greatethrun | Unsorted

Telegram-канал greatethrun - Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

-

This is the official Great Ethiopian Run Telegram channel, call 0116635757 for details Admin: @GER_BERUK @GER_BEDE

Subscribe to a channel

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ከቡድንዎ ፈጣን ማን ነው? 😱
በታህሳስ 6 አብረን እናያለን 😁

የ2017 አይ ኤፍ ኤች/አክራ የዱላ ቅብብል ሩጫ ✨

#IFH #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ዮሚፍ ቀጀልቻ ቫሌንሺያ በተካሄደው ግማሽ ማራቶን ሩጫ 57:30 በመግባት አዲስ የዓለም ክብረወሰን ሰብሯል!!

እንኳን ደስ አለን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

cc: Athletics weekly

#Greatethiopianrun #news

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ቅርብ ነው! 😮
3 ሳምንት ብቻ ይቀረናል!😍

የጀመሩትን ልምምድ ሳያቋርጡ ኃይልዎን ያሰባስቡ🙌

💫 2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪ.ሜ  💫⭐️🤩

📅 ሕዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም

#sofimalt #Foreverychild #Nutrition #Creatingmemories  #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

የእሑድ ልምምዳችን ይቀጥላል!🏃‍♀️🏃‍♂️

እኛም በአራቱም ልምምዶች ላይ ለእድለኞች የፓስታ ፓርቲ ጥሪ መሸለማችንን እንቀጥላለን!🤩✨✨

ያለፈው ልምምድ ባለዕድል ኤልያስ ካሳ ነበር . .  ቀጣዩ እርስዎ ይሆኑ?

ባለን ውስን ቦታ ይመዝገቡ:
https://docs.google.com/.../1FAIpQLSduom.../viewform...

💫 ለ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10 ኪ.ሜ ከአሁኑ
አስፈላጊውን ልምምድ እናድርግ  💫⭐️🤩

📍ወሎሰፈር አደባባይ

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ስለመጪው ሩጫችን ልናውቅ የሚገባን ነገር🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♀️🏃‍♂️

በፈጣን ማዕበል አብረውን ለመሮጥ ሲመጡ ከጠዋቱ 1:00 ላይ መገኘትዎን ያረጋግጡ።

ከ1:55 በኋላ በር ዝግ ይሆናል!
📍መነሻ - ግዮን ሆቴል ዋናው በር

2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪ.ሜ 💫💫

#sofimalt #ForEveryChild #Nutrition #Creatingmemories  #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

4 ሳምንት ብቻ ይቀረናል! እጅ እና እግር  በዝግጅት ላይ ናቸው? 😎

የአጫጭር ፍጥነት ልምምድ ይሞክሩ!

* በፍጥነት መሮጥ ከዛም ትንፋሽ መሰብሰብ
* ከ1 ደቂቃ እስከ 2 ደቂቃ ሶንሶማ (ከ6 እስከ 8 ጊዜ መደጋገም)

በተጨማሪም ማንኛውም ሰው በቀን 20 ደቂቃ መሮጡ ከተጋላጭ በሽታዎች ሩቅ ያደርገዋል 🙌

💫 2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪ.ሜ  💫⭐🤩

የተመጣጠነ ምግብ ለሁሉም ህፃናት 🥰

📅 ሕዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም

በግል ተመዝጋቢዎች በቴሌ ብር ባሉበት መመዝገብ ይችላሉ 🤳

ለድርጅቶች የምዝገባ ቦታ
📍 ላምበረት ሃይሌ ግራንድ ሆቴል አጠገብ: ኮረብታማ ህንጻ ቁጥር 2 4ተኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ
☎️ 0116 63 57 57
☎️ 0116 18 58 41

#sofimalt #Foreverychild #Nutrition #Creatingmemories  #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

'ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ' በሚለው ዘመቻ የ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪ.ሜ ምዝገባ ክፍት ሆኗል! 💫💫

