ነጻነታችን ያስጨነቀው ፈርኦን ብዙ ጊዜ እየመጣ የሚያቀርብልንን ጥያቄ ችላ ማለት የለብንም በ ቁ 25 ላይ ፈርኦን መፍትሄ ያለው ፣ነጻነት ያለው የሚመስል ግን ነጻነትን የሚከለክል ጥያቄ ጠየቃቸው አምላካችሁን ለምን እዚው አታመልኩትም? የሚል ጥያቄ የአምልኮ ነጻነት ሊሰጣቸው የሚችል የሚመስል ጥያቄ ነበር።
👉 ሁሌም ማስተዋል ያለብን እግዚአብሄር እልፍ ብለን የእርሱን ረዳትነት እያየን በነጻነት እንድናመልከው ይፈልጋል የጠላት አሳብ እዚቹ ለምን አታመልክም ከክልሉ ሳንወጣ ከመንደሩ ፈቀቅ ሳንል በፍጹም እግዚአብሄርን ልናመልክ አንችልም።
👉ፈርኦን አምልኮ የመሰለው ለደቂቃ የሚደረግ የሆነ ceremony ነበር☺️ ነገር ግን እግዚአብሄርን ማምለክ ጣኦታትን እንደማምለክ አይደለም ጣኦት አይናገርም አምልኮውን አልተቀበልኩም አይልም የቀረበውን ሁሉ ዝም በማለት ህያው ስላልሆነ የተቀበለ ይመስላል የኛ አምላክ ግን ህያው እና የሚሰማ የሚመልስ ስለሆነ አምልኮውን አልተቀበልኩም ሊል ይችላል ወይም ተቀብያለው ሊል ይችላል ምክንያቱም ህያው ስለሆነ(እንደ አቤል እና ቃየል)
👉 ስለዚህ ከምናቀርበው ነገሮች ላይ የኛ ምልልስ የመጀመሪያውና ዋነኛው አምልኮ ነው ምልልሳችን ግብጽ ሆኖ እንዴት እግዚአብሄርን እናመልከዋለን🤔? እግዚአብሄር እንደ ፈርኦን ጣኦታት አይደለም!! የቀረበለትን ሁሉ ዝም ብሎ የሚቀበል አይደለም የሚመልስ የሚናገር ስሜት ያለው አምላክ ነው። ዛሬ እንደ ፈርኦን እዚችሁ አምልኩ ለሚለን የአምልኮ ትርጉም ለገባን ለኛ መልሳችን አምላካችን ባለበት የምንኖረው እንደሆነ ኑሮ እንደሆነ እንነግረዋለን!!!!!!! Be blessed✋
@Hoyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
እግዚአብሄር በምትደሰተው በኩል ወይም እንዲሆንልህ በምትፈልገው በኩል በመምጣት ደስታህን የመፈጸም አላማ የለውም ይልቅስ የአብ ደስታ እንዲፈጸም ደስታህን ፍላጎትህን እያሳጣ ፍላጎቱን ለሰዎች ይገልጥብሀል። ብዙ ፍላጎቱን የገለጠባቸው ብዙ ክብሩን የገለጠባቸው ፍላጎታቸውን ክብራቸውን እያጡ እንጂ እንዳማረባቸው እንደተከበሩ አይደለም።
👉 አብርሀምን ከሞቀ ከአባቱ ቤት ምድረበዳ ተንከራታች ያደረገው ክብሩን ሊገልጥበት ነው
👉 ሙሴ እንዳማረበት በግብጽ ምድር ጮማውን እየቆረጠ አይደለም እግዚአብሄር የተገለጠለት እና እራሱን የገለጠበት በምድረበዳ ነው።
👉 አልአዛር እንደታመመ መጥቶ አይደለም ክብሩን የገለጠት እነ ማሪያም እና ማርታ ኢየሱስ እንዲመጣ የፈለጉት እንደታመመ ነበር ኢየሱስ ግን ያለፍላጎታቸው ሞቶ 4 ቀን ሆኖት መጣ ክብሩን መግለጥ ስለሚፈልግ አልአዛር እና እህቶቹ ባልፈለጉት በሞት በኩል ሰው እንዲሰበሰብ አድርጎ ክብሩን ገለጠ።
ወዳጆቼ ጌታ ክብሩን ሊገልጥብን ነው የምንል ከሆነ የወደድነውን ሳይሆን የወደደውን ፣ የመረጥነውን ሳይሆን የመረጠውን እያደረገ ክብሩን እንደሚገልጥብን አውቀን ለሚመራን መንገድ ሁሉ እራሳችንን እናዘጋጅ ክብሩን ሊገልጥ ነው!!!!!!!!!
