historyofislam2 | Unsorted

Telegram-канал historyofislam2 - History of islamic

-

👉ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል) 👉 ቁርአንና የቁርአን ተፍሲር እንድሁም ነብያዊ ሀድሶች 👉ኢስላማዊ ታሪኮች የነብያት የሱሀቦች የሰለፎች የሀገራት የታላላቅ ዳኢዎች ቃሪወች ሌሎችም ታሪኮች ይቀርባሉ ። 👉 እንድሁም ኪታቦች ይቀርባሉ አስተያየት (Comment)በ https://t.me/Abureyaan ፃፉልን እናመሰግናለን

Subscribe to a channel

History of islamic

ሳምንታዊው የእሁድ ሙሀደራ ጀርጀሮ


በመስጀደ ነጃሺ ስለታላቁ ፍትሀዊ የሀበሻ ንጉስ ነጃሺ ለሀቅ ምንያክል እንደቆመና ለሱሀባወች እንደተከላከለ የተደረገ ነሲሀ






በኡስታዛችን አቡ ኒብራስ አላህ ይጠብቀው



ይደመጥ ይደመጥ ይደመጥ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

/channel/Al_Miaraj_11

👇👇👇👇👇👇👇👇/channel/umuhilal1

Читать полностью…

History of islamic

🔴➢ የረመዷን የሁለተኛው ጁሙዓ ኹጥባ በአቡ ኒብራስ...
----

👌 آداب الصوم....❗️
-----
🔴➢ ከሪል ስቴት👈
------ -----===------===----------

🔴➢ /channel/AbuNamuse
--__
🔴➢ /channel/AbuNamuse/1769
------

Читать полностью…

History of islamic

🔴====-----👇 ግብዣዬ 👇-----====🔴

ሐሙስ ማታ በጀግኖቹ ሰፈር ጠካኬ

---- 🔴 ---------------🔴 ------

➢ በጣም አምሽተን ስለነበር ቤተሰብ እንዳይደክሙብን በሚል በኡስታዝ ሙሐመድ ሱሩርና በኡስታዝ ሙሐመድ አብዱ(ሏህ) አማካኝነት ተራዊሓችንን አጠር አድርገን ነበር የሰገድነው...

----- 👇 ---=--- ---------👇 ---------
🔴➢ የኡስታዝ ሙሐመድ አብዱ ቂርአት ስሟትማ.. ❗️
- - -
🔴➢/channel/AbuNamuse
-----

🔴➢/channel/AbuNamuse/1767
---===

Читать полностью…

History of islamic

مصباح:
ኒ ካ ህ ፣ሰ ር ግ ፣ኹ ሉ እ እና ፍቺን የተመለከቱ ሸሪአዊ ድንጋጌዎች

ክፍል 7️⃣

ከባለፈው የቀጠለ ……
18 | P a g e

አህለል ኪታቦች ደግሞ አጋሪያን ናቸውለዚህም ማስረጃው

وَقَالَتِ الْيَهُودُ عُزَيْرٌ ابْنُ اللَّهِ وَقَالَتِ النَّصَارَى الْمَسِيحُ ابْنُ اللَّهِ ۖ ذَٰلِكَ قَوْلُهُم بِأَفْوَاهِهِمْ ۖ يُضَاهِئُونَ قَوْلَ الَّذِينَ كَفَرُوا مِن قَبْلُ ۚ قَاتَلَهُمُ اللَّهُ ۚ أَنَّىٰ يُؤْفَكُونَ(30)

اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَـٰهًا وَاحِدًا ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ(31)

{{አይሁድ ዑዘይር የአላህ ልጅ ነው አለች፡፡ ክርስቲያኖችም አልመሲሕ የአላህ ልጅ ነው አሉ፡፡ ይህ በአፎቻቸው
(የሚናገሩት) ቃላቸው ነው፡፡ የእነዚያን ከነሱ በፊት የካዱትን ሰዎች ቃል ያመሳስላሉ፡፡ አላህ ያጥፋቸው፡፡ (ከእውነት)
እንዴት ይመለሳሉ!

ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ
ያልታዘዙ ሲኾኑ
ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡
ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው።54

በዚህ የቁርአን አንቀጽ ላይ አላህ ስለ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ካወራ በኋላ መጨረሻ ላይ ከሚያጋሩት የጠራ ነው
በማለት ተግባራቸው ማጋራት እንደሆነ ገልጿል።55በመሆኑም ሱረተል በቀራ ላይ ያለው አንቀጽ ሱረት ማኢዳ ላይ
ያለውን ሽሮታል አሉ። ይህ እንግዲህ ከመጀመሪያው መዝሀብ በተቃራኒው ነው የመጀመሪያዎቹ የሻረው ሱረት ማኢዳ
ላይ ያለው ነው የሚል አቋም እንዳላቸው አሳልፈናል። በመሆኑም በነዚህኞቹ ንግግር መሰረት ሱረት ማኢዳ የወረደች
ወደ መጨረሻ ቢሆንም አንዳንድ አንቀጾቿ ግን ከአንዳንድ የሱረት በቀራ አንቀጾች ቀድመው ሊሆን ይችላል አሉ።
ነገር ግን ይህ ማስረጃ ቀጥ ብሎ መቆም የሚችልበት አቅም እንደሌለው በቀላሉ መረዳት እንችላለን እሱም
1. ሱረት በቀራ ላይ ያለው ሱረት ማኢዳ ላይ ያለውን ሽሮታል ሱረት በቀራ ላይ ያለው አንቀጽ ከሱረት ማኢዳ ካለው
ዘግይቶ ነው የወረደው የሚለው ሙግት ምንም ማስረጃ የለውም እንደውም ሱረት ማኢዳ ላይ ያለው ነው የሻረው
የሚለው ይበልጥ ያስኬዳል ምክንያቱም በኡለሞች ስምምነት ሱረት ማኢዳ ከሱረት በቀራ ዘግይታ ነው
የወረደችው56
2. በሁለቱም የቁርአን አንቀጾች አስማምቶ መስራት እየተቻለ አንዱ ሌላውን ሽሮታል ወደሚለው አይኬድም።
ምናስማማበት መንገድ ደግሞ ሱረት በቀራ ላይ የተጠቀሰው ጥቅል ሙሽሪኮችን ከማግባት ያለ ክልከላ ሲሆን
ማኢዳ ላይ ያለው ደግሞ አህለል ኪታቦችን የነጠለ ነው
ሁለተኛ ማስረጃቸው ከከፊል ሰሀቦች የተወራው አህለል ኪታብን በማግባት ላይ የመጣ ክልከላ ነው።ይህን በተመለከተ
ግን አብዛኛዎች ኡለሞች መልስ ሲሰጡ
1. ከኡመር ኢብኑል ኸጣብ የተወራውን በተመለከተ ኡመር ጠላው እንጂ ሀራም ነው አላለም ኢብን አባስም ቢሆን
እንደሚፈቅድ ተዘግቧል57
2. ከአብደላህ ኢብን ኡመርም ቢሆን እንደሚጠላው ተወርቷልና የሱም ክልከላ በሀራምነት ሳይሆን በመጠላት ደረጃ
ነው ያሉ ኡለሞች አሉ።58 የኢብን ኡመርን ንግግር ስንመለከት ግን መከልከሉ ላይ ነው ይበልጥ ጎልቶ ሚያሳየው59
 በዚህም መሰረት በሙስሊም ሀገር ሆኖ ክርስቲያን ሴትን ማግባት የተጠላ ነው ባያደርገው ይሻላል ነገር ግን ቢያገባ
ወንጀለኛ አይሆንም።
2) በካፊር ሀገር (الحرب دار (እየኖረ አህለል ኪታብን ማግባት
የካፊር ሀገር የሚባሉት ከእስልምና ሸሪአ ውጪ ባለ ህግ የሚተዳደሩ ሀገሮች ናቸው። እዛ ሀገር ውስጥ ብዙ ሙስሊሞች
ቢኖሩ እንኳን ሚታዳደሩት በሰው ሰራሽ ህግ እስከሆን ድረስ ሀገሪቷ የካፊር ሀገር ተብላ ትጠራለች ይህ ማለት ግን እዛ
ሀገር የሚኖር በሙሉ ካፊር ነው ማለት አደለም።
አህለል ኪታቦችን ማግባት የሚፈቅደው የቁርአን አንቀጽ በሙስሊም ሀገር ያለንና በካፊር ሀገር ያለን ሳይለያይ በጥቅል ነው
የመጣው።በሙስሊም ሀገር የምትኖር አህለል ኪታብ ከሙስሊም ባል ስር ከሆነች ወደ እስልምና የመሳብ እድሏ የሰፍ
ነው ሚሆነው ነገር ግን በኩፍር ሀገር ላይ በሚኖር ግዜ የበላይነቱን እሷ ወስዳ ወደ ራሷ የመሳብ እድሏ የጠነከረ ነው
በመሆኑም በሙስሊም ሀገር እየኖሩ አህለል ኪታብን ማግባት እንደሚቻል ያስቀመጡ ኡለሞች በካፊር ሀገር ከሆነ
ሚኖረው ማግባት ይችላል ወይ በሚለው ላይ ተኻልፈዋል።
አብደላህ ኢብን አባስ በካፊር ሀገር ሆኖ አህለል ኪታብን ስለማግባት ተጠይቆ እንደማይቻል እንደተናገረ ኢማመል
ቁርጡቢ ጠቅሷል ከኢብራሂመ ነኸኢም እንዲሁ ተወርቷል
_ከዚህ በታች ማብራሪያ ነው ከላይ ለተፃፉት ቁጥሮች 👇🏻_
____
54 ሱረቱ ተውባ 30-31
55 አድዋኡል በያን ኪታብ 1/204-205 ተመለከት
56 መጅሙኡል ፈታዋ 32/178

