focus_youth | Unsorted

Telegram-канал focus_youth - 🎯focus- ትኩረት

1046

@focusyouth 🎯#ትኩረትህ 🎯#በማን እና 🎯#በምን 🎯#ላይ ነው? 🎯ራዕይህ አንድ ሁለት🎯 ራዕይ የለም 🎯አላማህ አንድ ነው🎯 ሁለት አለማ የለም 🎯እይታህ አንድ ነው🎯 ሁለት እይታ የለም 🎯መድረሻህ ፍጻመህ አንድ ነው🎯 ሁለት መድረሻ እና ፍጻሜ የለም

Subscribe to a channel

🎯focus- ትኩረት

#ጉድ_እኮ_ነው!!🙊🙆

✍️ I stand with......!!
*
I stand with...........አንድ አንድ አማኝ ወገኖቼ ጥያቄ አለኝ🙋🙋..........የገባችሁ ወንጌል ምን አይነት ነው?

Pray for Israel.....ክርስቲያኖች ሆይ የፍልስጤም አምላክ ይወዳችኋል!!

ቆይ ግን.....

✍️የእስራኤል ወዳጅ የፍልስጤም ጥላት ያደረጋችሁ የትኛው ወንጌል ነው?

✍️ ለእስራኤል ድል ለፍልስጤም ሽንፈት ያስመኛችሁ ወንጌል የትኛው ነው? እናንተ የሰላም መልዕክተኞች!!

አልገባችሁም ወይስ አልገባኝም?

✍️በበኩሌ ያመንኩት ወንጌል ገብቶኛል!! የእናንተ ግን አልገባኝም!!

✍️ ለእስራኤል ብቻ የሞተ ኢየሱስ የለም!!
እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ አይደለም.......አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነው!! ኢየሱስ ለሁሉም ነው የሞተው!!

✍️ደግሜ እላለሁ ለአለም የመጣውን ክርስቶስን ለሀገር አትስፋው!!

✍️በዚህ ዘመን ከእስራኤል ጋር ኪዳን ያለው እግዚአብሔር የለም!!

✍️ አሁን እስራኤል የእግዚአብሔር ልዩ አይደለችም!!

✍️ሰውን ሁሉ በክርስቶስ እይ!! ኢየሱስ መስቀል ላይ የተቸነከረውና ራሱን አሳልፎ የሰጠው አለምን ሊያድን እንደሆነ አስብ!!

✍️እግዚአብሔር በክርስቶስ ከመሆናችን ውጭ በተለየ ሁኔታ አያየንም!!

✍️አሁን የሚያስፈልገው ወንጌል ነው....ወዳጆቼ ሰዎች ስለክርስቶስ ሳይሰሙ እንደ ቅጠል እየረገፉ እንደሆነ አስተውላችኋል? ካልሰሙ እንዴት ያምናሉ ያለሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ? ያገኘነውን አጋጣሚ ሁሉ ኢየሱስን ለማውራት እንጠቀምበት!!

✍️ላለንባት የእንግድነት ሀገር በሽታ መፍትሔው የመጣንበት ሀገር መድኃኒት ነው........እሱም ኢየሱስ ይባላል!!

✍ አምናም ኢየሱስ!!
✍ ዘንድሮ ኢየሱስ!!
✍ ነገም ኢየሱስ!!
✍ ዘላለም ኢየሱስ!!

👉 ወዳጆቼ ያላችሁበትን ኪዳን እወቁ!!

ስለ ሰላም ጸልዩ!!
✍️ በመካከለኛው ምስራቅ ብቻ ሳይሆን በመካከላችሁም "Pray for" የሚያስብል ብዙ ጉዳይ እንዳለ ታውቃላችሁና!!

✍️ጎልያድን በወንጭፍ በለው በለው የሚል እስራኤላዊ ስሜት ገንፍሎ የሚወጣባችሁ የወንጌል አማኞች ሆይ ከዳዊት ይልቅ ክርስቶስን በማወቅ ስር መስደድ ይሁንላችሁ!!

