Beneath the Skin (2015)
👨🏼🤝👨🏻 #BeneaththeSkin 👨🏼🤝👨🏻
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣0⃣6⃣
#ራስን_የመቀበል_ጉዞ_እንጀምር
#የመጨረሻ_ክፍል
#ራስን_በመቀበል_የሰዎችን_ምሳሌነት_መከተል
ራስን በመቀበል የሰዎችን ምሳሌነት መከተል ማለት ማንነቴን በማይነካ መልኩ የሰዎችን አርአያነት መከተል ማለት ነው፡፡ ራሱን በሚገባ የተቀበለ ሰው ራሱን ሳይጥልና ሳይተው መልካም ምሳሌ የሆኑ ሰዎችን በማየት ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ምሳሌነታቸውን ይከተላል፡፡
መልካም ምሳሌዎችን የመምሰል ጤናማ ጎዳና የሚያጠቃልላቸው እውነታዎች፡-
1. #ከስህተት_በመታረም_ደረጃ
ራስን ስነ-ምግባር በመምራትና እየሄደበት ካለው የስህተት ጎዳና ተመልሶ ፥ በእውነተኛው መንገድ ላይ ለመሄድ አርአያ የሆኑ ሰዎችን መምሰል መልካም ልምምድ ነው፡፡ እንዲያውም፣ ይህ ሁኔታ ራሱን በሚገባ በመቀበል ለማደግ የሚፈልግ ሰው ምልክት ነው፡፡
#ማሕበራዊ_ጤናማነትን_በመጠበቅ_ደረጃ
ከግል ሕይወታችንም ሆነ ከስራችን አንጻር ለማሕበራ ግንኙት የማይመችን ማንኛውንም ጤና ቢስ የሕይወት ዘይቤ በማስወገድ ደረጃ አርአያ ያረግነውን ሰው ምሳሌነት መከተል እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣0⃣5⃣
#ራስን_የመቀበል_ጉዞ_እንጀምር
#ክፍል_አራት
#ራስን_ያለመቀበል_መንስኤዎችን_መለየት
ራሳችንን ጥለን ወደ ሌላኛውና የእኛ ወዳልሆነው ማንነት እንድንማረክ ጥሪ የሚያደርጉ ሁኔታዎች በዙሪያችን ሞልተዋል፡፡ እነዚህ ጥሪዎች ካለን የውስጥ ስነ-ልቦናዊ ፍላጎቶች ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ በውስጣችን ያለውን የመወደድና ተቀባይነት የማግኘት ፍላጎት ለማሟላት ብዙ ነገሮችን ለማድረግ ይቃጣናል፡፡ ሳናስበውም ራሳችንን ማለቂያ የሌለው ጉዞ ውስጥ ገብቶ እናገኘዋለን፡፡ ይህ እንዳይሆን በውስጣችን ያሉትን ስነ-ልቦናዊ ፍላጎቶች በማወቅ ትክክለኛ መረጋጋት የምናገኝበትን መንገድ መፈለግ አለብን እንጂ ራስን ባለመቀበል ስቃይ ውስጥ መማቀቅ የለብንም፡፡
ከራሳችን ለመሸሽ ራሳችንን ያሳመንንባቸው ስውር ስነ-ልቦናዊ ምክንያቶች፡-
1. #ሰዎች_እንዲቀበሉን፡፡
ሰዎች ቤተሰባቸውን ለማስደሰት፣ ፍቅረኛ እንዲቀበላቸው፣ እንዲሁም አንድ ቡድን ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘት ራሳቸውን ለመለወጥ ይሞክራሉ፡፡ መጨረሻው ግን አያምርም፡፡ መፍትሄው ራስን ሆኖ መኖር ነው፡፡
2. #የዘመኑን_ሰው_መስሎ_ለመገኘት፡፡
የዘመኑን ፋሽን፣ የዘመኑን ቁመና፣ የዘመኑን የንግግር ዘይቤ … ለመጨበጥ የሚደረግ መፍጨርጨር አስጊ ነው፡፡ የዘመኑ ነገር ጤናማ ባህል ወደ መሆን መጥቶ እኛንም ከነካካን ችግር የለበትም፡፡ ከእውነተኛ ማንነታችን ካስወጣን ግን መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡
3. #ስኬታማ_መስሎ_ለመታየት፡፡
አንዳንድ ሰዎች በስራውም ሆነ በኑሮ ሁኔታ ስኬታማ መስሎ ለመታየት የማያደርጉት ጥረት የለም፡፡ ስኬት ግን የታይታና የአንድ ጊዜ ክስተት ሳይሆን ሂደትና የኑሮ ዘይቤ ነው፡፡ መነሻውም ራስን ሆኖ መገኘት ነው፡፡
ይቀጥላል . . .
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
....እንደዘበት አወቅኩክ ፤ ልግጫን ተንተርሼ ቀረብኩክ ፤ ማላገጤ አላስቆጣህም አሳቀህ እንጂ።
አብረን ሳቅን ፤ አሳሳቅህ ደስ አለኝ ፤ ቀልድ እየፈለኩ ፣ እየፈጠርኩ ቀለድኩ ፤ ሳቅልኝ ፤ ስትስቅልኝ ደስ አለኝ ፤ አሳሳቅህ አሳቀኝ ፤ ከሩቅ ላየን በራሴ ቀልድ እንደምስቅ አይገምትም ።
በእርግጥ ሳቅህ ነው የሚያስቀኝ ።
በሂደት ውስጣዊ ውበትህ ተነበበኝ ፤ እሩህሩህነትህን ተመለከትኩ ፤ አለምን የምታይበት መንገድ አስቀናኝ መንሸውረሬን አጎላከው
ትምክህቴ በሂደት ሟሟ። ከክብር ፍቅር እንደሚበልጥ በሂደት ቀስ እያልኩ ገባኝ። ድንገት አንድ እለት አንደበቴ "ከክብር ፍቅር ይበልጣል!!!" ሲል ራሴን ሰማሁት ። ❤❤❤
**አንተን ሳላቅህ ባልፍ እና ይሄን ፅሁፍ ባነበው ኖሮ ግነት ነው እል ነበር
እውነት** !
