ibnyahya777 | Unsorted

Telegram-канал ibnyahya777 - Ibn Yahya Ahmed

2272

የተለያዩ ዲናዊ ፅሑፎችን ብቻ የማስተላልፍበት ቻናሌ ነው።

Subscribe to a channel

Ibn Yahya Ahmed

▪️ዘካተል ፊጥር.Pdf

🔻ከሸይኽ ኢብኑዑሰይሚን "መጃሊሱ ሸህሪ ረመዷን" ኪታብ እና ከሸይኽ ኢልያስ አሕመድ "ዘካተልፊጥር" ከሚለው ሙሐደራ የተወሰደ.
✍Ibn Yahya Ahmed (ረመዷን 27/1441ሂ.)
___
/channel/ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

"إذا رزق الزوج زوجة صالحة فليفرح بها وليعض عليها بالنواجذ"

#الشيخ رسلان حفظه الله🍂

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️ተጠንቀቅ/ቂ

🔻ረሱል - ሰለሏሁዓለይሂወሰለም - እንዲህ ይላሉ ፦ [ አንድ ወንድ የሌላውን ወንድ ሀፍረተ-ገላ አይመልከት ፤ ሴትም የሌላዋን ሴት ሀፍረተ-ገላ አትመልከት። ] (ሙስሊም ዘግቦታል)

t.me/ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

#ኡድሒያን_የሚመለከቱ_ነጥቦች

♦️ኡድሒያ ማለት በዒድ ሰበብ የዒደል-አድሓ ቀናት ላይ ወደአላህን ለመቃረብ ሲባል ከታወቁ እንስሳዎች የሚከናወን የእርድ ስነ-ሥርአት ነው። ይህም በቁርአን ፣ በሐዲስ እና በሙሥሊሞች ስምምነት የፀደቀ ጉዳይ ነው። ኡድሒያን ማረድ አቅሙ ላለው ሰው ምንም እንኳን ከፊል ዑለማዎች ግዴታ ነው ቢሉም የተሻለው አቋም በጣም የጠነከረ ሱና ነው የሚለው ነው። (መጅሙዓል ፈታዋ ሊብኑ ባዝ ፥ 18/36. ይመልከቱ).

♦️ኡድሒያ ላይ የሚታረዱ እንስሳዎች 3 አይነት ናቸው። እነርሱም ፦
◼️1.ግመል
◼️2.ከብት
◼️3.በግ እና ፍየል ናቸው።
ኡድሒያ የሚታረዱ እንስሳዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች አሉ። እነርሱም ፦
°
1️⃣.በሸሪዓው የተቀመጠላቸውን የእድሜ ገደብ መድረስ አለባቸው። እሱም ለግመል 5አመት ለከብት ሀለት አመት ለፍየል አንድ አመት እና ለበግ 6ወር ናቸው።
ረሱል - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ ሙሲናህን እንጂ አትረዱ. በናንተ ላይ ከተቸገራችሁ በስተቀር ፤ በዚህን ጊዜ ከበግ ጀዝዓን ማረድ ትችላላሁ። ] (ሙስሊም ዘግቦታል)
ሙሲናህ ማለት በሸሪዓው የተጠቀሰላቸውን እድሜ የደረሱ እንስሳዎች ማለት ነው። ጀዝዓ ማለት ደግሞ ከበግ 6ወር የሞላው ማለት ነው።
°
2️⃣.ከጉድለት የፀዱ መሆን አለባቸው። ረሱል - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ ከኡድሒያ አያብቃቃም ፡ የአንድ አይኗ መጥፋት ግልፅ የወጣ የሆነች አንድ አይናማ , አንካሳነቷ ግልፅ የወጣ የሆነች አንካሳ , ህመምነቷ ግልፅ የወጣ የሆነች ህመምተኛ , (አጥንት ውስጥ የሚገኝ) መቅኔ የሌላት ከሲታ የሆነች። ]. (ነሳኢይ ዘግቦታል / አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል)
