"አስጨናቂው በከበረ ነገርዋ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ:" ሰቆቃው ኤርሚያስ 1:10
የዮሐንስ ራእይ 12
12፤ ስለዚህ፥ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፥ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።
13፤ ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።
/channel/raiye_mariyam
ሀይማኖት፣ ፍቅር፣ ትህትና ከሌላችሁ ጨው እንደሌለው ምግብ ናችሁ። ሰው ሆይ እስከ መቼ ትሰንፋለህ ጠዋት የተመገብከው ሲመሽ አሠር አንደሚሆን አታቅምን ምሽት የተመገብከው ጠዋት አሰር የሚሆን አይደለምን በመቃብር ውስጥ ያንተ መትላት ከቆሻሻ ይልቅ ይበልጣል ፈጥኖም ይደረጋል ሩቅም አይደለም። ከዚህ በኋላ ጨለማ ይጠብቅሀል ይህ ከሆነ እንዳንተ ያሉ ሠዎችን ለምን ትንቃለህ ለምን እንዳንተ ያለውን ሰው አታከብረውም ለምን እንደራስህ አድርገህስ አቶደውም ነገር ግን ከእግር ጥፍርህ እስከ ራስ ፀጉርህ ትዕቢት የተሞላህ አንተ በሀሣብህ እስከ ደመናዎች ከፍታ ድረስ ከፍ ከፍ አልክ እነሆ የሚያስፈሩ ትዕቢታቸው የጣላቸው ጥቁር የሆኑ መልአክ ወዳሉበት ጥልቅ ትወርዳለህ ።
@raiye_mariyam
ተወዳጆቼ ፡ ሆይ! #በኢየሱስ_ክርስቶስ ፡ ስም ፡ እለምናችኋለሁ! የመዳናችሁን ፡ ነገር ፡ ከቶ ፡ ቸል ፡ አትበሉ!!
+ርእሰ-መነኮሳት አባ እንጦንዮስ [እንጦንዮስ እንጦንስ ፣ እንጦኒ] በኹሉም ቦታ ለሚኖሩ ዝርዋን ወንድሞች ከላከው ሁለተኛ መልእክት...
@raiye_mariyam
✝ የመለኮተ ስሞች ትርጓሜ ✝
ቅዱስ ጸባኦት፦ የሠራዊት አለቃ እግዚአብሔር
ቅዱስ አዶናይ፦ ከሁሉ በላይ ያለ እግዚአብሔር
ቅዱስ ኤልሻዳይ፦ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር
ቅዱስ ያሕዌ፦ ያለ የነበረና የሚኖር ሕያው እግዚአብሔር
ቅዱስ ኢየሱስ፦ መድኃኒት የሆነ
ቅዱስ ክርስቶስ፦ በሥጋ የተገለጠ የተቀባ ንጉሥ
ቅዱስ አማኑኤል፦ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ
#ጸባኦት_ይከተላችሁ
@raiye_mariyam
ለዩቲዩብ ተጠቃሚዎች በመሉ
እነሆ ዛሬ ማኅተቤ ቲዩብ የተሰኘ መንፈሳዊ የዩቲዩብ ቻናል ልንጠቁማችሁ ወደናል።
ሰብስክራይብ እና ላይክ እንዲሁም ሼር በማድረግ እናበረታታ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCxkJ20_IgJMj1yYZzL0hEVg
ወእንዘ ትፈትል
ወእንዘ ትፈትል(3) ወርቀ ወሜላት
አስተርአያ ገብርኤል አስተርአያ ለማርያም(2)
እግዚአብሔር አስቦ እናቱ ሊያደርጋት
ሳለች ብላቴና የአስራ አምስት አመት
በመጋቢት ወር ላይ በእሁድ እለት
መልአኩን ላከልን ብሎ አብስራት(2)
አዝ
ዘማሪ ዲ/ን ኤፍሮን ጥላሁን
ልጅን ትወልጃለሽ ብሎ ሲያበስራት
