hiwotemenekosatgroup | Unsorted

Telegram-канал hiwotemenekosatgroup - ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

245

✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን።✝️ ✞ይህ ሕይወተ መነኮሳት የተሰኘው ስለ ነገረ ምንኩስና ተባህትዎ የምንነጋገርበት የምንማማርበት መወያያ ግሩፕ ነው። ኑ እንደ አባቶቻችን በጥብዓት በተባሕትዎ እንኖር ዘንድ ሕይወታቸውን እንመርምር ሥርዓታቸውንም እንማር በፍኖተ አበው እንጓዝ በረከታቸውንም እናግኝ። 🔆 @hiwotemenekosat @hiwotemenekosatbot ሃሳብ መስጫ

Subscribe to a channel

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

🌼አባ ሰራፓሞን ሊቀ-ካህን
              ዘገዳመ አስቄጥስ🌼

ዳግመኛም በዚህች ዕለት በአስቄጥስ የቅዱስ ዮሐንስ ገዳም ሊቀካህን አባ ሰራፓሞን አረፈ።

🍒ይህ አባት በገዳመ አስቄጥስ ከሚገኙ ገዳማት በአባ ዮሐንስ ገዳም ሊቀካህናት ነበር፡፡ ይህ ቅዱስ በዚሁ ገዳም በወጣትነቱ መነኮሰ፡፡ በዚያ ገዳም እግዚአብሔርን እያመለከ እና አረጋውያንን እያገለገለ ለ ፴፪ ዓመታት ቆየ፡፡ከዚያን ወደ ገዳሙ ሊቀ ካህንነት ማዕረግ ተሸጋገረ፥ ኃላፊነቱንም ተረከበ፡፡ በጽድቅ ስራው እና በትሕርምት ሕይወቱም የበለጠ የሚተጋ ሆነ፣ ከመነኮሰበት ቀን አንስቶ እስከ ዕለተ ዕረፍቱ ቀን ድረስ ይጾም ነበር፡፡

🍒ለ፳፪ ዓመታት ገዳሙን ከመራ በኃላ በአንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ራሱ ላይ ዘጋ፥ በዚያም ለ ፲ ዓመታት ቆየ፥ ማንም አላየውም ነበር፡፡ በዚህን ወቅት ከቅዳሜ እና እሁድ በቀር አይመገብም ነበር፡፡ ዕለተ ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ የጌታ መልአክ በራዕይ ተገለጠለት እና የእሳት መስቀል ሰጠው እንዲህም አለው:- "ይህን መስቀል በእጅህ ተቀበለኝ" ቅዱሱም መልሶ "እንዴት በእጄ እሳት ይዛለሁ?" መልአኩም አለው" አትፍራ ክርስቶስ እሳቱ በአንተ ላይ ስልጣን እንዳይኖረው አድርጓል"፡፡ ቅዱሱም እጁን ዘርግቶ ከመልአኩ መስቀሉን ተቀበለ፡፡

🍒 መልአኩም እንዲህ አለው:-"በርታ ከቅዱሳት ምስጢራትም ተካፈል በሥስተኛውም ቀን መጥቼ ወስድሀለሁ፡፡" ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ስለ ራዕዩ ለአረጋውያኑ ነገረ፡፡ አረጋውያኑ በእንባ ተሰናበቱት፥ እንዲያስታውሳቸውም አማጸኑት፡፡ እርሱም በጸሎታቸው እንዲያስታውሱት ጠየቃቸው፡፡ በሥስተኛው ቀን አረጋውያኑ በዙሪያው ተሰብስበው ሳለ አረፈ፡፡

🙏ጸሎቱ ከኛ ጋር ትሁን፡፡ አሜን፡፡

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

🌸መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ🌸

🎥 ቪዲዮ

@Hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

🌸ምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ አንድነት ገዳም🌸

💠low quality💠

@Hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

🌺የጻድቃን መታሰቢያ ለዘልዓለም ይኖራል🌺
መዝ 111

🌷ተወዳጁ አንደበተ ርቱዕ ሰባኪ ሳንጠግባቸው በማለዳ የተለዮን ብጹዕ አቡነ መልከጸዲቅ በህይወት ዘመናቸው ከሰበኩት ስብከቶች በምድረ ከብድ ገዳም ከሰበኩት የማስታውሰው

🌳ምዕመናን እስቲ ቀና ብላችሁ የጻድቁን ስዕል እዮ የታለ
አጽፋቸው የታለ ቀሚሳቸው የታለ ፈረጂያቸው ❔❓ ክርስትና ሳይለብሱ የሚሞቁባት ናት። ከመስቀል ከመቁጠሪያ ከወንጌል ውጪ ውሐ መጠጫ ቅል እንክዋን አልያዙም እኛ አልፈን ተርፈን የመቃብር ፉካ እንሰራለን። ጻድቁ ማን ይቀብረኛል አላሉም ግን ይኸው እኛን ሁሉ በእምነት ወልደው ዝክራቸውን አናስታጉልም ።

🌷የዛሬ 900 አመት እንደነበሩ ዛሬም በአጸደ ነፍስ ይመላለሳሉ መሐላችን በሁሉ የተወደዱ ናቸው። ጻድቁ ወንጌልን ዘር ሳይለዮ ለፍጥረት ሁሉ መግበዋልና ድልድይ ናቸው። ድልድይነታቸው የሰማዩን መንግስት በምድር በመስበክ ብቻ አይደለም ተራራና ወንዝ የለየውን ህዝብ በቃለ ወንጌል ከትረዋልና ነው።

🌷በኤርትራ በትግራይ አባ ጋብር እያሉ ልጆቻቸው ይጠሩዋቸዋል። በሌላው የኢትዮጵያ ምድርም ገብረመንፈስ ቅዱስ "አቡዬ ጻድቁ" እየተባሉ በልዕልና ይጠራሉ። በኦሮሞ ወገኖቻችንም አቦ እያሉ በፍቅር ይጠሩዋቸዋል "አቦ ነባሲ"እያሉ ይመኩባቸዋል። ሊቃውንቱም አቡነ ገብረ ሕይወት ይሉዋቸዋል ድንቅ ነው።

🌼ራሳቸውን ሳይሆን ክርስቶስን ሰብከው ነው ያለፉ። መናፍቃን እንደሚያጠለሹት አይደለም አትስሙ። ጌታችንም ክብራቸው ጽድቃቸው ገድላቸውን ውለታ ዋጋ ከፋይ ነውና አደባባይ አወጣው። በአናብስት በአናብርት ተከበው የኖሩትን ባህታዊ ይኸው በአለም የተዘራው ኦርቶዶሳዊ ሁሉ አቡዬ አቡዬ አቡዬ ይላቸዋል።

🌷 በምልጃቸውም ብዙዎችን ታደጉ ይታደጋሉም።ምን መሰላችሁ ሐቁ በኛ ዘመን ራሳችንን ነው አልቀን (ከፍ አርገን) የምንሰብከው።

🥀እስክንመነኩስ እስክንጰጵስ ዘመድ የለን ሁሉ ወገናችን ነው። ልክ ከፍ ስንል ወንዝና ተራራ ቆጠራ ይመጣል። በየነገዳችን ባለጸጎች ቤት ለአድማ እንሰበሰባለን። ወንጌላዊነት ሐዋሪያነት ተረስቶ ሌላ ካባ እንለብስና ገጻችን ሌላ ውስጣችን ሌላ ይሆናል።

