጠፉ ነበር።በዚህ ጊዜ ፈጣሪ አዘነ።ተቆጣ።ለአህዛብም አሳልፎ ሰጣቸው።እስራኤላውያንም በውጊያው ተሸነፉ።ሁለተኛም ባዶ እጃችንን ስለወጣን ነው በማለት ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወጡ።ከእስራኤላውያንም ብዙ ሰዎች ሞቱ።ሁለቱም የኤሊ ልጆች ሞቱ።እነርሱም ተሸነፉ።ኤሊም ይህንን ሰምቶ ከወንበሩ ወድቆ ሞተ።ታቦተ ጽዮንም ተማረከች።ፍልስጤማውያንም ዳጎን የተባለውን ጣኦት ያመልኩ ነበርና ታቦቱን በዚያ አኖሩት።ዳጎንንም ከላይ ታቦቱን ከሥር አደረጉ።በማግስቱ ቢመለሱ ታቦቱ በክብር በዳጎን ላይ ሆኖ አገኙት።እነርሱም ተበሳጩ።ታቦቱንም ከታች መለሱ።በሁለተኛው ቀን ቢመለሱ ታቦት በክብር ተቀምጣ ዳጎን ተሰባብሮ አገኙት።እነርሱንም በእባጭ መታቸው።በዚህም ሰኣት ፍልስጤማውያን ታቦቱን ፈርተው በታላቅ ሽልማት ሸልመው ወደ ሀገሯ መለሱ።1ኛ ሳሙኤል 5:1።
ወርዕሳችን ስንመለስ በመጽሐፍ ቅዱስ ታቦት የሚለው ቃል በብዙ ቦታ ተጽፎ ይገኛል።
ታቦት ማለትም ማደርያ ማለት ነው።ቃሉ ተጽፎበታልና።በብሉይ ኪዳን ዘመን የታቦት አገልግሎት በብዙ ሁኔታም ተገልጧል።ሀይሉም ታይቷል።የአዲስ ኪዳኑ ታቦት ግን ለብዙ ሰው ጥያቄ ነው።ይሁን እንጂ በአግባቡ አላዩትም እንጂ በአዲስ ኪዳንም ታቦት አለ።ለምሳሌ
1ኛ ቆሮ 6:16 የእግዚአብሔርን ታቦት በጣኦት ቤት የሚያኖር ማነው ይላል
ራዕ 19:11 በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ።የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ ይላል
ምን አልባት ታቦት መብዛቱ ለምንድነው ከተባለ ለአገልግሎት ይውል ዘንድ ነው።እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ማለት ነው
በቅዱሳን ስም መሰየሙም ኢሳ 56:4 አብነት በማድረግ ነው።
ስለሆነም የተወደዳችሁ የተዋህዶ ልጆች እኛ ታቦትን በመያዛችን አልተሳሳትንም።ይበልጥ ቃሉን አከበርን እንጂ።ነገር ግን ታቦትን የሚያንቋሽሹ መናፍቃን መጨረሻቸው ጥፋት ነው።እንደ ዖዛ ማለት ነው።2ኛ ሳሙኤል 6:1 ጀምሮ።
እናም ሁላችንም በታቦቱ በመጠቀም እንደ ቅዱስ ዳዊት መባረክ ይገባናል።ለዚሁም አምላከ ቅዱሳን ይርዳን!!!!!!የእመቤታችንንም በረከቷ ይደርብን።ማህበራችንን ያስፋልን።በእምነታችንም ያጽናን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር !!!!!!.........(ከመ/ር እሸቱ)...... ይቆየን
@fkl00
@fkl00
#በዘንባባሽ_ባርኪኝ
#በዘንባባሽ_ባርኪኝ አርሴማ
#የተጋድሎሽ_ዜና በአለም ተሰማ
በረከትሽ ብዙ ቃልኪዳንሽ ሀያል
ስምሽን ጠርቼ ልቤ መች ይረካል
#በጨለማዉ_ልሂድ ቢበዛ መከራ
ሁሉን አለፈዋለዉ #ስምሽን_ስጠራ
ገድልሽን ስሰማ ደነቃት ሂወቴ
#ዘንባባሽን_ይዘሽ ግቢልኝ ከቤቴ
ፀሎቴ ደረሰ ስለቴ ተሰማ
ሞገሴ ሆነሻል #እናቴ_አርሴማ
አጋንት ወደቁ ሲጠራ ስምሽ
#ልዩ_ክብር_አለሽ አምላክ የሰጠሽ
#ነይ_ተመላለሺ ግቢ ከቤታችን
#የሂወትን_ፅዋ ይዘሽ ለነብሳችን 🙏
Join @fkl26
@fkl00
#ዛፏ_አስተማረችን
#አለም_ለስጋው ያንተን ፍቅር ትቶ
#ለክብሩ_ቢጨነቅ ዋጋውን እረስቶ
ለስጋው ሲያደላ ነብሱን እየረሳ
ከትቢያ ከደይኑ ያወጣውን ከአበሳ
#ለዲያቢሎስ ተገዝቶ
#ፀጋውን ተቀምቶ
ተስፋው ጨላልሞ
በጨለማ ቆሞ
የከፈለውን ዋጋ ለአፍታ እንኳን ቢረሳ
ጠላት እያደባ ሲያጓራ እንደ አንበሳ
ምንም እንኳን ቢረሳ የአምላክ ቸርነቱ
