halal_tube_official | Unsorted

Telegram-канал halal_tube_official - Ayuti Islamic Post 🕌📿

1193

🌜 <<ጌታችን ሆይ! አንተ በርሱ(ለመምጣቱ) ጥርጥር የሌለበት በሆነ ቀን ሰውን ሁሉ ሰብሳቢ ነህ። ምንጊዜም አላህ ቀጠሮውን አያፈርስምና።>>🌛 [ ሱረቱል-ኢምራን=9] አላምችን የምናውቀውን ማካፈል ነው ። ሀሳብ እና ለአስተያየት ካሎት በ👉 @Halaltube_bot Leave ከማለቶ በፊት ስህተቴን ያሳውቁኝ🙏🙏🙏

Subscribe to a channel

Ayuti Islamic Post 🕌📿

ይህ ቻናል በእጅ የተሰሩ የቤት ውስጥ ዲኮሮች የስልክ ከቨሮች ለ ኪችን ለሳሎን ለመኝታ የሚሆኑ ምርጥ በእጅ የተሰሩ እቃዎችን በጣም በተመጣጣኝ ዋጋ በትእዛዝ ይሰራል
/channel/hafsa_decore

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ ሀያ ሁለት 2⃣2⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን


አከራዮቹም ለብዙ ወራት ባለመክፈልዋ አባረዋት ጎዳና ወጥታለች።
ጀመአችንም እውቀት ያለው አስተዳደር በማጣቱ ምክንያት ፈረሰ እኔም 11ኛ ክፍል በተዋወኳቸው ሁለት ሀያት ሀያት ከሚባሉ እና ዚነት ከምትባል ልጅ ጋር ጋደኝነት መስርቻለው።

ሶላት የምንሰግደውም ከትምህርት ቤታችን ፊት ለፊት ካለው ኮንዶሚኒየም ቤቶች መካከል አንዱ በሆነው በማዘር ቤት ነው. ማዘር የእውነት እናት ናቸው ውሀ ሲጠማን እና ሲርበን ፊታችንን አይተው ይረዳሉ። ልንሰግድ ቤታቸው ስንሄድ እንክብካቤያቸው አይለየንም። ጉዳይ ገጥሟቸው ሌላ ቦታ መሄድ ቢኖርባቸው እንኳን በራቸውን አይዘጉትም ልጆቼ ይመጣሉ አስተናግዱአቸው ብለው ለጎረቤት መልክት ያስቀምጣሉ። አብዛኛው የጊቢው ተማሪም የሚሰግደው ማዘር ጋር እየሄደ ነው።እነ ሀዩ ልክ እንደ ዘቦ የምወዳቸው ልዩ ጋደኞቼ ናቸው በምሳሳት ጊዜ ይመልሱኛል በየአንዳንዱ እንቅስቃሴዬም ይደግፉኛል።ጀመአችን በኛ ምክንያት ፈረሰ።

እኛ እውቀት ቢኖረን ባንሰለች ግልምጫቸውን እና ስድባቸውን መቋቋም ብንችል ምናልባትም ባልፈረሰ ነበር። ስልጣን ትልቅ አደራ ነው። ሰው ስልጣን ለመያዝ ይፍጃል ይገዳደላል ይተራረዳል። ሰው ስልጣን ለመያዝ አፈር ድሜ ይበላል ነገር ግን ስልጣን ትልቅ አደራ ነው ስልጣን ትልቅ ሸክም ነው። ስልጣንህን በአግባቡ ካልተጠቀምክ ትጠፋለህ አልያም ሌሎችን ታጠፍለህ። ያለ እውቀታችን ያለ ቦታችን የማይገባንን ስልጣን ተረክበን ከ 14 አመት በላይ የቆየውን ጀመአ አፈረስን።እኛ ያፈረስነው አንዲት ትንሽዬ የተማሪዎች ጀመአ ነው ነገር ግን ሌሎች ያለ ቦታቸው ስልጣን እየያዙ ሀገር እያፈረሱ ነው። ለስልጣኑ ብቁ ካልሆንክ ስልጣን አትያዝ ምክንያቱም ትጠየቅበታለህ!!!

11 ክፍል ልንጨርስ አካባቢ ሰአዳ ልጅ አቅፋ አንገትዋ ላይ መስቀል አድርጋ አየኋት። ያየሁት ህልም እንዲሆን ተመኘሁ ቀርቤ ላናግራት ስሞክር ዞር በይልኝ እያለች ሸሸችኝ።በጣም ተናደድኩ ጅልባብ ለብሳ ያየኋት ልጅ መስቀል አርጋ ሳያት በሸቅኩ።


በሌላ ቀን ቤትዋ ሄድኩ።ያረጁት አያትዋ ይንደፋደፋሉ።
.....አሰላሙ አለይኩም ማዘር ብዬ ገባሁ።
........ወአለይኩም ሰላም እንኳን ሳይሉኝ የጠፋ ልጃቸው የተገኘ በሚመስል ሁኔታ በደስታ ሰከሩ።አለሽ ልጄ ምነው ጠፍሽ? ወይ ዘይባ!! ሰአዳ እኮ ስላንቺ አውርታ አጠግብም ምነው ተቆራረጣቹሳ? አሉኝ በሀዘኔታ።
.....እኔም የትምህርቱ ጉዳይ እኮነው ማዘር አሁን የት ሄዳለች ??ብዬ ወደሄድኩበት አላማ አመራሁ።
....ማዘርም አሁንማ እኔጋር ምን ትሰራለች ባልዋ ጋር ናታ አሉኝ በቁጭት።
.....አገባች እንዴ? ብዬ ስጠይቃቸው
......አንቺም አታውቂም ልጄ?ጉድ አረገችኝ እኮ ጉድ ሰራችኝ።አሳድጌ አሳድጌ ረግጣኝ ሄደች። ከፍራ አገባች እኮ።እንደሌላው ሰው በወጉ እንኳን ብታገባ ጥሩ ነበር ነገር ግን ሳትነግረኝ ወንድጋ ኮበለለች አሉኝ። በጣም አሳዘኑኝ።
.....ኮበለለች ማለት ለምን አልነገረቾትም? ብዬ ጥያቄዬን ቀጠልኩ።ማወቁንስ አውቄያለው ከረፈደ ሆነ እንጂ። በጅልባብ ደልላኝ ራስዋን ደብቃ 6 ወር ከሆናት በኋላ ነው ማርገዟን ያወከት አሉኝ። ለካ ጅልባብ ለብሳ የነበረው እርግዝናዋን ለመደበቅ ነበር።የሰው አስተሳሰብ ይገርማል።

እኔ እኮ ጅልባል ያለበስኩት ለልብሱ ካለኝ ክብር የተነሳ ልብሱን ለብሼ እብድ እብድ ስል ያዩኝ ሰዎች እስልምናን በኔ እንዳይገምቱት እምነቴን በኔ እንዳይመስሉት ካለኝ ፍራቻ አንፃር ነው።እስዋ ያለምንም ማፈር ለእርግዝናዋ መሸፈኛ ስትል አንስታ ለብሳዋለች ሱብሀን አላህ።
......ማዘር ቀጠሉ ከዛም ልደግስልሽ ብላትም አልፈልግም ብላ ልብስዋን ይዛ ቤቱ ድረስ ሄደችለት አሁን ልጅ ወልደው እየኖሩ ነው እየመጣች ትዘይረኛለች።ውድዋ ልጄ ተጎሳቁላለች እኮ። ልጁም ያሰቃያታል መሰለኝ ብቻ አላውቅም አሉ በንዴት። ትንሽ ካቀረቀሩ በኋላም።ፍቺው እኔ አሳድገዋለው ብላትም አሻፈረኝ አለች ከልጅነትዋም ጀምሮ ደረቅ ግትር ናት።ግን ስላንቺ ሳታወራ አልፍ አታውቅም እስዋን ብሰማት ኖሮ ጓደኝነቴን ባጠናክር ኖሮ እዚህ ባልደረስኩ ነበር ትላለች አሉ ማዘር።


ብስጭታቸው እየጠነከረ ሲመጣ ንግግሬን አቁሜ እየመጣሁ እዘይራቹሀለሁ በሉ ቻው ወሰላሙ አለይኩም ብያቸው ወጣሁ።እስከ አስፓልቱ ጫፍ እስክደርስ ድረስ አትጥፊ እራስሽን ጠብቂ እንደስዋ እንዳትሆኚ እያሉ እየሸኙ አስጠነቀቁኝ።


አመቱ አለቀ 12ተኛ ክፍል ገባን።ትምህርት በጀመርንበት 15 ቀን ሰአዳን የትምህርት ቤታችን በር ጋር ነጠላ ለብሳ ቆማ እኔኑ ስትጠብቀኝ አየኋት።

#የመጨረሻዉ_ክፍል_

ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል

@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ 2⃣0⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን

ብዙ ወላጆችም ልጆቻቸውን ከዛ ትምህርት ቤት አስወጥተው ወደ ሌላ ትምህርት ቤት አዘዋውረዋል...


የመርየም እና ሰአዳ ጉዳይ አይምሮዬን አላሳርፍ ሲለው ዘቦን ለምን ከነሱጋር ተመሳስለን ቀስ በቀስ አንመልሳቸውም?? ስል ጠየኳት።
.....ዘቦም በፍፁም አላህ ከሀዲዎችን አትምሰሏቸው ብሏል እኮ አለች፡፡ እኔ ግን ሀሳቤን አልቀየርኩም ሰአዲን እና መርየምን የምትቅሙበት ቤት ማየት እፈልጋለሁ አልኳቸው ያለምንም ማቅማማት እሺ ብለው ወሰዱኝ።

ቤቱ በተማሪ ተሞልቷል ግን ከመርየም እና ከሰአዳ ውጪ ምንም ሙስሊም ተማሪ አላየሁም። ሄሄሄ.....ጨቅጫቃዋ መጣችችችች እያሉ ጮሁ።ይሄ ስም የተሰጠኝ እየዞርኩ አሰላሙ አለይኩም እያልኩ ሰላት እንዲሰግዱ በመጨቃጨቄ ነው።ሙስሊም ተማሪ ባለማየቴ ተደሰትኩ። ወደ ክፍሉ ከገባሁ 30 ደቂቃ ያክል አስቆጠርኩ እኔ ግን አንድ አመት ያክል የቆየሁ ነበር የመሰለኝ በጣም ይጨንቃል ሽታው ያቅለሸልሻል።ሁሉም እየመጣ እንቺ ንከሺ እያለ ጫት ይሰጠኛል።ተቀብዬ እግሬ ስር አስቀምጠዋለው። አንዳንዱ ሺሻ ይስባል።አንዳንዱ ደሞ ሀሺሽ ይስባል። ተማሪው አንድ አንድ እያለ ይመጣል። ክፍሉ ከገባሁ 1 ሰአት አካባቢ ሆነኝ።


አንዲት ጅልባቢስት መጣች።እጅዋ ላይ ጓንት አጥልቃለች እግርዋም እስከላይ ካልሲ (ስቶኪንግ) ስላደረገች አይታይም።አለባበስዋ ትክክለኛ ሙስሊምን ይገልፃል። ምን ልትሰራ መጥታ ነው? እንደኔ ለማየት ነው ብዬ እራሴን አሳመንኩ።ወደውስጥ ዘለቀች ሀይ ጋይስ...! ብላ ሰላምታዋን ሰጠቻቸው።አይኔ ከእሷ ጋር ይንከራተታል ስትቀመጥ ዝቅ ይላል ስትቆም ወደላይ ያፈጣል። ቅድምያ ቦርሳዋን አስቀመጠችው።ቀጥላም ጅልባብዋን አወለቀች ግራ ተጋባሁ።አሁንም ቀጥላ ሂጃብዋን አውልቃ ቁጭ አለች። ለካ ሙስሊም ተማሪ የሌለ የመሰለኝ ሁሉም ሂጃቡን አውልቆ ስለሚቅም ነው። እንባዬ መጣ ስሜቴን መቆጣጠር አቃተኝ።እራሴን አመመኝ።የሺሻው እና የሀሺሹ ሽታ ሆዴን አገለባበጠው።ተዝለፍልፌ ወደቅኩ እራሴን ሳትኩ።

ወንዶቹም ይሄንን ተጠቅመው ሊጫወቱብኝ ሲሉ መርየም ጓደኛዬን አሳልፌ አልሰጥም ብላ ታደገችኝ። እዛ ቦታ የሚታየው ነገር ይዘገንናል።ሁሉም ወንድ እና ሴት ጥንድ እና ጥንድ ሆነው ነው የሚቀመጡት።ሌላው የገረመኝ ወንዶቹ በአንድ እጃቸው የሺሻ ገመድ ይዘው በአንድ እጃቸው ደሞ እሴቱቹ አካል ላይ ነዉ.....። ሴቶቹም ዩኒፎርማችን ሸሚዝ እና ሹራብ ስለሆነ ሹራቡን አውልቀው ሸሚዙን ጡታቸው አካባቢ ከፍተው ያቀብሏቸዋል። ስሜት መቆጣጠር ሲያቅታቸው ለዚህ ጉዳይ መፈፀምያ ተብሎ ወደተዘጋጀው ክፍል ያመራሉ።

አንዱም መልከመልካም ወጣት ነይ እንመቻች አዲስ ትመስሊያለሽ ሲለኝ --------በእድሜ ዘመኔ ያጠራቀምኩትን ስድብ ሁላ አወረድኩበት።መርየምም አዲስ ስለሆበች ነው ሌላ ቀን ስትለምደው ብላ ጠቀሰችው።እዛች መባለጊያ ክፍል አንዱ ተረኛ ፈፅሞ ሲወጣ ሌላኛው ይቀጥላል።ስሜቱን መቆጣጠር ያልቻለም ተራውን ሳይጠብቅ ተደርቦ ይገባል። በጣም የገረመኝ ያሻቸውን ፈፅመው ስሜታቸውን ካበረዱ በኋላ ሴቶቹም ወንዶቹም ሌላ ወንድ ጋር ወይም ሌላ ሴት ጋር ሄደው የሚቀመጡት ነገር ነው በሄዱበት ቦታም ከሌላ ሰው ጋር ልክ እንደዛው ስሜት ቀስቅልሽ አስነዋሪ ነገር ካደረጉ በኋላ ስሜታቸው ሲመጣ በድጋሚ ተያይዘው ወደዛች ክፍል ይገባሉ።በቀን ውስጥ አንዲት ሴት ከተለያዩ ወንዶች ጋር ስትወጣ አይቻለው። ታዳ እነዚህ ተማሪዎች ለHIV ኤድስ ተጋላጭ አይደሉ እንዴ???


የማየዉ ነገር ዘገነነኝ ከዚህ በላይ እዛ መቆየት አልፈለኩም። ሙስሊሙንም ክርስትያኑንም የሚመለከት ንግግር ተናገርኩ።ከተቀመጥኩበት ተነስቼ እኔ መፅሀፍ ቅዱስንም ቁርአንንም አንብቤያለው የትኛውም ሀይማኖት ይሄን ተግባር አይደግፍም ፈጣሪያቹን ፍሩ ከዚህ ዘግናኝ ሱስ እራሳቹን አርቁ ይሄ እኮ በቁም መሞት ነው። ለነጋቹ አስቡ......................ብዙ ነገር ተናገርኩ ግን አንድም የሰማኝ የለም።

ቀልድ ያወራሁ ይመስል ክትክት ብለው ሳቁ። በስተመጨረሻም መርየምንን እና ሰአዳን ቻው ብዬ ወጣሁ።ልብሴ ይሸታል መንገደኛው ሁሉ ያጨስኩ ይመስለዋል ብዬ ፈራሁ።አላህዬ ወደዚህ ቦታ በመምጣቴ ምህረትህን ለግሰኝ እያልኩ ተማፀንኩት።


በማግስቱም ለዘቦ እያንዳንዱን ነገር ነገርኳት።መጀመርያም አትሂጂ ብዬሽ ነበር ጥፋቱ የአንቺ ነዉ ብላ ወቀሰችኝ።

ከመሄዴ በላይ ያበሳጨኝ የጅልባቢስይዋ ጉዳይ ነው። ከኛ በፊት ከነበሩት አሚሮች መካከል አንድዋ እንደነበረች ሳውቅ ደግሞ ይበልጥ ተበሳጨሁ። ሰው እንዴት ለስሜቱ ይገዛል? እንዴት በስሜት ይነዳል? ራስን መቆጣጠር እንዴት ያቅታል?