💠 ታድያ ህዝቡ እንዴት ያክብረን❓ እንዴት ይከተለን❓ ከሁሉ ጋር ስናንቦጫርቅ ፤ ገብረመንፈስ ቅዱስ እኮ መንፈስ ቅዱስ ገልጾላቸው እንጂ አረባዊ ነው አንደበታቸው ግን ወገናችን ብለን እናከብራቸዋለን። ለአንድነታችን ምክንያት ናቸው። ዛሬም በስማቸው እንድንሰበሰብ ምክንያት የሆነው ጽድቃቸው ገድላቸው ነው እና አስመሳዮች አንሁን በተለይ እኛ አባቶች ከዕምነት መስመር ወጥተን መዘባረቅ የለብንም። ክብራችንን እንጠብቅ የጻድቁን መንገድ እንከተል የአመት ሰው ይበለን።

🌷በዛ ጣፋጭ አንደበታቸው ብዙ ነው ያስተማሩ ያስታወስኩትን ከመዝገብ አግኝቼ ነው እንደወረደ

🌹🙏የጻድቁ ምልጃ ታማኝ እረኛ አያሳጣን አሜን🙏🌹

Credit : anteneh haile (A.H) fb page

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

# በግብጽ ፤ የካቲት 30 ዕረፍታቸው የኾነው በቅድስና ሕይወታቸው በሚታወቁት ና ከግብፅ ከአቡነ ሺኖዳ 3ኛ በፊት የግብፅ ፓርትርያርክ የነበሩት እና እጅግ ብዙ ታምራትን እያደረጉ ያሉትን ቅዱስ ታሪካቸው እነሆ ።##
⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜
አቡነ ቄርሎስ 6ኛ ነሐሴ 27 ቀን 1895 ዓ/ም በግብፅ ደማንሁር በሚባል ከተማ ተወለዱ። የልደት ስሙ አዜር ዘኪ ነው ።አባቱ ዩሴፍ ዘኪ ይባላል ።የሦስት ልጆች አባት የሆነው ዩሴፍ ዘኪ በአካባቢው የተከበረ ዲያቆን ነበረ ።የልጆቹም የዕለት ተዕለት ተግባርም ቅዱሳት መፅሐፍትን ማንበብ እና ታሪካቸውን ማዳመጥ ነበረ ።የዩሴፍ ዘኪ ቤተኛ የሆኑ አባ ቴዎድሮስ የተባሉ መነኩሴ "ከእኛ እንደ አንዱ የሚሆን ልጅ ነው" በማለት ከልጆቻቸው አንዱ ስለሆነው ስለ አዜር ትንቢት ተናገሩ ።አዜር ዕድሜው ለትምህርት በደረሰ ጊዜ በአካባቢያቸው በሚገኝ ትምህርት ቤት ገባ።አዜርና ቤተሰቡ የትውልድ ቦታቸውን ለቀው ወደ እስክንድርያ ከመጡ በኃላ አዜር የ2ኛ ደረጀ ትምህርቱን አጠናቆ አንድ አውስትራልያዊ ባቋቋመው ድርጅት ውስጥ የመርከበኞች ረዳት ሆኖ ተቀጠረ ።አዜር ሃያ አምስት ዓመት ሲሞላው ለመሥሪያ ቤቱ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ
አቀረበ ።ዐሳቡን ለማስቀየር ብዙ ቢደረግም ከዕቅዱ ወደ ኃላ ሊያስቀረው የሚችል ሰው አልተገኘም ።
⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜
ወደ ገዳም ከሄደም በኃላም በታማኝነቱ በታዛዥነቱ በቅልጥፍናውና በንፅሕናው የመነኰሳቱን ፍቅር ያተረፈው አዜር በዓመት ውስጥ ምንኲስናውን በምርቃት ተቀብሎ ስሙ አባ ሚና አል- ባራሙሲ(Mina of the Roman Monasetery) ተባለ ።አባ ሚናስ በመነኰሰ በሦስት ዓመቱ በ1931 ዓ/ም ሁለት ወንድሞቹ በተገኙበት ቅስና ተቀበለ ።አባ ሚናስ ከቅስናው በኃላ መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብቶ እንዲማር ውሳኔ ተላልፎ እየተማረ እያለ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዩሐንስ የኮሌጁ አስተዳደር ተደርጐ ሲሾም ሹመቱን በመሸሽ ሶሃግ በሚገኘው የአባ ሲኑዳ ገዳም ተሸሽጎ መኖር ጀመረ ።ፓትርያርኩ አስጠርቶት አባ ሚናስን ስለ ጥፋቱ ቢገሥፀውም ሚናስ ግን ምኞቱ በገዳም መኖር እንደሆነ በግልፅ ስለነገረውና እርሱም ስለተረዳለት እንደ ፍላጎቱ እንዲኖር ሆነ።
⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜
ለንሰሐ አባቱ ለአባ አብድል መሲህ በማስፈቀድ አባ ሚናስም ካለበት ገዳም አንድ ሰዓት የእግር ጉዞ ወደሚርቀው በበረሃ ወደሚገኘው እጅግ አስፈሪና በመርዛም እባቦች በተከበው ዋሻ ሄዶ መኖር ጀመረ ።ዋሻውን በሦስት ከፍሎ ካደራጀ በኋላ በፆም በፀሎት በስግደት በርካታ ቅዱሳት ፅሑፎችን በማምበብ ዕረፍት የሌለውን ኑሮ ተያይዘው ።በየሳምንቱም ወደ ገዳም ይመጣ ነበረ ።በአንድ ወቅት ለዓቢይ ፆም በሰሙነ ሕማማት አባ ሚናስ እንደተለመደው ወደ ገዳም ሲሄድ አበምኔቱ ፀጥታ አስከባሪ አስመጥቶ አንጋፋ መነኰሳት ከገዳሙ ለማባረር ሲጋበዝ ደርሶ በዚህ ፍርድ መዛባት አዝኖ አብሮቸው ወደ ካይሮ ተሰደደ።
⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜
በእግዚአብሔር ፈቃድ ለፓትርያርኩ ነግሮ አባ ሚናስ መነኰሳቱን ወደ ገዳም አድርሶ ወደ ካይሮ በመመለስ ልዩ ልዩ ገዳማት ሲጎበኙ ቆይቶ ለብዙ ዓመታት በወፍጮ ቤትነት ሲያገለግል የነበረው በሸለቆ በተከበበው አሮጌ ቤት ያለምንም ቁሳቁስና ብርድ ልብስ ውሎ እያደረ ጠዋት ተነሥቶ በአካባቢው በሚገኘው በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እያስቀደሰ ማንም ሳያስተውለው ሹልክ ብሎ ይመለሳል ።ከምዕመናን ገንዘብ በመሰብሰብ ገዳማትን ይረዳ ነበረ ።የአባ ሚናስ የሥራ ፍሬ ታዋቂነትና ተወዳጅነት እየጨመረ በመጣ ቁጥር የገንዘብ እርዳታውም በዚያው ልክ ስለ ጨመረ በአሮጌው ካይሮ አምስት መቶ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ቦታ ገዝቶ ከልጅነቱ ጀምሮ እጅግ በሚወደውና በታምር ሰሪው በሰማዕት ቅዱስ ሚናስ ስም ትልቅ ገዳም አሳነፀ።
⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜
በዚህ ገዳም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ከልዩ ልዩ ሕመሞችና ርኲስ መንፈስ ድነዋል።ከአቡነ ዩሐንስ ዕረፍት በኃላ ለፕትርክና ውድድር ሲጠየቅ "እኔ ትል እንኳን የምትበልጠኝ መድረሻ ቢስ ሰው ስሆን እንዴት እንዲህ ዐይነት ግርማ ሞገስ ለሚጠይቅ የተቀደሰ ኃላፊነት እወዳደራለሁ?"።ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ሚያዚያ 11 ቀን 1952 ዓ/ም ፓትርያርክ አቡነ ቄርሎስ 6ኛ ተብሎ ተሾመ።
በዕለቱም ወንጌል ሲያነብ "እኔ መልካም እረኛ ነኝ" የሚለውን የጌታችንን ቃል ከትህትናው የተነሳ ደፍሮ መናገር ባለመቻሉ"ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ራሱ እንዳለው መልካም እረኛችን እርሱ ነው " ብሎ ዕንባ እያነቀው አነበበ።
⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜
አቡነ ቄርሎስ 6ኛ በብሕትውና ኑሮ ያደረገው የነበረውን ገድልም አልተወም።ኃላፊነቱን በትጋት ተወቶ የካቲት 30 ቀን 1964 ዓ/ም ከዚህ አለም በሞት ተለየ።
## # የባባ ሲሪልን(አቡነ ቄርሎስ 6ኛ ) ቅድስና በማስመልከት አቡነ ሺኖዳ 3ኛ እንዲህ ብሏል :- "በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ እንደ ባባ ሲሪል ያለ ታሪክ ያለው ሰው የለም ።እጅግ ብዙ የሆኑ፡- ከዐሥራ ሁለት ሺ በላይ ቅዳሴዎች ላይ ተሳትፏል።በዓለምም ሆነ በእስክንድርያ የፕርትርክና ታሪክ ውስጥ ይህን ያህል ቅዳሴ የቀደሰ ፓትርያርክ አልተመዘገበም።ባባ ሲሪል በዚህ ሥርዓቱ የሚደነቅ አባት ነው " ብለዋል
⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜
## # በግብፅ ካይሮ በዘይቱ በምትገኘው ቤተክርስቲያን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተገለጠችው በሳቸው ዘመን ነው ።
## # የቅዱስ ማርቆስ ቅዱስ አካል ከብዙ ዘመናት በኃላ ወደ ግብፅ ካይሮ እንዲመለስ እና በስሙ ባሳነፀው ካቴድራል ውስጥ በክብር አስቀምጧል ።
ካቴድራሉ ሲመረቅም ንጉሥ ኃይለ ስላሴ፣የግብፅ ፕሬዚዳንት ገማል አብድል ናስር እና ሌሎች ተገኝተዋል ።
ፀሎት እና ምልጃቸው አይለየን።
ቅዱስ ቄርሎስ የልብ የሚያደርስ
ቅዱስ ሚናስ ፈጥኖ የሚደርስ
አሜን ፫!!!!

