gedelat | Unsorted

Telegram-канал gedelat - ገድለ ቅዱሳን

8058

@Gedelat ለተለያዩ አስተያየት እና ጥቆማ ማድረስ ከፈለጉ በአድራሻችን ቢያደርሱን ይደርሰናል፡፡ በአድራሻችን ✍ @Mnfesawi_bot

Subscribe to a channel

ገድለ ቅዱሳን

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ ይህች ዕለት የተቀደች ናት  ❞ 

🕊  💖                 💖  🕊

❝  ዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲ ለውሉደ  ሰብእ  መድኀኒት ...

ይህች ዕለት የተቀደች ናት ። ለሰው ልጆችም  መድሃኒት ናት።በየጊዜውና በየሰአቱ መሪ ትሁነን። እግዚአብሔር ሰንበትን ቀደሰ።

ሁልጊዜ መሀሪ ሰውን ወዳጅ ክርስቶስ የዓለም ንጉሥ ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው ሰንበትን በእውነት አክብሩ። መዋደድን ገንዘብ አድርጉ። ሰንበትን አክብሩ ጽድቅንም ስሩ። ነቀዝ የማይበላውን የማያረጀውን የማይጠፋውን ሰማያዊ መዝገብ [ሃብት] አከማቹ። ❞

[    ቅዱስ ያሬድ    ]


እግዚአብሔር ለድሀ ዳኝነትን ለችግረኛም ፍርድን እንዲያደርግ አወቅሁ። ❞ [ መዝ.፻፬፥፲፪ ]


  🕊   ክብርት ሰንበት  🕊


💖                     🕊                    💖

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

፩. ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ደቅስዮስ [የእመቤታችን ወዳጅ]
፫. አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
፬. አባ ጳውሊ የዋህ
፭. ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
፮. ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ ሐዋርያ

" ልጆች ሆይ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ:: አሸንፋችሁአቸውማል:: በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና:: እነርሱ ከዓለም ናቸው:: ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ:: ዓለሙም ይሰማቸዋል:: እኛ ከእግዚአብሔር ነን:: እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል:: ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም::" † [፩ዮሐ. ፬፥፬]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ]

🕊             
             
❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ፤ ነፍስን ይመልሳል ፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።

የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ፥ ልብንም ደስ ያሰኛል ፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው ፥ ዓይንንም ያበራል። ❞

[ መዝ . ፲፱ ፥ ፯  ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ! ❞  ]

               [   ክፍል - ፴፯ -    ]

          💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                        👇

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

እርሱም ወደ ከተማ ወርዶ ታላቁ ሊቅ ነባቤ መለኮት ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ ባለበት በዓለ ሲመቱ ተከብሯል:: ቅዱስ ጐርጐርዮስ በዘመኑ ብዙ መጻሕፍትን ደርሶ: የክርስቶስን መንጋም ጠብቆ: ድንቅ ድንቅ ተአምራትንም ፈጽሞ በዚህች ቀን ዐርፏል:: ከተአምራቱም :-

ወንድማማቾች

ከአባታቸው በወረሷት አንዲት ሐይቅ እየተጣሉ ሲያስቸግሩ በጸሎቱ ሐይቁን የብስ አድርጐ አስታርቁዋቸዋል::


🕊  † ቅዱስ ዮሐንስ ዘአስዩጥ †   🕊

በ፬ኛውና በ፭ኛው መቶ ክ/ዘመናት ከተነሱ ከዋክብት ጻድቃን አንዱ ነው:: እድሜው በጣም ረዥም በመሆኑ የብዙ ቅዱሳን ባልንጀራም ነበር:: በገድል አካሉን ቀጥቅጦ: በስብከትም የአስዩጥን [አሲዩትን] ምዕመናን አንጾ: ብዙ ተአምራትንም ሠርቶ በተወለደ በ፻፳፭ ዓመቱ በ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ በዚህች ቀን ዐርፏል::

አምላከ ቅዱሳን የአማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያምን ጣዕሟን ፍቅሯን: ጸጋ በረከቷን ያሳድርብን:: ከአበው በረከትም አይለየን::

🕊

[  † ኅዳር ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅድስት ጽዮን ድንግል ማርያም
፪. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘሮሜ
፫. ቅዱስ ዮሐንስ ዘአስዩጥ
፬. ቅዱስ ቆዝሞስ ሊቀ ዻዻሳት
፭. ቅድስት ዲቦራ ዘድልበት
፮. ቅዱስ ዘኬዎስ ሐጺር

[   †  ወርኀዊ በዓላት   ]

፩. አበው ጎርጎርዮሳት
፪. አቡነ ምዕመነ ድንግል
፫. አቡነ አምደ ሥላሴ
፬. አባ አሮን ሶርያዊ
፭. አባ መርትያኖስ ጻድቅ

" ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግስት ይጠፋል:: እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ . . . የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ:: የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ:: የእግዚአብሔርም ከተማ: የእሥራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል:: " [ኢሳ.፷፥፲፪]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

🕯                    🕊                     🕯

🕊


❝   ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን። ❞

[ መዝ.፻፴፯፥፩ ]




🕊                        💖                     🕊

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ  ]

[            ክፍል  አርባ ስድስት           ]

💛

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

[ 🕊   የቅዱስ መቃርዮስ ዕረፍት  🕊 ]

                         🕊      

[ አባ በብኑዳ በቅዱስ መቃርዮስ ቦታ ተተካ ]

❝ የዚህ ቅዱስ አባት ደቀ መዛሙርት አለቃ የሆነው አባ በብኑዳም አኃውን የሚያጽናናቸውና የሚያረጋጋቸው ሆነ ፤ እርሱ አባትነቱንና ዕልቅናውን እንዲሁም መልካም የሆነውን ሥርዓተ ገዳም ተቀብሏልና ፣ የቅዱስ ኣባ መቃርዮስን ምግባር ፣ ትሕትናና ትሩፋት ሁሉ ገንዘብ አድርጓልና፡፡ ስለዚህም ከመልካም ሥራው የተነሣ ዜናው በየቦታው ሁሉ ወጣ፡፡ በዚያ ገዳም የነበሩ መነኰሳት ብቻ ሳይሆኑ በምድረ ግብጽና በሌሎች ሩቅ ሀገራት የነበሩ ማኅበረ መነኰሳትም ወደ እርሱ እየመጡ ከቅዱስ አባ መቃርዮስ የተቀበለውን የእግዚአብሔርን መንገድ ከእርሱ ይማሩና ይቀበሉ ነበር:: ❞

[ የጁቢር ሰዎች የቅዱስ መቃርዮስን የከበረ ሥጋ ወደ ሃገራቸው መውሰድ ]

❝ የሥጋው ፍልሰትም እንዲህ ሆነ ፣ እርሱ በሕይወት ሳለ ሥጋውን እንዳይሰውሩ ልጆቹን አዝዟቸው ነበር፡፡ የጁቢር ሰዎችም ቅዱስ መቃርዮስ ማረፉን በሰሙ ጊዜ ከብዙ ዘመን በኋላ ወደ ቅዱስ መቃርዮስ ገዳም ወደ አስቄጥስ መጥተው ለእርሱ ካላቸው ፍቅርና ከእምነታቸው የተነሣ የከበረ አባት የአባ መቃርስን ሥጋ ሊወስዱ ፈለጉ ፤ መጥተውም ለደቀ መዝሙሩ ለዮሐንስ ገንዘብ ሰጡ:: ይህን ደቀ መዝሙሩንም ከላይ ቀደም ብሎ እንደ ተገለጸው ገንዘብን ከመውደድ ተጠበቅ እያለ ይመክረውና ይገሥጸው ነበር፡፡ እርሱም መርቶ የቅዱስ አባ መቃርስን ሥጋ አሳያቸውና ወደ ሀገራቸው ወደ ሳሱይር ወሰዱት፡፡ ቤተ ክርስቲያንም በስሙ አነጹለት፡፡ ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ግን ገንዘብ ስለ መውደዱ ዝልጉስ ሆነ፡፡ መቶ ስልሳ ዘመን ያህል በዚያ ኖረ፡፡

በመጨረሻም መነኰሳቱ ተነስተው የከበረ አባት የኣባ መቃርስን ሥጋ ሊወስዱ ወደ ሳይሱር በደረሱ ጊዜ የሀገሩ ሰዎች ከመኰንኑ ጋር ተነሥተው ከለከሏቸው:: በዚያችም ሌሊት የከበረ አባ መቃሪ ለመኰንኑ ተገልጦ ፦ “ተወኝ ከልጆቼ ጋር ልሂድ” አለው:: መኰንኑም መነኰሳቱን ጠርቶ እንዲወስዱ ፈቀደላቸውና የአባታቸውን የከበረ ሥጋ ተሸክመው በታላቅ ደስታ ወደ ቅዱስ መቃርዮስ ገዳም ወደ አስቄጥስ መለሱት፡፡ የቅዱስ መቃርዮስን ሥጋውን ነሐሴ አሥራ ዘጠኝ ቀን በምሥዋዑ አጠገብ አኖሩት፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ቤተ ክርስቲያን እነጹለት ፣ እግዚአብሔርም በቅዱስ መቃርዮስ ጸሎት የሚረዳቸው ሆነ፡፡ ኤጲስ ቆጶሱንም ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጋር አምጥተው ቤተ ክርስቲያኑን ቀደሰላቸው:: ቀድሰውም ለሕዝቡ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን አቀበሉ ፤ እግዚአብሔርም በቅዱስ መቃርዮስ የከበረ ሥጋ አማካኝነት እጅግ ብዙ ተአምራትን አደረገ፡፡

የተጻፉትና የተነገሩት የቅዱስ መቃርዮስ ገድላትና ተአምራት ከብዙ በጣም ጥቅቶቹ ናቸው ፤ የዚህን ቅዱስ የትሕትናውን ብዛት የሃይማኖቱን ጽናት ለእግዚአብሔር ያለውን ፍቅር ጥልቀት መጠን ሊደርስበት የሚችል ማንም የለምና ፤ ስለዚህም ምክንያት የጠላትን ኃይላት ድል አደረገ ፣ ተንኰላቸውንና ማሳታቸውን ሁሉ በታተነባቸው ፤ በእግዚአብሔር ኃይል በመታመን ሰይጣንና ሠራዊቱም በፊቱ እስኪወድቁ ድረስ አማሰናቸው:: ❞

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን፡፡ ✞

[ እንኩዋን ለኃያል ሰማዕት "ማር ቴዎድሮስ" እና "ቅዱስ አንያኖስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ]

🕊 † ቅዱስ ቴዎድሮስ ማር ሰማዕት † 🕊

በቤተ ክርስቲያን የሰማዕታት አለቅነት ከተሰጣቸው ሰማዕታት አንዱ የሆነው ማር ቴዎድሮስ የተወለደው በምድረ አንጾኪያ በ፫ኛው መቶ ክ/ዘ ነው:: አባቱ ዮሐንስ በትውልድ ግብጻዊ የሆነ ክርስቲያን ነው:: እናቱ ግን አስቸጋሪና ጣዖት አምላኪ ሶርያዊት ነበረች::

ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ ሚስት ባሏ ክርስቲያን መሆኑን አታውቅም ነበር:: ቴዎድሮስ [የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው] በተወለደ ጊዜ ግን ጠብ ተነሳ:: እሱ ክርስትና ለማስነሳት ሚስት ደግሞ ወደ ጣዖት ቤት ለመውሰድ ተጋጩ:: ሚስት ወገኖቿ ባለስልጣኖች ናቸውና ልጁን ቀምታ ባሏን ዮሐንስን ወደ ግብፅ አሳደደችው::

ዮሐንስ በስደት ባለበት ሃገር ስለ ልጁ ፈጽሞ ይጸልይ: ያለቅስም ገባ:: እግዚአብሔር ደግሞ ልመናውን ሰማ:: ማር ቴዎድሮስ ወጣት በሆነ ጊዜ ማንም ሳይጠራው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ተማረ: ተጠመቀ:: ዕለት ዕለትም ጾምና ጸሎትን ከምጽዋት ጋር ያበዛ ድንግልናውን ለመጠበቅ ይተጋ ነበር::

በዛው ልክ ደግሞ ገና በ፳ ዓመቱ በጉልበቱ ኃያል በውበቱም ደመ ግቡ በጠባዩም ገራገር ነበርና ተወዳጅ ነበር:: ነገሥታቱም የአንጾኪያ የጦር ሠራዊት አለቃ አድርገው ሾሙት:: እነሆ እስከ ዛሬ "የሠራዊት አለቃ" ተብሎ ይጠራል::

ማር ቴዎድሮስ በተሳተፈባቸው ጦርነቶች ሁሉ ተሸንፎ አያውቅም:: ይልቁኑ የነገሥታቱን [የጠላት] ልጆች በመማረክ ነው የሚታወቀው:: እንዲያውም አንድ ጊዜ ከአሕዛብ ጋር በተደረገ ጦርነት ብቻውን አሸንፏቸዋል::

የፋርስ ሰዎች ሊዋጉ ሲመጡ መልአክ ከሰማይ ወርዶ ሰይፍ ሰጠው:: ፋርሶችን "በከንቱ ከምትጠፉ ወደ ሃገራችሁ ተመለሱ" አላቸው:: እነርሱ ግን ተሳለቁበት:: ከፈረሱ ወርዶ ወደ ምስራቅ ዙሮ ጸልዮ በመስቀል አማተበ:: በመካከላቸው ገብቶም በመልአኩ ሰይፍ ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር አጠፋቸው::

አንድ ቀን ወደ አንድ ከተማ ቢገባ ዘንዶ ሲመለክ አገኘ:: ይባስ ብሎ የአንዲት ክርስቲያን ልጆችን ለመስዋዕትነት ሲያቀርበቧቸው ተመለከተ:: በስመ ሥላሴ አማትቦ በፈረሱ ላይም ተቀምጦ ዘንዶውን በጦር ገደለው:: የዘንዶውም ርዝመት ፳፬ ክንድ ነበር::

ከነገር ሁሉ በሁዋላ ቅዱስ ቴዎድሮስ ስለ አባቱ ወሬ ሰምቶ ካለበት ሥፍራ አፈላልጎ አግኝቶ ደስ አሰኘው:: እስኪያርፍ አብሮት ቆይቶ ቀብሮት ወደ አንጾኪያ ሲመለስ ግን የሚያሳዝን ነገር ጠበቀው::

ክርስቶስ ተክዶ ጣዖት ቁሞ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለው የክርስቲያኖች ደም ፈሶ ከተማዋ በግፍ ተሞልታ ተመለከተ:: እርሱም በዚያች ሰዓት መወሰን ነበረበትና አደረገው:: የሁሉ ሠራዊት አለቃ ቢሆንም የክብር ልብሱን አውልቆ ባጭር ታጥቆ በንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ፊት ቆመ::

