hiwotemenekosatgroup | Unsorted

Telegram-канал hiwotemenekosatgroup - ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

245

✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን።✝️ ✞ይህ ሕይወተ መነኮሳት የተሰኘው ስለ ነገረ ምንኩስና ተባህትዎ የምንነጋገርበት የምንማማርበት መወያያ ግሩፕ ነው። ኑ እንደ አባቶቻችን በጥብዓት በተባሕትዎ እንኖር ዘንድ ሕይወታቸውን እንመርምር ሥርዓታቸውንም እንማር በፍኖተ አበው እንጓዝ በረከታቸውንም እናግኝ። 🔆 @hiwotemenekosat @hiwotemenekosatbot ሃሳብ መስጫ

Subscribe to a channel

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

#ክብረ_መነኮሳት

ጣማፍ ኄራኒ በአባ ጳኩሚየስ የአንድነቱን ሥርዓት እንዴት እንደ ተቀበለች እንዲህ በማለት ነግራናለች:-

"በክብር ጌታ ፊት ተንበረከኩ፡፡ ድንግል እናቱ በቀኝ ቆማለች፡፡ ጌታችንም ሊቀ መልአኩን 'ስለ ገዳማዊ ቀኖና ትረዳ ዘንድ ወደ አባ ጳኩሚየስ ይዘኻት ሂድ ስላለው፣ በረጅም እና ብርሃናማ መተላለፊያ በኩል ይዞኝ ሄደ፡፡ እንደ አልማዝ የሚያበራና በመስቀል የተዋበ ዙፋን አየሁ፡፡ በዙፋኑ ላይ ግርማው የሚያበራ ሰው ተቀምጧል፡፡ የለበሰው ልብስ በወርቅ መስቀሎች ያሸበረቀ እና
ልዩ፣ግሩም፣ ዐይንን የሚማርክ ነው፡፡ በእጁም መስቀል ይዟል፡፡

ሊቀ መልአኩም 'ሂጂና ለአባ ጳኩሚየስ ሰላምታ አቅርቢ' አለኝ፡፡ ስሄድ በመተላለፊያው ግራና ቀኝ በሺዎች የሚቆጠሩ መነኮሳትና መነኮሳይያት ነጭ ለብሰው ቆመዋል..."


*ቀሪውን ከመጽሐፉ እንድታነቡ እናበረታታለን፡፡ መጽሐፉን ከዚህ ቻናል በ'pdf' መልክ አውርደው ይጠቀሙ፡፡

/channel/hiwotemenekosatgroup/199


@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

​​☀️☀️☀️ክርስቲያኖች በዚህ የሚያልፍ ዓለም እንደ መላእክት ከሆኑ ከዚህ ዓለም ከተለዩ በኋላ ምን ዓይነት ይሆኑ? እንግዳ በሆኑበት ዓለም ይህን ያክል ደምቀው ካበሩ እውነተኛውን ርስታቸውን ሲያገኙ ምን ያክል ታላቅ ምን ያክል እጹብ ድንቅ ይሆኑ ?☀️☀️☀️

🌷ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ 🌷
/ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 12 ላይ በደረሰው ትርጓሜ /

🌼እንኳን ለአባታችን ለታላቁ ለደገኛው የመነኮሳት የሕይወት አባት ትኁት ቅዱስ ዩሐንስ ሐፂር (ጥቅምት 20) እና ለዘመናችን ኮከብ ሴቷ ጳኩሚስ ቅድስት ታማቭ ኤሪኒ (ጥቅምት 21) በዓለ እረፍት አደረሰን አደረሳችሁ ።🌸

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።✝

🌿🌷🌷🌷🌷🌿 ክፍል ፩ 🌿🌷🌷🌷🌷🌿

🌼በጥቅምት 21 ታላቋ ቅድስት ጻድቅ ተዓምር አድራጊዋ ሁለተኛዋ ቅዱስ ፓኩሚዮስ (ጳኩሚስ) የዋህ እና ርህርት የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ መርቆሪዎስ የሴቶች ገዳም እመምኔት እና የሰማዕቱ ወዳጅ የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቅድስት ታማቭ ኢሪኒ የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው።

🌸ይህች ቅድስት የተወለደችዉ በግብፅ አገር ልዩ ስሙ ጊርጋ በተባለ ስፍራ ነዉ፡፡ የልደተት ስሟ ፋውዚያ ይባላል፡፡ ይህች ቅድስት እንደ ሌላዉ ቅዱሳን በሰላም አልተወለደችም ማለትም እናቷ ከመጠን በላይ ነበር የታመመችዉ (እርሷን በምትወልድበት ጊዜ) በዚያ በጭንቅ ሰዓት አባቷ እና አያቷ ይፀልዮ ነበር። አባቷ አምላክን ለወለደች ለክብርት እመቤታችን አያቷ ደግሞ ለሰማዕታት አለቃ ለቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲያማልዷቸዉ
አጥቀብዉ ይጸልዮ ነበር።

