getamie | Unsorted

Telegram-канал getamie - 📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

608

❄ ግጥም ❄ 💎🅙🅞🅘🅝 👉 @getamie ?🅢🅗🅐🅡🅔 & ̲ 🅘🅝🅥🅘🅣🅔 ur Friends

Subscribe to a channel

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.



እወድሃለሁ ብየ ነግሬህ ባላቅም

እዉነቴን ነዉ አባ ባንተ ቀልድ አላቅም !

እወድሃለዉ አባ ❤️




Long life for fathers.

.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

[ ]



" እመጣለሁ "ብሎ ፡ እንደሄደዉ እሱ

እኔም " መጣሁ " ብየ ፡ ቀረኹ ከመቅደሱ ።

ግን ግን ይለያያል . . . .

'' እመጣለሁ " ተብሎ ፡ የሚገባዉን ቃል

ፍጡር ሲዘነጋ ፡ አምላክ ይጠብቃል ።



[ ]

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

~ ~



ያ ቀን. . . . . . .

ላየዘልቀን አስተዋወቀን . . . . . . .




~
~

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


ያኔ ልጅ እያለሁ ፡ በህፃን አንደበት ፧

ለላይኛዉ አምላክ ፡ በፀሎት ለመንኩት ፦፡

የጓዴን መጫወቻ ፡ አይነት ብትሰጠኝ ፡

አንተን አመስግኘ ፡ እኔም ደስ ባለኝ ፦፡

.............ብየ ጠየኩት

................ለመንኩት. ......

ዳሩ

መልሴን እስከማገኝ ፡ ብጠብቅ ከበሩ ፧

ደቂቃወች አለፉ ፡ ሰዓት ተቆጠሩ ፦ ፡

በሌለኝ እርጋታ . . . . . ....

ትንሿን ፀሎቴን ፡ ቢያልፋት በዝምታ ፧

የጓዴን ሰርቄ ፡ ቀና ብየ . . .አልኩት. . .

🙏ይቅር በለኝ ጌታ



.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


ሰዉ ፈለኩኝ

ሰዉ አጣሁኝ

ልጠገዉ ስል ከኔ ይርቃል

ከሰዉ ጋራ ሰዉ ለመሆን

ሰዉ መሆንን ይጠይቃል

ከሰዉ በራፍ አንጋጠጥኩኝ

ተዘግቶብኝ የእዉነት በር

እስከዛሬ ስፈልገዉ

ለካ ያጣሁት እኔን ነበር   🤔


.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.

ሳምባን ይጨርሳል

ጨጓራን አቃጥሎ

ሲጃራ ክፉ ነዉ

ከሴት ልጅ ቀጥሎ 😳😃



.😉

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


አብደሀል ተብየ ፡ ፀበል እስክነከር

ይሁዳን አየሁት  : ብየ ስከራከር

ሀሰት እንዳይመስለዉ ፡ ህዝበ ምዕመኑ

ና : ................... : አይተዉህ ይመኑ




.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.

ጊዜ ነዉ አሉ . . . . .

አመቻችቶ ሰጠዉና

ላንተ ይሁን አለዉ እና

የማይሆን ነገር ሆነ

ቅል በድንጊይ ላይ ጀገነ


.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


እኔ ሞኝ አይገባኝ ስቀሽ ስትጠጊኝ!

በጀርባዬ ሆነሽ እንደምትወጊኝ!

እኔ እማልጠረጥር፡

የሚጠጋኝ ሁሉ መስሎኝ ባልንጀራ!

ፈገግታሽ ስላቅ ነው ሳቅሽ አለው ሴራ!

.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


ንገሩልኝ ዘመድ        

ንገሩልኝ ወገን

እኔ በሷ ፍቅር

እንዴት እንደምሆን       

  

እኔ ቃል ጨረስኩኝ

ያችን ልጅ ንገሯት

ልክ እንደ ነፍሱ ነዉ

የሚወድሽ በሏት !!


