👉በዚህ ቻናል ድንቅ የሆኑ ህይወትን በእርግጥም ለዋጭ የሆኑ እዉነተኛ የፀጋ ተከታታይ ትምህርቶች በፅሑፍ እና በኦዲዮ ሪከርድ ያገኛሉ።joine በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።በእርግጥም ይማሩበታል፣ይለወጡበታል፣ይጠቀሙበታል።የሚለቀቁ ትምህርቶችን ለማግኘት ከታች ያለዉን link በመጫን join ያድርጉ።👇👇👇👇👇
👉 @Gracegosple
👉 @Gracegosple
👉 @Gracegosple
👉 @Gracegosple
ለሌሎችም እንዲደርስ share share በማድረግ አብረዉን ያገልግሉ።
✋ተባርካቹሀል!
በእርግጥ ይወዱታል ይጠቀሙበታል።
👉የአዲስ ኪዳን እዉነታዎች ነገር ግን በግልጠት ሲነገሩ የማንሰማቸዉ ህይወቶን በእርግጥም የሚቀይሩ እና የእግ/ርን ቃል በጥልቀት እንዲያዉቁ ብሎም የመፅሐፍ ቅዱስ ዕዉቀቶን በእርግጥም የሚያሳድጉበት ትምህርታዊ channel ነዉ። በፅሑፍ እንዲሁም በድምፅ ተከታታይና ርዕሳዊ ትምህርቶችን ያገኛሉ።
👉አዳዲስና በዚህ channel የሚለቀቁ ትምህርቶች ወድያዉ እንዲደርሶ አባል ይሁኑ።አባል ለመሆን ሊንኩን ተጭነዉ join ያድርጉ።
Join Us👉
@Gracegosple
@Gracegosple
@Gracegosple
ለሁሉም እንዲደርስ Share ያድርጉ
ርዕስ፦ወንጌል/Gosple
ወንጌል ማለት ደስ የሚያሰኝ፣ለጆሮ የሚስብ መልካም ዜና ወይም የምስራች ቃል ማለት ነዉ።አስተዉሉ!ወንጌል መልካም የምስራች ዜና ወይም መልካም ብስራት ነዉ።
ብዙ ጊዜ ሰዎች አዲስ ነገር ደስ የሚያሰኝ ነገር ሊያበስሩን ሲፈልጉ ቀድመዉ በብዙ ደስታን በተሞላ ፊት በፈገግታ"የምስራች"ይሉናል።ልክ ይህንን ድምፅ የሰማ ማንም ቢሆን ክፉ ወይም የሚያስከፋ ወይም የሀዘን ወሬ አይጠብቅም።ምክንያቱም አብሳሪዉ ቀድሞ የምስራች ብሏላ።ስለዚህ ሁሉም ያንን መልካም ዜና ለመስማት ይጓጓሉ።ከዚህም በላይ ወንጌል መልካም ዜና ነዉ።
👉ወንጌል ደግሞ ስለ ኢየሱስ ብቻ ነዉ።
❝ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።❞
ሮሜ 1: 3-4
👉ደስ የሚያሰኘዉ ዜና ኢየሱስ ይባላል።
ምክንያቱ ደግሞ ይህ ነዉ።ኢየስሱ ስለ እኔ ሀጢአት እና በደል በእኔ ምትክ በመስቀል ተሰቅሎልኛል፣ደሙን ለዘለአለም ቤዛ እና መስዋዕት አድርጎልኛል፣ነብሱን ሳይሰስት ሰጥቶ ሞቶልኛል፣ሞትን ድል አድርጎ ተነስቶልኛል፣ሀጢአትን ለዘለአለም እንዳይገዛኝ አሸንፎልኛል፣አጥቦኛል፣አንፅቶኛል፣ቀድሶኛል፣አፅድቆኛል፣በእርሱ ስራ በማመን ብቻ የእግ/ር ልጅ/ቤተሰብ አድርጎኛል፣አክብሮኛል።አሜን
👉ይህ ነዉ ወንጌል/መልካሙ ዜና
ትሞታለህ፣ትጠፋለህ፣ትቀጣለህ፣እግ/ር ተጣልቶሀል ብሎ መልካም ዜና/ወንጌል የለም።ይህም ብቻ አይደለም።ኢየሱስን ትተህ ከራስህም ይሁን ከመፅሐፍ እየጠቀስክ ስለ ሌል ጉዳይ ብታወራ ብትናገር ይህም ወንጌል አይደለም።ምክንያቱም ኢየሱስ ሲናገር መፅሐፍ ሁሉ ስለ እኔ ይመሰክራሉ/ይናገራሉ ብሏል።ኢየሱስን የማይሰብክ፣የማያስተምር፣በሁሉ ኢየሱስን ማዕከል የማያደርግ ሰዉ እርሱ እዉነተኛ የወንጌል ሰባኪም አስተማሪም አይደለም።ወንጌል ኢየሱስ ነዉ ኢየሱስ ደግሞ የማይሰለች መልካም ዜና የምስራች ብስራት ነዉ!!!አሜን
ወንድማችሁ አገልጋይ ቤኪ ነኝ
0926389464
Join Us👉
@Gracegosple
@Gracegosple
@Gracegosple
መልዕክቱን ለሌሎች share በማድረግ አብረዉን ያገልግሉ።
ርዕስ፦መልካሙ እረኛ/መሪ
ወዳጆቼ ዛሬ ነብስን እና መንፈስን ዘልቆ የሚገባ ደስ የሚያሰኝ እዉነት ልንገራችሁ።
እርሱም ስለ እዉነተኛዉ እና መልካሙ እረኛ ነዉ።እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነዉ።
ኢየሱስ ሲናገር እንዲህ አለ እኔ እዉነተኛ የበጎች እረኛ ነኝ።መልካም እረኛ ነኝ።መልካም እረኛ ስለ በጎቹ ራሱን አሳልፎ ይሰጣል።ያም ብቻ አይደለም በእኔ በኩል የሚገባ ሁሉ ይድናል።ያም አልበቃም...እንዲህ አለ ይገባልም ይወጣልም መሰርያም ያገኛል።
የሚገርም ነዉ ይህንን ቃል ሳስብ በዉስጤ አaንድ ነገር በራልኝ እርሱም የእረኛ እና የበግ ህይወት!
ወዳጆቼ አስተዉላችሁ ታዉቃላችሁ እረኞችን?
በጎቻቸዉን ወዴት እንደሚያሰማሩ፣ምን እንደሚያበሉ፣ምን እንደሚያጠጡ፣በጎቹን ደስተኛ ሊያደርጋቸዉ የሚችለዉ ቦታ እና አካባቢ የት እንደሆነ እየሰበ ይዉላል እያሰበም የድራል።ምክንያቱ ደግሞ...
የእረኛዉ ደስታ የበጎቹ መብላት፣መጠጣት እና መጥገብ ነዉ።እነርሱ ጠግበዉ መብላታቸዉ የእረኛዉ ደስታ ነዉ።
በተቃራኒዉ ደግም በጎችን እንይ ስለምንም ነገር አያስቡም አይጨነቁም ምክንያቱም እረኛዉ አስቦ ባደረዉ እነርሱ ግን እንዲያዉ ይሰማራሉ።
መዝሙረኛዉ ዳዊት በመፅሐፉ ላይ እንዲህ አለ...
