hiwotemenekosatgroup | Unsorted

Telegram-канал hiwotemenekosatgroup - ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

245

✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን።✝️ ✞ይህ ሕይወተ መነኮሳት የተሰኘው ስለ ነገረ ምንኩስና ተባህትዎ የምንነጋገርበት የምንማማርበት መወያያ ግሩፕ ነው። ኑ እንደ አባቶቻችን በጥብዓት በተባሕትዎ እንኖር ዘንድ ሕይወታቸውን እንመርምር ሥርዓታቸውንም እንማር በፍኖተ አበው እንጓዝ በረከታቸውንም እናግኝ። 🔆 @hiwotemenekosat @hiwotemenekosatbot ሃሳብ መስጫ

Subscribe to a channel

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ግዴታዩ ነው ግን አንድ ነገር መረዳት ያለባቹህ ሁልጊዜ 24ሰዓት ቴሌግራምን ከፍተን አንጠቀምም (online) ላንሆን እንችላለን ፣ ኔቶርክም እንደምታውቁት ነው ግን ከዚህ ግሩፕ አላማ የወጡ ማንኛውንም ለመንፈሳዊ ህይወት ጥቅም አልባ የሆኑትን ምስል፤ተንቀሳቃሽ ምስል፤ ድምፅ፤ማስፈንጠሪያ/link/ እያጠፋን ነው ሁላችንም አይተን ለቅፅበት አናልፍም።

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

አንዳንድ ሰዎች ከዚህ ጉሩፕ የወጣ ነገርን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሲለጥፉ በቻልነው በፍጥነት እያጠፍን ነው።

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

#ዝክረ_አበው_መነኮሳት

ቅዱስ አባ አብራክዮስ

ዳግመኛ በዚህች ቀን ቅዱስ አባት አባ አብራክዮስ አረፈ። የላዕላይ ግብጽ ሰው ሲሆን በ20 ዓመቱ ከገዳማት በአንዱ መነኮሰ። ሰይጣን እርሱን መፈተን እስኪታክተው ድረስ ፍጹም ተጋድሎን ተጋደለ። ሰይጣን ቅዱሱን አባት ወደ ተስፋ መቁረጥ ሊጥለው እንዲህ አለው፦"በዚህ ዓለም የምትኖረው ገና 50 ዓመታት ይቀሩሃል" ።ቅዱሱም መልሶ "ይህን በማለትህ አዝኛለሁ እኔ ያሰብኩት መቶ ዓመት ይቀረኛል ብዬ እና በተጋድሎዬ እና አምልኮዬ ሰንፌ ነበርና፤ አሁን ነገሩ አንተ እንዳልከው ከሆነ ከመሞቴ በፊት አብዝቼ መጋደል አለብኝ።" በዚህም መንገድ ሊያሰንፈው የሞከረውን ሰይጣን አሸነፈው። በጽኑ ሁኔታ ከተጋደለ በኃላ በዚያው ዓመት በሰላም አረፈ። 70 ዓመታትን በአምልኮ እና ትሕርምት ቆየ።

ጸሎቱ ከኛ ጋር ትሁን። አሜን።

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

#ዝክረ_መነኮሳት_ወመነኮሳይያት

አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

ጻድቁ የተወለዱት በአክሱም ጽዮን ነው፡፡ ነገዳቸው የአክሱም ገበዝ ከነበረው ከጌድዮን ነው፡፡ አባታቸው እስጢፋኖስና እናታቸው አመተ ማርያም ምግባር ሃይማኖታቸው የቀና ትሩፋት ተጋድሏቸው የሰመረ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ገና በ12 ዓመቱ ማይ ሹም በተባለው ባሕር ገብቶ ሲጸልይ ባሕሩ በብርሃን ተከቦ ይታይ ነበር፡፡ ከባሕሩም ወጥቶ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ እያለቀሰና እያዘነ ሲጸልይ ካህናቱ ‹‹ይህ ሕፃን የእኛ ኃጢአት እየታየው? ወይስ ምን ኃጢአት ኖሮበት ነው እንዲህ የሚያዝነውና የሚያለቅሰው?›› እያሉ ያደንቁና ይገረሙ ነበር፡፡አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ እናቱ አመተ ማርያም ቤተሰቧንና ቤት ንብረቷን ትታ ከመነኮሰች በኋላ እርሱም ካልመነኮስኩ በማለት አባቱ እስጢፋኖስን ቢለምነውም እምቢ ስላለው በራሱ ፈቃድ ከአንድ ሽማግሌ ጋር ወደ አባ
መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ደብረ በንኰል ገብቶ መነኮሰ፡፡ በዚያም ነፍሱን ‹‹ነፍሴ ሆይ! እነሆ ለክርስቶስ ታጨሽ፣ የቅዱሳንን ቀንበር እንሆ ተሸከምሽ፣ የመላእክትን ንጽሕና ትጠብቂ ዘንድ ዛሬ በእግዚአብሔርና በቅዱሳኑ ሁሉ ፊት ቃልኪዳን ገባሽ፣ቃልኪዳንሽን ብትጠብቂ መላእክት ይደሰቱብሻል፣ ባትጠብቂ ግን አጋንንት ይዘባበቱብሻል…›› እያለ ብዙ መከራን በራሱ ላይ በማብዛት ሰባት ዓመት
በዚያች ገዳም ኖረ፡፡ እህልም አይቀምስም ነበር ይልቁንም የሚሰጡትን እንጀራ ለሕጻናትና ለውሾች እየሰጠ አሠር ይመገብ ነበር፡፡ ዳግመኛም በሌላ ጊዜ ቅጠልን እየቀቀለ እስከ አምስት ቀን ከድኖ ያስቀምጠዋል፣ እስከሚተላም ድረስ ይጠብቀውና ያን ይመገባል፡፡ ኩስይ የምትባል ከሣር ሁሉ የምትመርን ሣር ምግቡ አደረገ፡፡ በኋላም አባቱም ልጁን ሳሙኤልን ተከትሎ ወደ እርሱ መጥቶ በአባ አድኃኒ እጅ መነኮሰ፡፡ ለአባቱም መምህር ሆኖት እያገለገለው ያስተምረው ነበር፡፡

በሌላም ጊዜ 17 ዓመት ከተቀመጠባት ወይና በምትባል ቦታ ሲኖር ከውኃ በቀር ምንም ሳይቀምስ 12 ዓመት ተቀምጧል፡፡ ለ50 ዓመትም ያህል ሣር፣ ቅጠል፣ የዛፍ ሥርና ፍሬን እነዚህንና የመሳሰሉትን እየበላ ኖረ እንጂ እህል የሚባል አልበላም፡፡ወጥቶም ወደ ዋሻ እየገባ ብዙ ጊዜ 40 ቀንና 40 ሌሊት በጾም በጸሎት እየኖረ እንቅልፍም እንዳያሸንፈው እስከሚነጋ ድረስ ሳይቆም ሳይተኛ እንደቆመ በጽኑ ተጋድሎ ተቀመጠ፡፡ ትልቅ ጉድጓድ ቆፍሮ በውስጡ እየገባ ሳይቀመጥ ሳይተኛ ሰውነቱ እንደ እንጨት እስኪደርቅ ድረስ በጾም በጸሎት በእጅጉ ይተጋ ነበር፣በዚህም ወቅት ጌታችን ተገልጦለት ሰውነቱን በሙሉ ምራቁን ስለቀባለትና
አውራ ጣቱን ስላጠባው ከዚህ ጊዜ በኋላ ርሀብና ጥሙ ጠፍቶለት ሰውነቱም ታድሶለታል፡፡ ዳግመኛም በአፉም ድንጋይ ጎርሶ፣ እግሩንም ታስሮና ማቅ ለብሶ ወደ ባሕር እየገባ ይጸልይ ነበር፡፡አባታችን አባ ሳሙኤል በሕይወተ ሥጋ ሳለ እጅግ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን አድርጓል፡፡ እንደሙሴ ባሕርን የከፈለበት ጊዜ አለ፤ በልዑልም ዙፋን ፊት እየቀረበ ከቅዱሳን መላእክት ጋር የሚያመሰግንበት ጊዜ አለ፣ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይም ጋር ሆኖ የሚያጥንበት ጊዜ አለ ፤በሰማያዊት ኢየሩሳሌምም ሆኖ ከእነ ቅዱስ ጴጥሮስና ከሁሉ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት ጋር በአንድ ላይ ማዕድ የሚቀርብበት ጊዜ አለ፤ በእጆቹ የያዛቸው መጻሕፍቶቹ ምንም ሳይርሱ ትልቅ ወንዝን በውስጡ እያቋረጠ የሚሻገርበት ጊዜ አለ፤ እመቤታችንንም ሲያመሰግናት ከምድር ወደ ላይ አንድ ክንድ ያህል ከፍ የሚልበት ጊዜ አለ፤ በቤትም ውስጥ ሆኖ ምስጋናዋን ሲጀምር የቤቱ መሠረት እየተናወጠ ዝናብ እንደያዘ ደመና ቤቱ ከምድር ከፍ ብሎ የሚቆምበት ጊዜ አለ፤ መንፈስ ቅዱስም በብርሃን ክንፍ እየወሰደው ወደተለያዩ ገዳማት ያደርሰውና ሥጋ ወደሙን እንዲቀበል ያደርገው ነበር፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም የሁልጊዜ ጠባቂው ነውና በሁሉ ነገር ይራዳውና እንደ ጓደኛም ያማክረው ነበር፡፡