ማር ቴዎድሮስ በአደባባይ እንዲህ ተናገረ :- "አንሰ አመልኮ ለክርስቶስ ንጉሠ ስብሐት በኩሉ ልብየ ወእሠውዕ ሎቱ - እኔስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን በፍጹም ልቤ አመልከዋለሁ ለእርሱም ብቻ እሠዋለሁ::" ንጉሡ በቁጣ መሬት ላይ ጥለው እንዲደበድቡት አዘዘ:: ወታደሮቹ ደሙ እስኪንጠፈጠፍ ገረፉት::

በብዙ መክፈልተ ኩነኔ አሰቃይተው በእሳት አቃጠሉት:: እርሱ ግን በጸሎቱ እሳቱን ውሃ አደረገው:: ወታደሮቹ እርሱን በብዙ አሰቃዩ:: እርሱ ግን በእግዚአብሔር ኃይል ጸና: ታገሠ::

በመጨረሻም ጌታችን በግርማ ወርዶ "ወዳጄ ቴዎድሮስ ስምህን የጠራ መታሠቢያህን ያደረገ: ገድልህን የጻፈ ያጻፈ ያነበበ ገዝቶ በቤቱ ውስጥ ያኖረውን ሁሉ እምርልሃለሁ" አለው::

በስሙም ረድኤት እንደሚደረግ ነግሮት ዐረገ:: ወታደሮቹም በዚህ ቀን አንገቱን ሰይፈው የክብር አክሊልን ተቀብሏል:: እጅግ ብዙ ሺህ ሰዎችም አብረውት ተሰይፈዋል::


🕊 † ቅዱስ አንያኖስ ዘግብጽ † 🕊

ይህ ቅዱስ አባት ውለታው ከፍ ያለ ነውና በምድረ ግብጽ እጅግ ይከበራል:: በተለይ ክርስትናን ከሐዋርያት ተቀብሎ ለምዕመናን ያስረከበ አባት በመሆኑ ልዩ ቦታ ይሰጠዋል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-

ወንጌላዊው ሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስ በሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ተመድቦ በፈቃደ እግዚአብሔር ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ በ፶ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ወደ ምድረ ግብጽ ወረደ::

እስክንድርያ ከተማ በሜዲትራኒያን ባሕር ዳርቻ እንደ መኖሯም መጀመሪያ ወደ እርሷ ደረሰ:: ልክ ወደ ከተማ ሲገባ ገና አንደበቱ ለወንጌል ሳይከፈት እንቅፋት መትቶት ጫማው ተበጠሰ:: ያን ሁሉ በርሃ የቻለች ጫማ በእንቅፋት በመበጠሷ እያዘነ ወደ ጫማ ሰፊ ዘንድ ደርሶ "ሥራልኝ?" ይለዋል::

ይህ ጫማ ሰፊ አንያኖስ [አንያኑ] ይባላል:: ጣዖት አምላኪ ግን ደግሞ ቅንና ገር የሆነ ሰው ነበር:: "እሺ" ብሎ ሲሰፋለት መሳፈቻው [መስፊያው] ስቶ መሐል እጣቱን ስለ ወጋው "ኢታስታኦስ [አታኦስ]" ብሎ ጮኸ:: ትርጉሙም "አንድ አምላክ" ማለት ነበር::

ይህንን የሰማው ቅዱስ ማርቆስ ቀና ብሎ "ጌታየ ሆይ! ጐዳናየን ስላቀናህልኝ አመሰግንሃለሁ!" ብሎ ምራቁን እትፍ ብሎ በጭቃ የአንያኖስን እጅ ቀባው::

ወዲያውም ደሙ ቁሞ ቁስሉም ድኖ እንደ ነበረው ሆነ:: በዚህ ተአምር ድንጋጤም ደስታም ቢሰማው "ማነህ አንተ?" ሲል ቅዱሱን ጠየቀው:: ወንጌላዊውም መልሶ "እኔ የክርስቶስ ሐዋርያ ነኝ" አለው::

አንያኖስም "እባክህ ወደ ቤቴ እንሒድ" ብሎ ሐዋርያውን ጋበዘው:: እቤት ሲደርሱም ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር አስተናግደውት የሕይወትን ቃል ለመኑት:: ቅዱስ ማርቆስም ከስነ ፍጥረት እስከ ጌታችን የማዳን ሥራ አስተምሯቸው አመኑ:: አጥምቆ ሥጋውን ደሙን አቀበላቸው::

ይህቺው የቅዱስ አንያኖስ ቤትም በምድረ ግብጽ የመጀመሪያዋ ጉባኤ ቤትና ቤተ ክርስቲያን ሆነች:: ቅዱሱ ሐዋርያ በ፷ ዓ/ም አካባቢ በቅዱስ አንያኑ ቤት ሆኖ በርካቶችን አሳመነ:: በሰማዕትነት ከማረፉ በፊትም ቅዱስ አንያኖስን የምድረ ግብጽ ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት አድርጐ ሾመው::

ቅዱስ አንያኖስም ለ፲፪ ዓመታት የክርስቶስን መንጋ እያበዛ ተጋደለ:: ከሐዋርያው የተቀበለውን ንጹሕ ዘር ዘራ:: የድኅነት የምሥራቹንም አዳረሰ:: ይሔው ይህ መልካም ተክል ዛሬም ድረስ ሳይጠወልግ አለ::

የአሁኑ ፓትርያርክ አቡነ ታውድሮስም ከቅዱስ ማርቆስ ፻፲፰ኛ ሲሆኑ ከቅዱስ አንያኖስ ፻፲፯ኛ ናቸው:: ቅዱሱ ለእኛ ኢትዮዽያውያንም የክህነት አባታችን ነው:: ይህች ቀንም ዕለተ ዕረፍቱ ናት::

አምላከ ቅዱሳን ክፉውን አርቆ ከበጐው ዘመን ያድርሰን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

🕊

[ † ኅዳር ፳ [20] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ማር ቴዎድሮስ ኃያል ሰማዕት
፪. ቅዱስ አንያኖስ

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
፪. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
፫. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ
፬. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
፭. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት

" በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኩዋ መከራን ብትቀበሉ ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት::" [፩ዼጥ.፫፥፲፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

           ❤ #ኅዳር ፳ (20) ቀን።

❤ እንኳን #በወንጌላዊ_ቅዱስ__ማርቆስ እጅ ጵጵስና ለተሾመው ለእስክንድርያ ሁለተኛ ሊቀ ጳጳስ #ለቅዱስ_አባት_ለአባ_አንያኖስ_ለዕረፍት በዓልና ለሠራዊት አለቃ ለከበረ #ለሰማዕት_ቅዱስ_ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያኑ ለከበረችበት በዓል በሰላም አደረሰን።

                             

                           ✝ ✝ ✝
❤ #ሊቀ_ጳጳስ_ቅዱስ_አንያኖስ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ አረማውያን ናቸዉ እርሱም ጫማ ሰፊ ነበር ቅዱስ ወንጌላዊ ማርቆስ ወደ እስክንድርያ አገር መጀመርያ በገባ ጊዜ እግሩን ተደናቅፎ ጫማው ተቆረጠ እንዲሰፋለትም ወደ ጫማ ሰፊ አንያኖስ ዘንድ ሔደና ጫማውን ሰጠው መስፋትም በጀመረ ጊዜ መስፊያው ጣቱን ወጋው በዮናኒም ቋንቋ "አቴኦስ" አለ ትርጓሜውም አንድ እግዚአብሔር ማለት ነው። ቅዱስ ማርቆስም የእግዚአብሔርን ስም ሲጠራ በሰማ ጊዜ ደስ ብሎት የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰገነው።

❤ ከዚህም በኋላ አፈር አንሥቶ በምራቁ ጭቃ አድርጎ በአንያኖስ ጣት ላይ አደረገውና በዚያን ጊዜ አዳነው አንያኖስም ከዚህ ድንቅ ምልክት የተነሣ አደነቀ ቅዱስ ማርቆስንም ወደ ቤቱ ወሰደው ስለ ሥራው ስለ አምልኮቱም የመጣውም ከወዴየት ቦታ እንደሆነ ጠየቀው። ቅዱስ ማርቆስም ከብሉያትና ከሐዲሳት መጻሕፍት የአንድ እግዚአብሔርን ህልውና ስለ ዓለም ሁሉ ድኅነት የወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን መከራ መስቀልንም ተቀብሎ ስለመሞቱ ስለ ትንሣኤውና ስለዕርገቱ ዳግመኛም ለፍርድ ስለ መምጣቱ ይነግረው ጀመረ። የአንያኖስ ልቡ ብሩህ ሁኖለት በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ከቤተሰብ ሁሉ ጋር ተጠምቀ። የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ በላያቸ ወረደ አዘውትሮ በመጠመድ የሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስን ትምህርት የሚሰማ ሆነ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ሕጓንና ሥርዓቷንም ተማረ።

❤ ቅዱስ ማርቆስም ወደ ሌሎች አገሮች ሒዶ ለማስተማር በፈለገ ጊዜ እጆቹን በአንያኖስ ላይ ጭኖ በግብጽ አገር ለወገኖቹ ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ሊቀ ጵጵስና ሾመው እርሱም ብዙዎችን አስተምሮ አጠመቃቸው በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው ቤቱንም ቤተ ክርስቲያን አደረጋት እርሷም በስተምራብ ከእስክድርያ ከተማ ውጭ ያለች ዛሬ የሰማዕት ቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሁና የታወቀች ናት።

❤ ይህ የተመሰገነ አባት አንያኖስም በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ዐሥራ ሁለት ዓመት አገልግሎ በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባ አንያኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 20 ስንክሳር።

                             

                             ✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኀይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 1፥5-12፣ 1ኛ ጴጥ 5፥1-8 እና የሐዋ ሥራ 20፥20-31። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ አንያኖስ የዕረፍት በዓልና የነቢያት (የገና) ጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
   

@sigewe

https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ  ]

[            ክፍል  አርባ አምስት           ]

💛

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

[ 🕊   የቅዱስ መቃርዮስ ዕረፍት  🕊 ]

                         🕊      

ያን ጊዜም ነፍሱን ሰጠ ..... !       

❝ ይህ ቅዱስ እንደ ልማዱ በመሬት ላይ ወድቆ ከደዌው ጽናት የተነሣ መነሣት የማይችል ሆነ ፤ ሰውነቱም እንደ እሳት የሚያቃጥል ሆነ፡፡ ሁለቱ ቅዱሳን በታዩት በስምንተኛው ሌሊት ፣ ይኸውም በመጋቢት ሃያ ሰባት ቀን ፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ ከእርሱ የነበረ ኪሩባዊ ከቅዱሳን አባቶች ማኅበር ጋር ሆኖ ወደ እርሱ መጥቶ ፦ “እነዚህ ሁሉ ቅዱሳን እየጠበቁህ ነውና ወደ እኛ ና” አለው፡፡ ያን ጊዜ ኣባታችን ቅዱስ መቃርዮስ በታላቅ ድምጽ እንዲህ በማለት ጮኸ ፦ “አቤቱ ነፍሴ የምትወድህ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፣ ነፍሴን ወደ አንተ ተቀበል፡፡" ያን ጊዜም ነፍሱን ሰጠ፡፡

እንደ ወትሮው ይመክራቸውና የሚያጸናቸውን መንፈሳዊ ነገር ይነግራቸው ስለ ነበር ሕማሙ ቢያደክመውም ብዙዎችም ዕረፍቱ ያን ጊዜ መሆኑን አላወቁም ነበርና ወደ እርሱ አልመጡም ነበር፡፡ በተራራው በአራቱ ገዳማት ውስጥ የነበሩት መነኰሳት ሁሉ በሰሙ ጊዜ እያለቀሱና ልባቸው አዝኖ ሁሉም ተሰበሰቡ፡፡ ሁሉም ከእርሱ የእግዚአብሔርን መንገድ አውቀዋልና ፣ እግዚአብሔርን መፍራትንና መልካም ምግባርን ከእርሱ ከሕይወቱ በተግባር ተምረዋልና ፣ የሰይጣናትን ኃይል ይቃወሙና በሰልፍ የጸኑ ቀዋምያን እንዲሆኑ የተጋድሎን ፈሊጥ አስተምሯቸዋልና ፣ በማይነዋወጽ ጽኑ መሠረት ላይ አንጾዋቸዋልና፡፡

ሌሎችም ሁሉ ማረፉን በሰሙ ጊዜ ከእርሱ ስለ መለየቱ በታላቅ ኃዘን ሆነው ከየበአታቸው እየወጡ መጡ:: መነኰሳትም መጥተው የከበረ ሰውነቱን አወጡት፡፡ ከዚያ በኋላ አባ እንጦንዮስንና የቅዱሳንን አንድነት ማኅበር ፣ ሰማያውያን የሆኑ የመላእክትንም ሠራዊት በእግዚአብሔር እጅ ነፍሱን እስከሚሰጥ ድረስ ያዩ ነበር፡፡

የቅዱስ መቃርስ ነፍስ ከሥጋው በተለየች ጊዜ ከፀሐይ ብርሃን ሰባት እጅ እያበራች ፍጹም ብርህት ሆና ከሰማይ የወረደው ኪሩባዊ በእጁ እንደ ተቀበላትና ከኪሩባዊውም ጋር ማንም ማን ክብራቸውንና ግርማቸውን ሊተረጉመው በማይችል በብዙ ሰማያውያን ኃይላት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ እንዳዩ ፣ ሰይጣናትንም ደቀ መዝሙሩ አባ በብኑዳ የናቅዮስ ኤጲስ ቆጶስ ፣ አባ ሰራጵዮን እና በዚያ የነበሩ ብዙ ቅዱሳን አረጋውያን እንደ ሰሟቸው ምስክር ሆኑ፡፡

ሰይጣናት ነፍሱን እንዲህ ሆና ባዩዋት ጊዜ እየተከተሉ ፦ “መቃርዮስ ሆይ ፣ ከእጃችን ዳንክ እመለጥክም” እያሉ ይጮኹ ጀመር፡፡ እርሱም ፦ “ገና አላመለጥኩም” አላቸው፡፡ አየር ላይ በደረሰ ጊዜ ሰይጣናት አሁንም እየጮኹ ፦ “መቃራ ሆይ ሄድክ እኮ” አሉት፡፡ እርሱም ፦ “የለም ገና ነኝ” አላቸው፡፡ አንድ እግሩ ወደ ውስጠኛው በር በደረሰ ጊዜ ሰይጣናት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እየጮኹ ፦ “መቃራ ሆይ ፣ ገባህ” አሉት ፤ እርሱም ፦ “ገና ነኝ” አላቸው፡፡ በደረሰ ጊዜ እና ሁለት እግሩን ወደ ውስጥ ባስገባ ጊዜ ፈጽመው እያለቀሱ ፦ “መቃራ ሆይ ፣ ደረስክ እኮ” እያሉ አብዝተው ጮኹ፡፡ ያን ጊዜ ቅዱስ መቃርዮስ በታላቅ ድምጽ እንዲህ ሲል አሰምቶ ተናገረ ፦