#እወድሃለሁ!
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
✅ ЯНГИ ҚУРИЛАЁТГАН УЙЛАРДАН УЙ ҚИДИРЯПСИЗМИ?
⚡️2023-2024-йилда қурилаётган уйлар ва уларнинг нархлари
⚡️12 ойдан 120 ойгача муддатли тўлов
⚡️Буларнинг барчаси @YangiBinolar телеграм каналимизда
የጌቱ ነገር
°°°°°°°°°
ያኔ እናቶቻችን እሳት ይሞቃሉ
ጌቱ ሲነግረኝ፡
" እማዬ ለምንድነው ማንደጃውን የምትሞቂው? "
" የአባትህን እራት እያሞቅሁ ነው "
ጌቱ አባቱ እራት እስኪበሉ ጓጓ!
ያቺውን ምስር ክክ አነከቱ!.......እስከነግሳታቸው።
አጎረሱት...
ጌቱ ግር አለው።
ጠበቀ...ጠበቀ....ምንም!
ቡና ከተጠጣ በኋላ እናቱ ማንደጃይቱን ሳብ አደረጉና በቀሚሳቸው ሸፈኗት!
" አባዬ! " አለ
" ምንድነው'ሱ?! ''
" ከዛም አጉርሰኝ!....''😳
ከወላጅ የማይጠበቅ ቅጣት ቀጡት!😜😜😂😂😂
ጌትሻ'ኮ ትለያለች!
'' ቲቸር! ጥያቄ አለኝ! "
'' ቀጥል! "
'' ሴቶች ከሸኑ በኋላ መሬቱ ለምን ይቦረቦራል? "😳
.......ጤናውን ስንቴ ተጠራጠርሁ......
" ቅዱስ ሚከአል አናትክን ይቦርቡረው!!...ይልቅ ከዘጠኙ ፕላኔቶች ሶስቱን ጥራ! "
ስራዬ ብሎ እናቶች ሲሸኑ ያጤናል...
ከዚያማ ጨርሰው ሲነሱ አዘናግቶ ያያል!
'' ፍቅርሻ!..አየሺው?..ብይ አያጫውትም? "
ይኸ ጦሰኛ!😂😂😂😂😜
አንድ ቀን ምሽት ላይ፡ እነጌቱ ቤት የጌቱ ድምጽ በለቅሶ ይደመጥ ያዘ!
ተሯሩጠው ሄደው አዩት!
ጌቱ እሳት ሲሞቅ ተያዘ!
.........ባላውቅህስ?! .......😂😂😂😂
© stolen
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣0⃣1⃣
#የብቸኝነት_ጎዳና
አንዳንድ ጊዜ ብቻችሁን የምትሄዱባቸው ጎዳናዎች እንዳሉ አትርሱ፡፡ የብቸኝነት ጎዳና ማለት በዙሪያችሁ አብረዋችሁ ያሉ ሰዎች አብሮነታቸውን ለማሳየት የማይፈልጉበት ወይም የማይችሉበት ሁኔታ ሲከሰት ማለት ነው፡፡
እነዚህ ጎዳናዎች ሰዎች ሊገነዘቧችሁ የማይችሉት ሁኔታ ላይ ስትሆኑ፣ አንዳንድ የተሳሳተ ውሳኔ ላይ ራሳችሁን ስታገኙትና ያንን ለማስተካከል እንኳን ጊዜ አልሰጥ ሲሏችሁ፣ ለማንም የማትነግሩት አይነት ችግር ሲያጋጥማችሁ፣ ለሕይወታችሁ አዲስ ምእራፍ ፈልጋችሁ ለውጥን ማምጣት ስትጀምሩ፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ምክንያቱን በማታውቁት ሁኔታ የብቸኝነትን ጉዞ እንድትያያዙት ትገደዳላችሁ፡፡
እንደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ ራሳቸሁን ስታገኙት . . .
💠 ሁኔታው ጊዜያዊ ነውና የከረሩ ውሳኔዎች ውስጥ እንዳትገቡ ተረጋጉ፡፡
💠💠 ሰዎች ገለል የማለታቸው ምክንያት ለምን እንደሆነ መነሻ ሃሳባቸውን ተወት አድርጉትና ውሳኔያቸውን አክብሩና ለቀቅ አድርጓቸው፡፡
💠💠💠 ራሳችሁን እንድትመለከቱ እድል የምታገኙበት አስገራሚ ጊዜ ስለሆነ በቂ ጊዜን ከራሳችሁ ጋር አሳልፉ፡፡
💠💠💠💠 ከሰዎች ጋርም ሆነ ከሰዎች ውጪ፣ ከችግር ጋርም ሆነ ከችግር ውጪ መኖር የምትችሉበት አቅማችሁ የሚፈተሸበት ጊዜ መሆኑን አትርሱ፣ ያንንም አዳብሩ፡፡
💠💠💠💠💠 ሁል ጊዜ ፈጣሪ ከእናንተ ጋር እንደሆነና ሁሉን ነገራችሁን እንደሚገነዛባችሁ በማሰብ ወደ እሱ የምትጠጉበት አጋጣሚ በማድረግ ተጠቀሙበት፡፡
#አይዟቸሁ!