©"ሰማዕቱ ሚናስ ወአቡነ ቄርሎስ" ገጽ, fb

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ስላካፈልሽን እናመሰግናለን ማህደር!

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

             †              

" እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሁሉ ፥ ኑ ፥ ስሙኝ ፤ ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ። " [መዝ.፷፮፥፲፮]


ስሙ Flecher Devid ይባላል የሳንዲያጎ ተወላጅ ሲሆን አግብቶ አንድ ልጅም ነበረው። አባቱ የእስልምና ተከታይ እናቱ ደግሞ ክርስትያን ናቸው። ከዚህ በፊት ኒውዮርክ መንትያ ህንጻዎች ላይ የደረሰውን የሽብር አደጋ የተመለከተው ወላጅ አባቱ በብስጭት አንድ ድምዳሜ ላይ ደረሰ። "አምላክ ቢኖር ኖሮ ይሄ አደጋ አይፈጠርም ነበር" ብሎ Atheist ወይም አምላክ የለሽ ሆነ።

በዚህ አደጋ የተነሳ ፍሌቸርም ልጁ ሞተበት ፤ ሚስቱም ሱሰኛ ሆና በDrug ምክንያት ሞተች። ከዚህ ሁሉ መከራ በኋላ ፍሌቸርም የልብ ህመምተኛ ሆነ። ሁለት ጊዜም የልብ ቀዶ ጥገና አድርጓል።

በሁለተኛው ቀዶ ጥገና ግን አንድ ክስተት ተፈጠረ። ፍሌቸር ኮማ ውስጥ ነበረ። ነብሱ ክንፍ አውጥታ ከመላዕክት ጋር ወደ ሰማይ እየወጣች ሳለ መላእኩ ክንፉን አራግፎበት መለሰው።

ፍሌቸር እዛው ኮማ ውስጥ እያለ አይኑ የእሳት ነበልባል ፤ እግሩ የብረት ነሀስ የሆነ ሰው ይመጣና ፦ "እድል እሰጥሀለው ከዚህ በኋላ መልካም ስራ እየሰራህ ጠብቀኝ" ብሎት ተሰወረ ።

ሲነቃም ዶክተሮች እሱን ለማዳን እየተረባረቡ ነበር። በሆነው ነገር ተደንቆም የተገለጠልኝ ማን ነው? ምንድን ነው? ብሎ ከቀዶ ጥገናው በኋላ በሕይወቱ ፍለጋውንና ምርምሩን ማድረግና ቅዱስ መጽሐፍን ማንበብ ጀመረ። ኋላ ይህ የተገለጠለት ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን መረዳት ቻለ። ከዛም ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መጥቶ ክርስትናን ለመቀበል ይወስናል። መጥቶም መሠረተ እምነትን ተምሮ በትላንትናው እለት በአዲሱ ሚካኤል አምሀ ሥላሴ ተብሎ የሥላሴን ልጅነት ተቀብሏል።

     †          †          †
▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

✝✝✝ ወንጌል ዘቅዳሴ

🌺📖የማቴዎስ ወንጌል ፮ ፥ ፲፮ - ፳፭
፲፮ ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥
ዋጋቸውን ተቀብለዋል።
፲፯-፲፰ አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።
፲፱ ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤
፳ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤
፳፩ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።
፳፪ የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤
፳፫ ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!
፳፬ ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።
፳፭ ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?