🌻 ከዚያም አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን ቅዱስ ጊዮርጊስን አስከትላ መጥታ ለእናትዋ ተገለጸችላት ቅዱስ ጊዮርጊስንም 'ጀርባዋን ዳስሰዉ' አለችዉ። እርሱም እጅ ነስቶ ጀርባዋን ዳሰሰዉ በሰላምም ተገላገለች። እመቤታችንም ህጻኗኗን ታቅፋ 'ይህች ልጅ የእኛ ናት' ብላ ህጻኗኗን ባርካ ወደ ሰማይ አረገች፡፡

🌸ከዚያም እያደገች በሄደች ቁጥር ለክርስቶስ ያላት ፍቅር እየጨመረ መጣ። ሳታውቀውም ወደ ገዳም ለመሔድ ትናፍቅ ጀመረ። እንደዚህ አይነት ፍላጎት የጀመራት ገና የ8 ዓመት ልጅ በነበረችበት ጊዜ ነዉ፡፡

🌺የምትማረዉ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ነበረ በዚያም ደናግላን (ሴት መነኮሳየያት) ነበሩ። እንደ እድሜ ጓደኞቿ መጫወትን ትታ እነርሱን ታይ ነበረ። እንድ ቀን በትምህርት ቤታቸዉ በሚገኝ የደናግላኑ ጸሎት ቤት ሄደች። ከዚያም አንዷ የካቶሊክ ደናግል ስትጸልይ አገኘቻት። ጸለሎቷን እስክትጨርስ ቁጭ ብላ መጠባበቅ ጀመረች።

🌼ያቺ መነኩሲት ጸሎቷን ፈጽማ ወደ ተቀመጠችዉ ቅድስት ሄዳ ልጄ ምን ሆንሽ አለቻት። ቅድስቲቱም እኔ እንደእናንተ መነኩሴ መሆን እችላሁ? ብላ ጠየቀቻት። መነኩሲቷም አዎን ትችያለሽ አለቻት። በመቀጠልም በመጀመሪያ እኔ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ስለሆንኩ በራሴ ቤተክርስትያን ልቁረብና ከዚያም ልቀላቀላችሁ አለቻት።

💐መነኩሲቷም መነኩሴ መሆን ከፈለግሽ ትችያለሽ ግን መቁረብ የምትችይዉ በእኛ ቤተክርስትያን ነዉ። ምክንያቱም የእኛ እምነት ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ይያልና አለቻት። ቅድስቲቱም ታዲያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ገዳማትን አላውቃቸውም አለቻት። መነኩሲቷም እኔ እገርሻለሁ ለምንኩስና የሚያስፈልጉትን ነገሮች ምን ምን እንደሆኑ አስተምርሻለሁ ። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖትሽን እንድትለቂ አልፈልግም አለቻት፡፡

🌾መነኩሲቷም እንደነገረቻት በቤቷም ሆነ በቤክርስትያን ትጸልይ ነበረ። በተለይም ጠዋት ጠዋት ደስ የሚል የቤተክርስትያን ዕጣን ይሸታት ነበረ። ግን ይህ የሚሆነዉ ከቅዳሴ በፊት ነበረ፡፡

🌼ይህ ነገር ያሳሰባት እናቷ ወደቤተክርስትያን ሄዳ ለካህኑ ነገረችዉ። እርሱም ልጅሽ የተባረች ናት ያ የዕጣን ሽታ ሥውራን ባህታውያን በሚጸልዩት ሰዓት የሚሸት ነዉ አላት፡፡

🍀 ከጥቂት ጊዜያት በኋላ እናቷ ታመመች ህመሙም የሚያነቃንቅ አልነበረም። ይህንን የምታውቀዉ ቅድስቲቱ እናቷን አጽናንታ ወደ ቤተ-ክርስትያን ሄዳ አምላክን በወለደች በእመቤታችን ሥዕል ፊት ቆማ መጸለይ ጀመረች። እመቤቴ ሆይ እባክሽ እናቴን ፈውሻት እኛ ልጆችሽ ነን አምንሻለሁ ብላ ጸለየች።

🌿በመቀጠልም አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን ለእናቷ ተገለጸቸላት እንዲህም አለቻት። ለምን ታለቅሻለሽ እናትየዋም ልጆቼ ህጻናት ናቸዉ እኔ ከሞትኩ እግዚአብሔር እንደሚፈልገዉ ላያድጉ ይችላሉ እባክሽን ከጌታ ፊት አማልጂኝ ታላቅ እህታቸዉ እስክታድግና ኀላፊነትን እስክትረከብ ድረስ አለቻት ። አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን መልሳ ከእኔ ጋር ነይ አለቻት።