#መልካም_ሠንበት
#ውብኛ_ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
The Marriage (2017)
👨🏼🤝👨🏻 #TheMarriage 👨🏼🤝👨🏻
✏️Sub: English
🌏 Country: Kosovo, Albania
📝 Language: #Albanian
🌟 Score: 6.8/10
🎭 Genre: Drama, Romance
🎬 1h 37min
✨ Storyline: Bekim and Anita are getting married, but she is unaware that he is still in love with his best friend Nol.
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
ፀጉሩን ጭብርር አደርጎ በቱታ በክፍት ጫማ ይመጣል፥ ያሻውን ያወራኛል። በሚያወራው ነገር የምይዘው አቋም አያስጨንቀውም ። ሲያወራኝ ፊቴን አያነብም ፣ ነገሬን በቁም ነገረ አይዘውም ።
የድሮ ፍቅረኛውን ኳሊቲ ሲትናገር ስለወንድሙ የምያወራ ነው የሚመስለው ። የሰጠውን ስጦታ አይነት ሊነግረኝ ሁላ ይችላል ። እማላቀውን ሰው በቅናቴ ምክንያት እጠላዋለሁ ።
ጀለስ ነገሬ ሁሉ ግድ አይሰጠውም
እኔ ...
የአለመወደድን ጠረን አውቀዋለሁ ። ያለመጥቀም ስሜት ከየትኛውም መጥፎ ሁኔታ በላይ አልወደውም ። የአልወድህም ምልክት ሲያሳየኝ ፤ ልቤ ላይ የማልወደው ስሜት ተንከላወሰ። ጠፋሁበት...
በሌላ ምክንያት ከሆነ ብዬ ፣ እለታዊ ሙድ ከሆነ ብዬ ተናዶብኝም ይሆናል ብዬ እጅግ ብዙ ቆይቼ ከሁለት ቀን በኋላ አግኘሁትና ስሜቱን ሰለልኩት...
ከአስር ደቂቃ በኃላ እንደተገናኘን ነበር ሁኔታው..አይኑ ላይ ያለው መሰልቸት በጉልህ የተነበበኝ ።
ሁኔታው ገፈተረኝ ...አገፈታተሩ እና አወዳደቄ ሳይዘጋጁ ከድንገተኛ መንጋለል ሁሉ ይበልጣል ። ህመሜ በማዘን አይነት እፊቴ ላይ የሚነበብ ይመስለኛል።
ጠፋሁ !!
ታግሼ ለመወደድ ብጥር እኔነቴን ባሳየው ፣ ፍቅሬ የውነት እንደሆነ በምንም ሁኔታዋ አብሬው ሆኜ ባሳየውጥሩ ነበር...
አለመወደድን መጋፈጥ አልችልም ። #አለመወደድን_ከምጋፈጠው_የምወደውን_ነገር_ሳጣ_የሚሰማኝ_ደባሪ_ስሜት_መቋቋምን_እመርጣለሁ።
ጉልምስናችን የልጅነታችን ባርያም አይደል ?!
አለመወደድን እንድታገስ ልጅነቴ አይፈቅድልኝም.....
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣0⃣0⃣
#በመጀመሪያ_ታከሙ
ካለፈው ስቃዩ ያልዳነ ሰው እድሜ ልኩን ሰዎችን እንዳሰቃየ ይኖራል፡፡ ለዚህ ነው በአንድ የስሜትና የስነ-ልቦና ህመም በሚዳርግ ልምምድ ውስጥ ካለፍን በኋላ ወደሌላ ግንኙት ዘልቀን ከማለፋችን በፊት ከመጀመሪያው ሕመም መዳናችንን እርግጠኞች መሆን ያለበን፡፡
አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ሲጎዱንና ሁለንተናችን ሲቃወስ ያንን ጉዳት ባለመልቀቃችን ሰዎቹን የምንበቀላቸውና የምንጎዳቸው ይመስለናል፡፡ እውነቱ ግን ከዚያ የራቀ ነው፡፡ በሰዎች ከደረሰብን የጉዳት ቀውስ መዳንና መውጣት የሚጠቅመው እኛንው ነው፡፡
የትናንትናውን ቁስሌን በተገቢው መልክ አክሜ ካልዳነ የዛሬውን ግንኙቴን ያዛባዋል፡፡ የዛሬው ግንኙነቴ መዛባት ደግሞ ለነገው ቁስል ይዞ ስለሚቆይ ዑደቱ እንደቀጠለ ይኖራል፡፡
በቅርብ ጓደኛ፣ በፍቅረኛ፣ በስራ አጋር፣ በአለቃ . . . ከተጎዳችሁ በኋላ ሌላ ተመሳሳይ ግንኙነት ውስጥ ዘልቃችሁ ከመግባታችሁ በፊ በመጀመሪያ ቁስላችሁን በሚገባ መታከማችሁን እርግጠኞች ሁኑ፡፡ ስፍራን መቀየርና ጓደኛን መለወጥ ያለው የራሱ የሆነ ጥቅም እንደተጠበቀ ሆኖ ዘላቂ መፍሄ ያለው ግን ከአንድ አቁሳይ ልምምድ በኋላ ሌላ ምንም አይነት የጠለቀ ግንኙነት ውስጥ ከመግባታችን በፊት ራሳችን ላይ መስራት ነው፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#ለጥንቃቄ_ቅድሚያ_እንስጥ
#ይነበብ
የአዲስ አበባ ፖሊስ አንድን ወጣት አግተው 10 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።
አጋችና ታጋች የአንድ ወር ጓደኛሞች እንደነበሩም አሳውቋል።