°
♦️አንድ እንስሳ ለባለቤቱ እና ለቤተሰቦቹ ያብቃቀዋል። ከአቢአዩብ አልአንሷሪ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው ፦ [ አንድ ሰው በነብዩ - ﷺ - ዘመን ለራሱ እና ለቤተሰቡ በአንዲት ፍየል ወይም በግ ኡድሒያ ያደርግ ነበር ፤  ራሳቸውም በልተው ሰዎችንም ይመግቡ ነበር። ] ( ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል / አልባኒም ሶሒሕ ብለውታል). ግመል ወይም ከብት ከሆነ ደግሞ ለ7ሰው ተጋርቶ ማረድ ይቻላል። ጃቢር - ረዲየሏሁ ዐንሁ - እንዲህ ይላል ፦ [ የሑደይብያ ዓመት ላይ ከረሱል - ﷺ - ጋር አንድ ግመልን ለሰባት (ሰዎች) ፣ አንድ በሬን ለሰባት (ሰዎች) አረደን። ] (ሙስሊም ዘግቦታል)
°
♦️በሚታረድም ሰአት ደም መፍሰስ እና የአላህ ስም መወሳት ይኖርበታል። ረሱል - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ ደም ያፈሰሰ እና የአላህ ሥም የተወሳበት ከሆነ ብላ ። ] (ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል). ባለቤቱ ራሱ ቢያርድም ተመራጭ ነው። ካልቻለ በሚታረድ ሰአት መገኘት ይኖርበታል። በሚያርድም ሰአት "ቢስሚሏህ አሏሁ አክበር አሏሁመ ሀዛ ሚንከ ወለከ አሏሁመ ሀዛ ዓኒ ወዓን አህሊ በይቲ". ይላል። ( መጅሙዓል ፈታዋ ሊብኒ ዑሰይሚን ፥ 25/55.ይመልከቱ). እርዱን ማሳመር ይኖርበታል። ቢላዋውን ፊትለፊቷ መሳል የበለትም እንደዚሁ ሌሎች እንስሳዎችን እያሳዩ ማረድም የለበትም።
°
♦️መታረድም ያለበት ከዒድ ሶላት በኋላ ነው። ረሱል - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ ከሶላት በፊት ያረደ ሰው ለራሱ እንዳረደ ነው (የሚቆጠረው) ፤ ከሶላት በኋላ ያረደ ሰው እርዱ ሙሉ ሆኗል የሙስሊሞችንም ሱንና አግኝቷል። ] ( ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል). ከዒድ በኋላ እስከ ሶስቱ የተሽሪቅ ቀናቶች ድረስ ማረድ ይቻላል።(መጅሙዓል ፈታዋ ሊብኒ ዑሰይሚን ፥ 25/167.ይመልከቱ).
°
♦️ከታረደ በኋላ ስጋውን ለሚስኪኖች መስጠትም ተገቢ ነው። ለሚስኪኖች የሚሰጠውም ከበሰለው ስጋ ሳይሆን ከጥሬ ስጋ መሆን አለበት።(መጅሙዓል ፈታዋ ሊብኑ ዑሰይሚን ፥ 25/132. ይመልከቱ). ለገፋፊው የሰራበትንም ዋጋ ከኡድሒያው መስጠቱ አይበቃም ፤ በስጦታ መልክ መስጠት ግን ይቻላል። (መጅሙዓል ፈታዋ ሊብኒ ዑሰይሚን ፥ 25/110. ይመልከቱ). የኡድሒያ ቆዳ መሸጥም እንደሚከለከል የሚያመላክት (ሶሒሑል ጃሚዕ ፥ 61118) ላይ የተዘገበ ሐዲስ አለ። አላህ ኡድሒያችንን ይቀበለን።
__________
✍አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ  @Ibn yahya ahmed
📆ዙልሒጃህ 9/1439ሂ. # ነሐሴ 14/2010.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦/channel/ibnyahya7

✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

📋የዐረፋ ቀንን መፆም
°
🔻ከአቢቀታዳ ተይዞ እንደተወራው ነብዩ - ﷺ - ስለ ዐረፋ ቀን ፆም ተጠየቁ እና እንዲህ አሉ ፦ [ ያለፈውን እና የወደፊቱን አመት ወንጀል ያብሳል ] (ሙስሊም ዘግቦታል)
~~~
@Ibnyahya777
በዘንድሮ ፡ ማክሰኞ ሰኔ 20/2015 ማለት ነው

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

#አስሩ_የዙልሒጃህ_ቀናትን_በተመለከተ 👇👇

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

‏قال الإمام ابن باز رحمه الله :

لا يترك متابعة المؤذن إلا محروم
، ولمتابعة المؤذن أربع فضائل كبيرة :

١- مغفرة الذنوب .
٢- دخول الجنة .
٣- الفوز بشفاعته صلى الله عليه وسلم .
٤- إستجابة الدعاء بعده .

قال ابن جريج :

السلف كانوا ينصتون للمؤذن إنصاتهم القرآن .

[فتح الباري(2\92)]| .

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

«ግርግር ለሌባ ያመቻል!» እንዲሉ፤ ሰሞኑን አንድ ቪድዮ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር እያዬሁ ነበር፤ ብዙዎችም በውስጥ እየላኩልኝ ሲጠይቁኝ ነበር።

አውቃለሁ እየተፈጸመብን ያለው ግፍ ስሜታዊ ያደርጋል። ነገር ግን መፍትሄው ሸሪዓውን ያማከለና የሰከነ አካሄድ እንጂ ስሌት የሌለው የስሜት ጉዞ መሆን የለበትም።

ዳዒሾች (አይኤስ አይኤስ) የሚባሉት ቡድኖች ከሙስሊም ጠላቶች በላይ የጎዱት ሙስሉሙን ማኅበረሰብ ነው።
ገና ለገና «ጂ'ሃድ» ስላሉ ብቻ በቁጭት ተነሳስተን መንገዳቸውን መከተል የለብንም።

እነርሱ በመደበኛው ሁኔታ ተከታይ ስለማያገኙ እንደዚህ አይነት የቁጭት አጋጣሚዎችን ተጠቅመው እየሰበኩ ነውና እንዳትሸወዱ።

ነፍስያችንን ከመታገል ጀምሮ፣ ከወንጀል ከመራቅ ጀምሮ ገና ያልጀመርናቸው የነፍስያ ጂሃድ ጉዞዎች አሉና ቅደም ተከተሉን ጠብቀን ሸሪዓውን ባማከለ መልኩ እንጓዝ።
መንግስት እንኳን ይህን አይነት ሰበብ አግኝቶ፤ እንዲሁም የዶክመንተሪ ግብዓት ለማግኘት የሐሰት ዶክመንተሪ ሲሠራ በቀደምት ጊዚያት እናውቀዋለንና ለጠላቶቻችንም በር አንክፈት። መቼም ቢሆን ዓልይን የገደሉ ኸዋሪጆች መንገድ መንገዴ አይደለም።

ብዙዎቻችሁ እንደምትሳደቡ ባውቅም፤ ሐቁን ከመናገር ወደ ኋላ አልልም። ሽንት በሽንት አይጸዳምና! ሰላም ቀናውን መንገድ በተከተለ ሁሉ‼

||
t.me/MuradTadesse

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

🪀የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 6
───────────
▪️ዓብዱሮህማን_ኢብኑ_ሐሰን ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

🔻«የአንድ እውቀት ፈላጊ ተማሪ ኢኽላስ ምልክቶች መካከል አንዱ ከማያገባው ነገር ዝምታን መምረጡ፣ ለጌታው መዋረዱ እና ለአምልኮው መዋደቁ፣ ፈሪሀ አሏህ መሆኑ፣ ሀቅ በማንም አንደበት ቢሆንም ለመቀበል አለማመንታቱ፣ ለነፍሱ ሲል ትምክህተኛ አለመሆኑ፣ ቅናተኛና ኩራተኛ አለመሆኑ፣ ወደ ዝንባሌው አለማጋደሉ እንዲሁም ለዱንያ ጥቅም አለመቋመጡ ናቸው።»

📚 ۞ الرسائل النجدية【4/406】۞
───────────
download app from: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.UlemaSpeech.Hudasoft

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️ከኛ ከሚጠበቀው ነገር አንዱ ዱዓ ላይ መበርታት ነው ..

🔻ዱዓችን ተቀባይነት አግኝቶ ውጤቱን እዚው በዱንያ በአይናችን ልናየው እንችል ይሆናል ካልሆነና እኛ ብንሞትና ባናየው እንኳን ልናዝን አይገባም! አሏሁ - ተዓላ - ለነብያችን ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲል ነበር ያፅናናቸው ፦

{ وَإِمَّا نُرِيَنَّكَ بَعْضَ الَّذِي نَعِدُهُمْ أَوْ نَتَوَفَّيَنَّكَ فَإِلَيْنَا مَرْجِعُهُمْ ثُمَّ اللَّهُ شَهِيدٌ عَلَىٰ مَا يَفْعَلُونَ }

[| የዚያንም የምናስፈራራቸውን ከፊሉን (በሕይወትህ) ብናሳይህ (መልካም ነው)፡፡ ወይም (ሳናሳይህ) ብንገድልህ መመለሻቸው ወደ እኛ ነው፡፡ ከዚያም አላህ በሚሠሩት ስራ ላይ ዐዋቂ ነው፡፡ |] (ሱረቱ-ዩኑስ ፥ 46)

