አድዋ
✍️አንቺንአየሁ ገብሬ(emuyee)
✨ያ ዘመን ላይ ለጦቢያ ጢያራና ግራማፎን ብርቅ ነበሩ... መኪናና የባቡር መንገድማ አይታሰቡም..ራዲዮና ስልክም አልነበሩም..እንደዉ ለጥበቡም ቢሆን ቴያትር ቤቶችም ገና"ሰይጣን ቤት"ከሚል ዉዝግብ አልወጡም ነበር...
✨በአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት ያስተጋባዉ የእምዬ" ወስልተህ የቀረህ እንደሁ ኋላ ትጣላኛለህ..ማርያምን አልምርህም!"የሚል አዋጅ ነበር....የጦቢያ ልጆች ዛሬም እንኳን በዘመናዊ መሳሪያዎች ገና አልበገር ያሉ ተራሮችና ቁልቁለቶቿን አቋርጠዉ የመጡት በእግሮቻቸዉ ነበር...ያዉም ስንቃቸዉን ተሸክመዉ!!የሃገሬ ገበሬ ሰዓትን በፀሐይ ዙረት በሚለካበት በዛ ዘመን ቀጠሮዉን ሳያዛንፍ ወረኢሉ ከቶ የተገኘዉ የሃገር ፍቅር እረፍት ቢነሳዉ ነዉ....የሃበሻ ቀጠሮ!!!
✨የወረኢሉ ታሪካዊ ምድርስ ምን አስተናግዶ ይሆን??ዳግማዊ ባቢሎን የሆነ መስሎት ደንግጦስ ይሆን እንዴ?ማን ያዉቃል..የተለያየ ቋንቋ...የተለያየ ባህል...አለባበስና ኑረት...ግና በሃገር ፍቅር ጠንካራ ክር.በአልሸነፍ ባይነት ወኔ:ወራሪን አደብ ለማስገዛት በመፋጠን:የማንነት ክብርን ለማስቀጠል..ልዩነት በአንድነት ተሸምኖ ፀጉራቸዉን ያበጠሩ:ጠላትን የሚያርድ ጥቁር ኮስታራ ፊት ያላቸዉ ለሃገራቸዉ ለመሞት ራሳቸዉን የሰጡ ህዝቦች ሲያቅራሩበትስ ምን ተሰምቶት ይሆን??
🔥አድዋ ብቻዉን ዓለም ነዉ እቴ....ብዙ ሺህ አመታትን ያስተናገደችዉ የምድራችን እልፍ ታሪካዊ ክስተቶች ዉስጥ አድዋ የዓለምን አይዲዎሎጂ ዘዉሯል።ልክነት አዉሮፓ ዉስጥ መሽጋ በነበረበት ዘመኗ ላይ እነርሱ የተናገሩት ሁሉ እዉነት:እነርሱ መሪ ሌላዉ ተከታይ በነበሩበት በዛ ጊዜ:ለጥቁሮች የሰጡት የበታችነት:የተገዢነት:የአገልጋይነት:የኋላቀርነት ስያሜ ያለአንዳች ጥያቄ ሲቀነቀንበት የነበረበት ያ ወቅት ላይ ኢትዮጵያ ሌላ እዉነት ይዛ ተነሳች።ያለ አንዳች የቃላት ማብራሪያ ዓለምን ማናወፅ ተቻላት...የዓለም ፊቶች ወደ እርሷ ዞሩ።
አፍሪካ ዉስጥ ካለች አንዲት ዘመናዊነት ብርቅ ከነበረባት ምድር እንዴት ይጠበቃል...በጭራሽ!!
ይህች ጉደኛ አገር ስሟን በጠላቶቿ አስገድዳ አስጠርታለች...ቪቫ ምኒልክ...ቪቫ ጣይቱ በእዝነት የተሰጠ ሳይሆን ተዓምራዊዉ የአድዋ ድል ብዕራቸዉን አስገድዶ ያፃፋቸዉ የጋዜጣ ላይ አዋጅ ነዉ...የሮም አደባባዮች የኢትዮጵያን ስም
በሚጠሩ የሮማ ልጆች የተሞላችዉ የተፃፈዉ የደም ታሪክ ዝም እንዲሉ ስላልፈቀደላቸዉ ነዉ...አድዋ ተነግረዉ የማያልቁ ድልና ነፃነት መነሻ በተጠጉት ቁጥር እየረቀቀ የሚሄድ ምስጢር ነዉ!!!
✨✨✨✨
ቆይ አንዴ ብቻ!!!
እምዬ ይላቸዋል የሃገሬ ሰዉ ሲጠራቸዉ...ከዚህ በፊት ይህንን ስያሜስ መች ለሌላ ሰማን...እምዬን ለንጉስ..እኔ አልሰማሁም🙌....እርሳቸዉ እቴ ስመ ገናና ስመ ብዙ ናቸዉ...ከሸዋ ዘንዳ የበቀሉ..የአንጎለላ ኪዳነምህረት ፍሬ!!
እንደዉ ሌላዉን ትተን ዋነኛ መጠሪያቸዉንስ ብናይ....ዳግማዊ የተባሉለት ምኒልክስ ቢሆን...ቀዳማዊዉ!!የዛች የጥበብ ፈርጥ:የዉበት ጥግ አለም የእኔ ናት እያለ የሚሻማላት ባለ እንቁ ጣጣ:የንግስት ማክዳ ልጅ አይደል..የታቦተ ፅዮን አምጫችን...የኢትዮጵያችን ታሪክ ላይ የራሱን አምድ ተክሎ ያለፈ..
ይሄ ስም ምንድን ነዉ ምስጢሩስ..ዳግማዊ ተብሎ ስሙ ሲደገም ሌላ የኛን ብቻ ሳይሆን የአፍሪቃን የዓለምን ታሪክ ቀየረ..አድዋ እያሰኘ!!
እንዲህ የተነባበሩ አመታትን እየተሻገረ በየጊዜዉ እንደ እንቁ የሚያበራ ታሪክ ሰሪ የኩራት ልክ!!
💙"ጥሩ ሚስት ካገኘህ ደስተኛ ትሆናለህ:ካልሆነ ግን ማለፊያ ፈላስፋ ይወጣሃል"ይለናል ሶቅራጥስ! የእምዬ ባልተቤታቸዉ ፀሀይቱ እንዴት ብትሆን ይሆን ጀግና:ኩሩ: ታሪክ የሆነ ንጉሷን የሰጠችን...ብልኃትማ የግሏ ነዉ...እንኳን ወዳጅም አድናቂም እኔ ልጇ ቀርቶ የጣሊያን ወታደርስ ይመሰክርላትም የለ እንዴ.".ዉሃ..ዉሃማ" በቀላሉ መች ትረሳለች!!
የእልፍኙንስ ማን አየባትና...ወደ ዉጪ የሚወጣ መነሻዉስ ከዉስጥ አይደል....የጓዳስ ጦርነት መች ቀላል ነበርና..አይዞህ ባይ ሔዋን ባትኖረዉ እምዬስ ከኑሮዉ በዘለለ ኢትዮጵያን የመስራት ሀሳቡን በምን ጊዜ ሊተገብረዉ...ታሪክ ነዉ!!ጠሃይቱ አስተባብራ ይዛቸዉ ለዘመተችዉ የጦቢያ እናቶች..አድዋ የብልሃታችሁ ድምር ዉጤት ነዉና እጅ እንነሳለን!!
🔥ክብር አድዋን ለሰጡን እናትና አባቶቻችን!!
🔥ክብር ጦቢያን በአጥንትና ደማቸዉ ድልድይ ገንብተዉ ለዛሬ ላሻገሩልን ጀግኖች!!