እናልህ ወንድሜ በወንጌል እንደዳነ ሰው....
✍️ምርጡን ነገር ላስታውስህ አንተ በክርስቶስ የሆንክ እግዚአብሔር በክርስቶስ እንደሚያይህ ሰውን ሁሉ በክርስቶስ የምታይ አዲስ ፍጥረት ነህ!!

✍️ እግዚአብሔር በክርስቶስ ላላቆመህ አትቁም!! እግዚአብሔር በክርስቶስ ላቆመህ ነገር አትቀመጥ!!

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

በኢየሱስ ስም!!!!

ምሽታችሁ የራዕይ ምሽት ይሁን
ራዕይ ምታዩበት መንፈሳዊ አለምን የምታዩበት አይናችሁ  የሚከፈትበት ጆሯችሁ የሚከፈትበት ምሽት ይሁንላችሁ❗️
ኢዮብ 33
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹⁴ እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።
¹⁵ በሕልም፥ በሌሊት ራእይ፥ አፍላ እንቅልፍ በሰዎች ላይ ሲወድቅ፥ በአልጋ ላይ ተኝተው ሳሉ፥
¹⁶ በዚያን ጊዜ የሰዎችን ጆሮ ይከፍታል፥ በተግሣጹም ያስደነግጣቸዋል
፥

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

መዳፉ ላይ ቁስል ካያችሁ
የህማም ሰው ካስተዋላችሁ
ውዴ እርሱ ነው ነፍሴን የያዛት
በዕንቁ ሳይሆን በደም የገዛት…😭😭😭😭


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ጥያቄ

ዛሬ እሁድ ቤተክርስቲያን የሄዳቹ ፤ የተኪፈላችሁ ምን ተማራችሁ? ምን ተሰበካችሁ? አጋሩን እስኪ...


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

እኛ የወንጌል አማኞች(ጴንጤዎች)የመስቀል ጠላቶች አይደለንም። መስቀሉ አርማችን ነው፣ መስቀሉ ምልክታችን ነው። መስቀል ስናይ የአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃዩ፣ ስለ እኛ መገረፉ፣ ስለ እኛ መሞቱን ፣ ስለ አኛ ደሙን ማፍሰሱን እናስታውሳለን። መስቀሉ ብቻውን ያድናል ግን አንልም መስቀሉን ሳይሆን የተቀሰለው ክርስቶስን እንሰብካለን። መስቀሉ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስ ያስታውሰናል እናም ምልክታችን አርማችን ነው። ከታች እንደምትመለከቱት የፕሮቴስታንት እናት ቤተክርስትያን ከሚባሉት መካነ ኢየሱስ፣ ሙሉ ወንጌል ፣መሰረተ ክርስቶሰ አርማቸው፣ ልዩ ምልክታቸው መስቀል ነው። በመስቀሉ ጠላታችን ዲያቢሎስ የተሸነፈበት፣ ሰማይ እና ምድር የታረቁበት ቦታ ነው።መስቀሉ ለእኛ ምልክታችን፣ አርማችን ነው። የምንሰብከው ግን የተሰቀለውን አምላካችንን ጌታችን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ነው። መዳን በሌላ በማንም የለም አምላካችን ኢየሱስ ያድናል።

ሃይላችን መስቀል ሳይሆን በመስቀል ላይ የተሰቀለው መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

"የመስቀሉ
#ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ሃይል ነው"

