982
💄ዘመናዊ ሴት ከሆንሽ💁♀ 🏵Periodሽ መች እንደሚመጣ ቀድመሽ ማወቅ፤ 🏵የውሸት እና የእውነት ፈገግታ መቻል፤ 🏵ረዥም ጆሮ_ጌጥ እና አጭር ጆሮጌጥ መቼ እንደሚደረገ ማወቅ ፤ 🏵ውሀ ቻፒስቲክ ወይም Color ቻፒስቲክ መች መጠቀም ……
ፍቃድ እና ፍቅር
ሰላም እንዴት ናችሁ የኔ ውድ ንግስቶች
እስኪ በዚህ ሳምንት ደግሞ ስለወሲብ እና ፍቅር እናውራ። በተደጋጋሚ የሚመጣልኝ ጥያቄ ቢሆንም ከዛሬ ነገ አነሳዋለሁ እያልኩ ብዙ ቆየሁ።
💁♀ፍቅረኛዬ እንድናደርግ ይፈልጋል፣እኔ ደግሞ ከጋብቻ በፊት ማድረግ አልፈግም
💁♀ከተዋወቅን 4 ወራችን ነው፣ ግን እንድንጀምር ደጋግሞ እየጎተጎተኝ ነው
💁♀ካላደረግን አትወጂኝም ማለት ነው ይላል
💁♀ትንሽ እንቆይ ስለው እምቢ አለኝ፡ እንደውም አኮረፈኝ……………
ብዙ ብዙ ነገር ይደርሰኛል። ሃሳቡ ሲጠቃለል "ፍቅረኛዬ እኔ ዝግጁ ባልሆንኩበ ለወሲብ እየገፋፋኝ ነው" የሚል ነው። #እያስገደደኝ የሚለው ቃል ሳይገልፀው አይቀርም።
በርግጥ ለወንዶች ወሲብ Big deal ነው። በየዕለቱ ሳያስቡት አያድሩም። ግን ደግሞ ስሜታችውን በምክንያታዊነት መግታት የማይችሉ እንስሳትም ደግሞ አይደሉም።
ከምንም በላይ shock የሚያደርገኝ "sex ካላደረግን እንለያያለን" የሚሉት ቦይፍሬንድ ተብዬዎች ጥያቄ ነው። ይሄ አይነት ነገር ሲያጋጥማችሁ ልባችሁን ጠንከር አድርጋችሁ ወደፊት ሕይወታችሁን መቀጠል ነው የሚኖርባችሁ። ጭራሽ ድርድር እና ልምምጥ ውስጥ አትግቡ።
ወሲብን እንደ ፍቅር ማስቀጠያ መስፈርት የሚመለከት ወንድ ጉዳዩ ከስጋዊ አካልሽ ጋር ነው ማለት ነው። በተለይ ለትዳር የምታስቢው ወንድ ከሆነ በስነስርዓቱ ቁጭ አድርገሽ ልታወሪው ይገባል።
ፍቅር በመስራት ወቅት ባለውና force ተደርጎ በመጠቃት መሐከል ያለው ልዩነት ቀጭን መስመር ነው። እርሱም ያንቺ ፍቃደኝነት ነው።
ፍቃደኛ ሳትሆኚ በግፊት የምታደርጊው ነገር ከጥቃት አይተናነስም። ስለዚህ No ማለትን ተለማመጂ። ፊትለፊት ዓይን ዓይኑን እያየሽ " ከጋብቻ በፊት ወይም ትምህርት ከመጨረሴ በፊት ማድረግ አልፈልግም። የምትወደኝ ከሆነ አታስገድደኝ። የማልፈልገውን ነገርም ትልቁ ፍቅራችን ጋር ሚዛን ላይ አታስቀምጠው። ሁለ ነገሬ ያንተ ነው፡ ነገር ግን ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው!" በዪው።
በተረፈ በበራስ መተማመን ተሞልተሽ የምትወስኚው እንደዚህ ዓይነት ቆራጥነት ያስከብርሻል እንጂ ኪሳራ አይሆንብሽም!
You Can Do This!
መልካም ቀን
@Heewans
ሔዋኖችን ምን እያሳሰባቸው ነው?
ትላንት በምን ጉዳይ Insecure ናችሁ ብዬ ለጠየኩት ጥያቄ በርካታ ምላሽ መጥቷል። የተወሰነውን ከዓይነት ዓይነቱ አድርጌ ላጋራችሁ። ምናልባት ተመሳሳይ ነገር ታገኙ ይሆናል።
🌺Ks
Hi Hi ከራሴ የሚያስጠላኝ ነገር ፡ጡቴ በጣም ትልቅ ነው። እንደውም ምቀንስበት መንገድ ሹክ ብትዪኝ ደስ ይለኛል።
🌺LT
እኔ ብዙም የተጋነነ ባይመሥልም ከፊት ፀጉሬን የሆነ ጊዜ በእጅ የፀጉር ካውያ እየተኮስኩት ስሩን ሳላስበው ጉድቼው ትንሽ ገባ ብሎ ተነስቷል። ከሌሎቹ ጋር እኩል እስኪሆን ፀጉሬን እየተንከባከብኩ ነው። ግን የሆነ ደስ ማይል ነገር አለው።
🌺 HN
Hi, ለረዥም ጊዜ ቻናልሽን ተከታትያለሁ። እና ስለራሴ insecurity ላካፍልሽና ዕድሜዬ ወደ 26 ነው። ግን ስታይ baby-face ስላለኝ ያየኝ ሁሉ ገና teenage የሆንኩ እና እንደ ህጻን ነው treat የሚያደርገኝ። beteley ke siraya ansar sew expect endemiyadergew ayinet sew aydelehum ena hulam erasan prove madreg endalebig endisemag nw sew emiyadergew am just sick of trying to prove myself to get respect and approved what should I do
🌺Ll
ፌቭ! እኔ አሪፍ የሚባል ሰውነት ነው ያለኝ! ቁመቴ ለሆስተስነት የተመረጠ ነው። በቃ ፀጉሬም ለስላሳ እና ዞማ ነው……… እና ምን ቀረሽ አትዪኝም???
ግንባሬ🙈🙈🙈
ግንባሬ ትንሽ ወጣ ያለ ነው። I feel like ሰዎች ስለኔ ሲያወሩ ያቺ ረዥሟ፣ ሳቂታዋ፣ L.. ምትባለው ልጅ ብሎ ሳይሆን ያቺ ግንባራሟ ሚል እየመሰለኝ እሳቀቃለሁ😊😊 I hate it , but it is nature እንዳልሽው በቃ
🌺Sm
የኔ insecurity ደረቴ ነው ፌቪ። ማለቴ ጡቴ haha😃 የምር ቀልድ እንዳይመስልሽ በየቀኑ እንዳዲስ ነው ራሴን የምጠላው። እንዳልኩሽ ከበፊት ሰውነቴ ቀንሶልኛል ግን ጡቶቼ ጭራሽ ግንን እያሉ የመጡ መሰለኝ😣😣
🌺Fs
የኔ እንዴት እንደሚታይ አላውቅም። በግራ ፊቴ በኩል በልጅነቴ የፈላ ውሃ የነካኝ ጠባሳ አለ። እና ፊቴ ቀይ ስለሆነ ይጎላል። በቃ ሁሌ ፀጉሬን በዛ በኩል ሸፈን ለማድረግእንደሞከርኩ ነው። ግን እስከመቼ😢 GOD!
════❁✿❁ ════
💁♀ከዚህም ውጪ በየዕለቱ የሚደርሱኝ መልዕክቶች አሉ። እዚህ ጋር ትልቁ ነጥብ እራስን መቀበል ነው። በቀጣይ የምናተኩረውም እዚህ ላይ ይሆናል። ማስተካከል የምትችሉትን ባላችሁ አቅም ታስተካክሉታሉ። ካልሆነ ግን በተለይ ከገፅታ ጋር የተያያዙ ነገሮች በስታይልሽ መስመር ለማስያዝ መሞከር ይኖርባችኋል። ስለሁሉም አለፍ አለፍ እያልን እናነሳለን።
ግን እነዛን comment ወደዚህ ያጋራኋችሁ በተመሳሳይ ሃሳብና ጭንቀት ውስጥ ብዙ እህቶቻችንም እንዳሉበት ላሳያችሁ ነው እሺ።
#Share them
@Heewans
በጣም ይገርማል! በአንድ ዓመት ውስጥ ብዙ ነገር ተቀያይሯል።
🍄በርካቶቻችሁ በዕቅዳችሁ መሠረት አግብታችኋል፣ አንዳንድ ችግሮችም ተፈተዋል።
🍄አንዳንዶቻችሁ እዛው የነበራችሁበት ውዝግብግብ ሕይወት ውስጥ ናችሁ😌
🍄ከነበራችሁበት አስቸጋር የካምፓስ ሕይወት ወጥታችሁ ተመርቃችሁ አዲስ የሕይወት track ውስጥ የገባችሁም ቀላል አይደላችሁም
🍄"በጣም በምታስፈልጊኝ ሰዓት ምላሽሽን አላገኘሁም፤ ችግሩ ግን አልፏል" ያለችኝ እህቴ አለች፣ በሁሉም member ፊት ለጠፋሁበት ጊዜ በድጋሚ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ🙏
🍄አመሰግናለሁ፣ ሕይወቴ መንታ መንገድ ላይ ነበር፣ እናንተን በማማከሬ ነገሮች ወደመስመር ገብተውልኛል ያለች አንድ ነበረ።
🍄 "አታምኚኝም ከዛ በኋላ 8 ኪሎ ቀነስኩ" የሚል ፍንድቅድቅ emoji የተሞላ መልዕክት ደርሶኛል።
ሁላችሁም በተለያየ የህይወት ጎዳና ላይ እየሮጣችሁ ነው። በርቱ እሺ። ጠንካራ ሴት ስትሆኑ ለራሳችሁ ብቻ ሳይሆን ለቤተሰባችሁም ሆነ ለማህበረሰቡ ትተርፋላችሁ።
ምንም ውስብስብ ነገር ሲያጋጥማችሁ ወደኔ አምጡት እና አብረን እናወራበታለን። ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር እንደሌለ አትርሱ።
እወዳችኋለሁ❤️
ከተገናኘን በጣም ረዥም ጊዜ ሆነን!
