hiwotemenekosatgroup | Unsorted

Telegram-канал hiwotemenekosatgroup - ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

245

✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን።✝️ ✞ይህ ሕይወተ መነኮሳት የተሰኘው ስለ ነገረ ምንኩስና ተባህትዎ የምንነጋገርበት የምንማማርበት መወያያ ግሩፕ ነው። ኑ እንደ አባቶቻችን በጥብዓት በተባሕትዎ እንኖር ዘንድ ሕይወታቸውን እንመርምር ሥርዓታቸውንም እንማር በፍኖተ አበው እንጓዝ በረከታቸውንም እናግኝ። 🔆 @hiwotemenekosat @hiwotemenekosatbot ሃሳብ መስጫ

Subscribe to a channel

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ቅዱስ እንጦንስ
(የበረሃው ኮከብ፣ የመነኮሳት አባት)
+++++++++++++++++++++

በዚያን ዘመን ምንኩስና ገና አልተወጠነም ነበርና የተባትሖን ሕይወት የሚሹ ሁሉ ወጥተው ከከተማው ጫፍ ይኖሩ ነበር፡፡አባ እንጦንስም የአምልኮ እና ትሕርምት ሕይወትን ሲመራ ይህንኑ ነበር ያደረገው፡፡
🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇
በዚያም ሰይጣን በማሰልቸት፣ በስንፍና እና በሴት ምስል ክፉኛ ተዋጋው፡፡ የሰይጣንን ወጥመዶች በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል አሸነፈ፡፡ ከዚያን በኃላ ከመቃብሮች ወደ አንዱ ሄዶ በዚያ መኖር ጀመረ፣ በራሱም ላይ በሩን ዘጋ፡፡ ከጓደኞቹም አንዳንዶቹ ምግብ ያመጡለት ነበር፡፡ ሰይጣን የትሕርምት ሕይወቱን እና ጽኑ አምልኮውን ሲረዳ ቀናበት፣ ያለ ምህረትም ደበደበው በዚያን በሞት እና ሕይወት መካከል ትቶት ሄደ፡፡ጓደኞቹ ሊጎበኙት ሲመጡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ አገኙት፤ ወደ ቤተክርስቲያንም ወሰዱት፡፡ የተወሰነ ካገገመ በኃላም ወደ በፊቱ ቦታ ተመለሰ፡፡ ሰይጣንም ድጋሚ ፈተናውን ቀጠለ፤ በዚህኛው ጊዜ ግን ማስፈራሪዎቹ በዱር አውሬዎች፣ ተኩላዎች፣ አንበሶች፣ እባቦች እና ጊንጦች አምሳል ነበር፡፡ የሚያጠቁት እና የሚሰባብሩት መስለው ይቀርቡ ነበር፡፡ ነገር ግን ቅዱሱ ይስቅባቸው ነበር፣ እንዲህም ይላቸው ነበር:-
"በእኔ ላይ ስልጣን ቢኖራችሁ ኖሮ እኔን ለመዋጋት አንዳችሁ ብቻ በቂ ነበራችሁ"፡፡
እንዲህም ሲላቸው እንደጢስ ይጠፉ ነበር፣ እግዚአብሔር በሰይጣናት ላይ ድልን ሰጥቶታልና፡፡ ዘወትር ይህን መዝሙር ይዘምር ነበር:-

"እግዚአብሔር ይነሳ፣ ጠላቶቹ ይበተኑ፣ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ...."___መዝ ፷፰፥፩
🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇
ቅዱስ እንጦንስ ለስድስት ወራት የሚበቃውን ዳቦ ያዘጋጅ ነበር፡፡ ማንም ሰው ወደ በዓቱ እንዲገባ አይፈቅድም ነበር፣ ማንም ወደርሱ ሲመጣ ውጭ ቆሞ ነበር ምክሩን የሚሰማው፡፡ በዚህ በተባትሖ አምልኮ ለ፳ ዓመታት ቀጠለ፡፡ ከዚያን በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ወደ ፋዩም ሄዶ በዚያ ያሉትን ወንድሞች በእምነት አጽንቶ ወደ ገዳሙ ተመለሰ፡፡ በመከራው ዘመን ሰማዕት ለመሆን ናፍቆ ነበር፤ ገዳሙን ትቶ ወደ እስክንድርያ ሄደ፡፡ ለክርስቶስ ሲሉ የታሰሩትን ጎብኝቶ አጽናናቸው፡፡ ገዥውም አባ እንጦንስ ስለሚደርስበት መከራ ሳይጨነቅ በአደባባይ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ሲመሰክር ተመልክቶ ድጋሚ በከተማው ውስጥ እንዳይታይ አዘዘው፡፡ ነገር ግን ቅዱሱ ለማስፈራሪያዎቹ ትኩረት አልሰጠም ነበር፡፡ ንጉሡንም ተከራከረው፣ ገሰጸው። አባ እንጦንስ ይህን ያደረገው የንጉሱን ቁጣ ለመቀስቀስ፣ ከዚያን ንጉሱ ተናዶ እንዲያሰቃየው እና ለሰማዕትነት ለመብቃት ነበር፡፡ እግዚአብሔር ግን ለብዙዎች ጥቅም ሲል እንደፈቃዱ ጠበቀው በዚህም ምክንያት ገዥው ምንም ሳያረገው ተወው፡፡
🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇
ከዚያን ቅዱሱ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ወደ ገዳሙ ተመለሰ፣ብዙዎችም ሊጎበኙት እና ትምህርቱን ለመስማት ይመጡ ነበር፡፡ እነዚህ ጉብኝቶች ከአምልኮው እየከለከሉት እንደሆነ ተረዳ፡፡ ስለዚህም ሸሽቶ ወደ ምስራቃዊው በረሃ ሄደ፡፡ ከጥቂት ተንቀሳቃሽ አርብቶ አደሮች ጋር ለ ፫ ቀናት ወደ ውስጠኛው በረሃ ተጓዘ፣ ምንጭ ውሃ እና የተምር ዛፍ አገኝቶ በዚያ ለመኖር መረጠ፡፡ ዛሬ በዚህች ቦታ ላይ ነው የታላቁ ቅዱስ እንጦንስ ገዳም ያረፈው፡፡ አርብቶ አደሮቹ ዳቦ ያመጡለት ነበር፤ እግዚአብሔርም ለዚህ ሲል እዛ ያሉትን የበረሃ አውሬዎች አራቀላቸው፡፡ አባ እንጦንስ አልፎአልፎ በገዳሙ የበረሃው ጫፍ በናይል ወንዝ አቅራቢያ ያሉትን ወንድሞች ጎብኝቶ ወደ ውስጠኛው ገዳሙ ይመለስ ነበር፡፡

ይቀጥላል....

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

እንኳን ለመነኮሳት አባት አባ እንጦንስ ዓመታዊ የእረፍት በዓል እና ለመልአኩ ቅዱስ ዑራኤል በዓለ ሲመት አደረሳችሁ!