ይህ እንዴት ይሆናል አለችው በእውነት
አለም ይህን ሰምቶ እጅግ አደነቀ
በሀሳብም ድንግል መሆኗን አወቀ(2)
አዝ
የጌታ ባሪያው ነኝ የእርሱ አገልጋይ
ይሁንልኝ ስትል ዳግሚት ሰማይ
አለምን ሊታደግ ከእስራት ሊፈት
በድንግል ማህፀን ተፀነሰ ጌታ(2)
አዝ
እንዴት እርሷን ልካድ እንዴትስ ልጥላት
ቃል ስጋ የሆነባት ማርያም ንጽሒት
ዳግሚት ሔዋንን የካደው የጠላው
ቀዳሚት ሔዋንን ያሳተው እርሱ ነው(2)
*ጌታዬ ከሰጠኝ*
*/////////////////*
ጌታዬ ከሰጠኝ አልፈራም ልወስድሽ /2/
የሐዘኔ መርሻ ማርያም እናቴ ነሽ /2/
እናት አግንቻለሁ ከመስቀሉ እግርጌ
ስሟን እየጠራሁ ከፍ እንዲል ማይረጌ
ምርኩዝ ድጋፍ ሁኖኝ ድንግል ሆይ ጸሎትሽ
በፎይታ ሞልቶኛል የሰላምታ ድምፅሽ
ፍፁም ላይረሳኝ ዘልቆ በደም ስሬ
ይቀሰቅሰኛል ፍቅርሽ ለዝማሬ
አዝ ።።።
በልጅሽ መከራ ቀራኒዮ ያለሽ
አትዘነጊኝም ዛሬም ከኔ ጋር ነሽ
መታወክ መጨነቅ ከቤቴ እንዲነቀል
የበረከቴን ቁልፍ ሰቶኛል ከመስቀል
ከጣራዬ በታች መነጨ ደስታ
ለጠቆረው ፊቴ እመቤቴ አብርታ
አዝ ።።።
በራስ ቅል ተራራ በነፍስሽ ሰይፍ አልፎ
ካሳ ሆነኝ ፍቅርሽ በልቤ ተፅፎ
እነኋት እናትህ ሲለኝ በርትቻለሁ
በልጅነት ክብር ከፊትሽ ቁሜአለሁ
የመስቀል ስጦታ እነኋት እናቴ
ማንንም ሳልፈራ ወሰድኳት ከቤቴ
አዝ ።።።
በመስቀል ላይ ሆኖ ልጅሽ እራራልኝ
በናትነት ፍቅርሽ ቤቴን ሸለመልኝ
በሚያፅናና ቃሉ መሰበሬን ክሶ
በልቤ ተከለ አፅናኟል ምሰሶ
ሞኝነት አይደለም ነገረ መስቀሉ
እጅግ ማትረፊያ ነው አንችን መቀበሉ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
የሰላም አለቃ ቸሩ መድኃኔአለም የድንግል ማርያም ልጅ ማንም የማይቀማንን ፅኑ ሰላም ይስጠን!! ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ማለት ምን ማለት ነው ?
1 ኦርቶዶክስ የሚለው ስም ከየት የመጣ ነው?
2 ተዋህዶ የሚለውስ ከየት የመጣ ነው?
3 ክርስትያን ማለትስ ምን ማለት ነው???
💒 ኦርቶዶክስ ማለት ቃሉ የግሪክ ሲሆን አማርኛው
ትርጉሙ እውነተኛ፤ቀጥተኛ መንገድ የሆነች ሃይማኖት
ማለት ነው፡፡
ቀጥተኛዋ መንገድ ጠይቁ በእርሷም ላይ ሂዱ
ለነብሳቹሁም እረፍት ታገኛላቹሁ፡፡[ኤር 6÷16]
ነብዩ ኤርምያስ እንዳለው እዚህ ላይ እንግዲህ ቀጥተኛ
ማለት ኦርቶዶክስ ማለት ሲሆን መንገድ ማለት ደግሞ
ሃይማኖት ማለት ነው፡፡
💒 ኢየሱስም ክርስቶስም አለ እኔ መንገድ እውነት
ሕይወት ነኝ ብልዋል፡፡[ዮሐ 14÷6]
ይህ ማለቱም የሃይማኖት መሰረታ ቹሁ እኔ ነኝ ማለቱ
ነው፡፡
ከሰማያዊው ጥሪ ተከፋዮች የሆናቹሁ ቅዱሳን ወንድሞች
ሆይ የሃይማኖታችንን ሊቀ ካህን የሆነውን ኢየሱስ
ክርስቶስን ተመልከቱ፡፡[ዕብ 3÷1]
ስለዚህ ኦርቶዶክስ ማለት ይህ ነው፡፡
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
2 💒ተዋህዶ ማለትስ ከየት የመጣ ነው?