ሌሎችን በመደገፍ አብረን እንሩጥ!🤩🏃‍♀️🏃‍♂️

በግል ተመዝጋቢዎች በቴሌ ብር ባሉበት መመዝገብ ይችላሉ 🤳

ለድርጅቶች የምዝገባ ቦታ
📍 ላምበረት ሃይሌ ግራንድ ሆቴል አጠገብ: ኮረብታማው ህንጻ 4ተኛ ፎቅ

#sofimalt #Creatingmemories  #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

5 ሳምንት ብቻ ቀረው! 🏃‍♀️🏃‍♂️

ሩጫን የአኗኗር ዘይቤዎ ለማድረግ ይህንን የ5 ሳምንት ልምምድ መሞከር መልካም አጋጣሚ ነው! 💪🤩

ባለፈው ሳምንት የጀመርነውን ልምምድ ቀስ በቀስ እንቀጥል. . .

⏳ ለ30 ደቂቃ ቢሮጡ እና ቢራመዱ ይመከራል

✅ በመጪው ሳምንት የሩጫ እና የእርምጃ ሰዓት ወደ 40 ደቂቃ እየጨመሩ ከአሁኑ ይዘጋጁ

👩‍⚕️👨‍⚕️ ጤናዎትን መከታተል አይዘንጉ!

#sofimalt #Creatingmemories #Greatethiopianrun #trainingtips

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

እንኳን ደስ አለን! 🤩🎉⭐💫🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♀️🏃‍♂️🇪🇹

2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ሩጫ በአለም አትሌቲክስ የውድድር ደረጃዎች ውስጥ ተካተተ!

መስከረም 28 ቀን 2017 አ.ም. ፦ የአለም አትሌቲክስ አስተዳዳሪ (World Athletics) የ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ሩጫን የሌብል ደረጃ ያለው የጎዳና ላይ ውድድር ((Label Road Race) ሲል ዕውቅና ሰጥቶታል።

የአለም አትሌቲክስ የሌብል ደረጃ ሲል የሰየማቸው ውድድሮች በጥራት ዝግጅቶችን ከማድረግ ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ ከመሆን እና የተሳታፊዎች ውድድሩ ላይ የነበራቸው ቆይታ ፣ የከተማ አስተዳደሮች ለዝግጅቱ ያላቸውን ድጋፍ ፣ እንዲሁም ዝግጅቱ በአትሌቲክስ ውድድር ዘርፍ አበረታች መድኃኒት ላይ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው።

እጅግ በርካታ የሩጫ ውድድሮች ባሉበት አለም ይህንን የሌብል ደረጃ ማግኘት ዝግጅቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ያሳየውን ዕድገት እና በአለማችን ካሉ ቀዳሚ እና ተመራጭ የጎዳና ላይ ውድድሮች መሀከል መሆኑን ያሳያል።

የአለም አትሌቲክስ አስተዳዳሪው አካል (World Athletics) ውድድሮችን በመመዘን በየአመቱ ደረጃዎችን ይሰጣል። የመሮጫ ኮርስ ልኬት ፣ የውድድር ሰዓት ምዝገባ እና የኤሊት አትሌቶች ተሳትፎ ከግምት ውስጥ የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው።

24ኛው ዙር ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪሜ ህዳር 8 ቀን 2017 በ50ሺ ተሳታፊዎች ይካሄዳል፡፡

#sofimalt #Creatingmemories #Greatethiopianrun #worldathletics

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

6 ሳምንት ብቻ ይቀረናል. . .ዱብ ዱብ እንጀምር!

2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪ.ሜ 💫💫

#sofimalt #Creatingmemories #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ስፖርትን ከቱሪዝም ጋር!
ሩጫ በእንጦጦ እንዲህ ደማቅ ነበር 🤗🙌

የዓለም ቱሪዝም ቀንን ቅዳሜን እንጦጦ ተገኝተን እንዲህ ስላሳለፍን እጅግ ደስተኞች ነን!🤩

እናመሰግናለን!

#Landoforigins #Greatethiopianrun #entoto #sporttourism

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

Spots are filling up fast for our entoto run on World Tourism Day!

Don't miss your chance to be part of this amazing event this Saturday!