57 ጃሚል በያን አን ታእዊሊ አየል ቁርአን (2/376 – 378)
58 አህካመል ቁርአን (ሊልጀሳስ1/332-333)
59 ፈትሁል ባሪ (9/416-417)
__
19 | P a g e
ከሀነፍዮች ዘንድ ካፊር ሀገር ያለችን አህለል ኪታብ ማግባት ሀራም ነው የሚሉ አቋሞች ያሉ ሲሆን የተጠላ ነው ብቻ ብለው ያለፉትም አሉ።
የኢማም አህመድንም መዝሀብ በምንመለከት ግዜ ካፊር ሀገር ያለችን አህለል ኪታብ ማግባት አይቻልም ወደሚለው
አቋም ይበልጥ አዘንብለው እናገኛቸዋለን።
ኸሪቂ እንዲህ ይላል
“ስሜቱ እስካላሸነፈው ድረስ በጠላት ሀገር ላይ ሆኖ ትዳር አያደርግም ስሜቱ ካሸነፈው ሙስሊሟን ያገባል....ከነሱ
አያገባም”
ሻፍእዮች በጠነከረ መልኩ እንደሚጠላ ያስቀምጣሉ60
 ከነዚህ የኡለሞች ንግግሮች የምንረዳው ነገር ቢኖር ካፊር ሀገር ላይ እየኖሩ አህለል ኪታብን ማግባትሙስሊም
ሀገር ላይ እየኖሩ እንደማግባት እንዳልሆነ ነው።ካፊር ሀገር ላይ ከሆነ ያለው ጉዳቱ በጣም ያመዘነ ነው።
ካፊር ሀገር ላይ እየኖሩ ክርስቲያንን ማግባት ያሉት ጉዳቶች
1.ኛ ባለቤቱ ክርስቲያን ከሆነች ወደ ሙስሊም ሀገር ለመሰደድ ቢፈልግ ራሱ ለመሰደድ ይቸገራል
2.ኛ ልጁ ወደ እናቱ እምነት ሊሄድ ስለሚችል የክርስቲያኑ ቁጥር ለመጨመር መንስኤ ይሆናል
3.ኛ የሙስሊሙ ቁጥር እንዳይበዛ መንስኤ ይሆናል፦ሙስሊም ሴት ቢያገባ ሲወልድ የሙስሊሙ ቁጥር ይበዛልና
4.ኛ ዘሩ ወደ ካፊር እንዲሄድ መንስኤ ይሆናል
5.ኛ የካፊር ህግ ስር እስካለ ድረስ ቢጣሉና ቢፈታል ልጆቹን ለሷ ይሰጥበታል
6.ኛ እሱ ክርስቲያንን በማግባቱ ሙስሊም ሴቶች የሚያገባቸው ሙስሊም ወንድ በማጣት ይቸገራሉ ከዛም አልፈው
ማይፈቀድላቸው ሆኖ ሳለ ካፊርን በማግባት ከባድ ወንጀል ላይ ይወድቃሉ።
7.ኛ ሚስቱ በቤቱ ውስጥ የምትሰራቸው አስቀያሚ የሆኑ ወንጀሎች ጠላና አረቄ መጠጣትን ይመስል ሁሌ ሲደጋገሙ
ቀስ በቀስ የሱንም ቀልብ ማድረቁ የማይቀር ነው
8.ኛ ቤቱ ውስጥ የምትሰራውን የኩፍር ተግባራቶች ሲያስተዋት አለመቻሉ እያደር ለቀልቡ መድረቅ መንስኤ ይሆነዋል
9.ኛ የሚኖረውም ከሀዲያን በሚበዙበት ሀገር እንደመሆኑ መጠን የሷ ተጽእኖ ከመሀበረሰቡ ጋር ተደምሮ እሱንም
መንገድ ሊያስቱት