🔥ክብር በሃገር ፍቅር ለነደደ ልባቸዉ!!
🔥ክብር ምርኮኛን በርህራሄ ላስተናገደዉ ልዕለ-ስብዕናቸዉ!!
🔥ክብር ከሰዉ በላይ ሰዉ ለሆነ ማንነታቸዉ!!
✨✨አቦ የኢትዮጵያ እናቶች እስኪ ዉለዱ..እምዬ ማህፀንሽ አይንጠፍ አሜን በይ.!!
ሃሌሉያ🙏
የካቲት ፪፫/፳፻፲፮
ትኩስ ❗❗
በምስራቅ ጎጃም ዞን፣የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ መቀመጫ የሆነችው ግንደ ወይን ከተማ በአራቱም አቅጣጫ በከባድ ተኩስ እየተናጠች መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
ቀን ስድስት ስዓት የተጀመረው የተኩስ ልውውጥ አሁንም ድርስ እንዳለ ምንጮች ይናገራሉ።
እስካሁን በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ በሰርግ ሥነ ስርዓት ላይ የነበሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው ንፁሃን መሞታቸውን ምንጮች ገለፀዋል።
"ወንድሞቻችን እየሞቱ ፣እናንተ እዚህ ተሰብስባችሁ ትጠጣላችሁ" በማለት በስርግ ዋዜማ ላይ የነበሩትን በርካታ ሰዎች መከላከያዎች በሩምታ ተኩስ በመክፈት መግደላቸውን የዓይን ምሥክሮች ይናገራሉ።
የተኩስ ልውውጡ አሁንም ድርስ ባለማቆሙ የሟቾችን ቁጥር ማወቅ እንዳልተቻለ ምንጮች ይናገራሉ።
በታጣቂዎች በኩል ከተማዋን ለመያዝ በአራቱም አቅጣጫ የተደራጀ ኃይል በመያዝ ወደ ውስጥ እየገሰገሱ መሆናቸውን ከቦታው በስልክ ያደረሱን እማኞች ተናግረዋል።
ከሁለቱም ወገን በቁጥር ያልታወቀ የሰው ኃይል መሞቱንና መጎዳቱንም አክለው ገልጸዋል።
የአፈር ማዳበሪያ ከወረዳው ከህብረት ሥራ ማህበር ለመግዛት በርካታ አርሶ አደሮች በከተማዋ መገኘታቸው የሟቾችንና የተጎጅዎችን ቁጥር የከፋ ሊሆን እንደሚችል ምንጮች ጠቁመዋል።
/channel//Gazetaw
ነፍስ ይማር🙏
ተማሪ ገደፈው አስማረ ሕይወቱ አልፏል። 😭😭😭
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ፣ ተማሪ የነበረው ተማሪ ገደፈው አስማረ ትናንት ሕይወቱ አልፏል።
ተማሪ ገደፈው አስማረ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር የ3ኛ ዓመት ተማሪ ሲሆን ባደረበት ህመም በደሴ አጠቃላይ ሆስፒታል ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ትናንት ሕይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
ተማሪ ገደፈው ህመሙ ቲቪ ነው ተብሎ የቲቪ መድሃኒት እንዲጠቀም ቢደረግም ፣ህመሙ ግን በተለምዶ "ወፌ" ተብሎ የሚጠራው በሽታ እንደነበራና ሕይወቱም ያለፈው በዚሁ በሽታ ነው ተብሏል።
የ"ወፌ" በሽታ መንስኤውና የበሽታው አስተላላፊ የሌሊት ወፍ ስትሆን በተለይ ደግሞ በጎንደር አካባቢ የታወቀና አደገኛ በሽታ ነው ።
የ"ወፌ"ን በሽታ በባህላዊ መንገድ ታክሞ መዳን የሚቻል ሲሆን በሽታው ከፍተኛ ደረጃ ከደረሰ የታማሚው የመዳን ዕድሉ ዝቅተኛ ነው ይባላል።
ለጓደኞቹ እና ለቤተሰቦቹ ቤታችን መፅናናት ተመኝታለች🙏
/channel//Gazetaw
ጂጂጋ ዩኒቨርስቲ የኮሌራ በሽታ መከሰቱን አንድ ምንጭ ጠቁሞኛል።
ዩኒቨርስቲው በበሽታው የተያዙ ተማሪዎችን በማቆያ ክፍል ለመነጠል ቢሞክርም ፣የታማሚዎች ቁጥር በመጨመሩ ምክንያት ተማሪዎች ችግር ላይ እንዳሉ ነግሮኛል።
ከግቢው ክሊኒክ በሪፈር ወደ ሆስፒታሎች እየታለኩ ቢሆንም በሽታውን መቆጣጠር እንዳልተቻለ ይናገራል።
በግቢው ለተማሪዎች እየቀረበ ያለው ውሃ ንፅህናው የተጠበቀ ባለመሆኑ ለበሽታው መንስኤ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል።
አሁንም አዳዲስ ህሙማን እየተመዘገቡ ነው መሆኑን የደረሰኝ ጥቆማ ያመላክታል።
የደሴ ውበት ከጦሳ ተራራ ሥር ይቀዳል።የልጆቿ ውበት እና ቅንነት ከምን እንደመነጨ ገና አልተረዳሁም።
ለሁሉም በላኮመልዛ ምድር ነኝ። ከአዲስ አበባ ዴሴ ለመድረስ ለገጣፎ፣ሰንዳፋ፣ሸኖ፣ደብረ ብርሃን፣ደብረሲና፣ሸዋሮቢት፣ሰንበቴ፣አጣየ፣ጨፋሮቢት፣ከሚሴ፣ሐርቡ፣ኮምቦልሻ የሚባሉ ከተሞች እና ከተማ ለመምሰል የሚንጠራሩ መንደሮችን አልፌአለሁ።
ጣርማበር እና ይፋት ለጸሐፊ የሚያጓጓ ተፈጥሮ እና ታሪክ የተሸከሙ ገጠሮች ናቸው።
የጣርማ በር ተራራ በዳኛቸው ወርቁ ውብ የሸዋ አማርኛ ቃላት የተገለጠ በተመለከትኩት ቁጥር የሚደላኝ የደብረ ሲና ኮፍያ ነው።
ደብረሲና ልገባ ስል «ዳኛቸው ወርቁ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት»የሚል ተገተር አይቸአለሁ።ያ ልዩ ደራሲ በትውልድ ቀየው አልተረሳም።
ይፋት ወትሮ ታላቅ እሥላማዊ መንግሥት ነበር።የኢትዮጵያ ክርስቲያን ነገሥታትን ያንቀጠቀጡት ኢማም አሕመድ አልጋሃዚ(አሕመድ ግራኝ የሚሏቸው) የመነጩበት የአዳል ሥርዎመንግሥት መነሻው ይፋት ነው።
የዛሬዋ የይፋት መዲና ሸዋሮቢት ትባላለች።ብስጩ ከተማ ናት።ራሳ የሚባለው ኮረብታዋ የጥይት ጩኸት አያጣም።እሸቴ ሞገስ እና ልጃቸው የዚህ አገር ሰዎች ናቸው።ኢክራምም የዚች የበረሃ ገነት ተክል ናት።
አማራ ላለፉት 50 ዓመታት ትግል ላይ ነው። ሸዋ ሮቢት፣አጣየ፣ኮምቦልሻ፣ዴሴ፣ሐይቅ፣ውጫሌ፣መርሳ፣ወልዲያ፣ቆቦን የመሳሰሉ በዚህ መሥመር የማውቃቸው ከተሞች በሕዝቡ ላይ የሚታየው ጠባሳ አለባቸው።
እስቲ ሌላ ወሬ...!
