አባ ቢሾይ በኢየሩሳሌም በጌታችን መካነ መቃብር
በመስከረም 1965(እኤአ) አባ ቢሾይ ብቸኛውን መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም አደረገ።
"...ቤተክርስቲያኑን ባዶ አገኘሁ ስለዚህ ለብዙ ሰዓት በውስጡ ቆየሁ። ግድየለሽነቴን፣ ስንፍናዬን እና ራሴን ከክርስቶስ ጋር መስቀልና መሞት አለመቻሌን ማሸነፍ እንድችል በጽኑ ጸለይኩ። ከዚያን በዚያ ተቀብሮ የነበረው በእስክንድርያ ያሉትን አገልጋዮቹን እንዲያስታውስ ጠየኩት። ስለኔ የተሰቀለውን እና የተገረፈውን አምላክ ይቅርታ ለመንኩ፤ ከክርስቶስ ሕይወት ወደእኔ ሕይወት የሚፈስ ወንዝን አገኘሁ።"
በታላቁ አባ እንጦንስ ገዳም መነኩሴ የሆነ ሰው በዚያ ነበርና አባ ቢሾይ ስዕላቱን ሲሳለም ይመለከት ነበር።ይህ የአይን ምስክር ከካህኑ ከአባ ቢሾይ ሰውነት ብርሃን ሲወጣ ይመለከት ነበር። አባ ቢሾይ በስቀለቱ ስፍራ በቆመባቸው ሰዓታት ውስጥ ብርሃን ከሰውነቱ ይወጣ ነበር።
@hiwotemenekosat
የአባ ሚካሂል ኢብራሂም(ሚካኤል አብርሃም) እረፍት መታሰቢያ(ሚያዚያ 12/ 1891 - መጋቢት 17/ 1967)
{April 20, 1899- March 26, 1975}
በመጋቢት 17 የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን በካይሮ ሹብራ የቅዱስ ማርቆስ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ካህን የነበሩ የአባ ሚካኤልን ዓመታዊ መታሰቢያ ታደርጋለች።
የጸሎት ሕይወት
አባ ሚካኤል በ1951(እኤአ) ክህነትን ተቀብለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እና ልጆቹን በታማኝነት አገልግለዋል።(በግብጽ አውራጃዎችና በካይሮ ጭምር)
እጅግ የበዙ ችግሮች ይደርሷቸው ነበር፥ በጥልቅ እና ጽኑ ጸሎትም ሁሉንም ይፈቷቸው ነበር፣ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ባለው ቃል መሠረት። “በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል።” — 1ኛ ዮሐንስ 5፥14
አባ ሚካኤል ከቤተመቅደስ ከመውጣታቸው በፊት ለቅዱሳን ኃላፊነት ሲሰጡ ብዙዎች ያዩ ነበር። ለቅድስት ድንግል እንዲህ ይሏታል "እባክሽ ይህን ጉዳይ አንቺ ተመልከችው" ለቅዱስ ማርቆስ "አንተ ይህን ጉዳይ ያዘው" ለቅዱስ ጊዮርጊስ "እባክህ ይህን ችግር ፍታ" ይሉ ነበር። ወደቤታቸው ሲሄዱ ሁሉም ነገር መፍትሔ እንደተገኘለት በማመን ነበር። የደብሩ ምዕመናንም እንዲጸልዩላቸው ይጠይቋቸው ነበር፣ አንዱ ሰው መጥቶ የሆነ ችግር ሲናገር "እንጸልይ!" ይሉታል። ምክር በመስጠት እምብዛም ነበሩ፥ በጸሎት ታላቅ ኃይል ያምኑ ነበርና። "እስቲ እንጸልይ፥ እግዚአብሔር መፍትሔ ይሰጠናል" ይሉ ነበር።
መንፈሳዊ ዓምድ እና መሪ
አባ ሚካኤል የብጹዕነታቸው የአቡነ ሺኖዳ ሣልሳይ እና የቀድሞው አባ ፒሾይ ካሚል(እኤአ 1931-1979) እንዲሁም የሌሎች ቅዱሳን አባቶች ነፍስ አባት ነበሩ። በእግዚአብሔር መንፈስ ተሞልተው(ኤፌ 5:18) ብዙዎችን በመንፈሳዊ ሕይወት በእውነት እና በየዋህነት መሩ። የወደቁትን እና የተሰነካከሉትን በመንፈሳዊነት እያበረቱ አነሷቸው።
አባ ሚካኤል ዘውትር ሲናዝዙ የልጆቻቸው ሸክም እና ኃጢአቶቻቸው ይሰማቸው ነበር። ምንም አይነት ቀኖና ቢሰጧቸው፥ ራሳቸው ያንን ቀኖና ይፈጽሙ ነበር። አንድ ሰው የከበዱ እና ለዘመናት ያስጨነቁትን ኃጢአቶቹን እየተናዘዘ ወደሳቸው መጣ፥ በርህራሄ እና በጋለ ስሜት አቅፈውት እንዲህ አሉት "ውዱ ልጄ ንስሐህን ከምትፈጽምባቸው እና ከምትጠብቅባቸው መንገዶች አንዱ 30 ስግደት መስገድ ነው። ነገር ግን የጤንነትህ ሁኔታ ስለማይፈቅድልህ ልጄ እኔ ስላንተ ፈንታ እንዳደርገው ፍቀድልኝ።"
የቤተሰብ ችግሮችን መፍታት
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ አቡነ ሚካኤልን በቤተሰብ ጉዳዮች ካውንስል እንዲመክሩ ተደራቢ አግልግሎት ሰጥተዋቸው ነበር። ከዕለታት በአንዱ ቀን አቡነ ሚካኤል የካውንስሉ ተጠሪ ጳጳስ እና ሌሎች ካህናት ባሉበት ጥንድ ባልና ሚስት ጥል ጉዳይ ሊመክሩ ተገኙ። በዚያ ካሉት ውስጥ ለችግሩ አንዳች መፍትሔ ሊያገኝ የቻለ አልነበረም። ጳጳሱም "አባ ሚካኤል እርሶ ያሰቡትን ለምን አይነግሩንም?" አሏቸው፥ አባ ሚካኤል ዝም ብለው ነበርና። አባ ሚካኤልም መልሰው፦" ብጹዕነትዎ እንጸልይ" አሏቸው። ጳጳሱም መልሰው "ከዚህ ጉባኤ አስቀድመን እኮ ጸልየናል" አባ ሚካኤልም ሲመልሱ"ለዚህ ችግር ግን አልጸለይንም" አሏቸው።በዚያ ያሉት ሁሉም እና የተጣሉት ጥንዶች ለመጸለይ ቆሙ፥ ጳጳሱም አቡነ ሚካኤልን እንዲጸልዩ ጠየቋቸው። ጸሎቱ ከተፈጸመ በኃላ የሰላም መንፈስ(ፊሊ 4:7) ጥንዶቹን ሞላ፥ በሁሉም ፊት ተቃቀፉ ክሳቸውንም ጣሉት። በዚያ ከነበሩት ካህናት አንዱ ለአባ ሚካኤል በጨዋታ እንዲህ አሉ፦"አባ ሚካኤል አስቀድመው ይህን መፍትሔ ጠቁመውን ቢሆን ኖሮ ቀድመው በገላገሉን ነበር"
ለድሆች ታላቅ ፍቅር
አባ ሚካኤል አብዝተው ለድሆች ያስቡ ነበር፥ አገልጋዮችን እንዲህ ይሉ ነበር "በጎ ሁኑላቸው፣ መከራን ጠግበዋልና(ያዩት ችግር ይበቃቸዋልና)"። ዘውትር ለድሆች ሲሰጡ በደስታ እና በደግነት ነበር፥
“እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና...”— 2ኛ ቆሮ 9፥7 የሚለውን የሐዋርያውን ቃል በማሰብ። ከዕለታት በአንዱ ቀን የ200 ድሆች ስም ዝርዝር ይዘው ስጋ እያከፋፈሉ ሳለ አንዲት ሙስሊም ሴት አባ ሚካኤልን ወደሚራዱት አገልጋዮች ክርስቲያን መስላ ቀረበች። አገልጋዮቹ ስለዋሸች ከለከሏት ከዚያን ሄዳ ለአባ ሚካኤል ነገረች። እጇን ይዘው ወደ አገልጋዮቹ አቀረቧት፥ እንዲረዷትም ጠየቋቸው። ያደረገችውን ለአባ ሚካኤል ቢነግሩም እሳቸው ግን "ማንም ቢለምናችሁ፥ አትመልሷቸው" ብለው ነገሯቸው።
ስድብን መቀበል
በአንዱ ቀን አባ ሚካኤል በሹብራ ውስጥ ባለች ትንሽዬ መንድር ከአባ ማርቆስ ዳውድ(እኤአ 1897-1986) ጋር በእግር እየተጓዙ ሳለ ልጆች ከበዋቸው መሳደብ ጀመሩ። አባ ማርቆስ በልጆቹ ስርዓት የለሽነት እጅግ አዘኑ፥ አባ ሚካኤል ግን ፈገግ እያሉ ለአባ ማርቆስ እንዲህ አሏቸው "ተዋቸው በአጋጣሚው ይደሰቱ፥ እኛ በአይሁድ ከተሰደበው ጌታችን የተሻልን አይደለንም"
የሕይወታቸው ሀዘኖች
አባ ሚካኤል የሀዘን ሰው ነበሩ። ሁለት ወንድ ልጆቻቸውን(ፊልሞን እና ጳውሎስ) ገና ሕፃን ሳሉ አጡ። ታላቁን ልጃቸውን አብርሃምን ገና ወጣት ዶክተር ሆኖ ሳለ አጡት፥ ይህ ብዙ ሳይቆይ ባለቤታቸው ማርያም አረፈች። ሊያጽናኑአቸው ለሚመጡ ሰዎች "ለኔ የሚጸልዩ ሶስት ልጆች እና እናታቸው ስላለኝ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለው" እያሉ ያጽናኗቸው ነበር። እጅግ ታላቅ ሰው ብቻ ነው በመከራ ፊት እንዲህ ያሉ ቃላትን የሚናገረው። የትዳር አጋራቸውን ማጣታቸው ካለባቸው ኃላፊነት አንፃር ቀላል አልነበረም። ቀናቸውን እና ምሽታቸውን እስከ ቀጣዩ ቀን ጠዋት በቤተክርስቲያን በአገልግሎት ካሳለፉ በኃላ የልጆቻቸውን ንስሐ ደግሞ በቤተክርስቲያን አቅራቢያ ባለው ቤታቸው ይሰሙ ነበር።
ከዚህ ዓለም መለየት