Читать полностью…

History of islamic

ኒ ካ ህ ፣ሰ ርግ፣ኹ ሉ እ እና ፍቺን የተመለከቱ ሸሪአዊ ድንጋጌዎች


ክፍል 6️⃣

ከባለፈው የቀጠለ ……

16 | P a g e

1) በሙስሊም ሀገር እየኖረ አህለል ኪታብን ማግባት
የሙስሊም ሀገራት የሚባሉት በእስልምና ሸሪአ የሚታዳደሩ ሀገራት ናቸው።እዛ ሀገር ውስጥ ክርስቲያኖች ቢኖሩበትም
ማለት ነው።
በሙስሊም ሀገር ውስጥ እየኖሩ አህለል ኪታብ የሆነችን ሴት በማግባት ላይ ኡለሞች የተለያየ አቋም አንጸባርቀዋል።
ይህንንም የኡለሞች አቋም በአጭሩ ሳስቀምጠው
የመጀመሪያው መዝሀብ፦
አራቱን አኢማዎች ጨምሮ አብዛኛዎች ኡለሞች ያሉብት ሲሆን እሱም ማግባት ይቻላል ነገር ግን ይጠላል የሚል ነው።
ከሀነፍይ ኡለሞች መሀከል ኢማም ሰረኽሲ38 እንዲህ ይላል፦
“ባሪያ ያልሆነችን አህለል ኪታብ ሙስሊም ቢያገባት ችግር የለውም”
39
ከማሊኪይ ኡለሞች መሀከል ደርደሪ 40 እንዲህ ይላል
“.....ጨዋ የኪታብ ባለቤት የሆነች ሴት ስትቀር እሷን ማግባት ኢማሙ (ማሊክ) ዘንድ ከመጠላቱ ጋር ይፈቀዳል።41
ከሻፍእያ ኡለሞች መሀከል ኢማመ ነወዊ42 እንዲህ ይላል፦
“አህለል ኪታብ የሆነች ሴት ማግባት ይፈቀዳል ነገር ግን ሀርብይ (በካፊር ሀገር ምትኖር) ከሆን ይጠላል ዚሚይንም
(በሙስሊም ሀገር ምትኖርም ከሆን) እንዲሁ ትክክለኛ በሆነው አቋም መሰረት እሷን ማግባቱ ይጠላል”
43
ከሀናቢላ ኡለሞች መሀከል ኢማመ ኢብን ቁዳማ44 እንዲህ ይላል፦
“በላጩ አሀለል ኪታብ የሆነችን ሴት ባያገባ ነው”
45
ኢማም ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላል
“በቁርአን ግልጽ ማስረጃ መሰረት አህለል ኪታብ ሴቶችን ማግባት ይቻላል...........አብደላህ ቢን አህመድ እንዲህ ብሏል
((አባቴን (ኢማም አህመድን) ጠየቅኩት ሙስሊም ወንድ ክርስቲያን ወይም አይሁድ ሴትን ስለማግባት። እንዲህ አለኝ፦
ይህንን ሊሰራ አልወድም ከሰራውም በርግጥም ከፊል የነብዩ ባልደረቦች ሰርተውታል))”46
እነዚህ ኡለሞች ማስረጃ ያደረጉት ከቁርአን እና ከሰሀቦች ተግባር ነው
የመጀመሪያው ከቁርአን ያሳለፍነው ነው እሱም

ۖ وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الْمُؤْمِنَاتِ وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَا آتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَافِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِي أَخْدَانٍ ۗ



_ከዚህ በታች ማብራሪያ ነው ከላይ ለተፃፉት ቁጥሮች👇🏻_

_
38 ስማቸው ሙሀመድ ቢን አህመድ ቢን አቢ ሰህል አሰረኽሲ ሲሆን በ490 ዓ.ሂ ነው የሞቱት ። መብሱጥ የተባለው ኪታባቸው
በሀከፊይ መዝሀብ ከተጻፉ ኪታቦች ውስጥ ትልቁ ነው ይህንን ኪታብ የጻፉት እስር ቤት ሆነው እንደሆን ይነገራል። ሰርኸሲ
የሀገራቸው ስም ነው ኹራሳን ላይ የምትገኝ ትልቅ ከተማ ናት

39 መብሱጥ 4/210

40 ስማቸው አቡ በረካት አህመድ ቢን ሙሀመድ ቢን አህመድ ሲሆን 1201 ዓ.ሂ ሀገራቸው ሚስር (ግብጽ) ነው
41 አሸርሁ ሰጊር 2/420

42 ስማቸው አቡ ዘከርያ ያህያ ቢን ሸረፍ አልሀዛሚ አነወዊ ሲሆን የኖሩት ከ 631- 676 ዓ.ሂ ነው በኢማሙ ሻፍእይ መዝሀብ ላይ
ከሚታወቁ ትልልቅ ኡለሞች መሀከል አንዱ ናቸው

43 ሚንሀጅ 3/187

44 ስማቸው ሙወፊቁ ዲን አቡ ሙሀመድ አብደላህ ቢን አህመድ ቢን ቁዳማ ሲሆን የኖሩት ከ 541 – 620 ዓ. ሂ ነው ።ሙግኒ
የተባለው ኪታባቸው በፊቅህ ላይ ከተጻፉ ትልልቅ ኪታቦች መሀከል በዋነኝነት የሚጠቀስ ነው
45 ሙግኒ 7/129

46 አህካም አህሉ ዚማ (2/795)
_____

17 | P a g e
{ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና (ዝሙተኞች) የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች
ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ (ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው)}47
በብዙዎቹ ኡለሞች አቋም መሰረት ይህ ሱረት ማኢዳ ላይ ያለው የቁርአን አንቀጽ በሱረት በቀራ ላይ ያለውን
ሙሽሪኮችን አታግቡ ከሚውን ክልከላ አህለል ኪታቦችን ሚነጥል ነው።ምክንያቱም ሱረት ማኢዳ ወደ መጨረሻ
ከወረዱ የቁርአን ሱራዎች መሀከል ናት። እንደውም አንዳንድ ኡለሞች ሱረት ማኢዳ ላይ የተሻረ ምንም ድንጋጌ
የለበትም እስከማለት ይደርሳሉ።
ሌሎች ኡለሞች ደግሞ ቀደሞውኑ ሱረት በቀራ ላይ የመጣው ክልለከላ አህለል ኪታቦችን አይመለከትም ምክንያቱም
ቁርአን ላይ በብዙ ቦታዎች ላይ እንደምንመለከተው ሙሽሪክ በሚለው ገለጻ አህለል ኪታቦች አይካተቱበትም ይላሉ።48
ያ ማለት ግን አህለል ኪታቦች ሽርክ አይሰሩም ነበር ማለት አደለም ኢሳን ጌታ አድርገው እንደተገዙት እዛው ሱረት
ማኢዳ ላይ ተጠቅሷል።
ሁለተኛው ደግሞ ከሰሀቦች ተግባር ነው
ከሰሀቦች መሀከል ጠልሀ ቢን ኡበይዱላህ ፣ሁዘይፋ ቢን የማምና ኡስማን ቢን አፍን አህለል ኪታብ ሴቶችን
ማግባታቸው ተወርቷል49
ሁለተኛው መዝሀብ
ሙስሊም ሀገር ላይ ቢሆኑም እንኳል አህለል ኪታቦችን ማግባት አይቻልም የሚል ነው።ይህ ከታላቁ ሰሀብይ አብደላህ
ኢብን ኡመር የተወራ ነው
ሰረኽሲ እንዲህ ይላል
“ኢብን ኡመር ይህን (የአህለል ኪታብ ሴት ማግባትን ) አይፈቅድም ነበር አህለል ኪታቦች ሙሽሪክ ናቸው ይል ነበር”
50
ኢብን ሀዝም እንዲህ ይላል
“ከአብደላህ ኢብን ኡመር አህለል ኪታቦችን ከማግባት መከልከሉን ዘግበናል”
51
ኢብን ጀሪር ከኡመር ቢን ኸጣብና ከአብደላህ ኢብን አባስም ይህንን የመሰለ አቋም ጠቅሷል52
የአህለል ኪታብ ሴቶችን ማግባት አይቻልም ያሉት አንደኛ ማስረጃ ያደረጉት በቁርአን ላይ አላህ ሙሽሪኮችን ከማግባት
መከልከሉን ነው።አላህ( سبحانه وتعالى (እንዲህ ይላል፦

وَلَا تَنكِحُوا الْمُشْرِكَاتِ حَتَّىٰ يُؤْمِنَّ ۚ

{{ (በአላህ) አጋሪ የሆኑ ሴቶች እስከሚያምኑ ድረስ}}53


_ከዚህ በታች ማብራሪያ ነው ከላይ ለተፃፉት ቁጥሮች 👇🏻__________________
47 ማኢዳ 5

48 ሙግኒ (7/129) እና መጅሙአል ፈታዋ (22/178)

49 ጃሚኢል በያን አን ታእዊሊል ቁርአን (2/332-376) አህካም አህሉ ዚማ (2/795)
50 መብሱጥ 4/210

51 ሚህላ 9/445

52 ጃሚኢል በያን 2/376

53 አል በቀራ 221
___

(ገፅ16-17)ድረስ

✍🏻ይቀጥላል ……ኢንሻአላህ

@historyofislam2

Читать полностью…

History of islamic

በመካነሰላም የነበረ ነሲሀ




በጎርደ መስጅድ (መስጅደ ፈትህ)