የእየሩስ አብሮ አደጌ ወንድም ዳግም ትዳር መሰረተ።ከመሰረተም በኋላ ቤቱ እንድትለቅለት አላስቀምጥ ሲላት ቤቱን ለቃለት ከጎረቤቶቿ ጋር መኖር ጀመረች። ጎረቤቶችዋም ይሄን የማድረግ መብት የለውም አንቺም ሀቅ አለሽ ብለው በፍርድ ቤት ተከራክረው ቤቱን እንድትካፈል አድርገውላታል።

በሌላኛው ቀን ደሞ ሌላ አስደንጋጭ ዜና ተሰማ


Part 2⃣1⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል




Join👇👇
@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ #አስራ_ስምንት 1⃣8⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን


ተማሪዎቹ ከአቅማችን በላይ ሁነዋል። ፈቱዲን ያለው ንግግር ትዝ አለኝ። ጀመአው ፈርሷል ማለት ይቻላል ብሎ ነበር አምና።አሁን ግን የምር ፈርሷል ማለት ይቻላል። ሰአዳ እና መርየም ብዙ ጊዜ አንዋር እና ብሩክ ከሚባሉ ልጆች ጋር አብረው ሲንቀሳቀሱ እመለከታለው። እኔና ዘቦ ሰአዳን እና መርየምን ለማስተካከል በጣም እየጣርን ነው። ግን ሊሳካልን አልቻለም። እንዳውም እየሸሹን መተዋል። ዛሬ ፓርቲ አለ ብለው እቅድ ሲያወጡ መስማት የተለመደ ነው።

ሰአዳ ግልምጫዋ አያስቀርብም መርየም ግን ገር ናት ፈገግታዋ በራሱ ይስባል። አሰላሙ አለይኩም ስንላት ወአለይኩም ሰላም ሳትለን አታልፍም። ከዚህ ሱስ እንድትወጣ በምንጠይቃት ጊዜም በኔ አልተጀመረም እኮ ደሞም እንዴትም ብዬ መውጣት አልችልም ሞክሬ ያቃጠኝ ነገር ነው ትለናለች ፡፡ ሰይጣኗ የተነሳ ቀን ደሞ ምናገባቹ አቦ ፍቱኝ ቀኔን አታበላሹ ትለናለች።

እንደተለመደው የአሚሮች ሹራ ላይ ስለ ተማሪዎቹ መበላሸት አወራን እናም ቀጣይ የዳእዋ ፕሮግራም በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲሆን እና የንግግር ችሎታ ያለው ኡስታዝ እድዲጠራ ወሰንን። የኡስታዝ ምርጫ ላይም ትንሽ ከተከራከርን እና ከተመካከርን በኋላ ኡስታዝ ሙሀመድ ፈረጅ(አይ ዱንያ!) በሚለው ትምህርቱ አፍሪካ ቲቪ ላይ የምናውቀው ኡስታዝ እንዲጠራ ወሰንን እና ተለያየን ።ቀኑ ደረሰ ተማሪዎችም እንዳይቀሩ ብዙ እንቅስቃሴ ከልመና ጋር አደረግን። አልሀምዱሊላህ ፕሮግራሙ ላይ ሰአዳን እና መርየምንም ጨምሮ በርካታ ተማሪዎች ተገኝተዋል።


ኡስታዝ ሙሀመድ ፈረጅ ንግግሩ ድንቅ ነው ቀልብ ይስባል ሲናገር ቁጣ እና እልህ በተሞላበት ስለሆነ እንድናዳምጠው ያስገድዳል። ስለ ተማሪዎች አለባበስ እና ሁኔታንም ጨምሮ ስለ ሰላት አለመስገድ ብዙ ነገር አስተማረ። ግማሹ ተክዟል ግማሹም ያለቅሳል ሳናውቀው ሰአቱ ሄደ 10 ደቂቃ የቆየን ሳይመስለን በንግግሩ እንደተመሰጥን ፕሮግራሙ አለቀ።ተማሪዎቹ ሄዱ እኛ የተበላበትን ሰሀን ማጠብ እና ቦታውን ማፀዳዳት ጀመርን። ኡስታዝ ሙሀመድ ፈረጅም በርቱ በዚሁ ቀጥሎ ለትውልድ አሻራ ጣሉ እኔም በፈለጋችሁ ጊዜ እገኝላችሆለሁ ብሎን ሄደ። ከዛን ቀን የዳእዋ ፕሮግራም በኋላ ብዙ ተማሪዎች እንደ አዲስ መስገጃ ቤታችን መጉረፍ ጀመሩ። ትግስትም ስራዬ ብላ የጀመአችን ፕሮግራም ከኛ እኩል ትከታተላለች።ሰአዳ እና መርየም ግን የባሰ ስራቹ ላይ በርቱ የተባሉ ይመስል ብሶባቸዋል።


የጀመአው ፕሮግራም ላይም መገኘት አቆሙ።መርየም ከአንዋር ጋር ሰአዳ ደሞ ከብሩክ ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀምረዋል።ሰአዳ የምትኖረው ከአያትዋ ጋር ስለሆነ አያትዋን አታላ ለፓርቲ እና ለመጠጥ መውጣት ለስዋ ቀላል ነው። ዘይባ ጋር ላድር ነው ብላ በእኔ አሳባ ወጥታ ከ ብሩክ ጋር ታድራለች። መርየም የምትኖረው ብቻዋን ስለሆነ ቁጥጥር የለባትም። ቤተሰቦችዋ ያሉት ገጠር ሲሆን ያሳደገቻት አክስትዋ ናት።ሆኖም ዘጠነኛ ክፍል መጨረሻ አካባቢ በዚህ ባህሪዋ ከ አክስትዋ ጋር ስለተጣላች ከቤት ተባራ ሌላ ቤት ለብቻዋ ተከራይታ ነው የምትኖረው። ለዛም ነው 10 ኛ ክፍል እኛ ትምህርት ቤት የመጣችው። የቤት ክራይ የምትከፍለው አብራቸው ከምታድራቸው የተለያዩ ወንዶች ብር እየተቀበለች ነው።


ጀመአችን ተዳክሞአል ብር የሚያዋጣ ሰው እና እስፖንሰር በማጣታችን ምክንያት የምንረዳቸው የቲሞች ቁጥር 10 ደርሷል። አመቱ እየተገባደደ ነው። አንድ ቀን ለታ It (informastion tecnology) ትምህርት ልንማር ኮንፒተር ወዳለበት ክፍል አመራን። የ አይቲ ላብራቶሪያችን ካለንበት ፎቅ ወርደን ሌላኛው ፎቅ ገብተን ስለሆነ የምንማረው ርቀት አለው። አይቲ ላብ ገብተን ወንበራችንን ይዘን እንደተቀመጥን ነበር መፅሀፍ መርሳቴን ያስታወስኩት።

አስተማርያችንን እስማኢልን አስፈቅጄ መፅሀፌን ላመጣ ወደ ክፍላችን አመራሁ። ክፍላችን 2ተኛ ፎቅ ላይ ነው ሚገኘው። በሩ አልተዘጋም ገርበብ እንዳለ ነው። ክፍት አድርጌው ወደ ቦታዬ አመራሁ።መፅሀፉንም ከቦርሳዬ አውጥቼ በእጄ እንደያዝኩ የሆነ ድምፅ ተሰማኝ።

#Part 1⃣9⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል

Join👇👇
t.me/Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ አስራ ሰባት 1⃣7⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን


በነገራችን ላይ 10ኛ ክፍል ከገባሁ በኋላ አንዲት አዲስ ልጅ ክፍላችን ገብታለች።መርየም ትባላለች ሲበዛ እብድ ናት እንደስሟም ቆንጆ ልእልት ናት።
ውሎዋ ከወንዶች ጋር ነው ደስ ሲላት ክፍል ትገባለች ደስ ሲላት ደግሞ ትቀራለች
ሂወቷ ላይ የሆነ አለመረጋጋት እንዳለ ስለተረዳሁ እስዋን ለመምከር የግድ ጓደኛዋ ሆኜ ስለስዋ በደንብ ማወቅ እንዳለብኝ ወሰንኩ እናም ከዘቦጋ ተመካክረን አቀረብናት።


መስገጃው ቤታችን እንድትሄድ ብዙ ጊዜ ብንጠይቃትም እናንተ ስለተመላለሳቹ ምን አገኛችሁ?? እያለች ታላግጥብናለች። መርየም ሲበዛ የዋህ እና እንደመሩዋት ምትመራ ሰው ናት ሞኝ ናት።እንዲህ እንድትሆን ያደረጉዋትም ሱሶችን ያስተማርዋት የሰፈርዋ ልጆች ናቸው። ትምህርት ብዙ ጊዜ የምትቀረው መቃሚያ ቤት እየሄደች እንደሆነ አረጋግጫለው። ሰአዳም ቀስ በቀስ ከኛ ጋር መሆን ሙሉ በሙሉ አቁማለች።ጓደኛዋ መርየም ሆናለች።ጭራሽ እንደ አዲስ ገቢ ተማሪዎቹ አሰላሙ አለይኩም ስንላት ትገላመጠን ጀምራለች ሰላትም አቁማለች።ከመርየም ጋር መውጫ እና መግቢያ ሰአታቸው እኩል ሆኖዋል። ሲቀሩ አብረው ይቀራሉ ሲመጡ አብረው ይመጣሉ።


የ እየሩስ አሳዳጊ በሽታውን መቋቋም ስላልቻለች ለሞት ተዳርጋለች። እንደ ነገሩ hiv ገደላት ይባላል እንጂ አላህ ከፃፈው ቀን ፍንክች የሚል የለም። ታመመም አልታመመም መሞቱ የማይቀር ነው።እየሩስም በአሳዳጊዋ ሞት በጣም አዝናለች።ያለስዋ ዘመድ አዝማድ ስለማታውቅ ኑሮ ሁሉ አስጠልቶአታል። ይባስ ብሎ ዳግም ያሉበትን ቤት ውርስ እንዳትካፈለው ብሎ ከቤት እንድትወጣለት ማያደርገው ጥረት የለም።
የትግስት እናት ዘይነባ ከልጅዋ አማር ጋር ወደ ከሚሴ የመሄድ ፍላጎት ቢኖራትም ትግስትን ትታ መሄድ አልፈለገችም ስለሆነም አማር ለብቻው ወደ ከሚሴ ተመልሷል።
መርየም እና ሰአዳ በተለይ የማትሪክ መፈተኛ ፎርም ከሞላን በኋላ ጭራሽኑ መግባት አቁመዋል።ፈተና ሲኖር ለመርየም ቴክስት ስለምናረግላት ይመጣሉ።

የሚውሉት ሺሻ እና ጫት ቤት ነው አሽሽም ያጨሳሉ። በሱስ ተዘፍቀው ካገኙት ወንድ ጋር ይተኛሉ። ትምህርት ቤትም በሚመጡበት ጊዜ ሱሱ አላስቀምጥ ሲላቸው ሽንት ቤት እየሄዱ አጭሰው ይመለሳሉ። የሴቶች ሽንት ቤት ጣራ ውስጥ ምሽግ ሰርተው ከክፍል ፎርፈው ቁጭ ብለው የሚያጨሱ ተማሪዎች አሉ
እዛው ቦታም ዚና የሚፈፅም ሞልተዋል።
የሴቶች ሽንት ቤት ኮርኒስ ውስጥ የሚሰሩትን ስራ ለመጀመርያ ጊዜ ያየሁት እኔና ዘቦ በ history ክፍለ ጊዜ ስናወራ አስተማሪያችን አይቶን አስወጥቶን አንበርክኮን እጅ ወደላይ አስብሎን የቀጣን ቀን ነው።

ስለ አድዋ ጦርነት እየተማርን ነበር ከተንበረከክንም በኋላ አስተማሪው ለ ዘቦ አንድ ጥያቄ ጠየቃት፦ ጣልያን ኢትዮጵያን ብትገዛት ኖሮ አባቶቻችን ታግለው ባያድኑን ኖሮ ምን ይፈጠር ነበር ሲል ጠየቃት ዘቦም ፦ ጣልያን ብትገዛንማ ኖሮ የካቲት 23 (የአድዋ ቀን) ትምርት አይዘጋልንም ነበር ስትል መለሰች። .
.....አስተማሪያችን በመልስዋ በጣም ስለተናደደ ሁለተኛ በኔ ክፍለ ጊዜ እንዳትገቢ ከክፍሉ ውጪ ብሎ አባረራት።እንዴት ታፌዝብኛለች ብሎ ተበሳጨ።

እኔን ደሞ ከተንበረከኩበት ተነሽና ወንበርሽ ላይ ተቀመጪ ብሎ ምህረት ቢያደርግልኝም ጓደኛዬን ትቼ አልገባም ያወራነው አብረን ነው ከተባረርንም አብረን ነው ብዬ መለስኩለት ያኔ አንቺም በኔ ክፍለ ጊዜ እንዳትገቢ ብሎ ከክፍሉ አስወጣኝ።

እውነት ለመናገር በዘቦ ንግግር እኔም ተናድጃለሁ። ክፍላችን ያለበት ፎቅ እየወረድን እንዴት እንዴ ትይዋለሽ ብዬ ጮህኩባት።ለነገሩ ሸር አስባ ወይም ለማላገጥ ብላ አልነበረም የእውነት ስሜትዋን ነው የተናገረችው። ትምህርት የለም ከተባለ ደስታዋን አትችለውም።ብዙውን ጊዜም ትቀራለች።

ፎቁን ከወረድን በኋላ ዳይሬክተራችን እንዳያየን እየሮጥን ወደ ሽንትቤት ሄድን ክፍለ ጊዜው አልቆ እስኪደወል ድረስ እዛው ለመቆየት አሰብን። እኔ በአርፋጅ ዘቦ ደግሞ በመቅረት ሪከርድ ስላለብን ዳይሬክተሩ ካየን መባረራችን የማይቀር ነው። ሽንት ቤት ደረስን።ለሴቶች ከተዘጋጀው 6 ሽንትቤት መካከል 6ተኛው ከወንዶች ሽንትቤት ጋር የተያያዘ ነው።እዛ ክፍል ውስጥ አንዳች ድምፅ ሰማን የሚንገጫገጭ ድምፅ። በሩን ከፍተን ምን እንደሆነ ለማየት ገባን።ለካ ክፍሉን መወጣጫ አድርገው ወደ ኮርኒሱ እየገቡ ነበር። የዛን ቀን ነው ኮርኒስ ውስጥ አሽሽ እንደሚያጨሱ ያወቅነው። በጣም የሚገርመው ደግሞ ያ ስድስተኛው ሽንት ቤት ከወንዶቹ ሽንትቤት ጋር የሚያገናኘውን ግድግዳ አፍርሰው ከወንዶች ጋር መገናኛ አድርገውታል። ውስጥ ለውስጥ ሳይታወቅባቸው ወንዱ በወንዶች በኩል ሴትዋ በሴቶች በኩል ገብተው ያሻቸውን ያደርጋሉ ዚና ይሰራሉ።ትምህርት ቤት ውስጥ(የሴቶች ሽንት ቤት) ማጨስ ሳይችሉ ሲቀር የግንቡን አጥር በድብቅ ዘለው አምልጠው ወደ ማጨሻ ቤታቸው ያመራሉ።...

Part 1⃣8⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል


Join👇👇
@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ አስራ አምስት 1⃣5⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን



አመቱ ማብቂያ ደረሰ ግንቦት ወር ላይ ሁሉንም ሙስሊም ተማሪ ያካተተ ሹራ በጀመአው ቤት ተደረገ።ጉዳዩ አሚር መረጣን በተመለከተ ነበር። አስረኛ ክፍሎች ማትሪክ ከተፈተኑ በኋላ ትምህርት ቤቱ ላይ ምንም ማድረግ ስለማይችሉ መምጣትም ስለማይፈቀድላቸው የስልጣን ሽግግር ያደርጋሉ። አሚር ተደርገው የሚመረጡት ዘጠነኛ ክፍል የሆኑት(ወደ 10 የሚሸጋገሩት) ነው። ዘጠነኛ ክፍል የነበሩትም 10 ገብተው ማትሪክ ሲፈተኑ በተመሳሳይ ሁኔታ ስልጣናቸውን ያስረክባሉ። በዚህ ጉዳይ ነበር ለሹራ የተሰባሰብነው።


ሹራው ተጀመረ።ጀመአው ሲመሰረት ከነበሩት ተማሪዎች መካከል የነበረው ፈትሁዲን ንግግር ጀመረ። ወንድ እና ሴት በመጋረጃ ስለተለያየ ፊቱን ማየት አልቻልኩም ግን ንግግሩ የንዴት እንደሆነ ድምፁ ያስታውቃል። ይሄ ቤት እኮ! አለ ድምፁን ከፍ አድርጎ።ይሄ ቤት እኮ መስዋትነት የከፈልንበት ቤት ነው ትምርታችንን ያጣንበት ለእስር የተዳረግንበት የተደበደብንበት አፈር ድሜ የበላንበት ቤት ነው ይሄ ቤት እኮ ለናንተ ለማስተላለፍ ለናንተ ለማበርከት እንቅልፍ ያጣንበት ያለቀስንበት ቤት ነው።እናንተ ግን የጥቂት ሰዎች ሰላት መስገጃ ብቻ አደረጋችሁት። ጀመአው ፈርሶዋል ማለት ይቻላል በኛ ጊዜ እኮ ቀጣይ ወር የሚደረገውን የዳእዋ ፕሮግራም አስቀድመን ነበር ምናዘጋጀው እናንተ ግን ብዙ ጊዜ ፕሮግራማቹን አይቻለው እንዳልተዘጋጃችሁበት ያስታውቃል። ጀመአውን ካልፈለጋችሁት ለሌሎች ስጡት ቤቱ ብዙ ነገር ሊሰራበት ይችላል፡፡ ጊቢው ውስጥ ካለው ከ 1000 በላይ ሙስሊም ተማሪዎች መካከል እዚህ የተገኘው 200 እኳን የማይሞላ ነው ይህ የሆነው የዳእዋ ጥሪ በተገቢው መንገድ ባለመደረጉ በደንብ ባለመሰራቱ ምክንያት ነው።

አላማ ይኑራችሁ goal ይኑራችሁ ዝም ብላችሁ አትነዱ።የራሳቹን ታሪክ ስሩ።እኛ ይሄን ቤት አስተካክለን ሰጠናችሁ እናንተ ደሞ ለቀጣዩ ትውልድ ሌላ አዲስ ነገር ፍጠሩ........ንግግሩን ቋጨ።

የጀመአዋ የሴቶች አሚር ሀናን ከዘጠነኛ ክፍል ሴት ተማሪዎች አሚር ለመሆን ጀመአው ላይ ለማገልገል ፍቃደኛ የሆነ እጁን ያውጣ አለች። ማንም እጁን አላወጣም።በርግጥ አሚር መሆን ማለት በጣም ከባድ ነው ለሰዎች አርአያ መሆን ማለት ነው አሚር መሆን ማለት ሌሎችን ሰዎች መምራት ማለት ነው አሚር መሆን ማለት ከራስ አልፎ ሌሎች ሰዎችን ማስተማር ሌሎች ሰዎችን ማስተዳደር ነው። እኛ ደግሞ እራሳችንን ማስተካከል ያልቻልን ሰዎች ነን። አሁንም በድጋሚ ጠየቀች ምላሽ አጣች
.....በስተመጨረሻም እራሴ የማውቃቸውን እሾማለሁ ብላ ስም ጠራች። ኢማን ጄኔራል አሚር(ዋና አሚር) ዘቢባ ሱልጣን እና ዘቢባ ነጃ የዳእዋ ዘርፍ(ተማሪዎችን ወደ ጀመአው መጥራት) አሚር፤ ሂክማ የፍይናንስ ዘርፍ አሚር ፤........... እያለች በፍላጎትዋ መደበች።ከጄነራል አሚርዋ ኢማን ጀምሮ ሁላችንም ደስተኛ አልነበርንም።

ዘቢባ ሱልጣን እና ዘቢባ ነጃ ማለት እኔና ዘቦ ጋደኛዬ ነን። በተለይ እኔ በፍፁም ለአሚርነት በቂ አልነበርኩም።ትልቅ ሀላፊነት እንደተሸከምኩ ተሰማኝ እራሴንም ማስተካከል እንዳለብኝ ወሰንኩ። በወንዶቹም በኩል አቡበከር ጄነራል አሚር ተደርጎ ተመረጠ።ከኢማን (ሴቶች ጄነራል አሚር) ጋር የአንድ ክፍል ተማሪዎች ናቸው።ከዛን ቀን ጀምሮ ማርፈድ አቁሜ በሰአቱ መግባት ጀመርኩ።

እንዳውም አንድ ቀን ለታ ሰልፍ ላይ ተገኝቼ ዳይሬክተሩ ሲመለከተኝ አንቺ ከመጣሽ የቀረ የለም ማለት ነው ብሎ መሳቂያ አድርጎኛል። አመቱ አለቀ አሚሮቹም ወጡ እኛም 10ኛ ክፍል ገባን።እኛ አስር 7 እነ ኢማን አስር 12 ናቸው።


