greatethrun | Unsorted

Telegram-канал greatethrun - Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

-

This is the official Great Ethiopian Run Telegram channel, call 0116635757 for details Admin: @GER_BERUK @GER_BEDE

Subscribe to a channel

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ምዝገባ ተጀምሯል🤩✨

ባላችሁበት ሆናችሁ በቴሌብር እና በዳሽን ባንክ ሱፕር አፕ ይመዝገቡ!

ሀገር በ10ኪ.ሜ.!✨

2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ.!

#GreatEthiopianrun #10k #25thEdition #Registration

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

የ2017 ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ውድድር ዛሬ በአርባምንጭ ከተማ ተጠናቀቀ

የ2017 ሳፋሪኮም ታላቁ ሩጫ በአርባምንጭ ዛሬ በአርባምንጭ ከተማ በድምቀት ተከናወነ።

ለሁለተኛ ጊዜ በተዘጋጀው የ2017 ሳፋሪኮም ታላቁ ሩጫ በአርባምንጭ በድምሩ 3000 ሯጮች የተሳተፉባቸው የ10ኪ.ሜ. ፣ 7ኪ.ሜ. እና የህፃናት ሩጫ ውድድሮች ተካሒደዋል።

በአትሌቶች የ10ኪ.ሜ. ውድድር በወንዶች እስራኤል አባተ በሴቶች ደግሞ ሰላም አበበ አሸናፊዎች ሆነዋል። እስራኤልን ተከትለው መለሰ ካሳሁን እና ሙሉነህ ፈቃደ በሁለተኛ እና ሶስተኝነት አጠናቀዋል። በተመሳሳይ በሴቶች ሰላም አበበን በመከተል ድንቅነሽ ኦርሴንጎ እና ሜሮን አበበ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።

በጤና ሯጮች መሀከል በተደረገው ውድድር በወንዶች ጃፈር ጀማል ፣ አብዮት ሞገስ እና ቲም ፊይዘር ከአንድ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ሲያጠናቅቁ ፤ በሴቶች ቴሬሳ ቦስትርፕ ስታሸንፍ ዝናሽ ታያቸው እና ፌቨን ሙላት ተከትለዋት በመግባት ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነዋል።

መነሻ እና መጨረሻውን ሲቀላ ዩኒቨርስቲ አደባባይ ላይ ያደረገውን የሩጫ ውድድሮች ያስጀመሩት የቱሪዝም ሚኒስትር ሚኒስቴር ዲኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) እና የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ መስፍን መንዛ (ዶ/ር) ናቸው።

በአራት የተለያዩ ከተሞች የተደረገው ይህ የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ተከታታይ ውድድር የሩጫ ተሳታፊዎቹን በመያዝ በሐዋሳ ፣ ጅማ እና ቦቆጂ ያደረጋቸው ውድድሮች መዝጊያ በሆነው የዛሬው የአርባምንጭ ሩጫ ላይ አራቱም ከተሞች ላይ ለሮጡ 50 ተሳታፊዎች ልዩ ባለ አራት ኮኮብ ሜዳሊያ ተበርክቷል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከቱሪዝም ሚኒስትር ጋር በመተባበር የሚያከናውነው ይህ የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ተከታታይ ውድድር በቀጣይ አመትም ተጨማሪ የመወዳደሪያ መዳረሻን በመጨመር ይከናወናል።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

📌 የዚህ ወር እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን ግንቦት 30 ይካሔዳል!

ቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ እንገናኝ!

አሁኑኑ ሲቢኢ ብር ፕላስ ላይ ተመዝግበው ይቀላቀሉን!

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ✨

#GreatEthiopianRun #EntotoCBERun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ከክረምቱ ዝናብ በፊት ለምናደርገው የዓመቱ የመጨረሻ ዙር እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን ምዝገባ ላይ ነን። ✨

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ ላይ ለመሳተፍ ሲቢኢ ብር ፕላስ ላይ ይመዝገቡ!

