focus_youth | Unsorted

Telegram-канал focus_youth - 🎯focus- ትኩረት

1046

@focusyouth 🎯#ትኩረትህ 🎯#በማን እና 🎯#በምን 🎯#ላይ ነው? 🎯ራዕይህ አንድ ሁለት🎯 ራዕይ የለም 🎯አላማህ አንድ ነው🎯 ሁለት አለማ የለም 🎯እይታህ አንድ ነው🎯 ሁለት እይታ የለም 🎯መድረሻህ ፍጻመህ አንድ ነው🎯 ሁለት መድረሻ እና ፍጻሜ የለም

Subscribe to a channel

🎯focus- ትኩረት

በባዶነቴ አግኝተኀኛል😭😭🙏❤️
የአንተ እኔን መውደድ ያስገርመኛል
አወዳደድህ ከመውደድ ያልፋል
ወደድኩህ ብልህ ምን ያስገርማል


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ጽድቅ እየተሰበከ፥ ጽድቅ የሌለበት ቤት

"ምግብ ቤት" ተብሎ ምግብ የሚሸጥበት፣ "ዳቦ ቤት" ተብሎ ዳቦ እሚቸበቸብበት፣ "ሥጋ ቤት" ተብሎ ሥጋ እሚቆረጥበት፥ "ወተት ቤት" ተብሎ ወተት እሚቀዳበት፣ "ሽሮ ቤት" ተብሎ ሽሮ በዓይነት እሚንደከደክበት ቤት መግኘት ጽድቅ ነው።

"ቤተ መጻህፍት" ተብሎ መጻህፍት የተከማቹበት፣ "ቤተ መንግስት" ተብሎ መንግስት ያለበት፣ "ቤተ መዘክር" ተብሎ እሚዘከር ነገር የያዘ ተቋም፣ "ቤተ ደናግል" ተብሎ ክብራቸውን የጠበቁ የተሰበሰቡበት፣ "ቤተ ክህነት" ተብሎ የካህናት መናኽሪያ የሆነ፣ ቤተ ክርስቲያን" ተብሎ ክርስትያኖች ያሉበትን ቦታ ማግኘት ጽድቅ ነው።

ነገሩ ግን እንዲህ የሆነ አይመስለኝም። እንዳይሆን፥ እንዳይሆን ነው። ጽድቅ እሚሰበክበት ቤተ ክርስትያን ጽድቅ ተርቦና ተጠምቶ ዓመፅ ነግሶበታል።

"ሰነፍ በታላቅ ማዕርግ ተሾመ፥ ባለጠጎች ግን በተዋረደ ስፍራ ተቀመጡ። ባሪያዎች በፈረስ ላይ ሲቀመጡ መሳፍንትም እንደ ባሪያዎች በምድር ላይ ሲሄዱ አየሁ።" አለ መጽሐፍ (መክ 10፡6-7)።

"ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም" (ራዕ 6:10)

ሲር አይናለም


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

#ጸጋ ብቻ
#እምነት ብቻ
#መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ
#ክርስቶስ ብቻ
#ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ወዳጅ
------------------------

ማንኛውም ሰው ማንነትክን ከልብ ተከታትሎ ሲያውቅህ ግን፥ ወዳጅህ ሆኖ ይቀራል። በዚህ ዘመን "የራስ" የሚባል ሰው የሚጠፋው፥ ሁሉም ላይ ላዩን ስለሚጋልብ ነው። እግዚአብሔርም ቢሆን የራስህ የሚሆነው፥ በችግሩ አብረኽው ስለቆምክ ሳይሆን የእውነት አጥብቀህ፥ ስትፈልገው፣ ስትከታተለውና ስታውቀው ነው። በግልቢያ (ላይ ላዩን) ብትሄድ አታገኘውም።

አብዛኛው ሰው እንደ ፊሊጶስ ነው፥ አብሮህ ኖሮ ኖሮ፥ አያውቅህም። "ኢየሱስም አለው። አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን?" (ዮሐ 14:9)። ሰው በክፉውም ሆነ በደጉ ዘመን አብሮህ ሲጓዝ ኖሮ ዛሬም ማን እንደሆንክ አያውቅህም።


      seer Ayenalem

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

#ጨለማ_በጨለመ_በበረታ_ጊዜ_
ከዋክብት_እና_ጨረቃ_ውበታቸው_እየወጣ_ድምቀታቸው_እየጨመረ_ይሄዳል
#ለምድር_እንዲታዩ_ጨለማውን_እንደ_ግብአት_ይጠቀሙበታል‼️

