ibnyahya777 | Unsorted

Telegram-канал ibnyahya777 - Ibn Yahya Ahmed

2272

የተለያዩ ዲናዊ ፅሑፎችን ብቻ የማስተላልፍበት ቻናሌ ነው።

Subscribe to a channel

Ibn Yahya Ahmed

ይገምቱ .. ይሸማሉ = ቁማር ነው በማለት ሸይኽ ኢልያስ ፌስቡክ ገጹ ላይ አጋርቷል።

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️ነሺዳ ወይስ የጴንጤ መዝሙር??

🔻"" አንዳንድ ኢስላማዊ ነሺዳ የሚባሉ የጴን*ጤ መዝሙር የሚመስሉ አሉ ፤ የለየለት ዘፈን የሚመስሉም አሉ። ይሄን ኢስላማዊ ማለት ኢስላም ላይ አዲስ ነገር መለጠፍ ነው የሚሆነው። "" // (ኡስታዝ አሕመድ አደም || ከዛዱል መዓድ ፈታዋ ቁ.198 የ13ኛው ጥያቄ ምላሽ ላይ የተወሰደ).

@ibnyahya7

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

إنا لله وإنا إليه راجعون

توفي الشيخ عبيد الجابري

اللهم اغفر له وارحمه وعافه واعف عنه وأكرم نزله ووسع مدخله وأسكنه الفردوس الأعلى من الجنة بغير حساب ولا سابقة عذاب

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

🍃 ጭንቀት #በተሰማህ #ጊዜ ለሰው
አታብራራ ወረቢ🌹 ከጌታህ ውጭ ጭንቀትህን አዋቂና ተረጅ የለም! ያውም በዚህ ውድ አውቃት


ነቢዩሏህ አዩብ ዐለይሂ ሰላም መከራ
ባገኘው ጊዜ ጌታውን ↴
«እኔ መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» ሲል በተጣራ ጊዜ አስታውስ፡፡
𝐓𝐞:/channel/dawatulanbiya

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

◼️ተሀጁድን ከፈጅር በላይ አታስበልጥ

🔻በረመዷን የመጨረሻዎቹ 10 ቀናቶች ውስጥ ከሚታዩ ስህተቶች ውስጥ አንዱ ተሀጁድን በጀመዓ ሰግዶ የፈጅርን ሶላት ማሳለፍ ነው። ወንድሜ ሆይ! ወደአሏህ ከምትቃርብበት ነገር በላጩ አሏህ ግዴታ ያደረገብህ ነገር መሆኑን ተገንዘብ።

/channel/ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️ትኩረት ይሰጠው ~ የለሊቱ የመጨረሻ ሲሶ

🔻የአላህ መልእክተኛ  - ﷺ - እንዲህ ሲሉ ይነግሩናል ፦ [ አላህ - ሱብሓነሁወተዓላ - የሌሊቱ ሲሶ(1/3)ኛ ሲቀር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል ከዛም ይላል ፦ ማንነው የሚለምነኝ እሺ የምለው ፤ ማንነው የሚጠይቀኝ የጠየቀውን የምሰጠው ፤ ማንነው መሀርታን የሚጠይቀኝ የምምረው። ] (ቡኻሪ ፥ 1145)
°
🔻ይህን ሐዲስ በብዛት ስንጠቀምበት የምንስተዋለው የጥመት አንጃዎች 'አሏሁ - ተዓላ - አይወጣም አይወርድም' ስለሚሉ እንደሚወርድ መልስ ለመስጠት ነው። ነገር ግን ከዛ ባለፈ ሌላ ትልቅ ቁምነገርን ይዟል እሱም ሁለተኛው ሀረግ ላይ ነው ፦ "ማንነው የሚለምነኝ እሺ የምለው ፤ ማንነው የሚጠይቀኝ የጠየቀውን የምሰጠው ፤ ማንነው መሀርታን የሚጠይቀኝ የምምረው። " እያለን ነውና ወንድሞቼ እና እህቶቼ በዚህ ሰአት ላይ ተነሰትን እጃችንን ወደአላህ መዘርጋትን አንርሳ!!
____
✍አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን የሕያ
➖➖➖➖➖➖➖➖
📣ጆይን ፦ /channel/ibnyahya777
✅ላይክ ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya7777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️ሰሑር ላይ ኢስቲግፋር እናድርግ

🔻አሏሁ - ተዓላ - የመተቆችን(እሱን የሚፈሩ ባሪያዎችን) ባህሪይ ሲገልፅ እንዲህ ይላል ፦
{ وَبِالْأَسْحَارِ هُمْ يَسْتَغْفِرُونَ }

[| በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ |] (አዝዛሪያት ፥ 18). በተለይም በዚህ በረመዷን ወቅት ሱሑርን ለመብላት ስለምንነሳ በዛውም ኢስቲግፋር ማድረግን መርሳት የለብንም። አላህ ይወፍቀን ፤ ወንጀላችንንም ይማርልን።
____
✍አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን የሕያ
➖➖➖➖➖➖➖➖
📣ጆይን ፦ /channel/ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️የረመዷን ወር መለያዎች

🔻ነብዩ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ የረመዷን ወር በመጣ ጊዜ የጀነት በሮች ይከፈታሉ ፤ የእሳት በሮች ይዘጋሉ ፤ ሸይጧኖችም ይታሰራሉ ] (ቡኻሪ ፥ 1799 / ሙስሊም ፥ 1079)
___
✍አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን የሕያ
📣/channel/ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

ነገ ሰኞ ሸዕባን 29 ነው እየተባለ ነው ..