በአንዲት ዕለትም በጎዳና ሲጓዝ ወንዝ መልቶበት አገኘው፡፡ አባታችንም መጻሕፍቶቻቸውንና እሳት በእጃቸው እንደያዙ በወንዙ ውስጥ ለውስጥ ውኃውን አቋርጠው ሲሻገሩ መጻሕፍቶቻቸው አልራሱም በእጃቸው የነበረው እሳትም አልጠፋም ነበር፡፡አባታችን ሊያስቀድሱ ወደ ቤተ መቅደስ በሚገቡ ጊዜ ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ ይወርድላቸው ነበር፡፡ የእመቤታችንንም ውዳሴዋን ሲደግሙ ክንድ ከስንዝር ያህል ከምድር ከፍ ይሉ ነበር፡፡ እመቤታችንም እየተገለጠች ንጹሕ ዕጣንንና የሚያበራ እንቁን ሰጥታቸዋለች፡፡ቅዱስ አባታችን ለክቡር ሥጋ ወደሙ እጅግ ትልቅ ክብር አላቸው፡፡በቤተክርስቲያን አስቀድሰው ሁሉም ሥጋ ወደሙን ተቀብለው ወደ ቤታቸው ሲወጡ ከአራቱ መነኮሳት ውስጥ አንዱ አስታወከ፣ በቤተክርስቲያንም ዳርቻ
ተፋው፡፡ ያዩትም ሁሉ ደንግጠው ቆሙ፡፡ የእግዚአብሔር ሰው ብፁዕ ሳሙኤል ግን ሁሉንም በአፉ ተቀበለው፣ በምላሱም መሬቱን ላሰው፡፡ ይህን ጊዜ ከሰማይም
‹ሳሙኤል ሳሙኤል› የሚልን ድምጽ ሰማና ወደላይ ባንጋጠጠ ጊዜ ሰባቱ ሰማያት ተከፍተው አየ፡፡ ከላይ ያለው ያ ቃልም መለሰ፡- ‹በሰው ፊት እንዳመሰገንኸኝና ፈጽሞም እንዳከበርከኝ የባልንጀራህን ትውኪያ ትቀበል ዘንድ
እንዳላፈርህ እኔም እንዲሁ አከብርሃለሁ፤ በሰማያት ባለው በአባቴም ፊት በመላእክት ማኅበር አመሰግንሃለሁ› አለው፡፡›› ሌሎቹም ቅዱሳን እነ አቡነ ተክለሐዋርያትም እንዲሁ ለሥጋ ወደሙ ክብር ሲሉ የቆረበ ሰው ሲያስመልሰው የዚያን ሰው ትውኪያ ይጠጡት እንደነበር በቅዱስ ገድላቸው ላይ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችንና እናቶቻችን ለክርስቶስ ያላቸው ክብር እስከዚህ
ድረስ ነው፡፡

‹‹አንድ ቀን አባታችን በገዳም ውስጥ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይጎበኘው ዘንድ ወደ እርሱ መጣ፡፡ ከእርሱም ጋር ተቀምጦ ‹ወዳጄ ሆይ! ሰላምታ ይገባሃል፡፡አንተ ግን ከትንሽነትህ ጀምሮ አገለገልኸኝ፣ ምን አደርግልህ ዘንድ ትወዳለህ?› አለው፡፡ ትሑት ሳሙኤልም ‹የነፍሴ ወዳጅ ጌታዬና አለቃዬ ሆይ! መልካም ሀብት ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና ምሕረትህንና ብሩህ ፊትህን ታሳየኝ ዘንድ እሻለሁ› አለ፡፡ጌታችንም ‹አገልጋዬ ወዳጄ ሆይ! የፈለግኸውን እሰጥሃለሁ፣ ዳግመኛም ያልፈለግኸውንም እጨምርልሃለሁ› አለው፡፡ አባ ሳሙኤልም ‹ጌታዬ ሆይ! አንዲት ልመናን እለምንሃለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ኃጢአቴን አይ ዘንድ
እወዳለሁ፡፡ የሌላውን ኃጢአት ግን አታሳየኝ› አለው፡፡›› አባ ሳሙኤልን የዱር አራዊትም ሁሉ ይገዙለት ነበር፡፡ ታላቅ የሆነ ዘንዶ፣ ነብር፣ጅብ፣ ቶራህ፣ ዝሆን፣ አንበሳና ሌሎችም የዱር አራዊት ሁሉ እየመጡ እግሩን እየላሱት ወደ ቦታቸው ይመለሱ ነበር፡፡ አንበሶቹንም እሾህም በወጋቸውና እግራቸው መግል በያዘ ጊዜ በመርፌ እያነቆረ ያድናቸው ነበር፡፡ ስንጥርም ሲወጋቸው ወደ እርሱ እየመጡ ያሳዩትና ያወጣላቸው ነበር፡፡ አንበሳም አጋዘንን ገድሎ ሲበላ ሲያየው ‹‹አንዴ ዞር በልልኝ ቆዳዋን ለልብሴ እፈልገዋለሁ›› ባለው
ጊዜ ይለቅለት ነበር፡፡ እንዲሁም አንበሳው ለአባታችን ምግብም ትሆነው ዘንድ ጅግራን እየያዘ በሕይወት ሳለች ያመጣለት ነበር፡፡ አባታችንም ከገዳም ወጥቶ መሄድ በፈለገ ጊዜ አንበሶችን እንደ ፈረስና በቅሎ ይጋልባቸዋል፣

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

አቡነ ዮስጦስ "አሁን ሰዓት ስንት ነው?" ለምን ይሉ ነበር?

+እኔን ከማውራት ጌታን አውሩት(ጸልዩ)፣ ለገነትም ራሳችሁን አዘጋጁ
+ከምታስቡት በላይ ወደ ሞት እየቀረብን ነው ምንሄደው....ለንስሐ ንቁ፥ ለመጨረሻው የፍርድ ቀን ራሳችሁን አዘጋጁ
+ጊዜው ይሮጦል፣ በሩ
በሞት ሳይዘጋ ተጠቀሙበት...ሲሉ ነው፡፡

+አባ ቢሾይ አልአንጦኒ


“ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች።”(ዕለተ ሞት ይመጣል)
— ዮሐንስ 9፥4

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

Watch "ዝምተኛው መነኩሴ አባ ዮስጦስ - ክፍል 2 / Aba Yostos - Part 2 Orthodox Tewahedo Film - Ye Kidusan Tarik" on YouTube
https://youtu.be/x0wDRbMjnKE

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

🕯"እግዚአብሔርን አመስግኑት" 🕯
ወይም
🕰"አሁን ስንት ሰዓት ነው?"🕰
በማለት የሚታወቁት አቡነ ዮስጦስ አልአንጦኒ (የአባ እንጦንስ ገዳሙ)

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ዳግመኛም ታህሳስ 8 የዘመናችን ቅዱስ አባት አቡነ ዮስጦስ ዘደብረ እንጦንስ(ዝምተኛው መነኩሴ) እረፍት መታሰቢያ ነው።

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

አሰኪ ስለምንኩስና አንዳንድ ነገር ንገሩኝ። ወንድሞች/እህቶች?

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

/channel/+SE9S2oBqVSkQxuAL

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

Watch "መዝሙረ ዳዊት ከ41 - 50 (በድምጽ)" on YouTube
https://youtu.be/Y-LQz0Lpjco

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

እንኳን ለእመቤታችን ጽዮን ማርያም እና ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት በዓል አደረሰን።

#ዝክረ_አበው_ሊቃውንት

አቡነ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት

የሮም ሰው ሲሆን ከልጅነቱ ጀምሮ ብሉይንና ሐዲስን ጠንቅቆ የተማረ ነው። በሌላም በኩል ሕግ አዋቂና ተርጓሚ ሊቅ ስለነበር አንድ ቀን ለተበደለ ድኃ
ሊከራከርለት ሲሄድ በመንገድ ላይ ሳለ መልአክ ጠርቶት ወደ ገዳም ገብቶ መነኮሰ፡፡ ከብዙ ቆይታውም በኋላ አረጋዊው የሀገሪቱ ኤጲስ ቆጶስ በሥራው እንዲራዳው በማሰብ ‹‹እኔን እርዳኝ፣ አንተ ተሾምና ገዳሙን አግልግል›› ቢሉት ሹመቱንና ውዳሴ ከንቱን አልፈልግም በማለት እምቢ አላቸው፡፡አረጋዊው ኤጲስ ቆጶስም ግድ ቢሉት ሸሽቶና ተደብቆም ገዳም ገብቶ በተጋድሎ መኖር ጀመረ፡፡ ኤጲስ ቆጶሱም ካረፉ በኋላ ማንን እንደሚሾሙ ሲመካከሩ የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ ለመነኮሳቱ ‹‹የመለኮትን ነገር የሚናገር ገዳማዊ ጎርጎርዮስን ፈልጋችሁ ሹሙት›› ብሏቸው ተሰወረ፡፡እነርሱም ሲፈልጉት አጥተውት ሲጨነቁ መልአኩ ድጋሚ ተገልጦ የክብር ልብሱን ሰጣቸው፡፡ መነኮሳቱም ወንጌልንና ልብሱን ከወንበሩ ላይ አኑረው እየጸለዩ እርሱ በሌለበት ሾሙት፡፡

