gracebygrace | Unsorted

Telegram-канал gracebygrace - GRACE BY GRACE

-

👇በዚህ Channel 👉 አስገራሚ የቃሉ እውነቶች😱 👉 እውነተኛ ወንጌል 📖 " ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 6:14) This Telegram Address https://t.me/GRACEBYGRACE

Subscribe to a channel

GRACE BY GRACE

የክርስቶስ ሕግ

✍️ የክርስቲያን የሥራ ሕግ ግን ዓሥርቱ ትዕዛዛት ሳይሆን “የክርስቶስ ሕግ” ነው። ይህ ማለት ግን ከዚህ በኋላ መስረቅ፣ ወይም ዝሙት መፈጸም፣ ወይም በሙሴ ሕግ ውስጥ ያሉ የጽድቅ መመሪያዎች ተለውጠዋል ማለት ሳይሆን፣ አሁን ታማኝነታችን ለክርስቶስ ሕግ እንጂ ለብሉይ ኪዳን ሕግ አይደለም ማለት ነው።

✍️ ክርስቲያን ከክርስቶስ ሕግ በታች እንጂ ከሥራ ሕግ ኪዳን በታች አይደለም፤ ክርስቶስ ደግሞ ለክርስቲያን የሙሴ ሕግ ካደረገው በላይ በጣም ግልጽና ከፍተኛ የሥራ መገለጥ ሰጥቷል። ይህ ማለት ግን የክርስቶስ ሕግ “ቅዱስ፣ ጻድቅና በጎ” የሆኑትን የሙሴን ሕግጋት አስወግዷል ማለት ሳይሆን ፈጽሞታል እና አስበልጦታል ማለት ነው።

👇በዚህ Channel

👉 አስገራሚ የቃሉ እውነቶች😱
👉 እውነተኛ ወንጌል 📖
" ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 6:14)

This Telegram Address /channel/GRACEBYGRACE

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

• ፍርሃት ርስትህን ከመውረስ አይክልክልህ!

እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ። ኢሳያስ 41፡10

✍️ ሙሴ እግዚአብሔር እስራኤላውያን እንዲወርሱ ወደ ሚፈልገው ተስፋ 12 ሰላዮችን ላከ። ከመካከላቸው ሁለቱ ኢያሱና ካሌብ ወደ ምድሪቱ መልካም ዜና ይዘው ተመልሰው “ለእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ ዞረን የሰለልናት ምድርr እጅግ መልካም ናት። እግዚአብሔርስ ከወደደን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር ያገባናል እርስዋንም ይሰጠናል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው ብለው ተናገሩአቸው።” (ዘኁልቁ 14 :7 - 9)።

✍️ ሆኖም ሌሎቹ 10 ሰላዮች “ከእርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን፦ በኃይል ከእኛ ይበረታሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት4 አንችልም አሉ። ስለ ሰለሉአትም ምድር ክፉ ወሬ ለእስራኤል ልጆች እያወሩ፦ እኛ ዞረን የሰለልናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ምድር ናት፤ በእርስዋም ዘንድ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ረጃጅም ሰዎች ናቸው። በዚያም ከኔፊሊም ወገን የሆኑትን ኔፊሊም፥ የዔናቅን ልጆች፥ አየን፤ እኛም በዓይናችን ግምት እንደ አንበጣዎች ነበርን፥ ደግሞም እኛ በዓይናቸው ዘንድ እንዲሁ ነበርን አሉ። ”(ዘኁልቁ 13:31-33)።

✍️ ሁሉም አሥራ ሁለቱ ተመሳሳይ መሬት፣ አንድ ዓይነት ግዙፍ ሰው ነበሩr የተመለከቱት፣ ግን በሪፖርታቸው በጣም ልዩ ንፅፅር ነው የታየው! ኢያሱ እና ካሌብ የተለየ መንፈስ ነበራቸው - የእምነት መንፈስ (ዘኁልቁ 14:24)። እነሱ በእግዚአብሔር ተስፋዎች እና መልካምነት ላይ አተኩረው ነበር። ሌሎቹ ግን በፍርሀት ተውጠው ግዙፍነታቸውንx ብቻ አዩ። እናም ፍርሃቱ ሽባ አደረጋቸው!

✍️ ዛሬ፣ ምንም ያህል ሁኔታ በፊትህ ቢኖር፣ በእግዚአብሔር ቸርነት ላይ ማተኮር ምረጥ። እግዚአብሔር ባልተጠበቀ ሞገስ፣ ሰላም፣ ጥበቃ እና, አቅርቦት እንድትደሰት ክርስቶስ ዋጋውን እንደከፈለ ማሰላሰል ምረጥ። የምታየው ነገር በፍርሃት አያርድህ። የእግዚአብሔር ታማኝነትን ማየትህን ቀጥል ያን ጊዜ በበረከት የምትራመድበት አድርጎ ያለህበትን ይለውጠዋል!

/channel/gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

#የሚመጥን_ሀሳብ

ማሰብ ከእ/ር የተካፈልነው አንድ ባህሪ ነው። ሃሳብን መርጦ መተግበር ደግሞ ሰው በራሱ ላይ የሚያመጣው በረከት ነው። ማንም #ለሆዱ የሚስማማውን ምግብ #እንደሚመርጠው ሁሉ ለአዕምሮውም #የሚመጥን_ሃሳብን መመገብ ራስን መጥቀም ነው። ንፁህ ምግብ ሰውን ከበሽታ እንደሚከላከለው ሁሉ ንጹህና መልካም ሀሳብ ሰይጣናዊ ተልዕኮ ካለው ተግባር ያቅበዋል። አንድ ሰው #ምርጥ_አሳቢ የሚባለው መልካም ሃሳቦችን #መርጦ ለሌሎች #አካፍሎ #ምርጥ አሳቢዎችን ለማፍራት #የሚተርፍና የሚጠቅም #አሳቢ ሲሆን ነው።ቃሉ ሁሉም ሰው በደረሰበት ይመላለስ ይላል ግን ያ ማለት #ያልደረስክበት ሀሳብ ሲነገርህ ፥ አይ እኔ #በደረስኩበት ነው #ምመላለሰው ብለህ #የማሰቢያህን በር እንዳትዘጋ። ዛሬ በደረስክበት #እውነት ስትመላለስ ፥ ያልደረስክበት #እውቀት ላይ #ነገ ለመድረስ #ዛሬ በአይምሮህ #እባብ(አስተዋይ) ፥ በልብህ #እርግብ(ቅን) መሆን አለብህ።

━━━━━⊱✿⊰━━━━━
Https://t.me/Gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

 ኢየሱስ እረፍት ይሰጣል

እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ማቴዎስ 11፤28

✍️ ዕረፍትን ለመረዳት የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር ወይም የስነ-መለኮት ምሁር መሆን አያስፈልግህም። የሚያስፈልግህ ኢየሱስን ብቻ የግል አዳኝህ እና ጌታህ አድርገህ መቀበል ነው። ምክንያቱም እርሱ እረፍት የሚሰጥህ ጌታ - ኢየሱስ ነው!

✍️ ምናልባት ዛሬ በሰውነትህ ውስጥ ከባድ ሁኔታን እየተመለከትህ ይሆናል። ለመፈወስ ባደረከው ጥረቶች ሁሉ ደክሞህ፣ ግራ ተጋብተህ እና ዝለህ ከሆነ አሁን ወደ እርሱ መጥተህ “ጌታ ሆይ፣ በጣም ደክሜአለሁ እና ግራ ተጋብቻለሁ። እናም ፈርቻለሁ። እባክህን በእጆችህ መዳፍ ውስጥ ሸሽገኝ እና እረፍት ስጠኝ። በለው።

✍️ በፊቱ ምንም ማለት የማትፈልግ ከሆነ ምንም ማለት የለብህም። በእርሱ ፊት ብቻ ማልቀስ መንደባለል ወይንም ሌላ ነገር ማድረግ ይችላል። ምክንያቱም ምን እንደምታደርግ እና ምን እንደሚያስፈልግህ አስቀድሞ ያውቃል። እንባዎችህን የሚያብስ እርሱ በእርግጥ ያሳርፍሃል፤ ሰላም ይሰጥሃል። በውስጥም በውጭም የእርሱ ሙሉ ሰላም እስኪያጥለቀልቅህ ድረስ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ያበረታሃል!

✍️ በየትኛውም አስቸጋሪ ጊዜያቶች የእግዚአብሔርን እጅ ማየት ካስፈለገህ ወደ እረፍት ጌታ ኢየሱስ በመምጣት ያሉብህን ቀንበሮች ባጠቃላይ ማውረድ ይቻላል።

✍️ ጌታችን ኢየሱስ በምድር በሥጋው ወራት ሲመላለስ ያለው ነገር ያስገርመኛል፤ ሕግን ባለመፈጸም ሸክም ከብዷቸው ለሚመላለሱ አይሁዶች ሸክም የከበዳችሁ ወደ እኔ ኑ ነበር ያላችው። ማንያውም ሰው ሊፈጽመው ማይችለው ነገር ሸክም ይሆንበታል፤ ነገር ግን ከሸክሙ መላቀቂያው መንገድ በበጎ ፈቃደኝነት በጌታ እግሮች ፊት ሽክምን ማስቀመጥ እና ሰላም እና ረፍቱን መቀበል ነው!

