getamie | Unsorted

Telegram-канал getamie - 📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

608

❄ ግጥም ❄ 💎🅙🅞🅘🅝 👉 @getamie ?🅢🅗🅐🅡🅔 & ̲ 🅘🅝🅥🅘🅣🅔 ur Friends

Subscribe to a channel

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.




ጌታየ
.

በሰነፍ ጭቃ እንደተለወስኩ

የክፉት ጣሙን በአፌ እየቀመስኩ

በስተት መንገድ እየተጓዝኩኝ ስርመጠመጥ

ከፈጣሪየ ፍጡር ስመርጥ

ሳላመዛዝን የበደል ልኬን

ሳልታጠበዉ የሀጢያት መልኬን

ከቤቴ ደረስክ ተንኳኳ ደጀ

ና  ክፈት አልከኝ : እኔ ነኝ ልጀ

ፈራሁኝ በጣም ዉስጤን ጨነቀዉ

ሰዉ ያላየዉን የወንጀሌን ልክ ስለምታቀዉ


            :::::::::::::::

            ፈራሁ !


          ይቅር በለኝ 🙏



👉@ getamie

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.



በተኛበት ቀርቷል : ስንቱ ጀግና ጉልበት
ከእንቅልፌ ስነቃ
አጥልቁልኝ ሀብል

ምክንያት

ለህልም መሞት ማቃት
ማሸነፍ ነዉ እና
ሰላም አድሮ መንቃት

እሱ ብቻ አይደለ......

አየዋለሁ ብሎ የአዳምነት ወጉን
ላብ አደሩ ሁሉ
ከዋለበት ሜዳ ወድቋል ጥግ ጥጉን
ስለዚህ ስንተኛ
አስጊጡን በጉንጉን

ምክንያት

ማሸነፍ ነዉ እና ሰላም
ወጥቶ
መግባት

.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


ከዚ ሁሉ ግራ ዉጥንቅጡን ካጣ

ከለቀቀ ነገር

ሰዉ ሁን ብለሽኛል

እዴት ነዉ ሰዉ መሆን ?

ቤት ? መኪና ? ሊያዝ ጥሩ ትዳር ?

ወይስ ለአንድ ነፍሴ ገዳም ሂጀ ልቅር?

ከደሙ ንፁ ነሽ . ..ከሁለት ነሽ አንች ሰዉ

ምርጫሽን ንገሪኝ

ሰዉ መሆን እንዴት ነዉ ?



.

@getamie

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


አብረሽኝ እያለሽ :

ቀን ሌሊት ለፍላፊ : ወሬኛ እንዳልነበርኩ

ጥለሽኝ ስትሄጅ ድምፄን ከፍ አርጌ

      አለሁ ማለት አፈርኩ።

ከልቤ መዉጣትሽ : የቀየረኝ ባንዴ

ፍቅር ብየ ሳስብ : ይዞኝ የነበረዉ

        ሰይጣን ይሆን እንዴ ?


.

🙏 join 👉 @getamie

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

አውቀዋለሁ
       :

አንደበትሽ እንጅ

ሚናደድ ሚቃጠል

መኖር ጣዕም አጥቶ

የሚነሳሽ አመል

         :

የምትናገሪኝ በቁጣ

     ቃል ፊደል

የኔ ውብ የኔ  አለም

    የ ም ት ኳ ረ ፊ ኝ

ናፍቄሽ ነው አይደል ?




ኤልያስ ሽታኹን

👉
@getamie

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


ሂወት ማለት አጭር

ሂወት ማለት ትንሽ

ሂወት ማለት ድንገት

በሆነበት አለም

ሚወዱትን መራቅ

ሚመስል ሞት የለም


.🙏 join & sher ur friends

👉
@getamie 🙏

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


ተስፉ 🔅
........



      ለፉሁ  ሞከርኩ

ጨበጥኩት ስል አሟለጨኝ

ያባዘነኝ ያባከነኝ ሙከራየ ሁሉ ቆጨኝ

ተስፋ አልቆርጥም ከሚል በቀር

ተስፋ እራሱ ተስፋ አሳጣኝ

ቃል ብቻዉን ተስፋ አይሆንም !

