#ኒ ካ ህ ፣ሰ ር ግ፣ኹ ል እ እና ፍቺን የተ መ ለ ከቱ ሸ ሪ አ ዊ ድን ጋ ጌዎች
#ክፍል 1️⃣2️⃣
ከባለፈው የቀጠለ.……
27 | P a g e
#በሀዲስ ደግሞ _የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسእንዲህ ብለዋል
{{لا نكاح إلا بولي }}
#{{ በወልይ እንጂ_ ኒካህ የለም}}94
#ይህ አብዛኛዎች# ኡለሞች ያሉበት# አቋም ነው ማንኛውም ሴት ያለወልይ ልትዳር #አትችልም ልጃገረድም_ ትሁን አግብታ
የምታቅም ብትሆን ያለ ወልይ ኒካህ የለም።
ወልይ መሆን የሚችለው ሰው እነዚህን መስፈርቶች ሊያሟላ ይገባል
# ብሉግ95 (አቅመ አዳም) የደረሰና አእምሮ ጤነኛ የሆነ መሆን አለበት
# ወንድ መሆን አለበት። እናት ልጇን ወልይ #ሆና መዳር አትችልም
#የኒካህን ጥቅምና የሚበጃትን መለየት የሚችል መሆን አለበት ሞኛሞኝ ሆኖ #ለጠየቀው ሁላ የሷን# ጥቅም ሳያገናዝብ
የሚድር ከሆን ወልይ ሊሆናት አይችልም
በእምነት ተመሳሳይ መሆናቸው ግዴታ ነው። #ሙስሊም ሴት _አባቷ ክርስቲያን# ከሆነ እሱ ለሷ ወልይ ሆኖ ሊድራት
#አይችልም። ካፊር ሙስሊም ላይ በምንም #ሁኔታ የበላይ ሊሆን አይገባም። አላህ #እንዲህ ይላል
ۗ وَلَن يَجْعَلَ اللَّهُ لِلْكَافِرِينَ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ سَبِيلًا
{{አላህም ለከሓዲዎች በምእምናን ላይ #መንገድን በፍጹም አያደርግም፡፡}}96
4. በግልጽ መሆኑ ወይ ደግሞ ምስክር መኖሩ፦ ኒካው በድብቅ መሆን የለበትም ሰዎች ሊያውቁት ይገባል።
መልእክተኛው እንዲህ ብለዋል
{{أعلنوا النكاح}}
#{{ኒካህን ግልጽ አድርጉ}}97
ምስክር መኖር እንዳለበትም የሚጠቁሙ ሀዲሶች ቢኖሩም ነገር ግን ደካማ መሆናቸውን ኡለሞች ተናግረዋል።ነገር
ግን ከኺላፍ ለመውጣት ምስክር ባለበት መሆኑ ተገቢ ነው እንላለን። ኒካሁ ሰው አውቆት በግልጽ መሆኑ ግን
ግዴታ ነው በዚህ ላይ ከላይ ያሳለፍነው ግልጽ ሀዲስ ስለመጣበት።በድብቅ የታሰረ ኒካህ ትክክል አይሆንም።
ምስክር ያለበት ሆኖ በግልጽ የተፈጸመ ኒካህ ሁለቱንም ያሟላ ሰለመሆን ከኺላፍም የጸዳው ነውና የተሻለው
ነው።
1.14 አባት ሴት ልጁን ያለ ፍቃዷ ስለመዳር
አብዛኛዎች ኡለሞች ሴት ልጅን አባቷ ፍቃዷን ሳይጠይቅ መዳር ይችላል የሚል አቋም አላቸው በዚህ ላይ ኢጅማእ
እንዳለበትም የጠቀሱ አሉ98 ሆኖም ነጥቡ ኺላፍ አለበት ኢብን ሺብሪማ አባቷም ቢሆን ማስገደድ አይችልም የሚል
አቋም ነበረው ከማስረጃ አንጻር ሚዛን ሚደፋውም አቋም ይህ ነው
_ከዚህ በታች ማብራሪያ ነው ከላይ ለተፃፉት ቁጥሮች 👇🏻_
_
94 አቡ ዳውድ (2085) ቲርምዚ (1101) ኢብን ማጃ (1881) አልባኒ ኢርዋእ ላይ ሰሂህ ብለውታል (1839)
95 አንድ ሰው ብሉግ ደርሷል የሚባለው ከሶስት አንዱን ምልክት ካየ ነው
1. ብልቱ አካባቢ ጸጉር ካበቀለ
2. የዘር ፈሳሽ በስሜት ከፈሰሰው
3. 15 አመት ከሞላው
ሴት ከሆነች ደግሞ ከነዚህ ሶስቱ በተጨማሪ
4. ሀይድ ካየች
ከነዚህ ምልክቶች ውስጥ አንዱን እንኳን ያየ ሰው ብሉግ ደርሷል
96አኒሳእ (141)
97 አህመድ (16175) ሀኪም (2748) አልባኒ ሰሂህ በለውታል ሰሂህ ጃሚእ 1072
98 አሸርሁል ሙምቲእ (5/155 ዳር ኢብንል ጀውዚ)
____
28 | P a g e
ማስረጃው መልእክተኛው صلى الله عليه وسلمእንዲህ ማለታቸው ነው
{{لا تنكح البكر حتى تستأذن ,ولا تنكح الأیم حتى تستأمر}}
{{ልጃገረድ የሆነች ሴት እስኪያስፈቅዷት አግብታ የፈታች ደግሞ እስኪያማክሯት ድረስ አትዳርም}}99
ይህ ሀዲስ ጥቅል ነው አባት ከሆን እሷን መዳር ይችላል የሚል ነገር አልመጣም። አባቷ እሷን ማስገደድ ከቻለ ለምን
ያስፈቅዳት ተባለ? እሷ ባትፈቅድም መዳርን ከቻል በማስፈቀዱ ምን ጥቅም አለው ?
እዚህ ጋር የሚነሳ ጥያቄ አለ እሱም አቡ በከር ሲዲቅ አኢሻን ለአላህ መልእክተኛ በስድስት አመቷ ድሮላቸው በ
ዘጠኝ አመቷ አብረው ሆነው የለ ወይ? ይህ ታዲያ አባት ልጁን ያለ ፍቃዷ ለመዳር ማስረጃ አይሆንም?