እና አብሽሩ ዱዓ ላይ በርቱ!!
@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

🪀የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 5
───────────
▪️ኢብኑ_ተይሚያህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

🔻«ዱንያ ውስጥ ካሉ ነገሮች አስደሳቹ አላህን ማወቅ ሲሆን አኺራ ውስጥ ካሉ ነገሮች አስደሳቹ ደግሞ አላህን መመልከት ነው ፤ ጥራት ይገባውና።»

📚 ۞ مجمـوع الفتـاوي【14/163】۞
───────────
download app from:
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.UlemaSpeech.Hudasoft

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

አተርፍ ባይ...

🔅የቁርኣን ቃላትን ከዐረብኛ ውጪ ባሉ ፊደሎች መፃፍ ክልክል ሆኖ ሳለ ቁርኣንን ለመማር ለማስተማር በሚል አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ቁርኣንን በሌላ ቋንቋ የሚፅፉ ብዙዎች ናቸው።
🔅ለሰለምቴ/አዲስ ወደ ኢስላም ለገቡ ወገኖችም ይሁን ሳይማሩ ዕድሜያቸው ለገፋ ሰዎች ቁርኣንን በሌላ ቋንቋ እየፃፉ የሚያስተምሩና እንደ ኣየተል-ኩርሲይ ወዘተ ያሉ ልዩ ትሩፋት ያላቸው አንቀፆችን በአማርኛ፣እንግሊዘኛ፣ኦሮሚኛም ይሁን በሌሎች ከዐረብኛ ውጪ ባሉ ፊደሎች እየጻፉ የሚሸጡ፤ ይህንንም የሚያሳትሙ ሰዎችና ድርጅቶች በሙሉ ለዲናቸው ሲሉ (አላህን ፈርተው) ከዚህ ሊታቀቡ ይገባል!።
🔅ስለዚህ የፈጀውን ያክል ጊዜ ፈጅቶ ቁርኣኑ በወረደበት ፊደል፣ ነቢዩ ﷺ እና ሰሓባዎች ባስተማሩበት መልኩ፣ ቀደምት ሙስሊሞች እንደተማሩት በዐረብኛ ፊደላቱን አጥንቶ ከዛም በየደረጃው ቃላትን እያጣመሩ፤ ለጀማሪ በተዘጋጁ መጽሐፍት እየታገዙ መቅራትና መማር ይገባል።
🔅ከላይ የተባለው ሁሉ የቁርኣንን የዐረብኛውን ቃል እራሱን በሌላ ፊደል መጻፍን በተመለከተ ነው እንጂ የቃላቱን ትርጉም ዕውቀትና ብቃት ባለው ሰው ወደ ሌላ ቋንቋ መተርጎሙ (መፈሰር) የተፈቀደና ለመላው የሰው ልጆች የቁርኣንን መልዕክት በሚገባቸው ቋንቋ ከማድረስ አንጻር ተፈላጊና ተወዳጅም ነው።
🔅ነገር ግን ማንኛውንም የትርጉም ስራ ለመስራት ሁለቱን ቋንቋዎች በሚገባ ማወቅና በሁለቱ ቋንቋዎች መካከል ሊኖር የሚችልን የንግግር ዘይቤ ልዩነት ከግምት ውስጥ ባደረግ መልኩ የትርጉም ስራውን ማስኬድ እንዲሁም ወደ ሌላ ቋንቋ የተተረጎመውን ቁርኣን ሳይሆን የቁርኣን መልዕክት ማለት (ብሎ መሰየም) ይገባል።

💥ቁርኣንን በሌላ ፊደል ከመጻፍ ይጠንቀቁ! ቁርኣን ከአላህ ዘንድ የወረደው በዐረብኛ ቋንቋ ነው። ከነቢዩ ﷺ ዙሪያ የነበሩ ሰሓባዎችም የጻፉት በዐረብኛ ቋንቋ እና ፊደል ብቻ ነው።

﴿نَزَلَ بِهِ ٱلرُّوحُ ٱلۡأَمِينُ١٩٣ عَلَىٰ قَلۡبِكَ لِتَكُونَ مِنَ ٱلۡمُنذِرِينَ١٩٤ بِلِسَانٍ عَرَبِيّٖ مُّبِينٖ١٩٥﴾ [الشعراء: 193-195]
ከአስጠንቃቂዎች ትሆን ዘንድ ቁርኣንን ግልጽ በሆነ ዐረብኛ ቋንቋ ታማኙ መንፈስ ጂብሪል (ከአላህ ዘንድ) ልብህ ላይ አወረደው።” (አሽ-ሹዐራእ 193-195) ።

✍ጥቅል መልዕክት ለማስተላለፍ ያመች ዘንድ "ቁርኣን የህይወት ብርሃን" ከሚለው መፅሀፍ ተቀንጭቦ የተዘጋጀ።

ዛዱል መዓድ
🔎  https://bit.ly/3BCYT1t
🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸

🌐/channel/ahmedadem

📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️መጠግያችን አሏህ!

🔻የጭንቅ ጊዜ ደራሻችን ከገባንበት መከራና ስቃይ የሚያወጣን ነብያችን ﷺ ወይም ሌሎች ወልይ ተብለው የተሰየሙ ሙታን ሰዎች ሳይሆኑ አሏህ ብቻና ብቻ ነው። በየመንዙማ ላይ የሚሰማው ግን በተቃራኒው ነው! ይህን የሚያዜሙትም ማዲሕ ተብለው ትልቅ ቦታ ተሰጥቷቸዋል! ጉዳዩ ግን የተገላቢጦሽ ነው!

@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 2
───────────
🪀ሸይኽ_ሷሊህ_አልፈውዛን ሐፊዞሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

🔻«አግብተህ፣ ነፍስህን (ከዝሙት) መጠበቅህ፣ ሴቲቱንም እንዲሁ መጠበቅህ እና ዝርያዎችንም መተካትህ ትርፍ ዒባዳዎችን ለመፈፀም ለብቻህ ከመገለልህ የበለጠ ነው።»

📚 ۞ شـرح إغاثـة اللهفـان【25/6/1437】۞
