hanoonab7 | Unsorted

Telegram-канал hanoonab7 - bookstore 📕📚

-

Islamic and other books አስተያየትዎን @Hananabbot 😊

Subscribe to a channel

bookstore 📕📚

ስለ ጀላሉዲን ሩሚ ማወቅ ለምትፈልጉ አሪፍ መፅሐፍ ነው🥰

Читать полностью…

bookstore 📕📚

የሩሚ ወግ
(አፈንዲ ሙተቂ)
-----
ሰሞኑን የምናየው ግርግር እና ጭቅጭቅ አንድን አሪፍ ወግ አስታውሰውኛል። ወጉን የጻፈልን የፋርሱ ተወዳጅ ባለቅኔ ጀላሉዲን ሙሐመድ በልኺ ሲሆን ይህንን ባለቅኔ የዓለም ህዝቦች በደንብ የሚያውቁት “ሩሚ” በሚለው ስሙ ነው (የሩም ተወላጅ እንደማለት ነው፤ ሩም የተወለደበት ከተማ ስትሆን አሁን በአፍጋኒስታን ግዛት ውስጥ ትገኛለች)፡፡

ባለቅኔው ሩሚ በአራት ሰዎች መካከል የተነሳውን ጭቅጭቅ እንደምሳሌ በማድረግ ታላቅ ቁም-ነገር ያስተምረናል፡፡
----
አራት ሰዎች በአንድ ደጃፍ ተሰብስበዋል፡፡ እነዚያም ሰዎች ግሪክ፣ ፋርሲ (ኢራናዊ)፣ ዐረብ እና ቱርክ ነበሩ፡፡ የሚፈልጉትን ነገር ይገዙበትም ዘንድ የተወሰነ ገንዘብ ተሰጣቸው፡፡
ግሪኩ “እኔ ስታፊል አምሮኛል፤ ስታፊል ግዙልንና እንብላው” አለ፡፡
ፋርሲው “የምን ስታፊል? ኡዙም ግዙልን እንጂ ሰዎች” አለ፡፡
ዐረቡ “አረ ወደዚያ! ኢነብ ነው የምንገዛው፤ ኢነብ መግዛት አለብን” በማለት ተናገረ፡፡
ቱርኩ “እንዴ! አንጉር ነው መግዛት ያለብን፤ አንጉር እንጂ ሌላ ነገር አትግዙብን” አለ፡፡

አራቱ ሰዎች ተከራከሩ፡፡ ተነታረኩ፡፡ በጭራሽ ሊግባቡ አልቻሉም፡፡ የቃላት ጭቅጭቅ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ፡፡ እንዲህ በመወዛገብ ላይ ሳሉም አንድ መንገደኛ መጣ፡፡ “ምንድነው የሚያጨቃጭቃችሁ?” በማለት ጠየቃቸው፡፡ ጉዳዩን ነገሩት፡፡ ሰውየውም “በዚህ ፍራንክ የሁላችሁንም ፍላጎት ማሟላት ይቻላል” አላቸው፡፡ ሰዎቹም “እንዴት?” በማለት ጠየቁት፡፡ ሰውዬም ገንዘቡን እንዲሰጡት ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም እንደተባለው አደረጉ፡፡

መንገደኛው ሰውዬ በአካባቢው ከነበረ የፍራፍሬ መሸጫ ገብቶ አንዱን የፍራፍሬ ዓይነት ገዝቶ ሲወጣ አራቱ ሰዎች ተያዩ፡፡ በዚያው በሳቅ ፈረሱ፡፡ ለካስ አራቱም አንዱን ፈራፍሬ በየቋንቋቸው እየጠሩት ነበር? አራቱም “ወይን እፈልጋለሁ” እያሉ ነበር የሚከራከሩት::
*
የታሪኩን “ማዕና” (ውስጣዊ መልዕክት) አገኛችሁት አይደል? ለኛም እንደ መንገደኛው ሰውዬ ያለ አስታራቂ ይላክልን፡፡ አንድ ውጥንና ግብ ያላቸው ሰዎች ዕድሜ ልካቸውን በአተገባበር ላይ ሲጣሉ ማየትን የመሰለ አሰቃቂ ህመም የለም፡፡ ሁሉም እይታውን ቢያስተካክል መግባባት ይቻላል፡፡ ሩሚ ይህንን ነው የመከረን፡፡

Читать полностью…

bookstore 📕📚

የኪታቡ ስም ፦ ሙተሚመቱል አጀሩም
የሚያጠናው ፦ ነህው

/channel/hanoonab7

Читать полностью…

bookstore 📕📚

የኸድር ታጁ " አግራሞታዊ ጉዞ " የተሰኘው መጽሐፍ ለንባብ በቃ ::

Читать полностью…
Subscribe to a channel