- በህይወታቹ ላይ በሚመጣ ጨለማ አትውደቁበት አቅማቹን ፣ ሃይላቹን፣ ማንነታቹን በመግለጥ የጨለማውን አመጣጥ እና አላማውን ቀይሩበት‼️

#ምክንያቱም👇👇

“እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።”
— ሮሜ 8፥28


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

the word

🎯እግዚአብሔር መልካም እንደሆነ ህይወታቹ ይመስክር❗️

🎯በእውነት እግዚአብሔር እንደሚምር ፤ እንደሚለውጥ ህይወታቹ ፤ ይመስክር ህይወታቹ ይናገር
‼️

🎯Let your life testify that God is good

🎯 God truly loves; that his life will change; Let his life speak

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

በውስጤ_በሞላው_ድምጽ_ልባርካቹ--
---------------------------
------------------------------------
🎯እግዚአብሔር አምላክ በእጃችሁ ስራ ሁሉ በመንገዳቹ ሁሉ ድልን ይስጣችሁ!!

በጌታ በኢየሱስ ስም ዳዊት ከእግዚአብሔር ጋር ሆኖ ከእግዚአብሔር አብሮነት የተነሳ የእስራኤልን ህዝብ በፍርሃት የሞላውን ጎሊያድን ጥሎ አሸንፎ ድል ነስቶ ለእስራኤል እረፍት እንደሆነ ..ለእናንተም በሚዋጋችሁ ጠላት ላይ በፈራህበት ጉዳይ ላይ እግዚአብሔር ድልን ይስጣችሁ ጠላታቹ ፈጽሞ ይውደቅ መልካም ነገራችሁን የሚቀማ ክፉ መንፈስ በፊታችሁ ይውደቅ አሸናፊነት እና ድል የእናንተ ይሁን ከጌታ አብሮነት የተነሳ ለብዙዎች ማረፍ እና ድል መንሳት ምክንያት ሁኑ!!!
🎯አሜን!

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

#ዳግማይ_ትንሳኤ?
የዛሬዋን ቀን የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን "ዳግማይ ትንሳኤ" ብለው ያከብሩታል። እኔ ደግሞ እነዚህን ሁለት ጥያቄዎች ልጠይቃቸው እፈልጋለሁ።
#የመጀመሪያው ክርስቶስ ዳግመኛ (ሁለተኛ) ተነስቷል ወይ? #ሁለተኛው ጥያቄ ትንሳኤን ስታስቡ ምንድር ነው የምታስቡት?

ለሁለቱም ጥያቄዎች የእኔ አጠር ያለ መልስ።
1. ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን አንዴ ከተነሳ በኋላ በኑሮ ዕለት ዕለት የሚገለጥ ሕይወት ሆኗል ዳመኛ አልተነሳም።

2. እንዲሁም የክርስቶስን ትንሳኤ ተሻግረን በደልና ኃጢአትን የምናስብ ከሆነ ክርስቶስ ከሙታን አልተነሳም እኛም አብረን አልተነሳንም ማለት ነው። (ሮሜ 6:4-5) ይነበብ። ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን ሲነሳ በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ ከእርሱ ጋር አብረን ተነስተናል። በመሆኑም ክርስቶስ በሞቱ ያልሻረውና ያላስወገደው ምንም በደልና ኃጢአት ስለሌለ ከትንሳኤ በኋላ ማሰብ ያለብን አዲስ ሕይወት እንጂ በደልና ኃጢአት አይደለም።
#Josef_demissie

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ኢየሱስ ከሙታን በመነሳቱ በአዲስ ህይወት እንድንመላለስ ከእርሱ ጋር አስነስቶናል። ከዛሬ ጀምሮ አሮጌው ነገር ሁሉ ከህይወታችሁ ላይ አልፏል ፤ እነሆ ሁሉ አዲስ ሆኗል። ብሩካን ናችሁ!!

መልካም የትንሳኤ በዓል!!

Through the resurrection of Jesus Christ from the dead, we have raised with Him so we too might live and behave in newness of life. Therefore, since today the old has passed away from your life. Behold, the fresh and new has come! You're blessed!!

Happy Passover!!


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

“ይህን ስለቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ፤”
— 2ኛ ቆሮ 5፥14


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

/channel/dawitademasu6710

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

24 ሚሊዮን....❌❌❌❌

አንተ ሰውዬ.....