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
ፊልጵስዩስ 2 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን ሊለቀው እንደማይገባ አድርጎ አልቈጠረውም፤
⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ፣ በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ ራሱን ባዶ አደረገ፤
⁸ ሰው ሆኖ ተገልጦም፣ ራሱን ዝቅ አደረገ፤ እስከ ሞት፣ ያውም በመስቀል ላይ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።
👉 በጣም ብዙ ሰው አምላክነቱን ትቶ እንደመጣ ይናገራል ክርስቶስ የተወው አምላክነቱን ሳይሆን የአምላክነት ክብሩን ነው ለዚህ ነው አምላክ በመሆኑ የነበረው ክብር ሰው ሲሆን ግን ያንን ክብር ተቀሞቷል
👉 ህጻኑ አለማት ሁሉ የእርሱ ሆነው ስፍራ እንደሌለው በበረት ተወለደ ጠፍጥፎ የሰራት ብርሀን ሰባ ሰገሎችን ''ኑ የብርሃኔን ምንጭ ላሳያችሁ'' ብላ እየተንቀሳቀሰች መራቻቸው ዝም ማለት አልቻለችም ሰማይ የነበረ አምልኮ ተቋርጦ ለጥቂት ሰአታት ምድር ላይ በግርግም ተደርጉአል መላዕክቶች የምስራቹን ይዘው ቤተመንግስት ሳይሆን ወደ እረኞች ይዘው ሄዱ እረኞቹም ይህን የሰማይ አምልኮ ተመልካቾች ሆኑ።
👉 እና አምላክ ሰው የሆነበትን እውነት እያዪ ኮኮቦች ዝም ማለት ካልቻሉ እኛ እንዴት ዝም እንላለን??
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
እግዚአብሄር ዮናስን በአሳነባሪ ሆድ ውስጥ ሆኖ ሲጸልይ ሰምቶት አሁነው የምትጸልየው ስትያዝ ነው የምትጸልየው አላለውም ምክንያቱም በምንም ሁኔታ ውስጥ ሆነው ፊቱን የሚፈልጉትን ይሰማቸዋል ደግሞም እግዜር የማንንም ጸሎት አይንቅም ብቻ አንተ/አንቺ ጸሎትን አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ አውቀን በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆነን እንጸልይ እንጂ እርሱ ሁሌም የሚሰማን ደግሞም የማይንቀን አምላክ ነው።
👉በእውነት ዛሬ ለአንድ ሰው መልዕክት ነው እንደ ዮናስ በተለያየ አይነት ነገሮች ውስጥ መዋጥ ውስጥ ያለን ካለን ምንም አይነት መውጫ የማይታይበት ነገር ውስጥ ብንሆንም ጸሎትን አማራጮ የሌለው ነገር መሆኑን አውቀን በጸጸት ሳይሆን በመመለስ ልብ ወደ ጌታ እንቅረብ እርሱ ሊሰማን ሊቀበለን ዝግጁ ነው
👉 የተለያዩ ሱሶች ውስጥ ያላችሁ ወጣቶች ለምሳሌ፦ የስልክ፣የchat፣የፖርኖግራፊ፣ የማስተርቤሽን፣የፊልም፣የዝሙት፣የሲጋራ ወይም drug addicted የሆናችሁ በብዙ ሱስ ያላችሁ ብቸኛውና አማራጭ የሌለው የማምለጫ መንገድ ወደ ጌታ አንድ እርምጃ መጠጋት ነው በተጠጋችሁ ቁጥር እየቀለለባችሁ እየተዋችሁት ትመጣላችሁ ዮናስ በመርከብ እያለ ያልጸለየው በአሳ ሆድ ውስጥ እንዴት መጸለይ ሊታየው ቻለ?🤔 አያችሁ ጸሎትን የሚተካ ሌላ ነገር ከፈለግን ከተዋጥንበት ልንወጣ ይቅርና መዋጣችን ጥልቀቱን እየጨመረ ሊመጣብን ይችላል። ስለዚህ በምንም አይነት ነገሮች ብንዋጥ ከመጸለይ ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም!!!!!!!!
