#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣4⃣5⃣
#ተለዋጭ_እቅዳችሁ_ምንድን_ነው?
አንዳንድ ሰዎች አንድን ግብ ወይም እቅድ ካወጡ በኋላ ጉዞው ከበድ ሲላቸው ይጨናነቃሉ።እቅዳቸውን መቀየር ሞት መስሎ ይታያቸዋል።ይህ ዝንባሌ የሚመጣው በዋና ራእይና ወደዚያ ለመድረስ በምናወጣቸው እቅዶች መካከል ያለውን ልዩነት ካለመለየት ነው።
የምንከተለው ራእይ ሊለወጥ አይችልም፣ ሕይወታችንን እንደ መልሕቅ ችከሎ የያዘ ዋናው ዓላማች ስለሆነ።እቅድ የምንለው ነገር ግን እዚያ ግብ ላይ ለመድረስ የምንከተላቸው የተለያዩ ተግባራዊ እርምጃዎች ናቸው።ስለሆነም ወደ ራእያችን ስንገሰግስ ሳለን የምንሄድበት ጎዳናና እቅዳችን አላስኬድ ሲለን እቅድንና ስልትን መቀየር ምንም ችግር እንደሌለበት ራሳችንን ማሳመን አለብን።
አንዳንድ ሰዎች ጉዞው ከባድ ሲሆን እድሜአቸውን ሙሉ የተከተሉትን የሕይወት ዋና አላማና ሕልም ትተውት ይሄዳሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ እንደየሁኔታው አላማቸውን ይለዋውጣሉ።ጉዞው ሲከብድ ግን መቀየር ያለበት አላማ ሳይሆን አደራረግ ነው።በሕይወትህ ልትከተል የምትችለው ዋነኛ የአላማ መልህቅ አንድ ብቻ ነው።ሌሎች እዚህና እዚያ ብቅ ብቅ የሚሉ አንዳንድ አዳዲስ እቅዶች ቢኖሩህም ከዋናው አላማህ ጋር አብረው የሚጓዙ መሆናቸውን እርግጠኛ መሆን አለብህ።
ዋናው ቁም ነገር ግን ይህ ነው፡- ትናንትና ደምህ ውስጥ ሲዘዋወር የነበረው ሕልምህ በአንድ ጊዜአዊ የሁኔታዎች አለመመቻቸት ምክንያት ሊጣልና ሊቀበር አይገባውም። ስለሆነም ሁል ጊዜ ወደ ዓላማህ የምትጓዝበት የመጀመሪያ እቅድ ይኑርህ።ያን ካወጣህ በኋላ ግን ድንገት እሱ መንገድ ካልሰራ ሁለተኛ፣ እሱም ካልሰራ ደግሞ ሶስተኛ እቅድ ይኑርህ።
በርቱና ላቃታችሁ ነገር እንደገና ሌላ እቅድ አውጡ ወደፊት!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣4⃣4⃣
#አንድ_እርምጃ_ወደፊት!
ሕይወት እንዳደረጋችሁት ነው፡፡ ስትንቀሳቀሱ ወደፊት ትሄዳላቸሁ፣ ስትቆሙ ወደኋላ ትቀራላችሁ፣ ስትወላውሉ ደግሞ ባላችሁበት ትረግጣላችሁ - ስሌቱ ይኸው ነው!
በዙሪያችሁ የሚገኙትን ሰዎችን ተመልከቷቸው፡፡ አንድ ቀን ከእንቅልፋቸው ሲነቁ አይደለም እዚህ ብዙዎች የሚመኙበት ደረጃ ደርሰው ራሳቸውን ያገኙት፡፡ ተንቀሳቅሰው፣ ሰርተው፣ አጠራቅመው፣ ታግለው . . . ነው፡፡
ነገ ከዛሬው፣ የዛሬ ዓመት ደግሞ ከዘንድሮው የተሻለ ሕይወት ከፈለጋችሁ ያንን የማድረጊያው ብቸኛውና እርግጠኛው መንገድ መንቀሳቀስ ነው፡፡ ይህ እቅስቃሴ ደግሞ የግድ ትልልቅ መሆን የለበትም፡፡ በየቀኑ የሚደረጉ ትንንሽ እርምጃዎች በዓመት ውስጥ አንድ ግዙፍ ነገር እጃችሁ እንዲገባ ያደርጋል፡፡
ይህንን ከላይ የተጠቀሰውን የማበረታቻ ሃሳብ ተግባራዊ ለማድረግ ልቦናችሁ ከተነሳሳ የሚከተሉትን ልምምዶች ለመጀመር ሞክሩ፡፡
1⃣ አሁን ካላችሁበት ደረጃ በተሻለ መልኩ ለማወቅ በምትፈልጉት በአንድ እውቀት ዙሪያ መጽሐፍን የማንበብ ወይም አንድን ስልጠኛ የመውሰድን አንድ እርምጃ ተራመዱ፡፡
2⃣ ቀረብ ብላችሁ ብትተዋወቁትና ብታውቁት ለሕይወታችሁ እድገት የክህሎ ወይም የስብእና መዋጮ ያደርጋል ብላችሁ የምታስቡትን አንድ ሰው የመቅረብንና የመተዋወቅን አንድ እርምጃ ተራመዱ፡፡
3⃣ በእጃችሁ ላይ ያለውን ገንዘብ ወይም አንድ ንብረት በማዋል (ኢንቨስት በማድረግ) የተሻለ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ለመድረሰ ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ አንድ እርምጃ ተራመዱ፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣4⃣2⃣
#ማቆም_የለም!!
ምንም ነገር ከመጀመራችሁ በፊት የምትጀምሩት ነገር በእርግጥም ያመናችሁበትና ከዋናው የሕይወት ዓላማችሁ ጋር የተገናኘ መሆኑን እርግጠኛ ሆኑ፡፡ ያንን ለማድረግ ማሰብ፣ ማቀድ፣ ማማከር . . . ካስፈለጋችሁ ያንን አደርጉ፡፡ ሆኖም አንድ ጊዜ ካመናችሁበት በኋላ ግን መብረር ነው፡፡
“መብረር ካልቻላችሁ ሩጡ፣ መሮጥ ካልቻላችሁ ተራመዱ፣ መራመድ ካልቻላችሁ ተንፏቀቁ፣ ምንም አረጋችሁ ምንም ወደፊት መንቀሳቀሳችሁን አታቁሙ” - Martin Luther King Jr.