ፈጥሮ አሳልፎ ማይሰጥ ለጠላቱ
#እየበደልነው የሚያነሳ
#ሚያስታውስ ብንረሳ
ብንወድቅ የሚያነሳን
ተርበን ያጠጣ ያበላንን
እንደ ወዳጅህ ይሁዳ ስንበድል አንተን
#ንስሃ_እንድንገባ ዛፏ አስተማረችን
#ለብዙ_ምክንያትም ወንጌል እያወጀች
መዳን አሁን ነው ብላ እየሰበከች
#አንታዘዝ ብለን አድልተን ለስጋ
#የሞታችን ጦማር ከፊት ቢዘረጋ
በሃጥያት ተጨማልቀን ቢገፈፍ ፀጋችን
በባርነት ግዞት ዲያቢሎስ ሲገዛን
በእጃችን ላይ ያለው አርነት ባርነት
#ነብሳችን_ከወዴት ከሲኦል ወይስ ገነት
#ንስሃ_ገብተን እንዲምረን በእውነት
#አምላክ_ይጠብቀን_በፍፁም_ቸርነት :: 🙏
@fkl00
@fkl26
የድንግል እናታችንን ስደት የምናስበት ምክንያት ብዙ ነው፡፡ ገብርኤል ካበሰራት በኃላ ብፅዕናዋን የሚያጎሉ ሃሳቦች ከመንፈስ ቅዱስ ይመነጩ ነበር፡፡ ልጇን በወለደች በአርባ ቀን በስምዖን አፍ የተለየ ዜና ሰማች፦ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል፡፡ ብዙ እናቶች በችግር ቀን ልጃቸውን በዘንቢል አስቀምጠው ይሸሻሉ፡፡ እርሷ ግን ከመስቀሉ ጋር ጉያዋ ሸሸገችው፡፡ ጌታን በመውለዷ ብፅዕት የሚሏት እንዳሉ የወንበዴ እና የእብድ እናት ብለው የሚረግሟት የእስራኤል ልጆችም ብዙ ነበሩ፡፡ ፈተናዋ ከተራ ሰዎች የሚመጣ አልነበረም፡፡ ከነገስታት ነበር፡፡ ሃገር ጥላ የሄደችው እንደአባቷ ሙሴ ስለክርስቶስ ነው፡፡ በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ስለርሷና ልጇ ክፉ የሚናገሩ ብዙ ቢሆኑም እርሷ ግን ሰለራስዋም ሰለልጇ ምስጢር አትናገርም ነበር፡፡ ያለጊዜው ወደመስቀል እንዳይወሰድ ዝም ማለት በተገባት ጊዜ በፀጥታ አገለገለችው፡፡ ስለልጇ መሰደዷን ያዩ ተከታዮቹ ጽናት ተምረንባታል፡፡ ስለ ክርስቶስ መሰደድን መርቃ የሰጠች እርሷ ነች፡፡ ብፅዕና ከመስቀል ጋ የተገመደ እንደሆነ አሳየችን፡፡ እመቤታችንን በደንብ እንደማናውቃት ይሰማኛል፡፡ ስለርሷ በመጽሐፍ ቅዱስ የተዘገበው ጥልቅ ትምህርት ወደ ሰው እንዳልደረሰ በሚወዷትም በማይወዷትም መረዳት ግልጥ ሆኖ ይታያል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ያሳየን መልኳ፣ የኑሮዋ መንገድ እጅግ ጥልቅ ነው፡፡ ሴቶችም ወንዶችም የሌላቸው ጸጋ አላት፡፡ ለእግዚአብሔር ሃሳብ ያላት ታማኝነት እስከመስቀሉ ቀን ጥብቅ ነበር፡፡ እናቴ ሆይ ስላንቺ እና ልጅሽ በመጻፌ ጣቶቼ እንደተባረኩ ይሰማኛል፡፡ በጽዮን ተራራ ላይሽ ናፍቃለሁ፡፡ አግኝቼሽ ቢሆን ብዙ እንድትነግሪኝ ጆሮቼን እከፍት ነበር፡፡ ከሰላሳ ዓመት በላይ ያየሽውን ስለልጅሽ የተገረምሽበትን እጠይቅሽ ነበር፡፡ የሚወዱሽ ሰዎች ምን መምሰል እንዳለባቸው ቃልሽን በጉጉት እሰማ ነበር፡፡ ከዮሴፍ ጋር ለስግደት ኢየሩሳሌም ስትወጪ ከኃላሽ እየተከተልኩ የምትናገሪውን በሰማሁ እወድ ነበር፡፡ መልካምን ያስተማሩኝ ብዙ ናቸው፡፡ ከቅዱሳን ከምትበልጪው መማር ምን አይነት ክብር ይሆን?!! በአእላፋት ቅዱሳን፣ በጻድቃን መንፈሶች፣ በበኩራት ማህበር፣ የሁሉ ዳኛ በሆነው በእግዚአብሔር አብ፣ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ከሆነ ከልጅሽ ጋር ህያው ነሽና ምርቃትሽ ይድረሰኝ፡፡ ጸሎትሽ ይብዛልኝ፡፡
በረከቷ ይደርብን
@fkl00
@fkl26
በማርያም ሼር በማድረግ ቢያንስ ድምጻችንን እናሰማ!!! የቻልን በአቅማችን ካልቻልን በአይነት እንደግፍ
•➢ SHARE "SHARE "SHARE •➢