አባ ሚካኤል መጋቢት 17/1967 ዓም(እኤአ 26 March 1975) ከዚህ ዓለም ተለዩ። ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐታቸውን መሩ፥ ቅዱሰነታቸውም እንዲህ አሉ:- "አባ ሚካኤል ሰማያዊ ሰው ነበሩ፥ ሰማይ በመሃላችን እንዲኖሩ፥ ለሰው ልጅ ብሩህ መልክ እና ሕይወት ያለው መንፈሳዊ ሕይወትን እንዲያስተምሩ፥ አርዓያ እንዲሆኑ ላከቻቸው"። አቡነ ሺኖዳ አባ ሚካኤል በካቴድራሉ እንዲቀበሩ አስደረጉ፥ የሚመጣው ትውልድም በረከታቸውን እንዲቀበል ስለክብራቸው የጸሎት ስፍራ በስማቸው አሰሩ። ከሁለት ዓመት በኃላ አቡነ ሺኖዳ "አባ ሚካኤል አብርሃም፤ የእረኝነት ተምሳሌት" የሚል መጽሐፍ አሳተሙ። ለአባ ሚካኤል ካላቸው ጥልቅ ፍቅርና ክብር የተነሳ ሚካኤል አብርሃም በሚል ስም ካህናትን ይሾሙ ነበር።
ጸሎታቸው ከኛ ጋር ትሁን፥ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን፥ ለዘላለሙ አሜን።
©Coptic websites
@hiwotemenekosat
እባካችሁ ጓዴ ጠፍቶኝ ነው ይህን ተፅፎ አገኘውት ⨳ታላቅ አምባ የተተከለች መንደር ናት እባካችሁ ባታውን የምታውቀው⨳ ባታውን የምታውቀው አናግሩኝ እባካችሁ 🙏🙏🙏🙏
Читать полностью…፲ ወኢትጽአል
አትሳደብ ።
ቧልተኛ አትሁን
(፩ም) ዋዛ ፈዛዛ አትናገር
ፈጽመህ/በፍጹም/ አትሳደብ
ፈጽመህ/በፍጽም/ አትማል
ነገርህ እውነቱን እውነት ሐሰቱን ሐሰት /ያለውን አለ የለለውን የለም/ ይሁን እንጅ።
፲፩ ወሶበ ያጌብሩከ በል አእምር እስመ ጽድቅ እብለከ ወኡይሔሱ።
ግድ ማል ቢሉህም እውነት እንድናገር ሐሰት እንዳልናገር እወቅ በለው እንጅ ይህም አትማል ላለው ነው።
የፈጣሪህን ስም በመሐላ አትጥራ
በሌላ መሐላ አትማል ማለት በኢየሩሳሌም በራሳቹህም እንዲሁም በሌላም።
ቅዱስ ወንጌል እንደተናገረ ይህ ሁሉ ክሕደት ነውና ሊሠሩትም አይገባምና እግዚአብሔርንም ሰውንም ደስ አያሰኝምና።
አባ ገብረኪዳን ስለ ክርስቶስ ካስተማሩት ውስጥ 1 ሰዓቱ አይደለም አንዱ ደቂቃ ክርስቶስን ያሳየናል! ❤️
በረከታቸው ይደርብን እግዚአብሔር ያበርታቸው በእውነቱ 🙏
🀄️ጥንት ስቅለት መጋቢት 27
👉የዓለም መድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በነሣው ሥጋ በቀራንዮ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሕይወቱን ለዓለም ቤዛ፣ አድርጎ የሰጠው መጋቢት ፳፯ ቀን ፴፫ ዓ.ም እንደሆነ ይታወቃል፡፡
📜ይህ ቀን ስለክርስቶስ ሕማም፣ ስለመከራ መስቀሉና ስለሞቱ የተነገሩት ትንቢቶችና ምሳሌዎች ሁሉ የተፈጸሙበት፤ ሰማያዊ አምላክ ስለሰው ልጆች ፍቅር ሲል ልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራዎችን የተቀበለበትና በሞቱ ሞትን ሽሮ የአዳምን ዘር ሁሉ ከሞት ሞት ያዳነበት፣ ለዓለሙ ሁሉ ፍቅሩን የገለጠበት፣ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙም ዓለምን ነፃ ያወጣበት፣ በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀል በትዕግሥት ተቀብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በገዛ ፈቃዱ የለየበት የስቅለቱና የሞቱ መታሰቢያ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ ጥንተ ስቅለት ተብሎ ይጠራል፡፡
በዓሉም በዓለ መድኃኔዓለም እየተባለ በየዓመቱ በመድኃኔዓለም ስም በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ታቦተ ሕጉ እየወጣና ዑደትም እየተደረገ በታላቅ ክብር ሲከበር የኖረ ታላቅ መንፈሳዊ በዓል ነው፡፡
👉መድኃኔዓለም ማለት ምን ማለት ነው❓ ክርስቶስ፣ ማለት መሲህ፤ ኢየሱስ ማለት መድኃኒት፣ አማኑኤል ማለትም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ተብሎ እንደሚተረጎም ሁሉ መድኃኔዓለም ማለትም👉 ዓለምን ሁሉ የሚያድን የዓለም መድኃኒት ማለት እንደሆነ ከቅዱሳት መጻሕፍት እንማራለን፡፡
👉ዓለም የዳነውም ከላይ እንደተገለጠው በመስቀሉ ላይ በአፈሰሰው ደሙና በሞቱ አማካይነት በተገኘው ጸጋ ነውና የጥንተ ስቅለቱና 👉የመስቀሉም ምሥጢር ዓለምን የማዳን ምስጢር ስለሆነ የጥንተ ስቅለቱ የመታሰቢያ በዓል በሚከበርበት በመጋቢት ፳፯ ቀን ምእመናን ሁሉ በቤተክርስቲያን በመገኘት በእሱ ደም ዓለም የዳነ መሆኑን በሚገልጠው መድኃኔዓለም በተሰኘው ስሙ እየተማጸኑና ዓለምን ለማዳን የተቀበለውን መከራ መስቀል እያስታወሱ በዓሉን በድምቀት ያከብሩታል፡፡🙏
ወደ 8 የሚሆኑ መቃርስ የተባሉ ቅዱሳን አሉ። ዋናዎቹ
1- ቅዱስ መቃሪ (ታላቁ መቃርስ)
2- መቃርስ ዘእስክንድርያ (ከታላቁ መቃርስ ጋር መጋ 13 ስደቱ የሚታሰበው)
3- መቃርስ ገዳማዊ (ቆቅ የሚበላው) ታኅ 13
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
አመ ፳፯ዑ ለመጋቢት መድሀኒአለም ስርአት ማህሌት
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ በመስቀሉ አተበነ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ በመስቀሉ ቤዘወነ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ በመስቀሉ ኮነ ሕይወትነ።
ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
ዚቅ
መድኃኔዓለም ወልድኪ ሥጋ ዚአኪ ዘለብሰ፤ ሐፃውንተ መስቀል ተአገሰ፤ በዓውደ ጲላጦስ ተወቅሰ አማዑትኪ ተካወሰ።
መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢረከቡ ተፍጻሚተ፤ መላእክተ ሰማይ ወምድር እለ ለመዱ ስብሐተ፤ መድኃኔዓለም ተወከፍ እንተ አቅረብኩ ንስቲተ፤ ዘሰተይከ በእንቲአነ ከርቤ ወሐሞተ፤ በሞተ ዚአከ ከመ ትቅትል ሞተ።
ዚቅ
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ፤ ወአስተዩኒ ብሂዓ ለጽምዕየ፤ ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ።
ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ወአቅደምከ ጸግዎ መንፈሰከ ቅዱሰ ለሥርየተ ኃጢዓት፤ አክሊል ዘሦክ አስተቀጸሉከ ዘበሰማያት ለነ አክሊለ ጽድቅ አስተዳሎከ፤ ሰቀሉከ ዲበ ዕፅ፤ ብሂዓ ዘምስለ ሐሞት አስተዩከ፤ ከመ ለነ ታስትየነ ወይነ ትፍሥሕት ወሐሤት፤ ረገዙከ በኲናት ወተርኅወ ገቦከ፤ ከመ ለነ ተሀበነ ሥጋከ ቅዱሰ ወደምከ ክቡረ፤ ከመ ትጸግወነ።
ወረብ
ወአቅደምከ 'ጸግዎ'/፪/ መንፈሰከ/፪/
አክሊለ ጽድቅ አስተዳሎከ በሰማያት አክሊለ ጽድቅ/፪/
መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለጒርዔከ ክቡር ወልዑል፤ ወለክሣድከ ዓዲ ዘሰሐብዎ በሐብል፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቀራንዮ ስቁል፤ በለኒ መሐርኩከ በእንተ ማርያም ድንግል፤ እስመ ኄር አልቦ እንበሌከ ቃል።
ወረብ
'በለኒ መሐርኩከ'/፪/ በእንተ ማርያም ድንግል/፪/