በሆነው ባልሆነው እየወላወልን፣ ተስፋ እየቆረጥን፣ እየቆምንና ወደኋላ እየተመለሰን ዓላማ ላይ መድረስ የሚባል ነገር የለም፡፡
አትቁሙ! አትመለሱ! በርቱ!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣4⃣1⃣
#እንቅፋቶቹ_መረማመጃዎች_ናቸው!
አንድ ትንሽ ልጅ እህቱን ወደ አንድ መንገዱ በጣም አስቸጋሪ ወደ ሆነ ኮረብታ ጫፍ ላይ ለማድረስ እየመራት ነው፡፡
“ነይ፣ መንገዱ በዚህ ነው” በማለት እንዳትንሸራተት ድንጋዮች ያሉበትን መንገድ በመምረጥ እየመራት ሲሄድ፣ በመንገዱ ላይ ባሉት ድንጋያማ “እንቅፋቶች” የተቸገረችው ልጅ፣ “ለምን በዚህ መራኸኝ፣ ይህ እኮ መንገድ አይደለም፣ ድንጋያማ ነው!” በማለት ተነጫነጨች፡፡
የልጁም መለስ፡- “እንቅፋት በመሰሉሽ ድንጋዮች ላይ ነው እኮ እየተረማመድሽ መሄድ ያለብሽ”፡፡
የሚገርም የሕይወት ፍልስፍና! በእንቅፋቶቹ ላይ እየተረማመድኩኝ ወደ ዓላማዬ እገሰግሳለሁ!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
"ያ የአካላችን ክፍል አእምሮ ይባላል።"
=======================
እንደሰው ልጅ የሚዝናና የለም። እስካሁን Meme አይቶ የሳቀ ድመት የለም። "እስቲ አሪፍ ፊልም አይቼ ዘና ብዬ ልምጣ" የሚል ሌላ ፍጥረት ተሰምቶ አይታወቅም።
"አጭር ግጥም፤
ለጆሮ የሚጥም።" ብሎ ቋንቋን መልእክት ከማስተላለፍ በዘለለ ውበትን ለመፍጠር የሚጠቀም የለም። "እስቴ ሆዴ ስር አረንጓዴ ቲሸርት ለብሶ ከቆመው ሰውዬ ጋር ፎቶ አንሱኝና ፌስቡክ ላይ ልለጥፍ።" የሚል ሊመር የለም።😉 ....ዝርዝሩ ላይ እናንተ ቀጥሉበት። ብቻ እንደ ሰው የሚዝናና የለም!
በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ሰው የሚጨነቅ የለም። "ተመርቄ ስራ ባላገኝስ?" የሚል አንበሳ መኖሩን እኔ'ንጃ! "የአየር ንብረት ለውጥ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል!" ብሎ የሚብሰለሰል አሞራ ያለ አይመስለኝም።"ልጄን የት ትምህርት ቤት ላስገባ?" ብሎ እንቅልፍ የሚያጣ ግመል መኖሩ ያጠራጥራል።
በአጠቃላይ ደስታችንን፣ ጭንቀታችንን፣ ፍላጎታችንን፣ ስጋታችንን የሚቆጣጠረው ያ የአካላችን ክፍል አእምሮ ይባላል።
ሳይቆጣጠረን በፊት እኛ እንቆጣጠረው
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣3⃣8⃣
#ሰበካው_ረገብ_ይበል!
ለፍቅረኛሞች . . .
አጋሮቻችሁ ያላቸውን የውስጥ ሃሳብ፣ ደካማ ጎን፣ የስሜት ቀውስ፣ ያታገላቸውን ነገርና ለሌላ ሰው የማይነገር የውስጥ ስሜት ሲነግሯችሁ እንደዚያ ሊሰማቸው እንደማይገባ፣ ማሰብ የሚገባቸው ምን እንደሆነ፣ ማካበድ እንደሌለባቸውና የመሳሰሉት እነሱን ለማድመጥ እረፍት እስከምታጡ ድረስ “የመስበክ” ዝንባሌ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡
አብዛኛውን ጊዜ አጋሮቻችሁ መደመጥንና የአይዞህ መልእክትን ብቻ ሊፈልጉ ይቻላሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ካደመጣችሁ በኋላ “በምን ላግዝ?” የሚለው ጥያቄ ወቅታዊ ሊሆን ይችላል፡፡ እነዚህንና መሰል የጥሩ አጋር ዝንባሌዎችና ልምምዶች ተግባራዊ እንዳታደር የሚጋፋችሁ እንቅፋት ቢኖር የሃሳብ ሰጪነት፣ የአቅላይነትና የቸልተኝነት ዝንባሌ ነው፡፡
ሰበካው ረገብ ይበል! አድማጭነቱና አብሮነቱ ጨመር ይደረግ!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣3⃣6⃣
#ለራሳችሁ_ዋጋ_ስጡ!
አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች እኛን በምን መልኩ እንደሚያስተናግዱን (Treat እንደሚያደርጉን) የምናስተምራቸውና የምንፈቅድላቸው እኛው ራሳችን ነን፡፡
ራሳችንን ከናቅን ሰዎች እኛን ይንቁናል፣ ራሳችንን ስናከብር ደግሞ ያከብሩናል፡፡ ራሳችንን ርካሽ አድርገን ካሰብንና ልክ የትም መሄጃ እንደሌለው አይነት ሰው ሆነን ራሳችንን ካቀረብን ሰዎች እንደ ተራና የትም መሄጃ እንደሌለው ሰው ያስተናግዱናል፣ ለራሳችን ዋጋ ከሰጠን ደግሞ ዋጋ ይሰጡናል፡፡
ሰዎች በምን መልኩ እየቀረቧችሁና እያስተናገዷችሁ እንዳሉ ተመልከቱትና ምናልባት በዚያ መልክ እንዲቀርቧችሁና እንዲያስተናግዷችሁ የፈቀዳችሁት እናንተው የመሆናችሁን ጉዳይም በዚያው ለመቃኘት ሞክሩ፡፡
እናንተ ሳትፈቅዱላቸው ሰዎች ሊንቋችሁና በወረደ መልኩ ሊያስተናግዷችሁ አይችሉም፡፡ ከእናንተ ፈቃድ ውጪ በዚያ መልክ እንዳይቀርቧችሁ ማድረግ ባትችሉም ሁኔታው ልክ በማስያዝ ድርጊታቸው የመጀመሪያና የመጨረሻ እንዲሆን የማድረግ መብቱም ሆነ አቅሙ አላችም፡፡
ፈጣሪ ከሰጣችሁ “ሰውነት” በታች አትኑሩ!