✥✥✥ቅዳሴ፦ዘኤጲፋንዮስ (ዐቢይ)


🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

Watch "F/taa D/n Dani'eel Dasalanyi, Addumaa Addaadha,Faarfannaa Afaan Oromoo,Ortodoksii Tewahidoo" on YouTube
https://youtu.be/OGVkjL3p2kw

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

አሜን እንኳን አብሮ አደረሰን።

አሜን አሜን አሜን ።

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ፕሮፋይላችሁን ሁሉ በዚህ ቀይሩት። ጓደኞቻችሁን ሁሉ በዚህ ሊንክ አስገቡ። ሰብስቧቸው። እንቅልፍ አትተኙ። በየሰአቱ መረጃ ተከታተሉ። ሊንኩን ለኦርቶዶክሳውያን ሁሉ ላኩ።
/channel/+oQKWtq5vrzk1YWY0
/channel/onesinod

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

​​🕯አንድ ጊዜ በተራራው ላይ የሚገኙ አረጋውያን አበው ወደ ገዳመ አስቄጥስ ከአባ መቃርዮስ ዘንድ እንዲህ ብለው መልዕክት ላኩ፣ "እባክህን ወደ ጌታ ከመሄድህ በፊት እኛን ለማየት ውጣ፣ ያለበለዚያ ሁሉም ሰው ሲያዝን ይኖራል" አባ መቃርዮስም ተነሥቶ ወደ ተራራው ወጣ፡፡

🕯 እዚያ በደረሰ ጊዜ ሁሉም ተሰበሰቡና "አንድ ምክር ንገረን" አሉት፡፡"ወንድሞቼ ኑ፣ እናልቅስ፣ እንባዎቻችንም ከዐይኖቻችን አንደ ጎርፍ ይውረዱ፣ እንባዎቻችን የገዛ ሰውነታችንን ወደ ሚያቃጥሉበት ሥፍራ ከመሄዳችን በፊት" አላቸው፡፡ ሁሉም ወደ ምድር ተደፍተው አለቀሱ፣ ከዚያም "አባ ሆይ ጸልይልን" አሉት፡፡


🗯ቅዱሳን አባቶቻችን ለዕለተ ምጽአት እንዴት ራሳቸውን እንዳዘጋጁ ከሕይወታቸው እንመልከት❕

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

‼️ አዋጅ አዋጅ አዋጅ ‼️

•✥ ለ1 ሳምንት ግዴታ ሁሉም ኦርቶዶክስ ነኝ የሚል ካለ ከላይ የላክነው የቅዱስ አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቀነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፎቶ ፕሮፋይል ፒክቸር በማድረግ በአባታችን ላይ እየደረሰ ያለው ጫና እና ተቃውሞ በመንቀፍ ከአባታችን ጎን መሆናችንን ለአባታችን ያለንን ክብርና በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እየደረሰ ያለውን ጫና እንቃወም::

"በመልክታቸው ላትስማማ ትችላለህ...ክብረ ፕትርክናቸውን ማክበር ውዴታ ሳይሆን መንፈሳዊ ግዴታችን ነው!!!።"
ሁሉም  ኦርቶዶክስ profile picture በማድረግ ግዴታውን ይወጣ::

መልዕክቱን በማስተላለፍ የበኩሉዎን ይወጡ።  ለ20 የኦርቶዶክስ ቤተሰብ ፎርዋርድ / SHARE እናድርግ ‼️

•✥ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ቡራኬዎ ይድረሰን አሜን !

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ቢያንስ ለ 20 ኦርቶዶክሳውያን SHARE በማድረግ ለሁሉም እናዳርስ ‼️ በየግሩፑ በሁሉም ቦታ ያዳርሱት ‼️

━━━━━━━━━━━━━━━━━━

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ሰበር ዜና

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ከኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ አዋጅ

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረው አስቸኳይ ምልዐተ ጉባኤ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ እና የብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ በሚል በሕገ ወጥነት በቀድሞ ስማቸው አባ ሳዊሮስ የተባሉ ግለሰብ መሪነት ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ቀን ድረስ በተለያዩ ክልሎች እና የፌዴራል መንግሥት በሚመራቸው ቦታዎች ውስጥ በሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ አህጉረ ስብከት የሆኑትን ሥርዓተ አምልኮዋን የምትፈጽምባቸው በየመዋቅሩ የሚገኙ አስተዳደር ቢሮዎችን  ከሕግ አግባብ ውጭ የቤተ ክርስቲያኗ እምነት ተከታይ ያልሆኑ ግለሰቦችን በማካተት በመንግሥት ልዩ ኃይል ድጋፍ በመውረር እና በመስበር የሕግ አግባብነት በሌላቸው  እንዲሁም መብት እና ጥቅም ሳይኖራቸው በማሸግ ቤተ ክርስቲያን ላይ ወረራ እየተፈጸመባት የሚገኝ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ለመረዳት ችሏል፡፡

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

አሜን እንኳን አብሮ አደረሰን 🥰🥰🥰

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

🌸መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ🌸

🎙ኦዲዮ

@Hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

🌸ምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ አንድነት ገዳም🌸

💠High quality💠

@Hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

​​🌷​​ከዚህ በኋላ በብዙ ትሩፋት ፣ ጾምና ፣ ጸሎት በብዙ እንባ ኖረ። በእያንዳንዲቱ ቀንም አርባ አራት ፣ አርባ አራት ሺህ ጊዜ ይሰግድ ነበር። የዳዊትን መዝሙር፣ የነቢያትን ፣ የሰሎሞንን ምሥጋና ፣ ውዳሴ ማርያምን ይጸልይ ነበር። የጌታን መከራ መስቀል እያሰበ እልፍ ጊዜ ቀኝ ፊቱን እልፍ ጊዜ ግራ ፊቱን በድንጋይ ይመታ ነበር። እንዲህም ይል ነበር፣ በብዙ ድካም፣ በብዙ መከራ መንግሥተ ሰማያትን እንወርሳታለንና። (ሐዋ.14-22)🌷

🕯ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ ዘሠሉስ ምዕራፍ ፲

@Hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

Watch "#season: ምስባክ ዘመጻጉዕ" on YouTube
https://youtu.be/S4RjQ2N1JQ8

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

❀✞ተረክቦተ ርእሱ ለዮሐንስ መጥምቅ በንዋየ ልሕኵት ወተዝካረ ሚናስ ሊቀ ጳጳሳት። ✞❀

የካቲት ፴ #ግጻዌ
🌺❤🌺❤🌺❤🌺❤🌺❤🌺

✝ ዘነግህ ምስባክ

‹‹የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ። የማነ እግዚአብሔር አልዐለተኒ። የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኀይለ።››

‹‹ የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች። የእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደረገችኝ፤ የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች።››
🌺📖መዝሙር ፻፲፯ ፥ ፲፭

✝✝✝ ወንጌል ዘነግህ

🌺📖የማርቆስ ወንጌል ፩ ፥ ፬ - ፱
፬ ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኃጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ።
፭ የይሁዳም አገር ሁሉ የኢየሩሳሌምም ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፥ ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።
፮ ዮሐንስም የግመል ጠጉር ለብሶ በወገቡ ጠፍር ይታጠቅ አንበጣና የበረሀ ማርም ይበላ ነበር።
፯ ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል።
፰ እኔ በውኃ አጠመቅኋችሁ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል እያለ ይሰብክ ነበር።
፱ በዚያ ወራትም ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ ከዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ።