───────────
download app from: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.UlemaSpeech.Hudasoft

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️ሙስሊም ጠልነት

🔻ከዚ በፊት ያስቸግረን የነበረው ኦርቶማራ ነበር አሁን ኦጴንጤ ሆኗል። እነሱ እርስበርስ አይስማሙም ፤ ሙስሊሙን መጥላት ላይ ግን አንድ ናቸው።
°
🔻ዑለማዎች እና በመንግስት ጥቅማጥቅም ያልታሰራችሁ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላችሁ ሰዎች ዝም አትበሉ! ተወያዩና ለህዝቡ አቅጣጫ አመላክቱ! እየተቀደደ ያለው የአሏህ ቃል ነው!! እየፈረሰ ያለው የአሏህ ቤት ነው!!

@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

" የተፈታች ሴት በፍፁም የውድቀት ምልክት አይደለችም። አሏህን ከፈራች ከፍቺውም ቡኃላ አሏህ ከችሮታው ያብቃቃታል። የተሻለ የህይወት መስመር ያበጅላታል። "
✍️ዐብዱረዛቅ አልሐበሺይ

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️የልብ ድርቀት

🔻´´ከመከራዎች ሁሉ ትልቁና ከባዱ የልብ ድርቀት ነው።´´ (ሑዘይፋህ ኢብኒ ቀታዳህ / አስሲየር ፥ 9/284). አሏህ ከልብ ድርቀት ይጠብቀን

t.me/ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

ከወንድሜ Abdu Musema.

🪀ከሰው ገለል ሲባል ስንት የሚፈፀም ጥፋት አለ?!
~
🔻 ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሐዲሣቸው እንዲህ ብለዋል፦
لَأَعْلَمَنَّ أَقْوَامًا مِنْ أُمَّتِي، يَأْتُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ بِحَسَنَاتٍ أَمْثَالِ جِبَالِ تِهَامَةَ، بِيضًا، فَيَجْعَلُهَا اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ هَبَاءً مَنْثُورًا
"የቂያማ ቀን እንደ ቲሃማ ተራሮች የነጡ በጎ ስራዎችን ይዘው ነገር ግን አላህ የተበተነ ትቢያ የሚያደርግባቸው ሰዎችን በእርግጥም አውቃለሁ።"

🔻በዚህን ጊዜ ሠውባን ረዲየላሁ ዐንሁ፡
“የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ምን አይነት ሰዎች እንደሆኑ ይንገሩን። ሳናውቀው ከነሱ እንዳንሆን ሁኔታቸውን ይግለጡልን” በማለት ጠየቁ። ነብዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፦
أَمَا إِنَّهُمْ إِخْوَانُكُمْ وَمِنْ جِلْدَتِكُمْ، وَيَأْخُذُونَ مِنَ اللَّيْلِ كَمَا تَأْخُذُونَ، وَلَكِنَّهُمْ أَقْوَامٌ إِذَا خَلَوْا بِمَحَارِمِ اللَّهِ انْتَهَكُوهَا
"እነሱማ የናንተው ወንድሞች የናንተው አይነቶች ናቸው። በሌሊት ዒባዳዎችን እንደምትፈፅሙት ይፈፅማሉ። ነገር ግን ከሰው ሲገለሉ ጊዜ የአላህን ክልከላዎች የሚዳፈሩ ናቸው።" [አሶሒሐህ: 505]

@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

#ኡድሒያን_የሚመለከቱ_ነጥቦች 👇👇

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

◾️በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና አዛኝ በሆነው

#አስሩ_የዙልሒጃ_ቀናት

🔻ዙልሒጃህ ብሎ ማለት የዐረበኛ 12ኛ ወር ሲሆን የዚህ ወር 10ቀናት ልዩ ትሩፋት እንዳላቸው ነቢያችን - ﷺ - ተናግረዋል። እንደዚሁ ቁርአን ላይም እነዚህ ቀናት ተጠቅሰዋል። አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - ከፈጠራቸው ፍጡር ውስጥ አንዱን ከሌላኛው አበላልጧል። የረመዷን ወር ከወሮች ሁሉ በላጭ ነው። የረመዷን የመጨረሻዎቹ 10ቀን ለሊቶች ከለሊቶች ሁሉ በላጭ ናቸው። ምክንያቱም ለይለተል ቀድር በውስጧ ስላለ ነው።
°
🔻የዙልሒጃ አስሩ ቀናት ደግሞ ከቀናቶች ሁሉ በላጭ ናቸው። ለዚህም ነው ሸይኸል ኢስላም ኢብኑተይሚያ - ረሒመሁሏህ - ከረመዷን የመጨረሻዎቹ 10 ቀናቶች የዙልሒጃ የመጀመሪያዎቹ 10 ቀናቶች እንደሚበልጡና ከዙልሒጃ10 ለሊቶች ደግሞ የረመዷን 10 የመጨረሻ ለሊቶች እንደሚበልጡ ተናግሯል። (መጅሙዓል ፈታዋ 25/287)
°
🔻አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - በተከበረው ቁርኣኑ ላይ እንዲህ ይላል ፦

