focus_youth | Unsorted

Telegram-канал focus_youth - 🎯focus- ትኩረት

951

@focusyouth 🎯#ትኩረትህ 🎯#በማን እና 🎯#በምን 🎯#ላይ ነው? 🎯ራዕይህ አንድ ሁለት🎯 ራዕይ የለም 🎯አላማህ አንድ ነው🎯 ሁለት አለማ የለም 🎯እይታህ አንድ ነው🎯 ሁለት እይታ የለም 🎯መድረሻህ ፍጻመህ አንድ ነው🎯 ሁለት መድረሻ እና ፍጻሜ የለም

Subscribe to a channel

🎯focus- ትኩረት

መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው
የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች
ናቸው:: ዘዳ 33:27

ይሄ ክንድ አይጎረብጥም
ይሄ ክንድ አይቆረቁርም
በዚህ ክንድ ተመቻችቶ ማረፍ ይብዛላችሁ! ይብዛልን!!


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ምንድነው እየሆነ ያለው ቆይ??🥺😭😭
እግዚአብሐሔር በመኪና አደጋ የሰውን ደም እየጠጣ ህይወት እየቀጠፈ ያለውን አውሬ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከምድሬ ላይ ይምታው ያርቀው🥺
🥺

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

“ደግሞም፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።”
— ሐዋርያት 1፥11


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ማንም ሰው በሰይጣን ግፊትና ሀሳብ ካልሆነ በቀር በራሱ ላይ ሞትን ወደ መወሰን አይደርስም ይሄን መንፈስ ጌታ ይምታው!! ወጣቱን ተስፋ እያስቆረጠ ሞትን እንዲያስቡና ራሳቸውን እንዲያጠፉ የሚገፋፋ መንፈስ በናዝሬቱ ጌታ በኢየሱስ ስም ከምድሬ ላይ ተገለበጠ‼️

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

የፍቅረኞች (Valentines) ቀን በዓል- ድብቅ ሠይጣናዊ ሴራ

-ስንቶቻችን ይሆን የቫለንታይን ቀን(የፍቅረኞች ቀን ብለን የምናከብረው)
-የሚከበርበት ምክንያትና መነሻው የምናውቀው? ወይስ ሰው ስለ አከበረውና የስልጣኔ መገለጫ መስሎን ነው የምናከብረው?