ምንጭ፡ የወንጌል ድምፅ


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ክርስቲያን ሼር አርግ
🎯ትኩረት🎯

#መስቀል_በዓል!! #መስቀል_መስቀል_ይላሉ!!
መስቀል አርገው፤ ምሽት ክለብ እያጨናነቁ
መስቀል አርገው፤ ለዓለም ክብር እየሞዘቁ
መስቀል አርገው፤ አልኮል መጠጥ እየተጠመቁ
መስቀል አርገው፤ አደንዛዥ ዕጥ ጫት እየቃሙ
መስቀል አርገው፤ የሰው ስጋ እየበሉ
መስቀል አርገው፤ አመፅና ግጭት እየጠሩ
መስቀል አርገው፤ የወደቀ አንድ ሰው ሳያነሱ
መስቀል አርገው፤ ክፋት እና ሴራ እየጎነጎኑ
መስቀል አርገው፤ ወንድሞቻቸው እየከሰሱ
መስቀል አርገው፤ የሞተውን ሳይብኩ
መስቀል አርገው፤ ፍጡር እያመለኩ
መስቀል አርገው፤ የሞተው እያለ ሌላ አማላጅና አስታራቅ እየፈለጉ
መስቀል አርገው፤ ከሞተው ይልቅ ለፍጡር ክብር እየሰጡ
መስቀል አርገው፤ ከሞተው በላይ ለፍጡር መሰዋዕት እያቀረቡ
መስቀል አርገው: የተሰቀለውን ሳይሆን የተሰቀለበትን እያወደሱ!!!
#ደሞ አንላቀቅም ይላሉ ከመንገዳቸው መመለስ ስቺሉ!!
ባይላቀቁ እንደሚወድቁ ሳያውቅ!!
#ኢየሱስ_ብቻ_ነው_አዳኝ_የሆነ_ጌታ!!

የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና፡፡ 1ቆሮ 1፥18


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

በድጋሚ
አዲስ ነገር ሊሆን ነው

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ልጆች፥ ስጦታዎች

ልጅን ያህል ነገር መሳደብ፣ መምታት፣ ማሸማቀቅ፣ ማሳቀቅ፣ ለአካል ጉዳት መዳረግ፣ በአንፃሩ ደግሞ አጉል ማሞካሸት ኃጢያት ነው።

መጽሐፍ "ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፥" ይላል (መዝ 127:3)።

የምንሰድባቸው፣ የምንመታቸው፣ የምናሸማቅቃቸው፣ የምናሳቅቃቸው፣ ለአካል ጉዳት የምንዳርጋቸው፣ በአንፃሩ ደግሞ ያልሆኑትን እንደ ሆኑ አድርገን የምናሞካሻቸው ልጆች ፥ ከየት የመጡ ናቸው?

በየቤቱ ሆናችሁ፥ ልጅ የምትሰድቡ፣ የምትቀጠቅጡ (የምታጋጩ)፣ የምታሸማቅቁ፣ የምታሳቅቁ፣ እልፍ ሲል ደግሞ ለአካል ጉዳት የምትዳርጉ፣ በአንፃሩ ደግሞ በአጉል ማሞካሸት፥ ልጆችን መረን የምትለቁ ኃጢያተኞች፥ እግዚአብሔር ልቦና ይስጣችሁ። ለማንኛውም የቤተሰብ ሕጉ ወይንም ወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ እንዳለ አንርሳ!

መልዕክቱን ማንበብ፣ ማጎልበት ወይም መተቸት ይገባል። ነገ በቀጣዩ መልዕክት እንገናኝ!!

@ Daily Bread/የዕለት እንጀራ


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

Something new is coming

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

የዳነ ሰው እኮ ያስተውቃል የተነካው መነካት ልደብቀው ቢል ራሱ በፍፁም አይደበቅም በህይወቱ እንደ ወንዝ ሲፍስበት ታያላቹ።
የማይታይ የተደበቀ የክርስትና ህይወት የለም።