🌿ከዚያም እናትየዋ ወዴት እኔ ለባለቤቴ ሳልናገር አልወጣም አለቻት። አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን መልሳ አንቺ በባልሽ ቦታ ብትሆኚ ከጌታ እናት ጋር ለመሔድ ደስ ይልሽ ነበረ ብላ ወደ ሰማይ ይዛት ሄደች። ከዚያም በመልካም መኝታ አስተኛቻት።

🌿 ከዚያም እመቤታችን ቅዱስ ጊዮርጊስን ጊዮርጊስ እስኪ እያት መርራት አለችዉ። እርሱም እናቴ እመቤቴ ሆይ እንደምታውቂዉ የእርሷ ጉዳይ አብቅቷል ድናለች አላት። ክብርት እመቤታችንም እኔ እንዳማልዳት ጠይቃኝ ነበረ እኔም ልመናዋን ተቀብዬ ለልጄ ለወዳጄ ነግሬዋለሁ አሁን ያለባትን ችግር ነቅለህ ጣልላት አለችዉ። ቅዱስ ጊዮርጊስም እናቴ ያንቺ እጅ ይዳሳትና ከዚያ አወጣወዋለሁ አላት። እመቤታችንም ዳሰሰቻት ቅዱስ ጊዮርጊስም አውጥቶ ለእናትየዋ ይህንን ይዘሽ ወደቤትሽ ሒጂ አላት፡፡

Credit : ከወንድሜ ዲያቆን ሚካኤል fb page

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

https://vm.tiktok.com/ZMhx5hkLB/

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

@bezakulu7
ክፍል ሁለትን እንዲሁም
በየቀኑ በተከታታይ ትምህርቱን በዚህ ቻናል ላይ ያገኙታል join ያርጉና ቤተሰብ ይሁኑን

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

/channel/bezakulu7/25

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

/channel/bezakulu7/11

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

እባክህ ስለ መነኮሳት ታሪክ የምናገር መጽሐፍ ላክን

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

❣ገድለ ተክለ ሃይማኖት ❣

📖 መጽሐፍ📚

@Hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

https://www.youtube.com/live/P82DOme_JE4?si=MpkEJ2qG5xQ7SCCo

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

❤️እንኳን ለጾመ ፍልሰታ ለማርያም እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን።🤲❤️

በየቀኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስንክሳር የሚታሰቡ

❣የቅዱሳን ታሪክ፣  ገድላቸው፣ ቃል ኪዳናቸው፣ የቅዱሳን ሰላምታ፣

❣የየቀኑ የቅዳሴ መልዕክታ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ የወንጌል ጥቅስ እና ምስባክ ይቀርብበታል።

🎙የነግህና የቅዳሴ ምስባክ በድምጽ

🎙ስንክሳር ምንባብ

እንዲሁም በባዕላት ቀን ማህሌትና ተጨማሪ መርሐ ግብሮችን ይዘን እንጠብቀዎታለን😊

💕join 💕በማለት ሁሉንም አንድ ላይ ያግኙ😊

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

"ኃጥእ ነኝ ማለት ብቻ እውነተኛ ትህትና እንዳይደለ በእውነት እናገራለሁ፣ እውነተኛ ትህትናስ ትሩፋት መስራት ነው፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

/channel/Orthodoxtewhado19

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ab65646/video/7388134195547196678?_r=1&u_code=0&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=dkcicd8me3ecdj&share_item_id=7388134195547196678&source=h5_m&timestamp=1721907406&social_share_type=0&utm_source=telegram&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7254179470089160454&share_link_id=f7df5c26-4bbc-4d46-b25c-bcfae8576586&share_app_id=1233&ugbiz_name=Main&ug_btm=b2001" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@ab65646/video/7388134195547196678?_r=1&u_code=0&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=dkcicd8me3ecdj&share_item_id=7388134195547196678&source=h5_m&timestamp=1721907406&social_share_type=0&utm_source=telegram&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7254179470089160454&share_link_id=f7df5c26-4bbc-4d46-b25c-bcfae8576586&share_app_id=1233&ugbiz_name=Main&ug_btm=b2001

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

https://vm.tiktok.com/ZMr91VFhV/

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

📸ይህ ሥዕል በቤተክርስቲያን ውስጥ ተሰርቶ ያለ የእርሷ ሥዕል ሲሆን ከስር የምትታየው ሕፃን ከሥዕሏ ስር ስትቆም ከሥዕሉ ላይ የእማሆይ ታማቭ ኢሬኒ እጅ ተነስቶ ሊባርካት በሕፃኗ ራስ ላይ ሲያርፍ የሚያሳይ ነው። ሕፃኗ ፎቶ ሳትሆን በትክክል የቆመች ናት።📸

