gazetaw | Unsorted

Telegram-канал gazetaw - እዚህ ቤት

1029

አገር አገር ስልሽ—ደስ ይበልሽ በጣም ኢትዮጵያዊ ሆነን —የሚያግባባ አናጣም! ዕወቂው ዐለሜ__‼ ኢትዮጵያዊ መሆን —የውርስ እንቁጣጣ በአጥንት ክስካሽ—በደም ቅብ የመጣ! (ታመነ መንግስቴ_አባ ወራው) ግቡ፦ስለ አገር፣ፍቅር፣ሰላም፣ባሕል ና ጥበብ እናወጋለን! ጀበናዋ ተጥዳለች—ስኒዎቹ ሳይሞሉ፣የገባችሁ ሳትቋደሱ ረከቦት አይነሳም! ክህሎት፣ጥበብ፣ መሻታችሁ በቤቱ ይስተናገዳሉ። ትውልድ❤

Subscribe to a channel

እዚህ ቤት

«...አምላክ ካለ እና እድሜ እና ጥንካሬ ካገኘሁ የጥንቱን የኢትዮጵያን ወሰን ከሕንድ ውቅያኖስ እስከ ካርቱም ያለውን ሳላስመልስ አልቀርም...»

ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ለእንግሊዟ ንግሥት ቪክቶሪያ መልዕክተኛ ሬኔል ሩድ የነገሩት!