💒 ተዋህዶ ማለት ተዋሃደ ከሚለው የግእዝ ግስ
የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙ አንድ ሆነ መለኮትና ስጋ አንድ
ሆነ ማለት ነው፡፡ ከሁለት አካል አንድ አካል ፤ከሁለት
ባህርይ አንድ ባህርይ ሆነ ማለት ነው በሌላ አካሄድ ደግሞ
ተዋሃደ ማለት መለኮት ስጋ ለበሰ ከድንግል ማርያም
ከስጋዋ ስጋ ከነብሷ ነብስ ነሳ ማለታችን ነው፡፡
💒 ይህም ደግሞ ግልፅ የሆነ እውነት ነው፡፡
በጀመርያ ቃል ነበረ ፤ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ
ነበረ፤ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፡፡[ዮሐ 1÷1]
ቃልም ስጋ ሆነ፤ፀጋንና እውነትን ተመልቶ በእኛ አደረ
እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡[ዮሐ1÷14]
ስለዚህ ተዋህዶ ስንል ቃል ስጋ ለበሰ ማለታችን ነው፡፡
💒 በበለጠ ደግሞ ብርሃናዊው የሆነ የዓለም ብርሃን
ቅዱስ ጳውሎስ ቃል በቃል ተዋህዶ የሚለው ፅፎልናል፡፡
ክርስቶስ እርሱ ሰላማችን ተውና፤ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ
የተነገረለት በራሱ አዲስ ሰውን ይፈጥር ዘንድ ሰላምም
አደረገ፡፡[ኤፌ 2÷14-15]
ስለዚ ተዋህዶ ማለትም ይህን ይመስላል፡፡
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
3💒 ክርስቲያን የሚለውስ ከየት የመጣ ነው?
💒 ክርስትያን ማለት ከክርስቶስ ስም የተወሰደ ሲሆን
ክርስቶስ ተከታዮች፤አማኞች ማለት ነው፡፡
ክርስቶስ አምላክ ነው፤ጌታ ነው፤ፈጣሪ ነው፤ፈራጅ ነው
ብለን የምናምን ክርስትያን ተብለን እንጠራለን፡፡
የክርስቶስ ሐዋርያትም በአንጾክያ ምክንያት ክርስቲያን
ተባሉ፡፡[ሐዋ 11÷26]
💒 በትዕቢት ተነፍቶ በዲያብሎስ ፍርድ
እንዳይወድቅ፤ሰው ሁሉ አዲስ ክርስቲያን አይሁን፡፡
[1ኛ ጢሞ 3÷16]
ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም
እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር፡፡
[1ኛ ጴጥ 4÷16]
ስለዚህ ሁሉም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተነሳ ነው፡፡
💒 ኦርቶዶክስ ነው ሃይማኖቴ ስን ቀጥተኛ ናት
ሃይማኖታችን እያልን ነው፡፡
የተዋህዶ ልጆች ነን ስንልም የክርስቶስ ልጆች ነን
እያልን ነው፡፡
ክርስቲያን ነን ስንልም ክርስቶስን የምናመልክ
የምናምን ክርስቲያን ነን፡፡
ማለታችን ነው፡፡
💒 ሌላው እምነት ፤ሃይማኖት ግን ጴንጤ ፤ፕሮቴስንት
፤ካቶሊክ፤ጆባዊስትን ክርስቲያን ነን ቢሉም እነዚህ
የመሳሰሉ ግን ከጥንትም ያልነበረ ስም አዲስ ድርጂት
ነው በመፅሐፍ ቅዱስም አንድም ቦታ ላይ የለም፡፡
ከግዜ ቡሃላ ከኦርቶዶክስ ወጥተው ወደ ምንፍቅና
የተመሩ ድርጅቶች ናቸው፡፡
💒ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ግን ከጥንት የነበረች የነብያት
የሃዋርያት የቅዱሳን ሰማዕታት ሃይማኖት ናት ፡፡አሁን እስከ ልጅ ልጅ ለዘላለም ትኖራለች፡፡
💒አንድ ጌታ💒እንዲት ሃይማኖት 💒አንዲት ጥምቀት
💒ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዘላለም ትኑር አሜን
🙏ወስብሐት ለእግዚአብሔር
🙏ወለወላዲቱ ድንግል
🙏ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን።
✞ቸር አገልጋይ ማነው✞
ቸር አገልጋይ ማነው ለንጉሥ የታመነ
መክሊቱን ያልቀበረ አትርፎ የከበረ (፪)
ባለ አምስቱ መክሊት መልካም ያደረገው
በመውጣት በመውረድ አትርፎ መጥቶ ነው
በጥቂቱ ታምኖ በብዙ የተሾመው
ባለ አምስቱ መክሊት ሊቀ ጳጳሱ ነው
አዝ= = = = =
ሳይሰለች የተጋ ባለሁለት መክሊት
የታመነ እረኛ በፍቅርና በእምነት
ግባ የተባለው ወደ ጌታው ደስታ
አጥምቆ ያቆርባል ካህኑ የጌታ
አዝ= = = = =
ለሚበልጠው ጸጋ ተጠርቶ የነበረ
መክሊቱን ደብቆ ቆፍሮ የቀበረ
ሰነፍ ባርያ ተብሎ ወደ ፍርድ ተጣለ
ማኔ ቴቄል ፋሬስ በአምላክ ፊት ቀለለ
አዝ= = = = =
ፈቃድህን ማድረግ ነፍሱ ለምትወደው
ወንጌልህን መግለፅ የየዕለት ግብሩ ነው
ህግህ ለዘለላም ተጽፎ ይኖራል
በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህ ይነገራል
መዝሙር
ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
ማቴ፳፭፥፲፬-፴፩
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ውድ የወልድያ መንበረ ንግስት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን የመሠረተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት አባላት እንኳን ለ 35ኛ የምስረታ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
🌸🌸ሁላችሁም🌹🌹🌹 ተጋብዛችኋል 🌺🌺🌺እንዳትቀሩ🙏🙏🙏
ከየካቲት 18-21/06/2013 ዓ.ም
<<በእርሱም ላይ ንጉስ አላቸው እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው ስሙም በዕብራይስጥ አባዶን በግሪክ አጶሊዮን ይባላል።>> ራእይ 9:11
✝ዛሬ ተቀደሱ✝
መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ
#ንቁ
@fikare_eyesus
✝ማቴዎስ 5✝
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
✝⁴³ ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
⁴⁴-⁴⁵ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
⁴⁶ የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?