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ 🤩✨

#ENTOTO #CBE #GreatEthiopianRun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

የ2017 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በቦቆጂ ግንቦት 17 ቀን ለ4ተኛ ጊዜ ይካሄዳል

ታላቁ ሩጫ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እያዘጋጀው የሚገኘው የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ (Discover Ethiopia Classics) የአራት ከተሞች ተከታታይ ውድድር ሶስተኛ የውድድር ከተማ ቦቆጂ ሆናለች።

የኢትዮቴሌኮም ታላቁ ቦቆጂ ሩጫ ግንቦት 17 እንደሚከናወን ዛሬ በቱሪዝም ሚኒስቴር በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ ተደርጓል። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ እንደገና አበበ፣ የባህልና ስፖርት ቱሪዝም ሚኒስቴር ደኤታ አቶ መኩዬ መሐመድ የተገኙ ሲሆን በተጨማሪም የበቆጂ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ በዙ አበበ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ፤ ንግግርም አድርገዋል።

በመጨረሻም ለ3ተኛው ከተማ የልወቅሽ ኢትዮጵያ አዘጋጅ ቦቆጂ የአዘጋጅ ከተማ ልዩ ባንዲራና ቲሸርት በሁለቱ ሚኒስቴር ደኤታዎች ለቦቆጂ ምክትል ከንቲባ ተበርክቱዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የዚህ ልወቅሽ ኢትዮጵያ ጠቀሜታ አጠር ባለ ጥናት የጅማን ተሞክሮ እንደ ምሳሌ በመውሰድ የቀረበ ሲሆን በዝርዝሩም የኢኮኖሚ ፣ የቱሪዝም ፍሰት እና የስፖርታዊ ግንኙነት ጥቅም ባጭሩ ቀርቧል፡፡

በአትሌቶች እና የጤና ሯጮች የ12 ኪ.ሜ. ውድድር ፣ የ16 ዓመት በታች የታዳጊዎች ሻምፒዮና እና የህፃናት የሩጫ ውድድሮች በኢትዮቴሌኮም ታላቁ ቦቆጂ ሩጫ ላይ የሚካሔዱ ውድድሮች ሲሆኑ ከአዲስ አበባ ለሚመጡ ተሳታፌዎች ምዝገባው እስከ ፊታችን እሁድ (ግንቦት 10 / 2017ዓ.ም.) የሚቀጥል እንደሆነም ታውቋል። ውድድሩ ከሩጫም በተጨማሪ በአርሲ ሰንሰለታማ ተራሮች ላይ የሚደረግ የእግር ጉዞን እና የካምፒንግ ፕሮግራምን ያካተተ እንደሚሆን ተገልዷል፡፡

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ልጆችዎን ለማስደሰት ዝግጁ 🤩

ለልጆች ሳቅ፣ ጨዋታ እና ጤና በአንድ ቦታ ከእኛ ጋር✨✨

የ2017 የአውሮፓ ቀን የልጆች ሩጫ 🗓ግንቦት 3ቀን!😊

300ብር ብቻ ልጆችዎን ዛሬውኑ ያስመዝግቡ!

📌የምዝገባ ቦታ፡ ላምበረት በሚገኘው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቢሮ 4ተኛ ፎቅ እና ቦሌ አለም ሲኒማ!

#EuropeDay #ChildrensRaces #GreatEthiopianRun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

በእንጦጦ ከእናታችሁ ጋር እንድታሳልፉ ምዝገባ ተጀምሯል!