የአምላኬና የመድኃኒቴ የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ተቀብያለሁ ፣ እኔም ከእጃችሁና ሥፍር ቁጥር ከሌለው ወጥመዳችሁ ያዳነኝን ፣ በምሕረቱ በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ የጠበቀኝን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሞ አመሰግነዋለሁ::” ያን ጊዜ ኪሩባዊው ከእነርሱ ሰወረው ፣  ከዚያም በፍጹም ልቡ ወደ ወደደው ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማኅደረ ስብሐት ገባ፡፡

ይህ በእውነት ቅዱስ የሆነ አባትም ከመልካም ነገር ሁሉ ወደ ተመላች ሰማያዊ ማደሪያ ሄደ፡፡ በበአታት ሁሉ እየዞሩ የቅዱሱን ዕረፍት በነገሯቸው ጊዜ የሁላቸው አጽናኝና መካሪ ፣ እንዲሁም መንፈሳዊ ምግብን የሚመግባቸው መጋቢያቸው የነበረው አባታቸው ከእነርሱ ዘንድ በመታጣቱ ሁሉም አረጋውያን እያዘኑና እያለቀሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጡ፡፡ እያለቀሱ ከቅዱሱ ሥጋ ይባረኩ ዘንድና ይስሙት ዘንድ ዙሪያውን ቆሙ:: የሥጋ በሽታ የነበረባቸው ሁሉ እግዚአብሔር ያን ጊዜ ፈውስን ሰጣቸውና ዳኑ:: ስለ እርሱም ብዙ ጸሎትን አደረሱ ፣ ቅዳሴ ቀድሰውም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀበሉ፡፡ ሥጋውንም በቤተ ክርስቲያኑ አጠገብ ባነጸው በአት ውስጥ ቀበሩት ፤ ከእርሱ ስለ መለየታቸው በታላቅ ሐዘን ሆነው ወደየ በአታቸው ተመለሱ፡፡ የዕረፍቱ ቀንም መጋቢት ሃያ ሰባት ቀን ነው:: ❞

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

      ❤ #ኅዳር ፲፱ (19) ቀን።

❤ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያት አንዱ ለሆነው #ለሐዋርያው_ቅዱስ_በርቴሎሜዎስ እልዋህ በሚባል አገር አስተምሮ ብዙዎችን እግዚአብሔር ወደማወቅ ለመለሰበት ለመታሰቢያ በዓሉና #ለቅዱስ_ቴዎፍሎስ_ከሚስቱ_ቅድስት_ጰጥሪቃ ከአምስት ወር ልጁም #ከቅዱስ_ደማሊስ ጋር #ሰማዕትነት_ለተቀበሉበት_ለዕረፍታቸው በዓልና  ሩጻፋ በሚባል አገር #ለሰማዕት_ቅዱስ_ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ለከበረችበት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።                            
                          

                            ✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_ቴዎፍሎስ_ሚስቱ_ቅድስት_ጰጥሪቃ የአምስት ወር ልጁ #ቅዱስ_ደማሊስ፦ ይህ ቅዱስ እግዚአብሔርን በመፍራትና በአማረ አምልኮ ያደገ ነው ሰዎች ሒደው ቅዱስ ቴዎፍሎስ ክርስቲያን መሆኑን ለመኰንኑ ለአንቲጳጦስ ነገሩሩት መኰንኑም በዜውስ ጣዖት ቤት ሳለ ወደርሱ ያመጡት ዘንድ አዘዘ። ቅዱሱንም በአቀረቡት ጊዜ "አንተ ከወዴት ነህ? ሃይማኖትህስ ምንድን ነው?" አለው። እርሱም "የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስን ክርስቶስ የማምን ክርስቲያን ነኝ" አለ መኰንኑም "በክፉ አሟሟት እንዳትሞት ለአማልክተሰ ሠዋ" አለው ቅዱሱም "ክብር ይግባውና ከጌታዬ ከኢየሱስ በቀር ለረከሱ አማልክት አልሠዋም" አለው።

❤ መኰንኑም የሆድ ዕቃው እስቲታይ ሰቅለው ይሠነጥቁት ዘንድ አዘዘ እርሱ ግን በጌታችን ኃይል ስለጠበቀ ምንም ምን አልደረሰበትም ሁለተኛም እሳትን አንድደው ከውስጡ እንዲጨምሩት አዘዘ ቅዱሱም በእሳት መካከል በጸለየ ጊዜ እሳቱ ተበተነ ምንም ምን ሳይነካው ከእሳት ውስጥ ወጣ። መኰንኑም ይህን አይቶ በረኃብ እንዲሞት አሥረው አጽንተው ይጠብቁት ዘንድ አዘዘ ከስምንት ቀንም በኋላ ሚስቱ ጰጥሪቃ ሕፃኗን ተሸክማ መጣች ምስክርም ሁኖ በክርስቶስ ስም ይሞት ዘንድ አጽናቸው።

❤ መኰንኑም ለቅዱስ ቴዎፍሎስ ምግብ የሰጠው እንዳለ ብሎ ሊመረምር ሔደ የእሥር ቤቱንም ደጅ በከፈተ ጊዜ ጣፋጭ የዕጣን መዓዛ ተቀበለው ቅዱስ ቴዎፍሎስንም በተነጠፈ መቀመጫ ላይ ተቀምጦ ሦስት መላእክት ማርና ወተት ሲመግቡት አገኘው በአየውም ጊዜ ደንግጦ ወደኋላው ተመለሰ። በማግሥቱም ቅዱስ ቴዎፍሎስን ወደ አደባባይ እንዲአመጡት አዘዘ እርሱም ሚስቱ ተከታትለው መጣ መኰንኑም "ዲዮስ ለሚባል አምላክ ሠዋ" አለው። ቅዱሱም "እኔ ዓለምን ሁሉ ለያዘ ለእውነተኛው አምላክ ለጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ለሌላ አልሠዋም" አለ።

❤ በዚያንም ጊዜ ለአንበሳ እንዲጥሉት መኰንኑ አዘዘ አንበሳውም ሩጦ እግሮቹን ሳመ ከዚያም በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ አቈሰለው ተጋድሎውን በዚህ ፈጽሞ ነፍሱን ሰጠ ቅድስት ሚስቱ ጰጥሪቃም ሥጋውን አንሥታ ከሣጥን ጨመረች መኰንኑም እርሷንም ወደ አደባባይ አምጥተው ለአንበሳ እንዲሰጧት አዘዘ ሕፃኑም አንበሳውን በአየው ጊዜ ሣቀ የአምስት ወርም ልጅ ሲሆን "አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምናለሁ" ብሎ በአንበሳ አፍ ከእናቱ ጋር ተበላ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

                              ✝ ✝ ✝
❤ #የሰማዕቱ_ቅዱስ_ሰርጊስ_ቤተ_ክርስቲያን_የከበረችበት፦ ይህም ቅዱስ ሰርጊስ በሩጻፋ አገር በሰማዕትነት በአረፈ ጊዜ ምእመናን ሥጋውን ወስደው ገንዘው በእርሱ ዘንድ አኖሩት በፊቱም መብራቶችን አኖሩ የመከራውም ዘመን እስቲያልፍ በእነርሱ ዘንድ ተሠውሮ ኖረ። ከዚያም በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያንን አነፁለት ዐሥራ አምስት ኤጲስቆጶሳትንም ሰብስበው አከበሩዋት በዚች ቀን ኅዳር 19 ቀን ሥጋውንም በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ድንቅ ተአምር ተገለጠ በእምነት ከእርሱ ለሚወስዱ ሁሉ በሽተኞችን የሚፈውሳቸው ሽታው እጅግ ጣፋች የሆነ የሽቱ ቅባት ከሥጋው የሚፈስ ሆኗልና። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።

                           ✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_እብል_ሐዋርያ_መስተጋድለ። በተወርዎ ባሕር ዕሙቅ እንዘ ሠቀ ጸጒር ጥብሉለ። #በርተሎሜዎስ ገዳመ አመ ምስሌሆሙ ዔለ። በማየ ጸሎቱ ጽምዐ ነጋድያን አጥለለ። ወአንሥአ ዓዲ ዘሞቱ አግማለ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 19።
                             

                           ✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ሕጉ ለእግዚአብሔር ንጹሕ ወይመይጣ ለነፍስ። ስምዑ ለእግዚአብሔር እሙን ወያጠብብ ሕፃናተ። ኵነኔሁ ለእግዚአብሔር ርቱዕ ወያስተፌሥሕ ልበ"። መዝ18፥7-8። የሚነበበው  ወንጌል ማቴ10፥1-16። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። መልካም በዓልና ጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።   


@sigewe

https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

🕊  💖  ▬▬    †    ▬▬  💖  🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[   ❝  ከአንቺ ግን .... !  ❞  ]

🕊

❝ እግዚአብሔር ዐሥሩን ቃላት በእጁ የጻፈባቸውን ሁለቱን ጽላት በደብረ ሲና ሰጠ ከአንቺም እግዚአብሔር ቅዱስ ጽላትን ፈጠረ ይኸውም ሥጋው ነው። [ዘፀአ.፴፬፥፳፰-፴]

ከደብረ ሲና እሳት ጨለማ መጣ ፤ ከአንቺ ግን ሰው የሆነ አምላክ ተገኘልን፡፡

በደብረ ሲና በአይሁድ ላይ ድንጋፄ ሀውክ ተደረገ ፤ በአንቺም በአይሁድ በሄሮድስ በዲያብሎስና በሠራዊቱ ላይ ጽኑ ድንጋፄ ተደረገ፡፡ [ዘፀአ.፳፥፲፰ ፡፡ ዕብ.፲፪፥፲፱]  ❞

[      ቅዱስ ኤፍሬም      ]



†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

🕊

[   † እንኩዋን ለታላቁ ጻድቅ "አባ ዮሐኒ" እና "ቅዱስ ለንጊኖስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ †   ]

[ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ትግራይ ውስጥ የሚገኘው አስደናቂው የጻድቁ ገዳም ነው ]


🕊  †  ታላቁ አባ ዮሐኒ  †   🕊

በምድረ ኢትዮዽያ ዝናቸው ከወጣና ቀደምት ከሚባሉ ጻድቃን አንዱ ቅዱስ አባ ዮሐኒ ["ኒ" ጠብቆ ይነበብ] ነው:: አበው ሊቃውንት የቅዱሱን ታሪክና ገድል ገና በልጅነት ስለ ነገሩን አንረሳውም:: እጅግ ጣፋጭ ዜና ሕይወት ያለው አባት ነውና:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-

በ፮ኛው መቶ ክ/ዘመን በሃገራችን ቅዱስ አፄ ካሌብ ነግሦ ሳለ: አንድ ቅዱስ ሰው ከግብጽ ወደ ኢትዮዽያ መጡ:: እኒህ ሰው "አሞኒ ዘናሕሶ" ይባላሉ:: ቅዱሱ ዓለምን ላለማየት ቃል ገብተው በትግራይ በርሃ ይጋደሉ ነበር::

በዘመኑ አፄ ካሌብ የናግራን [የመን] ክርስቲያኖችን ለመታደግ ዘመቻ አድርጎ ነበር:: ታዲያ አንድ የንጉሡ ወታደር ወደ ዘመቻ ሲሔድ ሚስቱን ይጠብቅለት ዘንድ ትንሽ ወንድሙን አደራ ይለዋል:: ወንድሙ ግን አደራውን ትቶ የትልቅ ወንድሙን ሚስት አስገድዶ ይደርስባትና ትጸንሳለች::

ከዘመቻ የተመለሱት ከ፩ ዓመት በሁዋላ ነውና ሚስቱን ምጥ ላይ ያገኛት ወታደር ደነገጠ:: ተቆጣ:: የጸነሰችው ከእርሱ እንዳልሆነ ያውቃልና ምጥ ላይ ሆና ሊያዝንላት አልፈለገም::

ለገልጋይ አስቸግሮ ሚስቱን ይደበድባት ገባ:: በዚህ ምጥ: በዚህ ዱላ ነፍሷን ከሥጋዋ ሊለየው የደረሰችው ያቺ ሴት ግን "ወንድማማችን አላጋድልም" ብላ ቻለችው:: በዚህ ጊዜ ቅዱስ መልአክ ያን ግብጻዊ ባሕታዊ [አባ አሞኒን] አምጥቶ ከሰዎቹ በር ላይ አቆመው::

"ከእሱ ነው በይ" አላት:: እርሷም "ከዚያ ባሕታዊ ነው" ብላ ተናገረች:: ወታደሩ ባሏም በቁጣ ወጥቶ ቅዱስ አሞኒን በዱላ ስብርብር እስኪል ድረስ ደበደበው:: ልጁ ልክ ሲወለድም ከእናቱ ነጥቆ ለባሕታዊው አሳቅፎ አባረረው::

ቅዱስ አሞኒም ሕጻኑን አቅፎ ወደ ተምቤን በርሃ አካባቢ ወሰደው:: ግን ምን ምግብ: ምን ልብስ: ምን መኝታ እንደሚሰጠው ጨንቆት ጻድቁ አለቀሰ:: በዚህ ጊዜም ቅዱስ መልአክ የጸጋ ምንጣፍን አነጠፈለት::

ጆፌ አሞራ መጥቶ ክንፉን ሲያለብሰው አጋዘን መጥታ ጡት አጠባችው:: በዚህ የተደነቀው ቅዱስ አሞኒ ሕጻኑን "ዮሐኒ" ሲል ስም አወጣለት:: ትርጉሙም "ወልደ አራዊት - ወላጆችህ [አሳዳጊዎችህ] አራዊት ናቸው" እንደ ማለት ነው::

ሕጻኑ ዮሐኒ በዚህ መንገድ ከአሞኒና ከአራዊቱ ጋር አደገ:: ፭ ዓመት በሞላው ጊዜም ትምሕርተ ሃይማኖትን: የቅድስና ሕይወትን ተማረ:: ልክ እንደ መንፈሳዊ አባቱ በጾምና በጸሎት ተወሰነ:: ግን እርሱ ከእርሱ: ከአሞኒና ከአራዊቱ በቀር ሌላ ፍጥረት: ዓለም [ብዙ ሰዎች] መኖራቸውን አያውቅም::

