holyspiritflow | Unsorted

Telegram-канал holyspiritflow - holyspirit flow

479

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ሃይልን ትቀበላላችሁ በኢየሩሳሌም በይሁዳ በሰማሪያም እስከ ምድር ዳር ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ ሐዋ 1:8

Subscribe to a channel

holyspirit flow

ሐዋርያት 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በሊቃኦንያ ቋንቋ፦ አማልክት ሰዎችን መስለው ወደ እኛ ወርደዋል አሉ፤
¹² በርናባስንም ድያ አሉት፤ ጳውሎስንም እርሱ በመናገር ዋና ስለ ነበረ ሄርሜን አሉት።
¹³ በከተማውም ፊት ቤተ መቅደስ ያለው የድያ ካህን ኮርማዎችንና የአበባን አክሊሎች ወደ ደጃፍ አምጥቶ ከሕዝቡ ጋር ሆኖ ሊሠዋላቸው ወደደ።
¹⁴ ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል እየጮኹ ሮጡ፥
¹⁵ እንዲህም አሉ፦ እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

. ለምድነው የምንኖረው
መስከረም ጌቱ | Worship
ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ
sʜᴀʀᴇ ◈ JOIN ◈ sʜᴀʀᴇ
🔰ስምህን እንዘምረዋለን
♻️ @Lezemer_tube
♻️ @Lezemertubebot
✨ለበለጠ ቤተሰብ ይሁኑ✨
https://youtu.be/EeMbkGrd23E
━━━━━━⊱ 👀 ⊰━━━━━━

Читать полностью…

holyspirit flow

ፍቅርህ ነክቶኛል
🎤 ለዓለም ጥላሁን

Читать полностью…

holyspirit flow

" አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:16)

Читать полностью…

holyspirit flow

የምንጠብቀው የተነገረንን ከሆነ ማሰብ ያለብን ጊዜው የኛ አይደለም ስለዚህ መልሱን ቶሎ ቶሎ ማድረግ አንችልም ልክ የክረምቱን ጊዜ ወደ በጋ ማምጣት ማቅረብ እንደማይቻለው የጌታንም ጊዜ እንዲሁ ነው ከኛ የሚጠበቀው የተነገረን ነገር ላይ በጸሎት በመጽናት መጠባበቅ ብቻ ነው ለሀዋሪያት በድንገት እንጂ እነሱ ባዘጋጁትለት ሰዓት አልመጣም በድንገት ስለሚል የጌታ ጊዜ መሆኑን ያሳያል። ጊዜው የኛ ካልሆነ የኛ የሆነው በመጸለይ መጠበቅ ብቻ ነው ብዙዎቻችን ጸሎቱንና ጽናቱን ትተን እየጠበቅን ነው ማለት የለብንም እየጠበቅን ከሆነ በመንቃት ብቻ ነው
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

👉 ክርስትና ማለት የክርስቶስ ተከታይ ነው፡፡ የሚከተለውን አውቆ እስከ መጨረሻው ድረስ የሚሄድ እንጂ፦
ደስ ሲለው😃 የሚሄድ ሚመስል ሲያዝንና ስሜቱ ሲጎዳ😞 የሚቆም አይደለም፡፡
➡️ ክርስቲያን✝ በሚሄድበት መንገድ ላይ ሊያስቆመው የሚፈልጉ ነገሮች ብዙ ናቸው፡፡ ግን ለነዚህ ሊያስቆሙት የፈለጉትን ነገሮች በሰማቸውና በተዘናጋ መጠን መቆሙ አይቀርም፡፡
👉የማይቆሙ ሰዎች መንገዳቸው ላይ ለገባውን ነገር ትኩረት እየሰጡ የሚያስተናግዱ ሳይሆኑ የፈለገ ነገር በኔ ህይወት(መንገድ) ይምጣ ዋናዬን አያስጥሉኝም እያሉ focus አርገው የሚቀጥሉ ናቸው፡፡
👉 በየቀኑ ድምፆች🗣 ይመጣሉ እናንተን ከፀሎት ለመከልከል እነዛን ድምፆች እያስተናገዳችሁ መደራደር እና መስማት ስትጀምሩ ከፀሎት እና ከጌታ መገኘት አንድ step መራቅ ትጀምራላችሁ ፡፡ አትደራደሩ፣ ለጸሎትም ቀጠሮ እየሰጣችሁ ነገ ወይም ቡሀላ እጸልያለው አትበሉ focus አርጉ፣ መንገዳችሁ ላይ የመጣ ነገር እንዳያስቆማችሁ💪💪
*⃣ እንትና ሰደበኝ ብላችሁ ጸሎት አታቁሙ
*⃣ ዛሬ ደብሮኛል አልጸልይም ነገ ምናምን አትበሉ ዛሬ ጸልዩ የነገው አይታወቅም ጸሎት በደበረኝ ወይም በተመቸኝ አይመራም በየትኛውም ቦታ በእስር ቤት፣ መንገድ ላይ ፣ taxi ውስጥ፣ በህብረት ፣ ብቻችንን መጸለይ እንችላለን 🔥🔥
ስማኝ ወንድሜ / ስሚኝ እህቴ🗣🗣
👉 የጀመርነው ከእግዚአብሄር አንፃር ከሆነ ለምን በሰዎች ምክንያት እንቆማለን🤷‍♂🤷‍♀ ?
👉 የጀመርነው ከእግዚአብሄር ደስታ አንፃር ከሆነ ለምን እንትና አዘነበኝ/ አዘነችብኝ 🤦‍♂ ብለን ከጀመርነው መንፈሳዊ ጉዞ እንቆማለን🤷‍♂ ?
➡️ ክርስቲያን በጌታ ፈገግ ብሎ የቀረ😁😄😀🤣 እንጂ እዚ እታች ያለ ምድራዊ ነገር ደስታውን የሚወስንለት ወይም ሲያገኝ ሲያገኝ የሚዘምር የሚያመሰግን፣ ካላገኘ ደግሞ የማይደሰት ጸሎት የሚያስጠላው ተደርጎ የተሰራ ማንነት አልተሰጠውም፡፡
➡️ዝም ብለህ በጌታ ተደሰት ያኔ ምድራዊ ነገር አንተን የማስደሰትም የማሳዘንም ሀይል የለውም ሀይሉ ከአንተ ይወሰድበታል፡፡
👉 @holyspiritflow 👈
👉 @holyspiritflow 👈
👉 @holyspiritflow 👈

