“ድሆችን እናስብ ዘንድ ብቻ ለመኑን፥ ይህንም ደግሞ ላደርግ ተጋሁ።”
— ገላትያ 2፥10
'ለድሆች የማይራራ አዲስ ፍጥረት የሆነ ክርስቲያን መባል አሳፋሪ ነው'
በስራችን እንደማንፀድቅ ብናውቅም, ምንም አድርገን እግዚአብሔርን impress ልናደርገው
እንደማንችል ብናውቅም እነጴጥሮስ ለጳውሎስ እንዳሳሰቡት ጳውሎስም ቀድሞም በልቡ ጉጉት እንዳለ እኛም ለድሆች ማሰብ እና መራራት ማንነታችን ሊሆን ይገባል። የመቆረስ ህይወት እንዲኖረን እግዚአብሔር ከእኛ ይፈልጋል። እግዚአብሔርን አውቃለሁ ብንል አምላኪ/ ሀይማኖቶች ብንሆንም ለድሆች የሚራራ ልብ ከሌለን ግን ተግባራችን, ንግግራችንን በግልጽ ይክደዋል። በአፋችን ተናጋሪዎች ብቻ ሳይሆን በተግባር ኗሪዎች እግዚአብሔር ያድርገን
“እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፥ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል።”
— ቲቶ 1፥16
“ከሩቅ ያሉትን ሕዝቦች የሚጠራበትን ምልክት ያቆማል፤ ከምድር ዳርቻም በፉጨት ይጠራቸዋል፤ እነርሱም እየተጣደፉ በፍጥነት ይመጣሉ።”
ኢሳይያስ 5፥26
📌 lesson of the day
አንድ አንድ ጊዜ በህይወታችን ብዙ የምንፈራባቸው የምንጨነቅባቸው ብሎም የምናዝንባቸው እልፍ ነገሮች ይኖሩናል, ነገርግን እግዚአብሔር ከዛ ሁሉ በላይ ነው ከምንፈራቸው እና ምናዝንባቸው እልፍ ምክንያቶች በላይ ጌታ ትልቅ ነው‼️
ስለሆነም ሳንፈራ ጌታችንን በመታመን, የታመነው እና የተደገፍነው ደሞ የማያሳፍረን መሆኑን ባለሙሉ እምነት ሆነን መኖር ይሁንልን 🤗
#ጸጋ
Gallery / profit picture
❣እግዚአብሔር ፍቅር ነው❣
#please_sHaRe_for_your_friends
For more spiritual wallpapers join us 👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEo2T-JmxkASvqrFaw
26 ዝማሬ በአንድ አልበም...
በኢትዮጵያ የወንጌላውያን ቤተክርስቲያናት የዝማሬ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 26 ትራክ የያዘው የአስቴር ሃሌሉያ የዝማሬ አልበም ለጊዜው በ youtube እስኪለቀቅ Spotify ላይ ኮምኩሙት ተባረኩበት።
አስቴር አበበ
ሃሌሉያ
ፌር (Fair) አይደለም! ኧረ ግን ፌር ነው!!
ስምንት (8) ጎረምሳ ባለበት ቤት ሁሉም እኩል ልጅ ተብሎ ተወልዶ ሁሉም የባላምባራስ እሴይ ልጅ ተብሎ እየተጠራ ታዲያ በምን ሂሳብ ነው የቤቱ ኅላፊነት በሙሉ የሁሉ ታናሽ ዳዊትዬ ላይ የወደቀው?
- በግ ጠባቂ ቢባል እሱ!
- አንበሳና ድብ ጋር ግብ ግብ ገጣሚ እሱ፣
- ምግብ አመላላሽ እሱ፣
- በገና ደርዳሪ እሱ፣
- ከነመፈጠሩ ቢረሳ እሱ፣
- ለቁም ነገር ባይጠበቅ እሱ፣
- እማያጉረመርመውም እሱ፣
- ለመብቱ ማይከራከረውም እሱ፣
ቆይ እሺ እነ ኤልያብ እነ አሚናዳብ ምን እያረጉ ነው ያን ሁሉ ዘመን?