ክርስቶስ ከመወለዱ ከብዙ ክፍለ ዘመናት በፊት አረማዊ ሮማውያን የካቲት14 ማታና የካቲት 15 "የተኩላ አዳኙ"ለሚሉት ሉፐርኩስ (Lupercus) ክብር በማለት በጣኦት አምልኮ ያከብሩት ነበር። ሮማውያን ይህ በዓል ሉፐርካልያ(Lupercalia) ይሉታል። ንጉሥ ቆንጠንጢኖስ ክርስትና የሮማውያን ይፋዊ ሃይማኖት መሆኑ በማወጁ ማነኛውም የጣኦት አምልኮ እንዲቀር
ቢያስጠነቅቅም የተወስኑ ሮማውያን ሰዎች ግን በዓሉን ማክበር አልተዉም። ይህንን አረማዊ በዓል ማለትም ሉፐርካልያ የሮማው ጳጳስ ገላስዮስ
ክርስትያናዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር አደረጉ። ጳጳስ ገላስዮስ በየካቲት 15 ሲከበር የነበረው በዓል
የቅዱስ ቫለንታይን ቀን በሚል አዲስ ስያሜ የካቲት 14 እንዲከበር አደረጉ።
-እንዴት ይህ አረማዊ በዓል የቅዱስ ቫለንታይን ቀን የሚል ስያሜ ተሰጠው?
ቫለንታይን የሚል ስም በሮማውያን ዘንድ የተለመደ ስያሜ ነው።ቫላንታይን ጥንታዊው ታዋቂው ሉፐርኩስ ነው።ሉፐርኩስ በግሪካውያን ፓን(pan) ተብሎ ይጠራል።በጥንታውያን አይሁድ
( በሂብሩ) ደግሞ ባል(Baal) በሚል ስያሜ ይታወቃል።ባል በመጽሓፍ ቅዱስ ዘፍጥረት 10፡9 ላይ ታላቁ አዳኝ ተብሎ ለተገለጸው ናምሩዱ ሌላኛው መጠሪያው ነው።ናምሮድ የሮማውያን የተኩላ አዳኙ ሉፐርኩስ ነበር። በዚህ መሠረትም
የቅዱስ ቫለንታይን ቀን የአረማውያን ለናምሩድ ክብር የሚያከብሩት የጣኦት አምልኮ ነው።
ቫለንታይን የሚል ቃል ቫለንቲኑስ(valentinus) ቫለንስ ከሚል የላቲን ቃል የመጣ ነው። ቀጥተኛ ትርጉሙ ጠንካራ፣ሃይለኛ ታላቅ ማለት
ነው።ዘፍጥረት10፡9 ላይ እንደምናነበው " እርሱም በእግዚአብሔር ፊት አዳኝ ነበረ ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ፊት ሃያል አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ።" ናምሩድ የሮማውያን
ጀግና ሃይለኛ ሰው ቫለንታይን ነበር። ሌላኛው የኒምሮድ ስም ሳንክቱስ(Sancutus) ወይ ሳንታ (santa) ነው ሳይንት(saint) የሚል የእግሊዝኛ ትርጉም አለው ማለትም ቅዱስ። የሮማውያን ሉፐርካልያ በመጨረሻ ቅዱስ ቫለንታይን የሚል ስያሜ ያዘ ማለት ነው።
ጥንታውያን ሮማውያን ከባቢሎናውያን በቀዱት አረማዊ የልብ (heart) ምልክት ይጠቀማሉ። በባቢሎናውያን ባል(bal) ልብ የሚል ፍቺ ነው ያለው። በአሁኑ ጊዜ ይህ አረማዊ የልብ ምልክት ለቫለንታይን ቀን(የፍቅረኛሞች ቀን የምንለው) መገለጫ እንጠቀምበታለን።ባል የባቢሎናውያን የጣኦት ጌታ ነበር።በሌላ መንገድም ናምሩድ ወይም ቅዱስ ቫለንታይን ሳተርን ተብሎ
ይጠራል። ሳተርን የሮማ-ባቢሎን ከአባራሮዎቹ ለመሸሽ በምስጥራዊ ቦታ የሚደበቅ ጣኦት ነው።ሳተርን የሚል የላቲን ቃል ሴመቲክ
(አይሁድ) ቋንቋ ከሚናገሩ ባቢሎናውያን የተገኝ
ነው። መደበቅ፣ራስን መደበቅ የሚል ፍቺ አለው። በጥንታዊ እምነትም ናምሩድ(ሳተርን) ከአባራሮዎቹ በመሸሽ ወደ ጣልያን እንደተጓዘ ይነገራል። የአፐኒን ተራራ ስያሜው ወደ ኔምብሮድ ወይም ኒምሮድ ተቀየረ። ይህ ተራራ ኒምሮድ በጣልያን የተሸሸገበት ቦታ ነበር።ሮማም በዚ ተራራ ላይ እንደ ተመሰረተች ይታወቃል። ሮም ፈርሳ እንደገና ከመሰራትዋ 753ዓ/ዓ በፊት ሳቹርንያ (ሳተርን፡ኒምሮድ የተደበቀባት ቦታ)የሚል ስያሜ ነበራት። ኒምሮድ በዚህ ቦታ ተይዞ በፈጸመው ወንጀል
ተገደለ።በንጉሥ ቆንጠንጦኖስ ጊዜም ክርስትያናዊ ሰማዕት የሚል የውሸት ክብር ተሰጥቶት በሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን መዘከር ጀመረ። ኒምሮድ፣ባል፣ቫለንታይን፣ታላቁ አዳኝ፣ፋውኑስና ሉፐርክስ 31ኛ፣32ኛና 33ኛና ደረጃ (ዲግሪ) ላይ ያሉ ፍሪማሶኖሪዎች ከሚያመልኩት ባፎሜት(የሜንደዝ ፍየል) ጋር የሚስተካከል ነው።
እንግዲህ በሰላቢ እጆች (ኢሊሙናቲ) ሴራ ዘመናዊነት ተላብሶ ድብቅ ጣኦት የሚመለክበት የቅዱስ ቫለንታይን ቀን እኛ ደግሞ የፍቅረኛሞች ቀን በማለት እያከበርን ማለትም እያመለክን ነው።
አንድ በአል የሚከበርበትን ምክንያትና
አስፈላጊነት ሊኖረው ግድ ነው። ሆኖም የምናከብረውን በአል የምናከብርበትን ምክንያትና አስፈላጊነት ሳናውቅ ከሴሮኞች ድብቅ አላማ ማስፈጸምያ ከመሆን መቆጠብ ይበጃል
ሳታወቅ ሳታውቂ ለሰይጣን ለ 666 አታምልኩ፡፡ እባካቹ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንጠንቀቅ።


እናትህ ታስታምምሃለች እንጂ አትታመምልህም..