የኤርትራ እንቆቅልሽ ገጽ 122

/channel/Gazetaw

Читать полностью…

እዚህ ቤት

ሥለ ቅርጫው😀

/channel/Gazetaw

Читать полностью…

እዚህ ቤት

https://vm.tiktok.com/ZMMGh5D3R/

ቤቴ ውስጥ ያለ ጉድ🙄

Читать полностью…

እዚህ ቤት

የበረከት በላይነህ ሥንኞች፡-
.
.
“ጎዳናው”
.
(በረከት በላይነህ )
.
.
ጎዳናው ይገርማል
ይገርማል መንገዱ
እግረኛው ይገርማል
.
ሸራ ጫማ ባ'ይነት በነጫጭ ካልሲ በሲኪኒ ሱሪ
ከመምህሩ ጋራ አይስክሬም ሚልስ ያይስኩል ተማሪ
ፀባይኛ ወጣት
ጃንቦ ተከልሎ በምርቃና ሆኖ ሐሳብ የሚፈትል
አንዲት ሙ...ደኛ እናት በ'ድሜ ከልጆቼ አንሳለሁ የምትል
ፒዛውን የሚገምጥ ጭማቂ የሚመጥ አራዳ አባወራ
በሚስቱ ትከሻ በልጆቹ ምላስ ቅምጥ የሚጣራ
.
አንድ ፍሬ ሴቶች
.
በተገዛ ቅንድብ በተገዛ ጸጉር በተገዛ ጥፍር በውሰት ወዘና የተብለጨለጩ
ማኪያቶውን ከበው ለውስኪ ‘ሚንጫጩ
ጅናም ጅንሳም ወንዶች በሴቶች ጫጫታ የሚቁለጨለጩ
.
ይገርማል ጎዳናው ይገርማል መንገዱ
ድንቡሽቡሽ ሕፃናት በቶም ኤንድ ጄሪ ሱስ ቀልባቸው የከሳ
በአይፎኑ አጮልቆ ያንጀሊናን ከንፈር የሚስም ጎረምሳ
.
ቀውጢ ዳያስፖራ...
.
የሎቲው የቁምጣው የቲሸርቱ ጥለት የተንዘረፈፈው
አማርኛን ሲሸሽ "what's up" የጠለፈው
.
ነቄ ብላቴና...
.
ከዮፍታዬ ቀዬ ካ'ዲስ ዓለማየሁ ከመዝገቡ መንደር
የአዲስ አ'ባ ጥሪ በቁምጣ ያበረረው
ከቅኔ ተጣልቶ ከግዕዝ ተኳርፎ ሎተሪ 'ሚያዞረው
.
ጸዴ ብላቴና...
.
ከባላገር ዘመን ከጨለማ ዘመን ወደ ብርሃን ጥግ ተሸጋገርኩ ብሎ
በሸንኮራ ምርኩዝ ከተማ ሚያካልል መቋሚያውን ጥሎ
ነፍሱ እየሰለለች በከተሜነት ወግ ባ'ራዳነት ልምሻ
ሲያዘግም የሚውል ሊስትሮውን ጭኖ በታቦት ትከሻ
.
ፎቆቹ..
.
በመስታወት ቁመት በቆርቆሮ ገጾች ባ'ልሙኒየም ጥራዝ የተብረቀረቁ
የጌቶቻቸውን ዕድሜ ‘ሚያሳብቁ
ሁሉም... ሁሉም... ሁሉም ጥግ ናቸው
ለወደቀ ወገን ይራራል ልባቸው
.
ሁሉም... ሁሉም
ከዘለለት ጥድፊያ ከሰርክ ውጣ ውረድ በተረፈች አንጀት
ለወደቀ ወገን ምርኩዝ ማበጃጀት
ሁሉም... ሁሉም ይችላሉ
ስለ'ግዚአር ላለ ይመፀውታሉ
.
.
እኔ ግን... እኔ ግን... ‘ቆጥራለሁ
የ'ድሜ ክቡር ጀንበር በጎዳና ፅልመት ሲዋጥ አስተውላለሁ
ጡረታ መንገድ ዳር ሲከፈል ዐያለሁ
‘ቆጥራለሁ... ‘ቆጥራለሁ
‘ቆጥራለሁ አዛውንት በየአቀበቱ በየቁልቁለቱ
ማረፊያ ፍለጋ የሚንከራተቱ
‘ቆጥራለሁ አዛውንት ከልጆቻቸው ፊት
የልመና መዝገብ የገለጡ አሮጊት
‘ቆጥራለሁ በየመንገዱ ዳር
እርጅና ሙሽራው ለምፅዋት ሲዳር
‘ቆጥራለሁ በየሸንተረሩ በየተፋሰሱ
አቀርቅሮ ሲያዘግም እርጅና ሞገሱ
.
.
‘ቆጥራለሁ በ'ያደባባዩ
የሽማግሌ ዐይኖች የልጅ ፊት እያዩ
‘ቆጥራለሁ በየሰርጣሰርጡ
በልመና ጉልበት ከሞት ሲፋጠጡ
የ'ርጅና መዳፎች እሾህ ሲጨብጡ
.
ቆጥሬ... ቆጥሬ... ቆጥሬ
በለማኝ አዛውንት ብዛት ተሳክሬ
የማሰንበቻ ሥንቅ ከኪሴ ቆንጥሬ
ያጽድቆቴን ዋጋ በሳንቲም መንዝሬ
ባ'ዛውንት ምርቃት ከሀገር ከቀዬው ትርፌን ሳመሳስል
በጎዳናው ቀለም ጻድቅ መልኬን ስሥል
ጎልቶ ሚታየኝ ግን የሚያሳፍር ምስል
በቀላል ጥያቄ የነተበ ምስል
.
.
ጥያቄ...
.
.
የዲጄ ኳኳታ የደናሽ ጋጋታ
የድራፍት እርካታ ያ'ረቄ ድንፋታ
ባጣበበው መንገድ
እንደምን ይቻካል ላ'ያት ሳንቲም ሰጥቶ በ'ርካታ መራመድ?
ለወጣት ሹክሹክታ ለገደል ዝምታ
ላስመሳይ ጫጫታ ላድርባይ እሪታ
በተሰራ መንገድ
እውነት ቀላል ነው ወይ ላ'ያት ሳንቲም ሰ’ቶ በ'ርካታ መራመድ?
ለቡቲክ ሰልፈኛ ለካፌ 'ድምተኛ
ለውስኪ ጭሰኛ ለበርገር ምርኮኛ
በተሰራ መንገድ
እንደምን ይቻላል ላ'ያት ሳንቲም ሰ’ቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
.
አያት....አያት...አያትነት ማለት
በደማቅ አሻራ የሸመኑት ጥለት
ለተራኪ ዕድሜ የተሰጠ አንደበት
ባ'ባት በ'ናት ጽናት የማይደክም ጉልበት
በልጅ ልጅ መነጽር የማያረጅ ውበት
በልጅ ልጆች ጥበብ የሚታደስ ዕውቀት
የሚታደስ እውነት
አያት ሆኑ ማለት
ድርብ አባትነት
ድርብ እናትነት
.
.
በተለይ እዚህማ... በዚህች ዓይነት ሀገር
ጎጆዋን ላቆመች በተጋድሎ ካስማ ባርበኝነት ማገር
በዚህች ዓይነት ሀገር
ጥያቄና መልሷን ባ'ዘን በቅዳሴ በምትሠራ መንደር
በዱአ በጸሎት በምናኔ ምርኩዝ በከረመች ሰፈር
የአያትነት ዋጋው በልኩ ቢሰፈር
ለሳንቲም ምርቃት ባልተሻማን ነበር!
ታሪክ በመዳፉ ስላደላደለው
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ንጉሥ አያት አለው
የልጅ ልጆች ስባት ባያመነምነው
ያያቶቻችን መልክ ሁሌም አንድ ዓይነት ነው
.
እላለሁ... እላለሁ....
የልጆች ምፅዋት ያ'ያቶች ልመና
ያ'ባቶች ግርግር በሞላው ጎዳና
መንገዱ አይልቅም
ጎዳናው አያልቅም
ይሰፋል ይረዝማል ይሄዳል ይጓዛል
እግረኛው ሞኝ ነው ሳንቲሙን ዘርዝሮ ከወደቁ አዛውንት ምርቃት ይገዛል
መንገዱ ያስፈራል
መንገዱ ይጨንቃል
ልጆች ሣቅ ሲያንቃቸው አያት እንባ ይጨምቃል
መንገዱ ያሠጋል መንገዱ ያረጃል
ከዘናጭ ልጆች ጎን እርዛት ያዘለ አያት ይወለዳል
ሰጪ ካለቀሰ ተበዳሪ ሥቆ
ጌታ ከለመነ አማኙ 'ግር ወድቆ
ልዑል ከዘመረ ንጉሡ ተዋርዶ
ገጹ ተመሳቅሎ ሽፋኑ ካማረ
ወለሉ ተንቆ ምንጣፍ ከከበረ
ባ'ገርኛ ስሌት ማነው ያልከሰረ?
.
እላለሁ... እላለሁ
.
ከየጎዳናው ገጽ ጥያቄ አነሣለሁ ጥያቄ እጥላለሁ
እርጅና ለማምሻው ጎዳናን ካመነ
አያት ከልጅ ልጁ ሳንቲም ከለመነ
ባገርኛ ስሌት ማነው ያልመከነ?
በ'ግዚኦታ ዘመን በምሕላ ዘመን
እመንገድ ዳር ወድቆ ትራፊ መለመን
በጥሞና ዘመን የሚያስቡት ማጣት
በማውረሻ ዕድሜ የሚሰጡት ማጣት
በማልበሻ ዘመን በ'ርዛት መቀጣት
በለጋሽነት ወቅት በማጉረሻ ዘመን
በጥማት መገረፍ በረኃብ መመንመን
ከሆነ ዕጣችን
ይጠየቅ ትርጉሙ የልጅነታችን
ይፈተሽ መንገዱ የልጅ ልጆቻችን
.
ግድ የለም እንመን
እንመን
.
በሰውኛ ስሌት ውጤቱ ሲሠራ
ትውልድ ያደኸያል ያያቶች ኪሣራ
በልጅ ልጆች ዓለም እንደጉድ ቢደለቅ ቢዘመር ቢዘፈን
አባት ይወራጫል ባ'ያቶች መታፈን
.
አባት ሆይ...
.
ለልጆችህ ርዕዮት ትላንቱን የረሳ ተስፋ ሲደራረት
ሕልሜ ነው ይልሃል ያ'ያቶቹ ቅዠት
ከልጅህ አንደበት ቋንቋ እንደዶፍ ቢዘንብ ትርጉም ቢንፎለፎል ሺ ቃላት ቢጎርፍም
የልጅ ልጅ አግባቢ ግማሽ ገጽ አይጽፍም
ከልጆችህ ባሕር ዓሣ የሚያጠግቡ ለዓሣ 'ሚስማሙ
ዕፅዋት ተክሎች እንደጉድ ቢራቡ እንደጉድ ቢያብቡ
ገበታ አይሞላም ተቀዷል መረቡ
.
ግድ የለም እንመን... እንመን
.
የስኬት ክብደቱ የምቾት አይነቱ የነገ ውበቱ ባሻው ቋት ቢለካ በምንም ቢሰፈር ባሻው ቃል ቢነገር
ጀግና ልጅ አትወልድም አያቶቿን ገድላ የምትሸልል ሀገር
.
ከፎቆቹ ጥላ...
.
ከያስፓልቱ ገላ ሲታተም ድምቀቴ
በመስታወት አጀብ ሲጠገን ጉልበቴ
ይኸው አነበብኩት አያቶቼ ፊት ላይ ተጽፏል ሽንፈቴ
በመኪና ብዛት በመስታወት አይነት ሲለካ ፍጥነቴ
በግንብ አጥር መአት በፎቆች ጋጋተ ሲሰላ ስኬቴ
ይኸው ይታየኛል አያቴ ገጽ ላይ ተስሏል ውድቀቴ
ተስሏል ሽንፈት።