✍️ ይሁን እንጂ በብዙ ቅዱሳን ዘንድ ይህ ነገር አይታይም፤ እንደውም በመጨነቅ ግራ በመጋባት ውጥረት ውስጥ ሲመላለሱ ይታያል። ወዳጄ ተጨንቀህ የማታስተካክለውን ሁሉ በጌታ አርፈህ ማስተካከል ትችላለህ!

✍️ ስለዚህ የሚያስጨንቅህንም ይሁን ግራ የሚያጋቡህን ነገሮች ወደ ጌን ብለህ ሁሉን ቻይ በሆነው ጌታ የተዘጋጀልህን እረፍት በየእለት ሕይወትህ አጣጥም!!!

/channel/gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

🔎እግዚአብሔር አባቴ ነው🔎

እግዚአብሔርን በሁሉም የሕይወታችን አቅጣጫ ማስገባት እና ከእርሱ ጋር እየተነጋገርን ኑሮአችንን ማራመድ እንችላለን። እግዚአብሔር 24/7 ከእኛ ጋር ለማሳለፍ እና አብሮን ውጫዊ ነገሮችን ለማስተዳደር ራሱን አቅርቦልናል። በራሳችን ጥበብና ጥረት ልንኖር አይገባንም እግዚአብሔርን የመሰለ አባት እያለን ደግሞ አሁን የምንኖረው አኗኗር ከኛ አይጠበቅም። ልጅነታችን ሰማይ ላይ የሚቀር ሳይሆን መሬት አውርደን ማጣጣም የምንችለው ነው። እግዚአብሔር አንድን እውነት ሲገልጥልን ወደውጭ የምንገልጥበትንም ጥበብ ያሳየናል። ችግሩና ግን ጥበቡን ሳንሰማ ያቺን እውነት ብቻ ይዘን እንሄዳለን ወይም ደግሞ ጥበቡን አውቀን ነገር ግን እርምጃ አንወስድም:: ስለዚህ የበራልንን እውነት በሙላት እስክንረዳው ድረስ እንስማ፤ ከዛም ባገኘነው ጥበብ እርምጃ እንውሰድ። በዚህ መልክ ነው እንደ እግዚአብሔር ልጅ በሙላት መኖር የምንችለው።

/channel/gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

ከዘር እርግማን ወደ ዘር በረከት
*******************
“በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤”

👉🏼 ብዙ አማኞች ምናልባት ኢየሱስ በሞተ ጊዜ ኃጢአታችን እንደተሰረየ ያውቁ ይሆናል፤ ምክንያቱም ደሙን አፍስሶአናል። በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት። (ኤፌ. 1 7፣ ዕብ 9 22) ግን ለምን በመስቀል ላይ መሞት ነበረበት፣ ምክንያቱም በኢየሱስ ዘመን በእስራኤል የነበረው ከፍተኛ ቅጣት በድንጋይ መወገር እንጂ መሰቀል አልነበረም።

👉🏼 ኢየሱስ በእንጨት የተሰቀለው "በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና ሬሳው በእንጨት ላይ አይደር፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር እንዳታረክስ በእርግጥ በዚያው ቀን ቅበረው።" የሚለውን ህግ ስለሚያውቅ ነው። (ኦሪት ዘዳግም 21 23) ከሕጉ እርግማን ሁሉ ሊቤዥን ፈልጎ ነበር፣ ስለዚህ “ርግማን ሊሆን” ወደ መስቀሉ ሄደ። የእርሱን በረከቶች ሁሉ መውሰድ እንድንችል ኢየሱስ ሁሉንም እርግማኖቻችን በመስቀል ላይ ወሰደ!


👉🏼 ኢየሱስን በተቀበለበት ቅጽበት በሕይወትህ ውስጥ ያለው እርግማን ሁሉ ተደምስሷል። ይህንን የምናገኝበት መንገድ ኢየሱስ ያደረገልህን በቀላሉ ማመን እና መመስከር ነው። “በኢየሱስ አማካኝነት የተባረኩ ነኝ” በል። በይበልጥ በተናገርከው እና ባመንከው መጠን የበለጠ አካል ታለብሰዋለህ።


👉🏼 ስለዚህ በሕይወትህ ውስጥ ጭቆና የሚሰማህ ቦታ ካለ፣ ለምሳሌ፣ መድኅኒት የሌለው በሽታ፣ “ክርስቶስ ከዚህ መድኅኒት አልባ በሽታ አድኖኛል። በእሱ ቁስል ተፈውሻለሁ አልቀበልም እና በኢየሱስ ስም ልቀቅ በል!” (1 ጴጥሮስ 2፡24) እስክታየው እና ፈውስህን አካል እስክታለብስ ድረስ አምነህ ተናገር!


“ነገር ግን አባቴ በካንሰር ሞተ፤ እናቴ በስኳር ሞተች እንደሰማሁት ከሆነ ደግሞ የዘር እርጋማን ነው። እኔም በወላጆቼ ዓይነት በሽታ እንደምሰቃይ አስባለሁ” ትለኝ ይሆናል



👉🏼 ወዳጄ፣ በመስቀል ላይ የፈሰሰው የክርስቶስ ደም ካንሰርን ጨምሮ በሽታዎችን ጨምሮ ከሁሉም እርግማንዎች ተቤዥቶሃል! እግዚአብሔር የካንሰርን ወይንም የስኳርን ብቻ የትኛውም ዓይነት በሽታ እና እርግማን በኢየሱስ ላይ በመስቀል ላይ ተወገወዷል። እናም ከዚህ በኋላ የኢየሱስን ሁሉም በረከቶች በአንተ ላይ ተደርገዋል። ስለዚህ፣ የኢየሱስ በረከቶች ብቻ በአንተ ላይ እንዲወርስህ እና እንዲቆጣጠርህ ጠብቅ!


👉🏼 ከዘር እርግማን ወደ ዘር በር በረከት በክርስቶስ የመስቀል ሞት ተሻግረሃል ስለዚህ በክርስቶስ ውስጥ ያለውን የዘርህን በረከት እንጂ በዘርህ ውስት የሌለውን እርግማን በማሰብ ጊዜህን አትፍጅ!

/channel/Gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

ጠባቂያችን እና መሸሸጊያችን - ኢየሱስ
********************
እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና። (መዝሙር 91፡3)

✍️ ዛሬ፣ በምንኖርበት ዓለም ከትውልድ እና ከዓመታት በፊት ያልተሰሙ አዳዲስ የቫይረሶች ዓይነት እንሰማለን። ዓለም ለብዙ ቫይረሶች ፈውስ አላገኘችም ከዚህ የተነሳ ብዙ ሰዎች በእነዚህ ቫይረሶች ለመያዝ ይፈራሉ።

✍️ ግን እንደ አማኝ እና የእግዚአብሔር ልጆች በዓለም ውስጥ ብንሆንም ከዚህ ዓለም አይደለንም። (ዮሐ. 17: 15–16) ስለዚህ ጥበቃችን ከዚህ ዓለም ሳይሆን ከጌታ ነው ማለት ነው። ከጌታ ነው ስል መጠጊያዬና ምሽጌ የሆነ ነው። እርሱም “ምናልባት” አይደለም፣ ግን በእርግጠኝነት ከአዳኝ ወጥመድ እና ከሚያስደነግጥ ቸነፈር ያድነናል ማለት ነው። (መዝሙር 91: 2)

✍️ በተለያየ ጊዜ እና ዓለም የተለያዩ ቫይረሶች ተከስተዋል ወደፊትም ይከሰታሉ። የእግዚአብሔር ልጆች እንደመሆናችን ግን ልባችንን በሚፈራረቁ ችግሮች ላይ ሳይሆ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው በሆነው እና በማይለዋወጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ልናሳርፍ ይገባል። (ዕብራውያን 13፡8)

✍️ ወዳጄ፡- የሌሎችን ሕይወት የገደሉ ገዳይ በሽታዎችን መፍራት አያስፈልግህም። እኔ ወይም ልጆቼ የቫይረስ ተጠቂ ሊሆኑ ይችላሉ ብለህ መፍራት የለብህም። ምክንያቱም ጌታ መጠጊያችን እና መሸሸጊያችን ሲሆን አንተም ሆንክ ቤተሰብህ አደገኛ ከሆኑ ቸነፈር ሁሉ ያድንሃል።

✍️ ምናልባት፣ አሁንም ይህንን ጽሁፍ እያነበብክ በሆነ ቫይረስ ተይዘህ ቢሆን እንኳ ከምታመልከው አምላክ የሚበልጥ ኃይል እንዳለው ማሰብህን ተው እና በክንፎቹ ፈውስን የተሸቀመውን የጽድቅ ጸሐይ (ኢየሱስ)፤ ከሙታን የተነሳውን ከዳዊት ዘር የሆነውን በቀን እና በለሊት ማሰብ እና ማሰላሰል ቀጥል! ፈውስህ ፈጥኖ በሰውነትህ አካል ይለብሳል! ሀሌሉያ ጌታ ለልጆቹ ሁል ጊዜ መልካም ነው!!!