ኢየሱስ ግን..................


“በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።”
  — ኢሳይያስ 53፥4


     @focus_youth
     @focus_youth
     @focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

በሕይወታችሁ በፍጹም ተስፋ አትቁረጡ‼️

ሰባስቲያን ሃለር ይባላል የዶርትሙንድና ኮትድቫር ተጫዋቾች ነዉ። በ2022 በካንሰር ህመም ተጠቃ። እናም ብዙዎች አበቃለት ድጋም አናየውም በ28 አመቱ ከእግር ኳስ ተሰናበቱ አሉ። የፈጣሪ ስራ ድንቅ ነዉና የተሳካ ቀዶ ህክምና አድርጎ በ2023 መጨረሻ ከካንሰር ነፃ ነህ ተባ። ሃለር ድጋሚ ተወለደ ።
ትላንት ምሽት ሀገሩ አይቮሪኮስት ኮንጎን 1ለ0 ስታሸንፍ የማሸነፊያ ጎል አስቆጥሯል ።

በህይወት አለቀለት የተባለዉን ነገር የሚቀይር ፈጣሪ አለ🙏🙏
ምንጭ፡ ከዚሁ ከሶሺያል ሚድያ የተገኘ


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ከእናንተ እና ከነገራችሁ ጋር በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የተነካካ ሁሉ በክርስቶስ ፍቅር ይጠመድ!!!❤ amen ይሁን። እኔ አሜን ብያለለው

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ዛሬ ቤተክርስቲያን ምን ተሰበካችሁ?🥰
@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ቲቪያቹን 📺  አስተካክሉት

Frequency :  ፀሎት

Symbol Rate : የእግዚአብሔር ቃል

Polarization : ጉልበቶቻቹን በ 90 ዲግሪ በኩል ብታንበረክኩት ታገኙታላቹ

ቆይ ግን የምር የቤታቹ Tv ምስል አጥፍቶ ድምፅ ቢያቆራርጥባቹ ቁጭ ብሎ ለማየት ትዕግስት ይኖራቿል ? በእርግጠኝነት ሁላቹም ተነስታቹ ለማስተካከል ትሞክራላቹ ታዲያ በመንፈሳዊ አለምም እኮ ይሄ ብልሽት አለ... አሁን ለምን ተነስታቹ  ህልማቹን... ራዕያቹን... ከጌታ ጋር ያላቹን ህብረት ለምን አታስተካክሉትም፤ ከጌታ የሆነን ህልም አለማለምን ራዕይ አለማየት የጌታን ድምፅ አለመስማትማ Normal አታድርጉት አሁን ተነሱና ምርኳቹን አስመልሱ።


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

እኛ ሰፈር አንዱ በዓሉን ለማክበር ጧት ፣ ሙሉ ነጭ ልብስ ለብሶ፣ ነጠላ ደርቦ አምሮበት ሲወጣ አየሁት፤ ግን ምሽት 3:00 አከባቢ ድች ዉስጥ ራሱን ስቶ ተኝቷል😘😘
ምከንያቱ ምን ይሁን ???