📌እስከ 1፡00ድረስ ስትመዘገቡ ለሁለታቹም በነፃ

📌 አናት አና ልጅ ሆናችሁ ለምትመዘገቡ ደግሞ አንዳችሁ በነፃ

በተጨማሪ- የመሮጫ ቁጥርዎን በራስዎት ዲዛይን ስለ እናትዎ ፅፈው ይሩጡ በልዩነት ይሸለሙ 👩‍👧‍👦

#GreatEthiopianRun #entotopark

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

25ኛ ዓመት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ህዳር 14 / 2018 ዓ.ም. ይካሔዳል

የብር ኢዮቤልዩ ላይ የደረሰው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ሊከናወን ሰባት ወራት ቀሩት። ህዳር 16 ቀን 1994ዓ.ም. ጅማሮውን ያደረገው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በቀጣይ ህዳር 14 ቀን 2018ዓ.ም. 25ኛ ዙር ውድድሩን ያከናውናል።

ከአፍሪካ ትልቁ የ10ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ውድድር የሆነው ዝግጅቱ ባለፉት 24 የውድድር ዓመታት ወደ 760ሺህ አካባቢ ሰው በ10ኪ.ሜ. ውድድሩ ላይ አሳትፏል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የዘንድሮ ውድድር በተጠናቀቀ ማግስት የ25ኛ ዓመት ክብረበዓሉን አስመልክቶ ለቀጣዩ ዓመት 5000 ተሳታፊዎችን ሲመዘግብ ቀዳሚ 500 ሰዎችን በነጻ መመዝገቡ ይታወሳል። ለሌሎች የውድድሩ ተሳታፊዎች ምዝገባ ሐምሌ ወር ላይ እንደሚከናወን ተገልጿል።

“25ኛ ዓመታችንን አብረውን በመሆን ካበረቱን ሁሉ ጋር ለማክበር ተዘጋጅተናል ፤ ደስታችንን ከራሳችን ለመጀመር በዚህ እሁድ ኬንያ በሚደረገው ኤልዶሬት ማራቶን ላይ ተሳትፈን እና ሩጫችንን አስተዋውቀን እንመለሳለን።” ያሉት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ “ከወዲሁ ከሩጫችን ጋር የተያያዙ የተሳታፊዎቻችንን ልዩ ልዩ ታሪኮች እና ገጠመኞች መሰብሰብ ስለጀመርን በማህበራዊ ሚድያ ገጾቻችን ላይ ቢነገር የሚሉትን ትውስታቸውን ያካፍሉን” ሲሉ ለተሳታፊዎች ጥሪ አቅርበዋል።

ከ24 ዓመታት በፊት ውድድሩ ሲጀመር ኃይሌ ገብረስላሴ እና ብርሃኔ አደሬ የመጀመሪያውን ዓመት ውድድር ያሸነፉ አትሌቶች ሲሆኑ ፤ በዘንድሮ ውድድር ላይ ወጣቶቹ አትሌቶች ቢንያም መሃሪ እና አሳየች አይቸው ማሸነፋቸው ይታወሳል።

የሩጫው ተሳታፊዎች ትዝታዎቻቸውን በ communications@ethiopianrun.org ላይ ማጋራት እንደሚችሉ ገልጿል።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

✨ ምዝገባ ተጀምሯል!!🤩

አትሌቶች መፍለቂያ በሆነችው በቆጂ ከእኛ ጋር  ይሩጡ ይዝናኑ ሀገርዎን ይወቁ!

ለመመዝገብ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSft3h5bfwiHdrbUDoLBa2INST8D0BtkEwJJp34C29RdfmNVqg/viewform?usp=sharing

#GreatEthiopianrun #Greatbokojirun #Bokoji

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

📌 የዚህ ወር እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን ሚያዝያ 04 ይካሔዳል!

ቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ እንገናኝ!

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ✨

ሚያዝያ 04/ 2017 ዓ.ም.

#EntotoCBERun #GreatEthiopianRun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ለመጋቢት ሩጫችን ምዝገባ ላይ ነን 📢

በሲቢኢ ብር ፕላስ ባሉበት ሆነው መመዝገብ ይችላሉ!

📌 ማስታወሻ - የዚህ ወር የእንጦጦ ሲቢኢ ሩጫችን የሚካሔደው  ሚያዝያ 04 (April 12) ነው!