/channel/Gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

ምክንያት እየፈሉ እግዚአብሔርን ማመስገን!

✍️ አመስጋኝ ልብ ያላቸው ሰዎች ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን ያወድሳሉ። ብዙ ጊዜ “እግዚአብሔር ቸር ነው!” ሲሉ ትሰማቸዋለህ። ለሚያገኙት ማንኛውም በረከት እግዚአብሔር እንደ ሆነ እውቅና ይሰጣሉ።

✍️ በረከቶችን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የሚያመለክቱ አሉ። ሲባረኩ ደስታቸውን መንገድ አድርገው ብቻ ይሄዳሉ። እግዚአብሔርን ለማመስግን ልባቸውን ምክንያት እንዲፈልግ ያደርጉታል ከዚያም ሁልጊዜ ይባርኩታል።

✍️ ኢየሱስ አንድ ቀን ወደ አንድ መንደር በሄደ ጊዜ ከሁለቱም ዓይነት ሰዎች ጋር ተገናኘ። በሥጋ ደዌ የተያዙ አሥር ሰዎች ወደ እሱ ጮኹ፣ “ኢየሱስ፣ አቤቱ፣ ማረን!” አሉ። (ሉቃስ 17 13)። አሁን፣ ኢየሱስን ለምሕረት ወደ እርሱ ስትጮህ እርሱ ሁልጊዜ ይሰማል። በሌላ ወቅት ✍️ ሁለት ዓይነ ስውራን “የዳዊት ልጅ ሆይ፣ ማረን!” ብለው ሲጮኹ። ተአምራቶቻቸውን ለመስጠት ጊዜ ወስዶላቸዋል (ማቴዎስ 9:27 እስከ 30 ተመልከት)።

✍️ እናም እነዚህ 10 የሥጋ ደዌ በሽተኞች ምሕረት ለማግኘት ወደ እሱ ጮኹ። ቆመ፣ ተመለከታቸውና “ሂዱ፣ ራሳችሁን ለካህናቱ አሳዩ” አላቸው። እና “ሲሄዱም ነጽተዋል” (ሉቃስ 17 14)። ግን አንድ ሰው ብቻ ተመልሶ አመሰገነው በኢየሱስ እግር ላይ ወደቀ። ቀጥሎ የተከተሉትን የኢየሱስ አሳዛኝ ቃላት ልብ በል: - “10ም የነጹ አልነበሩም? ዘጠኙ ወዴት አሉ? ” (ሉቃስ 17 17)።

✍️ ሌሎቹ ዘጠኙ ግልፅ በመሆነ መንገድ የሚያውቁት ያነፃቸው ኢየሱስ መሆኑን ነው። ሆኖም፣ ተመልሰው ሄደው እሱን ለማመስገን አልተቻላቸውም። ወዳጄ ሆይ፣ በረከቶች በሚመጡበት ጊዜ እግዚአብሔርን ማወደስ፣ ማክበር እና ክብር መስጠትን አስታውስ እና እርሱ በሕይወትህ ውስጥ ለሚገኙት ሁሉ በረከቶች ምንጭ መሆኑን እንደምታምን እውቅና በመስጠት ግለጥ።

✍️ ሰውየው ኢየሱስን ለማመስገን በተመለሰ ጊዜ የመፈወስ ተጨማሪ በረከት እንደ ተቀበለ ታውቃለህ? ኢየሱስም “ተነሳ፣ ሂድ፣ እምነትህ አድኖሃል” (ሉቃስ 17 19)። እሱ የሥጋ ደዌን ያነፃ ብቻ አልነበረም፣ የጎደሉትን ጣቶች አግኝቷል!

✍️ ወዳጄ ሆይ፣ ልብህ እግዚአብሔርን ሲያመሰግን ራስህ ለታላቅ በረከቶች ታዘጋጃለህ ትቆጥራለህ! ሁል ጊዜ ምክንያት እየፈለግክ እግዚአብሔርን አመስግን!

/channel/Gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

" እግዚኣብሄር በአንተም
በሌላም አይናደድም
ኣይቆጣምም ፡
መጥፎ ነገር እንኳን ብትሰራ

ራስህን ትጎዳለህ እንጂ
እርሱ በአንተ ላይ ያለዉን
ፍቅር ኣይቀይርም "

@Gracebygrace
@Gracebygrace
@Gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

📖ሮሜ 3 ቁ15-19
🏆የእግዚአብሔር ስጦታ

💢መጀመሪያ ከአዳም የተቀበልነው ስጦታ
#ሞት
#ኩነኔ

👆የአንዱ መተላለፉ ለዚህ ዳርጎናል።

💢የአምላካችን ስጦታ ግን
ኀያሌ መተላለፎችን ተከትሎ

✅ #ፀጋን

✅ #ፅድቅን

✅ #በህይወት_መንገስን አመጣ

"ከእንግዲ በአንድ ሠው መተላለፍ #ኩነኔ በሁሉ ሠው ላይ እንደመጣ፣እንዱሁ በአንዱ የፅድቅ ስራ ለሠው ሁሉ ህይወትን የሚሰጥ ፅድቅ ተገኘ።በአንዱ ሠው አለመታዘዝ ብዙዎች #ኀጢአተኞች እንደሆኑ፣በአንዱ ሠው መታዘዝ ደግሞ ብዙዎች ፃድቃን ይሆናሉ።"

⚠️በአንዱ ሠው አዳም አለመታዘዝ ኀጢአተኞች ተሠኝታችሁ ትኮነናላችሁ!!

⚠️በሁለተኛው አዳም በክርስቶስ መታዘዝ ደግሞ ፃድቀን ተሠኝታችሁ ከኩነኔ ነፃ ትሆናላችሁ!!

✅የምትታዩት ወይ በመጀመሪያው አዳም ነው ወይም ደግሞ በሁለተኛው አዳም በክርስቶስ ነው‼️‼️‼️‼️‼️
🕎ይ🀄️ላ🀄️ሉን🕎
👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾

/channel/gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

የመዳን ቀን አሁን ነው!

እርሱ፣ “በትክክለኛው ሰዓት ሰማሁህ፤ በመዳንም ቀን ረዳሁህ” ይላልና። እነሆ፤ ትክክለኛው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳንም ቀን አሁን ነው።
(2ቆሮን 6:2)

ይህ ጥቅስ ላልዳነ ሰው ለመስበክ የምንጠቀምበት ብቻ አይደለም:: ኢየሱስ የሰራልን ድነት በመንፈስ በነፍስና በስጋ ሁሉ የሚገለጥ ነው። ስለዚህ በመንፈስ ህያው ለመሆን ሰዓቱ አሁን እንደሆነ ሁሉ በነፍሳችንም ሆነ በስጋችን ኢየሱስ በከፈለው ዋጋ ለመዳን ሰዓቱ አሁን ነው። እግዚአብሔር ለማዳን ቀጠሮ አይሰጠንም። አንድ ያቃተንን ወይም ያልገባንን ነገር ብንጠይቀው በዛች ሰዓት ያበራልናል። ስለዚህ መዳን ወይም ማሸነፍ የምትፍልጉት ባህሪይ አስተሳሰብ ድክመት ወይም በሽታ አለ? ዕብ11:6 መጽሐፍ ቅዱሳችን "እንደሚለው ከልብ ወይም ያለምንም አማራጭ ከእግዚአብሔር ብቻ ለመቀበል ብንሻ ዋጋ ይሰጠናል።" ይለናል ስለዚህ አሁን ጠይቁት ያልገባችሁንና ያቃታችሁን ነገር ጠይቁት ከዚያም ምን ይህል እንደሚያወራን በግልጽ እናያለን።

