ሰይጣን አንድን ኃጢአት ሊያሠራን ሲፈልግ ቀድሞ ስለ እግዚአብሔር መሐሪነት በሰፊው ይሰብከናል። ያን ኃጢአት ከፈጸምን በኋላ ደግሞ ስለ እውነተኛ ፈራጅነቱና ምንም ቢሆን ከቁጣው የማናመልጥ መሆኑን ከቀድሞው ይልቅ እየጮኸ ይነግረናል። በመጀመሪያው ስብከቱ ኃጢአትን እንዳንቃወም ሰነፎች ያደርገናል። በሁለተኛው ስብከቱ ደግሞ ንስሐ እንዳንገባ ተስፋ ያስቆርጠናል።
ይህ የተገለባበጠ ስብከት "የሰይጣን" ነው። ሰው በኃጢአት ከመውደቁ በፊት ሊያስብ የሚገባው የእግዚአብሔርን ፈታሒነት (ፈራጅነት) ሲሆን በኃጢአት ከወደቀ በኋላ ግን ማሰብ ያለበት የእግዚአብሔርን መሐሪነት ነው።
ፈታሒነቱ ኃጢአትን እንዳንሠራ ይጠብቀናል፤
መሐሪነቱ ንስሐ እንድንገባ ያቀርበናል፤
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
selam@dnabel.com
/channel/Dnabel
አዲስ አበባ
ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com
"በፈጣሪ መንበር ዙሪያ የሚቆሙ የሰማይ ካህናት አክሊለ ክብራቸውን አውርደው በመንበሩ ፊት ይሰግዳሉ:: መብረቀ መለኮቱ በተገለጠ ጊዜም በፍርኃት ይንቀጠቀጣሉ:: ግሩም ባሕርየ ሥላሴን ሊቋቋመው የሚችል ፍጡር የለምና::"
✍️አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
...
አንድ ጊዜ ካይሮ በሚገኘዉ የሴቶች ገዳም በሚያስተዳድርበት ጊዜ የነዳያኑን አመጋገብ ለማየት ሲሄድ ለእነርሱ ከቀረበዉ ምግብ ይልቅ ለእርሱ የቀረበዉ ምግብ የተለየ እና የተሻለ ሆኖ አገኘዉ ይህ ነገር ስላላስደተዉ መጋቢዋን መነኩሲት ከምድቧ አሰናበታት፡፡አንድ ቀን ደግሞ ሃና ናክላ የተበለ ሀብታም አባታችን ለአባ አብርሐም ዶሮ እና ሌሎች ልዬ ልዬ ጥሩ ጥሩ ምግቦችን አዘጋጅቶ እንዲላክ አደረገ ነገር ግን አባ አብርሐም የአካባቢውን ድሆች እንዲሰበሰቡ አደረገ ከዚያም ሁሉንም ጋበዛቸዉ እያንዳንዱ ደሐ መመገቡን ቆሞ አይቶ ካረጋገጠ በኋላ እርሱ ጥቂት አትክልት በልቶ ተኛ፡፡ሌላ አልተመገበም፡፡በገዳሙ የሚገኙት ሊቃነ ጳጳሳት በሚያዘጋጁት አጋቢ(አጋፔ የፍቅር ገበታ)ላይ ለሐብታሞቹ የተጠሰ ዓሣ ለድሆቹ ደግሞ የተቀቀለ ዓሣ ቀረበ ይህንን ያስተዋለዉ አባ አብርሐም በጣም ተቆጥቶ የተጠበሰዉ ዓሣ እና የተቀቀለዉ ዓሣ እንዲደባለቅ አዘዘ ቀጥሎም እንዲህ አለ"""የተደባቀውን ዓሣ ለመመገብ የሚመኝ ሁሉ ይመገብ እግዚአብሔር ሐብተታም ደሐ ትልቅ ትንሽ አይልም አይለይም ሁሉ በእርሱ ዘንድ እኩል የአዳም ልጆች ናቸዉ፡፡""" አለ ይህን የተመከቱት ነዳያን ወዳጆቹ በእውተኛ አባትነቱ ሲደሰቱ ሀብታሞቹ ደግሞ በመንፈሰ ጠንካራነቱ ለድሐ ባለዉ ፍቅር የተደባለቀውን ዓሣ ቅቅል እና ዓሣ ጥብስ በደስታ ተመገቡ፡፡ አንዲት ሴት ስለችግሯ ባጫወተችዉ ጊዜ ትራሱ ስር ገንዘብ ሲፈልግ አጣ ከዚያም አንድ ወዳጁ ያመጣለትን ያንገት ልብስ አዲስ ያንገት ልብስ አውጥቶ ሰጣት(አዲስ ልብስ ገዝተዉ ሲሰጡት አይለብስም፡፡አሮጌ ብቻ ነዉ የሚለብሰዉ፡፡) ያንን ልብስ ወስዳ ሸጠችዉ የገዛዉ ደግሞ ያ ወዳጁ ነበር ገዝቶ ወደ አባ አብርሐም ቤት መጣ እና """አባታችን የሰጠሁን ሻርፕ የት አደረክኸዉ""" አለዉ አባታችን መልሶ """ላይ ቤት አስቀምጨዋለሁ""" አለዉ ወዳጁም ይኸዉ እንደገና ከሌላ ሰዉ ለይ አግኝቼ ገዛሁት አለዉ አባ አብርሀምም መልሶ"""ሙሉ ዋጋውን ነዉ የሰጠሃት???""" አለዉ """"አዎ ሙሉ ዋጋውን ነወዉ የሰጠኃኋት አላስከፋኋትም፡፡"""አለዉ መልሶ የአንገት ልብሱን ሰጥቶት ሄደ፡፡ በሌላ ጊዜ አንድ ሐብታም እጅግ ውድ ለስላሳ የሆነ የአንገት ልብስ ገዝቶ ሰጠዉ እንደ ተለመደዉ አስቀመጠዉ እና ከዚያም አንድ ገበሬ በብርድ ሲንቀጠቀጠጥ አየዉ ጭንቅላቱን እየነቀነቀ """" ወይ ጉድ ይህህን ያንገት ልብስ እንደሚያስፈልግ ያወቀ እግዚአብሔር ነዉ ያዘጋጀልህ""""ብሎ አውጥቶ ሰጠዉ፡፡ያ ገበሬ በጠዋት ያንገት ልብሱን ሲያየዉ ሐብታሞች የሚለብሱት ነዉ ወዲያውኑ ሸጦ ለእርሱ ርካሽ ጀለቢያ ገዛ የያንን የገዛዉ ደግሞ ያ መጀመሪያ የገዛዉ ሐብታም ነበር፡፡እንደገና ይለብሰዋል በሚል ተስፋ እንደገና ገዝቶ ሰጠዉ፡፡ አባ አብርሐም ተቀብሎ እግዚአብሔር ያዘዘለት ተረኛ እስኪመጣ ድረስ በትራሱ ስር አኖረዉ
...