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

🌿🌷🌷🌷🌷🌿 ክፍል ፪ 🌿🌷🌷🌷🌷🌿

🌿ቅድስቲቱ ገዳም የመግባት ፍላጎቷ እየጨመረ መጣ። ከዚያም ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆርዮስ ተገለጸላት። ስለእርሱ ሰምታ አታውቅም ነበረ። እርሱም ራሱን ካስተዋቃት በኋላ ወደ ገዳሙ ወሰዳት። ከወሰዳትም በኋላ ገዳሙን ሁሉ አስጎበኛት። በኋላ ወደ ቤቷ በደቂቃ መለሳት ገዳሙ ርቀት ነበረዉ። የወሰዳትም በሕልም ሳይሆን በውን በፈረሱ ነዉ፡፡

🌿 እመቤታችን ለእናትየዋ ተገልጻላት ያኔ ስትወልጂ የኛ ነች ብየሽ አልነበረ አሁንም ወደገዳም ውሰጃት አለቻት። (ምክንያቱም አባቷ አትሄጂም ብሎ ስለከለከላት)፡፡ ገዳምም ገብታ የገዳም ኑሮ ጀመረች በዚያ ገዳም እማሆይ አፍሮዚና የምትባል ኢትዮጵያዊት ቅድስት መናኝ ነበረች። እርሷም እንዳየቻት "ኢንቲ አልደብራ ረይሳ ደብራ አቡ ሰይፈን" አሏት። ትርጓሜውም አንቺ የደብረ አቡሰይፈን ገዳም እመምኔት (አለቃ) ትሆኛለሽ ማለት ነው።

(ግብፆች ቅዱስ መርቆሬዎስን አቡሰይፈን ብለዉ ይጠሩታል አቡሰይፈን ማለት የሁለት ሰይፎች አባት ማለት ነዉ፡፡)

🌿የበጎ ነገር ጠላት የሆነዉ ሰይጣን ቅድስቲቱን ይፈትናት ነበር። እርሷም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታባረዉ ነበር። እመቤታችንም በየጊዜዉ ትጎበኛት ነበር፡፡

💠የተተነበየላት ነገር ደረሰ እመምኔት እንድትሆን በቅዱስ ቄርሎስ ስድስተኛ ተመረጠች። እርሱም ፕትርክና ከመሾሙ በፊት አንድ ጊዜ አግኝቷት እመምኔት እንደ ምትሆን ነግሯት ነበር፡፡ ከዚያም ቅድስት ታማቭ ኢሪኒ እኔ እመምኔት መሆን አልፈልግም አለች። በግድ ጎትተዉ ወደ ጳጳሱ ወስደዋት ተባርካ አስኬማ ለብሳ እመምኔት ሆነች።

💠እመምኔት ከሆነች በኋላ በግል ፀባዩዋ ላይ የታየ ለውጥ አልነበረም። እንደድሮ ትህትናዋን ለብሳ እናቶችን ታገለግል ነበር። የቅዱስ ፓኩሚየስን ( ጳጉሚስ) የገዳማዊ ኑሮ ሥርዓት እንደገና በስራ ላይ እንዲውል ያደረገች ቅድስት ናት፡፡

💠ካለችበት ቦታ ወደ ፈለገችው ቦታ ልክ እንደቀደሙት ቅዱሳን ወዲያውኑ ሰከንድ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ትደርስ ነበር። ገነት እና የተሰወሩ የቅዱሳን ያሉበትን ቦታ በየጊዜው ትጎበኝ ነበር። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ድንግል እናቱ እና ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ ከሌሎች ብዙ ቅዱሳን ጋር መጥተው ያረጓጓት ነበር።የሰዎችን ችግር ማንም ሳይነግራት አውቃ እስከነመፍትሄው ነግራ ታጽናናቸው ነበር። በሽተኞችን ትፈውስ ነበር። ያዘነውን ታረጋጋ ነበር። ገዳሙን ከነበረበት ችግር አላቃ ወደ ትልቅ ገነትነት ለውጣዋለች ። እናም ብዙ ልጆችን(መነኮሳያት) አፍርታ እነርሱም እንደእርሷ የበቁ ለመሆን ችለዋል፡፡መሞት አይቀርምና ገዳሙን በደንብ ካስተዳደረች በኋላ በክብር አርፋለች፡፡

🙏ጸሎትና በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በታላቋ ቅድስት ጻድቅ ታማቭ ኢሪኒ ጸሎት ይማረን።🙏

Credit : ከወንድሜ ዲያቆን ሚካኤል fb page

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

#ዝክረ_አበው_መነኮሳት

ታላቁ ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር
''''''''''''''''''''''''''' '''''''''''''''''''''''''''
ይህች ቀን ታላቁ ብርሃን እና ቅዱስ መነኮስ ዮሐንስ አጭሩ ያረፈባት ናት። በላዕላይ ግብጽ የቤጻ ሰው ነበር፥ አንድ ወንድምም ነበረው። ወላጆቹ ጻድቃን እና እግዚአብሔርን የሚፈሩ፥በእምነት እና በጎ ስራ ባለጸጎች ነበሩ። 8 ዓመት ሲሆነው ልቡን ከዚህ አለም ምኞት እና ክብር መለሰ፤ የምንኩስናን ሕይወትም ይሻ ነበር።

