ወንጌል ስለ ልጁ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ስንል ከእግዚአብሄር ጋር የተዋወቅነው ወይንም መለኮትን ያወቅነው በእርሱ ስለሆነ እሱ እራሱ እግዚአብሄር ዘላለማዊ ንግግር ለፍጥረታት ያሰማው በልጁ ስለሆነ ልጁ ኢየሱስ የእግዚአብሄር መገለጥ ስለሆነ ነው ወንጌል
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
የሰሞኑ ጉዳይን በተመለከተ
====================
በክርስትና ውስጥ ማመቻመች የሚባል ነገር የለም ማለትም Tolerance / መቻቻል / የለም ከአለም እና ከጨለማ ጋር በማመቻመች አይኖርም እየገለጥነው እናም እየተቃወምነው እንቀጥላለን!!!! ጨለማ ላይ ያሉትም ወደ ብርሀን ይመጣሉ።
“ፍሬ ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር ምንም ዐይነት ግንኙነት አይኑራችሁ፤ ይልቁን ግለጡት፤”
— ኤፌሶን 5፥11 (አዲሱ መ.ት)
አንድ ታዳጊ ልጅ ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄድ ሁሌም የተማረውን ነገር ወደ ቤት ሲመጣ ማስረዳት አለበት አንድ ቀን እንደተለምዶ ወደ ቤተክርስቲያን ሄደ ስብከት ሰአት ደረሰ እናም ሰባኪው ከስብከቱ ይልቅ ብዙ ስለ ዞረበት ሀገር ስለ ሄደባቸው ከተሞች ይበልጥ ይናገራል። ከዚያም ይሄ ልጅ ወደ እቤት ሲመለስ ቤተሰቦቹ እንደተለመደው ምን ተማርክ ብለው ሲጠይቁት Geography ተማርን ስለ ውጭሀገር እና አንዳንድ ከተሞች ብሎ እርፍ 😂። እና ኢየሱስን የቀመሰ ሰው እንዴት ክብሩን ጥሎ እንደመጣ የተረዳ ሰው በፍጹም ክብሬ አይልም ክብሩንም አይፈልግም።
👉ተጠንቀቁ "ትዕቢት ውድቀትን ትህትና ክብርን ትቀድማለች " Order አለው የሚቀድመው ክብር አይደለም ትህትና ነው!!
ይሄንን አለመስማት አይቻልም 😭
እየጸለያችሁ ስሙት!!!!!
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ባመንክበት በዚያው ቅጽፈት የእግዚአብሄር ልጅ ነህ ፣ ድነሀል ፣ ጸድቀሀል!!!! ይህ እውነት በጣም የሚገርም ነው ምክንያቱም የኛን ምንም Contribution አይፈልግም።
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
(ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕ. 9)
----------
30፤ እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፤
31፤ እስራኤል ግን የጽድቅን ሕግ እየተከተሉ ወደ ሕግ አልደረሱም።
32-33፤ ይህስ ስለ ምንድር ነው? በሥራ እንጂ በእምነት ጽድቅን ስላልተከተሉ ነው፤ እነሆ፥ በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዓለት አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ እንደ ተጻፈ በእንቅፋት ድንጋይ ተሰናከሉ።
ፍቅርህ ወዳጅ አደረገን እንጂ ወዳጅ ሆነን አግኝተኸን አልወደድከንም።
@gospelofthekingd0m
@gospelofthekingd0m
@gospelofthekingd0m
ብዙ ልጆች እየጠየቁኝ ነበር ሰው ማነው? ሰጋ፣ነፍስ፣መንፈስ ወይስ ሰው መንፈስ ነው? የተወሰነ ነገር ለማንሳት እሞክራለው ተዘጋጁ!!!