መልስ ፦ አዎ ታሪኩ እውነት ነው ግን ማስረጃ አይሆንም ምክንያቱም አኢሻን አቡበከር ሲድራት ተጠይቃ እንቢ
አልፈልግም ብላ አባቷ አስገድዷት እንደዳራት በምን አወቅክ? ምንም እንደዛ ሚል ነገር አታገኝም እንደውም አኢሻ
አባቷ ቢያስፈቅዳት ፍቃደኛ ትሆን እንደነበረ ሚጠቁን ማስረጃ ነው ያለው። ይህን የቁርአን አንቀጽ እስኪ ተመልከት
يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ إِن كُنتُنَّ تُرِدْنَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا وَزِينَتَهَا فَتَعَالَيْنَ أُمَتِّعْكُنَّ وَأُسَرِّحْكُنَّ سَرَاحًا جَمِيلًا
(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 28)
{{አንተ ነቢይ ሆይ! ለሚስቶችህ (እንዲህ) በላቸው «ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የምትፈልጉ እንደ ሆናችሁ ኑ፤
አጣቅማችኋለሁና፡፡ መልካምንም ማሰማራት (በመፍታት) አሰማራችኋለሁና፡፡
وَإِن كُنتُنَّ تُرِدْنَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَالدَّارَ الْآخِرَةَ فَإِنَّ اللَّهَ أَعَدَّ لِلْمُحْسِنَاتِ مِنكُنَّ أَجْرًا عَظِيمًا
(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 29)
አላህንና መልክተኛውን የመጨረሻይቱን
አገርም የምትፈልጉ ብትሆኑም፤ እነሆ አላህ ከእናንተ ለመልካም ሠሪዎቹ ትልቅን ምንዳ አዘጋጅቷል፡፡}}
የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمይህ የቁርዓን አንቀጽ ሲወርድ መጀመሪያ በአኢሻ ነበር የጀመሩት እሷ ጋር ሄደው እንዲህ
አሏት “አባትሽን እሲኪ በዚ ጉዳይ(ፍቺ ይሻልሻል ወይስ ከኔ መቆየት በሚለው ጉዳይ ማለት ነው) አማክሪው” አሏት
እሷም “የአላህ መልእክተኛ ሆይ በዚህ ነው እንዴ አባቴን ማማክረው?! እኔ አላህንና አኼራን ነው ምፈልገው”
አለቻቸው።100
ስለዚህ ሴት ልጅን ማንም ቢሆን አስገድዶ ሊድራት አይችልም አባቷም ቢሆን ሊያስገድዳት አይችልም።እሱን
ካላገባሽ ከማህበረሰቡ ትገለያለሽ ከቤት ትባረሪያለሽ እያሉ በማስፈራራት እንድታገባው ማስገደድም እዚሁ ውስጥ
ይገባል።
_ማብራሪያ ከላይ ላሉት ቁጥሮች👇🏻_
_
99 ቡኻሪ (5136) ሙስሊም (1419)
100 ቡኻሪ (4785) ሙስሊም (1475)
___
(ገፅ27-28)
✍🏻ይቀጥላል ……ኢንሻአላህ
@historyofislam2
📚《الصحيح المصفى من سيرة النبي المصطفى 71
የነብዩ ሙሀመድ ﷺ ታሪክ /ሲራ/
ክፍል 71
በሼህ አቡ ኒብራስ ሙስጦፋ አብደላህ
@historyofislam2
ኒ ካህ ፣ ሰ ር ግ፣ ኹልእ እ ና ፍቺን
የ ተመለ ከቱ ሸ ሪ አ ዊ ድን ጋጌ ዎች
ክፍል 1️⃣1️⃣
ከባለፈው የቀጠለ ……
1.12 ኒካህን ጁምአ ቀን ማሰር የተወደደ ተግባር ነው?
ኒካህ ማሰርን የፈለገ ሰው በፈለገው ወር እና ቀን ኒካህ ማሰር ይችላል።በዚህ ቀን አትሰር በዚህ ቀን እሰር ተብሎ
የተቀመጠበት ገደብ የለም ነገር ግን በርካታ ፍቅሀዎች የጁሙአ እለት ኒካህ ማሰር እንደሚወደድ ይጠቅሳሉ
ኢማም ኢብን ቁዳማ እንዲህ ይላል፦
“የጁሙአ እለት ኒካህ ማሰር ይወደዳል “
86
ኢማም ነፍራዊ እንዲህ ይላል
“የኒካህ ኹጥባ ሚደረገውና ኒካህም ሚታሰረው ጁሙአ ቀን መሆኑ ይወደዳል”
87
ጁሙአ ቀን ኒካህን ማሰር ከተለያዩ ቀደምቶችም ተወርቷል ከዛም በተጨማሪ የጁሙአ እለት የተባረከ ቀን ስለሆነ
ኒካውም እንዲባረክለት ይከጀላል ያሉ ኡለሞች አሉ። እንዲሁም የጁሙአ ቀን ዱአ ተቀባይነት የሚያገኝበት ሰአት ስላለ
የዛህን ቀን ኒካ አስረው ባረከላሁ የሚለው ዱአ ቢደረግላቸው ተቀባይነት የማግኘት እድሉ የሰፋ ነው የሚሆነው።
_ማብራሪያ ከላይ ላሉት ቁጥሮች👇🏻_
86 ሙግኒ (7/64)
87 አልፈዋኪሁ ደዋኒ 2/11
__
26 | P a g e
በዚህ ላይ ግን የመጣ ሊደገፉብት የሚችሉት የሀዲስ ማስረጃ የለም በመሆኑም ኡለሞች ጁሙአ ቀን ኒካህ ማሰርን ሱና
ነው ከማለት ይልቅ ሙስተሀብ ነው የሚለውን ገለጻ ሲጠቀሙ ነው ሚስተዋለው።ምክንያቱም ይህ ተግባር ለመወደዱ
የሀዲስ ማስረጃ የሌለው ሲሆን ኡለሞች ከተለያየ ነገር አንጻር አይተውት ነው ይወደዳል ያሉት።
ኢብን ኡሰይሚን እንዲህ ይላሉ
“በዚህ ላይ (ጁሙአ ቀን ነጥሎና መርጦ ኒካህ በማሰር ላይ) የመጣ ሀዲስ አላዉቅም .......”88
ነገር ግን ጁሙአ ቀን እረፉቱ ስለሆነ ወይም ስለሚመቸው ብሎ ቢመርጠው ምንም ችግር የለውም
1.13 ኒካህ ለማሰር መሟላት ያለባቸው አራት መስረቶች
1. ማንነታቸው መታወቅ፦ ሁለቱም ኒካህ የሚያስሩት አካላት ማንነታቸው ተለይቶ መታወቅ አለበት። አንድ አባት
ለአንድ ሰው ከልጆቼ መሀከል አንዷን ድሬልሀለው ቢለው ይህ ኒካህ ልክ አይሆንም ምክንያቱም የትኛዋን ልጁን
እንደሆነ በግልጽ አላስቀመጠምና ነው። ግን ሰውየው ያለው አንድ ልጅ ከሆነና ልጄን ድሬልሀለው ቢል ትክክል
ይሆናል ወይም ደግሞ ልጁ አጠገቡ ኖራ ወደሷ እያመላከተ ይህችን ልጄን ድሬልሀለው ቢል ይሆናል።89ቁርአን
ላይ ያሉ ስለ ኒካህ ማሰር የሚናገሩ አንቀጾችም የግለሰቡ ማንነት በግልጽ ሚጠቁሙ ናቸው። ለምሳሌ ያክል
ۖ فَلَمَّا قَضَىٰ زَيْدٌ مِّنْهَا وَطَرًا زَوَّجْنَاكَهَا
{{ ዘይድም ከእርሷ ጉዳይን በፈጸመ ጊዜ እርሷን አጋባን }}90
2. ፍቃደኝነታቸው፦ ወንድም ይሁን ሴት ያለ ፍላጎታቸው ማንም አስገድዶ ሊድራቸው አይችልም።
ለዚህ ማስረጃው መልእክተኛውصلى الله عليه وسلمእንዲህ ማለታቸው ነው
{{لا تنكح البكر حتى تستأذن ,ولا تنكح الأیم حتى تستأمر}}
{{ልጃገረድ የሆነች ሴት እስኪያስፈቅዷት አግብታ የፈታች ደግሞ እስኪያማክሯት ድረስ አትዳርም}}91
በመሆኑም ያለ እሷ ፍቃደኝነት በጠለፋም ይሁን በቤተሰብ አስገዳጅነት የሚፈጸም ኒካህ ትከከለኛ አይሆንም መስፈርት
ስላላሟላ።
3. ወልይ፦ ለሴት ልጅ92 ኒካህ የሚያስርላት ወልዩዋ ነው ራሷ ለራሷ ኒካህ ማሰር አትችልም ማስረጃውም ከቁርአን
ۗ وَلَا تُنكِحُوا الْمُشْرِكِينَ حَتَّىٰ يُؤْمِنُوا ۚ
{{ለአጋሪዎቹም እስከሚያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው፡፡}}93
በዚህ አንቀጽ ላይ አትዳሯቸው ማለቱ ሴት ልጅ ራሷን እንደማትድርና የሚድራት ወልዩዋ መሆኑን ይጠቁመናል
_ከዚህ በታች ማብራሪያ ነው ከላይ ለተፃፉት ቁጥሮች👇🏻_
___
88 አሸርሁል ሙምቲእ 12/33
89 አሸርሁል ሙምቲእ (5/149)ዳር ኢብንል ጀውዚ
90 አህዛብ( 37)
91 ቡኻሪ (5136) ሙስሊም (1419)
92 ወንድ ልጅ ወልይ አያስፈልገውም ራሱን በራሱ ነው ሚድረው
93 አል በቀራ 221
_
(ገፅ 25-26)ድረስ
✍🏻ይቀጥላል ……ኢንሻአላህ
@historyofislam2
➷◉ ዘመን ተሻጋሪው ሁል ጊዜ ቢሰማ የማይሰለች አጠር ምጥን ያለችለጆሮ የምትስማማ የሆነች
👉ምርጥ ምክር ይዳመጥ 👈
🍀🍀◉ ተመከር ተመከር ተመከር
☘️☘️◉ ተመከር ተመከር ተመከር
✍️አልጫ አትሁን በሺተኛ አትምሰል!!