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

አባ አብርሃም
(የአባ ዮሐንስ ሊቀ ካህን ዘገዳመ አስቄጥስ ደቀመዝሙር እና የአባ ገዋርጋ ጓደኛ)
_______________
አባቱ ጻድቅ ሰው ነበር፣ ርህሩህ እና ለድሆች ደግ ሰው ነበር፡፡ ከመልካምነቱ እና ጠባዩ የተነሳ የመኖሪያ ሰፈሩ ሀብት እና የአጎራባች መንደሮችን ሀብት እንዲጠብቅ ተሰጥቶት ነበር፡፡ ግብጽ በረሃብ ስትሰቃይ ያለውን ሁሉ ለችግረኞች የሰጠ ነበር፡፡
ስለ አብርሃም እናት ስናወራ ደግሞ በፈሪሃ እግዚአብሔር የኖረች ናት፣ በዚህም ሰይጣን ቀንቶባት ክፉ ሰው አስነሳባት፡፡ በዚህም በፐርሺያኖች(ፋርሳውያን) ፊት ከሰሳት እነርሱም ወደ ፐርሺያ(ፋርስ) ይዘውዋት ሄዱ፡፡ በምርኮም ሆና ከዕለታት በአንዱ ሌሊት በራዕይ "ወደ ሀገርሽ ትመልሻለሽ" ተብሎ ተነገራት፣ ከአጭር ጊዜ በኃላም ራዕዩ ተፈጽሞ ወደ ሀገሯ ግብጽ በሰላም ተመለሰች፡፡
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ከባሏ ሞት በኃላም ልጇ አብርሃም እንዲያገባ ፈለገች፣ ነገር ግን እርሱ እምቢ ብሎ የእርሱ መሻት ምንኩስና መሆኑን ነገራት እርሷም ደስ አላት፡፡ እስከ ከተማው ጫፍ እየሸኘችው ቆይት ልትሰናበተው ስትል እጆቿን ወደ ሰማይ አንስታ እንዲህ ብላ ጸለየች:-"ጌታ ሆይ እባክህን ልጄን እንደ ስጦት(መባ) አድርገህ ተቀበለኝ"
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ቅዱስ አብርሃም ወደ አስቄጥስ(ሸሂት) በረሃ ሄደ፣ በዚያም የቅዱስ ዮሐንስ ሊቀ ካህን ዘአስቄጥስ ደቀመዝሙር ሆነ፡፡ አንባ አብርሃም እጅግ መራር የሆነ የምንኩስና ሕይወት ነበር የሚመራው፣ ራሱን በብዙ ጾም እና አምልኮ ይቀጠቅጠው ነበር፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ቅዱስ አብርሃም የበዓቱ ጣሪያ ተከፍቶ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማያዊ ሰረገላ ወደ ታች ሲወርድ ተመለከተ፣ ኪሩቤልም እያመሰገኑት ነበር፡፡ አባ አብርሃም በታላቅ ፍርሃት ሰገደ፣ ጌታም ባረከው፡፡ ከዚያም ጌታ ወደ ሰማይ አረገ፣ ጌታም እሱን ለመጎብኘቱ መታሰቢያ እንዲሆን ከበዓቱ ጣሪያ ላይ ምልክት አስቀረለት፡፡
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
በዓቱ ከመንፈሳዊ አባቱ ከአባ ዮሐንስ ጎን ነበር፣ በዓቱም "ባብጊ" ትባል ነበር፡፡ የጌታ መልአክ ከጊዜ ጊዜ ይጎበኘው ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ኦሪዮን ተራራ ወጥቶ አባ ገዋርጋን አገኘው፣ አባ ገዋርጋም ከአባ አብርሃም ጋር ወደ አስቄጥስ ተመልሶ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ አብረው ኖሩ፡፡ አባ ዮሐንስ በሞት ወደ ገነት ከሄደ በኃላ አባ አብርሃም ለ 18 ዓመታት ታሞ ነበር፡፡ የሞቱ ጊዜም(ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት) በቀረበ ሰዓት ከቅዱስ ምስጢር ተካፈለ፤ አንባ ዮሐንስም በመንፈስ ተገልጦለት ጌታ ክርስቶስ ሰማያዊ ግብዣ እንዳዘጋጀለት ነገረው፡፡ አንባ አብርሃም በ፹ ዓመቱ በሰላም አረፈ፡፡
ጸሎቱ ከኛ ጋር ትሁን፣ ለጌታችን ክብርና ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን!

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ቃለ ህይወት ያሰማልን አስተማሪ ነው! !

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

✞አባ ገብረ ክርስቶስ (ኢትዮጵያዊው ቅዱስ)
✞አባ ዮስጦስ (ዝምተኛው ቅዱስ)
✞ቅዱሳን፦ #ኒቆላዎስ #ሳዊሮስ #ጥዋሽ #ሱርስት #ተላስስ #ታውፋኔዎስ . . .

✞ቸር በዓል !
/channel/zikirekdusn

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

Watch "የበረሃው ምስጢር፡ ክፍል 1 : መቅድምና መግቢያ እውነተኛ ታሪክ #Emaretube |Ethiopian News |Seifu on Ebs| Besintu|" on YouTube
https://youtu.be/mUiJ2VjhB8Q

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

መልካም ... ጥያቄዎቹ ላይ እርስዎ ለማወቅ የፈለጉትን ዝርዝር ነገር ቢያስቀምጡ መልካም ነው። እንዲሁ በጠቅላላው ለመጠቆም ያህል ግን፦

#1. የምንኩስና ሕይወት ጀማሪ የነበረው አባታችን አባ እንጦንስ በነበረበት ዘመን ከዐበይት ሊቃውንት መካከል የሚጠቀሰው ቅዱስ አትናቴዎስ የነበረበትና እርሱም ሕይወቱን ከአባ እንጦንስ የተረዳበት ነበር። የአባ እንጦንስንም ገድል እርሱ እንደጻፈው ልብ ይሏል።

በመቀጠል የሚጠቀሱት የቀጰዶቅያውያን አበዉ እና የእነቅዱስ ቄርሎስም ሆነ የሌሎቹን አበው ዜና እና ገድል በማንበብ ስለነበረው አኗኗር ማግኘት ይቻላል። እና እርስዎ ከየት እስከ የት እና ከምንኩስናስ ማየቱንና ክፍል እንደፈለጉት ግልጽ ቢያደርጉልን። በጣም ሰፊ ስለሆነ...

2.ይሔም ሰፊ እና እንደጠያቂው የምንኩስና ሕይወት ደረጃ የሚለያዩ ናቸው። እንደየሰው ፈተናም የተለያየ ፈተና ሊፈተኑ ይችላሉ። እንጻፍበት ከተባለ በጣም ሰፊ ርእስ ስለሆነ እርስዎ የፈለጉበት ወይም ያሉበት ደረጃ አንጻር እንድንመልስልዎ ግልጽ ቢያደርጉልን።

3. የእግዚአብሔር ፈቃዱ እርሱን መስለን ክብሩን እንድንወርስ ነው። አምላካችን እግዚአብሔር በአርአያው ሲፈጥረን እንዲሁም በዳግም ልደቱ አርአያችንን አርአያው አድርጎ በድንግልና ሲወለድ ... ትልቁን የእርሱን ፈቃድ አስታውቆናል። እርሱን በመምሰል ከእርሱ ጋር ኅብረት በማድረግ ለእርሱ በመመረጥ የክብሩ ወራሽ እንድንሆን እና እንድንድን ነው። ይሔንን ፈቃዱን ደግሞ በዋናነት በቅዱሳት መጻሕፍት በተለይም በመጽሐፍ ቅዱስ አስታውቆናል።

ስለዚህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በምን ይታወቃል ላሉት ... በዚህ እግዚአብሔርን በመምሰል ጉዞ ላይ በመሆን ወይም በመጀመር ያሉበትን ቦታ በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረትነት መመርመር ነው።

ከዛ ባለፈ ነጻ ፈቃድ ለሁላችን ተሰጥቶናልና ... በእያንዳንዱ ጉዟችን እርሱን መምሰልን እስካልተውን ድረስ በመልካም ፈቃዳችን የምናደርገው መልካም ነገር በሙሉ ፈቃዱ ነው።

በሆነ ጉዳይ ላይ የተለየ ፈቃዱን ማወቅ ከፈለግን ግን ንስሐ ገብቶ ቆርቦ በሱባኤ በጾም በጸሎት ተግቶ በንጽሕና እና በፍጹም ልብ በመጠየቅ ነው።

ይህንን በተመለከተ አባታችን ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን እና ብዙ መምህራን ያስተማሩበት ስለሆነ youtube ላይ ቢያዩ ደግ ነው።

እግዚአብሔር ያክብርልን

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

መልካም ወንድማችን ምን ነበር ጥያቄዎ?