⁴⁷ ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?
⁴⁸ እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።✝
/channel/raiye_mariyam
"ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን"- ቅዱስ ሲኖዶስ
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የጾምና የምሕላ አዋጅ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
"የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ!
ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።"
ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 5
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በተከሰተው ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮቿን በመጣስ መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ኤጲስ ቆጶስነት ሢመት በሰጡትና በተሾመ ግለሰቦች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥር 18 ቀን 2015ዓ.ም. ቃለ ውግዘት ማስተላለፉ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ እነዚህ ሕገወጥ ቡድኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ካለመቻላቸውም በላይ በመንግሥት ኃይሎች በመታገዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተዳድራቸውን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረርና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረጉ ከመሆኑም በላይ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ሠራተኞች ካህናትና ምእመናን በማሰርና በማንገላታት ላይ ይገኛል፡፡ መንግሥትም ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር ስላልቻለ ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን በመማፀን ጸሎትና ምሕላ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተረድቷል።
በመሆነም ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ጥቁር ልብስ የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው፡፡
እንደሚታወቀው ጥቁር የእውቀት ምልክት ነው ተማሪዎች አውቀናል ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛ ከእውቀት በላይ የሆነውን አምላካችንን በመማፀን ከዚህም ማንም ሊያናውጽን እንደማይችል የምናረጋግጥበት፤ ጥቁር የእውነት ምልከት ነው ዳኞች እውነት እንፈርዳለን ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛም መከራው የሚያሰቅቀን ሳይሆን ይበልጥ ልንጸናና ልንበረታ የሚገባ መሆኑን ለዓለም ሕዝብ የምናሳይበት በመሆኑ ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ጥር 26 ቀን 2015ዓ.ም. አዲስ አበባ
*ነፍስህን ይፈልጓታል*
*መልካም ንባብ!*
*ምስጢሩን ይግለጥልን*
✝️ (ሉቃ 12 )
------------
16 *ምሳሌም ነገራቸው እንዲህ ሲል፦ አንድ ባለ ጠጋ ሰው እርሻ እጅግ ፍሬያም ሆነችለት።*
17 *እርሱም፦ ፍሬዬን የማከማችበት ስፍራ አጥቻለሁና ምን ላድርግ? ብሎ በልቡ አሰበ።*
18 **እንዲህ አደርጋለሁ፤ ጐተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፥ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤*
19 *ነፍሴንም፦ አንቺ ነፍሴ፥ ለብዙ ዘመን የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ፤ ዕረፊ፥ ብዪ፥ ጠጪ፥ ደስ ይበልሽ እላታለሁ አለ።**
20 *እግዚአብሔር ግን፦ አንተ ሰነፍ፥ በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል? አለው።*
21 *ለራሱ ገንዘብ የሚያከማች፥ በእግዚአብሔር ዘንድም ባለ ጠጋ ያልሆነ እንዲህ ነው።*
✝️ይገርማል! ይህን ታሪኩ የተነገረለት ሰው ሁሉ ነገር የተ ሳካለት ትርፋማ ሰው፣ እርሻው እጅግ ፍሬያማ የሆነችለት ሰው: ብሎ ነው ጌታችን የገለጠው።
✝️እናም ይህ ሰው እጅግ እጅግ እጅግ በጣም ትርፋማ ነበር።
✝️አሁን ወደ ሜዳ ወጥቶ ከትርፋማነቱ የተነሳ ደስታውን መ ቆጣጠር አቅቶት ብቻውን ያወራ ጀመር፦
✝️ *ጐተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፥ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ*
*ነፍሴንም፦ አንቺ ነፍሴ፥ ለብዙ ዘመን የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ፤ ዕረፊ፥ ብዪ፥ ጠጪ፥ ደስ ይበልሽ እላታለሁ አለ* ።
✝️ *ይገርማል! ሰውየው ሥራ መስራቱ መልካም፣ ትርፋማ መሆኑ መልካም ነበር: ምን ያደርጋል! መመጻደቁ እና ነፍሱን መርሳቱ አከሰረው እንጂ።*
✝️ *በሀሳቡ እንኳን እግዚአብሔር ከሰጠው ፍሬ ላይ አስራት ሊያወጣ አላሰበም፣ መንገድ ላይ ለወደቁት ችግረኞችም አላሰበም፣ለድሆች ዘመዶቹም አካፍላለሁ አላለም...በቃ ሀሳቡ ሌላ መጨመር ...እና ነፍሴ ብይ፣ ጠጭ እያለ ስለ ምግብ እና መጠጥ ሆኖ ነበር!*