እስም ኄር አልቦ እንበሌከ ዘይሜሕር ቃል መድኃኔዓለም/፪/
ዚቅ
በእንተ ማርያም ወላዲትከ፤ ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ፤ ወበእንተ ኲሎሙ ቅዱሳኒከ፤ ርድአነ ወትረ በኃይለ መስቀልከ፤ ኢታስተኃፍረነ እግዚኦ በቅድሜከ።
ወረብ
በእንተ ማርያም ወላዲትከ ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ/፪/
ርድአነ ወትረ በኃይለ መስቀልከ/፪/
ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
በአማን ቃልከ አዳም፤ ዘተሰቀልከ በእንተ ኃጥዓን ከመ ትቤዙ ነፍሰ ጻድቃን፤ በአማን ቃልከ አዳም፤ በአማን ቃልከ አዳም።
መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለልብከ እግዚአብሔር ናዝራዊ፤ ነቢይ ወመንፈሳዊ፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ህፃን ወአረጋዊ፤ እፎ ቀሰፉከ ካህናተ ይሁዳ ወሌዊ፤ በዓውደ ጲላጦስ መስፍን ከመ ገብር ዓላዊ።
ዚቅ
ወጸሐፈ ጲላጦስ መጽሐፈ፤ ወይብል መጽሐፉ ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ።
ወረብ
ወጸሐፈ መጽሐፈ ጲላጦስ ወይብል መጽሐፉ ጲላጦስ ዘጸሐፈ/፪/
ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ/፪/
መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለጸዓተ ነፍስከ አመ ዲበ መስቀል ቆመ፤ ወለበድነ ሥጋከ ምዑዝ እንተ ያጥዒ ሕሙመ፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከመ ትቤዙ ዓለመ፤ አሜሃ እግዚእየ ፀሐይ ጸልመ፤ ወወርኅኒ ተመሰለ ደመ።
ዚቅ
ምድር አድለቅለቀት ወሰማይ ተሀውከ ሶበ ትወጽእ መንፈሱ ለኢየሱስ።
ወረብ
ምድር አድለቅለቀት ወሰማይ ተሐውከ/፪/
ሶበ ትወጽእ መንፈሱ ለኢየሱስ/፪/
ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ሶበ ሰቀልዎ ሶበ ሰቀልዎ፤ ሶበ ሰቀልዎ ለእግዚእነ ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ፤ ዬ ዬ ዬ፤ አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት።
መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለግንዘተ ሥጋከ ዘመዓዛሁ ጽጌረዳ፤ ወለመቃብሪከ ዘኮነ ለኢየሩሳሌም በዓውዳ፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቅንዓተ ሰይጣን ዘይሁዳ፤ ሞተ ወተቀብረ በመቃብረ ሐዲስ እንግዳ፤ ኀበ ኢተቀብሩ ለሔዋን ውሉዳ።
ዚቅ
አውረድዎ እምዕፅ ዕደው ጻድቃን፤ ወአምጽኡ አፈዋተ ከርቤ ሕውስ ወልብሰ ገርዜን ንጹሕ ለግንዘተ ሥጋሁ።
ወረብ
'አውረድዎ'/፫/ እምዕፅ/፬/
ወአምጽኡ አፈዋተ ከርቤ ሕውስ/፪/
ምልጣን፦
መርሕ በፍኖት ሞገሶሙ ለጻድቃን፤ ዝንቱ ውእቱ መስቀል፤ ለአዳም ዘአግብዖ ውስተ ገነት፤ ወለፈያታዊ ኃረዮ በቅጽበት፤ መድኃኒት ዕፀ ሕይወት፤ ዝንቱ ውእቱ መስቀል።
አመላለስ፦
መድኃኒት ዕፀ ሕይወት፤
ዝንቱ ውእቱ መስቀል
ወረብ፦
ሃሌሉያ መርሕ በፍኖት ሞገሶሙ ለጻድቃን ሞገሶሙ/፪
ዝንቱ ውእቱ መስቀል ለአዳም ዘአግብዖ ውስተ ገነት/፪
እስመ ለዓለም
ብከ ንወግዖሙ ለኲሎሙ ፀርነ ይቤ ዳዊት በመንፈሰ ትንቢት፤ በእንተ ዕፀ መስቀል ዘተሰቅለ ዲቤሁ ቃለአብ፤ ወበስምከ ናኃሥሮሙ ለእለ ቆሙ ላዕሌነ፤ ወካዕበ ይቤ ወወሃብኮሙ ትዕምርተ ለእለ ይፈርሁከ፤ ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት፤ ወይድኃኑ ፍቁራኒከ፤ ወንሕነኒ ንትፈሣሕ ዮም ወንግበር በዓለ፤ በዛቲ ዕለት በዓለ እግዚእነ።
ወረብ፦
ብከ ንወግዖሙ ለኲሎሙ ፀርነ ብከ ንወግዖሙ ለኲሎሙ ፀርነ ይቤ ዳዊት በመንፈሰ ትንቢት/ ፪/
በእንተ ዕፀ መስቀል ዘተሰቅለ ተሰቅለ ዲቤሁ ቃለአብ/፪/
ማህሌቱን ለምትቆሙ ሁሉ መልካም አገልግሎት ይሁንላችሁ 🙏❤️
Join & Share
✨ @zkretewahdo
✨ @zkretewahdo
✨ @zkretewahdo
፰ ተዐቀብ ከመ ኢትኩን ዘክልኤ ነገሩ
ሁለት ነገርን ከመናገር ተከልከል ለአንዱ አንድ ለአንዱ አንድ።
(፩) ማታ አንድ ጧት አንት ከመናገር ተከልከል
በጧት የተናገረውን በማታ አይደግምም እንዲል
\ሐተታ\ መናፍቃን በጉባኤ ከተረቱ በኋላ ወደ ከተማ ገብተው ለአንዱ አንድ ነገር ለአንዱ አንድ ነገር ማታ አንድ ጧት አንድ ነገር የሚናገሩ ሁነዋልና /አቋምም እርጋታም ፅናትም የለላቸው ሁነዋል/ እንዲህ አለ
ሁለት ስራ ከመስራት ተከልከል ማለት አንድ ጊዜ ጽድቅ አንድ ጊዜ ኃጢአት አንድ ጊዜ ወደ ገዳም አንድ ጊዜ ወደ ዓለም አትበል።
ሐሰተኛ እንዳትሆን።
ነገረ ሠሪ አትሁን
ሁለት ነገር ከመናገር ተከልከል/በአንድ ራስ ሁለት ምላስ አትሁን/
\ሐተታ\ ምነው ? ይህን ነገርማ ከላይ ተናግሮት አልነበረም ስለምን ? ደገመው ቢሉ ያ የምግባር ይህ የሃይማኖት ነው በሃይማኖት አንደ አንተም ነኝ ለሌላውም እንደአንተም ነኝ ማለት አለና /ይህም የተገባ አይደለም/።
፱ ወኢታንሶሱ ዘእንበለ ዳዕሙ በተዐቅቦ
ያለተዐቅቦ አትኑር
(፩) ተዐቅቦ/ራስን ገዝቶ መሰብሰብ/ የሌለው አነዋወር አትኑር።
ሰነፍ አውታታ አትሁን።
ሰውን የማታፍር እግዚአብሔርን የማትፈራ አትሁን።
ፊት አይተህ የምታዳላ አትሁን
ክፉ ነገርን የምትናገር አትሁን።
እንደምን አላችሁ ቤተሰብ
በሚመቻችሁ ሰአት ሰርታችሁ ገቢያችሁን በደንብ የምትጨምሩበት አገር በቀል የስራ አማራጭ አለን፦
1. በግልም ሆነ በመንግስት ተቋማት ተቀጥራችሁ የምትሰሩ፣
2. የግላችሁን ስራ የምትሰሩ
3. ከዩኒቨርስቲ ተመርቃችሁ ስራ ያላገኛችሁ
4. 12 ተፈትናችሁ ነጥብ የመጣላችሁም ሆናችሁ ያልመጣላችሁ
5. ስርቶበአጭር ጊዜ ውስጥ ራስን መቀየር የሚፈልግ ማንኛውም ሰው
በውስጥ አናግሩኝ እደውላለሁ
በሐሰት አትመሥክር።
አትበድል።
፫ ተዐቀብ እምነ ማውታ
ሙቶ የተገኘውን ከመብላት ተከልከል
በወጥመድ በወፈንጠር የተያዘውን
(፩ም) በደም የታፈነውን አትብላ
ሐተታ \ አንገቱን ከልለው በጭራ ገመድ አስረው ደሙን ያጠጡታልና የላላው እንዲጸና የጸናው እንዲላላ::
(፩ም) በደም ይላል በቁሙ ደም ከመብላት ተከልከል አርግተው አዝግነው ይበሉታልና ይህ ሁሉ የአሕዛብ ስራ ነውና።
(፩ም) ብርንዶ ስጋ ከመብላት ተከልከል ደም አይለየውምና።
፬ ነጽር ወዑቅ ወኢያስህትከ መኑሂ ከመ ትትገኀስ እምዛቲ ሃይማኖት::
ከዚህች ሃይማኖት ትለይ ዘንድ ማንም እንዳያስትህ ዕወቅ ምነው የያዝከው የምግባር አይደለምን ? ስለምን ሃይማኖት አለ ቢሉ የሃይማኖት መግለጫው ምግባር ነውና።
(፩ም) በቁሙ የሃይማኖት ሥራ አለበትና
ይህ ካልሆነ ግን ከእግዚአብሔር አንድነት ትለያለህ።
፭ ወእሉ እሙንቱ ኀጣውእ ክሡታን
በኦሪት ፥ በሲኖዶስ፥በግብረ ሐዋርያት የታወቁ ኃጣውእ እሊህ ናቸው።
በኦሪት ፥ በሲኖዶስ፥በግብረ ሐዋርያት ያልታወቁ/ ያለተገለጹት/ ንዑሳን ትዕዛዛትም አሉ።
እኛ የነሱን ነገር እንናገራለን።
+++ ሕንፃ መነኰሳት +++
ምዕራፍ፪
፩ ለዛቲ ሃይማኖት እመ ፈቀድከ ከመ ትኩን ላቲ ድልወ።
ለሕንፃ መነኮሳት ልትበቃ ብትወድ...