መልካም እሁድ
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣3⃣4⃣
#ጊዜ_የለኝም!
ሰዎች በእኔ ላይ ስላላቸው አመለካከት ጊዜ የለኝም፡፡ ያንን ሃሳብ ያሰቡት እነሱ ናቸው፣ ሃሳቡን ወደየት እንደሚወስዱት መጨነቅና መወሰን ያለባቸውም እነሱ ናቸው፡፡
እኔ በቂ የሆነና ጊዜን በተገቢው መንገድ ካልተጠቀምኩበት ላጠናቅቀው የማልችለው የራሴ ዓላማና ስራ ስላለኝ ሰዎች በእኔ ላይ ስላላቸው ሃሳብ በማሰብ ለመጨነቅ ጊዜውም የለኝ፡፡
በአንድ ውላችሁ በምትገቡበት ቀን ውስጥ ሰዎች በእናንተ ላይ ስላላቸው አስተሳሰብ መጨነቅ ያቆማችሁ ጊዜ የቀኑን ሃምሳ በመቶ ድል አግኝታችሁ ነው የምትጀምሩት፡፡
ሰዎችን ለግል አመለካከታቸው ተወት አድርጓቸውና #ዓላማችሁ_ላይ_አተኩሩ!
መሕካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣3⃣2⃣
#ቀንደኛው_የደስታ_ሌባ! ራስን ከሌላው ሰው ጋር ማነጻጸር ቀንደኛው የደስታና የሰላም ሌባ ነው፡፡ የዚህ ራስን ከሌላው ሰው ጋር የማነጻጸር አራጋቢ ደግሞ ማሕበራ ሚዲያ ነው፡፡
ማሕበራዊ ሚዲያ ያደረገብን ነገር ቢኖር ይህ ነው፡፡ ሰዎች ያላቸውን ጉድለት በመሸሸግ እኛ እንድናየው የሚፈልጉትን የተቀባባ ሁኔታ ብቻ ነጥለው ያቀርቡልናል፡፡ እነሱ በሚዲያ ነጥለው ያቀረቡትን “የተሻለ” ነገራቸውን ካየን በኋላ መለስ ብለን ስለራሳችን ከምናውቀው “ዝቅተኛው” ማንነት ጋር ማነጻጸር እንጀምራለን፡፡ በውጤቱም የእኛ ሕይወት ምን ያህል ወደኋላ እንደቀረ ማሰብ እንጀምራለን፡፡ ይህ አጉልና የተዛባ እሳቤ፣ የምንፈልገው ነገር ምን እንሆነ እከማናውቀው ድረስ እንድንቅበጠበጥና ደስታ-ቢስ እንድንሆን ያደርናል፡፡
ፍቅረኛ ብናገኝ አንረጋጋ፣ ገንዘብ ብናገኝ አንረካ፣ ብንለብስ ያማረብን አይመስለን . . . የሌለውንና የማይደረስበትን እንደፈለግን እንኖራለን፡፡
ምናልባት ስሜት ቀስቃሽ (Sensational) ከሆኑት ማሕበራዊ ገጾች አጉል ተጽእኖ ረገብ ብንልና የራሳችንን የሕይወት ግብ፣ አቅጣጫና ከፍታ ከራሳችን ራእይ አንጻር ብናወጣው ቅጥ ያጣው የውስጥ ስሜታችን ይረጋጋ ይሆናል፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
🧐 Қайси доира ичидаги сонни кўрмаяпсиз?
🔬Шунга қараб сизга қандай витамин етишмаётганлигини билиб олинг!
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣3⃣0⃣
#ድል_ውስጣችሁ_ነው
አሸናፊነትንና ተሸናፊነት ከውጪ ከማግኘታችሁ በፊት የምታገኙት በውስጣችሁ ነው፡፡ በምሳሌ እንዳብራራ ይፈቀድልኝ፡፡
ለምሳሌ፣ አንድ ሰው ጥፋት ካጠፋችሁ ወይም ከጎዳችሁ በኋላ ሰውየውን ካልተበቀላችሁት ወይም ይቅርታ ካላስጠየቃችሁ በስተቀር እንደተሸነፋችሁ የሚሰማችሁ ከሆነ የአሸናፊነት ትርጉማችሁ ውጫዊ ነው ማለት ነው፡፡ ሰዎች ለጠፉት ጥፋት በሃላፊነት ሊጠየቁ እንደሚገባ ሳንክደው፣ ሰው ምንም አደረጋችሁ ምንም ሁኔታው ውስጣችሁን ሳይሰብረው መንገዳችሁን መቀጠል የለመዳችሁ ጊዜ ድል ውስጣዊ የመሆኑን ልምምድ ታረጋግጣላችሁ፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ሁኔታዎች አልሳካ ሲሉ የመሸነፍ፣ ሲሳኩ ደግሞ የማሸነፍ ስሜት የሚፈራረቁባችሁ ከሆነ የድልና የአሸናፊነት ጉዳይ ውጫዊ እንደሆነባችሁ አመልካች ነው፡፡ ለስኬት የመስራታችሁ ልምምድ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሁኔታዎች ቢሳኩም፣ ባይሳኩም በራሳችሁ ላይ ያላችሁ አመለካከት ሳይነካ ቀና ብላችሁ ወደፊት መገስገስን ካላቆማችሁ ድልን ውስጣዊ የማድረግን ስኬታማነት ተጎናጽፋችኋል ማለት ነው፡፡
የአሸናፊነት ስሜት እንዲሰማችሁ የውጪ ሁኔታችሁ እስከሚለወጥ አትጠብቁ! ድልን ውስጣዊ አድርጉት፡፡ አለዚያ እንደ ውጫዊ ሁኔታችሁ የሚለዋወጥ ስሜትና ጉዞ ውስጥ ራሳችሁን ታገኙታላችሁ፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣2⃣8⃣
#ሙሉ_ጤንነት_ከፈለጋችሁ . . .
#1_ለመንፈሳዊ_ጤንነት - ፈጣሪን ፍሩ! በየእለቱ ጸሎት አድርጉ!
#2_ለአካላዊ_ጤንነት - ወደሰውነታችሁ ስለምታስገቡት ነገር ተጠንቀቁ! የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አድርጉ!
#3_ለማሕበራዊ_ጤንነት - ራስ-ተኮር አትሁኑ! ትክክለኛ የተግባቦት ክህሎትን አዳብሩ!
#4_ለስነ_ልቦና_ጤንነት - #ራሳችሁን_ተቀበሉ! #ራሳችሁን_ከሌላው_ሰው_ጋር_አታነጻጽሩ!