✝️ *ይህን ሰው የመሰሉ ብዙዎች ዛሬም ድረስ በየሰፈሩ አሉ። አንዱን ይዘው በተሰጣቸው ሳያመሰግኑ፣ የእግዚአብሔርን አስራት ሳያወጡ ሌላው የሚያምራቸው...ሀሳብ ንግግራቸው ስለ ራሳቸው ብቻ ለዚያውም ስለ ሥጋ ብቻ የሆነ....ከዚህ ይሰውረን።*
✝️ *እናም ስለሚሰራው ጎተራ፣ ስለሚበላው ምግብ፣ ስለሚጠጣው መጠጥ እያሰበ ሲደሰት: በዚያችው ደቂቃ እግዚአብሔር መጣ፣ ነፍስህ በዚህች ሌሊት ትወሰዳለች አለው። ጨምሮም ይህ ያጥራቀምከው ሁሉ ለማን ይሆናል???? አለው። ተናግሮም አልቀረ ነፍሱን በዚያችው ቅጽበት ወሰዳት!*
✝️ *የዘራውን ሳያጭ ድ: ያከማቸውን ሳይበላ: የቀዳውን ሳይጠጣ በሞት ተነጠቀ። የምድሩንም የሰማዩንም አጣ። እኔ ጀግናው! እኔ ትርፋማው! ...ሲል የነበረው ሰው ከሰረ! እግዚአብሔር አምላካችን ከዚህ ይሰውረን!*
✝️ *ወገኖቼ ሁሉ ያልፋል። በተሰጠን ፍሬ እግዚአብሔርን እናክብርበት። እርሱ እግዚአብሔር ከሰጠን ላይ ለእርሱ ለእግዚአብሔር አስራት እናውጣ።ቤተ ክርስቲያንን እናስባት! በየስፍራው በግፍ ተፈናቅለው፣ ጎዳና የወደቁትን ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን፣ ልጆቻችንንም እናስባቸው። በተሰጠን ደግሞ እናመስግን ለሌሎች ማካፈልን፣ ድሆችን ማሰብን ህይወታችን እናድርግ። ለብዙ ዘመን የሚበቃኝ አለኝ ልብላ ልጠጣ እያልን እንደዚህ ሰው እንዳንከስር በማስተዋል እንኑር። በዚህች ሌሊት ነፍስህን እወስዳታለሁ ተብለን ድንገት ወደ መሬት ከመሄዳችን በፊት እናስብበት: አደራ! መንፈሳዊነት ይህ ነውና።*
✝️ *የመስቀለ ኢየሱስ በረከት በየቤታችን ይግባ።*
✝️ *ብሩህ ቀን* ✝️
#ጾመ_ነቢያት
እግዚአብሔር አምላካችን ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ መልበሱን፣ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ወደ ግብጽ ግብር መሰደዱን፣ በባሕረ ዮርዳኖስ መጠመቁን፣ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ማብራቱን፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል ልዩ ልዩ ዓይነት መከራ መቀበሉን፣ መሰቀሉን፣ መሞቱን፣ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ ማረጉንና ዳግም ለፍርድ የሚመጣ መኾኑን በአጠቃላይ የማዳን ሥራውን በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው አስቀደመው በትንቢት ተናግረዋል፡፡ ትንቢቱ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው ኾኖ ዓለምን የሚያድንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎትም በእግዚአብሔር ሰው መኾን ፍጻሜ አግኝቷል፡፡
ይህን ምሥጢር በማሰብ በየዓመቱ #ከኅዳር_15 ቀን ጀምሮ እስከ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ዋይዜማ ድረስ እንድንጾም አባቶቻችን መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርተውልናል፡፡ ይህ ጾም፣ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ሲኾን፣ በስያሜም #ጾመ_ነቢያት (የነቢያት ጾም) እየተባለ ይጠራል፡፡ ወቅቱ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ የተፈጸመበት ስለሆነም #ጾመ_አዳም (የአዳም ጾም) ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም #ጾመ_ስብከት (የስብከት ጾም) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ #ጾመ_ልደት (የልደት ጾም) በመባል ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም #ጾመ_ሐዋርያት እየተባለ ይጠራል፤ ምክንያቱም ቅዱሳን ሐዋርያት "በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?" በማለት ነቢያት በጾሙበት ማለት ከልደተ ክርስቶስ በፊት ባለው ወቅት ጾመዋልና፡፡
በሌላ አጠራር ይኸው ጾመ ነቢያት #ጾመ_ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም) በመባል ይታወቃል፤ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያ እና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ተሰወረባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ በዓት ዘግተው፣ ሱባዔ ገብተው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ቢለምኑት ልመናቸውን ተቀብሎ ሱባዔ በያዙ በ፫ኛው ቀን የቅዱስ ፊልጶስን ሥጋ (በድን) መልሶላቸው በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት 'ጾመ ፊልጶስ' እየተባለ ይጠራል፡፡
ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው፣ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካበሠራት በኋላ "ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?" በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ እመቤታችን ጾማዋለችና ይህ ጾም #ጾመ_ማርያም በመባልም ይታወቃል፡፡ በአጠቃላይ በዚህ በጾመ ነቢያት፣ ነቢያትም ሐዋርያትም፣ ቀደምት አባቶቻችንም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባናል፡፡
ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ ጾመ መድኃኒት ያድርግል!