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

🌼🌼🌼🌼እንኩዋን ለደመና⛈⛈⛈ አመታችን በሰላም አደረሳቹ🌼🌼🌼🌼

በአሉ ይበልጥ መንፈስ ቅዱስን ምትፈልጉበት 😭

🌼⛈⛈በደመና የምትገቡበት እና ምትወጡበት

🌼 የእግዚአብሔር ልጅነታቹ በሀይል የምትገጡበት አመት

🌼 መንፈስ ቅዱስን በሀይል ምትረዱበት አመት
ይሁንላቹ

🌼🌼🌼🌼🌼መልካም በዓል 🌼🌼🌼🌼🌼


🌼🌼🌼🌼🌼🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺🌼🌼🌼

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ጤናማ ትምህርት

👉🎯የአንድ መንፈሳዊ ትምህርት ትክክለኛነት እና ጤናማነት መለኪያው በጥቅስ ወይም በመገለጥ አይደለም።

👉🎯ልክ እና ጤናማ የመሆኛ መለኪያው ምንድነው ??በ

👉🎯የአንዳንዶች ትምህርት የመጽሐፍ ጥቅስ ብቻ ነው ህይወት አልባ ነው።
- የሌላኞቹ ትምህርት ህዝብኝ ወደራሳቸው የሚያሳድጉ ሆነዋል!!.

👉🎯የያዝከው ትምህርት ጤናማ የመሆኑ መለኪያ " ምን ያህል እግዚአብሔርን ወደ መምሰል ያሳድጋሉ??" የሚለው ነው!!

👉🎯ወገኖቼ እርሱን ወደመምሰል የማያሳድግ ትምህርት ሁሉ የትዕቢተኞች እና የአላዋቂዎች ትምህርት ነው!!
(
#1ኛ_ጢሞ:6:4)

👉🎯ውጠህ የማይፈውስህ መድሀኒት እና እግዚአብሔርን ወደ መምሰል ማያሳድግ ትምህርት አንድ ናቸው።

“በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር አድርገህ፥ ከእኔ የሰማኸውን ጤናማ ቃል ምሳሌ ያዝ፤”
  — 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥13

👉🎯ትኩረት አርግ ወደ ሰው ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር ለማደግ ምትሰማውን ምረጥ!!


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ስንት መስከረም ስንት ጥቅምት
ከእባብ ከጊንጡ የዳንኩበት🤔
ስንት ህዳር ነበር ስንት ታህሳስ
ከሞት ያዳንከኝ ደርሰህ ኢየሱስ🤗
ስንት ጥር አልፏል ስንት የካቲት
ወይ አለቀልኝ ብዬ ያልኩበት🤦‍♀️
ስንት መጋቢት ስንት ሚያዝያ
ሀዘን ሲሆነኝ መውጫና መግቢያ😭
ግንቦትስ ሰኔ ሀምሌ ነሃሴ
የጭንቅን ቀን አይቷል ይህ ነብሴ 😫
በዚ ሁለ ግን ደርሰህ ያዳንከኝ
እንዳመሰግን ዛሬን ሰጠኸኝ
🙌🙌🙌🙌🙌
@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ከ online ውጡ ዳይ ወደ ቤተክርስቲያን እንሂድ‼️ hardcopy መጽሐፍ ቅዱስ እንዳይረሳ

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ጥያቄ #4

4/ በህይወታችሁ እሄንን ባደርግ ነው ነፍሴ ምታርፈው❗️ምትረካው❗️ የምትሉት ነገር ምንድን ነው❓


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ፀሃይ በሞቀው የዓመፅ መንገድ እየሄደ ጎሽ ሲባል እንደሚደሰት ዓይነት ቂል ሰው አላየሁም::
Dr lealem

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

በድጋሚ አሜን‼️
ምርኮ_ይመለስ

1 ከዚህ በፊት የነበራችሁ ቅንነት
2 ከዚህ በፊት የነበራችሁ ታማኝነት
3 ከዚህ በፊት የነበራችሁ በጌታ ቤት ያላችሁ ትጋት💪
4 ከዚህ በፊት የነበራችሁ ለአገልግሎት ያላችሁ ፍቅር❤️
4 ከዚህ በፊት የነበራችሁ የመንፈስ ቅዱሽ ረሃብ.......😭
ነገር ግን አሁን በማንኛውም ምክንያት የቀነሰባችሁ አንዳንዶች ፈጽሞ የተወሰደባችሁ.....😭😭😭😭

ዛሬ ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ምርኮ ሆነው ይመለሱላችሁ!!!!

