gedlekidusan | Unsorted

Telegram-канал gedlekidusan - ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

3467

ይህ ገጽ ስለ ቅዱሳን ክብር ተዓምር ገድል ይናገራል::

Subscribe to a channel

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ ብሶይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ቅዱስ አባ ብሶይ ሰማዕት <3

ቅዱሱ አባታችን ከዘመነ ሰማዕታት ጣፋጭ ፍሬዎች አንዱና ግንባር ቀደሙ ነው።
ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦
በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማጠናቀቂያ አካባቢ ታግሕስጦስና ክሪስ የሚባሉ ክርስቲያኖች ነበሩ። በቀናው የጽድቅ ጐዳና ቢኖሩም ከጋብቻ በኋላ ለአሥራ ሰባት ዓመታት መውለድ አልቻሉም።

የአሥራ ሰባት ዓመት ልመናቸውን የተመለከተ እግዚአብሔር ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ አበሰራቸው። "ሕፃኑ ለሰማዕትነት ተመርጧልና ብሶይ በሉት።" አላቸው። ብሶይ በተወለደ በሰባት ዓመቱ ወላጆቹ ይማር ብለው ወደ ገዳም ወሰዱት። በገዳም ውስጥ መጻሕፍትን አጥንቶ ዲቁናን ተሾመ። ወደ ዓለም ተመለስ ቢሉትም እንቢ አለ።

ከባልንጀራው ቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ለሃያ አንድ ዓመታት በድንግልና በተጋድሎ ጾምና ጸሎትን እያዘወተሩ ኖሩ። ቅዱስ ብሶይ ሃያ ስምንት ዓመት በሞላው ጊዜ መልአኩ የተናገረው የትንቢት ዘመን ደረሰ። በርካታ ምዕመናን ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ታረዱ። ወደ እሳትም ተጣሉ። ሞትን የፈሩ ደግሞ በየዱር ገደሉ ተሰደዱ።

ቅዱስ ብሶይም በሚያውቁት ሰዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ። ድንገት ከሰማይ ፍጡነ ረድኤት ወሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ደረሰለት። "አይዞህ! እኔ እስከ መጨረሻው ከአንተ ጋር ነኝ።" አለው።

የጦር መኮንኑ ክርስቶስን እንዲክድ አባበለው። ቅዱሱ ግን ጣዖታቱ የአጋንንት ማደሪያ መሆናቸውን በገሃድ ነገረው። መኮንኑ ቢበሳጭ ወታደሮቹ እንዲጨምቁት አዘዘ። ደሙ እየወረደ ገረፉት። በፊትና በኋላ ብረት አድርገው ሥጋውን ጨፍልቀው እሥር ቤት ውስጥ ጣሉት። ሊቀ መላእክት መጥቶ ዳስሶ አዳነው።

መኮንኑ እርሱን ማሰቃየት ደከመው። የቅዱሳን ሕይወት ግርም ይላል። ተገራፊው እያለ ገራፊው ስቃዩን የሚቀበለው እያለ አሰቃዩ ይደክመዋል።
ይህንን መሰለኝ አባ ጽጌ ድንግል፦
"እመዐዛ ጽጌኪ ድንግል ውስተ ዐውደ ስምዕ ዘሰክረ።
ውግረተ አዕባንኒ ይመስሎ ሐሰረ።
እሳትኒ ማየ ባሕር ቆሪረ።" ያለው።

ቅዱስ ብሶይን ከአንዱ መኮንን ወደ ሌላው እያመላለሱ አሰቃዩት፤ አካሉን ቆራረጡት። ዓይኑን በጋለ ብረት አወጡት፤ በምጣድ ቆሉት። በጋን ውስጥ ቀቀሉት። እርሱ ግን በፈጣሪው ፍቅር የጸና ነውና ሁሉን ታገሰ። በእነዚህ ሁሉ የስቃይ ዓመታት ቁራሽ ዳቦ እንኳ አላቀመሱትም። በረሃብ ቀጡት እንጂ። ለእርሱ ግን ምግቡ የክርስቶስ ስም ነበር።

በመጨረሻ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ አንገቱን በሰይፍ አስመታው። ሥጋውንና የተቆረጠ አንገቱን ገንቦ (ጋን) ውስጥ ከቶ ጣለው። የቅዱሱን አካል የያዘችው ጋን ግን በእግዚአብሔር ቸርነት ማንም ሳይሸከማት ከመሬት ከፍ አለች። ለሃያ ቀናት ተጉዛ ከሶርያ ግብጽ (ቦሃ) ደረሰች። ክርስቲያኖች ተቀብለው ሲከፍቷት የቅዱስ ብሶይ ራሱና አንገቱ ተጣብቆ ተገኝቷል። በክብርም አሳርፈውታል።

<3 ቅዱስ ያዕቆብ <3

ዳግመኛ በዚህች ቀን ጻድቅና ተአማኒ (ታማኝ) የተባለ የምሥራቅ ሰው ቅዱስ ያዕቆብ መታሠቢያ ይደረግለታል።

ቅዱስ ያዕቆብ ቁስጥንጥንያ አካባቢ በርሃ ውስጥ ይኖር የነበረ አባት ነው። ከቅድሰና ሕይወቱ ባሻገር በደፋርነቱ (ጥብዐቱ) ይታወቃል። በ፫፻፵ዎቹ ዓ.ም ታናሹ ቆስጠንጢኖስ አርዮሳዊ በሆነ ጊዜ ይሔ አባት በይፋ ገስጾታል።

በዚህም ምክንያት መከራን ተቀብሏል። ታስሯል፤ ተገርፏል። እግዚአብሔርም መናፍቁን ንጉሥ ለጦርነት በወጣበት ቀስፎታል። ቅዱሱ በዚህች ቀን ዐርፎ ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔዷል።

ቸር አምላክ ከሰማዕቱ ቅዱስ ብሶይ እና ከቅዱስ ያዕቆብ በረከት ያሳትፈን። በምልጃቸውም ይቅር ይበለን።

ሰኔ ፭ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ አባ ብሶይ (ኃያል ሰማዕት)
፪.ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ
፫.ቅድስት ማርታ ለባሲተ ክርስቶስ (በቅድስናዋ የተወደሰች በስደት ያረፈች እናት)
፬.ቅዱስ ቢፋሞን ሰማዕት
፭.ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት
፮.ቅዱስ መርቆሬዎስና ማኅበሩ (ሰማዕታት)

ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፪.ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ
፫.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
፬.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮጵያዊ
፭.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
፮.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)

"ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ ወይስ ጭንቀት ወይስ ስደት ወይስ ራብ ወይስ ራቁትነት ወይስ ፍርሃት ወይስ ሰይፍ ነውን?
"ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን። እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን።" ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።"
(ሮሜ ፰፥፴፭-፴፯)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቴሌግራም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ተጠምቀ መድኅን እና ለእናታችን ቅድስት ማርታ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 አቡነ ተጠምቀ መድኅን <3

ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ፲፮፻፲ ዓ.ም ሲሆን ወላጆቻቸው ወልደ ክርስቶስና ወለተ ማርያም ይባላሉ። ታኅሣሥ ፪ ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር ፲፩ ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው። በምድረ ጐጃም ከበቀሉ ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕፃንነታቸው ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ።

ሕፃን እያሉ ቃለ እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው። እርሳቸው ግን በሕፃን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም።

ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን፣ ነብሩን፣ ተኩላውን ሰብስበው "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ።" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ። አራዊቱ ከበጉ፣ ከፍየሉ፣ ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ። ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ።

ተጠምቀ መድኅን በሕፃንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር። ሃያ ሦስት ዓመት ሲሞላቸው ወደ መርጡ ለማርያም ሔደው መንኩሰዋል።
ከዚህ ጊዜ በኋላ ለሠላሳ ሰባት ዓመታት
፩.በፍጹም ተጋድሎ ኑረዋል።
፪.ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል።
፫.ከጐጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል። (ካህን ናቸውና።)
፬.ሰባት ገዳማትንና አሥራ ሁለት አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል።

ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በስልሳ ዓመታቸው በ፲፮፻፸ ዓ.ም (በአፄ ዮሐንስ ጻድቁ ዘመን) ዐርፈዋል።

እግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን አጽማቸው ዛሬ በጋሾላ ቅዱስ ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም ውስጥ ይገኛል።

<3 ቅድስት ማርታ <3

እናታችን ቅድስት ማርታ በቀደመ ሕይወቷ እጅግ ኃጢአቷ የበዛ ሴት ነበረች። እጅግ ቆንጆ መሆኗን ሰይጣን ለኃጢአት እንድትጠቀምበት አባበላት። እርሷም ተቀበለችው። በወጣትነት ዘመኗ በመልኳና በገላዋ በርካቶችን ወደ ኃጢአት ሳበች።

መጽሐፍ እንደሚል ለሁሉም ሰው የመዳን ቀን ጥሪ አለውና አንድ ቀን (በበዓለ ልደት) ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች። ዘበኛው ግን ሲያያት ተጸይፏልና አትገቢም አላት። ተከራከረችው፤ ለመነችው። ግን አልተሳካላትም። ሰዓቱ የቅዳሴ ቢሆንም እርሷ እሪ አለች። ለቅዳሴ የቆሙ ሁሉ በመታወካቸው ጳጳሱ ወጥቶ ገሰጻት።

ያን ጊዜ ነበር ወደ ልቧ የተመለሰችው። በጉልበቷ ተንበርክካ መራራ ለቅሶን አለቀሰች። ጳጳሱንም ተማጸነችው፦ "እጠፋ ዘንድ አትተወኝ። ወደ ጌታዬ አድርሰኝ።" አለችው። ወዲያውም ወደ ቤቷ ሔዳ የዝሙት እቃዋን አቃጠለች። ጸጉሯን ተላጨች። ንብረቷን ሁሉ ለነዳያን አካፈለች። ጳጳሱም ንስሐ ሰጥቶ ወደ ገዳም አሰናበታት።

ወደ ገዳም ገብታ በዓት ተቀብላ ጾምና ጸሎትን ከእንባ ጋር አዘወተረች። ለሃያ አምስት ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ከበዓቷ ሳትወጣ አንድም ሰው ሳታይ ኖረች። ከማረፏ በፊትም ብዙ ተአምራትን አድርጋለች።

የቅዱሳን አምላክ ለእኛም እድሜ ለንስሐ ዘመን ለፍስሐ አይንሳን። ከበረከታቸውም ያድለን።

ሰኔ ፫ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.አቡነ ተጠምቀ መድኅን ጻድቅ (ኢትዮጵያዊ)
፪.ቅድስት ማርታ ተሐራሚት
፫.ቅዱስ ኢላርዮን ሰማዕት
፬.ቅዱስ ኮርዮን ሰማዕት

ወርኀዊ በዓላት
፩.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
፪.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
፬.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
፭.አቡነ ዜና ማርቆስ
፮.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል

"አልሞትም በሕይወት እኖራለሁ እንጂ። የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ።
መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ። ለሞት ግን አልሠጠኝም።
የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ። ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት። ጻድቃን ወደ እርስዋ ይገባሉ።
ሰምተኸኛልና መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ።"
(መዝ ፻፲፯፥፲፯-፳፩)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቴሌግራም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለተባረከ ወር ሰኔ እና ለቅዱሳን ዮሴፍ ጻድቅ ወለውንትዮስ ሰማዕት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ <3

ቤተ ክርስቲያን በዚህ ስም የሚጠሩ ብዙ ቅዱሳን አሏት። በተለይ ደግሞ "እስራኤል" የተባለ የቅዱስ ያዕቆብ ልጅ ቅዱስ ዮሴፍ ከሁሉም ቅድሚያውን ይይዛል። ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ላይ በስፋት ታሪካቸው ከተጻፈላቸው ቅዱሳን አንዱ ነው።

ስለዚህ ቅዱስ ዝርዝር መረጃን ለማግኘት ኦሪት ዘፍጥረትን ከምዕራፍ ፴፱ እስከ ፶ ድረስ ማንበብ ይኖርብናል። ከዚህ በተረፈም በዜና ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱሱ ብዙ ተብሏል።

መጽሐፍ ቅዱስ ሲጀምር ስለ ቅዱስ ሰው አዳም ይነግረናል። ቀጥሎም ስለ ቅዱሳኑ ሴት፣ ሄኖክ፣ ኖኅ፣ ሴም፣ አብርሃም፣ ይስሐቅና ያዕቆብ ነግሮን ቅዱስ ዮሴፍ ላይ ይደርሳል።

ቅዱስ ዮሴፍ ያዕቆብ (እስራኤል) ከሚወዳት ሚስቱ ራሔል ከወለዳቸው ሁለት የስስት ልጆቹ አንዱ ነው። ቅዱሱ ምንም እናቱ ብትሞትበትም በአባቱና በፈጣሪው ፊት ሞገስ ነበረው። ምክንያቱም ቅን፣ ታዛዥና የፍቅር ሰው ነበርና።

እንዲያ አምርረው ለሚጠሉት ወንድሞቹ እንኳን ክፋትን አያስብም ነበር። ይልቁኑ ለእነርሱ ምሳ (ስንቅ) ይዞ ሊፈልጋቸው በበርሃ ይንከራተት ነበር እንጂ።

መንገድ ላይ ቢርበው አለቀሰ እንጂ ስንቃቸውን አልበላባቸውም። የአባቶቹ አምላክ ግን ድንጋዩን ዳቦ አድርጐ መግቦታል። አሥሩ ወንድሞቹ ግን ስለ በጐነቱ ፈንታ ሊገድሉት ተማከሩ። ከፈጣሪው አግኝቶ በነገራቸው ሕልም "ሊነግሥብን ነው።" ብለው ቀንተውበታልና።

በፍጻሜው ግን በይሁዳ መካሪነት ለዐረብ ነጋድያን ሸጠውታል። በዚህም ለምሥጢረ ሥጋዌ (ለጌታ መሸጥና ሕማማት) ምሳሌ ለመሆን በቅቷል። ወንድሞቹ ለክፋት ቢሸጡትም ቅሉ ውስጡ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረበትና በባርነት በተሸጠበት በጲጥፋራ ቤት ፈጣሪው ሞገስ ሆነው።

ወጣትነቱን በፍቅረ እግዚአብሔር ሸብ አድርጐ አስሮ ነበርና የጲጥፋራ ሚስት የዝሙት ጥያቄ አላንበረከከውም። "ማንም አያየንም።" ስትለውም "እፎ እገብር ኃጢአተ በቅድመ እግዚአብሔር - ማንም ባያይስ እንዴት በፈጣሪዬ ፊት ኃጢአትን እሠራለሁ?" በማለት ከበደል አምልጧል። ስለዚህ ፈንታም የእሥር ቅጣት አግኝቶታል።

ጌታ ከእርሱ ጋር ቢሆን በእሥር ቤትም ሞገስን አገኘና አለቅነትን ተሾመ። "ኢኀደረ ዮሴፍ ዘእንበለ ሲመት" እንዲል መጽሐፍ። ከዚያም የንጉሡን (የፈርዖንን) ባለሟሎች ሕልም ተረጐመ። ቀጥሎም ንጉሡን በሕልም ትርጓሜ አስደመመ። ፈርዖንም ቅዱሱን በግዛቱ (ግብጽ) ላይ ሾመው።

ቅዱስ ዮሴፍ በምድረ ግብጽ ነግሦ ሕዝቡን ከረሃብ ታደገ። ለቅዱስ አባቱ ለእስራኤልና ክፉ ለዋሉበት ወንድሞቹም መጋቢ ሆናቸው። አስኔት (አሰኔት) የምትባል ሴት አግብቶም ኤፍሬምና ምናሴ የተባሉ ልጆችን አፍርቷል።