@historyofislam2
@historyofislam2

Читать полностью…

History of islamic

በመካነሰላም የነበሩ ጥያቄዎች


🎤 በአቡ ኒብራስ

በጎርደ መስጅድ (መስጅደ ፈትህ)

@historyofislam2
@historyofislam2

Читать полностью…

History of islamic

በመካነሰላም የነበረ ነሲሀ



በጎርደ መስጅድ (መስጅደ ፈትህ)

@historyofislam2
@historyofislam2

Читать полностью…

History of islamic

ኒ ካ ህ ፣ሰ ር ግ፣ኹ ሉ እ እና ፍቺን የተመለከቱ ሸሪአዊ ድንጋጌ ዎች

ክፍል 5️⃣
ከባለፈው የቀጠለ……

15 | P a g e

6. ዝሙተኛ ሴትን ከዝሙቷ እስክትቶብት ድረስ ማግባት አይፈቀድም ዝሙተኛ ወንድንም እንደዚሁ
ከዝሙቱ እስኪቶብት ድረስ ልታገባው አይፈቀድላትም። አላህ (سبحانه وتعالى (እንዲህ ይላል

الزَّانِي لَا يَنكِحُ إِلَّا زَانِيَةً أَوْ مُشْرِكَةً وَالزَّانِيَةُ لَا يَنكِحُهَا إِلَّا زَانٍ أَوْ مُشْرِكٌ ۚ وَحُرِّمَ ذَٰلِكَ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ

[ ሱረት አል-ኑር፣ - 3 ]

{ዝሙተኛው ዝሙተኛይቱን ወይም አጋሪይቱን እንጂ አያገባም፡፡ ዝሙተኛይቱንም ዝሙተኛ ወይም አጋሪ
እንጂ አያገባትም፡፡ ይህም በምእምናን ላይ ተከልክሏል፡፡}
36
በዚህ አንቀጽ ላይ በግልጽ እንደምንመለከተው ይህ (ዝሙተኛን ማግባት) በምእመናኖች ላይ እርም
እንደተደረገ ተነግሯል
ባሪያን ስለማግባት ያለን ብይን ያላመጣሁት በዚህ ዘመን ላይ እምብዛም ባሪያዎች ስለሌሉ ጽሁፎች
እንዳይበዙ በማሰብ ነው።
 እነዚህ የተዘረዘሩት ሰባቱ ደግሞ የተከለከባቸው ሰበቦች እስካልተወገዱ ድረስ ሊያገባቸው ማይችላቸው አካላት
ናቸው። እነዚህ ግን አጅነብይ ይሆናሉ ምክንያቱም የተከለከለበት ሰበብ ሲወገድ ሊያገባቸው ይፈቀዱለታልና ነው።
ለአንድ ወንድ አጅነብይ ማይሆኑት መቼም ቢሆን ሊያገባቸው ማይችላቸው ሴቶች ናቸው።በመሆኑም የሚስት እህት
አጅነብይ ናት ለእህቷ ባል ሂጃቧን መገለጥም ይሁን እሱን መጨበጥ አይፈቀድላትም። ልክ ለባሏ ወንድም
መገለጥም ይሁን እሱን መጨበጥ እንደማይፈቀድላት ሁሉ።

1.6 ክርስቲያን ና አይሁድ ሴቶችን ስለማግባት

ቁርአን አህለል ኪታብ(መጽሀፍ የተሰጡት) የሆኑ ሴቶችን ስለማግባት በሱረተል ማኢዳ ላይ ሲናገር እንዲህ ይላል

الْيَوْمَ أُحِلَّ لَكُمُ الطَّيِّبَاتُ ۖ وَطَعَامُ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ حِلٌّ لَّكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّ لَّهُمْ ۖ وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الْمُؤْمِنَاتِ وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَا آتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَافِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِي أَخْدَانٍ ۗ
{ ዛሬ መልካሞች ሁሉ ለናንተ ተፈቀዱ፡፡ የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ (ያረዱት) ለእናንተ የተፈቀደ
ነው፡፡ ምግባችሁም ለነሱ የተፈቀደ ነው፡፡ ከምእመናት ጥብቆቹም ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች
ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና (ዝሙተኞች) የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን
በሰጣችኋቸው ጊዜ (ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው)፡፡}
37
አህለል ኪታብ (መጸሀፍ የተሰጡት) የሚባሉት ደግሞ አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ናቸው።
ከቁርአን አንቀጹ ጉልህ መልእክት የምንረዳው ቁም ነገር ከመኖሩ ጋር በጉዳዩ ላይ አንዳንድ መብራራት አለባቸው ብዬ
ማስባቸው ነጥቦች ስላሉ የተወሰነ ላብራራው ወደድኩ። በመሆኑም ኡለሞች በሚጠቅሷቸው ዝርዝር ነጥቦች ላይ
ተንተርሼ ለማብራራት እንዲቀለኝ በማሰብ ርእሱን ለሁለት ከፈልኩት እነሱም
1. በሙስሊም ሀገር እየኖረ አህለል ኪታብን ማግባት
2. በካፊር ሀገር እየኖረ አህለል ኪታብን ማማግባት

ከዚህ በታች ማብራሪያ ነው ከላይ ለተፃፉት ቁጥሮች👇🏻__________________
36 አኑር 3

37 ማኢዳ 5
____
(ገፅ 15 )ድረስ
✍🏻ይቀጥላል …ኢንሻአላህ

@historyofislam2

Читать полностью…

History of islamic

አቡ አብደላህ

ከአለልቱ ወግድ


/channel/Al_Miaraj_11

Читать полностью…

History of islamic

በታላቁ ወንድማችን ሸይኽ ኸድር ጊምባ

አጠር ያለ ያማረ ነሲሀ

በታላቁ የወሎ ሰለፊዮች ፕሮግራም ላይ

👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/Al_Miaraj_11

Читать полностью…

History of islamic

ወንድማችን አቡ ጁኸይፋ

መሳጭና ገሳጭ እንድሁም ቀስቃሽ ግጥም

በመስጅደ ሰላም ዶሮ እርባታ

በታላቁ የሰለፊዮች ስብስብ ላይ ያቀረበው ግጥመ


/channel/Al_Miaraj_11



/channel/Tuaifetul_mensura

Читать полностью…

History of islamic

ተለቀቀ ተለቀቀ ተለቀቀ ቁጥር ሁለት
በአቡረይሃና መጋቢት ሶስትቀን የተከሰተውን በተመለከተ
👇👇👇👇👇👇👇👇✅
/channel/Abureyhana
⭕️/channel/Tuaifetul_mensura

Читать полностью…

History of islamic

ጉዞ ወደ ደሴ ሱንዮች በጋራ
ተጠፋፍተን ነበር በአንዳንድ ሴራ
ዳግም እንገናኝ በዳዕዋ በዚያራ

Читать полностью…

History of islamic

🔸የትብብር ኢክሊል የመኖር በጋራ

🔸የፍቅር ተምሳሌት የአንድነት ጮራ

🔸ፏ ብሎ ያለባት የተውሂድ ባንድራ

🔸የወሎ ሰግነት የእድገታችን ጣራ

🔸የሆነችው ውቧ የከተሞች አውራ

🔸ተከባ ያለችው በጦሳ ተራራ
-------🔴------
🔸ቀጠሮ ይዘዋል ልጆቿ ባንድነት

🔸ሊዘያየሩባት በደአዋ ሊያደምቋት

------===--🔴አዎ🔴---===-----

🔸ፊቶች ያበራሉ ደስ ይበልሽ ነፍሴ

🔸#መጋቢት ❸ቀን ትፈካለች ደሴ

👉#ተጠረጣችኋል👈

🔴👉''ተውሂድን''አጥብቀህ ያዝ❗
🔶/channel/historyofislam2

👉ሊንኩን ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፍይ ይሁኑ!!!