Https://t.me/gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገስጹ።ቆላ 2:16.
# የእግዚአብሔር ቃል ዘላለማዊነት ያለዉ ለሰዎች መዳን የሚገኝበት ጥበብ የምሰጥ ቅዱስ ቃል ነዉ።/2ኛጢሞ3:15/
# ቅዱስ መጽሐፍቶች በሙሉ በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፈ ነዉ።ይህን መጽሐፍ ቅዱስ መረዳት የሚቻለው እንደ መለኮታዊ መገለጥ ተደርጎ ስቆጠር ብቻ ነዉ።
# የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅ ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።
# ይህ መጽሐፍ የሚጠቅመውም የእግዚአብሔር ልጆች ፍጹም እንዲሆኑና ማንኛውንም መልካም ሥራ ለመሥራት ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ያደርጋል።
# ይህ ቅዱስ ቃል፤ኢየሱስ የጴንጤ አምላክ ብቻ ሳይሆን የዓለም መንግሥታት ሁኔታ የሚቆጣጠር ወደር የለሽ መር መሆኑን ያስረዳል።
# ይህ ወንጌል የተጻፈው አንባቢዎች ኢየሱስ አዳኝ ሆኖ ይመጣል የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንዲያምኑና በእርሱ በማመናቸው ምክንያት የዘላለም ሕይወት እንደሚኖራቸው እንዲረዱ ነዉ።ዮሐ20:31/1ኛዮሐ.5:13/.
# ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ከፍተኛ አድናቆትና ክብር የሚገባው ታላቅ ሥነ ጽሑፍ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ግዜና ሥፍራ ለሚገኙ ህዝቦች ሊጠቅምና ልያድን የሚችል የምሥራች ቃል ነዉ።
# ሰማይና ምድር ያልፋል ቃሉ ግን አያልፍም።/ማቴ.ወ13:31/
# የአምላካችን ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል። ብሎ ይነግረናል፤/
ት.እሳ40:8/
# ይህን የእግዚአብሔርን ቃል የምጠብቅ ቢኖር ለዘላለም ሞትን አያይም ተብሎ ተጽፈዋል።/ዮሐ.8:51

@Gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

ታላቅ በረከት ላንተ ነው

✍️ ዲያቢሎስ የሆነ ነገር በሚጥልብን ጊዜ ተስፋ መቁረጥ የለብንም። በእውነቱ እግዚአብሔር ከእኛ ወገን ስለሆነ ወደ ታላቅ በረከት እንደሚለውጠው እርግጠኞች መሆን እንችላለን።

✍️ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰውን ሲፈጥር በምድር ላይ ባለው ሁሉ ላይ ሰውን ገዥ አደረገ። (ዘፍጥረት 1 26) አዳም በወደቀ ጊዜ ግን ኃጢአትና ሞት ወደ ዓለም ገባ፣ እናም ሰው ሥልጣኑን ለዲያቢሎስ አጥቷል።

✍️ ታዲያ ዲያቢሎስ አሸነፈ? በፍጹም፣ እግዚአብሔር ቤዛውን ለእኛ እንዲሞት ልጁን ኢየሱስን በመላክ የቤዛነት ዕቅዱን ፈጸመ። እናም የኢየሱስ ሞት አዳም ወደ ነበረው ስፍራ ከማስመለስ የዘለለ ብቻ እንዳልሆነ እንድናውቅ ይፈልጋል።

✍️ አብ ኢየሱስን ከሞት ሲያነሳው እኛ በክርስቶስ ውስጥ ሆነን ከእርሱ ጋር ተነሳን። በሌላ አገላለፅ፣ አሁን እኛ በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጠናል፣ “ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል!” (ኤፌ. 1 21) አዳም እንዲህ ዓይነት አቋም አልነበረውም። ስለዚህ በኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ አማካይነት ብዙ ተጨማሪ በረከቶችን ተቀበልን።

✍️ በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት ነፃ ካወጣቸው ወተት እና ማር ወደምታፈሰው ምድር እንዳወጣ እናነባለን። ዲያቢሎስ እስራኤልን ርስት እንዳይወርሱ ለማድረግ በተስፋይቱ ምድር ውስጥ ግዙፍ ሰዎችን በማስገባት የእግዚአብሔርን ዕቅድ ሊረክስ ወይም ሊከሽፍ ይችላል ብሎ አሰበ። እግዚአብሔር ግን ዲያቢሎስን አሳለጠ። ግዙፎቹ ቤቶቻቸውና ከተማቸውን እንዲገነቡ፣ ጉድጓዶች ቆፍረው ሰብሎች እንዲያድጉ ፈቅዶላቸዋል። ከዛም፣ እስራኤላውያንን ወደ ምድሪቱ ያመጣና ግዙፍ ሰዎች አወጣቸው!

✍️ ስለዚህ እስራኤል ያልገነቧቸውን ትልልቅ ቆንጆ ከተሞች፣ ያልሞሏቸውን መልካም ነገሮች ሁሉ የተሞሉ ቤቶችን፣ ያልቆፈሯቸውን ጉድጓዶች እና ያልተተከሉትን የወይን እርሻዎች እና የወይራ ዛፎችን ወረሱ። (ዘዳግም 6 10-11) ዲያቢሎስ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለው ዕቅድ እንዳይፈጽም ለመከላከል ቢሞክርም፣ በጣም ብዙ ተቀበሉ።

✍️ ዲያቢሎስ እንቅፋቶችን እና እርኩስ ሁኔታዎችን በአንተ ላይ ሊጥል ይችላል፣ ግን እግዚአብሔር እነዛን ክፉ እቅዶች ለታላቅ በረከታችሁ ያዞራቸዋል ምክንያቱም እርሱ ለእናንተ ነው!


/channel/Gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

የእግዚአብሔር ቃል ሰይፍ ነው!
“ኢየሱስም መልሶ፦ መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግሥቴስ ከዚህ ዓለም ብትሆን፥ ወደ አይሁድ እንዳልሰጥ ሎሌዎቼ ይዋጉልኝ ነበር፤ አሁን ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለችም አለው።” ዮሐንስ 18:36

የክርስቶስ መንግሥት መንፈሳዊ ነው፣ በሰዎች ልብ ውስጥ - አካላዊ አይደለም፣ ስለዚህ፣ እንደ ክርስቲያን የምናደርገው ትግል ከሥጋዊ የጦር መሳሪያዎች ጋር መሆን የለበትም፣ ነገር ግን በመንፈሳዊ የጦር መሳሪያዎች መሆን አለበት። መንፈሳዊ ኃይሎች በሰዎች ሥጋዊ ጠጦር መሳሪያዎች ሊሸነፉ አይችሉም። ለዚያም ነው ሐዋርያው ጳውሎስ በ (2 ቆሮ. 10 3-5)

“በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤ የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥ መታዘዛችሁም በተፈጸመች ጊዜ አለመታዘዝን ሁሉ ልንበቀል ተዘጋጅተናል።”

የእግዚአብሔር እና መንግሥት አካል ስለሆንን ጥቃት ሲሰነዘርብን በመንፈሳዊ የጦር መሣሪያችን መታገል አለብን። ውጊያችን በሰዎች ላይ ወይንም ከሰዎች ጋር አይደለም፣ ነገር ግን በሰዎች በኩል ከሚታዩት በስተጀርባ ከሚሠሩት መንፈሳዊ ኃይሎች ጋር ነው። እውነተኛው ጠላት ማን እንደ ሆነ መገንዘብ እና ጌታ በሰጠን መንፈሳዊ የጦር ዕቃ መታገል አለብን።

“የሰው ቁጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራም” (ያዕ. 1 20)። በሰዎች ላይ የምንቆጣው ቁጣ በቀጥታ በዲያቢሎስ እጅ ውስጥ ያስገባናል። በሰዎች በኩል የሚመጣብንን መንፈሳዊ ኃይል ለማሸነፍ መንገዱ ጌታ እየሱስ እንዳለው ሌላኛውን ጉንጭ ማዞር እና በመላካም ክፉን ድል መንሳት ነው። መንፈሳዊ የጦር ዕቃን መጠቀም አጋንንቶችን በሽብር ውስጥ እንዲሸሹ ያደርጋቸዋል።

ሐዋሪያው ጳውሎስ ከተናገረው ዋና መሳሪያዎች አንዱ ወንጌል፣ ማለትም የመንፈስ ሰይፍ (የእግዚአብሔር ቃል) ነው። የሰይጣንን ምሽጎች ሊያፈርስ እና ሊደመስስ የሚችል በእግዚአብሔር መንፈስ የተደገፈ ቃል ነው።

/channel/gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

🔎የእግዚአብሔርን ቃል በልባችሁ ትከሉ!🔎


ዘር በውስጡ ያለውን አቅም የሚገልጠው መሬት ላይ ሲተከል ነው: ልክ እንደዚሁ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ያለውን በረከት የምንካፈለው ቃሉን በልባችን ስንተክለው ነው:: አንድ ቃሉን በልባችን የምንተክልበት መንገድ ደግሞ በማሰላሰል ነው: በቃሉ ውስጥ ራሳችንን እስክናይ ድረስ ስናሰላስል: የእግዚአብሔርን ቃል በልባችን ስር እንዲሰድ እና ፍሬ እንዲያፈራ እንፈቅድለታለን::

@Gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

 ተስፋው በእምነት ደርሷል!