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
ሁለት ጡረታ የወጡ ሽማግሌዎች ነበሩ፡፡ አንዱ ፓይለት ሌላው ደግሞ መምህር የሆኑ ጎረቤታሞች ናቸው፡፡ ሁለቱም አንድ ወቅት ላይ ተመሳሳይ ችግኞች በጓሮዋቸው ተከሉ፡፡
ፓይለቱ ለተከለው ችግኝ ያለው እንክብካቤ የተለየ ነበር፡፡ ከመጠን በላይ ይንከባከበዋል፡፡ ውሃ ከመጠን በላይ ያጠጣዋል። ለችግኙ የተለያየ ማዳበሪያ እየገዛ ያደርግለታል፡፡
መምህሩ ደሞ ጠዋት ይነሳና ዉሃ ያጠጣል፡፡ እንደ ፓይለቱ ግን ብዙ እንክብካቤ አያደርግም፡፡
አንድ ቀን ከባድ ዝናብ ጣለ። ሌሊቱን ሙሉ ዘነበ፡፡
ጠዋት ችግኞቻቸውን ለማየት ሁለቱም ወደ ጓሯቸው ሄዱ፡፡ የፓይለቱ መሉ በመሉ ወድሟል፡፡ ተነቃቅሎ ወድቋል፡፡ የመምህሩ ደግሞ በውሃ ከመሞላት ውጪ ምንም አልሆነም፡፡
ፓይለቱ ገረመው፡፡ እንደዛ የተንከባከበው ችግኝ ወድቋል፡፡ ምክንያቱን ለማወቅ በመጓጓት ወደ መምህሩ ሄዶ "አንድ አይነት ችግኝ በተመሳሳይ ጊዜ ተክለን እንደውም እኔ ችግኘን ከአንተ በላይ እየተንከባከብኩት ነበር የቆየሁት። ግን የኔ በዚህ ዝናብ ወደመ፡፡ ያንተ ደግሞ ምንም አልሆነም፡፡ እንዴት??? ለምን???" ብሎ እየተገረመ ጠየቀው፡፡
መምህሩም እንዲህ ሲል መለሰ፦
"አንተ ለችግኝህ የተለየ እንክብካቤ ብዙ ውሃ እና አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ትሰጥ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ችግኙ ውሃና ንጥረነገር ለማግኘት ስራ አይሰራም፡፡ ሁሉንም አንተ ታቀርብለታለህ። እኔ ደግሞ እንዳይደርቅ የተወሰነ ውሃ አጠጣዋለሁ፡፡ ከዚያ በላይ ከፈለገ ስሮቹን (roots) በመጠቀም እንዲፈልግ እተወዋለሁ፡፡ በዚህም ምክንያት ስሮቹ (roots) ተጨማሪ ውሃና ንጥረ ነገር ፍለጋ ወደ ውስጥ ይገባሉ፡፡ለዚህም ነው የዳነው። ስሮቹ ወደ መሬት በደንብ ስለተቀበሩ፡፡"
ይህን ችግኝ ልጅ ያላችሁ እንደ ልጃችሁ፤ ትንሺ እህትና ወንድም ያላችሁ ደግሞ እንዲሁ አንደሆኑ ቁጠሩት። ስታሳድጓቸው እንደ ፓይለቱ ሁሉን ነገር እየሰጣችሁ በራሳቸው እንዳይቆሙ ካደረጋችሁኋቸው፤ በችግር ግዜ ወድቀው ታገኟቸዋላችሁ።
እንደ መምህሩ ደግሞ የሚያስፈልጋቸውን ብቻ እያደረጋችሁ ካሳደጋችኋቸው በመከራ ተከበውም ቢሆን ቆመው ታገኟቸዋላችሁ።
ምርጫው የናንተ ነው!
ሰዎች ስለ እናንተ ሲያወሩ ምን ብለው የሚያወሩ ይመስላቹሀል? 🤔 ስለ መንፈሳዊነታችሁ ይወራል ፣ ስለ ጉብዝችሁ፣ ስለ ትጋታችሁ፣ ጸሎት ላይ ጉበዝ መሆናችሁ ወይስ ስለ ማስቸገራችሁ፣ተለምናችሁ ቸርች ስለ መምጣታችሁ፣ ስብከት ወይም ጸሎት ሲሰጣችሁ እንቢ ስለማለታችሁ ይወራል ስለምንድነው ሰዎች የሚሉአችሁ የሚመስላችሁ? 🤔
👉 እኔ እንደሚገባኝ እውነተኛ ምስክርነታችንን ከሰዎች አናገኝም ክርስቶስ ስለ እራሴ ብመሰክር ምስክርነቴ ውሸት ነው አለ ነገር ግን ስለ እኔ የሚመሰክር አለ አላቸው። በተግባርም ተራራ ላይ እንቆይ ባሉት ጊዜ አብ በደመና ተገልጦ መስክሮለታል። አስተውሉ!! ሰዎች ስለኛ ምንም ቢሉ የኛን ምስክርነት ከሰው ለማግኘት መታገል የለብንም እንደዚህ የምንኖር ሰዎች ካለን እንደኛ ምስጊን የለም ከሰማንማ ሰዎች ስለኛ ምን የማይሉት አለ 😁 በጣም ልንጨነቅ የሚገባው አብ መስክሮልኛል ወይ? የተመሰከረለት ህይወት ምስክርነቱንም ከላይ የተቀበለ ማንነት የምር አለን? ከሌለን ዛሬ የምንወስነው ሰማይ እንዲመሰክርልን ነወ ምክንያቱም ፈሪሳውያን የሚያስመስሉና ከሰዎች ምስክርነታቸውን የተቀበሉ በብዙሀኑ የተመሰከረላቸው ናቸው። ነገር ግን ጌታ ሲያያቸው የተለሰናችሁ የኖራ ልስን መቃብሮች ይላቸዋል ምክንያቱም በሰዎች ዘንድ የሚያስመስሉ ምስክርነታቸውን ከሰማይ ያልጀመሩ አስመሳዮች ነበሩ። የሚያስጨንቃቸው ሰዎች ስለ እነሱ መጥፎ ነገር እንዳያወሩ እንጂ ከላይ የሆነውን ምስክርነት ላይ ደንታ የላቸውም አሁንም እንዲህ የምንኖር አለን ብዬ አስባለው