—ሸዋ ሮቢትን እንዳለፍን ነው።ገበሬ ናቸው።ሲጋራ ያጨሳሉ።
—ካራቆሬ አካባቢ ነው።ሰውየው ያርሳሉ።ከወገባቸው በላይ ግን ልብስ አለበሱም።በቃ ሌጣቸውን ናቸው።
—ከከሚሴ ከፍ ብሎ ነው።ባጃጇ ላይ የተለጠፈው ሰንደቅ ዓላማ የፓኪስታን እሥላማዊት ሪፐብሊክ ሆኖ አየሁት።
አሁን
ዴሴ ነኝ።ይህ የአማራ ምድር ጉዞየ የሐምሌ 2015ቱ የአማራ ወጣቶች የጠብመንጃ ላንቃ ከተከፈተ ወዲህ ሁለተኛየ ነው።ከሳምንታት በፊት በሌላዋ የክልሉ ከተማ ጎንደር ነበርኩ።ጎንደር «ሙሽራ ነሽ»በሚያሰኛት የጥምቀት በዓሏ ሰሞን ጭር ብላ አስተናግዳኛለች። ከእሷ ጋር ሳነጻጽራት የአዘቦቷ ዴሴ ትሻላለች።
መርሓባ!
መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ‼
መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በአማራ ክልል ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት የመካነ ሠላም ካምፓስ የመማር ማስተማር ሥራ ባለመጀመሩ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን የዘንድሮ ሪሚዲያል ተማሪዎች ለመቀበል የሕንፃ እጥረት ስላጋጠመው ወደ ሌሎች የክልሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ አድርጓል።
እነዚህ ተማሪዎች ከተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች መካከል:-
1.ወልድያ ዩኒቨርሲቲ፣
2.ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ፣
3.ወሎ ዩኒቨርሲቲ እና ፣
4.ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ
ይጠቀሳሉ።
የዩኒቨርስቲው ማስታወቂያ 👆 ተያይዟል።
/channel/Gazetaw
ጫት እና ጠቢባን
[በታመነ መንግሥቴ ውቤ]
የጥላሁን ገሰሰ የ_መንዙማ ስልት_ አዚያዚያም እና ጫት አቃቃም አስደማሚ ነበር ይባላል።ዘፋኙ በምስቅልቅል ከተሞላው ውብ እና አሳዛኝ የሕይወት ጎዳናው አንዱ የሱሰኝነቱ ነገር ነው።ጉዳዩ ተራ ፍረጃ እንዳይመስል ዘካሪያ ሞሐመድን ለምሥክርነት እንጥራው።
ዘካራያ መሐመድ «ጥላሁን ገሠሠ የሕይወቱ ታሪክ እና ምስጢር» በሚል ርዕስ ጽፎት አቶ ዳንኤል በላይነህ በ Ethiopian Book Forum ላይ «...የሕይወት ታሪክ፣ እንዲህ ይፃፋል፣አልያም ባይፃፍ ይሻላል፤»ሲሉ የጀርባ አስተያየት የፃፉለት መጽሐፍ ገጽ _331 ላይ እንዳስነበበው የታላቁ ኢትዮጵያዊ የሙዚቃ ከያኒ ጥላሁን ገሠሠ ጫት አቃቃም ራሱ ጥበብ ነው።
ዘካሪያ በመጽሐፉ ገጾች ውስጥ ሥዕላዊ ድርሰት ተጠቅሞ «የሙዚቃ ንጉሥ»የተባለውን ሰውየ የጫት ቅጠል ሥር ቁጭ ያደርገዋል። ጋዜጠኛው ቃል በቃል «...ጥላሁን ጫት ለመቃም ሲቀመጥ ጀለቢያ አጥልቆ፣እግሮቹን አሰካክቶ አልያም የግራ እጅ ክርኑን ትራስ ላይ አስደግፎ፣እግሮቹን አዝናንቶ መቀመጥ ይመርጣል፤»ይለዋል።
ዘካሪያ ሞሐመድ ዘፋኙን «ሞቅ ሲለው በመንዙማ ቃና እንጉርጉሮውን ያዥጎደጉደዋል፤»ካለን በኋላ፦
«እስቲ አቦል ቀደሙ፣እኔ ደህና ልሁን
ጊዜ ሸማኔ ነው፣ይሠራኛል አሁን።
ጸንቸ ብቀመጥ፣አያልፍም ከልኩ
ኖሬ ልሙት እንጅ፣ኑሮን እንደመልኩ
ከእጄ የወጣው ነገር፣አልታወቀም ልኩ፤»
የሚሉ ሥንኞችን እንደሚጨምርበት ጽፎልናል።
ተሸላሚው ቀኝ ጌታ ጸጋዬ ገብረ መድኅን ጫት የሚቅሙትን የዘመኑ ከያኒያን አምርሮ ተቆጥቷቸው ነበር ይባላል።እንዲያውም እሱ በኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ አብሾ የሚወስዱትን ጨምሮ «የደባት እጣቢዎች»ሲል ይሰድባቸዋል።
በአፍሪካ ጉዳዮች ተመራማሪው እና በባለ ቅኔው ጸጋዬ ገብረ መድኅን ዙሪያ «ምሥጢረኛው ባለቅኔ»በሚል ርዕስ የቅኝት መጽሐፍ ያስነበበው ሚካኤል ሺፈራው ጸጋዬ እንደ ጥላሁን ገሠሠ ያሉትን ከያኒያን«ቀድሞ ቤተ-ክኅነትን በዕጸ ፋርስ እና በአብሾ ትፋት ያልኮሰኮሱ የደባት እጣቢዎች፣ዛሬ በጫት ዶካኪ ትፋት የመድረክ አልኮስኳሾች ተተክተዋል።ከአባት ወደ ልጅ ትፋት፤»ብሎ እንደገለጻቸው አስነብቦናል።
ወጣቶች እየሰለጠኑ ነው‼
በምስራቅ ጎጃም ዞን፣ በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የሚገኙ በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ወታደራዊ ሥልጠና እየወሰዱ ነው ተብሏል።
ቤታችን ከቦታው በደረሳት መረጃ መሠረት የአካባቢው ተወላጆች መከላከያ ሠራዊት እና ከሚሊሻ እንዲሁም ከፖሊስ ጋር በመሆን ወታደራዊ ሥልጠና እየወሰዱ መሆናቸውን አውቃለች።
የሥልጠናው ተሳታፊ ወጣቶች መበራከት እና የታጣቂዎቹ ዛሬ መጣን ፣ነገ መጣን ወሬ ለከተማዋ ነዋሪዎች ከፍተኛ ሥጋት እንደሆነ ተጠቁሟል።
/channel/Gazetaw
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተሰማ❗
በ2013 ዓ.ም የገቡት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰሞኑን ከሰኞ ጀምሮ የትምህርት ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ለቤታችን ተናግረዋል።
"ተማሪዎቹ የትምህርት አስጣጡና አካሄዳችን ከሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ጋር ሲነፃፀር እኛን ወደ ኋላ ያስቀራል" ሲሉ ለቤታችን ገልፀዋል።
"የዩኒቨርስቲው የአካዳሚክ ካላንደር እኛን አንድ ዓመት ወደ ኋላ የሚያስቀር ነው ሊሰተካክልልንና ከሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ጋር ሊያስመርቀን ይገባል" ሲሉ ለቤታችን ተናግረዋል።