ወዳጄ ጸሎተ ሃይማኖትን አጽንተህ ያዝ።
፩ድም ለሃይማኖተ ርእይ ልትበቃ ብትወድ ሃይማኖተ ሰሚዕን አጽንተህ ያዝ።
💠 ጉባኤ 💠
መቅድመ ኩሉ አፍቅሮ ለእግዚአብሔር አምላክከ።
ከሁሉም አስቀድመህ ፈጣሪህን እግዚአብሔርን ውደደው።
በፍጹም ልቡናህ በፍጹም ሰውነትህ ።
በፍጹም ሕሊናህ ፈጣሪህን ውደደው።
ባልንጀራህንም እንደራስህ አድርገህ ውደድ።
፪ ኢትቅተል ነፍሰ
ነፍስ አትግደል።
ከጉልማሳ ሚስት አትድረስ
አትሰስን።
ባል የሌላትን አትንካ።
ፅንስ አታስወርድ ።
ሳይድሩልህ ሕፃኒቱን አትንካ/ሳታገባት አትተኛ/።
ሕፃኑን ልጅህን የማያገባ ሠርቶ እንዲቀጣ አታድርግ / ሠረተህ ቀጥተህ ገርተህ አሳድግ/።
ሥራይኛ ሟርተኛ አትሁን።
የሰው ገንዘብ አትንካ።
❖ "ሰው ወደሚበዛበትና የዚህን ዓለም ፍርድ ወደሚሰጡ ቦታዎች አለመኼድ ስለማልችል፣ የምመራው ትልቅ የንግድ ድርጅት ስላለኝ፣ ሥራዬ ጥበበ እድ ስለሆነ፣ ጊዜ ስለሌለኝ፣ ትዳር ስላለኝ፣ ልጆችን ስለማሳድግ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪ ስለሆንኩ፣ እኔ የዓለም ሰው ስለሆንኩ መጻሕፍትን ማንበብ አይጠቅመኝም፤ "መጻሕፍትን ማንበብ በገዳም ለሚኖሩ መነኮሳት ነው" ብለህ አትንገረኝ።
❖ "አንተ ሰው! ምን ማለትህ ነው?" "ብዙ የዚህ ዓለም አሳብ ስላለብኝ መጻሕፍት ማንበብ ለእኔ አይደለም" ትለኛለህን? እንዲያውም ልንገርህ! አንተም ስማኝ! ከእነዚያ መነኮሳት ይልቅ ማንበብ ያለብህ አንተ ነህ፤ መጻሕፍትን በብዛት ማንበብ የሚገባቸው ብዙ የዓለም አሳብ ያላቸው ሰዎች እንጂ በምግባር በትሩፉት የተጠመዱ መነኮሳት አይደሉምና::
📌 ምንጭ
✍️ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
📚"የክርስቲያን መከራ"
አባ ቢሾይ ካሚል(እኤአ 1931- 1979)
የትውልድ ስሙ ሳሚ ካሚል ሲሆን፣ የተወለደው በሲርስ አልየን መኑፊያ ግብጽ እኤአ በ1931 ነው። ያደገው በደማንሁር ግብጽ ነው፥ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱም በዚው ነበር። በእስክንድርያ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ተማሪ ነበር፥ እኤአ በ1951 በ ቢኤስሲ ድግሪ ተመረቀ። በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሳይንስ መምህር ሆኖ እያስተማረ ትምህርቱን በእስክንድርያ ዩኒቨርሲቲ ቀጥሎ በ1954 በስነ ጽሁፍ ሁለተኛ ድግሪውን ተቀበለ። በዚያው በእስክንድርያ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ኮሌጅ መምህር ሆነ። በታህሣስ 1959(እኤአ) ካህን ሆኖ ተሾመ።
ብዙ ሰዎች ስለቀደመው ሕይወቱ ሲያወሩ አይታይም። በመምህርነት፣ በሰንበት ት/ቤት አገልጋይነት እና በትምህርት እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሕፃናት በነፃ ማስተማሩ ብዙም አይነገርም። ምክንያቱም ብዙዎች የሚያውቁት ካህን ሆኖ እንደ ትጉ ንብ መልካሙን ሲሰበስብና ንጹህ ማርን ሲሰራ በርሱም የሚያውቁትንም ሆነ የማያውቁትን ሰዎች ሕይወት ሲያጣፍጥ ነው። ብዙዎች አባ ቢሾይ እና አረጋዊው አባ ሚካኤል በዘመኑ ሲላላኩ የነበሩትን መልዕክታት አይረሱም። አረጋዊው እንዲጸልይለት እየጠየቀ ለወጣቱ ሰላምታን ይልክለታል። አሁን ሁለቱም በገነት አብረው ናቸው፥ አይን ያለየውን እያዩ ጆሮ ያልሰማውን እየሰሙ በውነት የወደዱትን የነገስታት ንጉስ የጌቶች ጌታ እያመሰገኑ በዚያ አሉ።
ለታናሹ መንጋ(ሉቃ 12:32) ያለውን ፍቅር በዚህ መልክ ገለጠው፦"ጌታሆይ እነዚህ ልጆችህ ናቸው፤ አንዳንዶች በበጎ ሀሳብ የሚጓዙ ሌሎች ደግሞ በክፉው የሚሄዱ፣ ሌሎች ራሳቸውን የሚያባክኑ ናቸው...እነዚህ ሁሉ ግን አንድ የጋራ ነገር አላቸው፣ ሁሉም ልጆችህ ናቸው። እኔ ደግሞ የልጆችህ አገልጋይ ነኝ፥ አገልጋይ ነኝና ከነርሱ አንዱንም መስደብም ሆነ መናቅ አልችልም፥ ይህን ካደረግክሁ አንተን መስደብ መናቅ ይሆናልና፥ እኔ የምችለው ላገለግላቸው፣ ልወዳቸው እና የዓለምን ኃጢአት የተሸከምክ እና ሁሉንም እንደምትወዳቸው የታመነ ቃልኪዳንህን ላሳስባቸው ነው።"
በስፖርቲንግ አሌክሳንደርያ የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተክርስቲያን ያቋቋመ እና በዚያ ያገለገለ ነው፤ የተቀበረውም በዚያ ነው። አንዳንዶች ረዳት ካህናትን በቅጥር እንዳይቀበል መክረውት ነበር፥ እርሱ ግን እንደ ፉክክር የሚያይ ሰው ስላልነበረ ተጨማሪ ካህናት ቁጥራቸው እስከ 5 ደረሰ(በዘመኑ ብዙ ነበር)፤ ሁሉም ከሚችሉት በላይ ብዙ አገልግሎት ነበረባቸው። በዘመኑ እጅግ ወጣት ሆኖ ትልቅ ካቴድራል የሚያስተዳድር ነበር፥ አገልግሎቱም ተከናውኖለት ነበር።
በደብሩ የካህናትን ቁጥር በመጨመር ብቻ ሳይሆን አዳዲስ አብያተክርስቲያናትን አገልግሎት በማስጀመር መሳሪያ ሆኗል። በአሜሪካ፣ በአውሮፓ እና አውስትራሊያ አዳዲስ አብያተክርስቲያናት እንዲቋቋሙ ትልቅ አስተዋጾ አድርጎ ነበር።
አባ ቢሾይ መስቀልን እጅግ ይወድ ነበር፣ በዚህም የተነሳ እረፍቱ በበዓለ መስቀል ሠለስት ነው(መጋቢት 12)። ሁለት ለጻፋቸው መጻሕፍት የሰጠው ርዕስ "በመስቀሉ ስር" እና "ከክርስቶስ ጋር የተሰቀለ" የሚል ነበር። የተሰቀለው ክርስቶስ እና መግደላዊት ማርያም ከመስቀሉ ስር ተንበርክካ የሚያሳየው ስዕል አድኀኖ በመኝታ ክፍሉ ግድግዳ ላይ አኑሮት ነበር።