Читать полностью…

እዚህ ቤት

ሙሉጌታ ተስፋዬ፣ባይራ ዲጂታል መጽሔት ላይ በውብአረገ አድምጥ እንደተጠቀሰ

/channel/Gazetaw

Читать полностью…

እዚህ ቤት

አያልነህ ሙላት/ሙላቱ

📝ሰውየውን የማውቃቸው ገጠር ሳለሁ በአማራ ራዲዮ ነው።ማራኪ ተናጋሪ ናቸው።ልጅነታቸው ይጣፍጣል።

📝የ ብንያም አቡራ «ወደ ፍቅር ጉዞ»መጽሐፍ የተመረቀ 'ለት ከወመዘክር ወጣ እንዳልነ አንዱ ገጣሚ ፣ጋዜጠኛ እና አሁንም ሥነ-ጽሑፍ የሚማር ጓደኛየ እንደዋዛ «ጋሽ አያልነህ የእርስዎን ግጥሞች እኮ መምህሮቻችን 'አብዮታዊ ግጥሞች'እያሉ ነው የሚያስተምሩን፤»ብሎ አበሸቃቸው።

ጨሱ።ጸያፍ ሥድብ አመለጣቸው።ልጁ ሲነግረኝ ረጅሙን የግጥም መጽሐፋቸው አንብቧል።እውነትም ሥንኞቻቸው ከኪናዊ ለዛ ይልቅ አቢዮታዊ ቃና እንደሚነበብባቸው አወጋኝ።

ሳላነብ አመንኩት።ግጥም ማንበብ ላይ ሰነፍ ነኝ።ከእናቴ የሚበልጥ ገጣሚ ስላላገኘሁ ይሆናል።

ለሁሉም ጋሽ አያልነህን እንዲህ ያስታወስኳቸው በጴጥሮስ ቶጃ(ርዕሰ ምሁር ናቸው፤) ግለ-ታሪክ የጀርባ ሽፋን ላይ የሚከተለውን ሥንኝ እና አሳዛኝ ሥሜቱን አጋርተው አግኝቻቸው ነው።

ኑ በአባቶቻችን አብረን እንዘን፤እንፈርም፣ወይም ከተገኘ እንኩራ፦

«በ1965 ዓ.ም አውሮፓ እያለሁ አንድ አጭር ግጥም ቋጥሬ ነበር።

እሳት ነደደ አሉ በአገራችን ጓዳ
ጓዶች ብርድ አይምታን ገብተን እንጣዳ።

እንለግስ ጭራሮ አንሁን ማገዶ
እሳቱ እንዳይጠፋ ጢሶ ጢሶ ነዶ።

(ጥገት ላም)

ይህ ግጥም ለእኔ ማዕበል ጠሪ ወፍ🦃 ነው።እጅግ በርካታ ጓዶችን ከውጭ አገር ዩኒቨርስቲዎች ቤተ-መጽሐፍት እያበረታታ ለአብዮት የሰደድ እሳት «ጭድ»^ያደረጋቸው መስሎ ስለሚታየኝ ለግጥሙ ያለኝ ፍቅር እጅግም ነው።»


🦃አዲሱ የዓለማየሁ ገላጋይ መጽሐፍ ርዕሱ «ማዕበል ጠሪ ወፍ»ይላል።የምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ነበርኩ።

^የጴጥሮስ ቶጃ ግለ ታሪክ ርዕሱ «የጭድ እሳት» ነው።

ሰላም ይስጥልነ!