✝✝✝ የእለቱ ቅዳሴ ምንባባት

🌺📖፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ፬ ፥ ፯- ፍጻሜው
፯ ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤
፰ በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፤ እናመነታለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፤
፱ እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፤ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፤
፲ የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን።
፲፩ የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለንና።
፲፪ ስለዚህ ሞቱ በእኛ ሕይወቱም በእናንተ ይሠራል።
፲፫ ነገር ግን፦ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፤
፲፬ ጌታን ኢየሱስን ያስነሣው እኛን ደግሞ ከኢየሱስ ጋር እንዲያስነሣን ከእናንተም ጋር እንዲያቀርበን እናውቃለንና።
፲፭ በብዙዎች በኩል የተትረፈረፈው ጸጋ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋናን ያበዛ ዘንድ፥ ሁሉ ስለ እናንተ ነውና።
፲፮ ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል።
፲፯-፲፰ የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።

🌺📖፪ኛ የጴጥሮስ መልእክት ፩ ፥ ፲፱ - ፍጻሜው
፲፱ ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ።
፳ ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤
፳፩ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።

🌺📖የሐዋርያት ስራ ፲፫ ፥ ፳፬ - ፴፪
፳፬ ከመምጣቱ በፊት ዮሐንስ አስቀድሞ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የንስሐን ጥምቀት ሰብኮ ነበር።
፳፭ ዮሐንስም ሩጫውን ሲፈጽም ሳለ፦ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ታስባላችሁ? እኔስ እርሱን አይደለሁም፤ ነገር ግን እነሆ፥ የእግሩን ጫማ እፈታ ዘንድ ከማይገባኝ ከእኔ በኋላ ይመጣል ይል ነበር።
፳፮ እናንተ ወንድሞቻችን፥ የአብርሃም ዘር ልጆች ከእናንተ መካከልም እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፥ ለእናንተ የዚህ የመዳን ቃል ተላከ።
፳፯ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችና አለቆቻቸው እርሱንና በየሰንበቱ የሚነበቡትን የነቢያትን ድምፆች ስላላወቁ በፍርዳቸው ፈጽመዋልና፤
፳፱ ለሞትም የሚያደርስ ምክንያት አንድ ስንኳ ባያገኙበት፥ ይገድለው ዘንድ ጲላጦስን ለመኑት፤
፳፱ ስለ እርሱም የተጻፈውን ሁሉ በፈጸሙ ጊዜ ከእንጨት አውርደው በመቃብር አኖሩት።
፴ እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሣው፤
፴፩ በሕዝብም ዘንድ ምስክሮቹ ለሆኑት ከእርሱ ጋር ከገሊላ ወደ ኢየሩሳሌም ለወጡት ብዙ ቀን ታያቸው።
፴፪ እኛም ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን፤

✝ ምስባክ ዘቅዳሴ

‹‹ገሥፆሠ ገሠጸኒ እግዚአብሔር። ወለሞትሰ ባሕቱ ኢመጠወኒ እርኀው ሊተ አናቅጸ ጽድቅ።››

‹‹መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ፤ ለሞት ግን አልሰጠኝም።የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤ ››
🌺📖መዝሙር ፻፲፯ ፥ ፲፰

✝✝✝ ወንጌል ዘቅዳሴ

🌺📖የማርቆስ ወንጌል ፮ ፥ ፳፩ - ፴፬
፳፩ በደስታም ይሰማው ነበር። ሄሮድስም በተወለደበት ቀን ለመኳንንቱና ለሻለቆቹ ለገሊላም ሹማምንት ግብር ባደረገ ጊዜ ምቹ ቀን ሆነላትና
፳፪ የሄሮድያዳ ልጅ ገብታ ስትዘፍን ሄሮድስንና ከእርሱ ጋር የተቀመጡትን ደስ አሰኘቻቸው። ንጉሡም ብላቴናይቱን፦ የምትወጂውን ሁሉ ለምኚኝ እሰጥሽማለሁ አላት፤
፳፫ የመንግሥቴ እኩሌታ ስንኳ ቢሆን የምትለምኚውን ሁሉ እሰጥሻለሁ ብሎ ማለላት።
፳፬ ወጥታም ለእናትዋ፦ ምን ልለምነው? አለች። እርስዋም፦ የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ አለች።
፳፭ ወዲያውም ፈጥና ወደ ንጉሡ ገብታ፦ የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን ልትሰጠኝ እወዳለሁ ብላ ለመነችው።
፳፮ ንጉሡም እጅግ አዝኖ ስለ መሐላው ከእርሱም ጋር ስለ ተቀመጡት ሊነሣት አልወደደም።
፳፯ ወዲያውም ንጉሡ ባለ ወግ ልኮ ራሱን እንዲያመጣ አዘዘው። ሄዶም በወኅኒ ራሱን ቈረጠ፥
፳፰ ራሱንም በወጭት አምጥቶ ለብላቴናይቱ ሰጣት፥ ብላቴናይቱም ለእናትዋ ሰጠች።
፳፱ ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው መጡ በድኑንም ወስደው ቀበሩት።
፴ ሐዋርያትም ወደ ኢየሱስ ተሰብስበው ያደረጉትንና ያስተማሩትን ሁሉ ነገሩት።
፴፩ እናንት ራሳችሁ ብቻችሁን ወደ ምድረ በዳ ኑና ጥቂት ዕረፉ አላቸው፤ የሚመጡና የሚሄዱ ብዙዎች ነበሩና፥ ለመብላት እንኳ ጊዜ አጡ።
፴፪ በታንኳውም ብቻቸውን ወደ ምድረ በዳ ሄዱ።
፴፫ ሰዎችም ሲሄዱ አዩአቸው ብዙዎችም አወቁአቸውና ከከተሞች ሁሉ በእግር እየሮጡ ወዲያ ቀደሙአቸው ወደ እርሱም ተሰበሰቡ።
፴፬ ኢየሱስም ወጥቶ ብዙ ሕዝብ አየና እረኛ እንደሌላቸው በጎች ስለ ነበሩ አዘነላቸው፥ ብዙም ነገር ያስተምራቸው ጀመር።

✥✥✥ ቅዳሴ፦ዘወልደ ነጎድጓድ።(ኀቤከ)

ቅዳሴ ከመሄድዎ በፊት ግጻዌ ያጥኑ
በየቀኑ ግጻዌ እና ትምህርት ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን አሁኑኑ ይጫኑ🤗

👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/joinchat/pekr9kZlf1c0ZDQ0

🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ቀራንዮ መድኃኔዓለም አዲስ አበባ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኝ ደብር ነው ከአዲስ አበባ አድባራት ሁሉ ቀዳሚው ነው የተተከለው በ1826 ዓ.ም. በንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ዘመን ነው። በዚያን ጊዜ ፊንፊኔ በኢቲሳ ተክለ ሃይማኖት አለቃ በአባ ዘወልደ ማርያም ሥልጣን ሥር ነበረች። በአካባቢው ያልተጠመቁትን ማጥመቅና ክርስትናን ማስፋፋት ከንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ለአባ ዘወልደ ማርያም የተሰጠ ተልእኮ ነበረ። የዚህ ተልእኮ መጀመሪያ ያደረጉትም ቀራንዮ መድኃኔዓለምን መትከል ነበር።
ሲተከልም በኢቲሳ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ሥር ነበር፤
ደብሩን ይጠብቁት የነበሩት 300 ወታደሮች በአንድ ሌሊት በአካባቢው ጦረኞች ተገድለው አደሩ በዚህ ምክንያት የንጉሡ ታላቅ ልጅ ደጃዝማች መሸሻ ሠይፉ ታዝዘው አካባቢውን አሠሡት።