Читать полностью…

History of islamic

ኒ ካ ህ ፣ሰ ር ግ ፣ኹ ሉ እ እና ፍቺን የተመለከቱ ሸሪአዊ ድንጋጌዎች

ክፍል 8️⃣

ከባለፈው የቀጠለ ……

20 | P a g e

*1.7 ዝሙት የሰሩ ሰዎች መጋባት በተመለከተ*

ዝሙት መስራት በጣም ከከባባድ ወንጀሎች ቢሆንም አንድ ሰው ተፀፅቶ ወደ አላህ ከተመለሰ አላህ እንደሚምርለት
ምንም ጥርጥር የለውም። በዚህ ቦታ ላይ ስለ ዝሙት አስከፊነት ለማብራራት ሳይሆን ከትዳር ጋር ተያይዞ የሚኖረውን
ብይን ብቻ ነው ምንመለከተው።
አመዛኝ በሆነው የኡለሞች አቋም መሰረት ዝሙትን የሰራ ሰው የተውባ መስፈርቶችን61 አሟልቶ ተውባ ሳያደርግ በፊት
የሚያስረው ኒካህ ትክክል ሆኖ አይገኝም።ለዚህ ማስረጃውም አላህ እንዲህ ማለቱ ነው

الزَّانِي لَا يَنكِحُ إِلَّا زَانِيَةً أَوْ مُشْرِكَةً وَالزَّانِيَةُ لَا يَنكِحُهَا إِلَّا زَانٍ أَوْ مُشْرِكٌ ۚ وَحُرِّمَ ذَٰلِكَ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ

(ሱረት አል-ኑር፣ - 3)

{{ዝሙተኛው ዝሙተኛይቱን ወይም አጋሪይቱን እንጂ አያገባም፡፡ ዝሙተኛይቱንም ዝሙተኛ ወይም አጋሪ እንጂ
አያገባትም፡፡ ይህም በምእምናን ላይ ተከልክሏል፡፡}}

በዚህ የቁርአን አንቀጽ ላይ ዝሙተኛን ማግባት በምእመናኖች ላይ ክልክል እንደሆን ተገልጿል።አንቀጹ የወረደበትንም
ሰበብ ስንመለከት መርሰድ ቢን አቢ መርሰድ ዝሙተኛ የሆነች ሴትን ሊያገባ መልእክታኛው ዘንድ መጥቶ ሲጠይቃቸው
ነው62
ሸይኩል ኢስላም ኢብን ተይሚያ እንዲህ ይላል
“አላህ ዝሙተኛ እንዲቀጣ ባዘዘ ግዜ እነሱን ከማግባትም ምእመናኖችን ከልከሏል, (ይህ የተደረገው) እነሱን ለማግለል
ነው.......... ዝሙተኛን ማግባት መከልከሉማ ከኢማም አህመድ ባልደረቦችም ከሌሎችም የሆኑ ፉቅሀዎች በርግጥም
ተናግረውበታል ከቀደምቶችም በዚህ ላይ የመጡ ነገሮች አሉ።በእርግጥ በርእሱ ላይ ፉቅሀዎች የተጨቃጨቁበት
ቢሆንም ለፈቀዱ ሰዎች ግን ሚደገፉበት ነገር የላቸውም”
63
ሌላ ቦታ ላይም እንዲህ ይላል
“ከዝሙቷ እስክትቶብት ድረስ ዝሙተኛን ማግባት ሀራም ነው።ዝሙት የሰራችው ከራሱም ጋር ይሁን ከሌላ ሰው ጋር
ያው ነው።ያለምንም ጥርጥር ትክክለኛው አቋም ይህ ነው”
64
ይህ አቋም ሀናቢላዎች ያሉበት65 ሲሆን ለጅነተ ዳኢማ በኢብን ባዝ መሪነት66፣ ኢብን ኡሰይሚን67ና ሙሀመድ ቢን
ኢብራሒም አሊ ሸይኽ68 ፈታዋ የሰጡበት ነው69።ከማስረጃም አንጻር ሚዛን ሚደፋው ይህው ነው።
በመሆኑም ዝሙትን ሰርቶ ከዛ ወንጀል ሳይቶብት በዛው ኒካህ ያሰረ ሰው ሁኔታው ከሁለት አንዱ ነው ሚሆነው
 ከዝሙት ሳይቶብቱ መጋባት እንደማይቻል እያወቀ ግን እሱ ሳይቶብት የገባበት ሰው፦
ይህ ሰው አሁንም ያለው ዝሙት ላይ ነው ኒካም እንዳሰረ አይቆጠርም። ልጅ ቢወለድም የዝሙት ልጅ ነው። በቶሎ
ቶብቶ መስፈርቱን አሟልቶ ኒካውን ሊያስር ይገባዋል። አልያ ሚስቱ አደለችም ሌላ ማግባት ትችላለች።


_ከዚህ በታች ከላይ ለተፃፉት ቁጥሮች ማብራሪያ ነው 👇🏻_
___
61 የተውባ መስፈርቶች የሚባሉት 1)መጸጸት 2)ከወንጀሉ መቆጠብ 3)ዳግመኛ ላይመለስበት መቁረጥ 4)የሰው ሀቅ ከሆነ ድግሞ
መመለስ 5)ጣረ ሞት ላይ ከመድረሱ በፊት መሆን

62 አቡ ዳውድ (2051) አልባኒ ሰሂህ ብለውታል

63 መጅሙአል ፈታዋ 15/316

64 መጅሙአል ፈታዋ 32/110

65 መጅሙአል ፈታዋ 32/110

66 ፈታዋ ለጅነተ ዳኢማ (18/383)

67 ፈታዋ አልመርአተል ሙስሊማ (2/698) አሽረፍ አብዱል መቅሱድ በሰበሰበው
68 ሙሀመድ ቢን ኢብራሂም (10/135)