Читать полностью…

እዚህ ቤት

ለመጽሐፍት ቀን

ኦሮማይ መጽናኛየ ነው።ተማሪ ሳለሁ አራት ጊዜ አነበብኩት።መመረቂያ ጽሑፌም ደራሲው በኦሮማይ ጋዜጠኝነትን እንዴት እንደተመለከተው ያትታል።

ትረካውን በጣም እወደዋለሁ።ፍቃዱ ተክለማርያም ፊያሜታን ሲያስመላት በቃ ሙትት እላለሁ።

ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲህ ያለ መጽሐፍ መኖሩን የጠቆመኝ እና PDF የላከልኝ አዲሱ አየለ ነው።

ሌላኛው የእኔ ምርጥ መጽሐፍ የ«ሐበሻ ጀብዱ» ይሰኛል።በንባብ ሁለት ጊዜ አጥንቸዋለሁ።ተርጓሚውን ተጫነ ጆብሬ መኮንን'ን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መጥተው ጠይቄያቸው አውቃለሁ።ምርጥ ሰው ናቸው።

መጽሐፉ በአማርኛ ተተርኳል።ትረካውን እንደ ሙዚቃ አደምጠዋለሁ።

ሶስተኛው ለልቤ የቀረበ መጽሐፍ «ሌላ ሰው»ነው።

ኮቪድ ሊገባ ሳምንታት ሲቀሩት የአብርሐም አፈወርቂን እና ፀሐይቱ ባራኪን ዘፈን ማጀቢያ አድርጌ ያነበብኩት ውብ ሥራ ነው።

ዘፈኖቹን በሰማሁ ቁጥር መጽሐፉ ትዝ ይለኛል።

ዛሬ ዛሬ ሳነብ ለቅንጦት አይደለም።በቀጥታ ለሥራዬ ሊጠቅመኝ ይገባል።

ሳድግ አንድ የሐዲስ ዓለማየሁን ፍቅር እስከ መቃብር የሚልቅ ልብወለድ የመጻፍ አሳብ አለኝ።ታዲያ ከዚያ በፊት ኑሮየ ሊደላኝ ይገባል።

ገጠመኞቸ'ን የያዘው «የትውልዴ ገድል»በቅርብ ዓመታት ውስጥ መነበቡ አይቀርም።

ግን አልቸኩልም።

/channel/Gazetaw

Читать полностью…

እዚህ ቤት

https://www.facebook.com/100064752820499/posts/837924401709313/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

Читать полностью…

እዚህ ቤት

ፍቅረ-ማርቆስ ደስታ በትዝታው መጣ!
(ሸጋው ማሬ)
የአአዩ ኬሚስትሪ ምሩቁ ፍቅረ-ማርቆስ ደስታ ደቡብ ኦሞ ጂንካ የሔደው በአስተማሪነት ነበር። በዚህ ዞን ብሔረሰቦች ፍቅር የተነደፈው ያኔ ነው። ”ከቡስካ በስተጀርባ”ን በ1987 አሳተመ። በ1990 ደግሞ ተወዳጅ መጽሐፉን ”ኢቫንጋዲ"ን ሠጠን። “የዘርሲዎች ፍቅር” (1991)፣ ”አቻሜ" (1992)፣ ”የንሥር ዐይን” (1993)፣ ‘Land of the yellow bull' (1995)፣ ”ጃገማ ኬሎ- የበጋው መብረቅ” (2001)፣ እና ”የሚሳም ተራራ” (2016) የቆንጅዬው ደራሲ ፍቅረ-ማርቆስ ደስታ ሥራዎች ናቸው። ፍቅረ-ማርቆስ በትውልዱ ጎጃሜ ቢኾንም፤ በሕይወቱና በፍቅሩ ሐመሬ ነው። ሐመሮችን ያወቅናቸው በፍቅረ-ማርቆስ ነው። ከፍቅረ-ማርቆስ ተወስዶም በዘፈንና በጽሑፍ ”ኢቫንጋዲ” ተለምዷል። ተወዳጁ ባሕላዊ ጭፈራ ቤተኛችን ኾኗል።
ፍቅረ-ማርቆስ ደስታ መጽሐፉ በእንግሊዝኛ የታተመለት ደራሲ ነው። በእንግሊዝኛ ቋንቋ ደቡብ ኦሞ በተሠሩ ጥናታዊ ፊልሞች ላይ ተሣትፎ ነበረው።
ጎጄው ፍቅረ-ማርቆስ፣ ሐመሩ ፍቅረ-ማርቆስ፣ ኢትዮጵያዊው ፍቅረ-ማርቆስ፣ አሜሪካዊው ፍቅረ-ማርቆስ... የዓለም ሰው ፍቅረ-ማርቆስ ደስታ!

Читать полностью…

እዚህ ቤት

"ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ"
ልዩ ዐውደ ርእይ በግዮን ሆቴል | ከሚያዝያ 5 - 13
ከሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት

የመግቢያ ትኬትዎን በኦንላይን https://event.hamereberhan.org ላይ ይቁረጡ!

Читать полностью…

እዚህ ቤት

የማኪያቪሊ ምክሮች

[በደሳለኝ ከፋለ]

… የጣልያን ፈላስፋ የሆነው ኒኮሎ ማካቬሌ(1469-1527) አስደናቂ የፖለቲካ ፍልስፍና አለው።

ይህን የፖለቲካ ፍልስፍና የቀመረው ደግሞ ጣልያን'ን ወደ አንድ ለማንጣት በእስር ላይ እያለ ምን ማድረግ እንዳለበት ሲያስብ ነበር።

ይህ ጣልያናዊው ፈላስፋ፣  "ጣልያንን ወደ አንድ ለማንጣት ምን አይነት መሪ ያስፈልጋል?" በማለት ወደ አራት የሚደርሱ የፖለቲካ  ፍልስፍናዎችን ያስቀምጣል።