እግዚአብሔር አለ እረኛዬ ነዉ።
የሚያሳጣን የለም።ምን ማለት ነዉ?በእርሱ ዉስጥ ላጣ የምችለዉ ነገር የለም።
በለመለመ መስክ ያሳድረኛል።መልካም በሆነ ጥጋብ ደስታ በምላበት ያኖረኛል።
በእረፍት ዉሃ ዘንድ ይመራኛል።ዋዉ
እረፍት እና የተረጋጋ የተመቻቸ ወይም እርካታ ባለበት ይመራኛል።
ይህ ሁሉ የመልካሙ የእዉነተኛዉ መሪ እና አባት ማንነት ነዉ።
እርሱ ባሰበልን እኛ በደስታ እንኖራለን።
የኔ ጥጋብ፣የኔ ማግኘት፣የኔ ስኬት፣የኔ ማማር፣የኔ ማደግ የእርሱ ደስታ ነዉ።አሜን
ተባርካቹሀል።
ወንድማችሁ አገልጋይ ቤኪ ነኝ
0926389464
Join Us👉
@Gracegosple
@Gracegosple
@Gracegosple
መልዕክቱን ለሌሎች share በማድረግ አብረዉን ያገልግሉ።
ርዕስ፦የእግዚአብሔር ማንነት
በዚህ ሀሳብ ዉስጥ ትልቅ ቁምነገር ለማንሳት እፈልጋለሁ እርሱም ትክክለኛዉ የእግ/ር ቃል የሚነግረንን የእግ/ር ማንነት እንድናዉቅ ነዉ።
ባህሪ እና ማንነት ፈፅሞ የተለያዩ ነገሮች ናቸዉ።ለምሳሌ
ፍቅር ለሰዉ ልጅ ከእግ/ር የተካፈለዉ ባህሪ ሲሆን የእግ/ር ግን ማንነቱ ነዉ።
መልካምነትም እንዲሁ ለሰዉ ልጅ የተካፈለዉ ባህሪ ሲሆን የእግ/ር ግን ማንነቱ ነዉ።
ምንድነዉ ባህሪ?
ምንድነዉ ማንነት?
ባህሪ ማለት በልምምድ፣በስልጠና፣እና ከሌሎች በመኮረጅ የሚመጣ ወይም የምንካፈለዉ ሲሆን
ማንነት ግን ልክ እንደ ፆታ በሉት።ወንድ ወንድነቱን ሴትም ምንም ወንድ ልትመስል ብትችልም ነገር ግን ሴትነትዋን መቀየር እንደማትችል ሁሉ...
መልካምነት፣አፍቃሪነት፣ደግነት እና አባትነት ሁሉ የእግ/ር ባህሪ ሳይሆኑ መቀየር የማይችላቸዉ የእርሱ ማንነቶች ናቸዉ።
አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በራሳቸዉ መለዋወጥ በሁኔታዎች መቀያየር እግ/ርም አብሮ የሚለዋወጥ ይመስላቸዋል።
አንዳንዴ መልካም ሲሻዉ ደግሞ ክፉ
አንዳንዴ አፍቃሪ አንዳንዴ ደግሞ የሚጣላ
ብርቱ ስንሆን የሚሰጥ ስንደክም ደግሞ የሚቀማ
ጥሩ ስንሆን የሚደሰት የሳትን ቀን ደግሞ ቀበቆ ወይ ጅራፍ አንስቶ የሚቀጣ
ብቻ ብዙ ብዙ
❝ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።❞
ዕብራውያን 4: 15
አስተዉል በአንተ መለዋወጥ ዉስጥ አብሮ የሚለወጥ የእግ/ር ማንነት የለም።
መፅሐፍ እንዲህ ይላል
❝በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።❞
ያዕቆብ 1: 17
አገልጋዮችህ ከነገሩህ ሀይማኖት ካስተማረህ እግ/ር ይልቅ ልጁ ኢየሱስ ስለ አባቱ የተረከዉን በደንብ አንብብ።
ሉቃ 15 ሙሉ ታሪኩን እንድታነቡ እጋብዛለሁ።
እግ/ርን በምድራዊዉ አባትህ መልክ እና ባህሪ አትሳለዉ።አንዳንድ ሰዎች ይገርሙኛል የእግ/ርን አባትነት የሚስሉት ልክ እንደ ስጋዊዉ አባት ነዉ።ለምሳሌ
ነጭናጫ እና ቁጡ ወይም ሁሌ ባጠፉ ቁጥር በዱላ የሚላቸዉ ስለሆነ እግ/ርም እንደዛዉ ይመስላቸዉል።
አንዳንድ አባት ደግሞ ሁሌም ፊቱ እንደጠቆረ እንደተኮሳተረ ብሎም ዱላ ከእጁ የማይለይ ነዉ።እንዲህም የሚስሉ አይጠፉም።
ወዳጄ እግ/ር ፍፁም ፍቅር እና መልካም በፈገግታ የተሞላ ልጆቹን ሲያይ የሚስቅ አባት ነዉ።
ተባርካቹሀል!
ወንድማችሁ አገልጋይ ቤኪ ነኝ
0926389464
Join Us👉
@Gracegosple
@Gracegosple
@Gracegosple
መልዕክቱን ለሌሎች share በማድረግ አብረዉን ያገልግሉ።
ርዕስ፡-የኢየሱስ ደም
ክፍል 2
የኢየሱስ ደም ለእርግማን,ለሞት,ለኩነኔ ወይም ለፍርድ የፈሰሰ ሳይሆን ለተቀበሉት ሁሉ መንፃትን,ፅድቅን,ቅድስናን,ቤዛነትን,ለእግ/ር መንግስት ብቁነትን እና የእግ/ር ልጆች/ቤተሰብ/ የመሆንን ስልጣን የሰጠን ደም ነዉ።
ሰዉ በራሱ ስራ, በራሱ ልፋት, በራሱ ጥረት እና ትጋት አለኝ ወይንም ሰርቻለሁ በሚለዉ በራሱ ፅድቅ ወደ እግ/ር ፊት የመቅረብ እና የመግባት ድፍረት የለዉም።
አሁን በእግ/ር ፊት የመቅረብ እና የመታየት አቅማችን,ብቃታችን,ንፅህናችን,ፅድቃችን,በአብ ፊት ለብሰን የምንታይበት የቅድስና ልብሳችን የኢየሱስ ደም ይባላል።
መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል...
ዕብራውያን 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥
²³ በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥
²⁴ የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።
የአቤልን ደም በደንብ አስታዉስ በወንድሙ ቃየል ምክንያት የፈሰሰ ደም ነዉ።እግ/ርም ቃየልን እንዲህ አለዉ"የወንድምህ ደም ወደ እኔ ይጮሀል"።ለምን የሚጮህ ይመስላቹሀል?
ለፍርድ እኮ ነዉ።ወንድሜ ላይ ፍረድበት የሚል የፍርድ ድምፅ።
የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።
የኢየሱስም ደም እኮ ልክ እንደ አቤል ደም ይጮሀል።የሚጮኸዉ ግን እንደ አቤል ደም ለፍርድ ሳይሆን ስለ እኔ እና ስለ አንተ ድምፁን ከፍ አድርጎ ለምህረታችን,ለፅድቃችን,ለቅድስናችን,ለደህንነታችን,ይጮሀል። ዋዉ ዋዉ ዋዉ ክብር ለደሙ!!