አባ ቢሾይ ካሚል ዘውትር ስለ ነፍሱ ድኅነት ይጨነቅ ነበር። ስለግል ሕይወት በማወራት እምብዛም ነው። እርሱ እና ባለቤቱ አንጌል በድንግልና ነው የኖሩት። ዘውትር ከመስቀል ጀርባ ራሱን ይደብቅ ነበር። አገልግሎቱ በእውነት የሚወድና የሚንከባከብ አባት፣ ወንድም፣ ጓደኛ አይነት ፍቅር ነበር። የቢሮ ስራ ብቻ እንደሚሰራ ካህን አልነበረም። በበዓላት ከሌሊት አገልግሎት በኃላ ችግረኞችን ለመጎብኘት ይፋጠናል። ከባለቤቱ ጋር አብረው ወይም ቦታ ተከፋፍለው ለመርዳት በተለያየ መንገድ እየሄዱ የሚችሉትን ሁሉ ያደርጋሉ። አንዳንዶቹን ሰዎች በበዓሉ ምሽት ወደቤታቸው ይዘው ይሄዱ ነበር።
እርሱ ባለበት ሰዎች ስለ ሌሎች ክፋት እንዲያወሩ አይፈቅድላቸውም ነበር፥ ሁልጊዜም ስለሌሎች የሚናገረው በጎ ነበር፥ በተለይ እርሱን የሚቃረኑ ሰዎችን በጎ ነገር ነገር ይናገራል። እንዲህ የሚለውን የሐዋርያውን ቃል በመከተል፦"
⁴ ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤
⁵ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤" 1ኛ ቆሮንቶስ 13:4-5
ስብከቱ መንፈሳዊ ትርጉሙ ጥልቅና በእግዚአብሔር ቃል የተቀመመ በተግባራዊ ቃላት የቀረበ ነው። ስብከቱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌ፣ ከቤተክርስቲያን ታሪክ፣ ትውፊት እና ከቅዱሳን ሕይወት ነበር። በቅዳሴ ድምጹ ዝቅ ያለ ነበር፣ ነገር ግን ለሚሰሙት የሚያጽናና ነበር። ይህም ብዙዎችን ወደቤተክርስቲያን ሳበ፥ ለቅዳሴ ብቻ ሳይሆን ለሰርክ ጸሎትም ቤተክርስቲያን መምጣትን አዘወተሩ። እጅግ ትሁት ስለነበር ሰዎች ለምን እንደሚያደንቁት ይገርመው ነበር። ሁሉ ጊዜ ራሱን እንደማይገ'ባው በቂ ነገር እንዳላደረገ አድርጎ ነው። ምሳሌነቱ እርሱን በሚያውቁ እና በሰሙ ላይ በግልጽ ይታያል። በርግጥ እረፍቱ በጊዜ ነበር፤ ነገር ግን በሰማይ ሆኖ ስለኛ እንዲማልድ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆነ።
በ1976(እኤአ) አባ ቢሾይ በሕክምና የካንሰር ምርመራ አድርጎ ክትትል ጀመረ፣ ከ3 ዓመታት ትግል በኃላም በመጋቢት 12/1971(እኤአ መጋቢት 21, 1979) በሰላም አረፈ። በዕረፍቱ አልጋ ላይ ሳለ አብረው በዘመኑ የነበሩት አባ ታድሮስ ማላቲ ሁኔታውን ሲያስታውሱ እንዲህ አሉ፦"እግዚአብሔር አባ ቢሾይ በአልጋ ላይ ሳለ ያገለገለውን አገልግሎት ከርሱ ሰወረ፥ ብዙ ሰዎች በሕመም ውስጡ ሆኖ እርሱን በመመልከታቸው ወይም ትዕግስቱንና ደስታውን በማየት ብቻ መጽናናትን አግኝተዋልና!"
በቅዱስነታቸው አቡነ ታዎድሮስ ዳግማዊ የተመራው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሰኔ 2/2014(እኤአ ሰኔ 9/2022) አባ ቢሾይ ካሚልን ቅዱስ ብሎ አውጇል።
ጸሎቱ ከኛ ጋር ትሁን ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
@hiwotemenekosat
❖❖❖❖ መስቀሉን እሸከማለሁ የሚል የመድኃኔ ዓለም ወዳጅ ?????????????????????????
አንተ ሰው እስኪ ልጠይቅህ? :ጌታ የተሰቀለ ዕለት ዕርጥብ መስቀል ተሸክሞ ወደ ቀራንዮ ሲሄድ ብትኖር ኖሮ ታግዘው ነበርን ? ወይስ አብረህ ትገፋው ነበር ? ወይስ በርቀት ሆነህ ይገባዋል እያልክ ትደነፋ ነበር ? ወይስ አላውቀውም ብለህ ትክድ ነበር ? ወይስ ጥለኸው ትጠፋ ነበር ? ወይስ በልብህ አምነህ አብረህ ከጠላቶቹ ጋር ታመዋለህ ? ወይስ ራቅ ብለህ ትከተለው ይሆን ? እስኪ ዛሬ የደመራ ነጭ ልብስህን እንደለበስህ ይህንን አስብና ምን እንደምታደርግ እርግጡን ለልብህና ለራሱ ለመድኀኔዓለም ንገረው !
አይ ጌታዬ ተሸክሞ እየደከመማ አግዘዋለሁ እንጅ አልክደውም ትለኝ ይሆናል ። እኔም እንዲህ እልሃለሁ ።
አንተ ሰው ! አሕዛብ ቤቱን በማቃጠል ፥ ልጆቹን በማረድ እያሳደዱት በአንተ ዘንድ በልጅነት ያድር ዘንድ በመጣ ጊዜ ሰውነትህን በዝሙትና በበደል አርክሰህ በንስሐ ሳትታጠብ ከቆየኸው ማደሪያ እየነሣኸው አይደለምን ? አብረህ እየገፋኸው አይደለምን ? እርሱ ስለአንተ ርጥብ መስቀል ተሸክሞ አንተ የወንድም እኅቶችህን አመል የማትታገሥ ከሆነ ምኑን መስቀሉን አገዝኸው ? እርሱ ለጠላቶቹ መስቀል ከተሸከመ የእኅት ወንድሞቻችን ሸክም የማንሸከም እኛ ምን እዳ ይጠብቀን ይሆን ? ወዳጄ ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን ሲል የተሸከመውን መስቀል አግዘዋለሁ ካልክ አንተ ለምን ለሚስትህ ብለህ ድካሟን አትሸከምም ? እጠቀም የማይል ጌታ የአይሁድን መስቀል ከተሸከመ መንግሥተ ሰማያት ትወርስ ዘንድ ለምን መከራ አትቀበልም ?
ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ ! አንዳንዶቻችን በልብ አምነን በአፍ ዝም ያልን ነን ! አንዳንዶቻችን ገብቶንም ሳይገባንም መስቀሉን ከሚገፉ ጋር ተባባሪዎች ነን ! አንዳንዶቻችን ራቅ ብለን እሰይ ይበላቸው እያልን በአባቶቻችን ውርደት የምንሳለቅ ነን ! አንዳንዷቻችን ደግሞ ቀርቦ ከመቃጠል ራቅ ብሎ መጠቅለል እያልን ከባድ ነገር መስማትን የማንወድ ሲነሣ ንገሩኝ አይነት ሰዎች ነን ! አንዳንዶቻችን እንደ ቀንድ አውጣ ደስታ ሲሆን ብቅ መከራ ሲመጣ በኑሯችን ሸማ ጥልቅ የምንል ነን ! አንዳንዶቻችን ጭራሽ ምን እየሆነ እያለ እንኳ የማይገባን አመት በዓል ሲመጣ ለምግብ ብቻ አለሁ ባዮች ጥለን የጠፋን የበረከተ ኅብስትና የድግሥ ክርስቲያኖች እንጅ ቀራንዮ ላይ የለንም ! የመጥፋታችን ምልክቱማ የመስቀል ዕለት መዝፈናችን
አይደል !
መስቀሉን እሸከማለሁ የሚል የመድኃኔ ዓለም ወዳጅ ?????????????????????????
