holyspiritflow | Unsorted

Telegram-канал holyspiritflow - holyspirit flow

479

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ሃይልን ትቀበላላችሁ በኢየሩሳሌም በይሁዳ በሰማሪያም እስከ ምድር ዳር ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ ሐዋ 1:8

Subscribe to a channel

holyspirit flow

“መልካም በማድረግ የአላዋቂዎችን ከንቱ ንግግር ዝም እንድታሰኙ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።”

1ኛ ጴጥሮስ 2፥15 (አዲሱ መ.ት)

Читать полностью…

holyspirit flow

ወንጌል ወንጌል ወንጌል ወንጌል🔥 ወንጌል ወንጌል ወንጌል ወንጌል🔥 ወንጌል ወንጌል ወንጌል ወንጌል🔥 ወንጌል ወንጌል ወንጌል ወንጌል🔥 ወንጌል ወንጌል ወንጌል ወንጌል🔥 ወንጌል ወንጌል ወንጌል ወንጌል🔥 ወንጌል ወንጌል ወንጌል ወንጌል 🔥

Читать полностью…

holyspirit flow

“በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም።”
— ማቴዎስ 13፥58

Читать полностью…

holyspirit flow

"እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤ ልመናቸውንም አይንቅም።"

(መዝ 102፥17 አመት)

Читать полностью…

holyspirit flow

አይዞአችሁ አንድ ቀን ዛሬ ያስጨነቀንን እናልፈዋለን እሱ ብቻ አይደለም እንዴት እንዳለፈ እያሰብን እግዚአብሄርን እናመሰግናለን።💪

Читать полностью…

holyspirit flow

በጽኑ እጅ ከ400 ዓመት ቡሃላ ከፈርኦን ግዞት ያመለጠው ህዝበ #እስራኤል ትልቁ ችግራቸው #ነጻነታቸውን #celebrate አለማድረጋቸው ነው ሊወጡ ከማይችሉበት ለሞት ከሚኖሩበት ቦታ #እንዴት #መውጣት #እንደቻሉ እያሰቡ ደህንነታቸውን enjoy ከማድረግ ይልቅ በሌሎች ጥቃቅን ነገሮች #የሚያማርሩ ትልቁን እና ከሁሉ የሚበልጠውን ማስተዋል አልቻሉም።

“ከእነርሱ አንዳንዶቹ #እንዳጒረመረሙና በአጥፊው እንደ ጠፉ፣ አታጒረምርሙ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 10፥10 (አዲሱ መ.ት)
#Enjoy #with #your #salivation

Читать полностью…

holyspirit flow

"ሰበር ዜና❗
▰▰▰▰▰
አንድ ሽማግሌ በባቡር ተሳፍሮ እየሄደ ብድግ ብሎ ተነሳና ወደ ተሳፋሪዎች ዘወር ብሎ፦ "ሁላችሁም ስሙ! ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል፤ ንስሐም ግቡ" ብሎ ሲሠብክ አንዲት ተሳፋሪ የነበረች ሴት ብድግ ብላ ተነሳችና "አፍህን ዝጋ፤ አንተ ምንም የምታውቀው ነገር የለም። የአንተ ኢየሱስ እንዲያውም ከነጭራሹ የለም!" አለችው።

ሽማግሌውም በንግግሯ ተደናግጦ መቀመጫዉ ላይ ቁጭ አለ። ነገር ግን እንደገና ተነስቶ ኢየሱስ እንደሚመጣ እንዲናገር፤እንዲሰብክ እግዚአብሔር ልቡን አነሳሳዉ።

እሱም የእግዚአብሔር ድምፅ እንደሠማ ታዘዘና እንደገና ተነስቶ "#ኢየሱስ
በቅርቡ ይመጣል። ሁላችሁም ንስሐ ግቡ፤ በልባችሁም እርሱን ተቀበሉ፤ ከዘላለም ሞትም ትድናላችሁ! ..." እያለ መስበኩን ቀጠለ።