.....ሰውዬው እኮ የቤቱን ሳይሆን የቤተ ክርስቲያኑን እስክሪን ነው በውድ ዋጋ ያስተከለው:: እዛ ግቢ 24 ሚሊዮን የሚያወጣ ንብረት እኮ ሌላም አለ:: የተገጠመው እስክሪን ሲሆን ሀጢያት ነው እንዴ? ምን ሆኖ ነው ግን ጩኸትህ ዝም ብሎ የሚጮኸው?

ሰው ከቤቱ ሲሰርቅም ለቤቱ ሲሰጥም ነቅፈን እንዘልቀዋለን እንዴ? ......."ስንት የተራቡ እያሉ ይሔ ሁሉ ገንዘብ እንዴት? ምናምን....." የሚለው ምክኒያትህን ለሁሉም ጉዳይ ነው እንዴ የምትጠቀምበት? 🧐 ይሁዳ ሆይ!ይህንንስ የተናገርከው ሌባ ስለ ሆንክ ነው እንጂ ለድሆች ተገደህላቸው አይደለም ብለን እናስብን?

እናት ቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል ሚሊዮኖችን አፍስሳ የተዋበ ቤተ ክርስቲያን ስትሰራ ድሆች አልታይ ብለዋት ይመስልሀል? ቀኝ እጇ ሲሰጥ አንተ ግራ እጇ እንዳታይ ብላ እንጂ:: እንዲሁም ማምለኪያ ስፍራውም ይዋብለት ብላ እንጂ!

እዚህም እንደዛው ነው:: ለእግዚአብሔር ሲሰጥ (ለቤቱ ሲደረግ) ይነገራል ታዘን እንጂ እግዜራችን ቸግሮት አይደለምና:: ሰሚውንም ያበረታታልና:: ደግሞኮ ለድሀ ካናቴራ ስትሰጡ ካሜራ አታምጡ አልክ እንጂ ለሀብታሙ እግዚአብሔር ስትሰጡ ይሄን ጉድ በሚዲያ አታውጡ መቼ አልክ?😡

ወንድሜ እዩ ጩፋ ወንጌል ሲሰብክ “ጎሽ” ብለኸውስ የማታውቀው አንተ “ካንጋሮ" ስለሆንክ ይሆን እንዴ? ኧረ እንደው በፈጠራችሁ ለእርሱ👆 እና ለኪስ👇 የተደረገን ነገር እየለያችሁ ምቱ እንጂ ደበላለቃችሁት እኮ .....አይይይይይይ🥲

ስንት ከፍሎኝ ይሆን?😂😂😂
ዳጊ ጥላሁን


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

የተደረገልህ የእውነት ሲገባህ
"ጌታ ሆይ ይህን አድርግልኝ ይህን ስጠኝ"ማለቱን ታቆምና
"ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ"
ብለህ የእርሱን ፈቃድ ለማድረግ ትተጋለህ።

#Eftah_eftah

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

➤ክርስትና ከአገልግሎት ያልፋል
➤ክርስትና ከንግግር ያልፋል
➤ክርስትና ጥቅስ ከመደርደር ያልፋል

➛ክርስትና ማለት ስለ ክርስትና መስበክ አይደለም
➛ክርስትና ክርስትናን መተረክ አይደለም

➛ክርስትና ክርስቶስ በክርስቲያን የሚኖረው ኑሮ፣ህይወት ነው

🎯ህይወት መኖር ነው

ህይወት አይተረክም
ህይወት አይሰበክም
ህይወት አይኮረጅም

➤ ህይወት ይኖራል
➤ህይወት ማለት መኖር ነው በቃ

በሞት ሳይሆን በህይወት ኑሩተ

ህይወት ክረስቶስ ነው
‼️

“ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው።”
— ቆላስይስ 1፥27

ክርስቶስ በውስጡ ያለው ሰው በህይወት አለ።
ክርስቶስ በውስጡ የሌለው ሰው በሞት ይኖራል ።

በህይወት እንኑር.....