                                 


✍


@getamie
@getamie
.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.......

    ሆድ ሲብስ ሲከፋን

    መሄጃ ሲጠፋን

    እንደ ወጀብ ሆኖ ሰዉ ሁሉ ሲገፋን


ከአበቦቹ ማሳ ፅጌሬዳ ቀጥፎ

አይዟቹህ የሚለን እንደ ህፃን አቅፎ

    
        ግን አንድ ሰዉ አለ .  .  .  .

   እሱ ሰዉ ናፈቅሁት አምጡልኝ የታለ ?


.......

@getamie
@getamie

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

አስተዉል



ስትማር የሰዉን ልክ ታዉቃለህ

ስትኖር የሰዉን ባህሪ ትረዳለህ

ስትቸገር የሰዉን ክፋት ትለያለህ

ስትደሰት አጨብጫቢህን ትመለከታለህ

አየህ ካስተዋልክ ከሁሉ ትማራለህ



.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.



አይጣል


በቀን የወደቀ ቢሄድ አጎንብሶ

አንድ ቀን ይነሳል በቀን ተመልሶ

በሰዉ የወደቀ አይቀርም ተንቆ

በፈጣሪ ይነሳል ጊዜዉን ጠብቆ

ያን ጊዜ ነዉ መፍራት ያኔ ነዉ ሰቀቀን

አንሽ ስለማይኖር እግዜር የጣለ ቀን


-----------------------/ /---------------------
@getamie



.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.

"ያለቅጥ ዝምታ ለበግም አልበጃት
አስራ ሁለት ሆና አንድ ነብር ፈጃት"

.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.3


በርቱማ ፮ ቦረን 1፩፤ ሁለቱ ወንድማማት 1፯ ልጆች
ወለዱ ።
የበርቱ ልጆች እኒህ ናቸው፤ ከረዩ፣ መረዋ፣ ኢቱ፣ አክቹ፣ ወረነሻ ፣ ሁበና ናቸው፡፡
የከረዩ ልጆች ስምንት ናቸው፡፡ ሊበን፣ ሜጫ፣ ትሎማ፣ ወሎ፣ ጅሌ፣ አቦ ፣ ሉባ፣ በላአ ።
የመረዋ ልጆት ፬ ናቸው ወርድያን፣ አሩሲ ፣
ኢቱ፣ ጥሙጋ ናቸው::

ወርድያን ፫ ይወልዳል አና፣ ኡር፣ አበጢ እኒህ
ሁሉ የመረዋ ልጆች በኃይልና በብዛት ከሁሉ ይበልጣሉ፡፡

የኢቱ ልጆች ፪ ናቸው፡፡ ጅሌ እና ሱባ፡፡ የአከቹ ልጆች ፪ ናቸዉ። ጅንጉር እና ጩፋ ናቸው።

የወረነሻ ልጆች ፰ ናቸው ሶዶ፣ አቡ፣ ጫቡ፣ ይሉ፣ ጉድሩ፣ ኩታይ ፣አምሩ፣ ሁሮ ናቸው፡፡

የሁበና ልጆት ፫ ናቸዉ ። ራያ፣ አዘቦ እና ሀሸንጌ ናቸው::

ከነዚህ የሜጫ ልጆች ከኦሮሞ ቤት ሜጫ ከታላላቆች ተነስተው በኢትዮጵያ ንጉሥ የጌታ አደሩ፡ ንጉሱም አጤ ዓምደ ጽዮን ነው::

እርሱም በመልካም ተቀብሎ በጣና ባሕርና በዳሞት መሀከል አሰጣቸው፡፡ እነርሳቸው ያን አገር ተቀብለው ያዙና ስሙን ባባታቸው ስም ሜጫ አሉት፡፡

ከዚህ በኋላ ክርስትና ተነስተው አብያተ ክርስቲያናትን
በተቀበሉት አገር ሁሉ ሠርተው ክርስትያኖች ሆነው ተቀመጡ፡፡
በአማራ ሕዝብ መሀከል ኦሮምኛን ፈጽመው አጥፍተው በአማርኛ ቋንቋ ብቻ ይናገራሉ።



join & sher

👇

@getamie

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.......