#5_ለስሜት_ጤንነት - የምታሰላስሉትን ሃሳብ በቁጥጥር ስር አውሉ! ትክክለኛውን ስሜት በትክክለኛው ጊዜ፣ ቦታና መጠን መግለጽን ተማሩ!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ-ማስታወሻ #2⃣2⃣6⃣
ብቁ ናችሁ!
ከሕይወት ትልልቅ የፍርሃት ምንጮች አንዱ “ብቁ ያለመሆን” ፍርሃት ነው፡፡ በሰዎች ለመወደድ፣ ለመፈቀር፣ ተቀባይነት ለማግኘት፣ ለማወቅ፣ ለመሰልጠን፣ እድገት ለማግኘት . . .ብቁ እንዳልሆንን የማሰብ ፍርሃት!
እውነት እውነቱን እንነጋገር፡፡ አንድ ሰው እናንተን ለመቀበልና ለመውደድ የማይችል ወይም የማይፈልግ ከሆነ፣ ይህ ማለት እናንተ የዚያ ሰው አይደላችሁም ማለት ነው - አለቀ! ይህ ማለት ግን እናንተ ተቀባይነት የማግኘትና የመወደድ ብቃቱና ማንነቱ የላችሁም ማለት አይደለም፡፡
እናንተን የመውደድም ሆነ የመቀበል ብቃቱና ፍላጎቱ ያለው ብዙ ሰው በዙሪያችሁ እንዳለ አስታውሱ፡፡ እነሱን ለማየትና ለመገናኘት ግን “ካልተቀበለኝና ከልወደደኝ” ብላችሁ ችክ ካላችሁት ሰው ላይ አይናችሁን ማንሳት፣ ስሜታችሁንም ማላቀቅ የግድ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ለጊዜው ከባድ ነው፣ ነገር ግን በሚልየን የሚቆጠሩ ሰዎች ችለውታልና እናንተም ትችላላችሁ!
አንድ ነገር አልሆን ሲላችሁ ሁል ጊዜ እናንተ ለዚያ ነገር ብቁ ስላልሆናችሁ እንደሆነ የማሰብን የእሳቤ ንድፍ መቀየር አለባችሁ፡፡ በዚያ ምትክ ያ ሰውም ሆነ ሁኔታ ለእናንተ የማይመጥን ስለሆነ እንደቀረላችሁ ማሰብም አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜም እንዳለ አትዘንጉ።
በአጭሩ፣ ለመወደድ ብቁ ናችሁ! ለማደግ ብቁ ናችሁ! ለማወቅ ብቁ ናችሁ! በዚህ ዓለም ፈጣሪ ለሰው ልጆች ደስታና ስኬት ለፈጠረው መልካም ነገር ሁሉ ብቁ ናችሁ! ሕይወት ትክክለኛውን ሰውና ስፍራ ገልጣ እስከምታቀርብላችሁ ድረስ ግን ራሳችሁን በመቀበል የድርሻችሁን መወጣት የግድ ነው።
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
በሂወቴ አንድም ቀን
- ፊቱ ጭፍግግ ኮስተር የሚል ፣ ያልገባውን አልገባኝም ፣ትክክል ካልመሰልኩት ትክክል አይደለህም እያለ የሚሞግት እና የሚገስፀኝ ሙሉ ስሜን ካለይሉኝታ ሳያቆላምጥ የሚጠራኝ ሰው ፥ ኑሮዬን አክብዶት አያቅም ።
ሳስቀይመው እንደተቀየመ የሚያሳየኝ ፤ ቅር ያለውን የሚያንፀባርቅ። አወዳዱ እኔ ጋ ከሚያገኘው ጥቅም ጋ ብቻ የማያጣብቅ ሰው ልብ ውስጥ ፍስስ የሚል በቀላሉ የማይቆም ሃዘን አፍልቆብኝ የሚያቅበትን ግዜ አላስታውስም ።
#ይልቁንስ
ቅልስልስ የሚሉ ። የሚያገኙት ጥቅም ያለ ከመሰላቸው የሚንሿከኩ ፣ እንደ ውሃ በተቀመጡበት ቦታ ቅርፅ የሚቀያየሩ ።
ከፊት እና ከጀርባ አቋም የሚቀያየሩ ። ፊት ለፊት ባልወደዱት ባልገባቸው ጉዳይ የማይወያዩ ልምጥምጥ ግለሰቦች እሾሃቸው የቱ ጋ እንዳለ ስለማይታይ የምድርን ቆይታ ከሆነው በላይ ብርቱ ሰልፍ ያደርጉታል ።
የሆነው ሆኖ #ቅልስልስ_ልምጥምጥ_አስመሳይ_ሰዎች_ዘግይተው_ሲጠሉ #ኮስተር_ክችች_ግትር_የሚሉት_እውነተኛ_ሰዎች_ዘግይተው_ይወደዳሉ ።
የሆነው ሆኖ
እኔ እና ልቤ ግን በዙርያችን የተኮለኮሉ ውብ ነብሶች ላይ እንመሰጣለን
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
የበደለህን ይቅር በለው ጤና ይሰጥሃል።
የተበላሸብህ ነገር ደግመህ ሞክረው- ጥንካሬን ስለምታገኝ።
ደስተኛ ለመሆን ቻል መከፋት ሲረዝም በብዙ ስለሚያሳጣ።
ፈጣሪህን አመስግን- የተሻለ ስለምታገኝ።
ካንተ የባሰበትን ተመልከት መጽጽናናት ስለሚሆንልህ።
ካንተ የተሻለውን አስተውል- ተስፋ ስለሚጎበኝህ።
ስለገጠመኝህ ሰዎችን አማክር- መፍትሄ ስለሚሰጡህ።
ጸልይ፣ ለብቻህ ተደብቀህ አልቅስ- ለእፎይታህ።
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣4⃣5⃣
#የአጋራችሁ_የስሜት_ቁልፍ
#ለፍቅረኛሞች. . .