ተባርካቹሀል።
ወንድማችሁ አገልጋይ ቤኪ ነኝ
0926389464
Join Us👉
@Gracegosple
@Gracegosple
@Gracegosple
መልዕክቱን ለሌሎች share በማድረግ አብረዉን ያገልግሉ።
ርዕስ:-የእግ/ር ልጅነት
በዛሬዉ ትምህርት አዘል መልእክቴ ላስተላልፍ የፈለኩት ስለ እግ/ር አባትነት እና ስለ እኛ ልጅነት ነዉ።
በዚህ ትምህርት ዉስጥ ብዙ አዳዲስ እዉቀት እና ህይወት ለዋጭ የሆነ እዉነት እንደምናገኝ አምናለሁ።
ብዙ ሰባኪዎች እና አስተማሪዎች ስለ እግ/ር አባትነት እና ስለ አማኝ ልጅነት ብዙ ብዙ ሲባል እንሰማለን።ዛሬ ግን እዉነታዉን እናያለን።
በመጀመርያ ሰዉ ሁሉ በእግ/ር መልክ እና አምሳል የተፈጠረ የእግ/ር ክቡር ፍጥረት ነዉ።ይህ ማለት ደግሞ ሰዉ ሁሉ የእግ/ር ክቡር የሆነ ፍጥረት እንጂ የእግ/ር ልጅ ነዉ ማለት ግን አይደለም።
ልጅነት የሚገኘዉ እየሱስ ክርስቶስን በማመን እና የህይወታችን ብቸኛ አዳኝ እና ጌታ አድርጎ በመቀበል የሚገኝ ነፃ ስጦታ ነዉ።
ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።
¹² ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤
¹³ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።
አየህ የእግ/ር ልጅ መሆን የሚቻለዉ በዚህ መንገድ ብቻ ነዉ።
አልያ ግን ከእግ/ር ጋር የሚኖርህ ግንኙነት የፈጣሪ እና የተፈጣሪ,የጌታ እና የባርያ አይነት ህይወት እንጂ ፈፅሞ የልጅ እና የአባት ግንኙነት አይኖርህም።
ልጅ ስትሆን እግ/ርን በስሙ,በአምላክነቱ,በጌትነቱ እና በፈጣሪነቱ በፍርሀት እና በጭንቀት ስሜት መጥራት እና መቅረብ ሳይሆን በልጅነት ስልጣን እና ስሜት አባቴ,አባዬ,አባ,አባባ....ብሎ የመጥራት መብት ይኖርሃል።ይህ ብቻ ሳይሆን በአንተና በእግ/ር መካከል ያለዉ ግንኙነት ፈፅሞ የአባትና የልጅ ግንኙነት ይሆናል።ዋዉ አሜን!
ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና።
¹⁶ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።
ይህ ነዉ ደስ የሚያሰኘዉ እዉነት።ይህ ነዉ የማይገኝ ዉድ ስጦታ።የትልቁ ሁሉ የእርሱ የሆነዉ የእግ/ር ልጅ መሆን።
ሌላዉ ደግሞ ፈፅሞ መዘንጋት የሌለብህ ጉዳይ ልጅ አባቱን የመዉረስ መብት እና በአባቱ ንብረት እና አባቱ ባለዉ ነገር ሁሉ ላይ ባለ ሙሉ ስልጣን መሆኑ ነዉ።ዋዉዉዉ
ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።
¹⁷ ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።
አሁን የእግ/ር ልጅ መሆንህን እርግጠኛ ሁን።ስለዚህ አንተ አባትህን የመዉረስ መብት አለህ።ቃሉ የአባትህን ንብረት ብቻ አይደለም አባትህን እግ/ርን ጭምር ወርሰኸዋል።
እግ/ር ያንተ ነዉ።
እግ/ር አባታችን ለልጆቹ የሚሰጠዉ ክፉ ስጦታ የለዉም።መልካም እና በጎ ስጦታ ብቻ እንጂ።
ያዕቆብ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ።
¹⁷ በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።
¹⁸ ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።
ዋዉ ዋዉ ዋዉ
አየህ በልጅነት ስልጣን ዉስጥ በመኖር የምትቀበለዉ የምትወርሰዉ ሁሉ ለአባትህ ያለዉን ብቻ እና ብቻ ነዉ።እንግዲያዉስ እግ/ር ያልሰጠን ያልተቀበልነዉ የለም። አሜን
አባትህ መልካም ብቻ ነዉ።አንዳንድ ቀን ክፉ አይሆንም።አንተን ሊጠላህ አይችልም።
ደክመህ እንኳን ቢሆን መፀለይ እንኳን ታክቶህ ቢሆን ከቤተ ክርስቲያን ርቀህ እንኳን ቢሆን በድካም እና በበደለኝነት ስሜት ዉስጥ እንኳን ብትሆን ቃሉ እንዲህ ነዉ የሚልህ አባትህ እንዲህ ይልሀል፡-
ላልጠላህ ወድጄሀለዉ
አንተ የኔ ብቻ ነህ
ከእጄ ማንም አይወስድህም
አልጥልህም
አልተዉህም
እኔ አሁንም አባትህ ነኝ አልቀየርም እንዲህ ነዉ የሚልህ።
ባንተ ብርታት እና አለመበርታት በአንተ ጥንካሬ ላይ የተመሰረተ አባትነት የለም።
አባትህ ዛሬም ይወድሀል።አባትህ አሁንም አንተን እያየ እየጠበቀህ ነዉ።አይደለም ክፉ ነገር ሊያመጣብህ እና ሊሰጥህ ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሀል።እንደ አይኑ ብሌን ያይሀል።
የበደለኝነት የጥፋተኝነት የሀጢአተኝነት ስሜት ዉስጥ ነህ?እመነኝ አንተን የሚቀጣ እጅ የለም እንደዉም በተቃራኒዉ የምህረት በሩን ከፍቶ እጁን ዘርግቶ ከመች መች ይመለሳል ከመች መች ይመጣል ብሎ የሚጠብቅ አባት አለህ።
ስትመጣ ስትመለስ እመነኝ በቁጣ ሳይሆን የሚጠብቅህ ግብዣ እና ድግስ አዘጋጅቶ ይቁበልሀል። Ohh My God
ሉቃስ 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ እንዲህም አለ፦ አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት።
¹² ከእነርሱም ታናሹ አባቱን፦ አባቴ ሆይ፥ ከገንዘብህ የሚደርሰኝን ክፍል ስጠኝ አለው። ገንዘቡንም አካፈላቸው።
¹³ ከጥቂት ቀንም በኋላ ታናሹ ልጅ ገንዘቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፥ ከዚያም እያባከነ ገንዘቡን በተነ።
¹⁴ ሁሉንም ከከሰረ በኋላ በዚያች አገር ጽኑ ራብ ሆነ፥ እርሱም ይጨነቅ ጀመር።
¹⁵ ሄዶም ከዚያች አገር ሰዎች ከአንዱ ጋር ተዳበለ፥ እርሱም እሪያ ሊያሰማራ ወደ ሜዳ ሰደደው።
¹⁶ እሪያዎችም ከሚበሉት አሰር ሊጠግብ ይመኝ ነበር፥ የሚሰጠውም አልነበረም።
¹⁷ ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ፦ እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ።
¹⁸ ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና፦ አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥
¹⁹ ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ።
²⁰ ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ። እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት፥ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው።
²¹ ልጁም፦ አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥ ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም አለው።
²² አባቱ ግን ባሪያዎቹን አለ፦ ፈጥናችሁ ከሁሉ የተሻለ ልብስ አምጡና አልብሱት፥ ለእጁ ቀለበት ለእግሩም ጫማ ስጡ፤
²³ የሰባውን ፊሪዳ አምጥታችሁ እረዱት፥ እንብላም ደስም ይበለን፤
²⁴ ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም። ደስም ይላቸው ጀመር።
እኔ የእግ/ር ልጅ ነኝ።
እግ/ር ደግሞ አባቴ ነዉ።
ወንድማችሁ አገልጋይ ቤኪ ነኝ
ተባርካቹሀል።
ወንድማችሁ አገልጋይ ቤኪ ነኝ
0926389464
Join Us👉
@Gracegosple
@Gracegosple
@Gracegosple
መልዕክቱ ለሌሎች share በማድረግ አብረዉን ያገልግሉ።
የክፋት እና የጥፋት ሁሉ ምንጭ ሌባዉ/ሰይጣን/ነዉ።ሰይጣን መልካም እና ደግ ነገር አስቦም አድርጎም አያዉቅም።ለወደፊትም አያደርግም።ምክንያቱም...
ዮሐንስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤
ኢየሱስ የመልካምነት ሁሉ, የደግነት ሁሉ,የቸርነት ሁሉ.የፍቅር ሁሉ,በቃ የህይወት ሁሉ ምንጭ ነዉ።
ዮሐንስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።
⁸ ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም።
⁹ በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል።
¹⁰ ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።
ኢየሱስ የሰጠን ህይወት ብቻ ሳይሆን የበዛ እና የሚትረፈረፍ ህይወትም ጭምር ነዉ።
እንዲህ ብያለሁ ...
የተቀበልኩት ህይወት እየበዛ እና እየጨመረ የሚሄድ ህይወት ነዉ።አሜን
እናንተም ይህን ቃል ለራሳችሁ አውጁ።
ተባርካቹሀል!
ወንድማችሁ አገልጋይ ቤኪ ነኝ
0926389464
Join Us👉
@Gracegosple
@Gracegosple
@Gracegosple
መልዕክቱን ለሌሎች Share ያድርጉ
Beki Bekisho:
ርዕስ፦ሁለቱ አዳሞች
የጌታ ሰላም እና ፀጋ ለእናንተ ይሁን!
ዛሬ በጣም ትልቅ እና ሁሉም አማኝ ክርስቲያን ሊማረዉ ብሎም ሊያዉቀዉ የሚገባ ወሳኝ ትምህርት አካፍላቹዋለሁ።
👆ከላይ በርዕሱ ላይ እንደገለፅኩት ዛሬ ስለ ሁለቱ አዳሞች በጥቂቱ እንማራለን።
👉 መፅሐፍ ቅዱስ ስለ ሁለቱ አዳሞች በብዙ ስፍራ በስፋት እና በግልፅ ያስተምራል።
👤የመጀመርያዉ/የቀድሞዉ አዳም ማን ነዉ ምንስ አደረገ?
የመጀመርያዉ አዳም መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን በዘፍ 1፥26 ላይ እግ/ር በመልኩ እና በአምሳሉ የተፈጠረዉ በፍጥረተ አለም የመጀመርያዉ ሰዉ ነዉ።
ይህ አዳም ለፍጥረታዊዉ ሰዉ እና አለም አባት ነዉ።ከዚያም በላይ በብዙ የተባረከ እና በፍጥረታት ሁሉ ላይ ገዢ እና አስተዳዳሪ ተደርጎ በሁሉ ላይ የተሾመ ባለ ሙሉ ስልጣን ነበር።
👉ይህም አዳም ያለ ምንም እጦት፣ችግር፣መከራ፣ፍርሀት፣ሀጢአት፣በሽታ እና ሞት ከዚህ ሁሉ ነፃ ሆኖ እግ/ር ባዘጋጀለት የክብር ህይወት ገዢ እና ባለስልጣን ሆኖ ይኖር ነበር።
👥ነገር ግን በዘፍ 3፥1 ላይ እንደምናገኘዉ እባብ በተንኮሉ ሄዋንን እንዳሳታት እና የተከለከለዉን የዛፍ ፍሬ እንደበላች እና ለባልዋም ለአዳም እንደሰጠችዉ እናያለን።ይህንንም ባደረጉ ቅፅበት አይናቸዉ እንደተከፈተ እና ማየት ያልነበረባቸዉን እንዳዩ በዛም ምክንያት ከእግ/ር ፊት እና ካስቀመጣቸዉ የክብር የገዢነት ቦታ እነደሸሹ እና እንደተደበቁ🏃♀🏃 በዚህ ክፍል እናያለን።
👉የእግ/ርን ህግ እና ትዕዛዝ በመተላለፋቸዉ በዚህም ምክንያት የእርግማን ዉጤት ማለትም፣ልፋት፣መከራ፣ስቃይ፣ጥል፣በሽታ፣ሞት እና ሀዘን ወደ ሰዉ ልጅ ሁሉ ማለትም አዳም በበላዉ እና በሀጢአት በወደቀዉ የሰዉ ልጅ ሁሉ በቀድሞዉ አባቱ በአዳም ምክንያት ሀጢአቱም እርግማኑም ደርሶታል።በአንዱ አለመታዘዝ ሁሉም ሀጢአተኞች ሆኑ።
👉👉አስተዉሉ አስተዉሉ👈👈
አንዱ አዳም በበላዉ ሁሉም በልቷል፣አዳም በመዉደቁ ሁሉም ወድቋል፣አዳም ሲረገም ምድር ሁሉ ተረግሟል፣ከኤደን ገነት ሲባረር/ሲወጣ ሁሉንም ይህ መዘዝ ደርሶታል።🙆🤦♀🙆♂🤦♂
በዚህም ምክንያት ለብዙ ዘመናት የሰዉ ልጅ በጨለማ እና ከእግ/ር ጋር ጥል ሆኖ ኖሯል።
👉ሁለተኛዉ አዳም ማነዉ ምንስ አደረገ?
ሁለተኛዉ አዳም ፍፁም ሰዉ እና ፍፁም አምላክ የሆነዉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክርስቶስ ነዉ።አሜን
👉❝እንዲሁ ደግሞ፦ ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።❞
1ኛ ቆሮንቶስ 15: 45
👉አስተዉሉ!በቀድሞዉ አዳም አለመታዘዝ ምክንያት የሰዉ ልጆች ያጡትን ህይወት ሙሉ ለሙሉ እንደዉም በተሻለ እና በሚበልጥ ሁኔታ መልሶታል።አሜን🙏🙏
ሮሜ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤
¹³ ሕግ እስከ መጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረና ነገር ግን ሕግ በሌለበት ጊዜ ኃጢአት አይቈጠርም፤
¹⁴ ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና።
¹⁵ ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን እንደዚያው አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎቹ ሞተዋልና፥ ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋና በአንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ።
¹⁶ አንድ ሰውም ኃጢአትን በማድረጉ እንደ ሆነው መጠን እንደዚያው ስጦታው አይደለም፤ ፍርድ ከአንድ ሰው ለኵነኔ መጥቶአልና፥ ስጦታው ግን በብዙ በደል ለማጽደቅ መጣ።
¹⁷ በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ።
¹⁸ እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ፥ እንዲሁም በአንድ ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ።
¹⁹ በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።
²⁰-²¹ በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ፤ ዳሩ ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ፥ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ።
👉እንዴት?