በመንገዱ ሁሉ እግዚአብሔርን አስደስቶ ከአባቱ ዘንድም ምርቃትና በረከትን ተቀብሎ በመቶ አሥር ዓመቱ በዚህች ቀን በመልካም ሽምግልና ዐርፏል። ወገኖቹም በክብርና በእንባ ቀብረውታል። "አጽሜን አፍልሱ።" ብሎ በተናገረው ትንቢት መሠረትም ልጆቹ (እነ ቅዱስ ሙሴ) ከግብጽ ባርነት ሲወጡ አጽሙን ወደ ከነዓን አፍልሠዋል።

<3 ቅዱስ ለውንትዮስ ሰማዕት <3

ቅዱሱ የተወለደው በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ ሲሆን ሃገሩ ጠራብሎስ ትባላለች። በወቅቱ በወታደርነት ነገሥታቱን ያገለግል ነበር። ድንግል ደም ግባት የሞላለት ወጣት ስለ ነበር በሰዎች ፊት ሞገስ ነበረው።

እርሱ ግን ምን ወታደር ቢሆን ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር። በተለይ ደግሞ የዳዊትን መዝሙር እየመላለሰ ይጸልየው ይወደው ነበር። ንግግሩ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት የታሸ ነውና ብዙ ጓደኞቹን ከክህደት ወደ ሃይማኖት ከክፋት ወደ ደግነት መልሷል።

የመከራ ዘመን በደረሰ ጊዜም በገሃድ ስመ ክርስቶስን ይሰብክ ነበር። ክፉ ሰዎች ከሰውት በመኮንኑ ፊት በቀረበ ጊዜም አልፈራም። ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው እየደበደቡት ደሙ እንደ ጐርፍ እየተቀዳ እርሱ ግን ይዘምር ነበር።

በመጨረሻም ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገቱን ተሰይፏል። ቅዱስ ለውንትዮስ እጅግ ተአምረኛ ሰማዕት ነውና በእምነት እንጥራው። ቤተ ክርስቲያንም ዛሬ የቅዱሱን ተአምራት ታስባለች። ቅዳሴ ቤቱም የተከበረው በዚህ ዕለት ነው።

አምላካችን ከቅዱሳኑ ጽናትን፣ ጸጋ በረከትን ይክፈለን።

ሰኔ ፩ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ (የያዕቆብ ልጅ)
፪.እናታችን አስኔት (የቅዱስ ዮሴፍ ሚስት)
፫.ቅዱስ ለውንትዮስ ክቡር ሰማዕት
፬.ቅዱስ ቢፋሞን ሰማዕት
፭.ቅዱስ ቆዝሞስ ሰማዕት

ወርኀዊ በዓላት
፩.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
፪.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት
፬.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
፭.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር

"እንዲህም አላቸው፦ "ወደ ግብጽ የሸጣችሁኝ እኔ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ። አሁንም ወደዚህ ስለ ሸጣችሁኝ አትዘኑ። አትቆርቆሩም። እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን ከእናንተ በፊት ሰዶኛልና።
.....እግዚአብሔርም በምድር ላይ ቅሬታን አስቀርላችሁ ዘንድ በታላቅ መድኃኒትም አድናችሁ ዘንድ ከእናንተ በፊት ላከኝ።" "
(ዘፍ ፵፭፥፬-፯)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቴሌግራም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለቅዱሳኑ አባ አፍፄ ወአባ ጉባ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 አባ አፍፄ ወአባ ጉባ <3

አባ አፍፄና አባ ጉባ ቁጥራቸው ከተስዓቱ (ዘጠኙ) ቅዱሳን ነው።

<3 አባ አፍፄ <3

ጻድቁ የተወለዱት እስያ ውስጥ በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው አቡሊዲስና አቅሌስያ ይባላሉ። ገና በሕፃንነታቸው ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቀው ወደ ግብጽ ወርደዋል። በዚያም በአባ መቃርስ እጅ መንኩሰዋል። አባ አፍፄ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በአልዐሜዳ ዘመን ከስምንቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ነው።

ጻድቁ ጠበል እያፈለቁ ብዙ ድውያንን ፈውሰዋል። ትግራይ ውስጥ የሐ የተባለው ቦታም ማረፊያቸው ነበር።

ስለ ጻድቁ በጥቂቱ እነዚህን እንጠቅሳለን።
፩.ከመቶ ዓመት በላይ አበ ምኔት ሆነው በኖሩበት ገዳማቸው በፍጹም ትጋት በጾምና በጸሎት አገልግለዋል።
፪.በመጀመሪያ ያስከተሏቸውን ሦስት መቶ ስልሳ ስድስት ደቀ መዛሙርት ጨምሮ ብዙ መናንያንን አፍርተው በሃገራችን ገዳማዊ ሕይወትን አስፋፍተዋል።
፫.ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሱርስትና ከጽርዕ ቋንቋ ወደ ግዕዝ ተርጉመዋል።
፬.በስብከተ ወንጌል ለሃገራችን ብርሃንን አብርተዋል። ሕዝቡ በጣዕመ ስብከታቸው ይገረም ስለ ነበር "አፍፄ (አፈ-ዐፄ)" ብሏቸዋል። "የዐፄ (የንጉሥ) አንደበት ያለው" ወይም "ንግግር አዋቂ" (Speaker) ማለት ነው።

ጻድቁ ከሁለት መቶ ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያንን አገልግለው በዚህች ቀን በ፮፻፹፬ ዓ.ም ተሠውረዋል። እግዚአብሔርም በስማቸው ለተማጸነ ገዳማቸውን ለተሳለመ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል።

<3 አባ ጉባ <3

ጻድቁ የተወለዱት ታኅሣሥ ፳፱ ቀን በ፫፻፴፮ ዓ.ም በመንፈቀ ሌሊት ነው። አባታቸው ጌርሎስ እናታቸው ቴዎዶክስያ ደጐች ነበሩ።

አባ ጉባ ("ባ" ጠብቆ ይነበብ።) በተወለዱ ቀን ጌታችን ከመላእክቱ ጋር በመውረዱ ቤታቸው ለሰባት ቀናት በብርሃን ተሞልቶ ነበር። ሕፃኑ ጉባም ፈጣሪያቸውን "ሃሌ ሉያ" ብለው አመስግነዋል።

በልጅነታቸው መጻሕፍትን አጥንተው ወደ ገዳመ አስቄጥስ ገብተው መንነዋል። ለበርካታ ዓመታት ከተጋደሉ በኋላ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል "ወደ ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ ሒድ።" ብሏቸው ከስምንቱ ቅዱሳን ጋር ወደ ሃገራችን መጥተዋል። በወቅቱ ዕድሜአቸው ከመቶ አርባ በላይ ነበር።

ጻድቁ አባ ጉባ እንደመሰሎቻቸው በስብከተ ወንጌል፣ መጻሕፍትን በመተርጐም፣ ገዳማትን በማስፋፋትና አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽ ቆይተዋል። በተለይ ራማ ኪዳነ ምሕረት የእርሳቸው ናት ይባላል።

ጻድቁ ቅዳሴ ሲቀድሱ ከመሬት ከፍ ብለው ነበር። ብዙ ጠበሎችን አፍልቀው ድውያንን ፈውሰዋል። ሙታንንም አንስተዋል። እመቤታችንም የብርሃን መስቀል ሰጥታቸዋለች። ጻድቁ ከበርካታ የቅድስና ዘመናት በኋላ በዚህች ቀን ዐርፈው በገዳማቸው ተቀብረዋል።

በዘመኑ ትኩረት ካጡ ታላላቅ ገዳማት አንዱ ይሔው ትግራይ ውስጥ የሚገኘው የአባ ጉባ ገዳም ነው።
በነገራችን ላይ "ጉባ" ማለት "አፈ-መዐር፣ ጥዑመ ልሳን" ማለት ነው።

ቸሩ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የጻድቃኑን በረከት ያድለን። በጸሎታቸውም በደላችንን ይቅር ይበለን።

ግንቦት ፳፱ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.አባ አፍፄ (ከዘጠኙ ቅዱሳን)
፪.አባ ጉባ (ከዘጠኙ ቅዱሳን)
፫.አባ ስምዖን ገዳማዊ (በሰባት ዓመታቸው መንነው ለሰማንያ አንድ ዓመታት በተጋድሎ የኖሩ ሶርያዊ)
፬.አባ ይስሐቅ ጻድቅ

ወርኀዊ በዓላት
፩.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
፪.ቅድስት አርሴማ ድንግል
፫.ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
፬.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
፭.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮጵያዊት
፮.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት)

"ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል። ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋበትም።"
(ማቴ ፲፥፵፩-፵፪)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቴሌግራም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

"ሰላም ለርደትከ አምሳለ ነፋስ ረቂቅ፤
ውስተ ጽርሕ አሐቲ ኀበ ሀለዉ ደቂቅ፤
ጰራቅሊጦስ ኃይል መንፈሰ ጸጋ ወጽድቅ፤
ይሰደድ እምላዕሌየ ጽልመተ ኃጢአት ጽፉቅ፤
ሶበ ያስተርኢ ስንከ መብረቅ።"
(አርኬ)

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለቅዱስ አልዓዛር ሐዋርያ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ቅዱስ አልዓዛር <3

ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእኅቶቹ ማርያና ማርታ ጋር ይኖር ነበር። ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከሰባ ሁለቱ አርድእት ማርያና ማርታን ደግሞ ከሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል።

በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደ ነበር ተገልጧል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም። ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደ ነበር ሲነግረን ነው እንጂ።

ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን ጌታችን በነ አልዓዛር ቤት በእንግድነት ይስተናገድ ነበር። በመጨረሻዋ ምሴተ ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው።

ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ ዐርፏል። ቅዱሳት እኅቶቹ ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል።
(ዮሐ. ፲፩፥፩)
ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከአራት ቀናት በኋላ ሊያስነሳው ይመጣል።

ለስም አጠራሩ ስግደት፣ ክብር፣ ጌትነት ይድረሰውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ። ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር ተቀበለችው። "አዳም ወዴት ነህ?" ያለ የአዳም ፈጣሪ "አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት?" አለ።
(ዘፍ. ፫፥፲፯)
ቸርነቱ ባሕርዩ ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ።

ከዚያም በባሕርይ ሥልጣኑ "አልዓዛር! አልዓዛር!" ብሎ አልዓዛርን አስነሳው። ይህች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ ግርምት ሆነች። ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጓት። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታስተምራለች።
(ዮሐ. ፲፩፥፩ - ፍጻሜው)

ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በኋላ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ (ቁጥሩ ከሰባ ሁለቱ አርድእት ነውና።) ለአርባ ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ በ፸፬ ዓ.ም አካባቢ ቆጵሮስ ውስጥ ዐርፏል።

የጌታችን ቸርነቱ የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን።

ግንቦት ፳፯ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ አልዓዛር ጻድቅ ሐዋርያ
፪.ቅዱሳት ደናግል ማርያ ወማርታ
፫.አባ ዮሐንስ ሊቀ ጳጳሳት

ወርኀዊ በዓላት
፩.የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
፪.አቡነ መብዐ ጽዮን ጻድቅ
፫.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
፬.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
፭.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
፮.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
፯.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት

"ጌታ ኢየሱስም "ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን?" አላት።
ይህንም ብሎ በታላቅ ድምጽ "አልዓዛር ሆይ! ወደ ውጭ ና።" ብሎ ጮኸ። የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ። ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ። ጌታ ኢየሱስም "ፍቱትና ይሂድ ተውት።" አላቸው።"
(ዮሐ ፲፩፥፵-፵፬)

በቴሌግራም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለእናታችን ቅድስት ሰሎሜ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል እና ለበዓለ ቅዱስ ሜሮን በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ቅድስት ሰሎሜ <3

የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ከመረጣቸው ሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት የቅድስት ሰሎሜን ያህል ያገለገለ ክብርም የተቀበለ የለም። ከእመቤታችን ቀጥሎ ከጽንሰቱ እስከ ዕርገቱ ያልተለየች ብቸኛዋ ሰው ናትና።
ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦
ቅድስት ሰሎሜ ከነገደ አሮን በሚመዘዝ የዘር ሐረግ እናቷ ማርያም ትባል ነበር። አባቷ ደግሞ ክቡር አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ነው። ቅድስት ሰሎሜና እመቤታችን የእኅትማማች ልጆች ናቸው።

ቅድስት ኤልሳቤጥም ዝምድናዋ ተመሳሳይ ነው። ሦስቱ እናቶች (ሐና፣ ማርያምና ሶፍያ) የማጣትና የሔርሜላ ልጆች በመሆናቸው እኅታማቾች ናቸው።

ጥቂት ነገሮች ስለ እናታችን ቅድስት ሰሎሜ
፩.የአረጋዊ ዮሴፍ ልጆችን (ወንድሞቿን) እንደሚገባ አሳድጋለች።
፪.ጌታችን በተወለደ ጊዜ በቤተ ልሔም ነበረች። የእመቤታችን መውለድ እንደ ሌሎች ሴቶች መስሏት ድንግልን ስለ ነካች እጆቿ ተቃጥለዋል። ምሕረት ጠይቃ ጌታን ስትዳስሰው ግን ተፈወሰች።
፫.እመ ብርሃን ስደት ስትወጣ ቅድስት ሰሎሜ "ባንቺ የደረሰ በእኔም ይድረስ።" ብላት አብራ ተሰዳለች። ረሃቧን ተርባለች። ጥሟን ተጠምታለች። በሐዘኗ አዝናለች። አብራት አልቅሳለች። ለሦስት ዓመት ከስድስት ወራት ያን ሁሉ ጭንቅ አብራ ተካፍላለች።

ድንግል እመቤታችን እሾህ ሲወጋት ታወጣላት እንቅፋት ሲመታት ደሟን ትጠርግላት ነበር። ባለቤቱ አድሏታልና ጌታችንን አንዴ በጎኗ ታቅፈው አንዴም በጀርባዋ ታዝለው አንዳንዴም ትስመው ነበር።

መለኮትን ማቀፍ፣ ማዘልና መሳም ምን ይደንቅ! ለቅድስት እናታችን አንክሮና ምስጋና በጸጋ ይገባል!