ማካቬሌ የጠቀሳቸውን አራቱን የፖለቲካ ፍልስፍናዎች ላካፍላችሁ ወደድኩ:-

ሀ/ "መሪ ሥነ ምግባርን አሽቀንጥሮ መጣል አለበት።

ህዝቡ በከፋበት ዘመን ከመሪ መልካምነት ሊጠብቅ አይገባም፣ ይላል ማካቬሌ። መሪው በባህሪው መጥፎነት ኖሮበት ሳይሆን መጥፎ ህዝብ መጥፎ መሪን ስለሚያመጣ ነው።

ህዝቡ ሥነ ምግባር የጎደለውና ሥርዓት የማያውቅ ከሆነ በዚህ ሁኔታ አንድ መሪ የራሱን ደኅንነት መጠበቅ ግዴታ ውስጥ ይገባል።

ለዚህ ያለው ብቸኛ አማራጭ ኃይልን በመጠቀም ጨካኝነቱን ማሳየት ነው ። ህዝቡ ገልበጥባጣ በመሆኑ መሪ ህዝቡን ማመን የለበትም፣ ህዝቡን ከማመን ይልቅ የራሱን ማንነት እንደሁኔታው አየቀያየረ መኖር ያስፈልገዋል።

ለ/ መሪ የሃይማኖተኛና የቅድስና ሕይወት ሊኖረው አይገባም።

ማካቬሌ ሲናገር፣ ሃይማኖትን ሕዝብ ይከተለው እንጂ መሪ ሊከተለውና ሊኖርበት አይገባም። መሪ ሃይማኖተኛ ከሆነ ትሁት ይሆናል፣ ትህትና ደግሞ ደካማ ያደርጋል። መሪ ደካማ ከሆነ በዙሪያው ያሉት ጠላቶቹ ስለባ ይሆናል።

ሐ/ መሪ ለሥልጣኑ ህጋዊነት መጨነቅ የለበትም።

ለማካቬሌ ህጋዊ መንግሥት የሚያስፈልገው መረጋጋት ባለበት ሀገር ውስጥ ነው። መረጋጋት ከሌለ ህግም ቢኖር ተግባራዊ አይሆንም፣ ህግ አልባነትም በህግ መመለስ አይቻልም።

ህግ በጠፋበት ዘመን ህጋዊ ሥርዓት መፍጠር የሚቻለው ጸጥ-ለጥ አድርጎ በጉልበት መግዛት ሲቻል ነው። መልካም ህግ ያለ መልካም ክንድ ሊኖር ስለማይችል ከህግ ይለቅ የበረታች ክንድን እመርጣለሁ፣ይላል ማካቬሌ።


መ/ መሪ አስመሳይና አታላይ መሆን አለበት ።

ያልተረጋጋን የፖለቲካ ሁኔታ ማለፍ የሚችሉት ተንኮለኛ ሰዎች ናቸው ብሎ ማካቬሌ ያምናል።

ተንኮለኛነቱ ለደኅንነቱ በጣም ጠቃሚ ነው። ተንኮለኛነቱ የሚገለፀው ደግሞ ህዝቡን ለማሳሳት አስመሳይ ሆኖ ስለሚቀርብ ነው። መሪ ጥሩ ሰው ሳይሆን ነገር ግን ጥሩ ሰው መስሎ መታየት ህዝቡን መቅረብ አለበት።

በዚህ ጊዜ አስመሳይነቱን ህዝቡ እንዳያውቅበት መጠንቀቅ አለበት፣ ለህዝቡ ሃቀኛ መስሎ ነው መታየት ያለበት።

የህዝቡን ድጋፍ ለማግኘት ደግ መስሎ መታየት፣ ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ግለሰባዊነት የቆመ መስሎ መታየት አለበት።

ነገር ግን በተግባር ከነዚህ እሴቶች  በተቀራኒ ሆኖ መኖር አለበት። ተቀናቃኞቹንና ደጋፊ መስለው በዙሪያው እየኖሩ ደባ የሚሰሩበትን ምቹ ሁኔታ ባገኘ ቁጥር ያለምንም ርህራሄ ማጥፋት አለበት።

መሪ እንደ ተኩላ የራሱን እኩይነት በማያስነቃ መልኩ ሸፍኖ መያዝ አለበት። ሊያጠቃቸው የሚፈልጋቸውንም የዋህ፣ደካማና በእነርሱ ላይ ክፋት የማያስብ መስሎ በመታየት ሊያዘናጋቸውና ባላሰቡት ጊዜ ሊያጠቃቸው ይገባል። ለፖለቲከኛ ብልጠት ወሳኝ ነው።


"በፍልስፍና መደመም" ከሚለው የዋለልኝን መጽሐፍ ከገፅ( 192-194)  የተወሰደ።

ለመሆኑ አገራችን ኢትዮጵያ'ስ ምን አይነት መሪ ያስፈልጋታል?

የፖለቲካ ፍልስፍናዎቹ ምን ቢሆኑ ለአገሪቱ ይበጃል ትላላችሁ?

ያሁኑ መሪያችን ከማካቬሌ  የፖለቲካ ፍልስፍና አንፃር ስናየው የትኛውን መንገድ የተከተለ ይመስላችኋል?

ሃሳብ ስጡበት!


@DKB27

Читать полностью…

እዚህ ቤት

እኒህ ሰውየ😀

/channel/Gazetaw

Читать полностью…

እዚህ ቤት

«ጎጃሜ ነሽ ቢሉኝ አልኩኝ ደፋ ቀና
ጀምሮ ማስጨረስ ታውቂያለሽ አልኩ'ና

ጎንደሬ ነሽ ቢሉኝ ፈራሁሽ አንችየ
አንችን ሳግደረድር መክረሜ ነው ብየ

ወሎየ ነሽ ቢሉኝ ወለል አልኩልሽ
ነፍሴ ከሥጋየ ተባበሱልሽ»

አየለ ማሞ እና ሲራክ ታደሰ ጽፈውለት ሻምበል በላይነህ ከዘፈነው «የወሎ ልጅ»ሙዚቃ ውስጥ የተቆነጠሩ ሥንኞች ናቸው።

/channel/Gazetaw

Читать полностью…

እዚህ ቤት

"ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ" ልዩ አውደ ርእይ አንድ ወር ብቻ ቀረው!