መፅሐፍ ቅዱስ ሲናገር እንዲህ ይላል...
👉አንዱ አዳም ባለመታዘዙ ሁሉም ሀጢያተኞች ሆኑ ልክ እንዲሁ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ መታዘዝ ሁሉም ፃዲቅ ሆኑ።
👉በአንዱ አዳም ሀጢአት ምክንያት ሁሉም ከገነት ተባረሩ እንዲሁ በአንዱ በኢየሱስ የፅድቅ ስራ ያመኑ ሁሉ ወደ መንግስቱ ገቡ።
👉በአንዱ አዳም አለመታዘዝ ምክንያት ሞት፣በሽታ፣ስቃይ፣ሀዘን፣ዉድቀት ወደ ሰዉ ልጆች ሁሉ ደረሰ እንዲሁ በአንዱ በኢየሱስ መታዘዝ እና በፈፀመዉ የመስቀል የመቤዠት እና የእርቅ ስራ ያመኑ በሙሉ በህይወት ላይ ይነግሳሉ።🙏🙏🙏
👉👉አስተዉሉ አስተዉሉ👈👈
የቀድሞዉ አዳም/አሮጌዉ ሰዉ አሁን በአዲሱ ሰዉ/በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አሮጌዉ ወይም ያለፈበት የተሻረዉ ሰዉ ሆኗል።በክርስቶስ ተሰርቶ ካለቀዉ ከደህንነት ከመስቀል ስራ በሁዋላ ምንም አቅም የሌለዉ ሙት ተደርጓል።ምንም ማስተላለፍ እንዳይችል ተደርጓል።ርግማን፣የዘር ሀጢአት በለዉ ሌላም ሌላም ማስተላለፍ እንዳይችል ተደርጓል።አቅሙን እና ሀይሉን በሙሉ አዲሱ ሰዉ ወስዶበታል።አሜን🙏🙏
👉❝ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።❞
2ኛ ቆሮ 5: 17
👉በክርስቶስ የሆነ ሁሉ አዲስ ፍጥረት ነዉ።አሮጌዉ ሰዉ ከህይወት ስርአቱ ጋር አልፏል።ሁሉም በኢየሱስ አዲስ ሆኗል።የአሮጌዉ የአዳም ዘር በክርስቶስ ኢየሱስ ተቆርጧል።ለአሮጌዉ አዳም ሞተን ለአዲሱ ዘር ህያዉ ሆነናል።ከአሮጌዉ ሰዉ ከአዳም በዘር ሲተላለፍ የነበረዉ እርግማን እና ሀጢያት በአዲሱ በዚህ የዘር ግንድ ዉስጥ አይሰራም።አሁን በአዲሱ አዳም/ሰዉ በኢየሱስ ዉስጥ ያለዉ ሰላም፣በረከት፣ፅድቅ፣ጤንነት፣ሁሉ በዚህ ዘር ዉስጥ ወዳሉት ይተላለፋል።አሜን🙏
👉1ኛ ጴጥሮስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።
…
²⁵ የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው።
👉እኛ በቀድሞዉ አዳም የህይወት ምልልስ ዉስጥ ያለን ሳንሆን በክርስቶስ አዲስ ዘር እና አዲስ የፅድቅ ህይወት ምልልስ ዉስጥ ያለን ነን።
🙏ክብር ሁሉ ለእርሱ ይሁን🙏
ተባርካቹሀል።
ወንድማችሁ አገልጋይ ቤኪ ነኝ
0926389464
Join Us👉
@Gracegosple
@Gracegosple
@Gracegosple
መልዕክቱን ለሌሎች Share በማድረግ አብረዉን ያገልግሉ።
የፀጋ/የኢየሱስ ወንጌል Ministry:
ድንቅ የዕለቱ መልዕክት
1ኛ ጴጥሮስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤
¹⁰ እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።
በዚህ ቃል ዉስጥ 👉ልቤን እና ሀሳቤን የሳበኝን👈ድንቅ ሀሳብ ላካፍላችሁ።እርሱም
👉👉የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ👈👈
ብዙ ጊዜ የተለያዩ አገልጋዮችን ማለትም አስተማሪዎችን እና ሰባኪዎችን ትምህርታቸዉን እና ስብከታቸዉን ለማስተዋል ሞክራለሁ።በብዛት ግን መልዕክቶቻቸዉ ላይ የእግ/ርን መልካምነት፣አባትነት፣ፍቅሩን፣ደግነቱን፣በጎነቱን ይበልጥ ከመናገር እና ከማጉላት ይልቅ በጣም በሚያስፈራሩ ለመስማት እንኩዋን በሚጨንቁ ቃላት ቁጣን፣አስፈሪነትን፣ቀጪነትን፣ብቻ ብዙ ብዙ በመልዕክቶቻቸዉ መሐል መስማት የተለመዱ ናቸዉ።
👉የአዲስ ኪዳን አገልጋይ መልዕክቱ ምንድነዉ?ስለ ምን እና ስለ ማን ነዉ?ይህ በሚገባ ሊታወቅ ይገባል ምክንያቱም ያሉበትን ኪዳን አለማወቅ በህይወት ሁል ጊዜም ተሸናፊ ያደርጋል።
👉በዚህ ዘመን ያለ ክርስቲያን ሁሉ ራሱን መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ቢኖር ማነዉ የጠራኝ?ለምንድነዉ የተጠራሁት?ብሎ በማስተዋል ራሱን ሊጠይቅ ይገባል።
👉ለስድብ አልተጠራንም፣ለሀሜት አልተጠራንም፣ጥቅስ እየጠቀስንም ሰዉን ለማስፈራራት እና ለማስጨነቅ አልተጠራንም።
የተጠራነዉ👉የእርሱን በጎነት፣መልካምነት፣ቸርነት፣ረዳትነት፣አባትነት፣ፍቅር ለመናገር ተጠርተናል።አሜን🙋♂🙋
ለዛም ነዉ ሐዋርያዉ ጴጥሮስ በመፅሐፉ ሲፅፍ...
👉ከጨለማ ወደ ሚደነቀዉ ብርሃን የተጠራነዉ የእርሱን በጎነት እንድንነገር ነዉ።
👉በጎነቱን ለመናገር የተመረጠ ትዉልድ።
👉በጎነቱን ለመናገር የተመረጠ የንጉስ ካህን።
👉በጎነቱን ለመናገር የተመረጠ ቅዱስ ህዝብ።
👉በጎነቱን ለመናገር ለርስቱ የተለየ ወገን።
👉በጎነቱን ለመናገር የተመረጠ የእግ/ር ወገን።
👉ምህረትን ያገኘን ነን።አሜን
ወዳጆቼ መልዕክታችን የጌታችን በጎነት ነዉ።የእርሱ የመስቀል ስራ ነዉ።የእርሱ የአባትነት ፍቅር እና መልካምነት ነዉ።ሌላ መልዕክት የለንም።የተጠራነዉም ለዚሁ ነዉ።
ወዳጆቼ ለራሳችሁ ይሄንን ቃል ልትገቡ እና ልትናገሩ ይገባል!