👉 ፖስተሮቻችን ወይም ሽማግሌዎቻችን ወይም ቤተሰቦቻችን ፊት እያስመሰልን ምስክርነታችንን ከእነርሱ ለመቀበል የምንዳክር ሰዎች አለን የምናገለግለው ለምንድነው? ማን እንዲመሰክርልን? ማን እንዲያጨበጭብልን? እግዚያብሄርስ ሲያየን ምን አይነቶች ነን የምናስመስል ውስጣችን ግን የሞተ ነው ከላይ ጸላይ የምንመስል ውስጣችን ግን የተለማመድናቸው ነገሮች አሉን? ዛሬ መንፈስቅዱስ የሚያወራን እኔን አስበልጡኝ ከምንም ነገራችሁ እኔ እበልጣለሁ ይለናል። ተባረኩ✋ share it please
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
(የዮሐንስ ራእይ ምዕ. 2)
----------
1፤ በኤፌሶን ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። በቀኝ እጁ ሰባቱን ከዋክብት የያዘው በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚሄደው እንዲህ ይላል።
2፤ ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንዳትችል፥ እንዲሁም ሳይሆኑ። ሐዋርያት ነን የሚሉቱን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤
3፤ ታግሠህማል፥ ስለ ስሜም ብለህ ጸንተህ አልደከምህም።
4፤ ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።
5፤ እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።
👉 ብዙዎቻችን የማናውቀው ነገር ብዙም ቦታ የማንሰጠው ነገር ግን እግዚአብሔር ሁሉን ነገር የሚመዝንበት ሚዛን ፍቅር ነው ነገር ግን እኛ የምናስተውለውና ብዙ ቦታ የምንሰጠው ነገር አገልግሎት፣ ድካም፣ ትዕግስት እና የመሳሰሉት ልክ የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ታደርግ እንደነበረው ማድረግ እንፈልጋለን ነገር ግን ማስተዋል ያለብን በኤፌሶን ድካም አለ፣ ጽናት አለ፣ ስለ ጌታ መከራን መቀበል አለ፣ ሀሰተኞችንም ጭምር መለየት አለ በጣም የሚገርመው ይሄን ሁሉ ትጋት እያሳየች የምነቅፍብሽ ነገር አለ ፍቅር ቀንሰሻል እንደውም ንስሃ ባትገቢ እመጣብሻለው መቅረዝሽንም ከስፍራው እወስዳለው እያላት ያስጠነቅቃታል ምክንያቱም የእግዚአብሄር የመጨረሻ እኛን የሚለካበት መለኪያው ፍቅር ነው ልሳን ብንናገር፣ ትንቢት ብንናገር፣ ሀሰተኞችን ብንለይ፣ አጋንንት ብናወጣ ልክ እንደ ኤፌሶናውያን የጸጋ ስጦታ ቢታይብን ለጌታ ብለን በመከራ ብናልፍ እግዚአብሄር ስራችንን ሁሉ በፍቅር ሚዛን ለይ⚖ አስፍሮ ያወዳድረዋል ያን ጊዜ ፍቅር ከሌለን ሁሉም ነገር ከንቱ ይሆናል። ዘንድሮ ጌታ ሰዎችንም እግዚአብሄርንም የምንወድበትን የመውደድ መንፈስ ይልቀቅብን አለበለዚያ ብዙ ማገልገል ብዙ መድከም በ ዜሮ ማባዛት ይሆንብናል። ተባረኩ ✋
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
ምሳሌ❾
“ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤ አሳፋሪ ሴት ግን በአጥንቱ ውስጥ እንደ ቅንቅን ናት።”
— ምሳሌ 12፥4
“መልካም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት፤ አሳፋሪ ሚስት ግን ዐጥንቱ ውስጥ እንዳለ ንቅዘት ናት።”
— ምሳሌ 12፥4 (አዲሱ መ.ት)
👉ለውጥ በአንድ ቀን የሚሆን ነገር አይደለም በአንድ ቀን ለውጥ አይመጣም ቀስ በቀስ ነው
👉 የብዙዎቻችን ችግር መለወጤ አይቀርም ስለዚህ አንድ ቀን እለወጣለው ምን አጨናነቀኝ እንላለን🤷♂። አንድ እውነት ልንገሪችሁ ለውጥ የአንድ ቀን ስራ አይደለም የቀን ተቀን ትጋታችንን ይፈልጋል። ለመለወጥ ካሰብን ማሰብ ያለብን በ process እንደሚመጣ እና ለውጥ ማለት በብዙ ቀናት ትጋት እንጂ አንድ ቀን ብቻ አለመሆኑን ማሰብ
👉 የተለወጠ ሰው ማለት እድገት ያሳየ ከነበረበት ከበፊቱ position አንድ step ወደ ነገሩ የመጣ ሰው እያደገ ነው ልንል እንችላለን በጣም የሚገርመው ደግሞ እድገት የሚመጣው በprocess ነው ማደግ ነብይ ጋር ወይም ፓስተር ጋር ያለ ነገር ሳይሆን የግል ትጋትን የሚጠይቅ ነው። በጌታ በኢየሱስም ዛሬ እንድታድግ እጸልያለው🖐 አይባልም!!!!😁 ምክንያቱም እድገትን ከነብዩ ወይም ከፓስተር አይገኝም እንደዛ የምናስብ ሰዎች ችግኝ ተክሎ ወዲያው እንደሚበቅል እንደማሰብ ነው። ችግኝ እንድታድግ በየቀኑ ለእድገቷ የሚያስፈልጋትን ማድረግ አለብን ማጠጣት አለብን ስሮቿ ምግብ ማግኘት እና አካላቶቿ መመገብ አለባቸው ያልበላ እና ያልጠጣ physicaly ሊያድግ እንደማይችል የጌታን ቃል የማያነብና የማይጸልይ መቼም እድገትን አያገኝም ማደግ ያለው በየቀኑ በምናሳየው መንፈሳዊ ትጋት ነው።
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiriflow
መንፈስ አለም ነገ የሚባል ነገር የለም! ዛሬ መስራት ያለብንን ቀጠሮ እየሰጠን አናስቀምጥ ምክንያቱም ነገም ቢሆን እንደምንሰራው እርግጠኛ አደለንም ዛሬን ለጌታ እንኑር።
Читать полностью…በጣም ቀላሉ ነገር በዚህ ምድር ላይ አንድን ነገር ማበላሸት ነው😁 ለምን መሰላችሁ ለምሳሌ፦አንድ ፎቅ ለመስራት ብዙ አመት ይቆያል ለማበላሸት ወይም ለመደርመስ አንድ ቀን በቂ ነው በጣም ቀላሉ ነገር ማበላሸት ነው። ለዚህ ነው በጣም ግዙፍ እና ጥራት ያላቸው ፎቆች በተለያዩ አደጋዎች በአንድ ቀን አመድ ሲሆኑ አይተናል።
👉 ወደ መንፈሳዊው ነገር ሳመጣችሁ እኛ የእግዚአብሔር ህንጻዎች ነን ክርስቶስን ለመምሰል እየተሰራን ነው ተሰርቶ ያለቀ ሰው የለም እየተሰራ የሚኖር፣እየተሰራ የሚያገለግል ነው ሁሉም ሰው በጣም የሚጠርመው ግን እኛ ህይወታችንን ከመሰራት ህይወት ብናወጣው ተራ ሰዎች እንሆናለን ብዙዎቻችን ችግራችን ተሰርቶ ማለቅን እያሰብን ማገልገል አንፈልግም መንፈሳዊ ነገሮች ላይ መሳተፍ አንፈልግም ይሄ ደግሞ ትልቅ ስህተት ነው እየተሰራን ነው መንፈሳዊ ነገሮች ላይ መሳተፍ ያለብን
👉ዛሬ አንድ ለማደግ ለመሰራት ትልቅ ነገር እየነገርኩችሁ ነው የማታገለግሉ ማገልገል ጀምሩ የምትሰሩበት ቦታ እሱ ነው በቤታችሁ ያላችሁን መንፈሳዊነት ለማሳደግ ማገልገል መጀመር መንቀሳቀስ አለባችሁ በጣም ቀላሉ ነገር መበላሸት ነው መስተካከል ነው ከባዱ ስለዚህ ዛሬ ጀምሩ ለመሰራት ለማገልገል በምንም ቦታ ውስጥ ሊሆን ይችላል መጀመር ካልቻላችሁ ማደግና በውስጣችሁ ያለውን ጥሪ መፈጸም አትችሉም ከተቀመጣችሁበት comfort zone መውጣት አለባችሁ መንቀሳቀስ መስራት አለባችሁ በአንዴው perfect ለመሆን አታስቡ perfect የሆነ ሰው የለም በአንዴው ውበት ወዳለው የመንፈሳዊ ህይወት level አትመጡም process ተከትላችሁ ነው በመሰራት ነው ወደዛ የምትመጡት
