.
መሄድ እየቻልኩኝ - ሳልሄድ በመቅረቴ
በቃ ልል ሲገባኝ -ዝም በማለቴ
ማቆም እያለብኝ - ሳ'ላቆም በተዉኩት
ብዙ ነዉ በህይወቴ - ዋጋ የከፈልኩት
.
.
አትሄድም ብዬ
አትሄድም ብዬ
ጎጆየን ላሰፋ ግድግዳ ስገፋ
አትሄድም ብዬ
ጥሪት ላጠራቅም ቆሎ ስቆረጥም
አትሄድም ብዬ
የብቻ ጎጆየን ሰዉ ልመጅ ስላት
ቡናዉ ሳያከትም ካፊያዉ ሳያባራ
ከአጠገቤ አጣኋት
በል ተከት ልቤ
ማግኘት ነበር ጣሩ
ማጣት ምን ይደንቃል
እንኳን በጅ ያሊያዙት
ጥሬ ካፍ ይወድቃል
✍ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
.
.
ጓደኛ አላችሁ?
ከአይን አይቶ የሚረዳ
ሚስጥረኛ የራስ ጓዳ
በዉጣ ዉረድ በፈተና
ሳይዝል ሳይሸሽ የሚፀና
ጓደኛ አላችሁ?
አቅም ሲዝል ጉልበት ሁኖ
በኛ መቻል ቀድሞ አምኖ
ወቅሶ ከሶ አሞጋግሶ
ስንቸገር ቀድሞ ደረሶ
ሚያበረታ ኩራታችን
ጓ'ዳችን ነዉ ጓደኛ'ችን
:
በሐዘንም በደስታችን ❤️❤️❤️
.
🎮🎮
.
ያውቃል የልቦናን መልስ አለው በጊዜው
አያደርግ ይመስል ለምን ነው ትካዜው?
በእኛ ጊዜ ላይሆን የፈጣሪ መልሱ
ባለበት እስኪሰጥ አምናቹ ታገሱ
.
✆
ምን_ይልሻል_ልብሽ# ?
ልጠይቅሽ እስኪ
አድምጭኝ
አንድ አፍታ
ልብሽ ምን አይነት ነው
ለኔ ያለው ቦታ?
የመውደድ የማፍቀር
ወይስ ሀዘኔታ?
ምን ይልሻል ልብሽ
እስኪ አንዴ ጠይቂው
እውን ከልብሽ ነው
ሳገኝሽ በደስታ
ሁሌም የምትስቂዉ
ውይስ ፍቅሬን አውቀሽ
በኔ ይሁን እንዴ #የምትሳለቂው?
☞ getamie
✉✉✉
~
........ጎዶሎ በረከት.......
◉
ሁሉም በጊዜ...
ሁሉም በተራ ፣
መንገድ ሲያበጃጅ
ዕድሜ ሲሰራ ፣
ዘንቦ ሲያባራ...
(መሽቶ ሲነጋ) ፣
እግዜር በሰጠኝ
የመኖር ፀጋ፣
(በወፍ ዝማሬ....
በዛፎች ጥላ...
በሰማይ ውበት )፣
ያንቺ ፈገግታ ቢጨመርበት ፣
ምን ነበረበት?!
.
በባርኮት መሀል...
በፀጋው መሀል...
በ'ሱ በረከት...
(በ'ሱ ስጦታ...)
በቅዱስ ቦታ ፣
(በዚህ መካከል)
ሳቅሽ ቢታከል...!
ይባረክ ነበር....
ህይወቴ ሁሉ ፣
(ሀሴቴ ፍፁም...)
ደስታዬ ሙሉ !!
ይሆን ነበረ፣
(በነበር ቀረ!)
◈
በተፈጥሮ ክር ውበትን ጠልፎ፣
ከመኖር ጓዳ መውደድ ጨልፎ፣
(ለነፍሴ ምጣድ የመና ድፎ....)
እግዜር ሲያድለኝ......፣
('ሞላሁ' እንዳልል)
ሳቅሽ ጎደለኝ።
.
''
- ወደ ገነት የገባዉ የመጀመሪያዉ ሰዉ
ወንበዴ ነበረ
- ወደ ሲኦል የወረደዉ የመጀመሪያዉ
ሰዉ
የጌታ ሐዋርያዉ ነበረ
- ስለዚህ፦
ልጥጨነቁ የሚገባዉ እናንተ በሰዉ አይን
ማን እንደሆናችሁ ሳይሆን
- በፈጣሪ አይን እኔ ማነኝ ብላችሁ
መሆን አለበት።
,,
.
ዘወትር ማለዳ : ከአጥቢያየ ደብር
ከሊቀ መላኩ : ከአደኩበት መንደር
በ ' ግሬ ስመላለስ : እግዜሩ ስላየኝ
ፅድቄን ቆጠረና : ካንች ገላገለኝ
ተመስገን🙏
.
.