የእገታ ወንጀል የተፈፀመበት ወጣት ልዑል መብራቱ ይባላል፡፡
ወጣቱ #በማህበራዊ_መገናኛ_አውታር (ማህበራዊ ሚዲያ) አማካኝነት ባንቴ ይድረስን የተባለውን ግለሰብ ይተዋወቃል፡፡
ትውውቃቸው አንድ ወር ከሞላ በኋላ ባንቴ ይድረስ የተባለው ወንጀል ፈፃሚ የወንድሜ ጓደኛ ቤት ላሳይህ በማለት ወጣቱን ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ/ም ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቁሊቲ መንደር 4 አካባቢ ይዞት ከሄደ በኋላ ከግብረ አበሩ ልዑል ጫላ ጋር በመሆን ያግቱታል፡፡
ወንጀል ፈፃሚዎች እጅግ ዘግናኝ ፊልሞችን እና ፎቶግራፎችን ለወላጆቹ በመላክ 10 ሚሊዩን ብር ካልተከፈላቸው ወጣቱን እንደሚገድሉት የማስፈራሪያ መልእክት ይልካሉ፡፡
የእገታ ወንጀል እንደተፈፀመ ሪፖርት የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ጋር ባደረጉት ክትትል ወንጀሉን በተፈፀመ በአራተኛው ቀን ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ወጣቱን ከእገታው ነፃ እንዳወጣው አሳውቋል።
ሁለቱ ግለሰቦች ወንጀሉን ለመፈፀም በ5ሺ ብር ቤት መከራየታቸውንና የታጋቹ ወጣት ወላጅ አባት ውጭ ሀገር ይኖራሉ በሚል መረጃ ወንጀሉን መፈፀማቸውን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።
ፖሊስ ፤ በልዩ ልዩ ምክንያት የምንቀርባቸው ግለሰቦች ማንነታቸውን ጊዜ ወስደን ማረጋገጥ አለብን ብሏል።
በተለይ ሙሉ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች የተከራዮችን ማንነትና ለምን እንደተከራዩ ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስቧል። ይህን ሳያደርጉ በሚፈጠር ችግር የህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስጠንቅቋል።
መረጃው ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘ ነው።
© tikvahethiopia
#ስለምናገኛቸው_ሠዎች_እንጠንቀቅ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
መደበሬን ፣ ማሸነፌን ፣ ሽራፊ ስሜቶቼን.....ሲያሞግሱኝና እና ስተች የሚሰማኝን ጥንጥ ብናኝ ስሜት ሳይቀር ....ደግሞም ስደክም እና ስበረታ የሚሰማኝን ላንተ አይደል የምነግረው? ?
ከንፈሬ ሲደርቅ ፣ ስከሳ ፣ አለመመቸት ሲጣበቀኝ፣ ጫማዬ ሲቆሽሽ ቲሸርቴ ከሱሪዬ ጋ አራምባ እና ቆቦ በሆነ መንገድ አልሄድ ሲል .....ሳያምርብኝ ሲቀር ፣ነገዬ የጨለመ ሲመስለኝ፣ ተስፋ ስቆርጥ በልብህ ውስጥ ያለሁትን እኔን ያሳየኸኝ እኔነቴን ስወደው❤❤❤ .... አሻግሬ የነጋ ነገን እመለከትበታለው😍
ስትኮራብኝ ....ስታምነኝ ...እርዳታ ሲያስፈልግህ በኔ ብቻ መታገዝ ስትፈልግ ፥ የወደድኩትን እንደምቶድልኝ ስታሳየኝ የሚሰማኝን ምቾት.....😘😘😘
ባትወለድ ህይወቴ ላይ የሚኖረው መጉደል አገዛዘፉ ተራራ ያህል ነበር !!
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#መች_ነው_ግን_ማገኘህ?
ቀልድህ ባያስቅም እንኳ አይንህን እያየው ፈገግ ስልልህ..በዝምታህ ውሰጥ እንደ እሳተ ጎመራ ቡልቅ ቡልቅ የሚለው ህመምህን ለማድመጥ ስጣጣር.. ኩራቴ ስሜቴን ስላሸነፈ አልነገርኩክም እንጂ ይሔ ሁሉ ናፍቆኛል...።
እኔን ለማሳቅ የባጥ የቆጡን ስትዘባርቅ..እኔ ደሞ እንደ ጉንዳን የደቀቀ መልሴን ስመልስልህ...ለቦጭህን ዘርግፈ ሌላ ቀልድ ስቀልድልኝ እንደ አዲስ ሌላ አለም ሌላ አፅናፍ እንደምትዘፍቀኝ አልነገርኩክም እንጂ የእውነት ናፍቆኛል ..ኩርፊያህ ሀዘንህ ሳቅህ ሁሉ ነገርህ ናቆኛል..።.
..አዎ ፍቅራችን የጋለ ምጣድ ላይ እንዳረፈ በረዶ ቀስ ቀስ ሲናድ ይታወቀኛል...አንተም ላትመልስ ከአይኔ ራዳር ሸሸህ..
እኔም መመለስህን በተስፋ ምጠብቅ ብኩን ፍጥረት እንድሆን ማን ነው የፈረደብን?።
ለዚ ተከሳሹ ማን ነው??
እኔ ወይስ አንተ....?