ይህን ቻናል የከፈትኩበትን አካውንት ማስተካከል አለመቻሌ ከራሴ የሕይወት ሩጫ ጋር ተደማምሮ በጣም አራርቆናል።
I wonder ብዙ ነገር ስንመካከር የነበርን እህቶቼ እንዴት እንደሆናችሁ☺️ እስኪ ከታች ባለው ሃሳብ መተንፈሻ ውስጥ ያኔ የነበራችሁበትን ነገር እና አሁን ያላችሁበትን ሕይወት አነፃፅራችሁ ጻፉልኝ።
አሁን ቀለል ያለ የስራ ባህርይ ላይ ስላለሁ እንደበፊቱ actively እንወያያለን የሚል ዕቅድ አለኝ።
ሰላም ንግስቶች👸 እንዴት ናችሁ😍
እየጠፋሁ እንዳስቸገርኩ ይታወቀኛል። በinboxም መልዕክታችሁን ቶሎ ቶሎ እየመለስኩ አይደለም። በጣም ይቅርታ ነገሮችን እስካስተካክል ነው።
በተረፈ ግን ከዚህ በፊት በውፍረት መቀነስና ቅርፅ ላይ regular exercise report አዘጋጅታችሁ ትልኩልኝ የነበራችሁ እህቶቼ ያን ነገር እንድትቀጥሉበት እፈልጋለሁ። ያላችሁበትንም progress ማወቅ ስለምፈልግ መላካችሁን ቀጥሉ።
ሌሎቻችሁም ሁኔታዎች የሚመቻችላችሁ ከሆነና የሰውነታችሁ ቅርፅ እና ጤናማ ክብደት ላይ ለመስራት የምትፈልጉ ከሆነ፣ ለእንቅስቃሲ እንዲሁም ምቹ የሆነ ሁኔታ ካገኛችሁ እንዲሁም ተገቢውን አይነት አመጋገብ ውስጥ ካለፋችሁ የትኛውንም አይነት ለውጥ ማግኘት ትችላላችሁና ይህን ፕሮግራም መጀመር ትችላላችሁ።
ከዚህ በፊት ስናደርግ የነበረው አንዲት ሴት ስለራሷ መቀየር የምትፈልገው ነገር ምን እንደሆነ ትናገራለች። በዚህም በምን ያህል ጊዜ ለውጥ ራሷ ላይ ማምጣት እንደምትፈልግ ታቅዳለች። ለዚያም የሚሆን ሰንጠረዥ አዘጋጅላችሁና በዚያ ሰንጠረዥ መሰረት ለውጣቸውን እየመዘገቡ ሪፖርት ይደረጋል። ይህ ነገር ለክብደት፣ ለቅርፅ፣ ለvocal፣ ለቋንቋ ፣ ለጥናት ፕሮግራም እንዲሁም ለሌሎች ክሕሎቶች መሆን ይችላል።
አቅሙን ካገኘሁ ይህ ፕሮግራም በአፕሊኬሽን እንዲሰራ ለማድረግ እሞክራለሁ። እስከዚያ ግን በዚሁ ቦት እየላካችሁልኝ ፎልደር አዘጋጅና በዛ እከታተለዋለሁ።
ለጊዜው እየሰራንበት የሚገኘው የሰውነት ክብደትና ቅርፅ ላይ ነውና ይህን ፕሮግራም መጀመር የምትፈልጉ @Fevis_bot ላይ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ። በድጋሚ መልዕክት ስትልኩልኝ ለምላሽ ከዘገየሁባችሁ በትዕግስት እንድትጠብቁኝ በትሕትና እጠይቃችኋለሁ።
እወዳችኋለሁ😍
@Heewans
ደሃ ስለሆንኩ ተወችኝ ይላል ።
ደሃ ስለሆነ አይደለም የተውኩት ስንፍናውን ድል እንዲነሳው እንዳግዘው ምቹ ስላልሆነ እነጂ ፤ እሱ ችግሩን የሚፈታው በጥቅስ ነው ።
ያለውም ይሞታል የሌለውም ይሞታል አይነት የደከመው ሰው ጥቅስ ውስጥ ስለሚወሸቅ ነው
ወዳጆቹ ፣ ቤተሰቦቹ ፣ ጓደኞቹ እና ዘመዶቹ ስላላገዙት ፣ ስላላበደሩት እሮሮ እንደሚያሰማ ሰው ደካማ የለም ፤ ከዚህ ሰው ጋ እንዴት ጎጆ እቀልሳለሁ ?
እሱ ጋ ስሆን እረፍት አይሰማኝም ፣ ነገ አያጓጓኝም ፤ ችግር ሲገጥመው የሚታገልበት መንገድ ጥቅስ ነው ፤ የተሸናፊዎች ጥቅስ አሸናፊ መፍጠር እንደማይችል አያውቅም ።
ህልም እንደሌለው ሰው ደሃ የለም ፤ ህልም አልባ መሆኑን ያከፋው የእኔን ህልም ቅዠት አድርጎ መቁጠሩ ነው ።
ማሬ አንድ ቀን በዚህ ሁለት አመት ራስህን ለመለወጥ ምን አደረግክ አልኩት
" በእናትሽ ይሄ አነቃቂ ንግግር ነው ኑሮሽን የሚያወሳሰበው ፤ እነሱ እንደሚሉት በመደመር ፣ በትግል አይደለም ኑሮ የሚቀየረው በአጋጣሚ እንጂ ፤ እጣ ፈንታችን ነው ነገሮችን የሚያደላድለው" አለኝ ።
እኔ በውርስ ሀብታም ከሆነ ይልቅ ታታሪ ህልም ያለው ደሃ እንደምመርጥ ውስጤ ያለውን እውነት ባወቀልኝ ፤ ስንፍናው ነገዬን የማጨለም አቅሙ ሲታየኝ ፣ ህልሜን ሲጋርደው ነው ከህይወቱ የሄድኩት ። እንኳን ሄድኩ !
Yemi
@Heewans
እንዴት ናችሁ🌺
ጥሩ የስኬት ሕይወትም ሆነ ጥሩ የፍቅር አጋር ከላይ ከፈጣሪ እንደሚሰጡ ሁላችንም የምናምን ይመስለኛል። በባሌም በቦሌም ብለሽ ጥሩ አካዳሚያዊ ሕይወትና ጥሩ ባል ኖሮሽ ተመስገን ማለት ትፈልጊያለሽ።
ግን አንዳንዴ ሁለቱም እኩል አንዱ በባሌ አንዱ በቦሌ አቅጣጫ ተነጣጥለው ይመጡና ግራ ይገባሻል። It's like ከቦሌ ልጅ ጋር ፍቅር ጀምረሽ በጥሩ ውጤት ባሌ አካባቢ ዩንቨርስቲ ስትመደቢ አይነት ነገር ማለት ነው😊።
Sounds funny አይደል? but it ain't funny. ብዙ እህቶቻችን የሚጋፈጡት መራር ምርጫ ነው። ይህ አይነት የምርጫ አጣብቂኝ በሌላም የህይወት መንገድ በኩል ሁላችንም ጓዳ ድረስ ስለሚመጣ ሁላችሁም ከልባችሁ እንድታብሰለስሉት እፈልጋለሁ።
👉 እዚህ ቻናል ላይ ያለች እህታችን ጠይቃው የነበረ ነገር ነው። ( እንደ #አማክሩኝ አይነት ነገር ነው )
ከጊዜያት በፊት በጣም ምትወደው ከነበረ ሰው ጋር ፍቅር ትጀምርና እጅግ ጣፋጭ ጊዜ ማሳለፍ ትጀምራለች። ፈጣሪ በዚህ ጥሩ ጊዜ ላይ "ጥሩ ዕድል" ጨመረላትና በጥሩ ውጤት አንድ ራቅ ያለ ዩንቨርስቲ ተመደበች።
ቦይፍሬንዷ በዚህ ዜና ደስተኛ አልነበረም። ምክንያቱም ዩንቨርስቲ ከገባች ሌላ ሰው ሆና የማያውቃት ሰው እንደምትሆን ፍቅራቸው ገደል ሊገባ እንደሚችል ያለውን ስጋት የሌሎች ጥንዶችን ምሳሌ ጭምር እየጠቀሰ እንዳትሄድ አስረግጦ ይነግራታል።
ይህ መልዕክት የደረሰኝ እኔ ከዚህ ቻናል ርቄ በነበረበት ወቅታና ምንም ላማክራት አልቻልኩም ነበርና ልጅቷ የራሷን የምርጫ ካርድ መዛለች።
ይህ ለብዙዎቻችን የሚጠቅም ነገር ሆኖ ስላገኘሁት ግን ደግሜ አነሳሁት። በዚህች ልጅ ቦታ ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር? መልካም ወንድ በቀላሉ የሚገኝ ነገር አይደለም፡ ሴት ልጅ በአካዳሚያዊ ሕይወት የላቀ ደረጃ ላይ ስትጓዝ ማየትም ብርቅ ነገር ነው። መንታ መንገድ አይደል?