69 ፈታዋ ሙሀመድ ቢን ኢብራሂም
___

21 | P a g e
ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሳሊህ ኡሰይሚን እንዲህ ይላሉ፦
“ዝሙተኛን ማግባት እንደማይቻል እያወቀ ከዛህም ጋር ዝሙተኛን ያገባ ሰው ሀራም የሆን ኒካህ ነው ያሰረው ኒካው
ሀራም ነው እንዳልታሰረ ነው ሚቆጠረው በሷም መጠቃቀም አይፈቀድለትም። ይህ ሰው በዚህ ሁኔታው ዝሙት እየሰራ
ነው ያለው”
70
 ከዝሙት ሳይቶብትም ኒካህ ማሰር የሚቻል መስሎት በዛው ኒካህ ያሰረ ሰው፦
ይህም ሰው ኒካው ትክክል አደለም ነገር ግን ኒካህ ካሰረበት ግዜ ጀምሮ ያለው እንደዝሙት አይቆጠርበትም።የዚህ
አይነቱን ኒካህ ኡለሞች የሹብሀ ኒካህ ብለው ይጠሩታል ። በዚ ግዜ ሚወለድም ልጅ እንደልጁ ይቆጠራል ነገር ግን
ኒካው ትክክል ስላልሆነ ከዝሙት ቶብቶ ኒካውን ማስተካከል ይጠበቅበታል።.
ኒካውን ለማደስ ሲፈልጉ ለሰዎች የግድ ድሮ ዝሙት ሰርተን ነበር ለዛ ነው ምናድሰው ማለት አይጠበቅበትም ዘዴዎችን
ተጠቅሞ ማደስ ይችላል። ኒካውን ለማስተካከል ፈትቼሻለሁ ማለትም አይጠበቅበትም።
ከዚህ ውጪ ግን ዝሙት የሰሩ ሰዎች ከዚህ ስራቸው ተፀፅተው የተውባን መስፈርት አሟልተው ከተመለሱ መጋባት
ይችላሉ የሚለው የአብዛኛው ኡለሞች አቋም ነው። ምክንያቱም ከቶበቱ በኋላ ዝሙተኛ ተብለው አይጠሩምና ነው
በዚህ መልኩ የተጋቡ ሰዎች ኒካቸው ትክክል ካልሆነ ሳይፈታት በፊት ሌላ ባል ማግባት ይፈቀድላታል?
ይህ ኒካይ ትክክል ባይሆንም እነሱ ሲጋቡ ትክክለኛ መስሏቸው እስከሆነ ድረስ ያሰሩት በአብዛኛዎቹ ኡለሞች አቋም
መሰረት ይህ “ቧሏ” እስካልፈታት ድረስ ኒካው ልክ ስላልሆነ ብላ ሌላ ባል ማግባት አይፈቀድላትም።ሻፍእዮች ኒካው
ትክክል እስካልሆነ ድረስ የሱ መፍታት አይጠበቅም ዝም ብላ ሌላ ማግባት ትችላለች የሚል አቋም ቢኖራቸውም
አብዛኞቹ ኡለሞች ያሉበት አቋም ሚዛን የሚደፍ ሆኖ እናገኘዋለን
ምክንያቱም ይህ ጉዳይ ሚስቴ ናት ብሎ አብሯት እየኖረ ባለውና አሁን አዲስ በሚያገባገባት ወንድ መሀከል ከባድ
ጭቅጭቅን የሚያስነሳ ስለሚሆንና አደጋም ያለው ስለሆነ ነው። በተጨማሪም መጀመሪያ ትክክል ነው ብላ አስባ
ስትኖርበት ከነበረው ነገር ሳትፈልገው ስትቀር ደግሞ ስህተት ነው ብሎ ማለት ለራስ ማመቻቸት ይሆናል።


____
70 ፈትዋ አልመርአተል አል ሙስሊማ(2/698)አሽረፍ አብዱል መቅሱድ በሰበሰበው
____
(ገፅ 20-21)ድረስ
✍🏻ይቀጥላል ……ኢንሻአላህ

@historyofislam2

Читать полностью…

History of islamic

------
ኡስታዝ ሙሐመድ አብዱ ዊትር ሶላት ሲያሰግድ
------
🔴----- ጠካኬ ---🔴
👇-----=====-----👇
🔴➢/channel/AbuNamuse
-___
🔴➢/channel/AbuNamuse/1768

Читать полностью…

History of islamic

#ከክፍል_7_የቀጠለ


ይችላሉ። በካፊር ሀገር ሲኖር እሱ በሷ ላይ ሊያሳድር ከሚችለው ተጽእኖ በላይ እሷ በሱ ላይ
ተጽእኖ ልታሳድር የመቻል እድሏ የሰፋ ነው
10.ኛ የሙስሊሞችን ተለምዶና ባህል ትቶ የክርስቲያኖችን ተለምዶና ባህል ይላመዳል። የነሱ ተለምዶ ደግሞ በብዛት
ከወንጀልና ቆሻሻ አይጠራም
11.ኛ አላህ ክርስቲያኖችንም ሆነ ሌሎች ካህዲያንን ለእምነታቸው ብለን እንድንጠላቸው አዞናል ክርስቲያን አግብቶ
በክርስቲያን ሀገር ሲኖር ደግሞ ይህ ነገር እየጠፋበት ሊሄድ ይችላል
12.ኛ ለሱ አጅነብይ የሆኑ ሴት ጓደኞቿና ቤተሰቦቿ አካላቸውን የተገላለጡ ሆነው ቤት ይመጣሉ ለፊትና ያጋልጡታል።
እሷም ከወንዶች ጋር በልቁ ትሳሳማለች
13.ኛ ልጆቿን ይዛ ወደ ሲኒማና ቤተ ክርስቲያን ትሄዳላች ካፊር ሀገር እስካለ ድረስ መከልከል አቅሙ ያነሰ ነው
ሚሆነው
14.ኛ ብዙ ግዜ ከዝሙት አይጠሩም።እነሱን ለማግባት ደግሞ ከዝሙት የጠሩ መሆናቸው መስፈርት ነው። በሌላም
አርግዛ በሱ ስም እንዲጠራ የማድረግ እድሏ ይሰፋል
15.ኛ የአላህ መልእክተኛ ሴት ልጅን ለአራት ነገር ተብሎ እንደሚያገቧት በተናገሩበት ሀዲስ ላይ ዲን ያላትን ምረጥ
ብለዋል። ይህቺ ደግሞ ዲን የላትም።
 እነዚህ ጉዳቶች እኔ ከማስታውሳቸው ውስጥ የተወሰኑት ናቸው ሌሎችም ብዙ ጉዳቶች እንደሚኖሩት
አያጠያይቅም። ብዙ ኡለሞችም ደግሞ በካፊር ሀገር እየኖሩ እነሱን ማግባትን ከልክለዋል የተቀሩትም ቢሆኑ በጣም
የተጠላ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል ብዙ ጉዳቶቹንም ደግሞ ዘርዝረናል ሙስሊም ደግሞ ብልጥ ሆኖ ጥቅሙ
ሚያመዝን ተግባርን ነው ሊፈጽም የሚገባው።
_
60 ሚንሀጅ ከነ ሀሺያው 2/187
__

