getamie | Unsorted

Telegram-канал getamie - 📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

608

❄ ግጥም ❄ 💎🅙🅞🅘🅝 👉 @getamie ?🅢🅗🅐🅡🅔 & ̲ 🅘🅝🅥🅘🅣🅔 ur Friends

Subscribe to a channel

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

❤️ እሷ ነች❓

ያለወትሮዉ

ልቤ ይጠይቀኛል

እና

እሷ ነች ?

የተፃፈችልህ

የተናገርክላት

ትመጣለች እያልክ

ዘላለም የጠበቃት

እሷ ነች⁉️


Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚




አንድ ቀን ደዉለሽ  .  እንዴት ነህ
ያላልሽኝ ፣

ዛሬ ሲቸግርሽ  .  በሰማይ በምድር
እያፈላለግሽኝ ፣

ከንፈህ ድረስ  .  ብለሽ  እንዲያ የፎገርሽኝ

የእርዳታ ድርጅት . አሙፑላንስ አረግሽኝ ?


Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚



፦እፈራለሁ



ቃል አይሸርም እንደ ቁስል ፣

አካል ሳይነድፍ ስለሚጥል ፣

ቃል አያልፍም እንደ ዘመን ፣

ቃል ያቀናል... የጠመመን ፡


አሁን አሁን........እፈራለሁ ፣

ልናገር ስል....... አስባለሁ ፣

አስብና… ዝም.እላለሁ ፣

መናገርን ..........እፈራለሁ ፡

ልናገር ስል.........አስባለሁ ፣

አስብና....ዝም.... እላለሁ ፣

መናገርን...........እፈራለሁ ፡


እርሾ ሁኖ የሚያኮፍስ ፣

እሾህ ሆኖ ሚያስተነፍስ ፣

ቃል ነውና ፅኑ ተስፋ ፣

የሚያኖርም የሚያጠፋ ፡፡


ልናገር ስል.........አስባለሁ ፣

አስብና ዝም..........እላለሁ ፣

መናገርን..........እፈራለሁ ።



Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

:

በዛሬ ማሸብረቅ ፡
የሀሴትን ጣራ የነኩ በጃቸዉ ፤

በዛሬ መጨከን ፡ በዛሬ መጨለም ፡
ግራ ለገባቸዉ ፣

ነገን ወዲ ስቤዉ :
ሌላ ቀን መሆኑን እንዴት ላሳያቸዉ ❓


Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^


አናወራዉ ነገር ለሰሚዉ አይገባ

እንዳንፅፈዉ ወዲ ከቃል አይግባባ

ወጌሻ አያ'ሽለን አይ'ለይ ስብራቱ

ሀኪም አያ'ክመዉ የ'ለዉ መዳኒቱ

እንዲሁ እም'ገፋዉ እያ'ልን ደህ'ና ነን

አንዳንድ ህመም አለ ስንሞት
የሚሻለን።

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

የማታ እንጀራ ስጠኝ 🙏



የማታ እንጀራ ስጠኝ

የጠዋት አታስመርጠኝ

ዘግ'ይተህ በኋላ አስጊጠኝ

ማታ  በክብሬ  ደብቀኝ

ከሰዉ በር አንተዉ አርቀኝ

ጉልበቴም  ፅናቱን ይዞ

አቅሜም እንዳቅም  ተጉዞ

ያል'ጠየቁኝን  ሳልመልስ 

መንገዴን  በወግ  ልጨርስ

በአይን  እሳት  አታስገርፈኝ

አመሻሹን  አንተዉ  ደግፈኝ

በጥላ  እንዳል'በረግግ 

በረፋድ  እንዳላጣ  ጥግ

አልጠብቅ እርጥባን ከሰዉ

የማታ' ምግቤን  አርሰዉ

ሲመሽ  አታንበርክከኝ

ሲደክመኝ  ወንዝ  አታሻግረኝ

ሲጨንቀኝ  ከኔ  አትራቀኝ

እንደ ንጋቱ  አንተዉ ጠብቀኝ

አንገቴ  እን'ዳለ  ቀና

የወዳጅ ደጃፍ ሳልጠ'ና

ዘራፍ  እንዳልኩ ያብቃልኝ

ሲጨልም  መንገድ  አቅናልኝ

አደራ ጌታየ አደራ

አትን'ሳኝ የማታ እንጀራ  🙏


🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.................................................