መልስ ፦ እኔ አለሁ የመድኃኔዓለም ወዳጅ ኃይል ባገኝ የቤተክርስቲያናችን ፈተናዎች ለማሳለፍ እተጋለሁ ። ባይቻለኝ ግን የራሴን ፦
1. የራሴን ሥጋዊ የፍትወት መከራ መስቀል እሸከማለሁ እንጅ የፈቃዴ ባርያ አልሆንም ።
2. ዘወትር የዕለት ዳዊትና ውዳሴ ማርያም በመጸለይ ያለ ማቋረጥ አምላኬን እመገባለሁ ።
3. በሠራኋቸው በደሎች ከነገ ጀምሮ ለንስሐ አባቴ እናዘዛለሁ ።
4. ጌታዬ በመስቀል የተሰቀለው ለእኔ ምግብ ሆኖ ሊፈተት ፥ መጠጥ ሆኖ ሊቀዳ ነውና ለእኔ ሲል መሞቱን ቅዱሥ ሥጋውን በመቀበል እመሠክራለሁ ።
5. ምንም ቢሆን ጌታዬ እኔን ፍለጋ ከሰማይ ወደ ምድር ወርዷልና እኔም እርሱን ፍለጋ ቤተክርስቲያን ኪዳን ሳላስደርስ አልውልም ።
6. እርሱ የእኔን ደዌ በመስቀል እንደተሸከመ እኔም የባልንጀራዬን ድካም ታግሼ ማንንም ሆነ ማንን ይቅር እላለሁ ።
8. በመከራዬም ሆነ በደስታየ ከመስቀሉ ሥር እገኛለሁ እንጅ ራበኝ ብየም አልጠፋም ጠገብሁ ብየም አልርቅም !
9. ቢቻለኝ የቤተክርስቲያንን ችግር እፈታለሁ መስቀሉን እሸከማለሁ እንጅ አባቶችን አልተችም ከገፊዎች ጋር አልቆምም ።
10. ጊዜየን በማይረባና ርብሐ ቢስ በሆነ አላባክንም ፤ በየጊዜው ና በየሰዓቱ ስለቤተክርስቲያን ባልናገር እንኳ ቢያን ጆሮየ ለቤተክርስቲያን የተከፈተ አደርጋለሁ ።
11. ሥጋውን ደሙን በለጋሥነት ሀሰጠኝ ጌታ ከጠፊ ገንዘቤ ከአሥር አንዱን በታማኝነት አወጣለሁ ።
12. ለተጠራሁበት የጸጋ ሥጦታ እታመናለሁ ። ድንግል የሆነ ለድንግልና ፣ ባለትዳር እንደሁ ለትዳር ፥ ዲያቆን እንደሁ ለዲቁና ፤ መነኩሴ እንደሁ ለምንኩስና ፣ ጳጳስ እንደሁ ለጵጵስና ፥ ሊቀ ጳጳስ እንደሁ ለሊቀጵጵስና ፥ ለመታመን በቆመበት ቁርጥ ሕሊና የሚከፈትበትን ሁለንተናዊ የአጋንንት ጦርነት የሚታገሥ እርሱ ጌታን በቀራንዮ ያገዘው የቀራንዮ ሰው ነው ! ወዳጄ ሆይ ባለህባት የመንፈሳዊነት ደረጃ የምትገጥምህ መሰናክል ያቺ ለአንተ መስቀልህ ። ከመልካምነትህ ያልተናወጽህ እንደሆነ በእውነት ግርማ አይሁድን ታግሠህ ከክርስቶስ ጋር የቆምክ የመስቀሉ ሰው ነህ !
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን
እባካችሁ ጓዴ ጠፍቶኝ ነው ይህን ተፅፎ አገኘውት ⨳ታላቅ አምባ የተተከለች መንደር ናት እባካችሁ ባታውን የምታውቀው⨳ ባታውን የምታውቀው አናግሩኝ እባካችሁ 🙏🙏🙏🙏
Читать полностью…እንደምን አላችሁ ቤተሰብ
በሚመቻችሁ ሰአት ሰርታችሁ ገቢያችሁን በደንብ የምትጨምሩበት አገር በቀል የስራ አማራጭ አለን፦
1. በግልም ሆነ በመንግስት ተቋማት ተቀጥራችሁ የምትሰሩ፣
2. የግላችሁን ስራ የምትሰሩ
3. ከዩኒቨርስቲ ተመርቃችሁ ስራ ያላገኛችሁ
4. 12 ተፈትናችሁ ነጥብ የመጣላችሁም ሆናችሁ ያልመጣላችሁ
5. ስርቶበአጭር ጊዜ ውስጥ ራስን መቀየር የሚፈልግ ማንኛውም ሰው
በውስጥ አናግሩኝ እደውላለሁ
#የጌታችን የኢየሱስ ፍቅር
#ዓለምን ለመናቅ ከሁሉ አስቀድሞ በክርስቶስ ፍቅር መነደፍ መያዝ ያስፈልጋል።
#እናም ሁልጊዜ ይሄንን ፍቅር በልባችን እናኑረው አንዴ በክርስቶስ ፍቅር የተያዘ ክርስቲያን መችም ቢሆን ሌላ ዓይነት ፍቅር ሊይዘው አይችልም፤ ምክንያቱም የፍቅር ምንጭ ክርስቶስ ነው ከክርስቶስ የሚበልጥ ሌላ ምንም ዓይነት ፍቅር የለም። ሮሜ 5-8 ፣ኤፌ 5-2 ፣2ተሰ3-5
#ዘወትርም እንዲህም ብለን እንጸልይ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ተቀድቶ እንደማያልቅ የአባይ (የግዮን) ፏፏቴ ፍቅርህን በልቤ ውስጥ ጨምረው በፍቅርህ የሰከርኩ አድርገኝ እንበለው እሳት የሆነውን ጣዕመ ፍቅርህን በልቦናዬ ውስጥ አቀጣጥለው ጌታዬ ሆይ በፍፁም ልቤ በፍፁም ሀሳቤ በፍፁም አካሌ እንድወድህ አድርገኝ እንበለው ያን ጊዜ ይሄንን ዓለም እስከነግሳንግሷ ትተን መራራ የሆነውን የክርስቶስን መስቀል ተሸክመን ሁሉን ነገራችንን ትተን እንከተለው ዘንድ ይቻለናል። ማቴ10-38፣ ማቴ16-24፣ ማር10-21፣ ሉቃ14-27፣ ሉቃ 9-23
"ከሐሙስ እራት እስከ አርብ ጠዋት
ከሄሮድስ ወደ ጲላጦስ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ ከቀራንዮ እስከ ጎለጎታ በዐይነ ሕሊናችን በእግረ ልቡናችን በአካለ ነፍሳችን እንከተለው እንደ ስምዖን መስቀሉን እናግዘው እንደ ቬሮኒካ ደሙን እንጥረግለት እንደ ገሊላ ሴቶች እናልቅስለት፣ በዚያን ሰዓት ሁሉም ለሸሹት ጌታ ከመስቀሉ ስር ሆነን አለሁልህ እንበለው ያኔ ተቆራርሶ መሬት ላይ ከወደቀው ቅዱስ ስጋው ያበላናል፣ ከእጆቹ ችንከር ቁልቁል ከሚፈሰው ደሙ ተጠግተን ያጠጣናል፣ከእግሩ ስር ወድቃ ደም የምታለቅሰውን፣ ሊቃነ መላዕክት እንኳን ሊያጽናኗት ያልቻሉትን፣ስለ እኛ ልጇ በመሰቀል የተሰቀለውን ያዘነችውን ወላዲተ አምላክ መጽናኛ አድርጎ እነሆ እናታችሁ ብሎ ይሰጠናል፣ በመጨረሻም "ዛሬ በመንግስተ ሰማይ አብረን እንሆናለን" የሚለውን የመጨረሻ ርስቱን ያወርሰናል አካሉን ከእኛ ጋር ያዋህደዋል።
"ስብሐት ለከ ክርስቶስ እግዚእየ ወአምላኪየ ኩሎ ጊዜ"
"ጌታዬ እና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ክብርና ምስጋና ሁልጊዜ ይገባሀል"
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት ያለ ፍቅር ነው! 🥰
✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ "ቅዱስ መቃርስ" ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*"+ ታላቁ ቅዱስ መቃርስ +"*+
=>ታላቁ ቅዱስ መቃርስ (ቅዱስ መቃሬ) 'ጽድቅ እንደ መቃርስ' የተባለለት: የመነኮሳት ሁሉ አለቃ: ከ80 ዓመታት በላይ በበርሃ የኖረ: በግብፅ ትልቁን ገዳም (አስቄጥስን) የመሠረተ: ከ50,000 በላይ መነኮሳትን ይመራና ይመግብ የነበረ ፍፁም ጻድቅ ነው::
+በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን አርዮሳውያን ደጉን ታላቅ አባት በሰንሰለት አስረው ከግብፅ ወደ እስያ በርሃ ከጉዋደኛው ቅዱስ መቃርዮስ እስክንድርያዊ ጋር አሰድደውታል:: በዚያ ለ2 ዓመታት ስቃይን ከተቀበሉ በሁዋላ በአረማውያን ፊት ድንቅ ተአምር አድርገው አረማውያንን ከነንጉሳቸው አጥምቀዋል::
+በተሰደዱባት ሃገርም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ (ስም አጠራሩ ይክበርና) እመቤታችንን: ቅዱሳን ሐዋርያትን:
አዕላፍ መላእክትን: በተለይ ደግሞ ቅዱሳኑን ዳዊትን:
ዮሐንስ መጥምቁንና ወንጌላዊውን: ማርቆስን: ዼጥሮስን:
ዻውሎስን አስከትሎ ወርዶ ተገልጦላቸዋል:: በቅዱስ
አንደበቱም የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል::
+ታላቁ ቅዱስ መቃርስና ባልንጀራው መቃርዮስ ከ2
ዓመታት ስደትና መከራ በሁዋላ ስደት በወጡባት ዕለት
መልዐኩ ኪሩብ በክንፉ ተሽክሞ ወደ ግብፅ
መልሷቸዋል:: በወቅቱም ጻድቁን ለመቀበል ከ50,000
በላይ የሚሆኑ ልጆቻቸው መነኮሳት በዝማሬ ወጥተዋል::
+ስለ ታላቁ ቅዱስ መቃርዮስ ቅድስና ለመጻፍ መነሳት
በረከቱ ብዙ ነው:: ግን 'ዓባይን በጭልፋ' እንዲሉ አበው
ከብዛቱ የተነሳ የሚዘለቅ አይሆንም::
+ቅዱስ መቃርስ ከዘመናት በላይ በቆየበት የበርሃ
ሕይወቱ:-
1.አባ ብሶይ: አባ ባይሞይ: አባ ሳሙኤል: አባ በብኑዳን
ጨምሮ እርሱን የመሰሉ (ያከሉ) ቅዱሳንን ወልዷል::
2.ለሕይወታችን መንገድ የሚሆኑንን ብዙ ቃላትን
ተናግሯል::
3.ከገዳማት እየወጣ በብዙ ቦታዎች ቅዱስ ወንጌልን
ሰብኩዋል::
4.አጋንንትን ድል ከመንሳት አልፎ እንደ ባሪያ ገዝቷቸዋል::
5.ለዓይንና ጀሮ ድንቅ የሆኑ ብዙ ተአምራትን ሰርቷል:: . .