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

#አጫጭር_የረመዷን_ፈትዋዎች 1⃣2⃣

📋#ሐይድ_ላይ_ያሉ_ሴቶች_መብላት_ግዴታ_ይሆንባቸዋልን

☪ከዛዱልመዓድ ፈታዋ ቁ.40 ላይ የ6ኛው ጥያቄ ምላሽ.

🏴ጥያቄ ፡

6⃣.በረመዷን ሐይድ ላይ እያለሁኝ ምግብ መብላት አያስፈልገኝም ፤ ፆመኛ አለመሆኔን አውቃለሁኝ የግድ መብላት እና መጠጣት አለብኝ ወይ? ባለመብላቴስ ሐራም ይሆንብኛል ወይ ?

🏳መልስ ፡
°
🔻የወሊድ ደም እና የሐይድ ደም ላይ ያሉ ሴቶች መፆም አይፈቀድላቸውም , ግዴታ አይሆንባቸውም ፤ ቢፆሙም ተቀባይነት አያገኙም። በመፆማቸው ሁሉ ወንጀለኛ ይሆናሉ ፤ ስለዚህ መብላት ይችላሉ ማለት ነው። ነገር ግን በሚበሉበት ጊዜ በግልፅ መብላት የለባቸውም ፤ ውጪ ላይ ሰው እያያቸው ወጥተው ሊበሉ አይገባም። ቤትም ቢሆን ምክንያታቸውን , "ዑዝራቸውን"  የማውያቁ ሕፃናት ባሉበት ሊበሉ አይገባም። ሕፃናት ግራ ይጋባሉ ፤ ባንድ በኩል ረመዷን ነው ሌሎች ቤተስቦች እየፆሙ ነው ፤ በሌላ በኩል እናት ስትበላ ካዩ ግራ ሊጋቡ ይችላሉ።
°
🔻ሁሉም የሚያውቁ እና "ዑዝርን" የሚረዱ ከሆኑ ሌሎች እያዩ ብትበላ ችግር የለውም። "ዑዝሩ"/(ምክንያቱ) ድብቅ የሆነ ሰው ውጭ ላይ ወጥቶ መብላት የለበትም ሌሎችን ግራ ያጋባል። ይህን የሚያደርጉ ስዎች ላይም የሙስሊሞች መሪ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባው "ፉቀሃዎች"/(የፊቅህ ሊቃውንቶች) ጠቅስዋል።
°
🔻#በጥቅሉ_የወሊድ_እና_የወር_አበባ_ላይ_ያሉ_ሴቶች_መፆም_አይፈቀድላቸውም ፤ መብላት ይችላሉ። መብላት "ይወጅባል"/(የግድ ይሆናል) ወይ? ፆሜያለሁ ብለው "እስካልነየቱ"/(እስካላሰቡ) ድረስ , ምግብ መተዋቸውን የፆም አካል እስካላደረጉ ድረስ መብላቱ ግዴታ አይሆንም። ፆመኛ ነኝ አልበላም ብለው ካሰቡ ብቻ ነው ወንጀለኛ የሚኮነው ፤ ነገር ግን እስካልፆሙ ድረስ የነፍስያን ሐቅ ቢጠብቁ ፣ ቢበሉ ፣ በልተው ፆመኞችን "ቢኻድሙ"/(ቢያገለግሉ) ፣ ፍጡር ቢያዘጋጁ የተሻለ ነው።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📕ምንጭ ፦ ከኡስታዝ አሕመድ አደም የዛዱልመዐድ ፈታዋ ቁ.40 ኦዲዮ ላይ የተወሰደ.
✍️ፈትሒያ ቢንት ሸምሱ
ኤዲት የተደረገው በአቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn Yahya Ahmed
📆ሰኞ ረጀብ 25/1440ሂ. # መጋቢት 23/2011. # April 1/2019.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦/channel/ibnyahya7

✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ፦ https://www.facebook.com/ibnyahya777/

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

#አጫጭር_የረመዷን_ፈትዋዎች 🔟

📋#ነፍሰ-#ጡር_እና_የሚያጠቡ_ሴቶች

☪ከዛዱልመዓድ ፈታዋ ቁ.41 ላይ የ7ኛው ጥያቄ ምላሽ.

🏴ጥያቄ ፡

7⃣.የስድስት ወር እርጉዝ ነኝ ፤ አንድ ቀን በጣም ፆሙ አድክሞኝ ባፈጥር ወንጀለኛ እሆናለሁ ወይ?