@hiwotemenekosat
አባታችን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ልጆቼ እስቲ ፍቀዱልኝና አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ይለናል።
#ምን_ፍሬ_አፈራችሁ?
ብዙውን ጊዜ ቤተክርስቲያን ትመላለሳላችሁ። መልካም ነው ግን ምን ለውጥ አመጣችሁ? ምን ፍሬ አፈራችሁ? ታገለግላላችሁን ከአገልግሎታችሁ ምን ረብሕ አገኛችሁ? ጥቅምን ካገኛችሁ በእውነት ምልልሳችሁ የብልህ ሰው ምልልስ ነበር ማለት ነው።
ነቢያት ፣ሐዋርያት ፣ወንጌላውያን እንዲህ እያስተማሩን ሳለ የማንለወጥ ከሆነ ግን የእስከ አኹን ምልልሳችን የአይሁድ ምልልስ ነበር ማለት ነው። አይሁዳዊያን ሕገ ኦሪትን የተሰጣቸው ኃጢአታቸውን በእርሷ መስታወትነት አይተው ንስሐ እንዲገቡባት ነበር። እነርሱ ግን የንስሐ ፍሬ ሳያፈሩባት እንዲሁ ይመኩባት ነበር። ስለሆነም ለህይወት የተሰጣቸው ሕግ ሞት ኾና አገኟት። እኛም እንዲ ለኩነኔ ያይደለ ለጽድቅ የተሰጠችን ወንጌል ፍሬ የማናፈራበት ከኾነ ከአይሁዳዊያን የባሰ ቅጣት ትፈርድብናለች ።
እስኪ ምሳሌ ምስዬ ላስረዳችሁ።አንድ የሚታገል ሰው ከተጋጣሚውን እንደምን ማሸነፍ እንዳለበት ልምምድ የሚያደርግ ከኾነ ክህሎቱ ይዳብራል። ተጋጣሙውንም በቀላሉ ማሸነድ ይችላል። በየጊዜው የሚያነብና እራሱን የሚያሻሽል ሐኪም ጎበዝና ዐዋቂና ሕመምተኞችን በአግባቡ የሚረዳ ይሆናል። በየቀኑ ቃሉ የሚነገረን እኛስ ምን ለውጥ አመጣን?
እየተናገርኩ ያለሁት ለአንድ አመት በቤተክርስቲያን የቆዩትን ብቻ አይደለም። እየተናገርኩ ያለሁት ከልጅነታችን አንስተን በቤቱ ለምንመላለስ እንጂ። ይኽን ያኽል ዘመን በቤቱ እየተመላለስን ፍራ ካላፈራን ቤተክርስቲያን ደርሰን ብንመጣ ምን ጥቅም አለው? አባቶቻችንስ አብያተ ከርስቲያናትን ያነጹልን ለምንድን ነው? ዝም ብለን እንድንሰባሰብ ነውን? መሰባሰቡንማ በገበያ ቦታም መሰባሰብ እንችላለን። አበው አብያተ ቤተክርስቲያናትን ያነጹልን ቃሉን እንድንማርበት፣ በተማርነው ቃልም የንስሐን ፍሬ እንድናፈራበት፣ ስጋ ወደሙን እንድንቀበልበት፣ እርስ በእርሳችን እንድንተራረምበት እንጂ ለሌላ ዓላማ አይደለም።
ታዲያ ምን ፍሬ አፈራን?