             

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ጥያቄ #6

በህይወታችሁ በብዙ የተደሰታችሁበትን "እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎልኝ በጣም ተደስቻለው" የምትሉት አንድ አጋጣሚ አለ?? ምስክርነት ካላችሁ...


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ከ online ውጡ ዳይ ወደ ቤተክርስቲያን እንሂድ‼️ hardcopy መጽሐፍ ቅዱስ እና ማስታወሻ ደብተር እንዳይረሳ

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ተገኘ መስቀሉ

ክርስቶስን ትተው ሊንቁት በይፋ
በየመሽታው ቤት እምቢልታ ሊነፋ
ቀረርቶ ሽለላው ዳንኪራው ሊደራ
በአልባሌ ነገር በከንቱ ጭፈራ
ክብሩን ገፈውበት ዋጋውን ሊያቀሉ
እሰይ እልል በሉ ተገኘ መስቀሉ
ወትሮስ እንጨት ሞልቶ መስቀል የት ይጠፋል
በየጌጥ ተሰርቶ ለሽያጭ ይውላል
ግና ከመስቀሉ የሞተው ይበልጣል!
የወንበዴው ነው ወይ የተገኘው መስቀል
ትውልዱን በዝሙት በርኩሰት ሚበክል
እንዲህ ያለ ምግባር ክርስቶስ የለውም
ጎልጎታ ሲሰቀል በደል አልፈፀመም
ወይም አንዳች ህጸጽ አልተገኘበትም
ስለዚህ ወገኔ ታገኘው አንደሆን ጠበቅ አርገህ ፈልግ
ምን አልባት ይሆናል ዋሻው ውስጥ ባንዱ ጥግ
ብኩን እንዳትሆን አንድ እውነት ልንገርህ
ህይወት እንድታገኝ መንገድ ልጠቁምህ
ምንም ብትደክም ሺህ ጉድጓድ ብትቆፍር
ዋሻ ብትፈለፍል ጠልቀህ ብትመረምር
የእየሱስ መስቀል አይገኝም ከአፈር
ውስጥህ ነው ወዳጄ እሱን ተሸከመው
ጽድቅን ልበስና ወደህ ተከተለው
መጽሐፍ እንደሚለን ይሄ ነው እውነቱ
ጌታችንን ትተን አንባክን በከንቱ
ይህንን አንሰማም እንጨቱን ለሚሉ
የሞተውን ትተው ለሚወላውሉ
አልል በሉላቸው ተገኝቷል መስቀሉ።

I HAVE NO SORRY ABOUT THIS POST


kibrom

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

♦#የመስቀል_በዓል_እውን_መጽሐፍ
#ቅዱሳዊ_ነውን?♦
==================================
✍️የመስቀል በዓል በአብዛኛው በክርስትናው አለም ያልተለመደ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በጥንት የቤተክርስቲያን ታሪክ የማይታወቅና እውቅና የለውም ነው።

✍️ መስቀል ሲነሳ መነሳት ያለበት እንጨቱ ሳይሆን የተሰቀለው ጌታና የመጣበት አላማ ሊሆን ይገባል። የተሰቀለውን ጌታና የመጣበትን አላማ ስተን የተሰቀለበት እንጨት ላይ ትኩረት ብናደርግ ሐይማኖታዊ ስርአትን ከመፈጸም ውጭ ደህንነትን ልንካፈል አንችልም።
ከዚህ የተነሳ ሁላችንም ወደ መጽሐፍ ቅዱሱ ሀሳብ በትህትና ልብ ልንመለስ ያስፈልገናል።

✍1 ቆሮንቶስ 2፡15፤
መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል

✍ዮሐንስ 8 (John)
32፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።

📌የመስቀል ፍቺ:-
----------------
Greek: σταυρός
Transliteration: staurĂłs
Pronunciation: stow-ros'
በጥንቱ ገጽ የግሪክኛ ቋንቋ ይህ “መስቀል ተብሎ የተተረጐመው ቃል [ስታዉሮስ ] ማንኛውም ነገር የሚሰቀልበትን ወይም [ለአጥር የሚሆንን] እንጨት ወይም ቀጥ ያለ ምሰሶ ወይም ግንድ ያመለክታል።