እናንተ ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር እስኪ @Fevis_bot ላይ ሁላችሁም የመሰላችሁን ሃሳብ እየሰጣችሁ ይሄን ጉዳይ እናብላላው። መጨረሻ ላይ ከራሴ ሐሳብ ጋር እመለሳለሁ።
ማንኛውም ሴት ብቻውን ምትብሰለሰልበት ጉዳይ መኖር የለበት የሚል ጠንካራ እምነት አለኝ። ያላችሁን ጭንቀት ሁሉ ወደዚህ አምጡት፥ ያኔ የጋራ ነገራችን መሆኑ ሲገባችሁ ትልቅ እፎይታን ታገኛላችሁ።
@Heewans
ሰላም እንዴት ናችሁ። ፌቨን ነኝ ። ከረዥም ጊዜ በኋላ የጠፋብኝን አካውንቴን አግኝቼ መልሼ ስላገኘኋችሁ በጣም ደስ ብሎኛል። እጅግ በጣም ብዙ ምናወራው ነገር በጣም ብዙ ምንመካከረው ነገር አለ እሺ።
በኔም ሕይወት በኩል አዳዲስ ነገሮች አሉ 💍
@Fevis_bot መስራት ጀምሯል፡ አካውንቴም መልዕክት ይቀበላል።
በጣም እወዳችኋለሁ የኔ ንግስቶች❤️❤️
GN🌝
ሰላም እንዴት ዋላችሁ እስኪ በአማክሩኝ (2) ላይ የደረሱኝን አስተያየቶች ላጋራችሁና በራሴ ሃሳብ ላጠቃለው
🌺Santa
"አብረሽዉ ስላለሽ ጊዜያዊ ስሜት ሊሆን ይችላል yene eht....kesu rkesh kerasish ga bedenb tenegageri"
🌺Ab
hi feve ከላይ የተነሳው ታሪክ ላይ ሃሳብ ለመስጠት ነበር
አሁን አይታ ሀሳብ ሊያስቀይራት ያለው ነገር ፍቅር ነው ለማለት ይቸግረኛል፡ coz ከሆነ ሰው ርቀን አዲስ ነገር ስናይ የሚሰማን ስሜት ነው። enji yezi mekegna demo ke fekeregnaw gar yemtasalfachew gizeyatoch selkenasu new selzi betechal meten ke befitu gar be akal megenagnet batechel beselk yalewun gap matbeb techalalch
🌺 Jerry
Selam post yaderegshw tyake lay comment lemestet new ...እንደኔ ሃሳብ 4 ዓመት ሙሉ ያፈቀረችውን ሰው በአንድዴ አሁን ለቀረብነው ሰው ስንል መተው ያለብን አይመስለኝም ...ሰዎቹ መልካም ቢሆኑ እንኳ በወንድምነት መቅረብ እንችላለን ...መልካም ሰውን ሁሉ ማፍቀር አይጠበቅብንም። ye erasachnn andun keyazn malet new....ena degmo ye mejemeriyaw lj mnm sayskeymen ahun yagegnenew sew Tru slehoneln ..beyekunu mnagegnew yhenn slehone gd Yann tten yhenn mafker yalebn aymeslegnm ...ena erasuan btadamt Bay negn
🤔🗯
በእያንዳንዱ ቀን የሆነ ቦታ ላይ ያለች ሴት በአንድ ሃሳብ እየተብሰለሰለች ነው። ምናልባት ያ ነገር በአለም ላይ እሷን ብቻ ያጋጠማት መስሎ ሊሰማት ይችላል። ግን እውነታው ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር አለመኖሩና አንቺ ጋር የተፈጠር ነገር እኔጋ ወይ ሌላ ሴት ጋር ተፈጥሮ የነበረ እየተፈጠረ ያለ እንዲሁም የሚፈጠር ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ በ @Fevis_bot ጭንቀትታችሁን ስሜታችሁን አካፍሉኝ። የግድ በአማርኛ ፊደል ለመፃፍ አትገደዱም፤ በእግሊዘኛ ኪይቦርድ ላኩልኝ።በተቻለ መጠን ምላሹ ወዲያውኑ የሚደርሳችሁ ሲሆን አስፈላጊ ከሆነና አስተማሪ መስሎ ከታየኝ ሚስጥራችሁን በጠበቀ መልኩ ጉዳዩን ወደቻናሉ ላመጣው እችላለሁ።
አንድም ሴት ብቻዋን በጭንቀት መታፈን የለባትም፡ ይህ የሴቶች ቤት ነው! በነፃነት ተንፍሱበት!!
መልካም አዳር
@Fevis_bot
@heewans
ወንዶችና ወሲብ
💁♀ሰላም እህቶቼ ተመልሻለሁ
ከላይ አንዲት እህታችን ባነሳችው ጥያቄ ላይ ተመርኩዤ ጥቂት ማለት ስለፈለኩ ነው።
በውስጥ መስመር ከሚላኩልኝ ጥያቄዎች አብዛኛውን እጅ የሚይዘው ይህ ጥያቄ ነው። " ፍቅረኛዬ ወሲብ እናድርግ ይለኛል፥ እኔ ግን ዝግጁ መሆኔን እርግጠኛ አይደለሁም" አይነት ነገር:: ለሁሉም እንደያሉበት ሁኔታ ተገቢውን ሃሳብ እሰጣቸዋለሁ።
አንድ የስነልቦና መፅሐፍ የወንዶች ጭንቅላት ብዙውን ግዜ ወይ ስለወሲብ ወይ ስለምግብ ነው የሚያስበው፥ ባልሽ የወሲብ ስሜት ላይ ከሌለ ያለጥርጥር ስለምግብ እያሰበ ነው፡ ሳንድዊች ስሪለት" ይላል። ነገርየው ቀልድ ቢጤ ቢመስልም እውነታው ግን በርግጥም ወንዶች sexን የromantic ህይወት #ዋነኛ አካል አድርገው መውሰዳቸው ነው።
በዚህም ምክንያት ፍቅር ውስጥ ስትሆኑ ወንዶች ይሄን ነገር ማንሳቱን ይጀምራሉ።
❓Sex መች ነው መደረግ ያለበት?
ስለሴክስ ርዕስ ሲነሳ ሁሌም አካብጄ ነው ማየው! በዚህ ጉዳይ ጓደኞቼ " ወግ አጥባቂ" አድርገው ይወስዱኛል። ግን ወግ አጥባቂነት አይደለም፡ የሴት ህይወት ትልቁ issue ነው ለኔ!!
ጤናማና አግባብ ያለው ወሲብ በትክክለኛው ጊዜ ከትክክለኛው ሰው ጋር ብታደርጊ በጣም ነው ደስተኛ የምትሆኚው። ግን ያንኑ ያህል ደግሞ የተሳሳተ አካሄድ ውስጥ ካለሽ ትልቅ ዋጋ ያስከፍልሻል።
Sex ከማድረግሽ በፊት እነዚህ ነገሮች ከግምት አስገቢ
👉በሙሉ ፍቃደኝነት ላይ መሆንሽንና አለመገፋፋትሽን እርግጠኛ ሁኚ
👉በአልኮልና መሰል ማነቂያቂያ እንዲሁም በከፍተኛ ወረትና ትኩስ ስሜት ውስጥ አለመሆንሽን አረጋግጪ
👉 አብረሺው የምትተኚው ሰው ምንም ነገር ቢፈጠር እንደማይከዳሽ ማወቅ መቻል አለብሽ
👉የምታደርጊው ነገር ከእምነትሽ አንፃር ስህተት መሆን አለመሆኑን አስቢ
👉 ምናልባት የምታደርጊው በትክክለኛ ጊዜ ካልነበረ ተገቢውን መከላከያ ማዘጋጀትሽን አረጋግጪ
👉ከተኛሽበት ስትነሺ እንደማይፀፀትሽ እርግጠኛ ሁኚ
ከነዚህ መስፈርቶች አንዱ እንኳን ከጎደለ በምታደርጊው ነገር እንድታስቢበት ልነግርሽ እፈልጋለሁ ፤ ይህ መልዕክት ለሁላችሁም ነው።
ብልህ ሴት በተለያዩ ነገሮች የምትገፋፋ ሳይሆን የራሷ ምርጫ እና ፍላጎት ያላት እንዲሁም ስለምታደርገው ነገር ሌላ ሰው እንዲያስብላት የማትፈልግና አሳማኝ ከሆነ ብቻ የምታደርግ ናት።
በጥቂት ደቂቃ ደስታ የእድሜ ልክ ፀፀት እንዳታተርፊ ሁሌም ከአንድ ትልቅ ድርጊት በፊት ደጋግመሽ አስቢበት። "አስር ጊዜ ለካ አንድ ጊዜ ቁረጥ " እንደሚለው የፖሊስ አባባል ማለት ነው።
መልካም ምሽት🌝
@heewans
🌺የኔ እህት አንድ ነገር ልንገርሽ ወሳኟ አንቺ ራስሽ ነሽ። ምንም ነገር አንቺ ማድረግ ከፈለግሽ it's OK ግን ሳትፈልጊ ማንም ሊያስገድድሽ አይችልም። yanchi smet yewesnewal manen fertesh weym yeman heg asfertosh nw madreg yematfelgiw yefetari weys yebeteseb? Anchi yerasesh heg ale malete semetshen adamchi endeza slesh gn esu lanchi yemigeba aynet wend kehone ena anchi lesu smet kalesh lmn ataregim?