{ لِّيَشْهَدُوا مَنَافِعَ لَهُمْ وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۖ فَكُلُوا مِنْهَا وَأَطْعِمُوا الْبَائِسَ الْفَقِيرَ }

[| ለእነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ (ይመጡሃል)፡፡ ከርሷም ብሉ፡፡ ችግረኛ ድሃንም አብሉ፡፡ |] (ሐጅ ፥ 28).
°
🔻እነዚህ ቀናት ብሎ ማለት ዐብደላህ ኢብኑ ዓባስ እንደገለፁት አስሩ የዙልሒጃ ቀናት እንደሆኑና በነሱም ላይ አላህን በጣም ማውሳት እንዳለብን ተናግረዋል።
°
🔻ከዚህም በተረፈ ዐብደሏህ ኢብን ዓባስ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ባስተላለፈው ነቢያችን - ﷺ - ሐዲስ እንዲህ ብለዋል ፦ [ ከዙልሒጃህ 10 ቀናት የበለጠ አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆኑባቸው ምንም አይነት ቀናቶች የሉም።] በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን! ተብለው ሲጠየቁ ፦ [ አዎ. በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን , ነገር ግን ንብረቱንና ነፍሱን ይዞ ወጥቶ ከዛ በምንም ነገር ያልተመለሰ ሰው ሲቀር ብለዋል። ] (ቡኻሪ ፥ 969).
°
🔻ኢብኑረጀብ - ረሒመሁላህ - እነዚህ አስር ቀናት ከሌሎቹ ሊበልጡ የቻሉበት ምክንያት ሲናገሩ ፦ |' በጣም ዋና የሚባሉት የዒባዳ አይነት በአንድ ላይ ስለሚሰባሰቡበት ነው እነሱም ሰላት ፣ ፆም ፣ ሰደቃ እና ሐጅ ናቸው ብለዋል። '| (ፈትሑልባሪ ፥ 2/460)
°
🔻ዋና ዋና በዚህ ወር ልንሰራቸው ከሚገቡ ተግባራቶች ውስጥ ፦
1️⃣.ፈርድ ሰላትን ወቅት ጠብቆ መስገድ ይኖርብናል። ሱጁድ በማብዛት ወደ አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - መቃረብ ተገቢ ነው። ነቢዩም - ﷺ - [ ሱጁድ በማብዛት ላይ አደራ ; አንተ እኮ ምንም ሱጁድ አታደርግም በሰጁዱህ ልክ አላህ ዘንድ ማእረግህ ከፍ ቢል እና ወንጅልህም ቢራገፍልህ እንጂ ብለዋል። ] (ሙስሊም ዘግቦታል). ሱና ሰላቶችንም ማብዛት ይጠበቅብናል። በተለይም 12ቱ "ራቲባ" የሚባሉትን እነሱም ፦ ከሱብሂ በፊት 2ረከዓ ፣ ከዙሁር በፊት 4ረከዓ , በኋላ 2ረከዓ ፣ ከመግሪብ በኋላ 2ረከዓ እና ከዒሻእ በኋላ 2 ረከዓ ናቸው።
°
2️⃣.ፆም መፆምም ተገቢ ነው። አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆንባቸው ቀናቶች የሉም ከነዚህ 10 ቀናቶች የበለጠ ሰለተባለ ፆም ደግሞ ከመልካም ስራ ስለሚገባ መፆም ተገቢ ነው። ኢማሙ ነወዊም አስሩ የዙልሂጃን ቀን መፃም የጠበቀ ሱና ነው ብለዋል።
3️⃣.ሰደቃ በመስጠት ላይም መጠናከር ይኖርብናል።
°
4️⃣.ተክቢር እና ተህሊልልን ማብዛትም ተገቢ ነው። ሰሓባዎችም በነዚህ ቀናት ውስጥ ተክቢርና ተህሊልን ያበዙ ነበር። በአሁን ሰአት ግን በጣም ከተረሳ ሱናዎች ውስጥ አንዱ ነው። ኢማም አል-ቡኻሪም እንዲህ ብለዋል ፦ ||" ኢብኑ ዑመርና አቡሁረይራ ወደገበያ ቦታ በመውጣት በነዚህ ቀናቶች ውስጥ ተክቢር ይሉ ነበር ሰዎችም በነሱ ተክቢራ ማለት ተነሳስተው ተክቢራ ይሉ ነበር። "||. አባባሉም ፦ አሏሁ አክበር , አሏሁ አክበር , ላኢላሀኢለላህ, አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር ወሊላሂል ሐምድ.
ሌሎችም በትክክለኛ ሐዲስ የተዘገቡ ተክቢራዎችን ማለት ይቻላል።
°
5️⃣.ከአስሩ ቀናት በተለየ መልኩ የ9ኛውን ቀንማለትም የዐረፋን ቀን መፆም ተወዳጅ ነው። ምክንያቱም ነቢዩ - ﷺ -  ስለዐረፋ ቀን ፆም እንዲህ ብለዋል ፦ [ ያለፈውን አመት እና የወደፊቱን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ አላህ ላይ ተስፋ አደርጋለው ] (ሙስሊም ዘግቦታል). በዚህም ቀን ዱዓን ማብዛት አስፈላጊ ነው።
°
6️⃣.ሌላኛው 10ኛው ቀን ላይ ሚተገበሩ ተግባሮች ናቸው። እነሱም ፦ ዒድ ሰላት መስገድ ፣ ኡድሂያን ማረድ ... ሐጅ ላይ ያሉ ሰዎች ደግሞ ጀመራት ይወረውራሉ ፣ ፀጉራቸውን ይላጫሉ ፣ ሀድይ የያዙ ሰዎች ሀድያቸውን ያርዳሉ ፣ ወደ መካ ተመልሰው ጠዋፈል ኢፋዷ ያደርጋሉ። በአጠቃላይ 10ኛው ቀን አላህ ዘንድ በጣም ትልቅ ነው።
°