ስሙንም ‹‹የመለኮትን ነገር በሚናገር በገዳማዊ ጎርጎርዮስ ስም ጎርጎርዮስ›› ብለው ሰየሙት፡፡ለእርሱም በበዓቱ ውስጥ ሳለ የታዘዘ ብርሃናዊ መልአክ መጥቶ ‹‹ተነሥተህ ወደ እነርሱ ሂድ፣ እነሆ በላያቸው ኤጲስ ቆጶስነት ሾመውሃልና፤ ይህም ከእግዚአብሔር የሆነ ነው›› አለው፡፡ አቡነ ጎርጎርዮስም ተነሥቶ ሲሄድ በሌለበት በልብሱ ብቻ ሹመውት አገኛቸው፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስም ‹‹ሹመቱን አልፈልግም›› ብሎ ከብቃቱ
የተነሣ በተአምር ከመካከላቸው ተሰውሮባቸው ሄደ፡፡መልአኩም እየመራ ወስዶ ያለበትን ካሳያቸውና ለእርሱም ሹመቱ ፈቃደ እግዚአብሔር መሆኑን ነግሮት በሹመቱ እንዲጸና አድርጎታል፡፡ከዚህም በኋላ እጅግ አስገራሚ ተአምራትን እያደረገ ሲያገለግል ኖሯል፡፡

ሁለት ወንድማማቾች በጋራ የሚጠቀሙበትና ብዙ ዓሣዎች የሚጠመድበት አንድ
ባሕር ነበር፡፡ እነርሱም በእኔ ይገባኛል ተጣልተው ባለመስማማት አቡነ ጎርጎርዮስ ዘንድ ሄዱ፡፡ አባታችንም ሊያስማማቸው ቢሉ ወንድማማቾቹ እምቢ አሉ፡፡ አቡነ
ጎርጎርዮስም ባሕሩን በተአምራት አድርቆ የሚታረስ መሬት አድርጎ ሰጣቸው፡፡ወንድማማቾቹም ተካፍለው በማረስ
በሰላምና በፍቅር ኖሩ፡፡ እግዚአብሔርም በአቡነ ጎርጎርዮስ እጅ ሌሎች ብዙ እጅግ አስገራሚ ተአምራትን አደረገ፡፡ በዚህም ጻድቁ ‹‹ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት›› ተብሎ ይጠራል፡፡ በስሙ አንድ ቅዳሴ አለው፣ ቅዳሴውም በዕለተ ሆሳዕና በዓል ይቀደሳል፡፡ ሃይማኖተ አበውና ሌሎቹም የሊቃውንት መጻሕፍት በስፋት የሚጠቅሱት ይህ ጻድቅ
አገልግሎቱን ከፈጸመ በኋላ በተወለደበትና በተሾመበት ዕለት ኅዳር 21 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፏል፡፡

በረከቱ ይድርብን በጸሎቱ ይማረን፡፡

© ገድለ ቅዱሳን


@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን።ቅድስት በረከታቸው ይደርብን።

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

የቅዱሱ ራዕይ

ለ ፭(5) አመታት በበረሃው ውስጥ ጥልቅ በሆነ ራስን መካድ፥ በጾምና በጸሎት፥ በአምልኮአዊ ተመስጦ እና መንፈሳዊ ምንባብ እየኖረ ከዕለታት በአንዱ ቀን ቆሞ እየጸለየ ሳለ የእግዚአብሔር ሰማያዊ ጸጋ በርሱ ላይ በራ። ሰማያት ተከፍተው ብሩሃን አእላፍ መላዕክት ዐይን የሚበዘብዙ ወርቃማ አክሊላትን ተሸክመው መከራቸውን እና ምስክርነታቸውን በፈጸሙ ቅዱሳን ራስ ላይ ሲያቀዳጁ ተመለከተ። ቅዱሳን እንደ ፀሐይ ያበሩ ነበር፥ መላዕክቱም በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ያሳርጎቸው ነበር። ከዚህን በኃላ ቅዱስ ሚናስ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰማዕት መሆንን አብዝቶ ናፈቀ።

እግዚአብሔር በፍቅር የተቃጠለ ልቡን መሻት ሰማ። ይህን እያሰበ እያለ ከሰማይ ድምጽ ወደርሱ መጣ፦ "ሚናስ ሆይ አንተ የተባረክ ነህ፥ ከልጅነትህ ጀምሮ አንተ ለቅድስና ተጠርተሃልና። ስለዚህ ሦስት የማይጠፉ አክሊላትን መከራ ስላገኘህበት በቅድስት ሥላሴ ስም ትቀበላለህ ፥ አንዱ ስለድንግልናህ፥ አንዱ ስለ ብሕትውናህ(በበረሃ) እና አንዱ ስለ ሰማዕትነትህ ይሰጥሃል። ስምህ ከሌሎች ሰማዕታት ይልቅ ይገናል፥ ሰዎች ከእያንዳንዱ ነገድ፥ ቋንቋ ሁሉ መጥተው በስምህ በግብጽ በተሰራ ቤተክርስቲያን መጥተው እንዲያመልኩኝ አደርጋለሁ። ከሁሉ ይልቅ የማይገለጥ ክብርና፥ ከፍታ በዘላለማዊ መንግስቴ ትቀበላለህ።"