Читать полностью…

holyspirit flow

“ክፋት በልቡ ሳለ ፍቅርን የሚናገር ከንፈር በብር ዝገት እንደ ተለበጠ የሸክላ ዕቃ ነው።”
— ምሳሌ 26፥23

Читать полностью…

holyspirit flow

አንዲት ሴት በእርግዝናዋ ወራት ምጥ የሚባል የተፈጥሮ ስርአት ይመጣባታል ለምን መጣ? እንዴት መጣብኝ? አትልም ምክንያቱም የመጣባት ምጥ በውስጡአ ምን እንዳለ ምስክር ነው፡፡ ስለዚህ በህይወታችን የሚመጡ ምጦች ወይም ፈተናዎች በውስጣችን ፕሮግራም እንዳለ ማሳያዎች ናቸው፡፡ስለዚህ ስንፈተን ለምን ጌታ ሆይ ፈተና መጣብኝ🤦‍♂?? ማለት የለብንም ምክንያቱም ውስጣችን ነገር እንዳለብን ማሳያዎች ናቸው፡፡ ያላረገዘች ሴት ምጥ የለባትም ውጋት የለባትም ምክንያቱም ውስጡአ ልጅ የለም፡፡ ዶክተሮች እንደሚሉት በውስጡአ ልጅ የያዘች ብቻ ነው ምጥ የሚባለው ነገር የሚመጣባት even በውስጡአ ልጅ ኖሮ ህይወት ከሌለው ወይም ከሞተ ምጥ የለም ይላሉ፡፡ ስለዚህ መፈተን በራሱ እድል ነው በውስጣችን ህይወት ያለው ፕሮግራም ወይም ያልጨነገፈ እንደሆነ የሚያረጋግጥልን ነውና፡፡ ዮሴፍ ሲፈተን የመጣበት ፈተና በውስጡ program ስላለበት የመጣ ነው፡፡ ሙሴ ሲወለድ ጀምሮ ሊገሉት ይፈልጉ ነበር ይሄ ፈተና ፕሮግራም ስላለበት የመጣ ፈተና ነው፡፡ እንዲሁም ከፈርኦን ቤት እምቢ ብሎ ወደ ጥሪው ሲመጣ ቀላል ፈተና አልገጠመው በንግስና በድሎት ያለምንም ፈተና ከሚኖርበት ቤት ወደ ጥሪው ወደ ፕሮግራሙ ሲመጣ በዘመኑ መቶበት የማያውቅ ፈተና ነው የመጣበት ይሄ በውስጡ ፕሮግራም እንዳለበት ማሳያ ናቸው፡፡ አሁንም ሴጣን stratagey ቀየረ እንጂ አሁንም ፕሮግራም ያለባቸውን እነ ሙሴ ዮሴፍ even እየሱስን ለመግደል እስከ መፈለግ ድረስ በፈተነበት መንገድ በዚህ ዘመን ፕሮግራም ያለባቸውን ለማስቆም ይፈልጋል ስለዚህ የመጡብን እና ገና የሚመጡብን ፈተናዎች በውስጣችን ፕሮግራም አለባችሁ ይሉናል እንጂ አያስቆሙንም😁፡፡ ፈተና ካለ የተሻለ የመለኮት ሀሳብ መስራት ሊጀምር ነውና አትጠራጠሩ Revival is coming ተዘጋጁ ተዘጋጁ ተዘጋጁ🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
@holyspiritflow
@holyspiritflow
@holyspiritflow
ይህን👆👆 ያነበበ ለሌሎች share ያርግ ተባረኩ 🖐

Читать полностью…

holyspirit flow

ሰዎች ስለ እናንተ ማውራታቸውን የሚያቆሙት እናንተ መስራት ስታቆሙ ነው ሁልጊዜ የሚወራበት ሰው እየሰራ ስለሆነ ነው!!!!!!!!
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

እርግጠኛ ነኝ አብዛኞቻችን አይኖቻችን ይከፈት ብለን ጸለየናል ግን ለምንድነው አይኖቻችን የሚከፈቱት? 🤔
👉 (የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 24)
----------
13፤ እነሆም፥ ከእነርሱ ሁለቱ በዚያ ቀን ከኢየሩሳሌም ስድሳ ምዕራፍ ያህል ወደሚርቅ ኤማሁስ ወደሚባል መንደር ይሄዱ ነበር፤

14፤ ስለዚህም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር።

15፤ ሲነጋገሩና ሲመራመሩም፥ ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር፤

16፤ ነገር ግን እንዳያውቁት ዓይናቸው ተይዞ ነበር።
👉 በዚህ ክፍል ኢየሱስ አጠገባቸው እያለ አላወቁትም ይለንና ምክንያቱን ሲነግረን አይኖቻቸው ተይዞ(አልተከፈተም ነበረ) የአይን መከፈት የሚሠጠን እየሱስን እንድናውቅ ነው
👉ብዙዎቻችን አይኖቻችን እንዲከፈቱ የምንፈልገው አጋንንት ለማየት ትንቢት ለመናገር የሆነ የሰው ጓዳ ጎርጓዳ ለማየት ይመስለናል ግን እንደዛም ለመሆን አይኖቻችን መከፈት ቢኖርባቸውም ዋናው የአይን መከፈት አላማ ግን የሰው ጓዳ ለማወቅ ሳይሆን ኢየሱስን እንዳውቀው ነው እነዚህን ነገሮች መናቄ አይደለም እነዚህም ሁሉ ግን ኢየሱስን ከማወቃችኝ የተነሳ የሚሆኑልን ነገሮች ናቸው።
👉

(የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 24)
----------
30፤ ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው፤

31፤ ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም፤ እርሱም ከእነርሱ ተሰወረ።
➡️ በመጨረሻም አይኖቻቸው ሲከፈቱ ኢየሱስን አወቁት እንደሚል ብዙ ተዓምር ሲሰራ በአይናቸው ቢያዪም ተዓምራት በማየት ብዛት ኢየሱስን አላወቁትም አይኖቻቸው ሲከፈት ግን አወቁት አያችሁ አይኖቻችን ሲከፈት መጀመሪያ ኢየሱስ ማን እንደሆነ እናውቃለን ከዚያ ቡሀላ ነው ሌላው የሚከተለው አይኖቻችን ይከፈቱ
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

“በዓይንህ ያለውን ምሰሶ ራስህ ሳታይ፥ እንዴት ወንድምህን፦ ወንድሜ ሆይ፥ በዓይንህ ያለውን ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ ልትል ትችላለህ? አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ ከዚያም በኋላ በወንድምህ ዓይን ያለውን ጉድፍ ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።”
— ሉቃስ 6፥42

Читать полностью…

holyspirit flow

👉 ብዙን ጊዜ ብዙዎቻችን የሚከብደን መጀመር ሳይሆን መጨረስ ነው አብዛኞቻችን ብንጠየቅ ጸሎት ጀምሬ ነበረ አሁን ግን....😏፣ መንፈሳዊ ነገሬ ጥሩ ነበር አሁን ግን አልቻልኩም 🤦‍♂ የምንል ብዙ ነን። እርግጠኛ የማደርጋችሁ እግዚአብሄር ጋር ችግር የለም ሙሉ ለሙሉ ችግሩ እኛ ጋር ነው።
👉 መንፈሳዊ ነገራችን በጅምር እንዳይቀር ብቸኛው በትዕግስት ለመጨረስ ዙሪያውን የሚያይ ሳይሆን ግቡን የሚያይ ኢየሱስ ላይ የሚያተኩር ልንሆን ይገባል።👇👇👇
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 14)
----------
28፤ ጴጥሮስም መልሶ። ጌታ ሆይ፥ አንተስ ከሆንህ በውኃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ አለው።

29፤ እርሱም። ና አለው። ጴጥሮስም ከታንኳይቱ ወርዶ ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውኃው ላይ ሄደ።