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ #1⃣9⃣7⃣
#እውነተኞቹን_ከአስመሳዮቹ_መለየት_ከፈለጋችሁ
ምናልባት በዙሪያችሁ ከሚገኙ ሰዎች መካከል እውነተኞቹንና አስመሳዮቹን ለመለየት ከፈለጋችሁ እናንተ ሁለት ነገር ማድረግ ይጠበቅባችኋል፡፡
❤ እውነተኛ ማንነታችሁን መኖር
አስመሳይ ማንነት አስመሳይ ሰዎችን ይስባል፤ እውተኛ ማንነት እውነተኛ ሰዎችን ይስባል፡፡ ይህ የማይለወጥ ማሕበራዊ ሕግ ነው፡፡ እውነተኛ ሆናችሁ ስትኖሩ፣ እውነትን ስትናገሩ፣ እውነታን ስትጋፈጡ . . . እውነተኞችና እውነት ወዳዶች ብቻ ወደ እናንት ይሳባሉ፣ ሌሎቹ ግን ስማይመቻቸው ይርቃሉ፡፡
❤❤ ትክክለኛ የሕይወት ዓላማችሁን መከተል
ያያችሁትን፣ የሰማችሁትንና ለጊዜው “ያበላል” ብላችሁ የምታስቡትን ነገሮች የምትከታተሉ አይነት ሰዎች ከሆናችሁ፣ ይህ የተዛባ ሂደት የተዛባ መርህና አመለካከት ያላቸውን አይነት ሰዎች ወደ እናንተ ይስባል፡፡
ሲጨመቅ፣ በዙሪያችን የሚመጡትንና የሚቆዩትን ሰዎች የሚወስኑ ሁለት ዋና ዋና ነገሮች ማንነታችን እና ዓላማችን ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ነገሮች መስመር ሲይዙ “የወዳጆቻችን” ነገርም ከዚያው ጋር ይስተካከላል፡፡
የሕይወት ዘይቤያችሁ ወደ እናንተ የሚመጡትንና የሚቆዩትን ሰዎች የመወሰን ጉልበት አለው፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
Beneath the Skin (2015)
👨🏼🤝👨🏻 #BeneaththeSkin 👨🏼🤝👨🏻
🌏 Country: UK, Canada
📝 Language: #English
🌟 Score: 4.3/10
🎭 Genre: Drama, Romance
🎬 1h 27min
✨ Storyline: After his family falls apart Joshua is forced to move to Canada to live with his estranged father. It is there he meets Jay, a local tattoo artist. The two becomes closer despite the negativity that surrounds them.
👇🏽👇🏽👇🏽
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#ከሱ_ጋ_ስሆን_ደስስ_ይለኛል
እርግት ማለቱ ፣ሳወራ የሚያሳየኝ አስተያየት..😍 ጉንጬን እየነከሰኝ የሚስመኝ አሳሳም፣እቤት ውስጥ ስራ እንዲያግዘኝ ስጠይቀው ፥ እጁን ለድብድብ በሚመሰስል እየሰበሰበ "ምን ላግዝ?" ሲለኝ 😘😘
የነገርኩትን ቀልድ "ደግመህ ንገረኝ" እያለ ደግሞ የሚስቅልኝ "መሀሙድ አህመድን ዝፈንልኝ " ሲለኝ በኔ ድምፅ ብዬ ስደነግጥ የሚስቀው ሳቅ 😂😂😂
ብሶቱን እየነገረኝ "አለሁልህ የት አባቱንና!!!" ብዬ አንገቱን ስስመው... ሲረጋጋልኝና..... "ታሾፋለህ ኣ?" ሲለኝ....
ሁለታችንም ደረት ከምንመታ ብዬ ነው ስላት ከብሶቷ ጋ ታግላ እየሰደበቺኝ የምትፈግገው ፈገግታ ።
አርፍጄበት የሚገላምጠኝ መገላመጥ... አንገቱን ግንባሩን ጉንጩን ለመለማመጥ የምስመው አሳሳም፣ የሚስመኝ አሳሳም😘😘😘
ታድዬ - እወደዋለሁ ❤
#መልካም_ጁምአ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣0⃣4⃣#ራስን_የመቀበል_ጉዞ_እንጀምር
#ክፍል ሶስት- #ራስን_ያለመቀበል_መገለጫዎችን_መመርመር
ራስን ያለመቀበል መገለጫዎችን መመርመር ማለት ራሴን ያለመቀበሌን ጠቋሚ የሆኑ ምልክቶችን በመለየት ማወቅ ማለት ነው፡፡ ራሳችንን ያለመቀበላችን ጉዳይ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም በዙሪያችን ላሉ ሰዎች የሚታይ ነው፡፡ እነዚህን ሁኔታዎች መለየት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም #አንዳንድ_ጊዜ_ራስን_ያለመቀበል_ችግር_እንዳለብን_እንኳ_በቅጡ_አናውቀውም፡፡ ምልክቶቹን ስናስተውል ብቻ የችግራችንን ምንጭ በማወቅ መፍትሄን የማግኘት እርምጃ መውሰድ እንጀምራለን፡፡
ራስህን አለመቀበልህን ለመለየት መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች፡-
1. #ንግግርህን_ተመልከተው
አንዳንድ ራሳቸውን ያልተቀበሉ ሰዎች አነጋገራቸው ዝቅተኝነትን ያመለክታል፡፡ ሌሎች ግን ያንን የውስጥ ትግል ለማሸነፍ ሳያስቡት የትእቢትን ቃላት ይለምዳሉ፡፡ በአጭሩ፣ ንግግርህን ብታጤነው ምልክትን ማየትህ አይቀርም፡፡
2. #አለባበስህን_አጢነው
አንዳንድ ሰዎች ማንነታቸውን ለመደበቅ ቀላል ሆኖ የሚያገኙት መንገድ የአለባበስ ሁኔታ ነው፡፡ በአጭሩ ይህንን ጥያቄ ጠይቅ፣ “አለባበሴ ከእኔ ጋር የማይመጣጠን አንድን ነገር ለመደበቅ ወይም ለማጉላት እንደሆነ ያሳያል?”