(Cross) “ክሮስ” የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል የተወሰደው "ክሩክስ" ከሚለው የላቲን ቃል ሲሆን
በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች “መስቀል” (“የመከራ እንጨት” ) ተብሎ የተተረጐመው ነው።

📌የመስቀል አይነቶች ፦
-----------------
👉1) ክሩክስ ኢሚሳ (ተ) = (Crux immissa) የላቲኖች መስቀል
👉2) ክሩክስ ኳዳርታ (+) = (Crux quadrata) የግሪኮች መስቀል
👉3) ክሩክስ ኮሚሳ (Crux commissa) (T) =ወይንም በተለምዶ የቅዱስ አንቶኒ መስቀል
(St. Anthony’s cross) ተብሎ ይጠራል፡፡
👉4) ክሩክስ ዲኩሳታ (Crux decussate) (X)= ወይንም በተለምዶ የቅዱስ እንድርያስ መስቀል (St.Andrew’s cross) ተብሎ ይጠራል።

📌መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል??
-------‒-----------------
✍1 ቆሮንቶስ 1፡18
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።.....
23፤ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥

✍መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ኃይል የሚለው የመስቀሉን ቃል እንጂ የመስቀሉን እንጨት(ቅርጽ) እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባናል።

✍አንድ ሰው ሆዱን ቢታመም እና ሽሮፕ ቢታዘዝለት የሚያድነውን ሽሮፑን ደፍቶ ጠርሙሱን ያድናል ቢልና ይዞት ቢዞር ከበሽታው ሊፈወስ አይችልም። እንዲሁ የተሰቀለው ጌታ እንጂ የተሰቀለበት እንጨት ሊያድነን አይችልም።

📌በተሰቀለው በ ኢየሱስክርሰቶስ የተቆጠሩልን በረከቶች፦
====================================
መጽሐፍ ቅዱስ በ1ኛ ቆርንቶስ 1፣23 ላይ " እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን" ይለናል።

ከዚህም የተነሳ በሰቀለው በኢየሱስ ክርስቶስ፦
👉የእግዚአብሔር ልጆች ሆነናል ዮሐ 1:12
👉-በተሰቀለው ደህንነት አግኝተናል። ዮሐ3:14-18
👉-በተሰቀለው ከሞት ወደ ሕይወት ተሻግረናል። ዮሐ 5:24
👉-በተሰቀለው ዘላለማዊ ስርየት አግኝተናል።ዕብ 9:22

👉-በተሰቀለው ለዘላለም ተቀድሰናል።ዕብ 10:10
👉-በተሰቀለው የዘላለም ፍጹማን ሆነናል። ዕብ 10:14
👉-በተሰቀለው የእድሜ ዘመን የሀጢያት ስርየት አግኝተናል ። ዕብ 10:17-18,ሮሜ4:5-6
👉- በተሰቀለው ከሕግ ርግማን ነጻ ወጥተናል ገላ3:13
👉-በተሰቀለው ከኩነኔ አምልጠናል። (ሮሜ 8:1)
👉-በተሰቀለው ከኃ ጢያትና ከሞት ሕግ ነጻ ወጥተናል። (ሮሜ 8፡2)።

📌መስቀል ሲነሳ መነሳት ያለበት እንጨቱ ሳይሆን የተሰቀለው ጌታና የመጣበት አላማ ነው። የተሰቀለበት እንጨት ላይ ትኩረት አድርገን የተሰቀለውን ጌታ አላማ ብንስት ሐይማኖታዊ ስርአትን ከመፈጸም ውጭ ደህንነትን ልንካፈል አንችልም።
የተሰቀለውን ጌታ እንጂ የተሰቀለበትን አንሰብክም
የተሰቀለበት እንጨት ከተሰቀለው ጌታ አላማ ውጭ ምንም ነው።