ከዚያ ሴትዮዋ እንደገና ተነስታ ከፍ ባለ ድምፅ "ዝም በል! አንተ የማትረባ" ብላ በጥፊ ደጋግማ ስትመታው፤ ከአጠገቧ ተቀምጦ የነበረው ወንድ ልጇ
"ተይ እንጂ እማዬ! ይህ ሰው እኮ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ ነው!" አላት።

ከዚያም ሴትዮዋ በግንባሯ ወለሉ ላይ ተደፍታ መጮህና ማልቀስ ጀመረች።
ሽማግሌውም ሴትዮዋን "ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ ትጮኺያለሽ?"ሲላት
"ልጄ መናገርም ሆነ መስማት የማይችል (ዲዳ) ነበር። ~አሁን ግን መናገር ቻለ።" አለችው!

ቃሉ ኃይል አለው! ቃሉን በድፍረት ስትናገር ተአምራት በአንተ ላይ መከናወን ይጀምራሉ! እርግጥም #ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል!

"ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።" ማቴዎስ - 10፥32-33

አንተም ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል በልና ለሌሎች share አድርግ!

Читать полностью…

holyspirit flow

ቁልፉን ትቶ ዳቦውን?!
_____
ከታች በምስሉ የምንመለከተው ሰው በታሰረበት ክፍል ሆኖ በፊቱ ሁለት አማራጮች ቀርበውለታል፤ አንድ ዳቦና የእስር ቤቱ በር መክፈቻ ቁልፍ። ሆኖም የእርሱ ምርጫ ለዘላቂው ከእስር ቤቱ የሚያወጣውን የበሩን ቁልፍ ሳይሆን ወቅታዊ ረሃቡን የሚያስታግስበትን ቁራሽ ዳቦ ማግኘት ሆኗል። ግን ለምን?

የብዙዎቻችንስ የምርጫ ዝንፈት ይሄው አይደለምን?! ለወቃታዊ ችግሮቻችን ፈጣን ማስታገሻ የሚሰጥ የሚመስለንን ቁራሽ "ዳቦ" ፍለጋ እንውተረተራለን እንጂ ዘላቂ መፍትሄ የሚቸረውን ቁልፍ (የእውቀት መክፈቻ) ለማግኘት እምብዛም እኮ አንተጋም። ከግብፅ የዘመናት እስራት ነፃ የወጡትን የእስራኤልን ልጆች ልብ ይሏል... ከምድረ በዳ ነፃነታቸው ይልቅ የግብፅ ሽንኩርት(የእስር ቤቱ ጥጋብ) ሲናፍቃቸው... ዘይገርም አሉ! ... ግን ለምን?

"ነፃነት" የሕይወት ወሳኝ እቅምና ውበት መሆኑን አለማወቅ አይመስላችሁም?

ስለዚህ ከውስጣዊና ውጫዊ እስራት ለዘላቂው ነፃ ከማያወጣ "የቁራሽ ዳቦ" ማስታገሻ ፍለጋ ፥ ነፍሳችንን አስገዝተንም ቢሆን እስከ ወዲያኛው አርነት ወደሚሰጠን የእውነት እውቀት "ቁልፍ" ፍለጋ ነፍሳችንን እናተጋ ዘንድ ይሁንል