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
ለየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ለOffice of the Prime Minister-Ethiopia
ለ ጠቅላይ ቤተክህነት
•➢ የአባታችሁ የአባታችን የአባ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ታላቅ ቦታ አሰቦት ገዳም ከነገዳማውያኑ ከሰአታት በኋላ ታሪክ ሊሆን ነው።
•➢ እሳቱ በአስፈሪ ፍጥነት ወደገዳሙ ተጠግቷል። ከገዳሙ በፊት እኛ እንጥፋ የሚሉ ኦርቶዶክሳውያን በእሳቱ ውስጥ በጭስ እየታፈኑ ራሳቸውን እየሳቱም ግብ ግብ ላይ ናቸው።
-ገዳማውያኑ በአባታችን ቦታ እሳት ይብላን አብረን እንቃጠላለን እንጂ አንሸሽም ብለው በአቋማቸው ፀንተዋል።
-መጨረሻው እየተቃረበ በመሆኑም ንዋየ ቅድሳትና ታቦታቱን ለማሸሽ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። በኛ ዘመን አይናችን እያየ የስውራኑ የግሁሳኑ ቦታ አሰቦት ታሪክ ይሁን? ከዚህ በላይ ዳግም ሞት አለ?
እንረባረብ!
በሰው ሀይል የማይጠፋ እሳት ነው ነገር ግን በጣም ከአቅም በላይ እየሆነ ነው ። ብፁዓን አባቶች በአስቸኳይ የሄሊኮፕተር ትብብር ይጠይቁ ቢያንስ ገዳሙንና ገዳማውያኑን እናትርፍ
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከዚህ በላይ አስቸኳይ ጉዳይ የለም!
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
@fkl26
@fkl00
@fkl26
✝ ሰው ወደ ኃጢአት በተራመደ መጠን ሃሳቡ ደካማ ይሆናል። ወደ ኃጢአትም ያዘነብላል። በውስጡም ለኃጢአት ሥፍራ ያዘጋጃል። ተጨማሪ እርምጃ በተራመደ ቁጥር በልቡ ውስጥ የነበረው ፍቅረ እግዚአብሔር ይቀንሳል። መውደቁም ግልጽ እየሆነ ይሄዳል። ስለዚህም በመጽሐፍ _"አንች ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው "ተብሎአል። [መዝ 136*8_9] የባቢሎን ልጅ [የምርኮ ሀገር) የተባለ ኃጢአት ነው። ልጆች የተባሉት ፈቃዳተ ኃጢአት ናቸው። እነዚህን ልጆች የተባሉ ፈቃዳተ ኃጢአት የሚፈጠፍጣቸው ዓለት የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። [1ቆሮ 10*4] ስለዚህ ኃጢአትንና ፈቃዳቱን ሁሉ በክርስቶስ አጋዥነት የሚቋቋምና በአእምሮው ሲታሰብ ጀምሮ ኃጢአትን የሚጠላ ሰው ብፁዕ ነው።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
Join @fkl26
@fkl00
#አካልህ_ምን_ይሁን
ለንሰሀ_አዘጋጅ ቀልብና ልብህን
አፍና_ከንፈርህ ፡ ይዘምር ያመስግን
አዕምሮህም ይትጋ ፡ ለጾምና ጸሎት
ጉልበትህ ትንበርከክ ለአምላክህ ስግደት።
እግርህም_ትገስግስ፡ ወደ በጎው ስፍራ
እጅህም_ይቀልጥፍ ፡ ለደግ ጥሩ ስራ
አይንህ አትቀላውጥ ፡ በኃጢአት አይቅና፡
ጽድቅን ግዛት እንጅ በውስጠ ሕሊና።
ራስክን ተቀባ ፡ የፍቅር ዘይት
ልሣንህ ይቆጠብ ፡ ሰውን ከማማት።
በወንጌል ፀሐይነት ፡ ይብራልህ_ልብህም
አይንህ_እንዳትሳብ ፡ ባብረቅራቂቱ አለም
ትከሻህ_ይደንድን ፡ መስቀል ለመሸከም።
አፍንጫህም_ያሽት ፡ በጎውን መዐዛ
በቤተመቅደስ ኑር : በፍቅር ተገዛ።
እንግዲህ ያልከትን ጠቅለል ስናደርጋት
እግዚአብሔርን አክብር፡ በመላው አካላት
ሞገስ ታገኝ ዘንድ ፡ ከአምላክ በረከት። 🙏
@fkl26
@fkl00