ተስፋየ ነዉ እንዲ የቀጣኝ

በተስፋ ነዉ የምኖረዉ

ያለዉጤት ያላንዲት ድል

ምን ሁኘ ነዉ እኔ እራሴን

በይሆናል እምበድል?


        በቃ!


በቃኝ !  መጥረቢያየን ሞረድ ሞረድ

ይህን ተስፋ ግንድስድስ

ይህን ተስፋ ከስር ጎረድ

         አረኩና

ያለተስፋ ስኖር ስኖር

ያለተስፋ ስጓዝ ስጓዝ

ምስቅልቅል ነዉ መቸም አለም

ዝብጥልጥል ነዉ የጊዜ ጓዝ

እንዴዉ ድንገት

አዲት ፍሬ

ያልወለደች የሌላት ባል

ተስፋየ ነሽ የምትባል

ልክ እንደኔ ተስፋ ቆርጣ

ነገን ትታ

ህልም አርጣ

በመንገዴ መንገድ ዘጋች

በመንገዷ መንገድ ዘጋሁ

በአርምሞዋ ከኔ አደረች

በዝምታ ከሷ ነጋሁ

ሳናወራ ተረዳዳን

ሳንናገር ተዋሀድን

መኖር ደጉ !

ህልም ሰጠን

ተስፋ እሚባል ልጅ ወለድን

ይዞ መጣ አዲስ ህይወት

ይዞ መጣ አዲስ እድል

ከዛ ወዲህ

ሙሉ ሆንኩኝ

ከተስፋየ የማልጎድል ።

.


🙏 join & sher ur friends

👉
@getamie

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

..


የፍቅር ፀብ


ባብሮነታችን ውስጥ

ጥላቻ ባይኖርም መናናቅ ነበረ

በናናቃችን

መለያት መጣ - አብሮ መኖር ቀረ

አብሮ መብላት ቀረ

አብሮ መዋል ቀረ

አብሮ ማደር ቀረ

ቀረ

ቀረ

ቀረ

ሁሉ ነገ ሲቀር - ናፍቆት ተጀመረ

በናፈቅሽኝ ጊዜ - እንዲህ ስል ነበረ

እንኳን ተለያን - እንኳን አብረን በላን

እንኳንም ናፈቅሽኝ - ፍቅር ነው ያጣላን።

ባብሮነታችን ልክ

መናናቅ ልብ ላይ - ያኔ የተሰቀለ

አሁን የሚታኝ

ናፍቆት የምንለው - ናፋቂ ፍቅር አለ።

እንኳን †ለያን!


..

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

-

ባንቺ እና በኑሮ ናላየ እየዞረ

እንኳን እኔ ቀርቶ ምኞቴም ሰከረ

እናልሽ አለሜ………….....

በሰከረ ምኞት. . ሰባራ ልብ ይዤ

እጠብቅሻለሁ……........

አልመጣም ብለሽኝ . .በፍቅርሽ ደንዝዤ



join &sher ur friends
@getamie
@getamie

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

:

ከኔ ጋር መታየት
ከሰዉ ካሳነሰሽ

ያዉልሽ መንገዱ
ሂጅ ወደ ፈለገሽ

እኔ የባህር ዳር ልጅ
ቀብራራዉ ጎጃሜ
ጣጣ አለኝ መሰለሽ !

:
#join &sher ur friends
@getamie
@getamie

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.       

            ማር ብየሽ ነበረ

ማር'ማ እኔ ነኝ ካንቺ የበለጠ

       ብትስሚኝ ጊዜ

አይኔ እንደ ጧፍ በራ ሰም ልቤም ቀለጠ



.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

ጨረቃ


……………………………………

ለብቻዋን ሳያት

በድቅድቅ ጨለማ ከዋክብት ሳይከቧት ፣

እኔን ትመስላለች

ብቻዋን የቀረች.....ማንም ሰው የሌላት ።

በቀናት መካከል----ጨረቃ ስትጎድል ፣

እሷንም እንደ እኔ ከፍቷት ነው ሚመስል ፣

ጠፍታለች ለሚሏት ..... አለሁኝ የምትል ።

እንዲ ናት ጨረቃ

አንዳንድ ጊዜ ደሞ.ጭራሽ ትቀራለች ፣

እኔንም አንድ ቀን

ሞት እንደሚወስደኝ....ታስታውሰኛለች ።

እንዲ ናት ጨረቃ

በሰማይ ሸራ ላይ መልኬን ትስላለች ፣

አስተውዬ ሳያት....እኔን ትመስላለች ።




#በረከት_ዘውዱ

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


ልሳምህ  አትበይኝ መሳም እፈራለሁ ፣

ተስሞ ተሽጦ ተሰቅሎ አይቻለሁ !