✍️1 ቆሮንቶስ 1 (1 Corinthians)
18፤ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።

✍️1 ቆሮንቶስ 1 (1 Corinthians)
23፤ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥

✍ዮሐንስ 8 (John)
32፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።

✍ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ለሁላችንም ይብዛ።

የወንጌል እውነት


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ልጆች፥ ስጦታዎች

ልጅን ያህል ነገር መሳደብ፣ መምታት፣ ማሸማቀቅ፣ ማሳቀቅ፣ ለአካል ጉዳት መዳረግ፣ በአንፃሩ ደግሞ አጉል ማሞካሸት ኃጢያት ነው።

መጽሐፍ "ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፥" ይላል (መዝ 127:3)።

የምንሰድባቸው፣ የምንመታቸው፣ የምናሸማቅቃቸው፣ የምናሳቅቃቸው፣ ለአካል ጉዳት የምንዳርጋቸው፣ በአንፃሩ ደግሞ ያልሆኑትን እንደ ሆኑ አድርገን የምናሞካሻቸው ልጆች ፥ ከየት የመጡ ናቸው?

በየቤቱ ሆናችሁ፥ ልጅ የምትሰድቡ፣ የምትቀጠቅጡ (የምታጋጩ)፣ የምታሸማቅቁ፣ የምታሳቅቁ፣ እልፍ ሲል ደግሞ ለአካል ጉዳት የምትዳርጉ፣ በአንፃሩ ደግሞ በአጉል ማሞካሸት፥ ልጆችን መረን የምትለቁ ኃጢያተኞች፥ እግዚአብሔር ልቦና ይስጣችሁ። ለማንኛውም የቤተሰብ ሕጉ ወይንም ወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ እንዳለ አንርሳ!

መልዕክቱን ማንበብ፣ ማጎልበት ወይም መተቸት ይገባል። ነገ በቀጣዩ መልዕክት እንገናኝ!!

@ Daily Bread/የዕለት እንጀራ


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ከ online ውጡ ዳይ ወደ ቤተክርስቲያን እንሂድ‼️ hardcopy መጽሐፍ ቅዱስ እና ማስታወሻ ደብተር እንዳይረሳ

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

በቶሮንቶ ሆስፒታል በአሰቃቂ ሁኔታ ለሞት የተቃረበው ይሄ ሙስሊም ወንድም ድንቅ ተአምር ሆነለት!

ነገሩን እንዲህ ሲል ይመሰክርልናል፦ በሆስፒታሉ ለሞት እያጣጣርኲኝ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ነበርኩ.

ቁርኣንን ትራሴ ስር አድርጌ ዱአ(ፀሎት) ማድረግ ጀመርኩ.

አላህ ሆይ እባክህ ፈውሰኝ! ለምን ስሰቃይ ዝም ትለኛለህ? የረሱል ወዳጅ ነኝ ያ ረብ ፈውሰኝ!
ብዬ አለቀስኩ!
ነገር ግን ምንም ለውጥ የለም ይባስ ህመሜ ባሰብኝ!
ዶክተሩም መጥቶ ልሞት እንደተቃረብኩና ከአንድ ቀን በላይ መቆየት እንደማልችል ነገረኝ.

ዶክተሩም ሙስሊም ነበርና እኔ ስቅስቅ ብዬ ሳለቅስ አይቶ በጣም አዝኖልኝ ቁርኣኑን ከትራሴ ስር ወስዶ ቀራ! ቁርኣኑን እየቀራ ወደኔ ይመለከታል! ነገር ግን አሁንም ምንም ለውጥ የለም. ህመሜ ባሰንኝ!

ቀኑ መሸ ሌሊት ላይ ደከምኩና እራሴን ሳትኩ! ዶክተሩ ልሞት መሆኔን አይቶ ሊገንዘኝ አጠገቤ ቆሟል.

እኔ ግን በሰመመን ውስጥም ሆኜ አንድ እድል እንዳለኝ አሰብኩ!
እስኪ መሞቴ ለማይቀር ድንገት ሊያድነኝ ይችላልና ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሉትን ጌታ ልጥራው ብዬ ወሰንኩ.