ረድኤቱ እና በረከቱ የወዳጁም የአቡነ ቄርሎስ ሣድስ ምልጃ አይለየን፥ አሜን።


@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

አመሠግናለሁ አዎ መጥፋት አለበት ክብር ይስጥልኝ

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

#ዝክረ_አበው_ባሕታውያን
#ዝክረ_ግሑሳን_አበው

ቅዱስ ክሪስቶዶለስ
``````` ````````````

ይህች ቀን ጌጣጌጥ ሰሪ የነበረው የቅዱስ ክሪስቶዶለስ ዕለተ ዕረፍት ናት። ከግብጽ አውራጃዎች ከአንዱ ከተማ ነበር። ከዕለታት በአንዱ ቀን አንዲት ቆንጆ ሴት የተሰበረ ዕቃ ይዛ መጣች እና ትፈትነው ጀመር። የእጇን ጣት እያሳየችው ለነዚህ ጣቶች ቀለበት ስራ፥ ለነዚህ እጆቼ የእጅ ጌጥ፥ ለዚህ ደረቴ መስቀል እና ለነዚህ ጆሮዎቼ ጆሮ ጌጥ ስራ አለችው። መልሶ እንዲህ አላት:-"ዛሬ አሞኛል፥ ለነገ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን።"

ሱቁን ዘግቶ ወደቤት ሄደ፥ ራሱንም ይወቅስ ጀመር፦"እኔ ከታላቁ ቅዱስ እንጦንስ ወይም ከአባ መቃርስ ወይም አባ ጳኩሚስ እና ሌሎች ይህን አለም ሸሽተው ወደ በረሃ ከሄዱ ይልቅ የበረታሁ አይደለሁም። ነፍሴ ሆይ መዳን ከፈለግሽ ከዚህ አለም ሽሺ"። የገጠመውን ለእናቱ ነግሮ ወደ ገዳም ለመሄድ እንድትፈቅድለት እናቱን በእምባ ጠየቀ። እናቱም፦"ነገሮች እንዲህ የሚሆኑ ከሆነ አስቀድመህ እኔን መመንኮስ ወደምችለበት ወደ እናቶች ገዳም ውሰደኝ አንተን ግን ጌታ ይከተለህ።"

ወደ አንዱ የእናቶች ገዳም ወስዷት ለእመምኔቷ ሰጣት። የሚያስፈልጋትን ገንዘብ ሰቶአት፥ ሌላውን ለድኾች አከፋፍሎ ወደ ገዳም ሄደ። ለሦስት ቀናት ከተጓዘ በኃላ ሦስት ሰዎችን አየ። እያንዳዳቸው ከፀሐይ ይልቅ የሚያበራ የእጅ መስቀል ይዘው ነበር።ወደነርሱ ሄዶ ተባርኮ ራሱን ለማዳን ምን ማድረግ እንዳለበት እንዲመክሩት ጠየቃቸው። ፍሬያማ ዛፍ እና ንጹህ ውሃ ወዳለበት ሸለቆ መሩት። በዚያም በማያቋርጥ ጸሎት፥ መዝሙር ዳዊት በመድገም እና ለረዣዥም ጊዜያት በመጾም ብዙ አመታት ቆየ። በዚያ ሸለቆ ካሉት ዛፎች ፍሬ ይመገብ ነበር።

ሰይጣን እርሱን ማሸንፍ ሲያቅተው በበርበራዊ ተመስሎ ለክፉ ሰዎች ተገለጠና ፦"በሸሎቆው ውስጥ ትልቅ ሀብት አለ፥ የተቀበረውን ሀብት ያገኘው ሰው እዚያው እየኖረ ነው፥ ኑ ላሳያችሁ " አላቸው። እስከ ተራራው ተከተሉት ነገር ግን ወደ ሸለቆው መውረድ አልቻሉም ነበር። ሰይጣን መነኩሴ ተመስሎ ወደ ቅዱስ ክሪስቶዶለስ መጥቶ እንዲህ አለው፦"በተራራው ራስ ላይ መንገድ የጠፋቸው መነኮሳተ አሉ፥ እጅግ ደክሞአቸዋል፥ በውሃ ጥምም ሊሞቱ ይችላሉ። እንዲተርፉ ወደነርሱ ሄደህ የሚበላ እና የሚጠጣ ነገር ስጣቸው።

ቅዱሱ እንደመነኮሳት ልማድ ፊቱን በመስቀል ምልክት አማተበ፥ ሰይጣኑ ወደ ጢስ ተቀየረ። በዚህ መንገድ ዘውትር ቅዱሱ ሰይጣንን ድል ይነሳ ነበር። አምልኮቱን ጨምሮ እስከ መልካም ሽምግልና ድረስ ኖረ። ዕለተ እረፍቱ በቀረበ ጊዜ ወደ ሸለቆው የመሩት እነዚያ ሦስት ግሑሳን አባቶች ተገልጠው አብረው ጸለዩ። እርስበርስ ከተሳለሙ በኃላ እንዲህ አሉት፦"ጌታ ለሌሎች ጥቅም ሲል ያንተን ገድል እንድንጽፍ ላከን።" በሕይወቱ የተከሰተውን ሁሉ ነገራቸው፥ ከትንሽ ሕመም በኃላ በሰላም አረፈ። በስጋው ላይ ከጸለዩ በኃላ ቀበሩት።

ጸሎቱ ከኛ ጋር ትሁን። አሜን።


@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

#ዝክረ_አበው_ባሕታውያን
#ዝክረ_ግሑሳን_አበው

ቅዳሴ ቤቱ ለቅዱስ አባ ሚሳኤል ግሑሳዊ

በዚህች ቀን የአባ ሚሳኤል ግሑሳዊን ቅዳሴ ቤት እናከብራለን። አባ ይስሐቅ የድብረ ቀልሞን(ኤልቀላሙን) አበምኔት በገዳሙ ተቀምጦ ሳለ አንድ ወጣት ሰው ወደርሱ መጣ። አባ ይስሐቅ በመነኮሳት ልማድ ፊቱን በመስቀል ምልክት አማትቦ ወደርሱ እንዲቀርብ ፈቀደ። ወጣቱ ወደርሱ ተጠግቶ ከቅዱሱ አባት ፊት ሰግዶ እንዲህ አለው፦"አባቴ አባ ይስሐቅ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስትል ደካማነቴን ተቀበል። ነፍሴን እንዳድናት እርዳኝ፥ ከልጆችህም ቁጠረኝ።

አበምኔቱ አባ ይስሐቅ በስሙ ስለጠራው አድንቆ "ስለ ስሜ ማን ነገረህ?" አለው። ወጣቱም መልሶ "በአንተ ውስጥ ያለው ጸጋ አሳወቀኝ" አለው። አበምኔቱ ሚሳኤልን እንዲቀመጥ ጠየቀው፥ እንዲህም አለው፦"ኃያሉ እግዚአብሔር ቅዱስ መቅደስ ያድርግህ፥ አሁን ስለራስህ ንገረኝ"። ወጣቱ ሰው መለሰ እንዲህ አለ፦"ስሜ ሚሳኤል ነው። አባቴ አለምን ይወድ ነበር፥ ይህም የእግዚአብሔርን አምልኮ ከልክሎት ነበር፥ ልጆችም ስላልነበሩት ያዘን ነበር።

ከዕለታት በአንዱ ቀን አንድ አረጋዊ መነኩሴን በእንግድነት ተቀበለ፥ ሀብቱን የሚወርስ ልጅ ስለሌለው ማዘኑን ገልጦ ለአረጋዊው መነኩሴ ነገረው። መነኩሴው እንዲህ አለው፦" መንገድህን(ሀሳብህን) ሰው ወዳጅ ከሆነው ከጌታ ጋር አስተካክል፥ እሱም የተባረከ ልጅ ይሰጥሃል።" አባቴም፦"ይህን እንዴት ማድረግ ችላለው?" አለው። ቅዱሱ አረጋዊ መነኮስም መልሶ "ፍጹም የሆነ ሕይወት ኑር፥ ከምዕመናን በሚጠበቀው በቤተክርስቲያን ትዕዛዛት መሰረት ኑሮህን መስርት፤ ከቤተክርስቲያን አትራቅ፥በሁሉም ጉዳዮችህ የምታማክረው አበ ነፍስ ይኑርህ።ይህን ካደረግክ አንተ እና ባለቤትህ የተመኛችሁን ታገኛላችሁ።"

ቅዱስ ሚሳኤል እንዲህ አለ:-"አባቴ ቅዱሱ አረጋዊ መነኩሴ ያዘዘውን ሀሉ ፈጸመ፥ ቃሉም ተፈጽሞ እናቴ እኔን ወለደች፥ 6 ዓመቴ ሳለሁ እናት እና አባቴ አረፉ፥ አቡኑ እኔን አሳደጉኝ፥ ትምህርት እያስተማሩ እና የቤተሰቦቼን ንብረት እየጠበቁልኝ አደግኩ። ቅዱሳት መጻሕፍትን ሳጠና የምንኩስና ሕይወትን መናፈቅ ጀመርኩ፥ ስለዚህ እዚህ መጣሁ።" አበምኔቱም ወጣቱ ሚሳኤል በሚናገረው ነገር ደስ ተሰኘ። በገዳሙ ውስጥ ካሉት አረጋውያን ለአንዱ ሰጠው፥ እርሱም በአምልኮ እና በመንፈሳዊ ሕይወት ተጋድሎ ውስጥ የትሕርምት ሕይወትን አስተማረው።ከዚህን በኃላ የመነኮሳትን ልብስ እና ቅዱሱን አስኬማ አለበሱት።

ከዚያች ሰዓት ጀምሮ በአምልኮ እና ትሕርምት የብሕትውናን ኑሮ ኖረ። ከዕለታት በአንዱ ቀን በገዳሙ ካሉ ወንድሞች አንዱ ወደ አባ ሚሳኤል መጣ። ቆሞ እየጸለየ አገኘው፥ የበዓቱን በር ባንኳኳ ጊዜ ከፈተለት። አብረው ጸልየው አንዳቸው የአንዳቸውን ቡራኬ ከተቀበሉ በኃላ ተቀምጠው እንዴት ክፉውን ጠላት ድል እንደሚነሱ እየወያዩ ቆዩ።

ቅዱስ ሚሳኤል እንዲህ አለው፦"ሰይጣን መንፈሳዊ ጸሎታችን ልባዊ እና የጋለ ሲሆን ይሸሻል" መንፈሳዊ ንግግራቸውን ፈጽመው እግዚአብሔርን አመሰገኑት፥ ይህ ወንድምም ወደ በዓቱ ተመለሰ። ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ያ ወንድም ወደ አባ ሚሳኤል ተመልሶ መጣ። እንዲህ ብሎ ሲጸልይም አገኘው፦"አምላኬ ሆይ አድነኝ፥ የዋሃነቴን እይ፥ ከበደሎቼ ዕጠበኝ አባቴ እና እናቴ ትተውኛልና፥ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ"። ይህ ወንድም አባ ሚሳኤል ምን ያህል ቀጭን እና አጥንቱ ከስጋው እንደተጣበቀ ሲመለከት ጮኾ እንዲህ አለው፦"ሰውነትህ እኮ የተቃጠለ ነው የሚመስለው!" ። ቅዱሱም እንዲህ አለው፦"አምላኬ እግዚአብሔር ቅዱሳት መጻሕፍትን የማነብበት አይን እና ቅዱስ ቃሉን የምሰማበት ጆሮ ስልሰጠኝ አመሰግነዋለሁ። ስጸልይ የምቆምበትንም ጥንካሬ ሰጥቶኛል።"