👉ስለዚህ ጀምሩ መጸለይ ጀምሩ ማገልገል ጀምሩ ሀላፊነትን መውሰድ ሳትነካኩ መቀመጥን ከመረጣችሁ ተመሳሳይ ህይወትን ትመራላችሁ መንፈስ ቅዱስ አንተን/አንቺን ነው የተናገረሽ/የተናገረክ
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
አንድ ትልቅ የእግዚአብሄር ሰው በማገልገል ላይ እያለ በጣም የ finance እጥረት አጋጥሞት በጣም ተማሮ በውስጤ ያለውን ጥሪ እንድፈጽም ገንዘብ ያስፈልገኛል ጌታ ሆይ ስጠኝ ብሎ ለመነው
👉ጌታም ተነስተህ ውጣ ብሎ የሆነ ገጠራማ ስፍራ ሂድ ብሎ ተናገረው ቦታው እሩቅ ቢሆንም ምን ሊያደርግ ነው ብሎ ሲሄድ እና በቦታው ሲደርስ ብዙም ቤቶች የሌሉበት ሜዳ ብቻ የሆነ ቦታ ነበረ እዛ እንደደረሰ ጌታ ይህንን የምታየውን መሬት ግዛው አለው ሰውየውም እንዴት ይህን ገጠራማ ቦታ እገዛለው በዛ ላይ ሰዎች ብዙም አይኖሩበትም ብሎ ከጌታ ጋር መከራከር ጀመረ በመጨረሻም የጌታን ትዕዛዝ በማክበር ቦታውን ከአንድ ገበሬ ይገዛዋል ነገሩ ብዙም ባይዋጥለትም ነገር ግን ከዕለታት አንድቀን የመዓድንና ነዳጅ ሚኒስትር ሰራተኞች እሱ መሬት የገዛበትን መሬት እንደሚፈልጉት ለእርሱ ጠርተው ይነግሩታል ምክንያቱን ሲጠይቃቸው ነዳጅ በዚህ መሬት ውስጥ ተገኝቶአል አሉት ከዛም በከፍተኛ ዋጋ ተምነውለት መሬቱን በውድ ሸጠው ትልቁን የfinance ጥያቄውን ጌታ ፈታለት። በውስጣቹ ስላለው የመለኮት ፕሮግራም ሲል ሰማይ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሰጣቹሀል ምክንያቱም በህይወት ያላችሁት ለዚህ ጥሪ ነው።
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
ዘጸአት 8 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ ከዚያም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ፣ “ሂዱና በዚሁ ምድር ለአምላካችሁ ሠዉ” አላቸው።
²⁶ ሙሴ ግን እንዲህ አለ፤ “ይህ ትክክል አይሆንም፤ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የምናቀርበው መሥዋዕት በግብፃውያን ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ ታዲያ በእነርሱ ዐይን አስጸያፊ የሆነውን መሥዋዕት ብናቀርብ አይወግሩንምን?
²⁷ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) እርሱ እንዳዘዘን መሥዋዕት ለመሠዋት ወደ ምድረ በዳ የሦስት ቀን መንገድ መሄድ አለብን።
ጸሎት ማለት ብዙ የምንቀበልበት ነገር ብቻ ማለት አይመስለኝም ለሚመጡጥ መልሶች ብዙ የምንሰራበት እንደውም ከመቀበል ይልቅ ብዙ ነገሮቻችንን የምናጣበት ነገር ነው ለምሳሌ፦
👉 ራስ ወዳድነቴን
👉 ትምክህቴን
👉 አለማዊ ምኞቴን
👉 የሀጢያትን ጣዕም
👉 በሀጢያት የሚገኝ ደስታን እና የመሳሰሉትን የማጣበት የምሰራበት ለሚመጣ መልስ ምቹ environment የሚፈጠርበትም ጭምር ጸሎት ነው ብዬ አስባለሁ ጸሎት ላይ ብዙ ትምህርት አይሰራም ይጸለያል እንጂ!!!!!!