"የመውጫ ፈተና በጥር ወር 2017 ዓ.ም እንደምንወስድ ተነግሮን የተስማማም ቢሆንም ፣በጥር ወር ድጋሚ የሚፈተኑት እንጂ መደበኛ ተማሪዎች እንደማይወስዱ በትምህርት ሚኒስቴር የተነገረ ስለሆነ የግድ ሰኔ ላይ እንድንወስድ ሲሆን አንድ ዓመት ይባክንብናል" ይላሉ።
"ትናንት ማክሰኞ በዚሁ ጉዳይ ስብሰባ ማድረጋቸውን የገለፁት ተማሪዎቹ፣ በጥር ወር 2017 ዓ.ም እንደምንመረቅ ቢነገረንም ነገሩ አሳማኝነት የለውም " ብለዋል።
"በባለፈው ዓመት ሶስት መንፈቀ ዓመት እንደምንማር ቢነገረንም ፣ጊዜው ሲደርስ ግን ካፍቴሪያ ተዘግቶ እንድንወጣ ተደርገናል"በማለት ያስታውሳሉ።
"ዘንድሮም ተመሳሳይ የማታለል ተግባር እየተሰራብን ነው፣ከውስጥ የሰማነው ግን በሚያዚያ ወር እንደምንወጣ ነው" ሲሉ ለቤታችን ገልፀዋል።
"ቤተሰቦቻችን በዚሁ ዓመት እንደምንመረቅ ነው የሚያውቁት፣ ከሩቅ ቦታ በብዙ ወጪ እየመጣን እያለ አንድ ዓመት መጨመሩ ከቤተሰብ ጋር እንድንሰለቻች ያደርገናል" ሲሉ የችግሩን አሳሳቢነት ያስረዳሉ።
"እየደረሰብን ያለው የስነልቦና ጫና እና ችግር በቀላሉ የሚታይ ነገር አይደለም፣ይባስ ብሎ መማሪያ ክፍል ካልገባችሁ በፌደራል ፖሊስ በግድ ከዶርም እያወጣ እንድትገቡና እንድትማሩ ይደረጋል እየተባልን ተጨንቀን ነው ያለነው" ሲሉ በተሰበረ ልብ ለቤታችን ተናግረዋል።
"ጥያቄአችንን በሰላማዊ መንገድ ለማቅረብ የሞከርን ቢሆንም ለማባረር እና በጥበቃዎች እንድንገርፍ እየተደረገ ነው " ይላሉ።
"ጥያቄአችንን ለማን አቅርበን ማን እንደሚፈታልን ግራ ተጋብተናል የሚሉት ተማሪዎቹ፣ ዛቻውንና ማስፈራሪያው በመፍራት ከዩኒቨርስቲው የሚወጡ ተማሪዎች እንዳሉም ለቤታችን ጠቁመዋል።
" በባለፈው ዓመት ዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ካላንደሩን በተደጋጋሚ እያስተካከለ፣ አሁንም እንዲሁ በየጊዜው እየቀያየረ ችግር ውስጥ ከተውናል" ሲሉ ይናገራሉ።
"የመማር ማስተማሩን ሥራ የሚያስኬድ ቋሚ የአካዳሚክ ካላንደር ይውጣልን፣እንደሌሎቹ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሰኔ ወር የመውጫ ፈተና ወስደን እንመመረቅ" ሲሉ ይጠይቃሉ።
"መቼ ተመረን ጨርሰን፣ መቼ የመውጫ ፈተና ተፈትነን፣መቼ እንደምንመረቅ አናውቅም። ለቤተሰብስ ምን እንበል? እነሱ ዘንድሮ እንደምንመረቅ ስለሚያውቁ፣ ግን ይህ ሳይሆን ሲቀር ምን እንበላቸው?" እያሉ ጭንቀታቸውን ለቤታችን አጋርተዋል።
ዩኒቨርሲቲው አዲስ ፕሬዚዳንት በቅርቡ መሾሙን ገልፀው፣ "አዲሱ ፕሬዚዳንትም በቀድሞው አካሄድ ነው እየመራን ያለ፣የለወጠው ነገር የለም" ይላሉ።
"በዩኒቨርስቲው ለምናነሳቸው ጥያቄዎች ሃላፊነት ወስዶ የሚመልስልንና የሚያናገረን ሰው የለም" በማለት ተማሪዎቹ በምሬት ይናገራሉ።
"የባለፈውን ዓመት የአካዳሚክ ካላንደር አርትኦት ሰርተው፣በቴሌግራም በመለጠፍ እያታለሉን ነው።"
"አምናም እንዲሁ ነው የሆነው" ይላሉ።
"የተማሪዎች ሕብረት ፕሬዚዳንት የሆነው ተማሪም ስለ ተመረቀና ሊወጣ ስለሆነ አዲስ ፕሬዚደንት ለመመረጥ የተጀመረ ሲሆን ለችግሩ ግን ሌላ እንከን ሆኖብናል" ይላሉ።
በ2013 ዓ.ም የገቡት እነዚህ ተማሪዎች 3ኛ ዓመት፣ የሁለተኛ መንፈቀ ዓመት ላይ ነን ብለዋል።
ተማሪዎቹ አክለውም "የ3ኛ ዓመት የሁለተኛ መንፈቀ ዓመት ምዝገባ ስናከናውን የምንሰጠው ውጤት (Grade report) ላይ 4ኛ ዓመት እንደሆን ነው የሚያሳየው" ይላሉ።
"ስለዚህ የዩኒቨርስቲው የምዝገባ ቢሮ እና ትምህርት ሚኒስቴር የሚያውቁት የ4ኛ ዓመት ተማሪ እንደሆን ነው ።"
"እኛ ያለው 3ኛ ዓመት ሆኖ እያለ እንዴት የትምህርት ማስረጃችን በ2016 ዓ.ም ይሰራል? ወይም በ2017 ዓ.ም ከተመረቅን በዚሁ ዓመት የትምህርት ማስረጃችን መሰራት አለበት" ሲሉ ይጠይቃሉ።
"ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ማስረጃዎችን የመንግሥት የሥራ መፈለጊያ ጊዜ ገደብ ሁለት ዓመት መሆኑን አሳውቋል" የሚሉት ተማሪዎች "እኛ ግን አንደኛውን ዓመት በዩኒቨርስቲው ውስጥ ነን ፣ይህ እንዴት ይሆናል "በማለት ይጠይቃሉ።
ተማሪዎቹ ታዲያ "በየኮሌጁና በየትምህርት ክፍሉ ተሰብስበን የነበረ ቢሆንም ምንም የሚያሳምን ነገር አልተነገረንም" ሲሉም አክለዋል።
"የተወሰኑ የትምህርት ክፍሎች ለመስክ እንዲወጡ ሊሆን ነው፣ ይህ የሚሆነው በመጨረሻው ዓመት ላይ ሆኖ እያለ፣ አሁን እንዲወጡ መደረጉ በተባለው ጊዜ እንደማንጨርስ አመላካች ነው" ይላሉ።
"የያዝነውን የትምህርት ጊዜ በየካቲት ጨርስን እንደምንወጣ በመስከረም ስንገባ ተነግን ነበር" የሚሉት ተማሪዎቹ ፣ "አሁን ግን በሚያዚያ ነው የምትጨርሱ ተብለናል።"
"ስለዚህ በሚያዚያ ዩኒቨርሲቲው የእኛን ባች እንደሚያስወጣን ከውስጥ መረጃ ደርሶናል፣ ነገር ግን እስከዚያው እያታለሉን ነው"ይናገራሉ።
ይህ የአካዳሚክ ካላንደር ችግር በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዳለም ከሌሎች ምንጮች መረጃው ለቤታችን ደርሷታል።
ቤታችን ሁኔታውን ለማጣራት ወደ ተማሪዎች ሕብረት ፕሬዚዳንት በስልክ ለማግኘት ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም።
የገንዘብ እጥረት ያለባቸው ተማሪዎች በታጣቂ ኃይሎች የተዘጉ መንገዶችን ለማለፍ በሌላ አማራጭ መንገድ ለመሄድ መቸገራቸውን እየተናገሩ ነው።
ከመርጡለ ማርያም ዐባይን ተሻግሮ መካነ ሰላም የሚያስገባው መንገድ ለተማሪዎች ዝግ መሆኑን ተከትሎ ከጎጃም ተነስተው ወደ መቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ መግባት የሚፈልጉ ተማሪዎች "ሸዋ ሲሄዱ ትግሬ ተሸኙ፤" የሚያሰኝ ሌላ ረጅም እና በሰቆቃ የተሞላ መንገድ መርጠዋል።