ትምህርት ገና ከመጀመራችን የትግስት አባት ፍራኦል ሞት ተሰማ። ሀዘንዋ መጠን አልነበረውም።እናትዋ ዘይነባም የባልዋን ሞት ተከትላ መስለምዋ ደግሞ ይበልጥ እንድታዝን አድርጓታል።እስዋን ለማፅናናት ብዙ ጊዜ ፈጅቶብናል በሁለት እግርዋ እንድትቆም ለማድረግ ብዙ ጥረናል።

የአባትዋ ሞት ተከትሎ ወንድሟም እናቱን እና ብቸኛ እህቱ ትግስትን ለመውሰድ ወደ አዲስ አበባ መጥቷል።

#Part 1⃣6⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል

@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ አስራ ሶስት 1⃣3⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን


በ Ayuti Islamic Post ቻናል የተዘጋጀ

ቀስ በቀስ ሁላችንም የየራሳችንን ጓደኞች አፈራን
ኬቢ(ኬብሮን) ራሄል የተባለች ጓደኛ ስታፈራ እኔ ደሞ ዘቢባ፣እየሩስ፣ትግስት፣ሰአዳ እና አሚራ የተባሉ ጓደኞችን አፍርቻለው። በባህሪዬ ሰው ለመግባባት ጊዜ ስለማይፈጅብኝ እነሱን ለመተዋወቅ አልተቸገርኩም።

...ሙስሊም ጓደኛ ኑሮኝ ስለማያውቅ አሚራን ሰአዳን እና ዘቢባን ከሌሎቹ በተለየ በጣም ነበር የምወዳቸው። በተለይ ደሞ ለዘቢባ ያለኝ ፍቅር ልዩ ነበር። ብዙ ነገሬን ቀይራዋለች አለባበሴን ስርአቴን እናም ሌሎች ባህሪዎቼን አስተካክላዋለች።

ቂርአቴ ላይ ጊዜ እንድወስድ ሶላት በሰአቱ እንድሰግድ ብዙ ነገር አስተምራኛለች።እኔ ዘቦ እና ሰአዳ ምሳ ይዘን ስለምንሄድ ምሳ ሰአታችንን ትምህርት ቤት ነው የምናሳልፈው አሚራ ምሳ ስለማትይዝ ወደ ቤትዋ እየሄደች ትመገባለች።እኔ ሰአዳና ዘቦ ምግቦቻችንን በየተራ ከተመገብን በኋላ ሶላት ለመስገድ ወደ ግቢያችን ጀመአ ቤት እናመራለን።


ትምህርት ቤታችን የሙስሊም ተማሪዎች ጀመአ እንዳለው የሰማሁት ከዘቦ ነው። ከዛን በፊት ጀመአ ምን እንደሆነ እራሱ በቅጡ አላውቅም ነበር። የትምህርት ቤቱ ጀመአ 14 አመት አስቆጥሯል። ብዙ ኡስታዞች መተው አስተምረውበታል ብዙ ዳእዋዎች ተደርገውበታል።ጀመአውን ትምህርት ቤቱ ስለማይፈቅደው ብዙ ተማሪዎች ብዙ ፈተና ደርሶባቸዋል።ከመባረር እስከ መታሰር ደርሰዋል።

ጀመአው በሊላሂ የተሰጠው አንድ ሰፋ ያለ ክፍል ቤት አለው።ምሳ ሰአት ላይ ሴቶች ይሰግዱበታል።በሳምንት ጁመአ ደግሞ አሚሮቹ ተሰብስበው ሹራ ያደርጉበታል።በየ ወሩ ደግሞ ሙሉ የጊቢው ሙስሊም ተማሪዎች ተጠርተው የዳእዋ ፕሮግራም ይሰጥበታል ። ከአሱር እስከ መግሪብ ደግሞ የሰፈሩ ህፃናት ቁራን ይቀሩበታል።ወንዶች ሰላት የሚሰግዱት መስጂድ ነው።የጀመአው ቤት ለሶላት ትንሽ ቢርቅም ሌላ አማራጭ ስለሌለ የግድ እንሄዳለን።
አልፎ አልፎም መንገዱ ሲሰለቸን እንዲሁም እየሩስ እና ትግስት አብራችሁን ዋሉ ብለው ሲለምኑን ክፍል ውስጥ የዩኒፎርም ሹራባችንን አንጥፈን አስተማሪ እንዳይደርስብን በሩን በውስጥ ቆልፈን እየሩስ እና ትግስት ከውጭ የሚመጣውን ሰው እየጠበቁልን እንሰግዳለን።


እየሩስ የምትኖረው ከአንዲት አሳዳጊዋ ጋር ነው እናትም አባትም የላትም ቢኖራትም የት እንደሚኖሩ ምን እንደሚመስሉ አታውቅም እነሱም ፈልገዋት አያውቁም። ለነገሩ እየፈለጓት ቢሆን እንኳን ያያቸው የለም። አሳዳጊዋ ያገኘቻት ቆሻሻ ውስጥ ተጥላ እንደሆነ ነግራታለች።የሰፈሩ ሰዎችም ይሄንን ታሪክ ስለሚያውቁ ምን በላሽ? ምን ጠጣሽ? የት ነሽ የት ዋልሽ? እያሉ ይንከባከብዋታል። በተለይ ደግሞ አሳዳጊዋ hiv ስላለባት እንድትጠነቀቅ ይመክሩዋታል።

ሌላኛው ከጎዳና አንስታ ያሳደገችው ልጅ ዳግምም ምንም እኳን አብረው ቢያድጉም ሴትነትዋን እንዳይነካ ያስጠነቅቁታል።ምክንያቱም ዳግም ብር ወዳድ እና ውለታ ቢስ ሰው ነው። አሳዳጊውንም መቃሚያ ብር ካልሰጠችው ይደበድባታል።


ትግስት ደግሞ የምትኖረው ከእናት እና አባትዋ ጋር ነው። ታላቅ ወንድም ቢኖራትም እስልምናን በመቀበሉ ምክንያት ከአባቱ ጋር ተጣልቶ ከሚሴ የምትባል ሀገር ሂዶ የራሱን ህይወት መኖር ጀምሯል። የትግስት እናት ዘይነባ ትባላለች የሙስሊም ልጅ ብትሆንም የትግስትን አባት ፍራኦልን በማፍቀሯ ምክንያት ሀይማኖቷን ቀይራ አግብታዋለች። የ ትግስት ታላቅ ወንድም መላኩ ከሰለመ በኋላ ስሙ አማር ሁኗል።

በመስለሙ ምክንያት ትግስትም በጣም ስለተበሳጨች ስሙን እንኳን መጥራት አትፈልግም።

Part 1⃣4⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል

Join👇👇
@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ አስራ ሁለት 1⃣2⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን


ለማግባት ዝግጁ እስካልሆንኩ ድረስ ከወንድ ጋር የሀራም ግንኙነት ላልጀምር በአላህ ቃል ቁርአን መትቼ ማልኩ

አመቱ ማብቂያ ደረሰ ሀምሌ ወር መጨረሻ ላይ ነን። የሚኒስትሪ ውጤት ወጣ። ይወድቃሉ ተብለን ስማችን ይጠራ የነበረው ዮናታን ዩሴፍ እና እኔ በተርታ 91.5 ,92.4 እና 93.6 አመጣን። ትምህርት ቤታችንም ሁላችንም የተፈተነዉ ተማሪዎች አልፈናል። ከዚህም ባሻገር ሁሉም ተማሪ ከ 77.3 በላይ በማምጣቱ ምክንያት ትምህርት ቤቱ ከ ኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የዋንጫ እና የማበረታቻ ሰርተፊኬት ሽልማት አግኝቶዋል። 4 ተማሪዎችም 99.9 በማምጣት በ ኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ተሸልመዋል። ከድርም 99.9 አምጥቶ ማለፉን ከሰፈሩ ልጆች ሰምቻለው። ደስ የሚል እና የሚያሳዝን አመት የማይረሱ ትዝታዎች ብዙ ነገር ተፈጥረዋል።

በከድር ፍቅር ታውሬ ዋናውን ነገር ረሳሁት። ሰባተኛ ክፍል መጨረሻ አካባቢ ማለትም የረመዳን ወር ላይ እነ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፤ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ፣ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፤ልጅ አቡበከር አደም...........የመሳሰሉት በአሸባሪነት ስማቸው ተነስቶ ታስረዋል።


ለ እስልምናዬ ቦታ መስጠት የጀመርኩት እነ አቡኪ (አቡበከር አህመድ) ፤ አህመዲን ጀበል እና እነ ያሲን ኑሩ የመሳሰሉትን ኡስታዞቻችን አሸባሪ ናቹ ተብለው የታሰሩ ጊዜ ነው። እምነት ማለት ምን እንደሆነ የገባኝ ያን ጊዜ ነው። ሰላትም መስገድ የጀመርኩት በዛ ምክንያት ነው።

በተለይ ደግሞ የዛን ጊዜ የረመዳን ወር ፆም ማብቂያ የኢድ ሰላት ላይ በተደረገው ተቃውሞ ምክንያት በተነሳው ረብሻ ፖሊሶች ህዝቡን በፍልጥ ሲያደቁ እኔንም በደረሰኝ አንድ ዱላ እና የጉልበት መላላጥ አማካኝነት ነው ይበልጥ እስልምናዬን እንድወድ መንገድ የከፈተልኝ።እድሜዬ 13 ወይም 14 አመት ገዳማ ይሆነኝ ነበር።እድሜያችን በጨመረ ቁጥር አዳዲስ ነገሮችን አብረን እንማራለን አይምሮአችንም ማገናዘብ ይጀምራል።በተለይ ደግሞ ከ elementary ትምህርት ቤት ወደ hign school ስንሸጋገር መቆሚያው እና መቀመጫው ይጠፍናል። dv ደርሶት አሜሪካ የሚሄድ ሰው እንኳን የኛን ያክል አይደሰትም።

የትምህርት ጥግ የደረስን እስኪመስለን ድረስ ደስታችን ወደር አይኖረውም።ይሄ ስሜት ሳይሰማው ያለፈ አንድም ተማሪ የለም።እኔም በዚህ ስሜት ውስጥ ሆኜ ነው ዘጠነኛ ክፍልን ድላችን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የገባሁት። ከ 1 እስከ 8 የተማርኩበት ትምህርት ቤት የግል ቢሆንም የሚኒስትሪ ውጤት ከወጣ በኋላ የሚመድበው ግን የመንግስት ትምህርት ቤት ባልቻ አባነፍሶ የሚባል ትምህርት ቤት ነው። እኔም የተመደብኩት ባልቻ ቢሆንም ካለሁበት ሰፈር ትንሽ ርቀት ስላለው አቅራቢያዬ ወዳለው ድላችን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ ጓደኛዬ አባት አማካኝነት ተመዘገብኩ።


ጓደኛዬ ኬብሮን ትባላለች ፕሮቴስታንት(ጴንጤ) ናት ኢለመንተሪም አብረን ነው የተማርነው። ከተመዘገብንም በኋላ ክፍል ተመደብን። ብዙ ተማሪ ስለነበር ዘጠነኛ ክፍል ብቻ 23 ክፍሎች ነበሩ።ዘጠኝ 1 ፤ ዘጠኝ 2 ፤ ዘጠኝ 3............ እየተባለ ነው ሚጠራው። እኔ የደረሰኝ ዘጠኝ 7 ሲሆን ኬብሮን የደረሳት ዘጠኝ 5 ነበር። ሁሉም ተማሪ ለኛ እንግዳ ስለነበር በ እረፍት እና በ ምሳ ሰአታት እየተገናኘን ብቻችንን እንቀመጣለን። ተማሪዎች ሲጫወቱ ሲላፉ እኛ ተመልካች ነን። ትምህርት ቤቱ በጣም ደብሮናል። ላይናችን ያስጠሉናል።


እኔም የሀብታሞቹ ልጆች ባህሪ ተጋባብኝ መሰለኝ ተማሪዎቹ ሊያናግሩን ሲሞክሩ ኩራት ኩራት ይለኛል። ገና ከትውውቃችን ስም ከተለዋወጥን በኋላ ቀጣዩ ከየት ትምህርት ቤት ነው የመጣሽው?? የሚል ጥያቄ ስለሆነ ይኬንን ጥያቄ እንዳቀረቡልኝ ስለ ትምህርት ቤቴ ዝና እና ስም እንዲሁም የልጥጥ ትምህርት ቤት እንደሆነ ክፍያውም ምን ያክል እንደሆነ ኮራ ብዬ በጋንኜ ቅመም ጨምሬ እነግራቸዋለው።
.....ቀስ በቀስ ሁላችንም የየራሳችንን ጓደኞች አፈራን

Part 1⃣3⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል

Join + share
👇👇👇👇👇
@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ አስር 🔟

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን



ፊት ለፊቱ ቆሜ አይኔን ከአይኑ ገጥሜ ጥርሴን ከጥግ እስከጥጉ ከፍቼ ከድሬ አልኩት። እሱም ያንን የሚያፈዘው ፈገግታውን ተጠቅሞ ልቤን እያቀለጠ ወዬ ዘቢ አለኝ።
......ታፈቅረኛለህ? ስል ጠየኩት።
.......እሱም ትጠራጠሪያለሽ እንዴ?? አለኝ
.......እኔም እሺ ለኔ ያለህን ስሜት ንገረኝ እስቲ በራስህ አንደበት እኔን ግለፀኝ ??? አልኩት።
......እሱም ሰምቼው በማላውቀው ንግግር አንቺ ማለት ለኔ ህይወቴ እናቴ እህቴ ሚስቴም ጭምር ነሽ በ እናቴ ያላገኘሁትን ፍቅር ያገኘሁት ባንቺ ነው። ካንቺ ሌላ ያፈቀርኩትም የተመኘሁትም የምመኝውም ሴት የለም።አንቺ ማለት ልቤ ውስጥ ልዩ ቦታ ያለሽ ብቸኛ ሴት ነሽ አንቺ ማለት የልጆቼ እናት አጋሬ ሀላል ሚስቴ ነሽ አለኝ።...ያለኒካ ሀላል አለ እንዴ? ወይ እኔ ሞኝ እኮነኝ የነገሩኝን ሁሉ አምናለው።

ከንግግሩም አስከትዬ የዚህን ያክል የምታፈቅረኝ ከሆነ አንተም አንድ ውለታ ዋልልኝ ...ዚና መስራት አልፈልግም ከኒካ በፊት ከማንም ጋር መተኛት አልፈልግም አላደርገው አልኩት።

ፊቱ ሲቀያየር ታየኝ።ያ የሚያምረው ቀይ ፊቱ እንደወረቀት ተጠቅልሎ ጭምድድ ብሎ ሲኮሰታተር አየሁት። ተረጋጋ ከድሬ ብዬ በጥርሴ ልደልለው ሞከርኩ።ጥያቄዬን ቀጥልኩ።
.....ከድሬ ከኔ ሌላ ሴት አትጨብጥም ማለት ነው? አልኩት
.......እሱም እያወቅሽ ለምን ትጠይቂኛለሽ እኔ አጂ ነብይ የሆነችኝን ሴት አልጨብጥም አንቺንም ስለማፈቅርሽ ነው አለኝ።
.......ለምንድነው የማትጨብጠው ?? ብየ ጠየኩት።
......እሱም መድረሳ የምትመላለሺው ዝም ብለሽ ነው እንዴ ይሄንን አታውቂም? ለኛ እኮ አልተፈቀደልንም ሀራም ነው ለምን እናደርገዋለን ሌሎቹም እኮ የአላህን ህግ ጥሰው እንጂ ተፈቅዶላቸው አይደለም ሀራም ነው መቼም ከሚስቴ ውጪ አልጨብጥም አልነካም ብሎ መለሰልኝ። ግን እኔ ሀራምነቱን ሳላውቅ ቀርቼ ሳይሆን የጠየቀኝን የዚና ጥያቄ ለማስቀየር ነው ጥረቴ።
......አሁንም ንግግሬን ቀጠልኩ።ታዳ ዚና መስራትስ ሀላል ነው እንዴ? ከ መጨበጥ እና ያለኒካ ከመተኛት የትኛው ነው የሚከብደው የትኛው ነው ትልቅ ወንጀል??? ብዬ ሌላኛውን ጥያቄ ጠየኩት።
......እሱም ይሄን ሁሉ እንቢ ለማለት ነው??? ሀራምነቱ ጠፍቶኝ አይደለም አንቺን ግን ስለማገባሽ ስለማፈቅርሽ ነው እናድርግ ያልኩሽ እንደዚህ ልትሆኝ አይገባም።ካሁን በኋላ ተስማምተሽ ከኔጋ ለመተኛት ካልወሰንሽ አጠገቤ እንዳደርሺ ብሎ ጥሎኝ ሄደ።

ምድር ከሰማይ ተደበላለቀብኝ ቀኑ ጨለመብኝ። ምነው አላህዬ ለምን ታሳጣኛለህ?? ብዬ ወቀስኩት። በርግጥ የዚና ጥያቄውን ያልተቀበልኩት አላህን ፈርቼ አልያም ሀራም ነው ብዬ አልነበረም።ጥያቄውን የተቀበልኩት ወንድሜ ጭንቅላቴ ውስጥ በቀረፀው ንግግሩ ምክንያት ነው። ታላላቆቻችን የሚያስተምሩን ጥሩም ይሁን መጥፎ ነገር ለኛ ለታናናሾች ትርጉም አለው።

ይሄንን ብቻ አይደለም ወንድሜ ያስተማረኝ
ከ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ ማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊ ነው እኔም ልክ እንደሱ የዩናይትድ ደጋፊ ነኝ።ጨዋታ ባለው ጊዜም እየተከታተልኩ አያለው።
በ ስፔን ላሊጋ ደግሞ የሪያል ማድሪድ ደጋፊ ነው እኔም የሪያል ማድሪድ ደጋፊ ነኝ።
ከሀገር ውስጥም ቡናን ይደግፍል እኔም እንደዛው።ምን ቸገራቹ ባጭሩ የወንድሜ ደጋፊ ነኝ።ልዩ የሆነ የግጥም ችሎታ አለው።ይኸው እኔም በሱ ወጥቼ ፈለጉን ተከትዬ የወጣልኝ ገጣሚ እና ደራሲ ሆኛለሁ😜 እንዳውም በከድሬ አሳብቤ የገጠምኩትን ግጥም ልበልላቹ

........እማማ ትሙት...........
ያ የኔ ሽምጋይ
የልቤ አታላይ
በአስመሳይ ጥርሱ
በቅቤ ምላሱ
እንደሚወደኝ አስበልጦ ከርሱ
እማማ ትሙት! እያለ ምሎ
እመኚኝ ግድ የለም ወደድኩሽ ብሎ
ቃላትን ቀምሞ
ሲነግረኝ ከርሞ
እውነቱን ነው ብዬ
ቃሉን ተከትዬ
መሀላው አምኜ