በገብረ እግዚአብሔር ኪደ ከተጻፈው ሰማዕትነት አያምልጣችሁ ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።
#ዝክረ_አበው_መነኮሳት
በዚህች ቀን ቅዱስ ስምዖን ዘዓምድ አረፈ። ሀገሩ ሶሪያ ሲሆን ከልጅነቱ ጀምሮ የአባቱ በጎች እረኛ ነበር። ዘውትር ቤተክርስቲያን ይሄድ ነበር። የእግዚአብሔር ጸጋ አነሳስቶት ከገዳማት ወደ አንዱ ሄደ። በዚያም እግዚአብሔርን በታላቅ ተጋድሎ እያመለከ ቆየ። ራሱን በብዙ ጾም እና መጠማት ይጫነው ነበር፥ ከዚህን በኃላ በወገቡ ላይ ገመድ አሰረ፥ ሰውነቱን በስቶት ነበር፥ ከውስጡም ጠረን መውጣት ጀመረ።
ሌሎች መነኮሳትም በዚህ ሽታ ሲረበሹ ከገዳሙ በመውጣት ወደ አንዲት ጉድጓድ መጣ ፥ በዚያም ለአጭር ጊዜ ኖረ። የገዳሙ አበምኔት በራዕይ "ለምን ወዳጄ ስምዖንን አስወጣኸው? ፈልገህ መልሰው" የሚል ተነገረው። ይህም ከገዳሙ ስላስወጣው እንደ ተግሳጽ ያለ መልዕክት ነበር።
አበምኔቱ ይህን ራዕይ ለወንድሞች ነገራቸው፥ እነርሱም ተረበሹ፤ ቅዱስ ስምዖንንም መፈለግ ቀጠሉ። በአንድ ጉድጓድ ውስጥ ያለ ምግብ እና ውሃ እየኖረ አገኙት። የበደሉትን በደል በፊቱ ተናዘው ይቅርታ ከጠየቁ በኃላ ወደ ገዳሙ መለሱት።
ከፍከፍ ያረጉት ሲጀምሩ እንደማይገባው ይሰማው ነበር፣ ስለዚህ ገዳሙን በምስጢር ለቆ ወጣ። ወደ አንድ አለት መጥቶ ያለ እንቅልፍ ለ60 ቀናት ኖረ። ከዚህ በኃላ የእግዚአብሔር መልአክ ወደርሱ መጥቶ ካጽናናው በኃላ እግዚአብሔር ለብዙዎች መዳን እንደጠራው ነገረው።
ከዚህን በኃላ 30ኩቢት(15 ሜትር) የሚረዝም ዓምድ ላይ መኖር ጀመረ። ለ15 ዓመታት በርሱ ላይ ኖረ። ብዙ ምልክቶችን እና ተዓምራትን ይሰራ ነበር፤ ወደርሱ የሚመጡትን ይሰብክ ነበር።
አባቱ በሕይወት ሳለ ብዙ ፈልጎት ነበር ነገር ግን አላገኘውም ነበር፥ ሳያየውም ሞተ። እናቱ ከረዥም አመታት በኃላ ስለርሱ አወቀች፥ ወደ ሚኖርበት ዓምድም መጣች። በዚያ አብዝታ አለቀሰች፥ ከዚያን ከዓምዱ(ምሰሶ) ስር ተኛች። ቅዱሱም ምህረቱን እንዲያደርግላት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ጠየቀው።እናቱ በተኛችበት በዚያው አረፈች፥ በዓምዱ ስር ቀበሯት።
ስለ መልካም ስራዎቹ ዲያብሎስ ቀናበት፥ በርሱም ላይ ተነሳሳበት። አንዱን እግሩን በቁስል ክፉኛ መታው። አንዱን እግሩን በመጠቀም ለብዙ አመታት እየጸለየ ቆየ። የታመመው እግር በስብሶ ትሎች ከርሱ ወደ ዓምዱ ስር ይወድቁ ነበር።
የሽፍቶች አለቃ ወደርሱ መጥቶ ከዓምዱ ስር አንቀላፋ፥ ቅዱሱም ስለርሱ ወደ ክርስቶስ ጸለየ፤ ጥቂት ቀናት ቆይቶ ሞተ። ቅዱሱ ጌታችን ውሃ እንዲሰጠው ጠየቀ፥ ከዓምዱ ስርም ውሃ ፈለቀ። ከዚያን ወደ ረዥም ዓምድ ተሻገረ፥ በዚያም ለ30 ዓመታት ኖረ።
48 ዓመታትን በአምልኮ ከቆየ በኃላ ወደ እግዚአብሔር ሄደ። ብዙ ሰዎችን ሰብኮ፣ አስተምሮ ወደ ክርስቶስ እውቀት መልሷል። የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ ከዚህ አለም ማረፉን ሲሰማ ወደርሱ መጥቶ ስጋውን በታላቅ ክብር ወደ አንጾኪያ ወሰደው።
ጸሎቱ ከኛ ጋር ትሁን። አሜን።
@hiwotemenekosat
ማህበራዊ ህይወት ወደ ሌሎች የመድረስ እንቅስቃሴ ነው፤ መንፈሳዊ ህይወት ደግሞ ወደ እግዚአብሔር የመድረስ እንቅስቃሴ ነው።
ለእግዚአብሔር ስራ ምላሽ የምትሰጥ ከሆነ ጸጋው ያንቀሳቅሥሐል። በውስጥ ለሚሰራ ጸጋው ምላሽ ስጥ። በጊዜያቱ ሁሉ እርሱ ያንቀሳቅስሃል።ለዚህ ሥራው ምላሽ ሥጥ፤ ተንቀሳቀስ፤ የፊትህንም ነገር ለመያዝ ተዘርጋ። ይህ ባንተና በመንፈሥ ቅዱስ መካከል ያለውን ኅብረት ያሳያል።
ወንድሞቼ በግል ህይወታችሁ ወደ መልካሙ ነገር ሁሉ ትንቀሳቀሱ ዘንድ እሻለሁ። ሌሎችን ለመርዳት ተንቀሳቀሱ። በአገልግሎትም አድኗቸው። ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር መንግስት የምትንቀሳቀሱበት ቀን ይመጣል። ታዲያ በዚያን ግዜ ምን ታደርጋላችሁ?