የእግዚአብሔር ጸጋ ወደ አስቄጥስ በረሃ እንዲሄድ አነሳሳው፤ በዚያም ወደ ተፈተነ እና ቅዱስ ወደ ሆነው ወደ አባ ጴምዋ(ባይሞይ) ወደ ሚባል የአል-ብህናሳ ሰው መጣ። ዮሐንስ አብሮት ይኖር ዘንድ አባ ጴምዋን ጠየቀው። ቅዱሱም ሲፈትነው እንዲህ አለ፦"ልጄ ከኛ ጋር መቆየት አትችልም፥ ይህ ከባድ በረሃ ነውና፥ በውስጡም የሚኖሩት በእጃቸው ከሚሰሩት ነው የሚመገቡት፥ ብዙ አጽዋማትንም ይጾማሉ፥ ጸሎትም እንዲሁ፣ መሬት ላይ መተኛት እና ይህን የመሰለውን ብዙ ትሕርምት ይፈጽማሉ። ሂድ እና ወደ አለም ተመልሰህ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር"
አባ ዮሐንስም እንዲህ አለው፦"እባክህን ስለ እግዚአብሔር ስትል አትመልሰኝ፥ እኔ የመጣሁት በትዕዛዝህ እና ጸሎትህ ስር ለመሆን ነውና። ከተቀበልከኝ እግዚአብሔር ልብህን በኔ ደስ እንደሚያሰኘው አምናለሁ።" አባ ጴምዋ ምንም ነገር ቢሆን በፍጥነት ያለማድረግ ልምድ ነበረው፥ ስለዚህ ወጣት ሰው ጉዳይ እንዲገልጥለት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸለየ።

የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦለት እንዲህ አለው፦"ምርጥ ዕቃ ይሆናልና ተቀበለው።" አባ ጴምዋ ወደ ራሱ አምጥቶት የራሱን ጸጉር ላጨው። የመነኮሳትን ቀሚስ ዘርግቶ ለሦስት ቀናት እና ሌሊቶች ጸለየበት። ቀሚሱንም ሲያለብሰው መልአኩ የመስቀል ምልክት አድርጎ ሲያማትብበት ተመለከተ።
ቅዱስ ዮሐንስ የምንኩስና ሕይወቱን በታላቅ ትሕርምት እና ታላላቅ ስራዎች ጀመረ። ከዕለታት አንድ ቀን አባ ጴምዋ ሊፈትነው ወደደ፥ ስለዚህም እንዲህ እያለው ከበዓቱ አስወጣው፦"ካንተ ጋር መኖር አልችልም" ዮሐንስ ለ 7ቀናት በውጭ ኖረ። በየለቱም አባ ጼምዋ እየወጣ በዘምባባ ቅርንጫፍ ይመታው ነበር፥ ዮሐንስም "በድያለሁ" እያለ በፊቱ ይሰግድ ነበር። በሰባተኛው ቀን ወደ ቤተክርስቲያን ሊሄድ ወጣ፥ 7 መላዕክትም 7 አክሊላትን በአባ ዮሐንስ ራስ ላይ ሲያደርጉ ተመለከተ። ከዚያች ቀን ጀምሮ በክብር እና ፍርሃት ይይዘው ነበር።

ከዕለታት በአንዱ ቀን አባ ጴምዋ ደረቅ እንጨት አምጥቶ "ይህን እንጨት ውሰድ፥ ተክለህም ውሃ፣ አጠጣው" ብሎ አዘዘው። ቅዱስ ዮሐንስም ታዞ ከረጅም ርቀት(25ኪ.ሜ በላይ) ተጉዞ በቀን ሁለት ጊዜ ውሃ ያጠጣው ጀመር።ከሦስት ዓመታት በኃላ እንጨቱ ለምልሞ ፍሬ አፍርቷል።አባ ጴምዋ ከዚያ ፍሬ ጥቂት ወስዶ ለአረጋውያን መነኮሳት ሰጣቸው፥ እንዲህ እያለ፦"ውሰዱ ከመታዘዝ ፍሬ ብሉ" ይህ ዛፍ ዛሬም ድረስ በገዳሙ ይገኛል።