©sem
🌺የሚወድሽ ወንድ እንደደውል የራሱን ሀሳብ ብቻ ተናግሮ ጆሮውን አይደፍንም የሚወድሽ ከሆነ ይሰማሻል ይረዳሻል ይ*ረዳሻል በዚህ ጉዳይ የፀና አቋም ያዢ እሱ ብቻ አይደለም ስሜት ያለው አንቺም አለሽ እሱ ብቻ አይደለም መብት ያለው አንቺም አለሽ እሱ ከፈለገ አንቺ ያለመፈለግ ደግሞ አትርሺ ከፍቅረኛሽ አምላክሽ ይበልጣል!! ውድ የዛሬ ውሳኔሽ እስከሂወትሽ መጨረሻ አብራሽ ናት ወይ ታኮራሻለች ወይ ትሰብርሻለች አ ስ ቢ በ ት!
©Netsi
🌺እኔም አጋጥሞኛል። ይሄን ጥያቄ መጠየቅ የጀመረው በጓደኞቹ ግፊት ነበር ግን እኔ በሀሳቤ ፅኑ ስለነበርኩ እንደማይሆን ስነግረው በግዱ እሺ አለኝ እውነት ለመናገር በጣም ሚገርም ስብዕና ነው ያለው ቢሆንም ግን ይሄን ሀሳቡን መተው ስላልቻለ ያንቺው ፍቅረኛ እንዳለሽ ካላረግ እናቆማለን አለኝ ላስብበት እንኳን አለልኩትም ምክንያቱም ምን እንደምፈልግና ምን እንደሚገባኝ አውቅ ነበረ ብቻ ተለያየን እኔም የራሴን ሂወት ቀጠልኩ እሱም የ ፈለገውን አገኘ ሚገርሽ ያ ሁሉ ከተፈጠረ ቢያንስ 5 ዓመት ይሆነዋል ከዚ ሁሉ ግዜ በኅላ ተፀፅቶ አብረን እንድንሆን ጠይቆኛ ከኔ ሌላ ፍቅረኛ መያዝ ከልቻለም ተጎዳ እኔ ግን ክብሬን ሚያከብርልኝን አጊንቼ ደስተኛ ሆኛለው
ግን ክብራቸውን value ያልሰጡ or የተሸወዱ ብዙ ሴቶችን አይቻለው በጣም ፀፀት አለባቸው እና እህቴ ዛሬን ሳይሆን ራስሽን ነገ ላይ አስቀምጠሽ አስቢው
እና ሁል ግዜም ያንቺ or የ ሴትነት ተፈጥሮሽ ምንያህል ውድ ዋጋ እንዳለው አትርሺ
©Ra
ይህ ጥያቄ የብዙዎቻችሁ ስለነበረ ነው ቅድሚያ ያቀረብኩት፤ ከዚህ ጋ የተያያዘ ገጠመኝ ያላችሁ ወይም ለእህታችን ሐሳብ መስጠት የምትፈልጉ @Fevis_bot ላይ startን በመጫን ሐሳብ ስጡ💁♀
Читать полностью…
ይድረስ ለአዲስ ተመራቂ ተማሪዎች በተለይ ለሴቶች❗️
(ክፍል 2)
በአለባበስ፣ በአነጋገር፣ በስራ ትጋት፣ በሰዓት አጠቃቀም እና በእውቀት ልቀሽ በመገኘት ራስሽን አክብሪው። ወንዶች እንዲህ አይነት ቁምነገረኛ ሴቶችን ያከብራሉ ፤ ግፋ ሲልም ለሕይወት አጋርነት ከልባቸው የሚመኙት እነዚህን ነው። ስለዚህ ምርጫው ያንቺ ነው።
በእርግጥ አንዳንዴ ጫናው በጣም ይበረታል። አሰሪዎቻችሁ ወስላታ ሆነው በእንጀራችሁ እና በሕይወታችሁ ይመጣሉ። በቅርብ የማውቃት በአንድ ትልቅ ሆቴል ውስጥ በ "Front Office (Reception)" የምትሰራ ልጅ በዚሁ ጉዳይ ተቸግራ የበላይ ሀላፊዋ በጣም ሲያስቸግራት ስራውን ትታ እንደወጣች ነግራኛለች። በየዩኒቨርስቲው፤ ሴትነታቸውን ፈልገው በመምህራን ውጤት የተበላሸባቸው (እየተበላሸባቸው) እንደሆነ ሴት ጓደኞቼ ብዙ ናቸው።
እኔ የምመክርሽ፤ ሁሉም ነገር ካንቺ ክብር ካንቺ ሴትነት እንደማይበልጥ ነው። ዛሬ ለማግኘት ብለሽ ራስሽን(ሴትነትሽን) አሳልፈሽ የምትሰጪለት ነገር፤ ነገ ላይ ተራ ሆኖ ስታገኚው ጸጸቱ አይለቅሽም። እናም በስራው አለም ስትገቢ (ስራም ላይ ካለሽ) ወሲባዊ ትንኮሳ ዋናው ፈተናሽ ነው። ስለዚህ እጅ ሳትሰጪ በጥበብ እለፊው። አንዴ ከገባሽበት መውጫው ከባድ ነውና። በአንድ የሬድዮ ፕሮግራም ላይ በሆቴል መስተንግዶ የምትሰራ ልጅ እንዲሁ ከደንበኛ የሚመጣን ትንኮሳ እንደቀልድ (በጊዜው ለገንዘብ ብላ) ገብታበት ለምውጣት እንደተቸገረች ስትናገር ሰምቻለው። እናም ራስሽን ጠብቂ!
☀️ የስራ ጫና ➕ የቤተሰብ ኃላፊነት
ሴት በተፈጥሮ ወደ ቤተሰብ እንደምታደላ ሃይማኖቱም ሳይንሱም ያረጋገጡት ነው። ኃላፊነት ይሰማታል። ስራ ላይ ስትሆኚ ከስራው በተጨማሪ የቤተሰብሽ ነገር ያሳስብሻል። ስራ ቦታ አካልሽም አእምሮሽም ደክሞ፣ ዝሎ እንደገና ቤት ገብተሽ ሌላ ኃላፊነት ይጠብቅሻል። በተለይ ካገባሽ እና ልጆች ከመጡ በኋላ ጫናው ይበረታል። ግን ቀላል ነው። ካንቺ የሚበልጥ ነገር የለም። ከቤተሰብ ጋር በመመካከር፣ ሞግዚት በመቅጠር፣ ከትዳር አጋርሽ ጋር የስራ ክፍፍል በማድረግ ነገሮች ከአድካሚነታቸው ይልቅ አዝናኝ እንዲሆኑ ማድረግ ትችያለሽ።
~ ቢያንስ በሳምንት አንዴ የጥሞና ጊዜ ይኑርሽ (ቤ/ክ ወይም መስጊድ እንደ እምነትሽ ሄደሽ ለደቂቃዎች ከጸጥታው ጋር አውሪ)
~ ዜማ ነገር አድምጪ፤ "Mental Therapy" ስለሆነ
~ ከባልሽ፣ ከፍቅረኛሽ፣ ከጓደኛሽ ጋር Silly የሆነ ወሬ አውሪ፣ ወክ አርጊ ብቻ
"Let Your Brain Have a Break"
~ ስለዚህ ለነገሮች ከወዲሁ "Mental" እና "Physically" ተዘጋጂ
☀️ የስራ ተቀናቃኝ (Gossip People)
እስካሁኑ ሰአት ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥም ውጭ ሀገርም ያስተዋልኩት እና በጣም የገረመኝ "Common" ነገር የትም ሀገር ብንሄድ፣ የትኛውም የስራ መስክ ውስጥ "ወሬ ለማመላለስ የተፈጠሩ" እስኪመስሉ ድረስ ስራቸውን ትተው ወሬ ሲያባዝቱ የሚውሉ ሰዎች አሉ። ሴትም ወንድም ሊሆኑ ይችላሉ። ዋና መገለጫቸው የሚሰራ ሰው ላይ እንከን እየፈለጉ መክሰስ፣ አቃቂር ማውጣት፣ ፊት ለፊት ከመጋፈትጥ ይልቅ ከጀርባ ማማት አውርቶ አደር ናቸው። ከእነዚህ አይነት ሰዎች ጋር አትደመሪ። መቼም አታድጊም። እነዚህ ባሉበት ነው የሚረግጡት። ምን ተሰራ ሳይሆን ምን ተወራ ነው አጀንዳቸው። "Stay Away From Them" ትኩረትሽ ስራሽ እና ስራሽ ላይ ብቻ ይሁን!
ስራ ቦታ ካሉ ሰዎች ጋር መጠነኛ ቀረቤታ ይበቃል። ሲበዛ መናናቅ ይመጣል። ስራ ቦታሽ የሕይወትሽን ረጅሙን ጊዜ የምታሳልፊበት ስለሆነ አንዴ ከሰው ጋር ከተናናቅሽ ስራሽን ሁሉ ያበላሻል። ከሰላምታ እና ስራ ነክ ከሆኑ ጉዳዮች ውጭ ቀልድ በስራ ቦታ ጉዳቱ ያመዝናል። "Keep Your Distance!" ለምንድነው በት/ቤትም በድርጅትም ያሉ አመራሮች "Serious" እና "Silent" የሚሆኑት? መጫወት እና መቃለድ ጠልተው አይደለም። ግን ለስራቸው ጤናማነት በማሰብ ነው። አንቺም እንደዛው አድርጊ። ከሚመጥኑሽ ሰዎች ጋር፣ እውቀት፣ ልምድ እና እርጋታ ካላቸው ሰዎች ጋር ተቀራረቢ።
ውዷ እህቴ ለዛሬ በዚህ ይብቃን። ትንሽም ቢሆን ትምህርት እንዳገኘሽበት ተስፋ አደርጋለሁ። ውስጥሽ ያለውን "Potential" ተጠቅመሽበት ሀገርንም ወገንንም እንደ ምታስመሰግኝ ተስፋ አለኝ። ምክንያቱም ትችያለሽ!!! ምክንያቱም ሴት ነሽ!!!