Paster abyy emishaw✍

Читать полностью…

holyspirit flow

መሪዎቻችኝ እባካችሁ በጸሎት የሚመጣውን አንድነት በሻይ ቡና አታመጡትምና አትሰቃዩ 🤷‍♂

Читать полностью…

holyspirit flow

እግዚአብሄር ሁሌም የሚደሰተው ወንጌልን በሚሰሩ ሰዎች ነው። ምክንያቱም የእርሱ መሻት ሁሌም ኢየሱስ የሚታይባቸው እንድንሆንለት ነው። የዚህ አለም ኑሮ አያረካም ሆዳችን ሁሌ ምግብን ይፈልጋል፣ ሰውነታችን እንቅልፍን ይፈልጋል ፣ አይምሮአችን እውቀትን ይፈልጋል ነገ እንደሚሞት እያወቅን እንደማይሞት ሰውነት ሁሌ የሚፈልገውን እንሰጠዋለን ስለዚህ ዘወትር ስጋችን #የሚለንን ብቻ የምናደርግ ከሆነ ምኑን #መንፈሳዊ ሆንን?? መንፈሳዊ ሰው ሁሌም ከሚበላው ከሚጠጣው ነገር የተሻለ ከሰማይ የሚመጣ #መንግስትን ይዞ የሚመጣ አንድ ጌታ እንዳለ ማሰብ ተገቢ ነው ምክንያቱም በመካከላችን የክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ስላሉ በጥንቃቄ መኖር አለብን!!!
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

ኢየሱስ ክርስቶስ ለአለም ቤዛ ( redemption ) ምክንያት የሆነው አባቱ #የሁላችንን #ጽድቅ ሲመለከት ከንቱ እና ከእርሱ ጽድቅ ጋር ስለ ማይገናኝ ነበረ ስለዚህም የእራሱን ጽድቅ በሰዎች ውስጥ እንዲያይ እራሱ እግዚአብሄር #ሰው #መሆን ነበረበት።
“እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአት የሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው።”
— 2ኛ ቆሮንቶስ 5፥21 (አዲሱ መ.ት)
➡ አሁን ጽድቃችን በእግዚአብሄር ጽድቅ ተተክቷል ይህም በክርስቶስ የእንጨት ላይ ሞት #ተፈጽሟል። ሀጢያታችንን ለማስተሰረይ የሀጢያት መስዋዕት ለሰው ልጆች ያስፈልግ ነበር ለዚህ ነው ክርስቶስ በእለተ አርብ ከዛሬ 2015 ዓመት በፊት በመስቀል ላይ የሞተው።
➡ በመስቀል ላይ ተጠማው ሲል ዝም ብሎ ሰው ሲደክመው የሚጠማውን አይነት አልነበረም። #ደሙ በየመንገዱ የፈሰሰ በመስቀል መሸከም እንዲሁም በመገረፍ #ቁስሉ የሰረጎደ አይነት ሰው የጥማት ጩኸት ነበር።
➡ በመስቀል ጎኑን ሲወጋ የፈሰሰው ደም ብቻ ሳይሆን ውሀ የቀላቀለ ነበር ይሆ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሁላችንን #እያማጠ የነበረበት ሰዓት ይመስለኛል ምክንያቱም ደም እና ውሀ የቀላቀለ ነገር የሚፈሰው ልጅ በሆዱአ ያዘለች እናት በምጧ ሰዓት የሚፈሳት እንሽርት ውሀ የሚባል ስለሆነ።
➡ ወዳጆቼ ኢየሱስ የሁላችንን በደል የተሸከመው ሁላችን የተቅበዘበዝን ከመንገድ የወጣን ስለነበርን ወደ እረኛችን ለመድረስ የሚከፈለውን ዋጋ ክርስቶስ ከፍሎልን በሰላም ወደ ነፍሳችን እረኛና ጠባቂ ተመልሰናል።
1ኛ ጴጥሮስ 2 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በእንጨት መስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል።
²⁵ ቀድሞ እንደ ጠፉ በጎች #ትቅበዘበዙ ነበር፤ #አሁን #ግን #ወደ #ነፍሳችሁ #እረኛና #ጠባቂ ተመልሳችኋል።
👉 ይህንን የምታነቡ ወዳጆቼ በክርስቶስ ኢየሱስ ማመን ማለት የእግዚአብሄርን ጽድቅ መቀበል ፣ የዘላለምን እረፍት ማግኘት ደግሞም 🪱 ትሉ በማይሞትበት ፣ 🔥 እሳቱም በማይጠፋበት የዘላለም ስቃይ ካለበት 🤢 ማምለጥ ነው ይሄ የምነግራችሁ የፍቅር መልዕክት ነው💌። ደካማነታችሁን እመኑ! ፣ ስረችሁ ሁሉ በእግዚአብሄር ፊት ከንቱ እንደሆኑ እመኑ! ፣ የሀጢያት ሸክም እንዳለባችሁ እመኑ!
ነገር ግን አንድ የምስራች ድምጽ ደግሞ አለ 🔊🔊 የጠፋነውን የተቅበዘበዝነውን ክርስቶስ ኢየሱስ ሸክማችንን ተሸክሟል።
ኢሳይያስ 53 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ እያንዳንዳችንም በየመንገዳችን ነጐድን፤ እግዚአብሔርም፣ የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ ጫነው።
⁷ ተጨነቀ፤ ተሠቃየም፤ ነገር ግን አፉን አልከፈተም፤ እንደ ጠቦትም ለዕርድ ተነዳ፤ በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፉን አልከፈተም።
👉 ይሄንን መልዕክት ላላመኑ ጓደኞቻችሁ ዘመዶቻችሁ share share አድርጉ ወንጌልን ስሩ ተባረኩ ✋።