🏳መልስ ፡

🔻ነፍሰ-ጡር የሆነች ሴት , አጥቢ የሆነች ሴት በእርግዝናውና በማጥባቱ ምክንያት #የሚደክማቸው_ከሆነ ፤ እንደዚሁ ደግሞ እራሳቸው ወይም ፅንሱ ወይም #የሚጠባው_ሕፃን_የሚጎዱ_ከሆነ_ማፍጠር_ይፈቀድላቸዋል። ከመፈቀድም አልፎ ሱንና ይሆንላቸዋል ፤ አጅር ያገኙበታል።
°
🔻በሽተኛ የሆነ ሰው ህመሙ የሚጎዳው , የሚከብደው ከሆነ መብላት አንደሚችለው ፤  እንደውም አንዳንድ "ፉቀኃዎች"/(የፊቅህ ሊቃውንቶች) | يسن | ሱንናህ ይሆንለታል እንዳሉት ሁሉ ነፍሰ-ጡር የሆነች ፣ አጥቢ የሆነች ሴትም እዚህ ውሰጥ ነውና የምትካተተው ያለ ምንም መጨናነቅና መቸገር እርጉዝ እና አጥቢ የሆኑ ሴቶች እርግዝናው , ማጥባቱ የሚከብዳቸው ከሆነ ረመዷን ላይ መብላት ከዛ በኋላ ቀዷእ ማውጣት ይችላሉ። #ነገር_ግን_ለይተው_የማያውቁ_ሕፃናቶች_ያሉበት_ቦታ_ላይ_እንደዚሁ_ውጪ_ላይ__ሰው_እያየ_አለመብላቱ_ተገቢ_ነው ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📕ምንጭ ፦ ከኡስታዝ አሕመድ አደም የዛዱልመዐድ ፈታዋ ቁ.41 ኦዲዮ ላይ የተወሰደ.
✍️ ኡሙሙሐመድ
ኤዲት የተደረገው በአቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn Yahya Ahmed
📆ቅዳሜ ረጀብ 23/1440ሂ. # መጋቢት 21/2011.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦/channel/ibnyahya7

✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ፦ https://www.facebook.com/ibnyahya777/

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

◼️ስለመጅሊስ ይመለከትሃል!!

🔻አንዳንዱ ሙስሊም ከመሆኑ ጋር የመጅሊስ ጉዳይ ምንም የማይመለከተው ይመስል ሁልጊዜ ስለመጅሊስ ርእስ ሲወራ ሲያብጠለጥል ትሰማዋለህ። ሌላው የሚገርመው ሰው ደግሞ ጠጋ ብሎ የመጅሊሱን ሁኔታ ለማስተካከል መሞከር ሲገባው ይሄ ሳያንሰው ውጭ ሁኖ ሊያስተካክሉ የሚለፉትን በምላሱ እና በእጁ ሲወርፍ ታየዋለህ።

@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

ቢስሚላህ አር-ረህማን አር-ረሂም
🎀'ከስሁር እስከ ኢፍጣር'
🎀

✨"መልካም ተግባራት፤መልካም ስራዎች መጥፎ አወዳደቅ እንዳይኖረን የሚጠቅምና የሚከላከል ነው" ረሱል


🔖ለ30 ቀናት የአንድ ቤተሰብ የኢፍጣር ተመን 2000-2500 ብር ብቻ

🔖የሚያስፈልጉ ግብዓቶች
1.ፍርኖ ዱቄት=15ኪግ
2. የሾርባ እህል=10ኪግ
3. ዘይት=5ሊ
4. ሩዝ=5ኪግ
5. ቴምር=2ኪግ

📌በአቅርቦት እገዛ ማድረግ ምተፈልጉ በመስጂዳችን ዉስጥ በሚገኘው ቢሮዓችን መጥተው ማስረከብ ትችላላችሁ! ባረክ አላህ ፊኩም!

📌የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000369282763
የኢማሙ አሕመድ መስጂድ ወጣት ዕደር

📍አለም ባንክ ወደ አንፎ በሚወስደው መንገድ አደባባዩ ጎን

✨''የአንድን አማኝ ጭንቀቱን ያቀለለለት አላህ የቂያማ ቀን ጭንቀቱን ያቀልለታል'' ረሱል ﷺ

☎️+118 33 83 87
📞+251 920 28 61 95
📞+251 967 65 77 13
📞+251 910 69 78 50

አዘጋጅ: የኢማሙ አሕመድ መስጂድ ወጣት ማህበር
.
.
ቻናላችንን ስለጎበኙን እናመሰግናለን!
t.me/ImamuAhmedYouth

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️#መንሀጅ_ነክ_ጥያቄና_መልሶች 2️⃣9️⃣

➠ጥያቄ ፡

29.ሶሓቦች በተለያዩበት ጉዳይ ላይ አንዳንድ ጊዜ የአንደኛውን ሶሓባ አቋም ሌላ ጊዜ ደግሞ የሌላኛውን ሶሓባ አቋም በተግባር ብናውል እንዴት ይታያል?