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

Sola - ብቻ

ሶላ (Sola) የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ብቻ" እንደማለት ነው። በውስጡም "ተጨማሪ የሆኑ ነገሮች አያስፈልጉም" የሚልን መልዕክት አዝሏል።

በፕሮቴስታንት ተሐድሶ ወቅት የተሐድሶ መሪዎች ከመጽሃፍ ቅዱሱ የወንጌል እውነት ፈቀቅ የተባሉባቸውን በርካታ ጉዳዮችን አንስተው ሞግተዋል። "አምስቱ ብቻዎች" | "The five solas" | በመባል የሚታወቁት ሃሳቦችም የተሐድሶውን አጠቃላይ አሳብ በአጭሩ ማንጸባረቅ የቻሉ አንኳር ነጥቦች ነበሩ።

አምስቱ ብቻዎች ("The Five Solas") በመባል የሚታወቁት ነጥቦች  አጋዥም ሆነ ጭማሪ የማያስፈልጋቸውን አምስት የክርስትና አንኳር ሃሳቦችን የሚገልጹ ሲሆኑ እንደአንድ አማኝ ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው  የተገቡ መሰረታዊ የክርስትና እውነቶች ናቸው።

እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፡ -

1 -በጸጋ ብቻ | Grace Alone | Sola Gratia01.

“በበደላችን ሙታን ሆነን ሳለ፣ በክርስቶስ ሕያዋን አደረገን፤ የዳናችሁት በጸጋ ነው።”
ኤፌሶን 2፥5 (አዲሱ መ.ት)

02. በእምነት ብቻ | Faith Alone | Sola Fide

“ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ፣ ሕግን በመጠበቅ እንደማይጸድቅ እናውቃለን። ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን፣ በክርስቶስ በማመን እንጸድቅ ዘንድ እኛም ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል፤ ሕግን በመጠበቅ ማንም አይጸድቅምና።”
ገላትያ 2፥16 (አዲሱ መ.ት)

03. በእግዚአብሔር ቃል ብቻ | Scripture Alone | Sola Scriptura

“ከሕፃንነትህም ጀምረህ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዐውቀሃል።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥15 (አዲሱ መ.ት)

04. • በክርስቶስ ብቻ | Christ Alone | Solus Christus

“ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”
ዮሐንስ 14፥6 (አዲሱ መ.ት)

05. ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ | For the Glory of GOD Alone| Soli Deo Gloria

“ሁሉም ከእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።”
ሮሜ 11፥36 (አዲሱ መ.ት)

• በፀጋ ብቻ
• በእምነት ብቻ
• በክርስቶስ ብቻ
• በእግዚአብሔር ቃል ብቻ
• ለእግዚአብሔር ክብር  ብቻ.

#hanna_tekle
@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ካንተ (ከኢየሱስ) ወዴት ሊኬድ?!

1. ጥበብ ቢባል---የሚሻሩትን የዚህችን ዓለም ጥበብ የሚያስንቅ ከየትኛውም ስመ ጥር የትምህርት ተቋማት የማይገኝ ሰማያዊ ጥበብ የሚቀዳብህ የጥበብና የዕውቀት ሁሉ መዝገብ አንተ!

2. ብልጥግና ቢባል----ምንጭህ ዝንተ ዓለም የማይነጥፍ እውነተኛ የሰው ልጅ አንጡራ ሃብት አንተ!

3. እርካታ ቢባል........ሲያሻህ ከጭንጫ ድንጋይ ማር አፍልቀህ ሲያሻህ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ምድረ በዳውን አጥግበህ እሱም ሳያንስህ በቀኝህ ባለው የዘላለም ፍስሃ ነፍሳችንን አምነሽንሸህ የምታኖራት እውነተኛ የእርካታ ምንጭ አንተ!

4. ክብር ቢባል........እስትንፋስህን በአፍንጫው እፍ ብለህበት እንጂ: ደሞ ከአፈር የተሰራ የሰው ልጅ ከአንተ ውጪ ምን ክብር አለውና? የክብር ዘውድ የማዕረግ አክሊል አንተ!

5. ተስፋ ቢባል----ለህያው ተስፋ: ለማይጠፋ እድፈት ለሌለበት ለማያልፍም ርስት እንደ ምህረትህ ብዛት የጠራኸን አንተ!

ኧረ ምን በወጣን እቴ!........እንዳማረብን አንተው ጉያ ውስጥ ሽጉጥ!


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ዛሬ አድስ ቀን ነው

ትናንት ተመልሶ አይመጣም ትናንትን ተወው አዲስ ነገር የለውም ይተርክልሃል እንጂ
#ነገህን አይነግርህም!