(ገፅ18-19)ድረስ

✍🏻ይቀጥላል ……ኢንሻአላህ


@historyofislam2

Читать полностью…

History of islamic

የዛሬ እሁድ ሙሀደራ በመስጅደል ሚእራጅ



ለወላጆች መልካም መዋል በሚል ርእስ


በኡስታዛችን አቡ ኒብራስ አላህ ይጠብቀው


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

/channel/umuhilal1

Читать полностью…

History of islamic

❌የረመዷን ውስጥ ስህተቶች❌



በረመዳን በብዛት የሚፈፀሙ ስህተቶች
~~~~
① ሶላት ሳይሰግዱ መፆም፣
② ሌሊቱን በጫት ካሳለፉ በኋላ ሱሑርን አስቀድሞ በመመገብ ፈጅር ሳይሰግዱ መተኛት፣
③ ቀኑን በእንቅልፍ፣ ሌሊቱን በተከታታይ ፊልም/ ሙሰልሰላት ማሳለፍ፣
④ ረመዳንን ጠብቆ መንዙማና ነሺዳ እየለቀቁ ሰዎችን ከቁርኣን ማዘናጋት፣
⑤ ተራዊሕን በንቃት እየሰገዱ ፈጅር ሶላትን በእንቅልፍ ማሳለፍ፣
⑥ ተራዊሕ ላይ በየ አራቱ ረከዐ መሐል የቢድዐና የሺርክ እንጉርጉሮዎችን ማስገባት፣
⑦ የተራዊሕ ኢማሞች ከሶላቱ ይልቅ ለቁኑት ዱዓእ የበለጠ ትኩረትና ጊዜ መስጠት፣
⑧ መግሪብ ሶላት ሲጠናቀቅ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ለፊጥራ መጣደፍ (ሰጋጆችን የሚያቋርጥ፣ የሰው ጫማ የሚያቀያይር፣…ብዙ ነው)
⑨ ሌሊት ላይ "ተሰሐሩ " እያሉ በእስፒከር መጮህ፣
(10) የሱሑር ጊዜ ሳያልቅ ለጥንቃቄ በሚል ቀድሞ አዛን ማድረግ፣
(11) ሱሑር ላይ "ነወይቱ ሰውመ ገዲን" እያሉ በቃል መነየት፣
(12) እያንቀላፉ ተራዊሕ መስገድ፣
(13) ልጆች "እንፁም" ሲሉ ማበረታታት ሲገባ መከልከል፣ "ውሃ አያፈጥርም፣ ተደብቀህ ብላና ትፆማለህ" እያሉ መዋሸትና ውሸት ማለማመድ፣
(14) ሴቶች በተጋነነ የምግብ ዝግጅት ሰፊ ጊዜያቸውን ማቃጠል፣
(15) ሴቶች ሽቶ ተቀባብቶ ለተራዊሕ መውጣት፣
(16) በተራዊሕ ወቅት የሴቶችና የወንዶች አላስፈላጊ መዝረክረክ፣
(17) ሃሜት፣
(18) ፊጥራ ላይ ከመጠን በላይ መመገብ፣
(19) ቀኑን በካርታ፣ በዳማ፣ ወዘተ ማሳለፍ፣
(20) ሙዚቃ ማዳመጥ፣
(21) የሰው ስራ የሚሰሩ ተቀጣሪዎች ጧት በሰዓት አለመግባት (አማና መጠበቅ፣ ቃልን ማክበር ግዴታ ነው። ግዴታ ያልሆኑ ዒባዳዎች ተፅእኖ የሚያሳድሩብን ከሆነ መተው ወይም መቀነስ ይገባል)፣
(22) በተለይ በስራ ቦታዎች ላይ በመንዙማና በነሺዳ ማሳለፍ (መሆን ያለበት ከተመቼ ቁርአን መቅራት፣ ካልሆነ ዚክር ማድረግ ወይም ደዕዋ ማዳመጥ፣ ካልሆነ ዝምታ ይሻላል።)
(23) ለይለተል ቀድርን ለማየት ሰማይ ሰማይ እያንጋጠጡ መጠበቅ (የሚታይ ነገር የለም)፣
(24) አንዳንድ አካባቢዎች ዒሻን በጣም በማዘግየት ሰው ጀማዐ ላይ እንዳይካፈል እንቅፋት መሆን፣
(25) አንዳንድ አካባቢዎች መስጂድ ውስጥ ጫት ይዞ ገብቶ መቃም፣
(26) አንዳንድ አካባቢዎች "ተርቲብ" ብለው ንፍሮ፣ ቆሎና መሰል ምግቦችን ወደ መስጂድ እንዲያቀርቡ ህዝብን ማዘዝ፣
(27) የምግብ ብክነት፣  

    
    👇👇👇👇👇👇👇👇👇/channel/umuhilal1

Читать полностью…

History of islamic

በመካነሰላም የነበረ ስለ ቁርአን አሳሳቢነት




በጎርደ መስጅድ (መስጅደ ፈትህ)

@historyofislam2
@historyofislam2

Читать полностью…

History of islamic

በመካነሰላም የነበረ ነሲሀ




በጎርደ መስጅድ (መስጅደ ፈትህ)

@historyofislam2
@historyofislam2

Читать полностью…

History of islamic

በመካነሰላም የነበረ ፈተዋ


🎤 በአቡ ኒብራስ

በጎርደ መስጅድ (መስጅደ ፈትህ)

@historyofislam2
@historyofislam2

Читать полностью…

History of islamic

ታላቁ አባታችን

ሸይኽ ሙሀመድ ሚሌ


/channel/Al_Miaraj_11

Читать полностью…

History of islamic

ይደመጥ ይደመጥ ይደነጥ
አድስ ግጥም መጋቢት ሶስት ቀን በሚለ
በአቡረይሃና ኸዲር ጊንባ

/channel/Tuaifetul_mensura

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ደቻናሉ ለመግባት
/channel/Abureyhana

Читать полностью…

History of islamic

ወንድማችን ሰይድ ጀሜ

ደስ ይበልሽ ደሴ

በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሀሪፍ ግጥም

ይደመጥ

👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/Al_Miaraj_11

🔴👉/channel/Tuaifetul_mensura

Читать полностью…

History of islamic

አቦ የጀግናው የተወዳጁ የምንወደውና የምንሳሳለት ኡስታዛችን ልጅ ስሙልኝማ

🌹🌹🌹 ኒብራስ 🌹🌹🌹

/channel/Tuaifetul_mensura

/channel/Tuaifetul_mensura

Читать полностью…

History of islamic

👉መጋቢት 3 እሁድ ሰለፍዮች ደሴ ላይ ፏ ይላሉ ። አዎ ከአራቱም ማዕዘን እንገናኛለን እንደት እንደጓጓን ...
اللهم احفظ إخواننا من كل سوء...
----
🔴👉/channel/AbuNamuse/1598
-----
🔴👉/channel/AbuNamuse


👇👇👇
/channel/historyofislam2

Читать полностью…

History of islamic

ኒ ካ ህ ፣ሰ ር ግ ፣ኹ ሉ እ፣እና ፍችን የተመለከቱ ሸሪአዊ ድንጋጌዎች

ክፍል 4️⃣

ከባለፈው የቀጠለ ……

13 | P a g e

*ከሆነ ምክንያት ጋር ተያይዞ ለግዜው ልናገባቸው የማይፈቀዱ*

1. እህትማማቾችን ማግባት ፦የሚስትህን እህት ሚስትህን እስካልፈታሃት ወይም እስካልሞተች ድረስ
ማግባት አይፈቀድልህም። ሚስትህን ከፈታሃት ግን እህቷን ማግባት ትችላለህ ስለዚህ ክልከላው
ለሁልግዜም ሳይሆን ከምክንያት ጋር የተያያዘ ነው እሱም በአንዴ እህትማማቾችን መሰብሰብ። ለዚህም
ማስረጃው ቁርአን ነው

وَأَن تَجْمَعُوا بَيْنَ الْأُخْتَيْنِ إِلَّا مَا قَدْ سَلَفَ ۗ
{በሁለት እኅትማማቾችም መካከል መሰብሰብ (እንደዚሁ እርም ነው}
22

2. አንድትን ሴት ካገባ በኋላ የሚስቱን አክስት ወይም የሚስቱን የእህቷን ልጅ ወይም የወንድሟን ልጅ ከሷ