እዉነትን መናገር ጥላቻ ቢያስከትል

አድር ባይ መሆኑ ህሊና ቢያቆስል

አዉጥቸ አዉርጀ

ወሰንኩኝ ዝም
ልል


✅

......

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.



የምተክዝበት

የምቆዝምበት. . . . .

የማዝንበት ቦታ ፡ ባጣ የማርፍበት

ሀሳብ ክንፍ ሰጠኝ ፡ በሱ በረርኩበት

ክንፍ ማለት አንች ነሽ

ትዝታዬ እንዴት ነሽ . . . . ?!


.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.



ላፍታ ብዘነጋሽ ፡ ለጋነቴን ፈጀሁ ፧

ጠዋት እረስቸሽ ፡ ማታዉን አረጀሁ ፧

መልዐከ ሞት መጣ

ቆመ ፡ ከቤቴ በር

ለካ አንችን መናፈቅ ፡ ያለመልም ነበር።



'

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

💔



ያልፋል አይደል?


ከሰዉ ቁጥር ሳልቆጠር

በጨርቄ ቅድ እንደተፉኝ

በተረፈኝ ባለኝ ዘመን . . .

አለሁ ያሉት እንዳለፉኝ ።

በድክመቴ ከወጉኝ ጋር

በአንድ ማዕድ መቋደሴ

ሆድ ሲገዛኝ በጠሉኝ ፊት

ነገም እርቦኝ መመለሴ


ያልፋል አይደል?


የሰዉ እግሮች እኔን ሽሽት

በአዲስ መንገድ መሄዳቸዉ

ጨርቃቸዉን እንዳፀዱ

ሰፍ ብየ ያቀፍኳቸዉ

የማወጋዉ ሲናቅብኝ

የማዉቀዉ . . . ሃቅ ' ለጠፋብኝ

ያልፋል አይደል መገፍተሩ

ከሚያስገምት ከሆድ በላይ

በሰዉ ልሳን መሰበሩ።


ያልፋል አይደል?


ሁሉም ያልፋል በእግዚያብሔር ቀን

ከሚያወጋን ድካም ጋርዶ

👆መኖሩ አይደል የጠበቀን!




💔

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.

ካልተገኘሽ እማ ፣ ካላየሁሽ ዳግም

ከብቸኝነት ጋ  ፣ በቃ ልሂድ ላዝግም

ሰዉ ከሚወደዉ ጋ ፣ አድሮማ ካልዋለ

ፍቅር ከነአካቴዉ ፣ ቢቀርስ ምን አለ😒



.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


ይሄዉልሽ ስሚ !

ይወደኛል የሚል ወሬሽን አቁሚ

ወፍዘራሽ ስንደዶ

የማንም... ልቅምቅም ቅራሪ

ምናባሽ ስለሆንሽ

ይወደኛል ብለሽ የምትናገሪ ?



.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


አብደሀል ተብየ ፡ ፀበል እስክነከር

ይሁዳን አየሁት ብየ ስከራከር

ሀሰት እንዳይመስለዉ ፡ ህዝበ ምዕመኑ

ና ፡ __ _ ፡ አይተዉህ ይመኑ




.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


ይሄዉልህ ዘመዴ......

አንዳንዴ.......

ወዳጅ ያልከዉ ሲርቅ

የቅርብ ያልከዉ ሲሸሽ

ትናንት የሳቀልህ

ዛሬ አይቶህ ሲረበሽ

ይረዳኛል ብለህ የተማመንክበት

ሞራልህን ጥሎ ሲረማመድበት

እያየህ መክረሙ ከባድ ነዉ ህመሙ




ተነስ!