30፤ ነገር ግን የነፋሱን ኃይል አይቶ ፈራ፥ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ። ጌታ ሆይ፥ አድነኝ ብሎ ጮኸ።
👉 ጴጥሮስ ጥሩ ጀምሮ እየሄደ ነበረ ለምን ዙሪያውን ወይም ንፋሱን አየ? 🤔 ያኔ ነው መስጠም ጀመረ የሚለን መጽሀፉ እየሱስን እያየን መንገዳችን ካልቀጠልን ሰይጣን ዙሪያችንን እያየን እንድንሰጥም ይሰራል። ያኔ ጥሩ ጀምሬ ነበረ አሁን ግን..😏 እንዳንል ኢየሱስ ላይ እንፍዘዝ ጠዋት ማታ የሚያንገበግበን ስለ ኢየሱስ ይሁን ኢየሱስ ላይ የፈዘዘ ሰው ችግር ሳይሆን የሚያስለቅሰው ፍቅር የሚያስለቅሰው 😭።
👉 እያነበብክ/ሽ ከሆነ ዛሬ አስተውል/ይ የወደቅሽባቸው ቀናት ዞረሽ ተመልከቺ ኢየሱስ ላይ ስላላተኮርሽ ለመንፈሳዊ ነገር ጊዜሽን ቀንሰሽ ለሌላ ነገር ስትሮጪ ነበረ አንተም ወንድሜ እንደዛው ዛሬ የተውነውን ነገር እንደገና እናንሳ ታላቅ የሆነ ሪቫይቫል በኢትዮጵያ🇪🇹 እና በኤርትራ🇪🇷 እየመጣ ነው በእውነት እየመጣ ነው በሚሰራበት ቀን አብሮ ሰራተኛ ለመሆን ለጸሎት ለቃሉ ለመንፈሳዊ ነገር ትኩረት እንስጥ
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

(መጽሐፈ ነሀምያ ምዕ. 6)
----------
1፤ እንዲህም ሆነ፤ ቅጥሩን እንደ ሠራሁ፥ ከፍራሹም አንዳች እንዳልቀረበት ሰንባላጥና ጦብያ ዓረባዊውም ጌሳም የቀሩትም ጠላቶቻችን ሰሙ፤ ነገር ግን እስከዚያ ጊዜ ድረስ በበሮቹ ውስጥ ሳንቃዎቹን አላቆምሁም ነበር።

2፤ ሰንባላጥና ጌሳም። መጥተህ በኦኖ ሸለቆ ውስጥ ባሉት መንደሮች እንገናኝ ብለው ላኩብኝ፤ ነገር ግን ክፉ ያደርጉብኝ ዘንድ ያስቡ ነበር።

3፤ እኔም። ትልቅ ሥራ እሠራለሁ፥ እወርድም ዘንድ አይቻለኝም፤ ሥራውን ትቼ ወደ እናንተ በመውረዴ ስለ ምን ሥራው ይታጐላል? ብዬ መልእክተኞችን ላክሁባቸው።
👉 ሁልጊዜ ውጊያ የሚገጥመን መስራት ስንጀምር ነው ነህሚያ ቅጥሩን ለመስራት ባይነሳ ኖሮ በንጉስ ቤተመንግስት ውስጥ ተመቻችቶ ይኖር ነበረ የሚነካውም አልነበረም ነገር ግን ምቾቱን ጥሎ የእግዚአብሄርን ሀሳብ ለማድረግ ሲነሳ ነው የሚፈታተኑት ሰዎች የተነሱበት።
👉 በጣም የሚገርመው እኛም comfort zone ውስጥ ተመቻችተን ካለን የሚነካን የለም ችግር አይበዛብንም ምክንያቱም ምቾታችን ውስጥ የራሳችንን እንጂ የጌታን ፈቃድ ስለማናደርግ ነገርግን ምቾቴን ለቅቄ ለጌታ ልኑር ብላችሁ መጸለይ ስትጀምሩ መቀጣጠል ስትጀምሩ አይታችሁት የማታውቁት ችግር ይገጥማቹሀል ምክንያቱም ሰይጣን እንደዛ እንድትሆኑ አይፈልግም እርግጠኛ የማደርጋችሁ የጌታ ጥሪ አለባችሁ ይህን በውስጣችሁ ያለውን ጥሪ ለመኖር ስትነሱ ለመስራት ስትነሱ በዙሪያችሁ ቶሎ ብለው የሚመጡት ለነህሚያ እንደተነሱበት እንደነ ሰንበላጥ እና ጦቢያ የሚባሉ አንተን ብሎ ዘማሪ፣ አንተን ብሎ ሰባኪ ከሰፈር አታልፋም የት ለመድረስ ነው? የሚሉን ሊነሱብን ይችላሉ ነገር ግን እንደነዚህ ያሉ ድምጾችን እየሰማን ከሆነ ወደፊት መቀጠል ወደ ግብ መድረስ መጨረስ አንችልም ለነህሚያ "ና ውረድና በ ኦና ሸለቆ እንነጋገር" ብለው መልዕክት ቢነግሩትም እሱ ግን የጀመርኩትን ሳልጨርስ አልወርድም ነበር ያለው።
👉 የአባቴ ልጆች የጀመራችሁትን የጌታን ጥሪ ሊያስጥላችሁ የድርድር መድረክ ጠላት አዘጋጅቷል እናንተ ከወረዳችሁ ከጥሪያችሁ ወይም ከጀመራችሁት ነገር ተመልሳችሁ እንዳትወጡ አድርጎ ጸጋችሁን ሊበላ ይፈልጋል ስለዚህ ዛሬ የሚመጣባችሁን ድምጾች እንድትወርዱ እንድታቆሙ የሚፈልጉትን አትስሙ አትውረዱ!!!!!!!!!! ወርዳችሁ ሀሜት ሰፈር፣ ወርዳችሁ ወሬ መንደር፣ ሀጢያት መንደር አትገኙ እናንተ ጥሪ አለባችሁ እንቢ በሉ!!!! ኑ እንዲህ እናድርግ ሲሉ አይ አይመጥነኝም የኔ level አይደለም አልወርድም ከዚህ ከፍታዬ በሉ!! አለበለዚያ ሰፈር ውስጥ እንቀራለን ከጥሪያችን እንጎላለን።
👉 ዮሴፍ ና እንተኛ ስትለው እሺ ቢል ኖሮ ከጥሪው ከተፈጠረበት አላማ ይጎል ነበረ ለዛ ነው እንቢ ብሎ ወደ ተነገረው ቦታ የደረሰው እንቢ የማንልና የምንደራደር ከሆነ ከተነገረልን እንቀራለን ተራ ሰዎች ሆነን እንሞታለን እናስተውል ሰይጣን አይተኛም!! እንቢ በሉ እንደ ሳምሶን ከደሊላ ጋር የምትደራደሩ ከሆነ ጥሪያችሁን ታጣላችሁ ይሄ ጥሪ ለድርድር አይቀርብም!! ወረዳችሁ አትደራደሩ እንቢ ብላችሁ ወደ ተነገረላችሁ ግቡ ምርጫው በእጃችን ነው ወይ እንቢ ብሎ ከጌታ ጋር መቀጠል ወይ እሺ ብሎ ከተፈጠርንበት አላማ መጉደል የቱ ይሻለናል?????🤔
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

👉 አንድ ህጻን ልጅ ለእድገቱ ወተት ያስፈልገዋል የሚመገበው ምግብ እርሱን physicaly mentaly እያሳደገው ይመጣል በጣም የተመጣጠነ ምግብ የሚበላ እድገቱ ጥሩ ይሆናል እንዲሁም በሽታ የመከላከል አቅም ያገኛል። ስለዚህ እድገተችንን የሚሰጠን የተመጣጠነ ነገርከ መብላታችን ነው። የፈለገ ሰው አታድግም አትለወጥም ቢለን መብላት እስካላቆምን ማደግ አይቀሬ ነው ምንም ቢባል እናድጋለን እንዲሁ መንፈሳዊ ህይወታችን የሚያድገው ቃሉን በመብላት እንዲሁም በጸሎት የምንኖረው ከሆነ የፈለገ ሰው ቢመቀኝ ባይመቀኝ እናድጋለን።
👉 ጌታ ኢየሱስ 33 አመት በምድር ሲኖር disciplined ነበር በጣም የሚገርመኝ ከእናትና አባቱ ጋር ወደ ሙክራብ(ቤተክርስቲያን) ይሄድ ነበር ስርአቱን ያከብር ነበር። የሚገርመው ያኔ ተራራ ላይ ለሙሴ የሰጠውን ህግ እንዳላወቀ ሆኖ ቁጭ ብሎ ሰምቶ ይወጣ ነበር እስከ 30 አመቱ በዚህ መንገድ disciplined ነበር ጌታ ሊያስተምረን የፈለገው የምንማርበት ጊዜ አለ የምናስተምርበት ጊዜ አለ የምንሰማበት ጊዜ አለ ሰዎች እኛን የሚሰሙበት ጊዜ አለ ግን የሚገርመው ጌታ ለመሞት ስለሚመጣ በአንድ ጊዜ 33ተኛው አመት ሰው ሆኖ አልመጣም process ተከትሎ እንደማንኛውም ሰው ነው የመጣው እራሱን የሚያዘጋጅበት ጊዜ እና እራሱን የማብቃት ስራ የሰራበት ጊዜ ነበር። የጌታ ልጆች ድግስ ደግሰን 500 ሰው ጠርተን ለ200 ሰው የሚሆን ምግብ እንደማናዘጋጀው ሁሉ ነገ ሚሊዮኖች ይብቁናል ለነሱ ሁሉ የሚበቃ ነገር የሚበቃ መልእክት ያስፈልገናል ለዚህ ደግሞ disciplined መሆን እና ወደፊት የሚመጣ የራሳችን ጊዜ እንዳለ አውቀን በትእግስት እንጠብቅ ለማደግ እንስራ ከተለምዶ ህይወት እንውጣ።
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

አዳምና ሄዋንን እግዚአብሄር በህልውናው ውስጥ እንዲኖሩ ትልቅ እድል ሰጥቶአቸው ነበር። በጣም የሚገርመው በህልውናው ውስጥ እራቁትነት የሚባል ነገር አይታያቸውም ነበር ምክንያቱም በመገኘቱ ውስጥ ሁሉ የሞላን እንጂ ጉድለት የሚባል ነገር አይታያቸውም። የሚያሳዝነው ግን በሀጢያት ምክንያት ከእግዚአብሄር ፊት ጠፉ የመጀመሪያው የሀጢያት ስራ የጌታን ፊት ነው የሚያሳጣን ለዚህ ነው እንዲህ የሆነው👇

(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 3)
----------
8፤ እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፤ አዳምና ሚስቱም ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ።

9፤ እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ። ወዴት ነህ? አለው።
👉 በዚህ ቃል ውስጥ ለምንድነው የእግዚአብሄር ድምጽ አዳምን ወዴት አለህ ብሎ የፈለገው?🤔 እግዚአብሄር የት እንዳሉ አያውቅም? ወይስ እሱ ሁሉን አዋቂ አይደለም?🤔
👉በጣም የሚገርመው እግዚአብሄር ሁሉን አዋቂ ስላልሆነ ሳይሆን ይፈልጋቸው የነበረው ከፊቱ ስለታጡ ወይም እሱ ባለበት ስላላገኛቸው ነው ወዴት እንዳሉ የሚጠይቀው። በዘመናችን ፊቱን ካጣን ወይም ከፊቱ ከታጣን የሴይጣን መጫወቻ እንሆናለን።
👉 እናስተውል ጌታ የቅባት ችግር የለበትም የአገልጋይ ችግር የለበትም እኛ ለሱ የቀናን መስሎን የምናደርጋቸው ነገሮች በራሳቸው ጥሩ ቢሆኑም በነዚህ ምክንያቶች ግን ፊቱ ከኛ ካዞረብን እንደኛ የከሰረ ሰው የለም ምክንያቱም እኛን በተለየ ቅባት አገልግለውን እነሱ ግን ከጌታ ፊት የታጡ አሉ ስለዚህ ስለ ጸጋ ስጦታ መጸለይ ጥሩ ቢሆንም ጌታ ግን አላቃተውም ለኔ እሱን ለመስጠት ከኔ የሚፈልገው ነገር አለ ያ ደግም ሁሌ ፊቱን እንድፈልግ እናም ፊቱን እያየው እንዳገለ ግልለት።
👉 በዚህ ዘመን ብዙ ሰው የጌታን ፊት እያየ ከማገልገል ይልቅ የሰውን ስሜት እያየ የሚያገለግል በዝቱአል ከዚህ የተነሳ ጸሎታችን ሁሉ ፊትህን አሳየኝ ፊትህን አትውሰድብኝ የሚለው ቀርቶ አጋንንትን ላውጣ፣ ትንቢት ልናገር ፣ ሽባ ይፈወስ ምናምን ሆኑአል እነዚህን ነገሮች መናቂ አይደለም ግን እነዚህ እኮ gift ናቸው እነዚህን ከሰጠን ቡሀላ ፊቱን ከከለከለን ኪሳራ ነው ስለነዚህ ጉዳይ መጸለይ ጥሩ ቢሆንም ዋና ጸሎታችን ፊትህን ሊሆን ይገባል😭 ዛሬ ፊቱን ከኛ የወሰደው ምንድነው? ስናገለግልስ ፊቱን እያየን ነው? ዛሬ ጸሎታችንን እንቀይራለን ፊትህን አሳየን ብለን
" አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ። አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።"
(መዝሙረ ዳዊት 27:8)
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

(መጽሐፈ መክብብ ምዕ. 5)
----------
10፤ ብርን የሚወድድ ሰው ብርን አይጠግብም፤ ባለጠግነትንም የሚወድድ ትርፉን አይጠግብም፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

11፤ ሀብት ሲበዛ የሚበሉት ይበዛሉ፤ ሀብቱን በዓይኑ ብቻ ከማየት በቀር ለባለቤቱ ምን ይጠቅመዋል?

12፤ እጅግ ወይም ጥቂት ቢበላ የሠራተኛ እንቅልፍ ጣፋጭ ነው የባለጠጋ ጥጋብ ግን እንቅልፍን ይከለክለዋል።
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

በጣም እርግጠኛ የማደርጋችሁ ነገ ማለት የዛሬ ድምር ውጤት እንደሆነ ነው። ነገአችን የሚመስለው ዛሬ እየሰራንበት ያለንበት ነገር ላይ ነው ነገ የመለኮት ሀይል በእኛ እንዲገለጥብን የምንፈልግ ከሆነ ዛሬ የምንጠማ መሆን አለብን። በጣም የሚሰማኝ እየቀረበ ያለ የመንፈስ ቅዱስ እሳት አለ ያንን ግን ለማግኘት የኛን expectation ይፈልጋል ሰማይ ደግሞ መለኮታዊ ሀይሉን expect ላላደረገ ሰው ሰጥቶ አያውቅም የምንጠባበቀው ነገር ከሌለ የሚወርሰን ነገር የለም።
👉እኔ የማምነው ለውጥ ያለው በ process ነው ብዬ ነው ለዚህ ደግሞ የእኔን ነገር ሰማይ በprocess ካስጨረሰኝ ቡሀላ ነው የሱን ነገር የሚሰጠኝ ስለዚህ በአንዴው ሁሉም ነገር እንዲለወጥ ጌታ በእኛ እንዲሰራ እንፈልጋለን ግን ዋናው ቁም ነገር ሰማይ በኛ ከመስራቱ በፊት እኛን ነው የሚሰራው ስለዚህ አሁን በጓዳችን ስላለው ህይወት አትኩረን እናስብ እንዘጋጅ!!!!!
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

የጌታ ልጆች አንድ መሰረታዊ ነገር ልንገራችሁ፦

(መጽሐፈ መሳፍንት ምዕ. 13)
----------
24፤ ሴቲቱም ወንድ ልጅ ወለደች፥ ስሙንም ሶምሶን ብላ ጠራችው፤ ልጁም አደገ እግዚአብሔርም ባረከው።

25፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ሊያነቃቃው ጀመረ።
*⃣ በዚህ👆ክፍል ውስጥ የሳምሶን እድገት የታየበት ክፍል ሲሆን ይህ እድገት ማሳየቱ ለቀጣይ ምእራፎች ሀላፊነት እንዲሰጠው አንዱ ምክንያት ሆኖታል ስለዚህ አንድ ሰው ካልበሰለ( matured ) ካልሆነ ቀጣይ ምዕራፎቹን የተለመደ እና ያልተለወጠ ያረጉታል ስለዚህ እግዚአብሄር የፈለገ ቃል ቢሰጠውም ፕሮግረሙን ቢነግረውም ላላደገ ሰው ሀላፊነት አይሰጠውም፡፡
*⃣ ቁጥር 25 እንደሚናገረው ዳን በሚባለው ሰፈር ውስጥ ያነቃቃው ነበር ይላል፡፡ መንፈስቅዱስ ወደ ሳምሶን ህይወት በመምጣት በማነቃቃቱ የሚቀጥለው ምእራፍ እንዴት ባለ ሀይል💪 እና አዲስ ማንነት እንድናየው እንዳረገን እናያለን ፡፡ ከዚህ ምዕራፍ ቡሀላ ባሉት ምዕራፎች ከሰው ስርዐት ውጪ አንበሳን እንደ ጠቦት ሲገነጥል ፣ እንይዘዋለን ብለው በር ዘግተውበት ገንጥሎ ይወጣ ነበር ፣ በአንድ መንጋጋ አንድ ሺህ ገደለ፡፡ ይህን እንደሰውኛ ስናስበው የሆነ adventure ለመስራት ይመስላል😁 ግን 🤔በሰው አይምሮ ሊገመት የማይችል እና ከሰው ስርአት ውጪ የሆነ ነገር በህይወቱ እንዲሆን ያደረገው ይህ መነቃቃት🔥 ነበር፡፡ ተወዳጆች ሆይ የየእለቱ መነቃቃቶቻችን እና ከመንፈስ የምንቀበለው ሀይል የቀጣይ ምዕራፎቻችን በሌላ power የመቀየር ምክንያት ይሆናል፡፡
👉 ሳምሶን ጥሪው በበቀል መንፈስ ፍልስጤምን ለመበቀል ነው፡፡ ግን ወደዚኛው የበቀል ቅባት ጥሪ operate እንዲያረግበት መንፈስ ቅዱስ ያነቃቃው ነበር፡፡ ስለዚህ አንዱ መንፈስቅዱስ ሲያነቃቃን ወደ መሻታችን ወደ ፍላጎታችን ሳይሆን ወደ ለጥሪያችን ነው የሚያነቃቃን፡፡ ወንድምቼ መነቃቃታችን መጮአጮሀችን ጸሎታችን ወደ ጥሪያችን ካልሆነ ጥያቄ?? የሚያስነሳ መነቃቃት ነው፡፡ stay blessed 🖐
@holyspiritflow
@holyspiritflow
@holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

ጊዜህን የሰጠኸው ነገር ይወርስሀል ስለዚህ ጊዜህን ለማን እንደምትሰጥ መለየት ነው በጣም ጊዜን የሰጠኸው በጣም ውጤታማ ትሆንበታለህ ጊዜህን ለጸሎት ለቃሉ ስጥ ያኔ መንፈሳዊ ድልን ማንም አይወስድብህም
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

ኢየሱስን እወደዋለው ምክንያቱም ማንነቱ ፍቅር ስለሆነ በጣም የሚገርመው ለኔ ያደረገልኝ የማይገባኝን ነው 😭😭 👇
" ምሕረትና እውነት ተገናኙ፤ ጽድቅና ሰላም ተስማሙ።"
(መዝሙረ ዳዊት 85:10)
👉 ዳዊት የሚናገረው ስለ ጌታችን መምጣት እና የማዳን ስራ ሲናገር "ምህረትና እውነት ተገናኙ" የማይገናኙ ነገሮች ናቸው ተገናኙ እያለን ያለው እውነቱ 👇
👉 በደለኛ ነበርን
👉 እግዚአብሄርን አሳዝነናል
👉 ለእግዚአብሄር አለም ምላሽ/response የማንሰጥ ነበርን
👉 ከሀጢያታችን የተነሳ ሞት የሚገባን ነበርን። በጣም የሚገርመው አንድ ሰው ፍርድ ቤት ቆሞ እውነቱ ሲጋለጥ ለምሳሌ፦ ሰው ገድሎ ከሆነ እውነቱ ከታወቀ እና ማስረጃ ከተገኘ ይፈረድበታል እንጂ መቼም ነጻ ወጥተሀል አይባልም ለዚህ ነው እውነትና ምህረት አይገናኝም ያልኩት። ግን የሚገርመው እውነቱን እያወቀ የኔ ጌታ ደግሞ
👉 ነጻ ወጥተሀል
👉 ጻድቅ ነህ አለኝ
👉 የዘላለም ቤት አዘጋጀልኝ
👉 ከእርሱ ጋር በሰማያዊ ስፍራ አስቀመጠኝ 🖐🖐🖐😭😭😭😭
➡️ የማይገናኙትን ሁለቱን ነገሮች በክርስቶስ ተገናኝተዋል እኛም አሁን ነጻ ለመውጣት የምንሰራው ነገር የለንም ብንሰራ እንኳን ልንሰራ የምንችለው ነጻ ስለወጣን ይሆናል እንጂ already ነጻ ወጥተናል። ለዚህ ነው ኢየሱስን የምወደው😭😭😭 የማይገባኝንና የማይገናኘውን እውነትና ምህረት ስላገናኘ
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

ዛሬ አዲስ ቀን ነው እስትንፋሳችንን የያዘው ጌታ ተንፍሱ ኑሩ ብሎ የዛሬውን ቀን ሰጥቶናል የተሰጠንን አዲስ ቀን ያገኘነው ከጌታ ነው። ደግሞ እሱ ከሰጠን እሱ በውሎአችን እንዲከብርበት ፈልጎ ነው። የሆነ ቀን አይደለም ጌታ የሚከብርብን በቀን ውሎአችን በዛሬአችን መክበር ይፈልጋል ዛሬህን/ዛሬሽን ስጪው/ስጠው ምክንያቱም አሁን እየተነፈስክ/ሽ ያለው እሱ እንዲከብርብሽ ስለፈለገ ነው።

Читать полностью…

holyspirit flow

ምስክርነትህን ከpaster ወይም ከቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች አትጠብቅ ምስክርነትህን የሚሰጥህ እግዚአብሄር ነው የእርሱን ምስክርነት ብቻ ተመልክተህ አገልግል/ተመላለስ
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

➡️የእውነተኛ ተሃድሶ(reformation) ማሳያ በንሰሀ፣ፊቱን በመፈለግ ወደ እግዚአብሄር መመለስ ነው፡፡ እግዚአብሄር በእኔ እግዚአብሄር ሲፈቅድ ይሆናል 🤷‍♂ በሚል ለስንፍና እራሳችሁን እየጋበዛችሁ አትኑሩ፡፡ ሁሌም ቢሆን ድል ያለው በትጋትና በትግል ነው አሁን የራሳችንን comfert zone ላለመልቀቅ የሚስማንንና ትግል የሌለበትን ህይወት ትተን እራሳችንን ለትግል እናዘጋጅ ሁሌም ወታደር👮 የሚያስበው ድል ያለው በትግል ነው እያለ ነው፣ ሁሌም ቢሆን ሩአጭ 🏃🏃 የሚያስበው ሽልማት ያለው 🥇 በትጋት እንደሆነ ነው እኔም እላቹሀለው መንፈሳዊ ድል ያለው በትጋትና በትግል እንዲሁም በፅናት ነው

(ወደ ዕብራውያን ምዕ. 10)
----------
36፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና።

37፤ ገና በጣም ጥቂት ጊዜ ነው፥ ሊመጣ ያለውም ይመጣል አይዘገይምም፤

38፤ ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም።
👉 የምር revival ይነሳል ለዛውም የመጨረሻ ዘመን ላይ እንዳለ ትውልድ 💪💪 የመጨረሻ ዝናብ🌨 ⛈⛈🔥🔥 ተዘጋጁ!! ተዘጋጁ!! ተዘጋጁ!! ተዘጋጁ!!
👉 @holyspiritflow
👉 @holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

ክርስትና ምንድነው( what is christianity)
👉 ክርስትና ማለት ከመነሻው እስከ መድረሻው ክርስቶስ የሚታይበት መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ህይወት አልፎ የሚሰራበት ነው
👉 ክርስትና ማለት ስለክርስቶስ በየእለቱ ለማወቅ ወደ አለማወቅ ወይም ክርስቶስ እሱ ታውቆ የማይጨረስ ስለሆነ ሁሌም ስለሱ ለማወቅ maturity ማሳየት ነው " ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን፥ ከሚቃጠልም መሥዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እወድዳለሁና። "
(ትንቢተ ሆሴዕ 6:6)
ክርስትና ክርስቶስ በማወቅ መኖር ነው
👉 ብዙ አማኞች የቃላት ብዛት በመደርደር ለእሱ ፍቅር ያለን ይመስለናል ግን የቃላት ብዛት ለሱ ፍቅር እንዳለን ማረጋገጫ አደለም ምክንያቱም 👇

(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 21)
15፤ ምሳ ከበሉ በኋላም ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ግልገሎቼን አሰማራ አለው።
16፤ ደግሞ ሁለተኛ። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው።
17፤ ጠቦቶቼን ጠብቅ አለው። ሦስተኛ ጊዜ። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። ሦስተኛ። ትወደኛለህን? ስላለው ጴጥሮስ አዘነና። ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ኢየሱስም። በጎቼን አሰማራ።
👉 ክርስቶስ ጴጥሮስን ሲጠይቀው በአንደበቱ እንደሚወደው ቢነግረውም ክርስቶስ ለኔ ፍቅር ካለህ ከወደድከኝ ዋጋ ክፈል አለው ቤተሰቦቼ ክርስትና መለኪያው ዋጋ የሚያስከፍል ጉዳይ ቢመጣ ዋጋ መክፈል መመዘኛ ሚዛኑ ነው
👉 ዋጋ ለመክፈል ያልተዘጋጀ ግን ጌታ ሆይ እወድሀለው በማለት ብቻ ሰማይ ፍቅር አላቸው አይልም ስለዚህ መንቃት አለብን🔔 ሰማይ የኔ ናቸው የሚለን ለሱ መሆን ያለብንን ሁሉ ስንሆን ነው ጳውሎስ እንዲህ አለ ፦
(የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 14)
19፤ አይሁድ ግን ከአንጾኪያና ከኢቆንዮን መጡ፤ ሕዝቡንም አባብለው ጳውሎስን ወገሩ የሞተም መስሎአቸው ከከተማ ወደ ውጭ ጐተቱት።
20፤ ደቀ መዛሙርት ግን ከበውት ሳሉ፥ ተነስቶ ወደ ከተማ ገባ። በነገውም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤን ወጣ።
21-22፤ በዚያችም ከተማ ወንጌልን ሰብከው እጅግ ደቀ መዛሙርትን ካደረጉ በኋላ፥ የደቀ መዛሙርትን ልብ እያጸኑ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩና። ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል እያሉ፥ ወደ ልስጥራን ወደ ኢቆንዮንም ወደ አንጾኪያም ተመለሱ።
በዚህ ዘመን ቢሆን "አገልግዬ ልጅነቴን ሰጥቼ አንተን ብዬ እንዴት እንዲ ሆንኩኝ" ይባላል የክርስትና ትርጉም አይደለም በእግዚአብሄር ሚዛን⚖ ወድቅ ነን መውደድ ሚታወቀው በዋጋ መክፈል ውስጥ ነው፡፡ stay blessed 🙏🙏 👉 @holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

❝ከሕግህ ድንቅ ነገርን እንዳይ፣ ዐይኖቼን ክፈት።❞
—መዝሙር 119: 18 (አዲሱ መ.ት)

❝Open my eyes, that I may see Wondrous things from Your law.❞
—Ps 119: 18 (NKJV)

Читать полностью…

holyspirit flow

የውልደቱ ሚስጥር

የተፈጥሮን ስርዐት
ሕግና ደንብ ጥሶ
ከድንግል የተወለደ
ከመንፈስ ተፀንሶ
ከሀጥያት የሚያነፃ
አስታራቂ የሆነው
ፈውስን የያዘ መጠሪያ የተሰጠው
ተስፋ የነበረው ቃል ሲባል የኖረው
ዛሬ በቤተልሔም
አካል ለብሶ አየነው
በጌታ ፍቃድ የተወለደ
መዳን ሊሆን ለአለም
በሞቱ ሊሰብር የትውድን መርገም
በጨለማ ላለን ብርሀንን ሊያወጣ
የእግ/ር ልጅ ኢየሱስ
ወደ ምድር መጣ
የእግዚአብሔርም መልአክ
ለሊት ለእረኞቹ በክብር ተገልጦ
እንዲህም አላቸው እንዳይፈሩ ከቶ
አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ
አዳኝ ተወልዶላቹሀል
ሔዳቹ ስገዱ በግርግም ተኝቷል
ገና እንደሰሙ የውልደቱን ዜና
እረኞቹ በሕብረት መጡ በምስጋና
ሰባ ሰገሎችም መወለዱን ሰምተው
መተው ሰገዱለት ዕጣን
ከርቤን ይዘው
አቤት ይሄ ጌታ
ግርማው ማስፈራቱ
ጌትነቱ ሲታወጅ በህፃንነቱ
የውልደቱን ዜና ሔሮድስ እንደሰማ
ቁጣው ገኖ ታየ በአይሁድ ከተማ
የአይሁድ ንጉስ ነው
መባሉንም ሰምቶ
ሊያጠፋው አሰበ
ለስልጣኑ ሰግቶ

የአለም መድሀኒት
ወደ ምድር ሲመጣ
ምንም እንኳን ቢገን የሄሮድስ ቁጣ
የእግዚአብሔር መልአክ እየተገለጠ
ከአሳዳጆቹ ልጁን አስመለጠ

የውልደቱ ሚስጥር
ምድር የመምጣቱ
እኛና እግ/ርን ሊያስታርቅ በሞቱ
ሊያፈርስ የተላከ የጥልን ግድግዳ
በደሙ ሊከፍል የሀጥያትን ዋጋ
የሀጥያተኞችን ሸክምን ሊሸከም
አዳኝ ተወለደ በበረት በግርግም

ለሀጥያታችን ስርየት
ለማግኘት ምህረትን
ማቅረባችን ቀርቶ
የደም መስዋዕትን
በንስሀ እንድንቀርብ
በፀሎት አድርገን
አማላጅ ይሆን ዘንድ
ኢየሱስ መጣልን

ኢትዮጵያን ለኢየሱስ
@e4jesus @e4jsong
@e4jgxm @e4jesus

Читать полностью…

holyspirit flow

‹‹ድንቅ ታሪክ ››
==============
አንድ ሰው በበረሃ እየተጓዘ እያለ የያዘው ውሃ አልቆበት በውሃ ጥም ይያዛል፡፡ ቀስ በቀስ
ውሃ ጥሙ ሰውዬውን እያደከመው ይመጣል በስተመጨረሻ ከአንድ የውሃ ጉርጓድ ጋር
ይደርሳል ጉርጓዱ በጣም ጥልቅ ነበረ ውሃ ይኑረው አይኑረው አይታይም፡፡ ከዚያም
ከጉርጓዱ ጎን አንድ አሮጌ የውሃ መሳቢያ ሞተር አለ ሞተሩ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ
ሰፍሯል፡፡ ‹‹ይህ የውሃ መሳቢያ ሞተር የሚሰራው በውሃ ነው›› ይላል፡፡ ከሞተሩ ጎን አንድ
ጆግ ሙሉ ውሃ ተቀምጧል ጆጉ ላይ እንዲሁ አንድ ፅሁፍ ሰፍሯል ‹‹ወዳጄ ሆይ ይህንን
ጆግ ውሃ ሞተሩ ውስጥ ጨምረው ሞተሩ ብዙ ውሃ ያወጣልሃል ታዲያ አደራ አንተም
እንዳንተ ላለ ሌላ መንገደኛ ይጠቅማልና ውሃው ከጉርጓዱ ሲወጣልህ ጆጉን ሞልተህ
ማስቀመጥን አትርሳ›› ይላል፡፡ በጆግ ያለውን ውሃ ሞተሩ ውስጥ ይጨምረው ወይስ
ይጠጣው? እዚጋር ሰውዬው በሁለት ሃሳብ ተወጠረ ‹‹አንደኛ ይህ ሞተር አርጅቷል
ጨምሬው ባይሰራ ይህንንም ውሃ አጣሁ ማለት ነው ሞትኩ ማለት ነው ስለዚህ
ልጠጣውና ህይወቴን ላድን ፡ ደሞ ማሳሰቢያውስ ውሃው ያለሞተር አይሰራም እንደኔ ውሃ
የተጠማ ሰው ቢመጣ ይህንን ማንቀሳቀሻ ከጠጣሁት ይሞታሉ›› ብሎ ለራሱም ለሌሎቹም
አሰበና በሃሳብ ተወጠረ በስተመጨረሻ በብዙ ጭንቀት ተወጥሮ ትልቅ ውሳኔ ወሰነ እንዲህ
አለ ‹‹ውሃውን ወደሞተሩ ብጨምረው ይሻላል ከሰራ ጥሩ ካልሰራ ግን እሞታለሁ እንጂ
በፍፁም ይህንን ጆግ ውሃ ጠጥቼ ሄጄ ዛላለሜን ስለዚህ ጉርጓድና ይህንን ውሃ አተው
ስለሚሞቱ ሰዎች እያብኩ መኖር አልፈልግም›› አለ፡፡
ከዚያም የጆጉን ውሃ ወደ አሮጌው ሞተር ውስጥ ጨመረውና የሞተሩን ማስነሻ ተጫነው፡፡
ሞተሩም ድምፅ እያሰማ ውሃ የማውጣት ስራውን ጀመረ፡፡ ሰውዬው ተደነቀ የሚፈልገውን
ያህል ጠጣ አካባቢው በሙሉ በውሃ እራሰ ከጠበቀው በላይ አካባቢው ሁሉ ውሃ በውሃ
ሆነ ከዚያም በተባለው መሰረት እሱም ጆጉን በውሃ ከሞላው ቦሃላ ጆጉ ላይ ፅሁፍ
ጨመረበት ‹‹እመኑኝ በትክክል ይሰራል›› አለ፡፡ እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው ለሌላው ማሰብ ሰው መሆን ነው መኖርም ነው፡፡ ያለህን በሙሉ ሳትሰስት
ከሰጠህ በእጥፍ ድርቡ ፈጣሪ ይሰጥሃል፡፡ ሰውዬው ጆግ ውሃ ሰቶ አካባቢን የሚያርስ ውሃ
እንደተቸረው አንተም የምትሰጣት ጠብታ ከልብህ ከሆነ በእጥፉ ይሰጥሃል፡፡ በምትሰፍረው
መስፈሪያ ይሰፈርልሃል በሰጠኸው ልክ ይሰጥሃል ስለዚህ ‹‹አመድ አፋሽ ሆንኩ››
ከማለትህ በፊት አመድ ሰተህ ከሆነስ፡፡ መስጠትን ብቻ ሳይሆን አሰጣጥህ ወሳኝነት
አለው፡፡ አንዳንዴ ከመንጠቅ የማይተናነስ መስጠትም አለ፡፡
ያለንን ሁሉ ያለስስት እንድንሰጥ ጌታ ይርዳን።

Читать полностью…

holyspirit flow

ድል የሚጀምረው ከጓዳ ነው
=========================
(መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕ. 17)
----------
33፤ ሳኦልም ዳዊትን። አንተ ገና ብላቴና ነህና፥ እርሱም ከብላቴንነቱ ጀምሮ ጦረኛ ነውና ይህን ፍልስጥኤማዊ ለመውጋት ትሄድ ዘንድ አትችልም አለው።

34፤ ዳዊትም ሳኦልን አለው። እኔ ባሪያህ የአባቴን በጎች ስጠብቅ አንበሳና ድብ ይመጣ ነበር፥ ከመንጋውም ጠቦት ይወስድ ነበር።

35፤ በኋላውም እከተለውና እመታው ነበር፥ ከአፉም አስጥለው ነበር፤ በተነሣብኝም ጊዜ ጕሮሮውን ይዤ እመታውና እገድለው ነበር።

36፤ እኔ ባሪያህ አንበሳና ድብ መታሁ፤ ይህም ያልተገረዘው ፍልስጥኤማዊ የሕያውን አምላክ ጭፍሮች ተገዳድሮአልና ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል።
👉 ኢትዮጵያ ያጣችው በነውጡ ውስጥ አብሮ የሚናወጥ አብሮ የሚያለቅስ ሳይሆን በሀገራችን ጎልያድ ላይ በበቀል የሚገለጠውን ዳዊትን ነው። ልክ እንደ ዳዊት የሀገር ስጋት የሆነው ነገር ላይ እኔ እችላለው የሚል በጉአዳው ድል ያደረገ ማስጣል፣ማስተፋትና መምታት የሚችል ዳዊቶች ያስፈልጉናል።
👉 ድል የሚጀምረው በጓዳችን ነው ብዙ ሰው ስኬቱን፣ድሉን አደባባይ ላይ ይፈልጋል በእውነት ነው የምነግራችሁ በጓዳችሁ ያላመጣችሁትን ድል አደባባይ አትፈልጉት በመጀመሪያ በቤታችሁ ላይ ድልን የተለማመዳችሁ ልትሆኑ ይገባል።

👉 ዳዊት አደባባይ ላይ ጎልያድን ድል ከማድረጉ በፊት በግሉ በጓዳው የተለማመደው ድል ስለነበረ አደባባዪ አልከበደውም ብዙዎቻችን ውጪ ተጽኖ መፍጠር አቅቶናል በchurch፣በትምህርት ቤት፣በሰፈር ድል ማድረግ ያልቻልነው በጓዳችን ድል ስለሌለን አደባባይ ላይ ያለ ስለመሰለን ነው። እናስተውል ሀገራችን የምትፈልገው ዳዊቶችን ነው የሚፈራ ሞልቶአል የሚሰጋ ሞልቶዋል ምን ልንሆን ነው የሚል ሞልቷአል። ሀገሬ ያጣችው ዳዊቶችን ነው "እኔ እመታዋለው የማንም ልብ አይውደቅ" የሚል ያስፈልጋታል 🔥🔥 በሚመጣው ዘመን ለሀገራችን የሚገለጡ ዳዊቶች እኛ ነን🔥🔥🔥
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

አለማንበብ አይቻልም👇👇
👉 ሰይጣን አንድ technique አለው ክርስቲያኖችን በተለይም አገልጋዮችን ለማስቆም የሚጠቀምበት እርሱም የኛን focus መውሰድ ይፈልጋል። ለምሳሌ👇
👉 አንድ ሰው ትምህርቱ ላይ ጎበዝ እንዲሆን ከፈለገ ለትምህርቱ ትኩረት መስጠት አለበት ያን ጊዜ ጊዜውን ይሰጣል ሌላ ነገር ላይ ከሚያጠፋው ጊዜ በላይ ለማጥናት የበለጠ ጊዜ ይሰጣል፣ አንድ ሰው physicaly ጡንቻ ለማውጣት ትኩረት መስጠትና በየቀኑ እሪሳችን ላይ የምንሰራው ነገር ይወስነዋል። ልክ እንደዚው አንድ ሰው መንፈሳዊ ነገር ላይ የሚጠነክረው ትኩረት መስጠት ሲችል ነው ያኔ ጊዜውን ይሰጣል ሌላ ነገር ላይ ጊዜውን አያጠፋም በአግባቡ ጊዜውን ይጠቀማል።
👉 አብዛኞቻችን መንፈሳዊ ነገር ላይ ጎበዝ መሆን እንፈልጋለን ነገር ግን ጊዜ አንሰጠውም ምክኒያቱም ትኩረታችንን ሰይጣን እየወሰደብን ነው። ደካማም ብርቱም የሚያደርገን ትኩረት የምናደርግበት ነገር ነው። ትኩረታችን ምን ላይ ነው? 🤔 ብዙ ጊዜ የሰጠነው ምንድነው?🤔 አንድ ነገር ላይ ጎበዝና ጠንካራ ለመሆን ጊዜ የሰጠነው፣ ትኩረት የሰጠነውን ነገር ብቻ ነው እንደዛ እንድንኖር የሚያደርገን ዛሬ ጊዜያችንን በአግባቡ ስንጠቀም ነው
👉ሰይጣን አገልግሎታችንን ጸሎታችንን ለጌታ ያለንን ነገር ለመውሰድ ሲፈልግ ትኩረታችንን ነው የሚወስደው ያን ጊዜ ምንም አናመጣም ሰይጣን ላይ ተጽኖ ማምጣት አንችልም ደግሞም ትኩረታችንን ለመውሰድ ሲል ምንም የማያደርገው ነገር የለም አስተውሉ ትኩረታችሁን ጠብቁ ሰይጣን ትኩረታችሁን ከወሰደው ለምንም እንደማትጠቅምና የምትፈጥሩስለት ነገር የለም ስለዘህ ትኩረታችሁን ጠብቁ!!!!!!
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

በትኩረት ይነበብ መልእክት ነው👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
እግዚአብሄር በየዘመናቱ አማካሪ ሳያስፈልገው ብቻውን እየሰራ ነበር አሁንም እየሰራ ይገኛል
👉 እግዚአብሄር ለመስራት የተነሳ ጊዜ ለ 2 ነገር ይመጣል።
1 እርሱን በመጠባበቅ ላይ ላሉት የሚያስፈልጋቸውን ለመስጠት
2 በአመጸኞች ላይ ወይም እርሱን ባስቆጡት ላይ የማጥራት ስራ ሊሰራ ይመጣል። ለዚህ ዋነኛ ማሳያ የሚሆነን 👇
👉 በዘፍ 18 እና 19 ላይ እግዚአብሄር 2 ነገር ሲያደርግ እናያለን አንዱ ለአብርሀም ለዘመናት ከእግዚአብሄር ሲጠብቅ ለነበረው የልጅ ጥያቄ መልስ ይዞለት መጣ ሁለተኛው ሰዶም እና ጎሞራ በሀጢያታቸው ለሰከሩት ቅጣትን ይዞ መጣ። ለዚህ ነው እግዚአብሄር የሚሰራበት የራሱ ጊዜ አለው ከተነሳ ግን ማንም አይመልሰውም እርሱን በመጠባበቅ ላይ ላሉ የጠበቁትን ነገር ይዞ ይመጣል እንደየ ስራችን ይከፍለናል።
👉 በጣም የሚገርመው በዚህ በአመጸኛው ትውልድ መካከል ሎጥና ቤተሰቦቹ በቅድስና ይኖሩ ስለነበር ሞት እና ጥፋት እቤታቸው እንዳይገባ እግዚአብሄር ውጡ ወደ ተራራው እቺን ምድር አጠፋታለው ባለ ጊዜ 👇

(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 19)
----------
15፤ ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን። ተነሣ፥ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውሰድ፤ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፋ እያሉ ያስቸኵሉት ነበር።

16፤ እርሱም በዘገየ ጊዜ እግዚአብሔር ስላዘነለት እነዚያ ሰዎች የእርሱን እጅ የሚስቱንም እጅ የሁለቱን የሴቶች ልጆቹንም እጅ ይዘው አወጡትና በከተማይቱ ውጭ አስቀመጡት።
👉 ሎጥ ወደ ተነገረው ስፍራ እንዳይወጣ ዘገየ ይላል ከዛም እግዚአብሄር እጃቸውን ይዞ አወጣቸው ይላል።
➡️ መልእክቴ ይሄ ነው የተናገረን ነገር እያለ በህይወታችን ምንም ጠብ ያለ ነገር ለምንል ከዘገየንበት የተስፋ ቃል አስቸኩሎ የሚያወጣ የጌታ እጅ ወደ እኛ ይመጣል። ለሀገሬም የተስፋ ቃል እያላት በተለያዪ ነገሮች ዘግይታ ከተበረችበት አስቸኩሎ የሚያወጣ የጌታ እጅ ይመጣል🔥🔥 ወደ ተናገረን ያወጣናል🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…
Subscribe to a channel