Start point: Entoto Park Main Entrance
Finish point: Old Entoto Race Start (Kaldis Coffee)

Starting time: 08:00 am
Location: Entoto park

Top three winners will be rewarded 🎉🎉🎉

Sign up now before it's too late! 🏃‍♂️🌍

Registration link: https://docs.google.com/forms/d/19_zw29Ohq1V25SGPu8wTmHxJn9GnBNGaoxVwOgUKhLg/viewform?edit_requested=true

Free for first 500 registrants!

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ነገ ነሐሴ 23/2016 ዓ.ም እና ነሐሴ 24/2016 ዓ.ም (ማለትም በተከታታይ ሁለት ቀናት) በቢሮዋችን እንደማንገኝ ለክብር ደንበኞቻችን እናሳውቃለን።

በዚህም መሰረት ጉዳይ ለማስፈጸም ቢሮዋችን መገኘት ለምትፈልጉ ከሁለቱ ቀናት ውጪ ይገኙ 🙏

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ

#greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ኢትዮጵያ የወርቅ ባለቤት! 🥇🇪🇹

💎 ኮርተናል!! 💎

ታምራት ቶላ በወንዶች የማራቶን ሩጫ በ2024 ፖሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ አስገኝቷል!

እንኳን ደስ አላችሁ! ⭐💫
እንኳን ደስ አለን! 💫

#Ethiopianathlete #Olympics #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

2ኛ! 🥈🇪🇹
በሪሁ አረጋዊ በ10,000ሜ በአስገራሚ ፉክክር የ2024 ፖሪስ ኦሊምፒክ ውድድር ለኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ አስገኝቷል!

እንኳን ደስ አላችሁ!
እንኳን ደስ አለን!

#Creatingmemories #Congratulationethiopia #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

እንጦጦ ተራራን መሮጥ እና መሄድ አንድ አይደለም! ⛰ 🦅

ወደ እንጦጦ መሄድ ማለት ተፈጥሮን ማወቅ ነው። በእንጦጦ መሮጥ ደግሞ ተፈጥሮን ከማወቅ በላይ መተዋወቅ ነው 😍🌳☁️🏃‍♀️🏃‍♂️

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ✨✨

#ENTOTO #CBE #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

በጠዋት የተቃጠለ ትንፋሽ! 😍
አንድ . . .ሁለት ዱብ ዱብ በ 5ኪ.ሜ አለቀ🙌

💫 2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪ.ሜ  💫⭐️🤩

📅 ሕዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም

#sofimalt #Foreverychild #Nutrition #Creatingmemories  #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

እርስዎን ለመቀበል ሁሌም ደስተኞች ነን! ሩጫችንን በደማቁ ለማሳለፍ እንጥራለን 😍 የእርስዎ ቀን የእኛም ቀን ነው!! 🤗❤️✨

💫 2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪ.ሜ  💫⭐️🤩

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

በዘና ማዕበል አብረውን ለመሮጥ ሲመጡ ከጠዋቱ 1:00 በቦታዎት መገኘትዎን ያረጋግጡ።

📍መነሻ- መስቀል አደባባይ

2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪ.ሜ 💫💫

#sofimalt #ForEveryChild #Nutrition #Creatingmemories  #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ሁላችንም በቦታችን ተገናኝተን ሶምሶማ ከሩጫ ጋር ተለማምደናል😁🏃‍♀️🏃‍♂️

እሑድ ጠዋት ከእኛ ጋር እንዴት አለፈ? 🤗

💫 2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪ.ሜ  💫⭐🤩

የተመጣጠነ ምግብ ለሁሉም ህፃናት 🥰

📅 ሕዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም

#sofimalt #Foreverychild #Nutrition #Creatingmemories  #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

የልምምድ ቀጠሮ ከእኛ ጋር ያዙ!