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
ክርስቶስ የተወለደው የሚሞት፣ የሚደማ፣ የሚቦጨቅ ስጋ ለመልበስ ነው ውልደትን enjoy እንድናደርግ የሚያደርገን ሊሞት ስለሆነ ነው መወለድ አንድ ደስታ አለው ከሁሉም በላይ የሚያስደስተው ግን የተወለደበት ሰው የሆነበት ምክንያቱ እኛን ከእርሱ ጋር ለማኖር መሆኑ ነው በክርስቶስ ልደት ውስጥ የዘላለም ውልደት ስላየንበት ነው enjoy የምናደርገው መሲሁ ኢየሱስ ተወልዶአል
Читать полностью…የፈለገ የሀጢያት ቀንበር ውስጥ ብትሆን ከወደክበት እንዳትነሳ የሚያደርግህ እግዚአብሄር ይቅር አላለኝም ወይም እንዴት ፊቱን አየዋለው የሚል ስሜት ነው ሌላው ደግሞ ጌታ ይቅር ብሎን ለራሳችን ይቅርታ ስለማናደርግ ከጌታ ጋር መስማማት አንችልም
👉ለራስህ ይቅርታ አድርግለት ልክ ነው ከባድ ነገር ውስጥ ነህ ግን ለራስህ ይቅርታ አድርግለት ጸጸት በሽታ ነው መጨረሻ ላይ መወሰን የሌለብህን ውሳኔ እንድትወስን ያደርግሀል በጸጸት ሳይሆን በንስሀ ወደ ጌታ ብንቀርብ ለራሳችን ይቅርታ ብናደርግለት የሚረዳ የጌታ እጅ ዛሬም አላጠረችም።
. ክርሰቲያን ነኝ
ዘማሪ በረከት ተስፋዬ | New ETHIOPIAN GOSPEL SONG
⏰5:40 📥23.1
sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯
🗣ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ
🚩@JESUSlovingly143
🚩@JESUSlovingly143
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
📲ሼር ማድረግዎን እዳይረሱ📲
── ❖ ── ✦ ── ❖ ──
የምር ለኢትዮጵያ ጸልዩ የፖለቲካውን የኢኮኖሚውን የማህበራዊውን ሁኔታ ሊቀይር እና መልካም ሊያደርግ የሚችለው በጸሎት ወደ ጌታ ሰንቀርብ ነው ውጪ እንዳሉት አላማኞች በእያንዳንዱ ነገር detail እየገባን አናወራም እኛ በጸሎት የጌታ ፍቃድ እንደሚፈጸም እናምናለን ስለዚህ የመጀመሪያም የመጨረሻም አማራጫችን መጸለይ ነው።
Читать полностью…✌✌✌አስተማሪ ታሪክ!✌✌✌
ፕሮፌሰሩ ክፍል ውስጥ የተሰበሰቡትን ተማሪዎች እንዲህ ብሎ ይጠይቃል "86,400 ብር አላችሁ እንበል፤
አንድ ሰው ይመጣና 10ብር ይዞባቹ ይሮጣል፤ እና ለዛች 10ብር ብላቹ 86,390ብሩን ትታቹ ሰውየውን ተከትላቹ ትሮጣላቹ ወይስ የቀረውን 86,390ብር ይዛቹ መንገዳችሁን ትቀጥላላቹ?"
ተማሪዎቹም ቀላል ጥያቄ ይሆንባቸውና "የቀረውን ብር ይዘን እንቀጥላለን እንጂ!" ብለው መለሱ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ፕሮፌሰሩም እንዲህ አላቸው "ይሄውላቹ በቀን ውስጥ 86,400 ሰከንዶች አላችሁ። እናም አንድ ሰው በ10 ሰከንድ ውስጥ ለተናገራቹ ነገር ቀኑን ሙሉ ስትበሳጩ፣ ስታዝኑ፣ ስትናደዱ የምትውሉ ከሆነ 86,390 ሰከንዶቹንም ታጣላቹ።
ሰው አሉታዊ ነገር የሚናገራቹ ከራሱ አንፃር ነው። እናም መንገዳችሁን ቀጥሉና የቀሩትን 86,390 ሰከንዶችን አትርፉ!"
በዚህ የሁለት ደቂቃ ንግግሩ እነሱ ስንት ሰአቶችን ያተርፋሉ ብላቹ ታስባላቹ? እናንተስ ይሄን በማንበብ ስንት ታተርፋላቹ?
የሆነ የምትጠብቁት ነገር ከሌለ የሚወርሳችሁ ነገር የለም የሚመጣ መለኮታዊ ጉብኝት አለ ብላችሁ የምትጠባበቁት ደግሞም ነገሮቼ እንዲህ አይቀጥሉም እያላችሁ በጸሎት መጠባበቅ ግዴታ ነው።
(የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 6)
----------
3፤ ወንድሞች ሆይ፥ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፥ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፤
. . .