መልካም ጊዜ❕❕❕
እነዚህ መፅሐፍት ስለሴትነትና ፈተናው ብዙ ስለሚያስተምሩ ብታነቢያቸው ይረዱሻል 👇
📚 ፈተና
📚 የህይወት ስንቅ
📚 ብርቅርቅታ
📚 የቀን ጨለማ
✍️ አዘጋጅ F.K
⤴️ ይህንን ጽሁፍ፤ ለእህቶቻችን በማጋራት ተባባሩን❗️
@Heewans
የምትፈልጊው ወንድ መስፈርት……
ሰላም እንዴት ናችሁ ንግሥቶች።
በinbox ( @fevis_bot ) ከአንዲት እህቴ ጋር ሳወራ ትዳር ሳትይዝ ብዙ ጊዜ መቆየቷን እንዲሁም ቤተሰቦቿ በዚህ ምክንያት ተፅዕኖ እንደሚያደርጉባት ሹክ አለችኝ።
ከዚያ ከወንዶች ጋር ስላላት ቅርበት እና የምትፈልገው ወንድ ምን ዓይነት እንደሆነ ጠየቅኳት - ነገረችኝ
ብቻ ምን አለፋችሁ ስጋ የለበሰ መልዓክ ሳለችልኝ☺️ In my heart i said " Look hony that is why you are still single"
እስኪ እስካሁን ያላገባችሁ የምትፈልጉት ወንድ መስፈርት ምንድነው። አደራችሁን ምድር(እውነተኛው ዓለም) ላይ የሌለ ወንድ እየሳላችሁ በillusion ደንዝዛችሁ ጊዜ አልፏችሁ አይሒድ ውዶችዬ።
እስኪ ራሳችሁን ተመልከቱ ፀጉራችሁ መቀመጫችሁ ጋር የሚደርስ፡ እንደዘፈን ግጥም ወይም እንደ ልብወለዶቹ ገፀባህሪያት ዓይናችሁ በጣም የሚያምር፣ ቆዳችሁ ጥርት ያለ፣ ድምፃችሁ ወፍ የሚያረግፍ፣ ቁመናችሁ ሎጋ ፣ አፍንጫችሁ ሰልካካ፣ ወገባችሁ ችቦ አይሞላም የሚባለውን አይነት ሴት ናችሁ?☺️ No! that is artistic characteristic.
ከላይ ካሉት ነገሮች የተወሰኑትን ብታሟሉ እንኳ የሆኑ እንከኖች አሏችሁ። በቃ ሁሉ ነገር አይሞላላችሁም። ጠቢቡ ፈጣሪ በራሳችን እንዳንኮፈስ ይመስለኛል ከሆነች እንከን ጋር የሚፈጥረን
So አንቺ perfect ካልሆንሽ ለምን ወንዶችን በዚያ መልኩ ትስያቸዋለሽ። ያንቺ ወንድ የተሳለው በፈርጣማ ሰውነቱ፡ በኢኮኖሚ አቅሙ፣ በቤተሰብ አክባሪነቱ፣ የእምነት ሰው በመሆኑ፣ በጊዜ ሰጪነቱ፣ በተደማጭነቱ፣ በተጫዋችነቱ፣ በተንከባካቢነቱ … አንድ ላይ አጠቃሎ የያዘ ወንድ ይሆን?😄😄😄 Dear stop it
Wake up! This is real world. ያንቺ የእምነት ሰው ወይ ገንዘብ አይኖረውም፤ ወይም ታዋቂ አፍቅረሽ ታማኝነቱ ሲያምርሽ ይቀራል፤ ሰውነቱ የሚያምር ወንድ አገኘሁ ስትዪ ለሴት ክብር የሌለው ሚስቱን መማታት የባልነት ግዴታው የሚመስለው ወንድ ይሆናል ፤…… ስንቱን ልጥቀስላችሁ። Ain't no body perfect በቃ።
ስለዚህ ምን ላድርግ???
Prioritizing የሚባል ነገር ተጠቀሚ
መስፈርቶችሽን ቅደምተከተል/ደረጃ ስጫቸው። ማለትም በጣም ከማትደራደሪበት tolerate ወደምታደርጊው ቅደምተከተል ሰጥተሽ አስቢው።
#ለምሳሌ
1 እምነታችን አንድ መሆን አለበት
2 ሴት የሚያከብር
3 የተማረ ቢሆን ደስ ይለኛል
4 እኔና ቤተሰባችንን የሚያስተዳድርበት በቂ ገንዘብ
5 ቆንጂዬ ነገር ቢሆን ደስ ይለኛል
6 አነጋገሩ ደስ የሚልና የተረጋጋ
7 ከኔ ረዘም ያለ ነገር ቢሆን
:
:
10…………
አስቡት ይህ መስፈርት ያላት 4 ቁጥር ላይ ያለውን ኢኮኖሚያዊ አቅም ከ 1'ኛ ደረጃው እምነት ጋር ጭራሽ አታወዳድረውም። ወይም ደግሞ ሌሎቹ መስፈርቶች ተሟልተው መስፈርት 6፣ 7፣8 ፣9 እና 10 ባይሟሉ tolerate አድርጋ ለዚያ ወንድ ዕድል ትሰጠዋለች ማለት ነው😊 አሁን ግልፅ ነው ውዶችዬ?
እስኪ ያገባችሁ መስፈርታችሁ ምን ምን እንደነበርና ምን ያህሉ እንደተሟላ ንገሩን። ሲንግሎችም መስፈርቶቻችሁን እያየን ፈገግ እንበል እስኪ
ለመተንፈስ 👉 Here
እወዳችኋለሁ😍😍
#share her
@Heewans
What is your insecurity?
ምንድነው የሚያሳስብሽ?
ለዛሬ በአካላዊ ገፅታ ጉዳይ ትንሽ ልበል።
ሁላችንም ስለሰውነታችን ደስተኛ አይደለንም። ትዝ ይለኛል ፍሬሽ እያለሁ ሞላ ያለ ሰውነቴን እንዴት እጠላው እንደነበር☺️☺️
አንቺስ ምንደነው የሚያሳስብሽ?
❓እንደድሮዋ እኔ ወፍራም ነሽ?
❓ በጣም ቀጫጫ ነኝ ብለሽ ታስቢያለሽ
❓ አጭር ነኝ ብለሽ ታስቢያለሽ
❓ከሌሎቹ ጎላ አድርጎ የሚያስተኩር ረዥም ቁመት ነው ያለሽ?
❓ፊትሽ ላይ ነጠብጣብ ወይም ብጉር አለ?
❓ፀጉስሽ በጣም ከርዳዳ ወይም አጭር ነው?
❓ድምጽሽ የወንድ ጎረምሳ የሚመስል/ወፍራም ነው?
❓ጡቶችሽ በጣም ጎላ ያሉ መስሎ ይሰማሻል
❓ ወይንስ ደረትሽ አካባቢ እንዲሁም ዳሌሽ ላይ flat እንደሆነ እና ቅርጽ እንደሌለለሽ ይሰማሻል???…… ፣ሌላም ሌላም
እንግዲያውስ ይሄ መልዕት ላንቺ ነው!! ይህ ሁሉም ሴት የሚብሰለሰልበት የግል ገመናችን ነው። ሁላችንም የየራሳችን ችግር ታቅፈን እሹሩሩ እንላለን። ምናልባት ማንም አያስተውልብን ይሆናል። ግን ሲበዛ እስኪስተዋልብን ድረስ ይጎዳናል።
መቀየር የምትችዪውን ነገር አቅም ሲኖርሽ ትቀይሪዋለች። ተፈጥሮ ያላደለሽን ግን ከየት ታመጪዋለሽ🤷♀ Open Your Eyes!! እራስሽን ተቀበይ አንቺ አንቺ ነሽ በቃ!! ታምሪያለሽ!
ለማህበረሰቡ የቆንጆነት ስታንዳርድ ቦታ አትስጪ። ውጫዊ ነገር በምንም በምን ቆንጆ ይሆናል፡ ውስጥሽ ብቻ እንዳያስጠላ ተጠንቀቂ።
አንብቢ፣ በየቀኑ አዳዲስ ነገር Google አድርጊ፣ life hack ቪዲዮዎችን እዪ፣ ተጠቀሚያቸው፣ ከሰዎች ጋር ተግባቢ፡ ሎተሪ እንደወጣላት ሰው ከልብሽ ፈገግ በይ😊 ከዚያ ፀሐይ ካንቺ ውስጥ የሚወጣ ይመስል የውበት ፀዳል ትጎናፀፊያለሽ።
ከላይ ስለጠቀስኳቸው ስለሁሉም አንደበአንድ እናነሳለን። ምንም ነገር በውስጣችሁ አታብሰልስሉት። አዲስ ተአምር አንቺ ጋር የለምና።
@Fevis_bot ላይ ተንፍሱ፡ ምን insecure ያደርጋቾኋል እስኪ አካፍሉን፡ ስም ሳልጠቅስ ለሌሎቹ ላጋራ። It feels good.