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

#ሟር #share
«ከታቦቱ መውጣት እና የሊቃውንቱ ዝማሬ ውጪ የጥምቀት በዓል የክርስቲያናዊ ለዛው ጠፍቷል» ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
የጥምቀት በዓል ራሳችንን ለማስደሰት የአመፃ ስራ የምንሰራበት እየሆነ ነው። ጥምቀት እስካሁን ያልጠፋው ከታቦቱ መውጣት እና የሊቃውንቱ ዝማሬ ውጪ የጥምቀት በዓል የክርስቲያናዊ ለዛው ጠፍቷል። ሲሉ ዲያቆን መምህር ዮርዳኖስ አበበ ተናገሩ

አባቶቻችን "ለእግዚዓብሔር አስመስለህ ለአጋንንት አትሰዋ" ይላሉ ብዙዎቻችን ለእግዚዓብሔር አስመስለን መስዋዕት የምናቀርበው ለአጋንንት ነው።

ለምሳሌ የጌታ በዓል የጌታ ከሆነ መከበር ያለበት ጌታ እንደሚፈልገው ነው። ስከሩ፣ አዲስ ልብስ ልበሱ፣ ሎሚ ወርውሩ የሚል ህግ የለም። ኢትዮጵያዊያን የሚተጫጩት ድሮም በጥምቀት እለት ነው የሚሉ አሉ ጥምቀት መተጫጫ አይደለም። የጌታ መወለድ ዋጋ ብዙዎቻችን ገና አልገባንም። በግልፅ መነጋገር አለብን የጥምቀት ቀን ብዙ የሚዘል አለ የሚዘለው ለእግዚዓብሔር አይደለም ሲሉ ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ በጥምቀት በዓል አከባበር ላይ ያላቸውን ቅሬታ ተናግሯል።

ትውልዱን ካላስተማርነው የጥምቀት በዓል የእግዚዓብሔር መሆን ቀርቶ አሁን ከግማሽ በላይ ሄዷል የሌላ በዓል ነው የሚሆነው። ይህን ሁሉ የምናገረው ትውልዱን እንድናስተምረው ነው ይህ የማይሆን ከሆነ በበዓሉ የምናገኘው በረከት የለም መቅሰፍት ነው።

የጥምቀት በዓል ለማድመቅ ውጪ ካሉ ሰዎች ብር አሰባስብልን ብለው ጠየቁኝ! ስንት ወገን ተርቦ ሜዳ ወድቆ የጥምቀት በዓል ለማድመቅ! በዲኮሬሽን እግዚዓብሔር ደስ አይለውም፣ ጥምቀትን እንደ ድሮ በስርዓተ ቤተክርስቲያን እናክብር ከእግዚዓብሔር አውጥተን የጠላት መጫወቻ አድርገነዋል የእኔ ስራ ማስተማር ነው ከዛ ውጪ ምንም ማድረግ አልችልም ሲሉ ዲያቆን ዮርዳኖስ መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

"ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ናት፤የግለሰብ አይደለችም።ነገር ግን የሰው በሆነች ጊዜ ከክርስቶሰ ጋር ያላት ህብረት ይቆማል።

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

-"ይቆረጥምሻል?"፤ "ወጋ ወጋ ነው የሚያረግህ?"፤ "ስንት ጊዜ ሆነሽ?"፤ "ምነው ቀደም ብትል?" ፤ "ዘገየሽ እኮ እንጂ?" ሳይል የ38 ዓመቱን ጥያቄ በሰከንዶች የሚመለሰው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ቤታችሁ ገብቶ ማንም መፍታት የተሳነውን የዘመናት እንቆቅልሻችሁን ፈትቶ ያስደንቃችሁ!

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ለጵንኤል አድርሱልኝ

#ትኩረት #ትኩረት #ትኩረት

ድምጽ ስላለህ ድምጻዊ እንጂ አምላኪ(ዘማሪ) መሆን አትችልም።

መድረኩ ለእግዚአብሔር ህያው መስዋዕት ምናቀርብበት እንጂ የድምጽ ቅላጼ ምናሳይበት performance ማሳያ አይደለም። ሲቀጥል እግዚአብሔር አምልኮን በሚያይበት እይታ ማየት ጀምር አምልኮ መስዋዕት እንጂ የድምጽ ውበት አይደለም( ድምጽ አያስፈልግም እያልኩ አይደለም ) ነገር ግን የአምልኮ(የመስዋዕት) ዋናው ንጹህ ልብ እንጂ ድምጽ አይደለም ።እግዚአብሔር ጥሩ አለው ብሎ መስዋዕትህን አይቀበለውም !!