🏃‍➡️🏃‍♀‍➡️ ጤናችን እየጠበቅን እየተደሰትን በእንጦጦ ዱብዱብ ማለታችንን እንቀጥላለን! 🏃‍♀🏃

እንዴት ልመዝገብ ካሉ:- ከስር ያለውን ተንቀሳቃሽ ምስል ይመልከቱ!👇✨

https://vm.tiktok.com/ZMkwk1JCa/

#EntotoParkCBERun #GreatEthiopianRum

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ከዝግጅት እስከ ሩጫ🤩

የ2017 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ውድድር✨

#GreatEthiopianRun #WomenFirst5k #allthewomenwelovetosee

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ክፍያ እና የገንዘብ ዝውውር በ M-Pesa ዘምነዋል!!!✨

የሩጫ ምዝገባችንም በM-pesa ቀላል ሆኗል💫🤩

#GreatEthiopianRun #WomenFirst5k #AllTheWomenWeLoveToSee

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ቶኘ ዉሀ ከቶኘ ሴቶቻችን ጋር!✨

የ2017 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ዉድድር ከቶኘ ጋር ተዉቦ ይጠብቃችኋል!✨

መጋቢት 7 ያንቺ ቀን!✨

#GreatEthiopianRun #WomenFirst5k #AllTheWomenWeLoveToSee

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

🌟 Get ready for an unforgettable experience on March 16,2025!

Join us for the 2025 Safaricom Women First 5km and treat yourself to a luxurious stay at the Hyatt Regency Addis Ababa. Run, celebrate, and create lasting memories with us! 🏃‍♀️✨

#GreatEthiopianRun #WomenFirst5k #AllTheWomenWeLoveToSee

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ምዝገባ ነገ ይጀመራል

የብር ኢዮቤልዩ ላይ የደረሰው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ውድድሩን ምዝገባ ነገ ይጀምራል።

የ25ኛ ዓመት ውድድሩ ላይ ለመመዝገብ እና ተሳታፊ ለመሆን የሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ በህያት ሬጀንሲ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ ምዝገባውን በዲጂታል / በኦንላይን እንደሚያከናውን የገለፀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ፤ ተመዝጋቢዎች ቴሌብር እና ዳሽን ባንክ ሱፐር አፕን በመጠቀም መመዝገብ እንደሚችሉ አሳውቋል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ “እንደ አንድ የአለም አትሌቲክስ ሌብል ያለው ውድድር (World Athletics Label Race) የምዝገባ መንገዳችን መዘመኑ አስደሳች ነው። በተጨማሪም እያደገ ለመጣው ውድድራችን እና ለተሳታፊዎቻችን የተሻለ እና ቀላል አማራጭ ማቅረብ የምንችልበት መንገድ ሆኗል” ብለዋል።

ህዳር 14 / 2018 ዓ.ም. ላይ የሚካሔደው ውድድሩ እንዳለፉት አመታት ሁሉ ሁለት የመሮጫ ማዕበሎች ይኖሩታል። በዚህም መሰረት ከነገ ጀምሮ በሚኖረው ምዝገባ ላይ ፤ የመመዝገቢያ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ለዘና ማዕበል 790 ብር እና ለፈጣን ማዕበል 950 ብር ይሆናል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የውድድሩን 25ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለእያንዳንዱ 25’ኛ ተመዝጋቢ ግለሰብ በነጻ የመመዝገብ ዕድል እንደተመቻቸ ፤ ይህም ከ700 በላይ ተሳታፊዎች በነጻ እንዲመዘገቡ ዕድልን ይፈጥራል ተብሏል።

ባለፈው የውድድር አመት ከነበረው የ50ሺህ ተመዝጋቢዎች ቁጥር በአምስት ሺህ ከፍ በማድረግ ፤ ዘንድሮ 55ሺህ ተሳታፊዎች ይመዘገባሉ ፤ በውድድሩ ቀንም ከዚህ ዓመታት የላቀ ቁጥር ያላቸው ተሳታፊዎች እንደሚኖሩት እና 10ኪ.ሜ. ርቀቱን እንደሚጨርሱ ይታመናል።