እወዳችኋለሁ❤️
ደህና እደሩ😘
@Heewans
💁♀አሁን ላይ ዓመቱም ወደመገባደዱ እየሔደ ነው።
አምና ብዙ ዕቅዶች የነበራችሁ እህቶቼ ነበራችሁ። እቅዳችሁ ከምን ደረሰ። ለመማር፣ ለማግባት፣ ልጅ ለመውለድ፣ በስነልቦና ጠንካራ መሆን የፍቅር ሕይወታችሁን የማስተካከል፣ የሰውነት ቅርፃችሁንና ክብደታችሁን ለመቀየር የነበራችሁ plan ተሳካ ወይስ በከፊል ብቻ ተገበራችሁት??
አሁንስ ምን ላይ ናችሁ፣ ምን ያስጨንቃችኋል? ምን ይቀራችኋል።
እንደበፊቱ @Fevis_bot ላይ መተንፈስ ትችላላችሁ እሺ። ብልህ ሴት በችግሮች የምታማርር ሳትሆን ነገሮችን እንደአመጣጡ ተቀብላ መፍትሔ የምትፈልግ መሆን አለባት። ሴትነት የጥበብ አርማ ነውና!
እወዳችኋለሁ😘
💄የሊፕስቲክ/ቻፕስቲክ ጥቅም ላንቺ
ብዙዎች በተለይም ኢትዮዽያውያን ስሙን እያቀያየሩ ሲጠቀሙት አስተውላለሁ። almost they are the same ግን አንደኛው ምርት perpose የማለስለስ ፤ የሌላኛው ደግሞ የከንፈርሽን ድምቀት መጨመር ነው። በተለይ እንደወይራ ካሉ Organic ማቴሪያሎች የሚሰሩት የከንፈር ማለስለሻዎች ራሷን መጠበቅ ከምትፈልግ ከማንኛዋም ሴት ቦርሳ አልያም የሜካፕ kit ውስጥ መጥፋት የለባቸውም ብዬ የማስባቸው ምርቶች ናቸው።
👄የሊፕስቲክን ጥቅም ግን በደንብ ተረድታችሁታል? በዘመናዊት በተለይም ራሷን መግለፅና የራሷ ስታይል እንዳላት ማሳየት በምትፈልግ ሴት personality ውስጥ እንደ አንድ መሣርያ ሊወሰድ የሚችል ነገር ነው። የሚሰጠው ስነልቦናዊ ጠቀሜታም ቀላል አይደለም።
💋ከቤት ወጣ ስትዪ በስሱ apply አድርገሽ የምትወጪ የከንፈር ቀለም ግርማሞገስሽና በራስመተማመንሽ ላይ ትልቅ ኃይል ከመጨመሩም በላይ በሌሎች በኩል የሚሰጥሽን ግምትና ክብደትም ይጨምረዋል።
በተለይ የሆነ ፕሮግራም፣ ስብሰባ፣ ፕረዘንቴሽን አልያም date ሲኖርብሽ ከልብስሽ እኩል ስለምትቀቢው የከንፈር ቀለምም ማሰብ አለብሽ
💄ሊፕስቲክ ስላንቺ ማንነት አፍ አውጥቶ ይናገራል። እውነት ነው፣ አንዲት ሴት የምትቀባው ሊፕስቲክ አይነት ፣የተቀባችበት way እና ከሌሎቹ ሜክአፖችና ከልብሷ አንፃር የሚጫወተውን ሚና በአንድ እይታ ገርምመን ይቺ ሴት እንደዚህ አይነት ሰው ነች ብለን በአንዴ ማንበብና መናገር ይቻላል። ስለዚህ የምንቀባውን ሊፕስቲክ ከቆዳሽ ከለር አንፃር ከምትገኚበት ጉዳይ አንፃር እንዲሁም ከምትለብሺው ልብስ አንፃር በደንብ ቢመረጥ መልካም ነው።
💄ግን በርካቶቻችሁ ታዳጊዎች/ተማሪዎች ከመሆናችሁና የአብዛኛውን የቤተሰብ አቅም ስለሚታወቅ እንደዚህ አይነት ነገር ላይ መጨነቅና ማወሳሰብ አያስፈልግም እሺ። ያ ማለት ደግሞ አቅም የለኝም ብለሽ ራስሽን መጣል የለብሽም። ወይም ደግሞ የምወጣበት ጉዳይ የለኝም ብለሽ ራስሽን care ማድረግ መተው የለብሽም።
💁♀ራስሽን ለመጠበቅ የግድ የብራንድ ተከታይ መሆንና ውድ product መግዛት የለብሽም። ባለሽ አቅም ራስሽን በደንብ መንከባከብና ቆንጆ ማድረግ ትችያለሽ።
ከዚህ አንፃር በተለይ ከሰውነታች ጋር በሚሄዱ ስታይሎችና Color match ጉዳይ እንደሌሎቹ ጉዳዮች @Fevis_bot ላይ ልታማክሩኝ ትችላላችሁ
እወዳችኋለሁ😍 ገና ብዙ ምናወራው ነገር አለ!
@Heewans
ሰላም እንዴት ናችሁ። ትላንት ባነሳሁት ሃሳብ ላይ አብዛኞቻችሁ አስተያየት ሰጥታችኋል። ሃሳቦቹ በሁለት ወገን ሆነው አብዛኞቹ ተመሳሳይ ስለሆኑ አንድ ሁለቱትን ለsample ላቅርባቸው
🌺Ri
ፌቪ ይቅርታ አርጊልኝና ካምፓስም ገብተን ወጥተን አይተነዋል። ላይፍ ልይ ካላላሽ በስተቀር እቺ ልጅ ለምን ብላ ክፍለአገር ትሔዳለች ለምንስ እዛው ያለችበት ከተማ ኮሌጅ አትማርም አቅም ካላት: ( መለያየቱን እሷም ማትወደው ከሆነ)
🌺Mah
I would choose to pursue my education. There should be no doubt about this.
በርሷ እድገት የማይደሰት ሰው ከሆነ በቃ he is not the one. He should be confident with the bond they built and let her be a better person.
May be what we don't see when we are in love is the value of ourself and our family. They want us to be better human being so we should not compromise it in the name of love. Because that is not love እኛ ይመስለናል እንጂ።
So for all the HEWANS out there please Please work on your self first lets not disrupt the ladder of human being it should be our thing after we accomplishes something we are proud of. If not it should at least not block us away from success and our dream
🌺Hil
Okay iam a campus student too ena I have a boyfriend it’s been 2 years since we are together Ik long distance relationship is hard but if yu guys don’t want to breakup or last እንዲያደር ከፈለጋችሁ just talk ፣ መጀመሪያ ተማመኑ it will be hard if yu guys don’t love each other enji in my opinion ጭራሽ ያላችሁን ነገር ነው ሚጨምረው
🌺Muna:
ልጅቷ ምን እንደወሰነችና ምን እንደተፈጠረ ብንሰማ ደስ ይለኛል። ይገርማችኋል የኔ ተገላቢጦሽ ነው። እሱ ነው ካምፓስ የሄደው እና ምሰማቸው ነገሮች ደስ አይሉም። ማለት ልጁን እየደገፍኩት ሳይሆን አንዳንዴ ሰው ደካማ መሆኑን ስታስቢ ይጨንቅሻል
🌺Bez
ሌዲስ አስባችሁታል ግን ይህ ወንድ ልጅቷ 12'th እንድትወድቅ ሲፀልይ ነበር ማለት ነው። what? no! ይሄ የሕይወት አጋሬ ነው ታድያ። የኔ መለወጥኮ የሱም ኩራት ነው። የምር በዚህ ምክንያት ሊርቃት ከፈለገ በትንሽ ነገር ሊለያት ይችል የነበረ ሰው ነው ማለት ነው። ኧረ በራሴ ሕይወትማ ቀልድ የለም
@Heewans
እንዴት ናችሁ
እስኪ መፅሔት ላይ ያገኘሁትን ፅሑፍ ላካፍላችሁ
🙏❤🙏❤ #አንባቢ_ሴት_ልባም_ትሆናለች 👇👇👇
🙏 ለኔ አማላይ የምላት ሴት አንባቢ ሴት ናት። አንባቢ ሴት አደገኛ ጭንቅላት ነው ያላት ይባላል። አንባቢ ሴት ከሆነች -ሀሜት አይመቻትም-በመቀመጫዋና በጡቷ የበዛ መመካት አታሳይም - ማንኛውንም ርዕስ ከሷ ጋር መጫወት ትችላለህ-ወንዶች አደነቋት አላደነቋት ግድ አይሰጣትም -የራሷ አስተሳሰብ ስላላት የሌላ ሰው ሀሳብን ለማክበር አትቸገርም።
👉ብርቱ ሴት ዋጋዋን ጠንቅቃ ታውቃለች፡፡ ራሷን በቁስ አትተምንም፡፡
👉እልፍ ግዜ ወድቃ ደግማ ደጋግማ የተነሳች ናት፡፡
👉በመሰናክል አትበገርም፣ፅኑ ናት፡፡
👉ከመንገዷ የሚገታት አንዳች ሀይል የለም፡፡
👉ክህደት ፣ አሉባልታ፣ ትችት አያዝሏትም፡፡
👉ህልመኛ ናትና ህልሟን ለመኖር ሰርክ ትተጋለች፡፡
👉ከእውነት ጋር ትጓዛለች እንጂ በነፈሰበት አትነፍስም፡፡
👉ከብዙ ስህተቶቿ ብዙ የተማረች ፣ በፈተና የተሞረደች ናት ብርቱ ሴት፡፡
👉ብዙ ያነባች ብትሆንም ፈገግታ ጌጧ ነው፡፡
👉እርሷ ላመነችበት ቆራጥ ፣ለወዳጆቿ ሟች ናት፡፡
👉ብርቱ ሴት የማይረሳ በጎ አሻራ አላት!