ወዴት ሄዱ ብለን የማንጠይቃቸዉ
ከመኖር ድርሰት ላይ ያጎዳደልናቸዉ
በዘመን ሽግግር ታልፈዉ ያልተረሱ
በሕይወታችን ሰርክ የሚመላለሱ
እልፍ ገፆች አሉ ጎ 'ለዉ ያጎደሉን
እንደዘበት ጠፍተዉ ትዝታ ያደሉን
.
.
አሜን በሉ!
ደጃፍ ላይ እንደ ስጥ ሽሮ
የበጋ ፀሐይ ያንቃቃሽ
ጥላሽን እንደ ዘረጋሽ
ተቃጥለሽ ለመ'ሞት ያብቃሽ
እድሜሽን የለፋሽበት
በሰከንድ ይጉደል ማዲጋሽ
ነፍስ ይማር የሚል ለሞትሽ
ዘላለም አይምጣ ደጋሽ
ከሲኦል ተፈናቀይ
ወደ ከፋዉ ሲኦል ያ'ንጋጋሽ
ተርበሽ ልትጎርሽ ስትይ
አልችልም ይበል መንጋጋሽ
አሜን በሉ!
አቃጥላት የቀጨኔ አድባር
ሜዳ ላይ አድርጋት ለማኝ
ምላሷን ቁርጥ አድርገዉ
ለሰወች ስለምታማኝ
አይቅናት እየለመነች
ክትፎና ቅቅል
ቀን'ም ሙሉ ጊዮርጊስ ዉላ
ስሙኒም እንዳትሸቅል !
ግንባሬን ላብ አጠመቀኝ
ደከመኝ ብዙ ለፍልፌ
በድንገት ብንን አልኩና
ነቃሁኝ ከሞት እንቅልፌ
በስመ አብ በወልድ
ህልም ነዉ?
ልተኛ እንቅልፍ እባክህ
ብትወስደኝ ዳግም ምናለ
በሷ ላይ ያለፈለፍኩት
የቀረኝ እርግማን አለ
አሜን በሉ
✍ አስታዉሰኝ ረጋሳ
@getamie
.
.
.
እረስቸሽ ነበር
እረስቸሽ ነበር
ጥለሽኝ ስትሄጂ
ማ ነበረች ፍቅር
ብለዉ ሲጠይቁኝ
አስታወስኩሽ እንጅ
እረስቸሽ ነበር
ከትዝታሽ ሸክም
እርሜን ልገላገል
አዲስ ሰዉ ለመዉደድ
ለመልመድ ስሞክር
አስታወስኩሽ እጅ
እረስቸሽ ነበር !
.
💟
ያማል በጣም
አብሮ ከርሞ መለያየት
እልፍ አስቦ ባጭር መቅረት
በ'ሰዐታት በደቂቃ
ሁሉም ቀረ በቃ ?
እረሳነዉ ተዉነዉ የምር
ጥቂት የለም የሚያፋቅር
አለቀብን ስንት ነገር እንዳልሆን
ሀዘን ደስታን አብረን አልፈን
ያማል በጣም
ቢሆንም ግን አንድ ችግር
ያንን ፍቅር አያሳጣም
ባይኖር እንጅ ከጅምሩ
አለት ፍቅር እንዴት ብሎ
ይሸበራል በጠጠሩ
ባይሆን እንጅ የልብ ቃል
በአንድ ጀንበር መች ያበቃል?
✍
.
👀
እንዳንተላለፍ
ጊዜ ወደ ሁላ
እኔ ወደ ፊት ሳልፍ
ስከንፍ ሲ'ሳፈፍ
ሲከንፍ ስ'ንሳፈፍ
ብቻ ግን ይሄ እንከፍ
ብቻ ግን ይሄ እንከፍ
እሱም ሲክለፈለፍ
እኔም ስንከረፈፍ
እሱም ወዲያ ሲሄድ
እኔም እንዲሁ ሳልፍ
እንዳንሸዋወድ
እንዳንተላለፍ
ባይሆን ተገናኝተን
ተያይተን እንለፍ 🕐 👀
.
,
ሀፅያተኛ ተብላ : ፍርድ ተጥሎባት
የግ'ዜሩን ባላቅም : ሰዉ ቤቱን ዘግቶባት....
አለም ተገልብጦ : ፊቱን አዙሮባት
ከሰዉ ተነጥላ :ሰዉ እንዳታይ ሆና
ተጥላ አልከፋትም : ትኖራለች ደ'ና
አይጎረብጣትም - የወደቀችበት
አይቆረቁራትም የተገፋችበት
ዝም ብላ መኖርን -እንዴት ቻለችበት
ልሂድ ልጠይቃት - ህግን ተሻግሬ
ምን ይገባኝ ይሆን - እሷን አናግሬ
ተስፋ አለ በዉስጧ . . . . .
ነገን ጥበቃ ነዉ ዛሬ አቀማመጧ
ወድቃለች ስትባል እሷ ተነስታለች
ሞታለች ተብላ ይሄዉ ትኖራለች
ፀሀይ ተከልክላ እሷ ትበራለች !
ኡፍፍ....
አብሬአት በኖርኩኝ....
ምን እንደሚሰማት የልቧን ባወ'ኩኝ
እኔ አስለቀሰችኝ- 😭
ታሳዝነኛለች!