ከስደት ከተመለሱ በኋላም ለሃያ አምስት ዓመታት ከጌታና ከድንግል ማርያም ጋር ኑራለች፤ አገልግላቸዋለችም።

ጌታችን ተጠምቆ ማስተማር ሲጀምርም ተከተለችው። እርሱም ከሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት ደምሯታል። ለሦስት ዓመት ከስድስት ወራት ከዋለበት ውላ ካደረበት አድራ ተምራለች። እንደሚገባም አገልግላለች።

አምላክ ሲሰቃይ ከጐኑ ሲሰቀልም ከእግረ መስቀሉ ነበረች። ብርሃነ ትንሣኤውም ከተገለጠላቸው ቅዱሳት አንስት አንዷ ናት። ከመድኃኔ ዓለም ዕርገት በኋላ መንፈስ ቅዱስን ተቀብላ በሐዋርያት ዘመን የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን አገልግላለች።

እድሜዋ ምን ቢገፋ ለወንጌልና ለማዕድ ተግባር ተግታለች። ወገኖቿ አይሁድ ብዙ አሰቃይተዋት በዚህች ዕለት በመልካም ዕረፍት ወደ ፈጣሪዋ ሔዳለች።

<3 ቅብዐ ሜሮን <3

ዳግመኛ በዚህች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ የምንከብርበትን ቅብዐ ሜሮን አፍልቆልናል።

በስደቱ ጊዜ ጌታችን በምድረ ግብጽ ደክሟቸው ካረፉበት ቦታ ላይ የዮሴፍ በትርን ቆራርጦ በኪነ ጥበቡ ውኃ አፍልቆ አጠጥቶ ትልልቅ ዛፎች አደረጋቸው። እዚያውም ላይ ቅብዐ ሜሮንን አፈለቀ። ቅብዐ በለሶንም ይሏቸዋል።

"እምበትረ ዮሴፍ አሜሃ ከመ ታርኢ ስልጣነ።
ገቢረከ በበስባር ኀበ ተከልከ መካነ።
ማኅተመ ቅድሳት ይኩን አውሐዝከ ሜሮነ።" እንዲል።
(አርኬ)

በኋላም የጌታችን ወዙ በታጠበ ጊዜ ተቀላቅሎበታል። ዛሬ እኛም ንዋየ ቅድሳትም የምንከብረው በዚሁ ቅዱስ ቅብዐት ነው።

አምላካችን እግዚአብሔር በቅድስት ሰሎሜ ላይ ያሳደረውን ጸጋ በእኛም ላይ ያሳድርልን።

ግንቦት ፳፭ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.እናታችን ቅድስት ሰሎሜ (ከሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት)
፪.ታላቁ አባ ሔሮዳ ሰማዕት
፫.ሠላሳ ሺህ ሰማዕታት (የአባ ሔሮዳ ማኅበር)
፬.ቅዱስ አብቁልታ ሰማዕት

ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
፪.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
፫.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
፬.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
፭.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
፮.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ

"ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም፣ የያዕቆብም እናት ማርያም፣ ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቱ ገዙ። ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን እጅግ በማለዳ ፀሐይ ከወጣ በኋላ ወደ መቃብር መጡ።
.....ወደ መቃብርም ገብተው ነጭ ልብስ የተጐናጸፈ ጐልማሳ በቀኝ በኩል አዩና ደነገጡ። እርሱ ግን አትደንግጡ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነስቷል። በዚህ የለም.....አላቸው።"
(ማር ፲፮፥፩-፯)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቴሌግራም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

"ከወርቅና ከብር ይልቅ ሞገሱ የሚበልጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረሱ እኛን ለመርዳት ይምጣ፤ ይመላለስም።"
(ስብሐተ ፍቁር ዘጊዮርጊስ)

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስ እና ለብፁዕ ቅዱስ ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ቅዱስ እንድራኒቆስ <3

ቅዱስ ወብፁዕ እንድራኒቆስ ሐዋርያ ነገዱ ከቤተ እስራኤል ሲሆን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ነው። ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ መቶ ሃያ ቤተሰቦቹን ሲመርጥ እርሱን ከአርድእት ጋር ደምሮ አስተምሮታል።

ሰብዐው አርድእት በጌታችን ተልከው አጋንንት ሲገዙላቸው ከእነርሱ አንዱ ቅዱስ እንድራኒቆስ ነበር። ይህ የተፈጸመ ገና መድኃኔ ዓለም ከመሰቀሉ በፊት ነው።
(ሉቃ. ፲፥፩-፳)

ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከሐዋርያት ጋር ለአሥር ቀናት በሱባኤ ሰንብቶ የመንፈስ ቅዱስን ሃብት ተቀብሏል። እንደ ባልንጀሮቹም ወደ ዓለም ወጥቶ የወንጌል የምሥራችን ሰብኳል። በተለይ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ለበርካታ ዓመታት አምላኩን አገልግሏል። ቅዱስ ጳውሎስም በቆረንቶስ እያለ ቅዱስ እንድራኒቆስ በሮም ያስተምር ነበር። ለዚያም ነው በሮሜ መልእክቱ ፲፮፥፯ ላይ "እንድራኒቆስን ሰላም በሉ።" ያለው።

ቅዱስ ጳውሎስ በሰማዕትነት ካረፈ በኋላ ከቅዱስ ዮልዮስ ጋር ሆነው የአህዛብን ልቡና በወንጌል አብርተዋል። እጅግ ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል። ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ትዕግስት ድል ነሥተዋል። በዚህም በርካታ የጣኦት ቤቶችን አፍርሰው አብያተ ክርስታያናትን አንጸዋል።
በአሕዛብም ፊት ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አሳይተዋል።

ቅዱስ እንድራኒቆስ ብዙ መከራን ቢቀበልም አንገቱን ይቆረጥ ዘንድ የጌታ ፈቃዱ አልነበረምና ጥቂት ታሞ በዚህች ቀን ዐርፏል። ባልንጀራው (ሐዋርያው) ቅዱስ ዮልዮስ በክብር ገንዞ ቀብሮታል።

<3 ቅዱስ ያዕቆብ <3

ዳግመኛ በዚህች ቀን ጻድቅና ተአማኒ (ታማኝ) የተባለ የምሥራቅ ሰው ቅዱስ ያዕቆብ መታሠቢያ ይደረግለታል።

ቅዱስ ያዕቆብ ቁስጥንጥንያ አካባቢ በርሃ ውስጥ ይኖር የነበረ አባት ነው። ከቅድስና ሕይወቱ ባሻገር በደፋርነቱ (ጥብዐቱ) ይታወቃል። በ፫፻፵ዎቹ ዓ.ም ታናሹ ቆስጠንጢኖስ አርዮሳዊ በሆነ ጊዜ ይሔ አባት በይፋ ገስጾታል። በዚህም ምክንያት መከራን ተቀብሏል፤ ታስሯል፤ ተገርፏል። እግዚአብሔርም መናፍቁን ንጉሥ ለጦርነት በወጣበት ቀስፎታል።

የአባቶቻችን አምላክ ልዑለ ባሕርይ ክርስቶስ ጸጋ ክብራቸውን ያድለን።

ግንቦት ፳፪ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ እንድራኒቆስ ሐዋርያ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት)
፪.ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ (ለክርስቶስ የታመነ)

ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
፪.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
፫.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
፬.አባ እንጦንዮስ (አበ መነኮሳት)
፭.አባ ጳውሊ የዋህ

"ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ ደግሞም ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ አብረውኝም ለታሰሩ ለዘመዶቼ ለአንድራኒቆንና ለዮልያን (እንድራኒቆስና ዮልዮስ) ሰላምታ አቅርቡልኝ።"
(ሮሜ ፲፮፥፮-፯)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቴሌግራም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል (ደብረ ምጥማቅ) በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ደብረ ምጥማቅ <3

የአርያም ንግሥት የሰማይና የምድር እመቤት የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህች ዕለት በምድረ ግብጽ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች።
ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦
ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብጽና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ፣ ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ ዐርፎ ነበር። ቦታውን ባርኮ ለዘላለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር።

ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ። እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት ፳፩ ቀን አእላፍ መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች።

በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም አሕዛብም ተሰብስበው ለአምስት ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ። እንግዲህ ልብ በሉት እንኳን የአርያም ንግሥት የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚህ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል።

እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው። ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው።

የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘላለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው። ፈልገው የሚያጡት ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም። ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግል፣ መነኮሳት፣ መላእክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና።
እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር።
እነዚያ እርሷን ያዩ ዓይኖች፣ በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል። አምስቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል። እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች።

<3 አባ መርትያኖስ <3

አባ መርትያኖስ በበርሃ ከስልሳ ስምንት ዓመታት በላይ በቅድስና የኖሩ አባት ናቸው። ሰይጣን እርሳቸውን ፊት ለፊት ተዋግቶ መጣል ቢያቅተው በዝሙት በተለከፉ ሴቶች ያስቸግራቸው ነበር።

አንድ ቀን አንዷ ሽቶ አርከፍክፋ በዝሙት ልትጥላቸው ብትል እግራቸውን እሳት ውስጥ ጨምረው እግራቸው እየተቃጠለ በሚወጣው ጠረን አጋንንትን አርቀዋል። እርሷንም በንስሃ መልሰው ለቅድስና አብቅተዋታል። ጻድቁ ከፈተና ለመራቅ በመቶ ስምንት ሃገራት መቶ ስምንት በዓቶች የነበሯቸው ብቸኛ አባት ናቸው።

ለአባት እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን። ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን፣ ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን ይደርብን።

ግንቦት ፳፩ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅድስት ደብረ ምጥማቅ (የእመቤታችን መገለጥ)
፪.አባ መርትያኖስ ጻድቅ (በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን በእሳት ያቃጠሉ አባት)
፫.ቅዱስ አሮን ሶርያዊ
፬.ቅዱስ አሞጽ ነቢይ

ወርኀዊ በዓላት
፩.አበው ጎርጎርዮሳት
፪.አቡነ ምዕመነ ድንግል
፫.አቡነ አምደ ሥላሴ

"የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ። ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው።
ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው።
በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ።.....
በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ።
በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ።
ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ።"
(መዝ ፵፬፥፲፪-፲፯)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለታላቁ ጻድቅና ገዳማዊ አባ ዓቢየ እግዚእ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 አባ ዓቢየ እግዚእ <3

አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በአሥራ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ነው። የተባረኩ ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ። አጥምቀው "ዓቢየ እግዚእ" ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ጳጳስ ሰላማ መተርጉመ መጻሕፍት ናቸው። ትርጉሙም "በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው" ማለት ነው።

ዓቢየ እግዚእ በሕፃንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ። ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደብረ በንኮል ሔደው መንኩሰዋል።

በገዳሙ በጾም፣ በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን አግኝተዋል። በጊዜው በአርባ ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ ይበሉ ነበር።

ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን አፍርተዋል። ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ አባትም ነበሩ። ከትግራይ እስከ ደንቢያ ደግሞ ሃገረ ስብከታቸው ነው።

አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ። ቀኑ ነሐሴ አሥር ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለሦስት ቀናት ባለመጉደሉ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ። ጻድቁ በአካባቢው የነበሩት ኢ አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ።

ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ። ይህን ድንቅ ያዩ ከዘጠኝ መቶ አርባ አንድ በላይ አሕዛብ አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል። ይህም ዘወትር ነሐሴ አሥር ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር) ይከበራል።

ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ። ያኔ ጐንደር በቀሃና አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች። ጻድቁ ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር።

በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ፣ እባብና መሠል አራዊት ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት። ይህንን የተመለከቱት አባ ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ። በፍጹም ልባቸውም ስለ ሕዝቡ ለመኑ።

የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ "በስምህ የተማጸኑ፣ በቃል ኪዳንህ ያመኑ፣ በምድር አራዊት አይሠለጥኑባቸውም። በሰማይም እሳትን አያዩም። ጎንደርንም አራዊት ገብተው ሰውን አይጐዱም።" ብሏቸው አርጓል።

ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል። ይሔው እኛ ምን ብንከፋ ጻድቁንም ብንረሳቸው እግዚአብሔር ግን ዛሬም በጻድቁ ምልጃ ከተማዋን ጠብቆ ይኖራል። ነገን ደግሞ እርሱ ያውቃል። ዛሬ ቤተ ክርስቲያኑ የታነጸበት ቦታ (ጎንደር ቀበሌ ዘጠኝ ኪዳነ ምሕረት) ጻድቁ የጸለዩበት ቦታ ነው። እንኳን በወርኀዊ በዓላቸው (በአሥራ ዘጠኝ) ይቅርና በዓመታዊ በዓላቸው (ግንቦት አሥራ ዘጠኝ) ለንግሥ የሚመጣው ሰው ቁጥር ያስተዛዝባል።

አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑረው፣ ሦስት ሙታንን አስነስተው፣ ብዙ ድውያንን ፈውሰው፣ ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው፣ የድኅነት ቃል ኪዳንም ተቀብለው በመቶ አርባ ዓመታቸው ግንቦት አሥራ ዘጠኝ ቀን ዐርፈዋል። የጻድቁ ክብር ለሁሉ ነውና እባካችሁ እናስባቸው።

አምላካችን በወዳጆቹ ምልጃ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይሠውርልን።

ግንቦት ፲፱ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ኢትዮጵያዊ)
፪.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም (የአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መቃብር ከጌታ የተገለጠላቸው ኢትዮጵያዊ)
፫.አቡነ ብስጣውሮስ ዘሐይቅ እስጢፋኖስ (ኢትዮጵያዊ)
፬.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ታላቁ (ሰባት ጊዜ ሙቶ የተነሳ)
፭.ስምንት መቶ አምስት ሺህ ሰባት ሰማዕታት (በአንድ ቀን ብቻ የተገደሉ)
፮.አባ ይስሐቅ ገዳማዊ

ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
፪.አቡነ ስነ ኢየሱስ

"በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ። አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
በእኔ ተማምኗልና አስጥለዋለሁ። ስሜንም አውቋልና እጋርደዋለሁ።
ይጠራኛል እመልስለትማለሁ። በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ። አከብረውማለሁ።
ረጅም እድሜን አጠግበዋለሁ። ማዳኔንም አሳየዋለሁ።"
(መዝ ፺፥፲፫-፲፮)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቴሌግራም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

"ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና።"
(ቅዱስ ያሬድ)
እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ በሰላም አደረሳችሁ!

