getamie | Unsorted

Telegram-канал getamie - 📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

608

❄ ግጥም ❄ 💎🅙🅞🅘🅝 👉 @getamie ?🅢🅗🅐🅡🅔 & ̲ 🅘🅝🅥🅘🅣🅔 ur Friends

Subscribe to a channel

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

....

ለሚጠሉኝ ሰወች

ሺ ጊዜ ቢጠሉኝ

እኔ ምን አገባኝ

የራሴ ስራ ' ንጂ

በራቸዉ አይደለም

ገነት
የሚያስገባኝ

።

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.

ሞት ነዉ የሚለየን.......ለመባባላችን

እባክሽ እንደ ፍቅር . . .አይርከስ ቃላችን

ወይ አብረን እንሁን

ወይ እንሙት አንዳችን.............


.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


ባላቅሽ .. እስከምል ባላየሁ

ላንች ስል . . ስንት ቦታ ታየሁ


እንጃልኝ ዘንድሮ መክረሜን

አግኝቸሽ በረታሁት ህልሜን


,

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

የሳት እራት


እንደ ታቦት ዙራኝ ቆመች ፤

ትድን መስሏት . . ተጠግታኝ ተሳለመች ።

እኔ ክፉ ሲያዩኝ መብራት

እሷም ትንኝ የሳት እራት !!

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.

" ይሄ ሁሉ ገጥሞት

እንዴት ቀረ ሳይሞት ? "

ይሉኛል እላለሁ

እኔ ምን አቃለሁ......?



.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

///


ልንሞት እኖራለን !

መልሰን ልንተኛ ፣

ደግሞ እንነሳለን ፣

መጥለቅ ላይቀርላት ፣

ፀሐይ የምትወጣዉ ፣

ጎህ ሲቀድ ጠብቃ ፣

የምታጮልቀዉ ፣

ከምስራቅ ጀምራ ፣

እከም ምዕራብ ድረስ ፣

ህይወት የምትዘራዉ ፣

ሀይሏን የምሰጠዉ ፣

በነፀብራቆቿስ የምትማርከዉ ፣

ከቶ ለምንድን ?

ብቅ ካለችበት ከተገኘችበት ፣

መመለሷ ላይቀር ፣

ተስፉየማትቆርጠዉ ፣

ደግሞ የማትሰንፈዉ ፣

የሷ መኖር እኮ ፣

ለሌሎች ነዉ እንጅ ፣

ለሷ ትርጉም የለዉ ፣

የኛ መኖር እኮ ፣

ለሌሎች ነዉ እንጅ ፣

ለኛ ትርጉም የለዉ  !!


///

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

❤️ እሷ ነች❓

ያለወትሮዉ

ልቤ ይጠይቀኛል

እና

እሷ ነች ?

የተፃፈችልህ

የተናገርክላት

ትመጣለች እያልክ

ዘላለም የጠበቃት

እሷ ነች⁉️


።

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

〰


አንድ ቀን ደዉለሽ  .  እንዴት ነህ
ያላልሽኝ ፣

ዛሬ ሲቸግርሽ  .  በሰማይ በምድር
እያፈላለግሽኝ ፣

ከንፈህ ድረስ  .  ብለሽ  እንዲያ የፎገርሽኝ

የእርዳታ ድርጅት . አሙፑላንስ አረግሽኝ ?


〰

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

፡

፦እፈራለሁ



ቃል አይሸርም እንደ ቁስል ፣

አካል ሳይነድፍ ስለሚጥል ፣

ቃል አያልፍም እንደ ዘመን ፣

ቃል ያቀናል... የጠመመን ፡


አሁን አሁን........እፈራለሁ ፣

ልናገር ስል....... አስባለሁ ፣

አስብና… ዝም.እላለሁ ፣

መናገርን ..........እፈራለሁ ፡

ልናገር ስል.........አስባለሁ ፣

አስብና....ዝም.... እላለሁ ፣

መናገርን...........እፈራለሁ ፡


እርሾ ሁኖ የሚያኮፍስ ፣

እሾህ ሆኖ ሚያስተነፍስ ፣

ቃል ነውና ፅኑ ተስፋ ፣

የሚያኖርም የሚያጠፋ ፡፡


ልናገር ስል.........አስባለሁ ፣

አስብና ዝም..........እላለሁ ፣

መናገርን..........እፈራለሁ ።



፡

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

:

በዛሬ ማሸብረቅ ፡
የሀሴትን ጣራ የነኩ በጃቸዉ ፤

በዛሬ መጨከን ፡ በዛሬ መጨለም ፡
ግራ ለገባቸዉ ፣

ነገን ወዲ ስቤዉ :
ሌላ ቀን መሆኑን እንዴት ላሳያቸዉ ❓


፡

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^


አናወራዉ ነገር ለሰሚዉ አይገባ

እንዳንፅፈዉ ወዲ ከቃል አይግባባ

ወጌሻ አያ'ሽለን አይ'ለይ ስብራቱ

ሀኪም አያ'ክመዉ የ'ለዉ መዳኒቱ

እንዲሁ እም'ገፋዉ እያ'ልን ደህ'ና ነን

አንዳንድ ህመም አለ ስንሞት
የሚሻለን።

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

የማታ እንጀራ ስጠኝ 🙏



የማታ እንጀራ ስጠኝ

የጠዋት አታስመርጠኝ

ዘግ'ይተህ በኋላ አስጊጠኝ

ማታ  በክብሬ  ደብቀኝ

ከሰዉ በር አንተዉ አርቀኝ

ጉልበቴም  ፅናቱን ይዞ

አቅሜም እንዳቅም  ተጉዞ

ያል'ጠየቁኝን  ሳልመልስ 

መንገዴን  በወግ  ልጨርስ

በአይን  እሳት  አታስገርፈኝ

አመሻሹን  አንተዉ  ደግፈኝ

በጥላ  እንዳል'በረግግ 

በረፋድ  እንዳላጣ  ጥግ

አልጠብቅ እርጥባን ከሰዉ

የማታ' ምግቤን  አርሰዉ

ሲመሽ  አታንበርክከኝ

ሲደክመኝ  ወንዝ  አታሻግረኝ

ሲጨንቀኝ  ከኔ  አትራቀኝ

እንደ ንጋቱ  አንተዉ ጠብቀኝ

አንገቴ  እን'ዳለ  ቀና

የወዳጅ ደጃፍ ሳልጠ'ና

ዘራፍ  እንዳልኩ ያብቃልኝ

ሲጨልም  መንገድ  አቅናልኝ

አደራ ጌታየ አደራ

አትን'ሳኝ የማታ እንጀራ  🙏


🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.................................................


<<< የስራዉን ይስጠዉ >>>

የሚል እርግማንሽ

ደረሰ መሠለኝ

ከሄድሽ ጀምሮ በስኬት ላይ

ስኬት እየተከተለኝ

የአንችን አይነት አሲድ ማየት ከለከለኝ😂


እየሄድሽ..........

...................................................

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

#አልፈጠረብሽም


ፀጉርሽ

አይንሽ

ጥርስሽን

:

:

ነጥየ ያምራል አልልሽም ፤

:

:

ምክንያቱም

:

:

የማያምር ነገር አልፈጠረብሽም ።


😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

👀ማፍቀር እፈራለሁ👀 ! !


ያፈቀረ አምላክ

ሲሰቀል ስላየሁ

ማፍቀር እፈራለሁ

መዉደድ ይከብደኛል

ልክ እንደ ክርስቶስ

እኔም ሰዉ ክዶኛል 💥

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


አላዉቅም ፡ የት ፡ እንዳለሁ ፣

አንችን ፡ ስፈልግ ፡ እኔ ፡ ጠፍቻለሁ ።


.
♻️

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

ስጠኝ !!!


ጠዋት በባዶ ሆዴ

እንደ  ወጉ ፁሜ

ነጠላ አደግድጌ

በሩን ተሳልሜ

ከገባሁ በኋላ

ምን እንደምፀልይ ፤ እረሳሁ ይቅርታ

      በቃ እንደዉም ፀለይኩ

ምን እንደ ምጠይቅ ፤ ፀሎት ስጠኝ
ጌታ

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

ሲሞት!

ደረት መቺ አፈር ዘጋኝ
የጨከነ ሁሉ አዛኝ

ሲሞት!

ካርታ ቁማር ገባ ወጣ
እራት ምስር እስኪመጣ
ጋቢ መልበስ ድንኳን መጣል
ወጪ ማብዛት አልፏል ሲባል

ሲኖር!!

ኑሮ ከብዶ ሲደቁሰው
ሚቀምሰው አቶ ሆድ ሲብሰው
የረገጠው ሁሉ ሲመክን
ያዝኩት ያለው በኖ ሲመን
አይዞህ ያላለው በድን ስጋ
ሞተ ሲባል ያርዳል ሰንጋ

።።።።።።

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

'

ወዳጀ ሰንፈሃል

ለብቻህ መታገል ልትለምድ ይገበሃል

ሰዉ አይታመንም ስሞ ይሸጥሃል

ሰምተሃል !!!

.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

❤.


ታጥበንም  ፡ ፁመንም ፣

ለምነን ፡ ባይሰጠን ፣

እግዜርን ፡ ሰታቢዉ ፤

በማግኘት ፡ በለጠን ።

ሰጭዉ ማነዉ ??     አልን .......