👉የእርሱን መልካምነት እናገራለሁ።
👉የእርሱን በጎነት እሰብካለሁ።
👉የእርሱን ፍቅር እና አባትነት እዘምራለሁ።አሜን
ተባርካቹሀል።
ወንድማችሁ አገልጋይ ቤኪ ነኝ
0926389464
Join Us👉
@Gracegosple
@Gracegosple
@Gracegosple
መልዕክቱን ለሌሎች share በማድረግ አብረዉን ያገልግሉ።
😳የብዙ ሰዎች ትልቅ ስህተት እና አስተምሮ🙊
2ኛ ጢሞቴዎስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤
⁸ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።
2 Timothy 4 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ I have fought a good fight, I have finished my course, I have kept the faith:
⁸ Henceforth there is laid up for me a crown of righteousness, which the Lord, the righteous judge, shall give me at that day: and not to me only, but unto all them also that love his appearing.
ከላይ ጀምሮ ቃል በቃል በትክክል እንዳነበባችሁ እርግጠኞች ሁኑ!
በጣም ብዙ ጊዜ ሰዎች ይሄንን የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ሲሰብኩም፣ሲያስተምሩም፣አብዛኞችም ደግሞ በመቃብር ሐዉልት ላይ ሲፅፉ እናያለን ነገር ግን ከቃሉ አፃፃፍ እስከ ትርጉም ፈፅሞ ሲሳሳቱ እንመለከታለን።
እስቲ ጥቅሱን በትክክል እንፍታዉ።
ይህንን መልዕክት የፃፈዉ ቅዱስ ጳዉሎስ ሲሆን ለመሞት ጥቂት ቀን ሲቀረዉ ለመንፈሳዊ ልጁ ለጤሞቴዎስ የመጨረሻ ምክር አዘል መልዕክቱን እያስተላለፈለት ነዉ።ይህም በህይወቱ ያከናወናቸዉን 3 ታላላቅ ነገሮችን ይነግረዋል።
1.መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ/I have fought a good fight
👉ይህም ተጋድሎ/fought መልካም ተጋድሎ ነዉ።እዉነተኛዉን፣ከምንም ነገር እና ከባህል ጋር ያልተቀየጠ ንፁህ የሆነዉን ወንጌል እርሱም ኢየሱስን በሁሉም ሰዉ ማንነት ዉስጥ ለመሳል ያሳለፈዉን ትግል በዚህ ቃል ዉስጥ እናያለን።
2.ሩጫውን ጨርሼአለሁ/I have finished my course
👉ብዙ ሰዎች እዚህ ጋር ሲያነቡ እና ሲናገሩት ይሳሳታሉ።ቃሉን በማስተዋል አንብቡት።እሩጫዬን ጨርሻለሁ አይልም።እሩጫዉን ነዉ የሚለዉ።እንደዉም የኢንግሊዘኛዉ ትርጉም my course ይለዋል።ምን ማለት ነዉ?ጳዉሎስ የራሱ ሩጫ የለዉም።ጳዉሎስ የሚሮጥለት ሌላ አካል አለ።ወይንም በእንግሊዘኛዉ እኔ የራሴ ትምህርት ወይም መልዕክት የለኝም እንድናገር እና እንዳስተምር እንዳስተላልፍ የተሰጠኝን ኮርስ ሁሉ ምንም ሳላስቀር አስተላልፌያለሁ እያለ ነዉ።ጳዉሎስ ለዛ ነዉ ሩጫዉን ጨርሻለሁ ወይንም ተልእኮዬን አጠናቅቂያለሁ ያለዉ።
😳ሰዉ ሁሉ ሩጫዬን ጨርሻለሁ ይላል የኔ ጥያቄ ግን የትኛዉን እሩጫ ነዉ?🙊
ሰዉ መልካምም ለክፉም ስራ ይሮጣል እና እሩጫዬን ስትሉ የቱን ሚለዉ ትልቅ ጥያቄ ነዉ።ሩጫችሁን ተዉና እሩጫዉን(የእርሱን,የላኪዉን)ሩጫ ሩጡ።
3.ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ/ I have kept the faith
👉የመጨረሻዉ ይሄ መልዕክት ነዉ።ብዙ ሰዎች ሀይማኖቴን ጠብቄያለሁ ይላሉ።የቱን ሀይማኖት?😂😂የኦርቶዶክስን ነዉ?የኘሮቴስታንትን ነዉ?የእስልምናን ነዉ?ወይስ የቱን ሀይማኖት ነዉ የጠበቃችሁት?😁
ጳዉሎስ ሀይማኖቴን ሳይሆን ሀይማኖትን ጠብቄያለሁ ሲል ምን ማለቱ ነዉ?በኢንግሊዘኛዉ ወይም Orignal translation ሀይማኖትን የሚለዉን እምነትን/faith ይለዋል።
ምን ማለት ነዉ?እምነትን ጠብቄያለሁ ያም እምነት በክርስቶስ ኢየሱስ ያለኝን እምነት እስከመጨረሻዉ ሳለዉጥ ጠብቄያለሁ እያለ ነዉ።
Relegion/ሀይማኖት ሳይሆን የጠበቀዉ faith/እምነቱን ነዉ የጠበቀዉ።
👉ስለዚህ ምክንያት የክብር አክሊል ይጠብቀኝል።🤛
ወንድማችሁ አገልጋይ ቤኪ ነኝ
0926389464
Join Us👉
@Gracegosple
@Gracegosple
@Gracegosple
መልዕክቱን ለሌሎች share በማድረግ አብረዉን ያገልግሉ።
ርዕስ፦ፍሬ አለማፍራት አልችልም።
ብዙ ጊዜ ሰዎች ፍሬ ማፍራት አለብህ ሲሉ ሰማለሁ።
ካላፈራህ ከግንዱ ተቆርጠህ ትጣላለህ ይላል ሲሉ ሰማለሁ።እዉነታቸዉን ነዉ።እኔም ደግሞ ቆንጆ መልስ አለኝ።
ዮሐ 15፥1 ጀምሮ
አስተዉል!
የትኛዉም ዛፍ ያለ ጥሩ ገበሬ ጥሩ ፍሬ አያፈራም።
በዛዉ ልክ ደግሞ ያለ ጥሩ ግንድ ከቅርንጫፍ የሚጠበቅ ፍሬ የለም።
የቅርንጫፉ የማፍራት ህልዉና ያለዉ በተጣበቀዉ ግንድ ላይ ነዉ።
ግንዱ የለም ማለት ቅርንጫፍም ፍሬም የለም።
ግንዱ ለመልካም ዛፍ እና ለብዙ ፍሬ ትልቁን ድርሻ ይጫወታል። ለዛም ነዉ ኢየሱስ ያለ እኔ ምንም ፍሬ ልታፈሩ አትችሉም ያለዉ።
ምክንያቱም ቅርንጫፍ የራሱ ፍሬ የለዉማ።ቅርንጫፍ ስራዉ ለፍሬ የሚያስፈልገዉን ሁሉ ከግንዱ በመዉሰድ
ግንዱ ዉስጥ ያለዉን ፍሬ ወደሚታይ ገሀድ ማዉጣት ነዉ።ዋዉ
ማለትም ግንዱ የራሱን ፍሬ በቅርንጫፎቹ አማካኝነት ያፈራል።
አየህ ለዛም ነዉ የትኛዉንም ቆንጆ ፍሬያማ ዛፍ ስታይ የምትደነቀዉ ወይም የምታደንቀዉ ቅርንጫፎቹን ሳይሆን የዛፉን ዘር ወይም ዋናዉን ግንድ ነዉ።ምክንያቱ ደግሞ በቅርንጫፎቹ ላይ የሚታየዉ መልካም ፍሬ የግንዱ ዉጤት እንጂ የቅርንጫፉ አይደለም።
አሁንም አስተዉል!