.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

∞


የዘንድሮ ፈረስ፣ አይቀድመም ጋሪዉን
አታውቀዉምና፣ ሒያጅና ቀሪዉን፣
አልሰማውም አትበል፣
እያነባህ ጠብቅ፣ መርዶ ነጋሪዉን።


-
sher &
join

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

:

አወ እሱን ቀን

አወ ከቀን የምወደዉ
አምጦ አልቅሶ አንችን
የመሰለች ለኔ የወለደዉ ።

አወ እሱን ቀን

ከወንድ አይን ያስመለጠሽ
ለኔ ብቻ መርጦ የሰጠሽ

አንችን ከሰዉ የጋረደዉ
አንችን ከኔ ያጋመደዉ
አወ እሱን
እሱን ቀን ነዉ የምወደዉ

እሱን ሰዐት
እሱን ቅፅበት
አንችን ያገኘሁበትን
እያሰብኩ ዘከርኩበት
:
ስለት ሰጠሁበት
ነዳይ መገብኩበት
ድዉይ ጠየኩበት
መቅደስ ቀረብኩበት
:
ይሄዉ ፀደኩበት

"ምን አግኝቶ"ይላል ነፍሱ ያልታደለ
አንችን ማሰብ ገነት ሳቅሽ ፅድቅ አይደለ?

:

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

።



"የሰዉ ፊቱ ሳይሆን ፡ ቢታይ ኑሮ ሆዱ

አይተዉ ባፈቀሩ : መርጠዉ በወደዱ"



፡

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


ቀን ሳወራሽ ዉዬ

የልቤን ለልብሽ
         
            ድብርት ወረረኝ

             አመሻሽ ላይ ሳጣሽ

ቀን ከሌት ባወጋሽ

አይናይንሽን እያየሁ

             ከቶ መች ጠግቤሽ

              መች ሰለቻለሁ


.
👉
@getamie

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫



አንችማ ክፉ ነሽ

መናፈቄን አዉቀሽ

ይለይለት ብለሽ

በህልሜ እኳ ቀረሽ !

🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።


የጠዋት ፀሐይ ነሽ ፤ ታይተሽ ምታሞቂ

የፀሎት መፅሐፍ ነሽ ፤ ከልብ የማትርቂ

አንች ስላለሽ ነዉ ፤ ያለሁት እወቂ !



።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
join 👉
@getamie

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

°



መሞቴ ነዉ ! 😭
°°°°°°°°°°°°


መሞቴ ነዉ ያልኩሽ

የስጋ ሞት አይደል

መሞቴ ነዉ ያልኩሽ

የነፍስ ሞት አይደል

መሞቴ ነዉ ያልኩሽ

ከዚ አለም መሄድ

መሠናበት አይደል

መሞቴ ነዉ ያልኩሽ

እንቅልፍ ነዉ ሞቴ

ስላስጨነቀኝ ነዉ

ተኝቸ እስክነቃ ካንች መለየቴ !


°
🙏 join & sher ur friends

👉
@getamie 👌

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

......'..'..... [ ' ' ]
....

ከመጥፎ ቀን ይልቅ

መጥፎ ሰዉ ይከብዳል ፤

ደስታህን በመንጠቅ

አንገት ያስደፋሃል ።

..............

🙏 join & sher ur friends

👉
@getamie 🙏

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.



እሱን ብሎ ህሊና
........................................