ተያቂ  ፡ ወዳጁ ፣

በመንሳት ፡ የቀጣዉ

ለካ .......

ለታረዘዉ ፡ ልጁ ፣

መንግስቱን ፡ ሊሰጥ ፡ ነዉ ፦

ዳግም የሚመጣዉ ።


❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

፡


እኔም ነይ አልልሽ . .አንችም አትመጭም

በዛሬዉ በደልሽ . . ባላዉቃት እያልኩኝ

በከንቱ አልቆጭም

ፈጣሪ በልኬ . . ሰርቶ የተመነሽ.........

ልቤን እንድትሰብሪ . . መርጦ የከወነሽ

ተወዳጅ ጥፋቴ . . ምርጧ ስህተቴ ነሽ ።

:

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

አፌ ባይናገር  : ቢያጣ የሚለዉ ፣

ይነግርሽ ነበረ : አይኔን ብታይዉ ፣

እኔም አይናፋር ነኝ ፡ አንችም ዝምተኛ ፣

ፍቅሩን ማን ይናገር ፡ ማን ይሁነን ዳኛ ❓


💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

!!!

ነፍሰህ ሰትወጣ ፡ ሲጋደም እሬሳህ፣

ስጋህ ሳይቀበር : ሰዉ እንደሚረሳህ፣

ባታዉቅ ነዉ እንጅ !

ብታዉቅ እማ ኑሮ ፡ ስለ ሁሉም ነገር ፣

የሰዉ አስተያየት ፡ አይገርምህም ነበር !!


"
a

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

።

ሳቅ ሳቅ ይጠራል ፡ ሲሉ ሰምተን ፣

መጭዉን ፡ችግር ፈርተን ፣

ነገን ከነገ ወዲያን ፡ በእንባ እንዳንዘልቀዉ

ፈርተን ነዉ የምንስቀዉ ።

😁➕😁➕😁➕😁➕😁➕😁

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

ተይ!

አሁን እንደ ድሮ
ሁሌ አላገኝሽም

የልቤዉ ይቅር ባይኔ
እንኳ አልጠግብሽም

ድምፅሽን አልሰማ
አላየዉ ሳቅሽን

እንዴት ነዉ ምረታዉ
ዉዴ
ናፍቆትሽን

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

መሄዱን ከወደድሽ

አትሂጅ አልልም ፣

መጥቸ አልወስድሽም ፥

ስልክም አልደዉልም ፤

እኔ ህልሜን እንጅ ፥

ሴት
አልከተልም ።

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.........ዘንግተኸው እንጂ.......



ከዚጋ ስትከንፍ ከዚያ ጋር ስትበር፤

እንደምጠብቃት - ተናግሬ ነበር።

እየጠበኩሽ ነው - በቃሌ ጸንቼ ፤

ስትመጪ ማፈርሰው - ትዳር አበጅቼ፡፡

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡


ደካከመኝ መሰል !


ሄድኩኝ ስል መሰበር ፣

ቀና አልኩ ስል ዘምበል ፣

ደካከመኝ መሰል.....


ማረፍን ተመኘሁ ማሰብ ማቆም ላፍታ ፣

ከድፍርስ ማንነት ከህሊና ሁካታ ፣

ከልቤ ተመኘሁ ማያቆም ዝምታ ….....


ከሚለዋወጥ ሳቅ ከሚደርቀው እንባ ፣

ከኑሮ ግርግር ተንኮልና ደባ ፣

መሞትን ተመኘሁ ገነትም ባልገባ .......


ለማላቀው እድሜ በጭንቀት መወጠር ፣

ለምን እንዲ ሆነ እያልኩኝ መቃጠል ፣

ደካከመኝ መሰል ..

ከኑሮ ትግል ጋር

የሚገለግለኝ ተዐምር ቢመጣ ፣

ምድር ሳትቀደድ

ሰማይ ሳይከፈት ከዚ አለም ብወጣ ።

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

#አልፈጠረብሽም


ፀጉርሽ

አይንሽ

ጥርስሽን

:

:

ነጥየ ያምራል አልልሽም ፤

:

:

ምክንያቱም

:

:

የማያምር ነገር አልፈጠረብሽ ።


😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦


ይብላኝ !!!

ለተራበች

ልጇን ላጣች እናት

ይብላኝ ! ! !

ለዛች እህት

ክብሯ ለጠፋባት

       አወ !

ይብላኝ !!!

የዘመን ድካሙን

ለተቀማ አባት

በጫካ በዱሩ

ለመከነዉ ወጣት

አዋጊዉ እማ ይሄዉ

ተቃቅፎ ታረቀ

ሟች አጥንቱ ሳይፈረስ

ገዳዩ ቦረቀ !!!



💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧

Читать полностью…
Subscribe to a channel