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሊቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ቅዱስ ኤጲፋንዮስ <3

ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ጽድቅ ከቅድስና፣ ድርሰት ከጥብቅና የተሳካለት አባት ነው። "ኤጲፋንያ" ማለት የመለኮት መገለጥ ሲሆን "ኤጲፋንዮስ" ማለት ደግሞ ምሥጢረ መለኮት የተገለጠለት ማለት ነው።

ቅዱስ ኤጲፋንዮስ የተወለደው ክርስቶስን ከሚጠሉ አይሁዳውያን ቤተሰቦች ቤተ ገብርኤል ውስጥ ነው። ቤተሰቦቹ ከአንድ አህያ በቀር ምንም የሌላቸው ድሆች ነበሩ። በዚያ ላይ በልጅነቱ አባቱ በመሞቱ ከእናቱና ከአንዲት እኅቱ ጋር በረሃብ ሊያልቁ ሆነ። ሕፃኑ ኤጲፋንዮስ በአህያው እንዳይሠራ አህያው ክፉ ነበርና ሊሸጠው ገበያ አወጣው።

ፊላታዎስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ለግዢ ሲደራደሩ አህያው የኤጲፋንዮስን ኩላሊቱን ረግጦት ለሞት አደረሰው። በዚህ ጊዜ አብሮት ያለው ክርስቲያኑ በትእምርተ መስቀል አማትቦ አዳነው። በፈንታው ግን አህያው ሞተ። ሕፃኑ ኤጲፋንዮስ እያደነቀ ሔደ።

ከቆይታ በኋላ ሀብታም አጎቱ ገንዘቡን አውርሶት በመሞቱ ገና በአሥራ ስድስት ዓመቱ ባለጠጋ ሆነ። ያቺ ገበያ ላይ ያያት ተአምር ግን በልቡ ውስጥ ትመላለስ ነበር።

አንድ ቀን ደግሞ ሉክያኖስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ሲሔዱ ነዳይ አገኙ። ባለጠጋው ኤጲፋንዮስ አለፈው። ያ ድሃ ክርስቲያን ግን የለበሳትን አውልቆ መጸወተው። በዚህ ጊዜ መልአኩ መጥቶ የብርሃን ልብስ ሲያለብሰው ኤጲፋንዮስ ተመለከተ።

ኤጲፋንዮስ ጊዜ አላጠፋም። ከእኅቱ ጋር በክርስቶስ አምኖ ተጠመቀ። ሃብት ንበረቱን ግማሹን መጸወተ። በተረፈው ደግሞ መጻሕፍትን ገዝቶ ወደ አባ ኢላርዮን ገዳም ገባ። በዚያም መናንያኑ እስኪያደንቁት ድረስ በፍጹም ትጋትና ቅድስና ተጋደለ።

በጸሎቱ ዝናም አዘነመ፣ ድውያንን ፈወሰ፣ ብዙ ተአምራትንም አደረገ።

እግዚአብሔር ደግሞ ለሌላ አገልግሎት ሽቶታልና በቆጵሮስ ደሴት ላይ ጳጳስ ሆኖ ተሾመ። ብሉይ ከሐዲስ የወሰነ ሊቅ ነውና ብዙ መጻሕፍትን ተረጎመ። በሺህ የሚቆጠሩ ድርሳናትን ደረሰ። በአፍም በመጽሐፍም ብሎ መናፍቃንንና አይሁድን ምላሽ በማሳጣቱ ቤተ ክርስቲያን "ጠበቃዬ" ትለዋለች።

ከደረሳቸው መጻሕፍት መካከል "ሃይማኖተ አበው ዘኤጲፋንዮስ፣ መጽሐፈ ቅዳሴውና አክሲማሮስ (ሥነ ፍጥረት)" ዛሬም በቅርብ ይገኛሉ። ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በመልካም እረኝነትና በሚደነቅ ቅድስና ተመላልሶ በአራት መቶ ስድስት ዓ.ም ዐርፏል። እድሜውም ዘጠና ስድስት ዓመት ያህል ነበር።

አምላካችን ከቅዱሱ ሊቅ በረከት ያድለን።

ግንቦት ፲፯ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆጵሮስ)
፪.ቅዱስ ኢላርዮን ገዳማዊ
፫.አባ ሉክያኖስ ጻድቅ
፬.ቅዱስ ፊላታዎስ ክርስቲያናዊ

ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
፪.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
፫.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
፬.አባ ገሪማ ዘመደራ
፭.አባ ጰላሞን ፈላሢ
፮.አባ ለትጹን የዋህ

"የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል። እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው። እኛ ግን የማይጠፋውን። ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም። ነፋስን እንደሚጐስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም። ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጐሰምሁ አስገዛዋለሁ።"
(፩ቆሮ ፱፥፳፭-፳፯)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቴሌግራምም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ ሐዋርያ ወልደ ነጐድጓድ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ <3

አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግሥተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ነው። ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ በገሊላ አካባቢ አድጐ ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል።
(ዮሐ. ፩፥፴፱)

ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር። ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕፃን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው። ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል።
(ዮሐ. ፲፱፥፳፭)

ከእርሷ ጋር ለአሥራ አምስት ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ። ስንኳን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላእክትም ማዕረጉ ከፍ አለ። ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል። ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል። ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው።

ቅዱስ ዮሐንስ በታናሽ እስያ ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መስበኩ ይታሰባል። ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ለሰባ ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው። ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል።

ሦስት መልእክታት፣ ራእዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል። ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል። ከእሳት እስከ ስለት እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል። እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጓቸዋል።

<3 ቅዱሱ በኤፌሶን <3
ይህች ኤፌሶን የሚሏት ሃገር መገኛዋ በቀድሞው ታናሽ እስያ (አሁን ቱርክ አካባቢ) ሲሆን ብዙ ሐዋርያት አስተምረውባታል። ያም ሆኖ የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ያመጣች አልነበረችምና ቅዱስ ዮሐንስ ሊሔድ ተነሳ።

ከደቀ መዛሙርቱ መካከልም ቅዱስ አብሮኮሮስን (ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ነው።) አስከትሎ እየጸለዩ በመርከብ ላይ ተሳፈሩ። ሐዋርያት አበው መከረኞች ናቸውና ማዕበል ተነሳባቸው። በጥቂት አፍታም መርከባቸው በማዕበሉ ተበታተነች።

ቅዱስ አብሮኮሮስ በስባሪ ላይ ተሳፍሮ ወደ አንዲት ደሴት ደረሰ። ግን ከንጹሑ መምህሩ ቅዱስ ዮሐንስ ተለይቷልና አለቀሰ። ፍቁረ እግዚእ ግን ያለ ምግብና ውኃ ማዕበለ ባሕር እያማታው ለአርባ ቀናት ቆየ።

እርሱ በፈጣሪው ፍቅር የተመሰጠ ነበርና አለመመገቡ አልጐዳውም። በአርባኛው ቀን ግን ደቀ መዝሙሩ ወዳለበት ደሴት ማዕበሉ አደረሰው። ሁለቱ ቅዱሳን ተፈላልገው ተገናኙ። እጅግም ደስ ብሏቸው ፈጣሪን አመሰገኑ።

አምላካቸው ወደዚህች ደሴት ያመጣቸው በጥበቡ ነውና ሲዘዋወሩ ሁለት ነገርን አስተዋሉ።
፩ኛ.የደሴቷ ሁሉም ነዋሪ የሚያመልኩት ጣዖትን ነው።
፪ኛ.አብዛኞቹ ልዑላን (የቤተ መንግሥት ውላጆች) ናቸው። ሮምና የሚሏት አንዲት ሴት ደግሞ እነዚህን ሁሉ እየመገበች ታስተዳድራለች።

ቅዱሳኑ በቦታው በቀጥታ ትምህርተ ወንጌልን ቢናገሩ እንደ ማይቀበሏቸው ስለ ተረዱ ሌላ ፈሊጥን አሰቡ። እንዳሰቡትም ወደ እመቤት ሮምና ቤት ሒደው በባርነት ተቀጠሩ።

ለእርሷም "ድሮ የአባትሽ ባሮች የነበርን ሰዎች ነን።" ስላሏት ሁለቱን ቅዱሳን እሳት አንዳጅና ገንዳ አጣቢ አደረገቻቸው። ለሰማይ ለምድሩ የከበዱ እነዚህ ቅዱሳን የካዱትን ይመልሱ ዘንድ በባርነት ግፍን ተቀበሉ። የመከር (የማሳመኛ) ጊዜ ሲደርስም አንዳች አጋጣሚ ተፈጠረ።

ቅዱሳኑ ዮሐንስና አብሮኮሮስ ወደ መታጠቢያ ቤቱ ሲገቡ ሰይጣን በውስጥ ኖሮ ደንግጧልና እወጣለሁ ብሎ ሲሮጥ የንጉሡን ልጅ ረግጦ ገደለው። ሮምናና የአካባቢው ሰዎች ከበው ሲላቀሱ ቅዱሳኑ ቀረቡ።

ሮምና ግን በቁጣ "ልትሣለቁ ነው የመጣችሁ?" በሚል ቅዱስ ዮሐንስን በጥፊ መታችው። መላእክት እንኳ ቀና ብለው ሊያዩት የሚከብዳቸው ሐዋርያ ይህንን ታገሰ። በጥፊ ወደ መታችው ሴት ቀረብ ብሎም "አትዘኝ! ልጁ ይነሳል።" አላትና ጸለየ።

ወደ ሞተውም ቀረብ ብሎ በጌታችን ስም አስነሳው። በዚህ ጊዜም ሮምናን ጨምሮ በሥፍራው የነበሩ ሰዎች ለቅዱስ ዮሐንስ ሰገዱ። እርሱ ግን ሁሉንም አስነስቶ ትምሕርተ ሃይማኖትን፣ ፍቅረ ክርስቶስን ሰበከላቸው።

በስመ ሥላሴ አጥምቆ ካህናትን ሹሞ ቤተ ክርስቲያንም አንጾላቸው ወጥቷል። በኋላም ለሮምናና ለደሴቷ ሰዎች ክታብ (መልእክትን) ጽፎላቸዋል። ይህች መልእክት ዛሬ ሁለተኛዋ የዮሐንስ መልእክት ተብላ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ትታወቃለች።

ቅዱስ ዮሐንስ ቀጥሎ የተጓዘው ወደ ኤፌሶን ነው። በዚህች ከተማ የምትመለክ አርጤምስ (አርጢሞስ) የሚሏት ጣዖት ነበረች። አርጤምስ ማለት መልክ የነበራት ትዕቢተኛ ሴት ስትሆን አስማተኛ ባሏ ነው እንድትመለክ ያደረጋት።

ቅዱስ ጳውሎስ ብዙ ምዕመናን ከእርሷ እንዲርቁ ማድረግ ችሏል። ጨርሶ ያጠፋት ግን ቅዱስ ዮሐንስ ነው። በቦታውም ብዙ ግፍ ደርሶበት በርካታ ተአምራትን አድርጓል። ቤተ ጣዖቱንም በተአምራት አፍርሶታል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን የመነኮሳት አባት ለተባለው ቅዱስ ጳኩሚስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ቅዱስ ጳኩሚስ (አባ ባኹም) <3

ዛሬን አያድርገውና ምንኩስና ማለት መላእክትን መስሎ የሚኖርበት ሕይወት ነበር። ምንኩስና በእግዚአብሔር ፈቃድ በአባ እንጦንስ ቢመሠረትም ሕይወቱን በማስፋፋት ደረጃ የቅዱስ ጳኩሚስን ያሕል የደከመና የተሳካለት ግን የለም።

ቅዱሱ በትውልዱ ግብጻዊ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን ከቀደመ ሕይወቱ ጋር በተያያዘ የሚተረክ ነገር በመጽሐፈ ገድሉ ላይ አለ። ጳኩሚስ ወደ ምንኩስናው ዓለም የመጣ በታላቁ አባ ጰላሞን አማካኝነት ነው። ለተወሰነ ጊዜም መንፈሳዊ አባቱን እየረዳ ሕይወተ መነኮሳትን አጥንቷል።

በመንፈሳዊ ሕይወቱና በተጋድሎ እየበረታና እየደረጀ ሲሔድ ከአባ ጰላሞን ተለይቶ ማኅበር መስርቶ ለመኖር አምላኩን ጠይቆ ፈቃድ በማግኘቱ በሕግ የሚመራ የመጀመሪያውን ገዳም መሥርቷል።

ቅዱስ ጳኩሚስ ጸሎቱ አጋንንትን ከአካባቢው አያስቀርባቸውም ነበር። አካሉ አልቆ በአጥንቶቹ እስኪቆም ድረስ ጾሟል። ዓርብ ዓርብ የጌታችንን ሕማማት እያሰበ ከእንባ ጋር ይሰግዳል። እንባውና ላበቱ ከፊቱ እየወረደ አካባቢው ጭቃ ይሆን ነበር። ጌታችንም መስቀል ተሸክሞ ይታየው ነበር።

ስለ ክብሩም መላእክት ወደ ሰማይ ወስደው ገነትና ሲዖልን አሳይተውታል። አባታችን ቅዱስ ጳኩሚስ ከርኅራኄው የተነሳ አጋንንት ያደሩባቸውን ሰዎች ሲያገኝ በቀጥታ ከመፈወስ ይልቅ ደዌውን ርኩሳን መናፍስቱንም ወደ እርሱ እንዲገለበጡ ያዝዛቸው ነበር።

ከዚያም በጾም፣ በጸሎትና በስግደት ያማስናቸዋል። ያኔ በግዳቸው እየጮሁ ሲወጡ ደጉ አባት "ምነው ትንሽ ቆዩ እንጂ።" ይላቸዋል።

አጋንንቱም እያደነቁ "ከገነት ካስወጣነው ከአዳም በቀር እንዲህ ዓይነት ፍጡርስ ዓይተን አናውቅም።" ብለው እንደ ጢስ በነዋል። አጋንንት ስለሚፈሩት "አርበኛው መነኩሴ" ይሉታል።

የቅዱስ ጳኩሚስ ፍሬዎች
፩.በግብጽ በርካታ ገዳማትን አቋቁሟል።
፪.ለሁሉም ገዳማት አበ ምኔቶችን ሹሞ እየዞረ ይጠብቃቸው ነበር።
፫.የመጀመሪያውን ሥርዓተ መነኮሳት አዘጋጅቷል።
፬.መነኮሳት ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ሹመት እንዳይሾሙ ከልክሏል።
፭.መነኮሳት ከገዳማቸው በፍፁም እንዳይወጡ ከልክሏል።
፮.ከግብጽ ውጪ ምንኩስናን ያስፋፉ አባቶችን አስተምሮ አመንኩሷል። (ለምሳሌ በኢትዮጵያ ምንኩስናን ያስፋፉት አቡነ አረጋዊ የዚህ አባት ደቀ መዝሙር ናቸው።)

ከዚህም ባለፈ በርካታ ሥራዎችን ሠርቷል። ቅዱስ ጳኩሚስ ጫማ ሳይጫማ እሾህን ሳይሰቀቅ ይረግጥም ነበር። የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እጥፍ ሆኖ የበዛለት ቅዱሱ መነኮስ ወደ ወደደው እግዚአብሔር በዚህች ቀን ሔዷል።

የጻድቁ መነኮስ ጸጋና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።

ግንቦት ፲፬ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ አባ ጳኩሚስ (አበ መነኮሳት ሣልሳዊ)
፪.አባ ሲማኮስ ሰማዕት

ወርኀዊ በዓላት
፩.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
፪.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
፫.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
፬.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)
፭.አባ ስምዖን ገዳማዊ
፮.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
፯.እናታችን ቅድስት ነሣሒት

"ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም። በእናት ማኅጸን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ። ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ። ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ። ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው።"
(ማቴ ፲፱፥፲፩-፲፪)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቴሌግራምም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለታላቋ ሰማዕት ቅድስት ሶፍያ እና ለቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ቅድስት ሶፍያ ተጋዳሊት <3

ሶፍያ ("ያ" የሚለው ላልቶ ይነበብ።) በቀደመው ዘመን በነበሩ ክርስቲያኖች ዘንድ ተወዳጅ ስም ነበር። ዛሬ ብዙ አሕዛብ ሲጠሩበት ብንሰማም ትርጉሙ "ጥበበ ክርስቶስ" የሚል ነው። በዚህ ስም የሚጠሩ አያሌ ቅዱሳት አንስት ሲኖሩ አንዷ ዛሬ ትከበራለች።

ቅድስቷ የተወለደችው በምሥራቅ ሮም ግዛት ውስጥ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው። ዘመኑ የጭንቅ የመከራ በመሆኑ ሕዝቡ በስደት ይኖር ነበር።

የቅድስት ሶፍያ ወላጆች ክርስቲያኖች ናቸውና በመልካሙ መንገድ በንጽሕና አሳድገዋታል። ባለጠጐች በመሆናቸው አገልጋይ ቀጥረውላት ያማረ ቤት ሠርተውላት በዚያ ትኖር ነበር። ሁሉ ያላት ብትሆንም ሁሉን ንቃ በጾምና በጸሎት ትኖር ነበር።

ለዐቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ ወላጆቿ ለከተማው መኮንን (ገዢ) ሊድሯት መሆኑን አወቀች። ወደ ቤቷ ገብታ መቶ ጊዜ ሰገደች። ወደ ፈጣሪዋም ጸለየች፦ "ጌታዬ ሆይ! የዚህን ዓለም ቀንበር አታሸክመኝ አልችለውምና። ያንተው ቀንበር ግን የፍቅር ነውና እችለዋለሁ።" አለች።