አባ ጴምዋ ለ12 ዓመታት ታሞ ተኛ፥ አባ ዮሐንስም ያገለግለው ነበር፥ ከአገልግሎቱ አንድም ቀን አጉድሎ አስታጉሎ አያውቅም ነበር። አባ ጴምዋ በብዙ የተፈተነ እና የደረቀ እንጨት እስኪመስል ድረስ ህመም ሰውነቱን ያደቀቀው ልምድ ያለው አረጋዊ ነበር፥ ይህም የተመረጠ መስዋዕት እንዲሆን ነው። አባ ጴምዋ ከዚህ አለም ለማረፍ ሲቃረብ አረጋዊ መነኮሳትን ሰበሰበ እና የአባ ዮሐንስን እጅ ይዞ እንዲህ እያላቸው ሰጣቸው፦"እርሱ ሰው ሳይሆን መልአክ ነውና ውሰዱት፥ አኑሩትም።" ዮሐንስም እንጨት በተከለበት ቦታ እንዲቆይ አዘዘው።

ከዚህን በኃላ የአባ ዮሐንስ ታላቅ ወንድም ወደ ገዳሙ መጣ፥ ከርሱም ጋር መነኮሰ። ክቡር መነኮስም ሆነ። ፓትርያርኩ አባ ቴዎፍሎስ አባ ዮሐንስን በገዳሙ መጋቢ እና አበምኔት አድርጎ እየሾመ ሳለ እጁን በራሱ ላይ ሲጭን እዚያ በነበሩት ሁሉ የተሰማ ድምጽ ከሰማይ መጣ እንዲህም የሚል፦"አግዚዮስ አግዚዮስ አግዚዮስ"(ይደሉ ወይም ይገባል ለማለት ነው)።

ይህ ቅዱስ መስዋዕት ባቀረበ ጊዜ ማን ሊቀበለው የተገባ እና ማን ያልተገባ እንደሆነ ያውቅ ነበር። አባ ቴዎፍሎስ በእስክንድርያ ለሠለስቱ ደቂቅ ቤተክርስቲያን ሰራ፥ ስጋቸውንም አምጥቶ በውስጡ ሊያኖረው ወደደ። አባ ዮሐንስን ጠርቶት ወደ ባቢሎን ሄዶ ቅዱሱን ስጋቸውን ይዞ እንዲመጣ ጠየቀው። ከብዙ ጽናት በኃላ አባ ዮሐንስ ይህን ተልዕኮ ለመሄድ ተስማማ። ከፓትርያርኩ ሲወጣ ደመና መጥቶ ወደ ባቢሎን ነጠቀው። ወደ ከተማዋ ገብቶ በውስጧ ሃውልቶቿን፣ ወንዞቿን እና ቤተመንግስቶቿን ተመለከተ፥ የቅዱሳኑንም ስጋ አገኘ። ከቦታቸው ሊያንቀሳቅሳቸው በጀመረ ጊዜ ከቅዱስ ስጋቸው እንዲህ የሚል ድምጽ መጣ፦"እስከ ሙታን ትንሳኤ(ዳግም ምጽአት) ድረስ ይህን ቦታ እንዳንለቅ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ቢሆንም ስለ አባ ቴዎፍሎስ ፍቅር እና ስላንተም ድካም ስንል በቤተክርስቲያን ውስጥ እንገለጣለን፣ ምልክት ይሰጣችኃል፦ ለአባ ቴዎፍሎስ እንዲህ በለው ሁሉንም ሰው በቤተክርስቲያን እንዲሰበሰብ እና በማብራዎቹ ዘይት እንዲጨምር ነገር ግን እንዳያበራቸው ንገረው ስንገለጥ መብራቶቹ ይበራሉ።"

አባ ዮሐንስ ወጥቶ ወደ እስክንድርያ ተመለሰ፥ ቅዱሳኑ ያሉትንም ለፓትርያርኩ ነገረው። ፓትርያርኩ እና ህዝቡ ሁሉ በቤተክርስቲያን ተሰብስበው ሳለ ድንገት መብራቶቹ በሩ፥ ሁሉም እግዚአብሔርን አመሰገኑት። ከዕለታት በአንዱ ቀን አንድ መነኩሴ ወደ አባ ዮሐንስ በዓት መጣ፥ መላዕክት ክንፋቸውን በላዩ እያርገበገቡ ተኝቶ አገኘው።

በኃላ ላይ በርበሮች ገዳሙን አጠቁት፥ አባ ዮሐንስም ሸሸ። ለምን እንደሸሸ ሲጠየቅ ሞትን ፈርቶ ሳይሆን እርሱን የሚገድለው በርበራዊ ሲዖል እንዳይገባ አዝኖ መሆኑን ተናገረ። ምንም እንኳ በአምልኮ ባይመስለውም በሰውነቱ ግን ወንድሙ ስለሆነ ነው። ከዚህን በኃላ በቀይ ባሕር። ወደ ሚገኘው ወደ አባ እንጦንስ ገዳም ሄደ። በዚያም በአንዲት መንደር አቅራቢያ ተቀመጠ፥ እግዚአብሔር የሚያገለግለውን ምዕመን ላከለት። እግዚአብሔር እረፍት ሊሰጠው እና ሊያሳርፈው በወደደ ጊዜ ዕረፍቱን እንዲነግሩት እና እንዲያጽናኑት የርሱን ሁለት ጻድቃን አባ መቃርዮስን እና አባ እንጦንስን ላከለት።