ሰው ሁሉ ዘወትር መንቀሳቀስ "ጌታ ሆይ ከአንተ ጋር ነኝ" ማለት ይገባዋል። ልባችን በፍቅር፣ በመንፈሳዊ ሙቀት፣ በናፍቆትም ወደ እግዚአብሔር መንቀሳቀስ አለበት። ቤተክርስቲያንም ጌታን ወደማያውቁ ለእርሱ ወዳልተገዙ ለመስበክና ለማስተማር መንቀሳቀስ አለበት።
(አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ)
bekishooo/photo/7386597925486431493?_r=1&u_code=0&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=dkcicd8me3ecdj&share_item_id=7386597925486431493&source=h5_m&timestamp=1721886927&aweme_type=150&pic_cnt=1&social_share_type=0&utm_source=telegram&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7254179470089160454&share_link_id=5669ad47-853e-4965-a4a1-41106f3218e4&share_app_id=1233&ugbiz_name=Unknown&ug_btm=b2001" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@bekishooo/photo/7386597925486431493?_r=1&u_code=0&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=dkcicd8me3ecdj&share_item_id=7386597925486431493&source=h5_m&timestamp=1721886927&aweme_type=150&pic_cnt=1&social_share_type=0&utm_source=telegram&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7254179470089160454&share_link_id=5669ad47-853e-4965-a4a1-41106f3218e4&share_app_id=1233&ugbiz_name=Unknown&ug_btm=b2001
Читать полностью…sewasew44/photo/7372428186530876689?_r=1&u_code=0&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=dkcicd8me3ecdj&share_item_id=7372428186530876689&source=h5_m&timestamp=1721322986&aweme_type=150&pic_cnt=1&social_share_type=0&utm_source=telegram&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7254179470089160454&share_link_id=a601f997-b9cc-4d42-bf26-03372ce6b563&share_app_id=1233&ugbiz_name=Unknown&ug_btm=b2001" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sewasew44/photo/7372428186530876689?_r=1&u_code=0&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=dkcicd8me3ecdj&share_item_id=7372428186530876689&source=h5_m&timestamp=1721322986&aweme_type=150&pic_cnt=1&social_share_type=0&utm_source=telegram&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7254179470089160454&share_link_id=a601f997-b9cc-4d42-bf26-03372ce6b563&share_app_id=1233&ugbiz_name=Unknown&ug_btm=b2001
Читать полностью…“ምንድር ነው እየሆነ ያለው?”
ጌታችን እና ሐዋርያት በጀልባ ሲጓዙ ድንገት ማዕበል ተነሳ ጌታም ተኝቶ ነበርና ሐዋርያት ፈሩ ተጨነቁ።ወደ ጌታም ቀርበው እንዲህ አሉ “ጌታ ሆይ ተነስና አንድ ነገር አድርግ መቼም እንድንሞት አትወድም” ጌታችን ግን በፍፁም መረጋጋት ውስጥ ነበር