ስሰልስ አምልኮ መዝሙር አይደለም መስዋዕት ነው ነገር ግን መዝሙር አንዱ መስዋዕት ነው።

ድምጽ ካለህ ድምጻዊ እንጂ አምላኪ(ዘማሪ) መሆን አትችልም። አምላኪ(ዘማሪ) ለህያው አምላክ የተቀደስ መስዋት የሚያቀርብ የሚያውድ ነው።


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

BBC, Africa በ TB, Joshua በ ሶስት part የሰራውን ዳክሜት አይቼዋለሁ። በእርግጥ ግለስቦች (አገልጋዬች) በሰሩት ልክ በፀጋው ዙፋን ፊት ሲቆሙ እንደ ስራቸው ወይ ይፈርድላቸዎል ወይ ደሞ ይፈረድባቸዎል።

ስለዚህ ዶክመንተሪ ያሳቀኝ ነገር ግን ፤ አንድ አገልግሎቱ ጨርሶ ወደ ጌታ ወደ ሄደ ሰው መሆኑ፣ ሁለት ደሞ I am gay እያለች ስለ አገልጋዩ ሀሰተኛነት የምታወራ ሴት ያለችበት በመሆኑ፣ ሶስት የ BBCን ዘገባ ልክ እንደ እግዚአብሔር ቃል መለኪያ አርገን መከራከራችን ያስገርማል ያስቃል!!

ይልቁንም ቢቢስ እንዲሸቅል በደንብ እረድተናቸዎል። ማስታወቂያ ሰራንላቸው። እያንዳንዱ ቪዲዬ ከሁለት ሚሊየን በላይ view አላቸው

የጌታ ተከታዬች የሆንን እኛ ግን ማስተዋል እና ጥበብ ከመቼውም በላይ ያስፈልገናል። ጌታ ሊመጣ በቅርብ ነው። እየሱስ ያድናል መልክታችን ይሁን!!


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ልቤ ላይ ከሞላው ቃል...

“እነሆ፥ የምስራችን የሚያመጣ ሰላምንም የሚያወራ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ፥ አጥፊው ፈጽሞ ጠፍቶአልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍምና ዓመት በዓሎችህን አድርግ፥ ስእለቶችህን ክፈል።”
— ናሆም 1፥15



@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ዋጋህን ማወቅ ከፈለክ ምትሄድበትን ቦታ እወቅ!

   "አንድ ልጅ አባቱን ሄደና 'ዋጋዬ ስንት ነው?' ብሎ ጠየቀው። አባትም አንድ የከበረ ድንጋይ ሰጠውና 'እሄን ይዘህ ሱቅ ሂድና ስንት ነው? ሲልህ ምንም ሳትናገር ሁለት ጣትህን ✌️አሳየው አለው።' ልጅም እንደተባለው የከበረ ድንጋዩን ይዞ ሱቅ ሄደ። ባለሱቁም 'ስንት ነው?' ብሎ ሲጠይቀው ሁለት ጣቱን አሳየው፤ ባለሱቁም '2 ብር' ሲለው ምንም ሳይመልስለት የከበረ ድንጋዩን ይዞ አባቱ ጋ ተመለሰና የሆነውን ነገረው።

   "ከዛ አባትየውም እራሱኑ የከበረ ድንጋይ ይዞ ወርቅ ቤት እንዲሄድና ስንት ነው? ሲልህ ለባለሱቁ የሰጠሀውን አይነት መልስ ስጠው' አለው። ልጁም እንደተባለው ወርቅ ቤት ይሄድና 'ስንት ነው?' ሲባል ሁለት ጣቱን አሳየ። የወርቅ ቤቱም ሰውዬ '2ሺ' ብሎ ሲጠይቀው፤ ምንም ሳይመልስ አባቱ ጋ ተመለሰ። ከዛ የሆነውን ነገረው።"

  "አባትየውም ለ3ተኛ ጊዜ እራሱኑ የከበረ ድንጋይ ይዞ 'የከበረ ድንጋይ ሚሸጥበት ሂድና ለሁለቱ የመለስክላቸውን አይነት መልስ ስጥ' አለው። ልጅም የከበረ ድንጋይ ሚሸጥበት ቦታ ሄደና 'ስንት ነው?' ሲባል እንደቅድሞቹ ሁለት ጣቱን አሳየ፤ ሰውየውም '200 ሺ' አለው፥ ልጁም ምንም ሳይናገር አባቱ ጋ ተመለሰ እና የገጠመውን ነገረው። አባትም 'አየህ ልጄ ያንተ ዋጋ ሚተመነው ቦታህን ስታውቅ ነው፤ ርካሽ ቦታ ከሄድክ ያረክሱሃል፥ ውድ ቦታ ከሄድክ ውድ ነህ!' ብለው አስተማሩት።"