✍️ ጀዝባ አትሁን ንቃ ማንኛዉንም ኪታብ አድማቂ አትሁን !!
🔗#በተወዳጁ ኡስታዝ አቡ ኒብራስ ሙስጦፋ ዓብደሏህ {{حفظه الله تعلى ورعاه}} አሏህ ይጠብቀዉ📘
@hitoryofislam2
🔴👉ዱኒያና ጅህልና በሚል ርዕስ የተደረገ ቆየት ያለ ሙሀደራ ከ 3 ዓመት በፊት በጣምምም ትውስታ ያጭራል... ❗️
------
------
🔴➢ ከ 1:04ኛው ደቂቃ በኋላ ያለችው ዘንድሮን አስታወሰችኝና ፈገግ አደረገችኝ...
🔴🔊በኡስታዛችን አቡ ኒብራስ حفظه الله
👇👇👇👇👇👇
---------
🔴➢ /channel/AbuNamuse
-------
🔴➢/channel/AbuNamuse/1956?single
@historyofislam2
የኢድ ስጦታ
ቁርዓን ተፍሲር በአፕሊኬሽን ቁጥር 7
✅ሰረቱል ካህፍ
✅ሱረቱል መርዬም
✅ሱረቱል ጣሃ
✅ሱረቱል አንቢያዕ
🎙በኡስታዝ አቡ ኒብራስ ሙስጦፋ حفظه الله تعالى
✅PDF የተገጠመለት
✅ጥራቱን የጠበቀ የድምጽ ማብራሪያ ያለው
ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ!
#የእህቶቻችን_ስጦታ
አፕሊኬሽኑን ለማግኘት👇👇
/channel/islamic_app_omi/366
✅ ለወዳጅ ዘመዶ ያካፍሉ/ሸር ያድርጉ።
/channel/islamic_app_omi
የኢድ ስጦታ
ቁርዓን ተፍሲር በአፕሊኬሽን ቁጥር 5
✅ሰረቱል ዩኑስ
✅ሱረቱል ሁድ
✅ሱረቱል ዩሱፍ
✅ሱረቱል ረዕድ
🎙በኡስታዝ አቡ ኒብራስ ሙስጦፋ حفظه الله تعالى
✅PDF የተገጠመለት
✅ጥራቱን የጠበቀ የድምጽ ማብራሪያ ያለው
ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ!
#የእህቶቻችን_ስጦታ
አፕሊኬሽኑን ለማግኘት👇👇
/channel/islamic_app_omi/364
✅ ለወዳጅ ዘመዶ ያካፍሉ/ሸር ያድርጉ።
/channel/islamic_app_omi
የኢድ ስጦታ
ቁርዓን ተፍሲር በአፕሊኬሽን ቁጥር 3
✅ሰረቱል ማዒዳህ
✅ሱረቱል አንዓም
🎙በኡስታዝ አቡ ኒብራስ ሙስጦፋ حفظه الله تعالى
✅PDF የተገጠመለት
✅ጥራቱን የጠበቀ የድምጽ ማብራሪያ ያለው
ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ!
#የእህቶቻችን_ስጦታ
አፕሊኬሽኑን ለማግኘት👇👇
/channel/islamic_app_omi/362
✅ ለወዳጅ ዘመዶ ያካፍሉ/ሸር ያድርጉ።
/channel/islamic_app_omi
የኢድ ስጦታ
ቁርዓን ተፍሲር በአፕሊኬሽን ቁጥር 1
✅ሰረቱል ፋቲሓ
✅ሱረቱል በቀራ
🎙በኡስታዝ አቡ ኒብራስ ሙስጦፋ حفظه الله تعالى
✅PDF የተገጠመለት
✅ጥራቱን የጠበቀ የድምጽ ማብራሪያ ያለው
ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ!
#የእህቶቻችን_ስጦታ
አፕሊኬሽኑን ለማግኘት👇👇
/channel/islamic_app_omi/359
✅ ለወዳጅ ዘመዶ ያካፍሉ/ሸር ያድርጉ።
/channel/islamic_app_omi
ይቀጥላል...
የ1444 ሒጅራ የዒደል -ፊጥር ኹጥባ
----
🔴👉 ባህር ሸሽ 👈🔴
----
🔴➢➢ በአቡ ኒብራስ ሙስጦፋ وفقه الله تعالى
----
👉 /channel/AbuNamuse
--
🔴➢ /channel/AbuNamuse/1922
✍️ ከምንም በፊት ሀቅ ላይ መሆንህን መጀመርያ በደምብ አረጋግጥ። ከዛም በዛ ላይ ፅና። ምክንያቱም በባጢል ነገር ላይ ሆነህ ብትፀና ይህ ጥፋት እንጂ ፅናት አይባልም። ሀቅ ላይ መሆንህን በቁርአን በሀዲስ ለክተህ እርግጠኛ ከሆንክ ለማንም ኡኡታ ቦታ አትስጥ። የፈለከው ብትደረግ በቀላሉ አትሸነፍ። በዚህ ሰአት ሀቅን ይዞ በሱና ላይ ፀንቶ መጓዝ ፍም እሳት ይዞ የመሄድ አክል ከባድ ነውና ታገስ።
Читать полностью…----
🔴👉 ኢዕቲካፍ የመላክተኛው ሱና ነው ።
---
🔴👉 ከገባን እንደት እንግባ..?
----_
🔴👉 መቼ እንግባ...?
----
🔴👉 የት እንግባ..?
-----
🔴👉 የሚጠበቅብን ምንድነው...?