- እስኪ እንርዳህ እናግዝህ ወንድማችን ተንገላታህብን እኮ አይባልም?
- እነሱ የራሳቸው ዓለም ላይ ናቸው ወዳጄ! ትዝም አላላቸውም::ዳዊት ደሞ ማነው?
- በጉብዝና ወራታቸው ራሳቸውን እንጂ እግዚአብሔርንም ዳዊትንም አላሰቡትም::
ታዲያ ይሄ ፌር ነው?
አዎ፣ ፌርም ባይሆን ግን ደግሞ ፌር ነው!
እንዴታ? እንዴታማ ጥሩ ነገር!
- አገር ጭንቅ ውስጥ ገብታ ስትታመስ አንድ ሰው ለመድኅኒትነት ቢገኝ እሱ!
- ዳዊት እልፍ ገደለ ቢባል እሱ፣
- በእስራኤል ዘንድ ንጉስ ቢጠራ እሱ፣
- እንደ ልቤ የሆነ ቢባል እሱ፣
- በቅዱሱ መፅሃፍ ከመዝሙረ ዳዊት 150 ምዕራፋት አብላጫውን ቢያስኮመኩመን እሱ!
ኧረ ተው! ይሄ ነገር ፌር ነው መሰል?! ከለአለም ጥላሁን የተወሰደ
======== ደክሞሀል?=======
ስንፍና ጓዳህ አድብቶ ፤ጉልበትህ ታክቶ ደክሞሀል?. . .
ድካምህ ደክሞት አያውቅም ፤ አውራው እንጂ
ይሰማሀል
ቸልተኝነት አያውቅም ፤ ስትጠራው ይደርስልሀል
በቀጠርከው ሰዐት ቀርቶ፤ በፈለከው ይገኝልሀል..
. . .
ብቻ ... እጁን ለዘረጋ ፤ ሳይሰስት ያትረፈርፋል
አንተ ባታምነውም እንኳን ፤ እርሱ ግን ታምኖ ይኖራል።☝️
.
.
.
“ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት”
— ያዕቆብ 1፥2-3
ጽድቅ ማለት በእግዚአብሔር ፊት ያለሀፍረት ያለመሸማቀቅ በድፍረት የመቆም መብት ነው እርሱም እየሱስ ነው
እኔ በእየሱስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ነኝ
“እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።”
— 2ኛ ቆሮ 5፥21
Christ እኛ ውስጥ ነው
በዚህ ምክንያት እኔ የእግዚአብሔር ጽድቅ ነኝ
ህይወት ከውስጥ ወደ ውጭ ነው
ለካስ ቀን ይመጣል
ለሁሉም ጊዜ አለው
ብድራትን ቆጥሮ ጌታ የምመልሰዉ
ቆሞ መጠበቅ ምነኛ መልካም ነዉ
በጊዜዉ ሲያደርገዉ ፍሬዉም ጣፋጭ ነው።
“ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።”
— ዮሐንስ 19፥30
ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆነ ተፈፀመ ካለ ቡኋላ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ወይም ሞገስ ለማግኘት የምንሰራው ምንም የቀረን ስራ የለም
Jesus paid it all ‼️
ለመዳኔ እኔ አላዋጣሁም እንጂ የተከፈለ ዋጋ ግን አለ እርሱም የክርስቶስ ደም ነው🩸✝
መልካም ስራ የምሰራው ለመዳን ሳይሆን ስለዳንኩ ነው‼️
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
— ዮሐንስ 3፥16
ያዕቆብ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ።
¹⁷ በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።
¹⁸ ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።