እግዚአብሔር ሁሉን ከመሆኑ በፊት ያውቃል እኛ የምንፈራው ምንም ስለማናውቅ ነው። ይልቁንም ስለማናምን። ጌታም ከእንቅልፍ በመነሳት ሆኖ እንዲህ አላቸው “ምንድር እየሆነ ነው?ምን ተከሰተ?”
ሁሉም ተረብሸው ነበረ ።ጌታም እጆቹን በማንሳት ማዕበሉን ፀጥ አረገው።
እኛንም እንዲህ ይለናል “ምንድነው የሚረብሻችሁ? የሚያስጨንቃችሁ?” በሕይወታችን እንድንጨነቅ፣እንድንረበሽ፣እንድንባክን የሚያረጉንን ነገሮች ሁሉ እርሱ ፀጥ ያረጋቸዋል።እነዚህ ነገሮች ከኛ የሚርቁት ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ጊዜ ስንሰጥ ነው። የሚጎድለንን እኛ ማሟላት የማንችለውን ሁሉን ማድረግ ከሚችል ከእግዚአብሔር እናገኘዋለንና።
🖋️ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
“ለእግዚአብሔር ጊዜ ማጣትና ሌሎችም”
++++ የገሊላዉ ጳጳስ፡፡++++
አንድ ክርስትያን ያልሆነ ሰዉ ባለቤቱ ልትወልድ ተጨንቃ ነበር ነገር ገን ለማሳከሚያ የሚሆን ገንዘብ የለውም ከዚያም <"የገሊላውን ጳጳስ"> አባ አብርሐን እጠይቀዋለሁ አለ ("<አባ አብርሐም የገሊላዉ ጳጳስ በመባል ይታወቃል>") ስለሆነም ወደ ቤቱ ሄዶ ገንዘብ እንዲሰጠዉ ለመነዉ አባ አብርሐምም """ጳጳሱ ለክርስትያን ብቻ መሰለህ እንዴ""" ብሎ በመቀለድ ከትራሱ አንድ ፖስታ እሽግ ብር ሰጠዉ፡፡ያ ሰዉ ሲከፍተዉ 1 ፓውንድ(የግብፅ በብር ፓውንድ ተብሎ ነዉ ሚጠራዉ)ነዉ በሚከፈፍትበት ጊዜ አንድ መነኩሴ አይቶት ነበር እና ያ ገንዘብ በወቅቱ ትልቅ ገንዘብ ነበረ መነኩሴዉ ለጳጳስ ወንድሙ በመቆርቆር እንዴት 1 ፓውንድ ሰጠህ ብሎ ሰውየዉ ላይ ያንን ገንዘብ ወስዶ በምትኩ 20 ፒያስትረስ ሰጠዉ ያ ሰዉ ተመልሶ አባ አብርሐም ተናገረ አባ አብርሐም መነኩሴዉን ጠርቶ ብሩን ተቀብሎ ሰውየው ሰጠዉ ያም ሰዉ አመስግኖ ባለቤቱን ይዞ ሄደ፡፡በመቀጠል አባ አብርሐም መነኩሴውን """ከጌታችን ምን ተማርን ምንቀበለዉ ልንሰጥ አይደለምን ከቀደሙት አባቶቻችንን የተማርነዉ ስስት ነዉ""" ብሎ ገሰፀዉ መነኩሴው አማላጅ ይዞ ይቅርታ ተባለ፡፡
++++ አንካችሁ ቅበሩት፡++++
አንድ ጊዜ 3 ወጣቶች በዘዴ ከአባ አብርሐም ገንዘብ መቀበል ፈለጉ ስለሆነም ዘዴ ሲያስቡ ከሶስታቸዉ አንዱ እንደ ሞተ በማስመሰል ሁለቱ ሄደዉ ገንዘብ ሊቀበሉ ሄዱ ከዚያም የውሸት እያለቀሱ ገንዘብ ጠየቁት አባ አብርሐም በመንፈስ የሆነውን ተረድቶ ነበርና ጭንቅላቱን እየነቀነቀ """ <እንካችሁ ቅበሩት>""" አላቸዉ በደስታ ገንዘቡን ይዘዉ ሄዱ በተቀጣጠሩበት ቦታ ሲደርሱ የያ ጓደኛቸዉ ሞቶ አገኙት በድንጋጤ እየሮጡ ያደረጉትን አባ አብርሐም እያለቀሱ ነግረውት ገንዘቡን ሊመልሱ ሲሉ አባ አብራም ግን ፈገግ ብሎ """ገንዘቡን ግን ቅበሩበት""" ብሎ ተወላቸዉ፡፡
++++ድርሻዉ ነዉ ይውሰደዉ፡፡እግዚአብሔር ችግሩን ስለሚያውቅ ነዉ ይህን የላከለት፡፡++++
አንድ ሐብታም በፖስታ ገንዘብ ሰጥቶት ሄደ አባ አብርሐም በፖስታ የሚሰጠውንም ገንዘብ ከፍቶ አያየውም እንደታሸገ ከትራሱ ሥር ያስቀምጠዋል እንጂ ስለሆነም አንድ ደሐ መጣና ገንዘብ ሲጠይቀዉ ያንን የታሸገ ገንዘብ አውጥቶ ሰጠዉ፡፡ከዚያም ያ ደሐ ከቤቱ ባለዉ በረንዳ ጋር ቆሞ ፖስታውን ሲከፍተዉ 10 ፓውንድ ነዉ፡፡ይህንን ያየ አንድ ደቀ መዝሙሩ መጥቶ ነገረዉ 10 ፓውንድ እንደ ሰጠዉ አባ አብርሐምም <"""ድርሻዉ ነዉ ይውሰደዉ እግዚአብሔር ችግሩን ስለሚያውቅ ነዉ ይህን የላከለት""">አለዉ፡፡
+++ቤቱን ገንብቻለሁ+++
የተወሰኑ አባቶች ተሰብስበዉ የአባ አብርሐም ቤት ለማሳደስ ወሰኑ ለምን ቤቱ እንኳን ጳጳስ ተራ ሰዉ የማይኖርበት በመሆኑ ነዉ፡፡በሌላ አጋገር በጣም አርጅቷል፡፡ስለሆነም አስፈላጊውን ወረቀት እና ፈቃድ አውጥተዉ ከጨረሱ በኋላ ለቤቱ ግንባታ የያሰባሰቡትን ገንዘብ ለአባ አብርሐም ሰጥተዉ ሄዱ አርሱም ተቀብሎ ገንዘቡን ለነዳያን አከፋፈለ በሚቀጥለዉ ወር ሲመጡ ቤቱ ምን ለውጥ አልታየበትም ወደ ውስጥ ዘለቁ እና """አባታችን ለምንድነዉ ቤቱን ያላሳደስከዉ???!!!""" ሲሉት """እኔ እኮ <ቤቱን ገንብቻለሁ ቤቱን ገንብቻለሁ>""" አላቸዉ """ታዲያ ምንም ለውጥ አላየንበትም""" ሲሉት <"""እኔ እኮ ለዘላለማዊ የሚሆን ቤት ገንብቻለሁ""""> አላቸዉ፡፡ገርመዉ እና ተደንቀዉ ተመልሰዉ ሄዱ፡፡