አጋሮቻችሁ ከእናንተ ጋር ባላቸውን ንግግር ወይም ግንኙነት ወቅት ስሜታዊ በሚሆኑበት ጊዜ ምንም ነገር ከማድረጋችሁ በፊት በቅድሚያ “#አጋሬን_ለዚህ_ስሜት_የዳረገው_የእኔ #ንግግር፣ #ሁኔታ ወይም #ተግባር_ምንድን_ነው?” በማለት የመጠየቅን ልምምድ ብታዳብሩ ከብዙ አለመግባባት የምትድኑበትን ጥበብና ብስለት እንዳዳበራችሁ አትዘንጉ፡፡
ንግግራችንና ተግባራችን በአጋራችን ላይ ስሜትን ያነሳሳል፡፡ መልካም ንግግርና ተግባር ጥሩ ስሜትን ሲፈጥር፣ መጥፎ ንግግርና ተግባር ደግሞ ጥሩ ያልሆነን ስሜት ያነሳሳል፡፡ በሌላ አገላለጽ ለንግግራችንና ለተግባራችን መጠንቀቅ ማለት ለአጋራችንን ስሜት መጠንቀቅ ማለት ነው፡፡
አብዛኛውን ጊዜ የአጋራችሁ የስሜት ቁልፍ ያለው እናንተ ጋር እንደሆነ አስታውሱ፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣4⃣3⃣
#ለማረፍ_ሳይሆን_ስላረፋችሁ!
አንዳንድ ሰዎች የፍቅር ግንኙነት ቢጀምሩ አሁን ያለባቸው ግራ መጋባት የሚለቃቸውና እረፍትን የሚያገኙ ይመስላቸዋል፡፡ ስለሆነም፣ በውስጣቸው እረፍትን ያጡት ትክክለኛውን ፍቅረኛ ስላላገኙ ስለሚመስላቸው በዚህ በተረበሸ ማንነት ፍቅረኛን ፍለጋ ያላቸውን አሰሳ ይቀጥላሉ፡፡
የዚህ እሳቤና አካሄድ #ትልቁ_ስህተት፣ ያላረፈ አእምሮ ያለው ሰው ትክክለኛውን ምርጫ የማድረግ አቅሙ የመወሰዱ ጉዳይ ላይ ነው፡፡
ልክ እጅግ የተጠማ ሰው ያገኘውን “ፈሳሽ” ሁሉ እንደ ጥም ማርኪያ እንደሚጠቀምበት . . . በጣም የተራበም ሰው ያገኘው “ምግብ” ሁሉ እንደረሃብ ማስታገሻ እንደሚያውለው ሁሉ ግንኙነት ስለጠማውና ስለራበው የተወዛገበውም ሰው ያገኘው እድል ሁሉ ከዚያ እረፍተ-ቢስ ስሜቱ የሚላቅቀው ይመስለዋ፡፡
እረፍት ፍለጋ ወደ ግንኙነት ከመግባት ይልቅ በመጀመሪያ #አርፎ_መግባት ✅ በብዙ እጥፍ የተሻለ ነውና በመጀመሪያ ባላችሁበት ሁኔታ አረፍ በሉ! ያንን ስታደርጉ ብቻ ለትክክለኛው ምርጫና ውሳኔ የተመቻቸ ምልከታ ይኖራችኋል፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
Бўлиб тўлашга 2024-йилда курилган уйлар!
🔥 Энг замонавий, арзон ва кенг уйлар!
🔥 2024-йилда қурилаётган уйлар ва уларнинг нархлари
🔥 12 ойдан 120 ойгача муддатли тўлов
👉 Нархларни кўриш
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣4⃣0⃣
#አንዱን_ምረጡ!
እስቲ በአሁን ሰዓት የተወዛገባችሁበትን ወይም ለውሳኔ የተቸገራችሁበትን ማንኛውንም ነገርና ሁኔታ አስቡት፡፡ ያላችሁን ምርጫ ባጠበባችሁት ቁጥር ስኬታማነታችሁ የጎላ ከመሆኑም ባሻገር በድንዛዜ ወራትና አመታትን ከማባከን ትድናላችሁ፡፡ ሁኔታውን ጠበብ ለማድረግ ደግሞ ታዋቂው ሄንሪ ፎርድ የጠቆመንን መንገድ መከተል እንችላለን፡፡
በስራም ሆነ በመሳሰሉት የወቅቱ ሁኔታችሁ አንጻር በብርታት ወደፊት ለመንቀሳቀስ ከፈለጋችሁ የወቅቱን ሁኔታችሁን መውደዳችሁን እርግጠኞች ሁኑ፡፡
ካልወደዳችሁት ግን ዝም ብሎ ከመነጫነጭና ስለሁኔታው ሲያወሩ ከመክረም በተቻላችሁ መጠን ሁኔታውን ለመቀየር ሞክሩ፡፡ ሁኔታውን የመቀየሩ ጉዳይ የማይታሰብ ከሆነ ደግሞ አንደኛችሁን ሌላ አቅጣጫና መስመር በመያዝ መንገዳችሁን ብትቀጥሉ ተመራጭ ነው፡፡
እነዚህን እጅግ ቀላል የሚመስሉና ለመተግበር ግን አስቸጋሪ የሆኑ ሶስት ደረጃዎች የማይለማመዱ ሰዎች ትኩረት የሌላቸው፣ ሁል ጊዜ የሚነጫነጩ፣ ሰውን መውቀስ የሚወዱ፣ ስለግላቸው ሁኔታ ሰው ላይ ማሳበብ የሚያዘውትሩና በየጊዜው ባሉበት የሚረግጡ ሰዎች ናቸው፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣3⃣9⃣
#ለመፈቀር_ሳይሆን_ስለተፈቀራችሁ..
አጋራችሁ #እንዲያፈቅራችሁ ምንም ነገር ማድረግ #እንደማይገባችሁ ላስታውሳችሁ፡፡ አጋራችሁ #ስላፈረቀራችሁ_ግን_ብዙ_ማድረግ_የሚገባችሁ_ነገር_አለ፡፡ ምንም ነገር ማድረግ ያለባችሁ ለመፈቀር ሳይሆን ስለተፈቀራችሁ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህ የሆነበት ዋነኛ መነሻ ግንኙነታችሁ የተጀመረው በፍቅር መሰረት ላይ ስለሆነ ነው፡፡ ስለተፋቀርን አብረን እንሁን ተባባላችሁ እንጂ ለመፋቀር አብረን እንሁን ብላችሁ አልጀመራችሁም፡፡
አጋራችሁ እንዲያፈቅራችሁ የምታደርጓቸው ነገሮች የፍቅር ግንኙነታችሁን #ሁኔታዊ ያደርገዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ግንኙነታችሁ በጎዶሎ (ወይም በሌለ) ፍቅር ጀምሮ እናንተ በምታደርጉት ነገር ወደሙላት እንደሚመጣ አይነት መልእክት አለው፡፡ ሆኖም ግን አጋራችሁ ለእናንተ ያለውን ፍጹም የሆነ ፍቅር ሊያበላሹ የሚችሉ ሁኔታዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ እትዘንጉ፡፡
ለመፈቀር አንድን ነገር ማድረግና ራስን ለመለወጥ መሞከር አሉታዊ ኃይል (Negative Energy) ነው፡፡ አጋራችሁ ስላፈቀራችሁና በዚያ ፍቅር ላይ በመልካም ለውጥ ለመገንባት መጣጣር አዎንታዊ ኃይል (Positive Energy) ነው፡፡ ይህንን አዎንታዊ ኃይል መጠቀም አረፍና ዘና ብላችሁ የተደላደለ ግንኙነት እንዲኖራችሁ ያደርጋችኋል፡፡ አሉታዊው ኃይል ግን ዘወትር የዝቅተኝነትና የመጦዝ ስሜት ስለሚሰጣችሁ የተጠንጠለጠለ ግንኑነት እንዲኖራችሁ ያደርጋል፡፡
#ለመፈቀር_ከመሯሯጥ_መለስ_በሉና_ለተሰጣችሁ_ፍቅር_ምላሽ_የሚሆንን_መልካም_ለውጥን_ለማምጣት_ሞክሩ፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣3⃣7⃣
#እስከመቼ !!! ???