ምንጭ፡–
#ዲያቆን_ኤፍሬም_የኔሰው -ማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ
ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭
"ብክዩ ሕዙናን ኀልየክሙ ስደታ፣
ወላሕው ፍሡሓን ተዘኪረክሙ ብዝኀ ሠናይታ፣
#ማርያም ተዐይል ከመ-ዖፍ ውስተ-አድባረ-ግብጽ ባሕቲታ፣
ተዐወዩ በኀጢኦታ ሀገረ-አቡሃ ኤፍራታ፣
ወደመ-ሕጻናት ይውሕዝ በኵሉ ፍኖታ።"
➖ሐዘንተኞች የእመቤታችንን ስደቷን አስባችሁ አልቅሱ...😢
ደስተኞች የበዛ መልካምነቷን አስባችሁ አልቅሱ...😢
#ማርያም እንደ ወፍ ብቻዋን በግብጽ ተራሮች ትዞራለች፣
የአባቷን አገር ኤፍራታን በማጣቷ ዋይ ዋይ በሉ፣
በመንገዷ ሁሉ የሕጻናት ደም ይፈስሳል። (ሰቆቃወ-ድንግል)
#በረከተ_ሥጋ_ወነፍስ_የምናገኝበት_የምሥጋና_ጊዜ_ይሁንልን።
@gosalbye ይቀላቀሉን።
# ቸሩ ሆይ
ቸሩ ሆይ ቸሩ ሆይ ናና
ቸሩ ሆይ አማኑኤል ናና
የእሥራኤል መና ቸሩ ሆይ ናና
ቸሩ ሆይ መድኃኒዓለም ናና
ቸሩ ሆይ - - - ለዓይነ ስውር መሪ
ቸሩ ሆይ - - - ምርኩዝ መመኪያ ነህ
ቸሩ ሆይ - - - አንተን የሚመስል
ቸሩ ሆይ - - - ምንም ነገር የለም
ቸሩ ሆይ - - - ምሕረትና ፍቅርህ
ቸሩ ሆይ - - - ወሰን ወደር የለው
ቸሩ ሆይ - - - ሳንወድህ ወደኸን
ቸሩ ሆይ - - - ፈልገህ ጠራህን
አዝ--------
ቸሩ ሆይ - - - ሰምተህ እዳልሰማህ
ቸሩ ሆይ - - - አይተህ እንዳላየህ
ቸሩ ሆይ - - - ሁሉን ታልፈዋለህ
ቸሩ ሆይ - - - ፍቅራዊ አባት ነህ
ቸሩ ሆይ - - - አማኑኤል ጌታ
ቸሩ ሆይ - - - ቸሩ ፈጣሪያችን
ቸሩ ሆይ - - -ውለታህ ብዙ ነው
ቸሩ ሆይ - - - ለእኛ የዋልክልን
አዝ--------
ቸሩ ሆይ - - - በከብቶች ማደሪያ
ቸሩ ሆይ - - - በዚያች ትንሽ ግርግም
ቸሩ ሆይ - - - ተወልዶ አዳነን
ቸሩ ሆይ - - - ጌታ መድኃኒዓለም
ቸሩ ሆይ - - - እልል በሉ ሰዎች
ቸሩ ሆይ - - - ባንድ ላይ ዘመሩ
ቸሩ ሆይ - - - ስብሐት ለእግዚአብሔር
ቸሩ ሆይ - - - በአርያም በሉ
ጨረቃ የጌታን ምጻት ትጠብቃለች በደም ደምቃ!