በእሁድ ዋዜማ ታሞ ተኛ፥ ረድዑንም የሆነ ነገር ከመንደሩ እንዲያመጣለት ላከው። መላዕክት እና የቅዱሳን ማህበር ቅድስት ነፍሱን ተቀብለው እሰክ ሰማያት አደረሷት። በዚያች ሰዓት አገልጋዩ ተመልሶ መጣ፥ የቅዱሱም ነፍስ በቅዱሳን ማህበር ተከባ፥ መላዕክቱም በነርሱ ፊት እየዘመሩ ተመለከተ። ከማህበሩም ሁሉ ፊት አንድ እንደ ፀሐይ የሚያበራ እና የሚዘምር አንድ ነበር። በዚህ ግሩም ነገር አገልጋዩ አደነቀ። አንድ መልአክ መጥቶም የእያንዳንዱን ቅዱስ ስም ነገረው። አገልጋዩም ከሁሉም ፊት ለፊት ያለውና እንደ ፀሐይ የሚያበራው ማን እንደሆነ ጠየቀው። የእግዚአብሔር መልአክም መልሶ እንዲህ አለው፦"ይህ የመነኮሳት አባት አባ እንጦንስ ነው።"አገልጋዩ ወደ በዓቱ ሲገባ ቅዱሱ ተንበርክኮ ነፍሱን እንደሰጠ አየ። ረድዑ በስጋው ላይ አለቀሰ፥ እንባውን አፈሰሰ፣ ፈጥኖም ተነስቶ የሆነወን ለመንደሩ ሰዎች ነገረ። ወደ አባ ዮሐንስ ስጋ መጥተው በታላቅ ክብር ተሸከሙት፥ ወደ መንደሩ ሲያመጡት ብዙ ድንቆች እና ተአምራት በስጋው ተፈጸመ።

ጸሎቱ እና በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፥ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን። አሜን።


@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

መጽሐፉ ይህንን አይልም የግኖስቲክ ትምህርት ኦርቶዶክሳዊ መልክ አሲዘን እናቅርብ

ምነው የመጥምቁ የዮሐንስን ልደት በሰኔ 30 አክብረን አይደል እንዴ

የጌታችንን የእመቤታችንን ብሎም የብዙ ቅዱሳንን ልደት እናከብራለን

ልደታችን እርኩሰት የለበትም ።የእግዚአብሔር ፍጥረት ነንና

ይልቁንም አከባበራችን ምን ይምሰል የሚለውን ብንነጋገር ይሻላል።

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

I am inviting you to download telebirr SuperApp, register and make a transaction to get reward. https://superapp.ethiomobilemoney.et:38443/customer/mgm/index0902.html#/?notoolbar=true&CampaignId=MGM1635518748044544&inviterId=1001927371008000&language=en&time=Sept-03-2024-Dec-02-2024

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

🔴ርዕሰ ዓውደ አመት🌼🔴ዘመነ❗️ማቴዎስ❗️የ2017 ዓ/ም🌼❗️ባሕረ ሐሳብ(አቡሻኽር) የዘመን ቆጠራ ትርጓሜ ❗️ቀጥታ🔴...
https://youtube.com/live/8hFriudWvdA?si=OCVfC_YM1RlEqeHe

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

#መጽሐፍተ መነኮሳት እንዲሁም
#መጽሐፈ ገነት ዘውእቱ ዜና አበው
በተጨማሪ ገድላትንም
group file ላይ ታገኛለህ ከዚህ ቀደም ተልከዋል

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

"በኃጢአት ወድቆ የነበረ ከወንድሞች አንዱ በካህኑ ከቤተክርስቲያን እንዲወጣ ተደረገ፥ አባ ቢሳሪዎንም "እኔም ኃጠአተኛ ነኝ" ብሎ አብሮት ወጣ።"
__በበረሃው ጉያ ውስጥ

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

#ዝክረ_አበው_መነኮሳት

ቅዱስ አባ ቢሳሪዮን ታላቁ
°°°°°°°°°°°°°    °°°°°°°°°°°°
በዚህች ቀን ታላቁ ተሓራሚ አባት አባ ቢሳሪዮን አረፈ። የተወለደው በምስር(ግብጽ) ከሀብታም ክርስቲያን ወላጆች ነው። ባደገ ጊዜ የምንኩስናን ሕይወት ይናፍቅ ነበርና ወደ አባ እንጦንስ ሄደ፥ በርሱም ስር ለተወሰነ ጊዜ ቆየ። ከዚያን ወደ አባ መቃርዮስ ሄደ፥ በርሱም ስር ለተወሰነ ጊዜ ቆየ።