@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

#ሕግ የምትሰርቅበትን እጅ ይቆርጥብሃል እንጂ የምትሰርቅበትን ልብ አያጸዳልህም!! #ጸጋ ግን ልብህን ያነጻልሃል ቅድስናን ያለማምድሃል።

Читать полностью…

holyspirit flow

ኢየሱስ በመስቀል "የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው " ያለው ሰው ሳያውቅ ብዙ ክፉ የሆነን ነገር ይሰራል የሚሰራውን አውቆ አይሰራም!! ባለማወቅ የምናበላሸው ብዙ ነገር አለ ስለዚህ የሚስተካከለው በማወቅ ብቻ ነው። በማወቃችን የምናስተካክለው ብዙ ነገር ስላለ በዙሪያችን ስላሉ #እየጎዳናቸው ስላሉ ነገር ግን ባለመረዳታችን ምክንያት የመጣባቸውን ለማወቅ መጣጣር አለብን።
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

በዚህ የዘመን መጨረሻ ኢየሱስን መስበክ እድል ነው ወንጌልን ስበኩ!!!

Читать полностью…

holyspirit flow

I want to challenge you to compare your screen time with your prayer time and the time you Meditate the word of God
In what your time is wasted!???

@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

“እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ #የሚረዳንን #ጸጋ #እንድናገኝ #ወደ #ጸጋው #ዙፋን #በእምነት #እንቅረብ።”
— ዕብራውያን 4፥16

Читать полностью…

holyspirit flow

"እናንተም ትጠሩኛላችሁ፤ ቀርባችሁ ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፤ እኔም እሰማችኋለሁ።"

(ኤር 29፥12 አ.መ.ት)

Читать полностью…

holyspirit flow

በታሪክ ውስጥ ፈር ቀዳጅ የሆኑ ክርስቲያን ሚስዮናውያን ነበሩ። እነዚህ ያለምንም ጥርጥር በክርስቶስ መንግስት ትልቅ ብድራት የሚጠብቃቸው ፤ ሁለንተናቸውን ለክርስቶስ ወንጌል የሰጡ ቅዱሳን ሰዎች ነበሩ። ብዙ ሚስዮናውያን በአለም ዙሪያ ታሪክ ያልተጻፈላቸው እንዳሉ እናውቃለን። በዘመናችንም አስደናቂውን የእግዚአብሔርን ምህረት ሰው በማይመርጠው ስፍራ የሚያገለግሉ ሚስዮናውያን አሉ።

Читать полностью…

holyspirit flow

…ከእነዚያም በኋላ እግዚአብሔርን ለእስራኤልም ያደረገውን ሥራ ያላወቀ ሌላ ትውልድ ተነሣ።

መጽሐፈ መሣፍንት 2:10

Читать полностью…

holyspirit flow

“አንበሶች ሊያጡ፣ ሊራቡም ይችላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጐድልባቸውም።”
— መዝሙር 34፥10 (አዲሱ መ.ት)