<<< የስራዉን ይስጠዉ >>>

የሚል እርግማንሽ

ደረሰ መሠለኝ

ከሄድሽ ጀምሮ በስኬት ላይ

ስኬት እየተከተለኝ

የአንችን አይነት አሲድ ማየት ከለከለኝ😂


እየሄድሽ..........

...................................................

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

#አልፈጠረብሽም


ፀጉርሽ

አይንሽ

ጥርስሽን

:

:

ነጥየ ያምራል አልልሽም ፤

:

:

ምክንያቱም

:

:

የማያምር ነገር አልፈጠረብሽም ።


😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

👀ማፍቀር እፈራለሁ👀 ! !


ያፈቀረ አምላክ

ሲሰቀል ስላየሁ

ማፍቀር እፈራለሁ

መዉደድ ይከብደኛል

ልክ እንደ ክርስቶስ

እኔም ሰዉ ክዶኛል 💥

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ልብሽ ዝም ብሎ ያለ'ረፍት ይከፋል

በትንሽ ንግግር፣

የዕንባ ዘለላ ጉንጭሽ ላይ ያካፋል

አይዞሽ ይታለፋል፡



አንተስ ወንድማለም

ሰልችቶሀል አለም

ዝለሀል ታመሀል?

ለምን እንደምትኖር አልገባ ብሎሀል?

ባክህን እንዳትወድቅ ባክህ እንዳትረታ

አይዞህ ጠንክር በርታ።


[ ሊጥለን ቢታገል መከራ ገዝግዞን

ልባችን ቢታመም፣

የኛ ካልሆነ ሰው ዕውር ፍቅር ይዞን

ዳግም እንቆማለን ይታለፋል አይዞን:: ]

።።።።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

//////////////////////////////////////////////


ሁሉም ታሪክ አለዉ

በዉስጡ ያመቀዉ

ትንሽ ይሁን ትልቅ

ህመም አሳልፉል

እኛ የማናዉቀዉ

ስለዚ የኔ አለም

መታገስ ልመጅ

ባነበብሽዉ ምእራፍ

ሰዉ ላይ አትፍረጅ



///////////////////////////////////////////////////

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

ታቦቷን አልሸኘሁ

በቅጡ አላወጣሁ

አስራት በኩራቷን

ለበረከት ብየ

መጥረጊያ ጨብጨ

አላፀዳሁ ቤቷን

ብቻ ግን እንዲሁ (2)

ዝናብ ሲመጣብኝ

ልጠለላት ገባሁ

እግሯ ስር ወድጌ

ከዶፍ የመረረ

ሀዘኔን አነባሁ

ብቻግን እንዲሁ

ፀሐይ ሲከርብኝ

አፀዷ አስጠለለኝ

ቀናብየ አየሁት

እነኋት ከአለም ግለት ይልቅ

ፀዳሏ አቃጠለኝ

ለምን አለቀስኩኝ(2)

እንደፈሪ ምርኮ

ፊቷ ተንበርክኬ

ከቅጥሯ በፊት

ሀዘን ያጠላበት

ምን ነበር ታሪኬ

ምን ነበረ መልኬ

እንጃ !

አልክሸ ሲደክመኝ

ጉሮሮየን ጠማኝ

ከፀበሏም ጠጣሁ

ብቻ ወደ ሀሩሩ

ብቻ ወደጎርፉ

ማርያም እያልኩኝ

ካለሁበት ወጣሁ


✍አስታዉሰኝ እረጋሳ

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ጠፋህ  አትበይ ዉዴ  ወዴት እጠፋለሁ ፣

የሚመጥኑኝ  ጋር  ሁሌም  እገኛለሁ ፣

         እዚዉ ነዉ እምኖረዉ

         ሰማይ ቤት  አልሄድኩም

ስልክ እማነሳለት ሰዉ ለየሁ እንጅ

ቁጥሬን አልቀየርኩም  ! !