እማማ ትሙት! እማማ ትሙት!
አሁንም ትሙት ደጋግማ ትሙት!
ሺ ጊዜ ሺ ጊዜ ገሎ በመሀላ
በዘረጋው ወጥመድ ከጣለኝ በኋላ
እንዳልገባኝ ገባኝ ያኔ እውነቱ
ሰንበትበት እንዳለ ከሞተች እናቱ


.......ከጅምሩ.......
ያኔ ስንገናኝ ከጅምሩ
እጆቻችን ሲያወሩ
ሬት ሳይልህ እኔነቴ
ስንባባል ያባረርከው
ድንበር ዘለው ልቦቻችን
ሲገናኙ አይኖቻችን
እያዜሙ የፍቅር ዜማ
ሊያበሩ የድል ሻማ
ወየው ዛሬ በነበረ
ትላንህናን ባልቀበረ
ድንገት ደርሰህ ስትለወጥ
አሁን ታየኝ ልቤ ሲሰምጥ
ሀ ብለህ ያስጀመርከው
ፐ ብለህ ሳጨርሰው
ለጋው ፍቅሬ ተሰበረ
ገና ሳያድግ ረገፈ
ውዴ ሲልህ ያባረርከው
ብሎ ቆሟል ትመጣ እንደው
.
.
ለ ከድር


ይሄ ነገሩ አድጎ ይኸው ከዚና ጠብቆኛል። ወንድሜ ባያስተምረኝ ኖሮ ዛሬ ከከድር ጋር በሀራም በተጨማለኩ ነበር

Part 1⃣1⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል

@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

http://youtu.be/bf79BGVGQWQ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
http://youtu.be/bf79BGVGQWQ

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

   ┏━━━ ◌͜͡༄ ━━━━💞━━┓
彡💞 Ayuti Islamic Post ☜join us
     ┗━━━ ◌͜͡༄ ━━━━💞━━┛

የፈጅር ሰላት የበረካዎች ሁሉ መጋዘን ነች !!
┈┈• •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈• •┈┈
የአሏህ ነብይ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም (( አሏሁመ ባሪክ ሊኡመቲ ፊ ቡኩሪሃ = አሏህ ሆይ ለኡመቴ የንጋት ወቅታቸውን ባርክላቸው )) ሲሉ ነው የተማጸኑት ። ቲሪሚዚ ፣ ኢብን ማጀህ እና አሕመድ የዘገቡት ሐዲስ ነው

የፈጅር ሰላት ወይም የሱብሒ ሰላት ከጤናችን ጋር ተያያዥ የሆኑ ወሳኝ ጠቀሜታዎችን በሙሉ ጠቅልሎ የያዘ የጤና በረከት ነው ። እነዚህንም የጤና በረከቶች እንደሚከተለው ተመልክተናቸዋል ፡
1/ ለጤናችን ወሳኝ ከሆኑ ሆርሞኖች ውስጥ አንዱ ኮርቲዞን የተሰኘው ሆርሞን ነው ። ይህ ሆርሞን ሰውነታችን ንቁ እንዲሆን የሚያደርግ ሆሮሞን ነው ። ታዲያ የሚደንቀው የዚህ ሆርሞን እንቅስቃሴ የሚጨምረውና ሰውነታችንን በከፍተኛ መጠን የሚያነቃው ልክ የፈጅር ሰላት ወቅት ሲገባ ነው ። በዚህ ወቅት የደም ዝውውራችን ሥርዓት በከፍተኛ መጠን በመጨመር መላ ሰውነታችንን ያነቃቃዋል ። ከጠዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ አንድ ሰዓት ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ አእምሮ ብሩህ የሚሆንበት ፣ ጉልበታችን የተሟላ ኃይል የሚያካብትበት እና ለማንኛውም ሥራ በታላቅ ስሜት የምንዘጋጅበት ወቅት ነው ። ለዚህም ነው ውዱ ነብይ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም አሏህን ዐዘ ወጀለ ፡ (( አሏሁመ ባሪክ ሊኡመቲ ፊ ቡኩሪሃ = አሏህ ሆይ ለኡመቴ የንጋት ወቅታቸውን ባርክላቸው )) ሲሉ የተማጸኑት ። ቲሪሚዚ ፣ ኢብን ማጀህ እና አሕመድ የዘገቡት ሐዲስ ነው

2/ በዙሪያችን ባለው ከባቢ ውስጥ የኦዞን ጋዝ O3 በከፍተኛ መጠን የሚገኝበት ዕንቁ ጊዜ ነው ። ይህ ጋዝ አእምሮን ብሩሕ በማድረግ ፣ የተለያዩ ነርቮችን ሚዛናዊ እንቅስቃሴ የሚያስተካክል ጋዝ ነው ። በሳይንሳዊ ጥናት እንደተረጋገጠውም በፈጅር ወቅት ይህ ጋዝ -OZONE - ወደ ውጫዊው የምድር ገጽታ እንደሚወርድ ተረጋግጧል ።


ከፍተኛ መጠን ያለውን የኦዞን ጋዝ ከእንቅልፍ ነቅተን የመሳብ ዕድል ማግኘት ለጠቅላላው የሰውነታችን አካላት ጤናማና ንቃት ያለው የተስተሰካከለ የሰውነት እንቅስቃሴዎችን እንዲያደርጉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ።


3/ ለፈጅር ሰላት ከእንቅልፍ መንቃት ከልብ በሽታ ይታደገናል። ረዥም እንቅልፍ መተኛት Atherosclerosis የተሰኘውን የልብ መታፈን በሽታ ያስከትላል ። ምክኒያቱም እንቅልፍ ገደብ የለሽ ስክነት በመሆኑ ነው ። በእንቅልፍ ውስጥ ለረዥም ሰዓታት ገደብ የለሽ ስክነት ተፈጠረ ማለት በደም ጋኖቻችን ውስጥ የሚዘዋወረው ስብ በአሪተሪዎች ውስጥ እንዲረጋ ስለሚያደርግ ነው ። ከዚህም የመነጨ በኮሮናሪ አርተሪስ ( Coronary Arteries ) ውስጥ የሚዘዋወረው ስብ በመርጋት የልብ መታፈን በሽታን ያስከትላል ። ይህ በሽታ እንዳይፈጠር የምንከላከልበት ብቸኛው መንገድ ደግሞ ለሱብሒ ሰላት ፈጥንነን በጊዜ በመነሳት ነው ።


እናማ ውድ ሙስሊሞች ለፈጅር ሰላት መነሳት ለአእምሮም ለሰውነትም ቀለብ ነው ።

ከተጨማሪ መረጃዎች ጋር በቀጣይ እንገናኝ እያልኩ ለዛሬ በዚሁ ላብቃ … አሏህ የዲናችንን ወደር የለሽነትና ታላቅነት ተረድተን በአግባቡ የምንጠቀምበት ሰዎች ያድርገን ሰላም !!

⁩✿┈┈┈┈┈•✶✾✶•┈┈┈┈┈✿
@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

እህቴ! ተምሳሌቶችሽ ተውኔታዊያን እና ሞዴሊስቶች ባለመሆናቸው እነሱን እርሺ ሰለፎችን ግን አስታውሺ። ከእነሱም

⇢ አኢሻ ቢንት አቡበከር رضي الله عنها

⇢ዛሬ ላይ የምናወሳት ተምሳሌትሽ ቀዳሚዋ ልእልት አኢሻ رضي الله عنها ናት ። ይህች ልእልት በእውቀቷ የላቀች ፣በጥብቅነቷ የታወቀች ናት ። ለሙናፊቆች ውንጀላ ያልተምበረከከች ድንቅ ስብእና ፣ስለ ንጽህናዋ በአዛኙ ጌታ የታወቀች ጥብቅ እንስት ፣የምእመናን ድንቅ እናት ፣የቁርጥ ቀን እንስቶች ዋና ማሳያ ድንቋ አኢሻ ቢንት አቡበከር።

⇢የዘመኑ ሴቶች በእውቀት ማነስ ቢወነጀሉም አኢሻ ግን በእውቀቷ ወደ ላይ ተስወንጭፋለች ። የእውቀቷ ደረጃ ከሴቶች ድንበር የተሸገረና ከወንዶችም መጥቃ ሰማይ ነክታለች ። ይህ የእውቀት ደረጃዋ ሲታሰብ የሷ አምሳሎች ተፈጥረው የምናይበት ቀንን የእውነት ያስመኛል ።

⇢ወንድሜ ዛሬ ሴቶች እውቀትን ለመፈለግ ወደ ወንዶች ሲያቀኑ ማየትህ አይሸንግልህ ። ምክንያቱም ትናንት ወንዶች እውቀትን ለመፈለግ አኢሻ رضي الله عنها ጋር ተገኝተዋል ። ያውም እንዳንተ ተራ ወንዶች ሳይሆኑ እጅግ ብርቱ ወንዶች ወይም የነብዩ ﷺ ባልደረቦች ፣እነዛ ትውልድን የመሩ ከዋክብቶች

⇢አቡል ሙሳ አል አሽአሪ رضي الله عنها የነብዩን ﷺሰሀቦች ድርጊትን ባወሳበት ሒደቱ ተከታዩን ብሏል፦

እኛ ሶሀቦች በነብዩ ﷺ ሐዲስ ላይ ችግር ሲገጥመን አኢሻን رضي الله عنها እንጠይቅ በሱም አዋቂ ሆና እናገኛት ነበር፨

[ሱነን አት - ቲርሚዚይ ቁ .3886 ሐዲሱን አልባኒ ሶሒህ ብለውታል]

⇢አየሽ እህቴ አኢሻ እንዲህ አዋቂ ነች ። እንደሷ እውቀትን ከሻሽ ድራማውን እርሺ አኢሻን ግን አስታውሺ!!!

ለሙስሊሟ እህቴ ማስታወሻ ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ

@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ ስድስት 6⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን


〰〰〰Ayuti Islamic post〰〰〰

ስገባም አልጋው ላይ እግሩን ወደ መሬት አንጠልጥሎ ተቀምጧል። ወይ የሰው መመሳሰል! አባዬ አልነበረም ግን በጣም ይመስላል።ቀድሞውኑ አይኔ ዋሽቶኝ ነው እንጂ አባቴ እንደዚህ አይነት ቅሌት እንደማይሰራ እና እንደዚህ አይነት ነውር እንደማያደርግ አውቃለው።


ቢሆንም አባዬ ስላልሆነ ንዴቴ አልቀነሰም ሊበርድልኝ አልቻለም ምክንያቱም ሰውዬው ወደ ሴተኛ አዳሪዋ ቤት የገባው ትልቅ ሰዉ ነዉ ። ቅሌታም ነህ ትልቅ ሰዉ አሰዳቢ እያልኩ ዘለፋዬን ቀጠልኩ
.......ሴተኛ አዳሪዋም ዞር በይ ገበያ አትዝጊብኝ ብላ እንደቆሻሻ አሽቀንጥራ ከቤትዋ አስወጣችኝ።

ቆሻሻውስ አንቺ ነሽ መገፍተር የሚገባሽ አንቺ ነሽ እያልኩ በልቤ የንዴት ስሜቴ ጥርሴን እያፈጫጨው ወደ ቤቴ ገባሁ።


ለከድር መናገር ያልቻልኩትንም ጭምር ንዴቴን አባብሶት እራስ ምታት እንደ መጋኛ አመመኝ።ቤትም እንደገባሁ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ። በማግስቱም እንደተለመደው ቦርሳዬን እና ምሳዬን ይዤ ወደ ትምህርት ቤት አመራሁ። መንገዱን እየተጓዝኩ የማስበው ስለ ከድር ነው። ስሜቴን ያወቀብኝ እየመሰለኝ በራሴ አፈርኩ። እሱን ማናገሩም ሞት መሰለኝ። ከዛን ቀን ጀምሮ ብዙ ጊዜ አሰላሙ አለይኩም ሲለኝ ባልሰማ አልፈው ጀምሬያለሁ
አስተማሪዎቼ ሁሉም ማለት ይቻላል በጣም ይወዱኛል። በተለይ ደግሞ ጥያቄ ለመጠየቅ እና የማስበውን ለመናገር ስለማልፈራ ያበረታቱኛል። ሀሳባቸውንም ቢሆን ለመቃረን ቅድሚያ የምነሳው እኔ ነኝ በዚህም ምክንያት ነው ለኔ ያላቸው ፍቅር ልዩ የሆነው.


ሰባተኛ ክፍል አጋማሽ ደረስን። የፋይናል(የመጀመርያ መንፈቅ አመት ማጠቃለያ ) ፈተናችንን ከተፈተንን በኋላ የ 15 ቀን እረፍት ተሰጠን። 15 ቀኑ 15 አመት ሆነብኝ ጊዜው አልቆ ትምህርት እስክንጀምር ጓጓሁ። የከድር ናፍቆት አላስቀምጥ አለኝ።መድረሳ ስሄድም ቆሜ ብጠብቀውም ላገኘው አልቻልኩም።አንዳንዴም እያለቀስኩ አላህዬ አንድ ጊዜ አይኑን ብታሳየኝ ምናለ እያልኩ አነባለሁ።

የእረፍት ጊዜያችን አብቅቶ የትምህርት ገበታችንን ጀመርን።እየሩስ ናፍቀሽኛል ብላ ተጠመጠመችብኝ።እኔም ናፍቀሽኛል ብዬ አንገትዋ ስር ተወሽቄ አለቀስኩ። ግን ያለቀስኩት በ ከድር ናፍቆት እንጂ በእሷ አልነበረም። ባለፉት 15 ቀን ውስጥ የተፈጠረውን አንድ አዳዲስ ነገር ማውራት ጀመርን።

ለእየሩስም ከድርን አፍቅሬዋለሁ ብየ ነገርኳት። በዚህ መሀል ይክፍላችን ልጅ የሆነው ሮቤል ንግግሬን ሰምቶ በፌዝ ዘቢባ ፍቅር ያዛት እያለ አወራ። ሙሉ የክላሱ ተማሪዎችም ማፍቀሬን እና ማንን እንዳፈቀርኩ አወቁ።


ከድር መኖሪያ ቤቱ ከትምህርት ቤታችን አጠገብ ስለሆነ ማንነቱን ለማወቅ አልተቸገሩም። እኔና እዩ ወንዶችን የፍቅር ጥያቄ መጠየቃችንን አላቆምንም
የ ስድስተኛ ክፍል ተማሪ የሆነውን ናትናኤልን ለመጠየቅ ወሰንን እና ይሄንን ድርጊት እኔ እንዳደርገው ወስነን ደብዳቤውን ሰጠሁት።

በማግስቱም ጠዋት የመጀመርያ ክፍለጊዜ ላይ እየተማርን እንዳለ የክፍል ሀላፊዬ የክፍልን በር አንኳኳ እናም ስሜን ጠርቶ ቢሮ እንደምፈለግ ነገረኝ።
....... እኔም ምክንያቱን ባላቅም ወደ መምህራን ቢሮ አመራሁ። ሁሉም ክፍለጊዜ የሌለው አስተማሪ ተደርድሮ ቁመዋል። በተጨማሪም ናትናኤል እና አባቱም አሉ። ጉዳዩ ግራ ገባኝ የጠረጠርኩት ነገር አልነበረም።


ዳይሬክተራችን ነገ ወላጅ ይዘሽ እንድትመጪ አሁን ቦርሳሽን ይዘሽ ወደ ቤትሽ ሂጂ አለኝ። ምክንያቱ ሊገባኝ አልቻለም።
....... እንዴ ለምን?? ምን አጠፍሁ ቲቸር??? እባክህ እያልኩ ለመንኩት
.......ዳይሬክተሩም እንዳንቺ አይነት ባለጌ ተማሪ አንፈልግም ብሎ እየገፈታተረ ከቢሮ አስወጣኝ....

Part 7⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል
Comment 👉 @Halaltube_bot

Join👇👇
@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

#የሕይወት__ምግብ__ተስፋ___ነው! ✔
♨"በሕይወት ያለ ሰው ሁሉ #ተስፋ አለው።

♨ የተደናቀፈና የወደቀም ሁሉ ወድቆ አይቀርም።

♨የተራበም ሁሉ ተርቦ አይቀርም።

♨ ያዘነም ሁሉ አዝኖ አይቀርም።

♨የታመመ ሁሉ ይሞታል ማለት አይደለም።

♨ከህመሙ ማገገሙ አይቀርም። በህይወት እስካለን ድረስ ሁሉም ነገር ጊዜውን ጠብቆ ካሰብነው በተሻለ ሆኖ እናገኘዋለን።

⭐️ብቻ በማንኛውም ቦታ፣ ሰአትና ጊዜ ተስፋ መቁረጥ የለብንም፤

⭐️የዛሬው መጥፎ አጋጣሚ ነገ ለበጎ ነው..ብሎ ማሰብ መልካም ነው!

⭐️አንተ ጠንካራ ከሆንክና ተስፋ ካልቆረጥክ፣ ትእግስት ካለህ ..ሁሉም ነገር የተሻለ ሆኖ ታገኘዋለህ።

♨የሕይወት ምግብ ተስፋ ነው! ስለዚህ እስትንፋሳችን እስካለ ድረስ ተስፋ አንቁረጥ! ተስፋ ካለህ፣ ጠንካራና ትእግስተኛ ከሆንክ፣ ሀይማኖትህን አክባሪ፣ ሀገር ወዳድ፣ ሰውን ከልብህ አፍቃሪ፣ ታታሪ፣ ምቀኝነት - ሴረኝነትና ሸረኝነት ከሌለብህ፣ የሰው ማግኘት የሚያስደስትህ - የሰው ሀዘን የሚያሳዝንህ፣ ውስጥህ ቅን ከሆነ...እመነኝ - ቢዘገይም ነገ መልካም ነገር ታገኛለህ! ብቻ ዋናው ነገር ጤና!!!