Читать полностью…

holyspirit flow

አለማንበብ አይቻልም ‼ ጥያቄ አለኝ 👇👇
በዚህ በተሰጠን አዲስ አመት ፣ ወራት ፣ ሳምንታት ፣ ቀናት ፣ ሰዓታት እንዲሁም ደቂቃዎች ምን ለመስራት አሰብክ/ሽ? 🤔
አሁን አምና በዚህ ጊዜ 2015 ስትቀበል/ይ በምን አይነት መንገድ ነበር? ምን ምን ጸሎቶች ነበሩን? በአመቱ ላይ እንድንሆነው የፈለግነው በርግጥ ተፈጽሞአል? ተዉት እሱን..... በዚህ አመት ከ2015 በተለየ መልኩ ምን አስበሃል/ሻል? አንዳንዶቻችን በዚህ አመት የመንጸልየው እና ማድረግ የምንፈልገው በ 2015 መጀመሪያ የጸለይነው ያንኑ እንደሆነ መገለጥ አያስፈልገውም እርግጠኛ ነኝ ነገር ግን ዘንድሮ እንዲህ አስቡ እስቲ 👇👇
👉 በchurch ሁሌ በፕሮግራም busy ፣ በህንጻ በተለያዩ ጉዳዩች የሆይ ሆይታ ሳይሆን የምንከተለውን ፣ የምናገለግለውን የምናጋፋውን ጌታን አውቀን በመነካካት ሀይል የምናስወጣ የእምነትን ኑሮ የሚለማመዱ ያድርገን።
2015 በፕሮግራሞች ፣ በስነስርአቶች በተለያዩ ነገሮች ስንጋፋ ለጌታ እንደ Guard ጠበቃ ሆነን የኖርን ፣ ለውጥ ማምጣት ያልቻልን ሆነን ነገር ግን የለውጥ ሰዎች እየመሰልን / እያስመሰልን / ኖረናል ዘንድሮ ግን የምናጋፋ ሳይሆን የምንከተለውን ጌታ #experience የምናደርገው አመት ለውጥን የምንለማመድ ያድርገን መልካም አዲስ አመት 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

/channel/holyspiritflow /channel/holyspiritflow /channel/holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

ፓስተሩ ፀጉሩን ሊስተካከል ገና ከመግባቱ....❓❌❓❌❓

ፀጉር አስተካካዩ ወንበሩ ላይ አስቀምጦ ሽርጡን እያስተካከለ በጥያቄ ያጣድፈው ጀመር....???

አስተካካዩ:- ፓስተር ነህ መሰለኝ?

ፓስተሩ:- እ....አዎ!

አስተካካዩ:- አይ እንደው እግዚአብሔር የሚባል ቢኖር ኖሮ ለምንድን ነው ይሔ ሁሉ ክፋት አለማችን ላይ የበዛው? እላለሁ ሁልጊዜ

እና ደግሞ.....ምናምን ምናምን እያለ ብዙም ለፓስተሩ የምላሽ ጊዜ እንኳን ሳይሰጠው ንግግሩን ቀጠለ

ፓስተሩ .....ምንም ሳይመልስለት ተቆርጦ ሲጨርስ ሒሳቡን ከፍሎ አመስግኖ ወጣ::

ከፀጉር ቤቱ አለፍ ብሎ ወደ ተቀመጠ ጎዳና ተዳዳሪ ፓስተሩ ጠጋ አለና "ወንድሜ ይሔንን ረጅም ፀጉርህን መስተካከል ትፈልጋለህ"? አለው::

ሰውዬውም ፈቃደኛ መሆኑን በደስታ ገለፀለት...