ልዩ ዝግጅቱ ላይ የሰራተኞቻቸውን ጤና በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የሚጠብቁ እና በተለያዩ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድሮች ላይ በተደጋጋሚ የሚያሳትፉ 11 ተቋማት ለሁለተኛ ጊዜ በተካሔደው የ'ኮርፖሬት ዌልነስ አዋርድ’ ላይ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከሚደረገው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ጎን ለጎን በ25 የአለማችን ከተሞች ላይ ኢትዮጵያን እና ሩጫውን በሚያስተዋውቅ መልኩ የርቀት (ቨርችዋል) ተሳታፊዎችን በማካተት ይካሔዳል።

የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ህዳር 14 ቀን 2018ዓ.ም. የሚከናወን ሲሆን ፤ ከነገ ጀምሮ ምዝገባቸውን የሚያከናውኑ ተመዝጋቢዎች መወዳደሪያ ቲሸርቶቻቸውን የውድድሩ ሳምንት ላይ በሚኖሩት 3 ቀናት የሚረከቡ ይሆናል።

የዘንድሮ ውድድር አጋሮች- ሶፊ ማልት የስያሜ አጋር ፣ ዩኒሴፍ የመልዕክት አጋር ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉዞ አጋር ፣  ኢትዮ ቴሌኮምና ቴሌ ብር የቴክኖሎጂ አጋር ፣ ዳሽን ባንክ የባንክ አጋር ፣ ፋብ የውበት ሳሙና የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫዎች የንዕህና አጋር ፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር ፣ ቶፕ ውሃ ፣ ሃያት ሬጀንሲ ፣ ኢ.ቢ.ሲ. እና አፍራን ሆስፒታል ናቸው።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

10% ቅናሽ በኤምፔሳ!

አሁኑኑ ተመዝግበው ሩጫችንን ይቀላቀሉን!🤩

✨የ2017 ሳፋሪኮም ታላቁ ሩጫ በአርባምንጭ✨

  📅 ሰኔ 22 እንገናኝ!

#GreatEthiopianRun #GreatRun #Arbaminch

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ጉዞ ወደ አርባምንጭ 🤩ምዝገባ ተጀምሯል !

በአረንጓዴዋ ከተማ አርባምንጭ ዱብዱብ ለማለት ለሰኔ 22 ቀጠሮ ይዘናል✨🤩

2017 ሳፋሪኮም ታላቁ ሩጫ በአርባምንጭ !

🗓ሰኔ 22/ 2017

ለመመዝገብ ከታች ያለወን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ!
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSch8HppuJTInPGFo1B5VBL-ouZbJY5CnpYlUefEQQPGBvmq1Q/viewform?pli=1

ለበለጠ መረጃ፡
📞 +251 116 635 757

#GreatEthiopianRun #GreatArbaminchRun #Arbaminch
#DiscoverEhiopiaClassics

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ስዩም ድሪባ እና መሰረት ጣፋ የ2017 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ የቦቆጂ ሩጫን አሸነፉ

አራተኛ አመቱን ያስቆጠረው የ2017 ኢትዮቴሌኮም ታላቁ የቦቆጂ ሩጫ ዛሬ መነሻና መድረሻውን በቦቆጂ ስታድየም በማድረግ ተከናውኗል።

በ12ኪ.ሜ. የአትሌቶች ፉክክር በወንዶች በግል የተወዳደረው ስዩም ድሪባ አሸናፊ ሲሆን አማን ቃዲ ሁለተኛ እንዲሁም ነጋሳ ደቀባ ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል። በሴቶች የጣፎ አትሌቲክስ ክለብ አትሌቷ መሰረት ጣፋ የአንደኝነቱን ቦታ ስታገኝ ደርቤ ተጫል እና ወርቄ አበጀ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።