ተማሪዎቹ "በከንቱ እየተጋላታን ነው፤" ይላሉ።
በመርጦለማርያም—ዐባይ በርሃ ከዚያም መካነ ሰላምን አልፈው በአንጻራዊነት በአጭር መንገድ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መግባት እየቻሉ፣በባሕር ዳር—ደብረታቦር—ጋሸና—ወልዲያ—ደሴ እያሉ መቅደላአምባ መድረስ ግዴታ ሆኖባቸዋል።
አዳር እና ውሎ የሚፈጥረውን ወጭ ጨምሮ ከዘረፋው ጋር ገንዘብ መክፈል የማይችሉ የድሃ ገበሬ ልጆች ከትምህርት ገበታቸው እየተገፉ መሆናቸውን ቤታችን ተረድታለች።
አስተያየታቸውን የሰጡን ተማሪዎች እንደሚሉት አማራጭ መንገዶችን ለመጠቀም የገንዘብ አቅም እንደሌላቸው ገልጸዋል።
ሾፌሮች ፈቃደኛ ከሆኑ በአስፈሪው ግን በአጭሩ የመርጡለማርያም መንገድ ተጉዘው የመጣውን ለመቀበል ማሰባቸውን የሚናገሩም አሉ።
ጋይንት ጨጨሆ መድሃኒዓለም አካባቢ በሚገኘው ጥቅጥቅ ጫካ ውስጥ ደግሞ ያላቸውን ገንዘብ፣ ሥልክ እና ሌሎችንም ነገሮች ማስረከብ የተማሪዎች ግዴታ ከሆነ እንደሰነበተ ከቦታው የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።
በአማራ ክልል ታጥቀው መንግሥትን የሚዋጉ ኃይሎች ተማሪዎች ከትምህርታቸው ርቀው እንዲቆዩ ፍላጎት እንዳላቸው የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምሥሎች እየወጡ https://youtu.be/vzS-D2CSyLQ?si=q6miUMg2L7MERZkw ነው።
የቤቱ አባወራ ከቀናት በፊት ከጎንደር አዘዞ አውሮፕላን ጣቢያ ወደ አዲስ አበባ በነበረው በረራ ቢያንስ ሁለት ተማሪዎች ውዱን የሰማይ ላይ መንገድ መርጠው ሲጓዙ ተመልክቷል።
ሁለቱም ሴት ልጆች ከአይከል ከተማ እንደተነሱ ነግረውታል።
መዳረሻቸውም ከጎንደር ፍጹም ወደምትርቀው ሐረር አካባቢ ነው።
ከሁለቱ ሴት ተማሪዎች አንዷ መሠረታዊ የሰው ልጅ ፍላጎት የሆነውን ልብስን ትታ የቤተሰቦቿን ገንዘብ የአውሮፕላን ትኬት መግዣ ያደረገች በሚመስል ሁኔታ አሳዛኝ አለባበስ ውስጥ ሆና ተመልክተናታል።
ፊቷም ክፉኛ ዳምኗል።
በርዕሰ ምሁሩ ብርሐኑ ነጋ የሚመራው ትምህርት ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ እስከዚህ መረጃ መለጠፍ ጊዜ ድረስ የሰጠው አሳብ የለም።
ለእጅጋየሁ ሽባባው
═════════════
ሙዚቃ ነሽ አንች የተኖረ ቅኔ
ሳቅና ትካዜ ጽድቅ እና ኩነኔ!
═════════════
/channel/Gazetaw
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተማሪ ገደፈው አስማረ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን ገለፀዋል።
ለተማሪ ገደፈው አስማረ የሕሌና ፀሎትና የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ያካሄዱት ተማሪዎቹ፣ የጎዳና ላይ ጉዞ በማድረግ የተሰማችውን ሐዘን ገለፀዋል።
የተማሪ ገደፈው አስማረ የቀብር ሥነ ሥርዓት በትውልድ ቦታው ደቡብ ጎንደር ዛሬ ተከናውኗል።
ለጓደኞቹና ለቤተሰቦቹ መፅናናትን ተመኝተዋል።
/channel//Gazetaw
ቋሪት ያለው መከላከያ ከነሚኒሻው ከተማዋን ለቆ መውጣቱን ከአንድ ምንጭ ጥቆማ ደርሶኛል።
መከላከያ ከክልሉ ሊወጣ ይችላል፣ በማለት መንገዶች እየተዘጉ ትጥቁን ለማስቀረት መታሰቡንም አድርሶኛል።
ለዚህም ይመስላል በተለያዩ አካባቢዎች መንገድ እንዲዘጋ የተደረገው።
ከአዲስ አበባ-ደሴ ያለው መንገድ መዘጋቱንም ሰምቻለሁ። ጎጃም'ም ስራዎች ተጀምሯል።
ቤተሰቦቼ እንዴት ዋላችሁ? እንዴት አደራችሁ??
•
ፍቅር ተፈትፍቶ የሚጎረስባትን መንደር ዴሴን ባለፈው መቃኘታችን ይታወሳል፡፡ ስለደሴ አውርተን አንጠግብም… ተወርቶላትም አያልቅም፡፡
ትናንት ምሽት ቤተሰቦቻችን በሙሉ ሐጂ መሐመድ ሕንጻ ላይ ቁብ ብለው… ስለ ሼሕ ሑሴን ትንቢቶችና ስለ ፊታውራሪ አመዴ ለማ ሥራዎች ሲወያይ ቆይቶ ለመዝናናት ወደ ሸምበቂት የባሕል ምሽት አምርቷል፡፡
የትናንት ምሽት ገጠመኛችን እነሆ፦
•
ሸምበቂት የባሕል ምሽት ትናንት ምሽት፡-
የዘወትር ደንበኞችና አንዳንድ እኛን የመሠሉ ዕንግዶች ሸምበቂት የባሕል ምሽት ሠፍረው የምሽቱን ጨዋታ መጀመር ይጠባበቃሉ፡፡ እኛም ገብተን የሚመቸንን ቦታ መርጠን በባሕላዊ መቀመጫዎች ተተቀመጥን በኋላ ቤቱን መቃኘት ጀመርን፡፡ ኹሉ ነገሩ ባሕላዊ የኾነ ማራኪ ቤት ነው፡፡ ተመቀመጫዎቹ እስተ መደገፊያው፤ ተጌጣጌጦቹ እስተ ሙሉ ሥርዓቱ ድረስ ባሕላዊ የኢትዮጵያን የጌጣጌጥ ሥርዓት ያሟላ ነው፡፡ ኹሉ ነገሩ ይማርካል፡፡
ሁሉም ሰው ገብቶ የሚጠጣ ነገር እየተያዘ… ሰውም ከጎን ሼጎጥ እየተዴረገ… የሙዚቃ አጫዋቾቻችን (አዝማሪዎች) በመረዋ ድምጻቸው ማንጎራጎር ጀምረዋል፤ ባሕላዊ 'ባንዱ' በከበሮ፤ በማሲንቆና በዋሽንት ያጅባቸዋል፡፡ የቤቱ ሰው በጭብጨባ ያሞቃቸዋል፤ ግጥም ያዋጣል፡፡ የተደሰተ ደግሞ ይሸልማል…. ያልተደሰተ ባይኖርም ድንገት ቢኖር ግን በይሉኝታ ይሸልማል፡፡ ቅር እያለውም ቢኾን ትንሽ ገንዘብ ያዋጣል፡፡ በተለይ ፍቅረኛው አጠገቡ ያለች ተኾነ ጥሩና ሐብታም መሥሎ ለመታየት መዥረጥ አድርጎ ይሸልማል፡፡ ታዲያ ይህ ነገር ሐበሾች ዘንዳ የተለመደ ነገር ነው፤ አዲስ ሰው እንደተጠጋን መልካም ሰው እንመሥላለን፡፡ ከሸንበቂት እስከ ደደቢት እናዝናናለን፡፡ ስንቆይ ግን ለእግር ጉዞም ብቻችንን እንሯሯጣለን፡፡ በይህ ዙሪያ በእግር ጉዞ የጀመሩት ጓደኞቼ ተረፈ ድንበሩና ስላንቺ ዴስታ ተደብረ-ሊባኖስ እስተ ጣና ገዳማት፤ ተደብረ-ዳሞ እስተ ግሸን ደብረ-ከርቤ… አሁንም ተነጣጥለው አይሔዱም፡፡ ክብር ይገባቸዋል!