¹⁹ ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤
²⁰ የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና።
²¹ ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።
²² ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።
²³ ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤
²⁴ ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል።
²⁵ ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል።
²⁶ አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።
²⁷ ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።
“እኔ በጽድቅ አስነሥቼዋለሁ መንገዱንም ሁሉ አቀናለሁ፤ እርሱ ከተማዬን ይሠራል፥ በዋጋም ወይም በደመወዝ ሳይሆን ምርኮኞቼን ያወጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”
— ኢሳይያስ 45፥13
አዝ፦ አቤት ምሕረት የበዛለት እንደ እኔ ያለው (፪x)
አቤት ፀጋ የበዛለት እንደ እኔ ያለው (፫x)
ያመስግን እንጂ ኦሆ
ስላደረግህለት ሌላ ምን ቃል አለው (፪x)
ሁሌ በልቤ እኔ የምመኘው
አንተን ማመስገን ሥምህን ማክበር ነው
ዓይኔ በርቶልኝ የውስጥ ሃሳቤ
ክብርህን አይቼ ልኑር ጠግቤ (፪x)
አንደበት ያለው ሁሉ ክቡር ሥምህን ከፍ ያድርገው
ክቡር ሥምህን ያመስግነው
ምሕረት ፀጋ የበዛለት ማዳንህን ይናገረው (፪x)
ከአማልክት መሃል አንተ ብቻህን ጌታ ነህ
አንተ ብቻህን አምላክ ነህ
አዝ፦ አቤት ምሕረት የበዛለት እንደ እኔ ያለው (፪x)
አቤት ፀጋ የበዛለት እንደ እኔ ያለው (፫x)
ያመስግን እንጂ ኦሆ
ስላደረግህለት ሌላ ምን ቃል አለው (፪x)
ሁሌ በልቤ እኔ የምመኘው
አንተን ማመስገን ሥምህን ማክበር ነው
ዓይኔ በርቶልኝ የውስጥ ሃሳቤ
ክብርህን አይቼ ልኑር ጠግቤ (፪x)
አቤቱ ጌታ አምላክ ሆይ
ወደ አንተ እገሰግሳለሁ (፪x)
ክብርህን ኃይልህን አይ ዘንድ
ይሄ ለእኔ ጥማቴ ነው (፪x)
ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው
ልበል ሥምህን ላክብረው
የአንተ መክበር ለእኔ ደስታ ነው
አዝ፦ አቤት ምሕረት የበዛለት እንደ እኔ ያለው (፪x)
አቤት ፀጋ የበዛለት እንደ እኔ ያለው (፫x)
ያመስግን እንጂ ኦሆ
ስላደረግህለት ሌላ ምን ቃል አለው (፪x)
ሁሌ በልቤ እኔ የምመኘው
አንተን ማመስገን ሥምህን ማክበር ነው
ዓይኔ በርቶልኝ የውስጥ ሃሳቤ
ክብርህን አይቼ ልኑር ጠግቤ (፪x)
#join_us👇
@GODIS_LOVE እግዚአብሔር ፍቅር ነው
ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ እነሆ፥ እፈውስሃለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወጣለህ።”
— 2ኛ ነገሥት 20፥5
መርዶክዮስ!!