〰〰〰⭐️ ጤና አላህ ስለሰጠህ አልሀምዱሊላህ በል...ለወደፊትም ኢንሻ አላህ አላህ ያሳካዋል በል፡፡

         
            
   
  T..➳ telegram.me/Halal_tube_official
✔️〰〰〰〰✔️〰〰〰〰〰✔️

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

ለጥያቄው መልስ

ሀ በመካ86 በመዲን 28

👏👏ማሻአላህ👏👏

@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ #የመጨረሻ_ክፍል

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን



አመቱ አለቀ 12ተኛ ክፍል ገባን።ትምህርት በጀመርንበት 15 ቀን ሰአዳን የትምህርት ቤታችን በር ጋር ነጠላ ለብሳ ቆማ እኔኑ ስትጠብቀኝ አየኋት።


በድርጊትዋ በጣም ስለተናደድኩ ላናግራት አልፈለኩም ዝም ብያት ባላየ ሸምጥቻት አለፍኩ።ዘይባ ዘቦ አናግሪኝ አንዴ ዘይባ እያለች ስትከተለኝ አላስችል ብሎኝ ዞሬ ምነው ችግር አለ?? አልኳት አይኗን ማየት አስጠልቶኝ መሬት መሬቱን እያየሁ።
.....እሷም አፉ በይኝ በአላህ አፉ በይኝ እያለች አንገቴ ስር ተወሸቀች።
.....እኔም መስቀል ገድግዶ ነጠላ ለብሶ ሂጃብ አውልቆ አፉ በይኝ አይከብድም? አልኳት።
.....ሰአዳም እባክሽ አሁን አትውቀሺኝ ይቅርታ ልጠይቅሽ ነው ብሩክን ቤተክርስትያን ነኝ ብዬው የወጣሁት አለችኝ። እኔ ይቅርታ ባደርግልሽም ባላደርግልሽም ችግር የለውም ችግሩ አላህ ጋር ነው ይቅርታ መጠየቅ ያለብሽ አላህን ነው አልኳት።
....ልጄስ?? አለችኝ
.....ልጅሽ ምን ሆነ ስል ጠየኳት?
......ብሩክን ከተውኩት ልጄ ማን ያሳድግልኛል?? አለች።
.....እኔም አንቺ ወደ እስልምና የመመለስ ፍላጎት ካለሽ አንጥፈን እየለመንም ቢሆን ሊላህ ወረሱል በሉን እያልንም ቢሆን ልጁን እናሳድገዋለን አያትሽም አሉ አብሽሪ አንቺ ብቻ ወስኚ አልኳት።
....ያለምንም ማቅማማት ተስማማች።እዛችው ቦታ ላይ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለን ስላሳለፈቸው ታሪክ ሁሉንም ነገር አጫወተችኝ። ብሩክ ውጪ በወጣች ቁጥር ሌላ ወንድ ጋር ሄደሽ ነው እያለ እንደሚጠረጥራት እና እንደሚደበድባት ነገረችኝ። ነገር ግን እስዋ ከዛ ሱስ ሙሉ ለሙሉ ወጥታለች ማጨስም መቃምም ብሩክን ፍራቻ አቁማለች።እሱ ግን እዛ ቤት ይመላለሳል።ከሌላ ሴት ጋር ተኝቶ እጅ ከፍንጅ እንደያዘችውም ነገረችኝ።
.....ለምን እዚህ ምን ትሰራለህ?? እንዴት ይሄን ታደርጋለህ ??ባለችው ጊዜም
..... አንቺን ያገኘሁሽ ይሄን ስትሰሪ አይደለም ወይ ምን እራስሽን እንደ ጨዋ ታያለሽ ብሎ እንዳሸማቀቃት እያነባች እያለቀሰች ነገረችኝ።አንዳንዴም አድሮ እንደሚገባ ሴት ይዞ መቶ አልጋዋ ላይም እንደሚተኛ ስትነግረኝ አብሬያት አለቀስኩ። ከዚህ ሰውዬ እንደማድናት ለራሴ ቃል ገባሁ። ንግግራችንን በመቋጨት ላይ እንዳለን ብሩክ መጣ።
......ቤተክርስትያን ነኝ ያልሽኝ ከዚች ጋር ለማውራት ነው ብሎ መደብደብ ጀመረ።
.....ሰአዳ እመቤቴን ቤተክርስትያን ነበርኩ አሁን ነው ያገኘኋት እያለች እያለቀሰች ትማፀነው ጀመር።
.....እሱ ምክንያትዋን አይሰማም ዝም ብሎ ይደበድባታል ይጎትታታል።እስከዛሬ ድረስ ያሳለፈችውን ሂወት ሳስብ ይበልጥ አሳዘነችኝ። ከነ ሀዩ ጋር እና ዘቦንም ጨምረን ሂወቷን ለመታደግ ቆርጠን ተነሳን ሀያትዋ ጋር ሄደን ስልክ ቁጥርዋን እና የመኖርያ አድራሻዋን ተቀበልን።ወደ ቤትዋም ሄደን ልብስዋን እና ልጅዋን ይዘን አያትዋ ቤት ወሰድናት።አያትዋም በደስታ ተቀበሉን

.....ትግስት አልፎ አልፎ እየደወለች ትጠይቀኛለች። ስራ እንዳላገኘች እና ቤት መዋል እንደሰለቻት ታጫውተኛለች።
እኔ ለልብስ መግዣ ተብሎ የተሰጠኝን 1000 ብር ሀዩ ቦርሳ መግዣ ብላ ያስቀመጠችውን 500 ብር ዚነት ከትምህርት በኋላ ስራ ስለምትሰራ ያገኘችውን 1000 ብር ሌላኛዋም ሀዩ ለቤተሰብዋ ታሪኩን ተናግራ የተቀበለችውን 2000 ብር በድምሩ 4500 ብር ለ ሰአዳ ለጊዜው ማቋቋሚያ እንዲሆናት ብለን ሰጠናት።

....እንደዛ እያልን ያለንን እያካፈልናት ብዙ ጊዜ ካሳለፍን በኋላ የራስዋ ስራ መስራት ጀመረች የኛንም እርዳታ እንደማትፈልግ ከምስጋና ጋር ነገረችን።


አንድ ቀን በማላውቀው ስልክ ተደወለልኝ ሄሎ! ሄሎ! አሰላሙ አለይኩም!
....... ወአለይኩም ሰላም ማን ልበል? ሴት ናት ድምፅዋ አዲስ አልሆነብኝም።
.....ፍርዶስ ነኝ ዘቦ አለችኝ።
......ፍርዶስ? አላወኩሽም አልኳት
........ውይ ይቅርታ ትግስት ማለቴ ነው አለችኝ።ግራ ተጋባሁ ትግስቴ እንዴት ነሽ ብዬ ሞቅ ያለ ሰላምታ ከሰጠኋት በኋላ ቅድም ግን ምንድነው ፊርዶስ ምናምን ያልሽኝ አልኳት
...... እስዋም ስሜ ፍርዶስ ሁኗል ሙስሊም ሆኛለሁ የጠፋሁብሽ ቁርአን ለመቅራት አዳሪ መርከዝ ስለገባሁ ነው።ኢንሻ አላህ ካሁን በኋላ አልጠፍብሽም እያለች በደስታ እየተፍለቀለቀች ነገረችኝ። ኢስላም ማለት ሰላም ነው ኢስላም ማለት ደስታ ነው።ይሄንን ደሞ ከትግስት(ከፊርዶስ) ተገንዝቤያለው።አልሀምዱሊላህ ትግስት እስልምናን ተቀበለች።

ብሩክ ሰአዳን ይዘናት ወደ ሀያትዋ ቤት የወሰድናት ቀን እዛ ማጨሻው እና መቃሚያው ቤት በመጣው ፀብ ምክንያት በሺሻ እቃ አንዱን ልጅ ጭንቅላቱን መቶት ለሞት ስለዳረገው ለእስር ተዳርጓል። አላህ አሟሟታችንን ያሳምርልን።
ፍርዶስም ጊዜ ሳትፈጅ ፍቅረኛ ምናምን ብላ ሳትጃጃል ወንድምዋ ያመጣላትን ባል አገባች
ከነ ሀዩ ጋ ከተዋወቅን 4 አመት አስቆጠርን።ከ preparatory school ጀምሮ እስከ ዩኒቨርስትይ ድረስ አልተለያየንም።ዘንድሮ የሁለተኛ አመት ተማሪዎች ነን። አላህ ኒያችንን በሀላል መንገድ እንዲያሳካልን ዱአቹ አይለየን።

አደራ አደራ!!!
የተሳሳቱ ሰዎችን መመለስ ባንችል እንኳን የተስተካከሉ ሰዎችን መበላሸት ምክንያት አንሁን
ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ

መጋቢት 10/07/2012
#ተ.......... #ፈ.......... #ፀ......... #መ


ዉድና የተከበራችሁ ቤተሶች ስለ ታሪኩ ያላችሁን አስተያየት በዚህ ላኩልኝ👇👇👇
@Halaltube_bot

@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ ሀያ አንድ 2⃣1⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን


በሌላኛው ቀን ደሞ ትምህርት ቤታችን ላይ ሌላ አስደንጋጭ ዜና ተሰማ
128 የድላችን ተማሪ ሺሻ ቤት እንደተያዘ ተሰማ። ከምንም በላይ የሚገርመው ከ 128ቱ 85ቱ ሙስሊም ተማሪዎች መሆናቸው ነው።ከ85ቱ ደግሞ 50ው ሴቶች ናቸው።
ከተያዙት መካከል መርየም አንዋር እና ሰአዳ እንዲሁም ብሩክ እንዲሆኑ ምኞቴ ነበር።ነገር ግን እነሱ የዛን ቀን ሌላ ቤት እንቀይር ብለው ወተው ስለነበር አልተያዙም።

ወላሂ በሙስሊሙ ተማሪ ብዛት ከልቤ አዘንኩ። የተማሪው ወላጆች እያነቡ የኔ ልጅ እንዲህ አያደርግም ልጄ ከሳምንት ሳምንት ትምህርት ቤት ነው(ናት) ቅዳሜና እሁድም ላይብረሪ ነው ሚያሳልፈው(ምታሳልፈው) እያሉ ወገባቸውን ይዘው ይከራከራሉ። አንዳንዱ ወላጅም በውንጀላ እንከስሀለን እያሉ ዳይሬክተራችን ላይ ይደነፋሉ።


ጁመአ ሳይደርስ አስቸኳይ ሹራ አደረግን ሁሉም አነባ መፍትሄው ምን እንደሆነ ተወያየን ግን የተሻለ ሀሳብ አላመጣንም። ሁሉም አሚር የጥሪ ስራ እንዲሰራ ተወሰነ ግን ለውጥ አልተገኘም። ትውልዱ ቀልቡ ደርቋል መሰለኝ በአንዱ ጆሮው ሰምቶ በአንዱ ጆሮው ያፈሰዋል። መርየምም ከ አንዋር ጋር የፍቅር ጨዋታዋን ቀጥላለች። አንዋር የሀብታም ልጅ ነው በእድሜውም ከኛ ተለቅ ይላል። ዲነኛ ቤተሰብ አለው እሱ ግን እንደምናውቀው። ማጨስ መጠጣት መቃም ስራው ነው


ሁኔታው ያላማራቸው ቤተሰቦቹም ማግባት አለብህ ብለው ወስነው ማትሪክ ሳይፈተን ያንተ መማር ትርጉም የለውም ብለው ትምህርት አስትተውታል። መርየምን እኔ ለማግባት ዝግጁ ነኝ እንጋባ ብትለውም ማግባት የምፈልገው ከነክብርዋ የተቀመጠችን ሴት ነው ንፁህ የሆነች ጋጠወጥ ያልሆነች ቤተሰቦቼ የመረጡልኝን ነው ማገባው ብሎ ቅስሟን ሰባብሮ ጢባጢቤ ተጫውቶ እንደ ሸንኮራ መጦ ቱቱቱ ብሎ ተፍቷቷል።

እስዋም በብስጭት ካገኘችው ወንድ ጋር እየተኛች እየተጃጃለች ትምህርቷን አቋረጠች። ሰአዳም እንደመርየም እንዳትሆን በመስጋት ግልምጫዋን ተጋፍቼ ልመክራት ወሰንኩ። ብሩክ ነገ ይተውሻል አላህ ግን መቼም አይተውሽም ተይ ተመለሺ ስል ተማፀንኳት። ሌላው ቢቀር እኮ እሱ ክርስትያን ነው ስላት... እሰልምልሻለሁ ብሎኛል ብላ አፍ አፌን አለችኝ። የፈለገውን እስኪያገኝ ነው እንደዛ ሚልሽ እንጂ እሱ አይሰልምልሽም ብላትም ልትሰማኝ አልቻለችም።


ማትሪክ ተፈተንን ስልጣንም አስረከብን። ውጤት መጠባበቅ ጀመርን ትግስት፤ ሰአዳ፣ አሚራ፣ብሩክ፣እየሩስ.......ሁሉም ጓደኞቼ ወደቁ እኔና ዘቦ ግን አለፍን

ትግስት ውጤት ባይመጣላትም ቀድሞውኑ እናቴን ማስደሰት አለብኝ የምትፈልገውን ማድረግ አለብኝ ወደ ከሚሴ እሄዳለው ብላ ወስና ስለነበር ውጤቱን እንደሰማች ከእናትዋ ጋር ወደ ከሚሴ ወደ ታላቅ ወንድምዋ አማር ቤት ተጓዙ። ከሚሴ እንደደረሱም ደውላ በእግዚአብሄር ፍቃድ በሰላም ገብተናል አትጨነቂ አለችኝ።


ትምህርት ቤታችን የሚመድበው አዲስ ከተማ የተባለ ትምህርት ቤት ቢሆንም በኛ ጊዜ እራሱ ትምህርት ቤቱ ወደ preparatory school ስለተቀየረ እዛው እንድንቀጥል ሆነ።እናም እኔ መሆን የምፈልገው አዋላጅ ዶክተር ስለነበር naturale science ገባሁ ዘቦ ጠበቃ መሆን ስለምትፈልግ social science ገባች።

ሰአዳ ጅልባብ ለብሳ አይቻታለው በዚህም ተደስቻለው መርየም በ አንዋር በደል ተጎሳቁላ እራስዋን መጠበቅ ባለመቻልዋ አብረዋት እያደሩ ብር የሚሰጡአት ወንዶችም ርቀዋት የቤት ኪራይ መክፈል አቅቷቷል ።አከራዮቹም ለብዙ ወራት ባለመክፈልዋ አባረዋት ጎዳና ወጥታለች።

Part 2⃣2⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል

@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ አስራ ዘጠኝ 1⃣9⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን


መፅሀፉንም ከቦርሳዬ አውጥቼ በእጄ እንደያዝኩ የሆነ ድምፅ ተሰማኝ
እእእእእእእ እእእእእ ቀስ.....ቀስ.... እእእእእእ የሚል የሴት ድምፅ።ፅው ፅው ፅው የሚለው ትቦ ውስጥ የሚኖሩት አይጦች ልፍያ ድምፅም መሰለኝ። ከክፍላችን ጣራ ላይ ያለው ክፍል ተማሪዎች እርግጫም መሰለኝ ብቻ አላወኩትም ወደ ኋላ ለመዞር አንገቴ አልዞር አለኝ ፈራሁ። አንዳች ነገር በ ፊልም እንደምናየው ሆረር የሚሉት ነገር የመጣብኝ መሰለኝ።

አንገቴን ሸርተት ባደረኩ ቁጥር ገና ከመዘሮ በጥፊ የሚደረግምብኝ ሰው ያለም መሰለኝ ብቻ እንደምንም ዞርኩ ዴስኩ ላይ ምንም አይታይም የሰው ዘር የለም።ሶስት ጊዜ አኡዙቢላህ አኡዙ ቢላህ አልኩ።ድምፁ ግን አሁንም አለ። የጥግ ወንበር ስር ወደ መሬት ስመለከት እንደ እንስሳ የሚንከባለሉ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ተማሪ ተመለከትኩ። ሰአዳ እና ብሩክ ...ያየሁትን ማመን አቃተኝ እውነት መሆኑን ላለማመን አይኔን ውሸት ነው ቅዠት ነው እያልኩ ልደልለው ሞከርኩ ግን አልቻልኩም እውነትን መደበቅ አይቻልማ!!! የእግሬ ኮቴን እንኳን መስማት እስኪሳናቸው በር ሰው ይመጣ ይሆናል ብለው እንኳን ማሰብ እስኪሳናቸው ድረስ በስሜት ጦዘዋል እንባዬ ከጎንጬ ተንቆረቆረ እያዞረኝ ከክፍሉ ድምፅ ሳላሰማ ወጣሁ።

በማግስቱም ለማንም ሳልናገር ሰአዳን ልመክራት ወሰንኩ እናም እፈልግሻለሁ ብያት ትናንት ስለሰራችዉ ስራ አናገርኳት
.... እስዋም ግን ምነው አንቺ ድንግል ነኝ ማለትሽ ነው? አታስቂኝ የኛ ገሀድ ስለወጣ ነው እንዴ ሁልሽም እናቅሻለን አንገት ደፊ ሀገር አጥፊ የናንተንስ ማን አየላቹ? ስንቱን የቤት ልጅ የተባሉ አይደል እንዴ እዛ ምናየው ብላኝ ሄደች

የሰአዲ እንዲህ መበላሸት በጣም ነው የገረመኝ አሳዝኖኛልም ጭምር። የስዋ ብቻ አይደለም የሁሉም ሙስሊም ተማሪዎች መበላሸትም እረፍት ነስቶኛል። አንድ ቀን ለት ጥዋት ሰልፍ ላይ ዳይሬክተራችን አጭር መልእክት አስተላለፈ እያንዳንዱን ጥጋበኛ ለቅመን እናባርራለን ሲል ፎከረ።ንግግሩ ከተማረ ሰው አይጠበቅም። ሁሌም ጋጠወጥ ንግግር ይናገራል።

ሳዲቅ የሚባል ልጅ ያለ ጥፍቱ አባሮታል።ምን ሆነ መሰላችሁ ሳዲቅ ሁሉም ተማሪ እንደሚያደርገው አስተማሪ እስኪመጣ ድረስ በርጋ ቆሞ እንዳለ ዳይሬክተራችን ደረሰበት ከዛም
ዳይሬክተሩ፦ አስተማሪ የለም?
ሳዲቅ፦-... አው
ዳይሬክተሩ፦...እና እንደሸሌ(ሴተኛ አዳሪ) በር ጋር ምን ትሰራለህ?
ሳዲቅ፦...ምነው ሄደህ ታውቃለህ እንዴ?

በማለቱ ነበር የተባረረው።ለ3 አመት የትኛውም ትምህርት ባት እንዳይማርም ታግዷል። በእርግጥ ሳዲቅም ጥፋት አለበት የዳይሬክተሩ ግን ይብሳል።

አንዲት ተማሪም ተኳኩላ ሊፒስቲክዋን ተቀብታ ሽቶዋን ነስንሳ ሲያያት ምነው ከሽርሙጥናው ቤት ነግቶብሽ ነው እንዴ የመጣሽው ብሎ አባሯት እናትዋ መታ ልጄን እንዴት እንዲ ትናገራታለህ?? ባለችው ጊዜ ሽርሙጥና እንድትሰራ መንገድ የከፈትሽላት አንቺ ነሽ ማለት ነው ብሎ ተናግሯት አገር ጉድ ብሏል።
ነገሩ የገባን በኋላ ላይ ነበር።ለካ የሴቶች ሽንት ቤት ኮርኒስ ውስጥ ተደብቀው የሚያጨሱት ተማሪዎች ተይዘው ተባረው ነው ሲደነፋ የነበረው።


የተያዙት ተማሪዎች ደግመው ድላችን ትምህርት ቤት መማር እንዳይችሉ ታግደው ተባረሩ። የሽንት ቤቱ ኮርኒስ እና የወንዶች እና የሴቶች ሽንት ቤት ማገናኛ ያደረጉት ያፈረሱት ግንብም እድሳት ተደረገለት። እኛም በጣም ቁጥጥር በዛብን። ለጥቂት ወራት እስኪረጋጋ ድረስ ምሳ ሰአታችንን ወደቤት ወይም ወደ መስጊድ እንዳንሄድ ተደረግን ሁሉም ተማሪ ትምህርት ቤት መዋል ጀመረ።በነዚህ ተማሪዎች ምክንያት ለብዙ ወራት ትምህርት ቤቱ መነጋገሪያ ርእስ ሆኖ ነበር።

በየተኬደበት የሚወራው ድላችን የሚባለው ትምህርት ቤት እኮ አሺሽ ሲያጨሱ ተማሪዎችን ያዘ የሚል ወሬ ነበር የሚሰማው።ብዙ ወላጆችም ልጆቻቸውን ከዛ ትምህርት ቤት አስወጥተው ወደ ሌላ ትምህርት ቤት አዘዋውረዋል...