አዝማሪው በተመሪነት ማንጎራጎር ጀምሯል፡፡
•
“እንዲያው ዝም ብየ ስመለከትኽ
ሰውነት ቢሻውን ትመስለኛለኽ!” (እኔን እየተመለከተ)
ቤቱ እኔን እያየ ሳቁን ለቀቀው… ነቀፋም ኾነ ሙገሳ የጨዋታ ቦታ አይረበሽም እንጂ ተበሳጭቼ ናበር፤ እህ…የሰውነት ቢሻውን ያህል ቦታ ቲሠጠኝ ደስ ሊለኝ ይገባል እንጂ የምን ብስጭት…..፡፡
“መቸም አይሳንህ ቸሩ የኔ ጌታ፤
ሸጋውን ሹምልን በትራምፕ ቦታ!” (እንደገና አነሳኝ - ያኔ ትራምፕ ፕሬዚደንት ነበር)
“ኧረ ደሴ ደሴ ገራዶ ገራዶ
አለቀልሽ ልቤ ተንዶ ተንዶ…” (ሰሊናን መኾኑ ነው… ተው አዝማሪ የሠሚር ዐይን በጨለማ ሲቀላ ሾፍኹት)
•
"እንደምነው ወሎ--የሚካኤል ሀገር
እንደምን ነው ጎጃም--የነበላይ ሀገር
እንደምን ነው ጎንደር--የመይሳው ሀገር
ጅማስ እንደምን ነው--የኣባ ጅፋር ሀገር
ትግራይስ እንዴት ነው-የዮሐንስ ሀገር
ሥማቸው ሲጠራ --ድንበር የሚያስከብር!”
“የነ ሒዊ ሀገር ወይ ደሴ ማማሩ
ቆንጆዎቹ ልጆች ጥለውን ባይበሩ”
“ራያ ተወልዶ ራያ ያደገው
ይኖራል ዘላለም እንዳስደገደገው
በዓለም መጀመሪያ የሠለጠነው
ጨረቃ ላይ ወጥቶ ዐይቶ ያጠናው
ወደድሽም ጠላሽም የራያ ልጅ ነው!”
.
ብታምኝም ባታምኝም አንድ ነኝ ላገሬ
ወሎም ሀገሬ ነው
ራያ አገሬ ነው..
ጎንደር ሀገሬ ነው
ጅማም ሀገሬ ነው
ኢትዮጵያ ቁጭ ብየ የሚነካኝ ማነው!”
.
“እኔን የሚያስቁኝ ሠሚርና መብራት
ደርሰው ይጠፋሉ እየተበላ ዕራት”
“የኔ አሕመድ ሙሣ በጣም ደብሮኻል…
የሰማንያ ምሽቱን የቀሙት መሥለኻል”
•
“ልጅ ወለድኹኝ ብላ ትኩራበት እናቱ
ፀሐይ የመሰለ የነጣ ካ’ናቱ” (ወይ እኔ መከራዬ- ካልሸለምኹ አልለቀቅም)…
•
“የታደለው አዳም እግዜር የመረቀው
ሔዋን ተሠጠችው እንቅልፍ እንደጣለው፤
ይብላኝ ለአሁኑ አዳም ለዚህ ለምስኪኑ
መቸ በተኛና ከጎኑ በሾለኩ… ለምትል ሔዋኑ…”
ይህቺ የሌላ ገጣሚ ብትኾንም ዘፈን ማን ላይ እንዳነጣጠረች ባይገባንም ስቀናል፡፡
•
በሸምበቂት የባሕል ምሽት ማፈር…መሸማቀቅ የለም፡፡ በማኅበረሰቡ የሚያሳፍሩ ንግግሮች እንደ ልብ ይነገራሉ፡፡ እንዲያውም ብዙ ነውር የመሥሉ ነግገሮች በዘፈን ቀለል ብለው ሲቀርቡ ቤቱ ውስጥ ብዙ ቀልደኞች የተጠራቀሙ መስለውኝ ነበር፡፡
“አንድ እግሯን አንስተህ--አንድ እግሯ ሰቅለኽ
ምን ዕቃ ጠፍቶሃል ትፈልጋለኽ…
ከፍ በል ዝቅ በል ታገኘዋለኽ”
•
“የፊት አሳይቶ ቢሠጠኝ የኋላ
እንደ አስቴር አወቀ ወይኔ ጉዴ ፈላ”
ዓለምዬ ደማሙ…. ኧረ ገዳሜዋ… ኧረ እንደምን አለ’ኽ…
ዘመዴ ዘመዴ
“ከወሎ ኮምቦልቻ አምባሰል ይርቃል
ሰው ወዶ መለየት እንደምን ይጨንቃል…”
“የኔማ ዘክዬ አትይ ከላይ ከላይ
ሚስቴን ከተጋራህ ዕርዳኝ የቤት ክራይ!”
.