ሀፅያተኛ ሆና ልብ ትሰብራለች
✍ yohannes fikade
.
.
ጥላሞት
(shadow)
አንድ ጥያቄ አለ
ነብሴን ሁልግዜ
የሚያብሰለስላት
ገሀድ የማይገልጠው
ማነው የኔ ጠላት?
ማነው እንቅፋቴ
ጉድባ ለመንገዴ
ሌላ አካል አለ
ወይስ ክፉ ገዴ?
ማነው ከነብሴ ጋር
ያረገኝ ባላንጣ
ህዋው ነው ጠላቴ
ወይስ ክፉ እጣ?
ጀርባዬን ለህልሜ
ማነው ያሰጠኝ ሰብ
ወይስ አቅቶኝ ነው
ተስኖኝ ነው ማሰብ?
ማነው ማነው ማነው?
በዳይ ስጋ ችሮኝ
'ሚያስረግም ዕለቴን
ሬት ሆኖ ኑሮ
'ሚያስናፍቀኝ ሞቴን
ማነው ማነው ማነው?
ስደምር ስቀንስ
ስመትር ስለካ
እኔ ፊት የቆምኩት
ራሴው ነኝ ለካ።
ይሄን ያወቅሁኝ ቀን
ይሄ የገባኝ 'ለት
ፊት የቆመው እኔን
ገለል አረግሁለት።
አሁን ጸሐይ ወጣ።
✍️Æ
.
. 👄አፍና ልብ❤️
🙅♂ አፌን አትመኝው አንዳንዴ ይዋሻል
🤥 በመግደርደር ብዛት እውነትን ያሸሻል
❤️ ልቤ ግን ሞኝ ነው ትንሽ ብትቀርቢው
ሁሉም ይታይሻል
💓ከሌላ አብልጦ አንቺን እንደሚወድ
በደንብ ይነግርሻል።❤️🔥
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝
✍️
=
አይ ጊዜ ደጉ 🕔
ሰው ከኔ ሲለየኝ
ያመንኩት ሲርቀኝ
መሄጃው ሲጨንቀኝ ብሶቴ እየናረ
እንዴት እሆን እያልኩ ስፈራ ነበረ
:
:
:
ለካ ጊዜ ደጉ ለሁሉም ይደርሳል
እምባዎች ያብሳል
ቁስል ይፈውሳል
ፈጠነም ዘገየም ሁሉንም ያስረሳል።
✍getamie
☞ @getamie
.
///
አባቴ ሆይ ማረኝ
በዋልክበት ቦታ
ባደርክበት ሁሉ
አብሬህ አድሬ ፤
ለኔ የሆንከዉን
መከራና ስቃይ
በመሳም ቀይሬ ፤
የ ማ ት ደ ፈ ረ ዉ ን
አንተን የደፈርኩህ ፤
በ 30 ዲናር
በብር የቀየርኩህ
ከሞተልኝ በላይ
ገንዘብ ያታለለኝ ፤
ይሁዳ ነኝ እኔ
አባቴ ሆይ ማረኝ 🙏
///
የዳዊት ልጅ ማረኝ 🙏
///
@getamie
.
እዛዉ ሁኝ !!
መሳቅ መጫወቱ
መቅበጥ መላፋቱ
ሁሉም ባይደክመኝም
ዉሸት ምን ያረጋል
አጠገቤ ሁነሽ
ናፍቀሽኝ አታዉቂም
አሁን ስትለይኝ
ከአካባቢየ ሳጣሽ
ከጎኔ ስትርቂ
ሁኜልሽ አረፍኩት
ቀልድሽን አስታዋሽ
ሳቅሽን ናፋቂ
አብረን ባለን ጊዜ
መች እንዲ ሁኛለሁ
ስሜሽ ባልጠግብ እንኳ
ስትሄጅ እረሳሁ
ጥርሴን መች አይተሽዉ
ካንች ጋር እያለሁ
ቀልድሽን እያሰብኩ
አሁን እስቃለሁ
አትፈልጊኝ በቃ
ቅሪብኝ አትምጭ
ናፍቆት መርጫለሁ
ያሻሽን ምረጭ
እንገናኝ ካልኩሽ
እምቢ በይ ግዴለም
አንችም አትመኝ
ናፍቆት ደስ ብሎኛል
በቃ እዛዉ ሁኝ
❣❣
.
.
ሽ ሽ ት
አሁን በቀደም ለት
መጣች ተቀበልኳት
አወጋች አመንኳት
ብዙ ብዙ አለችኝ
የትም ከርማ መታ
የሄደችበትን ምክንያት ነገረችኝ።
ትክክል ነሽ አልኳት
ባትሆንም ግድ የለኝ
ከመመለሷ እንጂ፣ ከመሄድ ምን አለኝ።
,
🫠
ፍቅረኛ ካለችህ : ያንን እብድ አትናቀዉ
ሊጠቅምህ ይችላል ፡ ታሪኩን ጠይቀዉ
ያሳለፈዉ ህይወት ፡ ከባህር ቢሰፋም
ለማበዱ ምክንያት አንዲት ሴት አጠፋም
✔️
.