የመግቢያ ትኬትዎን በኦንላይን ይቁረጡ!

https://event.hamereberhan.org

Читать полностью…

እዚህ ቤት

" ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ "

ልዩ አውደ ርእይ በግዮን ሆቴል | ከሚያዝያ 5 -13 |
ከሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት


የመግቢያ ትኬትዎች በመሸጥ ላይ ናቸው

ለበለጠ መረጃ ፦ 09 09 44 44 55 ወይም 09 66 76 76 76 ይደውሉ።

Читать полностью…

እዚህ ቤት

በመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም አገር በጣዕር ውስጥ ነበረች።

የዚያ ሰሞን የጭንቀታችን ምንጭ Covid-19 ይባላል።

በጊዜው አንድ የማኅበረሰብ ሣይንሥ ባለሞያ ደወለልኝ።

«ታሜ ለኮቪድ 19 ዘመቻ ታጭቻለሁ።ብዙ ሰው እንቢ እያለ ነው፤»

አለኝ።

እሱ በዘመቻው ላይ ጠለቅ ብሎ ባይሳተፍም ከዚያ በኋላ ብዙ ሐኪሞች በሞያቸው የኮቪድ 19 ታማሚዎችን ሲረዱ ተሰውተዋል።

ይህ ሐውልት የእነርሱ ማስታወሻ ነው።

የኢየሱስ ትንሳኤ በዓል 'ለት በዚያ ነበርኩ።

/channel/Gazetaw

Читать полностью…

እዚህ ቤት

https://vm.tiktok.com/ZMMGuWB39/

Читать полностью…

እዚህ ቤት

በኢትዮጵያ ቀን የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓልና ጁምዓ ተገናኝተዋል።

ኢየሱስ ለሰው ልጆች ሲል ራሱን ለሞት አሳልፎ የሰጠበትን ቀን እያከበርን የከፋው ጠባያችን ባመጣብን እዳ የተነሳ በየሜዳው፣ጫካው የተበተኑ፣በአውሬዎች የታረዱ ኢትዮጵያዊያንን እያሰብን እየተደጋገፍን እናስበው።

የኢትዮጵያ ትንሳኤ እየደረሰ ቢሆንስ?

ለሁሉም የመምህር ሃብታሙ አለማየሁን የክራር ግርፍ እየታደማችሁ ለዕለተ ስቅለት የሚሆኑ መልዕክቶችን፦

በጓዳ በኩል @GazetawBot ላይ

ለእኔ ለአባወራው @Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ።

የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!

Читать полностью…

እዚህ ቤት



/channel/Gazetaw

Читать полностью…

እዚህ ቤት

ትኩሳት ፣ሥብሃት ገብረእግዚአብሔር

ቃሉ የባሕራን ነው!

✍️ባሕራን በፈረንሳይ አገር ይማር የነበረ ኢራናዊ ወጣት ነው።ይችን ቁም ነገር ለጋሽ ስብሃት የነገረው በፈረንሳይኛው ደካማነት ሰበብ ከትምህርት በመውደቁ የተነሳ ነበር።

✍️የጋሽ ስብሃት አገር ኢትዮጵያ(አክሱም) እና የባሕራን አገር ኢራን(ፋርስ) የዛሬ 2ሺህ ዓመት ገደማ ከዓለማችን አራት ኃያላን አገራት መካከል ሁለቱ እንደነበሩ ማኒ ጽፏል።

/channel/Gazetaw

Читать полностью…

እዚህ ቤት

https://vm.tiktok.com/ZMMbd5pmD/

Читать полностью…

እዚህ ቤት

የእሁድ መደሰቻ❤

https://vm.tiktok.com/ZMMVhjhAK/

Читать полностью…

እዚህ ቤት

ማዳንና መግደል
(ሸጋው ማሬ)

የዐይኖቼን ዕይታ፥ ወደ ላይ ብልከው
አብ የልቤን ዐይቶ፥ ማኅፀኔን ባረከው!
ደግ ልቤን ብልክ፥ በአድማስ ተስፋዬ ላይ
እኔው ፀሐይ ኾኜ፥ ሠጠኝ ሌላ ፀሐይ!
የፍቅሬን መገለጥ፥ በማኅፀን መዝኜ
ሕይወቴን ስሠጣት- በአምላክ ተማምኜ
ይኼው በመባረክ፥ ብርሃን ተገኘ።
ወትሮም ልማዱ ነው፥ ፍቅር ከእናት አንጀት
ትንሣኤና ፍቅር፥ ለልጇ መመኘት
ገዳም ነው የ'ሷ ልብ፥ መቅደስ ነው መንፈሷ
በሥጋ ስዋትት፥ ተገኘሁ በነፍሷ!