ስለ ሙቀጫው መስፋትና ስለ መውቀጫው መቅጠን እንደ ልብ ይቀደዳል፡፡ የጨዋታ ማድመቂያ ኾው እንደ ልብ ይሳቅባቸዋል፡፡
“ወሎ…ወሎ…” የምትለው ዘፈን ታፋቸው አትጠፋም፤ ወሎን ቢያሞግሷትም፤ ከሌላው ቢያስበልጧትም ሌላውን ግን አይጥሉም፡፡ ወሎዬዎች ለኹሉም ኅብረተሰብ ፍቅርና አክብሮት አላ’ቸው፡፡
በተዘዋወርንባቸው ቦታዎች ኹሉ እንዳገኘኻቸው የሚያቀርቡኽና እንግዳ መኾንህን እንድትረሳ የሚያደርጉኽ ወሎዬዎች ከአዕምሮ አይጠፉም፤ ከልብ አይወጡም፡፡ በልብ የገባ ደግሞ ዘለዓለም ይኖራል፡፡
ወሎዬዎች ስለአጼ ቴዎድሮስ በጀግንነት ይፎክራሉ፤ ከውስጣቸው በወኔ ያዜሙለታል፡፡ ስለበላይ ዘለቀ ጀግንነት ኢትዮጵያዊ ሊኖረው በሚገባው ልክ አክብሮት አላቸው፡፡ ቡና ስለሚታፈስበት ለምለሙ ምድር ጅማና ስለ አባ ጅፋር ሀገራዊ አክብሮታቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ታሪክን ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ስለ ኹሉም የሃገራችን ክፍሎች በዕውቅና ላይ ተመሥርተው በየዜማው ያስደስታሉ፡፡
አቦ! ፍቅር መጀመሪያውም መጨረሻውም ወሎ ነው፡፡
ወሎ ገራገሩ…. ዛሬም ስለወሎ አልጨረስንም፡፡ አሕመድ ጸጉር ቤት አሕመድና ዳንኤል ጫት እንቀማምስ ብለውኝ ምንም እንኳ ባልቅምም ለውዝ ስለምጠቀም እንጫወትና እመለሳለሁ፡፡ አንዳንድ ቦታ እኮ "አሕመድና ዳንኤል" አብረው አይቅሙም፤ ምግብም አይበሉም፡፡ ሌላ የማይቅም ሰውም ካልቃመ ለውዝ ለይተው አያስበሉትም፡፡ ይኽ ወሎ አይሠራም…. ወሎ ሰብዓዊነት…ብፍቅር ይቀድማል፡፡
•
"የኔማ መላጣው ወይኔ ጉድ ሠራኝ
የሚሸልም መሥሎ ወርም አፕ አረገኝ….።"
ቀጥሏል...
ሸጋው ማሬ
ኅዳር 2007
ሸምበቂት፣ ዴሴ
መነነ ወታደር
ዳር ድንበር ጠባቂዉ ፣
ወቶ አደር የነበር ሀገር አስከባሪው ።
ዛሬ ገዳም ገባ ፣
ለሐጢያቱ ስርየት ባሩድ ይዞ መባ ።
ለህዝቡ ቢጨነቅ ቢያስብ ለሀገሩ ፣
መነነ ወታደር ወረደ ከክብሩ ፣
ሰገደ ዝቅ ብሎ ፣
ዲሽቃ ና ድሮኑን ባሩድ አቀባብሎ ።
መጀገን እንዲህ ነዉ ¡
ራስን ማወረድ ፣
የክርስቶስን ቤት ጉልላቷን መናድ ።
እንዲህ ነዉ ምናኔ ¡
ፅድቅን በማራከስ መሸመት ኩነኔ ።
እንኳን ደስ አላችሁ ፣ እንኳን ደስ አለን!
https://eventaddis.com/ የድረገጽ አገልግሎቱን በይፋ ጀመረ !
ላለፉት ሁለት ዓመት የኩነትና የመዝናኛ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲያሰራጭ የቆየው "EventAddis/ሁነት አዲስ" ዛሬ ሰኞ የካቲት 11 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ በይፋ የድረገጽ አገልግሎት ጀምሯል።
https://eventaddis.com/ በተሰኘው ይፋዊ ድረገፁም ትላንትን ዛሬንና ነገን የሚያስተሳስሩ ኩነትና ኪናዊ ጉዳዮችን ብቻ በስፋትና በጥራት ያቀርባል።
በዚህ ድረገፅም አምስት የይዘት ክፍሎች ይገኛሉ። እነዚህም የይዘቶች ክፍሎች።
1."ኩነተኛ":-ኩነት እና እኛ ከተሰኙ ሁለት ቃላት የተገኘ ቃል ነው። ትርጉሙም ኩነት እና እኛ ማለት ነው።በ"ኩነተኛ" ይዘት ክፍል በአዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች የሚከናወኑ ልዩ ልዩ ኩነቶች፣ዕለታዊ የኪነጥበብ መረጃዎች ፣ሀገራዊና ዓለምአቀፍዊ በዓላትን ጨምሮ ሌሎችም የኛ የሆኑ የኩነት መረጃዎች የሚቀርቡበት የድረገጽ ይዘት ክፍል ነው።
2."የሐሙስ መረጃዎች":-የሐሙስ መረጃዎች የሳምንቱ ዋና ዋና የኪነጥበብ መረጃዎች በአጫጭሩ ተመጥኖው የሚቀርቡበት የድረገጽ ክፍል ነው።
3."#እንዴት ነበር?":- ሀሽታግ እንዴት ነበር ? ልዩ ልዩ ኩነቶች ካለፉ በኃላ "እንዴት ነበሩ ?" በሚል ልዩ ልዩ የኩነት ዳሰሳዎችና እይታዎች በድረገጹ አዘጋጆችና ቤተሰቦች የሚቀርቡበት የድረገጽ ክፍል ነው።
4."ሥነ ኪን":- ልዩ ልዩ የኪናዊ ስራዎች ላይ ዳሰሳዎችና ሂሶዎች የሚቀርቡበት የድረገጽ ክፍል ነው።በዚህኛ የይዘት ክፍል ስለመጻህፍት፣ ቴአትር ፣ፊልም፣ ሥዕልና ቀራጻቅርጽ በአጠቃላይ ሥነ ጽሑፍዊ ፣ሥነጥበባዊ እና ኪነጥበባዊ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ ይተነትናሉ ።
5."ትዝታ ከመጽሔትና ጋዜጣ":በትዝታ ከመጽሔትና ጋዜጣ ቆየት ካሉ መጽሔትና ጋዜጣዎች ላይ የተገኙ አስገራሚ ዜናዎች ፣ ቃልመጠየቆች ፣ መጣጥፎች ወዘተ የሚቀርቡበት የድረገጽ ይዘት ክፍል ነው።
ድረገጹ ከእነዚህ ይዘቶች በተጨማሪም በቅርቡ ሌሎች አገልግሎቶችን ይጀምራል ።
የEventAddis/ሁነት አዲስ ቤተሰቦችም ይህን የተረጋገጡ ኪናዊና ኩነታዊ መረጃዎች የሚቀርቡበትን ድረገፅ በማስተዋወቅ እንዲሳተፉ በይፋ እንጠይቃለን።
#Event_Addis
https://eventaddis.com/
"ሰው ሠራሽ የአፈር ማዳበሪያ እንዳንገዛ ተከልክለናል" የጎንቻ ወረዳ ወጣት አርሶ አደሮች❗
የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ወጣት አርሶ አደሮች የአፈር ማዳበሪያ ከወረዳው የኅብረት ሥራ ማህበር መግዛት እንዳልቻሉ ለቤታችን ተናግረዋል።
ለ2016/7 ዓ.ም የምርት ዘመን የሚውል ሠው ሠራሽ የአፈር ማዳበሪያ በምስራቅ ጎጃም፣ ዞን በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ አርሶ አደሮች ስሞኑን እየተሰራጨ ይገኛል።
ይህ ሲሆን ታዲያ የአፈር ማዳበሪያ ሽያጩ ወጣት አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ አላደረገም ተብሏል።
የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የሌላቸው እነዚህ ወጣት አርሶ አደሮች፣ የአፈር ማዳበሪያ በመሬት ደብተር አማካኝነት በመሰጠቱ ማዳበሪያ ማግኘት እንዳልቻሉ ለቤታችን ተናግረዋል።