Читать полностью…ሳይነጋ ለሊቱ ሳትቀድመኝ ጀምበር
መጥቻለሁ ፊትህ ለሊት ላልከኝ ጉዳይ
አንተን ባየ አይኔ ይስሀቄን አይቼ ንቄዋለሁ
ሳላንገራግር ሳራን ሳላማክር ሰዋዋለሁ
አንተን ባየ አይኔ የኔን ሳቅ አይቼ ንቄዋለሁ
ሳላንገራግር ሰዎች ሳላማክር ሰዋዋለሁ
ይሁና የኔ ሳቅ ለእርሱ
ይሁና ደስታዬ ለእርሱ
ይበሉኝ ባዶ የቀረ
ይበሉኝ የተሞኘ
. አንተን ባየ አይኔ -||- በረከት ለማ
sʜᴀʀᴇ◈
በቃ ዝም ብለን እንስማው🙏
መስቀሉ ወይስ የመስቀሉ ቃል?
1ኛ ቆሮንቶስ 1 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉ ሞኝነት ነው፤ ለእኛ ለምንድ ነው ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤
👉 መስቀል ማለት በሮማዊያን የተረገመ ሰው የሚሰቀልበት የቅጣት ቦታ ነው። ብዙ ወንጀለኞች የሚሰቀሉበት ቦታ ነው መስቀል ላይ ክርስቶስም ሲሰቀል አብረውት ሰዎች ተሰቅለዋል። ክርስቶስ የተረገምን ሳለን እርግማናችንን በመስቀል ተሸክሞታል ታዲያ ይህ እውነት ከገባን በመስቀል የሞቱ ብዙዎች አሉ ሰለ መስቀሉ ሳይሆን ስለሞተልን በመስቀል ስለተንጠለጠለው ክርስቶስ ማውራት ነው እውነተኛ ክርስትና ነገሩ መስቀሉ ላይ ስላለው ሳይሆን ስለ ሆነ ቁስ መነጋገር የእግዚአብሄር ፍላጎት አይደለም ስለ ሞተልን ስለ ተሰቀለው እንጂ ስለ ተሰቀለበት ማውራት የከፈለልንን አምላክ credit አለመስጠት እንዳሆንብን። ጳውሎስ ለዚህ ነው የተሰቀለውን(ኢየሱስን) እንጂ የተሰቀለበትን(መስቀሉን) እሰብካለሁ ያላለው👇
1ኛ ቆሮ 1:23 (አዲሱ መ.ት)
እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ መሰናክል፣ ለአሕዛብ ደግሞ ሞኝነት ነው።
👉 መስቀሉ ሳይሆን የመስቀሉ ቃል ( ኢየሱስ) ዛሬም የሚያድን ፣ የሚታደግ የማይሰረቅብን ፣ የማይወሰድብንነው በልባችን የተቀመጠ ማህተማችን ነው።
👉 መስቀሉማ ቢሆን ማንም ወንበዴ የተባለ ሁሉ ተሰቅሎበታል ልዩነቱ ከመስቀሉ ሳይሆን ከኢየሱስ (የመስቀሉ ቃል) ነው።
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
ዘመኔ በከንቱ እንዲያልቅ አልፈልግም 😭
-------------------------------------------------------
አመታት ሲሰጡን በብቃታችን አይደለም የተሰጡን ያላለቀ የሰማይ አጀንዳ ወይም ትልቅ አላማ ስላለብን የተሰጡን ናቸው። ታዲያ የተሰጡንን ዘመን ወደ ኋላ ዘወር ብለን እንመልከተው 🤔 የምር የሚታይ ለውጥ ነበረ? እድሜ የተቀጠለልንን አላማ አግኝተነዋል? ወይስ ያልተጠቀምንባቸው ቀናቶች በዝተው ይታዩናል? በፍጹም ልናገኘው የማንችለው ግን የባከነ ዘመን ብዙ እንደነበረን አስባለሁ ነገር ግን 2015 ጌታ ሲሰጠን እንድናባክነው ሳይሆን ፍሬያችን የሚበዛበት እንዲሆን ነው።
👉 በወታደር ቤት👮♂ አሰልቺው ነገር ባለህበት ሂድ ነው። ማለት እንቅስቃሴ የለም ልክ እንዲሁ በኛም ህይወት ፈቀቅ ያለ ነገር የለም ነገሮቻችን ባሉበት ሲሄዱ ያው 2014 ከነበረው የተለየ ነገር የለም😒 የምንለው ህይወት አሰልቺ ነው ለውጥ ያስፈልጋል በመንፈሳዊ ነገራችን እንዲሁም ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት በወንጌል ጉዳይ ለውጥ የሚታይ ለውጥ!!!! ያስፈልጋል። ድሮ እንዲህ እንዲህ ነበረ አሁን ግን... ብለን የምንለው ለውጥ የታለ???