አገልጋዩዋን ጠርታ ብዙ ወይን አጠጥታት ልብስ ተቀያየሩ። በሌሊትም ወጥታ ወደ በርሃ ሔደች። ዓላማዋ ምናኔ ቢሆንም የእግዚአብሔር ፈቃዱ ግን ሌላ ነበር። በመንገድ ብዙ ክርስቲያኖች በመከራ ብዛት ሲሰደዱ አገኘቻቸው። እርሷ ስደትን አልመረጠችም።

እያጠያየቀች "ሰው በላ" ከተባለው አረመኔ ንጉሥ ዲዮቅልጢያኖስ ደረሰች። በንጉሡ ፊት ቀርባ "እኔ ክርስቲያን ነኝ።" አለችው። ንጉሡ ከመልኳ ማማርና ከድፍረቷ የተነሳ አደነቀ።

ሊያባብላት ሊያስፈራራትም ሞከረ። ግን አልተሳካለትም። ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው ጦር ባለው የብረት ዘንግ ደብድበዋታልና ደም አካባቢውን አለበሰው። መሬት ለመሬት እየጐተቱ እሥር ቤት ውስጥ ጣሏት። ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ፈውሷት ሔደ።

አንዴ በእሳት፣ አንዴም በስለት፣ ሌላ ጊዜም በግርፋት አሰቃዩዋት። ከሃይማኖቷ ግን ሊያነቃንቋት አልቻሉም። በመጨረሻ አንገቷን እንድትሰየፍ ንጉሡ አዘዘ። ወታደሮቹም ፈጸሙት። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቅድስት ሶፍያን በክብር አሳረጋት። "ስምሽን የጠራ መታሰቢያሽን ያደረገ ምሕረትን ያገኛል።" አላት።

<3 ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ <3

ቅዱሱ የነበረው በተመሳሳይ በዘመነ ሰማዕታት ነው። አባቱ ዘካርያስ፣ እናቱ ኤልሳቤጥ፣ እርሱ ደግሞ ዮሐንስ ይባላል። የሚገርም መንፈሳዊ ግጥጥሞሽ ነው። የቅዱሱ ወላጆች የሃገረ ሐራቅሊ አስተዳዳሪዎች ሲሆኑ የተመሰከረላቸው ደጐች ነበሩ።

ዘካርያስ ዐርፎ ዮሐንስ በመንበሩ የተቀመጠው ገና በሃያ ዓመቱ ነበር። በወቅቱ ከሁለቱ አንዱን መምረጥ ነበረበት። ለጣኦት ሰግዶ በምድራዊ ክብሩ መቀጠል ወይም ደግሞ በክርስትናው መሞት።

ቅዱስ ዮሐንስ ግን ልቡ በክርስቶስ ፍቅር የተሞላ ነውና ሁለት ከባድ ነገሮችን ፈጸመ። በመጀመሪያ በአካባቢው ያሉ ጣዖት ቤቶችን አወደመ። ቀጥሎ ወደ ንጉሡ ሔዶ በመኳንንቱ ፊት "ክርስቶስን የተውክ ሰነፍ" ብሎ ገሠጸው።

ከዚህ በኋላ በቅዱሱ ላይ የተፈጸመው መከራ የሚነገር አይደለም። ያላደረጉት ነገር አልነበረም። እሳቱ፣ ስለቱ፣ ሰይፉ፣ መንኮራኩሩ ከሁሉ የከፋው ግን ቆዳውን ገፈው በእሳት ጠብሰውታል። እርሱ ግን ስለ ሃይማኖቱ ይህንን ሁሉ ታግሶ በዚህች ቅን አንገቱን ተሰይፏል።

አምላካችን እግዚአብሔር ግፍዐ ሰማዕታትን አስቦ እኛን ከሚመጣው መከራ ሁሉ ይሰውረን። ከበረከታቸውም ይክፈለን።

ሰኔ ፬ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅድስት ሶፍያ ተጋዳሊት ወሰማዕት
፪.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)
፫.ቅዱስ ሳኑሲ ሰማዕት
፬.ቅድስት ማርያ ሰማዕት
፭.ቅዱስ አርቃድዮስና ባልንጀሮቹ (ሰማዕታት)
፮.ቅዱስ አሞን ሰማዕት

ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ወንጌላዊ)
፪.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ

"እንግዲህ አትፍሯቸው። የማይገለጥ የተከደነ የማይታወቅም የተሠወረ ምንም የለምና። በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ። በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ። ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ። ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።"
(ማቴ ፲፥፳፮-፳፰)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቴሌግራም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለቅዱሳን ነቢያት ዮሐንስና ኤልሳዕ ዓመታዊ የፍልሠት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ <3

የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ፦
በብሥራተ መልአክ የተጸነሰ፣
በማኅጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት፣
በበርሃ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ፣
እስራኤልን ለንስሐ ያጠመቀ፣
የጌታችንን መንገድ የጠረገ፣
ጌታውን ያጠመቀና ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው።

ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን፦
ነቢይ፣
ሐዋርያ፣
ሰማዕት፣
ጻድቅ፣
ገዳማዊ፣
መጥምቀ መለኮት፣
ጸያሔ ፍኖት፣
ቃለ ዐዋዲ..... ብላ ታከብረዋለች።

<3 ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ <3

ከነቢያተ እስራኤል አንዱ ኤልሳዕ፦
ከእርሻ ሥራ ቅዱስ ኤልያስን የተከተለ፣
መናኔ ጥሪት የተባለ፣
በድንግልና ሕይወት የኖረ፣
የታላቁ ነቢይ ኤልያስ መንፈስ እጥፍ የሆነለት፣
እጅግ ብዙ ተአምራትን ያደረገ፣
አንዴ በሕይወቱ አንዴ በአጽሙ ሙታንን ያስነሳ ታላቅ ነቢይና አባት ነው።

ቅዱሳት መጻሕፍት ሁለቱን ቅዱሳን በመልካቸውም ይገልጿቸዋል።

ቅዱስ ዮሐንስ፦
ቁመቱ ልከኛ፣
አካሉ በጸጉር የተሸፈነ፣
የራሱ ጸጉር በወገቡ፣
ጽሕሙ እስከ መታጠቃያው የወረደ ግርማው የሚያስፈራ የሠላሳ አንድ ዓመት ጎልማሳ ነበር።

ቅዱስ ኤልሳዕ፦
በጣም ረዥም፣
ራሱ ገባ ያለ (ራሰ በራ)፣
ቀጠን ያለ ፊቱ ቅጭም ያለ (የማይስቅ) ሽማግሌ ነበር።

በዚህች ቀን በ፫፻፶ ዓ.ም አካባቢ የሁለቱም ቅዱሳን አጽም ከኢየሩሳሌም ወደ ግብጽ ፈልሷል። በወቅቱ ክፋተኛ የነበረው ንጉሥ ዑልያኖስ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ሞክሮ ነበር። ለዚህ እንዲረዳው በ፸ ዓ.ም የፈረሰውን የአይሁድ ቤተ መቅደስ አንጻለሁ ቢልም ሦስት ጊዜ ፈረሰበት።

ምክንያቱን ቢጠይቅ "የክርስቲያኖች አጽም በሥሩ ስላለ እሱን አውጥተህ አቃጥል።" አሉት።

ሲቆፈር በመጀመሪያ የሁለቱ ቅዱሳን አጽም በምልክት በመታወቁ በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች በብዙ ብር ገዝተው ወደ ግብጽ አውርደው ለቅዱስ አትናቴዎስ ሰጥተውታል። እርሱም በስደት ላይ ነበርና በክብር ደብቋቸዋል።

በኋላም በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘመን ቤተ ክርስቲያናቸው ታንጾ በዚህች ቀን ተቀድሷል። በቅዳሴው ሰዓትም ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዮሐንስ መጥምቁና ቅዱስ ኤልሳዕ ወርደው ሕዝቡን ሲባርኩ በይፋ ተመልክቷል።

አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ፍቅር ያድለን።

ሰኔ ፪ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ፍልሠቱ)
፪.ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ (ፍልሠቱ)
፫.አባ ቀውስጦስ ኢትዮጵያዊ

ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
፪.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
፫.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፬.ቅዱስ አባ ጳውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
፭.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
፮.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

"ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ።
.....ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን.....
እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም።
.....ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ። ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው።
የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።"
(ማቴ ፲፩፥፯-፲፭)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቴሌግራም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለእናታችን አርዋ ቅድስትና ለሐዋርያው ቅዱስ ቆሮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ቅድስት አርዋ <3

እናታችን ቅድስት አርዋ በሥነ ገድላቸው ከደመቁ የቀደመው ዘመን ቅዱሳት አንስት አንዷ ናት። በሕፃንነቷ የሚገባውን የክርስትና ትምህርት ተምራለችና ምርጫዋ ሰማያዊው ሙሽርነት ሆነ።

ለሰዎች ሕይወት እንቅፋት እየሆኑ ከሚያስቸግሩ ነገሮች አንዱ መልክ ነው። እግዚአብሔር የፈጠረውን ደም ግባት (ቁንጅና) በማይገባ ተጠቅመው የአጋንንት ራት የሆኑ ሌሎችንም አብረው ያጠፉ ሰዎች ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ነው። አርዋ ግን ይህ ቀረሽ የማይሏት ውብ ብትሆንም እርሷ ለዚህ ቦታ አልነበራትም። በለጋ እድሜዋ በክርስቶስና በድንግል እናቱ ፍቅር ተጠመደች እንጂ።

ቅድስት አርዋ ሁሉ ያላት ስትሆን ስለ መንግሥተ ሰማያት ሁሉን ንቃለች። በተለይ ደግሞ ሥጋዊ ፍትወትን ትገድል ዘንድ ያሳየችው ተጋድሎ በዜና ቤተ ክርስቲያን የተደነቀ በመሆኑ "መዋኢተ ፍትወት" (የሥጋን ፍላጎት ድል የነሳች) አስብሏታል።

የሚገርመው የቅድስቷ እናታችን ሕይወት በጾምና በጸሎት ብቻ የተወሰነ አልነበረም። በሰው ሁሉ ፊት ብርሃን መሆን የቻለ የደግነት፣ ርኅራኄ፣ የፍቅርና የምጽዋት ሕይወትም ነበራት እንጂ።

አንድ ቀን በተንኮለኞች የሐሰት ምስክር ያለ ጥፋቷ ለፍርድ ቀረበች። ፍርደ ገምድል ዳኛ ሞት ፈረደባት። በአደባባይ በጭካኔ ቅድስት እናታችንን ገደሏት። እግዚአብሔር ግን ድንቅ ነውና ከሞት አስነስቷት ገዳዮቿ እንዲጸጸቱ አድርጓል። ከዚህ በኋላም በንጹሕ አኗኗሯ ቀጠለች።

አንድ ቀን ግን ከባድ ፈተና መጣባት። በደም ግባቷ ተማርኮ ሲፈልጋት የኖረ ጐልማሳ አሳቻ ሰዓትና ቦታ ላይ አገኛት። የሥጋ ፈቃዱን ይፈጽም ዘንድ አስገደዳት።

እርሱን መታገሉ ከአቅሟ በላይ ስለሆነባት እርሱ ልብሱን እያወለቀ እርሷ ከወደቀችበት ሆና ወደ ፈጣሪዋ ለመነች። "ጌታዬ ሆይ! የእኔንም ድንግልና ጠብቅ፤ እርሱንም ኃጢአት ይሠራ ዘንድ አትተወው። ስለዚህም ነፍሴ ተቀበላት።" ብላ አለቀሰች።

እመቤታችን እንደ ዓይን ጥቅሻ ወርዳ ነፍሷን አሳረገች። ጐልማሳው ወደ ጣላት ቅድስት ዘወር ቢል ዐርፋ አገኛት። እርሱም ተጸጸተ። ወገኖቿ በዝማሬ እናታችን ቅድስት አርዋን ቀብረዋታል።

<3 ቅዱስ ቆሮስ <3

ዳግመኛ በዚህች ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቆሮስ ዐርፏል።
ቅዱስ ቆሮስ ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ሲሆን ከጌታችን እግር የተማረ ለስብከተ ወንጌል ብዙ ሃገራትን የዞረ ታላቅ ሐዋርያ ነው። ባስተማረባቸው ቦታዎች ብዙ ሕማማትን ተቀብሏል።

ብዙ አሕዛብንም ወደ አሚነ ክርስቶስ መልሷል። በተለይ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ለዓመታት አገልግለዋል። ቅዱስ ጳውሎስ ሲታሠር መልዕክቶችንም ይወስድለት ነበር።

አምላካችን ከወዳጆቹ በረከትን ይክፈለን።

ግንቦት ፴ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅድስት አርዋ እናታችን
፪.ቅዱስ ቆሮስ ሐዋርያ
፫.ቅዱስ ዲማዲስ ሰማዕት
፬.አባ ሚካኤል ሊቀ ጳጳሳት

ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፪.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ
፫.አባ ሣሉሲ ክቡር
፬.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
፭.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት

"መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ። አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ።
ውበት ሐሰት ነው። ደም ግባትም ከንቱ ነው።
እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች። ከእጇ ፍሬ ስጧት። ሥራዎቿም በሸንጐ ያመስግኗት።"
(ምሳሌ ፴፩፥፳፱-፴፩)

በቴሌግራም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለእናታችን ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ <3

ቅድስቷ እናታችን በነገድ እስራኤላዊ ስትሆን የተወለደችው ኢየሩሳሌም ውስጥ በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ ነው። ወላጆቿ ክርስቲያኖች በመሆናቸው በሚገባው ፈሊጥ አሳድገው ወደ ትምህርት አስገቧት።

አስተማሪዋ ገዳማዊ መነኮስ ነበርና ከተማ ውስጥ አያድርም። አስተምሯት ዕለቱኑ ወደ በዓቱ ይመለስ ነበር እንጂ። ዓመተ ክርስቶስ ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቃ ተማረች።

አንድ ቀን እንደ ልማዷ ልትማር ብትጠብቀውም መምህሯ ሊመጣ አልቻለም። ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ መነኮሱን ልትጠይቅ አንድም ልትማር ወደ በዓቱ ሔደች።

በሩ ላይ ደርሳ ብታንኳኳም መልስም የሚከፍትም አልነበረም። ከውስጥ ግን ምርር ያለ የለቅሶ ድምጽ ተሰማት። "ጌታ ሆይ! ይቅር በለኝ?" እያለ በተደጋጋሚ ይጮሃል። ያ ደጉ መነኮስ ነበር።

ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ በቅጽበት አንድ ሐሳብ መጣላት። "እርሱ በንጽሕና እየኖረ ስለ ነፍሱ እንዲህ ከተማጸነ እኔማ እንደምን አይገባኝ!" ብላ ወደ ቤቷ ተመለሰች። የለበሰችውን ልብስ አልቀየረችም። ቤተሰቦቿን አልተሰናበተችም። ከቤቷ አተር በዘንቢል እና ውኃ በትንሽ እቃ ይዛ ወደ ጐልጐታ ገሰገሰች።

ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ላይ ወድቃ አለቀሰች፤ ጸለየችም። "ጌታ ሆይ! ነፍሴን ወደ ዕረፍት አድርሳት? ከክፉ ጠላትም ጠብቀኝ? ይህንን አተርና ውኃ ለእድሜ ዘመን ሁሉ ባርክልኝ።"