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ለዚህ አምላክ ምስጋና ይገባል። ለክብርት እናቱም እንዲሁ። ቃለ ሕይወት ያሰማልን። ከብርሃነ ልደቱ ያሳትፈን።

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ዝክረ ቅዱስ ዮሐንስ ከማ
(ታህሳስ ፳፭)
_______________

ወላጆቹ ፈጣሪን የሚፈሩ ክርስቲያኖች ነበሩ፣ ብቸኛ ልጃቸው ነብር፡፡
ያለፈቃዱም እንዲያገባ አስገደዱት፣ ወደ ሚስቱም በገባ ጊዜ ለረዥም ሰዓታት ቆሞ ከጸለየ በኃላ ወደ እርሷ ቀርቦ:- "እህቴ ሆይ ይህ አለም እና ምኞቱ አላፊ እንደሆነ ታውቂያለሽ ሰውነታችንን ንጹህ አድርገን ብንጠብቅ ከኔ ጋር ትስማሚያለሽ?" አላት፡፡ መልሳ እንዲህ አለችው "ወንድሜ የጌታ ስሙ ሕያው ነው፣ ይህ የኔም ፍላጎት ነው፣ ጌታ ልቤ ሚሻውን ሰጠኝ" አለችው፡፡
ሁለቱም እንደ ወንድም እና እህት እየኖሩ ድንግልናቸውን ለመጠበቅ ተስመሙ፡፡
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

ሲተኙም የጌታ መልአክ እየመጣ ክንፉን ያለብሳቸው ነበር፡፡ ስለ መልካም ስራቸው እግዚአብሔር የመኝታ ቦታቸውን እስኪሸፍን ድረስ ያደገ ሐመልማል አበቀለላቸው፡፡ የንጽሕናቸው እና ቅድስናቸው ምልክት ነበር ያደረጉት ነገር ከሰው ተፈጥሮ በላይ ስለሆነ፣ እነዚያ ሁለት ወጣቶች ወንድና ሴት ሆነው ፍትወት ሳይቀሰቀስባቸው አጠገብ ለአጠገብ ይተኙ ነበር፣ ወደ እሳት ቀርቦ ማነው የማይቃጠል? የፈጣሪ ኃይል እና ጥበቃ የሚጠብቃቸው ካልሆነ በቀር፡፡
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

ወላጆቻቸውም ለብዙ አመታት አብረው ኖረው ያለ ልጅ መኖራቸውን ሲያዩ ገና ወጣቶች ስለሆኑ ይሆናል ብለው አሰቡ፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ቅዱስ ዮሐንስ ለሚስቱ እንዲህ አላት:- " እህቴ ወደ ገዳም ሄጄ መመንኮስ ፈልጋለሁ፣ ይህን ያላንቺ ፈቃድ ማድረግ አልችልም" እሷም ፈቀደችለት፣ እርሷንም በአንዱ ምኔት(የእናቶች ገዳም) አስገባት፣ በዚያም በጸጋ የተሞላች መነኩሲት ሆነች እመምኔታቸውም አድርገው መረጧት፡፡
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ስንመለስ ከተማውን ለቆ ሲወጣ የጌታ መልአክ ተገለጦለት ወደ አስቄጥስ በረሃ መራው፡፡ በአስቄጥስ በረሃ ውስጥ ካሉት ገዳሞች በአባ መቃርዮስ ገዳም ውስጥ በቅዱስ ዳሩዲ ስር መነኮሰ፡፡ ከርሱም ጋር መልካም ነገርን እየተማረ ቅዱሱ እስኪያርፍ ድረስ በርሱ ዘንድ ቆየ፡፡ ከዚያን በኃላ የጌታ መልአክ ከአባ ዮሐንስ ሐጺር ገዳም በስተምዕራብ ለራሱ በዓትን እንዲሰራ ነገረው፡፡ በዚያም ሄዶ መልአኩ እንዳዘዘው አደረገ፡፡
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

300 ወንድሞች በዙሪያው ተሰብስበው ደቀመዛሙርቱ ሆኑ፡፡
ቤተክርስቲያን እና ለራሳቸው የሚሆን አጸድ ያለው ቤት ሠሩ፣ ቅዱስ ዮሐንስም እንዴት እንደሚጸለይ እና የሌሊቱን መዝሙራት እና ውዳሴ አስተማራቸው፡፡ በአንድ ሌሊት የሠለስቱ ደቂቅን መዝሙር እየዘመሩ እያለ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ተገለጠላቸው እና ብዙ ምስጢር ገለጠላቸው፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ድንግል ማርያም ተገልጣለት :-" ይህ ለዘላለሙ መኖሪያዬ ነው፣ ካንተ ጋር እንደነበርኩ ከነርሱም ጋር እሆናለው፣ ይህ ገዳምም በስሜ ይሰየማል" አለችው፡፡ የገዳሙ ቤተክርስቲያንም በድንግል ማርያም ስም ተሰየመ፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ ከማ የሚሰራውን ከጨረሰ በኃላ በሰላም አረፈ፣ ጸሎቱ ከኛ ጋር ትሁን፣ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን፡፡

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ዛሬ የምሥራች ቀን ነውና ቀኑ ሳያልቅ እንጠቀምበት

ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም አዲስ መጽሐፍ በመንገድ ላይ ነው:: ጸሎታችሁ ብትረዳኝ እስክ አስተርእዮ ማርያም ታትሞ ይደርሳል::
@diyakonhenokhaile

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

​ዝክረ አባ ጢሞቴዎስ ባሕታዊ
(ታህሳስ ፳፫)
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ወላጆቹ ፈጣሪን የሚወዱ እና በክርስቲያናዊ ስርዓት አስተምረው ያሳደጉት ነበር፡፡ የምንኩስናን ሕይወት ይሻ ነበርና በአንዱ ገዳም መነኮሰ፡፡ የተባትሖን ሕይወት በመውደዱ ከገዳሙ አቅራቢያ ለራሱ በዓትን ሠራ፡፡ በእዚያ ቦታ የእጅ ስራ እየሰራ ለተወሰነ ጊዜ ኖረ፡፡
🐟🐟🐟🐟🐟🐟🐟🐟🐟
የመልካም ነገር ሁሉ ጠላት በመነኩሲት አምሳል የእጅ ስራውን እንደሚገዛለት ተመስሎ ቀርቦ ሊያስተው ሞከረ፡፡ በተደጋጋሚ ትጎበኘው ስለነበር ለየት ያለ ግንኙነት በመሃላቸው ተፈጠረ፡፡ በአንድ መዓድ ለምግብ ይቀመጡ ነበር፡፡ ቅዱሱ አባት ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ዲያብሎስ በኃጢአት አታሎ ሊጥለው እንደሆነ አወቀ፣ የሞትን ሰዓት እና የሚያስፈራውን ፍርድ አስታወሰ፣ በዚህም ተነስቶ ከዚያ ስፍራ ሸሸ፡፡
🐟🐟🐟🐟🐟🐟🐟🐟
እግዚአብሔርም ምንጭ ውሃ እና የተምር ዛፍ ወዳለበት ወደ ሌላ ስፍራ መራው፡፡ በዚያም በአምልኮ እና ትሕርምት ቆየ፣ የበረሃ አውሬዎች እስኪቀርቡት ድረስ በትሕርምት ሕይወቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ፡፡ በዚህም ሁኔታ ለ 30 አመታት ኖረ፣ የሰውነቱ ጸጉር አድጎ ልብስ ሆኖለት ነበር፡፡
🐟🐟🐟🐟🐟🐟🐟🐟
መልካሙን ገድል ከተጋደለ እና ስራውን ከጨረሰ በኃላም በሰላም አረፈ፡፡
ጸሎቱ ከእኛ ጋር ትሁን፣ ለአምላካችን ምስጋና ይሁን፣ ለዘላለሙ አሜን!