ሰውየው የጄነራል ማዕረግ የሚያሰጥ ትልቅ ስራ ሰርቶ ወይ ትንፍሽ እሱ! ገበታና ታራ የተባሉት የንጉሱ ጃንደረቦች በንጉሱ በአርጤክስስ ላይ ሲነሱበት የንጉሱን ህይወት ከጥፋት ያተረፈው መርዶክዮስ ነበር:: ታዲያ እወቁልኝ የለ ነጋሪት ምቱልኝ የለ አለሁ አለሁ የለ ፀጥ ብሎ የሚኖር ካልታየሁ ካልተወደስኩ የማይል የተረጋጋ ሰው ነበር መርዶክ! የዛች ሌሊት መዝገብ ባይገለጥ እኮ ኖሮ እንዲሁ ይሞታት ነበር እንጂ አትርሱኝ እኔ እኮ ነኝ ዝባዝንኬ አይወጣውም ነበር::
ታዲያ ይሄው gentleman ነው አንድ ቀን ላይ ግን ነብር ሆኖ የተገለጠው! "አይሁድ ሊገደሉ ከምድረ ገፅ ሊደመሰሱ ነው" የሚል ዜና ሲሰማ ውሎ አላደረም! ከተማይቱን የሱሳን ግምብ ቀውጢ አደረጋት:: ስለራሱ ጉዳይ አንዳች የማይተነፍሰው ሰውዬ የእግዚአብሔር ህዝብ ጉዳይ ግን አንገበገበው! ንግስቲቱን ሸሚዝ ቀይሪልኝ ብሎ ማያውቀው ሰውዬ አሁን ግን ቅጭም ባለ ቋንቋ አስቴሯን ተናገራት! "ወይ ታድኚናለሽ ወይ አንቺ ራስሽ ከነአባትሽ ቤት ትጠፊያለሽ" ለማለት ቅንጣት ታክል አላንገራገረም:: ምን አለፋችሁ?! የማታ ማታ በአይሁድ ላይ የተፃፈውን የሞት አዋጅ አስገልብጦ ህዝቡን ከጥፋት የታደገ ምርጥ ጀግና ነበር::
ዋው! ለራሳቸው ጉዳይ ሞኞች መስለው ለእግዚአብሔር ህዝብና ለቤቱ ጉዳይ ግን በነፍሳቸው የሚወራረዱ እንደነዚህ ያሉትን መርዶክዮሶች ኧረ በኛም ዘመን ያብዛልን!!
- - - - - - - - ትልቅ አልልህም... - - - - - -
ቃላቶች አይበቁኝ ፤ ተናግሬህ አልጨርስ
እስክትገባኝ ድረስ፤ ፅፌህ አንተን ባወድስ
ጠቢብ በሚለው ቃል፤ ለኔ እስካትመሰል
የጥበትህን ጥግ፤ ትልቅነትህን ሳስብ ሳሰላስል...
የትልቅ ሰው ዳሩ፤ እጅግ አትባልም
እጅግን ጨምሬ ፤ ትልቅ ከልልህም::
* * *
ብዬ ፅፌ ነበር ፤ ከአመታት በፊት
ከአይምሮዬ ሲያልፍ፤ የእርሱ ትልቅነት
አሁንም አነሳው፤ ብህሬን እንደገና
ባይገልፀዉም እንኳን፤ የእግዚአብሔርን ዝና
ትልቅ ከሚባሉት ፤ በነህገሌ መጠን
በቃላቱ ማነስ ፤ እንዳይመዛዘን
ከእርሱ ትልቅነት፤ የእነርሱ ባይገጥምም
የሰው ትልቅነት ከፈጣሪ ጋራ ባይዘማመድም
ትልቅ ከሚባሉት ከጥቃቅኖቹ፤ ቃሉ እንዳይሄድ ብዬ
የእርሱ ገናናነት ከእነርሱ ጎራ ፤እንዳይሆን ነጥዬ
በትልቆች ሚዛን ፤ ስለማላስበው
ትልቅ የሚለው ቃል ፤ ለሰው ከተሰጠው...
. . .
ብዬ ነበር ያኔ ፤ አልልህም ያልኩት
ከእነርሱ ስለሌለ ፤ በግጥም የለየሁት
አሁን ግን ፤ ዞሬ መጥቻለው
ለእርሱ ገናናነት ፤ ቃልን አጥቻለው
ስላላገኘሁኝ ፤ አንድ የሚገጥም ቃል
እርሱን ሚያብራራ ፤እግዚአብሔርን የሚል።
ዛሬም ተመልሼ ፤ ይኸው ገጥሜያለው
ታላቅ ሰውን ሳይሆን ፤ ትልቅ ነህ ብያለው።
“እግዚአብሔር ትልቅ ነው፤ በአምላካችን ከተማ በተቀደሰው ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው።”
— መዝሙር 48፥1
“ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን።”
— 1ኛ ተሰሎንቄ 4፥13