የዓለምም ወራሽ እንዲሆን ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው የተስፋ ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም። ሮሜ 4፡13

✍️ በሮሜ ምዕራፍ 4 ቁጥር 13 ውስጥ፣ እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዘሩ የዓለም ወራሾች እንደሚሆኑ የገባው ቃል በሕግ ሳይሆን፣ በእምነት ጽድቅ ነው።

✍️ ዛሬ፣ እኛ የኢየሱስ በመሆናችን፣ በተስፋ ቃሉ መሠረት የአብርሃም ዘር እና ወራሾች ነን (ገላትያ 3፤29)። በክርስቶስ ጻድቃን እንደሆንን ባመንን መጠን የእርሱን አቅርቦት የበለጠ እንለማመዳለን።

✍️ የዓለም ወራሽ እና የአብርሃም በረከቶች፣ ጥበቃ እና የተትረፈረፈ አቅርቦት በእምነት ወደ እኛ መጥቷል። ምንም እንኳን ምንም ዓይነት የእግዚአብሔር በረከት ባይገባንም፣ የልጁ የኢየሱስ መስዋእትነት እና የተፈጸመ ሥራ ጻድቅ ሆነናል፣ ለሁሉም በረከቶች ብቁ እንደሆንን ይህ እምነት ዋስትና ነው።

✍️ በመስቀል ላይ፣ ኢየሱስ ኃጢአታችንን ወስዶ ጽድቁን ሰጠን። ድህነትን ወስዶ የተትረፈረፈውን ሰጠን። ኃፍረታችንን ወስዶ ድሉን ሰጠን።

✍️ ዛሬ፣ በኢየሱስ የተፈጸመ ሥራ ያጸደቀንን እውነት፤ እናምናለን፣ እናሰላስለዋለን፤ ያን ጊዜ በአብርሃም በረከቶች መመላለስ እንጀምራለን።


/channel/Gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

እግዚአብሔር - ይወድሃል!

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዩሐንስ 3፡16

✍️ ደወል እስካልደወልከው ድረስ ደወል አይደለም። መዝሙር እስካልዘመርከው ድረስ መዝሙር አይደለም። ፍቅርም እስካልሰጠኸው ድረስ ፍቅር አይደለም። እግዚአብሔር ከ 2,000 ዓመታት በፊት አንድ እና ብቸኛ የሆነውን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰጠን፣ ይህም በምን ያህል ጥልቅ በሆነ ፍቅሩ እንደሚወደን ያሳየበት መንገድ ነው።

✍️ ለዚህ ነው የገናን በአል ባሰብክበት ወይም በምታከብርበት ጊዜ ሁሉ ይህንን አስታውስ - ገና እግዚአብሔር እንደሚወድህ ከሰማይ የተላከ ምልክት ነው። እግዚአብሔር ኢየሱስን እንደወደደ (በኢሱስ ቦታ ስምህን ማድረግ ትችላለህ) ይወድሃል። አንድያ ልጁን ሰጠህ። በልብህ ውስጥ የሚሰማህ ሥቃይ ሁሉ፣ የሚያልፍብህ ማናቸውም ብስጭት፣ ከዓይኖችህ የሚዘንቡ ዘለላ እንባዎች ሁሉ፣ እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል ምክንያቱም እርሱ በጥልቀት ስለ አንተ ያስባልና።

✍️ ኢየሱስ “እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።” (ዮሐንስ 10 10)። ጌታ በጣም ስለሚወድህ ስለ አንተ በመሞት የሚትረፈረፍ እና የሚበዛ ሕይወትን ሊሰጥህ መጣ። እሱ ደስተኛ እና ጥሩ ስኬት እንድታገኝ ይፈልጋል። የማይታየውን ነገር ግን በልጁ የተገለጠውን ፍቅሩን በማሰላሰሉ ወደ ታላቅ የተትረፈረፈ ሕይወት መግለጥ ጀምር!

/channel/Gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

ማን ነገረህ?

ዘፍጥረት 3:10

10 እርሱም አለ። በገነት ድምፅህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ ፈራሁ፥ ተሸሸግሁም።

11፤ እግዚአብሔርም አለው። ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን?

የአዳም መገኛ እግዚአብሔር ስለሆነ፣ ስለ አዳም ከእግዚአብሔር በላይ ሊያውቅና ሊናገር የሚችል አካል የለም! አዳም የእባቡን የስህተት መርዝ ከመስማቱ በፊት በእወነት ውስጥ ነበር የሚኖረው። አዳምን መገኛው እግዚአብሔር ከሚያውቀው እውነት ያጎደለውና በውሸት ክልል ውስጥ የከተተው የሰማው የውሸት እውቀት ነው።

ሰው ከእግዚአብሔር እውነት የሚጎድለው፣ ከመገኛው ውጪ ያለውን ድምጽ ሲያስተናግድ ነው። በመጀመርያ እግዚአብሔር አዳምን ሲፈጥረው እራቁቱን እንደሆነ አልነገረውም፣ አዳምም እራቁቱን እንደሆነ አያውቅም! እግዚአብሔር አዳም እራቁቱን እንደሆነ ያልነገረው፣ በእግዚአብሔር እውቀትና እውነት ውስጥ አዳም እራቁቱን ስለሌለ ነው! ለእግዚአብሔር አዳም ለብሶ ነው ያለው፣ ሥጋን!

የሰይጣን የውሸት ቃላት ያለህን እንደሌለክ አድርጎ መናገር ነው! ከእግዚአብሔር እውቀትና እውነት ውጪ ያለውን ቋንቋ ማስተናገድ ስትጀምር፣ እግዚአብሔር የሚጠይቅህ ነገር ማን ነገረህ የሚለውን ነው! አዳም እራቁቱን እንደሆነ እግዚአብሔር ካልነገረው፣ አዳምን ከእውነተኛው እውቀት ያጎደለውን ውሸት የሰበከው አካል አለ ማለት ነው! ለዝያም ነው እግዚአብሔር እኔ ስላንተ የማላውቀውን ነገር ማን ነገረህ ብሎ የጠየቀው።

ዛሬም በእግዚአብሔር አዕምሮ ውስጥ በሌለው ቋንቋ እራሳችንን የምንተረጉም ሰዎች አለን። እኔ የማልረባ ነኝ፣ ሀጢአተኛ ነኝ፣ ውዳቂ ነኝ፣ ተስፋ የለኝም የሚሉ ነገሮችን በራሳችን ላይ የምንናገር ሰዎች ብዙ ነን! ዛሬም የእግዚአብሔር ጥያቄ ማን ነገረህ? የሚል ነው! ምክንያቱም እግዚአብሔር ሀጢአተኛና የማይረባ ልጅ ስለሌለው!

ጽድቅ በውልደት የሚገኝ ዝርያ እንጂ በድርጊት የሚመጣ ልምምድ አይደለም! ብዙ ሰው ሀጢአተኛ ነኝ የሚለው ከድርጊቱ አንጻር እራሱን ለክቶ ነው! ነገር ግን እራሳችንን ማየትና መተርጎም ያለብን በድርጊታችን ሳይሆን በመስቀል ከተሰራው ሥራና እግዚአብሔር በክርስቶስ ውስጥ በሚጠራን ስያሜ ነው!

ሀጢአተኛና የማልረባ ነኝ ብሎ ማሰብና መናገር የመስቀሉን ሥራ ማኮሰስና እግዚአብሔርን መሳደብ ነው! ምክንያቱም ከእግዚአብሔር አብራክ ሀጢአተኛ ሰው መውጣት ስለማይችል! አዳም ሲወልድ ሀጢአተኛና የሞተን ሰው እንደሚወልድ ልክ እንደዝያው እግዚአብሔር ሲወልድ ክቡርና ጻድቅ ልጅን ነው የሚወልደው!

እግዚአብሔርን ማክበርና ማላቅ እራስን በማሳነስ ሳይሆን እራስን እግዚአብሔር በሚጠራው አጠራር በመጥራት ነው! ከእግዚአብሔር ስያሜ በሚያንስ ቃል እራስን መጥራት፣ እግዚአብሔር በመስቀል የሰራውን ሥራ ማግፋፋት ስለሆነ፣ እግዚአብሔርን ማክበር ሳይሆን መሳደብ ይሆንብናል!

ስለዚህ እራሳችንን በቃሉ ነህ በታባልነው እውነታ ውስጥ ነኝ በሚል ማንነት መኖር ተገቢ ነው!