➠መልስ ፡

🔻ይሄኛው ሲመቸኝ ይሄኛውን ፤ ያኛው ሲመቸን ደግሞ ያኛውን መያዝ አይቻልም። ምክንያቱም ዲን ነው ፤ ዲን ደግሞ መከተል ነው እንጂ ራስን ለመጥቀም ወይም እንደፈለግክ የምታደርገው አይደለም። ከማስረጃ አንፃር ይሻላል የሚለውን ነው የምትከተለው እንጂ ሲመችህ ይሄን ሳይመችህ ያን አይደለም።
°
🔻ድሮ እንደማስታውሰው አንድ መፅሔት ላይ በተለያዩ ርእሶች ላይ የአራቱ መዝሀቦች አቋም ተሰርቶ ቀርቦ ነበር። ለምሳሌ የወዱእ ርእስ ላይ ያጠፋል አያጠፋም የሚለው ላይ ሐነፍያ ፣ ሻፍዒያ ፣ ማሊኪያና ሐንበሊያ አቋማቸው ይዘረዘርና የፈለጋችሁትን ስሩ ተብሎ ማለት ነው። ስለዚህ ሰው የሚመርጠው ሁሉንም ይቻላል ይቻላል ወይም ዉዱእ ላይ ከሆነ አያጠፋም ኣያጠፋም የሚለውን ነው። ይሄ ደግሞ አደጋ ነው። | تتبع رخص العلماء | ይባላል ፤ የዑለማዎችን የማግራራትን ፍቃድ መለቃቀም አደጋ ነው።
°
🔻የሸሪዓን ማግራራት መከተል ይቻላል። ረሱል - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦
[" إن الله تعالى يحب أن تؤتى رخصه ، كما يكره أن تؤتى معصيته "] (رواه إمام أحمد).
አሏህ ያግራራውን ሰዎች እንዲሰሩት ይፈልጋል ፤ ልክ የከለከለውን እንዲርቁ እንደሚፈልገው ሁሉ ማለት ነው። እና የሸሪዓ ማግራራትን መከተል ይወደዳል። በእርግጥ የሸሪዓህ ፍቃድ በቁርአን እና በሐዲስ የተዘገበ ነው ፤ ነገር ግን የሰዎች ለምሳሌ ዑለማዎች "ኢጅቲሃድ" አድርገው ይሳሳቱ ይሆናል ፤ እነሱ አጅር ሊያገኙ ይችላሉ አንተ ግን መሳሳታቸውን እያወቅክ አማርጠህ ይሄ ይቀላል ብለህ ስትመዝ ሁልጊዜ ቀላል ቀላሉን መርጠህ ስታጠራቅም መጨረሻ ላይ አንተ ጋር የሚቀረው ኪታብ ስሙ "አልሓላል ወልሓላል" ይሆናል። ይሄ ደግሞ አደጋ ነው።
°
🔻ሱለይማን አትተይሚ የተባሉ አንድ ትልቅ የሰለፍ ሊቅ ልጃቸውን ሲመክሩት እንዲህ አሉ ፦
||" لو أخذتَ برخصة كُلِّ عالِم اجتمع فيك الشرُّ كلُّه "|| ①.
|| የሁሉንም ዐሊም "ሩኽሷህ"(ፍቃድ) ማለትም በስህተትም ይሁን በምን ያግራራውን ነገር የምትለቃቅም ወይም የምትሰበስብ ከሆነ ሸር የተባለ ሁሉ ይሰባሰብብሃል አሉት።
°
🔻አንድ ዐሊም የሆነ ኸሊፋህ ጋር ሲገባ ኪታብ አገኘውና አንስቼ ሳነበው የዑለማዎች "ሩኽሷህ" የተሰበሰበት ነው አለ ፤ ይሄን ኪታብ ያስቀመጠው ሰው ዚንዲቅ ነው አልኩት አለ። ሰነዱ ምናምን ትክክል አይደለሁም እንዴ ሲለው ፤ ሰነዱ ትክክል ሊሆን ይችላል ግን ይሄኛውን የፈቀደ ያንን አልፈቀድም ያንን የፈቀደ ደግሞ ሌላውን አልፈቀድም ፤ ከብዙ ሰዎች የፈቀዱትን ብቻ ነው የሰበሰበው ማለት ነው።
°
🔻ለዚህ ነው ዑለማዎች ብዙዎቹ ምን ይላሉ ፦ ||" من تتبع رخص العلماء تزندق "|| | የዑለማዎችን ሩኽሷ የተከተለ ሰው መጨረሻው ዚንዲቅ ይሆናል። | ምክንያቱም ሃሳቡ ቁርአን እና ሐዲስን መከተል አይደለም ፤ የሱ ሓሳብ ዲኑን ቀይሮም ቢሆን የሚመቸውን መያዝ ነው። ይሄ አደጋ ነው ፤ ዲን ራሱን የቻለ ገር ነገር ነው ፤ አሏህ ነው ያገራው ራሱ ገር አድርጎታል። ከዚህ ውጭ የሚፈልጉ ካሉ እነሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው።
°
🔻ነገር ግን ይሄ ከአቋም መቀየር አንፃር ከሆነ ችግር የለውም። ማለትም መጀመሪያ ይሄ ትክክል ነው ብለህ ታምን ነበረ ፤ ከጥረትህ በኃላ ያኛው ነው ይበልጥ ሐቅን ያማከለው ብለህ ካሰብክ ይሄ ችግር የለውም።
_
①.أخرجه ابن عبد البر في جامع بيان العلم (2/927) وإسناده صحيح، وانظر ፡ المسودة (ص518-519).
__