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሰላም

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

#ዝክረ_አበው_መነኮሳት
#ዝክረ_አበው_ባሕታውያን

ዝክረ ቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ ወፍልሰተ አጽሙ
'''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
ይህ ቅዱስ በፋርስ(ፐርሺያ) ከክርስቲያን ቤተሰቦች የተወለደ ነው።ወታደር ሆኖ እስከመቶ አለቃነት ደርሶ ነበር። በኃላ ላይ ሕይወቱን በብሕትውና ሕይወት ይመራ ዘንድ ወደደ። አለምን እና የምትሰጠውን ከንቱ ክብር በመተው በምስራቅ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ መነኮሰ። መልካም ስራው ሲታወቅ ለዚያ ገዳም ካህን ሆኖ ተሾመ።

ከዚህች ሰዓት ጀምሮ ራሱን በትሕርምት ሕይወት ጾምና ጸሎት የሚያተጋ ሆነ። በአንድ ጊዜ ለ6 ቀናት ይጾም ነበር፥ በሰባተኛው ቀን ከቅዳሴ በኃላ በረከት እና ከርጥብ ባቄላ በመመገብ አፉን ይሽር ነበር። ከዚህን በኃላ በድንጋይ(ዓምድ) ራስ ላይ ለ3 ዓመታት ኖረ። ከዕለታት በአንዱ ቀን ከዚያ ላይ እንዲወርድ በስሙ የሚጠራውን መልአክ ድምጽ ሰማ። በወረደ ጊዜ መልአኩ የብርሃን መስቀል አሳየው። ድምጹን ተከትሎ ሲጓዝ መስቀሉ በፊቱ ይሄድ ነበር፥ ከዚያም ወደ ተራሮች አደረሰው። በዚያም የሚጎበኙትን ምዕመናን የድኅነት መንገድ እያስተማረ ለትንሽ ጊዜ ቆየ።

ወደ ቁስጥንጥንያ አቅራቢያ እንዲሄድ እግዚአብሔር አነሳሳው። በዚያ ሄዶ በአቅራቢያው መንደር በድንጋይ ዓምድ ላይ መንፈሳዊውን ተጋድሎ እየተጋደለ ለ45 ዓመታት ኖረ። እግዚአብሔር የትንቢት እና ተአምራትን የማድረግ ጸጋ ሰጥቶት ነበር። ወደርሱ የሚሄዱትን ሁሉ ይፈውስ ነበር። መንፈሳዊ ተጋድሎውን ከፈጸመ በኃላ ታህሳስ 15 አረፈ። ደቀመዝሙሩ ሄዱ የዕረፍቱን ነገር ለፓትርያርኩ ነገረ። ፓትርያርኩ ከካህናት ጋር ጽናህ፥ መስቀል አስይዞ የቅዱሱ ስጋ ወዳለበት መጣ። ካረፈ በሦስተኛው ቀን(ታህሳስ 17) በዝማሬ እና በጸሎት ወደ ቁስጥንጥንያ ወሰዱት። በቤተክርስቲያን አኑረውት የሦስተኛውን ቀን ጸሎት ከፈጸሙ እና ምዕመናን ከቅዱስ ስጋው ቡራኬ ከተቀበሉ በኃላ በዕምነበረድ በተሰራ ሳጥን ስጋውን አኑረው ከቅዱሳን አጠገብ አሳረፉት። እግዚአብሔር ከስጋው ብዙ ተአምራት ገለጠ።

ጸሎቱ እና በረከቱ ከኛ ጋር ትሁን፥ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን። አሜን።

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ቅዱስ እንጦንስ የመነኮሳት ሁሉ አባት በመባል ይታወቃል፡፡ የተወለደው በላዕላይ ግብጽ በቤኒስዎፋ ከተማ በ 250 ዓም ነው፤ እንጦንስ ሃያ አመት ሳይሞላው አባቱ አረፈ፡፡ አንድ ጊዜ በቤተክርስቲያን የሚከተለው ጥቅስ ሲነበብ ሰማ
:-"...... ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ....."
(የማቴ ወንጌል 19:21)
ሰለዚህም ያለውን ሀብት ሁሉ ለድሆች አከፍፈለ፣ የምንኩስና ሕይወቱን መኖር ለመጀመር ወደ በረሃ ሄደ፡፡ ገዳሙም ቀይ ባህር ዳር ነው፡፡ በዘመናችን የምናውቃቸው ቅዱሳን እንደ አቡነ ዮስጦስ ያሉት ከዚያ የወጡ ናቸው፡፡
☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️
የተወሰኑ ዓመታትን በተጋድሎ ከኖረ በኃላ ሰዎች ሊጎበኙት፣ ጸሎቱን እና ቡራኬውን ለማግኘት ወደ እርሱ ይመጡ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ የሆነ የሩቅ ሀገር ንጉስ መልዕክተኞችን ልኮ የታመመ ልጁን መጥቶ እንዲፈውስለት ጠየቀው፡፡ መልዕክተኞቹ ለአባ እንጦንስ ስጦታ አምጥተው ነበር እርሱ ግን አልተቀበላቸውም፤ ወደዚያ ሩቅ ሀገርም ከነርሱ ጋር እንደማይሄድ ነገራቸው፡፡ ቅዱስ እንጦንስ ጸለየ፣ በዚያው ቀን በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል በደመና ተነጥቆ ወደዚያ ሩቅ ሀገር ሄደ፤ በዚያም ከአንድ ገዥ ጋር በማዕድ ተቀመጠ፡፡ ገዥው የታመሙ እና የታወሩ የቤት እንስሳት ነበሩት፣ ቅዱስ እንጦንስ ፈወሳቸው፡፡ ንጉሱም ይህን ሰማ እና ልጁን እንዲፈውስለት አባ እንጦንስን ወደ ቤቱ ጋበዘው፡፡ እርሱም ወደ ቤቱ ሄዶ ልጁን ፈውሶለት ወደ ገዳሙ ተመለሰ፡፡
☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️
በቀጣዩ ቀንም የንጉሱ መልዕክተኞች እዛው ገዳሙ ውስጥ ነበሩ፤ የአባ እንጦንስን ጉዞ አላወቁም ነበር እና ከነርሱ ጋር ሄዶ የንጉሱን ልጅ እንዲፈውስ ጠየቁት፡፡ ቅዱስ እንጦንስም እነርሱ እንዲቀድሙት እና እርሱ በኃላ እንደሚከተላቸው ነገራቸው፡፡ ራሱን ከውዳሴ ከንቱ ፈተና ለማራቅ ይህን አላቸው፡፡ሰዎቹም ከብዙ ቀናት በኃላ ተጉዘው ወደ ቤተ መንግስቱ ደረሱ፡፡ በዚያም የተደረገውን ነገር ሁሉ ሲረዱ ለዚህ ተዓምር ምስክር በመሆናቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡

የአባታችን አባ እንጦንስ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ አሜን፡፡
〰〰〰〰〰〰〰〰〰
➋➋.
@hiwotemenekosat
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ቅዱስ ቴዎፍሎስ መነኩሴው

ከሮም ደሴቶች የአንዱ ንጉስ ብቸኛ ልጅ ነበር፡፡ በክርስቲያናዊ እምነት እና እውቀት በደንብ ነበር ያሳደገው ፤ ፲፪ ዓመቱ እያለ በቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዕብራውያን መልዕክት ላይ ይህን አነበበ:-

"......ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤ እነርሱም ይጠፋሉ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም"
"___(ወደ ዕብራውያን ምዕ. ፩፤፲-፲፪)
በመቀጠልም የሐዋርያውን የመጀመሪያ መልዕክት ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች የሚከተለውን አነበበ:-"
ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወዳለሁና፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የጸጋ ስጦታ አለው፥ አንዱ እንደዚህ ሁለተኛውም እንደዚያ።
ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ። እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው፤ ምዕ. ፯፤፯,፰)
🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸
በወንጌልም ጌታ:-" ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው።"
(የማቴ ወንጌል 19:21)
የሚለውን አነበበ፡፡ ቴዎፍሎስ የአባቱን ቤት እና የራሱን ንብረት ትቶ ማንም ሳያየው ወጣ፡፡ከአንዱ ገዳም ወደ አንዱ እያለ እስክንድርያ ደረሰ፡፡ ከዚያም ተነስቶ ወደ "መስታወት ገዳም" ሄደ፡፡ የገዳሙ አበምኔት ቅዱስ ቪክቶር አይቶት እና በመንፈስ ተረድቶ የነገስታት ልጅ መሆኑን አወቀ፡፡ በሚገባ ተቀብሎት ከባረከው በኃላ ታሪኩን ጠየቀ፡፡ ቅዱስ ቪክቶር ታሪኩን ከሰማ በኃላ እጅግ አደነቀ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነ፣ በገዳሙም ተቀበለው፡፡ ስኬታማ፣ ፍሬያማ እና የጸና መንፈሳዊ ሕይወት እንደሚመራ ባየ ጊዜ ቅዱሱን አስኬማ አለበሰው፡፡
🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸
ከ ፲ ዓመታት በኃላ በቴዎፍሎስ አባት የተላኩ ወታደሮች መጥተው በኃይል ይዘውት ሄዱ፡፡ ወደ አባቱ ባመጡት ጊዜም አባቱ ሊያውቀው አልቻለም፤ የትሕርምት ሕይወት ገጽታውን ቀይሮት ነበርና፡፡ ቅዱሱም አባቱን ማስተማር ጀመረ፤ ስለ ሕይወት፣ ስለ ሞት እና ፍርድ ሰበከው፡፡ የቅዱሱ ቃላት የአባቱ ልብ ላይ ምልክት ተው፣ አባቱም ከራሱ ላይ ያለውን አክሊል አውልቀ፤ ዙፋኑንም ለወንድሙ ተወለት፡፡ ከሚስቱ እና ልጁ ቴዎፍሎስ ጋርም ወደ "መስታወት ገዳም" ሄደ፡፡ በዚያም ንጉሱ መንኩሶ ከልጁ ጋር ቆየ፡፡ የቅዱስ ቴዎፍሎስ እናትም በእናቶች ገዳም መነኩሴ ሆነች፡፡ ሁላቸውም በምናኔ ሕይወት በጽድቅ ስራ እና አምልኮ እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ኖሩ፡፡ ተጋድሎአቸውን ከፈጸሙ በኃላ በሰላም አረፉ፡፡
ጸሎታቸው ከኛ ጋር ትሁን፤ አሜን!

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

https://selfforgingman.wordpress.com/2022/12/15/becoming-like-god/

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

[መኖር እንዲህ ነበር]

ገና ሲወለዱ ይችን ምድር ሲያዩ፣
የዓለምን ጣዕምና ምሬቷን ሳይለዩ ፣
መኖር እንዲህ ነበር ጌታን ብቻ እያዩ፣
ገና በማለዳ ገና በጠዋቱ ፣
ገና ቀትር ሳይሆን ሳይመጣ ምሽቱ፣
ገና ሳይሰለጥን ጨለማው ሌሊቱ፣
ገና ብርሃን ሳለ ሥራን ሳይታክቱ ፣
መኖር እንዲህ ነበር እንዲያርግ ጸሎቱ፣
በዓለም ያለውን ዓለምን ሳይወዱ ፣
ዓለምን አግብቶ ሌላ ዓለም ሳይወልዱ፣
መኖር ይሻል ነበር ለአንተ መሰደዱ ፣
በጸሎት በስግደት በፆም ተጋድሎ፣
ሰይጣንን ድል ነስቶ ወደ ጥልቁ ጥሎ ፣
መኖር እንዲህ ነበር አንተን ብቻ ብሎ ፣
ገዳሙ ገዳሙ ሰምተሃል? ገዳሙ ፣
ለልማት ይመንጠር ብሎሃል ዓለሙ ፣
በዚህ ትስማማለህ? መልስ ስጥ ገዳሙ ፣
ልማት አይደለም ወይ? ጸሎቱና ፆሙ
ይህንን ከመስማት ደግሞም ከማየት ፣
የዓለምን ጥላቻ ኩርፊያ ለመርሳት፣
ለኃጢአት ሞተን ኖረን ለሕይወት፣
መኖር እንዲህ ነበር መንኖ በእውነት ፣

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

Watch "የበረሀው ምስጢር ክፍል 2፡ ልብስሽን ልበሽና ተከተይኝ እውነተኛ ታሪክ #Emaretube |Ethiopian News |Seifu on Ebs| Besintu |" on YouTube
https://youtu.be/Hh0562t4oKI

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

1 ወንድማችን አብራርቶ መልስ ሰጥቷል ጥያቄዎቹም ግልፅ ቢሆኑ በቀላሉ ለመረዳት ይስችላሉ።
2, በምንኩስና ሕይወት ውስጥ የሚታዩት ችግሮች(ፈተናዎች)
ከሁለት ይመጣሉ
፩ ከግል ፍላጎት(ልማድ , ያለፈ አኖኖር) ወዘተ...
፪ ከጠላት ፈተና
አንድ ሰው በዓለም(በከተማ) ሳይኖር በገዳም አድጎ ወደ ምኩስና ሕይወት ሊገባ ይችላል ይህ ሲሆን ለአለም የሚኖረው ዕውቀት ትንሽ ስለሚሆን (በትውስታ በቀደመ ልማድ ወዘተ) በሳብ ይቀንሳል ምክንያቱም ሰው የሚያየው የሚሰማው የሚዳሰው በአጠቃላይ የስሜት ህዋሳቱ ውጤት ወደ ውስጡ ይገባል ከውስጥ የገባ ደግሞ ለመመለስ ቅርብ ይሆናል...
ስለዚህ መንምኩሴ ፫ ነገሮችን ከማድረግ ወደኋላ ማለት የለበትም
፩ ከጸሎት
፪ ከስራ / እንዳቅም እንደችሎታ ሽመና እርሻ እንስሳትን ማገድ መቁጠሪያ መፈልፈል ....
፫ ከመጽሃፍት / ከስርዓት ከገድላት ወዘተ.../