---- ----- ----
➢ መልሶቻቸውን እንካ ➢
👇------------------------------------------------👇
---
🔴➢ /channel/AbuNamuse
---
🔴➢/channel/AbuNamuse/1865
👇👇👇👇👇👇👇/channel/umuhilal1
ለይለተል ቀድር
▬▬▬▬▬▬
🔴➢/channel/Al_Miaraj_11
--==
በኡስታዝ አቡ ኒብራስ ሙስጠፋ - حفظه الله
---
🔴➢/channel/AbuNamuse
----
🔴➢/channel/AbuNamuse/1823
ጫት እና ወጣቱ
በሚል ርዕስ
የተዘጋጀ ገሳጭ ሙሀደራ ሲሆን ይህንን ሙሀደራ ላልደረሰው በማድረስ የበኩሎዎን ድርሻ ይወጡ።
👂👂 ይደመጥ
🎙 በሼኽ : አቡ ኒብራስ ሙስጦፋ አብደላህ حفظه الله
የተደረገ ሙሀደራ
🌐/channel/Tuaifetul_mensura
🟢👉 ምርጥ ነሲሀ ለሴቶች
ቆየት ካሉ የአቡ ኒብራስ ሙሰጦፋ አብደላህ ምክሮች
እንጠቀምባቸው ምክሮቹ ለማንኛውም ጊዜ የሚሆኑና ዘመን ተሻጋሪ ናቸው
📮 በውዱ ኡስታዛችን አቡ ኒብራስ
🌐 /channel/Al_Miaraj_11/1127
====
🌐 /channel/yusuf_dessie/617
📚《الصحيح المصفى من سيرة النبي المصطفى 72
የነብዩ ሙሀመድ ﷺ ታሪክ /ሲራ/
ክፍል 72
በሼህ አቡ ኒብራስ ሙስጦፋ አብደላህ
@historyofislam2
ወሊይ እና አታላይ ይለያያል
~
በሱፊያው ዓለም ሶላት የማይሰግዱ፣ ፆም የማይፆሙ፣ ከአላህ ተእዛዝ ያፈነገጡ በርካታ ወሊዮች አሉ። ለወንጀላቸው ሽፋን ይሆን ዘንድ “ትልቅ ወሊይ ለሰዎች ሲታይ ይወነጅላል። እሱ ግን ወንጀለኛ አይደለም” በማለት ኪታብ እስከመፃፍ የደረሱ አሉ። [አልኢብሪዝ፡ 2/23] እነዚህ የአላህ ሳይሆን የሸይጧን ወሊዮች ናቸው። የአላህ ወሊዮች በኢማን የደመቁ፣ በተቅዋ ያሸበረቁ ናቸው። አላህ እንዲህ ይላል፦
{أَلَاۤ إِنَّ أَوۡلِیَاۤءَ ٱللَّهِ لَا خَوۡفٌ عَلَیۡهِمۡ وَلَا هُمۡ یَحۡزَنُونَ (62) ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ وَكَانُوا۟ یَتَّقُونَ (63)}
{ንቁ! የአላህ ወሊዮች አይፈሩም አይተክዙም። እነሱም እነዚያ ያመኑትና የሚፈሩ የሆኑት ናቸው።} [ዩኑስ፡ 62-63]
የአላህ ወሊይ ለመሆን የሚያስፈልገው ኢማንና አላህን መፍራት ነው። ኢማንና ተቅዋ ያለው ሁሉ ወንድ ይሁን ሴት፣ ነጋዴ ይሁን ገበሬ፣ ወታደር ይሁን ወዛደር፣ ሐኪምም ይሁን አስተማሪ፣ ሊስቲሮም ይሁን ተላላኪ ሁሉም የአላህ ወሊይ ነው። “አማኞች በሙሉ የአረሕማን ወሊዮች ናቸው። አላህ ዘንድ ይበልጥ የተከበሩት ይበልጥ ታዛዦቹና ይበልጥ ለቁርኣን ተከታዮቹ ናቸው” ይላሉ ጦሓዊይ ረሒመሁላህ። [አልዐቂደቱ ጦሓዊያህ፡ 64]
የአላህ ወሊይ ለመሆን የወሊይ ዘር መሆን አያስፈልግም። ጋርዶ መቀመጥን አይጠይቅም። አጃቢ እንዲኖር አይጠበቅም። ትንቢት መናገር አይደለም መስፈርቱ።
ወሊይ ሞቶ ቀርቶ በህይወት እያለም የሰው ልጅ ከሚያደርገው የተሻገረ ምንም ሊያደርግ አይቻለውም። እንዲያውም “ልጅ፣ ዝናብ፣ ሲሳይ፣ ጤና፣ ህይወት እሰጣለሁ፣ እነሳለሁ፣ ዱስቱር ያለን እጠቅማለሁ፣ እምቢ ያለን እጎዳለሁ” ብሎ የሚሞግት ካለ እራሱን ለአላህ ባላንጣ ያደረገ ሸይጧን የሸይጧን ወሊይ ነው። ጌታችን እንዲህ ይላል፡-
{أَمَّن یُجِیبُ ٱلۡمُضۡطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَیَكۡشِفُ ٱلسُّوۤءَ وَیَجۡعَلُكُمۡ خُلَفَاۤءَ ٱلۡأَرۡضِۗ أَءِلَـٰهࣱ مَّعَ ٱللَّهِۚ قَلِیلࣰا مَّا تَذَكَّرُونَ}
{ወይስ ያ ችግረኛ በለመነው ጊዜ መልስ የሚሰጥ፣ ክፉንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደርጋችሁ (ይበልጣል ወይስ የሚያጋሩት?) (ይህን የሚያደርግ) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን?! ጥቂትንም አትገሰፁም!} [ነምል፡ 62]
እንኳን ወሊይና ነብይም ሌሎችን መጥቀም መጉዳት የሚችልበት ስልጣን የለውም። ሃያሉ ጌታ ነብዩን ﷺ ይህን አዋጅ እንዲያሰሙ አዟቸዋል፦
{قُلۡ إِنِّی لَاۤ أَمۡلِكُ لَكُمۡ ضَرࣰّا وَلَا رَشَدࣰا (21) قُلۡ إِنِّی لَن یُجِیرَنِی مِنَ ٱللَّهِ أَحَدࣱ وَلَنۡ أَجِدَ مِن دُونِهِۦ مُلۡتَحَدًا (22)}
{“እኔ ለናንተ መጉዳትንም ማቃናትንም አልችልም” በላቸው። “እኔ ከአላህ ቅጣት ማንም አያድነኝም። ከርሱም ሌላ መጠጊያን አላገኝም” በላቸው።} [ጂን፡ 21-22]
ወሊይነት በኢማንና በተቅዋ የሚገኝ እንጂ ከአባት፣ ከአያት የሚወረስ እቃ አይደለም። ማንም ቢሆን በስራው ያላገኘውን ማዕረግ በዘሩ አይቆናጠጠውም። ነብዩ ﷺ {ስራው ያስቀረውን ዘሩ አያስቀድመውም} ብለዋልና። [ሙስሊም፡ 2699]
ወሊይ ፍፁም የሆነ፣ የተናገረው መሬት ጠብ የማይል የሚመስላቸው አሉ። ወሊይ ሰው ነው። እንደማንኛውም ሰው ይሳሳታል። ነብዩ ﷺ {የሰው ልጅ ባጠቃላይ ተሳሳች ነው። ከተሳሳቾች ሁሉ በላጩ መመለስን የሚያበዙት ናቸው} ብለዋል። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 4515] ወሊዮች ሰዎች አይደሉም እንዴ? ለነገሩ አንዳንዶቹ መላእክት ናቸው ብለው ነው የሚያምኑት። አባቱ! ሶሐቦቹም መላእክት አልነበሩም።
የአላህ ወሊዮች የራሳቸው መጨረሻ የሚያስጨንቃቸው እንጂ “አብሽሩ እኛ አለንላችሁ”፣ “እኛን ያየ ጀነት ይገባል”፣ “ከቀብራችን የቆመ እሳት አይነካውም” የሚሉ አልነበሩም። “ሰላሳ የሚሆኑ የነብዩ ሶሓቦችን አግኝቻለሁ። ሁሉም በራሳቸው ላይ ንፍቅናን ይፈሩ ነበር” ይላሉ ታቢዒዩ ኢብኑ አቢ ሙለይካህ። [ፈትሑል ባሪ፡ 1/51]