#Part 2⃣0⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል

Join👇👇

@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

"በሰለዋት የደመቀ የፍቅር ጁምዐ ይሁንልን❣
❤️የታመሙት የሚድኑበት
የታሰሩት የሚፈቱበት
ያፈቀሩ የሚዘወጁበት
ሀጃ ያለበት ሁሉ የሚሳካለት
🤲 ጁምዓ ይሁንልን 🤲

አሚንን

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ አስራ ስድስት 1⃣6⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን



የአባትዋ ሞት ተከትሎ ወንድምዋ እናቱን እና ብቸኛ እህቱን ትግስትን ለመውሰድ ወደ አዲስ አበባ መጥቷል
ነገር ግን ትግስት ወደ ከሚሴ የመሄድ ሀሳብም ፍላጎትም አልነበራትም ከናንተ ጋር መኖር አልፈልግም ከሀዲዎች ናቹ የአባቴ ሞት ተጠቀማቹበት። አልወዳችሁም እያለች ብትጮህባቸውም እነሱ ሊተዋት አልቻሉም።በተለይ እናትዋ ዘይነባን እስከዛሬ ድረስ አባቴን ስትደልዪ ኖረሻል አፈቅርሀለው ብለሽ አታለሽዋል አባቴን ክደሽዋል ገና ከመሞቱ ሙስሊም ሆንሽ እያለች ነጋ ጠባ ትሰድባታለች።

ወንድሟም ወደ ከሚሴ ልውሰዳቹ ትምህርትሽን እዛ መቀጠል ትችያለሽ አሪፍ ሀገር ነው ለሙስሊምም ለክርስትያንም የሚሆን ሀገር ነው።ሁሉ ነገር አስተካክያለው የራሴንም ቤት ገዝቻለው ቢላትም አሻፈረኝ አላችው።


ትምህርት በጀመርንበት ወር አዲስ ለገቡት ለዘጠነኛ ክፍሎች የ well come ( የ እንኳን ደህና መጣቹ ) ፕሮግራም አዘጋጀን። well come ፕሮግራም አላማው ለአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ ጀመአውን እና የመስገጃው ቤት ማስተዋወቅ ነው። ያለንን አዋጥተን ኩኪስ እና ለስላሳ እንዲሁም ቴምር ገዝተን የ ዌልካም ፕሮግራሙን አዘጋጀን። አልሀምዱሊላህ ብዙ ተማሪዎች ተገኝተዋል።ትግስትንም የተለየ ነገር የለውም ብለን አባብለን ወደ ጀመአው ወሰድናት። ብቸኛዋ ሂጃብ ያለበሰች ሴት ስለነበረች የተማሪዎቹ አይን ቢያስፈራትም ተቋቁማው ፕሮግራሙን ከኛ እኩል ተካፍላለች። ሀዲስ ከሰማን በኋላ የጀመአው ጄነራል አሚር አቡበከር ትንሽ ንግግር አድርጎ ፕሮግራሙ ተቋጨ።

እኔና ዘቦም የጀመአው (የዳእዋ) ጥርያችንን እያቀላጠፍን ነው።በየክፍሉ እየዞርን የማይሰግዱትን ተማሪዎች እንዲሰግዱ የጀመአውን ቤት የማያውቁትን እያሳየን ጥሪ እናስተላልፍለን። ሂክማ(የፍይናንስ ዘትፍ አሚር) ለጀሙአው እርዳታ የሚያደርግ ሰው ልታገኝ ባለመቻልዋ አዝናለች። የምታውዋቸው የጠየቀቻቸው ሀብታም ናቸው ያለቻቸው ሰዎች ነገ ነይ ሳምንት ነይ እያሉ ያመላልሱዋታል እንጂ አይስጥዋትም።እኔም ላግዛት በማሰብ የማውቃቸውን ሰዎች ስጠይቅ አንዴ ደብዳቤ ፃፊ ይሉኛል ደብዳቤውን ፅፌ ስመለስ ደሞ ማህተም የለውም ይሄ የውሸት ጀመአ ነው ይሉኛል።

እኛ ደሞ ጀመአችን ከትምህርት ቤቱ እውቅና ውጪ ስለሆነ በትምህርት ቤቱ ስም ማህተም መጠቀም አንችልም። የሂክማ ስራ ከባድ እንደሆነ ስሰራው ነው የተረዳሁት። ግን ወላሂ ከሁሉም ስራ ተማሪን ወደ ጀመአው መጥራት ይከብዳል።ከ ሀ እስከ ፐ ማንነታችንን ያውቃሉ። እነዚህ ጨቅጫቃዎች መጡ እያሉ ይጠሩናል።አሰላሙ አለይኩም ስንላቸው የሚያፌዙብን ሴቶች ቁጥራቸው ብዙ ነው።ወአለይኩም ሰላም ከማለት ወአለይኩም ኩርኩም እያሉ ያላግጡብናል።አንዳንዶቹም ሰላም ይንሳቹ ሳይሉን አይቀሩም። አስተያየታቸው ግልምጫቸው ተስፋ ያስቆርጣል ሆኖም ግን የተሰጠን ሀላፊነት ከባድ ስለሆነ ፊታቸው እየገረፈን እየተመላለስን እንዲሰግዱ እንማፀናለን። እሺ ኢንሻ አላህ ነገ እመጣለሁ፤ሀይድ ላይ ነኝ፤ወደ ቤት ልሄድ ነው ፤እዚህ ነው የምሰግደው .......እያሉ የሚዋሹን ብዙዎች ናቸው።

የጊቢው ሰቃይ ተማሪም ሙስሊም ናት ሀናን ትባላለች። ውሎዋ ጊቢ ውስጥ ነው።ሶላት እንድትሰግድ ጥሪ ባደረግንላት ጊዜም እኔ ከትምህርት ከወጣሁ በኋላ ቤቴ ነው የምሰግደው አለችን።ከዚህ እስክትሄጂ አሱር ያዝናል እኮ ለምን እዚህ ከኛጋ አትሰግጂም ??ስንላት
..... እኔ ቀስሬ ነው ምሰግደው ምሳ ሰአቴን ላይብረሪ ነው ማሳልፈው ብላ በፈጣጣ መልሳልናለች።ከኛ ድክመት ይሁን ከተማሪው ስንፈት ባላውቅም ከለት ወደየ እለት ጀመአው ቤት እየሄዱ የሚሰግዱት ሴቶች ቁጥር በጣም ቀንሷል። ቤቱ ጠቦን ምንሰግድበት ቦታ አጥተን ለሁለት ጀመአ ተከፋፍለን በየተራ እንዳልሰገድን አሁን አሁን ቤቱም እየሞላ አይደለም።እንዳውም አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰልፍ ሰጋጆች ብቻ የሚኖሩበት ጊዜ አለ። ወላሂ እኛ የጀመአው አባላት ወደዛች ቤት ለመሄድ ምክንያት አንፈልግም ነበር ጁምአ ጁመአ ቅዳሜ እና እሁድ አልፎ ሰኞ እስኪደርስ እንጓጓለን። እርስ በራሳችን እንዋደዳለን ። ሀይድ ላይ ብንሆንም ባንሆንም ወደዛች ቤት መሄዳችንን አናቆምም ይናፍቀናል።

ምሳ የያዝን ምሳችንን ካልያዙት ጋር ተካፍለን ነው የምንበላው። ከ እህትማማቾች በላይ ነው ፍቅራችን።አንዳንዶቹ እዛች ቤት ላለመሄድ ስበብ ይደረድራሉ። ሰአዳም እንዲህ እንዲህ እያለች ነው የጀመአው ቤት መሄድ ያቆመችው። ውሎዋ ከነ እየሩስ እና ትግስት ጋር ነው። አሚራ ድሮውንም የምትሰግደው ቤትዋ ነው።በነገራችን ላይ 10 ክፍል ከገባሁ በኋላ አንዲት አዲስ ልጅ ክፍላችን ገብታለች መርየም ትባላለች ሲበዛ እብድ ናት።

#Part 1⃣7⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል

Join👇👇
@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ አስራ አራት 1⃣4⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን

በመስለሙ ምክንያት ትግስትም በጣም ስለተበሳጨች ስሙን እንኳን መጥራት አትፈልግም።

ጀመአችን በራሱ መዋጮ የሚያስተዳድራቸው 30 የቲም ልጆች አሉት።ልብስ እና ዩኒፎርም እንዲሁም ደብተር የመሳሰሉትን ይሸፍንላቸዋል። አሚሮቹ በአጠቃላይ የ 10ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው እኛ ደግሞ ቀጣይ ስልጣን የምንይዘው እኛ ስለሆንን የሴቶች አሚር የሆነችው ሀናን ሁል ጊዜ .......አደራ አደራ እኛን አይቶ የሚበላሽ ብዙ ሰው ስላለ ቅድሚያ እራሳችንን እናስተካክል የዘንድሮ ዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች በጣም ትንንሽ ናችሁ ከናንተ በኋላ የሚመጡት ደግሞ ይበልጥ ትንንሾች ናቸው እኛን እያዩ ክፍት እና ብልግና እንዳይማሩ እያለች ትመክረናለች።

ይሄ ንግግርዋ ዳይሬክተራችንም ሲናገር ሰምቼዋለው የዘንድሮ ተማሮዎች በጣም ልጆች ናችሁ በዛውም ልክ ጋጠወጥ ናቹ አልበሰላቹም ከናንተ በኋላ የሚመጡትም እናንተን እያዩ ነው የሚማሩት ጥሩ ከሆናቹ ጥሩ ይሆናሉ መጥፎ ከሆናቹም መጥፎ ይሆናሉ ብሎ ሲጨቃጨቅ ሰምቼዋለው።
የጀመአው አሚሮች ተማሪውን ወደ ጀመአው ለመጥራት በጣም ይደክማሉ። ጊቢው ውስጥ እየዋሉ ሰላት ሳይሰግዱ የሚውሉ ብዙዎች ናቸው። ይሄንን ለመቅረፍ በየክፍሉ እየዞሩ ምክር ይሰጣሉ።አንዳንዶቹም መጡ ደግሞ እያሉ እንደጠላት ሲያዩቸው ተመልክቻለው እኛ ክፍልም ብዙ ተማሪዎች እንዳያዩያቸው ብለው ሲደበቁ ተመልክቻለው። ትምህርት ቤቱ ስመ ገናና ስለሆነ ቁጥጥር ያበዛሉ።

ቤቴ ቅርብ ቢሆንም ልምድ ሆኖብኝ ሳላረፍድ ክፍል ገብቼ አላውቅም። ሪከርድ ተይዞብኝ ተባርሬ ሳምት ከተቀጣሁ በኋላ ወላጅ አምጥቼ ምህረት ተደርጎልኝ ተመልሻለው። ያው የልምድ ነገር አይለቅም አይደል የሚባለው? ማርፈዴን አላቆምኩም። ጊቢው እጅግ በጣም ሰፊ ስለሆነ ከአንዱ በር ወደ ሌላኛው በር ለመጓዝ 20 ደቂቃ ያክል ይፈጃል። ዳይሬክተራችንም ወላጅ ማስመጣት እና ማባረር ስለሰለቸው እኔን የሚቀጣኝ በአንዱ በር ወተሽ በአንድኛው በር ተመለሺ ብሎ ነው። በአንዱ በር ወቶ በሌላኛው መመለስ ከ 25 እስከ 30 ደቂቃ ይፈጃል። ይሄ የለት ተእለት ተግባሬ ሆኖዋል። ለመድከት መሰለኝ ቅጣቱም አይከብደኝም።

ትምህርት ቤቱን ለምጄዋለው በጣም ወድጄዋለው። ትብብራቸው ደስ ይላል። አንድ ተማሪ ቀርቶ መምህሩ አቴንዳንስ ሲይዝ ሌላኛው ተማሪ የጓደኛቸውን ድምፅ አስመስለው አቤት ይላሉ።አስተማሪውም ሳይነቃ መምጣቱን ራይት በማድረግ ይመሰክራል። ፈተናም ስንፈተን የቀረ ተማሪ ካለ በሱ ስም ተፈትነው ከራሳቸው ጋር ደባልቀው ይሰጡታል። አስተማሪውም ሳይነቃ አርሞ ይመልሳል። አንድ ተማሪም ያለ ጥፍቱ አስተማሪ ሲመታው ካዩ አስተማሪውን ለማስቆም ሁሉም ተማሪ ከተቀመጠበት ተነስቶ ይጮሀል ያምፃል።
አመቱ ማብቂያ ደረሰ ምኑንም ለይቼ ሳላውቀው ግንቦት ወር መጨረሻ ደረሰ።በዚህም ወር ሁሉንም የጊቢው ማለትም የትምህርት ቤቱ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ ተጠርተው ሁሉንም ያካተተ በጀመአው ቤት ሹራ ተደረገ።...

Part 1⃣5⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል

@HALAL_TUBE_OFFICIAL

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

✨የሱመያ ሰማዕት መሆን✨

ሱመያ(ረ.ዐ) የአማር እናት ነበረች። ልክ እንደ ልጇ አማርና ባልተቤትዋ ያሲር በኢስላም ጎዳና በተለያዩ ቅርፆች የተቃጡባትን ችግሮች በትዕግስት ተቀብላለች። ያን ሁሉ ስቃይ ብትቀበልም ለኢስላም ያላትን ፍቅርና ታማኝነት አልቀነሰችም።አንድ ቀን ሱመያን(ረ.ዐ) እና ባልተቤትዋን(ያሲር) አቡጀህልየፍጥኝ አስሮ አሰቃየችው።በመጥፎ ቃለት ይሰድባትም ጀመር።ከዚያም በጦሩ ሀፍረተ ገላዋን ወጋት።ሞተች።በነብዩ ሙሀመድ(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የትግል ህይወት ታሪክ በአላህ መንገድ ላይ ሰመአት ከሆኑት የመጀመሪያዋ ሱመያ(ረ.ዐ) ነች።

በእውነቱ የእነዚህ ሴቶች ትዕግስትና መስዋዕትነት የሚያስቀና ነው።አንድ በኢስላም መንፈስ የተባረከ ሰው ለመቀበል የቆረጠው ማንኛውም አይነት ስቃይ የማይቻል አይሆንም ።በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ለተለያዩ ዓላማዎች እንደሚሞቱ እንሰማለን።ለአላህ ብሎ መሞት ብቻ ነው ዘላቂ ደስታና ለመጪው አለምም ተድላ የሚያጎናጽፈው።ቁሳዊ ጥቅም ለማግኘት ህይወታቸውን የሚያጡ በእርግጥ ከሳሪዎች ናቸው---በዚህም አለምም ሆነ በመጪው ።

@Halal_Tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ አስራ አንድ 1⃣1⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን


ሚኒስትሪ ልንፈተን 2 ወራት ብቻ ቀርተውናል።ከድሬ ሳናግረው ይሸሸኛል። ያቺን የለመድኳት ፍቅሬን የምታሳየኝ ፖልም ብቻዋን ተገትራ ነው የማገኛት። አንዳንዴም እኔ በተራዬ ድንገት ከመጣ ብዬ ፖሉን ተደግፌ እቆማለው። እየሩስ ይሄ ተግባሬ ያናድዳታል ። ወንድ ልጅ ኮራ ስትይበት ነው የሚወደው ትለኛለች። አብረን እንድንተኛ እንደጠየቀኝ ግን አልነገርኳትም። ናፍቆቱ ሲበረታብኝ አላስችል ብሎኝ ነገርኳት።
.....እዩ መፍትሄ ብዙ ናት ምክንያት ሰበብ እና ዘዴ አታጣም።ሁል ጊዜ እስዋ ጋር የችግር ቁልፍ አለ። አሁን ግን ለኔ ምንም ልታገኝልኝ አልቻለችም።ገና በዚ እድሜሽ ሴክስ ከጀመርሽ መጨረሻሽ ሴተኛ አዳሪ ነው የምትሆኚው እውነት የሚያፈቅርሽ ከሆነ በራሱ ጊዜ ይታረቅሻል የማያፈቅርሽ ከሆነ ግን ብትርቂው ነው የሚሻልሽ ለስሜቴ ነው ማለት ነው ሚፈልግሽ ብላ ተስፍ አስቆረጠችኝ።
.....ያፈቀረ እና ያበደ አንድ ነው አይደል የሚባለው ንግግርዋን ከምንም አልቆጠርኩትም ። እንደተለመደው ከትምርህት ቤት ወጥተን ወደ መድረሳ ስሄድ ከድሬ ፖሉን ተደግፎ ቆሞ ጠበቀኝ። ሳላቅማማ ወደርሱ አመራሁ። ናፍቀከኛል ለምን ጠፋህብኝ?? ስልክስ ለምንድነው የማታነሳው ??በተለያየ ስልክ ደውዬልሀለው ግን አታነሳም አልኩት።
.....እሱም ንግግሬን ካዳመጠ በኋላ ወደ ገደለዉ እንግባ የጠየኩሽን ምን ወሰንሽ ??አለኝ
.......ማለት አልገባኝም ??አልኩት
.......ባለፈዉ የጠየኩሽን ፍቃደኛ ነሽ አይደለሽም ???ብሎ ጠየቀኝ
......ምንም የተለወጠ ነገር እንደሌለ በባለፈዉ አቋሜ እንደሆንኩ ነገርኩት።
....ከድር ጥሎኝ ወደቤቱ ገባ። እዛው ፖሉ ጋር ሆኜ አነባሁ።ያየኝ ሁሉ ሰዉ ምን ሆንሽ ልጄ የምታለቅሽዉ?? እያለ ይጠይቁኛል።
....እየሩስም እንባዬን ጠራርጋ ተነሽ በቃ ዛሬ መድረሳ ይቅርብሽ ወደቤት እንሂድ በጌታ እያለች ለመነችኝ
......ግን አይሆንም አላህ ፊት ቆሜ ማንባት ነው የምፈልገው ሂጅልኝ ብዬ ትቻት ወደ መድረሳ ሄድኩ። ግን አላህ ያለው መድረሳ ብቻ ነው እንዴ? አይ ልጅነት ይገርማል ንግግር እንኳን አናውቅም።