በጓደኝነት፣ በስራ፣ በንግድ፣ በአለቃ-ሰራተኛ፣ በስራ ባልደረባነት፣ በጉርብትናም ሆነ በሌላ ማሕበራ መስክ ውስጥ ባላችሁ ግንኙነት፣ #ጊዜው_ሳይዘገይና ሁኔታው #ወደማንነት_ቀውስ ከማዝቀጡ በፊት መንቃት እንዳለባችሁ የሚያመለክቱ ጠቋሚዎች . . .
🔔 የራሱን ፍላጎት፣ ሃሳብና አቋም ብቻ እንዲሟላ እያደረገ የእናንተን ግን ለማሟላት ፈቃደኛ ያልሆነ ግንኙት፡፡
🔔 የስሜት፣ የአካል ወይም የወሲብ ጥቃት የሚያደርስባችሁ ግንኙነት፡፡
🔔 ሰዎቹን ስታስቡ ወይም ካገኛችኋቸው በኋላ ኃዘን፣ ድብርት፣ ንዴት፣ ቁጭትና የመሳሰሉት ስሜቶች እንዲያጠቃችሁ የሚያደርግ ግንኙነት፡፡
🔔 ሁል ጊዜ እናንተ ሰጪዎች እነሱ ተቀባዮችች እናንተ ይቅርታ ጠያቂዎች እነሱ ይቅር ባዮች፣ እናንተ ተለማማጮች እነሱ ተለማመጡኝ ባዮች፣ እናንተ ፈላጊዎች አንሱ ተፈላጊዎች የሆነበት ግንኙነት፡፡
🔔ፈጽሞ መተማመን የሌለበትና በጥርጣሬና በጭቅጭቅ የተሞላ ግንኙነት፡፡
🔔 እናንተን እስከመጉዳት አልፎ የሚመጣ ልማድ፣ ሱስና አጉል ባህሪይ ካለበት ሰው ጋር ያላችሁ ግንኙነት፡፡
ይታሰብበት!!!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣3⃣5⃣
#መገፋትን_ለጥቅም_ማዋል!
በጓደኝነት፣ በቤተሰብ፣ በፍቅር ግንኑነትና በመሳሰሉት ማሕበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ የመገፋትን፣ የመገለልንና ያለመፈለግን ልምምድ በምትቀምስበት ጊዜ የሁኔታውን መልካም ጎን ለማየትና ወደፊት ለመዝለቅ የሚከተሉትን ሃሳቦች እንደመነሻ መጠቀም ትችላለህ፡፡
• አንዳንድ ጊዜ በሰዎች መገፋትህ ከእነዚያ ከሚገፉህ አላስፈላጊ ሰዎችና ሁኔታዎች የምትለይበትና የምትጠቀምበት ብቸኛ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ፡፡
• አንዳንድ ጊዜ አንዱ ሰው ስለገፋህ ሌላ የተሻለ ሰው፣ አንዱ ተቋም ስላገለለህ ሌላ የተሻለ ተቋም . . . የምታገኝበት ብቸኛ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ማስታወስ፡፡
• አንዳንድ ጊዜ በመገፋት ውስጥ በተደጋጋሚ ስታልፍ ምናልባት ካለአግባብ የምትገፋበት አጉል ባህሪይ ሊኖርህ ስሚችል ራስህን እንድትጠይቅና ያንን አጉል ባህሪይ ለመለወጥ የምትችልበትን መንገድ መጀመር፡፡
አዎን! የመገፋትን ልምምድ ወደመልካም መለወጥ ይቻላል!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣3⃣3⃣
#ብልህ_ሁኑ!