የትኛውም የአላህ ወሊይ ከሸሪዐ አጥር የመውጣት ፍቃድ የለውም። ከነብዩ ﷺ ሸሪዐ ከወጣ እንኳን ትልቅ ወሊይ ተራ ሙስሊምም መሆን አይቻልም። ኢስላም አንድ ነው። ስውር የሚባል ሌላ ሸሪዐ የለም። “ሸሪዐ ሁለት አይነት ነው። ግልፅና ስውር። ግልፁ የመሀይማን ነው። ስውሩ የወሊዮች ነው” የሚሉ ሰዎች ያለጥርጥር ከሃ*ዲዎች ናቸው። አላህ ሶላት የማይሰግድ አጭበርባሪ ወሊይ የለውም።
{فَخَلَفَ مِنۢ بَعۡدِهِمۡ خَلۡفٌ أَضَاعُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَٱتَّبَعُوا۟ ٱلشَّهَوَ ٰتِۖ فَسَوۡفَ یَلۡقَوۡنَ غَیًّا}]
{ከነሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ፣ ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የጀሀነምን ሸለቆ ያገኛሉ።} [መርየም፡ 59]
ታላቁ የአላህ ወሊይ ዑመር ብኑል ኸጧብ ረዲየላሁ ዐንሁ “ሶላት የተው ሰው በኢስላም ውስጥ ምንም ድርሻ የለውም” ይላሉ። [አልሙወጦእ፡ 2/54] ስለዚህ “ዐርሽ ላይ ነው የምሰግደው”፣ “ሐረም በርሬ ሄጄ ነው የምሰግደው” የሚል ሰው አጭ *በርባሪ ማጅራት መቺ እንጂ የአላህ ወሊይ አይደለም።
#ከክፍል_10_የቀጠለ
በሁለቱ ወገን
መሀከል ግጭት ተፈጥሮ ዝምድና ወደ መቁረጥ ያደርሳል የሚል ነው።83
ይህ የከፊል ፊቅህ አዋቂዎች ጥረት ግን ሁሉንም ሊቃውንት የሚያስማማ አደለም ሌሎች በዚህ ተቃራኒ የሚሉ አሉ።
ሸይኽ ኢብን ባዝ እንዲህ ይላሉ፦
"ለዚህ (ቅርብ ዘመድን ከማግባት ለመከልከል) መሰረት የለውም እንደውም ቅርብ ዘመድህን ማግባትህ በላጭ ነው።
የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمለቅርብ ዘመዳቸው ድረዋል የአንዳንድ ፉቅሀዎች ንግግርማ ይህ መሰረት የለውም። እንደውም
እሱ ምርጫ አለው ከፈለገ ቅርብ ዘመዱን ያገባል ያጎቱን ልጅ ይመስል። ከፈለገ ደግሞ ሩቅ የሆነችን (ባዳ የሆነችን)
ያገባል ምንም ችግር የለውም።........"84
ሸይኽ ኢብን ኡሰይሚን ደግሞ እንዲህ ይላሉ፦
ፉቅሀዎች ባዳን (ዘመድ ያልሆነችን) ያግባ ሲሉ ያስቀመጡትን ምክንያት ከገለፁ በሗላ እንዲህ ይላሉ።
"(ፉቅሀዎች) የተናገሩት ትክክል ነው። ነገር ግን ከቅርብ ዘመዶች መሀከል በሌሎች ነገራቶች(በዲን በቤተሰብና በውበት)
ከሷ የተሻለ ከተገኘ ያ የተሻለ ይሆናል። ነገር ግን እኩል ከሆኑ ባዳዋ የተሻለች ናት።........ጥቅሙ ሚያመዝንበትን
መመልከት ነው ያለበት; በዚህ ነጥብ ላይ የመጣ ልንይዝበት ግድ ሚለን የሸሪአ ማስረጃ የለም።”
85
_ከላይ ለተፃፉት ቁጥሮች ማብራሪያ 👇🏻 _
82 ሙግኒ 7/83, መጣሊብ ኡሊኑሀ 5/9
83 መጣሊብ ኡሊኑሀ 5/9
84 ፈታዋ ኑሩን አለደርብ ካሴት ቁጥር
85 አሸርሁል ሙምቲእ 5/123
____
(ገፅ23-25)ድረስ
✍🏻ይቀጥላል ……ኢንሻ አላህ
@historyofislam2
حق الله لا ينتهي بانتهاء
رمضـــــــــــان
العلامة الشيخ د. صالح بن فوزان الفوزان - حفظه الله -
-----
🔴➢ """ ረመዷን በመጠናቀቁ የالله ሐቅ አይጠናቀቅም ረመዷን በማለቁ የالله ሐቅ በሞት እንጂ አይቋጭም ። የረመዷዷን አምላክ የሸዋልም ሆነ የሌሎች ወራቶች አምላክ ነው ። በሒይወታችሁ ሙሉ ድናችሁን ጠብቁ ድናችሁ ማለት ትልቁና ዋናው ካፒታላችሁ ነው ። መዳኛችሁም ነው። ይቀጥላሉ .......... """
------
🔴➢/channel/AbuNamuse
-----
🔴➢/channel/AbuNamuse/1959
@historyofislam2
📮📤🎁🎁የኢድ ስጦታ
ቁርዓን ተፍሲር በአፕሊኬሽን
ቁጥር 1⃣
✅ሱረቱል ፋቲሃ ሱረቱል በቀራ
/channel/islamic_app_omi/359
ቁጥር 2⃣
✅ሱረቱል ኢምራንና ኒሳዕ
/channel/islamic_app_omi/361
ቁጥር 3⃣
✅ሱረቱል ማዒዳህ እና አንዓም
/channel/islamic_app_omi/362
ቁጥር 4⃣
✅ሱረቱል አዕራፍ,አንፋል,ተውባ
/channel/islamic_app_omi/363
ቁጥር 5⃣
✅ሱረቱል ዩኑስ,ሁድ,ዩሱፍ,ረዕድ
/channel/islamic_app_omi/364
ቁጥር 6⃣
✅ሱረቱል ኢብራሒም,ሒጅር, ነህል ኢስራዕ
/channel/islamic_app_omi/365
ቁጥር 7⃣
✅ሱረቱል ካህፍ,መርዬም,ጣሃ,አንቢያዕ
/channel/islamic_app_omi/366
✅PDF የተገጠመለት
✅ጥራቱን የጠበቀ የድምጽ ማብራሪያ ያለው
ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ!
#የእህቶቻችን_ስጦታ
✅ ለወዳጅ ዘመዶ ያካፍሉ/ሸር ያድርጉ።
/channel/islamic_app_omi
የኢድ ስጦታ
ቁርዓን ተፍሲር በአፕሊኬሽን ቁጥር 6
✅ሰረቱል ኢብራሒም
✅ሱረቱል ሒጅር
✅ሱረቱል ነህል
✅ሱረቱል ኢስራዕ
🎙በኡስታዝ አቡ ኒብራስ ሙስጦፋ حفظه الله تعالى
✅PDF የተገጠመለት
✅ጥራቱን የጠበቀ የድምጽ ማብራሪያ ያለው
ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ!
#የእህቶቻችን_ስጦታ
አፕሊኬሽኑን ለማግኘት👇👇
/channel/islamic_app_omi/365
✅ ለወዳጅ ዘመዶ ያካፍሉ/ሸር ያድርጉ።
/channel/islamic_app_omi
የኢድ ስጦታ
ቁርዓን ተፍሲር በአፕሊኬሽን ቁጥር 4
✅ሰረቱል አዕራፍ
✅ሱረቱል አንፋል
✅ሱረቱ ተውባ
🎙በኡስታዝ አቡ ኒብራስ ሙስጦፋ حفظه الله تعالى
✅PDF የተገጠመለት
✅ጥራቱን የጠበቀ የድምጽ ማብራሪያ ያለው
ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ!