መድረሳ ሄጄ ቁርዐኔን ከፍቼ እየቀራሁ አነባሁ።እንባዬ ቁርዐኔን አርሶ አበላሸብኝ።
......ኡስታዛም ምን ነክቶሽ ነው አይዞሽ እያለች አባበለችኝ። የሆንኩትን ለማንም ሳልናገር ወደ ቤቴ ሄድኩ። ከዛም መግሪብ ከሰገድኩ በኋላ እራቴን ሳልበላ መስገጃዬ ላይ ቁጭ ብዬ የሙሀመድ አወል ሳላህን መስገጃሽ ላይ ታገሺ የሚለውን ነሺዳ እየሰማሁ እያነባሁ እንባዬንም እየጠረኩ ኢሻ እስኪያዝን ጠበኩ። ኢሻም አዛን ካለ በኋላ ሰላቴን ሰግጄ ዱአ አደረኩ። ከዛም አላህዬ ከድር የወደፊት አጋሬ ነው አይደለም? ለኔ ሀላሌ ነው አላህዬ? አሁን ምንም ብናደርግ ችግር የለውም? አላህዬ አሳውቀኝ እያልኩ አፍ እንዳልፈታ ህፃን ልጅ እየተንተባተብኩ ዱአዬን ጨርሼ ሰላተል እስቲሀራ ሰግጄ ስለከድሬ የሆነ ነገር እንዲያሳየኝ ለምኜ ተኛሁ።

ግን አላህ ምንም ያሳየኝ ነገር አልነበረም። በማግስቱም ሱብሂ ከሰገድኩ በኋላ አልፎም አላህዬ እሺ ከድር ለኔ የማይሆን ከሆነ ከልቤ አውጣልኝ ከዚህ ስሜት አስወጣኝ ብዬ ተንሰቅስቄ አለቀስኩ። ያለወትሮዬ ሰላቴን በሰአቱ መስገድ ጀመርኩ በዱአም በረታሁ። ባላሰብኩት ፍጥነት ከከድር መራቅ እንዳለብኝ ልቤ ተሰማው። ከዛሬ ጀምሮ ከድሬን ላለማናገር እና በፍቅር ላለማሰብ ወሰንኩ ።ከዛም ቀን ጀምሮ ፖሉን ተደግፎ ቆሞ ሲጠብቀኝ ባይም ባላየ ማለፍ ጀመርኩ። አልፎ ሲናፍቀኝ አይኔን አጣምሜ ሰርቄ አየዋለው ግን አላናግረውም።


የሚኒስትሪ ፈተና ከወሰድን አንድ ወር አለፈን። የሚኒስትሪ ውጤት ተለቀቀ የሚል የሀሰት ወሬ ብዙ ጊዜ ይሰራጭ ስለነበር በሰማን ቁጥር ለማረጋገጥ እኔና እዩ ትምህርት ቤት እንሄድ ነበር። አንድ ቀንም ይሄንን የሀሰት ወሬ ሰምተን ለማረጋገጥ ስንሄድ ከድሬን አገኘሁት።
.....ዘይባ ዘይባ እያለ ጠራኝ። አላስችል ብሎኝ ላናግውረ ወደርሱ ሄድኩ።
....ጠፋሽ ምን ሆነሽ ነው?? ናፈቅሽኝ እኮ ለምን አትደውይም?? እያለ ጥያቄ አዘነበብኝ።
.....ያን ሁሉ ያሳለፍኩትን መከራ ረስቼ ስልክ ስላላገኘሁ ነው ካሁን በኋላ እደውልሀለው አልኩት።

አሁንም ጥያቄውን ቀጠለ። ከኔጋ የጠየኩሽን ለመፈፀም ዝግጁ ሆንሽ ? ብሎ የረሳሁትን ጥያቄ ድጋሚ ጠየቀኝ።
..... የማውቀውን እና ይገባዋል ያልኩትን ስድብ በሙሉ ሰደብኩት ለሱ ያለኝ ስሜት ከዛን ቀን ጀምሮ ሞተ።ለማግባት ዝግጁ እስካልሆንኩ ድረስ ከወንድ ጋር የሀራም ግንኙነት ላልጀምር በአላህ ቃል ቁርአን መትቼ ማልኩ


Part 1⃣2⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል
ለአስተያየት 👉 @Ruyye

Join👇👇
@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ ዘጠኝ 9⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን

ስልኩም እንደተላከ ሰው ላጥ ብሎ የሽንት ቤቱ ቀዳዳ ውስጥ ገባ......
ወይኔ ጉዴ ብዬ እዛው እንዳለሁ ጮህኩ። አጯጯሄ የሆነ ዱብዳ የመጣበት እንጂ ስልክ የገባበት አይመስልም ነበር።
.....አባዬም ደንግጦ ምን ሆንሽብኝ?? ብሎ መጣ።
......እኔም ስልኬ ሽንት ቤት ገባብኝ አልኩት።
......እሱም ጦስሽ ይውሰድ እኔ ሌላ የተሻለ እገዛልሻለው ይሄ ሊያሳስብሽም ሊያስደነግጥሽም አይገባም ብሎ አረጋጋኝ። ወደቤት አስገብቶኝ ትንሽ ከቆየን በኋላ እንዳዲስ ሽንት ቤት ስልክ ይዘሽ ምን አስገባሽ ??ብሎ ተቆጣኝ በተጨማሪም የትምህርት ውጤቴ እያሽቆለቆለ በመምጣቱ ለትንሽ ጊዜ ስልክ መያዝ እንደሌለብኝ ወሰነ።

በዚህም ምክንያት ከከድር ጋር የምገናኝበት ጊዜ አጥሮዋል። ልክ እንደድሮው እዛቹ ፖል ተደግፎ ይጠብቀኝ ጀመር። ሁል ጊዜ ከመድረሳ ስወጣ ጠብቆኝ የኛን እና የነሱን ሰፈር ማለትም አብነትን ከሰባተኛ ወይም ልደታ ክፍለ ከተማን ከ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚለየው ድንበር የሆነው የሚገነጥላቸው ዋነኛ አስፓልት ማለትም አብነት አደባባይ የሚባለውን አስፓልት ድረስ ሸኝቶኝ አባት ልጁን እንደሚያሻግረው እጄን ይዞ አሻግሮኝ ወደቤቱ ይመለሳል። አስፓልቱን ሳያሻግረኝ ተለያይተን አናውቅም ድንገት ዞር ስል መኪና ቢገጭሽስ እያለ በሚያሳሳ አስተያየት ይመለከተኛል።

ከ 15 ቀን እረፍት መልስ እኔም ትምህርቴን በስርአቱ መከታተል ቀጠልኩ እናም ለሚኒስትሪ ፈተና እራሴን ማዘጋጀቱን ተያያዝኩት።ትምህርት ቤቱ 31 ተማሪ ነው ሚኒስትሪ የሚያስፈትነው ።ከሰላሳ አንዱም እኔ ዮናታን እና ዮሴፍ ከክፍሉ ሰነፍ ተማሪዎች እንዲሁም ሚኒስትሪን አያልፉም ተብለው ከሚታሰቡ ተማሪች መካከል ዋነኞቹ ነበርን፡፡ እናም ላለመውደቅ እራሴን መታገል ጀመርኩ።
ከድርም ሰቃይ ተማሪ ስለሆነ ብዙ ጊዜ እየተገናኘን ያስጠናኛል። እንኳን አስረድቶኝ ዝም ብሎ ሲመለከተኝም ይገባኛል። አላህዬ ሰርጋችንን ዛሬ አድርገው እያልኩ ሁል ጊዜ ዱአ አደርጋለው። ከድሬም ከአንቺ አትለየኝ ብሎ ሁል ጊዜ ዱአ እንደሚያደርግ ነግሮኛል። በአለም ላይ እንደኔ ደስተኛ ያለም አይመስለኝም መሳቅ መደሰት ብቻ ነው የሚታየኝ።

እንደተለመደው አንድ ቀን ሊያስጠናኝ ገዳመ እየሱስ መዝናኛ ሄድን እና እንደወትሮው ጥናታችንን ቀጠልን።ከብዙ ጥናት በኋላም እረፍት ማድረግ እንዳለብን ወስነን መቀላለድ ጀመርን።
..... ከድሬም ድንገት ሳላስበው ልክ እንደባለፈው ሳመኝ።
.....እኔም ኮስተር ብዬ ምን መሆንህ ነው ??አንተ እኮ ሴት የማትጨብጥ ሰው ነህ ከ ትዳር በፊት እንደዚህ መሆን የለብንም ብዬ ተኮሳተርኩ።
..... ከድርም አኩርፎ ወደቤት እንሂድ ብሎ ትቶኝ ወጣ። ከዛን ቀን ጀምሮ ለኔ ያለው ፍቅር እየቀነሰ መጣ እናም አንድ ቀን ለምንድነው የምትርቀኝ?? እያልኩ በግልፅ ጠየኩት
...... እሱ አልራኩሽም አሁንም አፈቅርሻለሁ አለኝ ያኔ ልቤ እንዳዲስ አንሰራራ።በተለይ ደሞ የስኳር በሽተኛ ስለሆነ በቻልኩት አቅም እሱን መንከባከብ ጀመርኩ። ለሱ ያለኝ ፍቅር ከለት ወደየለት በበርሜል እንደሚያጠራቅሙት ውሀ እየጨመረ እየጨመረ መቶዋል።

አንድ ቀን ዛሬ ትምህርት ስንለቀቅ የምነግርሽ አለ አለኝ
....እኔም ምን ይሆን የሚነግረኝ እያልኩ ብቻየን ማሰብ ሁኗል ትምህርት ሰአት መምህሮቹ ቢያስተምሩም ምንም ማዳመጥ አልቻልኩም፡፡

ትምህርት ተለቀቅን ከድርም ያለምንም ማፈር አብረን ማደር እንዳለብን ነገረኝ
.....እኔም በጭራሽ አይሆንም አልኩት
.......ከድርም አንቺ እኮ ሚስቴ ነሽ ምን ችግር አለው?? ዛሬም ሆነ ነገ ለውጥ የለውም ነገ ስንጋባ ማድረጋችን አይቀርም ስለዚህ እናድርግ አለኝ።
....እኔም ቆሜ ማሰብ ጀመርኩ።ግራ መጋባቴን ሲመለከት
...... እንዳውም እንቢ የምትይኝ ከሆነ ይሄ እኔን አለማፍቀርሽ ነው የሚያሳየው እንቢ ምትይኝ ከሆነ ፍቅራችንን ማቋረጥ እና መለያየት እፈልጋለው ብሎ ወሽመጤን ቆረጠው።አስከትሎም የምታፈቅሪኝ ከሆነ ይሄን ውለታ ብትውይልኝ ምን ችግር አለው?? አለኝ።

የከድር እንደዚህ መናገር አስደንግጦኛል በሚስተካከለው መልኩም አናዶኛል።አፈቅርሻለው እያለ ለጆሮዬ የነገረኝንም ደጋግሜ እያስታወስኩ በመሀል ፈገግ እላለው።እሱን አጥቼ መኖር አልችልም እሱ ማለት ለኔ ደስታዬ ተስፍዬ ኩራቴም ጭምር ነው ከሱ ተለይቼ መኖር አልችልም እሱ ከሌለ ኑሮዬ ጨለማ ነው አለም ለኔ ጨለማ ትሆናለች። እሺ ብዬ ላስደስተው ብዬ አሰብኩ ፍቅሬን ላሳየው ብዬ ልቤ አመነታ ትንሽ እንደተራመድኩም ግን ለምንድነው ይሄንን የምንፈፅመው ??? ገና እኮ 15 አመቴ ነው እያልኩ ከራሴ ጋር ታገልኩ ከብዙ ትግል ከብዙ ማሰብ እና ከብዙ ጭንቀት በኋላ ውሳኔዬን ላሳውቀው ወደ ከድሬ አመራሁ።
........ ፊቱ ቆሜ አይኔን ከአይኑ ገጥሜ ጥርሴን ከጥግ እስከጥጉ ከፍቼ ከድሬ አልኩት

Part 🔟
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል

@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ ስምንት 8⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን


〰〰〰Ayuti Islamic Post 〰〰〰


ከድርም ያለምንም ማቅማማት ጥያቄዬን እንደተቀበለው በፈገግታ አጅቦ ነገረኝ። በደስታ ሰከርኩ።ምንም ቃል ሳልተነፍስ ወደ እደሩስ አመራሁ እናም ይሆነውን ሁሉ አስረዳኋት እስዋም ደስታሽ ደስታዬ ነው ብላ ሳቅዋን አቀለጠችው።

ጊዜያት ነጎዱ ከከድር ጋም ከትምህርት ሰአት ውጪ ክላስ እየቀጣን ሰው ዝር የማይልበት አካባቢ መገናኘት ጀመርን ግን አንድም ቀን አቅፎኝ ወይም ነክቶኝ አያውቅም። ጊዜው ነጎደ 7ተኛ ክፍልን ጨረስን።ብዙ ተማሪዎች ወደ 11 የሚጠጉ ተማሪውምች 7ተኛ ክፍልን ወድቀው ደገሙ እኛም 8ተኛ ክፍል ገባን።በዚህ አመት ስልክ ተገዛልኝ። ከድርም ስልክ ስለነበረው ተለዋውጠን ማታ ማታ በድብቅ ሽንት ቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ አውርቼው እተኛለሁ።

በዛ መሀል ሲናፍቀኝም ሚሴጅ እልክለታለው። ከለት ወደየለት ፍቅሩ እየጨመረብኝ መጥቷል።እሱም በስስት ያየኛል።ድንገት ትምህርት የቀረሁ ለትም ዛሬ ሳላይሽ ላድር ነው ማለት ነው ??ብሎ ያኮርፈኛል።በትምህርቴ በጣም እየደከምኩ ነው እንደድሮ አይደለሁም።ሰባተኛ ክፍልንም 2 ትምህርት ከ 50 በታች አምጥቼያለው።


ከድርን እንደማገባው እና የወደፊት አጋሬ እንደሆነ 100% እርግጠኛ ሁኛለው። ባገኘሁት ቁጥር ነብስያዬ እቀፊው ሳሚው እንደልብሽ ሁኚበት ይለኛል ነገር ግን ወንድሜ ያለኝን ንግግር ሳስታውስ ወደ ቀልቤ እመለሳለው።ወንድሜ ከልጅነቴም ጀምሮ ከትዳር በፊት ፍቅረኛ ምናምን ብሎ ነገር መያዝ እንደሌለብኝ ከአላህ መንገድ እንደሚያስወጣኝ እና ክብሬን መጠበቅ እንዳለብኝ በፍፁም በወንድ ተታልዬ ከማንም ጋር ዚና መስራት እንደሌለብኝ።አላህ ዘንድ የዚናን ያክል ከባድ ወንጀል እንደሌለ ሴት ልጅ ክብርዋን በሀራም ካስወሰደች ማንም እንደማያከብራት እና ሂወትዋ እንደሚበላሽ ብዙ ጊዜ ነግሮኛል።

ምንም እንኳን ካዱኩ በኋላ አላህ ዘንድ ከሁሉም ወንጀል ከባዱ በእርሱ በአላህ ላይ ማጋራት ወይም ማሻረክ እና ዚና እንደሆነ ነው አይምሮዬ የፃፈው ። እንደተለመደው ክላስ ቀጥተን ተደዋውለን ሁል ጊዜ ምንፎርፍባት ገዳመ እየሱስ የሚባለው መናፈሻ ቦታ አመራን እዛም ሳሩ ላይ ጫማችንን አውልቀን ተንደላቀን ቁጭ አልን።

ከድሬም ከኪሱ አንድ ነገር አወጣና ይሄ ላንቺ ነው አለኝ። ረጅም ቸኮላት ነበር እናም ለመብላት ጓጓሁ።ስጠኛ ብዬ አይኔን አቁለጨለጭኩ።ከድሬም እንዲ በቀላሉማ አልሰጥሽም አህያ ነኝ በይና እሰጥሻለው አለኝ እኔም ለመብላት ካለኝ ጉጉት የተነሳ አህያ ነኝ አልኩት ቀጥሎም አይ ውሻ ነኝ በይ አለኝ። እኔም አስከትዬ ውሻ ነኝ ስጠኝ በቃ አልኩት።እሱም ውሻ ከሆንሽ እንደ ውሻ በአፍሽ ተንጠራርተሽ ውሰጂ አለኝ
....እኔም እንዴት አድርጌ ስለው ቸኮላቱን ከፈተውና በአፉ ይዞ ይኸው እንዲ እይዝልሻለው አንቺ እየገመጥሽ ብይ አለኝ።
......እኔም ሳላቅማማ በሀሳቡ ተስማምቼ አንድ ሁለት ሶስት እያልኩ በአፌ ከአፉ ላይ እየወሰድኩ ተመገብኩ።አንዴ በጎረስኩ ቁጥር ወደ ከንፈሩ እየተጠጋሁ ነው።አንድ ጊዜ ምትጎረስ ያክል ስትቀር ልጎርሳት ስጠጋው ቸኮላቱን እራሱ ጎርሶት ከንፈሬን ከከንፈሩ አገናኘው። የሰርጋችን ቀን ዛሬ የሆነ መሰለኝ። ደስ አለኝ ከንፈሬ ከከንፈሩ ሳይላቀቅ ነገን ማለም ጀመርኩ። ልቤ ከአካሌ ተንሸራታ ስትወድቅ ተሰማኝ። ድንገት የወንድሜ ንግግር ትዝ ሲለኝ ከእንቅልፍ እንደነቃ ህፃን ብንን ብዬ ተነሳሁ።
......ከድሬንም ቻው እንኳን ሳልለው በፍጥነት ወደቤት አመራሁ። ህልም ያየሁ መሰለኝ ከንፈሬ ኪሎ የጨመረ እስኪመስለኝ ድረስ ከበደኝ። ከዛን ቀን በኋላ ከከድሬ ጋር መተፍፈር አቆምን። እዛዉ መነፈሻ በተደጋጋሚ እየሄድን ነዉ ከሄድንም በኋላ እቅፍፍፍፍፍ አድርጎ ጉንጬን ይስመኛል ደረቴ ላይ ተኝቶም ስላንዳንድ ነገሮች ያወራኛል።
ሁለታችንም ተጋብተን ልጆች የምንወልድባቸውን ቀናቶች ናፍቀውኛል በጉጉት እየጠበኩትም ነው።


የመጀመርያው መንፈቅ አመት የማጠቃለያ ፈተና ከመድረሱ በፊት የሚኒስትሪ ተፈታኝ ተማሪዎች እንደመሆናችን መጠን ሞዴል ተፈተንን እናም የ 15 ቀን እረፍት ተሰጥን።
..... ከድሬን በስልክ ስለማገኘው ትምህርት መዘጋቱ አላሳሰበኝም ማታ ማታም ከመተኛታችን በፊት የፍቅር ቃላትን ተለዋውጠን እንተኛለን።


እንደተለመደው ሽንት ቤት ቁጭ ብዬ እያወራሁት እንዳለ አባዬ ውሀ በውዱእ በማንቆርቆርያ ላስቲክ ይዞ ወረፋ ሲጠብቅ በቀዳዳ ተመለከትኩት።
......የሰማኝ ስለመሰለኝ በድንጋጤ ስልኩን ጣልኩት። ስልኩም እንደተላከ ሰው ላጥ ብሎ የሽንት ቤቱ ቀዳዳ ውስጥ ገባ......