የገዳሙ አበምኔት የቅዱስ ሚሳኤልን ትሕርምት ሲሰማ ሊጎበኘው ወደርሱ መጣ። ቅዱስ ሚሳኤል ለአበምኔቱ እንዲህ አለው፦"ቅዱስ አባቴ ከሦስት ቀናት በኃላ ወታደር የሚመስሉ ጥቂት ሰዎች(ግሑሳን) ይመጣሉ፥ እኔን ይጠይቁሃል፥ እኔን ከነርሱ አትከልክል(ሊወስዱኝ ስለሆነ)፥ የእግዚአብሔር ፈቃድ ስለሆነ አትፍራ፥ አትዘንም።ይህንም ማወቅ አለብህ፦ ቀጣይ አመት ድርቅ ይከሰታል፥ በዚያን ጊዜ ላይህ እመለሳለው።" ከቀናት በኃላ ወታደር የሚመስሉት ሰዎች መጡ፥ ቅዱሱን ወስደው ሄዱ።

አበምኔቱ ቅዱሱ ያለውን ሰምቶ ከእህሉ አብዝቶ ገዛ። ቅዱስ ሚሳኤል እንደተነበየው ድርቅ ተከስቶ የስንዴ እጥረት ተፈጠረ።ገዥው በገዳሙ የሚገኘውን የትኛውንም እህል ለመውሰድ ከነወታደሮቹ መጣ። ሌሎች ወታደሮች በገዥው ፊት ወጥተው ከለከሉት፥ ባዶ እጁንም ተመለሰ። አበምኔቱም እኚህን የረዱትን ወታደሮች ተቀበላቸው፥ አመሰገናቸው፥ የሚበሉትን ምግብም ሰጣቸው። "ከርሱ አይነት ምግብ እኛ አንመገብም" አሉት። ከነርሱ አንዱ ወደፊት ቀርቦ የአበምኔቱን እጅ ይዞ ወደ ጎን ፈቀቅ ብሎ እንዲህ አለው፦"እኔ ልጅህ ሚሳኤል ነኝ፥ እነዚህ ወታደር የሚመስሉ ሰዎች ግሑሳን ናቸው፥ ያለፈው አመት መጥተው የወሰዱኝ ናቸው።አሁን የምጠይቅህ ነገር ወደ አባ አትናቴዎስ ወደ አደግክሁበት ከተማ ጳጳስ ሄደህ ስለ እኔ ንገረው በስሜ ቤተክርስቲያን የምታሰራበትን የአባቴን ገንዘብ ጠይቀው፥ ከዚያን ቤተክርስቲያኑን እንዲመርቀው አቡኑን ጥራው"። አበምኔቱ ቅዱስ ሚሳኤል እንደጠየቀው አደረገ።

ወደ ጳጳሱ ሄዶ ብዙ ወርቅ፥ ብር እና ብዙ መጻሕፍት እንዲሁም 500 በጎች ተቀበለ። ከዚህም ሌላ አልባሳት፥ ጌጣጌጦች እና ልዩ ልዩ ንዋየ ቅዱሳት ተቀበለ። አበምኔቱ የቅዱሱን አሮጌ ቤት አፍርሶ ከአጠገቡ ያለውን መሬት በመግዛት ቤተክርስቲያኑን እዚያ ሰራ። ጳጳሱ ቅዳሴ ቤተክርስቲያኑን እያከበሩ ሳለ ቅዱስ ሚሳኤል እና ግሑሳን አባቶች መጥተው ጸሎቱን ተሳተፉ። ቅዱስ ሚሳኤል ለአበምኔቱ አባ ይስሐቅ በቀጣዩ አመት ከዚህ ዓለም እንደሚያርፍ ነገረው። ከዚያን ቅዱስ አባ ሚሳኤል እና ግሑሳነው ከወደመጡበት ተመለሱ።

የነዚህ ቅዱሳን ጸሎት ከኛ ጋር ትሁን፥ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን። አሜን።

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

መጻሕፍቶቹንም ይጭንባቸዋል፤ መንታ የወለደች አንበሳም ብትኖር ልጆቿን እየታቀፈ በየተራ ያጠባቸው ነበር፡፡ወደ ደብረ ዋሊም በሄደ ጊዜ ጌታችን ተገልጦለት በዕለቱ የእመቤታችን በዓል ስለነበር እንዲቀድስ ነግሮት ከሰማይ ኅብስትና ጽዋ መጥቶለት ቅዱሳን ሐዋርያት በቀኝ በግራ እየተራዱት ሲቀድስ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ ኅብስቱንና ጽዋውን ጋርዶታል፡፡
ጌታችንም ቦታዋንና በዚያ ያሉትን መነኮሳት ሁሉ ልጆቹ ይሆኑ ዘንድ አስራት አድርጎ ሰጠው፡፡

ዋልድባ የተመሠረተው በቀደምት ጥንታዊያን አበው ቢሆንም አባ ሳሙኤል ሲገቡበት ምድረ በዳ ሆኖ ጠፍቶ ቋያ በቅሎበት የወባ ትንኞች መፈልፈያ ሆኖ ነበር፡፡ አባታችን ግን የተበታተኑትን መነኮሳት ሰብስበው ዋልድባን እንደገና አደራጅተውና አድሰው አቀኑት፡፡ የተባሕትዎ ኑሮንም አጠናከሩበትና ገዳሙን የመናንያን አበው መሰብሰቢያ አደረጉት፡፡ አባታችን ዋልድባን እንደ ሞሰብ አንስተው
አስባርከዋታል፡፡አባ ሳሙኤል ጊዜው ደርሶ ከማረፉ በፊት ቅዱስ ሚካኤል ነሐሴ 16 ቀን ወደ ገነት ነጥቆ ወስዶ ከዕረፍቱ በኋላ ከልጆቹ ጋር የሚኖርበትን ሥፍራ አሳይቶታል፡፡
በገነት ያሉ ቅዱሳንን ሁሉ ካሳየው በኋላ በእግዚአብሔርም ዙፋን ፊት ቀርቦ ምስጋናና ቃልኪዳንን ተቀብሎ ወደ በዓቱ ተመልሶ ታኅሣሥ 12 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፎ ነፍሱን ጌታችን በእጆቹ ተቀብሏታል፡፡
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ የገባላቸው ልዩ ቃልኪዳን፡- ‹‹መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም ወደ ገነት ነጥቆ ወስዶ በዚያ ያሉ ቅዱሳንን ሁሉ መኖሪያቸውንና ክብራቸውን አሳየኝ፡፡ ‹እነሆ የተጋድሎህን ሥራ ፈጽመሃልና
አንተም ወደተዘጋጀችልህ ትመጣ ዘንድ ጊዜህ ቀርቧል› ብሎ ጌታዬ የሰጠኝን መኖሪያዬን አሳየኝ፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ልዑል ዙፋን ወደ አርያም አደረሰኝ፡፡በዚያም በክብሩ ዙፋን በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ተወዳጅ ወልድን አየሁት፡፡ በዚያም
እመቤታችን ማርያምን ከተወዳጅ ልጁዋ ቀኝ አየኋት፡፡ የብዙ ብዙ ቅዱሳን መላእክትና ጻድቃን ሰማዕታት ሁሉ በየወገናቸው ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ፍጹም አሸናፊ እግዚአብሔር የክብር ምስጋና ሰማያትንና ምድርን መላ› እያሉ በፊቱ ይዘምሩ ያመሰግኑ ነበር፡፡ እኔም በአምላኬ ፊት ሰገድኩ፡፡ ተወዳጅ ወልድም ተናገረኝ፣እንዲህም አለኝ፡- ‹ወዳጄ ሳሙኤል ሆይ! ሰላምታ ይገባሀል፣ ደስ ይበልህ፡፡
በጥቂቱ የታመንህ ባሪያዬ ሆይ በብዙ እሾምሃለሁ፡፡ እኔን በመውደድ ብዙ ደክመሃልና የመስቀሌንም መከራ በመሸከም እኔን መስለሃልና እኔም በመንግሥቴ መልካም የሆነውን የድካምህን ዋጋ እሰጥሃለሁ፡፡እነሆ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የተካከለ መቀመጫህንና አክሊልህን አዘጋጀሁልህ፣ ዕድል ዕጣህም ከአሥራ ሁለቱ ቅዱሳን ሐዋርያቶቼ ጋር ነው፡፡ አፅምህ በተቀበረበት፣የገድልህ መጽሐፍ በተነበበት፣ መታሰቢያህ በተደረገበት፣ ሥፍራ ሁሉ ምሕረትና ድኅነት ይሁን፡፡ በጸሎትህ የሚታመነውን፣ መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ ለአንተ አሥራት ሰጥቼሃለሁ፡፡ ስለ እኔ የተቀበልከውን ድካም ሁሉ ዛሬ ያገኘኸውን የአንዲት ቀን የደስታ ልክ አይሆንም፡፡›››


የአቡነ ሳሙኤል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን፡፡

©ገድለ ቅዱሳን

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

#ዝክረ_አበው_ባሕታውያን

ቅዱስ አባ ፒግሚ
****************

ይህ አባት ግብጻዊ ነው። በ 12 ዓመቱ የአባቱን በጎች እየጠበቀ ሳለ የጌታ መልአክ በወጣት ሰው አምሳል ተገለጠለት እና "ሄደን መነኮሳት እንሁን(እንመንኩስ)" አለው። አባ ፒግሚም ተሰማምቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም አብሮት ሄደ፥ ሦስት አረጋውያን መነኮሳት ወደሚኖሩበት ቦታ አደረሰው። ይህ ቅዱስ ከነዚህ አባቶች ጋር ከዚህ ዓለም እስከተለዩበት ጊዜ ድረስ ለ 24 ዓመታተ ኖረ።