.
+በእነዚህና ሌሎች ምክንያቶችም ቤተ ክርስቲያን "ርዕሰ
መነኮሳት (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)" ስትል ትጠራዋለች::
በ97 ዓመቱ መጋቢት 27 ቀን ሲያርፍ መላእክት ብቻ
ሳይሆን አጋንንትም ስለ ድል አድራጊነቱ ዘምረውለታል::
=>ታላቁ ቅዱስ መቃርስ ካረፈ በሁዋላ ከክቡር ሥጋው
ብዙ ተአምራት ይታዩ ነበርና የሃገሩ (የሳስዊር) ሰዎች
ሊወስዱት ፈለጉ:: ሳስዊር ማለት ቅዱሱ ተወልዶ
ያደገባት: ወላጆቹ (አብርሃምና ሣራ ይባላሉ) የኖሩባት ቦታ
ናት:: የምትገኘውም ግብጽ ውስጥ ነው::
+በምድረ ግብጽ: በተለይም በገዳመ አስቄጥስ የአባ
መቃርስን ያህል ክቡርና ተወዳጅ የለምና የሃገሩ ሰዎች
የነበራቸው አማራጭ መስረቅ ነበር:: መሥረቅ ኃጢአት
ቢሆንም እነሱ ግን ስለ ፍቅር: አንድም ለበረከት (በረከትን
ሲሹ) አደረጉት::
+ወደ ሳስዊርም ወስደው: ቤተ ክርስቲያን በቅዱሱ ስም
አንጸው በክብር አኖሩት:: በዚያም ለ160 ዓመታት
ተቀመጠ:: በ7ኛው መቶ ክ/ዘመን ግን ተንባላት
(እስላሞች) መጥተው ቤተ ክርስቲያኑን አጠቁ:: በዚህ
ጊዜም ሕዝቡ የጻድቁን አጽም ይዘው ሸሹ:: በሌላ ቦታም
እንደ ገና በስሙ ቤተ ክርስቲያን አንጸው በዚያ አኖሩት::
+በእነዚህ ሁሉ ዓመታት የመንፈሳዊ አባታቸውን ሥጋ
ያጡት የገዳመ አስቄጥስ ቅዱሳን ያዝኑ ይጸልዩ ነበርና
ልመናቸውን ፈጣሪ ሰማ:: አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት
በነበረበት ዘመን: ከገዳሙ ለሌላ ተግባር ወደ ሳስዊር
የተላኩ አበው ከታላቁ አባት ቤተ ክርስቲያን ሲደርሱ
ሰውነታቸው ታወከ::
+ይዘው ለመውሰድ ሙከራ ቢያደርጉ ሊሳካላቸው
አልቻለም:: ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂ ደወል
ደውሎ ሕዝቡን ሁሉ ጠርቶ ነበርና:: ሕዝቡና ሃገረ ገዢው
የሆነውን ሲሰሙ "የቅዱሱን ሥጋ ብትነኩ እንገላቹሃለን"
ብለው ሰይፍ: ዱላ: ጐመድና ጦር ይዘው መጡባቸው::
+መነኮሳቱ ግን ባዷቸውን ሊመለሱ አልፈቀዱምና ሌሊቱን
ሲያለቅሱና ሲጸልዩ አደሩ:: መንፈቀ ሌሊት በሆነ ጊዜም
ታላቁ መቃርስ በግርማ ወርዶ መኮንኑን "ለምን ወደ ልጆቼ
እንዳልሔድ ትከለክለኛለህ?" ሲል በራዕይ ተቆጣው::
በዚህ ምክንያትም መነኮሳቱ የቅዱሱን ሥጋ ተቀበሉ::
+ሕዝቡም በዝማሬና በማሕኅሌት: ከብዙ እንባ ጋር
ሸኟቸው:: ታላቁ መቃሬ ወደ ገዳሙ ሲደርስም ታላቅ ደስታ
ተደረገ:: ቅዱሳን ልጆቹ ከመንፈሳዊ አባታቸው ተባርከው
በክብር አኑረውታል::
=>አምላከ ቅዱሳን የታላቁ ቅዱስ መቃርስን ትሕትናውን:
ትእግስቱንና ቅንነቱን ያድለን:: በበረከቱም ይባርከን::
=>+"+ እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+ (መዝ. 36:28-31)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
በዛሬው ዕለት(መጋቢት 27) የታላቁ የመናኞች እና የመነኮሳት አባት የዋህ ገዳማዊ ሕይወትን ያስፋፋ ታላላቅ የሊቃነ ጳጳሳት እና የፓትርያርኮች አባት (ማለትም ከእርሱ ገዳም ብዙ ሊቃነ ጳጳሳት ፓትርያርኮች ከእርሱ ገዳም ወጥተዋል። ) የሁላችን አባት የቅዱስ አባ መቃር(መቃርስ፣ወይም መቃርዮስ) የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ሌሎች ሁለት በመቃር (መቃርስ) ስም የሚጠሩ ቅዱሳን አሉ ነገር ግን የዚህ ይህ ቅዱስ ከሌሎቹ የመጀመሪያ ስለሆነ * ታላቁ ቅዱስ አባ መቃር (መቃርስ) ተብሎ ይጠራል * ። ለብዙ መነኮሳት መመሪያን የሰጠ የልጆቹን ወደ ቅድስና መድረስ አብዝቶ የሚፈልግ የታመሙትን የሚፈውስ ከልጆቹ አንዱ ኃጥያት ቢሰራ ለፍርድ የማይቸኩል በስውር የሚመክር ታላቅ ቅዱስ አባት ነው።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በታላቁ አባት በቅዱስ አባ መቃር ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ጸንታ ትኑር አሜን። አሜን። አሜን።
©Michael Misrue
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
አመ ፳፯ዑ ለመጋቢት መድኃኔዓለም ሥርዓተ ዋዜማ
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
ዋዜማ
ዘበእንቲአሃ ለቤተክርስቲያን ተፀፋዕከ በውስተ ዓውድ፤ ከመ ትቀድሳ በደምከ ክቡር፤ ዘበእንቲአሃ ዝግሐታተ መዋቅሕት ፆረ፤ ወተዓገሠ ምራቀ ርኩሰ እንዘ አልቦ ዘአበሰ፤ አምላክ፤ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሰቅለ።
አመላለስ፦
አምላክ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሰቅለ፤
አምላክ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሰቅለ።
ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ፦
በኃይለ መስቀሉ ይዕቀበነ፤ ወይክሥት አዕይንተ አልባቢነ፤ በኃይለ መስቀሉ ይዕቀበነ።
እግዚአብሔር ነግሠ፦
መስቀል ቤዛነ ኃይልነ፤ መስቀል ጽንዕነ፤ መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ፤ አይሁድ ክህዱ፤ ወንሕነኒ እለ አመነ በመስቀሉ ድኅነ።
ይትባረክ፦
ኃበሩ ቃለ ነቢያት ወይቤሉ፤ መስቀል ብርሃን ለኲሉ ዓለም።
ሰላም
መስቀል ብርሃን ለኲሉ ዓለም፤ መሠረተ ቤተክርስቲያን፤ ወሃቤ ሰላም መድኃኔዓለም፤ መስቀል ለእለ ነአምን መድኅን።
አመላለስ፦
ወሃቤ ሰላም መድኃኔዓለም፤
መስቀል ለእለ ነአምን መድኅን።
✨ @zkretewahdo
✨ @zkretewahdo
✨ @zkretewahdo
Join & share
፮ መቅድመ ኩሉ ይርኅቁ ጻድቃን ወመነኮሳት እምአንስት
ጻድቃን ወጣንያን/ጀማሪዎች/ መነኮሳት ፍጹማን ናቸው
(፩ም)ጻድቃን ናዝራውያን መነኰሳት በቁም መነኮሳት ናቸው እነዚህ ሁሉ በገቢር/በመስራት፥በመተግበር/ እንዳይበድሉ አስቀድመው
ከሴቶች ይለዩ።
ወደነሱ አይቅረቡ
በነቢብ/በመናገር/ እንዳይበድሉ ከእነርሱ ጋር አይነጋገሩ አለ ? በቦታ ይለዩ
ምንም ምን እንዳይመልሱላቸው ሴቶችን በቦታ አይገናኙ።
፯ ወፈድፋደሰ ገሀደ ይረስዩ ኩሎ ጻሕቆሙ ከመ ኢይርአይዎን።
ይልቁንም በርእይ/በዕይታ/ እንዳይበድሉ መልካቸውን ከማየት ይከልከሉ
መልካቸውን በማየት በዝሙት መነደፍ እንዳይመጣባቸው
(፩ም) ማየቱ በዝሙት ቀስት መነደፍን እንዳያመጣባቸው
ዓይን ካየ ዘንድ ልብ ይበድላልና።
†✝† እንኳን ለጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓለ ፅንሰት በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝†
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ †††
††† ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዐይን ናቸው:: ጻድቁን መንካት የቤተ ክርስቲያንን ዐይኗን መጠንቆል ነው::
ተክለ ሃይማኖት እንደ ሊቃውንት ሊቅ: እንደ ሐዋርያት ሰባኬ ወንጌል: እንደ ሰማዕታት ብዙ ግፍ የተቀበሉ: እንደ ጻድቃን ትሩፋት የበዛላቸው: እንደ ደናግል ንጽሕናን ያዘወተሩ: እንደ ባሕታውያን ግኁስ: እንደ መላዕክትም ባለ ክንፍ አባት ነበሩ:: ለዚሕ ነው ተክለ ሃይማኖትን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዐይኔ የምትላቸው::
††† ልደት †††
††† መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ: ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው:: እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ: በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::
በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል: ጸጋ ዘአብን ከሞት: እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል:: በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል::
ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጸነሱት መጋቢት 24 ቀን በ1206 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታኅሣሥ 24 ቀን በ1207 ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል::