#የእህቶቻችን_ስጦታ
አፕሊኬሽኑን ለማግኘት👇👇
/channel/islamic_app_omi/363
✅ ለወዳጅ ዘመዶ ያካፍሉ/ሸር ያድርጉ።
/channel/islamic_app_omi
የኢድ ስጦታ
ቁርዓን ተፍሲር በአፕሊኬሽን ቁጥር 2
✅ሰረቱል ኢምራን
✅ሱረቱል ኒሳዕ
🎙በኡስታዝ አቡ ኒብራስ ሙስጦፋ حفظه الله تعالى
✅PDF የተገጠመለት
✅ጥራቱን የጠበቀ የድምጽ ማብራሪያ ያለው
ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ!
#የእህቶቻችን_ስጦታ
አፕሊኬሽኑን ለማግኘት👇👇
/channel/islamic_app_omi/361
✅ ለወዳጅ ዘመዶ ያካፍሉ/ሸር ያድርጉ።
/channel/islamic_app_omi
👉እውር ሲጠግብ ከመሪው ይጣላል..👈
---- ------ ____ :------ ----
🔴👉 ወንድማችን አቡ ጁሐይፋ አህመድ ወረባቦ ስለጀምዒዩ ተሳዳቢ ላሊ በላ ኑረድነል አረቢ ማሲንቆውን የሚያስጥል ግጥም ሰጥቶታል...
----
🔴👉 እህቶቻችንን አንሰጥህም ሲሉት ከነ አባታቸው እያጥረገረገ ጥሏቸዋል... ❗️❗️
---
🔴👉/channel/AbuNamuse/1187
----
🔴👉/channel/AbuNamuse
በያኮርፈኛል፣ እንጣላለን፣ እንለያያለን ሰበብ በፍርሃት እና በንቀት ጥላ ሥር የሚኖሩት ጓደኝነት ትክክል አይደለም። ባርነት ነው።
ወዳጄ!
መለያየትን ሳይሆን በጓደኝነት ሰበብ ተንቆ መኖርን ፍራ።
መለያየት የአላህ ቀደር ነው። ተንቆ መኖር ግን የራስ ምርጫ ነው።
ሲጀመር ጀምሮ ሙእሚን ቀጥ ያለ ብርቱ ነው። የሚደገፈዉም በአላህ ብቻ ነው።
ሰባሐል ኸይር
مصباح:
ኒ ካህ ፣ ሰ ር ግ፣ ኹልእ እ ና ፍቺን
የ ተመለ ከቱ ሸ ሪ አ ዊ ድን ጋጌ ዎች
ክፍል 1️⃣0️⃣
ከባለፈው የቀጠለ ……
23 | P a g e
2. እሷ ሳታቅና ሳትፈቅድ መመልከት ይፈቀድለታል?
አዎ ይፈቀድለታል እሷን ለመመልከት የሷ ማወቅና መፉቀድ መስፈርት አደለም ሊያገባት አቅዶ እስከሆነ ድረስ
በምትዘናጋበት አጋጣሚ ጠብቆ በድብቅ መመልከት ይችላል።ነገር ግን መመልከት ያለበት ሊያገባ ሲወስን ነው እንጂ
ዝም ብሎ ስሜቱን ለማርካት መሆን የለበትም።
ሀፊዝ ኢብን ሀጀር እንዲህ ይላል :-
"አብዛኞቹ ኡለሞች ወደሷ መመልከትን ከፈለገ ያለ ፍቃዷም ቢሆን መመልከትም ይችላል ብለዋል።77 ሸይክ
ናስረዲነል አልባኒም ሲልሲለተ ሰሂህ78 ላይ ይህንን የኢብን ሀጀር ንግግር በሀዲስ ያጠናክሩታል።
እንደውም ነግሯት ተመልክቷት ካልፈለጋት አልፈልግሽም ሲላት ቀልቧን እንዳይሰብራት ሳታቅ ቢመለከታትና
ካልፈለጋት በዛው ቢተዋት የተሻለ ይሆናል።
3. ደጋግሞ መመልከትስ ይፈቀድለታል?
በመጀመሪያ ምልከታው ለኒካህ የሚጠራውን ነገር በደንም ካልተመለከተና ዳግመኛ መመልከት ካስፈለገው ደግሞ
ቢመለከታት አይከለከልም።አሁንም ቢሆን መታወቅ ያለበት የሚመለከታት ስሜቱን ለማርካት መሆን እንደሌለበት
ነው።እሷን ለመመልከት ካልተመቻቸለትና ካልቻለ ሴት ተመለክታት ያየችውን ልትነግረው ትችላለች።
ኢማመ ነወዊ እንዲህ ይላል፦
"...በፍቃዷም ይሁን ያለ ፍቃዷ ደጋግሞ መመልከት ይፈቀድለታል። እሷን መመልከት ካልገራለት ሴት ተመልክታት
ያየችውን ትገልፅለታለች።"
79
4. ሊመለከተው የሚፈቀዱለት አካላቶች
ሊመለከታት የሚፈቀደውን አካሏን በተመለከተ በኡለሞች መሀከል ልዩነት ያለ ሲሆን
ሶስቱ አኢማዎች (ማሊኪይ : ሀነፍይና ሻፍእዮች) ጨምሮ አብዛኞቹ ኡለሞች ያሉበት አቋም መመልከት የሚችለው
እጇንና ፊቷን ነው የሚል ነው። ከአቡ ሀኒፍ እግሯንም መመልከት እንደሚችል ተወርቷል።80
ሁለተኛው አቋም በተለምዶ ቤት ውስጥ ስትንቀሳቀስ ምትገልጣቸውን አካላቶች መመልከት ይችላል የሚል ነው።
በመሆኑም በተልምዶ ብዙ ግዜ ቤት ውስጥ ምትገለጣቸውን ፀጉሯን እና እግሯን ይመስል መመልከት ይችላል የሚል
ነው።
ይህ ሁለተኛው አቋም ጠንካራው አቋም ነው ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ እሷ ሳታቅ መመልከት ከፈቀዱ ሳትዘጋጅ
ባለችበት የቤት ውስጥ የተለመደ አለባበሷ ላይ ሆና ሊመለከታት ተፈቅዶለታል ማለት ነው።በተጨማሪም ሴትን ሲያገባ
የፀጉሯን ውበት ማየት ሚፈልግ አለ።እንደውም አንዳንድ ወንዶች ለጸጉር ትልቅ ትኩረት ይሰጣሉና ጸጉሯን ሳያይ
ካገባት በኋላ ችግር ሊፈጥርበት ይችላልና ለጸጉር ቦታ ያለው ወንድ ጸጉሯን ቢመለከት ይችላል።ኢብን ባዝም
በፈተዋቸው ይህን አቋም ደግፈውታል።
5. በተጨማሪ መታወቅ ያለባቸው ነጥቦች
በሚመለከታት ግዜ ለብቻቸው ማግለል አይፈቀድላቸውም።ሊያገባት ስላሰበ ብቻ አጅነብይ መሆኗ አይወገድም
ፈቃደኝነቷን ገልጻ ለመጋባት ቢስማሙ እንኳን ኒካህ እስካላሰሩ ድረስ ብቻቸውን ካገለሉ ሶስተኛቸው ሸይጣን ነው።
የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمእንዲህ ብለዋል " አንድ ወንድ በአንድ ሴት አያገልም ሶስተኛቸው ሸይጣን ነው ሚሆነው"
_ከዚህ በታች ማብራሪያ ነው ከላይ ለተፃፉት ቁጥሮች👇🏻_
____
77 [ፈትህል ባሪ 9/157]
78 ሲልሲለተ ሰሂህ (1/156)
79 (ረውደቱ አጣሊቢን 9/34)
80 አልሀዊ አልከቢር(9/34) ፡ ረውደቱ ጣሊበይን (7/ 19-20) ቢዳየት አልሙጅተሂድ( 3/10 ) ሙግኒ (454) ተህዚብ አሱነን(3/
25-26)
____
24 | P a g e
በተጨማሪም በሚመለከታት ግዜ በስሜት መሆን የለበትም።ሊጨብጣትም ይሁን የትኛዋን አካሏ ሊነካ
አይፈቀድለትም።ልክ እንደ ወንዱ ሁላ ሴቷም ሊያገባት የፈለገውን ወንድ መመልከት ይፈቀድላታል።
*1.10 ለመተያየት ፎቶ መላላክ*
ለመተያየት ብሎ ፎቶ መላላክ ብዙ ጉዳቶች አሉት።
ከነዛ መሀከል
1. በፎቶ ማየት በአይን እንደማየት አይሆንም።ስንት ሰው ነው በፎቶ አይቷት ወዷት በአካል ሲመለከታት ሀሳቡን
የሚቀይር
2. ፎቶ ላይ የሌላትን ነገር edit አድርጋ ልትጨምርበት ትችላለች።ያለባትንም ጉድለት በቅንብር ልታጠፋ ትችላለች
3. ፎቶውን ለሱ ስትልክለት ለሌላ ሰው አሳልፎ ሊያሳየው ይችላል
4. ካየው በኋላ ሳይጋቡ ቢቀሩ እሱ ፎቶውን እንደሚያጠፋው እርግጠኛ መሆን አንችልም።አንዳንድ አላህን ማይፈሩ
ወንዶች ይባስ ብለው ይህንን ፎቶ ባደባባይ ፌስ ቡክ ላይ ሊለቅባት ይችላል።በተለይ ከተጣሉ ይህን ሊያደርግ
ይችላል።
ሙሀመድ ቢን ሳሊሀል ኡሰይሚን እንዲህ ተብለው ተጠየቁ
ጥያቄ ፦ “ሊያገባት የሚፈልግ ሰው ሩቅ ሀገር ካለ እንዲመለከታት ብላ በኢንተርኔት ፎቶዋል መላክ ትችላለች?