👉 ድሮም ቸርች ትሄዳለህ አሁንም ትሄዳለህ
👉 ድሮም አትጸልይም አሁንም አትጸልይም
👉 ድሮም ለውጥ ትፈልጋለህ ግን አትንቀሳቀስም
👉 ድሮም ፍላጎት አለህ ግን አልወሰንክም
👉 ድሮም ታገለግላለህ ነገር ግን የተለወጠ አገልግሎት የለህም
👉 ድሮም ትጸልያለህ ግን የምር አትጸልይም
፨ እና ይሄ ባለህበት ሂድ አይደለም ልትል ነው? 🤔 የምር ካልጸለይን ፣ የምር ካልጮህን የተጠማነውን አናገኝም ዘመናችንን እያባከንን እንሄዳለን
👉 ይህ ያለንበት ዘመን የመጨረሻ መጨረሻ ነው የሚባለው ሀጢያት ስር እየሰደደ ፣ ሰው ሁሉ የራሱን መንገድ መርጦ እንደወደደ የሚኖርበት ዘመን ላይ ነው ያለነው ጌታ ሊመጣ በደጅ ነው።
፨ በእግር ኳስ ሊያልቅ ሲል ተጨማሪ ደቂቃ ተብሎ እንደሚሰጥ እንዲሁ ተጨማሪ ሰዓት ላይ ነን⏰ ነገር ሁሉ ወደ መጨረሻ ሊመጣ ነው በዚህ የመጨረሻ መጨረሻ ዘመን ሲሰጠን እንደ ሌላ ዘመን የምንባክንበት አይደለም ለትውልድ ጌታ ተጠቅሞብን እንደወደደው የምንኖርለት ዘመን ነው የተሰጠን extra time ላይ ነው ያለነው በጥንቃቄ እንኑር ለውጥን የምንፈልግ ከመሆን ህይወት ወደ ለውጥ አምጪነት የምንለወጥበት ዘመን ተሰጥቶናል አናም ይህ ውድ ዘመን እንዲባክንብኝ አልፈልግም 😭።
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
ጌታ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛችን ስንቀበል የተቀበልነው ሰላም አለ በምግብ በገንዘብ በሁኔታዎች የማይለካ አለ ነገር ግን እነዚህ ነገሮች ደስታችንን እንዳይቀሙን ደስታችንን ካስቀመጥንባቸው ነገሮች አንስተን ወደ ክርስቶስ ማስቀመጥ አለብን።
👉 ይህ የክርስቶስ ሰላም እንዲጠበቅ ከየትኛውም ምድራዊ ነገር በላይ መሆን አለበት ደግሞም ሰው በጌታ ካልሆነ በፍጹም ይህንን ሰላም መለማመድ አይችልም ምክንያቱም የመደሰቻው ቁልፍ አሁንም ምድር ላይ ስለሆነ 😊።
1ኛ ጴጥሮስ 4 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ የሁሉ ነገር መጨረሻ ተቃርቦአል፤ ስለዚህ መጸለይ እንድትችሉ ንቁ አእምሮ ይኑራችሁ፤ ራሳችሁንም የምትገዙ ሁኑ።
⁸ ፍቅር ብዙ ኀጢአትን ይሸፍናልና ከሁሉ በላይ እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ፤
⁹ እርስ በርሳችሁ ያለ ማጒረምረም እንግድነት ተቀባበሉ።
¹⁰ እንደ ታማኝ የእግዚአብሔር ልዩ ልዩ ጸጋ መጋቢ እያንዳንዱ ሰው በተቀበለው የጸጋ ስጦታ ሌላውን ያገልግል፤