*በእርሱ ዘመን ድሐ ፆሙን አያድርም ነበር፡፡ድሆቹም የእርሱ ቤት እንደ ሁለተኛ ቤታቸዉ ነበር፡፡ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከእርሱ ጋር ሲሆኑ ሰላም ይሰማቸዋል፡፡**
+++ ዕለተ ዕረፍቱ +++
አባ አብርሐም አንድ ካህንና አንድ ዲያቆን ጠርቶ መዝሙረ ዳዊት እንዲደግሙ አዘዛቸዉ ከዚያም ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ በዓቱ እንዲገቡ አዘዛቸዉ ሲገቡም አርፎ አገኙት፡፡
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፡፡ እኛንም በድሆች ጳጳስ በቅዱስ አባ አብርሐም ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለም ጸንታ ትኑር፡፡አሜን አሜን አሜን፡፡
በዛሬዉ ዕለት አብረዉ ከሚዘከሩ ቅዱሳን ሰማዕቱ ቅዱስ ኢላዲዮስ ጳጳስ የሰማዕታት አለቃ የሚሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተክርስትያኑ በግብፅ ታነጸ ሰማዕቷ ቅድስት ማርታ ግብጻዊት ብፁዕ ወቅዱስ አባ ቀስማ የግብፅ 44ተኛዉ ፓትርያርክ አቡነ ያሳ ሚካኤል ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፡፡እኛንም በሰማዕቱ ኢላዲዮስ ጳጳስ፡፡ በሰማዕታት አለቃ የሚሆን በቅዱስ ጊዮርጊስ በሰማዕቷ ቅድስት መርታ ግብጻዊት፡፡ በብፁዕ ወቅዱስ አባ ቀስማ የግብፅ 44ተኛዉ ፓትርያርክ፡፡ በአቡነ ያሳ ሚካኤል ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ጸንታ ለዘላለም ትኑር፡፡አሜን አሜን አሜን፡፡
ለወንድማችን Dn. Michael Misrue ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
@hiwotemenekosat
#ዝክረ_መነኮሳት_ወመነኮሳይያት
#ዝክረ_አበው_ጳጳሳት
በ Dn. Michael Misrue('My Beloved')
++++ የድሆች ጳጳስ፡፡ ++++
በዛሬዉ እለት(ሰኔ 3) የፋዩም ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ቅዱስ አባ አብራአም(አብርሐም)አረፈ፡፡
አባታችን ቅዱስ አባ አብራአም(አብርሐም)የተወለደዉ በግብፅ ውስጥ ጋላድ በሚባለዉ የማላዊ መንደር ከቅዱሳን ቤተሰብ ተወለደ፡፡የልደት ስሙ ጳውሎስ ይባላል፡፡ዕድሜዉ ለትምህርት ሲደርስ በአካባቢዉ በሚገኝዉ ቤተክርስትያን ገብቶ መማር ጀመረ መምህሩ አባ ሩፋኢል(ሩፋኤል) ይባላል፡፡ብሩህ አዕምሮ ስለነበረዉ ሁሉንም የቤተክርስትያን ትምህርቶች አጠና፡፡
ስምንት አመት በሞላዉ ጊዜ
እናቱ ባደረባት ህመም በመሞት ተለየችዉ፡፡ነገር ግን ጳውሎስ በሕፃንነት ዕድሜዉ እግዚአብሔርን መጽናኛዉ አደረገ፡፡15 ሲሞላዉ ስሙ የተጠራ ጎበዝ ተማሪ ስለነበር የዲያቆናት ሐላፊ የነበረዉ ሊቀጳጳስ በዲቁና ሾመዉ፡፡ 19 አመት እስኪሞላዉ ደድረስ በመልካም አገልግሎት አገለገለ ልክ 19 አመት ሲሞላዉ አባ ጳውሎስ አል-ሞሐራቂ(የሞሐራቂዉ አባ ጳውሎስ እንደ ማለት ነዉ፡፡)ተብሎ ምንኩስናን በሞሐረቅ ገዳም ተቀበለ፡፡አባ ያኮቦስ የተባለ ሊቀጳጳስ ዝናውን ስለሰማ ከእርሱ ጋር እንዲኖር ጋበዘዉ፡፡አባ ጳውሎስም ከእርሱ ጋር መኖር ጀመረ ሊቀጳጳሱን ቀን ከሌሊት ማገልገል ጀመረ፡፡ቀስ በቀስ የሊቀጳጳሱን ቤት ወደ ድኃ መጠለያነት ለወጠዉ፡፡ለአራት አመታት የሊቀጳጳሱን ቤት አገለገለ በነዚያ አመታት ድሆች ጠግበዉ ያድሩ ነበር ማንም አይቸግረውም፡፡ከዚያም የሊቀጳጳሱን ቤት ለመልቀቅ ወሰነ ለምን ቢባል በከተማዉ ያሉ ሰዎች እያወደሱት ስለነበር ከንቱ ውዳሴን ለመሸሽ ሲል ነበር፡፡ሊቀጳጳሱም የቅስና መዓረግ ሰጥቶት እና መርቆት ባርኮት ሸኘዉ፡፡