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
         
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

                                          ✍Abay

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

"""""""""" """"""""""""""""""""""" """"""""""""""


ሂድና ለምናት
👨‍💼
ይቅር በይኝ በላት

እዴ!
💁‍♂
በራሷ ጥፉት

እረፍ ተዉ !
👨‍💼
ያለሷ እማትኖረዉ አንተዉ !


""""""""""""" """""""""""""""" """"""""""""""

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

....................................................

እኔስ ኑሬዋለሁ. . ሲከፉኝ. . ሲደላኝ ፣

🫄 ከእንግዲህ ተወልዶ ፥ 🤰

👫 ሰዉ . . ለሚሆን ይብላኝ ! ! 🧍‍♂

....................................................

✍ሎሬት ፀጋየ ገ/
መድህን

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

አፌ ባይናገር  : ቢያጣ የሚለዉ ፣

ይነግርሽ ነበረ : አይኔን ብታይዉ ፣

እኔም አይናፋር ነኝ ፡ አንችም ዝምተኛ ፣

ፍቅሩን ማን ይናገር ፡ ማን ይሁነን ዳኛ ❓


💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

!!!

ነፍሰህ ሰትወጣ ፡ ሲጋደም እሬሳህ፣

ስጋህ ሳይቀበር : ሰዉ እንደሚረሳህ፣

ባታዉቅ ነዉ እንጅ !

ብታዉቅ እማ ኑሮ ፡ ስለ ሁሉም ነገር ፣

የሰዉ አስተያየት ፡ አይገርምህም ነበር !!


"
a

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚



ሳቅ ሳቅ ይጠራል ፡ ሲሉ ሰምተን ፣

መጭዉን ፡ችግር ፈርተን ፣

ነገን ከነገ ወዲያን ፡ በእንባ እንዳንዘልቀዉ

ፈርተን ነዉ የምንስቀዉ ።

😁➕😁➕😁➕😁➕😁➕😁

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

ተይ!

አሁን እንደ ድሮ
ሁሌ አላገኝሽም

የልቤዉ ይቅር ባይኔ
እንኳ አልጠግብሽም

ድምፅሽን አልሰማ
አላየዉ ሳቅሽን

እንዴት ነዉ ምረታዉ
ዉዴ
ናፍቆትሽን

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

መሄዱን ከወደድሽ

አትሂጅ አልልም ፣

መጥቸ አልወስድሽም ፥

ስልክም አልደዉልም ፤

እኔ ህልሜን እንጅ ፥

ሴት
አልከተልም ።

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.........ዘንግተኸው እንጂ.......



ከዚጋ ስትከንፍ ከዚያ ጋር ስትበር፤

እንደምጠብቃት - ተናግሬ ነበር።

እየጠበኩሽ ነው - በቃሌ ጸንቼ ፤

ስትመጪ ማፈርሰው - ትዳር አበጅቼ፡፡

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡


ደካከመኝ መሰል !


ሄድኩኝ ስል መሰበር ፣

ቀና አልኩ ስል ዘምበል ፣

ደካከመኝ መሰል.....


ማረፍን ተመኘሁ ማሰብ ማቆም ላፍታ ፣

ከድፍርስ ማንነት ከህሊና ሁካታ ፣

ከልቤ ተመኘሁ ማያቆም ዝምታ ….....


ከሚለዋወጥ ሳቅ ከሚደርቀው እንባ ፣

ከኑሮ ግርግር ተንኮልና ደባ ፣

መሞትን ተመኘሁ ገነትም ባልገባ .......


ለማላቀው እድሜ በጭንቀት መወጠር ፣

ለምን እንዲ ሆነ እያልኩኝ መቃጠል ፣

ደካከመኝ መሰል ..