በዝግጅቱ ላይ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ፣ ሚኒስትር ዲኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) ፣ የአርሲ ዞን መስተዳደር አስተዳደር አቶ ኢብራሂም ከድር እንዲሁም የቦቆጂ ከተማ ከንቲባ አቶ በዙ አበበ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በተጨማሪም በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ13 የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ፤ ወደ 75 የሚጠጉ ተሳታፊዎች ከአዲስ አበባ ወደ ቦቆጂ ተጉዘዋል።

በአርሲ አባቶች ባህላዊ ምርቃት የተጀመረው የዛሬው ውድድር ከአትሌቶች ጠንካራ ፉክክር ባሻገር የጤና ሯጮች የ12ኪ.ሜ. ውድድር ተከናውኖበታል። በውጤቱም በወንዶች ጃፈር ጀማል እንዲሁም በሴቶች ዴንማርካዊቷ ስቲነ ማርች አሸናፊ የሆኑበት ውጤት ተመዝግቧል።

ጠንካራ ፉክክር የታየበት የ15 ዓመት በታች የታዳጊዎች ሻምፕዮና የብዙ ተመልካቾችን ቀልብ የሳበ ውድድር ሲሆን ፤ የ2000ሜትር ርቀትን የሸፈነ ነበር። በተጨማሪም የ11 ዓመት በታች እና የህጻናት ውድድሮችም የዝግጅቱ ተጨማሪ ድምቀቶች ነበሩ።
የ'ልወቅሽ ኢትዮጵያ’ ተከታታይ ውድድር ቀጣይ እና የዚህ አመት የመጨረሻ መዳረሻ አርባምንጭ ከተማ ስትሆን ውድድሩ ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ይደረጋል።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

በአውሮፓ ቀን የህፃናት ሩጫ የአዲስ አበባ ታዳጊዎች የአትሌቲክስ ሻምፕዮና ተካሔደ

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የ16 ዓመች በታች የታዳጊዎች የአትሌቲክስ ሻምፕዮና በአውሮፓ የህፃናት ሩጫ ላይ ተካሔደ።

ዛሬ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በነበረው የአውሮፓ ቀን የህፃናት ሩጫ ውድድር ላይ ለመዝናናት ከተሳተፉት ህፃናት ባሻገር የፌደሬሽኑ የታዳጊዎች ውድድር ከፍተኛ ፉክክር የታየበት ነበር።

በውድድሩ በሁለቱም ፆታዎች ያሸነፉት ታዳጊዎች የማበረታቻ ሽልማት ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አትሌት መልካሙ ተገኝ እና በአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኤመስበርግ ሽልማቶቻቸውን ተረክበዋል።

አምባሳደር ሶፊ በውድድሩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር “ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ፣ ከትምህርት ቤቶችና ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ይህንን ዝግጅት በማድረጋችን እንዲሁም የቀጣዩ ትውልድ አትሌቶችን የምንፈጥርበት በመሆኑ ደስተኞች ነን” በማለት ተናግረዋል።

የአውሮፓ ህብረትና የኢትዮጵያ ወዳጅነትን 50ኛ ዓመት በተከበረበት የዛሬው የአውሮፓ ቀን ሩጫ ላይ ወደ 1800 የሚደርሱ ህፃናት የተሳተፉበት ነበር።

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ለልጆችዎ ልዩ ቀን !

የልጆችዎ ደስታ የኛም ደስታ ነው!

የ2017 የአውሮፓ ቀን የልጆች ሩጫ 🗓 ግንቦት 3 ቀን!😊

በቀሩት ጥቂት ቦታዎች በ300ብር ብቻ ልጆችዎን ዛሬውኑ ያስመዝግቡ!

📌 የምዝገባ ቦታ፡ ላምበረት በሚገኘው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቢሮ 4ተኛ ፎቅ #እና ቦሌ አለም ሲኒማ!