ሳገኛት የት ነበርክ

ስቀጥራት የት ነበርክ

ስስማት የት ነበርክ

ጉድለቷን ስሞላ

ጉድለቴት ስትሞላ

ችያት ተሸክሚያት

የኔን እሷ ችላ

አንተ ስትመጣ

አንተ አጉል መካሪ

እንዲህ አይደለም ባይ

ከሳሽ አስተማሪ

ብቻ ብቻችንን

ደርሰህ እምትጋረፍ

ነፍስ እና ስጋየን ደርሰህ ምታኳርፍ

የት ነበርክ ሳገኛት

የት ነበርክ ስቀጥራት

የት ነበርክ ስስማት

ከሷ ጋራ ስሆን

አላዉቀዉ እግዜሩን

አይደለም ህጎችን እነዛን አስሮቹን

ስደሰት ስታየኝ

ሲሆን ሳትነግረኝ

ካለፈ በኋላ

ለምን የምትለኝ

አንተን ብሎ ህሊና

እ ና ት ን ና !



.

🙏 join & sher ur friends

👉
@getamie

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

-


መጣላት አለና

ሚስጥር አትናገር

:

መታረቅም አለና

ክፉ አትናገር

:

በዚህ አለም ስትኖር

ሚሻለዉ ነገር

ብዙ ማዳመጥ ነዉ

ብዙ ከመናገር ።


🙏 join & sher ur friends

👉
@getamie

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

-


ዛሬም እንደ ሁሌ

ቀኔን ልትረብሽ

በሀሳቤ መጠሻል

እኔን ምን አገባኝ

አለቃሽ አረቂ

ባናት ባናቱ ላይ ይቸለስብሻል

..........

join & she ur friends

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.

እንደ ልጅነት
ትዝታ
እንደ ትልቅ ሰዉ
ሰላምታ
እንደ ፍቅርኛ
ጨዋታ

እንደ ሚወደድ
ዝምታ
እንደ ሚናፈቅ
እርጅና

እንደ ሚጣፍጥ
ህፃን አፍ
እንደ እናት ቀሚስ
ወይ በራፍ

እንደ ዝናብ ቀን
ሩጫ
እንደ አባት መዳፍ
ማምለጫ

እንደዛ ያለ
ስሜቴ
ልቤን አተራመሰው

:

መባሉን እንጃልኝ
እንጂ
እግዜር ናፈቀኝ
እንደሰው።




✍ኤልያስ ሽታኹን

@getamie
@getamie
@getamie

.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

ግማሽ ሰው🧏‍♂



ልክ እንደ ጨረቃ.ማንም ሰው ያላየው ፣

የተሸፋፈነ.......ሰው ግማሽ ጎን አለው ፣

በማስመሰል አጥር.......ቢሆን የታጠረ ፣

ሰው ሌላ ሰው አለው...ውስጡ የታሰረ ።




#በረከት_ዘውዱ

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

አስደግማብኝ ነው❗️❗️

...
አስደግማብኝ ነው...

ለነ ጥላ ወጊ ለመጫኛ ነካሽ

ለነ አፍዝ አደንግዝ ለዱር ቅጠል በጣሽ

ላውልያ ለጠንቋዩ ለኑግ ቂጣ ቆራሽ

ለመንገድ ገርጋሪ ለውቃቢ ዘራሽ

ለገሃድ ስውሩ ለነ ጽናት አፍራሽ

ለምድር ላየሩ ለየሎስ አጎንባሽ

ለባህር ለየብሱ ለጠቋሪት ደጋሽ

አስደግማብኝ ነው

ወለም ያላለኝን ዘላለም የምታሽ

አስደግማብኝ ነው...


© ✍ሰለሞን
ሳህሌ

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


የአበቦችን መርገፍ
እያየህ አትክሰም

የፈጠነ ሁሉ
የአለምን ሩጫ
ፍፁም አልጨረሰም

ተማር ከነበረዉ
ተማር ከወደቀዉ

ምናልባት እንደ እድል
የወደፊት ምኞት
ነገ ነዉ የሚያልቀዉ ።


.
😭

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

"

አምሮበታል ብሎ
ቢነግራት አንድ ሰዉ

ንዴት ጨርቅ አስጣላት
ቦርዷን አቃወሰዉ

ትበድ የታባቷ
ህመሜን ትቅመሰዉ

በምድር የበደለ በምድር
ሲቀጣ ነዉ የልብ የሚደርሰዉ!

"

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

አንዲት ሴት ነበረች


ልክ እንደጉሽ ጠላ አ 'ሰ' ሩ እንደ ሚታይ

ቱ! ልላት ነዉ መሰል ሰፈፍ አለች ከላይ።


,

Читать полностью…
Subscribe to a channel