ያለ ኢየሱስ ምንም ፍሬ አታፈራም።አንተ ቅርንጫፍ እኮ ነህ።ዋናዉ የፍሬዉ ምንጭ ደግሞ ግንዱ ኢየሱስ ነዉ።ያንተ የሚባል ፍሬ የለም እርሱ ነዉ በአንተ ሆኖ ብዙ ፍሬን የሚያፈራዉ።አንተ በእርሱ ስትሆን የማይቆጠር በግንዱ በኢየሱስ ዉስጥ ያለዉን መልካም ፍሬ ሁሉ ታፈራለህ ወይም በእርሱ ዉስጥ ያለዉ በአንተ ይገለጣል።አሜን
በኢየሱስ ላይ ሆኖ አለማፍራት የማይታሰብ ነዉ።እርሱ በእኔ ሆኖ የማይቆጠር ብዙ ያፈራል።ፅድቅን፣ቅድስናን፣ሰላምን፣ደስታን፣ፍቅርን፣ቸርነትን፣በጎነትን፣ርህራሄን...ወዘተ ጨምሩበት ሌላም ሌላም በእኛ ያፈራል።
ብቻ በእርሱ ላይ ሁኑ።አብዝቶ ፍሬ ይታይባቹሀል።
አለማፍራት ከቶ አልችልም።
ተባርካቹሀል!
ወንድማችሁ አገልጋይ ቤኪ ነኝ
0926389464
Join Us👉
@Gracegosple
@Gracegosple
@Gracegosple
መልዕክቱን ለሌሎች share በማድረግ አብረዉን ያገልግሉ።
ርዕስ፡-የኢየሱስ ደም
ክፍል 3
*ደሙ ፅድቃችን
*ደሙ መታያችን
*ደሙ ቤዛችን
*ደሙ ንፅህናችን
*ደሙ ወደ አብ መግቢያችን ነዉ።
ኤፌሶን 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።
…
¹⁸ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።
*****
❝የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።❞
—ዕብራውያን 9: 12
****-******
ዕብራውያን 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ፥ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው።
¹⁶ ኑዛዜ ያለ እንደሆነ የተናዛዡን ሞት ማርዳት የግድ ነውና፤
¹⁷ ሰው ሲሞት ኑዛዜው ይጸናልና፥ ተናዛዡ በሕይወት ሲኖር ግን ከቶ አይጠቅምም።
¹⁸ ስለዚህም ፊተኛው ኪዳን እንኳ ያለ ደም አልተመረቀም።
¹⁹-²⁰ ሙሴም ትእዛዛትን ሁሉ እንደ ሕጉ ለሕዝቡ ሁሉ ከተናገረ በኋላ፥ የጥጆችንና የፍየሎችን ደም ከውኃና ከቀይ የበግ ጠጕር ከሂሶጵም ጋር ይዞ፦ እግዚአብሔር ያዘዘላችሁ የኪዳን ደም ይህ ነው ብሎ በመጽሐፉና በሕዝቡ ሁሉ ላይ ረጨው።
²¹ እንዲሁም በድንኳኒቱና በማገልገያው ዕቃ ሁሉ ደምን ረጨ።
²² እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፥ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም።
²³ እንግዲህ በሰማያት ያሉትን የሚመስለው ነገር በዚህ ሊነጻ እንጂ በሰማያት ያሉቱ ራሳቸው ከእርሱ ይልቅ በሚበልጥ መስዋዕት ሊነጹ የግድ ነበረ።
²⁴ ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ።
²⁵ ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤
²⁶ እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል።
²⁷ ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥
²⁸ እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል።
******
❝ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።❞
—1ኛ ጴጥሮስ 1: 18-19
*********
ሮሜ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤
²³ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤
²⁴ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።
²⁵ እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥
²⁶ ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው።
*******
ሮሜ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን።
¹⁰ ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤
¹¹ ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን አሁን መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን።
********
❝በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።❞
—ኤፌሶን 1: 7
**********
ከዚህ ነገር ሁሉ በሁዋላ አስተዉል።አንተ በራስህ ምንም አይነት ብቃት የለህም።ራስህን በደሙ ዉስጥ ተመልከት።ለደሙ ክብር እና እዉቅና ስጠዉ።የሆንኩትን ሁሉ የሆንኩት በፈሰሰልኝ በኢየሱስ ደም ነዉ።
ንፁህ ነኝ,ፃዲቅ ነኝ,ቅዱስ ነኝ, ስል ራሴን እያኮፈስኩ ሳይሆን ራሴን በደሙ ዉስጥ በመደበቅ ነዉ።ደሙ እዉቅና ስለሚገባዉ ደሙ ያደረገኝን ነኝ ብዬ እዉቅና እየሰጠሁት ነዉ።
ዋጋ እንዳልተከፈለለት, ከእዳ ነፃ እንዳልሆንኩ, ኩነኔ እና እስራት ዉስጥ እንዳለሁ ራሴን ብቆጥር በህይወት ተሸናፊ እና ደካማ ነዉ ምሆነዉ።
አየህ ራስህ ያለህበትን ሁኔታ ተዉና አሁን ስላንተ የፈሰሰዉን ንፁ የኢየሱስን ደም አስብ።ከዚያን አቅም ታገኛለህ ከማንም በላይ ደስተኛ ትሆናለህ ከድካምህ ትበረታለህ እርሱ የሰራልህን ስራ የኔ ነዉ ብለህ አምነህ ተቀበል የዛኔ ህይወትህን ትወደዋለህ።
የኢየሱስ ደሙ ሁሉ ነገሬ ነዉ!!
ተባርካቹሀል!
ወንድማችሁ አገልጋይ ቤኪ ነኝ
0926389464
Join Us👉
@Gracegosple
@Gracegosple
@Gracegosple
መልዕክቱን ለሌሎች share በማድረግ አብረዉን ያገልግሉ።
ርዕስ፡-የኢየሱስ ደም
ክፍል 1
ከዚህ በፊት ባስተላለፍኳቸዉ ትምህርቶች እና መልዕክቶች እንደተጠቀማችሁ አምናለሁ።
ዛሬ ደግሞ የኢየሱስ ደም በሚል ርዕስ ድንቅ እዉነት እና ልዩ መገለጥ ያለበትን ትምህርት እናያለን።
ስለ ደም ካነሳን አይቀር ስለ ብሉይ ኪዳን እና አዲስ ኪዳንን ማንሳት የግድ ይላል።ምክንያቱም ሁለቱም ኪዳኖች የተከፈቱት በደም ስለሆነ።የተመሰረቱትም እንዲሁ በደም ስለሆነ።
ብሉይ ኪዳን በኮርማዎች ወይም በእንስሳት ደም ሲሆን አዲስ ኪዳን ደግሞ በክርስቶስ ደም ነዉ የተመሰረተዉ።
ብሉይ ኪዳን ላይ ወይንም በአሮጌዉ ስርአት ላይ ሰዎች ለሰሩት ሀጢአት ሁል ጊዜም ያለመታከት እና ያለ መሰልቸት ለሀጢአታቸዉ ማስተሰረያ ይሆን ዘንድ በየጊዜዉ መስዋዕት የሚሆን እንስሳ ወደ ቤተ መቅደስ ካህን የወስዳሉ።ካህኑም ያለ ዕረፍት እና ያለምንም መቀመጥ እድሜ ልኩን እንደቆመ ይሄንን ስርአት ያከናዉናል።ምክንያቱም የህዝቡን ሁሉ በነብስ ወከፍ የእያንዳንዱን ሀጢአት ማስተሰረያ የመጣዉን እንስሳ ሲያርድ እና ሲያስተሰርይ ያለ እረፍት እንደ ቆመ ያገለግላል።አይገርምም እረፍት የሌለዉ አገልግሎት?