ተባርካቿል!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

#የአዲስ_ኪዳን_ህይወት
/channel/gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

✍ስለ #ኢየሱስ መማር ለምን አስፈለገ??
1. እግዚአብሔር #ሌላ ትምህርት #ስለሌለው።
እግዚአብሔር ከዚህ ውጪ አስተምህሮ የለውም፤ ከኢየሱስ ጋር መጥተው የማይሰኩ የማይገጥሙ እርሱን የማያሳይ አስተምህሮዎችን አያውቃቸውም። 66ቱ መጽሐፍት በሙሉ በደንብ ካደመጥናቸው አንድ sound የሆነ አስተምህሮ አላቸው እርሱም #ኢየሱስ እርሱ #ክርስቶስ የእግዚአብሔር #ልጅ ነው የሚል፤እግ/ር ድንቆች ታምራቶች ምልክቶች ቢሰጥ እነዚህ ሁሉ ስለ ኢየሱስ የተማሪናቸውን ትምህርት ማጽናዎች ናቸው።እግዚአብሔር ቅዱሳን እንድማሩለት የሚፈልገው እንዲመሰረቱበት ሚፈልገው ትምህርት "ኢየሱስ"የሚለው ነው።
2.እግ/ርን #ለመስማት ስለ ኢየሱስ እንማራለን።
ማቴ 17:5 እግ/ር ተናገረ "ኢየሱስን ስሙት" ብሎ፤እግዚአብሔር መታዘዝ ማለት እርሱን #መስማት እና #ያለንን ማረግ ነው፤ ስለዚህ ኢየሱስን #ስንሰማ #ስንማሪ እግ/ርን እየሰማን ነው።
3.የስብከታችን ርዕስ #ኢየሱስ ስለሆነ
2ኛቆሮ 4:5
የስብከታችን ርዕስ መነሻው የሚሰሙን ሁሉ ይዘን የሚናስጉዙበት በዝርዝር በጥልቀት የሚናብራራው እርሱ ስለሆነ ስለ እርሱ እንማራለን፤
ንእሱ ሀሳቦች ዋናውን ሀሳብ ርዕስ እንደሚደግፍ በስብከታችን መሀል ሙሴ አብርሃም መባረክ ብንል የሚያጎሉት የሚያሳዩት ተደማምረው የሚመሩት የሚያደርሱት ወደ #ኢየሱስ ነው።
4. ሁሉ #በእርሱ #ለእርሱ #ከእርሱ ስለሆነ እንማራለን።
ፍጥረት በእርሱ ስለሆነ(ዘፍ 1፤ዮሐ 1:3)
ስለ ፍጥረት ስታጠኑ ሁሉም #የተፈጠሩት #የተጋጠሙት #የተደገፊት በእርሱ ነው።ለእርሱ ነው የተፈጠሩት።
የዘላለም ህይወት በአርሱ(1ኛዮሐ 5:11)
የእድሜ ርዝመት ብቻ ያልሆነው የክርስቶስ ህይወት መካፈል የሆነው የዘላለም ህይወት የሚገኘው በእርሱ በማመን ነው።
መዳን በእርሱ ስለሆነ(የሐዋ.ስራ 4:12)
ሰው የፈለኩትን #ማመን መብቴ ነው ይላል፤ይበል ዋናው ግን #ከዘላለም ሞት ያድነዋል የሚል ነው።መዳን በእርሱ ብቻ ነው።
ወደ እግዚአብሔር የሚንደርሰውብቸናው መድረሻ እርሱ ነው።(ዮሐ14:6)
ምድር ላይ ወዳሉ ነገሮች ለመድረስ 2እና ከዛ በላይ ብዙ መንገዶች አሉ ወደ እግ/ር መድረሻ ብቸኛው እርሱ ነው።......
✍ስለ ኢየሱስ ተምረን ተምረን እርሱን ሰምተን ሰምተን #አንጨርሰውም፤አስተምህሮው #እየቀጠለ እኛ #እንጨርሳለን የምድር ጉዛችንን።
እነዚህ እና በሌሎች ብዙ ምክንያቶች
ስለ ኢየሱስ እንማራለን።
#እውነትን #መግለጥ
Https://t.me/Gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

🔎የእግዚአብሔር ቃል ብርሀን ነው!🔎

የእግዚአብሔር ቃል ብርሀን ነው: ልክ ስንሰማው በውስጣችን ያለውን ጨለማ ሁሉ ያጋልጣል: ስለዚህም ልክ ሲበራልን ድሮ ጥያቄ የሚሆንብን ነገር ስለሚመለስልን በልባችን ነፃነት ይሰማናል:: ነገር ግን 'ገና' በውጫዊ ነገር ላይ ምንም የተቀየረ ነገር አይኖርም ምክኒያቱም: የቃሉን ብርሀን ስናገኝ አይናችንን ይከፍትልናል እንጂ: ወድያውኑ እኛ ወይም ሁኔታችን ተቀይሮ እንደቃሉ አንሆንም:: በጨለማ የነበረውን ሁሉ በግልፅ እናየዋለን:: ከዛ በብርሀን ያየነውን የጨለማን ስራ ሳንክድ: በበራልን እውነት ችግሩን የምናጠፋበትን ጥበብ በማግኘት እርምጃ መውሰድ አለብን:: ቃሉ አብርቶልን እንዳላየ የምንሸፋፍነው ከሆነ ግን: በምቹ ቦታችን(comfort zone) ላይ ነን: ምንምም ለውጥ ማምጣት አንችልም: የቃሉንም ፍሬ ማፍራት አንችልም::

Https://t.me/gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

በሽታ በአንተ ዘንድ ቦታ የለውም!!
እግዚአብሔር አባት እስራኤላውያንን ከግብፅ ምድር በታላቅ እጁ ካወጣቸው በኋላ በ(ዘፀ15፥26) የገባላቸው ኪዳን ነበር ትእዛዙንና ቃሉን ቢጠብቁ በግብፃውያን ላይ የመጣበቸውን በሽታ በእነሱ ላይ እንዲመጣ እንደማይፈቅድ እርሱ ፈዋሽ አባት መሆኑን ነግሯቸው ነበር።ይህንንም ቃሉን ለአርባ አመት በምድረበዳ ጠብቆ አኑሯቸዋል።አሁንም በክርስቶስ እየሱስ ሆነን በዚህ በፀጋ ዘመን ለምንኖር አማኞች የተሰጠን ቃል አለ በ(2ኛቆሮ5፥17)ማንም በክርሥቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት እንደሆነና አሮጌው ማንነቱ ልክ በክርስቶስ ሲሆን ተቀይሮ እግዚአብሔራዊ ህይወት(Zoe life) በውስጡ ስለገባ ሁሉም በአዲስ መልክ ተቀይሯል።ለምን ቢባል ሁሉም አማኝ በክርስቶስ እየሱስ ሲሆን የእርሱ የነበረው ውድቀትን የተላበሰውን ማንነቱን ልክ ክርሥቶስ እየሱስን የህይወቱ ንጉስ አድርጎ ሲሾም የዛሬ 2000 ዓመት የተሰሩለትን የፀጋ ስራዎች ተካፋይ ሆነ ማለት ነው።ስለዚህ ሁለንተናችን የክርስቶስ እንደሆነ እና ስጋው የመንፈስ ቅዱሥ ማደሪያ መሆኑን በትክክል በተረዳ አማኝ ላይ በሽታ ምንም አይነት ቦታ የለውም።
#ተፈፀመ!! #ተፈፀመ!! #ተፈፀመ!! #ተፈፀመ!!

/channel/Gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

(ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕ. 14)
----------
7፤ ከእኛ አንድ ስንኳ ለራሱ የሚኖር የለምና፥ ለራሱም የሚሞት የለም፤

8፤ በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፥ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን።