🎯 ይልቅ ዛሬን ተጠቀም ለመኖር ዛሬ ብቻ እንዳለ ዛሬን የምር ፣ የእውነት ኑር‼️

🎯ዛሬ ላንተ የተሰጠች እንድትሰራባት ፣ እንድታገልግልባት ፤ እንድታመሰግንባት

🎯ትኩረት አርግ ዛሬን ያልኖረ ነገን አያይም ነገን ለማየት ቀነገው ቀን ህያው ሆኖ ለመድረስ ዛሬህን የምር ተጠቀመው‼️
የራዕይ ቀን


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

እየተፎካከርን ያለነው ሰው ካለ አደጋ ውስጥ ነን!
Dawit getachew

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

#መልካም #የአርበኞች #ቀን
የሚወደን የፍቅር አርበኛ ስለ እኛ ተዋጊ፡ ጦረኛ፡ በጎልጎታ ሜዳ ታሪክ ሰርቶ ያለፈ: ለእኔ እና ለእናንተ ነጻነት ሕይወቱን የሰጠ: አርነት ያወጣን ኢየሱስ ነው። ኑ ወደ ኢየሱስ ነፃነት ያለው በእርሱ ነው።
“በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ " ገላትያ 5፥1


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

🎯ከእውነት ጋር ደስ ይበላችሁ ፍቅር እርሱ ነውና ‼️

- የውሸት ጤንነት እስከ እውነት መጸነስ ድረስ ነው።

-የውሸት ህይወት እስከ እውነት መወለድ ድረስ ነው

-እውነት ሲጸነስ ውሸትክፉኛ ትታመማለች!!

-እውነት ሊወለድ የምጥ ለቅሶ ሲጀመር ውሸት ለሞት የሲቃ ለቅሶ አሰምታ ትሞታለች!!

-እወነት ሲወለድ የውሸት ህይወት በቀብር ይፈጸማል!!


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

🎯# ስለእኔ_የእኔ_እምነት

🎯የኔም ነው የሚል
#አሜን ይበል
👇👇👇👇👇👇👇

🎯መልካም ነገሮች ሁሉ ይገቡኛል ምክንያቱም እኔ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ።

🎯የማገኘውን ሁሉ የማገኘው ስለሚያስፈልገኝ እንጂ እኔን ስለሚያክል አይደለም። ራሴን ከነገሮች ጋር አላነጻጽርም!

🎯 እኔ ልጅ እንጂ ባሪያ አይደለሁም
🎯እኔ በዚህ አለም እንጂ ከዚህ አለም አይደለሁም!!

🎯 እኔ የተከፈለልኝ ዋጋ አክላለሁኝ ወጋዬ በእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ነው።

🎯ስለዚህ ሀጥያት በእኔ ዘንድ የረከሰ ነው በእኔ ሊያድር አይችልም ምክንያቱም እኔ የእግዚአብሔር መቅደስ ነኝ ።



@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ሀይማኖተኛ የማልሆንበት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክንያቶቼን እነሆ

1. ጌታ ኢየሱስ ብቻ አዳኝና አስታራቂ እንደሆነ ስለማምንና ከርሱ ውጪ እንዳልሰብክ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር 1ኛ ቆሮ 1፥23

2. መዳን በጸጋ እንጂ በሰው ጥረት እንዳልሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር ኤፌ 2፥1

3. ልጅነት በእምነት እንጂ በ40 እና 80 ቀን ጥምቀት እንደማይገኝና ጥምቀት ያመኑ ሰዎች ብቻ የሚፈጽሙት ስርአት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር። ዮሐ 1፥12

4.የጌታ እራት(ቁርባን) የሞቱ መታሰቢያ ከክርስቶስና ከአማኞች ጋር ህብረት የምናደርግበት ስርአት እንጂ ሀጥያትን የሚያስተሰርይ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለማያስተምር ማቴ 26፥26

5. እግዚአብሔር ኃጥያታችንን ለማስተስረይ በልጁ ደም ኪዳን እንደገባ እንጂ ለየትኛውም ፍጡር ቃልኪዳን እንደገባና የፍጡርን ምልጃ እንደሚቀበል መጽሐፍ ስለማያስተምር ዕብ - 8

6. ስግደት ለእግዚአብሔር እንጁ በእጅ ለተቀረጸ ምስል (መስቀል ታቦት ስዕል) እንድንሰግድ መጽሐፍ ቅዱስ ስለማያስተምር ሐዋ 7፥29

7.መዝሙር የሚገባው እግዚአብሔር እንጂ ፍጡራን እንዳልሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር መዝ 9፥11

8. በየቀኑ በልባችን ጌታ ኢየሱስ ብቻውን እንዲነግስ እንጂ ቀን ተመድቦላቸው ፍጡራን እንዲነግሱ መጽሐፍ ቅዱስ ስለማያስተምር ቆላ 2፥16