¹¹ ከእናንተ ማንም የሚናገር ቢኖር እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢኖር እግዚአብሔር በሚሰጠው ብርታት ያገልግል፤ ይኸውም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እንዲከብር ነው፤ ክብርና ኀይል ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን፤ አሜን።
👉 በዚህ ክፍል ጴጥሮስ ሁለት ነገሮች ላይ focus እያደረገ ይናገራል
1. ለኖረን ስለሚገባው ህብረት ማለትም ከልብ መዋደድ የሚል ሀሳብ ያለው መልዕክት ይጽፍልናል።
2. ሊኖረን ስለሚገባው አገልግሎት ማለትም በተሰጠን ጸጋ ሌሎችን ማገልገል የሚልን ሀሳብ ያነሳል።
👉 ወዳጆቼ በመመረታዊ ደረጃ ልናገር የምንችለው በዚህ ክፍል ውስጥ ሌሎችን በተሰጠን የጸጋ ስጦታ ማነጽ አለብን ማገልገል አለብን እንደተቀበልነው የጸጋ ስጦታ መጠን ለሌላው መትረፍ አለብን። ብዙን ጊዜ የተሰጠን ነገር ይቀልብናል እግዚአብሄር ወዶ በውስጣችን ላስቀመጠው ነገር careless የመሆን አዝማሚያ ይታይብናል በዚህ ክፍል "እንደ ታማኝ መጋቢ" የሚል ቃል አለ ለተሰጠን የእግዚአብሄር ሀሳብ ታማኞች መሆን አለብን።
👉ነገር ግን ይህን ሁሉ ከማድረጋችን በፊት አንድ መቅደም ያለበትን ነገር ሀዋሪያው ጴጥሮስ ያነሳልናል ይኸውም እርስ በእርስ ከማገልገላችን በፊት እርስ በእርስ ያለን ከልብ መዋደድ ለቀጣይ ህይወት እና አገልግሎት መሠረት ነው።
"ከሁሉ በላይ እርስ በእርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ" ይህን በመጀመሪያ መፈጸም ካልቻልን ቀጣይ የምናደርገው ነገር አይጸናም so ዛሬ ለማስተላለፍ የፈለኩት ከልብ የሆነ መቀባበል ካለ በመካከላችን በህብረችን ያን ጊዜ የጸጋ ስጦታዊቻችን flow ማድረግ ይጀምራሉ። የትኛውም ህብረት የሚቀጥለው በጸጋ ስጦታ አይደለም! የሚቀጥለው በፍቅር ነው ሌሎች ድርጊቶቻችን እንዲገለጡ የግድ መቀባበል እና ከልብ የሆነ መዋደድ ሊኖረን የግድ ነው!! በዚህ አመት ጌታ ከልብ በመዋደድ ይባርከን!!!!!!!!
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
" ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት በ 1947 ነበር..አሁን አርጅቻለሁ 90 አመቴ ነው...ግን አሁንም ተመልሼ ወደ ደቡብ ኦሞ ብሄድ ደስ ይለኝ ነበር…እነዚህን ከጎማ የተሰሩ ነጠላ ጫማዎች ለማስታወሻ ያመጣሁት እነሱን አድርገዉ በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን በሸለቆው የተራመዱ ወንጌላዉያንን ለማስታወስ ነው...አሁን የሚሄደዉ ማነዉ? "
Missionary Maclellan at Sodo Christian Hospital chapel this morning, author of these amazing books.