፲፪ ዓመት በሞላው ጊዜ ግን ክህነት ይገባዋል ብሎ መንፈስ ቅዱስ ስላሳሰባቸው ቅዱሱ አሞኒ ዮሐኒን ወደ ዻዻሱ ወሰዱት:: መንገድ ላይም ቅዱስ ዮሐኒ ወጣት ሴቶች ተሰብሰበው ሲጫወቱ ተመልክቶ "አባ! እነዚህ ጸጉራቸው የረዘመ: ደረታቸው ወደ ፊት የወጣ ፍጥረቶች ምንድን ናቸው?" ሲል ጠየቀ::

አባ አሞኒም "ልጄ! እነዚህ ሴቶች ናቸው:: ግን ለእንደ እኔና አንተ ያሉ የበርሃ ሰዎች አይሆኑምና አትቅረባቸው" አለው:: ቅዱስ ዮሐኒ መልሶ "አባቴ!ድንገት ቢመጡብኝ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀ:: አባ አሞኒም "ልጄ! ከዘለዓለም ርስት ከምትነቀል ሩጠህ ብታመልጥ ይሻላል" አለው::

ከ፮ ዓመታት በሁዋላ [ዮሐኒ ፲፰ ዓመት ሲሞላው ማለት ነው] ቅዱስ አሞኒ ኅዳር ፭ ቀን ዐረፈ:: ለ፲፬ ዓመታትም ቅዱስ ዮሐኒ ከአራዊትና አባ አበይዶን ከመሰሉ አባቶች ጋር ኖረ:: ከንጽሕናው የተነሳም ቅዱሳን መላእክት ያነጋግሩት ነበር::

ስም አጠራሩ በምድረ ትግራይ ሲወጣ ወላጅ እናቱ በሕይወት ነበረችና ሰማች:: የአካባቢዋን ሴቶች ሰብስባም ልትገናኘው ወዳለበት ተራራ ገሰገሰች:: ወደ ተራራው ደርሳ ስትጠራው ቅዱሱ ተመለከታት::

ወዲያው ትዝ ያለው አባቱ ቅዱስ አሞኒ "ሴት ስታይ ሩጥ" ያለው ነውና እግሩን አንስቶ ሮጠ:: እናቱ ስትከተለው: እርሱ ሲሮጥ ከገደሉ ጫፍ ደረሰ:: ወደ ሁዋላ ሲመለከት ሊደርሱበት ነው::

በስመ ሥላሴ ፊቱን አማትቦ ወደ ገደሉ ተወረወረ:: በዚህ ጊዜ ግን መንፈሳዊ ክንፍ ተሰጥቶት ተሰወረ:: ቅዱስ መልአክም ብሔረ ሕያዋን አስገብቶታል:: ይህንን ታሪክ ሲያደንቁ አበው እንዲህ ብለዋል::

"ሰላም ዕብል ለዘኮነ ሱቱፈ::
ምስለ እለ ገብሩ ሰብእ ብሔረ ሕያዋን ምዕራፈ::
እምሥርዓተ መላእክት ዮሐኒ ምንትኒ ኢያትረፈ::
ከመ ሕይወቶሙ ሕይወተ ተጸገወ ዘልፈ::
ወከመ ክንፎሙ አብቆለ አክናፈ::" [አርኬ]


🕊  † ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት †  🕊

ለንጊኖስ ማለት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስብከት ዘመን የዺላጦስ ወታደር የነበረ ሰው ነው:: ስለ ጌታችን ተአምራት በየጊዜው ይሰማ ነበር:: ሔዶ እንዳያገኘው ግን አይሁድን ይፈራ ነበር:: እነርሱ "በክርስቶስ ያመነ ሁሉ ከምኩራብ ይባረር" ብለው ነበርና:: [ዮሐ.፱፥፳፪]

ጌታችን በተሰቀለባት ዕለተ ዐርብ ግን ጭንቅ ሆነበት:: ጌታን እንዲሰቅሉ ከታዘዙ ወታደሮች እንደ አንዱ ተመርጦ ነበርና በዘዴ አሞኛል ብሎ እስከ ፱ ሰዓት ድረስ ቆየ::

በሁዋላ ግን አይሁድ "በክርስቶስ ሞት ያልተባበረ ሁሉ ወንጀለኛ ነው" የሚል አዋጅ በማስነገራቸው እየፈራ ወደ ቀራንዮ ሲደርስ "ጐኑን ውጋው" ብለው ረዥምና ጥቁር ጦር ሰጡት:: ለንጊኖስ ወደ ጌታችን ዐይን ተመለከተ:: እያየው እንዳልሆነ ገመተ::

ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ ለይቷልና ጦሩን ጨብጦ ወደ ጌታ ጐን ልኮ ወጋው:: ከጌታ ቀኝ ጐንም በ"ለ" አምሳል ትኩስ ደምና ውሃ ፈሰሰ:: አንዷ ፍንጣቂ ሔዳ የታወረች ዐይኑ ላይ ዐርፋ ዐይኑን አበራች::

ለለንጊኖስ ታላቅ ደስታ ሆነ:: ለእኛ ግን ማየ ገቦና ደመ ገቦ ፈለቀልን:: የጌታችን ትእግስቱና ቸርነቱ ግን ይደንቃል::
"ከመ ኢየሐስብ ቦቱ ዘኩናተ እዱ ርግዘቶ::
በኃጣውኢሁ ለዘኢፈቀደ ሞቶ::
ምሕረቶ እሴብሕ ወዐዲ ትዕግስቶ::" እንዳሉ ሊቃውንት::

ጌታችን ከተነሳ በሁዋላ ለንጊኖስ ወደ ቅዱስ ዼጥሮስ ዘንድ ሒዶ ስለ እውነት: ስለ ሃይማኖትም ተማረ:: ተጠምቆ: ምድራዊ ወታደርነቱን ትቶ እየሰበከ ከኢየሩሳሌም ወደ ቀዸዶቅያ ወረደ:: ለዘመናትም ጌታችን ክርስቶስን በሥርዓተ ወንጌል አገለገለ::

በመጨረሻ በጢባርዮስ ቄሣር ዘመን አይሁድ አሳደዱት:: አንገላቱት:: የነርሱ ወገን ስለነበረም መከራ አጸኑበት:: የጽቅድ አርበኛና የክርስቶስ ሐዋርያ ቅዱስ ለንጊኖስ ግን ጸና:: አይሁድም አንገቱን ቆርጠውት ለሰማዕትነት በቃ:: ቅዱሱ በሕይወቱም በዕረፍቱም ተአምራትን ሠርቷል::

" አስተርዮተ ርዕሱ "

ይሕች ዕለት አስተርዮተ ርዕሱ ትባላለች:: እርሱን ከገደሉ በሁዋላ አይሁድ ራሱን ወደ ኢየሩሳሌም ወስደው ጥለዋት ነበር:: የእርሱን ሰማዕትነት ያየች አንዲት ክርስቲያንም ከለቅሶ ብዛት ዐይኗ ቢጠፋ ሕጻን ልጇን ይዛ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች::

ወዲያው ግን ሕጻን ልጇ ሞተባትና ሐዘኗ ከልኩ አለፈ:: ለአንዲት እናት ዐይንንና ልጅን በአንዴ ማጣት እጅግ ጭንቅ ነው:: በሌሊት ግን ቅዱስ ለንጊኖስ በራዕይ ተገልጦ ደስታ ነገራት::

"ልጅሽ በገነት ሐሴትን ያደርጋል:: አንቺ ግን ራሴን ከተቀበረችበት አውጪ" አላት:: ወደ ጠቆማት ቦታ በመሪ ስትቆፍር ብርሃን ወጥቶ ዐይኗ በራላት:: በታላቅ ሐሴትም ቅድስት ራሱን ወደ ሃገሯ ወስዳታለች::

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ  ]

[             ክፍል  ሠላሳ ሰባት            ]

💛

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

[  በእርሻው መካከል እያለቀሰች ትለቅም ስለ ነበረች አንዲት መበለት ሙት እንዳስነሣ  !   ]

                         🕊                         

❝ አባ ሲሶይ እንዲህ አለ ፡- “ አንድ ጊዜ ከአባ መቃርዮስ ጋር በነበርንበት ወቅት ሰባት ሆነን ከእርሱ ጋር ወደ እርሻ ልንሠራ ሄድን፡፡ በእርሻው መካከልም ከኋላችን ሆና እያለቀሰች ቃርሚያ የምትለቅም መበለት ሰማን ፤ ማልቀሷን ፈጽማ ማቆም አልቻለችም፡፡ አባ መቃርዮስም የእርሻውን ባለቤት ጠራውና ፦ " ይህች ሴት ይህን ሁሉ ሰዓት የምታለቅሰው ምን ሆና ነው?” አለው፡፡ እርሱም ፦ " አንድ ሰው ለባሏ ገንዘብ እንዲያስቀምጥለት አደራ ሰጥቶት ነበር ፤ ነገር ግን የት እንዳስቀመጠው ሳይነግራት በድንገት ባሏ ሞተ፡፡ የገንዘቡ ባለቤትም እርሷንና ልጆቿን በገንዘቡ ፋንታ ለባርነት ሊወስዳቸው ነው ፤ የምታለቅሰው ስለዚህ ነው" አለው፡፡ አባመቃርዮስም ፦ " ኋላ ሙቀቱ ሲበረታ በምናርፍበት ጊዜ ወደ እኛ እንድትመጣ ንገራት" አለው፡፡

አባ መቃርዮስም ሲያርፉ ጠራትና ወደ እነርሱ በመጣች ጊዜ ፦ " ይህን ሁሉ ሰዓት የምታለቅሽው ምን ሆነሽ ነው?” አላት፡፡ እርሷም ፦ “ባሌ ገንዘብ እንዲያስቀምጥለት አንድ ሰው ሰጥቶት ነበር ፤ ነገር ግን የት እንዳስቀመጠው ሳይነግረኝ ሞተ አለችው፡፡ አባ መቃርስም ፦ " ነይ ባልሽ የተቀበረበትን መቃብር አሳዪኝ" አላት፡፡ አኃውንም ከእርሱ ጋር ይዟቸው ሄደ፡፡ ወደ ቦታውም በደረሱ ጊዜ አሁን ወደ ቤትሽ ሂጅ አላት፡፡ እነርሱም ከጸለዩ በኋላ ኣባ መቃርዮስ የሞተውን ሰው ጠራውና ብዙ ካናገረው በኋላ ፦ "የዚያን ሰው ገንዘብ የት ነው ያስቀመጥከው?" አለው፡፡ እርሱም ፦ "በቤቴ ውስጥ ከአልጋው ሥር ነው" አለው፡፡

አባ መቃርዮስም ፦ "አሁን እስከ ትንሣኤ ድረስ ማረፍ ትችላለህ" አለው፡፡ አኃውም ይህን ባዩ ጊዜ በፍርሃት ከእግሩ ሥር ወደቁ ፤ አባ መቃርዮስም ፦ "ይህ የሆነው ከእኔ የተነሣ አይደለም ፤ እኔ ምንም ነኝና ፣ ነገር ግን ስለዚች መበለትና አባት ስለ ሌላቸው ልጆቿ ሲል እግዚአብሔር ይህን አደረገ" አላቸው፡፡ ወዲያውም ለዚያች መበለት ባሏ ገንዘቡን የት እንደ ቀበረው ቅዱስ መቃርዮስ ነገራት ፣ እርሷም ገንዘቡን ለሰውየው መለሰችለትና ልጆቿን ነጻ አወጣች ፤ ይህን የሰሙ ሁሉ እግዚአብሔርን አመሠገኑ፡፡ ❞

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

🕊

[  †  እንኩዋን ለቅዱሳን ሰማዕታት "ቶማስ" : "ያዕቆብ ወዮሐንስ" : "አቢማኮስ ወአዛርያኖስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †  ]


🕊  † ቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ †  🕊

ቅዱስ ቶማስ በ፯ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ተወልዶ ያደገ ሶርያዊ ክርስቲያን ነው:: ከልጅነቱ እንደሚገባ መጻሕፍትን ተምሮ ለዲቁና: ለቅስና: ከዚያም ለዽዽስና በቅቷል:: በወቅቱ የሶርያ ዋና ከተማ በሆነችው ደማስቆ ላይ ተሹሞ ያገለግልም ነበር::

ታዲያ ዘመኑ በየቦታው ደም የሚፈስበት ነበርና የክርስቶስን መንጋ መጠበቁ ቀላልና የዋዛ ሥራ አልነበረም:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ያፈሱ የነበሩት ደግሞ ተንባላት [የመሐመድ ተከታዮች] ናቸው:: ፯ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲደርስም ተንባላት ግብጽንና ሶርያን በቁጥጥር ሥር በማድረጋቸው ክርስቲያኖች ተቸገሩ::

በወቅቱም ቅዱስ ቶማስ ሲያስተምር የሰማው አንድ መሐመዳዊ "እንከራከር" አለው:: ቅዱሱም ሊቅ ነበርና ስለ መሐመድ ሐሰተኛነት: ስለ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ካስረዳው በሁዋላ ንጹሕና ሰማያዊ ሕግ ቅዱስ ወንጌል እንጂ ቁርዓን እንዳልሆነ ነገረው::

በአደባባይ በመረታቱ ያፈረው መሐመዳዊም በብሽቀት ሒዶ ለደማስቆው ገዢ ከሰሰው:: ቅዱስ ቶማስም ተይዞ ቀረበ:: "እንዴት እምነታችን እስልምናን ትሳደባለህ?" ቢለው ቅዱሱ "እውነቱን ተናገርኩ እንጂ አልተሳደብኩም" ሲል መለሰለት::

መኮንኑም "እሺ! ክርስቶስ ማን ነው? ስለ ወንጌልና ቁርዓንስ ምን ትላለህ?" ሲል የተሳለ ሰይፍ አውጥቶ ጠየቀው:: የቀናችው እመነት ክርስትና ክብርነቷ በሰማይ ነውና መጨከንን ትጠይቃለች::

ቅዱስ ቶማስ ምንም ሳይፈራ "ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይና የምድር ፈጣሪና አምላክ ነው:: ቅዱስ ወንጌል ሰማያዊና የሕይወት ሕግ ሲሆን ቁርዓን ደግሞ የመሐመድ የፈጠራ መጽሐፍ ነው::" ይህንን የሰማው መኮንን በቁጣ አንገቱን እንዲመቱት አዘዘ:: ቅዱስ ቶማስም በዚህች ቀን ስለ ቀናች ሃይማኖቱ አንገቱን ሰጠ::


🕊 †  ቅዱሳን ያዕቆብ ወዮሐንስ  †  🕊

አሁን ደግሞ ወደ ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን ተመልሰን: ወደ ምድረ ፋርስ [ኢራን] ወርደን ቅዱሳንን እናዘክር:: እነዚህ ቅዱሳንም በሃገረ ፋርስ [ኢራን]: በመንግስተ ሳቦር ዘመን የነበሩ አበው ናቸው:: ሳቦር ማለት ጸሐይንና እሳትን የሚያመልክና እጅግ ጨካኝ የነበረ ንጉሥ ነው::