9.ጸሎት በኢየሱስ ስም ወደእግዚአብሔር እንጂ ወደ ፍጡራን እንዳልሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር ዮሐ 16፥24

10. ሰዎች በህይወት ዘመናቸው በኢየሱስ በማመናቸው ምክንያት እንደሚድኑ እንጂ ከሞቱ በኋላ የሚኖር ፍትሀት እንደማይጠቅም መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር ዮሐ 3፥16

አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ፤ እኔም እጅግ ተቸገርሁ።
መዝ 116፥10

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

12 የዶሮ ብልቶች የ12ቱ ደቀመዛሙርት ምሳሌ ነው፣ 3 ምድጃ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው የሚሉ መምህር መጥተዋል ብዙዎችም በዚህ ሲስቁ አይተናል😭 ይህ ያስለቅሳል እንጅ አያስቅም ጎበዝ ምድሪቷ በተረት ተሞልታለች::
ወንጌል ገና በምድራችን አልተሰበከም
☹️

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

He is risen

ኢየሱስ_ተነስቷል

🎯ከሙታን መካከል የለም አሁን ህያው ሆኖ እኛን ይዞ በአብ ቀኝ ከብሯል

እስኪ በዚህ ምሽት በቴሌግራም ላይ "ተነስቷል'' በማለት ትንሳኤውን እናውጅ....


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ልጇን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ ሲቀበል “የማርያም ጠላት!” አሉት🤔🤔🤔 ልጄን ተቀብለውልኝ ጠላቴ እንዴት ይሆናሉ? የሰቀሉት ወዳጆቹ ናቸው እንዴ እናንተ?🤨

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

በህይወቴ ከጠቀመኝ የህይወት መርህ....

አሁኑኑ join በማድረግ ለ ክርስቲያን ወጣቶች ከተዘጋጀው መልዕክት ይጠቀሙ

👇👇👇👇👇
@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ተወዳጆች ሆይ:

የሰማይ አምላክ በትውልዱ ላይ መልካምን አሻራ ጥላችሁ የምታልፉበትን ጥበብ ይስጣችሁ!

በምሬት በተሞላች ምድር ላይ ከህይወታችሁ የእግዚአብሔር መልካምነት ይቀዳ!

ከጓዳችሁ የመድሃኒት ምንጭ ይፍለቅ!

ሰዎች ወደ እናንተ ጠጋ ብለው የክርስቶስን መዓዛ የሰማይን ጠረን ሳያሸቱ አይመለሱ!

እወዳችኋለሁ!!
Dr lealem tilahun


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ካነበብኩት....

ተነስቷል!!
---------------------
---------
እኔ እሞታለው - ደግሞም እነሳለው
ያለው ትዝ ብሏቸው - መቼ ተረጋግተው
ተመካክረው ገለው - አፈር ገባ ብለው
ተደርጎ የማያውቅ - መቃብር ሲጠበቅ
ኢየሱስ ተነስቷል  - አልም ሁሉ ይደነቅ::

እልልልልል እርሱ አሁን ህያው ነው
‼️ አሜን

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

አጋንንት በኢየሱስ ስም ይወጣል
ፈውስ በኢየሱስ ስም
ህይወት በኢየሱስ ስም
ጸሎት በኢየሱስ ሰም
መዳን በኢየሱስ ስም
ስብከት በኢየሱስ ስም
መኖር በኢየሱስ ስም
ክርስትና በኢየሱስ ስም
መዝሙር በኢየሱስ ስም

“እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።”
— ቆላስይስ 3፥17


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ቤተክርክርስታያን ህብረት ለማድረግ ለመገልገል የሚመጡ ህፃናት ወጣቶችና በእድሜ የገፉ አባቶች እና እናቶች ያሉባት ትልቅ ጉባዔ ናትና እኛ አገልጋዬች መድረክ ላይ የምንጠቀማቸውን ቃላቶች አክብሮትን የሚያሳዩ ሰሚዎችን የሚያንፁ ቃላቶች ይሁኑ እላለሁ::
ከነዚህም ቃላቶች መካከል:-
  * አንተ
  *ምን ታየኛለህ
  * አሜን አትለኝም
  * ካልፈለክ ውጣ
  * መሬቱን ልቀቀው
  * የቀረውን እናንተ ኮሜንት ላይ አስቀምጡ ደግሞም ሼር በማድረክ የቤተክርስቲያንን የቃላት አጠቃቀም እንለውጥ!!!

#agabe_love

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…
Subscribe to a channel