📕ምንጭ ፦ በ2002 ሐሙስ ሐሙስ አብነት ከነበረው መርከዝ የተቀዳ
✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን የሕያ   @ Ibn yahya Ahmed
📆ሸዕባን 16/1442ሂ. # መጋቢት 20/2013 # March 29/2021
➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦ /channel/ibnyahya777
✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/ibnyahy7

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

◼️ደርስ ቁ.29

🔻በኡስታዝ አቡየሕያ አብዱልዋሲዕ የተቀራውን የ "መጃሊሱ ሸህሪ-ረመዷን" ኪታብ ሙሉ ደርስ ዳውንሎድ ለማድረግ
👇👇
/channel/derses7/962

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️የኳስ አንዱ ችግር ..

🔻እግር-ኳስ አንዱ ችግሩ የደጋፊዎችን አዕምሮ ማሳቱ ነው። ቡድኔ አሸነፈ ብለው በደስታ መረበሽ ፤ ተሸነፈም ብለው ህዝቡን ሰላም መንሳት ፣ ንብረት ማውደም.. ወላጆችን ማስቸገር .. እረ ስንቱ! ወጣቱሆይ. አሏህን ፍራ

@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️ዳግማዊ የሉጥ ህዝቦች ስራ

🔻የሉጥ ህዝቦችን ተግባር ካልሰራን የሚሉ ሰዎች ከመብዛታቸው የተነሳ አሏህ በኛ ላይ መሬትን አለመገልበጡ ጌታችን ምነኛ ኣዛኝ እና ታጋሽ መሆኑን እንረዳለን!!

@ibnyahya7

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️የዘካተልፊጥር ፈታዋ ሊንኮች

🔻በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ አደም የተሰጡ የዘካተል ፊጥር ፈትዋዎችን በቀላሉ በዩቲዩብ እና በቴሌግራም ለማዳመጥ ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ።
°
🔻ፈታዋ 1.
የዘካተልፊጥር አወጣጥ እንዴት ነው? ግዴታ የሚሆነውስ በማን ላይ ነው?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4877
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/0O53UmqajcQ
°
🔻ፈታዋ 2.
ዘካተልፊጥርን በብር ማውጣት ይቻላልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4883
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/No2g9w820n8
°
🔻ፈታዋ 3.
ዘካተልፊጥርን ከፆምንበት አከባቢ ውጭ ማውጣት ይቻላልን? የሚወጡ እህሎችስ?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4886
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/_fpK_5NyM8c
°
🔻ፈታዋ 4.
ዘካተልፊጥራችንን እንዲሰጡልን ብራችንን ወደሌላ ሀገር መላክ እንዴት ይታያል? በዚህ ስራ ላይ ለተሰማሩ ጠቃሚ ምክር ተዳሶበታል።
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4890
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/08wBfgJitpA
°
🔻ፈታዋ 5.
የዘካተል ፊጥር መስጫ ጊዜ መቼ ነው? ለማውጣት ውክልና የተቀበለ ሰው ከሌላ ብር ላይ ማውጣት እንዴት ይታያል?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4893
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/xmFB3TMqNcM
°
🔻ፈታዋ 6.
ዘካተልፊጥርን ማውጣት ካልተመቸን ቤተሰቦቻችን ቢያወጡልን ይቻላልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4898
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/GPV_dditp6o
°
🔻ፈታዋ 7.
አንድ ሰው ሳይወክከል ለሌላ ሰው ዘካተልፊጥርን ማውጣት ይችላልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4903
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/BWd1sedsCU4
°
🔻ፈታዋ 8.
ያለሱ እውቅና ዘካተልፊጥር የወጣለት ሰው ድጋሜ ማውጣት አለበትን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4908
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/5QFFNF6b9Vg
°
🔻ፈታዋ 9.
ቤተሰብ ውስጥ ዘካተልፊጥር ማውጣት የማን ግዴታ ነው?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4915
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/LPv4acHkWyA
°
🔻ፈታዋ 10.
ከራሴ ገንዘብ የቤተሰቦቼን ዘካተልፊጥር ማውጣት እችላለሁን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4918
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/h-gUQ77TbxA
°
🔻ፈታዋ 11.
ሺርክ ለሚሰሩ ቤተሰቦቻችን ዘካተልፊጥር ማውጣት ይቻላልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4924
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/x-fuiNdEao4
°
🔻ፈታዋ 12.
በስጦታ ብር ዘካተልፊጥር ማውጣት ይበቃልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4927
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/bFTgF9ZFlVw
°
🔻ፈታዋ 13.
ዘካተልፊጥራችንን ሶላት የማይሰግድ ሰው ቢያወጣልን ይቻላልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4930
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/4StgcVsmO8s
°
🔻ፈታዋ 14.
የወንድሜን እና የእህቴን ዘካተልፊጥር ማውጣት እችላለሁን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4933
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/iBSyHad6RUg
°
🔻ፈታዋ 15.
ዘካተልፊጥር የሚሰጥጠው ለማን ነው?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4936
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/MEUFvII9__k
°
🔻ፈታዋ 16.
ዘካተልፊጥርን ለቤተሰቦች(ለእናት ፣ አባት እና ልጆች) መስጠት ይቻላልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4939
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/5MQTasTn78o
°
🔻ፈታዋ 17.
ዘካተልፊጥርን ለአጎት እና ለአክስት ልጅ መስጠት ይቻላልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4942
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/XLnlRB_zjC0
°
🔻ፈታዋ 18.
ዘካተልፊጥርን ለእህትና ለወንድም መስጠት ይቻላልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4945
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/EpN5BMxgxxI
°
🔻ፈታዋ 19.
ባለማወቅ የብዙ አመት ዘካተልፊጥር ያላወጣ ሰው ምን ማድረግ አለበት?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4948
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/vbB8WQnZn9U
°
🔻ፈታዋ 20.
ዘካተልፊጥርን ከዒድ በፊት መስጠት ያልቻለ ሰው ከዒድ በኋላ ቢሰጥ ያብቃቃውልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4951
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/deK2ih25FPE
_
✍ጥንቅር ፡ አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን የሕያ / Ibn Yahya Ahmed
📆(እሮብ ረመዷን 27/1441ሂ. # ግንቦት 12/2012 # May 20/2020.)
__
©ዲን መመካከር ነው - الدين النصيحة
📣ጆይን ፦ /channel/ibnyahya7
✅ላይክ ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya7777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️የለይለተል ቀድር ዱዓ