ከዚህን በኃላ ቦታውን ለቆ ወደ በረሃው ውስጥ የሦስት ቀናት ጉዞ ተጓዘ። አጋንንት በዱር አውሬዎች፥እርያዎች እና እባቦች መልክ በፊቱ ተገለጡ። ሊውጡትም ከበቡት። ሃሳባቸውን በመንፈስ ተረድቶ ጸለየ፥ ከዚያን ጠፉ። ከዚህን በኃላ በሸለቆ ውስጥ ለሦስት ዓመታት ኖረ። በአንድ ጊዜ ለሳምንት እየጾመ በሳምንቱ መጨረሻ አንድ መዳፍ ጥራጥሬ ይመገብ እና ጥቂት ውሃ ይጠጣ ነበር።

የጌታን ጸሎት "አባታችን ሆይ..." ዘውትር በቀንና ሌሊት ይጸልያል። በአንድ ጊዜ ለ40 ቀናት በሌላ ጊዜ ደግሞ ለ80 ቀናት አጥንቱ ከስጋው እስኪጣበቅ ሲጾም መልአክ መጥቶ የሚበላውን ሕብስት እና የሚጠጣውን ውሃ ሰጠው። ያ ሕብስት እና ያ ውሃ ለብዙ ዓመታት ቆይቷል።

ከዚህን በኃላ በሌሊት የጌታ መልአክ በራዕይ ተገልጦለት ወደ ከተማ እንዲመለስ አዘዘው። አባ ፒግሚ ለራሱ ከከተማው ጫፍ ላይ ትንሽ በዓት ሰራ። ብቻውን በዚያ እየኖረ በአምልኮ እና ትሕርምት እየተጋ ቆየ። ለተመለከቱት ሁሉ ጥሩ ምሳሌ እና አርዓያ ሆነ። የከተማው ሰዎች ከመንፈሳዊ አስተምህሮቱ ይረኩ ዘንድ ወደርሱ ይመጡ ነበር።

ከዕለታት በአንዱ ቀን የጌታ መልአክ ነጥቆት ወደ ኤፍራጠስ ምድር ወሰደው፥ ህዝቦቹ ከኦርቶዶክስ መንገድ ወጥተው ነበርና። ሁሉንም ወደ እምነት መልሷቸው ወደ ቦታው ተመለሰ። በአንድ ወቅት ለመንደሩ ሰው ቅርጫት ለመሸጥ ተሸክሞ ሲሄድ ደክሞት ትንሽ ለማረፍ ተቀመጠ። የእግዚአብሔር ኃይል ነጥቆት መሄድ ወደ ፈለገው ቦታ አደረሰው።

ከዕለታት በአንዱ ቀን ታላቁ ቅዱስ አባ ሺኖዳ እጅግ የሚያበራ ዓምድ(ምሰሶ) ተመለከተ፥ እንዲህም የሚል ድምጽ ሰማ፦"ይህ አባ ፒግሚ ነው።" አባ ሺኖዳ እርሱ ወዳለበት ከተማ እስኪደርስ ደረስ በእግሩ ተጓዘ። በመለኮታዊ ምሪት ሁለቱም እርስ በርስ ተዋወቁ። አባ ሺኖዳ ለጥቂት ቀናት በርሱ ዘንድ ጥቂት ከሰነበተ በኃላ ወደ ገዳሙ ተመለሰ።

ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ቀን በደረሰ ጊዜ ደቀመዝሙሩን ጠርቶ ስለ ዕረፍቱ ነገረው፥ ስጋውንም አሁን ባለበት ቦታ እንዲቀብረው አዘዘው። ታሞ ተኝቶ ትኩሳት ነበረው፥ በዚህ ሁኔታ ሳለ የቅዱሳን ማህበር ወደርሱ ሲቀርቡ ተመለከተ። ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። መላዕክት ነፍሱን ተቀብለው እየዘመሩ ወደ ላይ ወጡ። አባ ፒግሚ ለ70 ዓመታት ኖረ። 12 ዓመታት በአለም እና 58 ዓመታት በአምልኮ(ምንኩስና እና በሕትውና) ኖረ።

ጸሎቱ ከኛ ጋር ትሁን፥ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን።አሜን።

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

አቡነ ዮስጦስ(ዝምተኛው መነኩሴ ): ዘገዳመ እንጦንስ

"እግዚአብሔር አቡነ ዮስጦስን ወደ 20ኛው መክዘ ያመጣቸው የ4ኛው መክዘ አባቶችን ሕይወት በገሃድ ለማሳየት ነው"__አቡነ ሺኖዳ

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

Watch "ዝምተኛው መነኩሴ አባ ዮስጦስ - ክፍል 1 / Aba Yostos - Part 1 Orthodox Tewahedo Film - Ye Kidusan Tarik" on YouTube
https://youtu.be/JSQrV9Bp4zg

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

🌿Aba Bishoy Al-Anthony🌿
🍃(የእንጦንስ ገዳም መነኩሴ)🍃

🌷 ስለ አቡነ ዮስጦስ እና እማሆይ ታማቭ ኢሪን አንድ ታሪክ ይናገራሉ ።🌷

📺ቪዲዮ

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

#ዝክረ_አበው_መነኮሳት

ቅዱስ አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀለሞን
::::::::::::::::::::: :::::::::::::::::::::::::::

በዚህች ቀን አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀለሞን አረፈ። የተወለደው በግብጽ ነው፥ ለወላጆቹም ብቸኛ ልጅ ነበር። ካህን አባቱ አርሴላዎሶ በማታ በራዕይ በሚያበራ ሰው አንዲህ የሚል መልዕክት ተነገረው፦" ልጅህ ብዙ ማህበር(ምዕመናን) ሊሰጠው ግድ ነው፥ የሕይወት ዘመኑ ሁሉ የርሱ እንዲሆን በጌታ ተመርጧልና።"

ሳሙኤል ልክ እንደ ነቢዩ ሳሙኤል ከልጅነቱ ጀምሮ ንጹህ እና ዘውትር የምንኩስናን ሕይወት በልቡ የሚያመላልስ ነበር። በአንዱ ቀን ወደ አስቄጥስ በረሃ የመሄድ አጋጣሚ ተፈጠረለት፥ ነገር ግን መንገዱን አያውቀውም ነበር። የጌታ መልአክ በጉዞው ላይ ለራሱ ወደ ገዳሙ በሚሄድ መነኩሴ ተመስሎ ተገለጠለት እና እስከ ገዳሙ አብረው ተጓዙ።

መልአኩ አባ አጋቶን ለሚባል ቅዱስ ሰው አደራ ሰጠው፥ አባ አጋቶንም የጌታ መልአክ እንደነገረው አድርጎ ተቀበለው።አባ ሳሙኤል በሁሉም ነገር በፍጹም ታዛዥነት ለ3 ዓመታት ከአባ አጋቶን ጋር ኖረ። ከዚህን በኃላ ቅዱሱ
አረጋዊው አባ አጋቶን አረፈ። አባ ሳሙኤል በብዙ ጾም እና ጸሎት የሚተጋ ነበር። በአንድ ጊዜ ለአንድ ሳምንት ይጾማል። በአስቄጥስ የአባ መቃርዮስ ቤተክርስቲያን ላይ ካህን ሆኖ ተሹሞ ነበር።

የፓፓ ሊዮን የሃይማኖት ክህደት ቅጽ የያዙ መልዕክተኞች ወደ ገዳሙ መጡ። በአረጋውያኑ መሃልም ባነበቡት ጊዜ አባ ሳሙኤል የጌታን ቅናት ቀንቶ በተሰበሰቡት መነኮሳት ፊት በመውጣት መልዕክቱን ይዞ ቀዳደደው። እንዲህም አለ፦ "ይህ የክህደት ቅጽ እና በርሱ የሚያምን ሁሉ የተወገዘ ይሁን፥ የአባቶቻችንን የአርቶዶክስ እምነት የሚቀይር የተረገመ ነው"። መልዕክተኛው(ባለስልጣን ነበርና) ይህን ሲያይ እጅግ ተበሳጭቶ ተቆጣ።እንደ ሚስማር በሆኑ ብረቶች እንዲደበደብ እና በክንዶቹ እንዲሰቅሉት፥ ፊቱንም እንዲመቱት አዘዘ። በዚህም አንድ አይኑ ጠፋ።

ከዚህን በኃላ ከገዳሙ አስወጡት። የእግዚአብሔር መልአክ ለቅዱስ አባ ሳሙኤል ተገልጦ ወደ ደብረ ቀለሞን ሄዶ እንዲኖር አዘዘው። ወደዚያም ሄዶ ገዳም ገደመ፥ በዙሪያው የተሰበሰቡትንም እያስተማረ እና በኦርቶዶክስ ሃይማኖት እያጸና ለተወሰነ ጊዜ ቆየ። የኬልቄዶውያን ተወካይ ሰው(እንደ ፓትርያርክ፥ እንደ ገዥም የሚሰራ) ስለ አባ ሳሙኤል ሲሰማ የኬልቄዶንን ጉባኤ እንዲቀበል ጠየቀው።

ሊሰማው ባልወደደ ጊዜ አስመታው፥ ከገዳሙም አስወጣው። ለተወሰነ ጊዜ ከአብያተክርስቲያናት በአንዱ ከኖረ በኃላ ወደ ገዳሙ ተመለሰ። በርበሮች ገዳሙን ባጠቁት ጊዜ እርሱን በግዞት ወደ ሀገራቸው ወሰዱት። ከነርሱ እንዲያድነውም ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸለየ። ግመል ላይ ባስቀመጡት ጊዜ ግመሏ መነሳት አልቻለችም። ስለዚህ ትተውት ሄዱ ወደ ገዳሙም ተመለሰ።