አልሆን ያለህ እንደው መጉላትና መግዘፍ
ከትልቆች መሀል አንዱን መርጠህ ዝለፍ😂😂😂
👉 እንዲህ አይነቱን አገልጋይ ነኝ ባይ አትስሙት እየሱስን ልናይ ልንሰማ እንወዳለን በሉት ✋
ሰው ማነው?? Part 1 ስጋ ምንድነው በመጽሀፍቅዱስ?
በጣም ጠቃሚ ትምህርት ነው ስሙት ለሌሎችም ላኩላቸው።
Share it please
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
በክርስቶስ ፍጹም ሰው አድርጎ ሊያቀርበን መንፈስ ቅዱስ ሁሌም በእኛ ውስጥ ትጉህ ነው።
@gospelofthekingd0m
@gospelofthekingd0m
ትንሽ የለው ትልቅ ይሰጥሀል
ሁሉን አጠራቅሞ ሞት ይከፍልሀል
አይ ሀጢያት 🤔
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
“#ከእምነት_የሆነውን_ሥራችሁን፣ #ከፍቅር_የመነጨውን #ድካማችሁንና_በጌታችን_በኢየሱስ #ክርስቶስ_ባላችሁ_ተስፋ #የተገኘውን_ጽናታችሁን በአምላካችንና በአባታችን ፊት ዘወትር እናስባለን።”
— 1ኛ ተሰሎንቄ 1፥3 (አዲሱ መ.ት)
🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑
የተሰሎንቄ ቤተክርስቲያን በብዙ መልካም በሆኑ መንፈሳዊ ነገሮች የተመሰከረላት ናት። አሁን ላይ ላለን የክርስቶስ አካል ለሆንን አማኞች እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ህብረት እንደ ሞዴል አድርገን እንድንማርባት መንፈስ ቅዱስ ዕድሉን ሰጥቶናል።
ከላይ ባለው ቅዱስ ቃል ውስጥ በተገለጠው የጳውሎስ ንግግር ላይ እንደምናየው ሶስት የተሰሎንቄ አማኞችን መልካም ዕሴት (Quality) እንመለከታለን፦
፩. ከእምነት የሆነ ሥራ
የተሰሎንቄ አማኞች በክርስቶስ ላይ ካላቸው እምነት የተነሣ የጽድቅ ፍሬ በሆነ ሥራ ተሞልተዋሉ፤ እነዚህ አማኞች ሲሰሩ የሚታዩት ለመጽደቅ ብለው ሳይሆን በክርስቶስ ላይ ካላቸው እምነት የተነሣ ስለጸደቁ ያፈሩት ፍሬ ነው። ስለዚህ እነዚህ አማኞች ከውስጥ የጀመረ የህይወት ለውጥ እንዳላቸው በውጭ ከሚያሳዩት ምግባር ያስመሰክራሉ።
፪. ከፍቅር የመነጨ ድካም
የተሰሎንቄ አማኞች የሚያሳዩት ፍቅር ከመንፈስ ቅዱስ የሆነ ፍቅር ሲሆን ይሄም በተፈጥሮ ሳይሆን በክርስቶስ በመሆናቸው ከመንፈስ የጀመረ ፍቅር ነው፤ ይሄ ፍቅራቸው ትጋትን/ድካምን በህይወታቸው ፈጥሯል ለወንድሞቻቸው ሆነ ለጌታ ለሚያደርጉት በጎ ነገር ሁሉ ሳያጉረመርሙ እንዲተጉ የሚያደርጋቸው ይሄ ከመንፈስ የሆነ ፍቅር ነው። ፍቅር ደግሞ ዋነኛው የመንፈስ ፍሬ የጌታ ደቀመዝሙር ለመሆናችን መለያ እና ከሁሉ የላቀው የፀጋ ስጦታ ነው።
፫. ተስፋ
እነዚህ አማኞች በተስፋ የተሞሉ ናቸው ይሄን ተስፋ ያገኙት በውስጣቸው በሚኖረው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሀይል ነው ተስፋቸውም ያልተጨበጠ ነገር ሳይሆን እርግጥ የሆነው የጌታቸው የአዳኛቸው የዘላለም ህይወት የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ መምጣት እና ከሚመጣው ቁጣ እነርሱን ማዳኑ ነው፤ ስለዚህ ኢየሱስን በተስፋ ከመጠበቃቸው የተነሳ በመጽናት ህይወት ውስጥ ይገኛሉ።
🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋
ከቃሉ እንደተማርነው በትክክለኛ አቋም ላይ ከሚገኙ ክርስቲያኖች
✔ከእምነት የሆነ ሥራ
✔ፍቅር [ከፍቅር የሆነ ትጋት]
✔ተስፋ [በተስፋ የሆነ ጽናት]
የሚጠበቁ ነገሮች ሲሆኑ ለእነዚህ ነገሮች መሠረቱ ግን ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ እምነታችን በክርስቶስ ነው ፍቅራችን በክርስቶስ ከክርስቶስ እንዲሁም ለክርስቶስ ነው ተስፋችንም እራሱ የተባረከው ተስፋችን ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
ሁሌም ቢሆን እንደ አማኝ አቋማችንን ስንመረምር፦ እምነቴ በውጭ ላሉት በማሳየው ምግባር እየተገለጠ ነው ወይ?
ትጋትን በሚፈጥር ፍቅር እየተመላለስኩ ነው ወይ?
የጌታዬን መምጣት በተስፋ እየተጠባበቅሁ በመጽናት ላይ ነኝ? ብለን መጠየቅ አለብን ማስተዋል ያለብን አማኝ ሁሌም ቢሆን የኢየሱስን መምጣት ተስፋ በማድረግ መታወቅ አለበት ምልልሱም ይሔን አቋሙን ሊያንፀባርቅ ይገባል።
✍ Henok Jesus's
/channel/gospelofthekingd0m
" በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፥ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ።"
(ትንቢተኢሳይያስ 27:6)
፦ 2015 ስር የምንሰድበት ደግሞም በፍሬአማነት የምንገለጥበት ዘመን ይሁንልን ፍሬአችንም ምድርን የሚሞላበት አብዝተን የምናፈራበት አመት ይሁንልን።እወዳቹሀለሁ!!
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holysiritflow
ልካችንን እንወቅ
=======================
ሀዋሪያት ላይ ይሰራ የነበረው መንፈስ በውስጣችን ነው!!!!!!!!
እንደ ሀዋሪያቱ እናስተናግደው በ church ፣ በግላችን፣ በህብረታችን ያን ጊዜ የሰራው ዛሬ አልደከመም ልካችን እስከ ሀዋሪያት እንደሆነ እንወቅ ያንን መልክ እና የወንጌል ጉልበት እስከምናይ እንታገል ግባችን እርሱ ነው ፣ አተኩረን ልንፈገውና ልንጠብቀው ይገባል። ልክህን/ልክሽን እወቅ/እወቂ!!!!
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
ሁሌም ክርስትና ማለት በተሰማራበት የትኛውም ቦታ ኢየሱስን የሚገልጥ እንጂ ኢየሱስን መግለጥ ለሆኑ የተወሰኑ ሰዎች የተሰጠ ስራ አይደለም አሁን ምን አይነት ቦታ ላይ ነው ያለኸው በትምህርት፣በስራ፣በንግድ በየትኛውም ቦታ ብትሆን ኢየሱስን መግለጥ ህይወታችን ስለሆነ ኢየሱስን ግለጥ/ጪ ምክንያቱም ክርስትና መብላት እና መጠጣት አይደለም ያለፈ ነገር አለው እርሱም ኢየሱስን መግለጥ ይባላል።
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow