hiwotemenekosatgroup | Unsorted

Telegram-канал hiwotemenekosatgroup - ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

245

✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን።✝️ ✞ይህ ሕይወተ መነኮሳት የተሰኘው ስለ ነገረ ምንኩስና ተባህትዎ የምንነጋገርበት የምንማማርበት መወያያ ግሩፕ ነው። ኑ እንደ አባቶቻችን በጥብዓት በተባሕትዎ እንኖር ዘንድ ሕይወታቸውን እንመርምር ሥርዓታቸውንም እንማር በፍኖተ አበው እንጓዝ በረከታቸውንም እናግኝ። 🔆 @hiwotemenekosat @hiwotemenekosatbot ሃሳብ መስጫ

Subscribe to a channel

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

፲፮ ለሥጋከሂ ዕቀቦ እምኲሉ እኩይ:
ሰውነትህን ከክፉ ነገር ሁሉ ከልክለው
ከዝሙት
(፩ም) መጻሕፍት ከከለከሉት ሁሉ ከልክለው
ወደ አንተ ትገባ ዘንድ ሴትን አታሰናብት(እሽ ብለህ አትፍቀድ)።
ሴትን በቦታ አትገናኝ
ወዳጅ እንደሚያበጁ ሰዎች የጡት ልጅ ፤ አበ ልጅ እያሉ ኋላ ግን ጠላት ሆነው ይገኛሉና።

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

፲፬ ኢትኩን መሰግለ ወኢመሠርየ::
ጠንቋይ ሥራየኛ ሟርተኛ አትሁን
አንተም በታመምክ ጊዜ ማንም ማን ይህን ያደርግልህ ዘንድ አድርጉልኝ አትበል።
እባብ ዘንዶ በነደፈህ ጊዜ ምች ባገህ ጊዜ



፲፭ ኢትሑር ኀበ ረቃይያን ይርቀዩ ለከ
ይረጩህ ዘንድ ቅጠል ዘፍዝፈው አስማት ደግመው በአጋንንት ስም ከሚረጩ ሰዎች አትሂድ።
በጥቁር ወረቀት በአርጃኖ ቁርበት ጨ፤ጨ፤ጅ፤ጀ የሚለውን ቃል አድርጉልኝ አትበል።
ቅጠል ዘፍዝፈው የሚረጩትን የሚያጠምቁትን እርጩኝ አጥምቁኝ አትበል
አንተም ይህን ለሌላውም ለራስህም አታድርግ።

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

፲፪ ወዓዲ ተዐቀብ መከኢትትዐረቅ እምልብስከ ቅድመ መኑሂ
በማንም በማን ፊት ዕራቁትህን ከመሆን ተከልከል
ቢወፍር ውጦ ውጦ ይሉታል ቢከሳ ውዳሴ ከንቱ ይሆንበታልና
የምትራቆትበት ምክንያት ቢያገኝህ ነው እንጅ ማለት የምትተኮስበት የምትታገምበት የምትጸበልበት(የምትታጠብበትም) ጊዜ ቢሆን ነው እንጅ።
፲፫ ወኢትበሎ ለእኁከ ዘጸርቅ።
ወንድምህን ታናሽ ጨርቅ ለባሽ ብለህ እትስደበው
ዲዳ ደንቆሮም አትበለው
በበዓል ከአሕዛብ ጋር አንድ አትሁን
\ሐተታ\ እንደ አረፋ ወዘተ ያለ በዓል አላቸውና
ቀዳም ቀዳምን /ቅዳሜን/ እንደ አይሁድ አትጠናቀቅ
\ሐተታ\ ከቆሙ አያርፉም ከዘረጉ አያጥፉም የሞተ አይቀብሩም ድውይ(የታመመ) አይጠይቁምና

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

፲ ወኢትጽአል
አትሳደብ ።
ቧልተኛ አትሁን።
(፩ም) ዋዛ ፈዛዛ አትናገር
ፈጽመህ/በፍጹም/ አትሳደብ።
ፈጽመህ/በፍጽም/ አትማል
ነገርህ እውነቱን እውነት ሐሰቱን ሐሰት /ያለውን አለ የለለውን የለም/ ይሁን እንጅ።

፲፩ ወሶበ ያጌብሩከ በል አእምር እስመ ጽድቅ እብለከ ወኡይሔሱ።
ግድ ማል ቢሉህም እውነት እንድናገር ሐሰት እንዳልናገር እወቅ በለው እንጅ /ይህም አትማል ላለው ነው/።

የፈጣሪህን ስም በመሐላ አትጥራ
በሌላ መሐላ አትማል ማለት በኢየሩሳሌም በራሳቹህም እንዲሁም በሌላም።
ቅዱስ ወንጌል እንደተናገረ ይህ ሁሉ ክሕደት ነውና ሊሠሩትም አይገባምና እግዚአብሔርንም ሰውንም ደስ አያሰኝምና።
እንዲህ ያሉትን ሰዎች ክብርት ቤተክርስቲያን በቀኖና ትለያቸዋለች እንጅ።
ከነሱ በግዝት ፤በተአምራት፤ በቀኖና፤ የምትለያቸውም አሉ።

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

📚⛪️ፊልክስዩስ⛪️📚

📜መጽሐፈ መነኰሳት ክፍል ሁለት📜
➥ይህ ፊልክስዩስ የተባለው መጽሐፍ ከጥንት የኢትዮጵያ ሊቃውንት የጻፉትና የተረጐሙት የኢትዮጵያ ቅርስ እንዳይጠፋ ቤተከርስቲያን በመጽሐፍ እጦት አንዳትቸገር የተለመደው ጸሎች እንዳይታጐል መነኰሳት ዘወትር እየመረመሩ እንዲጠቀሙበት ታተመ።

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

  🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

መጽሐፈ መነኮሳት ካላችሁ ብታጋሩኝ

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ክርስቶስ ተንስአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወስልጣን፤
አሠሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሰላም፤
እምይእዜሰ፤
ኮነ፤
ፍሥሐ ወሰላም።
   
📖 ተነስቷል! እንደ ተናገረ፤ ተነስቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ:: ማቴ (28:6)

📖 “ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል እንጂ በዚኽ የለም" ሉቃ 24፥5


"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:20፤)

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሰን!❤️

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ፈጣሪ ያስብህ ወንድሜ እኔማ መች ጸልዬ ፈጣሪ ይስማህ

አሜላ ላንተም መልካም በዓል!!!

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

እግዝአብሔር ይስጥልኝ ግን እመነኝ ለዚህ ቅዱስ ህይወት የተገባው አይደለሁም ሰው ስለጠየቀኝ ነው ሀሳብ ያነሳሁት ወንድሜ

ፈጣሪ እንዳሰብክልኝ በመንግስቱ ያስብህ

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ሰውነትህን ለመከራ አዘጋጅ✝
                         
Size 14.3MB
Length 40:58

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ስለ ገዳማዊ ህይወት የተዳሰሰበት ትምህርት ይጠቅማችሁ ይሆናል።

አድምጡት! 👂👈👈👈

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

በድጋሜ አመሰግናለሁ
ፈጣሪ ያክብርልኝ

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

እንዴት አመሻችሁ
እኔ ማን ሆኜ ነው ወደ ቅዱሳን መኖርያ ምሄደው? ሁሉን ጥለው ተከተሉት ሲል የትርጓሜ ስህተት እንዳይኖር ብዬ ነው ምክንያቱም አንድ ወጣኒ ገዳሙ ይቀበለው አይቀበለው ምንም አያውቅም ምናልባት ወደ ሌላ ገዳም ቢሄድ እንኳን አንድ አንድ ነገሮች ያስፈልጉታል ወይ ብዬ ግራ ስለገባኝ ነው

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ይቅርታ ግን ለምን እንደዚ ብለህ ጠየክ?

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

እግዚአብሔር ይመስገን እኔ እንደሚመስለኝ አንድ ሰዉ ለመመንኮስ ሲዘጋጅ ራሱን እንኳን ይዞ ገዳም አይገባ ( ማለትም ንብረት መያዙ ቀርቶ ራሱን እንኳን ገድሎ የሞተ ሰዉ ሆኖ ነዉ ገዳም የሚሄደዉ የሞተ ሰዉ ደሞ ምንም አይዝም ) ስለዚህ ምንም ነገር መያዝ የለበትም ባይ ነኝ ከተሳሳትኩ አርሙኝ

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ሰላም የእግዚአብሔር ልጆች
1, በሆሳእና /ህማማት ሳምንት የሚደረጉ እና የማይደረጉ/ የተከለከሉ ነገሮች ምንድን ናቸው
2,እና ሚፀለዩ እና ማይፀለዩ ፀሎቶች ምን ምን ናቸው ምታቁ እባካችሁ ንገሩኝ

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

አሜን እንኳን አብሮ አደረሰን።አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን ለሁላችሁም በርቱልን ።

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ስብከት የሚገኝበት ግሩፕ ካወቃችሁ ንገሩኝ

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

. The Orthodox Miracle
Of The Holy Light
Irrefutable evidence of the Truth of the Orthodox church is an event that has been occuring annually Jerusalem for nearly 2000 years. Various Christian religions perform their individual Easter prayers around the Tomn of Christ.
However, when the orthodox patriarch enters the cave ( which has been thoroughly searched), while holding 33 candles, symbolic of the 33 years of christ, an unexplained phenomenon occurs: Flashes of light suddenly appear from nowhere and light up the candles held by the patriarch as well as other candles held by the faithful in the crowd. Many expert scientists ( such as Pyro Analyst Alexandrovic Volkov), who officially researched this event in 2008 have given a responsible testimony confirming that the appearance of the Holy Light is unexplainable and is beyond the laws of nature. This fact has drawn so much attention that it is now been televised world-wide and is also streamed live over the internet.

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

📚⛪️አረጋዊ መንፈሳዊ⛪️📚

📜መጽሐፈ መነኰሳት ክፍል ሦስት📜
➥ይህ አረጋዊ መንፈሳዊ የተባለው መጽሐፍ ከጥንት የኢትዮጵያ ሊቃውንት የጻፉትና የተረጐሙት የኢትዮጵያ ቅርስ እንዳይጠፋ ቤተከርስቲያን በመጽሐፍ እጦት አንዳትቸገር የተለመደው ጸሎች እንዳይታጐል መነኰሳት ዘወትር እየመረመሩ እንዲጠቀሙበት ታተመ።

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

  🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

📚⛪️ማር ይስሐቅ⛪️📚

📜መጽሐፈ መነኰሳት ክፍል አንድ📜
➥ይህ ማር ይስሐቅ የተባለው መጽሐፍ ከጥንት የኢትዮጵያ ሊቃውንት የጻፉትና የተረጐሙት የኢትዮጵያ ቅርስ እንዳይጠፋ ቤተከርስቲያን በመጽሐፍ እጦት አንዳትቸገር የተለመደው ጸሎች እንዳይታጐል መነኰሳት ዘወትር እየመረመሩ እንዲጠቀሙበት ታተመ።

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

  🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

​​☀️ክርስቶስ ተንስአ እሙታን☀️
✨በዐቢይ ኃይል ወስልጣን
☀️አሠሮ ለሰይጣን☀️
✨አግዐዞ ለአዳም✨
☀️ሰላም☀️
✨እምይእዜሰ✨
☀️ ኮነ☀️
✨ፍሥሐ ወሰላም✨

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

#እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ የህይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት ቤተሰቦች ዛሬ እስኪ ካነበብኩት ትምህርት ላጋራችሁ የምፈልገው ነበረኝ
#በእንተ ምንኩስና ወገዳማዊ ህይወት በሚል ርዕስ ከገጽ 392 እስከ 445 ክፍል 4 መናፍቃን ምንኩስና ላይ የሚያነሱትን ጥያቄዎች አፋቸውን ከሚያሲዛቸው መልስ ጋር በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ተቀምጧል። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከትምህርተ ምንኩስና በተጨማሪ ሌሎችም የቤተክርስቲያን ዶግማ እና ቀኖናዎችን የሚያስተምር የመናፍቃንን ኑፋቄ እንደ መዶሻ ቀጥቅጦ በመልስ የሚያሰክራቸው መጽሐፍ ነው።

እና የለቀኩትን መጽሐፍ ከማንበባችሁ እና ከመክፈታችሁ በፊት መጽሐፉን አውርዳችሁ ከመጽሐፉ በስተቀኝ በኩል የሚገኙትን ሶስት ነጥቦችን በመንካት save to downloads የሚለውን ተጫኑት።

ምክንያቴ ደግሞ download ውስጥ በስልካችሁ ከተቀመጠ ለሌላ ጊዜም በነፃነት ታነባላችሁ ብዬ ነው።

#እግዚአብሔር በሚያውቀው ልብን የሚያረጋጋ ተመስጦን የሚሰጥ ምንኩስናን ከ"ሀ" እስከ "ፐ" ማለት በሚቻል መልኩ ከክርስቶስ እስከ አበው ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ከዛም እስከ ዳግም ምጽአት ድረስ ለሚኖሩ ክርስቲያኖች የተተላለፈውን የምንኩስናን ትምህርት የሚሰብክ አሪፍ ትምህርት ነው።

#እመኑኝ እስከ መጨረሻው በማንበባችሁ ትጠቀሙበታላችሁ እንጂ
ምንም አትከስሩም።

መልካም ንባብ!
መልካም የትንሳኤ በዓል!

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

አሜን! ግን አንተም ለክርስቶስ ሙሽራነት ይሁን ወይም ለተቀደሰው ትዳር ይሁን የተመረጥከው ላታውቅ ትችላለህ! እና ላንተም ይጠቅምሀል። ሁለቱንም ማለትም ትዳርንም ምንኩስናንም እወቅ ተማር ከዛም ከሁለቱም ኒውትራል ሁን ጸልይ በሱባኤ ሱባኤውን መያዝ ያለብህ ስለ ሁለቱም በቂ ዕውቀት ከኖረህ በኋላ ይሁን የዚያን ጊዜ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከላይ እንደፃፍኩልህ በተለያዩ ነገሮች ታውቃለህ እና ከመመንኮስ በፊት በት/ቤት ማለትም በአብነት መጽሐፍትን ማጥናት እንዳለብን ከማግባታችን በፊት ደግሞ በእጮኝነት መጠናናት እንደሚገባ ማወቅ አለብን!

#በምንኩስና ውስጥ ኖረህ በቆብ የምትወልዳቸው ብዙ የመንፈስ ልጆች ሊኖሩክ ይችላሉ።

ወይም

#በትዳር ውስጥ ከባለቤትህ ጋር በተቀደሰ ንፁህ መኝታ ካህናት፣ መነኮሳት፣ ጳጳሳት ወይም ምዕመን ክርስቲያኖችን ልትወልድ ትችላለህ።

ድንግል እናታችን የመዳናችን ምልክት የሀና እና የኢያቄብ ትዳር ውጤት ነች።

እና በደንብ ከእግዚአብሔር ጋር መወያየት መልካም ነው ይህም በጸሎት ነው። ዳዊት ሰኞ፣ ማክሰኞ እና ሀሙስ 30 መዝሙር።
ረቡዕ፣ አርብ እና ቅዳሜ 20 መዝሙር።
እሁድ ጸሎተ ነብያት እና መሐልየ ዘሰሎሞን።
ውዳሴ ማርያም የዕለት እና ይዌድስዋ መላእክት።

ጸልይ በርግጥ አንተን ለመምከር የማልችል ደካማ ፍጡር ብሆንም በጸሎትህ እንድታስበኝ ነው። 🥰

እናም ሌላው ከንስሐ አባትህ ጋር በደንብ መወያየት ንስሐ ገብተህ ቅዱስ ቁርባን መቀበል። ህይወትህን በቅዱስ ቁርባን ስትመራ የዚያን ጊዜ በአንተ የሚያድረው ክርስቶስ የህይወትህን መንገድ እንደ ፈቃዱ ይመራሀል። ዮሐ 6-50 ጀምሮ አንብብ።

ይሄን ካደረክ በቃ ሌላው ትርፍ ነው። እግዚአብሔር ያበርታህ።

መልካም የትንሳኤ በዓል!

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

እና ትንሽ የምጨምርልህ ሀሳብ አለኝ ከጠቀመክ ማለቴ ነው።
ከስሜት የተነሳ ወይም የቅዱሳንን ገድላት በማንበብ የመነጨ የምንኩስና ፍላጎት ከሆነ እመነኝ መንኩሰህ ከትንሽ ጊዜ በኋላ አዲስ አበባ ትገኛለህ ስለዚህ ተረጋግተህ አስበህ ምክንያትህ የክርስቶስ ፍቅር እንጂ የመነኮሳት አንድነት፣ የገዳም ውበት ወይም ዓለምን መጥላት አይደለም። ዓለም የሚጠላ ሳይሆን የሚናቅ ነው ዓለምም እግዚአብሔር የፈጠረው ለእንደኔ አይነት ደካሞች በመሆኑ ሊጠላ አይገባም ግን ከክርስቶስ ፍቅር የተነሳ ሊናቅ ይቻላል ምኑን በቅድሜከ በፊትህ የተናቀ ሊሆን ይገባል።

እና

ከምንኩስናም ከጋብቻም neutral ሁን ሁለቱንም እወቃቸው ተማራቸው ቀጥሎ ለንስሐ አባትህ አላማህን ነገረህ ሱባኤ ያዝ ከዛ ሆኖ፣ ታይቶህ ወይም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከንስሓ አባትህ ሰምተኸው ታገኘዋለህ። ወንድማዊ ምክር!

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ነጻ የምንሆነው መቼ ነው?✝
                         
Size 20MB
Length 57:29

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ስለ ምንኩስና በሰፊው ተዳሶበታል ይጠቅማችሁ ይሆናል።

አዳምጡት 👂 👈👈👈

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ምንም አያስፈልግም ቀጥታ የሚገቡ አሉ። ዋናዉ የንስሐ አባት ፈቃድ ነዉ። ከዛ ግን ያሉ ንብረቶች ካሉ ለነድያን ሰጥቶ መሄድ ብቻ ነዉ። በራቸዉን ሳይዘጉም ወጥተዉ የሚሄዱም አሉ። ገዳሙም ሳይደርሱ በጫካ የሚኖሩም አሉ እና ሁሉን ጥሎ ሲባል ያለፈዉን አንድ ሳይቀር መስቀሉን ብቻ ተሸክሞ መሄድ ነዉ።

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

የንስሀ አባትህን ማናገርና ንስሀ መግባት ይኖርብሀል ስርአቶችን መጠየቅም ተገቢ ነው ልቴድ አስበህ ነው

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

#የጌታ ፍቅር ክፍል 2

"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤

ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ሰላም እንደምን ናችሁ አንድ ጥያቄ ነበረኝ

አንድ ሰው ወደ ገዳም ለመግባት(ለመመንኮስ) ሲዘጋጅ ከውስጣዊ ዝግጅቶች በተጨማሪ ከቤቱ ሲወጣ ምን ሞን ነገሮችን መያዝ ይገባዋል ማለትም ከመንፈሳዊ መጽሐፍት በተጨማሪ ምን መያዝ አለበት ብታብራሩልኝ እወዳለሁ

ፈጣሪ ያክብርልኝ

Читать полностью…

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት መወያያ ግሩፕ

ቅድስት ሆይ ደስ ይበልሽ??? የልጄ የወዳጄ መቅደስ ማደሪያ የሆነ ሰውነታችሁን በሃጢአት እያነደዳችሁት እያፈረሳችሁት ልጄንም ዳግም እየሰቀላችሁብኝ አይደለምን? ታዲያ ስለምን ደስ ይበልሽ ትሉኛላቹ?! የልጄን ሕማም የልጄን ዋጋ ሁሉ ትታችሁ እረስታችሁ ስለምን ደስ ይበልሽ ትሉኛላቹ?! ከአይሁድ ይልቅ በልጄ ላይ እጅግ ከፍታቹበት የለምን እነርሱስ አንዴ ሰቀሉት እናንተ ግን ልጄ ወዳጄን የገረፋችሁብኝ የሰቀላችሁብኝ ቀናት ስፍር ቁጥር የላቸውም!!! ታዲያ ስለምን ደስ ይበልሽ ትሉኛላቹ?! በልጄ በወጃጄ ላይ ስለምን ይህን ያህል ከፋችሁበት ? ስለእናንተ ብሎ በመስቀል ስለተሰቀለ ነውን? ደሙንስ ስለናንተ ፍቅር እንደ እህል ስለዘራ ነውን? ቅዱስ ስጋውን ሳይሳሳ ስለቆረሰ ነውን? ታዲያ ስለምን ደስ ይበልሽ ትሉኛላቹ?! ቅድስት ሆይ ደስ ይበልሽ ስትሉኝ ከልቤ ደስ ይለኝ ዘንድ ልጄን ዳግም አታቁስሉብኝ አታድሙብኝ።

©የተዋህዶ ልጅ
@hiwotemenekosat

Читать полностью…
Subscribe to a channel