ወደ ፀጉር ቤቱ ይዞት እንደገባ ፓስተሩ ወደ አስተካካዩ እየተመለከተ "ፀጉር አስተካካይ የሚባል ቢኖር ኖሮ የዚህ ሰውዬ ፀጉር እንዲህ ባላደገ ነበር" አለው🧐

አስተካካዩም:- ፀጉር ቆራጭ እማ አለ ብዙዎች ወደ እኔ አልመጡም እንጂ…..

❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌

አዎ እግዚአብሔር ስለሌለ ሳይሆን ወደ እርሱ ለመፍትሔ የሚቀርብ ጠፍቶ ነው🥲

የለም አትበለኝ አንተ እሱ ጋር ሳትኖር😔

“ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥ ፊታችሁም አያፍርም" መዝ 34:5

Читать полностью…

holyspirit flow

አንብብ‼️👇👇

✳️ በምድር ላይ ማንም ሊያድነን ሊታደገን የሚችል እንደሌለ ስላወቀ አንድ መንገድ ብቻ እግዚአብሄር አዘጋጅቷል። ይህም በልጁ #ኢየሱስ #ብቻ❕❕ የሆነ የደህንነት መንገድ ነው።" #ከእኔ #በቀር " ካለ ከሱ በቀር ማንም የለም!!!!!
👉 ኢየሱስ እውነት ከሆነ ሌላው ውሸት ነው
👉 ኢየሱስ መንገድ ከሆነ ሌላው ገደል ነው!
👉 ኢየሱስ ህይወት ከሆነ ሌላው ውሸት ነው
አለቀ!!!!!

Читать полностью…

holyspirit flow

#የአንተን_ኢየሱስ_አልፈልገውም።
👉👉ከብዙ ጊዜያት በፊት በአሜሪካን ሀገር በጊዜው ታዋቂ በነበረችው ተዋናይት (Actress) ማርሊን ሞንሮይ የሚዘጋጅ ሾው ነበር። እናም በዚህ ሾው ላይ የፊልም ተዋንያን፣ የንግድ ዓለም ቁንጮ ሰዎች፣ የተማሩ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ የፖለቲካ አቀንቃኞችና የሀይማኖት አባቶች ብቻ ምን አለፋችሁ ተሰሚና ትልቅ የተባለ ሰው ሁሉ ይጋበዝና የሕይወት፣ የስራ እና የስኬት ልምዱን ያካፍልበት የነበረ ተወዳጅ ሾው ነበር። አንድ ቀን በአሜሪካን ሀገር ውስጥ ተሰሚነትን ያገኘውን የወንጌል ሰባኪ #ቢሊ_ግርሀምን ጋበዘችውና ብዙ የተለያዩ ጉዳዮችን ከጠየቀችው እርሱም ከመለሰላት በኋላ ወደ ፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ የፈለገውን መልዕክት ማስተላለፍ እንደሚችል ስትገልጽለት #ቢሊ _ግርሀምም ጊዜውን ሳያባክን በቀጥታ እንደዚህ አላት። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉ዛሬ #መንፈስ_ቅዱስ ለአንቺ ወንጌልን እንድሰብክ ልኮኛል በማለት የወንጌልን ቃል በሚገባ ይሰብክና ከጨረሰ በኋላ የደህንነት ጥሪ ሲያደርግላት በፕሮግራሟ ላይ ተገኝቶ ስለሰጣት ቃለ ምልልስ አመስግናው ነገር ግን ስላቀረበላት የደህንነት ጥሪ #የአንተን_ኢየሱስ_አልፈልገውም
( I don't need your Jesus) በማለት መለሰችለት። ከአንድ ሳምንት በኋላ ግን በራሷ የመኖሪያ አፓርትመንት ውስጥ ሞታ ተገኘች። የአንተን ኢየሱስን ያለችውን የራሷ ማድረግ ስትችል ማለትም ኢየሱስንም የራሷ እሷም የኢየሱስ ሳትሆን ከዚህ ዓለም በሞት ተሸኘች። አሁንም ምን አልባት ይህን ጽሁፍ የምታነብ ወንድሜ/ እህቴ ጌታ ኢየሱስን የግልህ አዳኝ አድርገህ/ አድርገሽ ካልተቀበልክ/ሽ ጊዜው አይርፈድብህ/ሽ ነገ ወይም ይህን ጽሁፍ አንብበህ ስትጨርስ/ሺ ምን እንድትሆን አታውቅምና አሁኑኑ ወስን መጽሐፍ ቅዱስ የመዳን ቀን አሁን ነው ይላልና። እኛም ቅዱሳን አማኞች ጊዜው ለወንጌል አመቺ ነው በያለንበት ወንጌልን መስራታችንን መቀጠል አለብን። ዕድሉ ተገኝቶ ከሆነ በየሚዲያው ካልሆነም በግል ብቻ በእያንዳንዱ አቅጣጫ የጸጋውን ወንጌል መስበክ ይጠበቅብናል። በነ እንትና ጉዳይ ከምንያዝ በእነ እንትና ሾው ላይም ስንቀርብ #ወንጌሉን_እርሱም_ኢየሱስን_አድምቀን_ብንወርድ መልካም ነው እላለው። የተስማማ ካለ #ወንጌሉን_እርሱም_ኢየሱስን_እሰብካለው_ይበል።

