greatethrun | Unsorted

Telegram-канал greatethrun - Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

5807

Official Great Ethiopian Run Telegram Channel. Call 0116635757 for more details.

Subscribe to a channel

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ውብ ቅዳሜን ከእኛ ጋር ያሳልፉ!🌟

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ💫🏃‍♀️

ነገ - ቅዳሜ - መጋቢት 26 ቀን 2018ዓ.ም. እንገናኝ!

#EntotoParkCBERun #GreatEthiopianRun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

📌 የዚህ ወር እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን መጋቢት 26 ይካሔዳል - ሰኞ ማለዳ በሲቢኢ ብር ፕላስ ይመዝገቡ 📌

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ✨

መጋቢት 26  / 2018ዓ.ም.

#EntotoCBERun #GreatEthiopianRun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ባንክ ኦፍ አሜሪካ በኢትዮጵያ ከሩጫ ጋር እያሳደገ የሚገኘው አጋርነት አካል አድርጎ የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. የስያሜ አጋር ሆነ

ከመጋቢት 2019 (March 2027) ጀምሮ ባንክ ኦፍ አሜሪካ ከአፍሪካ ትልቆቹ የሴቶች-ብቻ ሩጫ ውድድሮች አንዱ የሆነው ውድድር የስያሜ አጋር (Presenting Partner) ይሆናል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከባንክ ኦፍ አሜሪካ ጋር እያሳደገ የሚገኘው አጋርነት አካል ሆኖ፣ ዓመታዊው ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ውድድርም አዲስ የስያሜ ስፖንሰር (presenting sponsor) እንደሚኖረው ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ በህዳር ወር 2018ዓ.ም. የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መታወቂያ የሆነው የ10ኪ.ሜ. የጎዳና ሩጫ የስያሜ አጋር (Presenting Partner) እንደሚሆን ያሳወቀው ባንኩ፣ የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ.ን መጨመሩ የበለጡ ሰዎችን ወደረዥም ርቀት ሩጫ ለማምጣት የያዘውን ተልዕኮ እንዲያሰፋ እና በማህበረሰቡ ዘንድ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ እንዲያጠናክር ያስችለዋል፡፡

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ሶስቱም ትልልቅ የሩጫ ሁነቶች (events) ፤ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ.፣ የልጆች ሩጫዎች እና የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ውድድሮች ላይ ባንክ ኦፍ አሜሪካ አዲሱ የስያሜ አጋር (Presenting Partner) ይሆናል።

ማህበረሰብን ያስቀደመ መርሆን መሰረት ያደረገው አጋርነት በርካታ ግቦችን ለማሳካት አቅዷል፡፡ ባንክ ኦፍ አሜሪካ በ10ኪ.ሜ. እና የልጆች ሩጫዎች ላይ ነፃ ተሳትፎዎችን በገንዘብ በመደገፍ የተሳታፊነትን ተደራሽነት የማስፋት ግብን ያግዛል፡፡ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቀጣዩን የሯጮች ትውልድ የማበርታት ተልዕኮም ከባንኩ ልጆች እና ወጣቶች በስፖርት እንዲሳተፉ የበለጡ እድሎችን ከማቅረብ ዓለምአቀፍ ስትራቴጂ ጋር ይዛመዳል፡፡ ባንክ ኦፍ አሜሪካ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለሚዘጋጁ ውድድሮች የሚውሉ ቴክኖሎጂዎችን ለማዘመን የሚያስችል ሀብትም ያቀርባል፤ ይህም በተራው የተሳታፊዎች ቁጥር ይበልጥ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ፣ ባንክ ኦፍ አሜሪካ የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. አዲሱ የስያሜ አጋር መሆኑን ይፋ ሲያደርጉ ‹‹ባለፉት ሀያ ዓመታት የልጃገረዶች እና ሴቶች ዓመታዊ ሩጫችንን ለማሳደግ ብዙ ወጪ ፈሰስ አድርገናል፡፡ አሁን በባንክ ኦፍ አሜሪካ የአጋርነት ድጋፍ ደግሞ የበለጡ እድሎች ይከፈቱልናል፡፡ ባንክ ኦፍ አሜሪካ ለሩጫዎቻችን እና በሩጫዎቻችን አማካይነት ልናገለግላቸው ለምንሻው ማህበረሰቦች እንዲሁም ከሴቶች እና ልጆች ጋር ላሉን ሰፊ ስራዎች አብረውን ለመስራት ላሳዩት ቁርጠኝነት ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ›› ብለዋል፡፡

በማርች 8 ከሚከበረው ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ጋር ተያይዞ የሚዘጋጀው የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ባለፈው እሁድ 23ኛ ውድድሩን ሲያደርግ፣ ከ12ሺህ የበለጡ ተሳታፊዎችም ውድድሩን አጠናቅቀዋል፡፡ ከኢትዮጵያ የፖሊቲካ፣ ቢዝነስ እና ባህል ህይወት ብዙ ስመ-ጥር እንስቶችን እንዲሁም በኢትዮጵያ እያገለገሉ የሚገኙ በርካታ የውጪ አምባሳደሮችን የሚያሳትፈው ውድድር ተካፋዮቹ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሴቶችን ስኬቶች ለማክበር ሲሰባሰቡ የተለየ አይነት የህብረት ስሜት እንዲሰማቸው እንደሚያደርግ ተስተውሏል፡፡

የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ አምባሳደር እና የጥንድ የኦሊምፒክ 5000ሜ ሻምፒዮኗ መሰረት ደፋር በእሁዱ ውድድር ወቅት ስትናገር ‹‹ይህ ውድድር ሁሌም የተለየ ነው፡፡ በሁሉም የማህበረሰቡ ክፍሎች ወስጥ የሚገኙ ሴቶችን ስኬቶች ለማክበር እና ለሌሎቾ ሴቶች ስኬታማ የመሆን በራስ መተማመንን ለመስጠት አስደናቂ መድረክ ነው፡፡ ሁሌም በየዓመቱ እኛን ሴቶችን ማነሳሳት አይሳነውም›› ብላለች፡፡

ባንክ ኦፍ አሜሪካ አዲስ እና ጠለቅ ያለ የደንበኛ ግንኙነትን የመፍጠር፣ የቡድን አጋሮችን የማሳተፍ እና በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘላቂ የኢኮኖሚ ተፅዕኖን የማገዝ እንቅስቃሴው አካል አድርጎ በስፖርት ውስጥ ካሉ እጅግ ታዋቂ ብራንዶች ጋር በአጋርነት ይሰራል፡፡

ባንክ ኦፍ አሜሪካ ዓለምአቀፋዊውን የብርታት መድረኩን በኢትዮጵያ ሁለቱም ውድድሮች - በአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ሩጫ በሆነው የኖቬምበሩ ዓለምአቀፍ የ10ኪ.ሜ. እና የመጋቢቱ የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. - ላይ ከሚወዳደሩ የቀጣይ ትውልድ ሯጮች ጋር በማስተሳሰር ስፖርት እንዴት ዕድሎችን ሊፈጥር እንደሚችል እና ሰዎች እና ማህበረሰቦችን እንደሚያዋህድ ማሳየቱን ቀጥሏል፡፡

ባንክ ኦፍ አሜሪካ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር ካለው አጋርነት ባሻገር በሩጫ፣ እግር ኳስ እና ጎልፍ ከዓለም አቀፍ ብራንዶች እና ሁነቶች ጋር በአጋርነት ይሰራል፡፡ እነዚህም Boston Marathon presented by Bank of America፣ Bank of America Chicago Marathon እና Chicago Distance Series፣ የ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ፣ የአሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ሁሉም 27 የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድኖች እንዲሁም በጎልፍ የማስተርስ ውድድር እና Augusta National Women’s Amateur ናቸው፡፡

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚገኘውን የካንሰር ህሙማን ማዕከል ጎበኙ።

መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ከሚካሄደው የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ አስቀድሞ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘውን የካንሰር ህሙማን ማዕከል ላይ ጉብኝት ተደርጓል። 

በጉብኝቱ ከዶ/ር ኤርጎጌ በተጨማሪም የአዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ብርሀኑ ደስይበለው እና የአክቲቭ መስራች ኤሌ አኒሰን ተገኝተዋል።

‘AKTIVE AGAINST CANCER’ በዘንድሮ 2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ውድድር ላይ ሴቶች የካንሰር ህመምን ቀድሞ ለመከላከል ሩጫን በማዘውተር ጤናቸውን ይጠብቁ ዘንድ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።

ዛሬም በጉብኝቱ ላይ ዶ/ር ኤርጎጌ "የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር እንደዚህ ያሉ ትብብሮችን ሁልጊዜ ይደግፋል ፤ ይህ ለኢትዮጵያ ሴቶች ትልቅ ትርጉም አለው ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ዉድድር ሴቶችን የሚያበረታታ መድረክ ነው" በማለት ገልፀዋል።

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ ለካንሰር ማዕከሉ ያደረገውን ድጋፍ በማመስገን ንግግር ያደረጉት የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብርሀኑ ሰንደቅ "ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ስለ ካንሰር ግንዛቤ ለመፍጠር ብዙ ተስፋ አለን" ብለዋል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫ ካንሰርን ለመከላከል ብሎም በማገገም ሒደት ውስጥ ባለው ጠቀሜታ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ለመስራት የሚችልበትን ስምምነት ለአራት ተከታታይ አመታት ከአክቲቭ አጌንስት ካንሰር ጋር ፈፅሟል።

የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ.  ነገ መነሻ እና መድረሻውን ቦሌ አትላስ በማድረግ ለ23ኛ ጊዜ ይከናወናል።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ጋዜጣዊ መግለጫ

የ23ኛው ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪ.ሜ ሩጫ የቅድመ-ውድድር ጋዜጣዊ መግለጫ በእቴጌ መነን የልጃገረዶች ትምህርት ቤት በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ

እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄደውን የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች  ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ አስመልክቶ፤ የመጨረሻው የቅድመ-ውድድር ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬ በታሪካዊው እቴጌ መነን የልጃገረዶች ትምህርት ቤት ተካሒዷል።

በዝግጅቱ ላይ የውድድሩ አምባሳደር የሆነችው አትሌት መሰረት ደፋር እና የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪ የነበሩት ታዋቂዋ ፖለቲከኛ ወ/ሮ ብርቱካን ሚደቅሳ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

"ሴቶች በዓላማ ጠንክረው ከሰሩ ያሰቡበት ደረጃ መድረስ ይችላሉ፤ እናንተ ለሀገር ተስፋዎች ናችሁና በርቱ" ስትል አትሌት መሰረት ደፋር በመድረኩ ላይ ንግግር አድርጋለች።

ሌላው በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአ.አ. ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ኃ/ጊዮርጊስ "እቴጌ መነን ወደ ትክክለኛ ማንነቱ የተመለሰ ታሪክ ሆኗል ፤ ጎበዝ፣ አስተዋይ እና የወደፊቷ ኢትዮጵያ መሪ የሆኑ ሴቶች እየተማሩበት ነው። ስፖርት በጤና እና ስነምግባር የበለፀገ ማህበረሰብን ይፈጥራል ዛሬ አብረን የተሳተፍንበት እንቅስቃሴ የዚህ ማሳያ ነው። መጋቢት 13 የሚኖረው ሩጫ ከምንም በላይ አብሮነታችንን የምናሳይበት እንዲሆን አብረን እንሰራለን" ብለዋል።

የቀድሞ የፖለቲካ ሰው ብርቱካን ሚደቅሳ ቀደም ሲል ይማሩበት በነበረው በዚህ ትምህርት ቤት ተገኝተው ለተማሪዎቹ እና ለመምህራኑ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ለአሁኑ ትውልድ ተማሪዎች ማበረታቻ እንዲሆን አዲስ ካሳተሙትን 'መመለስ' የተሰኘ መጽሐፍ የተወሰነ ክፍልን በማንበብ የራሳቸውን ታሪክ ከማጋራታቸው ባሻገር መፅሐፋቸውን በስጦታነት ለት/ቤቱ አበርክተዋል።

በልዩ ዝግጅቱ ማጠቃለያ ላይ በትምህርት ቤቱ ተማሪዎች መሀከል ጠንካራ የፉክክር መንፈስ የታየበት የዱላ ቅብብል የሩጫ ውድድር የተካሄደ ሲሆን፣ ይህም በውድድሩ ዋዜማ በትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ዘንድ ልዩ መነቃቃትን ፈጥሯል።

ስለ የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች  ኪ.ሜ. አጠቃላይ መረጃ

* የውድድሩ ቀን፦ እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም።
* መነሻ እና መድረሻ፦ ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ።
* ተሳታፊዎች፦ 16,000 ሴቶች፣ ከ150 በላይ ጠንካራ ተፎካካሪ አትሌቶች እና ከ25 ተምሳሌት ሴቶች።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ23 ዓመታት ያለማቋረጥ ሲያካሂደው የቆየው ይህ ውድድር፣ ዘንድሮም "በመላ ኑሪ በኮንፊደንስ ሩጪ" በሚል የውድድር መልዕክት በደመቀ ሁኔታ ለመካሄድ ዝግጅቱን አጠናቋል።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ነፃነት ፣ ድል ፣ ጀግንነት፣ ኩራት ፣… በዓድዋ!

እንኳን ለ130ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ!

#Adwa #GreatEthiopianRun #Ethiopia #AfricanVictory

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

✨ቅዳሜን በቆንጆ ሁኔታ ያሳለፍንበትን ሩጫችን ላይ በድጋሚ ለመገኘት አሁኑኑ ይመዝገቡ!🤩

ለቀጣይ ሩጫችን ምዝገባ ላይ ነን!✨📣

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ✨

#EntotoCBERun #GreatEthiopianRun #EntotoPark

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

🚨 ማስታወቂያ 🚨

💫የእንጦጦ ፓርክ ሲ.ቢ.ኢ. ሩጫችን ወደ የሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ ተዘዋውሯል 💫

🤩ቀጣይ ሳምንት የካቲት 14 እንገናኝ🤩

✨እንጦጦ ፓርክ ሲ.ቢ.ኢ. ሩጫ✨

የካቲት 14 እንገናኝ!

#EntotoCBERun #GreatEthiopianRun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

በየወሩ የሚካሄደው የእንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ ከየካቲት ወር ጀምሮ ተመልሷል።

የካቲት 05 ቀን 2018 ዓ.ም.

በጉጉት የሚጠበቀውና በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚዘጋጀው ወርሃዊው 'እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ' የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር ዳግም ተጀመረ። የፊታችን የካቲት 7 ቀን 2018ዓ.ም. በሚካሄደው በዚህ ውድድር፣ ከተለመደው የስፖርት እንቅስቃሴ እና ውድድር ባለፈ የፍቅረኛሞች ቀንን (Valentine's Day) ታሳቢ ያደረጉ ልዩ ዝግጅቶች ተካተዋል።

ሩጫ ወዳጆች ሁሉ በውድድሩ ላይ እንዲሳተፉ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር ባሉበት ቦታ ሆነው በሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ አማካኝነት በነፃ እና በቀላሉ መመዝገብ እንዲችሉ አድርጓል።

በተጨማሪም ወደ እንጦጦ ፓርክ የሚደረገውን ጉዞ ምቹ እና ቀላል ለማድረግ የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ለተሳታፊዎች በመሄጃ መንገዳቸው ላይ ያሉትን የአዲስ አበባን አዳዲስ መዳረሻዎች እየጎበኙ ወደ ፓርኩ አድርሶ የሚመልስ የትራንስፖርት አገልግሎት በነፃ አዘጋጅቷል።

የወሩ የሩጫ መርሃ-ግብር «የእኔ አጋር ይሮጣል» (My Valentine is Running) በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን፣ጥንዶች በጋራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበትን መንገድ ታሳቢ አድርጎ ተዘጋጅተል። ይህንንም ለማበረታታት ጥንዶች የሚፎካከሩበትና አሸናፊዎች የሚሸለሙበት ልዩ ፉክክር አንዱ የውድድሩ ድምቀት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በውድድሩ አሸናፊ ለሚሆኑ ጥንዶች በኩሪፍቱ ሪዞርት ልዩ ሽልማቶች ይበረከቱላቸዋል።

ስለ ውድድሩ መግለጫ

የእንጦጦ ፖርክ ሲቢኢ ሩጫ በየወሩ የተለያየ ጭብጥ በመያዝ የሚዘጋጅ የ5ኪ.ሜ. የፓርክ ሩጫ ነው። ውድድሩ ማህበረሰቡ በስፖርት እንዲነቃቃ፣ ተፈጥሮን እንዲያደንቅ እና ሩጫን ቋሚ ልምምዱ እንዲያደርግ ዓላማ ያደረገ ወርሀዊ ውድድር ነው።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ጋዜጣዊ መግለጫ
 
የእንግሊዝ ሃገር አንጋፋ አትሌቶች ስብስብ የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክ አካል የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ሀዋሳ ሃይቅ ግማሽ ማራቶን ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ።
 
ሐሙስ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም.፦


ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ የሆኑ አንጋፋ አትሌቶችን ያሰባሰበ ቡድን በዛሬው ዕለት ከእንግሊዝ ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ እንግሊዛዊያኑ ተሳታፊዎች የፊታችን የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም. በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በሚካሄደው 14ተኛው ሀዋሳ ሃይቅ ግማሽ ማራቶን ላይ ይወዳደራሉ፡፡
 
ከተሳታፊዎቹ ውስጥ ከ55 አመት በላይና ከ5000 ሜትር በላይ ውድድር የዓለም ሻምፒዮን እንዲሁም ከ65 ዓመት በላይ  የማራቶን ሪከርድ ባለቤት የሆነው ቤን ሬይኖልድስን ይገኝበታል የሪከርዱ ሰዓትም 2 ሰዓት ከ47 ደቂቃ ነው። በተጨማሪም ቡድኑ በ5 ኪ.ሜ. ርቀት ውድድር በጣም ፈጣኑን የእንግሊዝ ከ60 ዓመት በላይ አንጋፋ አትሌት ሯጮች መሐከል ሁለቱን ያካትታል።
 
የእንግሊዛውያኑ ቡድን የመጀመሪያዎቹን ዘጠኝ ቀናት ቆይታውን በአዲስ አበባ በልምምድና በጉብኝት ያሳልፋል፡፡ አባላቱም በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ አንዳንዶቹ በመንገድ፣ በትራክ እና በሀገር አቋራጭ ውድድር ላይ በተለያየ የዕድሜ ክልል ባሉ የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች ላይ ይሳተፋሉ።
 
በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሞብላይዜሽን አስተባባሪ ሃላፊ የሆኑት አብዱራዛቅ አሌዊ ስለ ቡድኑ ሲናገሩ "እነዚህ ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ አንጋፋ አትሌቶች ምን ያህል ፈጣን ሰዓት እንዳላቸው ማየት አስደናቂ ነው። ኢትዮጵያ ያሉ ሯጮችም ይህን ማየት እንደሚያበረታታቸውና የራሳቸውን የሩጫ ግቦች ማስቀመጥን እንዲቀጥሉ እንደሚያነሳሳቸው ተስፋ አደርጋለሁ። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያም በሀዋሳ በሚገኘው የግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ከእንግሊዝ ከመጡት አንጋፋ አትሌቶች ጋር ለመወዳደር ኢትዮጵያዊ አንጋፋ አትሌቶችን ያቀፈ ቡድን አዘጋጅቷል" ብለዋል፡፡
 
የእንግሊዝ ቡድንን አስተባባሪ የሆነው ስቲቭ ዋትሞው እንደተናገረው "ይህ ጉዞ ለውጤት የበቃው  የእኔን ወደ ኢትዮጵያ ስለመምጣት ከሪቻርድ ጋር ባደረግነው ውይይት ነው። ስለ ዕቅዶቼ ለጓደኞቼ መንገር እንደጀመርኩ ሌሎችም መቀላቀል ፈለጉ። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ስልጠና እና ውድድር ለመካፈል እንዲሁም የዚህን አስደናቂ ሀገር ባህልና ታሪክ ለማየት በጣም ጓጉተናል።" ብለዋል፡፡
 
የ2018 የኢትዮ ቴሌኮም የሀዋሳ ሃይቅ ዓለም አቀፍ ግማሽ ማራቶን በቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ቴሌብር ፣ ዳሽን ባንክ፣ ፔፕሲ፣ ፋብ የውበት ሳሙና፣ ቶፕ ውሃ፣ ኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት እንዲሁም በአፍራን ሆስፒታል ድጋፍ የተዘጋጀ ነው።
 
የ2018ቱ ኢትዮ ቴሌኮም የሀዋሳ ሃይቅ ግማሽ ማራቶን በሀዋሳ ሃይቅ ዳርቻ ላይ በሚገኝ መንገድ ላይ የካቲት 1 ቀን 2018ዓ.ም. በድምቀት ይካሔዳል።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ጋዜጣዊ መግለጫ

የቡድን ስራ እና የመንገድ ደህንነት መልዕክቶች የጎሉበት 20ኛው አይ.ኤፍ.ኤች./አ.አ.መ.ባ. የዱላ ቅብብል ሩጫ ዛሬ ተካሔደ

20ኛው የአይ.ኤፍ.ኤች./አ.አ.መ.ባ. የዱላ ቅብብል ሩጫ ከቦሌ ቡልቡላ ወደ ኮዬ ፈቼ በሚወስደው መንገድ ላይ ዛሬ ተካሒዷል።

በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አማካኝነት የተዘጋጀው ይህ ልዩ ውድድር፣ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ ተሳታፊዎችን አወዳድሯል። ዝግጅቱ የሁለት አስርት ዓመታትን የአካል ብቃት እና የኢትዮ-ቻይና ወዳጅነት የጠነከረበት እንዲሁም የመንገድ ደህንነት መልዕክቶች የተላለፉበት መድረክ ሆኗል።

የአዲስ አበባ የቀለበት መንገድ ምረቃን ተከትሎ የተጀመረው ይህ የዱላ ቅብብል ሩጫ፤ በአሁኑ ወቅት በብዙ ተቋማት ዘንድ የሚጠበቅ የሰራተኞች የጋራ ቀን ሆኗል።

የዘንድሮው ውድድር “የ6ታችን ቃልኪዳን” (Our Pact) በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን፣ ይህም በቡድን አባላት መካከል ያለውን ትስስር እና በመተባበር ማሸነፍን የሚያጎላ ነው።

አራት የቡድን አባላቶች እያንዳንዳቸው አራት ኪሎ ሜትሮችን በሮጡበት የአትሌቶች ምድብ ከፍተኛ ፉክክር ታይቷል። በዚህም መሰረት በሁለቱም ፆታ ከኢ.ኮ.ስ.ኮ. የተሰባሰቡ አትሌቶች በአንደኛ እና ሶስተኝነት ሲያጠናቅቁ የኢትዮ ኤሌክትሪክ አትሌቶች ሁለተኛ ሆኘዋል።

ከአትሌቶች ውጭ እያንዳንዱ ቡድን ስድስት አባላትን የያዘ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ተወዳዳሪ 1 ኪሎ ሜትር በመሮጥ በድምሩ 6 ኪሎ ሜትር ርቀትን ሸፍነዋል። ውድድሩ በዘጠኝ የተለያዩ ዘርፎች አሸናፊዎችን የሸለመ ሲሆን፤ ይህም የመንግስት ተቋማትን፣ የንግድ ድርጅቶችን፣ ጂም እና የጤና ቡድኖችን፣ ኤምባሲዎችን፣ ባንክና ኢንሹራንስን፣ ሆቴሎችን፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን (NGOs) እንዲሁም የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አባላትና ጓደኞችን ያካተተ ነበር።

ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የኤምባሲ ዘርፍ የቻይና ኤምባሲ ቡድን ልዩ ቅንጅት በማሳየት ውድድሩን ሲያሸንፍ፣ በሆቴሎች ዘርፍ አሸናፊዎቹ ኃይሌ ግራንድ ሆቴሎች ደግሞ ከምድባቸው ባሻገር የአጠቃላይ የውድድሩ አሸናፊ በመሆን ድልን ተቀዳጅተዋል።

ይህ የ20 ዓመታት የውድድር ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን የቻይና ኮሙኒኬሽን ፈርስት ሃይዌይ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ (CCFHEG/CCCC) የሚያበረክተው ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል። የሲ.ሲ.ሲ.ሲ (CCCC) የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ ዌይ ቺያንግዩ በመድረክ ላይ ሲናገሩ “ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን እና የስፖርታዊ ጨዋነትን ለማሳደግ ብቻ ሳይሆን፣ የማህበራዊ ኃላፊነታችንን ለመወጣት በተለይም የመንገድ ደህንነት ግንዛቤን ለማስጨበጥ ይህንን ዝግጅት በቋሚነት ለማዘጋጀት ቁርጠኞች ነን” ብለዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን (AACRA) የጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ተክለፃዲቅ በበኩላቸው የመንገድ ደህንነት የጋራ ትብብርን የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸው፤ "ይህ ውድድር ስፖርትን ከማሳደጉም ባለፈ የአብሮነትና የትብብር ተምሳሌት ሆኖ ለሁለት አስርት ዓመታት ዘልቋል" ብለዋል። ወ/ሮ ትዕግስት አክለውም "የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ የብዙ አካላትን ርብርብና የተጠቃሚዎችን ተሳትፎ ይፈልጋል፤ ስለዚህ የመንገድ መሰረተ ልማት ሀብቶችን በባለቤትነት ስሜት በመጠበቅ የራሳችንን እና የሌሎችን ህይወት እንድናድን አሳስባለሁ" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

🎄ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች መልካም የገና በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኝላችኋል። 🎄

#GreatEthiopianRun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

💫መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ!
ሩጫን የአኗኗር ዘይቤያችን እናድርግ💫

#GreatEthiopianRun #DiscoverEthiopiaClassics #2026Registration #6CitiesSeries #DebreBirhan

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

✅ በቴሌብር ምዝገባ ጀምረናል! 🤩

ለፈጣን ማዕበል 900.00 ብር ወይም ለዘና ማዕበል 700.00 ብር በመክፈል ይመዝገቡ! ✨

በባንክ ኦፍ አሜሪካ የሚቀርብላችሁ የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ.

ቀድመው ይመዝገቡ!

#GreatEthiopianrun #PowerToDo #InspireNextGeneration #2026Registration

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

የቦስተን እና ሺካጎ ማራቶን የውድድር ዳይሬክተሮች በኢትዮጵያ በተደረገላቸው የሞቀ አቀባበል ደስታቸውን ገለፁ።

የሺካጎ ማራቶን የውድድር ዳይሬክተር ኬሪ ፒንኮቭስኪ እና የቦስተን ማራቶን የውድድር ዳይሬክተር ጃክ ፍሌሚንግ ዛሬ ረፋድ በቅድመ-ውድድር ፕሬስ ኮንፈረንስ ላይ ባደረጓቸው ንግግሮች፣ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ አዘጋጆችን አድንቀዋል። ሁለቱም ይህ የመጀመሪያ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ነው።

ጃክ ፍሌሚንግ ሲናገሩ "በአስደናቂ ሀገር በጣም ጥሩ ጊዜ እያሳለፍን እንገኛለን። እዚህ ያለው ሁሉም ሰው ቤታችን ያለን ያክል እንዲሰማን እያደረገን ነው። እሁድ ሩጫውን እስከማይ እጅግ ጓጉቻለሁ" ብለዋል።

በትናንት ምሽቱ ልዩ የዕራት ግብዣ ስነስርዓት ላይ ኬሪ እና ጃክ፣ እንደ ብርሀኔ አደሬ፣ ኃይሌ ገብረስላሴ እና እራሱም የአዘጋጆቹ የክብር እንግዳ ሆኖ አዲስ አበባ የሚገኘው ሞሰስ ታኑይን ጨምሮ በርካታ የቀድሞ የውድድሮቻቸውን አሸናፊዎች የመገናኘት እድል ነበራቸው።

የፊታችን እሁድ የሚካሄደው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 25ኛ ዓመቱን የሚያከብርበት ሲሆን ፤ ውድድሩ የሚወክለውን የማሰባሰብ መንፈስ በማስታወስ "ሀገር በ10 ኪ.ሜ" የሚል መፈክርን ይዘዟል።

በአርቡ ፕሬስ ኮንፈረንስ ላይ ከተዋወቁ ሌሎች እንግዶች መካከል አሜሪካዊው የቀድሞ የማራቶን የዓለም ሬኮርድ ባለቤት ካሊድ ካኑቺ እና ኬኒያዊው የቀድሞ የ3000ሜ እና 5000ሜ የዓለም ባለ ሬኮርድ ዳንኤል ኮመን ይጠቀሳሉ። ኮመን በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ሶስት የ5000ሜ የዓለም ሬኮርዶች ያሰበረውን (ሁለት የኃይሌ እና አንድ የኮመን) ከኃይሌ ገብረስላሴ ጋር የነበረውን ተፎካካሪነት አስታውሷል።

የሩጫው ቀናት የሚጀምረው ነገ (ቅዳሜ) ማለዳ በእንጦጦ ተራራ በሚካሄደዉ የንጋት የ3ኪ.ሜ. ሩጫ ሲሆን፣ ከዚያም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የ2018 ዩኒሴፍ የልጆች ሩጫ ይደረጋል። ተጠባቂው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ውድድር የሚካሄደው እሁድ ይሆናል።

ተሳታፊዎች ጠዋት 1፡00 መስቀል አደባባይ እንዲደርሱ የውድድሩ ኦፕሬሽንስ ዳይሬክተር ዳግም ተሾመ ሲያሳስብ ፤ የፈጣን ማእበል መነሻ ግዮን ሆቴል እና የዘና ማዕበል መነሻ መስቀል አደባባይ እንደሚሆንም አስታውሷል፡፡

25ኛው ዓመት ልዩ ውድድር ላይ 55ሺህ ተሳታፊዎች ይጠበቃሉ። የዘንድሮ ውድድር አጋሮች ፤ ሶፊ ማልት የስያሜ አጋር ፣ ዩኒሴፍ የመልዕክት አጋር ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉዞ አጋር ፣ ኢትዮ ቴሌኮምና ቴሌ ብር የቴክኖሎጂ አጋር ፣ ዳሽን ባንክ የባንክ አጋር ፣ ፋብ የውበት ሳሙና የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫዎች የንዕህና አጋር ፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር ፣ ቶፕ ውሃ ፣ ሃያት ሬጀንሲ ፣ ኢ.ቢ.ሲ. እና አፍራን ሆስፒታል ናቸው።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

📌 ምዝገባ ተጀምሯል!!! ✍️

🗓 የዚህ ወር እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን መጋቢት 26 ይካሔዳል - በሲቢኢ ብር ፕላስ ይመዝገቡ📱

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ✨

መጋቢት 26  ቀን 2018ዓ.ም. እንገናኝ!

#EntotoParkCBERun #GreatEthiopianRun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች የ4 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም.

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ በተሰኘው የ2018 ሶፊማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለምአቀፍ 10ኪ.ሜ. የበጎ አድራጎት ዘመቻው አማካኝነት ያሰባሰበውን 4 ሚሊዮን ብር በቼሻየር ኢትዮጵያ መናገሻ ቢሮ በተከናወነ ደማቅ ስነ-ስርዓት ለተመረጡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረክቧል።

በዘንድሮው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ድጋፍ የተደረገላቸው ተቋማት ቼሻየር ኢትዮጵያተስፋ ማህበራዊና ልማት ማህበርየኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን እና እዘነት አካል ጉዳተኞች ህፃናት እና ወላጆች መርጃ ድርጅት በኢትዮጵያ ናቸው።

​በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ባስተላለፉት መልዕክት "ዛሬ ማዕከሉን ተገኝቼ በመጎብኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል ፤ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከስፖርታዊ እንቅስቃሴው ባሻገር ህዝብን ከማስተሳሰር ባለፈ፣ ችግረኞችን ለመርዳት የሚያደርገው ጥረት ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተግባር ነው።በቀጣይም ሌሎች በርካታ ተቋማትን ማገዛችንን እንቀጥላለን" ብለዋል።

​አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ በበኩሉ "ይህን 'ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ ዘመቻን ስንጀምር ዓላማችን ስፖርታዊ ውድድሩ ለወገኖቻችን መድረሻ እንዲሆን ነበር። ዛሬ ላይ በየአመቱ ተጠናክሮ መቀጠሉ አስደሳች ነገር ነው። ከምንሰበስበው ገንዘብ በላይ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ በሚሰጠው ትኩረት ትልቅ ኩራት ይሰማኛል" ሲል ገልጿል።

​በዕለቱ በግላቸው ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ላሰባሰቡና ለዘመቻው ስኬት ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦች ልዩ ዕውቅና ተሰጥቷል። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ወደፊትም ስፖርትን ከበጎ አድራጎት ጋር በማስተሳሰር ማህበራዊ ግዴታውን መወጣቱን እንደሚቀጥልም በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

​ይህ ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ የተሰኘው ዘመቻ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድርን ከማዘጋጀት ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከሚወጣባቸው መንገዶች ዋነኛው ሲሆን፤ ከተጀመረም 20 ዓመታትን አስቆጥሯል። ባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ከተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች በማሰባሰብ ለተለያዩ ተቋማት ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል። ዘመቻው ከገንዘብ ድጋፍ ባለፈ ተቋማቱ ተከታታይ የድጋፍ ምንጭና የመገናኛ ብዙኃን ሽፋን እንዲያገኙ በማድረግ ለህጻናት፣ ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለተፈናቃዮች የላቀ ፋይዳ ያለው ስራ ሲያከናውን ቆይቷል።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

አትሌት በርነሽ ደሴ ለተከታታይ ዓመት የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪ.ሜ. አሸናፊ ሆነች

የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ውድድር ዛሬ በድምቀት መነሻና መዳረሻውን ቦሌ አትላስ በማድረግ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በሩጫው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ውድድሩን ከማስጀመራቸው አስቀድሞ ባደረጉት ንግግር “ሴቶች በጥበብ ይኖራሉ፤ በራስ መተማመን ይሠራሉ፤በራስ መተማመን ይሮጣሉ፤ ይችላሉም!“ ብለዋል።

በውድድሩ 16 ሺህ ሴቶች የተሳተፉ ሲሆን በአትሌቶች ዘርፍ ያለፈው ዓመት አሸናፊ የነበረችው በርነሽ ደሴ ከፀደይ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ 15:22.91 በመግባት አሸናፊ ሆናለች።

ሮቤ ዲዳ 15:23.90 በመግባት 2ኛ ስትሆን በመድረኩ ተጠባቂ የነበረችው ሰናይት ጌታቸው 15:30.35 በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

በባለፈው አመት ለአሸናፊ አትሌቶች የነበረው የ50 ሺህ ሽልማት በዚህ አመት በዕጥፍ አድጎ 100 ሺህ ብር ለአሸናፊዋ አትሌት ተበርክቷል።

በውድድሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ መኪዩ መሀመድና ሌሎችም የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

የ23ኛው ዓመት ውድድር "በመላ ኑሪ በኮንፊደንስ ሩጪ" በሚል የውድድር መልዕክት ሲከበር የውድድሩ አምባሳደር አትሌት መሰረት ደፋርን ጨምሮ ታላላቅ አትሌቶችም የታደሙበት ነበር።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው ዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ዒድ ሙባረክ!

#GreatEthiopianRun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

አትሌት መሰረት ደፋር ለ16ሺህ ሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫን ከ’35 ደቂቃ በታች’ የማጠናቀቅ ፈተናን አቀረበች፡፡

ከተለያዩ የስራ ዘርፎች የተመረጡ ተምሳሌት ሴቶች የውድድሩ አንድ አካል በመሆን ስኬታቸው የሚወደስበት ፕሮግራም በሩጫው ቀን ይከናወናል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚያዘጋጀውና መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሚካሄደውና 16,000 ሴቶች ለሚሳተፉበት የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. የሩጫ ውድድር ልምምድ ቀጥሏል። የሁለት ጊዜ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ የውድድሩ አምባሳደር መሰረት ደፋር ሴቶች አስቀድመው እንዲለማመዱ እና እንዲሮጡ ለማበረታታት ዓመታዊውን የ’35 ደቂቃ በታች’ ፈተና ይፋ አድርጋለች።

ተሳታፊዎች ይህንን ግብ እንዲመቱና በስፖርት የዳበረ ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤን እንዲለማመዱ ለመርዳት፣ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ4 ተከታታይ ሳምንታት የሚቆይ የስልጠና መርሃ ግብር በማከናወን ላይ ነው። ስልጠናው በሙያዊ አሰልጣኞችና አሯሯጮች (pace-makers) የሚታገዝ ሲሆን፣ በመሰረት ደፋር የአራት ሳምንታት የልምምድ ምክሮች የታጀበ ነው።

እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ የውድድሩ መነሻና መድረሻ በቅርቡ እድሳት በተደረገለት ቦሌ አትላስ አካባቢ የሆነው ይህ ውድድር ከስፖርታዊ እንቅስቃሴ ባለፈ የሴቶች ስኬት የሚዘከርበት ፣ ስራቸው የሚነገርበት እና ዕውቅና የሚያገኝበት እንዲሁም አንዳቸው ሌላቸውን የሚያበረቱበት ልዩ መድረክ ሆኖ ለ22 ዓመታት ቀጥሏል።

ዘንድሮም በ‘ተምሳሌት ሴቶች’ (Icons Women) መሐከል የሩጫ ውድድር የሚከናወን ሲሆን፣ የአሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት በስማቸው ለመረጡት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይለገሳል። በ23ኛው ዓመት ሩጫ ውድድር ላይ ከስምንት የተለያዩ ዘርፎች የተመረጡ ታዋቂ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ይሳተፋሉ። ዘርፎቹም፦ ከኪነጥበብ፣ ከበጎ አድራጎት፣ ከመምህራን፣ ከሰራ አመራሮች፣ ከሚዲያ ባለሙያዎች፣ ከስራ ፈጣሪዎች፣ ከጤና ባለሙያዎች እና ከማህበራዊ ሚድያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የተውጣጡ ናቸው። በዚህም መሰረት፦ ሉላ ገዙ፣ እማሆይ ዜና ማርያም፣ ሊያ ሳሙኤል፣ ቤተልሄም ደሴ፣ መቅደስ ሙሉጌታ (መቅዲዬ) እና ቤቲ ጂ በውድድሩ ላይ በተምሳሌት ሴቶች ዘርፍ ከሚሳተፉ ባለሞያዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።

ለውድድሩ የተመዘገቡ ተሳታፊዎች ከመጋቢት 2 እስከ 4 ቀን 2018 ከአለም ሲኒማ ጋር ቲሸርታቸውን መውሰድ እንደሚችሉም ታውቋል፡፡ ውድድሩ በሳፋሪኮም፣ ኤም-ፔሳ፣ ዲ.ኬ.ቲ (DKT)፣ ዳሽን ባንክ፣ አክቲቭ (Aktive)፣ የአየርላንድ ኤምባሲ፣ ዩኒሴፍ (UNICEF)፣ ፋብ የውበት ሳሙና፣ ቶፕ ውሃ፣ ህያት ሬጀንሲ፣ ኢቲቪ እና አፍራን ሆስፒታል አጋርነት ይዘጋጃል።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

በአምስት ቀናት 10ሺህ ሴቶች ለ2018 የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ ተመዘገቡ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ 10,000 የውድድር ቦታዎች መያዛቸውን አስታወቀ።

ምዝገባ በተጀመረ የመጀመሪያ ሳምንት ከ60በመቶ በላይ ተሳታፊዎች መመዝገባቸውን በመጥቀስ ከጠቅላላው 16,000 የውድድር ቦታዎች ውስጥ አሁን የቀሩት 6,000 ቦታዎች መሆኑን ገልፅዋል።

በየዓመቱ ለሴቶች ብቻ የሚዘጋጀውና እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ሊከናወን የታቀደው ይህ ውድድር ዘንድሮ 23ኛ ዓመቱን ያከብራል። ውድድሩ በኢትዮጵያ ውስጥ የሴቶችን ስኬት በማክበር ረገድ እየተጫወተ ባለው ሚና እና የውድድር ቀን ባለው ልዩ ድባብ ምክንያት በተሳታፊዎች ዘንድ ተጠባቂ ቀን ሆኗል።

የዘንድሮው የውድድር መልዕክት ‘በመላ ኑሪ ፤ በኮንፊደንስ ሩጪ’ (‘Live Smart - Run Confident’) የሚል ነው። ይህ መልዕክት ሴቶች ህይወታቸውን በእውቀት እና በዕቅድ በሚመሩ የጤና ውሳኔዎች ላይ እንዲመሰርቱ በማሰብ በዲኬቲ ኢትዮጵያ አማካኝነት የቀረበ መልዕክት ነው።

ምዝገባው ለቀሩት 6,000 ቦታዎች በ 590 ብር ክፍያ ክፍት ሆኖ ይቀጥላል።

ተሳታፊዎች በዲጂታል መንገድ በ ኤም-ፔሳ (M-Pesa) እና በ ዳሽን ሱፐር አፕ (Dashen SuperApp)፣ ወይም በአካል በ ሳፋሪኮም ሱቆች (ፍየል ቤት ፣ አራት ኪሎ ፣ መገናኛ እና ጀሞ) እንዲሁም በ ዳሽን ባንክ ቅርንጫፎች (ፒያሳ ፣ ጣና መርካቶ እና ልደታ) መመዝገብ ይችላሉ።

የሴቶችን ተሳትፎ ለማበረታታት በየመተግበሪያዎቻቸው ለሚመዘገቡ ኤም-ፔሳ የ15% እንዲሁም ዳሽን ባንክ የ10% ቅናሽ እያደረጉ ይገኛሉ።

በተጨማሪም የተማሪነት መታወቂያ ማቅረብ ለሚችሉ ተማሪዎች የ30% ልዩ ቅናሽ በታላቁ ሩጫ አማካኝነት ተዘጋጅቷል።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. 23ኛውን ውድድር ምዝገባ ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም.

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄደውን የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ ውድድር ምዝገባ ዛሬ በይፋ አስጀምራል።

ይህ በየዓመቱ ለሴቶች ብቻ የሚዘጋጀው ሩጫ በቦሌ አትላስ ሆቴል አቅራቢያ በሚገኘው የተለመደ ስፍራ መነሻ እና መድረሻውን በማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር ውድድሩን ያካሒዳል። ውድድሩ የኢትዮጵያ ሴቶችን ስኬት በማብሰር እና ለሌሎች ተምሳሌት በማድረግ 23 ዓመታትን ተጉዟል።

ዛሬ በህያት ሬጀንሲ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተወከሉ የስራ ሃላፊዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የውድድሩ አምባሳደር አትሌት መሰረት ደፋር ተገኝተዋል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ፣ በውድድሩ ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ከዚህም በላይ ማሳደግ እና ማስፋፋት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። ዳግማዊት ሲናገሩ "የውድድሩን መመዝገቢያ ዋጋ ለሁሉም ሰው ተደራሽ እንዲሆን በማሰብ፣ ተመጣጣኝ ለማድረግ የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ነው" ብለዋል። ኤም-ፔሳ (M-Pesa) መተግበሪያውን ተጠቅመው ለሚመዘገቡ የ15% ቅናሽ ፤ እንዲሁም ዳሽን ባንክ በሱፐር አፑ ለሚመዘገቡ የ10% ቅናሽ እንዳዘጋጁም አያይዘው ተናግረዋል።

የስያሜ አጋር የሆነውን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በመወከል የብራንድ እና ኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ የሆኑት ሔርሜላ ይልማ በበኩላቸው፡ "እንደ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ የሴቶችን ጥንካሬ የምናንጸባርቅበት፣ ድምፃቸውን የምናሰማበት እና ስኬታቸውን የምናከብርበት የዚህ ዓመታዊ ውድድር ዋና ስፖንሰር በመሆናችን ትልቅ ኩራት ይሰማናል። ጠንካራ አጋርነታችንም ወደፊት እንደሚቀጥል ላረጋግጥ እወዳለሁ" ብለዋል።

የዘንድሮው ውድድር በዲ.ኬ.ቲ ኢትዮጵያ (DKT Ethiopia) የቀረበውን ‘በመላ ኑሪ - በኮንፊደንስ ሩጪ’ የሚል የውድድር መልዕክት ይተላለፍበታል። በመክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት የዲ.ኬ.ቲ. ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አዲቲያ ፑትራ "ዲ.ኬ.ቲ. ኢትዮጵያ የውድድሩ የመልዕክት አጋር በመሆኑ ደስታ ይሰማዋል። ‘በመላ ኑሪ - በኮንፊደንስ ሩጪ’ የሚለው መሪ ቃል፣ በቂ ግንዛቤ ያለው፣ የስነ-ተዋልዶ ጤና ምርጫ በራስ መተማመንን እና ዕድሎችን ይፈጥራል የሚለውን ዕምነታችንን ያንጸባርቃል። በኢትዮጵያ ያልተሟላ የቤተሰብ ምጣኔ ፍላጎት አሁንም እንደ ፈተና ቢቀጥልም፣ ይህ አጋርነት የጤና ግንዛቤን ከማህበረሰብ ተሳትፎ ጋር ለማስተሳሰር ይረዳል" ብለዋል።