  🗣:- ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

#Share
እኔ የማምነው እግዚአብሔር ሃጢያተኞችን ሁሉ የሚወድ እንጂ የሰው ፊት እያየ የሚያደላ፣በሃይማኖት እና በዘር የሚከፋፍል አምላክ አይደለም::

ኢየሱስም በመስቀል ላይ ሲሰቀል ለአለም ህዝብ ሁሉ ሃጢያት እንጂ በሃይማኖት መካከል ልዩነት አድርጎ እየመረጠ አልሞተም::

የሁላችንም ጠላት ሃጢያት ነው::ምክንያቱም የሃጢያት ደሞዝ የዘላለም ሞት ነውና::

የሚገርመው ሃጢያትም ሆነ የዘላለም ሞት ሃይማኖት የላቸውም::የሰው ልጆች ሁሉ ጠላት ናቸው::

ለዚህም ነው መጽሐፍ ሲናገር "የልጁ የክርስቶስ ኢየሱስ ደም ከሃጢያት ሁሉ ያነፃናል::" የሚለው::(1ኛ ዮሐንስ 1:7)

ወንድሜ እግዚአብሔር በልጁ ሁሉን ከፍሎ ስለጨረሰልህ በእምነት ደሙን ጥራው ከማንኛውም ሃጢያትህ ያነፃሃል::

ኢየሱስ አሁንም ይወድሃል !!

pastor tesfatsyon dawit
(feb 19 2022)

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

Valentine ማን እና ምን እንደሆነ ሳታውቁ የኔ Valentine ኢየሱስ ነው የምትሉ ሰዎች እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጣችሁ።

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

እናትህ ታስታምምሃለች እንጂ አትታመምልህም..

ኢየሱስ ግን..................


“በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።”
— ኢሳይያስ 53፥4


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

እስቲ ይሄን ምን ይሉታል🤔

በሸንጎ ፊት ዳኛ ቀርቦ ፣ ለተከሳሽ እዳ መክፈል
በሚወዱት አንድያ ልጅ ፣ ከራስ ቁጣ መከላከል
ማልገባውን ለወዳጅ ፣ በምን ታምር ልጅ አረገኝ
እንደሚወደኝ በተግባር ፣ በቋንቋው ነው የነገረኝ
በክርስቶስ 1ልጁ ፣ በቋንቋው ነው የነገረኝ

...............✍ጄሪ


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

እውነትና መብት

መብት ከውቂያኖስ ይሰፋል። እንደመብት ማንም ሰው የፈለገውን ማመን ይችላል። ኃይማኖትማ፥ በሽ በሽ ነው።

እውነት ግን አንድ ብቻ ነው። እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ዬሐ 14፡6)።

Truth and right

Right extends from Oceanus. As a matter of right, anyone can believe what they want. Haimanotma, it's a shame.

But there is only one truth. He is Jesus Christ (John 14:6).
              
Seer_ayinalem


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth
/channel/boost/focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

በቃ ውጡ online ይበቃችኋል

ዳይ ወደ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ(hard copy) እና ማስታወሻ ደብተር እንዳይረሳ።


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

አንተ እጅ ላይ ካልዋለ ለምንም የማይሆን…

ያ ሰው እኔ ነኝ😭

ኢየሱስዬ


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ቲዊያቹን 📺 አስተካክሉት

Frequency : ፀሎት

Symbol Rate : የእግዚአብሔር ቃል

Polarization : ጉልበቶቻቹን በ 90 ዲግሪ በኩል ብታንበረክኩት ታገኙታላቹ

ቆይ ግን የምር የቤታቹ Tv ምስል አጥፍቶ ድምፅ ቢያቆራርጥባቹ ቁጭ ብሎ ለማየት ትዕግስት ይኖራቿል ? በእርግጠኝነት ሁላቹም ተነስታቹ ለማስተካከል ትሞክራላቹ ታዲያ በመንፈሳዊ አለምም እኮ ይሄ ብልሽት አለ... አሁን ለምን ተነስታቹ ህልማቹን... ራዕያቹን... ከጌታ ጋር ያላቹን ህብረት ለምን አታስተካክሉትም፤ ከጌታ የሆነን ህልም አለማለምን ራዕይ አለማየት የጌታን ድምፅ አለመስማትማ Normal አታድርጉት አሁን ተነሱና ምርኳቹን አስመልሱ።