🙏 #ከውብ_ገላ_ውብ_አዕምሮ_ይበልጣል💕
@Heewans
ማጠቃለያ፡-
ውድ እህቶቼ ፡ ወደፍቅር ሳንገባ፥ ፍቅር ላይ ሆነንም ሆነ ፍፃሜውን ካገኘ ግንኙነት በኋላ ውስብስብ ነገሮች ሊያጋጥም ይችላል። ያን ደግሞ በጥበብ ነው ማለፍ ያለብን።
ይቺ እህታችን ያጋጠማት ነገር illution ይባላል። አይናችን ላይ ያምራል ግን በቦታው ላይኖር ይችላል። ከድሮም የሚባል ነገር አለ፡ " አንድ ልብ በአንዴ ሁለት ሰው ማፍቀር አይችልም"
አራት ዓመት አብራው ያሳለፈችው ልጅ ጥሩ እንደሆነና treat እንደሚያረጋት እሷም እንደምትወደው ነግራኛለች። ይህ በሆነበት ሁኔታ ሌላ ስሜት ከተሰማሽ በእውነቱ እውነተኛ ፍቅር ሳይሆን ፈተና ነው! ይሄን ፈተና ጠንክረሽ ካላለፍሽ ሌላ ጊዜ ለሚደርስብሽ መጎዳት ፈጣሪን ለመለማመን የሚያበቃ ንፁህ ልብ አይኖርሽም። ስለዚህ በትዕግስት ጊዜሽን ስራ ላይ አተኩረሽ የወደፊት ባልሽ ሊሆን ወደሚችለው ፍቅረኛሽ ተመለሺ።
እርግጠኛ ነኝ ታደርጊዋለሽ እህታችን!
❤️💝❣
" ፍቅር በየትኛውም ሰዓት ሊመጣላችሁ ይችላል - ግን ሁሌም ስታፈቅሩና ልባችሁን💕 ስትሰጡ ትንሽ ልብ ለራሳችሁ ማስተረፍ ተለማመዱ "
©wise women
#አማክሩኝ (02)
💁♀ እስኪ በዚህ የአማክሩኝ ጥያቄ ሁላችሁም ለመሳተፍ ሞክሩ። ትንሽ ፈታኝ ቢጤ ስለሚመስል ነው ያጋራኋችሁ
ባንዴ ሁለት ሰው ያፈቀራችሁ መስሏችሁ ተሰምቿችሁ ያውቃል? እስኪ ለማንኛውም የልጅቷን ጥያቂ ስሙ👇
<< Hello feven how are u... ለ ማንም መንገር ያቃተኝን ነገር ነው ምነግርሽ... በጣም ምወደው ፍቅረኛ አለኝ ነገር ግን አሁን በ ስራ ምክንያት ያለሁት ሌላ ቦታ ነው። almost አሁን 3 ወር ሆኖኛል ለ ስራ ከ ወጣሁ ግን ሰሞኑን ግራ ሚያጋባ ነገር ገጥሞኛል። 4 አመት ሙሉ ከ ጓደኛዬ ውጪ ማንም ሌላ ወንድ ቀና ብዬ አይቼ ሁላ አላቅም ሰሞኑን ግን አብሮኝ ለ ሚሰራው ልጅ የ ተለየ ስሜት እየተሰማኝ ነው... he's በጣም ጎበዝ engineer ሲያወራ ደስ ይላል ምናምን ... ማታ እራሱ እንቅልፍ አልወስድ እያለኝ ተቸገርኩ.. ብዙ መጨረስ ያለብኝ project እራሱ እያለኝ ስንፍ ማለት ጀመርኩ.... ena beza lay demo ሀጥያት እየሰራሁ መሆኑን እያሰብኩ እራሴን እወቅሳለሁ... so pls give me some advice... i'm in a bad mood... i really need help!! >>
@Fevis_bot ላይ ራሳችሁን በልጅቷ ቦታ አድርጋችሁ ሃሳብ ስጡበት🙏
🌺
የኔ ቆንጆ ህይወት ውስጥ ችግሮችሽ ሳይሆኑ የምትሰጫቸው ምላሾች ናቸው ህይወትሽን ቀላልም ከባድም የሚያደርጉት የአብዛኞቻችን ሴቶች ጥያቄ ይህ ነው ። ፍቅር የሰው ልጅ በሙሉ ልቡ እንዲረካ የሚያደርገው ብቸኛ መንገድ ነው ። ፍላጎት ካለመርካት የሚመጣ ነው ፍቅረኛሽ በፍቅር ውስጥ ቢሆን ኖሮ በሌሎች ፍላጎቶች አይሞላም ነበር ።አሁን እንደማየው ፍቅር ውስጥ ሳይሆን ድርድር ውስጥ ናችሁ ።
ከሁሉም በላይ ከውጪ ከሚደርሱሽ አስተያየቶች በላይ ውስጥሽ የሚልሽ ይበልጣልና እራስሽን አዳምጪ ።
©Min
🌺
እናቴ ሴትነት ማለት ክብር ነው!,,, endi neger agatemogn bayakem bezu metsaf lay anbebewalew miwedesh kehone ena ewnet lanchi migeba mihonesh kehone bezi seat endi ayleshem nber wed mehonesh atzengi atgebiwem,,, kebreshn be fetsum endatachi yene enat atcheneki ayzosh
©Hemr
🌺
የኔ እህት፡ ወንድ ልጅ መቼም ቢሆን መጀመሪያ ሚፈልገው sex ነው፡፡ ሁሌም ቢሆን sexual attraction ስላለ ነዉ እሚቀርቡን ከዛ ነዉ መዋደድ ምናምን እሚመጣው፡፡ ውሳኔው ያንቺ ነው ግን ደግሞ አስቢው መጀመሪያ ለምን እነደማትፈልጊው እምነትሽ/ ቤተሰብ/ይሆናል ወይም ሌላ ምክኒያት ግን ሊያስገድድሽ አይገባውም ሄዳለው ካለ መጀመሪያም ያንቺ አልነበረም ማለት ነዉ፡፡ በምንም ነገር ካስፈራሽ/ካስፈራራሽ ወደፊትም በህይወትሽ ለራሱ ነው1st የሚጨነቀው፡፡ እንደኔ ላመንሽበት ነገር ፅኚ፡፡
©L
እስካሁን በ #አማክሩኝ( 01) ዙርያ የደረሱኝን አስተያየቶች ላጋራችሁ
🌺fev የእሳትራት ታውቂያለሽ? እንደዛ ነው ሆኜ የነበረው። ይሄ ታሪክ ከሞላ ጎደል የኔው ነው። በልደቱ ቀን ፍቅረኛዬ ፓርቲ ነገር ነበረውና ዛሬ ልዩ ቀኔ ነው አብረን ካላደርን ብሎ አስጨነቀኝ። ከዛ ቆይ ላስብበት ብዬው መታጠቢያ ቤት ውስጥ ገብቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ።
ከዛ ባልፈልግም ስለምወደው ብቻ ያን ቀን አደርኩ። ከዛን ቀን በኋላ እየመሰለኝ ይሁን ፍቅሩ ቀንሶ ይሁን አላውቅም ብቻ ተቀይሮብኛል
©Jry
🌺የኔ ቆንጆ እኔም እንደዚ አይነት የፍቅር አጋር ገጥሞኝ ነበር ግን sexም ሆነ kiss ካልተጋባን እንደማናደረግ ነገርኩት በጊዜው ተማሪም ስለነበርኩ,ከዛ ሀሳቤን እንደማልቀይር ሲያውቅ ተወኝ እኔም ሌላ ህይወት ጀመርኩ,አሁን ላይ በውሳኔዬ ደስተኛ ነኝ ክብሬንም ለማንም አታላይ ወንድ ስላልሰጠው በራሴ እኮራለው አንቺም በውሳኔሽ ፅኚ የእውነት እንደሚያፈቅርሽም በዚ ማረጋገጥ ትችያለሽ
©Nd
🌺 እኔም አጋጥሞኛል፡ የገረመኝ እስካሁን በዚህ ጉዳይ እየተነዛነዝን ባለበት time ሃሳቡን ማንሳታችሁ ነው። እኔም ትክክለኛውን ነጥብ መስማት እፈልጋለሁ
©D
🌺ሰላም እህቴ እኔ የምለሽን አድርጊው እያልኩሽ ባይሆንም ግን እንድታስቢበት ይረዳሻል። አንቺም በራስሽ ያለሽ አቁዋም የማያወላውል መሆን አለበት እሱ እሺ ካላሽ እናቁም እያለ እንደሚያስፈራራሽ(ባንቺ አባባል) እንጂ እንደዚ አይነት ፍቅር አይደለም ደግሞ በሀይማኖት ፍፁም ክልክል ነው ለቤተሰብሽም ክብር መኖር አለበት። ስለዚህ ብሁዋላ ከመቆጨት በምንም አይነት መልኩ ፈቃደኛ እንዳልሆንሽ ንገሪው። አንቺ እሱን ተረድተሽው እንደምታስቢው እሱም ሊረዳሽ ግድ ነው የሚወድሽ ከሆነ ካልሆነ ግን አጉል ሆኖም መለያየት አለው አንቺ ልክ ነሽ ፍቅር እውር ነው እያልሽ አንዳታለቅሺ ካሁኑ እወቂበት💪💪👏።እንደሚረዳሽ ተስፋ አረጋለሁ