ለ23ኛው ዓመት የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ ምዝገባ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. በኤም-ፔሳ፣ በዳሽን ሱፐር አፕ እና በአራት የሳፋሪኮም ሱቆች ይጀምራል። የዘንድሮው የውድድር መመዝገቢያ ዋጋ 590 ብር ነው። ውድድሩ በሳፋሪኮም፣ ኤም-ፔሳ፣ ዲ.ኬ.ቲ. ኢትዮጵያ፣ ዳሽን ባንክ፣ አክቲቭ (Aktive)፣ የአየርላንድ ኤምባሲ፣ ዩኒሴፍ (UNICEF)፣ ፋብ ውበት ሳሙና፣ ቶፕ ውሃ፣ ህያት ሬጀንሲ፣ ኢ.ቲ.ቪ እና አፍራን ሆስፒታል አጋርነት የተዘጋጀ ነው።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ለታላቁ ሩጫ አባላት በሙሉ!

ከእናንተ ቤተሰቦቻችን ጋር ሁሌም የምናሳልፋቸው ጊዜያት አስደሳች መሆናቸው ይታወቃል።

በመጪው ቅዳሜ ማለዳ በሚደረገው የእንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን ላይ ደግሞ እየተዝናናን ከታላቁ ሩጫ አባላት ጋር ዕውቅና የምንሰጣጥበት ልዩና አዝናኝ ዝግጅት ይኖረናል።

ስለሆነም በፎቶው ላይ በተጠቀሱት ዘርፎች ውስጥ የምትመርጧቸውን ዕጩ ተሸላሚዎች ለ @Zak_Abdu በመላክ እንድታሳውቁን በትህትና እንጠይቃለን።

በየዘርፉ ከሚጠቆሙ ተሳታፊዎች መሐከል በተደጋጋሚ የተመረጡትን የመጨረሻ ዕጩዎች እናሳውቃለን።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ!

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

🤩 የልወቅሽ ኢትዮዽያ ክላሲክስ 2ኛ መዳረሻችን በነበረችው ሀዋሳ ውብ የእረፍት ቀናት እና ሩጫ ውድድር ነበረን ✨

2018 ኢትዮ ቴሌኮም ሀዋሳ ሃይቅ ግማሽ ማራቶን✨

ቀጣይ መዳረሻችን - ጅማ - ሚያዝያ 18 ቀን 2018ዓ.ም.

✨ይጎብኙ፣ ይሩጡ፣ ሀገርዎን ይወቁ ✨

#GreatEthiopianRun #DiscoverEthiopiaClassics #2026Registration #6CitiesSeries #LHHM

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ምዝገባ ተጀምሯል!
ሲቢኢ ብር ፕላስ ላይ ገብተው በነፃ ይመዝገቡ!

በድጋሚ የተመለሰው እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ - የመጀመሪያ ወር ውድድር✨

ቅዳሜ የካቲት 7 በእንጦጦ እንገናኝ ✨

#EntotoPark #CBE #GreatEthiopianRun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

🚨 ማስታወቂያ! ለአትሌቶች በሙሉ 🏃🏾‍♀️🏃🏾

የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ሐዋሳ ሃይቅ ግማሽ ማራቶን የአትሌቶች ምዝገባ ላይ ነን!

ውድድሩ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ሐዋሳ ላይ ይካሄዳል።

ምዝገባ:- ላምበረት ማራቶን ህንፃ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሯችን በመግኘት አልያም በስልክ በመደወል እንድትመዘገቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ለበለጠ መረጃ
011-663-5757

#GreatEthiopianRun #Ethiopia

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ኢትዮ ቴሌኮም እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ2018 የ“ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ” ተከታታይ ውድድሮችን በአጋርነት

ለማከናወን የሚያስችል ስምምነት አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ - ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም - ኢትዮ ቴሌኮም እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ2018 የ”ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ”
(Discover Ethiopia Classics) ተከታታይ ውድድሮችን በአጋርነት ለማከናወን የሚያስችል ስምምነት አድርገዋል። በስምምነቱ መሰረት
ኢትዮ ቴሌኮም በአምስት ዋና ዋና ክልላዊ ውድድሮች ላይ የስያሜ ስፖንሰር (Title Sponsor) በመሆን የሚሳተፍ ሲሆን፤ ይህም ኩባንያው
ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ለቱሪዝም እድገት ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት እና ጽኑ ቁርጠኝነት አንዱ ማሳያ ነው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የ2018 የሩጫ ተከታታይ ውድድሮችን በአምስት ከተሞች ማለትም በደብረ ብርሃን፣ ሐዋሳ፣ ጅማ፣ በቆጂ እና ሐረር
የሚደረጉት ውድድሮች የስያሜ አጋር ሲሆን፣ የመጀመሪያው ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በደብረ ብርሃን ጥር 3 ቀን 2018 ዓ.ም የሚጀምር
ይሆናል፡፡ ይህም ጤናማ እና አምራች ዜጋን ከመገንባት ባሻገር የኢትዮጵያን ውብ መልክዓ ምድሮች፣ ታሪካዊ ቦታዎችና ባህሎች ለማስተዋወቅ
እና መልካም ማህበራዊ ትስስሮችን ለማጠናከር የላቀ ሚና ይኖረዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የታላቁ ሩጫ የቴክኖሎጂ አጋር በመሆን ተሳታፊዎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ተሞክሮ እንዲኖራቸው የሚያስችል ልዩ
የሩጫ መተግበሪያ (Running App) በማበልፀግ በስራ ላይ ያዋለ ሲሆን፣ ይህም መተግበሪያ በየትኛውም የሀገራችን አካባቢዎች ለሚከናወኑ ውድድሮች በውድድር ወቅት ያሉ መረጃዎችንና መገኛ ቦታን በቀጥታ ለመከታተል ከፍተኛ ጠቀሜታ ይሰጣል። ይህ የቴክኖሎጂ ትስስር ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የአኗኗር ዘይቤን ለማስተዋወቅ ከሚያከናውናቸው ስትራቴጂዎች መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡

በስምምነቱ ወቅት የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ኮሙኒኬሽን ኦፊሰር መሳይ ውብሸት እንደገለፁት ኩባንያው ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር ዘመኑ
የደረሰባቸውን አዳዲስ የቴሌኮም ቴክኖሎጂዎች እና የዲጂታል ሶሉሽኖችን በሀገራችን ተግባራዊ በማድረግ የዲጂታል ኢትዮዽያን ራዕይ እውን
ለማድረግ እያከናወነ ከሚገኘው መጠነ ሰፊ ስራዎች በተጨማሪ ከሌሎች ተቋማትና ድርጅቶች ጋር በመተባበርና በመቀናጀት ለሀገራችን
ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አብራርቷል፡፡

አክለውም “ይህ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ“ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ” ተከታታይ ውድድሮች አጋርነት ስምምነትም የዚህ ኢንሸቲቭ አንዱ
አካል ሲሆን፣ ኩባንያው በአካልና በስነ-ልቦና የተገነባ ጤናማ ትውልድ ለመገንባት፣ የሩጫ ውድድሮቹ የሚካሄድባቸው ከተሞችን ይበልጥ
ለማስተዋወቅና የቱሪዝም መዳረሻ ፍሰትን ለመጨመር እየተከናወኑ የሚገኙ ጥረቶችን ለማጠናከር እንዲሁም በሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍ
እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው በመግለጽ በቀጣይም ለሀገራችን እድገት ቁልፍ ሚና ያላቸውን ተግባራት በመለየትና በቴክኖሎጂ
እንዲታገዙ በማድረግ አጋርነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ በበኩላቸው “ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሁልጊዜም ከሩጫ በላይ መሆኑን
በመግለፅ ባህላችንን እና ህዝባችንን የምናውቅበት እና የምናስተዋውቅበት መድረክ ነው” ብለዋል። ዋና ስራ አስኪያጇ አክለውም “ኢትዮ
ቴሌኮምን እንደ ዋና አጋር ማግኘታችን ውድድሮቹን ወደ ላቀ ደረጃ እንድናሸጋግር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው” ብለዋል፡፡