.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


  ንገሩልኝ ዘመድ   ንገሩልኝ ወገን 🙏

 እኔ በሷ ፍቅር  እንዴት እንደምሆን    

 እንደተዋለበት ጤናዉን እንዳጣ

በጠላ አስተናግር በጥብጦ እንደጠጣ

ያስለፈልፈኛል __ 😞

ጩህ ጩህ ያሰኘኛል __

የቀኑ ሳይበቃዉ ሌሊት ያዞረኛል

.

.


    እኔ ቃል ጨረስኩኝ ፤ ያችን ልጅ ንገሯት

  ልክ እንደ ነፍሱ ነዉ ፤ የሚወድሽ በሏት !


                                 


✍


@getamie
@getamie
.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.

ይሄዉልሽ አንዳንዴ

ሽበት ያለዉ ሁሉ ሽምግልና አይዳኝም

ያፈቀረ ሁሉ ፍቅሩን አያገኝም

የሚሮጠዉ ሁሉ አይሆንም አንደኛ

ይሄዉልሽ አንዳንዴ

እንደዚ ነን እኛ


.


@getamie
@getamie
@getamie

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.



ድሮ አብረዉ ሳይኖሩ ሳያገባት በፊ.....ት

ከመሬት ስትወድቅ ድንገት አደናቅፏት

'' ልደፋልሽ '' ብሎ እጇን እንዳሊያዛት

ካገባት በኋላ የራሱ ሲያደርጋት

ድንገት እመንገድ ላይ እንቅፋት ቢመታት

ትንሽ እራመድ ብሎ አይት እንዳረጋት

'' እያየሽ አትሄጅም '' ? ብሎ ገለመጣት

...
😞😞😞😞😞😞😞😞😞

ይሄን ይመስላል ከትዳር በኋላ የሚከሰተዉ ነገር😊

@getamie
@getamie
@getamie

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.


ሰዉ


በሰዉ ያላደገ ሰዉ ያልቆነጠጠዉ ፤

ሰዉም ሰዉ አያደርግ

እሱም አይሆንም ሰዉ ፤


.
@getamie
@getamie

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.

አምሐራ ፦


አምሐራ ሶስት ጥንተ መሰረቶች ያሉ ነው።

ቀዳሚው ጥንተ መሠረቱ ፦ ከከለዳውያን ከጥንተ ሜስጴጦሚያ ፡ የሚመዘዘው ፡ የአጋዚያን የቀደምት ሳባዊያን እና ሕማርያዊያን የሚመዘዝ ማንነት ነው ።

ነገደ ዮቅጣን ፡ የሚባለው ይህ ነው ።

በተጨማሪ ደግሞ የጥንተ እስራኤላውያን ዘር ያለው ነው

ይህ ደግሞ ከንጉስ ሰሎሞን ዘመን ጀምሮ የተዋሐደ ሲሆን የአምሐራ ነገስት ሐረግ የሚመዘዘዉ ከዚ ነዉ።

ሕዝቡም የጥንት እስራኤላዉያን ደም ያለዉ ሲሆን
በእምነት እና በባህል ከዛ ከመጀመሪያዉ ሙክራብ ዘመን የሚቀዳ ማንነት አለዉ።

እነዚ ሴማዉያን ናቸዉ ። ሌላዉ ደሞ የቀደምት አገዉ ማንነት ነዉ።

ቀደምት አገዉ የሚባለዉ ጥንት የነበረ እና አሁን በጥንተ ዉሕደት ወደ አምሐራ ማንነት እና ዘመናዊ አገዉ ማንነት ያደገ ነዉ።

ይሁዳ የሚባለዉ ነገድ እንጅ ሐይማኖት አይደለም።

መድሐንያለም እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ከእናቱ ከድንግል ማርያም በስጋ ከይሁዳ ነገድ የተገኘ ነዉ።