በ1901 ዐፄ ምኒልክ ደብሩ ከኢቲሳ ተክለ ሃይማኖት አስተዳደር ወጥቶ ራሱን እንዲችል በማድረግ ስሙን ቀራንዮ ብለው ሰየሙት። 15 ጋሻ መሬት ለደብሩ 2 ጋሻ መሬት ለአለቃው ተሰጥቶ ነበር።

ምንጭ፦ከበደ ተሰማ ፣ የታሪክ ማስታወሻ / 1962/ ገጽ 39 ፤ የኢትዮጵያ ብራና መጻሕፍት መጽሔት ፣ ቅጽ 1 ቁጥር 1 /1967/ ፤ Haile Gabriel Dagne, oral information on the
Establishment of churches in Addis ababa, International symposium on the centenary of Addis ababa(24 -25,Nov, 1986).IES library, page 275.



@karanyo
@karanyo
@karanyo

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

#ብሒለ_አበው

"ድኀነት እና የእግዚአብሔር ቁጣ"

' እንዴት ያለ ድንቅ አምላክ ነው ያለን፣ ታጋሽ እና ምህረቱ የበዛ፣ እስከመጨረሻው የማይቆጣ፣ ለዘላለሙ የማይቆጣ፣ በንስሐ ወደርሱ እንደተመለስን ቁጣውን የሚረሳ! ነገር ግን እንዲህ ያለውን መሐሪ እና ታጋሽ
አምላክ የቁጣውን በትር እንዲያነሳ ልናስገድደው እንችላለን፥ ምንም እንኳ ምህረቱ የማያልቅና ርህሩህ ቢሆንም።'

__ባሕታዊው ቴዎፋን

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

❀✞ ዐቢይ ጾም ፪ኛ እሑድ ቅድስት ✞❀

መዝሙር ዘቅድስት፦
ሃሌ ሉያ(፭) ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ፤ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ፤ ሀቡ ስብሐተ ለስሙ፡፡አክብሩ ሰንበተ ተገብሩ ጽድቀ፤ዝግቡ ለክሙ መዝገበ ዘበሰማያት፤ኀበ ፃፄ ኢያማስኖ ወኢይረክቦ ሠራቂ፤ድልዋኒክሙ ንበሩ ዘበላዕሉ ሐልዩ፤ኀበ ሀሎ ክርስቶስ፡፡

የየካቲት ፲፱ #ግጻዌ
🌺❤🌺❤🌺❤🌺❤🌺❤🌺

✝✝✝ የዕለቱ ቅዳሴ ምንባባት

🌺📖፩ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ፬ ፥ ፩ - ፲፫
፩ እንግዲህ በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ልትመላለሱ እግዚአብሔርንም ደስ ልታሰኙ እንዴት እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ እንደ ተቀበላችሁ፥ እናንተ ደግሞ እንደምትመላለሱ፥ ከፊት ይልቅ ትበዙ ዘንድ በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን እንመክራችሁማለን።
፪ በጌታ በኢየሱስ የትኛውን ትእዛዝ እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁና።
፫ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤
፬-፭ ከዝሙት እንድትርቁ፥ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፥ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን
ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ፤
፮ አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ
ወንድሙንም አያታልል።
፯ ለርኵሰት ሳይሆን እግዚአብሔር በቅድስና ጠርቶናልና።
፰ እንግዲህ የሚጥል ሰውን የጣለ አይደለም፥ መንፈስ ቅዱስን በእናንተ እንዲኖር የሰጠውን እግዚአብሔርን ነው እንጂ።
፱ እናንተ ራሳችሁ እርስ በርሳችሁ ልትዋደዱ በእግዚአብሔር ተምራችኋልና ስለ ወንድማማች መዋደድ ማንም ይጽፍላችሁ
ዘንድ አያስፈልጋችሁም፤
፲-፲፪ እንዲሁ በመቄዶንያ ሁሉ ላሉት ወንድሞች ሁሉ ታደርጋላችሁና። ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ከፊት ይልቅ ልትበዙ፥ በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን።
፲፫ ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን።

🌺📖፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት ፩ ፥ ፲፫ - ፳፭
፲፫ ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።
፲፬ እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።
፲፭-፲፮ ዳሩ ግን። እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።
፲፯ ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።
፲፰-፲፱ ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።
፳-፳፩ ዓለም ሳይፈጠር እንኳ አስቀድሞ ታወቀ፥ ነገር ግን እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ ከሙታን
ባስነሣው ክብርንም በሰጠው በእግዚአብሔር በእርሱ ስለምታምኑ ስለ እናንተ በዘመኑ መጨረሻ ተገለጠ።
፳፪ ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደደ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ
አጥብቃችሁ ተዋደዱ።
፳፫ ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው
እንጂ።
፳፬ ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤
፳፭ የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው።

🌺📖የሐዋርያት ሥራ ፲ ፥ ፲፯ - ፴
፲፯ ጴጥሮስም ስላየው ራእይ። ምን ይሆን? ብሎ በልቡ ሲያመነታ፥ እነሆ፥ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች ስለ ስምዖን ቤት ጠይቀው
ወደ ደጁ ቀረቡ፤
፲፰ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው። ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን በዚህ እንግድነት ተቀምጦአልን? ብለው ይጠይቁ ነበር።
፲፱ ጴጥሮስም ስለ ራእዩ ሲያወጣ ሲያወርድ ሳለ፥ መንፈስ። እነሆ፥ ሦስት ሰዎች ይፈልጉሃል፤
፳ ተነሥተህ ውረድ፥ እኔም ልኬአቸዋለሁና ሳትጠራጠር ከእነርሱ ጋር ሂድ አለው።
፳፩ ጴጥሮስም ወደ ሰዎቹ ወርዶ። እነሆ፥ የምትፈልጉኝ እኔ ነኝ፤ የመጣችሁበትስ ምክንያት ምንድር ነው? አላቸው።
፳፪ እነርሱም። ጻድቅ ሰው እግዚአብሔርንም የሚፈራ በአይሁድም ሕዝብ ሁሉ የተመሰከረለት የመቶ አለቃ ቆርኔሌዎስ ወደ ቤቱ ያስመጣህ ዘንድ ከአንተም ቃልን ይሰማ ዘንድ ከቅዱስ መልአክ ተረዳ አሉት።
፳፫ እርሱም ወደ ውስጥ ጠርቶ እንድግድነት ተቀበላቸው። በነገውም ተነሥቶ ከእነርሱ ጋር ወጣ፥ በኢዮጴም ከነበሩት ወንድሞች አንዳንዶቹ ከእርሱ ጋር አብረው ሄዱ።
፳፬ በነገውም ወደ ቂሣርያ ገቡ፤ ቆርኔሌዎስም ዘመዶቹንና የቅርብ
ወዳጆቹን በአንድነት ጠርቶ ይጠባበቃቸው ነበር።
፳፭ ጴጥሮስም በገባ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ተገናኝቶ ከእግሩ በታች ወደቀና ሰገደለት።
፳፮ ጴጥሮስ ግን። ተነሣ፤ እኔ ራሴ ደግሞ ሰው ነኝ ብሎ አስነሣው።
፳፯ ከእርሱም ጋር እየተነጋገረ ገባ፥ ብዙዎችም ተከማችተው አግኝቶ።
፳፰ አይሁዳዊ ሰው ከሌላ ወገን ጋር ይተባበር ወይም ይቃረብ ዘንድ እንዳልተፈቀደ እናንተ ታውቃላችሁ፤ ለእኔ ግን እግዚአብሔር
ማንንም ሰው ርኵስና የሚያስጸይፍ ነው እንዳልል አሳየኝ፤
፳፱ ስለዚህም ደግሞ ብትጠሩኝ ሳልከራከር መጣሁ። አሁንም በምን ምክንያት አስመጣችሁኝ? ብዬ እጠይቃችኋለሁ
አላቸው።
፴ ቆርኔሌዎስም እንዲህ አለው። በዚች ሰዓት የዛሬ አራት ቀን የዘጠኝ ሰዓት ጸሎት በቤቴ እጸልይ ነበር፤ እነሆም፥ የሚያንጸባርቅ ልብስ የለበሰ ሰው በፊቴ ቆመና።