አንድን ነገር ከመወሰናችሁና እርምጃ ከመውሰዳችሁ በፊት ትክክለኛውን ሰው ማማከራችሁን አትዘንጉ፡፡
ማንኛውንም ወሬና መረጃ ከማመናችሁና ስሜታዊ ከመሆናችሁ በፊት ትክክለኛውን መረጃ ማግኘታችሁን አስታውሱ፡፡
ማንኛውንም ሃሳብ በግልም ሆነ በማሕበራዊ መገናኛ መንገዶች ወደሌላው ሰው ከማስተላለፋች በፊት መልእክታችሁ በሰዎች ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ተጽእኖ በሚገባ ማጤናችሁን አትርሱ፡፡
እነዚህን ቀላል የሆኑ መመሪያዎች ተግባራዊ ማድረግ በፍቅር ግንኙነታችሁ፣ በጉርብትናችሁ፣ በመስሪያ ቤታችሁም ሆነ በወቅቱ ዓለም-አቀፍና ሃገር-አቀፍ እውነታ አንጻር እጅጉን የተረጋጋችሁና ብልህ ሰዎች እንድትሆኑ ከማገዙም በሻገር ከእውነት ጋር እንድትቆሙ ያደርጋችኋል፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣3⃣2⃣
#ጎበዝ_የመሆኛው_መንገድ
በሕይወታችን ጎበዝ መሆን ከፈለግን ሰለሁሉም ነገር ሙሉ ሃላፊነት መውሰድ አለብን፡፡ ለስህተቱ፣ ለውድቀቱም ሆነ ላልተሳካው ነገር የሚወቀስ ሰው ከመፈለግ ይልቅ ሙሉ ሃላፊነቱን የሚወስድ ሰው ከዚያ ሁኔታ የመውጣቱም ሃላፊነት እሱ ጋር እንዳለ ያስባል፡፡ ስለሆነም፣ ሁኔታውን ለመለወጥ የቻለውን ያህል ስለሚጣጣር በሂደቱ ውስጥ ጎበዝ ይሆናል፡፡
በተቃራው በሆነው ባልሆነው የሚነጫነጭና ሰዎችን የሚወቅስ ሰው ራሱን አቅመቢስና የሰዎች ሰለባ አድርጎ ስለሚያስብ ከሌሎች ሰዎች እርዳታ ውጪ ከሁኔታው መውጣት እንደማይችል ያስባል፡፡ ስለሆነም፣ አይሞክርም፣ አይታገልም፣ አይጣጣርም፣ ዝም ብሎ አንድ ሰው ከሁኔታው እስከሚያወጣው ቁጭ ብሎ ይጠብቃል፡፡ እንደዚህ እየተባለ ነው ሰነፍ የሚኮነው፡፡
አንድ ነገር ላስታውሳችሁ፣ ሰዎች በእናንተ ላይ ባደረጉባችሁ ነገር እንኳን ሳይቀር እናንተው ሃላፊነቱን ውሰዱ፡፡ እነዚህ ሰዎች ያንን ነገር እንዳያደርጉባችሁ የማድረግ አቅሙ ባይኖችሁም እንኳ በሁኔታው ተሰብሮ ከመቅረት ይልቅ ትክክለኛውን ምላሽ በመስጠት ቀና ብሎ ለብሩህ የወደፊት ሕይወት የመስራትን ሃላፊነት መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
ጎብዙ!!!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣3⃣1⃣
#30_የነጻነት_ቀናት
ከአንድ ለእናንተ ከማይመጥን ተገቢ ካልሆነ ሰው ወይም ተገቢ ካልሆነ ጤና-ቢስ ሁኔታና ልምምድ ሙሉ ለሙሉ ነጻ የመውጫው ዋነኛ መንገድ ከዚያ ሰው ወይም ከዚያ ሁኔታ ውጪ መኖር እንደምትችሉ ራሳችሁን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማሳመን ነው፡፡
ከማንኛውም አጉል ሰውም ሆነ ሁኔታ ለመላቀቅ እየፈለግን ያለመቻል ሁኔታ መነሻው ከዚያ ሰው ወይም ሁኔታ ውጪ መኖር እንደማንችል ያለን የውስጥ አመለካከት ነው፡፡
አንድን ነገር ልሞግታችሁ፡- መርዛማ ከሆነው ግንኙነታችሁ፣ ጤና-ቢስ ከሆነው ልምምዳችሁን፣ አላስፈላጊ ከሆኑት ቦታዎች ለሚቀጥሉት 30 ቀናት ፈጽማችሁ ለመራቅ ሞክሩና ውጤቱን ተመልከቱት፡፡ ለ30 ቀናት ማድረግ ከቻላችሁ እስከወዲያኛው እንደምትችሉ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣2⃣9⃣
#የመነቃቂያ_ጎዶሎነት
ዘመኑ የመነቃቂያ ንግግሮች፣ ጽሁፎች፣ ዝግጅቶች እና መሰል ልምምዶች የተበራከቱበት ዘመን ነው።ይህ ምንም ጥርጥር የሌለበት እውነታ ነው።በዚያው ልክ ደግሞ “አንድን ነገር በከፍተኛ መነሳሳት እጀምርና ከጥቂት እርምጃ በኋላ መቀጠል ግን ያቅተኛል” የሚሉ ሰዎችም ቁጥር እየበዛ መጥቷል።
በተነቃቃንና በተነሳሳን ቁጥር የተሳካ ጉዞ ውስጥ የምንገባ መስሎን ከአንዱ መነቃቂያ ፕሮግራም ወደሌላኛው አነሳሽ ዝግጅት ስንዳክር ራሳችንን ልናገኘው እንችላለን፡፡
ይህ ከላይ የተጠቀሰው ልምምድ ችግር ባይኖረውም የጉዞው ግማሽ መንገድ ላይ ብቻ እንደሚያደርሰን ግን ማስታወስ አስፈላጊ ነው።በመነቃቃት (Motivation) የተጀመረው ጉዟችን በመመሪያ (Instruction) ካልቀጠለ ስኬታማነቱ አጠራጣሪ ነው፡፡
መነቃቃት ያነሳሳል፣ ያስጀምራት፣ ጉጉትን ይፈጥራል...
መመሪያ ግን የተጀመረውን ነገር እንዴት እንደምንቀጥለውና ወደ ስኬታማ ፍጻሜ እንደምናደርሰው መንገዱን ያመላክተናል፡፡
#መነቃቃት አብዛኛው ስራው ስሜት ላይ ሲሆን፣ #መመሪያ ግን አብዛኛው ተግባሩ ወደፊት የመቀጠልን ስሌትና ጥበብ ማመላከት ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱ ልምምዶች አብረው ካልዳበሩ ብዙም አያስኬዳችሁም።
እውነታው ሲጨመቅ፡- አንድን ጉዞ ጀምራችሁ በስኬታማነት ማጠናቀቅ ከፈለጋችሁ ሁለት ዋና ዋና ልምምዶች ያስፈልጓችኋል፡- 1) መነቃቃት (Motivation)፣ 2) መመሪያ (Instruction)፡፡
አስቡበት!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣2⃣7⃣
#ጎዶሎው_ነገሬ. . .
መልኬ ላይ፣ ቁመናዬ ላይ፣ ማንነቴ ላይ፣ ዘሬ ላይ፣ ቋንቋዬ ላይ . . . የሆነ የጎደለ ነገር (Missing Piece) እንዳለ ሲሰማኝ ሰነባብቷል፡፡ ብቻ ምን አለፋችሁ ከማንነቴ ላይ ተቆርጦ የወጣ የሆነ ነገር እንዳለ እስከሚሰማኝ ድረስ ጎዶሎነትና ባዶነት ይሰማኝ ነበር፡፡ ከዚያም ያንን የጎደለ ነገር አግኝቼና አምጥቼ ማንነቴ ላይ ብለጥፈው ሙሉ የምሆን ስለመሰለኝ ያልሄድኩበት ቦታና ያላደረኩት ነገር የለኝም፡፡
በዚህ ጥረቴ ብዙ ነገሮችንም ሞክሬአለሁ፡፡ የሚቀባውንም ተቀብቼ፣ የሚለበሰውንም ለብሼ፣ የሚቀየረውንም የራሴን ሁኔታ ለመቀያዬር ሞክሬ፣ ያልሆንኩትን ሆኜና የሆንኩትን ትቼ፣ በዙሪያዬ ያሉትንም እስከመምሰል ራሴን ለውጬ . . . ሞከርኩት፡፡ አሁንም ግን ያ ጎዶሎው ነገር አልሞላም ነበር፡፡
አሁን አሁን ግን አንድ እውነት እየገባኝ ስለመጣ መረጋጋት ጀምሬአለሁ፡፡ ለካስ የጎደለኝ ነገር መነሻው ውጫዊ ሳይሆን ውስጣዊ ነው፡፡ ምንም አይነት ውጫዊ ነገሬን በማሟላቴ ደስተኛ ለመሆን ከመሞከሬ በፊት በመጀመሪያ ራሴን ከነማንነቴ (ብርቱውንም ደካማውንም) መቀበልና መረጋጋት እንዳለብኝ ገብቶኛል፡፡
የጎደለው ነገሬ “ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ራስን መቀበል” የሚባለው ዘመን የማይሽረው እውነታ ነው፡፡
ለናንተም ይህን ተመኘሁኝ
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣2⃣5⃣
#ጤናማ_ሕመም!