🔻በነዚህ በረመዷን የመጨረሻዎቹ 10ለሊቶች ላይ ለይለተል ቀድር ስለሚከጀል ይህን ነብዩ -ﷺ- ለአዒሻ -ረዲየሏሁዓንሃ - ያስተማሯትን እና በሶሒሕ የሐዲስ መዛግብት ላይ የተዘገበውን ዱዓ ማድረግን እናብዛ ፦

{ اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌّ تُحِبُّ الْعَفْوَ فَاعْفُ عَنِّى }
በአማርኛ ሲነበብ ፡ "አልሏሁመ ኢንነከ ዐፉውዉን ቱሒብቡል ዐፍወ ፈዕፉ-ዓንኒ"
°
ትርጉሙም ፡ ´´አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅርታንም ትወዳለህና ይቅር በለኝ።´´
➖➖➖➖➖➖➖➖
📣/channel/ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️ዘካተል ፊጥር.Pdf

🔻ከሸይኽ ኢብኑዑሰይሚን "መጃሊሱ ሸህሪ ረመዷን" ኪታብ እና ከሸይኽ ኢልያስ አሕመድ "ዘካተልፊጥር" ከሚለው ሙሐደራ የተወሰደ.
✍Ibn Yahya Ahmed (ረመዷን 27/1441ሂ.)
___
/channel/ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

👆👆
#ፆማችንን_ያስፈጥራሉን? 1⃣3⃣ (የመጨረሻው)
13.ከግሳት ጋር የሚወጣውን ምግብ አፍ ሳይደርስ በፊት መዋጥ እንዴት ይታያል?
🔻"በሚያገሳ እና አየር ከጨጓራው በሚወጣ ጊዜ ከምግብ ወይም ከውሃ ትንሽ ነገር ሊወጣው ይችላል። እናም አፉ ጋር ሳይደርስ በፊት ቢውጠው ምንም ነገር የለበትም። "
_______________________
👤ሼይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አልዑሰይሚን
📕ምንጭ ፦ ["መጅሙዓል ፈታዋ"(19/232)]
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣ጆይን ፦ /channel/ibnyahya7
✅ላይክ ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️ተራዊሕ እና ተሀጁድ ላይ አንዘናጋ

🔻በረመዷን የሌሊት ሶላትን መስገድ ትልቅ የሆነ ትሩፋት አለው።  ነብዩ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ የረመዷንን ወር በአላህ አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አገኛለው ብሎ በመስገድ የቆመ ሰው በፊት ያሳለፈው ወንጀሎች ይማሩለታል ] (ሙተፈቁን ዓለይሂ)
°
🔻የረመዷንን ወር መቆም የመጀመሪያውን ሌሊትም የመጨረሻውንም ሌሊት ያካትታል። በመሆኑም ተራዊሕን መስገድ ረመዷንን ከመቆም ውስጥ ነው። ስለዚህም እነዚህን በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች ማሳለፍ የለብንም።
__
📣/channel/ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

ለቴሌግራም ቻናሌ ተከታታዮች እንኳን አሏህ ለ1442ሂ.የረመዷን ወር ፆም በሰላም አደረሰን። አሏህ ከሚጠቀሙት ባሮች ያድርገን
ረመዷን ሙባረክ!!
@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

የኮሮና ክትባት ፆምን አያጠፋም!