ይህን ብላ እየፈጠነች ከኢየሩሳሌም ተነስታ በእግሯ ቃዴስን ሲናይ በርሃን አቋርጣ ግብጽ ደረሰች። ምርጫዋ ብሕትውና ሆኗልና ልምላሜ ከሌለበት ፀሐዩ እንደ ረመጥ ከሚፋጅበት በርሃ ገባች።

በዚያም ከያዘችው አተር ለቁመተ ሥጋ እየበላች ከውኃውም በጥርኝ እየተጐነጨች ማንንም ሰው ሳታይ በፍጹም ተጋድሎ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ቆየች። የቀኑ ሐሩር የሌሊቱ ቁር (ብርድ) ልብሷን ቆራርጦ ቢጨርሰው እግዚአብሔር ፀጉሯን አሳድጐ አካሏን ሸፈነላት።

ጊዜ ዕረፍቷ ሲደርስ የቅዱሳንን ዜና የሚጽፈው ታላቁ አባ ዳንኤል ወደ እርሷ ደረሰ። እንዳያት ተከተላት። እርሷ ግን በተሰነጠቀ አለት ውስጥ ገብታ ተደበቀች። አባ ዳንኤል በውጪ ሆኖ ተማጸነ። "እባክህ አባቴ! ውጣና ባርከኝ?" አለ። ሴት መሆኗን አላወቀም ነበርና። እርሷ ግን "ራቁቴን ነኝና አልወጣም።" አለችው።

ልብሱን አውጥቶ ሰጥቷት ወጥታ ተጨዋወቱ። በፈቃደ እግዚአብሔር ዜናዋን ሁሉ አወቀ። ወደ በዓቷ ዘወር ሲል በዘንቢል የሞላ አተር ተመለከተ። ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ተበልቶ ዛሬም ሙሉ ነው። አባ ዳንኤል ይፈትነው ዘንድ ከአተሩ በደንብ በላለት፤ ከውኃውም ጠጣለት። ግን ሊጐድል አልቻለም።

እያደነቀ "እናቴ ሆይ! ልብሴን ውሰጅው።" ቢላት "ሌላ አዲስ አምጣልኝ።" አለችው። ይዞላት በመጣ ቀን ግን ተሠውራለችና አላገኛትም።

አንድ ቀን ግን (ማለትም ግንቦት ፳፰) አረጋውያን መነኮሳት መጥተው የገጠማቸውን ነገር ነገሩት። እንዲህ ሲሉ፦ "ሰው ተመልክተን ወደ በዓቱ ስንገባ አተር በዘንቢልና ውኃ በመንቀል አገኘን። ስንበላው ወዲያው አለቀ።" አባ ዳንኤል ነገሩን ገና ሳይጨርሱለት አለቀሰ።

አተሩ አለቀ ማለት ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ዐርፋለች ማለት ነውና። አረጋውያኑ ግን ቀጠሉ፦ "ከበዓቱ ስንወጣ በጸጉሯ አካሏ ተሸፍኖ ወደ ምሥራቅ ሰግዳ ዐርፋ አግኝተን ከሥጋዋም ተባርከን ቀበርናት።" አሉ። አባ ዳንኤል ዜናዋን ጽፎላት ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ታከብራታለች።

አምላካችን በቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ጸሎት ይማረን። ከበረከቷም ያድለን።

ግንቦት ፳፰ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ተጋዳሊት (ገዳማዊት)
፪.ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሊቅ (ሥጋው ቆጵሮስ የደረሰበት)
፫.አባ መርቆሬዎስ ገዳማዊ
፬.አባ ጌርሎስ (ጻድቅና ሰማዕት)
፭.አርባ አምስቱ ሰማዕታት (የአባ ጌርሎስ ደቀ መዛሙርት)
፮.ቅዱስ አጋቦስ ሰማዕት

ወርኀዊ በዓላት
፩.አማኑኤል ቸር አምላካችን
፪.ቅዱሳን አበው (አብርሃም፣ ይስሐቅና ያዕቆብ)
፫.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፬.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)

"ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።"
(፩ጴጥ ፫፥፫-፬)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቴሌግራም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ (መንፈስ ቅዱስ) በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 በዓለ ጰራቅሊጦስ <3

ከዚህ በፊት እንደተመለከትነው የጌታችን ዐበይት በዓላቱ ሁለት ጊዜ (ማለትም ጥንተ በዓልና የቀመር በዓል ተብለው) ይከበራሉ።
በዚህች ዕለት አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ መውረዱን እናስባለን።
ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦
ቸር አምላክ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል
ከልዑል ማዕርጉ ወርዶ፣
በማኅጸነ ድንግል ተጸንሶ፣
በኅቱም ድንግልና ተወልዶ፣
ከኃጢአት በቀር በግዕዘ ሕፃናት አድጐ፣
በሠላሳ ዘመኑ ተጠምቆ፣
ቅድስት ሕግ ወንጌልን አስተምሮ፣
በፈቃዱ ሙቶ፣
በባሕርይ ሥልጣኑ ተነሥቶ በአርባኛው ቀን ያርጋል።

ታዲያ ደቀ መዛሙርቱን የቅዱስ መንፈሱን ጸጋ ተስፋ እንዲያደርጉ ነግሯቸው ነበርና በተነሣ በሃምሳኛው ቀን በዐረገ በአሥረኛው ቀን ተስፋውን ፈጸመላቸው።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ እንድትይዝ በአንድ ላይ ሰብስባ ለክብረ መንፈስ ቅዱስ አብቅታቸዋለች። መቶ ሃያው ቤተሰብ ከጌታችን እናት ጋር ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በአውሎ ንፋስ አርአያ ወርዶ በአምሳለ እሳት አደረባቸው።

ቅዱሳን ሐዋርያት ፈሪዎች የነበሩ ደፋሮች፣ አሮጌ ሕሊና የነበራቸው ሐዲሶች ሆኑ። በአዕምሮ ጐለመሱ፣ ቋንቋ ተናገሩ፣ ምሥጢርም ተረጐሙ። በቅጽበትም ብሉይ ከሐዲስ በልቡናቸው ውስጥ ተሞላ።

ሐዋርያቱ ቅዱስ መንፈስን ተቀብለው ዓለምን በወንጌል ዕርፈ መስቀል አርሰዋል። አልጫውን ዓለም ጨው ሆነው አጣፍጠዋል። ሳይሳሱም አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተዋል።

"ኪያሁ መንፈሰ ነሢኦሙ ለለአሐዱ።
ሐዋርያት ለሰቢክ አሕጉራተ ዓለም ዖዱ።
ሰማዕትኒ ለሕማም ነገዱ።" እንዳለ ደራሲ።

በዚህች ቀን ሁለት ነገሮች በትኩረት ይነገራሉ።
፩. የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክነት
እርሱ ከአብ የሠረጸ ፣ ቅድመ ዓለም የነበረ፣ በባሕርይ ሥልጣኑ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል የሆነ የራሱ ፍጹም አካል ያለው ፍጹም አምላካችን ነውና።

፪. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አብ ያሰባት፣ ወልድ በደሙ የቀደሳት፣ መንፈስ ቅዱስ በጸጋው ያጸናት የክርስቲያኖች አማናዊት አንድነት አንድም ቤት ናትና። ዛሬ በጉባዔ ተመስርታለች።

አምላከ ቅዱሳን ከቅዱስ መንፈሱ ጸጋ ለኃጥአን ባሮቹ ያድለን።

"በዓለ ሃምሳም የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ። ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው። እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው። በእያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው። በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው። መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።"
(ሐዋ ፪፥፩-፬)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስና ለጻድቁ ቅዱስ ሃብተ ማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ <3

ከአሥራ ሁለቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ብዙ መከራን በማሳለፉና የጌታችንን ጐን በመዳሰሱ ይታወቃል።

ቅዱስ ቶማስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት በእስራኤል ተወልዶ በዚያውም በሥርዓተ ኦሪት አድጐ ገና በወጣትነቱ የሰዱቃውያንን ማኅበር ተቀላቅሏል። ሰዱቃውያን ሰው ከሞተ በኋላ አይነሳም (አልቦ ትንሣኤ ሙታን) የሚሉ ናቸው።

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሲጀምር ግን ቅዱስ ቶማስ ከነበረበት ማኅበር ወጥቶ ጌታችንን ተከተለ። ጌታችንም ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ይሆን ዘንድ ሾመው። የቀደመ ስሙ ዲዲሞስ ሲሆን ጌታችን ቶማስ ብሎታል።

ቅዱስ ቶማስ ጌታ አልዓዛርን ለማስነሳት በሔደ ጊዜ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን "አይሁድ ይገድሉሃል ቅር።" ሲሉት እርሱ ግን "እንሒድና አብረን እንሙት።" ሲል ፍቅሩን አሳይቷል።
(ዮሐ. ፲፩፥፲፮)

ጌታችን ትንሣኤውን ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠ ጊዜ ያልነበረው ቶማስ ካላየሁ አላምንም አለ።
ምክንያቱም፦
፩.ለጌታችን ከነበረው ፍቅር የተነሳ እውነት አልመስልህ ቢለው።
፪.አንድም ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሣኤውን አየን እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብየ ማስተማሬ ነው ብሎ በማሰቡ ነበር።

ለጊዜው ጌታ ተገልጾ ቢገስጸው "እግዚእየ ወአምላኪየ (ጌታዬ፣ አምላኬም)" ብሎ ፍጹም ሃይማኖቱን ገልጿል። ለፍጻሜው ግን የጌታችንን ጎን (መለኮትን) ይዳስስ ዘንድ ባለቤቱ እንዳደለው ያጠይቃል። መለኮትን የዳሰሰች ይህች ቅድስት እጁ ዛሬም ድረስ ሕያው ናት። በሕንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም በክብር ተቀምጣለች።

ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ሃገረ ስብከት ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ቶማስ ሕንድና በዙሪያዋ ያሉ ሃገራት ደረሱት። ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ዘርዝረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ የፈጸመው። ቅዱሱ በነበረው ፍጹም ትጋት አባቶቻችን "ዘአሠርገዋ ለብሔረ ሕንደኬ (ሕንድን በወንጌል ያስጌጣት)" ሲሉ ያከብሩታል።

ቅዱስ ቶማስ ንጉሥ ሉክዮስንና የሃገሩን ሕዝብ ለማሳመን በችንካር መሬት ላይ ወጥረው ቆዳውን ገፈውታል። ቆዳውንም እንደ ገና ሰፍተው አሸዋ ሞልተው አሸክመውታል።

በየመንገዱ የተገፈፈ ገላውን ጨው ቢቀቡት በጎች መጥተው ግጠው በልተውታል።
በዚህ ምክንያት፦
"ኩሉ የአኪ እንዘ የአኪ ዘመኑ
አባግዒሁ ለቶማስ እስመ አራዊተ ኮኑ።" ብለዋል ሊቃውንቱ።

በኋላ ግን ከፎቅ ወድቃ የሞተችውን የንጉሡን ሚስት በተገፈፈ ቆዳው በማዳኑ ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል።

ቅዱሱ ሐዋርያ ልክ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ አንዳንዴ በፈሊጥ ሌላ ጊዜም በመከራ ለወንጌልና ለቤተ ክርስቲያን ተጋድሏል። ያለ ማቋረጥም ከሕንድ እስከ ሃገራችን ኢትዮጵያ ድረስ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ወንጌልን ሰብኳል።

በመጨረሻም በ፸፪ ዓ.ም በዚህች ቀን በሰማዕትነት ዐርፏል። መቃብሩና ቅድስት እጁ ዛሬ ድረስ ሕንድ ውስጥ አሉ። ከኘሮቴስታንቶች በቀር መላው ዓለም ያከብረዋል።

እንደ አባቶቻችን ትርጉም ቶማስ (ቶማስስ) ማለት ፀሐይ (ኦርያሬስ) እንደ ማለት ነው። በተሰጠው የወንጌል ጸጋ በሃገረ ስብከቱ አብርቷልና።

<3 አቡነ ሃብተ ማርያም ጻድቅ <3

እኒህ ጻድቅ ደግሞ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው። "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው። ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል።

ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች። በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ፣ ምጽዋትን ወዳጅ፣ ቡርክት ሴት ነበረች። እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር።

ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማኅጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ።" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች። ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ ሰባት አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች።

ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕፃን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ። ይህችን ጸሎት በሕፃን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር።

የአምስት ዓመት ሕፃን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል። ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ። ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል። የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል።

ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ትምህርት ቤት ገብተው መጻሕፍትን አጥንተው መንነዋል። በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በኋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም።
ባሕር ውስጥ ሰጥመው አምስት መቶ ጊዜ ይሰግዳሉ።
በየቀኑ አራቱን ወንጌልና መቶ ሃምሳውን መዝሙረ ዳዊት ይጸልያሉ። (መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው።)
በአርባ ቀናት ቀጥሎም በሰማንያ ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ።
ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው።
በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ። (ካህን ናቸውና።)
ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ፤ ክቡር ደሙን ይጠጣሉ።
በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን፣ መከፋትን አላሳደሩም።

በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር። ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በኋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከትሎ መጥቶ አላቸው።
"ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ፣
ስለ ምናኔህ፣
ስለ ተባረከ ምንኩስናህ፣
ስለ ንጹሕ ድንግልናህ፣
ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ፣
ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ፣
ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ ሰባት አክሊላትን እሰጥሃለሁ።"

"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን አምስት መቶ የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ። በስምህ የሚለምኑ፣ በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ።" አላቸው።

ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው። ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ ሦስት ጊዜ ሳማቸው። ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች፤ በዝማሬም ወሰዷት።

አምላከ አበው ጣዕመ ፍቅራቸውን፣ ክብራቸውን፣ ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን።

ግንቦት ፳፮ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት)
፪.ቅድስት አርሶንያ (የቅዱስ ቶማስ ተከታይ የሆነች ንግሥት)
፫.አቡነ ሃብተ ማርያም ጻድቅ

ወርኀዊ በዓላት
፩.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
፪.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
፫.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

"ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ። በመካከላቸውም ቆሞ "ሰላም ለእናንተ ይሁን።" አላቸው። ከዚያም በኋላ ቶማስን "ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ። እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው። ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን።" አለው። ቶማስም "ጌታዬ አምላኬም" ብሎ መለሰለት። ኢየሱስም "ስላየኸኝ አምነሃል። ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው።" አለው።"
(ዮሐ ፳፥፳፮-፳፱)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የስደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

የአርያም ንግሥት የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ልጇን አዝላ በዚህች ቀን ወደ ምድረ ግብጽ ወርዳለች።

በወንጌል ላይ ማቴ. ፪፥፩-፲፰ እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በሁለት ዓመቱ የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት ወርቅ እጣን ከርቤውን ገበሩለት፤ አገቡለት።

ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሄሮድስ መቶ አርባ አራት ሺህ ሕፃናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን አዝላ በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቋጥራ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች።

ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ በመከራ፣
በረሃብና በጥም፣
በሐዘንና በድካም፣
በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚህች ቀን ምድረ ግብጽ ገብታለች።

የአምላክ እናቱ
እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች።
ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች።
የሕይወትን ውኃ ተሸክማ ተጠማች።
የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች።
የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች።
እመ አምላክ ተራበች፣ ተጠማች፣ ታረዘች፣ ደከመች፣ አዘነች፣ አለቀሰች፣ እግሯ ደማ፣ ተንገላታች።

ለሚገባው ይህ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው። በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው። አራዊት፣ ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኳ ለአምላክ እናት ክብር ይሰጣሉ።

አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል። ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና።

መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ?
ለምንስ ስደቱን ወደ ግብጽና ኢትዮጵያ አደረገ?
፩.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ
በፈጣን ደመና ወደ ግብጽ እንደሚወርድ ተነግሯልና።
(ኢሳ. ፲፱፥፩ ፣ ዕን. ፫፥፯)
፪.ምሳሌውን ለመፈጸም።
የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም፣ ያዕቆብ (እስራኤል)፣ ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና።
፫.ከግብጽ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ።
(ኢሳ. ፲፱፥፩)
፬.የግብጽና የኢትዮጵያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ።
፭.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ። ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበርና። ሄሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም። ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዓርብ ደሙ አይፈስምና።
፮.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠትና
፯.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው።

ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግሥተ ሰማያት ስደት ይሠውረን። ከስደቱ በረከትም ያድለን።

ግንቦት ፳፬ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ
፪.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊና ቅድስት ሰሎሜ
፫.ቅዱስ አብቁልታ ሰማዕት
፬.ቅዱስ አልዓዛር ካህን (የአሮን ልጅ)

ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
፪.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤጲስቆጶስ)
፫.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፬.ቅዱስ ሙሴ ፀሊም
፭.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
፮.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
፯.ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ (ሱራፌል)
፰.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ (ኢትዮጵያዊ)

"ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃኑዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ። አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች። ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ። ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች።"
(ራእይ ፲፪፥፬-፮)

በቴሌግራም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለቅዱሳን ሐዋርያት ዮልዮስና አፍሮዲጡ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ዮልዮስ ወአፍሮዲጡ ሐዋርያት <3

ቅዱሳን ሐዋርያትና አርድእት በቁጥር ሰማንያ አራት ቢሆኑም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታሪኩ በዝርዝር የተጻፈለት ቅዱስ ጳውሎስ ነው። የሌሎቹ አልፎ አልፎ የተጠቀሰ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ግን የት እንደ ደረሱም አልተጻፈም።

በዚህ ምክንያት ወደድንም ጠላንም አዋልድ መጻሕፍትን መጠቀማችን አይቀርም። ምክንያቱም "ሑሩ ወመሐሩ" ያላቸው ሁሉንም ሐዋርያትና አርድእት ነውና።

የቅዱሳን ሐዋርያትን ሕይወት ከያዙ ቅዱሳት መጻሕፍት መካከል በቀዳሚነት ዜና ሐዋርያትና ገድለ ሐዋርያት የሚጠቀሱ ሲሆን ስንክሳራችንም አልፎ አልፎ ያወሳቸዋል። በዚህም መሠረት ዛሬ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሰባ ሁለቱ አርድእት የሚቆጠሩትን ቅዱስ ዮልዮስንና ቅዱስ አፍሮዲጡን ታከብራለች።

ሁለቱም ከጌታችን እግር ሥር ለሦስት ዓመታት ተምረው በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ከባልንጀሮቻቸው ሐዋርያት ጋር ለወንጌል አገልግሎት ሃገራትን ዙረዋል። በሐዋርያት ሲኖዶስም ጵጵስናን ተሹመዋል።

በአገልግሎት በነበሩባቸው የእስያና አውሮጳ ሃገራት አእላፍ ነፍሳትን ወደ ሕይወት ሲማርኩ ግፍን በአኮቴት ተቀብለዋል። ከጌታቸውም የማይጠፋ የሕይወት አክሊልን ተቀዳጅተዋል።

በተለይ ቅዱስ ዮልዮስ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር መከራን በመቀበሉ በሮሜ መልእክቱ ፲፮፥፯ ላይ አወድሶታል። ከቅዱስ እንድራኒቆስ ጋርም በጣም ይዋደዱ ነበርና ትናንት እርሱን ገንዞ ቀብሮ በእንባ ወደ ጌታው ፀለየ። ጌታችንም በማግስቱ (ማለትም ዛሬ) አሳርፎታል።

አምላከ ቅዱሳን ከሐዋርያቱ ትጋትና በረከት ያድለን።

ግንቦት ፳፫ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ ዮልዮስ (ዮልያን) ሐዋርያ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት)
፪.ቅዱስ አፍሮዲጡ ሐዋርያ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት)
፫.ቅዱሱ ሕፃን ሰማዕት (በዘመነ ሰማዕታት ገና የሁለት ወር ሕፃን ቢሆንም ጌታችን አፉን ከፍቶለት "ክርስቲያን ነኝ።" በማለቱ ከእናቱ ጋር የተሠየፈ)
፬.አባ አንስያ ሰማዕት
፭.ቅዱስ ታኦድራጦስ

ወርኀዊ በዓላት
፩.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
፪.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
፫.ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እስራኤል
፬.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
፭.አባ ሳሙኤል
፮.አባ ስምዖን
፯.አባ ገብርኤል

"ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ ደግሞም ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ አብረውኝም ለታሰሩ ለዘመዶቼ ለአንድራኒቆንና ለዮልያን (እንድራኒቆስና ዮልዮስ) ሰላምታ አቅርቡልኝ።"
(ሮሜ ፲፮፥፮-፯)

በቴሌግራም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

"ኦ ንግሥት ይገንዩ ለኪ ነገሥት ወለኪ ንግሥታት ይትቀነያ
ወኪያኪ የአኲታ ወለስምኪ ይገንያ
ወለኪ ይሰግዳ ወለክብርኪ የሐልያ
ጢሮስ ወሲዶና ሰብአ ግብጽ ወኢትዮጵያ
ፊንቂ ወሮምያ ማሮን ወአርማንያ
በሥነ ጸዳልኪ ይትፌሥሓ ወበላሕይኪ ይትሐሠያ።"

(ንግሥት ሆይ ነገሥታት ለአንቺ ያገለግላሉ፤ ንግሥታትም አንቺን ያመሰግናሉ፤ አንቺንም ያሞግሳሉ፤ ለስምሽም ያጐነብሳሉ፤ ለአንቺ የጸጋ ስግደትን ይሰግዳሉ፤ ለክብርሽም ምስጋናን ያቀርባሉ፡፡ ጢሮስና ሲዶና የግብጽና የኢትዮጵያ ሰዎች፣ ፊንቄና ሮምያ፣ ማሮንና አርማንያ በወጋገንሽ ውበት ደስ ይሰኛሉ፤ በደም ግባትሽም እሰይ ይላሉ።)
(አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ)

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለመናኙ ንጉሥ ቅዱስ አፄ ካሌብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 መናኙ ንጉሥ ካሌብ <3

ቅዱሱን ንጉሥ አፄ ካሌብን በዓለም ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በትልቁ ያከብሩታል። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን አክሱም አካባቢ ካልሆነ ከነ ስም አጠራሩ እንኳ እየተዘነጋ ይመስለኛል።

ነገር ግን ውለታው፣ ምናኔውና ቅድስናው የማይረሳ ነውና እንኳን በእምነት የሚመስሉን ይቅርና የማይመስሉን ምሥራቅ ኦርቶዶክሶችና ካቶሊኮች ዓመታዊ በዓሉን በወርኀ ጥቅምት ያከብራሉ።

ከአክሱም ነገሥታት በኃይሉም ሆነ በሃይማኖታዊ ቅድስናው አፄ ካሌብ ዋናው ነው። ቅዱሱ የነገሠው በ፬፻፹፭ ዓ.ም አካባቢ ሲሆን እስከ ፭፻፲፭ ዓ.ም ድረስ በዙፋኑ ላይ ቆይቷል። ከመልካም ትዳሩ አፄ ገብረ መስቀልን ጨምሮ ልጆችን ወልዷል።

ስለ ቅዱስ አፄ ካሌብ እስኪ እነዚህን ነገሮች ብቻ እናንሳ።
፩.በንግሥና ዙፋን ከመቀመጡ በፊት የሚገባውን መንፈሳዊ ትምህርት ጠንቅቆ ተምሯል።
፪.ሃይማኖቱ የጠራና እጅግ የሚደነቅ ነበር። በእርሱ ዘመን ሃይማኖት ለነገሥታቱ የፖለቲካ ማስፈጸሚያ ነበር። እርሱ ግን እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ አምልኳል።
፫.ለእመቤታችንና ለቸር ልጇ የነበረው ጥልቅ ፍቅር የተገለጠና የሚያስቀና ነበር።
፬.ገና በዙፋኑ ሳለ ጸሎትን ያዘወትር ነበር።

ዛሬም ድረስ ሁሉም ክርስቲያኖች የማይረሱትን መንፈሳዊ ቅንዓትን አሳይቷል።
ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦
በወቅቱ ዐመፀኛው የአይሁድ መሪ ፊንሐስ በሃገረ ናግራን (የአሁኗ የመን) ውስጥ የነበሩ ክርስቲያኖችን ክርስቶስን ካዱ በሚል ጨፈጨፋቸው።

ከተማዋንም ለአርባ ቀናት በእሳት አነደዳት። ዜናው በመላው ዓለም ሲሰማ በርካቶቹ ቢያዝኑም የተረፉትን ለመታደግ የሞከረ አልነበረም።

ቅዱስ አፄ ካሌብ ግን የሆነውን ሲሰማ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ በግንባሩ ሰገደ። ወደ ፈጣሪም ጸለየ "ጌታዬ ሆይ! የክርስቲያኖችን ደም እመልስ ዘንድ እርዳኝ? እኔ በጦሬ ብዛት አልመካም። እኔ ተሸንፌ ክርስትና ከሚናቅ እዚሁ ግደለኝ።" ብሎ በበርሃ ላሉ መነኮሳት እንዲጸልዩ ላከባቸው።

ጊዜ ሳያጠፋ በመርከብና በፈረስ፣ በበቅሎና በግመል ናግራን (የመን) ደረሰ። ፊንሐስን ገድሎ ሠራዊቱንም ማርኮ ክርስቲያኖችን ነጻ አወጣ። ደምና እንባቸውንም አበሰ። አብያተ መቅደሶችን አንጾላቸው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ።

ወዲያው እንደተመለሰ ወደ አክሱም ጽዮን ገብቶ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስላደረክልኝ የምሰጥህ ሰውነቴን እንጂ ሃብቴን አይደለም።" ብሎ መንግሥቱን ለልጁ ገብረ መስቀል አውርሶ ከዙፋኑ ወጣ። የወርቅ አክሊሉን ወደ ኢየሩሳሌም ልኮ እርሱ በአባ ጰንጠሌዎን እጅ መንኩሶ መነነ።

ከዚህች ዓለም ከአንዲት ረዋት (ኩባያ)፣ ከአንዲት ሰሌንና ከአንዲት ቀሚስ በቀር የወሰደው አልነበረም። ከዚያም በበዓቱ ውስጥ በጾምና በጸሎት ተወስኖ አንድም ሰው ሳያይ በሰባ ዓመቱ በ፭፻፳፱ ዓ.ም ዐርፏል። ጌታችንም በሰማይ ክብርን አጐናጽፎታል።

ለቅዱስ አፄ ካሌብ የተለመነ አምላክ ለእኛም ይለመነን። በጻድቁም ጸሎት ከመከራ ይሠውረን።

ግንቦት ፳ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ አፄ ካሌብ (መናኙ ንጉሠ ኢትዮጵያ)
፪.ቅዱስ አሞንዮስ ገዳማዊ (ታላቁ አሞኒ ዘቶና)
፫.ቅድስት ሳድዥ የዋሂት
፬.አባ ሖር ጻድቅ
፭.አባ ዳርማ ገዳማዊ
፮.ቅዱስ ዘካርያስ አንጾኪያዊ
፯.አባ በትረ ወንጌል ዘደብረ ሊባኖስ

ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት)
፪.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
፫.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ

"አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል። በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል።
የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው። የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም።
በበጐ በረከት ደርሰህለታልና። ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ።
ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም። ለረጅም ዘመን ለዘላለሙ።
በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው።"
(መዝ ፳፥፩-፭)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቴሌግራም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለጥንተ በዓለ ጰራቅሊጦስ (መንፈስ ቅዱስ) እና ለጻድቁ አባ ገዐርጊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 በዓለ ጰራቅሊጦስ <3

ከዚህ በፊት እንደተመለከትነው የጌታችን ዐበይት በዓላቱ ሁለት ጊዜ (ማለትም ጥንተ በዓልና የቀመር በዓል ተብለው) ይከበራሉ።
በዚህች ዕለት አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ መውረዱን እናስባለን።
ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦
ቸር አምላክ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል
ከልዑል ማዕርጉ ወርዶ፣
በማኅጸነ ድንግል ተጸንሶ፣
በኅቱም ድንግልና ተወልዶ፣
ከኃጢአት በቀር በግዕዘ ሕፃናት አድጐ፣
በሠላሳ ዘመኑ ተጠምቆ፣
ቅድስት ሕግ ወንጌልን አስተምሮ፣
በፈቃዱ ሙቶ፣
በባሕርይ ሥልጣኑ ተነስቶ በአርባኛው ቀን ያርጋል።

ታዲያ ደቀ መዛሙርቱን የቅዱስ መንፈሱን ጸጋ ተስፋ እንዲያደርጉ ነግሯቸው ነበርና በተነሳ በሃምሳኛው ቀን በዐረገ በአሥረኛው ቀን ተስፋውን ፈጸመላቸው።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ እንድትይዝ በአንድ ላይ ሰብስባ ለክብረ መንፈስ ቅዱስ አብቅታቸዋለች። መቶ ሃያው ቤተሰብ ከጌታችን እናት ጋር ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በአውሎ ንፋስ አርአያ ወርዶ በአምሳለ እሳት አደረባቸው።

ቅዱሳን ሐዋርያት ፈሪዎች የነበሩ ደፋሮች፣ አሮጌ ሕሊና የነበራቸው ሐዲሶች ሆኑ። በአዕምሮ ጐለመሱ፣ ቋንቋ ተናገሩ፣ ምሥጢርም ተረጐሙ። በቅጽበትም ብሉይ ከሐዲስ በልቡናቸው ውስጥ ተሞላ።

ሐዋርያቱ ቅዱስ መንፈስን ተቀብለው ዓለምን በወንጌል ዕርፈ መስቀል አርሰዋል። አልጫውን ዓለም ጨው ሆነው አጣፍጠዋል። ሳይሳሱም አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተዋል።

"ኪያሁ መንፈሰ ነሢኦሙ ለለአሐዱ።
ሐዋርያት ለሰቢክ አሕጉራተ ዓለም ዖዱ።
ሰማዕትኒ ለሕማም ነገዱ።" እንዳለ ደራሲ።

በዚህች ቀን ሁለት ነገሮች በትኩረት ይነገራሉ።
፩. የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክነት
እርሱ ከአብ የሠረጸ ፣ ቅድመ ዓለም የነበረ፣ በባሕርይ ሥልጣኑ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል የሆነ የራሱ ፍጹም አካል ያለው ፍጹም አምላካችን ነውና።

፪. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አብ ያሰባት፣ ወልድ በደሙ የቀደሳት፣ መንፈስ ቅዱስ በጸጋው ያጸናት የክርስቲያኖች አማናዊት አንድነት አንድም ቤት ናትና። ዛሬ በጉባዔ ተመስርታለች።

<3 አባ ገዐርጊ <3

ዳግመኛ በዚህች ቀን ጻድቁ አባ ገዐርጊ ዐርፏል። ጻድቁ ገዳመ አስቄጥስ ካፈራቻቸው ቅዱሳን አንዱ ሲሆን የአባ ዮሐንስ አበ ምኔት ደቀ መዝሙርም ነበር። ለአሥራ አራት ዓመታት ሳይቀመጥና ሳይተኛ በመጸለዩ ሰውነቱ አልቋል። መልአከ እግዚአብሔርም "ገድልህን በመጠን አድርገው።" ብሎታል።