ከዚህን በኃላ በበረሃ ውስጥ ዞረ፥ ጣሪያ ባለው ስፍራ አርፎ አያውቅም ነበር። ከዚህ አለም በፍጹም አንዳች ነገር አልነበረውም፥ ከአንዲት ሸካራ የቁርበት ልብሱ በቀር። ወንጌል ተሸክሞ የመነኮሳትን በዓት እያነባ የመዞር ልምድ ነበረው።

የሚያለቅስበትን ምክንያት ሲጠየቁት እንዲህ ብሎ ይመልስላቸዋል፦ "ሀብቴ ሁሉ ተሰርቋል፥ ከሞትም አምልጫለሁ። ቤተሰቦቼም ከክብር ወደ ወርደት ወድቀዋል"። ቃላቱ የሚገልጹት በመጀመሪያው አባት አዳም የቀደመውን ትዕዛዝ መጣስ ምክንያት የመጣውን የሰውን ልጅ ስላገኘው ውድቀት ነበር። ምን ለማለት እንደፈለገ ያልገባቸው እንዲህ ብለው ያጽናኑት ነበር፦" እግዚአብሔር የተሰረቀብህን ነገር ይመልስልህ"።

አባቶች ብዙ ተአምራቱን እና ስራዎቹን መዝግበውልናል። ከነርሱም አንዳንዶቹ፦
× በአንድ ወቅት ከሁለት ደቀመዛሙርቱ ዮሐንስና ዱላስ ጋር በቀይ ባሕር ዳር እየተጓዙ ሳለ ውሃ ተጠሙ። ቅዱስ ቢሳሪዮን ጥቂትቱን ጨዋማ ውሃ ወስዶ ሲጸለይበት ጣፋጭ ሆነ፥ ከርሱም ጠጡ።

× በሌላ ጊዜ ደግሞ በእርኩስ መንፈስ ተይዞ ያበደ ሰው አረጋውያኑ ይጸልዩለት ዘንድ ወደ አስቄጥስ አመጡ። አባ ቢሳሪዮን ውዳሴ ከንቱን እንደሚጠላ አረጋውያኑ ስለሚያውቁ ለታመመው ሰው እንዲጸልይለት አልጠየቁትም፥ ነገር ግን ሰውዬውን ቤተክርስቲያን ውስጥ ቅዱስ ቢሳሪዮን ዘውትር በሚቆምባት ስፍራ አስቀመጡት።
ቅዱስ ቢሳሪዎን ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣ ሰውዬውን በዚያ አንቀላፍቶ አገኘው፥ ሲቀሰቅሰው ሰውዬው በሙሉ ጤንነት ተፈውሶ አዕምሮው ተመለሰለት። እግዚአብሔር በእጆቹ ብዙ ተአምራት ፈጸመ። በሰላምም አረፈ።

ጸሎቱ ከኛ ጋር ትሁን። አሜን።

@hiwotemenekosat

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

❤️እንኳን ለጾመ ፍልሰታ ለማርያም እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን።🤲❤️

በየቀኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስንክሳር የሚታሰቡ

❣የቅዱሳን ታሪክ፣  ገድላቸው፣ ቃል ኪዳናቸው፣ የቅዱሳን ሰላምታ፣

❣የየቀኑ የቅዳሴ መልዕክታ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ የወንጌል ጥቅስ እና ምስባክ ይቀርብበታል።

🎙የነግህና የቅዳሴ ምስባክ በድምጽ

🎙ስንክሳር ምንባብ

እንዲሁም በባዕላት ቀን ማህሌትና ተጨማሪ መርሐ ግብሮችን ይዘን እንጠብቀዎታለን😊

💕join 💕በማለት ሁሉንም አንድ ላይ ያግኙ😊

JOIN

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

/channel/Orthodoxtewhado19

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

/channel/Orthodoxtewhado19

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

https://vm.tiktok.com/ZMr9LnHCb/

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

micky_yetewahedo/video/7369317533679144197?_r=1&u_code=0&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=dkcicd8me3ecdj&share_item_id=7369317533679144197&source=h5_m&timestamp=1721890036&social_share_type=0&utm_source=telegram&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7254179470089160454&share_link_id=89e19ff4-c384-49ae-a9f5-ba06e68fda9b&share_app_id=1233&ugbiz_name=Main&ug_btm=b2001" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@micky_yetewahedo/video/7369317533679144197?_r=1&u_code=0&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=dkcicd8me3ecdj&share_item_id=7369317533679144197&source=h5_m&timestamp=1721890036&social_share_type=0&utm_source=telegram&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7254179470089160454&share_link_id=89e19ff4-c384-49ae-a9f5-ba06e68fda9b&share_app_id=1233&ugbiz_name=Main&ug_btm=b2001

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

https://vm.tiktok.com/ZMr91T5ug/

Читать полностью…
Subscribe to a channel