ቅዱሳኑ ያዕቆብና ዮሐንስ የሐዋርያትን ስም ብቻ ሳይሆን ግብራቸውን: ቅድስናቸውንም የያዙ ነበሩ:: ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ባይሆንም ፋርስ ግን በዚህ ዘመንም ለክርስቲያኖች የግፍ ከተማ ነበረች::

ከቅዱስ ጊዮርጊስ እስከ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ: ከቅዱስ መርምሕናም እስከ ቅዱስ ኮቶሎስ ሰማዕትነትን የተቀበሉት በዚህችው ሃገር ውስጥ ነው:: ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስም ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በልኩ ተምረው: መጻሕፍትንም ተረድተው ለክህነት ተመርጠዋል::

በሁዋላም ቤተ ክርስትያን "ይገባቹሃል" ስትል ዻዻሳት አድርጋ ሾመቻቸው:: እነርሱም አላሳፈሯትም:: የክርስቶስን መንጋ እያስተማሩ: እየናዘዙ ጠበቁላት:: ንጉሡ ሳቦር ግን ሕዝቡን ለፀለሐይና ለእሳት ሊያሰግድ ላደረገው ጥረት እንቅፋት ሁነውበታልና ጠላቸው::

በወታደሮቹ አስይዞም በፍርድ አደባባይ አቆማቸው:: ሕዝቡን በአዋጅ ጠርቶ: አስፈሪ እሳት አስነድዶ "ሕዝቡ ለፀሐይ እንዲሰግድ እዘዙ" ቢላቸው "እንቢ" አሉት::

ከነ ልብሳቸው አንስተው ወደ እሳቱ ወረወሯቸው:: ቅዱሳኑም በመከራው [በነደደው እሳት] መካከል ሆነው ለሕዝቡ ተናገሩ:: "አምላክ አንድ እግዚአብሔር ነውና እንዲህ በሃይማኖታችሁ ጽኑ" አሏቸው:: እሳቱም አቃጥሎ ገድሏቸው የክብርን አክሊል ተቀዳጁ::


🕊 †  ቅዱሳን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ †  🕊

አሁን ደግሞ ወደ ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን: ወደ ዋናው ዘመነ ሰማዕታት እንመለስ:: በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩ ቅዱሳን ሰማዕታት ፪ቱ አቢማኮስና አዛርያኖስ ናቸው:: አውሬዎቹ መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ ዓለምን ለ፪ ተካፍለው በክርስቲያኖች ላይ ግፍን ሲሰሩ ፪ቱ ቅዱሳን በሮም ግዛት ሥር ይኖሩ ነበር::

በዘመኑ እንኩዋን ቤተ ክርስቲያን ማነጸ: መዘመር: እምነትን መግለጥ ይቅርና ሲያማትቡ መታየት እንኩዋ ያስገድል ነበር:: ነገሥታቱ የሾሟቸው ተከታዮቻቸው ክርስቲያኖችን ከዋሉበት አላሳድር: ካደሩበትም አላውል አሉ::

ታላቅ ግፍ: ሰቆቃና ጭንቅ በሆነበት በዚያ ወራት የሞተው ሙቶ እኩሉ ሲሰደድ: አቢማኮስና አዛርያኖስ ግን በከተማ መሐል ተረጋግተው ክርስቶስን ያመልኩ ነበር:: ይህም ተደርሶባቸው ተከሰሱና ተይዘው ቀረቡ::

መኮንኑ ፪ቱን ክርስቲያን ወጣቶች ሲመለከታቸው ምንም የፍርሃት ምልክት አልተመለከተባቸውምና ተገረመ:: "ማንን ታመልካላችሁ?" አላቸው:: እነርሱም "የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን!" ሲሉ መለሱለት::

"ክርስቶስን ትክዳላችሁ ወይስ ትሞታላችሁ?" ቢላቸው "ሰነፍ!" ሲሉ በአደባባይ ገሰጹት:: "የፈጠረ: ያከበረ: ሥጋውን ደሙን የሰጠ ጌታ እንዴት ይካዳል?!" ሲሉም እቅጩን ነገሩት:: በድፍረታቸው የደነገጠው መኮንኑም በዚያች ሰዓት ሞትን አዘዘባቸው:: በዚህች ቀንም አንገታቸውን ተሰይፈው ለክብረ ሰማዕት በቅተዋል::

አምላከ ቅዱሳን ሰማዕታት በነርሱ ያሳደረውን ትእግስትና ጽናት በእኛም ላይ ያሳድርልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

[  ኅዳር ፬ [ 4 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ
፪. ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስ
፫. ቅዱሳን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ
፬. አባ አበጊዶ ዘትግራይ
፭. ታላቁ አባ ዘካርያስ
፮. ጉባኤ ቅዱሳን ሰማዕታት

[     ወርኀዊ በዓላት     ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
፪. ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
፫. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ [ሰማዕት]

"ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን? 'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን' ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::" [ሮሜ.፰፥፴፭-፴፰]

🕊

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

                          †                          

💖  [    የትሕርምት ሕይወት !    ]  💖

🕊                      💖                      🕊

[  ክፉ ሰዎች ፣ አጋንንትና ዲያብሎስ በዚህ ዓለም ላይ እንዲኖሩ የተፈቀደላቸው ለምን አንደ ኾነ ?  ]

------------------------------------------------

“ እነዚህ ኹሉ እንዲኖሩ ለምን እንደ ፈደቀ ብትጠይቅ ፣ ስለማይነገረው የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ ቦታ ባትሰጥ ፣ ኹሉንም ነገር እጅግ አጥብቀህ ብትመረምር ፣ ይህንንም ብትዘልቅበት ሌሎች ብዙ ነገሮችን ታጣለህ፡፡

ለምሳሌ ፦ መናፍቃን በዚህ ዓለም ላይ እንዲኖሩ እግዚአብሔር ለምን ፈቀደ ? ለምን ዲያብሎስ እንዲኖር ፈቀደ ? ለምን አጋንንትስ ? ብዙ ሰዎች እንዲሰናከሉ የሚያደርጉ ክፉዎች ሰዎችስ ? ከዚህ ኹሉ በላይም ጌታችን ክርስቶስ እንደ ተናገረ ፥ ቢቻለውስ የተመረጡትን እንኳን እስኪያስት ድረስ ኃይል ያለው የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚመጣው ለምንድን ነው? [ማቴ.፳፬፥፳፶]

ስለማይመረመረው የእግዚአብሔር ጥበብ ኹሉን ነገር መተው እንጂ እነዚህን ነገሮች ልትጠይቅ አይገባህም፡፡ አስቀድሞ በእውነትና በጽኑ መሠረት ላይ የቆመ ሰው ብዙ ሞገዶች ቢያላትሙት እንኳን ፣ ስፍር ቍጥር የሌላቸው ማዕበላት ሲነሣሡበት እንኳን አይጎዳም ብቻ ሳይኾን እንዲያውም የበለጠ ብርቱ ይኾናል፡፡

ደካማ ፣ ልፍስፍስና ግድ የለሽ ሰው ግን ምንም መከራ ባይገጥመውም እንኳን አዘውትሮ ይወድቃል፡፡ ምክንያቱ ምን እንደ ኾነ ማወቅ ከፈለግህም በኹላችንም ዘንድ በደንብ የታወቀውን አድምጠው፡፡ በብዙና ልዩ ልዩ በኾነ መንገድ በእኛ ላይ የሚኾነውን እያንዳንዱን ነገር የሚያዝዘው እግዚአብሔር ሌሎች ብዙ ግልፅ የኾኑ ምክንያቶችም አሉትና፡፡

እስከዚያው እኛ የምናውቀው ይህንን ነው ፦ እነዚህ መሰናክሎች እንዲመጡ የፈቀደው ቅዱሳን የሚያገኙት ክብር እንዳይቀንስ ነው ብለናል። እግዚአብሔር ከኢዮብ ጋር ሲነጋገር ግልፅ ያደረገው ይህንን ነው ፦ “ ጽድቅህ እንድትገለጥ እንጂ እኔ በሌላ መንገድ የምፈርድብህ ይመስልሃልን? ” እንዲል። [ኢዮ.፵፥፰]

እንደዚሁም ቅዱስ ጳውሎስ ፦ “በእናንተ ዘንድ የተፈተኑት [የተመሰገኑት የተመረጡት] እንዲገለጡ ፥ በመካከላችሁ መለያየት [ምንፍቅና] ደግሞ ሊኾን [ሊኖር] ግድ ነውና” አለ [፩ኛ ቆሮ.፲፩፥፲፱] “በመካከላችሁ መለያየት [ምንፍቅና] ደግሞ ሊኾን [ሊኖር] ግድ ነውና” የሚለውን በሰማህ ጊዜ ግን ፥ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን የተናገረው እንደ ትእዛዝ ወይም እንደ ሕግ አድርጎ እንደ ኾነ አታስብ፡፡ በጭራሽ አይደለም ! ይልቅ ፥ ሊመጣ ያለውን ነገር ትንቢት እየተናገረና ትጉሃን ከዚያ እንደሚያተርፉ ነው እያመለከተ የነበረው፡፡

ከዚያም ያልተታለላችሁ የእናንተ ሃይማኖታችሁ ምግባራችሁ ይገለጣል” አለ፡፡ "

🕊

[  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ   ]


🕊                        💖                    🕊

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

           ❤ #ኅዳር ፳፪ (22) ቀን።

❤ እንኳን በንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበሉ በድዮማ ከተማ አረምያ ከምትባል አገር ለሆኑ #ለቅዱሳን_ለቆዝሞስና_ለድምያኖስ ለወንድሞቻቸው #ለአላድዮስ_ለአቢሞስ_ለአብራንዮስና ለእናታቸው #ለቅድስት_ቴውዳዳ_ለዕረፍታቸው_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ቆዝሞስ ማኅበር #ሰማዕታት_ከሁለት_መቶ_ስልሳ_ሁለት ወንዶችን፣ #ከአርባ_ዘጠኝ_ሴቶችና_ከቀሌምንጦስ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

                     

                            ✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱሳን_ቆዝሞስና_ድምያኖስ ወንድሞቻቸው #አንቲቆስ_ዮንዲኖስና_አብራንዮስ እናታቸው #ቅድስት_ቴዌዳዳ፦ እሊህም ድዮማ ከምትባል ከተማ ስለ እግዚአብሔር ልጅ የታነፀች ግምብ ከአለችበት አረምያ ከምትባል አገር ናቸው። እናታቸውም ቴዌዳዳ እግዚአብሔርን የምትፈራና የምትራራ መጻተኞችንና ድኆችን የምትወዳቸው የምትረዳቸው ናት አባታቸውም ከሞተ በኋላ ልጆቿን እያስተማረች አሳደገቻቸው። እሊህም ሁለቱ ቆዝሞስና ድምያኖስ የሕክምና ጥበብን ተምረው በሽተኞችን ያለ ዋጋ የሚፈውሱአቸው ይልቁንም ድኆችን አብዝተው የሚረዷቸው ሆኑ። ወንድሞቻቸው ሦስቱ ግን ወደ ገዳም ሒደው መነኰሱ በጾምና በጸሎትም ተጠመዱ።

❤ ከአባ አጋግዮስ አደራ በአስጠበቀው በንጉሠ ቊዝ ልጅ ምክንያት ዲዮቅልጥያኖስ ክዶ የረከሱ ጣዖታትን በአመለከ ጊዜ በምዕመናን ላይ መከራ ሆነ ገንዘብ ወዳጅ አጋግዮስ ብዙ ወርቅን ተቀብሎ የንጉሠ ቊዝን ልጅ ወደ አባቱ ልኮታልና ከዚህም በኋላ የንጉሠ ቊዝን ልጅ ዲዮቅልጥያኖስ ዳግመኛ ከጦር ሜዳ አግኝቶ ማረከው እርሱንም ንጉሡን ልጅ ሠውሮ አባ አጋግዮስን ጠራው ያንንም አደራ የሰጠውን የንጉሠ ቊዝን ልጅ እንዲአመጣ አዘዘው  አጋግዮስም ሙቶ ተቀብሮአል ብሎ በሐሰት ተናገረ በዚያንም ጊዜ በመሠዊያው ፊት አማለው እሳትም ከሰማይ ወርዳ እንደምታቃጥለው ጠበቀ የእሳትም መውረድዋ በዘገየ ጊዜ ወርቅን በእሳት አቅልጦ አጠጣውና አቃጠለው ስለዚህም ከወርቅና ከብር የተሠሩ ጣዖታትን አመለከ።

❤ ቆዝሞስና ድምያኖስ በአገሩ ሁሉ ስለ ክርስቶስ እነርሱ እንደሚያስተምሩ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ወደርሱ እንዲአቀርቧቸው አዘዘ በደረሱም ጊዜ ለአገረ ገዢው ለሉልዮስ እንዲአሠቃያቸው ሰጠው። እነርሱም በብዙ ሥቃዮች ማሠቃየትን ጀመረ በእሳት የሚያቃጥልበት ጊዜ አለ በግርፋት የሚገርፍበት ጊዜ አለ ሦስት ወንድሞችም እንዳሏቸው ሰምቶ እነርሱንም ወደርሱ አስመጣቸውና አምስቱንም በመንኰራኵር ውስጥ እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ። ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ጨምሩዋቸው በውስጡም ሦስት ቀኖችና ሌሊቶች ኖሩ ያለ ጥፋትም በጤንነት ወጡ ዳግመኛም ከብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከበታቻቸው እሳቱን አነደዱ እግዚአብሔርም ያለ ጥፋት ጠበቃቸው።

❤ መኰንኑም እነርሱን ማሰቃየት በሰለቸው ጊዜ ወደ ንጉሥ መለሳቸው ንጉሡም ዳግመኛ ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው ቴዎዳዳ እናታቸውም የምታስታግሣቸው ንጉሡንና የረከሱ ጣዖቶቹን የምትረግም ሆነች። በዚያንም ጊዜ አንገቷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለች ሥጋዋ ግን በምድር ላይ ወድቆ ነበር ቆዝሞስም እንዲህ ብለሸ ጮኸ "የዚች አገር ሰዎች ሆይ ይችን አሮጊት መበለት ሥጋዋን አፈር አልብሶ ይሠውራት ዘንድ ከውስጣችሁ ርኅራኄ በልቡ ያደረበት የለምን?" የህርማኖስ ልጅ ቅዱስ ፊቅጦርም በሰማ ጊዜ ተደፋፍሮ ሥጋዋን ገንዞ ቀበራት።