/አንቺ የምጻቱን ትንቢት ትናገርያለሽ፣እኛ ደግሞ ግርዶሽ እንላለን/
ከሁለት ሺ ዓመታት በፊት ሲጨረቃ ፈጣሪዋ በቀራንዮ አደባባይ በፈጠረው ፍጡር በሰው ልጅ ግፍን ተቀብሎ እራቁት ገላውን ሲሰቀል ከሰማይ ጣራ ስር ሆና በጌታ ላይ የሆነውን ማመን ስላቃታት ተጨንቃ በደም ተጥለቅልቃ ያየች፡፡
ይኸው ከሁለት ሺ ዘመን በላይ በተለይ በመቶ ዓመት ውስጥ እንደ ትላንቱ በደም ተሸፍና በዓመት ውስጥ ደግሞ በትንሹ ከሰባት ጊዜ ላላነሰ በደም ትቀላለች፡፡ የትላንቱ ልዩ የሚያደርገውና በልዩነት የተወራው ከዚህ በፊት ታይታ በማትታወቅበት ሁሌታ በደም ተመታ መታየትዋ ነው፡፡
ትላንት ጨረቃ በደም ደምቃ ስትታይ ብዙ አዋቂዎች ብዙ አሉላት፡፡ እርሷ ግን ምሁራን ያሉትን ሳይሆን ትንቢቱን ልትፈጽም በደም እንደተሸፈነች ማንም አላወቀላትም፡፡
ነብዩ ኢዮኤል ታልቁ የፍርድ ቀን ሲደርስ፣የጨረቃ በደም መረስረስ፣ምልክት እንዲሆነን ‹‹ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፣ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል›› ያለው ትንቢት ከነ ምልክት መፈጸሙን ያሳየናል፡፡ /ኢዮ 2÷31/
ባለ ራዕዩ ዮሐንስም ‹‹ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነ›› ያለውም ይኸው ደረሰ አየነው፡፡ /ራዕ 6÷12/
እኔ ምለው ጨረቃ፤ቀድሞ ጌታሽ እራቁት ገላውን ሲሰቀል ከፀሐይ ጋር በማበር፤ ፀሐይ በመጨለም፣አንቺ ደም በመልበስ ገላውን ለግፈኞች አይሁድ አናሳይም ብላችሁ ተአምር ሰራችሁ፡፡
ጨረቃ ሆይ እኔማ እንደ ያኔው በዘመናችን በጌታሽ ላይ ከጥንተ ስቅለት ባልተናነሰ እንዲሁም በባሰ መልኩ የእኛን ግፉ ተመልክተሸ ደም የለበስሽ መሰለኝ፡፡
ጨረቃ ይኸው አንቺ ደም ያለቀስሽለት፣ደም የለበስሽለት ጌታሽ በእኛ ባልታደልነው ትውልድና ዘመን እንደ ያኔው ጌታን በክህደት ሲሰቅሉት፣አምላክሽን ‹አማላጅ ነው›› ሲሉት፣አንዳንዶች በስሙ ሲሸቅጡበት፣እንደ ነብያትና ሐዋርያት ያልሾማቸው ነብይ ነን፣ሐዋርያ ነን እያሉ በጌታሽ ስም ስተው ሲያስቱ፣ህጉ ሲፈርስ፣ባላደራው አባት በኃጢአት ሲረክስ፣ከጌታ ይልቅ ገንዘብ ሲነግስ፣አማኝ አማሳኝ ሲሆን፣በቤተ እምነት ሌብነት ዘረኝነት ሲስፋፋ፣ደም ለብሼ ደም ልትፋ ያልሽ ነው የመሰለኝ፡፡
ጨረቃ ሆይ ከሰማይ ጣራ ላይ ሆነሽ ደም የለበሽው ጌታ የሞተላቸው ሰዎች ደማቸው በከንቱ ሲፈስ አይተሸ ነው?
ይኸው የአለም ፍጻሜ እየደረሰ ሲመጣ አንቺ በደም እንደምትሸፈኚ ትንቢት ተነግሯል፡፡ ትውልዱ ግን የጨረቃ ግርዶሽ እያለ ያንቺ ትንቢት ተጋርዶበት አለ፡፡
ጨረቃ ሆይ ብዙ ምስጢር የተሸፈነብን ትውልድ ሆነን ያንቺ በደም መሸፈን ትንቢት ሳይሆን እንደ ሰበር ዜና ‹‹በዚህ አከባቢ ከዚህ እስከዚህ ሰዓት የጨረቃ ግርዶ ይታያል/ታየ›› ሲባል እኛ ከማዘንና ከማልቀስ ይልቅ ያለቀስሽውን አንቺን ፎቶ እያነሳን ከአንዱ ወደ አንዱ በደም የራሰ ፎቶሽን እንቀባበላለን፡፡ እንደው ጨረቃ አንቺን አይተን ከዘመን እንቅልፋችን እንዳንነቃ እኛ ተጋርዶብን አንቺ ተጋረድሽ ስንል ምን አለሽን ይሆን?