©Yp
#አማክሩኝ (01)
ከቦይፍሬንዴ ጋር ፍቅር ከጀመርን ስድስት ወር አልፎናል፡ በጣም እወደዋለሁ! ከሚባለው በላይ ማለት ነው።
ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዲስ አመል አመጣ። ማለት S*x ካላደረግን ማለት ጀመረ። እኔ ከበፊቱም አላማዬ ከትዳር በፊት ምንም አለማድረግ ቢሆንም እሱ ግን ተፅዕኖ እያደረገብኝና ሐሳብ ሊያስቀይረኝ እየሞከረ ነው።
ቢያንስ እሺ ትምህርቴን እስክጨርስ እንኳ በkiss እና በመሳሰሉት ነገሮች እንድናሳልፍ ብለምነውም የምትወጂኝ ከሆነ ምን አስከለከለሽ፥ ሴክስ ከሚወዱት ሰው ጋር የሚደረግ ነው፡ ካለፈለግሽ ማቆም እንችላለን እያለ ያስፈራራኛል። በጣም እወደዋለሁ ምን ላድርግ ፡ ስለጨነቀኝ ነው
©Rt
@Heewans
#Repost
ይድረስ ለአዲስ ተመራቂ ተማሪዎች
👩🦳 "በተለይ ለሴቶች" 👩🦳
ከ6 ዓመታት በፊት በማስተማር (Lab Assistant) እሰራበት በነበረው አድማስ ዩኑቨርስቲ መገናኛ ካምፓስ፤ ከተማሪዎች ያስተዋልኳቸውን እና በስራው ዓለምም ላይ የታዘብኳቸው እውነታዎች ይህን እንድጽፍ አነሳሱኝ።
ሁላችንም የተሻለ ኑሮን ስለምንመኝ ነገን እንናፍቃለን። ዛሬ ውስጥ ሙጥኝ ብሎ ያቀፈንን ሞልቶ ያልሞላ ኑሮ ገፍትረን "ነገ" ውስጥ በአበባ ተጠቅልሎ ተስፋችንን ሰርቆ የሚጠብቀንን ከዛሬ የተሻለ የተደላደለ "መኖር" እንደ ተስፋይቱ ምድር እንጠብቀዋለን።
በትምህርት ዓለም ላይ ላሉት በተለይም ብዙ ነገር ለሚያሳስባቸው ሴቶች፤ ይህ ሃሳብ ጠንከር ይላል። ሆኖም ትምህርታቸውን ጨርሰው ወደ ስራ ሲገቡ ለብዙ ነገሮች አዲስ ስለሚሆኑ በቀላሉ ተታለው ያላሰቡት እና ያልጠበቁት ሁነት ውስጥ ራሳቸውን ያገኙታል። እንዳየሁት የስራው አለም ብዙ አስደሳች እና የማደግ እድልን የያዘ እንደሆነው ሁሉ በዛው ልክ ደሞ የሕይወት ቁማር እና ፈተናም አለው። ለሁለቱም የመጀመርያ ገፈት ቀማሾች እኒሁ ሴቶች ናቸው። ቀላል ምሳሌ ለመጥቀስ፣ በስራ ቅጥር ሂደት ላይ ሴት ልጅ በወሊድ ምክንያት የስራ ገበታ ላይ ስለማትኖር ይህ የጊዜ ክፍተት እንዳይፈጠር ብቻ አንዳንድ ድርጅቶች ወንዶችን ወደ መቅጠር ያደላሉ። ሌላው ሴት በሴትነቷ ብቻ የሚደርስባትን ወሲባዊ ትንኮሳ ቢሮው ይቁጠረው።
ታዲያ አንዳንድ ሴቶች በመዘናጋትም ባለማወቅም ለእንዚህ አይነት የሕይወት ፈተናዎች እጅ ሲሰጡ እና ተስፋ ሲቆርጡ ማየት እየተለመደ ነው፤ ለዛሬ ብቻ መኖርን መምረጥ!
በእኔ እምነት ሴት ልጅ በዚህች ምድር ላይ ካሉ ፍጥረታት ሁሉ በላይ እምቅ ብቃት (Potential) አላት። ሴት ልጅ ያላት የአስተሳሰብ ብስለት (IQ) ማንም የለውም። ፈጣሪም ሲፈጥራቸው እንደዛ አድርጎ ነው። የዚህች ምድር ቅመም ናቸው። ግን ይህን ስጦታቸውን ሳይጠቀሙበት ሲቀር ጉዳት ይሆናል።
ባጭሩ ውዷ እህቴ ወደ ስራው ስትገቢ ከሚገጥሙሽ እውነታዎች እነዚህን አወጣሁ፦
🌐 ዝቅ ያለ ግምት(Underestimation)
ይህ በ21ኛው ክ/ዘ እንኳን ስልጡን ነን የሚሉ አገሮችን ጨምሮ አለቀን ያለ ክፉ የአስተሳሰብ መዥገር ነው። Oprah Winfray፤ አሁን ድረስ በዚ ጉዳይ ትሟገታለች። ሴት ስለሆንሽ ብቻ ዝቅ ያለ ግምት ይሰጥሻል። ላንቺ ኃላፊነት ለመስጠት ሰዎች ያንገራግራሉ። ስለ ሚድያው ሳይሆን ታች ስላለው እውነታ ነው የማወራው። ትላልቅ ውሳኔ የሚጠይቁ፣ የመምራት ክሕሎትን የሚሹ፣ ጫና ያለባቸውን ወዘተ የስራ ሃላፊነቶች ትነፈጊያለሽ። ሩቅ ሳትሄጂ ለዚህ ቀላሉ ማሳያ ሴት የሀገር መሪዎች ለምን በቁጥር ሆኑ? ከትንንሽ እስከ አለም አቀፍ ብራንድ ድርጅቶች አመራሩን የወረረው ማን ነው? የምርምር ስራዎች ላይ ከስንት አንድ ሴት ስትገኝ ወሬው ሁሉ እሷ አደል የምትሆነው? ታዲያ ይሄ ኖርማል ነው? ይሄ የሚያሳየው ላንቺ የተሠጠሽን ግምት ነው።
እነዚህ ደረጃዎች ላይ ለመድረስ በጣም ብዙ መስራት ይጠበቅብሻል። የፈለግሽበት ለመድረስ ምንም የሚያግድሽ ነገር የለም። ስትፈጠሪ ከኛ በላይ Mega Minded ሆነሽ ነው የተፈጠርሽው። ተጠቀሚበት!
አንዳንድ ሴቶችን አያለሁ። የተመኙት ስኬት ላይ ለመድረስ የስኬትን መሰላል ከመውጣት ይልቅ ሴትነታቸውን ሲጠቀሙ። እንደዛ አታድርጊ። የተመኘሺው ነገር #የጊዜ እና #የጥረት ጉዳይ እንጂ ወዳንቺ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። እስቲ ስለ ፈረንሳዩዋ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የግል ህይወት Google ላይ አንብቢ። ሞሮኮ ውስጥ እረኛ ነበረች። የ "Newzealand" ሚንስትሯን እያት፤ የሚጠባ ልጅ አቅፋ እያጠባች ፓርላማ ውስጥ ስትሟገት ለስራዋ። አየሽ እንደነዚ በልፋትሽ ብታድጊ ለአለም መንገድ ታሳያለሽ፤ ህሊናሽ ያርፋል፤ ለልጆችሽ Role model ትሆኛለሽ፤ በንቀት ያዩሽ ሁሉ አይናቸው ይሰበራል። ሴትነትሽን ከተጠቀምሽ ግን ለልጆችሽ ምን ልትመክሪያቸው ነው? ህሊናሽስ እንዴት የሰላም እንቅልፍ ያስተኛሻል? እናም ባጭሩ ስራው ዓለም ላይ ለሚያጋጥምሽ Underestimation እጅ ሳትሰጪ፣ ተስፋ ሳትቆርጪ ጠንክረሽ በመስራት በጥረትሽ ይህን ስንኩል አስተሳሰብ ስበሪው።
🌐 ወሲባዊ ትንኮሳ
ይሄኛው ሳስበው የየቀን ውሎሽ ሁለት ነጥብ ይመስለኛል። ልክ እንደ አረፍተነገሩ ማለት ነው። ሁሉም ሴቶች ማለት በሚያስችል ሁኔታ የዚህ ጥቃት ሰለባ ናቸው። በሄድሽበት ሁሉ ትንኮሳ አይቀርም። ውሻ ቀሚስ ለብሳ ብትሄድ ሁላ ከመላከፍ ወደኋላ የማይሉ ጀግኖች አሉ። በተለይ ደግሞ ተቀጥረሽ በምትሰሪበት መ/ቤት ከጥበቃ እስከ አስተዳደር ድረስ በዚህ ይፈትኑሻል። ምርጫው ያንቺ ነው።የምትሰጪው ምላሽ ይወስንሻል። "አፍህ ላይ ህይወት አለ" እንደሚባለው። አሜን ብለሽ ተቀብለሽ ፊት ከሰጠሽ መስራት እስከማትችይበት ደረጃ ልትደርሺ ትችያለሽ። ግን ኮስታራ ከሆንሽ(In a Positive Way) እና ራስሽን ካከበርሽ ማንም ጫፍሽ አይደርስም። ራስሽን አስከብሪ።
ይቀጥላል...
F.K (A.A.Ethiopia)
💥 ይህንን ጽሁፍ፤ ለእህቶቻችን በማጋራት ተባባሩን❗️
@Heewans