❤ ንጉሡም እነርሱን ማሠቃየት በሰለቸ ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ  እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ከመከራውም ዘመን በኋላ ቤተ ክርስቲያን ተሠርታላቸው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከእርሳቸውም ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
                                              
@sigewe

https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

🕊

[  † እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታት ቆዝሞስና ድምያኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊 † ቅዱሳን ቆዝሞስ ወድምያኖስ  † 🕊

† እስኪ ዛሬ ስለ ክርስትናና ወጣትነት እነዚህን ቡሩካን ወንድማማች ክርስቲያኖች መሠረት አድርገን ጥቂት እንመልከት:: ከዚህ በፊት የበርካታ ወጣት ሰማዕታትን ዜና ሰምተናል:: መጽሐፍ እንደሚል "ወኩሉ ዘተጽሕፈ ለተግሣጸ ዚአነ ተጽሕፈ" - "የተጻፈው ሁሉ እኛ ልንማርበት: ልንገሠጽበት ነውና" [ሮሜ.፲፭፥፬] ልናስተውል ይገባናል::

† ዜና ቅዱሳን የሚነገረን እንደ ታሪክ እንዲሁ ሰምተን እንድናልፈው አይደለም::

፩. ከልቡ ለሚሰማው [ ለሚያነበው ] በረከት አለው::

፪. ከቅዱሱ [ቅድስቷ] ቃል ኪዳን በእምነት ተካፋይ መሆን ይቻላል::

፫. ቅዱሳኑ ክርስትናቸውን ያጸኑበት: የጠበቁበትና ለሰማያዊ ክብር የበቁበትን መንገድ እንማርበታለን:: ትልቁም ጥቅማችን ይሔው ነው::

ቁጥራችን ቀላል የማይባል የተዋሕዶ ልጆች ሕይወተ ቅዱሳንን እንደ ተራ ታሪክ ወይ ጀምረን እንተወዋለን:: ምናልባትም በግዴለሽነት እናነበዋለን:: ደስ ሲለንም ምስሉ ላይ 'like' የምትለውን ተጭነን እናልፈዋለን::

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በደንብ አንብበን "ወይ መታደል!" ብለን አድንቀን እናልፋለን:: ማድነቃችንስ ጥሩ ነበር:: ግንኮ ቅዱሳኑ ለዚህ የበቁት የታደሉ ስለ ሆኑ ብቻ አይደለም:: ከእነርሱ የሚጠበቀውንም በሚገባ ሥለ ሠሩ እንጂ::

እግዚአብሔር የሚያዳላ አምላክ አይደለም:: "ኩኑ ቅዱሳነ እስመ ቅዱስ አነ-እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ" [ዘሌ.፲፱፥፪ , ፩ጴጥ.፩፥፲፭] ብሎ የተናገረው ለጥቂት ወይም ለተለዩ ሰዎች አይደለም:: በስሙ ለሚያምኑ ሁሉ ነው እንጂ::

ስለሆነም እኛ ክርስቲያኖች: በተለይም ወጣቶች ከቀደምቶቻችን ተገቢውን ትምሕርት ወስደን ልንጸና: ልንበረታ: ለቤተ ክርስቲያናችንም "አለሁልሽ" ልንላት ይገባል:: ዛሬ እናት ቤተ ክርስቲያን በተለይ በከተሞች የወላድ መካን እየሆነች ነው::

"ይህን ያህል ሚሊየን ሰንበት ተማሪና ወጣት አላት" ይባላል:: ሲፈተሽ ግን በትክክለኛ ቦታው የሚገኘው ከመቶው ስንቱ እንደ ሆነ ለመናገርም ያሳፍራል:: የሆነውስ ሆነ: መፍትሔው ምንድነው ብንል:- እባካችሁ ከቅዱሳን ቀደምት ክርስቲያኖች መሥራት ያለብንን ቀስመን: ከዘመኑ ጋር አዋሕደን [ዘመኑን ዋጅተን] ራሳችንን: ቤተ ክርስቲያንንና ሃገራችንን እንደግፍ:: ካለንበት ያለማስተዋል አዘቅትም እንውጣ::
ለዚህም ቁርጥ ልቡና እንዲኖረን አምላካችን ይርዳን ብለን ወደ ቅዱሳኑ ዜና ሕይወት እንለፍ::

ቅዱሳን ቆዝሞስና ድምያኖስ በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ በምድረ ሶርያ ተወልደው ያደጉ የዘመኑ ክርስቲያኖች ናቸው:: አባታቸው በልጅነታቸው በማረፉ ፭ ወንድ ልጆችን የማሳደግ ሃላፊነት በእናታቸው ትክሻ ላይ ወደቀ:: እናታቸው ቅድስት ቴዎዳዳ ትባላለች::

እጅግ የምትገርም: ቡርክት እናት ናት:: አምስቱ ልጆቿ "ቆዝሞስ: ድምያኖስ: አንቲቆስ: አብራንዮስና ዮንዲኖስ" ይባላሉ:: በእርግጥ ለአንዲት እናት የመጀመሪያ ጭንቀቷ "ልጆቼ ምን ይብሉ" ነው:: ለቅድስት ቴዎዳዳ ዋናው ጉዳይ ይሔ አልነበረም::

ጌታችን እንዳስተማረን "ኢትበሉ ምንተ ንበልእ: ወምንተ ንሰቲ: ወምንተ ንትከደን - ምን እንበላለን: ምን እንጠጣለን: ምንስ እንለብሳለን ብላችሁ አትጠጨነቁ" ብሏልና ዘወትር የምትጨነቀው ስለ ልጆቿ ሰማያዊ ዜግነት ነበር:: [ማቴ.፮፥፴፩]

በዚህም ምክንያት አምስቱም ልጆቿን ዕለት ዕለት ወደ ቤተ እግዚአብሔር ትወስዳቸው: ከቅዱስ ቃሉ ታሰማቸው: መንፈሳዊ ሕይወትን ታለማምዳቸው ነበር:: አምላክ ከእኛ የሚፈልገው በጐ ፈቃዳችንንና በቅንነት የሆነች ትንሽ ጥረታችንን ነውና ቅድስት ቴዎዳዳ ተሳካላት:: ልጆቿ በአካልም: በመንፈሳዊ ሕይወትም አደጉላት::

ዘመኑ እንደ ዛሬ ተድላ ሥጋ የበዛበት ሳይሆን ክርስቲያን መሆን ለሞት የሚያበቃበት ነበር:: ከዚህ በፊት እንደ ተመለከትነው ከክርስቶስ ልደት ፪፻፸፭ ዓመታት በኋላ በሶርያና በሮም የነገሡት ሁለቱ አራዊት [ዲዮቅልጢያኖስና መክስምያኖስ] ክርስቲያኖችን ከዋሉበት አላሳድሩ: ካደሩበትም አላውሉ አሉ::

ቀዳሚ ፈተናዋን በሚገባ የተወጣችው ቅድስት ቴዎዳዳ ይህኛውንም ትጋፈጠው ዘንድ አልፈራችም:: ግን ከልጆቿ ጋር መመካከር ነበረባትና ለውይይት ተቀመጡ:: ሦስቱ ልጆቿ ከልጅነታቸው ጀምረው ሲሹት የነበረውን ምናኔ መረጡ::

ቅድስቷ እናት በምርጫቸው መሠረት ቅዱሳን አንቲቆስ: ዮንዲኖስና አብራንዮስን መርቃ ወደ በርሃ ሸኘች:: እርሷም ከሁለቱ ቅዱሳን ልጆቿ ቆዝሞስና ድምያኖስ ጋር ቀረች::

እነዚህ ቅዱሳን በከተማ የቀሩት ግን ዓለም ናፍቃቸው አይደለም:: በእሥራት መከራን የሚቀበሉ የእግዚአብሔርን ቅዱሳን ያገለግሉ ዘንድ ነው እንጂ::

ቅድስት ቴዎዳዳ በቤቷ ነዳያንን ስትቀበልና ስታበላ ሁለቱ ቅዱሳን ልጆቿ ቀኑን ሙሉ እየዞሩ እሥረኞችን [ስለ ክርስቶስ የታሠሩትን] ሲጠይቁ: ሲያጽናኑ: ቁስላቸውን ሲያጥቡ አንጀታቸውንም በምግብ ሲደግፉ ይውሉ ነበር::

ይሕ መልካም ሥራቸው ለፈጣሪ ደስ ቢያሰኝም አውሬው ዲዮቅልጢያኖስን ግን ከመጠን በላይ አበሳጨው:: ወዲያውኑ ተይዘው እንዲቀርቡለት አዘዘ:: በትዕዛዙ መሠረትም ቆዝሞስና ድምያኖስ ታሥረው ቀረቡ::

"እንዴት ብትደፍሩ ትዕዛዜን ትሽራላችሁ! አሁንም ከስቃይ ሞትና ለእኔ ከመታዘዝ አንዱን ምረጡ" አላቸው:: ቅዱሳኑ ምርጫቸው ግልጽ ነበር:: ከክርስቶስ ፍቅር ከቶውኑ ሊለያቸው የሚችል ኃይል አልነበረምና:: [ሮሜ.፰፥፴፮]

ንጉሡም "ግረፏቸው" አለ:: ልብሳቸውን ገፈው: ዘቅዝቀው አሥረው: በብረትና በእንጨት ዘንግ ደበደቧቸው:: ደማቸውም መሬት ላይ ተንጠፈጠፈ:: እነርሱ ግን ፈጣሪን ይቀድሱት ነበር::

ይህ ዜና ፈጥኖ ወደ እናታቸው ደርሶ ነበርና ቅድስት ቴዎዳዳ እየባከነች ወደ ሰማዕታት አደባባይ ሮጠች:: አንዲት እናት ልጆቿ በአደባባይ ተሰቅለው ደማቸው ሲንጠፈጠፍ ስታይ ምን ሊሰማት እንደሚችል የሚያውቅ የደረሰበት ብቻ ነው::

ግን ክብራቸውን አስባ ተጽናናች:: ፈጥናም በሕዝቡ መካከል ስለ ሰነፍነቱ ከሀዲውን በድፍረት ዘለፈችው:: ንጉሡም በቁጣ አንገቷን በሰይፍ አስመታት:: ሁለቱ ቅዱሳን ይህንን በዓይናቸው አዩ:: አንዲት ነገርንም ተመኙ:: የእናታቸውን አካል የሚቀብር ሰው::

ግን ደግሞ ሁሉ ስለ ፈራ የቅድስቷ አካል መሬት ላይ ወድቆ ዋለ:: ያን ጊዜ ተዘቅዝቆ ሳለ ቅዱስ ቆዝሞስ አሰምቶ ጮኸ:: "ከእናንተ መካከል ለዚህች ሽማግሌ ጥቂት ርሕራሔ ያለው ሰው የለም?" ሲልም አዘነ:: ድንገት ግን ኃያሉ የጦር መሪ ቅዱስ ፊቅጦር ደረሰ::

ሰይፉን ታጥቆ: በመካከል ገብቶ የቅድስቷን አካል አነሳ:: በክብር ተሸክሞም ወስዶ ቀበራት:: በመጨረሸ ግን የሦስቱ ወንድሞቻቸው ዜና በመሰማቱ ከበርሃ በወታደሮች ተይዘው መጡ:: ከዚያም በብዙ መከራ አሰቃይተው በዚህች ቀን አምስቱንም አሰልፈው ገደሏቸው:: የክብር ክብርንም ከእናታቸው ጋር ወረሱ::

† አምላከ ሰማዕታት ከትእግስታቸው: ከጽናታቸውና ከበረከታቸው ያሳትፈን::

🕊

[  † ኅዳር ፳፪ [ 22 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱሳን ቆዝሞስ ወድምያኖስ [ሰማዕታት]
፪. ቅድስት ቴዎዳዳ [እናታቸው]
፫. ቅዱሳን አንቲቆስ: ዮንዲኖስና አብራንዮስ [ወንድሞቻቸው]
፬. "፫፻፲፩" ሰማዕታት [የነ ቆዝሞስ ማኅበር]

[   † ወርኀዊ በዓላት    ]

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

                           †                           

      [   🕊 ድንግል ሆይ ፦  🕊    ]  

🕊                        💖                       🕊


" ድንግል ሆይ ፦ እታመንሻለሁ ከተሠወረው መከራ በግልጽም ከሚመጣብኝ ጥፋት ሁሉ በዚህ ዓለም እንድታድኝኝ ፤ በሚመጣውም ዓለም ከገሃነመ እሳት ጥርስ ማፏጨት ፥ ጽኑ ልቅሶም ካለበት ከሚያስጨንቅ መቅሠፍት ትሠውሪኝ ዘንድ ፤ እኔም ባንቺ አማላጅነት በልጅሽም ምሕረት የታመንሁ ነኝ፡፡

በፈረሰኞች ሰልፍ በሠረገላም መንኰራኩር የምታመን አይደለሁም፡፡ ባንቺና በልጅሽ ብቻ እታመናለሁ እንጂ፡፡ "

🕊

[  አርጋኖን   ]


🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

🕊

[  ✞ እንኩዋን ለጽዮን "ማርያም ማሕደረ አምላክ" እና ለቅዱሳኑ "ጐርጐርዮስ ወዮሐንስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞   ]


🕊   †  ጽዮን ማርያም  †   🕊

"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው:: አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል::

እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር: ሞገስ: አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል:: [ዘጸ.፴፩፥፲፰] ከዚያም ለ፭ መቶዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች::

ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ: በቀዳማዊ ምኒልክ [እብነ መለክ-እብነ ሐኪም] አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች:: እነሆ በሃገራችን የ፫ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው:: ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን::

ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን:: ግን አንጨነቅም:: ምክንያቱም የመጣችውም: የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም:: በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም:: ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም::

ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን: ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች:: "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው:: "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው::

"ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው:: ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል:: ጽላት [ታቦትን] ያመጣ ፈጣሪ ነው:: በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም ፪ ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን:: [፪ቆሮ.፮፥፲፮ , ራዕይ.፲፩፥፲፱]

በመጨረሻም ኅዳር ፳፩ [ 21 ] ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን:: በዚህች ቀን :-

፩. ታቦተ ጽዮን [ጽላተ ኪዳን] ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን:: ይሕ ሲሆንም ቅዱስ ሙሴ ፵ መዓልት: ፵ ሌሊት ጾሞ እንደ ተቀበለ ሳንዘነጋ ማለት ነው:: [ዘጸ.፴፩፥፲፰ , ዘዳ.፱፥፲፱]

፪. በዘመነ ኤሊ ሊቀ ካህናት ታቦተ ጽዮን በታሪኩዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ [ኢሎፍላውያን] እጅ ተማርካለች:: ግን ደግሞ ዳጐንን ቀጥቅጣዋለች:: [፩ሳሙ.፭፥፩]

፫. በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና: ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ: አገለገለ:: ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ ተቀኘላት:: በዚህም ሜልኮል ንቃው ማሕጸኗ ተዘግቷል:: [፩ዜና.፲፭፥፳፭] ሊቃውንትም "ድንግል እመቤታችን ማርያም በትንቢት መነጽር ተመልክቷል" ብለውናል::

"ሰላም ለኪ ማርያም እምነ::
ዘሰመይናኪ ጸወነ::
ሶበ እምርሑቅ ርእየ ዘጽላሎትኪ ስነ::
ለቢሶ ዳዊት ልብሰ ክብር ዘየኀይድ ዓይነ::
ቅድመ ታቦተ ሕግ ኀለየ ወዓዲ ዘፈነ::" እንዲል:: [አርኬ ዘኅዳር ፳፩]

፬. በዘመነ ንጉሥ ሰሎሞን [መፍቀሬ ጥበብ] ግሩም የሆነ ቤተ መቅደስ ተሰርቶላት ስትገባ ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: እግዚአብሔርም በደመና ወርዶ ንጉሡን አነጋግሯል:: [፪ዜና.፭፥፩ , ፩ነገ.፰፥፩]

፭. በዚያው ዘመንም በፈጣሪ ፈቃድ ንጉሥ ምኒልክ ቀዳማዊ [ዕብነ ሐኪም] ታቦተ ጽዮንን ይዞ ወደ ኢትዮዽያ ገብቷል::

፮. በዘመነ አፄ ባዜን [በ፬ ዓ/ም አካባቢ] አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች:: በዚህ ጊዜም ፪ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታል::

፯. በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመንም ነገሥት ጻድቃን አብርሐ ወአጽብሐ ፲፪ መቅደሶች ያሏትን ግሩም ቤተ ክርስቲያን ለእመ ብርሃን ሠርተው በዚሁ ቀን በጌታችን ተቀድሷል::

፰. በተጨማሪም በየጊዜው: ማለትም በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ ወደ ዝዋይ ትሰደድ ነበር:: ተመልሳ ስትታነጽም ቅዳሴ ቤቷ የሚከበረው ኅዳር ፳፩ ቀን ነው:: በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህ በዓል ልዩ ነው::

" አማናዊት ጽዮን እመ ብርሃን ድንግል ማርያምን እንዲህ እንላታለን "

"ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ "ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን" ናትና::

ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና::

እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው::

፩. "ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ቅዱሳን ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት::

"ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: [ተአምረ ማርያም]

፪. "ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በሁዋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና::

- "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: [ቅዱስ ያሬድ]
- ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: [መጽሐፈ ቅዳሴ]

፫. ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው:: እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና::

፬. እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን [ሐሊበ ድንግልናዌን] ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና::


🕊  † ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘሮም  †  🕊

በቤተ ክርስቲያን እጅግ ስመ ጥር ከሆኑት ሊቃውንት አንዱ ሲሆን ብዙ ጊዜ የሚታወቀው "ገባሬ መንክራት" በሚለው ስሙ ነው:: ገባሬ መንክራት የተባለውም እጅግ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በመሥራቱ ነው::

በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር ተወልዶ ያደገው ቅዱስ ጐርጐርዮስ ከመመነኑ በፊት ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል:: እርሱ በበርሃ እያለም ከሮም ዻዻሳት የአንዱ በማረፉ ተሿሚ ፍለጋ አበው ሱባኤ ገቡ:: እግዚአብሔርም "የበረሃውን ጐርጐርዮስን ፈልጉት" አላቸው::

"እሺ!" ብለው ፍለጋ በርሃ ቢሔዱ ውዳሴ ከንቱን ይጠላልና ተሰወረባቸው:: እነርሱም እያዘኑ ተመልሰው በመንበረ ዽዽስናው ላይ ወንጌልን አኖሩና ተለያዩ:: በዚህ ጊዜ ቅዱስ መልአክ ወርዶ "ጐርጐርዮስ ሆይ! ልትሔድ ይገባሃል" አለው::

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

                       †                       

  [  🕊   ጽዮን ማርያም    🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               
                   
[  ✞ እንኩዋን ለጽዮን " ማርያም ማሕደረ አምላክ " ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞  ]

🕊

"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው:: አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል::

-----------------------------------------------

[             እናታችን ጽዮን                ]


[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]
----------------------------------------------------

" ሰው እናታችን ጽዮን ይላል ፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።" [ መዝ.፹፯፥፭ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
      
                       👇

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ዕሩቅ ብእሲ የወለደች አይደለም .... !  ]

🕊

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

❝ [ እመቤታችን ] መውለድ ጊዜ የሚሆን ምጥ ፈጽሞ አላገኛትም ፤ የአምላክነት ሥራ ስለሆነ መፅነሷ በጣም ይደነቃል ፤ የመውለድዋ ምሥጢር ኀይልም አይመረመርም ፤ ማንም ማን ባሕርዩን የማያውቀውን እርሱን ወለደችውማኅተመ ድንግልናዋም አልተለወጠም

ዕሩቅ ብእሲ የወለደች አይደለም። የመለኮቱ መገኘት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ከመወለዱ ወዲህ አይደለም አስቀድሞ የነበረ ዓለሙን አሳልፎ የሚኖር ነውና ። [ ራእ.ዮሐ.፩፥፰ ]

ሁሉን የፈጠረ ነው ፤ ሰው ከመሆኑ አስቀድሞ ፤ ሰውም ሆኖ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከተወለደ በኋላ እግዚአብሔር ቃል ነውና እርሱ መቸም መች አንድ ነው ፤ የመለኮቱ ባሕርይ ወደ ሰውነቱ ባሕርይ አልተለወጠም ፤ የሰውነቱ ባሕርይም ወደ መለኮቱ ባሕርይ አልተለወጠም ድንግል ማርያም አንድ አካል ሁኖ ወለደችው እንጂ ፤ ሰብአ ሰገልም አንድ ባሕርይ ሁኖ ሰገዱለት እንጂ። [ማቴ.፩፥፲፰—፳፭ ፤ ፪፥፬-፲፪ ]

መለኮትን ከትስብእት ሲዋሐድ የእግዚአብሔር ቃል ተዋሕዶ [ የተዋሕዶ ምስጢር ] ሁለት አካል ፤ ሁለት ባሕርይ የሚባል አይደለም ፥ መለኮትን በሥጋ አልተወለደም የሚሉት ክፉ ጥፉ ወራዶች የሚሆኑ ሰዎች እንደ ተናገሩ ፤

በማይመረመር ግብር ነው እንጂ። ❞

[    ቅዱስ ጎርጎርዮስ  ዘእንዚናዙ    ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

#አፋልጉኝ_ማስታወቅያ።

#ሼር_ሼር_ሼር_በማድረግ_ተባበሩ።

😭 ኤፍሬም እሸቱ ይባላል ኅዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም ቡልጋ ሀገረ ማርያም አውራጃ ሸንኮራ ዮሐንስ ማዶ ወደ ሚገኘው ዶፋ ቅዱስ ሚካኤል በዓል ለማክበር እንደሄደ አልተመለሰም። ያለበትን የሚያወቅ ወይም ያየው ሰው ካለ ከታች ባሉት በእነዚህ ቁጥሮች ደውሎ የሚያሳውቀን ካለ ወሮታው ከፍይ ነን ይላሉ ቤተሰቦቹ።

☎️፦ 0922787035
         0943067047

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊

▷  " አንተነትህ በእግዚአብሔር ፊት ! "

[   " ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ... ! "   ]

[                        🕊                        ]
-----------------------------------------------

❝ እኔ መተላለፌን አውቃለሁና ፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና። አንተን ብቻ በደልሁ ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ ፥ ❞

[ መዝ . ፶፩ ፥ ፫ ]


🕊                        💖                     🕊
                             👇

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

🕊

[  † እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታት ሰርጊስ ወቴዎፍሎስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊  †  ቅዱሳን ባኮስ ወሰርጊስ  †  🕊

† ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ [መስዋዕትነት] ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::

ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::

እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ:: የሚረግሟችሁን መርቁ:: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ::" ብሎናልና:: [ማቴ.፭፥፵፬] ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::

በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና:: እስኪ ለዛሬ ደግሞ በአጭሩ የቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስን ዜና እንካፈል::

እነዚህ ቅዱሳን የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ናቸው:: ባኮስ እና ሰርጊስ [ሰርግዮስ] ከልጅነት ጀምሮ ባልንጀሮች ናቸው:: በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር መክስምያኖስና ዲዮቅልጢያኖስ እስከ ነገሡበት ዘመን ድረስ በአንጻሩም ቢሆን ሰላም ነበር::

ታዲያ በዚህ የሰላም ጊዜ ሁለቱ ቅዱሳን ሥራ አልፈቱም:: ጾምን: ጸሎትንና በጐ ምግባራትን ሁሉ ይከተሉ ነበር:: ለመከራ ዘመን ስንቅ የሚሆነን በሰላሙ ዘመን የተያዘ ስንቅ ነውና::

በዚያው አንጻር ደግሞ ሠርቶ መብላት ይገባልና ሥራ ሲፈልጉ መክስምያኖስ ሠራዊት መሰብሰብ ጀመረ:: እነርሱም ከሠራዊቱ ዘንድ ተቆጥረው የምድራዊ ንጉሥ ጭፍሮች ሆኑ:: በእርግጥ በዘመናችን ለክርስትና አይመቹም ከሚባልላቸው ሥራዎች አንዱ ውትድርና ነው::

ነገር ግን ብዙ ቅዱሳንን ስትመለከቷቸው ሙያቸው ይሔው ነበር:: ቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስ ጊዜው የሰላምም ይሁን የጦርነት ይጾማሉ:: ይጸልያሉ:: ይመጸውታሉ:: እንዲህ እንዲህ እያሉም ዘመናት አለፉ::

ከቆይታ በኋላ ግን ሰይጣን ያደረበት ንጉሡ መክስምያኖስ ጣዖት አመለከ:: አዋጅም አውጥቶ ክርስቲያኖችን ያሰቃይ: ይገድልም ያዘ:: ቅዱሳኑ ይህንን ሲሰሙ አዘኑ::

ቁጭ ብለውም ተወያዩ:: በልባቸው ፍቅረ ክርስቶስ ይነድ ነበርና ወጣትነታቸው: መልካቸው: ተወዳጅነታቸው ሁሉ ሊያታልላቸው አልቻለም:: እንደ አንድ ልብ መካሪ: እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ስለ ሃይማኖት ሊሰው ወሰኑ::

በማግስቱም ንጉሡ ወደ ሾመው የቅርብ አለቃቸው ቀረቡና "የምንነግርህ ነገር አለን" አሉት:: "እሺ" ሲላቸው በወገባቸው ያለውን የክብር መታጠቂያና የክብር ልብሳቸውን በፊቱ ወረወሩለትና "እኛ የክርስቶስ ጭፍሮች ነንና ከዚህ በኋላ ላንተ: ለጣዖት አምላኪው አንታዘዝም" አሉት::

መኮንኑ ነዶታልና አስገረፋቸው: አሳሰራቸው:: በረሃብና በጥም: በብዙ መክፈልተ ኩነኔም አሰቃያቸው:: እነርሱ ግን ጽኑዓን ነበሩና አልቻሏቸውም:: ጥቅምት ፬ [4] ቀን በሆነ ጊዜ ግን ሁለቱን ለያዩዋቸው:: ቅዱስ ባኮስን ለብቻው ወስደው ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ ላይ አሠሩበትና ባሕር ውስጥ አሰጠሙት::

ነፍሱም ከስጋው ስትለይ ባሕር ወደ ዳር አስወጣችው:: በአካባቢውም "ባባ" እና "ማማ" የሚባሉ ባሕታውያን ነበሩና እግዚአብሔር እንዲገንዙት አዘዛቸው:: ሲሔዱም ቅዱስ ሥጋውን አንበሳና ተኩላ ሲጠብቁት አግኝተው: በታላቅ ዝማሬ ገንዘው: በራሳቸው ተሸክመው ወስደው: በበዓታቸው ውስጥ ቀበሩት::

ቅዱስ ሰርጊስን ደግሞ ለ፮ ቀናት ካሠሩት በኋላ እጁንና እግሩን በእንጨት ላይ ቸንክረው: በእንስሳት ጭራ ላይ አስረው ሲጐትቱት ውለዋል:: አንገቱን በሰየፉት ጊዜም አንዲት ወጣት ደሙን ተቀብላ በረከትን አግኝታለች:: የመከራ ዘመን ካለፈ በኋላም ለቅዱሳኑ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ በዚህች ቀን ተቀድሷል: ተአምራትም ታይተዋል::


🕊  † ቅዱስ ቴዎፍሎስና ቤተሰቡ †  🕊

† ቅዱስ ቴዎፍሎስ በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር ይኖር የነበረ ጽኑዕ ክርስቲያን ነው:: እግዚአብሔር ሲያድለው ደግሞ ጸንታ የምታጸና: በርትታ የምታበረታ ሚስትን ሰጠው:: ስሟም ጰጥሪቃ ይባላል::

በክርስትናዋና በፈጣሪዋ ፍቅር ላይ ይሉኝታና ድርድርን የማታውቅ ብርቱ ሴት ናት:: ሁለቱ ተጋብተው በሕጉና በሥርዓቱ ሲኖሩ እግዚአብሔር በረድኤት ጐበኛቸውና ቅድስት ጰጥሪቃ ጸነሰች:: በወለደችውም ጊዜ "ደማሊስ" ስትል በሃገራቸው ልሳን ስም አወጣችለት::

ልክ ግን ከአራስነት አልጋዋ በተነሳችበት ወራት ያ የመከራ ዘመን [ዘመነ ሰማዕታት] ድንገት ደረሰ:: እሷም አካሏ አልጸናም: ልጇም ገና ፭ ወሩ ነው:: ባሏ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ደግሞ በጨካኙ ንጉሥ እጅ መውደቁን [መታሠሩን] ሰማች::

ይኼ እጅግ ከባድ ፈተና ቢመስልም እርሷ ግን ልጇን አዝላ ወደ እሥር ቤት ሔደች:: ባሏንም "ወንድሜ! እኔና ልጅህን በክርስቶስ ዘንድ ስለምታገኘን ጽና:: ክብርህን እንዳትተው" አለችው:: እርሱም ደስ ብሎት ብዙ መከራን ተቀበለ::

ግርፋቱ: እሳቱ ስለቱ ሁሉ ሲያልፍበት በተአምራቱ አሕዛብን ማረከ:: ቅዱስ መልአክም ከሰማይ ወርዶ ማርና ወተትን መገበው:: ከዚያም በዚህ ቀን ለአንበሳ ተሰጠ:: አንበሳውም ለቅዱሱ ሰግዶ: እግሩንም ስሞ: አንገቱን ተጭኖ ገደለው::