ጌታችን ከባልንጀራው አባ አብርሃም ጋር ዘወትር ይገለጽላቸው የነበረ ሲሆን ያቺ በዓታቸው "በግቢግ" ትባላለች። ግብጽ ውስጥ ዛሬም ድረስ አለች።

አምላከ ገዐርጊ ከቅዱስ መንፈሱ ጸጋ ለኃጥአን ባሮቹ ያድለን።

ግንቦት ፲፰ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱሳን ሐዋርያት ወአርድእት
፪.አባ ገዐርጊ ገዳማዊ
፫.ቅዱስ ሲኖዳ ሰማዕት

ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
፪.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
፫.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
፬.ማር ያዕቆብ ግብጻዊ

"በዓለ ሃምሳም የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ። ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው። እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው። በእያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው። በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው። መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።"
(ሐዋ ፪፥፩-፬)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቴሌግራምም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላምና በፍቅር አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ዕርገተ እግዚእ <3

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ዕርገትን ሁለት ጊዜ ታከብራለች። አንዱ "ጥንተ በዓል" ሁለተኛው ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል። ጥንተ በዓል ማለት ጌታችን በትክክል ያረገበትን ቀን ያመለክታል።

የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በኪነ ጥበቡ (በሕማሙ፣ በሞቱ) ዓለምን አድኖ አርባ ቀን ለሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን ትምሕርተ ኅቡዓትን አስተምሯቸዋል፣

በአርባኛው ቀን መቶ ሃያውን ቤተሰብ ይዟቸው ወደ ቢታንያ ወጣ። በዚያም እስከ ሊቀ ጵጵስና ድረስ ሾሟቸው ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡም አዝዟቸው የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ጠብቁ ብሏቸዋል። እየባረካቸው በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማያዊ ዙፋኑ አርጓል።

ሰማያት፣ ምድር፣ ደመናት፣ ነፋሳት፣ መባርቅትና መላእክት ፍጥረት በሙሉ አመስግኗል። አይሁድ መናፍቃን ዕርገቱን ምትሐት ነው እንዳይሉ ጌታችን ትንሣኤውን አማናዊ እንደሆነ ለማስረዳት በአርባኛው ቀን ዐረገ።

አንድም ራስ ባለበት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊኖሩ ይገባልና ጌታችን ዕርገቱን በገሃድ አደረገው። "ዐርገ እግዚእ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን" እንዲል።

<3 ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ።
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን።
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ። <3
(መዝ. ፵፮፥፮)

"እስከ ቢታንያም አወጣቸው። እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ። ወደ ሰማይም ዐረገ። እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ።"
(ሉቃ ፳፬፥፶-፶፫)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

<3 የፍቅር ሐዋርያ <3
ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን "የፍቅር ሐዋርያ" ትለዋለች። ለሰባ ዘመናት በቆየ ስብከቱ ስለ ፍቅር ብዙ አስተምሯል። ፍቅርንም በተግባር አስተምሯል። በየደቂቃውም "ደቂቅየ ተፋቀሩ በበይናቲክሙ - ልጆቼ ሆይ! እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።" እያለ ይሰብክ ነበር።

በተለይ ደግሞ ከፈጣሪው ክርስቶስ ጋር የነበረው ፍቅር ፍጹም የተለየ ነበር። በዚህ ምክንያትም ጌታ ባረገ ጊዜ እንዲህ ብሎታል፦ "ለፍጡር ከሚገለጥ ምሥጢር ከአንተ የምሠውረው የለኝም።"

ቀጥሎም በንጹሕ አፉ ስሞታል።
ሊቁ፦
"ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ
ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ።" እንዳለው።
(መልክአ ኢየሱስ)

ቅዱስ ዮሐንስ ከእመቤታችንም ጋር ልዩ ፍቅር ነበረው። እርሷ እንደ ልጇ ስትወደው እርሱ ደግሞ እንደ እናቱ ልቡ እስኪነድ ድረስ ይወዳት ነበር። እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ ተከትሎ ያገኛት እመቤቱ ናትና።

ከዚያ ሁሉ ጸጋና ማዕረግ የመድረሱ ምሥጢርም ድንግል ናት። ለአሥራ አምስት ዓመታት በጽላሎተ ረድኤቷ (በረዳትነቷ ጥላ) ተደግፎ አብሯት ሲኖር ብዙ ተምሯል። ከመላእክትም በላይ ከብሯል። ከንጽሕናዋ በረከትም ተካፍሏል።

ስለ ድንግል ማርያምም "ነገረ ማርያም" የሚል ድርሰት ሲኖረው "የሰኔ ጐልጐታንም" የጻፈው እርሱ ነው።

ድንግል ባረፈችበት ቀንም ልክ እንደ ልጇ ክርስቶስ እርሷም ስማው ታቅፋው ዐርፋለች። ሊቃውንቱ ለዚህ አይደል በንጹሕ ከንፈሮቿ መሳምን (መባረክን) ሲሹ፦
"በከመ ሰዓምኪ ርዕሰ ዮሐንስ ቀዳሚ
ስዒሞትየ ማርያም ድግሚ።" ያሉት።

ታላቁ ቅዱስ ሐዋርያ ዕድሜው ዘጠና ዓመት በሆነው ጊዜ ተሰውሯል። ከዚያ አስቀድሞም የዓለምን ፍጻሜ ተመልክቷል። ዛሬ ያለበትን የሚያውቅ ቸር ፈጣሪው ነው።
ይህች ዕለት ለሐዋርያው ቅዳሴ ቤቱ ናት።

እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲህ ነው፦
ወንጌላዊ
ሐዋርያ
ሰማዕት ዘእንበለ ደም
አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ)
ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት)
ወልደ ነጐድጓድ
ደቀ መለኮት ወምሥጢር
ፍቁረ እግዚእ
ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ)
ቁጹረ ገጽ
ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ)
ንስር ሠራሪ
ልዑለ ስብከት
ምድራዊው መልአክ
ዓምደ ብርሃን
ሐዋርያ ትንቢት
ቀርነ ቤተ ክርስቲያን
ኮከበ ከዋክብት.....

በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር።

ቅዱስ ዮሐንስን የወደደ ጌታ በፍቅሩ ይጠግነን። ከእናቱ ፍቅር አድርሶ በሐዋርያው በረከት ያስጊጠን።

ግንቦት ፲፮ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ስብከቱና ቅዳሴ ቤቱ)
፪.ቅዱስ ኢያሱ ሲራክ ነቢይና ጠቢብ (መጽሐፈ ሲራክን የጻፈ)
፫.ቅድስት እናታችን ዐስበ ሚካኤል (ኢትዮጵያዊት)

ወርኀዊ በዓላት
፩.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
፪.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
፫.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮጵያ (የቅዱስ ላሊበላ ወንድም)
፬.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
፭.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
፮.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
፯.አባ ዳንኤል ጻድቅ

"በጌታ ኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፣ የእናቱም እኅት፣ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፣ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር። ጌታ ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን 'አንቺ ሆይ! እነሆ ልጅሽ።' አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን 'እናትህ እነኋት።' አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።"
(ዮሐ ፲፱፥፳፭-፳፯)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቴሌግራምም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ቅዱስ ናትናኤል <3

በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ዘግይቶ ሰማዕትነትን የተቀበለ ይህ ቅዱስ ሐዋርያ ነው።

ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእስራኤላውያን ወላጆቹ ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው። ይህ በምን ይታወቃል ቢሉ እርሱ ሕፃን እያለ ሔሮድስ መቶ አርባ አራት ሺህ ሕፃናትን ሲፈጅ እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል። እናቱ በቅርጫት ውስጥ አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው ነበር።

ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም ስምዖን ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ናትናኤል ብሎታል። በባልንጀሮቹ ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን (ገሊላ ቃና አካባቢ ስላደገ) አንዳንዴም ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር። ምሑረ ኦሪት ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር።

በገሊላ ቃና ሰርግ የደገሰው ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል የአጎት ልጅ ነው። ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ የጠራበት አንዱ ምክንያትም ይሔው ነው።

ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን ከገማልያል ተምሮ ከበለስ ቁጭ ብሎ ይተክዝ ነበር። "መሲሕ ምነው ቀረህ?" እያለም ያዝን ነበር። ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን አውቆ በፊልጶስ አማካኝነት ጠርቶታል።

ናትናኤል ለጊዜው ተከራክሮ ነበር። በኋላ ግን የጌታችንን ማንነት በደቂቃዎች ተረድቶ አምኗል። ጌታችንም "ክዳት ሽንገላ በልቡ ውስጥ የሌለበት ንጹሕ እስራኤላዊ" ሲል አመስግኖታል።

ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ከጌታችን እግር ሥር ምሥጢረ መንግሥተ ሰማያትን ተምሮ በጸጋ መንፈስ ቅዱስም ሰክሮ ብዙ አሕዛብን ከጨለማ (ጣኦት አምልኮ) ወደ ብርሃን (አሚነ ክርስቶስ) መልሷል። እጅግ ብዙ መከራንም ተቀብሏል።

የጌታችን ወንድም የተባለ ቅዱስ ያዕቆብ በአይሁድ ከተገደለ በኋላም ቅዱስ ናትናኤል የኢየሩሳሌም ሁለተኛ ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ አገልግሏል። ከአይሁድም ዘንድ ብዙ መከራ ደርሶበታል። በመጨረሻም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት አልፏል። በገድለ ሐዋርያት ላይ እንደተጠቀሰው ቅዱሱ ሰማዕት የሆነው በመቶ ሃምሳ ዓመቱ ነው። ያ ማለት ደግሞ ከሐዋርያት አባቶች በመጨረሻ ያረፈው እርሱ ነው ያሰኛል።

እግዚአብሔር በቅዱስ ናትናኤል ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት ሕዝቦቿንም ከመቅሰፍት ይሰውርልን። ከበረከቱም አይለየን።

ግንቦት ፲፭ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ (ቀናተኛው ስምዖን)
፪.ቅዱስ ሚናስ ባሕታዊ
፫.ቅዱስ ቀርጢኖስ ሰማዕት
፬.አራት መቶ ቅዱሳን ሰማዕታት

ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
፪.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
፫.ቅዱስ ሚናስ ግብጻዊ
፬.ቅድስት እንባ መሪና
፭.ቅድስት ክርስጢና

"ጌታ ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ 'ተንኰል የሌለበት በእውነት የእስራኤል ሰው እነሆ' አለ። ናትናኤልም 'ከወዴት ታውቀኛለህ?' አለው። ጌታ ኢየሱስም መልሶ 'ፊልጶስ ሳይጠራህ ከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ።' አለው። ናትናኤልም መልሶ 'መምህር ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ። አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ።' አለው።"
(ዮሐ ፩፥፵፰-፶፩)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቴሌግራምም t.me/GedleKidusan ላይ ያገኙናል።

Читать полностью…

ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints

እንኳን ለታላቁ ገዳማዊ ቅዱስ አርሳንዮስ (አርሳኒ) ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)
በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

<3 ቅዱስ አርሳኒ <3

ቅድስት ሃይማኖት ዛሬ እኛ ጋር የደረሰችው በበርካታ ሰማዕታትና ጻድቃን ደም ነው። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ግድግዳዎቿ እንጨትና ድንጋይ እንዳይመስሏችሁ። አጽመ ቅዱሳን ነው እንጂ።

ቅዱሳን ልዑለ ባሕርይ ክርስቶስን እንደ እኔ እና እንደ ዘመኑ ትውልድ በከንፈራቸው የሚሸነግሉ አልነበሩም። እነርሱ በፍጹም ልባቸው ስለ ፍቅሩ ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጡ እንጂ። በቅድስናቸው ከተመሰከረላቸው ቀደምት ቅዱሳን አንዱ ደግም ቅዱስ አርሳንዮስ ነው።

ቅዱሱ የተወለደው በ፫፻፵፭ ዓ.ም ሮም ውስጥ ነው። በወጣትነቱ ይህ ቀረህ የማይሉት የጥበብና የፍልስፍና ሰው ነበር። በተለይ በትልቁ የሮም ቄሳር ቴዎዶስዮስ ዘመን በቤተ መንግሥት አካባቢ የተከበረና የንጉሡ ልጆች መምህር ነበር። አኖሬዎስና አርቃዴዎስን ቀጥቶ ያሳደጋቸውም እርሱ ነበር።

በድንግልና እስከ አርባ ዓመቱ ድረስ ሮም ውስጥ ቆየ። ከዚህ በኋላ ግን ስለ ሰማያዊ ነገሮች ሲያስብ መልአኩ በሕልም ወደ ግብጽ ሒድ አለው። በመጀመሪያ ወደ እስክንድርያ ቀጥሎ ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሒዶ መነኮሰ። በቆይታ ግን ብሕትውና ምርጫው ሆነ።

ቅዱስ አርሳኒ በእነዚህ ነገሮቹ ይታወቃል።
፩.በምንም ምክንያት ከማንም ጋር አያወራም። (ለስልሳ ዓመታት በአርምሞ ኑሯል።)
፪.በቤተ መቅደሱ ግድግዳ ተጠግቶ እንባውን ሲያፈስ የእርሱን አካል አርሶ በመሬት ላይ ሲፈስ ይታይ ነበር። ከእንባው ብዛት ቅንድቦቹ ተላልጠው አልቀው ነበር።
፫.በርካታ ድርሳናትን ደርሷል። ብዙዎቹ ዛሬም ግብጽ ውስጥ አሉ።
፬.ሸንጎበቱን ወደ ደረቱ አዘንብሎ ስለሚቆም ማንንም ቀና ብሎ አያይም ነበር።
፭.ለጸሎት አመሻሽ አሥራ አንድ ሰዓት አካባቢ ላይ ይቆምና ጸሎቱን የሚጨርስ ፀሐይ ግንባሩን ስትመታው ነው።
፪.ሁል ጊዜ ራሱን "አንተ ሰነፍ (ሐካይ)" እያለ ይገስጽ ነበር።
፯.በገዳማውያን ታሪክ የእርሱን ያህል በቁመቱ ረዥም አልተገኘም ይባላል። የራሱ ጸጉር በጀርባው የወረደ ሲሆን ጽሕሙ ነጭና እስከ መታጠቂያው የወረደ ነበር።
እነዚህ ግን በጣም ጥቂቶቹ ናቸው።

ቅዱስ አርሳንዮስ አካሉ በተጋድሎ ደቆ ለስልሳ ዓመታት በግሩም መንፈሳዊነት ኑሮ በመቶ ዓመቱ በዚህች ዕለት ዐርፏል።

አምላካችን እግዚአብሔር ከታላቁ የቅድስና ሰው አርሳኒ በረከት አይለየን።

ግንቦት ፲፫ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ አርሳንዮስ - አርሳኒ (ጠቢብ ገዳማዊ)

ወርኀዊ በዓላት
፩.እግዚአብሔር አብ
፪.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
፫.ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት
፬.ቅዱስ አስከናፍር
፭.አሥራ ሦስቱ ግኁሳን አባቶች
፮.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

"የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል። ደግሞ ተገርቷል። ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው አይችልም። የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት ነው። በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን። በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን። ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።"
(ያዕ ፫፥፯-፲)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Читать полностью…
Subscribe to a channel