ማን ያውቃል ጌታ ለፍድ ሲመጣ የማይጠቅም ዕንባ ከምናነባ እኔ አልቅሼ ህርሜን ላውጣላችሁ ብለሽ ቢሆንስ?
ማን ያውቃል ከቤቱ በህይወቱ የወጣ ሰው ሞቶ በአስከሬኑ ሲመለስ አይተሸ አንብተሸ ቢሆንስ?
ማን ያውቃል ደም ለብሰሽ መታየትሽ ግርዶሽ ሳይሆን እርስ በእርሳችን ደም ለመፋሰሳችን ትንቢት ቢሆንስ?
ማን ያውቃል ያንቺ በደም መጥለቅለቅ፣በከንቱ በሚፈሰው በንጹሐን ደም መጨነቅ ቢሆንስ?
ጨረቃ ለመሆኑ አንቺ ትጋርጃለሽ? ወይስ እኛ ነን እንዳናስተውል የተጋረደብን?
ደግሞስ ተጋረድሽ ነው ወይስ አለቀስሽ፣እንደ ቀድሞሽ በደም ተሸፈንሽ ነው የምንለው?
አንቺ በየዓመቱ፣በየዘመናቱ የተነገረልሽን ትንቢት፣የጌታን የእለተ ምጻት መቅረብ ደም በመልስ ንገሪን፤እኛም ትንቢት ሳይሆን ‹‹የጨረቃ ግርዶሽ›› እያልን እንደ ተጋረደብን እንኖራለን ጌታንም እንጠብቃለን፡፡
‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ?›› ኢሳ 53÷8
መ/ር ሄኖክ ወ/ማርያም
#ንቁ
@fikare_eyesus
ክፍል አንድ(1)
1.ሩሐንያ- ሩሕ አባድ
የአህዛብ የሴሰኝነትና የግብረሰዶም ክፉ መንፈስ
✝<< ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደ ሆነ አታውቅምን? እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ የጋለሞታ ብልቶች ላድርጋቸውን? አይገባም።>> 1ቆሮ 6፥20
ሩሐንያ ሩሕ አባድ ከሚለው የአረብኛና የእብራይስጥ ቃል የተወሰደ ሲሆን፤ ትርጉሙም፦ የጥፋት መንፈስ ሀይል ማለት ነው።
ሩሐንያ በእግዚያብሄር ፍቅርና በአርአያ ሥላሴ የተፈጠሩትን ሴቶችና ወንዶችን፤ ተፈጥሮአዊ ባህርያቸውን አዛንፎና ከመንገድ አስወጥቶ፤ ሥልቱን በከፍተኛ ደረጃ እየለዋወጠ፤ ትክከለኛ ወሲባዊ ግንኙነትን ተቃራኒ ወደ ሆነ የሴሰኝነትና የአመንዝራነት ግብር፣ ጠባይና አቅጣጫ የሚቀይር፣ የሚያዘበራርቅና የሚያስት፤ ሴቷን እንደ ወንድ፤ ወንዱን እንደ ሴት የሚያደርግ፤ በመጨረሻም የእግዚያብሄርን የተፈጥሮ ህግ ወደሚጻረረው ምግባር ማለትም፤ ሴቶች ከሴቶች ጋር፣ ወንዶች ከወንዶች ጋር ወሲባዊ ግንኙነት እንዲፈፅሙና የግብረ ሰዶማዊነት ኃጥያትን እንዲያዳብሩ የሚያነሳሳና የሚገፋፋ በተለይ ሠዎች እዚህ የጨለመ ህይወት ውስጥ ገብተው እንዲዳክሩ የሚያደርግ፤ በተለይ አሁን ያለውን ዘመናዊ ትውልድ አጥብቆ ለመግዛት የሚከተልና ተሳክቶለትም ብዙዎችን የያዘ፣ በዘር የሚዋረስና ቡዳ ሆኖ ከአይን ለይ እየተነሣ የሚስፋፋ፣ እንዲሁም፤ አይነ ጥላ ሆኖ የሚቀመጥና የሚያጠቃ አደገኛ መንፈስ ነው።
ይቀጥላል
#ንቁ
@fikare_eyesus
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹ማንኛውንም ዓይነት የኦርቶዶክስ ዝማሬዎች 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀በ tik tok ለማግኘት ከፈለጉ በዚህ link @mezmurzetewahido 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺follow ያርጉን።🙏🙏🙏🙏🌸🌸🌸🌸
Читать полностью…