ዮቅጣን እና አብርሐም ከኤቦር እንደመወለዳቸዉ ሁለቱም ከ አንድ ግንድ ናቸዉ ።

ነገር ግን ፦አምሐራ ፡ ከሁለቱም ከዮቅጣንም ከአብርሐምም የተገኘ እንደመሆኑ የዮቅጣን ዘር ብቻ አይደለም።

መታወቅ ያለበት ነገር ፡ እስራኤል - ሲባል የዛሬዎች ከአዉሮፖ ከመላዉ አለም የተሰባሰቡ አይሁዶችን ማለት ሳይሆን ፣ የነሱ ሁሉ ጥንት አያቶች የነበሩ የንጉስ ሰለሞን የንጉስ ዳዊት ዘመን እስራኤላዉያንን ነዉ።

የዛሬወቹ አሽከናዚ እና ሴፉርዲ አይሁዶች ከነጭ አዉሮፖዉያን ጋ የተዳቀሉ ናቸዉ።

ከነሱ በላይ እኛ ዘንድ የጥንት እስራኤላዉያን ባህል እምነት እና ስመልቦና አለ።

ለምሳሌ ከኛ በቀር በመላዉ አለም የታቦተ እስራኤል አምልኮ እና ትርክት ያለዉ የለም ።

ነጠላችን ላይ ያለዉ ጥለት እና ቁጭት ሳይቀር የጥንተ እስራኤላዉያን ሕብራዉያን የአምልኮ ባህል ነዉ።

ይቀጥላል. . . .

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

.

እኔ ቃል ጨረስኩኝ ፣ ያችን ልጅ ንገሯት
ልክ እንደ ነፍሱ ነዉ ፣ የሚወድሽ በሏት !

.

Читать полностью…

📚📖 እኔ ካነበብኩት📖📚

የኦሮሞ ነገድ ፦ ክፍል - 2


ፈረንጆች ስለኦሮሞ የጻፉት በራስ እውቀትና በምርምር ነው፡፡
እኛ ግን ካገሩ ውስጥ የሚገኘውን አዛዥ ጢኖ የጻፈውን ታሪክ አይተን ነው፡፡


ኦሮሞዎች ሲመጡ በገላኔ ወንዝ መጥተው ሆር ውላቦ በሚባልአገር ገቡ፡፡

በሆር ውላቦ ዋናተኛ በዋና የሚቆርጣትና የሚሻገራት ትንሽኩሬ ባሕር አላት፡፡
ኦሮሞዎች አባታችንና ፍጥረታችን ከዚህ ወጣን ይላሉ፡፡

ስለዚህም ኡሜን ውላቦ ባቴ ይላሉ፡፡ ይህም ከውላቦ ውሃወይም ባሕር ፍጥረት ወጣ ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ኦሮሞዎች ለውሃ ይሰግዳሉ፡፡ ሰውም እንስሳም ከዝያች ውሃ አይጠጣም hልክል ነው፡፡

ኦሮሞ ሁሉ ከዚያ ለውሃዶቱ ይሰግዳል፡፡ ከዚያ ብዙ ሰንጋ ፍሪዳ በግ ፍየልም ያርዳሉ፡፡

በሆር ውላቦ ልዩ ቋንቋ ያላቸው ጥቂት ሕዝብ አሉ፡፡ደራስ ይባላሉ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ይመስላሉ፡፡ ከሲዳሞ እስከ ውላቡ ፬ ቀን ከውላቡ እስከ ቦረን ፭ ቀን ያስኬዳል፡፡

ስለ ኦሮሞ ትውልድ የኦሮሞ ትውልድ እንዲህ ነው፡፡

ኦሮሞዎችሁለት ነገድ ናቸው፡፡

በርቱማ እና ቦረን ይባላሉ፡፡ ወንድማማች ናቸው ።

join &sher ur friends

👇

@getamie
@getamie

Читать полностью…
Subscribe to a channel