በባለፈው ዓመት ተከስቶ የነበረውን የአፈር ማዳበሪያ እጥረት ድጋሚ እንዳይከሰት በማሰብ ሰሞኑን ጀምሮ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች እየተሳራጨ ይገኛል።
"ከባለፈው ዓመት የተሻለ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት እንዳለ ቢነገረንም እኛ ግን እያገኘን አይደለም" ብለዋል።
"ከወረዳው ግብርና ጽ/ቤት በአካል ተገኝተን " የአፈር ማዳበሪያ የምናገኝበት መንገድ እንዲመቻች ብንጠይቅም፣ ከቤተሰቦቻችሁ ውሰዱ "የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ወጣቶች ይናገራሉ።
"ከወረዳው ኅብረት ሥራ ማህበር ለመግዛት ሙከራ ብናደርግም፣ በመከላከያ እና በሚኒሻ እየተደበደብን ድምፃችንን የሚሰማን አተናል" ይላሉ።
"ከቤተሰብ እንዳንጠይቅ እየተሰጡ ያለው ግማሽ ፣ግማሽ ኩንታል ስለሆነ እንዴት አድርገን ስጡን እንበል" ይላሉ።
የአፈር ማዳበሪያ እየተሰጠ የሚገኘው በመሬት ማረጋገጫ ደብተሩ ላይ ባለው የጥማጅ ብዛት ስለሆነ ወላጆች ለልጆቻቸው ለማካፈል መቸገራቸውን ይገልፃሉ።
ከመጋቢትና ሚያዝያ ወር ጀምሮ የሚዘሩ ሰብሎች መኖራቸው ችግሩን የበለጠ አሳሳቢ አድርጎታል።
"በየአፈር ማዳበሪያውን በወቅቱ አግኝተን በወቅቱ ለሚፈለገው ዓላማ እንድናውለው አፋጣኝ መፍትሔ ይሰጠን" ሲሉ ይጠይቃሉ።
ባለፈው ዓመት የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት እጥረት በአርሶ አደሮች ላይ ችግር ሆኖ ማለፋ ይታወሳል።
@Gazetaw
ቲክቶክ ለሚቀላችሁ፦
https://vm.tiktok.com/ZM6Tx3Wjk/
ፌስቡክ ለሚሻላችሁ፦ https://www.facebook.com/100064752820499/posts/pfbid02f9aEDyDcQs8kh4kQTaHzG199GmmHU9baEg45QAfHiYUqQtpbXHUuobRpTK5wxLwnl/?app=fbl
ውስጥ አለላችሁ።
ታመነ መንግሥቴ ውቤ
/channel/Gazetaw
From Inbox❗
ከመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ:-
ሠላም እንዴት አለህ?
ይገርምሃል ዛሬ የካፌ ሰልፍ የሰለቸው ተማሪ እረብሻ አንስቶ በአንድ ገፅ ያለውን የበር መስተዋት አርግፎታል።
በብዙ ጥረት ካረገቡት በኋላ ቁርስ መብላት የተጀመረ ቢሆንም በድጋሜ ሊረበሽ ይችላል ብለው የሰጉ ተማሪዎች ቁርሳቸውን ከውጭ በልተዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ስብሰባ ያካሄዳል።
የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ መካነ ሰላም ካምፓስ ይሂዱ ወይስ አይሂዱ የሚለውን ውሳኔ ያሳርፋሉ ተብሏል።
በዩኒቨርስቲው የመመገቢያ አዳራሽ የተፈጠረው የዛሬው ረብሻ ለውሳኔው ያግዛል ተብሎ በተማሪዎች ዘንድ በጉጉት ይጠበቃል።
በሌላ በኩል ደግሞ ዩኒቨርሲቲው ከአካባቢው የኮማንድ ፖስት ፋኖ'ን ያደራጃሉ ወይም ይገድፋሉ ተብለው የተጠረጠሩትን የአስተዳደር ሠራተኞች እና መምህራን ላይ ክትትል እያደረገ ነው።
ተጠርጣሪዎች ደግሞ በዩኒቨርስቲው ውስጥ ከዝቀተኛ እስከ ከፍተኛ የስራ መደብ የሚሰሩ ናቸው።
በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደት መቋረጡ ተሰምቷል❗
በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደት ከተቋረጠ ሳምንት ማለፋን ለቤታችን የደረሳት ጥቆማ ያመለክታል።
በምን ምክንያት እንደተቋረጠ እንደማያውቁት የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ለቤታችን ነገረዋታል።
ይህን ተከትሎ በዩኒቨርስቲው በካፍቴሪያ አግልግሎት ላይ የምግብ ጥራት ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን ተማሪዎቹ ለቤታችን ገልፀዋል።
በተለይ በዋናው ግቢ ችግር ይበረታል የሚሉት ተማሪዎቹ፣ የዋይ ፋይዳ አግልግሎት እንደተቋረጠም አክለዋል።
"የመማር ማስተማር ሂደቱ መቼ እንደሚጀምር አናውቅም" የሚሉት ተማሪዎቹ፣ በነቀምት ከተማና አካባቢዋ የትራንስፖርት እና የንግድ አግልግሎት እንደተቋረጠም ጨምረው ገልጸዋል።
ስለተቋረጠው የመማር ማስተማር ሂደት ከሚመለከታቸው የአስተዳደር አካላት ምንም የተባሉት ነገር እንደሌለም ለቤታችን ገልፀዋል።
ሥለ አዲሱ ትውልድ
[በታመነ መንግሥቴ ውቤ]
የሰንበት ወግ...
የትውልድ ወግ በርክቷል።
እልፍ ያዝዙ የነበሩት መንግሥቱ ኃይለማርያም «ትግላችን»በሚሉት መጽሐፋቸው «የእኔ ትውልድ»ማለት ያበዛሉ።
ትውልዱን የመምራት ዕድል አግኝተው የሆነው ሆኗል።
የእኛው መሪ ዐቢይ አሕመድ ዐሊ «የመደመር ትውልድ»የሚል መጽሐፍ እስከመክተብ ደርሰዋል።
በመጽሐፏ ገጾች ላይ ውብ አገላለጾች አሏቸው።እየመጣ ያለውን ትውልድ በተስፋ አየር ሞልተውታል።
ዘመነ ካሴ ጫካ ሆኖ ሥለ አዲሱ ትውልድ ደጋግሞ የሚናገር ጎልማሳ ሆኖ እናየዋለን።
እሱ እንደሚለው ከሆነማ የትግላቸው ዓላማ አዲሱን ትውልድ በአሮጌው ላይ ለመትከል እየተሰው ነው።
ሮፍናን ኑሪ ትውልድን በሙዚቃ ውስጥ ሊኩል ቆሞ አለ።
ፎፊ ደጋግሞ «የእኔ ትውልድ» ሲል ይደመጣል።
ኧረ የዘፈን ድግሶቹ ሁሉ ከዚሁ ሐረግ ይመነጫሉ።
የዚች ወሬ ጣፊ የትውልድ ተጋድሎ መጀመሩን ለመረዳት ሕዳር 26 ቀን 2014 ዓ.ም መምሸት ነበረባት።
በዚያች እሁድ ዕለት «የትውልዴ ገድል»የሚል አሳብ በአዕምሮው ተሰነቀረ።
እነሆ ከዚች ማታ ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 2014 ዓ.ም የዘገበውን የለውጡ ዘመን ጦርነት«የትውልዴ ገድል»በሚል ማስታወሻ ሥር ሸክፎታል።
ብዙ የዚህ ትውልድ አባላት አባቶቻቸው የዛሬ አምሳ ዓመት ጀምረው ያልፈጸሙትን ዐቢዮት እየቋጩ እንደሆነ ይሰማቸዋል።
እንደ ቃላችን ያውለን...!
/channel/Gazetaw