🔻ስለዚህ ጠቅለል ባለ መልኩ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን በምናገኝበት ጊዜ ተውበት አድርገን ራሳችንን ለኸይር ስራ ዝግጁ አድርገን ከወንጀላችን ታቅበን ሌሎችንም ከዙሪያችን ያሉ ሰዎችን ይሄን እድል እንዲጠቀሙ መገፋፋት ያስፈልጋል ። እንደዚህ አይነት እድል በሚመጣ ጊዜ ሳናውቀው ስለሚያልፈን መስነፍ አያስፈልግም መጠንከር እና ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል።
°
🔻በመጨረሻም ኡድሂያን ማረድ የፈለገ ሰው ከሰውነቱ ላይ ፀጉሩንም ሆነ ጥፍሩን እስኪያርድ ድረስ መቁረጥ የለበትም። ምክንያቱም ነቢዩ - ﷺ - ኡሙሰለማ ባስተላለፈችው ሀዲስ እንዲህ ስላሉ ፦ [ የዙልሒጃህን ጨረቃ ካያችሁና , ከእናንተ አንድኛችሁ ኡድሂያን ማረድ ከፈለገ ፀጉሩን እና ጥፍሩን ከመቁረጥ ይቆጠብ። ] (ሙስሊም ፥ 1977 ላይ ዘግቦታል). አላህ ተጠቃሚዎች ያድርገን።
___
📕ምንጭ ፦ ከኡስታዝ አሕመድ አደም የድምፅ ፋይል የተወሰደ
✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ  @ Ibn yahya Ahmed 
📆ዙልቂዕዳህ 28/1438ሂ. # ነሐሴ 15/2009 ላይ የተፃፈ

📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦/channel/ibnyahya7

✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

🔖ዝሙተኛ ናት❗️

💥በትክክለኛ የነቢዩ صلى الله عليه وسلم
ሐዲሥ "ሽቶ ወይም መልካም ሽታ ያለውን ነገር ተቀብታ ወጥታ ሽታዋ ወንዶች ጋ የደረሰ ሴት ዝሙተኛ ናት" ከመባሉ ጋር ሽቶ ተለቅልቀው ከቤታቸው በመውጣት ያለፉበት መንገድና የቆዩበት ቦታ ሁሉ በሽታቸው እንዲታወድ ማድረግ የብዙ ሴቶችን የኢማን ወይም የእውቀት ድክመት በይፋ ከሚያሳዩ ነገሮች መካካል አንዱ ነው።

💥እህቴ ሆይ አላህን ፍሪ! የሸሪዓን ህግ አክብሪ!

💥ከቤት ውጪ ሽቶም ይሁን የሚቆይና ከራስ አልፎ ሌሎች ጋ የሚደርስ ሽታ ያላቸው ቅባትና ክሬሞችን አትጠቀሚ።

@ ዛዱል-መዓድ
/channel/ahmedadem

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

🪀የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 7
───────────
▪️ሱፍያን_ኢብኑ_ዑየይናህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ :-

🔻«አስተዋይ ማለት መልካምና  እና መጥፎን ያወቀ ሰው አይደለም።እነሆ አስተዋይ ማለት መልካምን ባየ ግዜ የተከተለና መጥፎን ባየ ግዜ ደግሞ የራቀው ማለት ነው።»

📚 ۞ حليـة الأوليـاء لأبي نعيـم【8/339】 ۞
───────────
download app from: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.UlemaSpeech.Hudasoft

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

🔻ከባድ ጥንቃቄ!
አሏሁ - ተዓላ - ወይም ነብያችን - ሰለሏሁዓለይሂወሰለም - ከመሰከሩላቸው ሰዎች ውጭ እከሌ የጀነት ነው ማለት አይቻልም። ስለዚህ የጀነት ሙሽራ እያሉ ከመናገር እንጠንቀቅ!!

@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

በቁርኣን አስታውስ 3

إِنَّ الَّذِينَ فَتَنُوا الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ثُمَّ لَمْ يَتُوبُوا فَلَهُمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمْ عَذَابُ الْحَرِيقِ }

[| እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የጀሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡ |] (ሱረቱል-ቡሩጅ ፥ 10)

@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

🔻ሙስሊም ከመሆናችን ውጭ ሌላ ምን አደረግናቸው?? እስልምናዬን ተምሬ ጌታዬን የማመልክበትን መስጄዴን አታፍርሱ ከማለት ውጭ ሌላ ምን አደረግናቸው??

{ وَمَا نَقَمُوا مِنْهُمْ إِلَّا أَن يُؤْمِنُوا بِاللَّهِ الْعَزِيزِ الْحَمِيدِ }

[| ከእነርሱም በአሏህ አሸናፊው፣ ምስጉኑ በሆነው (ጌታ) ማመናቸውን እንጅ ሌላ ምንም አልጠሉም፡፡ |] (ሱረቱል-ቡሩጅ ፥ 8)

@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

🪀የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 4
───────────