ኢየሱስ ክርስቶስ ልታድነኝ ትችላለህ አልኩ

ወዲያው የሆነ እጅ ሲዳስሰኝ ተሰማኝ! ከአልጋዬ ላይ ዘለልዬ ተፈወስኩ ተፈወስኲ ብዬ ጮኽኩ!

ለዶክተሩም ኢየሱስ ክርስቶስ እንደፈውሰኝ ነገርኩት.

በጣም ተገርመ
እኔ እዛው በኢየሱስ ክርስቶስ አመንኩ! ዶክተሩም የኔን ፈውስ አይቶ በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ!
ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክ ነው! ይሰማል ይናገራል ይመልሳል ይፈውሳል ያድናል!

ኢየሱስ ክርስቶስ ይለያል!

#ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከስጋ_ደዌም
#ከዘለአለም_ሞትም_ያድናል!
የሚያምን ብቻ
#አሜን ይላል!

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ትኩረት
ለጓደኛ ተብሎ ኢየሱስ አይተውም
ለኢየሱስ ተብሎ ሁሉም
ይተዋል እንጂ🤗
from ela


@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

የ @focus_youth ቤተሰቦች እንኳን ለአዲሱ በጤንነት አደረሳችሁ ‼️

አዲሱ ዓመት በራዕያቹ እና በአላማቹ ላይ ከልብ ትኩረት የምታደርጉበት አላማቹን ለመፈጸም ወደ ራዕያቹ ግብ ለመድረስ ወስናችሁ የምትተጉበት ዓመት ይሁንላችሁ በኢየሱስ ስም
‼️

@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

አሜን‼️

@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

“እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።”
  — ራእይ 22:12

- ይሄ ቃል እኮ ለሚያገለግሉ ብቻ አደለም ለሁሉም  ነው አስቡበት ስህተት በአገልግሎት ብቻ አይደለም ወደራሳችን እንመልከት።
- በአሁን ጊዜ አብዛኛው ሰው "ሀሰተኛ ነብይ ፣ የስህተት ልምምዶች" የሚባሉ ዘገባዎችን እና አስተያየቶችን post ሲያደርግ የሚጠቀመው ጥቅስ ይሄ ነው ራሳቸው አግልለው ይሄን ቃል ለነብያቶች ለአገልጋዮች ብቻ የተጻፈ እስኪመስል ድረስ ከ ቃሉ ራሳቸውን አውጥተውት ቃሉን መስታወት ሳይሆን መነጽር አድርገውት እታዘባለው።

- ይሄ ቃል ለእያንዳንዱ ነው እንኳን ለአገልጋዮች ብቻ ይቅርና ለክርስቲያን ብቻ አይደለም ለሁሉ ለሰው ፍጥረት ነው
‼️

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

በኢየሱስ ስም!!!!

ምሽታችሁ የራዕይ ምሽት ይሁን
ራዕይ ምታዩበት መንፈሳዊ አለምን የምታዩበት አይናችሁ  የሚከፈትበት ጆሯችሁ የሚከፈትበት ምሽት ይሁንላችሁ❗️
ኢዮብ 33
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
¹⁴ እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።
¹⁵ በሕልም፥ በሌሊት ራእይ፥ አፍላ እንቅልፍ በሰዎች ላይ ሲወድቅ፥ በአልጋ ላይ ተኝተው ሳሉ፥
¹⁶ በዚያን ጊዜ የሰዎችን ጆሮ ይከፍታል፥ በተግሣጹም ያስደነግጣቸዋል
፥

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…

🎯focus- ትኩረት

ጥያቄ #3

3/ ስኬት ላንተ/ቺ ምንድን ነው❓
ምን ስትሆን/ኚ ተሳካልኝ ትላላችሁ
❓
What is success for you❓
What do you say I have succeeded ❓

@focus_youth
@focus_youth
@focus_youth

Читать полностью…
Subscribe to a channel