3. #አጠቃላይ_ሁኔታህን_አስተውለው
አንዳንድ ሰዎች ሁኔታቸው “የእነሱ” አይደለም፡፡ እንቅስቃሴአቸው፣ አረማመዳቸው፣ ሰላምታ አሰጣጣቸው … የእነሱ እንዳልሆነ ያስታውቃል፡፡ እስቲ ሁኔታህን አጢነውና ከአንተነትህ ውቺ የሆነ ነገር ካስተዋልክ ወደ ትክክለኛው ማንነትህ ለመመለስ ሞክር፡፡
ይቀጥላል . . .
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣0⃣3⃣
#ራስን_የመቀበል_ጉዞ_እንጀምር
#ክፍል_ሁለት
#ራስን_ያለመቀበል_ድምጾችን_መለየት
ራስን ያለመቀበል ድምጾችን መለየት ማለት ራሴን እንዳልቀበል ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡትን ድምጾችን የመለየትን ብስለት ማዳበር ማለት ነው፡፡ ማንነታችን ሙሉ እንዳልሆነ የሚያሳስቡን ድምጾች በቶሎ ካልለየናቸው ነገሮች ከተበላሹ በኋላ ነው የምንነቃው፡፡
የሚከተሉትን እራሳችንን እንዳትሆን የሚገፋፉንን ጠንቆች መንጥረህ እናውጣቸው፡-
1 🔇 #የራስ_በራስ_ድምጽ፡፡
ጥናት እንደሚነግረን አንድ ሰው በአማካኝ በቀን ውስጥ 50 ሺህ ጊዜ ከራሱ ጋር እንደሚያወራና ከእነዚህ መካከል 80 በመቶው አሉታዊ ሃሳች እንደሆኑ ይነግረናል፡፡ ስለዚህ ስለራሳችን ከራሳችን ጋር የምንወያየውን ሃሳብ መቃኘት አስፈላጊ ነው፡፡
2 🔇 #የሰዎች_ድምጽ፡፡
ሰዎች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በራሳችን ላይ ያለን አመለካከት እንዲወርድ የሚያደርጉ ነገሮችን ይናገሩናል፣ ሁኔታዎችንም ያሳዩናል፡፡ እነሱን ማስቆም ባንችልም ሃሳባቸው ግን በእኛ ላይ የሚኖረውን ጫና ለመቀነስና ለማስወገድ መስራት እንችላለን፡፡
3 🔇 #የማሕበራዊ_ሚዲያ_ድምጽ፡፡
ማንነታችንን ተገቢ ባልሆነ ሚዛን እንድንመዝን የሚገፋፉ ማሕበራዊ ገጾች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ እነሱ መርጨት የሚፈልጉትን የመርጨት መብታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ እኛ ደግሞ መቀበል የምንፈልገውን ነገር የመምረጥ መብቱም ሆነ አቅሙ አለን፡፡ አንድን ነገር ግን አንርሳ፣ አንድን ነገር ከገባ በኋላ ለማስወጣት ከመታገል መጀመሪያውኑ ራስን መጠበቅ አስፈላጊ ነው፡፡
ዛሬም አልጨረስንም...
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣0⃣2⃣
#ራስን_የመቀበል_ጉዞ_እንጀምር!
#ክፍል_አንድ - #ራስን_መሆን
ራስን መሆን ማለት፣ ማንነትን ተቀብሎ፣ ሳይደባብቁና ሌላውን ሰው ለመሆን ሳይሞክሩ በነጻነት መኖር ማለት ነው፡፡ ራስን የመሆን ጉልበት የሚመነጨው ማንነቴን የሰጠኝ ፈጣሪ እንደሆነ ከማመን ነው
አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን ስለማይቀበሉ ራሳቸውን ሆነው መኖር አይችሉም። ራሱን መቀበል ያስቸገረው ሰው ላይ የሚታየው የመጀመሪያው ምልክት ራስን አለመሆን ነው፤ የማይቀበሉትን ማንነታቸውን ለውጠው ለመታየት ሲሞክሩ ራሳቸውን ያገኙታል። ወጣሪ በሰጠን ማንነት ስንደላደልና ስንቀበለው ቀና ብለን መኖር እንጀምራለን።
ራስህን ለመሆን መውሰድ የምትችላቸው #እርምጃዎች፡-
❇️#መለወጥ_ወይም_ማሻሻል_የምችለውን_መለወጥና_ማሻሻል
በማንነቴ ላይ የማልቀበለውን ነገር ለማሻሻል ጤናማ መንገዶችን መሞከሩ ክፋት አይኖረውም፤ ከተሳካልኝ። ቁም ነገሩ፣ አሻሻልኩትም አላሻሻልኩት ራሴን ወደ መቀበል መምጣቴና ጤናማ የሕብረተሰቡ አካል ሆኜ መኖሬ ነው
❇️#መለወጥ_ወይም_ማሻሻል_የማልችለውን_መቀበል
ዘሬን፣ መልኬን፣ ማንነቴንና የመሳሰሉትን ከፈጣሪ የተቀበልኩትን አሁን የሆንኩትን ማንነት ለመቀየር አስቸጋሪ ወይም የማይቻል እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ምርጫዬ አንድ ነው፣ #ራሴን_ተቀብዬ፣ በተደላደለ አመለካከት ዓላማዬ ላይ በማተኮር በሰላም መኖር
❇️#አዎንታዊነትን_ማዳበር
በራሳችንም ሆነ በማንነታችን ላይ ያለንን አመለካከት ከጨለምተኝነት አውጥተን ወደ አዎንታዊነት የማሸጋገር ስራ ካለማቋረጥ መስራት ይጠበቅብናል። ይህ ነገሬ ልክ አይደለም እያልን ስንጨናነቅ ከመኖር፣ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለት መመሪያዎች እየተከተልን አዎንታዊነትን ማዳበር ተመራጭ ነው።
አልጨረስንም...