9፤ ስለዚህ ነገር ሙታንንም ሕያዋንንም ይገዛ ዘንድ ክርስቶስ ሞቶአልና ሕያውም ሆኖአልና።

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

🛐🛐🛐🛐🛐🛐🛐🛐🛐🛐🛐
እግዚአብሔር በሚያይበት ዓይን ራስን መመልከት
እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝ 1፤3
✍️ ጨለማ ምድርን በሸፈነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር “ብርሃን ይሁን” አለ ብርሃንም ሆነ። (ዘፍጥረት 1: 3) ለ 38 ዓመታት በቤተሳይዳ ውስጥ ሽባ የነበረ እና በቃሬዛ ላይ ተኝቶ የነበረውን ሰው ኢየሱስ “ተነስ፣ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” አለው። ወዲያውኑ ሰውዬው ተፈወሰ አልጋውን ተሸክሞ ተጓዘ። (ዮሐንስ 5፤ 8 - 9)
✍️ ሌሎች ማየት ያልቻሉትን ካላየህ በቀር እንደዚህ ዓይነት ቃላቶችን መናገር ቀላል አይሆንም። እግዚአብሔር ሰው በሚያይበትን መንገድ አያይም። ሰው ግን፣ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚመለከት ማየት ይገባዋል። ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ራዕይ ማየት መታደል ነው።
የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ በወረደ ጊዜ ነቢዩ በለዓም የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ፥ ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥ የወደቀው፥ ዓይኖቹም የተከፈቱለት እንዲህ ይላል፦ ያዕቆብ ሆይ፥ ድንኳኖችህ፥ እስራኤል ሆይ ማደሪያዎችህ ምንኛ ያምራሉ!” (ዘኍልቍ 24: 5-6)
✍️ በለዓም እስራኤልን እግዚአብሔር እንደሚያየው ካላየ በስተቀር በተፈጥሮ ዓይኖቹ በሚያየው ዕይታ ይህን ሊናገር አይችልም። በዚያን ጊዜ፣ እስራኤላውያን በምድረ በዳ ያጉረመረሙ እና ያማርሩ ነበር። እግዚአብሔር ግን ሲመለከታቸው በወንዙ ዳር እንደ ተተከሉ፣ ፍሬያማ እና የበለፀጉ የአትክልት ስፍራዎች ነበር።
✍️ ወዳጆች ሆይ፣ እግዚአብሔር በሚያይበት መንገድ እራስህን እንድታይ ትፈልጋለህ - እንግዲያው “በውሃ ወንዞች አጠገብ እንደ ተተከለች፣ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣ ቅጠሉ እንደማይጠወልግ፣ የሚሠራውም ሁሉ እንደሚከናወንለት ዓይነት ሰው ራስህን።
✍️ ምክንያቱም አንተ በክርስቶስ በውሃ ወንዞች አጠገብ እንደተተከለው ዛፍ በወቅቱም ያለወቅቱም ፍሬ የምታፈራ ተደርገሃል እና ራስህን እንደሚያፈራ ዛፍ አድርገህ ተመልከት። እንደማይጠወልግ፣ ጤናው እንደማይጠፋ ሰው ራስህንተመልከት። የምታደርገው ሁሉ እንደ ሚከናወንለት ዓይነት ሰው! ሀሌሉያ።
✍️ ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ራዕይ ተመልከት። የእርሱ ራዕይ ሁል ጊዜ ጥሩ እይታ ነው። ሁኔታዋችን በእግዚአብሔር ዓይኖች ውስጥ ባየህ ቁጥር የአንተ ሁኔታ እንደሚለወጥ ጥርጥር የለውም፤ ምክንያቱም እርሱ እንደሚያይ ስታይ በሕይወትህ ሁሉም አቅጣጫዋች ሁሉን ቻዩ አምላክ እንዲሠራ ትፈቅድለታለህ እና!

/channel/Gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

#ለእኔ_ሕይወት_ክርስቶስ_ሞትም_ጥቅም_ነውና።”
— ፊልጵስዩስ 1፥21

ለብዙ ሰዎች ህይወት መኖር አለመሞት ስለሆነ እንድን ሰው ህይወት እንዴት ነው ስትለው ነገሮች በሚፈልገው መንገድ እየሄደ ከሆነ ምርጥ ነው ይልሀል በፈለገው መንገድ እየሄደ ካልሆነ ደግሞ ህይወት ያስጠላል ይልሀል።።።

ጌታን የምናውቅ ግን አለም እንደሚያይ አናይም ለእኛ ህይወት #situation አይደለም #ህይወት በአዲስ ኪዳን #person ነው #ህይወት_እራሱ_ኢየሱስ_ነው

👉ኢየሱስም፦ ትንሣኤና #ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤”
— ዮሐንስ 11፥25

ኢየሱስ የሌለው ሰው ህይወት የለውም #ሙት ነው
#ሞት_የህይወት_ስርአት_ነው
ኤፌሶን 2
¯¯¯¯¯"¯¯¯¯¯
¹-² በበደላችሁና በኃጢአታችሁ #ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው #ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት #ተመላለሳችሁባቸው።


⁵ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን #ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥

#ኢየሱስ_ለኔ_ህይወት_ነው።።።።።።።።።
ህይወት ነው ስል #የመኖሬ ምክንያት እሱ ነው #ከሞት👈 ወደ #ህይወት👈 የተሻገርኩበት ከጨለማ ወደ ብርሀን የወጣሁበት እሱ ነው.......

#በሞተው ማንነቴ ላይ #ኢየሱስ ሲመጣ(#እንደ_ግል_አዳኜ_ስቀበለው) 👉እሱ #ህይወት ስለሆነ #ህይወቱ_በእኔ ላይ ሰራና #ህያው ሆንኩ ዛሬ በእኔ የሚኖረው እሱ ነው በአብ ፊት #መታያዬ እሱ ነው ልጅነት የዘላለም ህይወት ፅድቅ ያገኘሁት በእሱ ነው

ስለዚ አሁን👇👇 #አለኝ የምለው #ህይወት የሱ👈 ነው #ድኛለው #አምልጫለው ስል #ህይወቱ_በእኔ_ሆኖ_ነው።።።

የደረሰልን #ከዘላለም👈 #ፍርድ ከዘላለም #ሞት #ያስመለጠን ጌታ ስሙ ይባረክ.... #የራራልን #ኢየሱስ ቅጣታችንን #የተቀጣልን አበሳችንን ከኛ የወሰደ #ኢየሱስ ስሙ ይባረክ...... ተስፋ የሆነን #የማይጠፋ_ህይወት የሰጠን #ኢየሱስ👈 ስሙ ይባረክ.... #ድፍረት የሆነን #እረፍት የሆነን #ዋስትናችን_ኢየሱስ ስሙ ይባረክ....

#ፅድቃችን_ኢየሱስ 👉ስለወደድከን ስለታደከን ስላስመለጥከን ከለላ ስለሆንከን ተባረክ #ድፍረታችን አንተ #ብቻ👈 ነህ #ብቃታችን💪 አንተ #ብቻ👈 ነህ

#ህይወት_የሆንከን_ኢየሱስ_አንተ_ብቻ_ነህ


/channel/Gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

የእግዚአብሔርን ጸጋ ታምናለህ?🤔

የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ። ገላትያ 2፤21
✍️ ሐዋርያው ጳውሎስ በዛሬው ጥቅስ ላይ ምን እንደሚል በጥንቃቄ ልብ በል። እርሱ በሙላት እና በድፍረት እየተናገረ ያለው በመልካም ሥራህ ላይ እና፣ ባከናወንከው በአስርቱ ትእዛዛት ፍጹም ጻድቅ ለመሆን እየሞከርክ ከሆነ። ኢየሱስ በከንቱ ሞተ! “በከንቱ” ማለት - ያለምክንያት!

✍️ ስለዘህ ራስህን ጻድቅ በማድረግ እና እግዚአብሔርን ከአንተጋር እንዲሆን ለማድረግ በመልካም ስራዎችህ ላይ በመመርኮዝ የእግዚአብሔርን ጸጋ አታሳዝን። የኢየሱስ መስዋእትነት ለጽድቅ ከበቂ በላይ ነው። አንተም ሥራህ ምንም ይሁን ምን በኢየሱስ ሥራ ብቻ ጻድቅ እንደሆነክ ስታውቅ፣ የእግዚአብሔር ጸጋ በአንተ በሙላት ይገለጣል፣ ከአንተ ጎን መሆኑንም እርግጠኛ መሆን ትችላለህ።
✍️ ሁሉጊዜ በየቀኑ ለአንተ መልካም ነገር እንደሚመጣ መጠበቅ ትችላለህ ከጸጋው የተነሳ!

/channel/gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

ፍቅራችን ሳይሆን ፍቅሩ

የሕጉ አጠቃላይ መልዕክት “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ። ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት። በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል። የሚል ነው!” (ማቴዎስ 22 37-40)። ነገር ግን ይህንን ልጠይቅህ አንድ ሰው እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ፣ በፍጹም ነፍሱ እና ሐሳቡ መውደድ ይችላል?

✍️ መልሱ ግልፅ ነው። አንድም ይህን ማድረግ የቻለ የለም። በሕጉ መሠረት ማንም ሰው ያንን ፍጹም ፍቅር ሊለውጠው እንደማይችል እግዚአብሔር ሁሉን ያውቅ ነበር። ስለዚህ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ? ልጁን ኢየሱስን ላከ። ይህን ሲያደርግ እርሱ በትክክል ይህንን እያለን ነበር፣ “ሙሉ በሙሉ ልትወደኝ እንደማትችል አውቃለሁ፣ አሁን እኔን ተመልከት። በሙሉ ልቤ፣ በሙሉ ነፍሴ፣ አዕምሮዬ እና ኃይሌ ሁሉ እወድሃለሁ።” ይንንም ብሎ እጆቹን በስፋት ዘርግቶ ለእኛ ሞተ!

✍️ ወዳጄ ሆይ፣ ዛሬ ይህንን ልብህ ውስጥ ለማስገባት ጊዜ ውሰድ -ምክንያቱም የክርስቶስ መስቀል ሰው ፍጹም ፍቅር መገለጥ እና ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር መገለጫ አይደለም። መስቀሉ የእግዚአብሔር ፍጹም ፍቅሩ መገለጫ እና የእርሱ ፍጹም ጸጋ (ለእኛ የማይገባ ሞገስ) መገለጫ ነው።

✍️ ይህንን የበለጠ ግልፅ ለማድረግ ለአንተ የመጽሐፍ ቅዱስ ፍቅር ፍቺን ልንገርህ “በዚህ ፍቅር ፍቅር እግዚአብሔርን ስለ ወደድነው ሳይሆን እርሱ ስለ ወደደን እና ስለ ኃጢአታችን ማስተሰረያ እንዲሆን ልጁን ልኮታል።” የአዲሱ የጸጋ ቃል ኪዳን አፅንኦት (ያልተገባ ሞገስ) - እሱ ለእኛ ያለው ፍቅር እንጂ ለእሱ ያለን ፍቅር አይደለም። እናም ለእኛ ባለው ፍቅር ላይ ስናተኩር ለእርሱ እና ሌሎችን ያለ ምንም ጥረት በመውደድ ኃላፊነታችንን እንፈፅማለን!