5፤ ይህም ቃል ሕዝብን ሁሉ ደስ አሰኛቸው፤ እምነትና መንፈስ ቅዱስም የሞላበትን ሰው እስጢፋኖስን ፊልጶስንም ጵሮኮሮስንም ኒቃሮናንም ጢሞናንም ጳርሜናንም ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን የአንጾኪያውን ኒቆላዎስንም መረጡ።
👉 እስጢፋኖስን የምናውቀው በትልቅ የሀይል መንፈስ ሲያገለግል እና በተጽእኖ ፈጣሪነት ቢሆንም ወደዚህኛው ጥሪ ከመምጣቱ ከመለየቱ በፊት አስተናጋጅነት የሚሰራ ሰው ነበር ግን ደግሞ መንፈሰ የሞላበት ሰው ነበረ🖐 ምንማለት መሰላችሁ በላችሁበት የትኛውም ቦታ ብትሆኑ እየተማራችሁ ቢሆንም፣ እየሰራችሁ ቢሆንም፣ የትኛውም ቦታ ሆናችሁ ዝም ብላችሁ ተቀጣጠሉ ጸልዪ አንድ ቀን ወደ ጥሪያችሁ ያመጣቹሀል አንድ ቀን ይለያቹሀል🖐
👉 እኔ የሚገርመኝ አስተናጋጅነት እየሰራ እንዴት መንፈስ የሞላበት ሆኖ ተገኘ?🤔 አያችሁ እስጢፋኖስ እያስተናገደም ቢሆን ወንበር እየጠረገ ቢሆንም ባለበት ቦታ እየጸለየ ነበር ማለት ነው እየተቀጣጠለ ነበረ ወንበር እየጠረገ ይቀጣጠል ነበረ እያስተናገደ ይቀጣጠል ነበረ
👉ዛሬም እንደ እስጢፋኖስ ውስጣችን ትልቅ ጥሪ ያለብን በብዙ ነቢያቶች የተነገረን መንፈስ ቅዱስም በውስጣችን የመሰከረልን አለን ነገር ግን ያለንበት ቦታ ላይ ተስፋ መቁረጥ የለብንም የማይሆን የማይፈጸም እንዳይመስለን ይልቅ ባለንበት ቦታ እንቀጣጠል እየጸለይን እንጠብቀው አንድ ቀን ይለየናል።
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
የጌታ ልጆች ትናንትና ማታ እየጸለይን የጌታ መንፈስ ሲናገረን ነበረ በጣም የቀረበ የሰማይ ጠል አለ ምድራችንን ለማረስረስ 🌨🌨 ነገር ግን እንድታስተውሉ የምፈልገው ሰይጣን ደግሞ በቁጣ ተነስቶአል ትውልድን ለማጥፋት ተጠንቀቁ እየዞረ ነው ሰይጣን ተስፋ ለማስቆረጥ እና ጸሎትን ለመብላት ተዘጋጁ ዝም ብላችሁ ጓጀኞቻችሁ ቢንቋችሁም የቸርች ሰዎች ቢንቋችሁም አጥብቃችሁ ጸልዩ እንትና ለምን ሰደበኝ/ችኝ ብላችሁ ከመጸለት እንዳታቆሙ ደግሞም ትውልድን እያስለቀቃችሁ ጸልዩ በእርግጠኝነት በደጃችን ነው ያለው ሊዘንብ ነው🌨🌨
Читать полностью…(የዮሐንስ ራእይ ምዕ. 2)
----------
2፤ ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንዳትችል፥ እንዲሁም ሳይሆኑ። ሐዋርያት ነን የሚሉቱን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤
3፤ ታግሠህማል፥ ስለ ስሜም ብለህ ጸንተህ አልደከምህም።
4፤ ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።
5፤ እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።
እኔ ምጥ ይዞኛል😭
በዚህ ዘመን ብዙ ሰው ለመታወቅ የሚሰራበት ዘመን ነው በባሌም በቦሌም ብቻ famous ለመሆን የሚሰራበት ዘመን ነው። እኔ ግን የምጸልየው የሚነሳው ትውልድ ለማታወቅ ሳይሆን ኢየሱስን ለማሳወቅ የሚሰራ እንዲሆን ነው ካሜራ፣የሆነ ግርግር የማይጠብቁ፣የሰዎችን ብዛት እና ማነስ የማይጠብቅ copy የሆነ ነገር የሌለው ማለትም ያልተነካ ሰማያዊ መዝሙር ያልተነካ ሰማያዊ ስብከት ያላቸው እንዲነሱ እጸልያለው ኢየሱስን ለመስበክ የተመቻቸ ቦታ አንጠብቅም በየትኛውም ስፍራ ኢየሱስ የሚታይባቸው እና ደግሞ ጸሎት ዳገት ያልሆነባቸው ሲጸልዪ ደግሞ ሰማያትን የሚያስከፍቱ ጀግና ትውልዶች ይታዩኛል
👉 ለመልካቸው ብዙ ማይጨነቁ ለጌታ መልክ ግን የሚጨነቁ ለታይታ የማይሰሩ ኢየሱስ እንዲታይ ግነ የሚሰሩ ለስማቸው ብዙ የማይጨነቁ ለጌታ ስም ግን የሚጨነቁ ፍላጎቶቻቸውን የገደሉ እንደ ወታደር የነቁ ሁሌ ዝግጁ የሆኑ ይታዩኛል። እኔ ምጥ ይዞኛል እንዲህ አይነት ትውልድ ሆነን እስከምንገለጥ ድረስ 😭😭
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
👉 ጴጥሮስ ይሁዳን በሰይፍ ቢገለው ኃጢያተኛን አንጂ ኃጢያትን አይገልም። #ኢየሱስ ግን በሰይፍ ቢሞት ኃጢያትን እንጂ ኃጢያተኛውን አይገልም። ስለዚህ የኔና የእናንተ ክፋት ኃጢያተኛውን ሲገለው ኃጢያትን ግን አይገለውም። ኃጢያትን የሚገለው ክፋት አይደለም #ፍቅር ነው።
Читать полностью…