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣0⃣2⃣
#ፍቅር_ስራን_ይጠይቃል!
አንድ ሰው እንዲህ ሲል ተናገረ፣ “የዘመኑ አሳዛኝ ሁኔታ፣ አንዳንድ ሰዎች #እየተፋቀሩ_አብረው_ግን_መሆን_አለመቻላቸው፣ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ #አብረው_ሆነው_አለመፋቀራቸው_ነው”፡፡ የብዙ ሰዎችን ወቅታዊ ሁኔታ የሚገልጽ አባባል!
በፍቅር አብራችሁ ከሆናችሁ አይቀር ተፋቀሩ፡፡ ፍቅር ደግሞ በምትሃት የሚመጣና በተአምራት የሚቀጥል ጉዳይ አይደለም፡፡ በፍቅር የተጀመረው ግንኙነት በፍቅር እንዲቀጥል ስራን ይጠይቃል፡፡ እለት እለት በሚሠራ ሰራ መታደስን ይፈልጋል።
ፍቅርን የሚያሳዩ ተግባሮችን መስራት፣ የፍቅር ንግግሮችን መናገር፣ ለአጋር መጠንቀቅ፣ ችግርን መፍታት፣ መወያየት፣ ማቀድ . . . የሚባሉ ስራዎች አሉ፡፡
ምናልባት “እንፋቀራለን ነገር ግን አብረን አይደለመንም” የምትሉ ከሆነ፣ ይህም ሁኔታ ስራን እንደሚጠይቅ አትርሱ፡፡ በሚገባ መተዋወቅ፣ ወደፊት አብሮ የመሆንን እቅድ አብሮ መንደፍ፣ በየጊዜው ወደ አብሮነት ለመምጣት አንድ ተግባራዊ እርምጃን መራመድ . . . ሌሎችም እልፍ ስራዎች አሉ፡፡
እየተፋቀርን
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
The Marriage (2017)
👨🏼🤝👨🏻 #TheMarriage 👨🏼🤝👨🏻
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#Диккат
Иш топиб хар куни минглаб одамлар ишга жойлашаётган канални топдик!
/channel/+D7WFl10oI21kZjcy
Ўзбекистоннинг энг йирик Компаниялари элон берувчи канал шу экан!
Ойликлар 3млн дан 25млн гача!
Билиб олиш учун каналга уланинг:
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/+D7WFl10oI21kZjcy
#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣0⃣0⃣
#ሰዎችን_ግራ_አታጋቡ!
አንድን ሰው ስትቀርቡ የምትፈልጉት ነገር ሌላ ሆኖ አቀራረባችሁን ግን ሌላ አታስመስሉ፡፡ በሌላ አገላለጽ ከአንድ ሰው ጋር ጠጋ ያላችሁበትን ዋነኛ ፍላጎታችሁን ሳትደብቁ ግልጽ አድርጉ፡፡
ፍላጎታችሁ የፍቅር ግንኙነት ከሆነ በግልጽ ተናገሩ፡፡ ፍላጎታችሁ ቀላል ጓደኝነትና ወዳጅነት ከሆነ በግልጽ ተናገሩ፡፡ ፍላጎታችሁ ከእነሱ የምታገኙት ጥቅም ከሆነ በግልጽ ተናገሩ፡፡
ለሰዎች አንድን ገጽታ እያሳየንና አንድን ነገር እየተናገርን በውስጣችን ሌላ ፍላጎት ደብቀን አንያዝ፡፡ #ሰዎችን_የስውር_ፍላጎታችን_መጠቀሚያ_አናድርግ፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
አንዳንዴ useless እንደሆንን ሊሰማን ይችላል፤
🌈አንዳንዴ ሰዎች እንዲረዱን ፈልገን አልተረዱን ይሆናል፤
🌈አንዳንዴ ምክንያቱንም ሳናውቀው በምንወዳቸው ሰዎች ፊት ላይ ጥላቻ ተስሎ አይተን ይሆናል፤
🌈አንዳንዴ ለሰዎች ከሰጠነው አክብሮት በተቃራኒ ንቀት ተቀብለን ይሆናል፤
🌈አንዳንዴ እድሜያችንን ሙሉ ስንመኘው የነበረና ትልቅ የመሠለን ነገር ስናገኘው ትንሽ ሆኖብን ይሆናል፤
🌈አንዳንዴ ለሰዎች መድረስ ፈልገን ሁኔታ፣ ጊዜና አቅም አጥተን መድረስ አልቻልን ይሆናል፤
🌈አንዳንዴ አንደመልአክ የምናያቸውን ሰዎች በህይወት አጥተን ይሆናል፤
🌈አንዳንዴ ለቤተሰቦቻችን ልንፈጥርላቸው እንፈልግ የነበረውን ዓለም ቀርቶ ትንሽ እንኳን ልንደግፋቸው አለመቻላችን አሳዝኖን ይሆናል፤
🌈አንዳንዴ ሁሉም ነገር ትርጉም አጥቶብን ይሆናል፤
🌈አንዳንዴ ሁሉም ቀን አሰልቺ፣ በድብርት የተሞላ እና ተመሳሳይ ሆኖብን ይሆናል፤
🌈አንዳንዴ ከዛሬ የበለጠ ነገ ጨለማ ሆኖ ታይቶንም ሊሆን ይችላል፤
🌈አንዳንዴ ሁሉም ነገር መኖር ራሱ ሳይቀር ከብዶን ይሆናል፤
አንዳንዴ ...