Читать полностью…

holyspirit flow

ሁሉም ሰው መስማት ያለበት መዝሙር 🎹🎹🎹🎸🎤🎧

ጻድቅ ጠፍቶ አንድስ እንኳ በህጉ ፊት ሲመዘን በህጉ ፊት ሲመዘን
እንኳንስ በደላችን ጽድቃችን መርገም ሲሆን.......👐👐👐👐👐👐👐

@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

🛑#ኬንያዊው "#እየሱስ_ክርስቶስ" #ችግር ላይ ወድቋል!!😂😂👇👇

"ከ2000 አመታት በፊት የነበርኩት ትክክለኛው እየሱስ እኔ ነኝ" የሚለው ኬንያዊው ፓስተር ሙአሊሙ የሱ ታንጎሌ በኬንያ በርካታ ተከታዮችን አፍርቷል።

ሚስት እና 8 ልጆች ያሉት ሙአሊም ተአምራቶችን ሲፈፅም አይተናል በሚሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ታጅቦ ስርአተ አምልኮ ያስፈፅማል።

12 ደቀመዝሙሮችን ሳይቀር የሰየመውና አለምን ለማዳን ከእግዚብሔር የተላኩኝ መሲህ ነኝ የሚለው ሙአሊም በሽተኞችን ከመፈወስ አንስቶ በሠርግ ላይ ውሃን ወደ ሻይ ሲቀይር አይተናል የሚሉ ተከታዮቹን ማፍራት ችሏል።

ተከታዮቹ የቡግማን ሰዎች ታዲያ መጪው ፋሲካ ከመድረሱ በፊት ትክክለኛው መሲህ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ የፈለጉ ይመስላል።

ይህንን መሲህ ነኝ ባይ ፓስተር እንሰቅለው እና በ3ኛ ቀን ከሞት ይነሳ እንደሆነ እናረጋግጥ በማለት ውሣኔ ላይ ደርሰው ዝግጅታቸውን ጀምረዋል።

አሟሟቱ መስቀል ላይ በሚስማር ተቸንክሮ እንዲሆን እና ስርዓተ ቀብሩ ከተፈፀመ በኋላ ቀጣዩን 3 ቀናት ከሞት ይነሳ እንደው በጉጉት ለመጠበቅ ውሣኔ ላይ ደርሰዋል።

ይህንን የተረዳውና ሃሳባቸው ምንም ያልጣመው ሙአሊም ወደ ኬንያ ፖሊስ በመደወል ከስቅላት አንዲያስጥሉት ተማፅኗል።

ተከታዮቹ ግን በውሳኔያቸው ፀንተዋል፦

"ፖሊስ በእምነታችን ጣልቃ እንዲገባ አንፈቅድም። ይህ በእኛ እና በአዳኝ እና መሲሃችን መካከል የሚያልቅ ጉዳይ ነው።" ብለዋል!!