ለአራት ሳምንት በሚቆየው የሩጫ ልምምድ በተከታታይ ተሳትፈው የፓስታ ፓርቲ ነጻ ጥሪ ያሸንፉ 🤩

ባለን ውስን ቦታ ይመዝገቡ:
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSduom_4qKJa3gAwbPIrFSJ110dOVXD6O49brvRlt-JikMsLUQ/viewform?usp=sf_link

💫 ለ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10 ኪ.ሜ ከአሁኑ አስፈላጊውን ልምምድ እናድርግ  💫⭐️🤩

📍ወሎሰፈር አደባባይ እንገናኝ

📅 ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም

ለበለጠ መረጃ
☎️ 0116 63 57 57
☎️ 0116 18 58 41

#sofimalt #Creatingmemories  #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

የ2017 ዩኒሴፍ የህጻናት ውድድር እና ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ በይፋ ተከፈተ! 🏃‍♀️🏃‍♂️😯🤩🤩

የተመጣጠነ ምግብ ለሁሉም ህጻናት የዘንድሮው ውድድር መልዕክት ነው፡፡ 🍽️
     
ጥቅምት 05 ቀን 2017 ዓ.ም. ፦ በዛሬው እለት በይፋ የተከፈተው የ2017 ዩኒሴፍ ህጻናት ውድድር ምዝገባ እና ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የተለያዩ የህብረተሰብ አካላትን አሳታፊ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡

የዘንድሮ የህጻናት ውድድር መልእዕክት ‘’የተመጣጠነ ምግብ ለሁሉም ህጻናት’’ ነው።

የዚህ አመት ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተመረጡት ማለትም አዲስ ህይወት አይነ-ስውራን ማዕከል; የአረጋውያን ድጋፍ እና እንክብካቤ ሰጪ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ህብረት;  ቪዥን ማየት የተሳናቸው ህፃናት ወላጆች በጎ አድራጎት ድርጅትን በይፋ ማስተዋወቅ ይገኝበታል ፡፡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዘንድሮው የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻ ላይ 3 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ ያቀደ ሲሆን፤ ከማሰባሰቢያ መንገዶቹ ውስጥ የተወሰኑ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መሮጫ ቲሽርቶችን በተጨማሪ ዋጋ መሸጥ አንዱ መንገድ እንደሆነም ታውቋል፡፡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባለፉት 23 አመታት ከ 30 ሚልዮን ብር በላይ አሰባስቦ አከፋፍሏል፡፡

የህጻናት ውድድር ላይ ለመመዝገብ በአለም ሲኒማ እና በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቢሮ በመገኘት መመዝገብ የሚቻል ሲሆን የመመዝገቢያ ዋጋውም 400 ብር መሆኑ ተገልጧል፡፡

#sofimalt #UNICEF #creatingmemories #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሃ/የተ የግል ማህበር እና በአዲስ አበባ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌደሬሽን መካከል የሶስት አመት የስራ መግባቢያ ሰነድ ተፈረመ፡፡

ጥቅምት 2 ቀን 2017 አ.ም. ፦ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተልዕኮው አድርጎ ከሚሰራባቸው ስራዎች አንዱ የአገራችንን አትሌቲክስ መደገፍ ነው፡፡  ይህንንም ለማጎልበት እና የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌደሬሽን በጋራ ለመስራት ጥቅምት 2 ቀን 2017 አ.ም. በይፋ ተስማምተዋል፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የአ.አ. አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት መልካሙ ተገኘ እና የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ ሲሆኑ በፕሮግራሙ ላይ የፌደሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ አባላት እንዲሁም የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የጋራ ስምምነቱም ካካተታቸው ተግባራት ውስጥ በፌደሬሽኑ በኩል የሙያዊ ድጋፍ ማቅረብና አትሌቶች በውድድሩ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማመቻቸት ተጠቃሽ ሲሆኑ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ ለተተኪ አትሌቶች የውድድር ዕድል ማመቻቸት፤ ፌደሬሽኑ ለሚያደርጋቸው ውድድሮች ሙያዊና ቁሳዊ እገዛ ማድረግ፤ ፌደሬሽኑ የሚሰራባቸውን የታዳጊ አትሌቶች ፕሮጀክቶች መደገፍ እንዲሁም የአትሌቲክስ መሰረት ልማት ላይ በጋራ መስራት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ህዳር 8 ቀን የሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪሜ በየአመቱ ከክፍያ ነፃ በሆነ ተሳትፎ ከ500 በላይ አትሌቶችን በውድድሩ ላይ ያሳትፋል፡፡ በ24 አመት ውስጥ በውድድሩ አሽናፊ የሆኑ አትሌቶች ለማስታወስ በሪሁ አረጋዊ፤ ሰለሞን ባረጋ፤ ሞስነት ገረመው፤ መልክናት ውዱ፤ ትግስት ከተማ፤ ያለምዘርፍ የኋላው፤ አቤ ጋሻው፤ ፎይተን ተስፋይና ቢንያም መሃሪ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