/channel/gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

በቃሉ አማካኝነት ከኢየሱስ ጋር መነጋገር

ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው። ዪሐንስ 6፡63

በየቀኑ መጽሐፍ ቅዱስን ስትከፍት ኢየሱስ በውስጥህ በመንፈሱ እንዲያነጋግርህ ጠይቀው። እውቀትን ለመሰብሰብ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ አያነቡ። የጥሞና ጊዜ እንደወሰድክ እንዲሰማህ በስሜት እንዲሁ አትንቀሳቀስ። መጽሐፍ ቅዱስን ስትከፍት በእውነት ከኢየሱስ ጋር ህብረት አድርግ።

✍️ ኢየሱስ አለ፣ “… እኔ የምነግራችሁ ቃል መንፈስ ነው፣ ሕይወትም ነው።” ስለዚህ እራስህን በሕይወት ቃሉ ለመመገብ እና ማለምለም። ከእርሱ ጋር ህብረት ለማድረግ ወደ እግዚአብሔር ቃል ስትሔድ እርሱ ያነጋግርህ። እናም መጽሐፍ ቅዱስህን ስትዘጋ፣ ነቢዩ በኢሳያስ ምዕራፍ 55 እንደተናገረው “እናንተም በደስታ ትወጣላችሁ በሰላምም ትሸኛላችሁ፤ ተራሮችና ኮረብቶች በፊታችሁ እልልታ ያደርጋሉ፥ የሜዳም ዛፎች ሁሉ ያጨበጭባሉ። በእሾህም ፋንታ ጥድ በኩርንችትም ፋንታ ባርሰነት ይበቅላል፤ ለእግዚአብሔርም መታሰቢያን ለዘላለምም የማይጠፋ፥ ምልክት ይሆናል።” እንዳለ በሕይወትህ ስኬት ይሆናል (ኢሳይያስ 55 12-13)። በሌላ አነጋገር፣ የመርገም እና መካንነት ማስረጃዎች በፍሬያማ እና በበረከቶች ይተካሉ!

✍️ ወዳጆች ሆይ፣ መጽሐፍ ቅዱስህን ዛሬ ክፈት እና የጌታን ሕይወት ሰጪ ቃላቱን እግዚአብሔርን ጠይቅ። “ኢየሱስ ሆይ፣ ከአንተ ጋር መገናኘት እፈልጋለሁ። እንደቃልህ መግበኝ። በለው እርሱ በእርግጥ ከአንተ ጋር አብሮ ይገናኛል፣ የሕይወት ቃላቶች ለአንተ ያገለግሉሃል፤ በውጤቱም ወደ ጥሩ ስኬት ይመራሃል!

/channel/gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

ራሱ እግዚአብሔርን ለመምሰል የምንችልበትን ማንነት እና አቅም በክርስቶስ እየሱስ እኛ ዉስጥ አስቅምጦ በቃሉ ውስጥ ለሕይወትና እርሱን ለመምሰል የሚረዳንን እያንዳንዱን ነገር የሰጠን ጌታ አግዚአብሔር ይመስገን::

እግዚአብሔር አለም ከመፈጠሩ በፊት ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸውን የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና(ሮሜ 8:29) የልጁን መልክ በሙላት እንመስል ዘንድ የተለየን ከንቱነት ማንነታችን ያልሆነ ማንነታችን በማንነቱ ይሻር ዘንድ የእግዚአብሔር የልጁ ደም የፈሰሰልን የተመረጥን ጥርት ያልን የእርሱ ትውልዶች ነን የክርስትናችን ትርጉሙ ይሄ እውነታ ነው:: እግዚአብሔርን በማወቅ ዉስጥ እውነተኛ ማንነታችንን ማወቅ እና በእርሱ ማንነት መመላለስ አለ ፥ እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ(ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2 : 6) እንደሚል በእርሱ መመላለስ እርሱን በማወቅ የሚመጣ የእምነት ውጤት ነው:: እምነት ድርጊት ነው እምነት ስራ ነው እምነት በእርሱ መመላለስ ነው ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማስኘት አይቻልም(ወደ ዕብራውያን 11:6) በእርሱ መመላለስ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኝት የምንችልበት እግዚአብሔር እርሱ አባታችንን ማመስገኛ ሃይላችን ነው እደግመዋለው እምነት በእርሱ መመላለስ ነው:: እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው( ሮሜ ሰዎች 10:17) እምነት የእግዚአብሔር እውቀት ውጤት ነው እምነት እርሱ እግዚአብሔርን በማወቅ ውስጥ ያለውን እርሱን መምሰል የሚፈጥረው በእርሱ እንደ አግዚአብሔር ልጅ መመላለስን ይወክላል:: ቃሉ ያለኝን ያንኑ ነኝ:: ክብር ለመንፈስ ቅዱስ ይሁን!!

Https://t.me/Gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

ራስን በእግዚአብሔር ጸጋ ስር ማድረግ
************

✍ በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ምክንያት፣ እግዚአብሔር በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ በጽድቅ ለመባረክ ፈቃደኛ ነው። ኢየሱስ የኃጢአታችንን ቅጣት ስለ ተሸከመ፣ እኛ የማይገባን ጊዜም እንኳን ቢሆን፣ እግዚአብሔር በእኛ ላይ ጸጋን እንዲያሳርፍ ያደርገዋል። ይህንን ባመንክ ቁጥር እና በዚህ እውነት ላይ ካሰላሰልክ ራስህን ከእግዚአብሔር ጸጋ ሥር ታደርጋለህ።

✍ በእግዚአብሔር ጸጋ ሥር ስትሆኑ ምን ይከሰታል? በእግዚአብሔር ጸጋ ሥር ስትሆኑ ኃጢአት እና ውጤቶቹ ሁሉ በሕይወትህ ውስጥ የበላይ እንደማይሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።

✍ ሐኪምዎ ኮሮና (ኮቪድ 19) እንዳለህ ነገረህ እንበል። ወደ እግዚአብሔር ሂድና “አባት ሆይ፣ ጤንነቴን ወደ አንተ አመጣሁ እናም ከጸጋህ በታች አኖረዋለሁ።” በለው። ያንን ስታደርግ አንድ ነገር ይከሰታል። በምድር በምትኖረው ጤንነትት ላይ የተመረኮዘ አይደለም፣ የሕክምና ባለሞያዎች በተናገሩት ወይም የበሽታው ምልክቶች ምን ያህል ከባድ መሆኑ ላይ የተመሠረተ አይደለም። ይህንን ወይም ያንን ለማድረግ ባለህ ችሎታ ላይም አይመሠረትም። ከአንተ በማይጀምር መለኮታዊ በሆነ ያልተገባን፣ ያልደከምንበት እና በሥራችን ያልተሸለምነው የእግዚአብሔር ሞገስ ላይ የተመሠረተ ነው!

✍ የተወደድክ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ፣ እያንዳንዱን የሕይወትህን ክፍል እና ስፍራ በእግዚአብሔር ጸጋ ሥር አምጣው። አንድ በአንድ፣ ሁሉንም በማይመች የሕይወት ክፍል በእግዚአብሔር ጸጋ ሥር አስቀምጣቸው። አእምሮህን በመቆጣጠር እንድትጨነቅ የሚያደርግህ አሉታዊ ሐሳብ አሁንም ጠላት ሊሰጥህ ይችላል። ጠላት ያንን ካደረገ፣ ጠላት ፍላፃውን በወረወረበት አካባቢ በብዛት በእግዚአብሔር ጸጋ ሥር መሆኑን የሚያስታውስ ትንኮሳ ነው!

Https://t.me/Gracebygrace

Читать полностью…

GRACE BY GRACE

(1ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕ. 5)
----------
18፤ #ከእግዚአብሔር_የተወለደ_ሁሉ_ኃጢአትን_እንዳያደርግ፥ ነገር ግን #ከእግዚአብሔር_የተወለደው_ራሱን_እንዲጠብቅ_ክፉውም_እንዳይነካው_እናውቃለን።

19፤ #ከእግዚአብሔር_እንደ_ሆንን_ዓለምም_በሞላው_በክፉው_እንደ_ተያዘ_እናውቃለን።

20፤ የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።

Читать полностью…
Subscribe to a channel