*ለ“ግንቦት ፳፱”

Читать полностью…

እዚህ ቤት

ያንድ ምሽት ሓሳብ
(በዕውቀቱ ሥዩም)

ልማድ ኾኖበት፥ ሌቱ ቢገፋ
ምን ሊጠቅመኝ፥ ነው የማንቀላፋ
ሕልም ሸክም ነው፥ ፈቺው ከጠፋ፤
ሳይጎድለኝ ለዛ
ሳያንሰኝ ውበት
የቀን ጨረቃ፥ ላይንሽ ኾኜበት፥
ቀልብን የማይስብ፥ የሳር ቀለበት
መወደዴ ብላሽ
ምኞቴ ዘበት፤
የአሻንጉሊት ላም፥ ጡት እንደማለብ
የፈረስ ሐውልት፥ እንደመጋለብ
ሲሣይሽ ፈልቆ፥ ጣት አያርስም
የትም ብትኖሪ፥ የትም አልደርስም፥
የሚፈሰውን አልፎ ገደቤን
-ዕንባየን ልሼ
ደረቴን ሠብሮ ፥ የሸሸ ልቤን
ቦታው መልሼ
በፍቅር ፈንታ ፥ ዕረፍት ሸመትኹኝ
ቁርጤን ዓወቅሁኝ፤
ለካ ሰው ቢማር፥
ከሊቅ፥ ከመጻፍ፥ ከኑሮ ከዕድሜ
ቁርጥን ማወቅ ነው የዕውቀት ፍጻሜ፡፡

Читать полностью…

እዚህ ቤት

ዘመናት እንደቀልድ ይነጉዳሉ፤
ሥራዎች ግን ዘመናትን ይሻገራሉ።

"ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ"
ልዩ ዐውደ ርእይ በግዮን ሆቴል
ከሚያዝያ 5-13

የመግቢያ ትኬትዎን በኦንላይን event.hamereberhan.org
ላይ ይቁረጡ!

Читать полностью…

እዚህ ቤት

እባክዎትን ትክክለኛውን የትዕምርተ ጥቅስ ምልክት በማስረጃዎች በማስደገፍ ለይተው ያሳውቁኝ።በምርጫው ላይ የተጠቀሱት ሁሉ ምን እንደሚባሉ ቢጽፉልኝ እደሰታለሁ።

ሀ. «»
ሁ.‟”
ሂ." "
ሃ.❝ ❞

/channel/Gazetaw

Читать полностью…

እዚህ ቤት

የሰንበት ወግ

መደበኛ፣ የኮረናና የቻይና ዲያቆን!

    [ ደሳለኝ ከፋለ]

በቤተ ክህነት ከሚገኙ ማዕረጋት መካከል "ዲቁና" አንዱ ነው። ዲቁና፣ቅስናና ጵጵስና በቤተ ክህነት ውስጥ በትምህርት የምናገኛቸው #የክህነት_ማዕረጋት ናቸው።


#ዲያቆን ከምዕመናን ከፍ ያለ ከጳጳስናና ከቄሰ ደግሞ ዝቅ ብሎ ለትልዕኮ ምስጢር የሚፋጠን የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ነው።

#ዲያቅን ቤተ ክርስቲያን ታሪክ የቀዳሚ ሰማዕትና ሊቀ ዲያቆናት በመባል የሚታወቀው የእስጢፋኖስ አምሳያ ነው።

በዚህም የእሱን ተግባርና አዕርአያ ተከትሎ ሥራዎቹን(አግልግሎቱን) እንዲያከናውን ይመከራል።

ከመነሻዬ እንዳያችሁት በቤተ ክርስቲያን'ም ሆነ በቤተ ክህነት የሌለ ግን  የሥልጣን ወይም የማዕረግ አከፋፈል አይታችሁ ጥያቄ እንደምታነሱ እገምታለሁ።

እኔም ብሆን እንደሰማሁት ተገርሜ ጥያቄ አንስቼ ነበር። ሰምቸው አላውቅማኣ!

ከጓደኞቼ ጋር ሞቅ ያለ ጭዋታና ወሬ ይዘን ብዙ ነገሮችን ከዳሰስን በኋላ ቤተ ክህነት ውስጥ ገባንና ከላይ ያያችሁትን የዲያቆን አከፋፈል አነሳው።

በወቅቱ በጭዋታው ከነበሩት ጓደኞቼ መካከል ዲያቆናት'ም  ነበሩበት። ይህንን የዲያቆን አከፋፈል ስርዓት  ያመጡት'ም እነሱ ናቸው።

#ልዩነታቸውም:-

#መደበኛ_ዲያቆን ማለት ዓለማዊ ትምህርት ከመግባቱ በፊት በአብነት ትምህርት ተምሮ ፣ዲቁና ያገኘ ማለት ነው።

በእውቀቱ'ም ጎበዝና ቅኔ እስከመቀኘት የደረሰ ፣ ራሱን የሚደብቅ ፣ከዘመናዊነት ራቅ ያለና እዩኝ፣እዩኝ የማይል በአገልግሎቱ አንቱ የሚባል ነው።

#የኮረና_ዲያቆን የሚባለው ደግሞ በኮረና ስዓት ብቻ ተምሮ ዲቁና ያገኘ ማለት ነው።

እንደሚታወቀው የኮረና ቫይረስ ከቻይና ተነስቶ በፍጥነት በመዛመት ዓለምን ያዳረሰ የቫይረስ አይነት ነው።

በአገራችን ኢትዮጵያ'ም በ2012 ዓ.ም ከገባ በኋላ፣ የአገሪቱን  ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮቿን አናግቶ ማለፉ አይዘነጋም።

እኔም የመሰናዶ ተማሪ እያለሁ ፣ መጋቢት ሰባት 2012 ዓ.ም ላይ ለሶስት ሳምንት ተብሎ ትምህርት ቤታችን እንዲዘጋ ከተደረገ በኋላ፣ በዚያው ተዘግቶ እንደቀረ አሳታውሳለሁ።

ታዲያ በዚያ ሰዓት ሁሉም ተማሪ ወደ ቤተሰቡ እንደተቀላቀለ ቀረ። ትምህርቱም ነገ  ከነገ ወዲያ ሲባል የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ።