Part 9⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል


Join👇👇
@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

     ┏━━━ ◌͜͡༄ ━━━━💞━━┓
彡💞 Ayuti Islamic Post ☜join us
     ┗━━━ ◌͜͡༄ ━━━━💞━━┛

👉 የምግብነት ጠቀሜታ የሌላቸውን ልዩ ልዩ ነገሮች የሚያስበላ ወይም ለመብላት የሚያነሳሳ የስነ ልቦና ወይም የጤና ችግር ፒኮ ይባላል።
በርካታ የፒኮ አይነቶች ያለ ሲሆን ስማቸው ሁሉ ፍጂያ በሚለው ቃል የሚያልቅ ነው። ከእነዚህም ውስጥ ታዋቂዎቹ

▪️ጂኦፋጂያ -አፈርን አሸዋና ሸክላን መብላት

▪️አሚሎፋጂያ -እንጨትና ቅጠል መብላት

▪️አሚሎፋጂያ -ወረቀት መብላት

▪️ሐይሎፋጂያ -መስታወት ቆርጥሞ መዋጥ

▪️ሪሞኮፋጂያ - ንፍጥ መብላት

▪️ኑዶዋፋጂያ -ለስላሳ ድንጋይ መብላት

▪️ፓጎፋጂያ -በረዶ መብላት

▪️ትራይኮፋጂያ -ፀጉር መብላት

▪️ጋርቤጆፋጂያ -ቆሻሻ መብላት

▪️ኮርፓሮፋጂያ -ሰገራ መብላት

▪️ዮሮፋጂያ -ሽንትን መጠጣት . ይጠቀሳሉ።


ለእንደዚህ አይነት የስነልቦና ችግር የሚያጋልጡ አጋጣሚዎች
▫️ ርሃብና ጉስቁልና

▫️ የአዕምሮ ዝግመት

▫️ ከባድ ሃዘንና አደገኛ ትካዜ

▫️ መረን የለቀቀ ድህነት

▫️ አደገኛ ብቸኝነት

▫️ የኑሮ መመሰቃቀል

▫️ የቅርብ ዘመድ ሞት

▫️እርግዝና ሊሆኑ ይችላሉ

⁩✿┈┈┈┈┈•✶✾✶•┈┈┈┈┈✿
📮•〔➣ T.me/Halal_tube_official 〕•

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ ሰባት 7⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን


〰〰〰Ayuti Islamic Post〰〰〰


እኔም እግሩ ስር ተደፍቼ እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ ሁለተኛ አይለመደኝም የፈለከውን ቅጣኝ ወላጅ አታስመጣኝ ብዬ ለመንኩት በስተመጨረሻም 15 ግርፍት ተፈርዶብኝ ቂጤ እስኪላጥ ጠረፔዛ ላይ አስተኝተው ገረፉኝ።

እውነት ለመናገር አባቴን ከማመጣው አይደለም ቂጤ እስኪላጥ አካሌ እስኪሰባበር ቢገርፉኝ እመርጣለው። ምክንያቱም አባቴ ሱናደድ ሰይጣን ነው አንቆም ሊገለኝ ይችላል። ግርፋቱ እና ፍርሀቱ ተጨማምሮ እያንቀጠቀጠኝ ወደ ክፍል ገባሁ። ናትኔኤል የሆነች ልጅ ጠየቀችኝ ብሎ ለአባቱ ደብዳቤውን አሳይቶት አባቱ ደሞ ትምህርት ቤት መቶ ከሶኝ ነው ለዚህ የተዳረኩት። ከዛን ቀን ጀምሮ እኔና እየሩስ ደብዳቤ መፃፉን እርም ብለን ተውን።


እየሩስ ለከድር ያለኝን ስሜት ከነገርኳት ቀን ጀምሮ ካልነገርሽው እያለች ትጨቀጭቀኛለች። ለሱ ደብዳቤ ብትፅፊለት እኮ የሚመታሽ የለም እያለች የናቲን ጉዳይ እያስታወሰች ታስቀኛለች። በዚህ በኩል እስዋ በዛ በኩል ደሞ ይክላስ ተማሪዎች አላስቀምጥ አሉኝ እናም ደብዳቤ ፅፌ ልሰጠው ወሰንኩ።

ከድር ተክለ ሰውነቱ ረጅም እና ወፈር ያለ ነው ቡኒ አይን እና አመዳማ ወርቃማ የሚመስል ፀጉር አለው።እኔ ደሞ የሱ ተቃራኒ አጭር ቀጭን ነኝ። አብረን ስንሆን ላየን ሰው አባት እና ልጅ ነው የምንመስለው።

ሰኞ ረፋድ አካባቢ ደብዳቢውን ፃፍነው። ተፃፈ በ 20/06/2006 መልሱ ለ ጁመአ 24/06/2006 ብለን ቋጨነው። እናም ከክላስ ስንወጣ ልሰጠው ተስማማን


ከዛም ከመድረሳ ስወጣ እንደተለመደው ሰላምታ ተለዋውጠን ብቻ ደብዳቤውን ሳልሰጠው አለፍኩ። ልቤ በጣም ፈራ። እየሩስም ተናደደችብኝ እናም ነገ እኔ እሰጠዋለው ብላ በንዴት ቀማችኝ። አይነጋ የለ ነጋ ስንማር ውለን አስተማሪ አዳርቀን ..ወደ መድረሳ ስሄድ አገኘነው እና እዩ እሰጠዋለው ብላ እንዳልደነፍች ስታየው ተንቀጠቀጠች።ኧረ እራስሽ ስጭው ብላ ደብዳቤውን ሰጠችኝ። እኔም ሳልሰጠው አለፍኩ።
...... እዩ ተናዳለች ምክንያቱም ደብዳቤው ላይ ተፃፈ በ 20/06/2006 የሚለው ፅሁፍ ቀኑ በጨመረ ቁጥር ልንሰጠው ፈርተን እንዳቆየነው ይናገርብናል ብላ ተጨንቃለች።በስተመጨረሻም እሮብ በ 22/06/2006 አመተምህረት ደብዳቤውን ሰጠሁት። ከሰጠሁት በኋላ አይኑን ማየት ሞት መስሎ ታየኝ ፈራሁት። አላፈቅርሽም ተይኝ ቢለኝስ ምንድነው የማደርገው??? እያልኩ እራሴን በሀሳብ ወጠርኩ።

በሀሳብ ብዛት ሳልተኛ ስላደርኩ እራሴን በጣም አመመኝ በዚህም ምክንያት ሀሙስ ትምህርት ቤት ከመሄድ ቀረሁ። ጁመአም እራስ ምታቱ ቢሻለኝም አልተሻለኝም በሚል ስበብ በድጋሚ ቀረሁ።

ትምህርት ቤት ቀርቼ የማላውቀው ልጅ ዛሬ አመመኝ ብዬ ስቀር አባቴ በጣም ተጨንቆ ሀኪም ቤት መሄድ አለብሽ ብሎ ቢጋተተኝም ደህና ነኝ እረፍት ላድርግ ብዬ ነው ብዬ አረጋጋሁት። ደስ እንዲለውና ደህንነቴ እንዲታየው ብዬ ከተኛሁበት ተነስቼ ቤቱን አፀዳድቼ ቆንጆ ምስር ወጥ ሰርቼ ቤቱን ፏ ሽክ አደረኩት ።

ጁመአ ማምሻ አካባቢ እየሩስ ቤታችን መጣች እኔም ለምን እንደቀረሁ ጠየቀችኝ
.....እኔም አባቴ ስለነበር ትንሽ አሞኝ እንደሆነ ነገርኳት። ሻይ አፍልቼላት ከጠጣች በኋላ ልሸኝሽ ብያያት ተያይዘን ከቤት ወጣን እናም የቀረሁት ከድርን ላለማየት ብዬ እንደሆነ ነገርኳት።
....እስዋም የስንቱን ወንድ ፊት እንዳልፈተንን ዛሬ ምን ነክቶሽ ነው እንዲህ የምትሆኚው ??ብላ አደፍፈረችኝ እናም ነገ ቅዳሜ የማጠናከሪያ ትምህርቱን እንዳልቀር አስጠንቅቃኝ ሄደች።

ቃልዋን ተቀብዬ ቅዳሜ ጥዋት ቦርሳዬን ይዤ ለሜካፕ ክላስ ዩኒፎርም ስለማይለበስ ሽቅርቅር ብዬ ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ። ከድርን የማገኝባት ያቺ ፖል ብቻዋን ተገትራለች።የናፍቆት አይኔ እየተንከራተተ ትምህርት ቤቴ ገባሁ።
ተምረን ከጨረስን በኋላም ከእየሩስ ጋር ተያይዘን ወጣን። ከድር በተለምዶው ቦታው ቆሞዋል። ላናግረው ፈራሁ።
......አሰላሙ አለይኩም ሳልለው ዝም ብዬ ላልፍ ወሰንኩ እናም እየፈጠንኩ ስራመድ እዩ እንዳልሄድ እላዬ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቃብኝ መልሱን ሳንሰማ ዛሬ አንሄድም ብላ ትመልሰኛለች።አሁንም አመለጥኳት ብዬ ስጓዝ ከየት መጣች ሳልል ገፍትራ ወደነበርኩበት ትመልሰኛለች።

ሳልፈልግ በግዴ እየተንቀጠቀጥኩ ወደ ከድር አመራሁ እናም መልሱን ለመስማት እንደወታደር ፊት ለፊቱ ተገትሬ ቆምኩ
.......ከድርም

Part 8⃣

ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል

Join👇👇
@Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

ከሚወዱት መራቅ ከባድ ነው። ከአላህ መራቅ ግን ህመም ነው። ከአላህ መራቅ ማለት ወንጀል መሥራት በኀጢአት መዘፈቅ ነው ።
:¨·.·¨: ❀
 `¡. @Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ አምስት 5⃣

✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን


〰〰〰Ayuti Islamic Post 〰〰〰


ሰባተኛ ሰፈርን ከሰባተኛ ክፍል ጋር ተቀላቀልን። ሰባተኛ ሰፈር መጠጥ ቤት እና ቡናቤት ይበዛል። ሴተኛ አዳሪዎችም ቤት ተከራይተው ወንድን በሚወሰውስ አለባበስ ወንዶችን ሲቀበሉ ማየት የተለመደ ነው። እዛ አካባቢ ከሚኖሩት ነዋሪዎች 50 % ማለት ይቻላል ሴተኛ አዳሪዎች ናቸው። ወላሂ እዛ አካባቢ ተወልዶ ያደገ ልጅ ሰው ሚሆንም አይመስለኝም። ሴተኛ አዳሪዎቹ ቤት ገብተው ከሴተኛ አዳሪዎቹ ጋር የሚተኙት ሰዎችን መመልከት ያሳፍራል። አብዛኛዎቹ በኛ እድሜ ላይ ያሉ ማለትም ከ 16_25 እድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ወጣቶች ናቸው። የተቀሩት ደሞ ጎዳና ተዳዳሪዎች ናቸው።

ሰባተኛ ክፍል ስንገባ እድገት ተሰምቶኛል ደስተኛም ነኝ። ሁሉም ተማሪ የየራሱ ለውጥ አሳይቶአል ወንዶቹ ድምፃቸው እየጎረነነ ሴቶቹም ጡታቸው እያጎጠጎጠ መጥቷል። በትምህርት ቤታችን ህግ መሰረት ሰባተኛ ክፍልን 3 ትምህርት ቀይ(flat) የገባበት ማለትም ከ50 በታች ያመጣ ተማሪ ወደ ስምንተኛ ክፍል ማለፍ አይችልም ስለሆነም በዚህ ምክንያት እና በአንዳንድ ትምህርቶች ለውጥ ማለትም ኬሚስትሪ ሶሻል እና ባዮሎጂ የተባሉ ትምህርቶች በ እንግሊዘኛ መማር በመጀመሩ ምክንያት ሁሉም ተማሪ ስጋት ላይ ነው።

እኔ ግን እያሰጋኝ ያለው ትምህርቱ ሳይሆን ከከድር ጋር የያዘኝ ፍቅር መናገር አለመቻሌ ነው። ከ እየሩስ ጋር ወንዶችን መፈታተኑን ቀጥለንበታል።ከክፍላችን ወንዶች አንድም የቀረን የለም ሁሉንም ጠይቀናል።
ከመድረሳ ስወጣ እንደተለመደው ከድርን አገኘዋለው። ይሄን ያክል ጊዜ ስንገናኝ አሰላሙ አለይኩም ከመባባል ውጪ ሌላ ንግግርም ሆነ ቀረቤታ አልነበረንም።


አንድ ቀን ግን ስሜቴን ለከድር መናገር እንዳለብኝ ወሰንኩ እናም ለ እየሩስ ሀሳቤን ሳልነግራት ከትምህርት ቤት ስወጣ እዛቹ ፖል ተደግፎ አገኘሁት። እናም ወደርሱ አመራሁና አሰላሙ አለይኩም አልኩት
........እሱም በሚያምረው ፈገግታው ድምፁን አለሳልሶ ወአለይኩም ሰላም ወራህመቱላህ አለኝ።
.......ከዛም ለሆነ ጉዳይ ፈልጌህ ነበር ይመችሀል አሁን ብናወራ??? አልኩት።
......እሱም አይ አሁን መድረሳ ይረፍድብኛል ከመድረሳ በኋላ አለኝ።
......እኔ ደሞ ከመድረሳ በኋላ ስለሚመሽብኝ በቃ ነገ
9፡30 እዚሁ ቦታ ላይ እንገናኝ ብዬው ቀጠሮ ይዘን ተለያየን።


አይነጋ የለ ነጋ የቀጠሯችን ሰአት ደረሰ። የማጠናከሪያ ትምህርቴን ትቼ ከድርን ለማግኘት ሄድኩ።ቦታውም አገኘሁት። እንደተለመደው ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ እዛችው ፓል አጠገብ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለን ለምን ነበር የፈለግሽኝ ብሎ በጥያቄ ጀመረኝ።

ጥያቄውን ለመመለስ ተቸገርኩ በቃ ስለማፈቅርህ ያላንተ መኖር ስላልቻልኩ ይሄንን ልነግርህ ነው የመጣሁት ብዬ የሆዴን ለማውጣት ታገልኩ ግን አልቻልኩም።ከጥቂት ዝምታ በኋላ ምን ሆነሻል ንገሪኛ??? ብሎ ጥያቄውን ደገመው።
.....እኔም ወድያው ሀሳቤን ቀይሬ ስለ ኑሮህ ማወቅ ፈልጌ ነው.. ማለት ከማን ጋር ነው የምትኖረው?? ብዬ አስቀየስኩት
......እሱም እናቱ አረብ ሀገር እንደሆነች እና የሚኖረው ከ አባቱ ጋር እንደሆነ ነገረኝ።
......ንግግሩን ከጨረሰም በኋላ በቃ ለዚህ ነው የፈለግሽኝ? ብሎ ሌላ ጥያቄ አስከተለብኝ።
......እኔም ምን ያለበት ምን አይችልም እንደሚባለው ታዳ ሌላ ምን ይኖራል ??ብዬ ተኮሳተርኩበት። እናም ቀጥታ ወደ መድረሳ አመራሁ።


ከመድረሳ ቆይታዬም በኋላ ስወጣ እየሩስ የመድረሳችን በር ጋር ቆማ አገኘኋት። ግልምጫዋ ይገፍተራል። ከክፍል የወጣሁት ሳልነግራት ስለሆነ ተጨንቃለች። ጥያቄ ሳታነሳብኝ በፊት አስቀድሜ እኔ ስለደበረኝ አንቺንም እንዳትማሪ እንዳላደርግሽ ብዬ እኮነው ትቼሽ የወጣሁት እዩ አትቆጪ ብዬ አስቀድሜያት ሳኩ። ሳቄ ያስቃታል ጭንቀት ውስጥ እንኳን ብትሆን ፈገግታዬን ስታይ ትስቃለች። እነዛን ጥናኒጥ የአይጥ ጥርስ የሚመስሉት ጥርሶችዋን ከፈታ አሰጣችልኝ እናም ተቃቅፈን ጉዞአችንን ቀጠልን።



ለከድር ያለኝ ስሜት መናገር ባለመቻሌ አዝኛለው ደካማ እንደሆንኩ ተሰምቶኛል። ከመድረሳም ከወጣሁ በኋላ እዩን ሸኝቼ ስመለስ መሽቶብኝ መግሪብ አካባቢ ወደ ሰፈር ስገባ አቋራጭ መንገድ ለመጠቀም ብዬ በሴተኛ አዳሪዎቹ ቤት በኩል ሳልፍ አንድ ሰውዬ ተመለከትኩ። አባዬ ሴተኛ አዳሪ ቤት ሲገባ አየሁት። እግሬ ተንቀጠቀጠ ድንጋጤዬ ሰውነቴን ወረረው እንባዬ መዝነብ ጀመረ።አባዬ ብዬ ለመጥራት አፌ ተለጎመ። በደመነፍስ ወደ ቤቱ አመራሁ ሴተኛ አዳሪዋም በሩን ዘጋችው።

እየተንደረደርኩ ሄጄ የተዘጋዉን በር እየደበደብኩ አንቺ ውሻ ክፈቺው አባቴን አታሳስችው ክፈችው እያልኩ በሩን በእጄ እየወገርኩ።
......ልጅትዋም ከፈተችው።ገፍትሬያት አባቴን ለማናገር ወደ ውስጥ ዘልቄ ገባሁ......


#Part 6⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል
አስተያየቶችን 👉 @Halaltube_bot

Join👉👉 @Halal_tube_official

Читать полностью…

Ayuti Islamic Post 🕌📿

ጥያቄ እና መልስ

1,በመካና መዲና የወረዱት የቁርዓን ምዕራፎች ስንት ናቸው ( ማስታወሻ በመካም በመዲናም የወረዱ ምዕራፎች አሉ)?

ሀ,በመካ 86 በመዲና 28❤
ለ,በመካ 84 በመዲና 30🧡
ሐ,በመዲና 86 በመካ 28💛
መ,በመዲና 14 በመካ 100💚

@Halal_tube_official

Читать полностью…
Subscribe to a channel