✝ ምስባክ ዘቅዳሴ
«እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ። አሚን ወሠናይት ቅድሜሁ። ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ።»

«እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ። ምስጋናና ውበት በፊቱ፥ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።»
🌺📖መዝሙር ፺፮ ፥ ፭

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

አሜን አሜን አሜን
እንኳን አብሮ አደረሰን

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

የሕይወተ መነኮሳት ቤተሰቦች እንኳን ለታላቁ ጾመ ኢየሱስ(ዐቢይ ጾም) አደረሳችሁ። ስሙ የከበረ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይርዳን፥ ቸርነቱን ያብዛልን፥ አሜን።

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ምንም ተፈጠረ ምን እደው በማርያም ንስሀ ግቡ እባካቹ 🙏🙏🙏

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ስለ ድንግል ብሎ

ስለ ድንግል ብሎ ኢትዮጵያን ይጎብኛት
ድሮስ ከአምላክ በቀር ይቺ ሀገር ማን አላት
በሠራዊት ብዛት መች ትጠበቃለች
በቅዱሳን ጸሎት እሳት ካልታጠረች[፪]
~~~~~~~~~~~~~~
ዓለም ሸምቆባት ጠላት ይሳለቃል
በልጆቿ ዕንባ አውሬው ይቀልዳል
ታላቅ ሕዝብ መሆኑን ማን በነገራቸው
ከዘመናት በፊት አምላክ የጎበኘው[፪]
~~~~~~~~~~~~~~
እውነተኛው ዕንባ ፈለቀ ከምድር
በፍጡራን ዋይታ ፍጹም ብትማረክ
ዕንባ ና ደማችን ተደባልቆ ፈሷል
አምላክ ቅጣት ይብቃን አሁን ይቅር በለን[፪]
~~~~~~~~~~~~~~
ቅዱሳንን መንቀፍ ወገኔ ተውና
ይልቅ ስለነርሱ በጽድቅ ጎዳና
በረድኤታቸው በክብራቸው ጥላ
እንከተላቸው ከፍቅራቸው ኋላ[፪]
~~~~~~~~~~~~~~

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

መንግሥትም ሰላም እና ደህንነትን ከማስጠበቅ ባለፈ የሕይወት እና የአካል ደህንነት መብትን እንዲሁም የመንቀሳቀስ መብትን በመገደብ ያለአግባብ ታግተው መቆየታቸውን ከሊቃነ ጳጳሳት ውስጥ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን ከዚህ ቀደም መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ድርጊታቸውም ሳይታቀቡ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብጹዕ አቡነ ያሬድን በሕገ ወጥ መልኩ የዜግነት መብታቸው ተጥሶ በደረቅ ሌሊት በማሰር እና በማዋከብ ከሀገረ ስብከታቸው ለቀው እንዲወጡ የተደረጉ ሲሆን እንዲሁም የተለያዩ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትን ወደየ አህጉረ ስብከታቸው እንዳይሄዱ ማስፈራሪያ በመላክ የቤተ ክርስቲያችንን ክብር እና ልዕልና እጅጉን የሚጎዳ እና አሳዛኝ ድርጊት እየተፈጸመባት ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የየሀገረ ስብከት ሥራ አኪያጆችንና ሠራተኞችን፤ አገልጋይ ካህናትንና ምእመናን በሕገ ወጥ መልኩ በማሰር እንደ መንግሥት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ባለመወጣቱ ቤተ ክርስቲያናችን እጅጉን አዝናለች፡፡

ከዚህም አልፎ መንግሥትም በቤተ ክርስቲያችን በኩል በተደጋጋሚ የተሰጠውን ማሳሰቢያ ችላ በማለቱ ምክንያት በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ ሕገ ወጦቹ መንግሥትን ተገን በማድረግ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ወጥ መልኩ ወረራ ለመፈጸም ባደረጉት እንቅስቃሴ ቤተ ክርስቲያንችንን ለመጠበቅ በወጡ ምእመናን ላይ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የአደባባይ የግድያ ወንጀል ተፈጽሟል፡፡ ሌሎች በቁጥር ያልታወቁ ምእመናንም ላይ ከፍተኛ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 

ይህንንም ሕገ ወጥ ተግባር በተመለከተ ተገቢውን ሕጋዊ የሰላም እና የደህንነት ከለላ እንዲያደርጉ ለሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት በተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ቤተ ክርስቲያናችን ብትሰጥም ይህንን ማሳሰቢያ ወደጎን በመተው መንግሥት ሕገ ወጡን ቡድን በመደገፍ እና በማስፈጸም ከላይ የተገለጹትን አሳዛኝ ድርጊቶች በይፋ በአደባባይ ፈጽሟል፡፡

ስለሆነም የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጠራው አስቸኳይ ጉባዔ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡

1. በብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት እና የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፤ የክፍል ኃላፊዎች፤ ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ላይ የተፈጸመውንና እና እየተፈጸመ ያለውን ሕገ ወጥ እስር እና ወከባ ቅዱስ ሲኖዶስ በፅኑ አውግዟል፤
2. በጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፤ ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የወጡት ምዕመናን ላይ ጭካኔ በተሞላ ሁኔታ የተፈጸመው ሕገ ወጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የተፈጸመው አሰቃቂ የሞት ድርጊትን ፍጹም ታወግዛለች፤ ተገቢውን ሲኖዶሳዊ እና ሃይማኖታዊ ጸሎት በማድረግ በሁሉም አጥቢያ ሥርዓተ ፍትሐት እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3. ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ባስተላለፈው ውሳኔ እና በሰጠው መግለጫ መላው የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮች ጾመ ነነዌን ሙሉ የሱባዔ ጊዜ በማድረግ ጥቁር ልብስ ያለውን ትርጓሜ በመግለጥ እንድንሰነብት መግለጫ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
3.1. ለዚህም ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 3 ቀናት በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የምትገኙ ማናቸውም ካህናት እና ምዕመናን ሙሉ ጥቁር ልብስ በመልበስ በየአብያተ ክርስቲያናት እና በገዳማት ያለውን ሥርዓተ ጸሎት እንድትመሩ እና እንድትከታተሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.2. በየትኛውም እንቅስቃሴ ይህንን ጥቁር ልብስ በመልበስ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ንቁ በመሆን እንድትፈጽሙ፤ ሆኖም ግን ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ዓለም አቀፍ የጸሎትና የምህላ መርሐ ግብር ካወጀበት ቀን በኃላ በተለያዩ ከተሞች የጥቁር ልብስን ሆነ ተብሎ ከገበያ እንዲወጣ እየተደረገ መሆኑን በመረዳታችን ምዕመናን ያላችሁን ተመሳሳይ አልባሳት በመጠቀም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን በእንቅስቃሴያችሁ ሁሉ እንድትፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.3. በነዚህ ቀናት ውስጥ አገልግሎቱ በድምጽ ማጉያ እንዲከናወን እና የሙሉ ጊዜ ሆኖ በሰባቱ የጸሎት ሰዓታት እየተጠበቀ በተመሳሳይ ሰዓታት ለአምስት ደቂቃ ያህል በማያቋርጥ ደወል በመደወል የማስተጋባት ሥራ እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.4. ይህንንም የየአህጉረ ስብከት፤ የወረዳ ቤተ ክህነት እና የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤያት በመከታተል እንድታስፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
3.5. የአኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የኦርቶዶክስ ዓለም፤ እውነቱን የምታውቁና የምትደግፉ ማናቸውም ኃይማኖታዊም ሆነ ማህበራዊ ተቋማት እና ግለሰቦች የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመደገፍ በአንድነት ትቆሙ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላፋለን፡፡
4. በነዚህ የጸሎትና የምሕላ ጊዜያት የደነደኑ ልቦች ወደ ልቦናቸው ተመልሰው የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥሪ ሰምተው የማይፈጽሙ እንደሆነ
4.1. በየካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ከጠዋቱ 11፡00 ጀምሮ በየአጥብያቸው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጠዋቱ 1፡30 ድረስ ሥርዓተ ቅዳሴው ከተፈጸመ በኃላ ከጠዋቱ 2፡00 ላይ ሁሉም ገዳማት፣ አድባራት እና አብያተ ክርስቲያናት በተመሳሳይ ሰዓት ደወል በመደወል ምእመናን በሙሉ እስከ ጠዋቱ 2፡30 ድረስ እንዲሰባሰቡ በማድረግ ከየአጥቢያው በመነሳት የጥምቀተ ባህር ወይም የመስቀል አደባባይ ላይ ታቦተ ሕጉን በማክበር፤ በማጀብ በዝማሬ እና በእልልታ በአንድ ቦታ በመሰባሰብ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
4.2. የዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምናሳውቃችሁ መሆኑን አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡ 
5. ማንኛውም የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ቤተ ክርስቲያን ያዘዘችውን ሰላማዊ ጥያቄ በሚከወንበት ማንኛውም የአገልግሎት ጊዜ ተግባራቱ ሰላማዊ መሆናቸውን በመገንዘብ ተገቢውን ጥበቃ የማድረግ ግዴታ እንዳለበት አውቆ እንዲያስፈጽም ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፤

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

Endemin walachihu Selam nachihu woy
Eeee kalaschegerkuachihu መፅሐፈ ምዕዳ simun kaltesasatku ye aba gebrekidan metshafu nw be PDF yalew sew yinoral ebakachihu

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

የቀጠለ....

የአባ እንጦንስ ዝና ተሰራጭቶ ንጉሠ ነገስት ቆስጠንጢኖስ ጋር ደረሰ፡፡ ንጉሱ አባ እንጦንስን የሚያወድስ እና የጸሎት ጥያቄን የያዘ ጽሁፍ ላከለት፡፡ በንጉሠ ነገስቱ ደብዳቤ ወንድሞች ተደሰቱ ቅዱስ እንጦስ ግን ትኩረት አልሰጠውም፤ እንዲህም አላቸው:- "የእግዚአብሔር መጽሐፍ ፣ የነገስታት ንጉስ እና የጌቶች ጌታ ዘውትር ያዙናል፤ ለሚሉን ነገር ግን ትኩረት አንሰጥም፣ ጀርባችንንም እናዞርባቸዋለን፡፡"
የነገሩት ወንድሞች ደጅ በመጽናታቸው "ንጉሠ ነገስቱ እኮ ቤተክርስቲያንን ይወዳል" ብለውት ደብዳቤውን መልሶ ለንጉሱ ለመጻፍ ተስማማ፤ ለቤተክርስቲያን እና ለግዛቱ ሰላም እና ደኸንነት ጸሎት እና ቡራኬ የያዘ ጽሁፍ መለሰለት፡፡

ቅዱስ እንጦንስ ቤተክርስቲያን ላይ የሚደርሰውን መከራ እና መናፍቃን ለአጭር ጊዜ እንደሚቆጣጠሩት፣ ቤተክርስቲያን ድል ነስታ ወደ ቀደመው ክብሯ እንደምትመለስ እና የዘመኑን ፍጻሜ ተንብዮአል፡፡ ቅዱስ መቃርዮስ ታላቁ አባ እንጦንስን ሲጎበኘው አባ እንጦንስ የመነኮሳትን ልብስ አለበሰው፣ በርሱም ላይ ስለሚሆነው ነገር ተነበየ(የምንኩስና መስፋፋትን፣ የልጆቹ መብዛትን)፡፡

የአባ ጳውሊ ርዕሰ ባሕታውያን ዕረፍት ሲደርስ ቅዱስ እንጦንስ ወደርሱ ሄደ፡፡ ከቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ፣ የእስክንድርያ(ግብጽ) ፳ ኛው ፓትርያርክ በተሰጠ የስጦታ ልብስ ገንዞ ቀበረው፡፡ ቅዱስ እንጦንስ ዕለተ እረፍቱ መድረሱን በተረዳ ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ...ስጋውን እንዲሰውሩ፣ መቋሚያውን ለቅዱስ መቃርዮስ እንዲሰጡ እና አንዱን የበግ ቆዳ ልብስ ለአባ አትናቴዎስ፣ አንዱን ለአባ ሰራፕዮን ለደቀመዝሙሩ እንዲሰጡ አዘዛቸው፡፡ ራሱን በምድር ላይ አሳርፎ ነፍሱን ሰጠ፡፡ መላዕክት እና ቅዱሳን ነፍሱን ተቀብለው ወደ ዘላለም እረፍት አስገቡት፡፡ ይህ ቅዱስ በቅድስና እና ንጽህና ሕይወት ለ፻፭ ዓመት ኖረ፡፡

ጸሎቱ ከኛ ጋር ትሁን፤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን፡፡ ለዘላለሙ አሜን፡፡

@hiwotemenekosat

Читать полностью…
Subscribe to a channel