ዕድገት
የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁናም ከወቅቱ ጳጳስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል::
መጠራት
አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አእላፍ መላእክት እያመሰገኑት በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ::
የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ:: "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን:: ከዚህ በኋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላ ሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ::
አገልግሎት
ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከጳጳሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ:: ያን ጊዜ ኢትዮጵያ 2 መልክ ነበራት::
1ኛ. ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል::
2ኛ. በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር::
ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቋዮችን) አጥፍተዋል::
ገዳማዊ ሕይወት
ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮጵያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል::
እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል::
በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ (ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል::
ስድስት ክንፍ
ኢትዮጵያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::
የወቅቱ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር::
ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-
-በቤተ መቅደስ ብስራቱን
-በቤተ ልሔም ልደቱን
-በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
-በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
-በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::
የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖትን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው::
በዚያም:-
*የብርሃን ዐይን ተቀብለው
*ስድስት ክንፍ አብቅለው
*የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
*ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
*ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
*ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
*"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::
ተአምራት
የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው::
*ሙት አንስተዋል
*ድውያንን ፈውሰዋል
*አጋንንትን አሳደዋል
*እሳትን ጨብጠዋል
*በክንፍ በረዋል
*ደመናን ዙፋን አድርገዋል::
ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕፃናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::
ዕረፍት
ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን በ1306 ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::
=>ይህች ዕለት ለጽንሰታቸው መታሰቢያ በዓል ናት፡፡
††† አምላከ ቅዱሳን ከጻድቁ አባታችን በረከትን ይክፈለን::
††† መጋቢት 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት (ጽንሰቱ)
2.ቅዱሳን እግዚእ ኃረያና ጸጋ ዘአብ
3.ቅዱስ አባ መቃርስ ሊቀ ጳጳሳት
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አጋቢጦስ ጻድቅ
2.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
3.ቅዱስ ሙሴ ፀሊም
4.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
6.ሃያ አራቱ ካኅናተ ሰማይ
††† "በረከት በጻድቅ ሰው ራስ ላይ ነው:: የኀጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው:: የኀጥአን ስም ግን ይጠፋል::" †††
(ምሳሌ ፲፥፮)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† ምንጭ ዝክረ ቅዱሳን
+++ ሕንፃ መነኰሳት +++
ምዕራፍ፪
፩ ለዛቲ ሃይማኖት እመ ፈቀድከ ከመ ትኩን ላቲ ድልወ።
ለሕንፃ መነኮሳት ልትበቃ ብትወድ።
ወዳጄ ጸሎተ ሃይማኖትን አጽንተህ ያዝ።
፩ድም ለሃይማኖተ ርእይ ልትበቃ ብትወድ ሃይማኖተ ሰሚዕን አጽንተህ ያዝ።
💠 ጉባኤ 💠
መቅድመ ኩሉ አፍቅሮ ለእግዚአብሔር አምላክከ።
ከሁሉም አስቀድመህ ፈጣሪህን እግዚአብሔርን ውደደው።
በፍጹም ልቡናህ በፍጹም ሰውነትህ ።
በፍጹም ሕሊናህ ፈጣሪህን ውደደው።
ባልንጀራህንም እንደራስህ አድርገህ ውደድ።
፪ ኢትቅተል ነፍሰ
ነፍስ አትግደል።
ከጉልማሳ ሚስት አትድረስ
አትሰስን።
ባል የሌላትን አትንካ።
ፅንስ አታስወርድ ።
ሳይድሩልህ ሕፃኒቱን አትንካ/ሳታገባት አትተኛ/።
ሕፃኑን ልጅህን የማያገባ ሠርቶ እንዲቀጣ አታድርግ / ሠረተህ ቀጥተህ ገርተህ አሳድግ/።
ሥራይኛ ሟርተኛ አትሁን።
የሰው ገንዘብ አትንካ።
✞ዝክረ ቅዱሳን እማት✞
በዚህች ቀን ጻድቅ እና ተሓራሚት የምትሆን ቅድስት ሳራ መነኩሲት አረፈች፡፡ ከላዕላይ ግብጽ ነበረች፡፡ወላጆቿ እጅግ ባለጠጎች ክርስቲያኖች ነበሩ፤ ሌሎች ልጆች አልነበራቸውም፡፡በክርስቲያናዊ ስርዓት እና ማንበብና መጻፍን አስተምረው ነበር ያሳደጓት፡፡
ዘውትር የቤተክርስቲያን መጻሕፍትን ታነብ ነበር፣ በተለይ የአባቶች መነኮሳትን ገድል እና ብሒል፡፡ በነርሱ ሕይወት ተጽዕኖ ተፈጥሮባት የትሕርምትን ሕይወት ትሻ ነበር፡፡ በላዕላይ ግብጽ ከሚገኙት ወደ አንዱ ቤተ ደናግል ሄዳ በዚያ ደናግላንን እያገለገለች ብዙ ዓመታት ቆየች፡፡ ከዚያንም የምንኩስናን ልብስ ለብሳ ሰይጣናዊ ፍትወትን እየተዋጋች ሰይጣን እስኪደክመው ድረስ ለ ፲፫ ዓመታት ቆየች፡፡
ሰይጣን ከጽናቷ እና ንጽህናዋ የተነሳ ቀንቶ በትዕቢት ሊጥላት አሰበ፡፡ ለጸሎት ቆማ ሳለ የበዓቷ ጣሪያ ላይ ተገለጠላት እና "ሰይጣንን ድል አርገሻልና ደስ ይበልሽ" አላት፡፡ እርሷም መልሳ "እኔ ደካማ ሴት ነኝ፥ ያለ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል አንተን ማሸነፍ አልችልም" አለችው፡፡ ሰይጣኑም እንደ ጢስ ጠፋ፡፡
ይህች ቅድስት ለመነኮሳይየት የምትነግራቸው ብዙ በሂሎች ነበሩ፡፡ ከብሂሎቿ አንዱም:-
"ሰይጣን ረጅም እድሜ እንደምኖር አስመስሎ በከንቱ ተስፋ እንዳያታልለኝ ስል እግሬን በመሰላሉ መርገጫ ላይ ሳላስቀምጥ እና ወደ ቀጣዩ ደረጃ ሳልሻገር ልሞት እንደምችል በፍፁም ሳልረሳ ነው፡፡" እንዲህም ትል ነበር:-
"ለሰው የቸርነትን ስራ መስራት መልካም ነው፥ ምንም እንኳ ሰዎችን ደስ ለማሰኘትም እንኳን ቢሆን፤እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚሆንበት ጊዜ ይመጣልና"
በመጽሐፈ ገነተ አበው የተፃፉ ሌሎች ብዙ ብሂሎችም አሏት፡፡ በወንዝ አቅራቢያ ባለ ዋሻ ውስጥ ለ፷ ዓመታት በታላቅ ተጋድሎ ቆየች፡፡ አርፋ ወደ ዘላለማዊ መኖሪያ እስክትሄድ ድረስ ማንም አላያትም ነበር፡፡ ስታርፍም ፹ ዓመቷ ነበር፡፡
ጸሎቷ ከኛ ጋር ይሁን፡፡ አሜን፡፡
@hiwotemenekosat