ወደ ገዳሙ ሲመለስ ሁለት ሰዎች ተጣልተዉ ነበር የደረሰዉ ነገር ግን በሁለቱ መሐል መግባት አልፈለገም፡፡በገዳሙ በቅድስና እና በትህትና ሆኖ ማገልገል ጀመረ፡፡ከዚያም ከጥቂት አመታት በኋላ የገዳሙ አበምኔት ሆኖ እንዲሾም ተመረጠ ገን እርሱ አልፈለገም በግድ ተጎትቶ የገዳሙ አበምኔት(አለቃ) ሆነ፡፡ጊቢውንም የድሐ እና የነዳያን አደባባይ አደረገዉ፡፡ዝናውን የሰሙ ወጣቶች ከየቦታዉ መጥተዉ ወንጌል እየተማሩ በመመንኮስ የመነኮሳቱን ቁጥር እጥፍ አደረሱት አሳደጉት፡፡ከእነርሱም መካከል 1ኛ አሲዮት የተወለደዉ አባ ማርቆስ አል ሞሐራቂ ጳጳስ(በብፁዕ ወቅዱስ አባ ቄርሎስ 5ተኛ የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን 113ተኛ ፓትርያርክ በጵጵስና ወደ ባራሙስ ገዳም ላከዉ በተላከባቸውም ቦታዎች ሁሉ ጸሎተኛነቱ ባሻገር አሮጌ አብያተክርስትያናትን በማሳደስ ስሙ የተጠራ አባት ነበር፡፡) 2ተኛ ቆሞስ አባ ሚካኤል አል ባሂሪ(ይህ አባት ትክክለኛ የመምህሩን የአባ ጳውሎስ ምግባር የወረሰ ሲሆን የቅድስና ማዕረግ ያለዉ ነዉ በሁለቱ አባቶች ያለዉ ፍቅር እና ወንድማማችነት በቃላት አይገለጽም ጸሎትም ለምግብም ለስራም አንድ ላይ ነበር የሚሄዱት፡፡
በሌላ ጊዜ የዚህን አባት ታሪክ ይዤ እመጣለሁ፡፡ታሪኩ አባ ሉቃስ በተባለ ሊቀጳጳስ ተጽፎ ይገኛል) 3ተኛ አባ ማቴዎስ ሊቀጳጳስ ወደ ኢትዮጵያ የተላከ፡፡የመልካም ነገር ጠላት የሆነዉ ሰይጣን በጥቂት ሰዎች አድሮ አባ ጳውሎስ ለ 5 ዓመት ካለበት ገዳም እንዲባረር አደረገዉ፡፡ እነዚያ ሰዎች ምክንያት አድርገዉ ያቀረቡት የገዳሙን ገንዘብ ጨረሰዉ በሚል ነዉ ገዳሙ ለድሆች ክፍት ነበር እንደዚሁም ብዙ ወጣት መነኮሳት እየመጡ ስለነበር ነዉ፡፡ለ5 አመታት ካገለገለበት ገዳም ማስተማር እና ማገልገል እንዲተዉ በመገደዱ ገዳሙን ለቆ ከአራት ደቀ መዝሙሮቹ ጋር ወደ ካይሮ ዋዲ አል ናትሮን ወደ ሚባለዉ በረሐ ወደ ታላቁ አባት ወደ ቅዱስ አባ ቢሾይ ገዳም ሄዱ ከዚያም ከቅዱስ አባ ቢሾይ ገዳም ጥቂት ቆይታ ካደረጉ በኋላ ወደ የባራሙስ ገዳም አመሩ ያኔ የባራሙስ ገዳም አበምኔት የነበሩት አባ ዮሐንስ(((( በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ አባ ቄርሎስ 5ተኛ የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን 113ተኛ ፓትርያርክ የሆነዉ፡፡)))) በደስታ ተቀብሎ ለሁሉም በዓት ሰጥቶአቸዉ አስቀመጣቸዉ፡፡
ምንም እንኳን አባ ጳውሎስ በትምህርት እና በጸሎት የተጠመደ ቢሆንም ለአካባቢዉ ላሉት ድሆች ግን መራራቱን ፍቅሩን አልተሻማበትም በተለይም አካባቢዉ ለሰፈሩት አረቦች ልዬ ፍቅር ነበረዉ ልብሱን ምግቡን ሳይቀር ያለውን ነገር ሁሉ ከእነርሱ ጋር ይጋራ ነበር፡፡ኢትዮጵያዊዉ ንጉስ አጼ ዮሐንስ ብፁዕ ወቅዱስ አባ ቄርሎስ 5ተኛን አራት ጳጳሳትን እንዲልክ በመጠየቁ ከእርሱ ጋር የተሰደዱት አራት አባቶች ለጵጵስና ተመረጡ እና ተሾሙ፡፡ 1ኛ አባ ዮክላዴዎስ አል-ሜሪ የተባለዉ አባት ብፁዕ አባ ጴጥሮስ ተብሎ ለአስመራ(ኤርትራ) የተመደበ፡፡ 2ተኛ አባ ዮክላዴዎስ አልካላዲ አል-ሞሐራቂ ብፁዕ አባ ማቴዎስ ተብሎ ለአዲስ አበባ የተመደበ እና ተዓምር የሚያደርግ እና አይን የሚያበራ ነበር፡፡(((((አጼ ዳግማዊ ምንሊክ ለአድዋ ጦርነት ሲሄድ አብሮ የነበረ እንዲሁም አንዲት የገጠር ሴት አይኗ ጠፍቶ ወደ ሐዋርያዉ ቅዱስ ማርቆስ ስትጸልይ ቅዱስ ማርቆስ በሕልም ተገልጦ"""ወደ ጳጳሱ ወደ አባ ማቴዎስ ሂጂ እሱ ቅብዐ ቅዱስ ሲቀባሽ እኔ እጄን አሳርፍብሻለሁ""" አላት እሷም እሺ ብላ ልክ ጳጳሱ ጋር ቀርባ በታላቅ ድምጽ አባቴ ቅዱስ ማርቆስ ልኮኛል ፈውሰኝ አለችዉ ሰዉ ሁሉ ፊት ግን አባ ማቴዎስ እኔ አልችልም አላት ውዳሴ ከንቱ ለመሸሽ ነገር ግን በመንፈስ ተረድቶ ነበርና በምስጢር ሰዉ ልኮ አስመጣት እና ቅብዓ ቅዱስ ቀባት ተፈወሰች፡፡)))))፡፡ 3ተኛ አባ ሰሎሞን አልደጋዊ አልሞሐራቂ ብፁዕ አባ ሉቃስ ተብሎ ለአክሱም የተመደበ፡፡ 4ተኛ አባ ሚካኤል አል መስሪ አልሞሐራቂ ብፁዕ አባ ማርቆስ ተብሎ (ኤክላድዮስ) ተብሎ የተሾሙት አባቶች ናቸዉ፡፡