ሕመምን የሚመኝና የሚከታተለው ሰው ባይኖርም፣ ሕመም የጤናማ ሕይወት ምልክት የሚሆንበት ጊዜም እንዳለ እናስታውስ፡፡ ለማደግ ከፈለግን ሕመም የግድ ነው፡፡
🌈❤️ ጡንቻችን እንዲጎለብትና ኃይላችን እንዲጨምር፣ ከስፖርት የሚመጣውን የጡንቻ ህመም መታገስ የግድ ነው፡፡
🌈❤️ ከህመም ለመዳንና ጤንነታችን እንዲመለስ፣ የመርፌውን ህመምና የመድሃኒቱን መራራነት መቻል የግድ ነው፡፡
🌈❤️ ነግዶ ለማትረፍ፣ ከኪሳራ የሚመጣን ሕመም መታገስ የግድ ነው፡፡
🌈❤️ #ፍቅርን_ለማጣጣም_የመገፋትን_ሕመም_መታገስ_የግድ_ነው፡፡
🌈❤️ ማሕበራዊ ግንኙነታችን ሰላም እንዲሆን፣ ጤና-ቢስ አመለካከቶችን የመሞገትን ሕመም መጋፈጥ የግድ ነው፡፡
💠💠💠💠. . . አያለ የሕመምና የእድገት ግንኙነት ታሪኩ ይቀጥላል . . . 💠💠💠💠
No Pain, No Gain!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣2⃣4⃣
#የከባድ_ቀላል!
ማንኛውም ጥሩ ውጤት የሚያመጣ ጉዞ ከባድ መሆኑ ምንም ጥርጥር የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም፣ አንድን ከባድ ስራ ለመስራት ወይም ረጅም ጉዞን ለመጓዝ ሰትጀምሩ ለዚያ ተግባር ወይም ጉዞ ያነሳሳችሁ ዓላማ ከጉዞው አስቸጋሪነት ከብዶና ልቆ ካልተገኘ በጉዞው መሃል መድከማችሁ አይቀርም፡፡
አንድን ከባድ የሆነን ነገር በብርታት ጀምሮ የመጨረስ ዋነኛ #ምስጢር_ያለው ነገሩን ለማድረግ ያነሳሳችሁ ዓላማ ከስራው ክብደት የመብለጡ ጉዳይ ነው፡፡
መማር ከባድ ነው፣ ሆኖም ከተማራችሁ በኋላ የሚታያችሁ የለውጥ ዓላማ ከዚያ ልቆ ሲገኝ ግን መማር የከባድ ቀላል ይሆናል፡፡
በየቀኑ እየተነሱ ስራ መሄድ ከባድ ነው፣ ሆኖም ስራን በመስራታችሁ ምክንያት ልትደርሱ የምታስቡበት ዓላማ ልቆ ሲገኝ ግን ስራ የከባድ ቀላል ይሆናል፡፡
የፍቅርን ግንኙነትንና የመሳሰሉትን ጥልቅ ግንኙነቶች መጀመር ከባድ ነው፣ በዚያ ግንኙነት ውስጥ ያላችሁ ዓላማ ልቆ ከተገኘ ግን የግንኙነት ውጣ ውረድ የከባድ ቀላል ይሆናል፡፡
ይህንን መርህ በሁሉም የሕይወት ዘርፍ ውስጥ ተግባራዊ አድርጉትና ለእናንተ የከበዳችሁ ነገር ለምን ለሌሎች ሰዎች እንደቀለላቸው ማየት ትጀምራላችሁ፡፡ ከዚያም ጉዟችሁ እንዴት እንደሚቀልል ትደርሱበታላችሁ፡፡
ከባዱ ነገር የሚቀልለው የዓላማችሁ ክብደት ከስራው ክብደት ልቆ ሲገኝ መሆኑን አትርሱ!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
🫵🏾#ስሜትህን_ቀይር!
እንበልና የሆነ ሰው አበሳጨህ፣ ዝቅ አድርጎሃል! ጉዳት ተሰምቶሃል እና? በመጀመሪያ ስሜቱን አትካደው ነገር ግን ለምን እንደዛ ሊሰማህ እንደቻለ ራስህን ጠይቅ... ምናልባት ያ ሰው እንደዛ እንዲሰማህ አልፈለገም... ምናልባት ያ የራስህ የአረዳድ ችግር ይሆናል... ምናልባት ያለብህ የበታችነት ስሜት... ምናልባትም ለዛ ሰው ያለህ ድብቅ ጥላቻ... ወይም በትክክል ያበሳጨህ ሰው ሆን ብሎም ሊሆን ይችላል።
የፈለገ ይሁን የሚረብሽ ስሜት ለምን ውስጥህ ቀረ? ይሄን ጥያቄ ምትመልሰው አንተ ሁነህ ሳለ እኔም የምጠቁምህ ነገር ይኖራል።
እዚህ ጋር- ህይወት ሁሌም ደስታ፣ መፈለግ፣ ማግኘት፣ እኩል መሆን፣ ስኬት እንዳልሆነች ተገንዘብ። ብስጭት ወይም የስሜት መረበሽ ሲያጋጥምህ ዝም ያለ ቦታ ሂድ፤ ከራስህ ጋር በፍቅር ተነጋገር። የመጥፎ ገጠመኞችን ጥሩ ጎን ለማየት ራስህን በአዎንታዊነት እንዲመራ አስገድድ...
👇🏽👇🏽