♻️በአሁን ወቅት በብዛት ከሚጠየቁ ጥያቄዎች መካከል የኮሮና ክትባት ፆምን ያጠፋል ወይስ አያጠፋም የሚለው ነው።

ትክክለኛው የዑለማዎች ምልከታ የኮሮና ክትባት ፆምን አያበላሽም የሚል ነው። ይህ ክትባት ምግብም ሆነ መጠጥ ባለመሆኑና እንዲሁም በምግብና መጠጥ ምልከታ ወይም ትርጓሜ የሚስተናገድበት ሁኔታ ባለመኖሩ ፆምን አያጠፋም። እንደውም ይህ ክትባት እንደ ማንኛውም የህክምና መርፌ የሚቆጠር ነው።

ምግብን የማይተኩ የህክምና መርፌዎች ደግሞ በአብዛኛው የዘመናችን የኢስላም ሊቃውንት ስምምነት መሰረት ፆምን አያበላሹም የሚል ነው።


➡️ከፕሮፌሰር ሰዓድ አል' ኸሥላን የቲውተር ገፅ የወስድኩት!


/channel/abdurezaq27

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

#አጫጭር_የረመዷን_ፈትዋዎች 1⃣1⃣

📋#ሶላት_ሳያሰግዱ_እና_ሳይፆሙ_በረመዷን_ዝሙት_መፈፀም

☪ከዛዱልመዓድ ፈታዋ ቁ.39 ላይ የ4ኛው ጥያቄ ምላሽ.

🏴ጥያቄ ፡

4⃣.ሶላት አልሰግድም , ፆምም አልፆምም ነበር ፤ በረመዷን በቀኑ ክፍለ-ጊዜ ሁለት ጊዜ ዚና ሰርቻለሁኝ ፤ አሁን ዲኑን አውቄያለሁኝ ፤ ላለፈው ወንጀሌ ምን ማድረግ አለብኝ? 