Читать полностью…

holyspirit flow

When a baby is born he cries ; when a sinner is born again he #prays.

Читать полностью…

holyspirit flow

እግዚአብሄር የሚፈልገው የሚደግፈውን ሳይሆን የሚደገፈውን ሰው ይፈልጋል።

Читать полностью…

holyspirit flow

አንተ ትውልድ ጠይቅ!!
👉ዛሬ የሚከበረው የጥምቀት በአል ላይ ማነው የሚከብረው?
👉 ስለ ማን ነው በጥምቀት የሚዘመረው ማነው ጎልቶ የሚታየው?
👉የዚህን ስርአት ትምህርት ከየትኛው ሀዋሪያት ስርአት አገኘነው?
👉 ከጥምቀት ጋር ተያይዘው የመጡት ድርጊቶች እግዚአብሄር ይከብርባየዋል??
ጠይቅ አንተ ትውልድ የትኛውንም ነገር ስለ ተሰጠህ አትቀበል ፣ ከመጽሀፍ ቅዱስ ጋር እየተላተመ የሚደረግን ስርአት አትቀበል።
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow
@Holyspiritflow

Читать полностью…

holyspirit flow

ሰው በመሆኑ ራሱ ተዋርዷል!!
-------------------------------------------------------
ፊልጵስዩስ 2 (አዲሱ መ.ት)
⁶ እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን ሊለቀው እንደማይገባ አድርጎ አልቈጠረውም፤
⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ፣ በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ ራሱን ባዶ አደረገ፤
⁸ ሰው ሆኖ ተገልጦም፣ ራሱን ዝቅ አደረገ፤ እስከ ሞት፣ ያውም በመስቀል ላይ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።
👉 በጣም ብዙ ሰው አምላክነቱን ትቶ እንደመጣ ይናገራሉ ነገር ግን ክርስቶስ የተወው አምላክነቱን ሳይሆን የአምላክነት ክብሩን ነው ለዚህ ነው አምላክ በመሆኑ የነበረው ክብር ሰው ሲሆን ግን ያንን ክብር አጥቷል ምክንያቱም ሰው መሆን በራሱ መገደብ ፣ ራስን ባዶ ማድረግ ነው።
👉 ህጻኑ አለማት ሁሉ የእርሱ ሆነው ስፍራ እንደሌለው በበረት ተወለደ ጠፍጥፎ የሰራት ብርሀን ሰባ ሰገሎችን ''ኑ የብርሃኔን ምንጭ ላሳያችሁ'' ብላ እየተንቀሳቀሰች መራቻቸው ዝም ማለት አልቻለችም ሰማይ የነበረ አምልኮ ለህጻኑ ምድር ላይ በግርግም ተደርጉአል መላዕክቶች የምስራቹን ይዘው ቤተመንግስት ሳይሆን ወደ እረኞች ይዘው ሄዱ እረኞቹም ይህን የሰማይ አምልኮ ተመልካቾች ሆኑ። እናም አምላክ በመስቀል የተሰቀለበት ፣ የሞተበት እናም የተዋረደበት በጣም የሚያስገርም ሆኖ ሳለ ነገር ግን በመጀመሪያ የሚገርመው እንዲሁም ፍጥረት የተገረመበት እውነት አምላክ ገና ሰው ሲሆን ነው።
👉 እና አምላክ ሰው የሆነበትን እውነት እያዪ ኮኮቦች እንዲሁም ፍጥረታት ዝም ማለት ካልቻሉ እኛ እንዴት ዝም እንላለን??
ወንጌል የፍቅር መልዕክት ነው!!!!!!!!!
✍ @solascripturia

Читать полностью…
Subscribe to a channel