ወዲያው ሚስቱ ቅድስት ጰጥሪቃ ተይዛ እርሷም ከነ ልጇ ለአንበሳ ተሰጠች:: በዚህ ጊዜ የ፭ ወር ሕጻን ቅዱስ ደማሊስ አፉን ከፍቶ "እኔስ በሥላሴ አምናለሁና አንበሳን አልፈራም" ሲል እየሳቀ ጮኸ:: ወዲያውም እናትና ልጅን አንበሳው ገደላቸው:: ቅዱሱ ቤተሰብም ለክብር በቃ::

† አምላከ ሰማዕታት ጽንዐታቸውን: ትእግስታቸውንም ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

🕊

[  † ኅዳር ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ሰርጊስ ሰማዕት
፪. ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሰማዕት
፫. ቅዱሳን ጰጥሪቃና ደማሊስ [የቅዱሱ ሚስትና ልጅ]
፬. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ [ልደቱ]

[   †  ወርሐዊ በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
፫. አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
፬. አቡነ ስነ ኢየሱስ
፭. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
፮. ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ

† "እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን::" † [ሥርዓተ ቅዳሴ ቁ. ፸፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

          ❤ #ኅዳር ፲፱ (19) ቀን።

❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_ለዓለም_ብርሃን ለሆኑት እመቤታችን ዕጣን እየሰጠቻቸው #ከሃያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ_ጋር_የሥላሴን_መንበር ላጠኑት #ለአቡነ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋት_ለልደታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።

                          ✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋት፦ አባታቸው ንጉሡ ዐፄ ዳዊት እናታቸው ዳግም ሞገሳ ይባላሉ፡፡ ትውልድ ሀገራቸው ወሎ መቄት እንጂፋ ነው፡፡ አባታችን አባ ዮሴፍ ኅዳር 19 ቀን ሲወለዱ በርካታ ሙታን ተነሥተዋል፡፡ ይህም ቅዱስ ያዩትና የሰሙት እስቲያደንቁት ድረስ በአባቱ ቤት ሳለ የዚህን ዓለም ጥበብ ሁሉ ተማረ የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት ተረጐመ ከዚህም በኋላ ዲቁና ሾሙት።

❤ የነፍሱንም ድኅነት እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ ብርሃናዊ መልአኩን ቅዱስ ሚካኤልን ላከለትና "ዮሴፍ ሆይ ይህን ኃላፊውን ዓለም ትወድዋለህን አስጸያፊ አይደለምን በውስጡም ያለ ሁሉ" አለው። ከዚያችም ጊዜ ጀምሮ እርሱ የመረጠውን መንገድ ይመራው ዘንድ እግዚአብሔር እየለመነ ጾምና ጸሎትን ጀመረ።

❤ ከወለቃ አውራጃም ስሙ አባ ዘካርያስ የሚባል ነበረ እርሱም ለዮሴፍ ዘመዱ የሆነ በጭልታም ዮሴፍን ወስዶ የምንኵስና ልብስ አለበሰው። ወደትግራይ ምድርም ወስደውና በዚያ ተግባረ እድ ለምንኵስና ሥራ የሚገባ ጽሕፈትን ስፌትን ተማረ።

❤ ከዚህም በኋላ ወደ በረሀ ዱር ገብተው የእንጨት ፍሬ እየበሉ ከዝኆኖች ከአንበሶችና ከዘንዶዎች እየተፈተኑ በየአይነቱ በሆነ ተጋድሎ በመድከም ኖሩ። በጽድቃቸውም ኃይል ብዙ ተአምራትን አደረጉ አባ ናትናኤልም የጋለ ምንቸት በመሐል እጁ ይዞ በመነኰሳቱ ፊት ዞረ። አባ ዮሴፍም የሚያበስሉበት ማሰሮ በተሰበረ ጊዜ ወጡ ሳይፈስ አገናኝቶ እንደ ቀድሞው አደረገው። ገብረ ኄርም ሕዝባዊ ሲሆን በሞተ ጊዜ ሊአጠምቁት ሲሉ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ኤጲስቆጶስነት ሹሞኛልና እኔ በእጄ አጠምቃችኋለሁ" አላቸው። እሊህም ቅዱሳን የትሩፋታቸውንና የጽድቃቸውን የአማረ ሥራቸውን አሳዩ።

❤ ከዚህም በኋላ አባ ዮሴፍን ወደ ጳጳስ ወሰዱትና ቅስና ተሾመ። አባ ዘካርያስም በዐረፈ ጊዜ አባ ዮሴፍ ወደ ሌላ ገዳም ሒዶ ሳይቀመጥ ቁሞ አርባ መዓልትም አርባ ሌሊት ጾመ። ከድካም ጽናትም በወደቀ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል አነሣው። ሁለተኛም ከገደል አፋፍ እጁን ዘርግቶ ሳይሰበስብ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ቆመ። ሰይጣንም መጥቶ ወደ ቆላ ወረወረው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ተቀብሎ ወደ መቆሚያው መለሰው።  ደግሞም ከደንጊያ ወሻ ውስጥ ገብቶ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ያለ መብልና ያለ መጠጥ ኖረ። ሰይጣናትም ወደርሱ እየመጡ በየራሳቸው ምትሐት በማሳየት ያስፈራሩት ነበር መላእክትም ያበረቱትና ያጸኑታል። ናላው በአፍንጫው እስቲፈስ ድረስ በየእልፍ እልፍ እየሰገደ ኖረ።

❤ ከዚያም የትራይን አውራጃዎች ሁሉ ዞረ። ወደ ሰሜንም ምድር ተሻግሮ ከቅዱስ ያሬድ መቃብር ገባ በደጃፉም ላይ ተቀርጾ አግኝቶ አንቀጸ ብርሃን ተማረ። ሲመለስም ሽፍቶች አግኝተውት በደንጊያ ወገሩት በበትርም ደበደቡት በጦርም ወግተው ጥለውት ሔዱ። አምላክን የወለደች እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም ወደርሱ መጥታ አዳነችው። አንዲት ቀንም የሴት በድን አግኝቶ በላይዋ ባማተበ ጊዜ ተነሣች።

❤ ወደ ኢየሩሳሌምም ሦስት ጊዜ ሒዶ ከከበሩ ቦታዎች ተባርኳል ወደ አባቶቻችን ሐዋርያት መቃብም እስከ አገረ ባርቶስና ሕንደኬ ደረሰ። ውኃው ከመላበት ወንዝም በሚደርስ ጊዜ በላዩ አማትቦ እንደ የብስ በእግሩ እየረገጠ ይሻገረዋል። አንበሶችና ነብሮች ይከተሉታል ምግብ በአጡ ጊዜ ድንጊያውን ባርኮ ሥጋ አድርጎ ይሰጣቸዋል።

❤ ከዚህ በኋላም ወደ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ገዳም ደብረ ሊባኖስ ሔደ። ከአባ ተወልደ መድኅንም እጅ አሰሰኬማ ተቀበለ። አባ ተወልደ መድኅንም ሊፈትነው ወዶ ሰባት የጽድ ቅርንጫፍ ሰብሮ ትከለው ብሎ ሰጠው በተከላቸውም ጊዜ ወዲያውኑ በቅለው አደጉ እስከ ዛሬም አሉ። ብዙዎችም ወደርሱ መጥተው በእርሱ እጅ መነኰሱ እግዚአብሔር አብና አምላክን በወለደች በእመቤታችን ድንግል ማርያም ስም በአነፃቸው አብያተ ክርስቲያን በአንድነት ኖሩ።

❤ በአንዲት ዕለትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕጣንን ሰጠችውና ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋራ የአሸናፊ የእግዚአብሔርን መንበር አጠነ። ብዙ ጊዜም ወደርሱ ሐዋርያት እየመጡ ይባርኩታል። በአንዲት ዕለትም ነብር ከእናቱ እጅ ሕፃንን ነጥቆ ወሰደ በአባ ዮሴፍም ስም በአማጸነችው ጊዜ በሦስተኛው ቀን መለሰላት።

❤ ለልጆቹም ገንዘብም ሆነ የእንስሳ ጥሪት እንዳያደርጉ ሥጋ እንዳይበሉ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ ትሕትናን ቅንነትን እንዲማሩ ከንቱ ነገር ቧልትን እንዳይናገሩ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዳይስቁ ይህ ሁሉና የመሳሰለውን ሥርዓትን ሠራላቸው።

❤ ከዚህም በኋላም ሩጫውን በፈጸመ ጊዜ ግንቦት19 ቀን በሰላም በፍቅር ዐረፈ ደብረ ታቦር ብሎ በሰየማት ቤተ ክርስቲያንም ተቀበረ ከእርሱም ቊጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሴፍ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑረሰ ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት19 ስንክሳር።    

@sigewe

https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

አምላከ ቅዱሳን የቀደምቶቻችንን የዋህነት ለእኛም ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

🕊

[  † ኅዳር ፭ [ 5 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ታላቁ ቅዱስ ዮሐኒ [ዘትግራይ]
፪. አባ አሞኒ ዘናሕሶ
፫. ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት
፭. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት

[   †  ወርሐዊ በዓላት    ]

፩. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፪. ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
፫. ቅድስት አውጋንያ [ሰማዕትና ጻድቅ]
፬. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ

" ወደ ጌታ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም:: ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጐኑን በጦር ወጋው:: ወዲያውም ደምና ውሃ ወጣ:: ያየውም መስክሯል:: ምስክሩም እውነት ነው:: እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ: እርሱ እውነት እንዲናገር ያውቃል:: ይህ የሆነ:- "ከእርሱ አጥንት አይሰበርም" የሚል የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው:: ደግሞም ሌላው መጽሐፍ:- "የወጉትን ያዩታል" ይላል::" [ዮሐ.፲፱፥፴፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

🔔


[ " ቶሎ ባለማስቆማችን ምክንያት ... ! " ]



በሐሰተኛ መንፈስና አሠራር ቅድስት ቤተክርስቲያንን እየፈተኑና ምዕመናንን እያጎሳቆሉ ስለሚገኙ ሐሰተኛ አጥማቂያን ተከታታይ መርሐ-ግብር ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የሚቀርብ ይሆናል !

ይከታተሉ !



                †       †       †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ እርሱ ራሱም እግዚአብሔር እንደሆነ !  ]

🕊

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

❝ የከበሩ መጻሕፍት ክርስቶስ ሰው እንደሆነ እንደሚነግሩን አምላክም እንደሆነ እነርሱ እንዲሁ ይነግሩናል።

ግዙፍ እንደሆነ እንደሚነግሩን ረቂቅም እንደሆነ። የእግዚአብሔር ቃልም እንደሆነ እርሱ ራሱም እግዚአብሔር እንደሆነ እንዲሁ ይነግሩናል። [ዮሐ.፩፥፩-፲፬ ። ፬፥፳፬ ። ፭፥፳-፳፯] ግዕዙን ተመልከት። ሉቃ.፳፬፥፴፱] ❞

[      ቅዱስ ኤጲፋንዮስ      ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

                       †                       



እግዚአብሔርም ለድሆች መጠጊያ ሆናቸው ፥ እርሱም በመከራቸው ጊዜ ረዳታቸው ነው። ❞ [ መዝ . ፱ ፥ ፱ ]





💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን

                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ  ]

[             ክፍል  ሠላሳ ስድስት            ]

💛

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

[  ለተልዕኮ የወጣ ደቀ መዝሙሩ በቅዱስ መቃርዮስ ጸሎት ከፈተና እንደ ዳነ  !   ]

                         🕊                         

❝ ከቅዱስ መቃርዮስ ደቀ መዛሙርት አንዱ የእጁን ሥራ ይዞ ወደ አንድ ሀገር ሄደና የያዘውን የተግባረ እድ ውጤት ሰዎች ይገዙት ዘንድ በመንገድ ይዞር ነበር፡፡

ያን ጊዜ አንዲት ሴት አየችውና በዚያ ወጣት ረድእ ላይ ሰይጣን በልቧ ውስጥ ክፉ ፍትወትን አሳደረባትና ከበሯ ላይ ሆና ከእርሱ ለመግዛት የፈለገች መስላ ጠራችው ፣ ቤቷንም ከፈተችለት፡፡ ከዚያም በሯን ዘጋችና በሌላ ነገር ትናገረው ዘንድ ጀመረች፡፡ ይበላ ዘንድ ማዕድ ልታቀርብለት ፈለገች፡፡ እርሱም ፦ “ መነኰሳት በዚህ ሰዓት አይበሉም ፣ ገና ጧት ነውና ” አላት፡፡ ሰይጣንም አቻኮላት ፣ በኃጢአት ፍትወትም አነደዳት፡፡ እርሷም ያለ ኃፍረት ፦ “ እኔ ስበላ የማትበላ ከሆነ ተነሥና ከእኔ ጋር ተኛ " አለችው:: ያ እሱም በታላቅ ድምጽ እንዲህ እያለ ጮኸ ፦ “የአባቴ የቅዱስ መቃርዮስ አምላክ ሆይ ፣ በጸሎቱ አጽናኝ ፣
እርዳኝም
” አለ፡፡ ያን ጊዜም ያ ወጣት መነኰስ ቅርጫቱን እንደ ያዘ ተመሰጠና ራሱን በገዳሙ ውስጥ በቅዱስ መቃርዮስ በኣት በር ላይ ሆኖ አገኘው፡፡

እግዚአብሔርም በዚህ እሱ ላይ ገጥሞት የነበረውን መከራ ለቅዱስ መቃርዮስ ገልጦለት ስለ ነበር ረድኡ ወደ እርሱ እስከሚመለስ ድረስ ስለ እርሱ ቆሞ እየጸለየ ነበር፡፡ ያ ረድእም ቅዱስ መቃርዮስን እጆቹ ተዘርግተው እግዚአብሔር ያድነው ዘንድ ስለ እርሱ እግዚአብሔርን እየማለደ አገኘው፡፡ ቅዱስ መቃርዮስም ያን ረድእ ባየው ጊዜ ፦ “ ልጄ ሆይ ፦ ስለ ቸርነቱ እግዚአብሔርን አመስግነው ! ቀድሞ ፊልጶስን ከኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ፊት እንደ መሰጠው አሁንም አንተን ተሽክሞ እዚህ አድርሶሃልና " አለው፡፡ ያ ረድእም እግዚአብሔር በአገልጋዩ በቅዱስ መቃርዮስ እጅ የሚያደርጋቸውን ድንቅ ድንቅ ተኣምራትና መንክራት ይናገር ነበር፡፡ ❞

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…
Subscribe to a channel