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ #ሀበሻ_ቢራ 3ቱ መቶ ብር አላሉም..🙊

😠እውነትህን ነው ቀዮ🙄
Please አባባ ቀሱ እና ምእመናን መጨረሻው ደርሷል በኢየሱስ ክርስቶስ እመኑ
#ጥምቀት አንድ ናት እሷም መንፈስ ያለባት የተቀደሰች ነች🙏❤

@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ወደ ኦርቶዶክስ የማልመለስበት 10 ምክንያቶች፦
ዲያቆን ኤርሚያስ ኪሮስ

አንዳንድ ሰዎች ለምን በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ወደነበረኝ አገልግሎትና ሕይወት እንደማልመለስ ይጠይቁኛል? መልሴ "አልመለስም ነው።" መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክንያቶቼን እነሆ፦

1. ጌታ ኢየሱስ ብቻ አዳኝና አስታራቂ እንደሆነ ስለማምንና ከርሱ ውጪ እንዳልሰብክ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር 1ኛ ቆሮ 1፥23

2. መዳን በጸጋ እንጂ በሰው ጥረት እንዳልሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር ኤፌ 2፥1

3. ልጅነት በእምነት እንጂ በ40 እና 80 ቀን ጥምቀት እንደማይገኝና ጥምቀት ያመኑ ሰዎች ብቻ የሚፈጽሙት ስርአት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር። ዮሐ 1፥12

4.የጌታ እራት(ቁርባን) የሞቱ መታሰቢያ ከክርስቶስና ከአማኞች ጋር ህብረት የምናደርግበት ስርአት እንጂ ሀጥያትን የሚያስተሰርይ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለማያስተምር ማቴ 26፥26

5. እግዚአብሔር ኃጥያታችንን ለማስተስረይ በልጁ ደም ኪዳን እንደገባ እንጂ ለየትኛውም ፍጡር ቃልኪዳን እንደገባና የፍጡርን ምልጃ እንደሚቀበል መጽሐፍ ስለማያስተምር ዕብ - 8

6. ስግደት ለእግዚአብሔር እንጁ በእጅ ለተቀረጸ ምስል (መስቀል ታቦት ስዕል) እንድንሰግድ መጽሐፍ ቅዱስ ስለማያስተምር ሐዋ 7፥29

7.መዝሙር የሚገባው እግዚአብሔር እንጂ ፍጡራን እንዳልሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር መዝ 9፥11

8. በየቀኑ በልባችን ጌታ ኢየሱስ ብቻውን እንዲነግስ እንጂ ቀን ተመድቦላቸው ፍጡራን እንዲነግሱ መጽሐፍ ቅዱስ ስለማያስተምር ቆላ 2፥16

9.ጸሎት በኢየሱስ ስም ወደእግዚአብሔር እንጂ ወደ ፍጡራን እንዳልሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር ዮሐ 16፥24

10. ሰዎች በህይወት ዘመናቸው በኢየሱስ በማመናቸው ምክንያት እንደሚድኑ እንጂ ከሞቱ በኋላ የሚኖር ፍትሀት እንደማይጠቅም መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር ዮሐ 3፥16

አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ፤ እኔም እጅግ ተቸገርሁ።
መዝ 116፥10


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ዛሬ በቸርች ምን ተሰበካቹ.....

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

BBC News Africa ላይ ቀርባ ነብይ ቲቢ ጆሽዋ የእግዚአብሔር ሰው አይደለም ብላ የመሰከረችው Sihle sibisi ልጇ በድንገት እንደሞተችባት ተናገረች። ያሳዝናል እግዚአብሔር ምሕረት ያድርግልን! #ትኩረት

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

እውነተኛው እረኛ "በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ" እንጂ ያለው BBC,CNN ይሰማሉ አላለም። ከBBC ከዲያብሎስ አፍ እውነትና ፅድቅን እንዴት ትጠብቃላችሁ።#ንቁ።

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…
Subscribe to a channel