#EuropeDay #ChildrensRaces #GreatEthiopianRun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

በእንጦጦ የማይረሱት የእናት እና ልጅ ጊዜ ያሳልፉ ✨

በነጭ ወረቀት በራስዎት ዲዛይን ስለ እናትዎ ፅፈው ይሸለሙ 👩‍👧‍👦

📌በወረቀቱ መቅረት የሌለባቸው ነገሮች 📌

የመሮጫ ቁጥር ፣ የሩጫው ስም / ሎጎ

#EntotoCBERun #GreatEthiopianRun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

2017 የአውሮፓ ህብረት የልጆት ሩጫ

ሁሉም ልጆች የሚወዱት ቀን!

ለትናንሾቹ ኮከቦች የማይረሱት ቀን እንፍጠርላቸው!✨

😊በ300ብር ብቻ ልጆችዎን ዛሬውኑ ያስመዝግቡ!

ቀን: ግንቦት 3 2017 ዓ.ም.

📌የምዝገባ ቦታዎች:- * ላምበረት በሚገኘው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቢሮ
እና ቦሌ አለም ሲኒማ

ለበለጠ መረጃ👇
☎️ +251116635757
#GreatEthiopianRun #EU #children #race

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ሳቅ ጨዋታ የሞላበት የማይረሳ ድንቅ ማስታወሻ!!

💫 የ2017 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ጅማ ሩጫ
#GreatEthiopianRun#GreatJimmaRun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

እስካሁን አልተመዘገባችሁም!? 🤭

በከፍታው ላይ መሮጥ ፣ ጤናን መጠበቅ እና አዳዲስ ጓደኞችን ማፍራት
ሁሉንም በእንጥጦ ሲቢኢ ሩጫ ላይ ያገኛሉ!

አሁኑኑ ሲቢኢ ብር ፕላስ ላይ ተመዝግበው ይቀላቀሉን!

ማስታወሻ - የዚህን ወር ውድድር የምናደርገው ሚያዝያ 04 ነው!

# EntotoParkCBERun #GreatEthiopianRun

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ቀጣይ መዳረሻችን ጅማ ነው!✨

ሃዋሳ የጀመርነውን በሩጫ ሃገርን ማወቅ በጅማ እንቀጥላለን !🤩

እየሮጡ ሃገርዎን ይወቁ!ለመመዝገብ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ!👇
https://shorturl.at/1nCSN

#GreatEthiopianRun #jimma #discoverethiopiaclassics

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

የማይረሳ ድንቅ ማስታወሻ!!

የ2017 ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ውድድር!

#GreatEthiopianRun #WomenFirst5k #AllTheWomenWeLoveToSee

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ደስታሽ በኢቲቪ ይታይልሽ!

የሩጫ ቀንሽን በቀጥታ ስርጭት ኢቲቪ ያስተላልፋል !

የ2017 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ውድድር ✨

#GreatEthiopianRun #WomenFirst5k #AllTheWomenWeLoveToSee

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

ሩጫችን ልክ እንደ ስንቃችን!✨

ለ2017 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ውድድር ሰብሰብ ብለን የስንቅ ማልት የ4 ሳምንታት ልምምዳችን እሁድ እንቀጥላለን!

🗓እሁድ የካቲት 30 /2017 ዓ.ም
📍 ወሎ ሰፈር
⏰ ጠዋት 1:00


ለበለጠ መረጃ
011-6635757
011-6185841

#GreatEthiopianRun #WomenFirst5k #AllTheWomenWeLoveToSee

Читать полностью…

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)

Hey ladies!

Join us on March 16th, 2025, for an incredible day celebrating women, strength, and community.

With the support of the Irish Embassy, we're making this year's race bigger and better than ever!

Let's run, empower, and inspire together!

#GreatEthiopianRun #WomenFirst5k #AllTheWomenWeLoveToSee

Читать полностью…
Subscribe to a channel