አንዳንዴ...
አንዳንዴ...
✅ግን It's okay to feel bored, sad, useless, and hopeless at times..
live
Lough
Love
ከሁሉም በላይ የተሻለ ጊዜ ከፊት አለ። 🧑🤝🧑
በውስጣችን ያለውን ክፋት በውስጣችን ባለው መልካምነት የምናሸንፍበት የተዋበ ቀን ይሁንልን።
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 1⃣9⃣9⃣
#ዓለም_እኮ_ሰፊ_ነች!
ዓለም እናንተ ስታጠቧት ትጠባለች፣ ሰፊነቷን ስትቀበሉና ስታዩላት ደግሞ በስፋቷ ልክ ታስተናግዳችኋለች፡፡
ቀና በሉ! ከሰፈራችሁ ውጪ ሌላ ሰፈር አለ! ከቡድናችሁ ውጪ ሌላ ቡድን አለ! ከመስሪያ ቤታችሁ ውጪ ሌላ መስሪያ ቤት አለ! በአካባቢች ካሉት ሰዎች ውጪም ሌሎች ሰዎች አሉ! አሁን ካላችሁ የገቢ ምንጭ ውጪ ሌላ የገቢ ምንጭ አለ!
#ከፈጣሪ_የተሰጣችሁን_ሰፊ_ዓለማችሁን_አታጥብቧት፡፡ ምርጫችሁ አንድና አንድ ብቻ እንደሆነ ስታስቡና በዚያ ዙሪያ ብቻ ስትሽከረከሩ ዓለማችሁ እሱ ብቻ እስከሚመስል ድረስ ትጠባላችሁ፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 1⃣9⃣9⃣
#መስመር_ማበጀት_አለመቻል
ከዚህ በፊት በሚወዳቸውና በአፈቀራቸው ሠዎች ከተከሰተበት የመገፋት ቁስል ያልተላቀቀ ሰው ፥ ወደፊት በሚኖረው የፍቅር ግንኙነቶች ውስጥ ለፍቅረኛው ገደብና መስመር ማበጀት ያስቸግረዋል፡፡
እንደማንኛውም ሰው ወደሕይወቱ ለሚመጣ ሰው ሊያስቀምጥ የሚገባውን ተቀባይነት ያለውንና የሌለውን ነገር ከማስመር ይልቅ ሰዎች እንደፈለጉ እንዲቆጣጠሩት ይፈቅዳል፡፡ ለአንዳንድ ተቀባይነት ለሌላቸው ጥያቄዎች እምቢ ካለና ትክክል ላልሆኑ ነገሮች እርማት ከሰጠ ሰዎቹ ጥለውኝ ይሄዳሉ ብሎ ስለሚሰጋ ለሁሉም ነገር እሺ በማለት የቁጥጥር ሰለባ ሊሆን ይችላል፡፡
ከእንደዚ አይነት መልካም መሳይ ጎጂ ጥቃት ከመጋለጥ ተቆጠቡ። የማይሆነውን አይሆንም ፤ ልክ ያልሆነውንም ልክ አይደለም ማለትን እንለማመድ
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 1⃣9⃣8⃣
#ሕይወታችሁ_በከንቱ_እያለፈ_እንደሆነ_ለምታስቡ...
አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ በአማካኝ 10 ሺ ሰዎች ላይ ተጽእኖ ያመጣል ይባላል፡፡ ይህ ተጽእኖ ለክፉውም ሆነ ለደጉ የሚሰራ ሂደት ነው፡፡
በሕይወታችሁ ቢያንስ የአንድ ሰውን ሕይወት ተጨብጭ በሆነ ሁኔታ የሚለውጥ ተግባር ካከናወናችሁና ፥ ግባችሁን ከመታችሁ ሕይወታችሁ በከንቱ እንዳላለፈ ላስታውሳችሁ!!!
አንድን ሰው ስትለውጡ፣ የአሁኑን ወይም የወደፊቱን እጩ የፍቅር አጋር፣ ጓደኞች ፣ ወዳጆችና በዚያ ሰው ተጽእኖ ስር የሚወድቁ ሰዎችን ሁሉ ሕይወት ትነካላችሁ፡፡ ከዚህ ስሌት የተነሳ ነው ቢያንስ ከ10 ሺ ያላነሰ ሰው ላይ መልካም ተጽእኖ የምታመጡት፡፡
ዘንግታችሁት ነው እንጂ፣ #መልካም_ተጽእኖ_የማምጣት_ብቃት_ያላችሁ_ሰዎች_ናችሁ!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
ስራ ቀጣሪዎች "Portfolio ላኩ" ሲሉ ሰምታችሁ ይሆናል። ለመሆኑ Portfolio ምንድን ነው? እንዴጽ ማዘጋጀት ይቻላል?
Portfolio ማለት የአንድ ባለሙያ በተለይም ደሞ ጥበባዊ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ችሎታና ልምድ ለማሳየት የሚጠቅም ገፅ ነው።
በብዛት Portfolio በመጠቀም ስራና ችሎታን በደንብ ማስተዋወቅ የሚችሉ ባለሙያዎች እነዚህ ሊሆኑ ይችላሉ።
1. አርክቴክቶች
2. ግራፊክስ ዲዛይነሮች
3. ፎቶግራፈሮች
4. የማስታወቂያ ባለሙያዎች
5. ዌብሳይት ዲቨሎፐሮች እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ።
Portfolio ለማዘጋጀት እነዚህን ዌብሳይቶች መጠቀም ትችላላችሁ።
1. Behance
2. Wix
3. Weebly
4. WordPress
5. Crevado
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0