ለምን እረፍት እንደሌለዉ ታዉቃለህ?ሀጢአትም አልቆመም በዚያዉ መጠን መስዋእትም አልቆመም ሁል ጊዜም ለሀጢአት ደም ይፈሳል ምክንያቱ ደግሞ አንዴ ፈሶ ፈፅሞ የሚያነፃ እና የሚያነፃ ደም ባለመኖሩ ለእያንዳንዱ ሀጢአት ሁሌም መስዋዕት ያስፈልግ ነበር።ለዛ ነዉ የብሉይ ኪዳኑ አገልግሎት እና ክህነት መቀመጥ የሌለበት እረፍት የማይታሰብበት የድካም አገልግሎት ነዉ ያልኩህ።
ዕብራውያን 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ቀጥሎ፦ እነሆ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ ብሎአል። ሁለተኛውንም ሊያቆም የፊተኛውን ይሽራል።
¹⁰ በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል።
¹¹ ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፤
¹² እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥
¹³ ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደ ፊት ይጠብቃል።
¹⁴ አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና።
¹⁵-¹⁶ መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፤ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ ብሎ ከተናገረ በኋላ፥
¹⁷ ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል።
¹⁸ የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም።
¹⁹-²⁰ እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን
አየህ አሁን ያለነዉ በአሮጌዉ ኪዳን ዉስጥ አይደለንም በኢየሱስ ፍፁም እና ንፁህ ደም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተመርቆ በተከፈተልን በአዲሱ ኪዳን ዉስጥ ነን። ዋዉ
አሁን የቆመ ካህን የለንም።ፍፁም የሆነዉን መስዋዕት የራሱን ደም አንድ ጊዜ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ወደ አባቱ ይዞ በመግባት ለዘላለም ካነፃን ከቀደሰን በሁኋላ በአባቱ በግርማዉ ቀኝ የተቀመጠ ሊቀ ካህን አለን። አሜን
ተባርካቹሀል።
ወንድማችሁ አገልጋይ ቤኪ ነኝ
0926389464
Join Us👉
@Gracegosple
@Gracegosple
@Gracegosple
መልዕክቱን ለሌሎች share በማድረግ አብረዉን ያገልግሉ።
ርዕስ:-በእርሱ ስራ
ደህንነትም ሆነ ፅድቅ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የሚገኝ ነፃ ስጦታ እንጂ፡-
እኔ እና አንተ ሰርተን የምናመጣዉ ደሞዝ አይደለም።
መልካምን ስራ መስራት ጥሩ ሰዉ እና መልካም ስብዕና ያለህ መሆንህን የሚያሳይ እንጂ መዳንህን ወይም መፅደቅህን ፍፁም አያደርገዉም።
አየህ...
ሰርተህ እና ለፍተህ በጥረትህ ያመጣኸዉ ደህንነት ወይም ፅድቅ ካለህ በራስህ መመካት ትችላለህ መብትህም ነዉ።ምክንያቱም ደግሞ የጥረትህ እና የድካምህ ዋጋ ነዋ።
ነገር ግን ማንም ደህንነትንም ሆነ ፅድቅን በራሱ ስራ ማምጣት አይችልም።ምክንያቱ ደግሞ የሰዉ ፅድቅ እኩል ይሆናል የመርገም ጨርቅ ነዉ ሂሳቡ።
ደህንነትም ሆነ ፅድቅ ስጦታ ናቸዉ።ነፃ ስጦታ!
ነፃ ስጦታ ደግሞ 2 አይነት ነዉ።
*የመጀመሪያዉ በጣም ርካሽ የሆነ ነገር በሳንቲም ቤት መግዛት ምትችለዉን ነገር ማንም በነፃ ይሰጥሀል ምክንያቱ ደግሞ ርካሽ ስለሆነ።
*ሁለተኛዉ ደግሞ በጣም ዉድ እና ማንም ባለዉ በገንዘብም ሆነ ሀብት ልክ መግዛት የማትችለዉ ዉድ ነገር ሲሆን እንዲሁ ሰጪዉ በነፃ ይሰጥሀል።
የሆነዉም እንዲሁ ነዉ እኔ እና አንተ መቼም ልንገዛ የማንችለዉን እርሱ ግን በነፃ ሰጥቶናል።
ለዚህ ነዉ በራስ ስራ ወይንም የኔ ፅድቅ የሚባል ነገር የለም።በራስህም የሚያስመካ ምንም ትምክት የለህም።
1ኛ ቆሮንቶስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁹ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ።
³⁰-³¹ ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።
የሆንከዉን ሁሉ ተደርገህ ነው።
*የእግ/ር ልጅ
*ፃዲቅ
*ንፁ
*ቅዱስ
*የታጠበ
*የዳነ
*ካህን
ሌላም ካለ ጨምሩ ሁሉንም የሆነዉን የሆነዉ በእርሱ በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሰርቶ በጨረሰዉ ስራ ነዉ።።።።።።።።።።።።አሜን
No እኔ
No የኔ ስራ
No የኔ ፅድቅ
በቃ No No No
ሁሉ በእርሱ።
ለእርሱ ክብር ሆኖአል።
ተባርካቹሀል።
ወንድማችሁ አገልጋይ ቤኪ ነኝ
0926389464
Join Us👉
@Gracegosple
@Gracegosple
@Gracegosple
መልዕክቱን ለሌሎች share በማድረግ አብረዉን ያገልግሉ።
የፀጋ/የኢየሱስ ወንጌል Ministry:
👉የአዲስ ኪዳን እዉነታዎች ነገር ግን በግልጠት ሲነገሩ የማንሰማቸዉ ህይወቶን በእርግጥም የሚቀይሩ እና የእግ/ርን ቃል በጥልቀት እንዲያዉቁ ብሎም የመፅሐፍ ቅዱስ ዕዉቀቶን በእርግጥም የሚያሳድጉበት ትምህርታዊ channel ነዉ። በፅሑፍ እንዲሁም በድምፅ ተከታታይና ርዕሳዊ ትምህርቶችን ያገኛሉ።
👉አዳዲስና በዚህ channel የሚለቀቁ ትምህርቶች ወድያዉ እንዲደርሶ አባል ይሁኑ።አባል ለመሆን ሊንኩን ተጭነዉ join ያድርጉ።
Join Us👉
@Gracegosple
@Gracegosple
@Gracegosple
Share ያድርጉ