በርበሮች ድጋሚ ገዳሙን ባጠቁት ጊዜ አባ ሳሙኤልን ወደ ሀገራቸው ይዘውት ሄዱ። ከዚህ ቀደም አባ ዮሐንስ ሊቀ ካህናት ዘገዳመ አስቄጥስን ይዘው ነበርና ከአባ ሳሙኤል ጋር ተገናኙ፥ እርስ በርሳቸውም ተጽናኑ።አባ ሳሙኤልን የያዘው በርበራዊ ፀሐይ እንዲያመልክ ለማግባባት ሞክሮ ነበር፥ ባቃተውም ጊዜ ከሴት ባሮቹ ከአንዷ ጋር እግሩን አስሮ ግመል እንዲጠብቁ ላካቸው። ይህን ያደረገው አባ ሳሙኤል ከርሷ ጋር በኃጢአት ከወደቀ ለርሱ ተገዥ ይሆናል በሚል የሰይጣን ምክር ነው። በነዚህ ነገሮች ሁሉ ውስጥ ግን ቅዱሱ የበለጠ ብርታትን እያገኘ እና ልበ ጽኑ እየሆነ ሄደ።

በነዚህ ሁኔታዎች እየኖረ ሳለ የበርበራዊው ልጅ በጽኑ ታሞ እስከሞት ደረሰ፤ አባ ሳሙኤል ጸለዮለት ከሕመሙ ዳነ። ዜናው በሀገሩ ሁሉ ተሰራጭቶ የታመመ ሁሉ ወደርሱ መምጣት ጀመሩ፥ ወደርሱ የሚመጣውን ከጸለየለት በኃላ ከቅባ ዘይት ሲቀበው ይድን ነበር። የርሱ አሳዳሪ አብዝቶ ወደደው፥ አባ ሳሙኤልን ይቅርታ ጠየቀው። ያሻውንም እንዲጠይቅ ፈቀደለት። አባ ሳሙኤል ወደ ገዳሙ ለመመለስ ጠየቀ፥ ሰውዬውም ፈቀደለት።

አባ ሳሙኤል በተመለሰ ጊዜ ብዙዎቹ ልጆቹ በዙሪያው ተሰበሰቡ፥ በሺዎች እስኪቆጠሩም ድረስ በዙ። እመቤታችን ድንግል ማርያም ተገልጣለት "ይህ ቦታ ለዘላለሙ የኔ ማደሪያ ይሆናል" አለችው። ከዚያች ቀን ጀምሮ በርበሮች ዳግመኛ ይህን ገዳም አላጠቁትም። አባ ሳሙኤል ብዙ ዲስኩሮችን እና አንቀጾች ጽፏል። የእስልምናን ወደ ግብጽ መምጣት ተንብዮአል።ዕለተ ዕረፍቱ በቀረበ ጊዜ ልጆቹን አንድ ላይ ሰብስቦ በፈሪሃ እግዚአብሔር የበረቱ እንዲሆኑ አዘዛቸው፤ በትዕዛዛቱ እንዲጓዙ እና ስለ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት እስከመጨረሻው ማሕቅታ እንዲጋደሉ አዘዛቸው። ከዚያን በሰላም አረፈ።

ጸሎቱ ከኛ ጋር ትሁን፥ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን፥ ለዘላለሙ አሜን።

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

የአቡነ ሺኖዳ ርዕሰ ኩሎሙ ባሕታውያን መታሰቢያ(ቅዳሴ ቤቱ)

ከዚህ ቅዱስ አባት ረድኤት በረከት ይክፈለን።

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

There has been a notable increase in the amount of myrrh streaming from the icon of the Panagia Parigoritria at the Church of Saint Dimitrios in Vyronas, Athens. The icon began weeping myrrh over two years ago.

Most Holy Theotokos, save us!

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

☆•♥• ☆ #ቅዳሴ ☆•♥• ☆
+
♥ በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ ምሥዋዕቶች ምን ምን ናቸው?
♥ 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት እነማን ይሆኑ?
♥ ካህናት በቅዳሴ ወቅት 2: 3: 4: 5: 7: 12: ወይም 24: ሆነው ከቀደሱ ምሳሌነቱ ምን ምን ይሆን?
♥ እኛ ክርስቲያኖች ቅዳሴን ባስቀደስን ቁጥር 4 ነገሮች እናገኛለን ምን ይሆኑ?
♥ አምስቱ የስሜት ሕዋሳት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ እንዴት?
♥ ♥ ♥
አውቀነው እንጠቀምበት ዘንድ ይነበብ.....ለሌሎች ሰማያዊ ምሥጢርን አካፍለን የተሰጠንን መክሊት እናተርፍበት ዘንድ እንትጋ +
☆•♥• ☆ #ቅዳሴ ☆•♥• ☆
ቅዳሴ በሥርዓተ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት ነው፡፡ ከፀሎቶች ሁሉ የላቀ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ ፭ቱ ምሥዋዕቶች ተሞልተው ይገኙበታል እዚህንም ፭ቱን መሥዋዕቶች ማንኛውም ክርስተያን ለፈጣሪው የሚያቀርበው ነው፡፡♥
፩. የቁርባን መስዋዕት፡-
+
በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ውስጥ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆነው በቅዳሴው ፀሎት ነው ሳናስቀድስ አንቆርብምና የቁርባን መስዋዕት የሚፈጸመው በሥርዓተ ቅዳሴ ብቻ ነው፡፡ መስዋዕቱም በቤተልሔም ይዘጋጃል በቤተክርስቲያን ውስጥ በቤተ-መቅደስ ውስጥ ደግሞ ይቀርባል ወይም ይታደላል፡፡ ጌታችን ሲወለደ በቤተልሔም ተወልዶ ቀራንዮ ለዓለም ሁሉ መስዋዕት ሆኗልና ቀራንዮ በተባለች በቤተክርስቲያን ቅዱሱ መስዋዕት ለሕዝብ ይታደላል፡፡

፪. የከንፈር መስዋዕት፡- +
ካህኑ፣ ዲያቆኑና ሕዝቡ በመቀባበል በአንድነት ምስጋና ለፈጣሪያቸው የሚያቀርቡበት የከንፈራችን ፍሬ የሚሰዋበት የፀሎት ክፍል ፀሎተ ቅዳሴ ነው፡፡

፫. የመብራት መስዋዕት፡- +
በቅዳሴ ጊዜ የሚበራው ጦፍ ለእግዚአብሔር
የሚቀርብ የሚሰጥ የመብራት መስዋዕት ነው፡፡ ምሳሌነቱም የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው ይህውም ጌታችን ጨላመ ለሆነ ዓለም
ብርሃን ሆኖ ብርሃንን ሊያበራ ወደ ዓለም መቷልና ነው፡፡

፬. የዕጣን መስዋዕት፡- +
የዕጣን ፀሎት ካህኑ ብቻ የሚያጥነው ሲሆን ይህውም በማዕጠንቱ አማካኝነት ቅዱሱን እጣን በመንበሩ፣ በቅዱሳን ስዕላቱ፣ በሕዝቡ መካከል ያጥናል ይህውም የሕዝቡን ፀሎት ወደላይ በደሥላሴ መንበር ይዞ ይወጣል በሰማይም ያሉ ቅዱሳን መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሥላሴን መንበር እንደሚያጥኑ ሁሉ በምድርም ያለው ካህን የሰማያዊው ምሳሌ ነውና በምድር ያውን መንበር በማጠን ለእግዚአብሔር የዕጣን መስዋዕት ያቀርባል፡፡

፭. የሰውነት መስዋዕትነት፡- +
በቅዳሴ ጊዜ አብዛኛውን ሰዓት ሙሉውን ማለት ይቻላል በመቆም የሚፀለይ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በመሐል 2 ጊዜያት ብቻ የስገዱ ትዕዛዝ ሲተላለፍ ሕዝቡ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪው አዞሮ እራሱን አዋርዶ ይሰግዳል በእግዚአብሔር ፊት መቆምም ሆነ መስገድ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ የሰውነት መሥዋዕት ነው፡፡
☆•♥• ☆ •♥• ☆•♥• ☆
ይህ የፀሎት ክፍል (ቅዳሴ) በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላ
፩. የዝግጅት ክፍል
፪. የንባብና የትምህርት ክፍል
፫. ፍሬ ቅዳሴ
እዚህ ፍሬ ቅዳሴያት እንደየበዓሉ ይለዋወጣተሉ ብዛታቸውም ፲፬ (14) ናቸው እነዚህም፡-

፫.፩. ሥርዓተ ቅዳሴ
፫.፪. ቅዳሴ ዘሐዋርያት
፫.፫. ቅዳሴ እግዚእ
፫.፬. ቅዳሴ ማርያም
፫.፭. ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጓድጓድ
፫.፮. ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት
፫.፯. ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ
፫.፰. ቅዳሴ ባስልዮስ
፫.፱. ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
፫.፲. ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ
፫.፲፩. ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ
፫.፲፪. ቅዳሴ ዘቄርሎስ
፫.፲፫. ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ
፫.፲፬. ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ
♥♥♥
-የጌታችን በዓል ከሆነ … (ቅዳሴ እግዚእ)
-የጌታችን ምጽአት፣ ጶጉሜ እሁድ ቀን ከዋለች ሰንበት … (ቅዳሴ አትናቴዎስ)
-የእመቤታችን በዓል ከሆነ ቅዳሴ ማርያም … (ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ)
-የመላእክትና የሐዋርያት በዓል ከሆነ … (ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ)
-ከዘመነ ልደት እስከ ዘመነ ግዝረት … (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ካልዕ)
☆•♥• ☆ •♥• ☆•♥• ☆
ቅዳሴን ለመቀደስ ብዙ ጊዜ ፭ሆነው ይቀድሳሉ ይህው የአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ምሣሌ ናቸው፡፡ ነገር ግን ከዚያም በሚያንስም ሆነ በሚበዛ ሰው ቅዳሴን መቀደስ ይቻላል ለምሳሌ ፯ ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ይመስላሉ ፲፫ በ12ቱ ሐዋርያት እና በጌታችን ምሳሌ ሆነው ይቀድሳሉ፤ 24 በሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ይህ የሚሆነው እንደ ካህናቱ ብዛት ነው ጭራሽ ካህን ከጠፋ ደግሞ 1 ቄስና 1 ዲያቆን ሆነው መቀደስ ይችላሉ ሁለትነታቸው የመለኮትና የትስብዕት (የሥጋ) ምሳሌ ሆነው ይቀድሳሉ በሦስት ከሆነ በሦስቱ ሥላሴዎች አራት ከሆኑ በ4ቱ ወንጌላውያን ይመሰላሉ ከሁለት ባነሰ ግን 1 ሆኖ ግን ቅዳሴ አይቀደስም ቀኖናው የቤተክርስቲያኒቱ ሥርዓት ይከለክላል፡፡
☆•♥• ☆ •♥• ☆•♥• ☆
“ጸልዩ” ይህ የቅዳሴው የፀሎት ዓይነት ሲሆን ለ13 ጊዜያት ይባላል፡፡
በሦስተኛው ክፍለ ቅዳሴ 4 ጊዜ ይባላል ፀልዩን ዲያቆኑ ሲያውጅ ፊቱን ወደ ህዝቡ ይመልስና እንዲጸልዩ ያውጃል፡፡ በዚህ ጊዜ ተሰጥዖ ካለ ተሰጥዖ ይመለሳል ከሌለ ግን “አቡነ ዘበሰማያት” ሕዝቡ እንዲደግሙ ያውጃል፡፡+
ለምሳሌ፡-
ንፍቁ ዲያቆን “ፀልዩ በእንተ እለያበዕኡ መባዕ … መባን ስለሚያገቡ
ሰዎች ፀልዩ” ሲል በዚህ ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት አይደገምም ምክንያቱም
የራሱ ተሰጥዖ ስላለው “ተወከፍ መባዖሙ ለአሃው ወተወከፍ መባዖን…”
ይህ አቡነ ዘበሰማያት የሚተካ ፀሎት ነው፡፡
ድርገት ሲወርዱ “ፀልዩ በእንቲአነ” በሚባልበት ጊዜ እንድንጸልየው
የሚያዘው የዳዊትን መዝሙር 150ኛውን መዝሙር ነው፡፡ ፀልዩ ብሎ
ያዘዘው በዚህ ክፍል ያለ የዳዊትን 150ኛውን የመዝሙር ክፍል ነው
ማለት ነው፡፡
☆•♥• ☆ •♥• ☆•♥• ☆
እኛ ክርስቲያኖች ቅዳሴን ባስቀደስን ቁጥር
1ኛ የኃጢአት ሥርየት ይገኛል ምክንያቱም በአንቃዕዶ ሕሊና ይቅርታን ስለሚጠይቅ፣
2ኛ በነፍስም በስጋም በረከትን ያገኛል፣
3ኛ ጸሎቱም ይደመጣል፣
4ኛ የመላእክትን በረከት በቀጥታ እንሳተፋልን ቅዳሴን አስቀድሶ ሥጋ ወደሙ ሲቀበል የዘለዓለምን በረከት ያገኛል፡፡ +
በተጨማሪም ቅዳሴ በማስቀደስ
4 ነገሮች ይገኛሉ እነዚህም፡-

፩. ትምህርት+
የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማ እና የሥርዓተ ቤተክርስቲያን ትምህርት በቅዳሴ ገዚ ያገኛል፡፡ ለምሳሌ የማርያምን ቅዳሴ አባ ሕርያቆስ የደረሰውን ይህን ቅዳሴ ሲቀደስ በውስጡ ምሥጢረ ሥላሴ፣ እና ምሥጢረ ሥጋዊ እና ነገረ ማርያምን አምልቶ ይነግራል፡፡

፪. ታሪክ+
14ቱንም ቅዳሴ የሚያስቀድስ ሰው የቤተክርስቲያንን ታሪክ በቅዳሴ ውስጥ እንማራለን፡፡

፫. ምክር+
በቅዳሴ ውስጥ ተፋቀሩ፣ መጽውቱ፣ ተስማሙ፣ ጹሙ፣ ጸልዩ እየተባለ በቅዳሴ ውስጥ ሰፋ ባለመልኩ ምክር ይሰጣል ስለዚህ ቅዳሴን በማስቀደስ ምክርን ማግኝት ይቻላል ማለት ነው፡፡

፬. ተግሣጽ+
ቅዳሴ ውስጡ ተግሣጽን ይዞ እናገኝዋለን ለምሳሌ በቅዳሴ እግዚእ ላይ ከወንድሙ ጋር የተጣለ ቢኖር ይተውለት ይላል በዚህ የቅዳሴ ክፍል ውስጥ ራሳችንን ምን ላይ እንደቆምን ከሰዎች ጋር ያለንን ኅብረት ስምምነት ለፈጣሪ ራሳችንን ማስገዛታችንን እየገሠፀ ይነግረናል፡፡ እነዚህን መሠረታዊ የሆኑትን ለሰው ልጆች ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን ቅዳሴ በማስቀደስ እናገኛቸዋለን፡፡
♥ ♥ ♥ ♥ ♥
-ቅዳሴ ንባብም ዜማም የሚቀርብበት የፀሎት ክፍል ነው፡፡ ሁላችንም የምንሳተፍበት ቄሴም ዲያቆኑም ምእመኑም የሚሳተፉበት ነው፡፡
“ኢትቁም እራቀከ ቅድመ ነቢየ እግዚአብሔር …
@orthodox1

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

መዝሙረ ዳዊት 21 - 30 (በድምጽ)
https://youtube.com/watch?v=USTd0BZvNr4&feature=share

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

"ስለ ብዙዎቹ ቅዱሳን ሰማዕታት እንዲህ ተብሎአል:-

በመንፈሳዊ ራዕይ ወይም በጓደኞቻቸው የሰማዕትነት አክሊል የሚቀበሉበት ቀን ሲነገራቸው ዋዜማውን ምንም አይነት ምግብ አይቀምሱም ነበር፡፡ ነገር ግን ከዋዜማው እስከ ጠዋት ድረስ በጸሎት ቁመት፥ በንቃት እና እግዚአብሔርን በመዝሙራት፥ በምስጋና እና መንፈሳዊ ጣዕመ ዝማሬዎች እያመሰገኑት ያድራሉ፡፡ ይህም በደስታ ሆነው ልክ የሰርግ ቤት እንደሚገቡ ሰዎች ሆነው ያቺን ሰዓት ይጠብቃሉ፡፡ በጾም ውስጥ ሳሉ የአንገታቸውን በሰይፍ መመትር እና የሰማዕትነትን አክሊል ይጠብቃሉ፡፡"

__ቅዱስ ይስሐቅ ሶሪያዊ


@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ቅዱስ ሚናስ በበረሃ(ገዳም)

ዲዮቅልጥያኖስ እና ማክስሚያን ሰዎች ለጣኦታት እንዲሰግዱ እና መስዋዕት እንዲሰው የሚያዝ አዋጅ ባወጁ ጊዜ ቅዱስ ሚናስ ብዙ ሰዎች ይህን የሰይጣናዊ ሽንገላ ትዕዛዝ ተቀብለው በሰይጣን ሲያዙ መመልከትን መቋቋም አልቻለም። ቅዱሱ በብርታት ተነሳስቶ ሀብቱን ለችግረኞች አከፋፍሎ እና ከወታደራዊ ግዳጁ ለቆ ወደ በረሃ ሄደ። በዚያም ያሻውን ኑሮ ለመኖር ተችሎት ነበር፥ ይህም በተወዳጅ ጌታ ኢየሱስ የሆነ የቅድስት ሥላሴ አምልኮ ነው።ብዙ ጊዜ እንዲህ ይል ነበር፦ "በከተማው ውስጥ አመጽ እና ጥልን አየሁ፥ ስለዚህ ሸሽቼ ወደ በረሃ ሄድኩ"። በበረሃው ሳለ እስከ ምሽት ድረስ ይጾም ነበር፥ ሌሊቱንም በጸሎት ያሳልፍ ነበር።


@hiwotemenekosat

Читать полностью…
Subscribe to a channel