▪️ኢማሙል_አልባኒይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

🔻«ልክ ከአላህ ውጪ በእውነት የሚገዙት አምላክ እንደሌለ ሁሉ፥ በእውነት የሚከተሉትም የለም ረሱል ﷺ ብቻ ቢሆኑ እንጂ።»

📚 ۞ متفرقات شريط رقم【6】۞
───────────
download app from: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.UlemaSpeech.Hudasoft

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

🪀የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 3
───────────
▪️ኢብኑ_ተይሚያህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

🔻«ሰውየውን መልክተኛውን ﷺ  እንዳይከተል የሚያደርጉት ሁለት ነገር ናቸው። ወይ መሐይምነቱ ነው ወይም የብልሹ አሥተሣሰብ ባለቤት መሆኑ ነው።»

📚 ۞ الفتاوي【15/93】۞
───────────
download app from: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.UlemaSpeech.Hudasoft

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

📱አዲስ አፕልኬሽን “ሩቂያ መንፈሳዊ ህክምና”📱
-----
🔻በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኁሩህ እጀግ በጣም አዛኝ በሆነው፤ የአላህ ሰላትና ሰላም በውዱ ነብያችን ላይ ይስፈን።አላህ ﷻ በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ይላል፦“ከፍርሃትና ከረኃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር፡፡” (البقرة), 155
°
🔻አላህ ﷻ ሙእሚኖችን በዱኒያው ህይወታቸው እንደሚፈትናቸው በተለያዩ የቁርአንና የሐዲስ መረጃዋች ላይ ተጠቅሷል። በዘመናችን ሙእሚኖች ከሚፈተኑባቸው ፈተናዋች መሀከል ድግምት/ሲህር/አይነናስ እየተበራከተ መጥቷል።
°
🔻የአላህ ነብይﷺ ይህን በተነበዩበት ሀዲሳቸው "ከህዝቦቼ ብዙዎቹ ከአላህ ውሳኔ በኋላ የሚሞቱት በአይነናስ/በሰው ዐይን/ ነው ብለው" ብለዋል። ስለዚህ አይነናስም ይሁን ድግምት ከመከሰታቸው በፊት እራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንዳለብን ማወቃችን አስፈላጊ ነው።
°
🔻ይህ አፕ ከሩቃ/መንፈሳዊ ህክምና/ ጋር ተያያዥ ነጥቦችን ለንባብና ለመረዳት አመቺ በሆነ መልኩ ተዘጋጅቷል። አፑ ከተለያዩ ፈተናዋች እራሳችንን እንድንጠብቅ ሰበብ ከተደረገልን የተከበረ ቃል ከሆነው ቁርአን፣ሐዲስና የዑለሞች ንግግርን መሰረት በማድረግ የቀረበ ነው።አፑን ለሙስሊሙ ኡማ በማሰራጨት የኸይር ሰበብ የአጅር ተቋዳሽ ይሁኑ።

✍ዝግጅት፦ አብዱ ሙሰማ ሀሰን
📕አፕልኬሽን ስራ፦ HUDA SOFT || ሁዳ ሶፍት

🪀አፑን በሚከተለው ሊንክ ከፕለይስቶር ይጫኑ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.Ruqa.HudaSoft
------
ለሚፈልጉ ሁሉ ሼር አድርጉላቸው።
____👇👇👇

📣https://play.google.com/store/apps/details?id=com.Ruqa.HudaSoft
-------

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 1
───────────
🪀ኢብኑል_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - ኢብኑ ተይሚያህ አንድ ጊዜ እንዲህ ሲሉ መከሩኝ —

🔻«ቀልብህን የፈሰሰበትን ሁሉ እንደሚመጠውና ሲጨምቁትም ያንኑ እንደሚተፋው እስፖንጅ አታድርገው። ይልቁንስ እንደ መስታወት አድርገው። ብዥታዎች በገፅታው ላይ ያልፋሉንጂ ወደ ውስጡ አይገቡም። አጥርቶ ይመለከታቸዋል፣ በጠጣርነቱ ደግሞ ይመልሳቸዋል። አንተም ባንተ ላይ የመጣውን ብዥታ ሁሉ ለልብህ ካጠጣኸው የብዥታዎች መኖሪያ ይሆናል።»

📚 ۞ مفتاح دار السعادة【1/443】۞
───────────
download app from:
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.UlemaSpeech.Hudasoft

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

#በመስጂዶች_ፍርስራሽ_የምትገነባዋ_ከተማ_ሸገር
#ሕገወጥ_አስተዳደር_እንጂ_ሕገወጥ_መስጂድ_የለም!
#ዓሳ_ያለ_ውሃ_ሙስሊም_ያለ_መስጂድ_መኖር_አይችሉም!
#መስጂዴን_አታፍርስ_ያፈረስከውንም_መልስ!

Читать полностью…
Subscribe to a channel