፪ ከክፉ ጠላትም ችግር (ፈተና) ይመጣል
ከፈተናውም ዋናው ከገዳም ውጡ ውጡ ሚል ነው/ሌሎች ፈተናዎች እንዳሉ ሆኖ/ ይህም ለክፉ ሃጢያት ለማመቻቸት ነው አሳ ከባህር ወጥቶ እንደማይኖር ሁሉ መነኩሴም ከገዳም ባይወጣ ይመከራል እስካልታዘዘ ድረስ /በመፅሐፍተ መነኮሳት ተከልክሎአል/

3 አንድ ሰው ለመመንኮስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት ማወቅ ይችላል ? ከሆነ ጥያቄው
ራስን በጥልቅ በመመርመር ነው የእግዚአብሔር ፈቃድ በአንድም በሌላም መንገድ ይታወቃል አንድ ሰው ከወር ውስጥ 20 ቀን ትዳርን እያሰበ 6 ቀን ምንኩስናን 4 ቀን ሌላን እያሰበ የሚኖር/የነዚህ ፍላጎት ከፅኑበት/ ምንኩስ የጠላት ፈተና ሊሆን ይችላል ግን ደግሞ እርግጠኛ ለመሆን ገዳም ከመግባት በፊት ከ2-3 አመት ዓላማየ ብሎ ይዞ የምንኩስናን ስርዓት እየፈፀሙ እራስን ገዳም እንደገቡ አድርጎ በፍፁም ታማኝነት መመርመር ተገቢ ነው።
ለምሳሌ
ብዙ ማውራትን መቀነስ
ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል
ለሊትን በትጋት(በመስገድ ...ማሳለፍ)
ከተመቸ የፍራሽ አልጋ ላይ አለመተኛል... ወዘተ
በእነዚህ ፈተናዎች እራስን ከመረመሩ በኋላ በገዳምም ከመመንኮስ በፊት በእርድና/በረጅነት አገልጋይነት/ መቆየት ገዳም ገብተው ተሎ ካልመነኮሱ አንዱ ትልቅ አባት ውስጥ የሚጠሩት ከአራት ቀን በፊት በገድል ወንድማችን ያዘከራቸው አባታችን በግዑ ናቸው በገዳም እንደ ግዳማውያን ስርዓት ሲኖሩ እናም ሲበቁ ምንኩስናን አልተቀበሉም ሊያርፉ ጥቂት ጊዜ ሲቀራቸው ነው የመነኮሱት።

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

1.ምንኩስና ህይወት በዘመነ ሊቃዉንት
2.በምንኩስና ህይወት ጊዜ የሚታዩ ችግሮች
3.ፈቃደ እግዝአብሔር በምን ይታወቃል?

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

አባ ዮሐንስ አበምኔት
(ሊቀ ካህን ዘገዳም አስቄጥስ)
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

በቅዱስ መቃርዮስ ገዳም ሊቀካህን ሆኖ ሲሾም ሙሉ በረሃው በትምህርቱ በራ፣ ለብዙዎች ቅዱሳንም አባት ሆነ፡፡ ከነዚህም ቅዱሳን መሃል አንባ ገዋርጋ እና አንባ አብርሃም ሁለቱ ከዋክብት፣ አንባ ሚና የታማይ ጳጳስ፣ አንባ ዘካሪያስ እና ለብዙ ነፍሳት መዳን ምክንያት የሆኑ ብዙ ቅዱሳን ይገኙበታል፡፡
🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇
ከቅድስናው እና ጽድቁ የተነሳ ቅዳሴ ቀድሶ በሚያቆርብበት ሰዓት በኃጢአት ውስጥ እና ጽድቅ ውስጥ ያሉትን ይለይ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ በመሰዊያው ላይ መላዕክት ክርስቶስን ከበውት ይመለከት ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ከካህናት አንድ መጥፎ ምግባር ያለው ካህን ርኩሳን መናፍስት ከበውት ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣ ተመለከተ፡፡ ወደ ቤተክርስቲያኑ በርም በቀረበ ጊዜ የጌታ መልአክ ነበልባላማ ሰይፍ ይዞ ከመቅደሱ በመውጣት ርኩሳን መናፍስቱን አባረራቸው፡፡ ካህኑ ወደ ቤተክርስቲያኑ ገብቶ ቀድሶ ካቆረበ እና ቅዳሴውን ከፈጸመ በኃላ ልብሰ ተክህኖውን አውልቆ ከቤተክርስቲያኑ ሲወጣ ርኩሳን መናፍስቱ ተመለሱበት፡፡ ይህን አስመልክቶ ቅዱስ ዮሐንስ ወንድሞችን እንዲህ አላቸው:- "የቤተክርስቲያንን ምስጢራት በመፈጸም በኃጢአተኛ እና ጻድቅ ካህን መካከል ልዩነት የለም፡፡ ምክንያቱም የክርስቶስ ስጋ እና ደም የሚለወጠው ለህዝቡ ሲባል ስለሆነ፡፡" እንዲህም ብሎ ምሳሌ መሰለላቸው:- "የአንድ ንጉስ ምስል ከወርቅ የተሰራ ማህተምም ሆነ ከብር ከተሰራ ማህተም ላይ ሲቀረጽ ማህተሙ አንድ እንደሆነ ሁሉ ክህነትም በኃጢአተኛው እና ጻድቁ ካህን አንድ ነው፣ ጌታ ሁሉንም እንደስራው ይከፍለዋል፡፡"
🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇
ቅዱሱ ብዙ መከራዎች ደርሰውበታል፡፡ በርበሮች ማርከው ወደ ሀገራቸው ወስደውታል፣ በዚያም ብዙ አመት በስቃይ ቆይቷል፡፡ በምርኮ ወቅትም የደብረ ቀለሞኑን አበምኔት ቅዱስ ሳሙኤል አግኝቷል፡፡ በኃላም በእግዚአብሔር ጸጋ ወደ ገዳሙ ሊመለስ ችሏል፡፡ ከዚህ አለም የሚለይበትን ጊዜ በራዕይ ከተረዳ በኃላ ወንድሞችን ጠርቶ የጌታን ትዕዛዛት እንዲጠብቁ እና በቅዱሳን አባቶች መንገድ ተጉዘው መልካሙን የመንግስተ ሠማይ ፈንታ እንዲጋሩ አዘዛቸው፡፡
ወዲያው ሕመም ተሰማው፣ የቅዱሳን ማህበርም ነፍሱን ለመውሰድ ሲመጡ ተመለከተ፣ ነፍሱንም በጌታ እጅ ሰጠ፡፡ ወንድሞችም ስጋውን ወደ ቤተክርስቲያን ተሸክመው አስገቡ፣ ለርሱ ስላላቸው ፍቅር እና በቅድስናው ስላላቸው እምነት ከመግነዙ ጥቂት ለራሳቸው አስቀሩ፣ መግነዙም የብዙ ሕመሞች መፈወሻ ምክንያት ነበር፡፡ ይህ አባት በምድር ላይ ለ ፺ አመታት ኖረ፡፡
ጸሎቱ ከኛ ጋር ትሁን፣ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን፣ ለዘላለሙ አሜን!

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

እንኳን ለ2015 ዓ.ም ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

ሰው ለመሆንህ ሰላም እላለሁ !

ሰው ፣ ሰው መሆንን ሲጠየፍ አንተ ግን ሰው ሆንህ ። ሰው አምላክነትን በሕግ አፍራሽነት ሲሻ ፣ አንተ ግን በፍቅር ሰው ሆንህ ። ሰው የሌለውን አምልኮት ሲያስስ ፣ አንተ ግን የሌለህን ሰው መሆን ገንዘብህ አደረግህ ። ሰው የሌለውን ከፍታ ሲናፍቅ ፣ አንተ ግን የማይገባህን ዝቅታ ሰው በመሆን ወረስህ ። ሰው ጌትነትን ሲፈልግ ፣ አንተ ግን በባሪያ መልክ ተገለጥህ ። ሰው ፣ ሰውን ሲሸሸው ፣ አንተ ግን ሰውን በፍቅር ተከተልከው ። ሰው ፣ ሰውን ለመርዳት ሰው መሆኔ በቂ አይደለም ሲል ፣ አንተ ግን ሰው ለማዳን ሰው መሆን ያስፈልጋል ብለህ መጣህ ። ሰው ከሆነችው ከባሕርያችን መመኪያ ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ፣ ከንጽሕትና አዛኝ ከምትሆን እናትህ ሰው ሆንህ ። ሰው ከእናቱ ማኅፀን ሲወጣ ቀዳማዊ ልደቱ ነው ፤ አንተ ግን ከድንግል ማርያም ስትወለድ ዳግማዊ ልደትህ ነው ። አዳም ከመሬት ፣ ሔዋን ከገቦ አዳም ፣ አቤልና ቃየል ከዘር ከሩካቤ ተወለዱ ። ያንተ ሰው መሆን ያንተ ልደት ግን ከድንግል ነው ። ልዩ ለሆነው ልደትህ ሰላም እላለሁ ! ለዳግም ልደት ታበቃን ዘንድ ዳግም ለተወለድከው ፣ ሰውነትን ታከብረው ዘንድ ሰው ለሆንከው ፣ ደናግላንን ከፍ ታደርጋቸው ዘንድ በድንግልና ለተወለድከው ፣ ለምስኪኖች ታዛ ትሆን ዘንድ በበረት ለወደቅኸው ክርስቶስ ሰላም እላለሁ !

ክርስቶስ ሰው ሆነ ፤ ሰዎች ሆይ ደስ ይበለን !

.

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

#ዝክረ_መነኮሳት_ወመነኮሳይያት
#ዝክረ_መነኮሳት_ተነሳሕያን


የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ
+ + + + + +

አባ በግዑ በመጀመሪያ ሽፍታ የነበረ ሲሆን በመንገድ ላይ ንብረት የያዘን ሰው ማንንም የማያሳልፍ ቀማኛ ሰው ነበር፡፡ ከኃይለኛነቱ የተነሳ ሕዝቡም ሁሉ ይፈራው ነበር፡፡ በእጁ ሰይፍና ጦር ይዞ ሊዘርፍ ወደ ወደደው ሀገር ይገባል፡፡ እየዘረፈ በሚያገኘው ገንዘብም ራሱን በተለያዩ ምግቦችና መጠጦች ያስደስት ነበር፡፡ ባማሩ ልብሶችም ይዋብ ነበር፡፡ ገንዘቡ የተወሰደበት ሰውም እርሱ እንደወሰደበት ባወቀ ጊዜ ዳግመኛ መጥቶ የተረፈውን ቀምቶ እንዳይወስድበት ምንም አይከሰውም ነበር፡፡ በጉልምስናው ኃይለኛና ብርቱ ስለነበር ወደ እርሱ ማንም አይቀርብ ነበር፡፡
በእንደዚህ ያለ የውንብድና ሥጋ ብዙ ዓመታት ከኖረ በኋላ አባ በግዑ በስም ክርስቲያን ነበረና ከዕለታት በአንደኛው ቀን መንፈስ አነሳስቶት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደ፡፡ ካህኑም ባየው ጊዜ ከመንገድ ገለል አደረገውና ‹‹የሕይወት ዘመንህን ሁሉ በከንቱ አሳለፍክ ዛሬ ስማ ልንገርህ፣ በዘመንህ ፍጻሜ እግዚአብሔር ይጎበኝሃል፣ መንፈስ ቅዱስም ያድርብሃል፣ ፍጹም መነኩሴ ትሆናለህ፣ በብዙ መከራና ተጋድሎ ትኖራለህ በዚያም የነፍስህ መዳኛ ይሆናል፣ እግዚአብሔርንም ደስ ታሰኘዋለህ›› አለው፡፡ ከዚህም የበዛውን ብዙ ነገር ነገረው፡፡

ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ቁርባን ተቀበለ፡፡ ወደቤቱም ከተመለሰ በኋላ ካህኑ የነገሩትን እያሰበ ‹‹እስከመቼ በስንፍናዬ እኖራለሁ? እስከመቼስ የነፍሴን መዳኛ ሳላስብ እኖራለሁ? …›› እያለ አሰበ፡፡ ከዚህም በኋላ ከዘመዶቹ ተለይቶ ከሀገሩ ወጥቶ ሄደና ወደ ባሕር ዳርቻ ደርሶ የቅዱስ እስጢፋኖስን ቤተ ክርስቲያን እጅ ነሣ፡፡ ከመነኮሳትም ማኅበር ገብቶ እነርሱን ማገልገል ጀመረ፡፡ አባ በግዑ በእግዚአብሔር ጥሪ ወደ ልቡ ተመልሶ ከመነነ በኋላ ግን እስከሞተበት ዕለት ድረስ የላመ እህል ሳይቀምስ ኖረ፡፡ ምግቡን የዛፍ ፍሬና ሜዳ ላይ የሚበቅል ቅጠል አደረገ፡፡ ዓቢይ ጾም ሲመጣም ከሰኞ እስከ ቀዳሚት ሰንበት ምንም ሳይቀምስ የሚጾም ሆነ፡፡ ውኃንም ሳይጠጣ ኖረ፣ ማንም ሰው ሳያውቅበት ለ5 ወር ምንም ውኃ ሳይጠጣ ተቀመጠ፡፡ ከ5 ወር በኋላም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደ አባ በግዑ መጣና ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሰላም ለአንተ ይሁን! በምን ትታወካለህ? ምንስ ያሳዝንሃል? ››አለው፡፡ አባ በግዑም ‹‹ጌታዬ ከውኃ ጥም የተነሣ በጣም ስለተጨነቅሁ ነው›› አለው፡፡ መልአኩም ነጥቆ ወደ ገነት ወሰደውና ከገነት ቅጠል አንሥቶ አቀመሰው፡፡ ወዲያም የአባ በግዑ ሰውነት ታደሰች፡፡ ከዚህም በኋላ ‹‹ውኃ ሳልጠጣ ተጋድሎዬን እፈጽም ይሆን!›› የሚለው የኅሊና መታወክ ከእርሱ ጠፋለት፡፡

ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አባ በግዑ ለሚወደው ለአንድ ወዳጁ ለማንም እንዳይናገር በእግዚአብሔር ስም ካስማለው በኋላ ለ5 ወር ምንም ውኃ እንዳልጠጣ ምሥጢሩን ነገረው፡፡ ያ ወዳጁም ይህን ሲሰማ ደንግጦ አለቀሰ፡፡ አባ በግዑም አብሮት አለቀሰ፡፡ ወዳጁም ‹‹እስከዛሬ ከውኃ የተከለከለ በማን ዘንድ ሰማህ? አሁንም ቅዱሳን መነኮሳትና አበ ምኔቱ አያምኑህም፡፡ ይህን ምሥጢር ዛሬ ብሸሽግ በመጨረሻ ይገለጣል፡፡ ሕዝቡ፣ ነገሥታቱና መኳንንቱም ይህን ነገር ይሰማሉ ነገር ግን አያምኑም፡፡ አሁንም የምነግርህን ስማኝና ትኅርምቱን ትተህ ውኃ ጠጣ›› አለው፡፡ የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑም ‹‹የነገርከኝ ሁሉ እውነት ነው ሐሰት የለውም ነገር ግን እኔ ከዚህ በኋላ እስክሞት ድረስ ዳግመኛ ውኃ እንዳልጠጣ ስለ እግዚአብሔር ትቻለሁ፡፡ ሰዎች ባያምኑ እኔ ምን ገዶኝ፣ ነገር ግን በዚህ ገድል እግዚአብሔር ረዳት ይሆነኝ ዘንድ ጸልይልኝ›› አለው፡፡

ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ ብረት አመጣና ሰንሰለቶችን ይሠራለት ዘንድ ለአንጥረኛ ሰጥቶ አሠራ፡፡ ያንን ወዳጁን ጠራውና እጆቹንና እግሮቹን በብረት ችንካር እንዲያስረው አዘዘው፡፡ ‹‹አበ ምኔቱን ጥራልኝ›› አለውና ጠራለት፡፡ አባ በግዑም አበ ምኔቱ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ሲመጣ በፊቱ ሰገደለትና ‹‹አባቴ ሆይ! የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እፈጽም ዘንደ በላዬ ላይ ጸልይልኝ›› አለው፡፡ ‹‹ከዛሬ ጀምሮ ከበዓቴ አልወጣም፣ ሰውም ወደኔ አይገባም›› አለው፡፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐም በላዩ ከጸለየለት በኋላ ‹‹ለእኔም ጸልይልኝ›› አለው፡፡ አባ በግዑም በቅዱስ ሚካኤል በዓል ቀን በአባ ኢየሱስ ሞዐ እጅ ቁርባንን ከተቀበለ በኋላ እጆቹንና እግሮቹን በብረት ችንካር ታስሮ ብቻውን ዘግቶ በጽኑ የተጋድሎ ሕይወት ኖረ፡፡ በዓቱንም ዙሪያውን መውጫ መግቢያ እንዳይኖረው መረገው፡፡ ለምግብ የሚሆነውን የዛፍ ፍሬና የሜዳ ቅጠል ማስገቢያ የሚሆን ትንሽ ቀዳዳን አበጃና ያ ወዳጁ ያስገባለታል፡፡ አባ በግዑም ያንን በሦስት ቀን አንድ ጊዜ ብቻ ይመገባል፡፡
የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ በእንዲህ ዓይነት ጽኑ በሆነ የተጋድሎ ሕይወት ሲኖር ሰውነቱ ላይ ከቆዳውና ከአጥንቱ በቀር የሚታይ ነገር እስኪጠፋ ድረስ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ፡፡ ውኃንም እስከ ሰባት ዓመት ድረስ አልጠጣም፡፡ መቆምም አይችልም ነበርና መነኮሳቶቹ ለቁርባን በቃሬዛ አድርገው ወደ ቤተ ክርስቲያን ይወስዱት ነበር፡፡

የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ በእንደዚህ ዓይነቱ ለመስማት በሚከብድ እጅግ የበዛ ጽኑ ተጋድሎ ካደረገ ከብዙ ድካም በኋላ በዚህች ዕለት ታህሳስ 27 ቀን ዐረፈ፡፡
በዕረፍቱ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያምና ከአእላፍ ቅዱሳን መላእክቶቹ ጋር መጥቶ እንዲህ የሚል ቃል ኪዳን ገባለት "ስምህን ለጠራ ፣መታሰቢያህን ላደረገ፣ ወደ ተቀበርክበት ቦታ ሄዶ ለተሳለመ፣ በበዓልህ ቀን ምፅዋት ለሰጠ እስከ ሰባት ትውልድ እምርልሃለሁ ዳግመኛም በጸሎትህ አምኖ መልካም ሥራ የሠራ የገድልህን መጽሐፍ የሰማ ሁሉ የእሳቱን ባሕር በግልጽ ይለፍ። ወደ መንግሥተ ሰማያትም ይግባ" አለው።
የእግዚአብሔር ሰው የአባ በግዑ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
ምንጭ፦ከገድላት አንደበት(ገድለ ቅዱሳን)

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

https://youtu.be/QJUfx-bocNo

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የልደት በዓል አደረሰን፥ እግዚአብሔር አምላክ በአገልጋዩ ጸሎት ይማረን፥ አሜን።

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ዜና ሥላሴ ፣ ድርሣነ ፅዮን መጽሐፍ ካላችሁ እስኪ ላኩልኝ....?

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

https://youtu.be/UUPiFzMwsdM

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

#ዝክረ_አበው_መነኮሳት
#ዝክረ_ሊቃውንት_ቅዱሳን

ቅዱስ ጎርጎርዮስ
[የአርማኒያውያን ፓትርያርክ]

በዚህች ቀን የአርማኒያውያን ፓትርያርክ ቅዱስ ጎርጎርዮስ የሰማዕትነቱን መታሰቢያ እናደርጋለን። እርሱም ደሙን ሳያፈስ ሰማዕት የሆነ ነው[ሰማዕት ዘእንበለ ደም]። በ270 ዓም በአረማዊው ንጉስ ድርጣድስ ዘመን ራሱን የሀገሪቱ ባሪያ አድርጎ ነበር(ፓትርያርኩ)። ንጉሱ ለጣዖታቱ ዕጣን ሊያቀርብ ወደ ቤተ ጣዖቱ ሲመጣ ቅዱሱም አብሮት ዕጣኑን እንዲያቀርብ ጠየቀው፥ ነገር ግን ቅዱሱ እንደማያረገው ነገረው።

ንጉሱ ብዙ ጽኑ መከራዎችን ካደረሰበት በኃላ ወደ ጉድጓድ አስጣለው። ቅዱሱም በዚያ ለ15 ዓመታት ኖረ። በጉድጓዱ አጠገብ የምትኖር አንዲት መበለት በራዕይ ዘውትር ህብስት(ዳቦ) እንድትሰራ እና ወደዚህ ጉድጓድ እንድትጥል ተነገራት፤ ይህንንም ለ15 ዓመታት ቀጠለች።

ከዚህ በኃላ እንዲህ ሆነ፤ ንጉሱ ደናግላኑን ቅድስት አርሴማ፣ ቅድስት አጋታን(ጋባታ) እና ከነርሱ ጋር ያሉትን ጓደኞቻቸውን ሁሉ አስገደለ[መስከረም 29]። ቅድስት አርሴማን ለማግባት ሽቶ ነበርና በመገደሏ አብዝቶ ተጸጸተ፥ አዕምሮውንም ሳተ። ለእህቱም በሕልም እንዲህ ተብሎ ተነገራት፦ "ጎርጎርዮስን ከጉድጓዱ ካላወጣቹት ወንድምሽ ሊድን አይችልም"።
ቅዱሱን ከጉድጓዱ አወጡት፥ በንጉሱም ላይ ጸለየ፤ ከታመመበትም ዳነ። ከዚህን በኃላ ንጉሱ ክርስቲያን ሆኖ የሰማዕቷን ቅድስት አርሴማ አጽም እና ከርሷ ጋር የነበሩትን አጽም አስፈልጎ አጽማቸውን በውስጡ አኑሮት ቤተክርስቲያን ሰራ።

የፓትርያርኩ ጸሎት እና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን። ለዘላለሙ አሜን።

@hiwotemenekosat

,

Читать полностью…
Subscribe to a channel