ከትምህርት የቀረንበት ይህ ወቅት ለቤተሰብ ሥራ የምናግዝበት ስዓት አልነበረም። ዝምብሎ ማዳመጥ ሆነ።

ይባስ ብሎ ከቤተሰብ እና በልጆች መካከል ግጭትም ይፈጠር ጀመረ።

በአንዳንዶቹ በሽታው በወቅቱ እንደመቅሰፍት ሲያዩት(መንፈሳዊ ሰዎች) ፣ሌሎቹ(የፓለቲካው ዓለም ገባን የሚሉት) ደግሞ መንግሥት የወቅቱን ምርጫ ለማራዘም የተጠቀመበት  የፓለቲካ ፍጆታ ነው ብለው ይቆጠሩት ነበር።

አንዳንድ ተማሪዎች ከዚህ ውዝግብ ለመውጣትም ሆነ፣ ከበሽታው ለማምለጥ ወደ ቤተ ክርስቲያን እና ገዳማት ተጠግተው የአብነት ትምህርት መማር ጀመሩ።


በነገራችን ላይ በርካታ ቁጥር ምዕመናን ይሄዱባቸው የነበሩ ገዳማትና አድባራት እስከ መከልከል ደርሰው ነበር።

እንግዲህ በዚህ ስዓት ተምረው ዲቁና  ላመጡ ዲያቆናት የተሰጠ ስያሜ መሆኑ ነው።

እነዚህ ዲያቆናት ዘግይተው ስለገቡ( እድሜያቸው ከ15 እና ከዚያ በላይ የሆኑ) ስለሆኑና የተማሩት ለትንሽ ጊዜ ስለነበር የእውቀት አደማሳቸው ጠባብ ነው ይሏቸዋል። ትምህርት ሲጀምር የመጡም ፣ሳይመጡ በዚያው የቀሩ'ም ነበሩ።


#የቻይና_ዲያቆን የሚባለው ደግሞ ዩኒቨርሲቲ ከገቡ በኋላ ከትምህርታቸው ጎን ለጎን በግቢ ጉባኤ አማካኝነት የአብነት ትምህርት ተምረው ዲቁና ያገኙ ናቸው።

እነዚህ ዲያቆናት ታዲያ በትህትና የሚታወቁ ሲሆኑ ሌላ ጉባኤ ቤት(የአብነት ትምህርት ቤት) ለመማር ዕድሉ ስለሌላቸው እዚያው ባገኙት መምህር የእውቀት ደረጃ የሚማሩ ናቸው።

"#የቻይና_ዲያቆን" የሚል ስያሜ ያገኙትም በአጭር ጊዜ ተምረው ለአግልግሎት  መብቃታቸው ነው።

ታዲያ አሁን ላይ "እከሌ እኮ ዲያቆን ነው፣ሲባል የየትኛው የዲያቆን አይነት ነው?" የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

በአንዳድ ስዎች ዘንድ'ም #ለመደበኛ_ዲያቆን የተለየ ክብር ሲኖራቸው፣ ሌሎቹን በጥርጣሬ ሲመለከቷቸው እየተስተዋለ ነው።

አንዳድ ዲያቆናት'ም ከሌሎቹ ከፍ ለማለትና ሌሎቹን (የቻይናና የኮረና ዲያቆናትን) ክብር ለመንካት ሲፈልጉና "እኔ'ኮ የቻይና ወይም የኮረና ዲያቆን አይደለሁም፣ ከህፃንነቴ ጀምሮ ነው የተማርኩት" እያሉ የዲቁና መታወቂያ የተቀበሉበትን ዓ.ም ሲያሳዩ ታዝቤያለሁ።
እርስ በራሳቸውም ሲናናቁ ተመልክቻለሁ።


ጸሐፊው @DKB27 ውስጥ አለ።

Читать полностью…

እዚህ ቤት

«ከጎራው ዘልቄ እስቲ ልነጋገር
ያለ ሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል አገር?»


መሥሉን ያሰማመረችው ፍርቱና ናት!

/channel/Gazetaw

Читать полностью…

እዚህ ቤት

ለክቡር ሚኒስትር አብርሐም በላይ

መጀመሪያውኑ የፌዴራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ አማርኛ ብቻ በሆነበት አገር የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስትር ለምን የሥራዎትን ጉዳይ፣በአገሪቱ የሕዝብ ቴሌቪዥን ከዚህ ቋንቋ ውጭ ይናገራሉ? ሕገ-መንግሥቱ አልተሻሻለም።አሁንም አንቀጽ አምስት ንዑስ አንቀጽ ሁለት «አማርኛ የፌዴራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ ይሆናል፤»ይላል።

ላለፉት ሥድስት ዓመታት ግን ይህን የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ በርካታ የፌዴራሉ መንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ጥሰውታል።

በሕጉ አለመስማት ሌላ ጉዳይ ነው።ያንን ሕግ ለማስከበር መንግሥት ሆኖ በይፋ መጣስ ግን የዘመናችን ወለፈንዲ(Paradox) ሆኖ ይገኛል።

በዚህ አካሄዳችሁ በአደባባይ እያየናችሁ ሕገ-መንግሥት ከጣሳችሁ ቢሯችሁ ውስጥ ሕግ እንደማትጥሱ በምን እንተማመናለን?

ታመነ መንግሥቴ ውቤ

እናንተ በፈጠራችሁት የግል መገናኛ ብዙኃኑን የማግለል ልማድ የተነሳ በይፋዊ የቃል መጠይቅ ሊጠይቃችሁ ያልታደለ ጋዜጠኛ

/channel/Gazetaw

Читать полностью…

እዚህ ቤት

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ሁለተኛ የመንግሥት አካል ሆነዋል ማለታችን ለዚህ ነው።

/channel/Gazetaw

Читать полностью…
Subscribe to a channel