እንዲህ ብለው መለሱ፦
“ይህን አልመለከትም(አልደግፈውም)፦ አንደኛ ሌላም ሰው (ይህንን ፎቶ) ሊመለከት ይችላል። ሁለተኛ ፎቶ ትክክለኛ
ማንነቷን አይገልጽም ስንትናስንት ፎቶ ተመልክቶ ራሷን ሲመለከት ተቃራኒ የሆነች።ምናልባትም ይህች ፎቶ ሰውየው
ጋር ትቀራለች እሱ ማጨቱን ይተዋል(ይተዋታለ) ከዛም በዚህ ፎቶ እንደፈለገ ይጫወትበታል።
በመሆኑም ይህንን በር በልቁ ክፍት ማድረጉ ተገቢ አደለም።ባይሆን ምናልባት አማራጭ በጠፋበትና ከላይ
የተጠቀሱ ጉዳቶችም አይከሰቱም ተብሎ በሚታመንበት ሁኔታ መሆን አለበት።
1.11 የቅርብ ዘመድን ስለማግባት
አንዳንድ ፉቅሀዎች ቅርብ ዘመድን (ያጎት ልጅን ይመስል) ማግባት ይጠላል ይላሉ።በዚህ ላይ የመጡም ባዳ(ዘመድ
ያልሆነን) በማግባት የሚያነሳሱ ሀዲሶች አሉ።ነገር ግን ባዳን (ዘመድ ያልሆነን) እንድናገባና ዘመድን እንዳናገባ የሚናገሩ
ሀዲሶች በሙሉ ደካማ መሆናቸውን የሀዲስ ሊቃውንታት አስቀምጠዋል
ታላቁ የሐዲስ ሊቅ ሸይኽ አልባኒ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦
ባዳን በማግባት ላይ የሚያነሳሳ ትክክለኛ ሀዲስ መጥተዋል?
ሲመልሱ " አይ (አልመጣም)" በማለት ነበር81
በተቃራኒው ግን ቅርብ ዘመድን ማግባት እንደሚፈቀድና ምንም ችግር እንደሌለው የሚጠቁሙ በርካታ ክስተቶች አሉ
ከነዛም መሀከል ፦
1ኛ፦ የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمየአክስታቸው ልጅ (በአባት በኩል) የሆነችውን ዘይነብ ቢንት ጃህሽን አግብተዋል።
2ኛ፦ የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمልጃቸውን ዘይነብን ለአክስታቸው ልጅ (በእናት በኩል) ለሆነው ለአቢል አስ
ድረውለታል።
____
81 ሲልሲለት ሁዳ ወኑር ካሴት ቁጥር 594/ 53ኛው ደቂቃ
______
25 | P a g e
3ኛ፦የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمልጃቸውን ፋጢማ ያጎታቸው ልጅ (በአባት በኩል) ለሆነው ለአልይ ድረውለታል
ቅርብ ዘመድን ከማግባት የሚከለክሉ ሀዲሶቹ ደካማ ቢሆንም ብዙሀኑ የፊቅህ ሊቃውንታት ቅርብ ዘመድን ማግባት
አይደግፉትም። ባዳን ማግባት የተሻለ ነው ይላሉ።ለዚህ ደግሞ እንደምክንያት የሚያቀርቡት የሀዲስ ማስረጃ ባይኖርም
በጥረታቸው (ኢጅቲሀዳቸው) ያገኟቸውን ምክንያቶች ነው። ከነዛ ምክንያቶች መሀከል ሁለቱን ልጥቀስላቹ፦
ባዳ ከሆነች ሴት ጋር መጋባት የሚወለደው ልጅ ያማረ እና ጠንካራ አካል እንዲኖረው ያደርጋል የሚል ነው። ባዳ
ከሆነች ሴት መውለድ ልጅን ያጠነክራል ከቅርብ ዘመድ መውለድ ያደክመዋል ይባላል።82
ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ምናልባት እነዚህ ባለትዳሮች ተጣልተው ቢለያዩ ቅርብ ዘመዳሞች ከሆኑ
@historyofislam2
✅ ጥያቄ 01
1/ሰው ማማት ፆም ያስፈታልን?
2/ ግንኙነት ሳያደርግ ፈሳሽ ቢመጣው ፆም ያስፈታልን?
3/ ደም ፆም ያስፈታልን?
4/ ውሀ በጆሮው እና ባፋንጫው ቢገባ ፆም ያስፈታልን?
5/ እረስቶ ቢበላ ፆም ያስፈታልን?
6/ እንድ ሰው ቢያስታውከው ፆም ያስፈታልን?
7/ ዋግምት መሰራት ፆም ያስፈታልን?
8/ምራቅ እና አክታ ፆም ያስፈታልን?
9/ሽታ ፆም ያስፈታልን?
♻️እና ሌሎችም ጠቃሚ የሆኑ ጥያቄወች ይገኙበታል?