ጋር አብሮ ማግባትም አይቻልም። ሚስቱን ከፈታት ግን እነዚህን ማግባት ይችላል
ማስረጃውም አቢ ሁረይራ ባስተላለፈው ሀዲስ የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمእንዲህ ብለዋል
لايجمع بين المرأة وعمتها ولا بين المرأة وخالتها
“በአንድት ሴትና ባባት በኩል ባለች አክስቷ እንዲሁም በእናት በኩል ባለች አክስቷ አይሰበሰብም ”
በተጨማሪም ኡለሞች በዚህ ላይ ተስማምተውበታል23

* ጥቅል የሆነው መርሆ*

ሁለት ሴቶች ቢኖሩና ከነሱ ውስጥ አንደኛው ወንድ ቢሆን ሌላኛዋን ማግባት ማይችሉበት አይንት ዝምድና
ያላቸው ከሆኑ ለአንድ ሰው እነዚህ ሁለት ሴቶችን አንድላይ ማግባት አይፈቀድለትም።24 አንደኛዋን ሲፈታ
ግን ሌላኛዋን ማግባት ይችላል።
ኢዳህ25 ምትቆጥርን ሴት ኢዳዋ እስኪያበቃ ድረስ ሌላ ወንድ ሊያገባት አይቻልም።
አላህ سبحانه وتعالى (እንዲህ ይላል፦


ۚ وَلَا تَعْزِمُوا عُقْدَةَ النِّكَاحِ حَتَّىٰ يَبْلُغَ الْكِتَابُ أَجَلَهُ ۚ
{የተጻፈውም (ዒዳህ) ጊዜውን እስከሚደርስ ድረስ ጋብቻን ለመዋዋል ቁርጥ ሐሳብ አታድርጉ፡፡}”
26

_ከዚህ በታች ማብራሪያ ነው ከላይ ለተፃፉት ቁጥሮች 👇🏻___________________
22 አኒሳእ 23

23 አልፊቅሁል ሙየሰር 320 (መጅመእ መሊክ ፉሀድ 1424 ዓ.ሂ ያሳተመው)

24 አልፊቅሁል ሙየሰር 320 (መጅመእ መሊክ ፉሀድ 1424 ዓ.ሂ ያሳተመው)

25 ኢዳህ ሚባለው አንድት ሴት ባሏ ከፈታት ወይ ከሞተባት በኋላ ሌላ ከማግባቷ በፊት ምትቆየው ግዜ ነው። በዚህ ግዜ ውስጥ
ባሏ እሷን የመመለስ ስልጣን አለው ፍቺው በሶስት እስካልሆን ድርስ ዝርዝር ነጥቡ ገጽ 75 ላይ ተብራርቷል

26 አል በቀራ 235
__

14 | P a g e

3. በሶስት የፈታትን ሴት ትክክለኛ በሆነ ኒካህ ሌላ ባል አግብታ ያ ባል ተገናኝቷት27 እስካልፈታት ድርስ
የመጀመሪያው ባሏ ሊያገባት አይችልም28። ቁርአን እንዲህ ሰለሚል

فَإِن طَلَّقَهَا فَلَا تَحِلُّ لَهُ مِن بَعْدُ حَتَّىٰ تَنكِحَ زَوْجًا غَيْرَهُ ۗ
“(ሦስተኛ) ቢፈታትም ከዚህ በኋላ ሌላን ባል እስከምታገባ ድረስ ለርሱ አትፈቀድለትም”
29
4. ለሀጅ ስራ ኢህራም ያደረገች ሴት ከኢህራሟ እስክትፈታ ድረስ ከሷ ጋር ኒካህ ማሰር አይቻልም።
መልእክተኛው صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል
{لاينكح المحرم المحرم،ولا ينكح ولا يخطب}
“ኢህራም ላይ ያለ ሰው አያገባም ፣አይዳርለትም ፣አያጭም”
30
5. ሙስሊም ሴት ከሙስሊም ወንድ ውጭ የየትኛውንም እምነት ተከታይ ማግባት አይፈቀድላትም። አላህ
ቁርአን ላይ እንዲህ ስላለ

ۗ وَلَا تُنكِحُوا الْمُشْرِكِينَ حَتَّىٰ يُؤْمِنُوا ۚ

{{ለአጋሪዎቹም እስከሚያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው}}31
ሙስሊም ወንድም ከሙስሊም ወይም ከአህለል ኪታብ32 ሴት ውጪ የሌላ እምነት ተከታይን ማግባት
አይፈቀድለትም ። አላህ سبحانه وتعالى (እንዲ ይላል

وَلَا تَنكِحُوا الْمُشْرِكَاتِ حَتَّىٰ يُؤْمِنَّ ۚ

{{ (በአላህ) አጋሪ የሆኑ ሴቶች እስከሚያምኑ ድረስ አታግቧቸው}}33
አህለል ኪታብን ስለማግባት34 አስመልክቶ እንዲህይላል

وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَا آتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَافِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِي أَخْدَانٍ ۗ
{ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና (ዝሙተኞች) የምስጢር
ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ (ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ
ናቸው)}
35

_ከዚህ በታች ማብራሪያ ነው ከላይ ለተፃፉት ቁጥሮች👇🏻_ _

27 ግንኙነት ስል የምፈልግበት ግብረ ስጋ ግንኙነት ነው።
28 ዝርዝር ነጥቡ ወደ ፊት ይመጣል

29 አልበቀራ 230

30 ሙስሊም (1409)

31 አል በቀራ 221

32 አህለል ኪታብ ማለት መጽሀፍን የተሰጡ ማለትሲሆን አህለል ኪታብ ሚባሉት አይሁድና ክርስቲያኖች ናቸው

33 አል በቀራ 221

34 ስለዚህ ነጥብ በቀጣዩ ርእስ ላይ በሰፊው ተብራርቷል
35 ማኢዳ 5

(ገፅ13-14)ድረስ

✍🏻ይቀጥላል ……ኢንሻአላህ

@historyofislam2

Читать полностью…

History of islamic

ስማ ወንድሜ ላንተ ነው ‼️

ማለቴ ደዩስ ሆነህ የሚስትህን
ፎቶ በየሚድያው ለምታንጠለጥለው

እህቴ ሆይ ‼️

ባልሽ የህዝብ ንብረት አይደለም
በየሚዲያው ፎቶውን አትለጥፊ

#ፎቶ ማንሳት ሀራም ነው ሲባል እከሌ እኮ ፈቅዷል እከሌ እኮ ይቀርፃል ይላል

#ወንድሜ የሰዎችን ስተት ማስራጃ አድርገህ ይዘህ አትከራከር

ከጅምሩ የተከለከለውን ሀራም የተደረገው ጥፋት ሰርታቹኋል ያኔ ካሜራ ይዛቹሁ ባነሳቹሁ ሰአት ፖስት በምታረጉ ሰአት አይኑን መሰረዝ መቁረጥ አይነ ስውር ወይም ፊቱን ማጥፋቱ ዋጋ የለውም

ኢላሂ አንዳድ ሰዎችማ ገርመው ይገርማሉ ፎቶ ሀራም ነው ፎቶ እራቁ ይሉና ሙናሰባ ወይ የመሳሰለ ነገር ሲኖር ፎቶ ተነስተው ከዛ መፖሰት ሲፈልጉ አይንን ሰረዝ ወይም ግማሽ ፊት ቆረጥ ናቅስ አቅል ነፍስያቹሁን ማታለላቹሁ ነው አቤት ሞኝነታቹሁ

ሙሉ ፎቶ ተነስታቹሁ ለሰዎች በምታስተላልፉ ጊዜ አይኑን ወይም ፊቱን ሰርዛቹሁ መፖሰት ይቻላል የተባለ ይመስል አንዳድ ሰዎች በፎቶ ላይ ግድ የለሽ ናቸው ይህም የፎቶ ሀራምነት እያወቁ አውቆ ማጥፋት ወንጀሉ ከባድ ነው

ጭራሹኑ ፎቶ ማንሳትም መነሳትም ነው ሀራምነቱ እንጂ አንስታቹሁ ልትፖስቱ ባስፈለጋቹሁ ጊዜ አይኑን ሰረዝ ወይም ፈቱን በማጥፋት ከጅምሩ የተከለከለውን ሀራምነቱ የተደረገው ጥፋት ሰርታቹኋል ያኔ ካሜራ ይዛቹሁ ባነሳቹሁ ሰአት አላህ ይዘንልን እና በፎቶ ላይ የመጡ ሀዲሶች የሰማ ያነበበ መቸም ችልተኝነት አይኖረውም


/channel/historyofislam2

Читать полностью…
Subscribe to a channel