እነዚህ አባቶች ይህን ማዕረግ ሲሰጣቸዉ እነርሱም መምህራቸዉ ሹመት እንዲያገኝ ለፓትርያርኩ ጠየቁ አባ ጳውሎስ ሹመት ባይፈልግም ነገር ግን ብፁዕ አባ አብራአም (አብርሐም) የፊዩም አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ተብሎ ተሾመ፡፡ወደ ነበረበት አካባቢም ተመለሰ ህዝቡም የዛፍ ዝንጣፊ ይዞ በታላቅ ደስታ ተቀበሉት፡፡ጳጳስ ከሆነ በኋላ እንኳን ብሕትውናውን አልተወም ነበር ልብሱ አልቀየረም የእጁ መስቀል ያዉ መነኩሴ እያለ የሚይዘዉ መስቀል ነበር፡፡በቤተ ክርስትያን ሥርዐት ለጳጳሳት የተለየ ወንበር ነዉ የሚዘጋጀዉ ልክ እንደ ንጉስ ነገር ግን አባ አብርሐም ምዕመናን ከሚቀመጡበት የተለየ ወንበር ከተጋጀለት ሌላ ተራ ወንበር ካላመጡለት አይቀመጠጥም ነበር፡፡ሌላዉ እንደ ቤተክርስትያን ሥርዓት በሥርዐተ ቅዳሴ ለላይ ለሊቃነ ጳጳሳት የሚፀለየዉ ጸሎት "ጸልዬ በእንተ ሊቃነ ጳጳሳት" ላይ የእርሱ ስም እንዲጠራ አይፈልግም ነበር፡፡ሌላዉ ካህናት ወደ እርሱ አካባቢ ማዕጠንት ይዘዉ እንዲያጥኑ አይፈቅድም ነበር(በግብፅ ቤተክርስትያን ስርዐት ካህናት ጳጳሳትን ያጥናሉ ቅዳሴ ላይ ይህም ትህትናን ያመለክታል እንደዚሁም በኢትዮጵያ ምዕመናን ይታጠናሉ፡፡)አባቶች ፊት ሰግዶ መስቀል እና እጃቸውን መሳም የተለመደ ሲሆን አባ አብርሐም ግን እንዲሰገድለትም ሆነ እጁን እንዲስሙ አይፈቅድም መስቀሉን ብቻ እና ብቻ፡፡ ምዕመናን አለቃችን ጌታችን((በግብፅ ቤተክርስትያን ሥርዐት ጳጳሳትን ""ሰይድና"" ተብለዉ ነዉ ምዕመናን የሚጠራዉ ትርጉሙ አለቃችን ጌታችን ማለት ነዉ))ብለዉ ከሚጠሩት ይልቅ አባታችን ሲሉት በጣም ደስ ይለወዋል፡፡ራሱን የመጨረሻ አድርጎ ነበር የሚቆጥረዉ፡፡
....
@hiwotemenekosat
በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በኢትዮጲያዊው ጃንደረባ ትውልድ እና በአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት 1ኛዙር ተማሪዎች መካከል በቡድን 17 አባላት እየተሰራ ለሚገኘው የመመረቂያ ጽሁፍ መረጃ ማሰባሰቢያ ነው። የእርስዎ ትክክለኛ ምላሾች ለጥናቱ ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስላላቸው መጠይቁን በጥሞና በማንበብ እንዲመልሱ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፤ መጠይቁን በመሙላት ለሚያደርጉልን ትብብር ከወዲሁ እናመሰግናለን። https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfdabZSomPsf33UyQaNOcAEaMlxfBtZRjefqxe19UWuZMplAw/viewform?usp=sf_link
Читать полностью…17 በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ፥ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው። ✍️1ጢሞ 6
Читать полностью…እግዚአብሔር አብ በሰማይ ሁኖ ምስራቅንና ምዕራብን ሰሜንንና ደቡብን ዳርቻወችንም ሁሉ በእውነት ተመለከተ። ተነፈሰ አሻተተም እንዳንቺ ያለ አላገኘም የአንቺን መአዛ ወደደ ደም ግባትሽንም ወደደ የሚወደውን ልጁንም ወደ አንቺ ሰደደ። አንቺን የወደደ እግዚአብሔር አብ ቅዱስ ነው በማህጸንሽ ያደረ ወልድ ዋህድም ቅዱስ ነው ያጸናሽ የጽድቅ መንፈስ ጰራቅሊጦስም ቅዱስ ነው። ምስጋናን የተመላሽ ድንግል ሆይ በማንና በማንስ ምሳሌ እንመስልሻለን። አማኑኤል የማይተረጎም የስጋን ልብስነት ከአንቺ የለበሳት መሥሪያ ነሽ። ዝሐውን ከአዳም ጥንተ ሥጋ አደረገ ማጉም ያንቺ ስጋ ነው መወርወሪያውም ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
✍️ቅዳሴ ማርያም