ይህ አጋርነት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ቱሪዝምን ለማሳደግ ያለውን የጋራ ራዕይ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ የደብረ ብርሃንን ታሪካዊነት፣
የሐዋሳ ሃይቅን ውብ ገፅታ፣ የጅማን የቡና መገኛነት፣ የአትሌቶች መፍለቂያ የሆነችውን በቆጂን በማጉላት እና የሐረርን የቱሪስት መስህብነት
አጉልቶ በማሳየት ኢትዮጵያን የስፖርት ቱሪዝም ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ ያለመ ነው።

ኢትዮ ቴሌኮም እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ
ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ጋዜጣዊ መግለጫ

የ2018 ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ደብረ ብርሃን እና ሐረርን በመጨመር ዛሬ በይፋ ተጀመረ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ በሚል ስያሜ በስድስት የክልል ከተማዎች ላይ ተከታታይ የሩጫ ውድድር ሊያዘጋጅ ነው።

በ2017ዓ.ም. በ4 መዳረሻ ከተማዎች ላይ የተካሔደው የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ተከታታይ ውድድር ፤ በዚህም ዓመት ደብረብርሃን እና ሐረርን በመጨመር 6 ከተማዎች ላይ ይካሔዳል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባለፈውም ዓመት አዘጋጅ በነበሩት ሐዋሳ፣ ጅማ፣ ቦቆጂ እና አርባምንጭ ላይ ለተከታታይ ዓመታት እንዳደረገው ሁሉ ዘንድሮም ስኬታማ ውድድሮችን ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ይህ ስፖርት እና ቱሪዝምን በማቀናጀት የሃገራችንን ከተሞች እና የቱሪዝም ስፍራዎችን በስፋት እያስተዋወቀ የሚገኘው መርሃግብር አዳዲስ ከተሞችን በመጨመር ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የሚካሔድ ሲሆን ከጥር እስከ ሐምሌ ፤ ከአንኮበር እስከ ሐረር በር የሚል መርህ ተሰጥቶት ይካሔዳል።

የ2018 ልወቅሽ ኢትዮጵያ የስድስት ከተሞች ተከታታይ ውድድር ይፋ በተደረገበት የዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የቱሪዝም ሚኒስቴር እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስፖርት እና ቱሪዝምን በማስተሳሰር እየሰሯቸው ያሉትን ስራዎች ይበልጥ አጠናክሮ ለመስራት የሚያስችላቸው የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) “ልወቅሽ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያንን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ሀገራት ተሳታፊዎችን መሳብ የቻለ ዝግጅት ለመሆን በቅቷል። በዚህ አጋጣሚ ደብረ ብርሃን እና ሐረር የዘንድሮውን ልወቅሽ ኢትዮጵያ መቀላቀላቸዉን ማብሰር እፈልጋለሁ” ብለዋል።

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ መኪዩ መሃመድ በበኩላቸው “ስፖርትን ከቱሪዝም ጋር በማጣመር ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እየሰራ ያለዉን ስራ እንደ ሚኒስትር መስሪያ ቤት የምናደንቀው እና የምንደግፈው ነው ፤ ከዚህ በኋላ አብረን የምንሰራ ይሆናል ’’ ብለዋል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ በበኩላቸው “ለሃገራችን ‘ልወቅሽ ኢትዮጵያ’ የሚባል አዲስ የቱሪዝም ምርት በማስተዋወቃችን እና ከሩጫ ውድድርነት ባሻገር ኢትዮጵያን በትንሹም ቢሆን ማሳየት በመቻላችን ደስተኞች ነን ፤ ይህ እንዲሳካልን ለሚያግዙን ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ሁሉም አጋሮቻችን ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ተሳታፊዎችም አብረውን እንዲጓዙ እጋብዛለሁ” ብለዋል።

ጤናማ የአኗኗር ዘይቤዎን፣ ጓደኝነትን እና አንድነትን የሚያበረታታው ልወቅሽ ኢትዮጵያ በደብረ ብርሃን ከተማ በጥር 03 ቀን 2018ዓ.ም. የማራቶን ዱላ ቅብብል እና የሀገር አቋራጭ ውድድሮችን በማካተት ጅማሮውን ያደርጋል።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ለ2019 ሩጫችን ነገ ነው ምዝገባችን!✨

በባንክ ኦፍ አሜሪካ ለሚቀርብላችሁ የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ዝግጁ?✨

ቀድመው በቴሌብር ይመዝገቡ!

ለፈጣን ማዕበል 900.00 ብር ወይም
ለዘና ማዕበል 700.00 ብር በመክፈል ይመዝገቡ።

#GreatEthiopianrun #PowerToDo #InspireNextGeneration #2026Registration

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

የስፖርቶች ተደራሽነትን ለማስፋት ባንክ ኦፍ አሜሪካ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአጋርነት ለመስራት ተስማሙ

እ.አ.አ. በ2026 የሚጀምረው አጋርነት የስኬታማውን ውድድር ዓለም አቀፋዊ ስም የበለጠ ከፍ ያደርጋል እንዲሁም ለልጆች የሩጫ እድሎችን በእጅጉ ያሰፋል፡፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እ.አ.አ. ከ2026 ጀምሮ ከባንክ ኦፍ አሜሪካ ጋር አብረው ለመስራት የበርካታ ዓመታት የአጋርነት ስምምነት ማድጋቸውን ዛሬ አሳውቋል፡፡ አጋርነቱ ባንኩ በረዥም ርቀት ሩጫ ላይ የነበረውን ግዙፍ እንቅስቃሴ ከአፍሪካ እጅግ ተለዋዋጭ እና በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ የሩጫ ማህበረሰቦች ወደ አንዱ እንዲያሰፋ ያግዘዋል፡፡

ባንክ ኦፍ አሜሪካ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሶስት ትልልቅ የሩጫ ሁነቶች (events) ላይ በጋራ ይሰራሉ - የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ ፣ የልጆች ሩጫዎች እና ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ.። ባንክ ኦፍ አሜሪካ እነዚህን ውድድሮች ተጠቅሞ የኢትዮጵያን ደማቅ የሩጫ ባህል እይታ ለማሳደግ እና በስፖርት፣ ቱሪዝም እና ንግድ አማካይነት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ ለማድረግ ተዘጋጅቷል፡፡

ባንክ ኦፍ አሜሪካ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አጋር የመሆኑ ምክንያት ተቋሙ ቀጣዩን ትውልድ ለማነሳሳት እና በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የፅናት ስፖርቶችን ለማስፋፋት ካለው ማህበረሰብ-ተኮር መርሆ የተነሳ ነው፡፡ ይህ ባንክ ኦፍ አሜሪካ በስፖርት አማካይነት እድገትን የማነሳሳት እና ማህበረሰቦችን የማገዝ የረዥም ጊዜ ቁርጠኝነቱን ሲያጠናክር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫን የሁሉም የህይወት ዘይቤ የማድረግ ዋነኛ ራዕይ ጋርም የተስማማ ሆኗል።

ዝርዝሩን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ

Читать полностью…
Subscribe to a channel