https://youtu.be/F5K-j9p7464?si=cS1_u252XizPRO5d

2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪ.ሜ እየደረሰ ነው! 💫💫

ከሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ እና አፋራን አጠቃላይ ሆስፒታል አጭር የሩጫ ልምምድ እና የራስ ክትትል እንውሰድ 🙌

#sofimalt #Creatingmemories #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ደማቅ ሩጫ ÷ ደማቅ ሕዳር! 🥳

በ2017 ሶፊ ልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪ.ሜ ተቀላቀሉን 💫💫

#sofimalt #Creatingmemories  #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

300 people have registered! 🎉
Secure your place before registartion is closed!😁🏃‍♀️🏃‍♂️

It is going to be an adventurous Saturday!

Start point: Entoto Park Main Entrance
Finish point: Old Entoto Race Start (Kaldis Coffee)

Starting time: 08:00 am
Location: Entoto park

Top three winners will be rewarded 🎉🎉🎉

Sign up now before it's too late! 🏃‍♂️🌍

Registration link: https://docs.google.com/forms/d/19_zw29Ohq1V25SGPu8wTmHxJn9GnBNGaoxVwOgUKhLg/viewform?edit_requested=true

Free for remaining 200 registrants!

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪ.ሜ በቅርቡ ይካሄዳል 💫💫

እየተዘጋጃችሁ ነው? 🏃‍♀️🏃‍♂️

#sofimalt #Creatingmemories  #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ኢትዮጵያ በማራቶን ሜዳልያ ደገመች! 🥈🇪🇹

ትግስት አሰፋ በሴቶች የማራቶን ሩጫ በ2024 ፖሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ለኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ አስገኝታለች!

እንኳን ደስ አላችሁ! ⭐💫
እንኳን ደስ አለን! 💫

#Ethiopianathlete #Olympics #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ድል በብር ተገኝቷል! 🥈🇪🇹

ጽጌ ዱጉማ በ800ሜ  ደማቅ ሩጫ የ2024 ፖሪስ ኦሊምፒክ ውድድር ለኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ አስገኝታለች!

እንኳን ደስ አላችሁ! ⭐💫
እንኳን ደስ አለን! 💫

#Ethiopianathlete #Olympics #Greatethiopianrun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

የውድድር መጀመሪያ ሰዓት: 2:00/2:10
የፈጣን ማዕበል መነሻ: ግዮን ሆቴል

የፈጣን ማዕበል ቲሸርት ዋጋ: 880 ብር
የዘና ማዕበል ቲሸርት ዋጋ: 640 ብር

በግል ተመዝጋቢዎች በቴሌ ብር እና በ6 የተመረጡ ዳሽን ባንክ ቅርንጫፎች! 🤩😎

ፒያሳ- ከመብራት ኀይል ህንጻ ፊት ለፊት
አድዋ አደባባይ- መገናኛ ከዘፍመሽ ሞል አጠገብ
ቦሌ ኖክ- ኖክ ዋና ቢሮ
ጣና - መርካቶ ጣና የንግድ ማዕከል/ ውስጥ
ልደታ - ከልደታ ቤ/ክ ፊት ለፊት
ሰሚት - ክዊንስ ሱፐር ማርኬት

በመገኘት የ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫን ከነገ ጀምሮ መመዝገብ ይችላሉ! 😁

Registration is tomorrow! 😎

#Creatingmemories #Goodluckethiopia #Greatethiopianrun

Читать полностью…
Subscribe to a channel