ከኑሮ ትግል ጋር

የሚገለግለኝ ተዐምር ቢመጣ ፣

ምድር ሳትቀደድ

ሰማይ ሳይከፈት ከዚ አለም ብወጣ ።

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

#አልፈጠረብሽም


ፀጉርሽ

አይንሽ

ጥርስሽን

:

:

ነጥየ ያምራል አልልሽም ፤

:

:

ምክንያቱም

:

:

የማያምር ነገር አልፈጠረብሽ ።


😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦


ይብላኝ !!!

ለተራበች

ልጇን ላጣች እናት

ይብላኝ ! ! !

ለዛች እህት

ክብሯ ለጠፋባት

       አወ !

ይብላኝ !!!

የዘመን ድካሙን

ለተቀማ አባት

በጫካ በዱሩ

ለመከነዉ ወጣት

አዋጊዉ እማ ይሄዉ

ተቃቅፎ ታረቀ

ሟች አጥንቱ ሳይፈረስ

ገዳዩ ቦረቀ !!!



💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

||||||||||||||

🪞 ምነዉ በሞትሽልኝ



አንችን እንደሸኘሁ

ልክ እንደሄድሽልኝ

ሰላሜን አገኘሁ

ምነዉ በሞትሽልኝ


አለ አንዱ የመረረዉ


|||||||||||||

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

ታቦቷን አልሸኘሁ

በቅጡ አላወጣሁ

አስራት በኩራቷን

ለበረከት ብየ

መጥረጊያ ጨብጨ

አላፀዳሁ ቤቷን

ብቻ ግን እንዲሁ (2)

ዝናብ ሲመጣብኝ

ልጠለላት ገባሁ

እግሯ ስር ወድቄ

ከዶፍ የመረረ

ሀዘኔን አነባሁ

ብቻግን እንዲሁ

ፀሐይ ሲከርብኝ

አፀዷ አስጠለለኝ

ቀናብየ አየሁት

እነኋት ከአለም ግለት ይልቅ

ፀዳሏ አቃጠለኝ

ለምን አለቀስኩኝ (2)

እንደፈሪ ምርኮ

ፊቷ ተንበርክኬ

ከቅጥሯ በፊት

ሀዘን ያጠላበት

ምን ነበር ታሪኬ

ምን ነበረ መልኬ

     እንጃ !

አልቅሸ ሲደክመኝ

ጉሮሮየን ጠማኝ

ከፀበሏም ጠጣሁ

ብቻ ወደ ሀሩሩ

ብቻ ወደ ጎርፉ

ማርያም እያልኩኝ

ካለሁበት ወጣሁ ።

        
                   ✍አስታዉሰኝ እረጋሳ

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

A፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤b
A።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።y



ስትወጅኝ ወደድኩሽ _  ይቅር ስትይ ቀረ

       ካንች  መምጣት በፊት

ህይወቴን  የኖርኩት _ ያላንች ነበረ ።



A።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።b
            
A፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤y

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

~~
~

ትቆይ  ጥሩ  ነዉ

ብትሄጅ  አይገደኝም



  ከመኖርሽ  በፊት

የኖርኩትን ህይወት

መድገም አይከብደኝም

~
            ~
                                                 
Abay

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ፍቅርማ ክፉ ነዉ ።

እራስን ያስታል ፡ ቀልብ እያሰከረ ፣

በየአደባባዩ

ዝም ብለሽ ፡ ስስሚኝ ፡ ደስ ይለኝ ነበረ ፣

አሁን ግን ፈራሁኝ ፡ ልቤ ስጋት ፡ ገባዉ ፣

ጀመርኩኝ ፡ መብሰልሰል ፣

መሳም ያበዛሽዉ ፡ ልክ እንደ ፡ይሁዳ ፣

ልሸጭኝ ነዉ መሠል ! !


።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

እቴ  ...........

       ምንም ብትዋቢ ምንም ብትቆነጅ ፣
        
     አድናቂ ክፉ ነዉ .. አድናቂ አትዉደጅ ፣

እሚደነቅ አበባ .. 🌹

ታይቶ አይታለፍም ይቀጠፋል እጅ ።🥀

❣❣❣❣❣❣❣❣❣❣❣❣

Читать полностью…
Subscribe to a channel