🕌 በነስር መስጂድ
🔴👉 አቡ ኒብራስ حفظه الله
----
🔴👉 /channel/AbuNamuse
👇👇👇👇👇👇👇/channel/umuhilal1
🔜 ሰዎች መሳል እያሉ ስለሚሳሉበት እና ስለሚምሉበት የሽርክ ቦታ
🔜 ኡስታዝ አቡ ኒብራስ (ሐፊዘሁሏህ)
🔜 /channel/Tuaifetul_mensura/3255
🔜 ሸር አድርጉ ‼️
ኒ ካ ህ ፣ሰ ር ግ ፣ኹ ሉ እ እና ፍቺን የተመለከቱ ሸሪአዊ ድንጋጌዎች
ክፍል 9️⃣
ከባለፈው የቀጠለ ……
*1.8 መተጫጨት*
*አንድ ወንድ ለትዳር ሊያጫቸው ማይፈቀዱለት ሴቶች*
1. ባሏ ፈቷን ኢዳዋን እየቆጠረች ያለችን ሴት ኢዳሽ ሲያበቃ እኔ አገባሻለው ብሎ ማለት አይቻልም።ይህ ማለት
ኢዳዋ ሳያበቃ ልትታጭ አትችልም ማለት ነው። ምክንያቱም በዚህ ጊዜ ውስጥ የፈታት ባል እሷን የመመለስ ሙሉ
ስልጣን አለዉና። በዚህ ላይ በኡለሞች መሀከል ምንም ኺላፍ የለበትም
የተፈታችው ግን በሶስት ከሆነ ወይም ደግሞ ባሏ ሞቶ ከሆነና ኢዳዋ ካላለቀ ሊያገባት ሚፈልግ የሆነ ሰው በቀጥታ
ሳይሆን በአሽሙሩ እንደሚፈልጋት ሊነግራት ይችላል። ምሳሌ እኔ ያንቺን አይነት ሴት እፈልጋለሁ ይላታል።ኢዳዋ
እስካላለቀ ድረስ ግን ሊጋቡ አይችሉም በግልጽም አንቺን ላገባሽ እፈልጋለሁ አይላትም።አላህ (سبحانه وتعالى (እንዲህ
ይላል
وَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ فِيمَا عَرَّضْتُم بِهِ مِنْ خِطْبَةِ النِّسَاءِ أَوْ أَكْنَنتُمْ فِي أَنفُسِكُمْ ۚ عَلِمَ اللَّهُ أَنَّكُمْ سَتَذْكُرُونَهُنَّ وَلَـٰكِن لَّا تُوَاعِدُوهُنَّ سِرًّا إِلَّا أَن تَقُولُوا قَوْلًا مَّعْرُوفًا ۚ وَلَا تَعْزِمُوا عُقْدَةَ النِّكَاحِ حَتَّىٰ يَبْلُغَ الْكِتَابُ أَجَلَهُ ۚ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِي أَنفُسِكُمْ فَاحْذَرُوهُ ۚ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٌ
(አል-በቀራህ - 235)
{{ሴቶችንም ከማጨት በርሱ ባሸሞራችሁበት ወይም በነፍሶቻችሁ ውስጥ (ለማግባት) በደበቃችሁት በናንተ ላይ
ኃጢኣት የለባችሁም፡፡ አላህ እናንተ በእርግጥ የምታስታውሷቸው መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ (ስለዚህ ማሸሞርንና ማሰብን
ፈቀደላችሁ፡፡) ግን በሕግ የታወቀን ንግግር የምትነጋገሩ ካልኾናችሁ በስተቀር፤ ምስጢርን (ጋብቻን) አትቃጠሩዋቸው፡፡
የተጻፈውም (ዒዳህ) ጊዜውን እስከሚደርስ ድረስ ጋብቻን ለመዋዋል ቁርጥ ሐሳብ አታድርጉ፡፡ አላህም በነፍሶቻችሁ
ያለውን ነገር የሚያውቅ መኾኑን ዕወቁ፤ ተጠንቀቁትም፡፡ አላህም መሓሪ ታጋሽ መኾኑን ዕወቁ፡፡}}71
2. አንድትን ሴት አንድ ወንድ ለትዳር ከጠየቃትና እሺ ካለችው በኋላ እሱ ለትዳር ጠይቋት እሺ እንዳለችው እያወቀ
ሌላ ሰው ያችን ሴት ለትዳር መጠየቁ አየፈቀድልንም። ለትዳይ ጠይቆ መልስ እየተጠባበቀ መሆኑን ካወቅንም
መልሱ ምን እንደሚሆን ሳናውቅ እኛም ለትዳር መጠየቅ አይፈቀድልንም። መልእክተኛውصلى الله عليه وسلمእንዲህ ብለዋል
{ َلايبع أحدكم على بیع أ َ خیه ولايخطب خطب على خطبة أخیه}
{አንዳችሁ በወንድሙ ሽያጭ ላይ እንዳይሸጥ ወንድሙ ባጨው ላይም እንዳያጭ}
72
ለትዳር የጠየቃትን ግለሰብ ግን አስፈቅደነው እኔም ለትዳር ልጠይቃት ነው ስንለው ከፈቀደልን እኛም መጠየቅ
እንችላለን ምክንያቱም ሀቁ የሱ ነው ከፈቀደ ችግር አይኖረውም።ቀድሞ እሱ ጠይቆ መልስ እየጠበቀ ቢሆን እንኳን
እኛም እንድንጠይቃት ከፈቀደልን ከመጠየቅ። ግን የፈቀደልን ፈርቶን ወይም እፍረት ተሰምቶት መሆን የለበትም።73
ሙስሊም ወንድማችን ያጫትን ሴት ማጨት ምንከለከለው አልፈልግህም የሚል መልስ እስካልተሰጠው ድረስ
ብቻ ነው።ለትዳር የጠየቃት ልጅ አልፈልግህም ብላ ከመለሰችው እኛም በተራችን መጠየቅ እንችላለን። እሷ
ሙስሊም ሆና ሊያገባት የጠየቃት ደግሞ ካፊር ከሆነ እሱ እንዳያገባት ብለን ቢሆን እንኳን እኛ እሷን ለትዳር
መጠየቅ እንችላለን።ምክንያቱም ሙስሊም ሴት ለካፊር ወንድ አትፈቀድም።
*1.9 ሊያገባት የፈለጋትን ሴት መመልከት*
1. ሊያገባት የፈለጋትን ሴት ማየት መፈቀዱን በተመለከተ
አንድ ወንድ ሊያገባት የፈለጋትን ሴት መመልከት እንደሚችል የሚጠቁሙ በርካታ ሀዲሶች አሉ። ከነዛህ መሀከል ጃቢር
ቢን አብደላህ በዘገበው ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል።
{اذا خطب أحدكم المراة فإن استطاع أن ینظر الى ما یدعوه الى نكاحھا فلیفعل }
((አንዳችሁ ሴትን ሊያገባ ካጫት ወደ ኒካህ ሚጠራውን ነገር መመልከት ከቻለ ይስራው (ይመልከት)።))74
ኢብን ቁዳማ እንዲህ ይላል፦
"ኒካህ ሊያስርላት የፈለጋትን ሴት መመልከት እንደሚችል በኡለሞች መሀከል ምንም ኺላፉ አናውቅም።75
ኒካህ ከተደነገገባቸው ምክንያቶች አንዱ ራሱን ከዝሙት ለመጠበቅ ነው።ሚስቱ ስሜቱን ልታረካለት ምትችል አይነት
ካልሆነች ደግሞ አግብቶም ቢሆን ዝሙት ላይ ሊወድቅ ይችላል።ስለዚህ ይህች ሴት አይኑን ሊያሳርፍባት የምትችል
አይነት መሆኗን ለማወቅ አስቀድሞ ሊመለከታት ተገቢ ነው። በመሆኑም ሊያገባት የፈለጋትን ሴት መመልከቱ
እንደውም የተወደደ (ሙስተሀብ) ተግባር ነው76።በመሀከላቸው ፍቅር እንዲኖርም አይቷት እና ወዷት ቢገባበት የተሻለ
ነው።ነገር ግን ሳያያት ቢያገባት ኒካሁ አይበላሽም ትክክለኛ ነው።
_ከዚህ በታች ከላይ ለተፃፉት ቁጥሮች ማብራሪያነው 👇🏻_
_
71 አል በቀራ 235
72 ቡኻሪ (2140) ሙስሊም (1413)
73 አሸርሁል ሙምቲእ (5/139 ዳር ኢንል ጀውዚ1430 ዓ.ሂ)
74 [ሰሂህ አቡ ዳውድ 1832; 1834]
75 [ሙግኒ 9/489]
76 አሸርሁል ሙምቲእ
(ገፅ 21-22)ድረስ
✍🏻ይቀጥላል ……ኢንሻ አላህ
@historyofislam2