🏳መልስ ፡
°
🔻#እያንዳንዱ_ሙስሊም_ኢስላም_ማለት_ስም_ብቻ_እንዳልሆነ_ሊያውቅ_ይገባዋል። ዲኔን ሳላውቅ ነው ዝሙት የሰራሁት አይባልም። ዝሙት ቆሻሻ ተግባር እንደሆነ , ነውር እንደሆነ ማንኛውም ህሊና ያለው ፣ የትኛውም አይነት ኃይማኖት ያለው ሰው በሙሉ ያውቃል። ለማንኛውም ከልቡ ተፀፅቶ ተውበት ያደረገን ሰው ሁሉ "ሸርጡን"/(መስፈርቱን) ካሟላ አላህ ይምራል። ስለዚህ "መነደም" , መፀፀት ፣ ለምን አደረግኩኝ ማለት ፣ እራስን መውቀስ ፣ ሁለተኛ እንዲህ ዓይነት ነገር አላደርግም ብሎ ለአላህ ቃል መግባት ፣ በብዛት "ኢስቲግፋር" ማድረግ ያስፈልጋል።
°
🔻ወደዚህ ዓይነት መጥፎ ስራ የሚወስዱ ጓደኞች ካሉ ከመጥፎ ሰው መራቅ ፤ አካባቢው መጥፎ ከሆነ አካባቢ መቀየር ፤ ሃገሩም መጥፎ ከሆነ ሙሉ በሙሉ ሀገሩንም መልቀቅ ነው። ብልግና የተስፋፋባቸው ሃገሮች ላይ ከግራ , ከቀኝ , ጧት , ማታ ሓራምን የሚያይ ሰው የዲን ጥንካሬ ከሌለው ፣ ባለትዳር ካልሆነ ፣ ረመዷን ነው ከረመዷን ውጭ ለሱ "ሓጃውም"/(ጉዳዩም) አይደለም።
°
🔻የተከበረው የረመዷን ወር ላይ ሓራም ፊልም አይቼ የዘር ፈሳሽ ወጣኝ እያሉ ስለፆማቸው የሚጠይቁ ሰዎች አሉ። እንደዚሁ ደግሞ ማታ ላይ ዝሙት ሰራሁ ብለው የሚጠይቁ አሉ። ከሴት ጋር እየቀለድኩኝ , እየተላፋሁኝ ሓራም ላይ ወደቅኩኝ ወይም  የዘር ፈሳሽ ወጣኝ የሚሉ አሉ ፤ ይሄ የቀልብ መድረቅ ምልክት ነው።
°
🔻#ረመዷን_ላይ_አላህን_ያልፈራ , #ረመዷን_ላይ_ወንጀል_ያልተወ_መቼ_ነው_ወንጀል #የሚተወው? ረመዷን ላይ አላህ ያልማረዉ መቼ ነው የአላህን ምህረት የሚያገኘው?  አላህ - ተባረከ ወተዓላ - የጀነት በሮች ከፍቶ ፣ የጀሀነም በሮችን ዘጋግቶ "ኸይር"/(መልካም ነገር) ፈላጊ ሆይ! ና ፤ "ሸር"/(መጥፎ ነገር) ፈላጊ ሆይ! ባለህበት ቁም እየተባለ(①) ኸይርን ለሚፈልጉ ሰዎች ብዙ እርዳታዎች እየተደረጉ በዛው በመጥፎ ስራው ላይ የሚዘወትር ሰው የቀልቡን መድረቅ እንደውም የቀልቡን መሞት ሊያውቅና አላህ ንፁሕ ቀልብ እንዲሰጠው ዱዓእ ሊያደርግ ያገባዋል።
°
🔻በጥቅሉ ጥያቄውን በተመለከተ ሙሉ በሙሉ ሶላትን ከተዉ ከእስልምና መውጣትን ያስከትላልና ባለፈው ያልሰገድከውን ስገድ , ያልፆምከውን ፁም አይባልም(②)። ተውበት አድርጎ እንደገና እስልምናን አስተካክሎ መያዝና ለቀጣይ ሁሌ አላህን ምህረት ከመጠየቅ ጋር ሱንና ሶላትና ሱንና ፆሞችን ማብዛት ነው።
{ ..  ۚ إِنَّ الْحَسَنَاتِ يُذْهِبْنَ السَّيِّئَاتِ ۚ ذَٰلِكَ ذِكْرَىٰ لِلذَّاكِرِينَ .. }
ተብሏል።
[| .. መልካም ሥራዎች ኀጢአቶችን ያስወገድዳሉና፡፡ ይህ ለተገሳጮች ግሳጼ ነው፡፡ |] (ሁድ ፥ 114).
°
🔻መልካም ስራ ማብዛት ወንጀሎችን ጠራርጎ ያስወግዳል ተብሏልና ፈርድ ሶላትን በወቅቱ መስገድ ፣ ሱንና ሰላቶችን ከፊት ከኋላ ያሉትን ጠብቆ መስገድ ፣ የተቻለውን ያክል ዊትር , ለይል ሶላት መስገድ ፣ "አዱሓ" መስገድ ፣ ከጥሩ ሰዎች ጋር መዋል ፣  ቁርአንን ዘወትር መቅራት ፣ ያለፈውን ወንጀል እያስታወሱ ማዘንና ማልቀስ ፣ አላህን ምህረት መጠየቅ  ኢንሻ ኣሏሁ ተዓላ ያለፈውን የሚያሰርዝ ነው።
°
🔻#ነፍስያውን_መቆጣጠር_የማይችል_ሰው_የገዛ_ሚስቱን እንኳን በረመዷን በቀኑ ክፍለ-ጊዜ #መሳም_በዲኑ_አይፈቀድለትም። መላፋትና መቀራረብም አይፍፈቀድም ፆምን የሚያፈርስን ነገር የሚያስከትል ከሆነ። ከሌላ ሴትጋር ሲሆንና አላህ የከለከለው ዚና ሲሆን ያውም በረመዷን ምድር ነገሩ እጅግ በጣም ያስፈራል። አላህን ልንፈራ የወቅቱን ክብደት እና ደረጃውን ልናውቅ ይገባናል።
___
(①).(ኡስታዝ ለመጥቀስ የፈለገው በሱነን አት-ቲርሚዚይ ፥ 682 ላይ የተዘገበ እና / አልባኒ በሶሒሕ አትተርጊብ ወተርሂብ ፥ 998 ላይ ሶሒሕ ያሉትን ሐዲስ ነው።)
(②).(ከፋራው ያልተጠቀሰው ሶላት የማይሰግድ ሰው ይከፍራል በሚለው የዑለማዎች ንግግር መሰረት ተሂዶ መሆኑ ይታወቅ።).
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📕ምንጭ ፦ ከኡስታዝ አሕመድ አደም የዛዱልመዐድ ፈታዋ ቁ.39 ኦዲዮ ላይ የተወሰደ.
✍️ኡኽት አቡበክር
ኤዲት የተደረገው በአቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn Yahya Ahmed
📆እሁድ ረጀብ 24/1440ሂ. # መጋቢት 22/2011.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦/channel/ibnyahya7

✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ፦ https://www.facebook.com/ibnyahya777/

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

◼️መጅሊስ እና የሱና ሰዎች

🔻መጅሊሱ የሱና ሰዎች የሚኖሩት አንተ ገብተህ ተሳትፎ ስታደርግ ወይም የሚሳተፉ የሱና ሰዎችን ስትደግፍ ነው እንጂ ውጭ ሆነህ ሱኒዮች የሉበትም እያልክ በመለፍለፍ አይደለም!!

@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

🚩 بعض دعاة الذين يزعمون أنهم سلفيون مثلهم كمثل التكفريين 👇
● التكفريون يكفرون الناس بالشبه و اللوازم الباطلة
و هؤلاء يبدعون الناس بالشبه و اللوازم الباطلة كذلك

● التكفريون يهجرون الناس لأنهم كفار عندهم
و هؤلاء يهجرون الناس لأنهم مبتدعة عندهم

● التكفريون ممقوتون عند العامة و الخاصة قديما و حديثا
و هؤلاء كذلك ممقوتون عند العامة و الخاصة

● تجد التكفريين جهلة
و هؤلاء تجد دعاتهم جهلة بل الذين عندهم شيء من العلم لا يكاد يسمع لهم همس لأن جهالهم قد استولوا عليهم
● أينما حل فيه التكفريون تفرق الناس وقل الخير و كثر الجهل و القول على بلا علم
وكذلك أينما حلوا تجدهم يبحثون أسباب الخلاف ليختلفوا فتجدهم يفرقون بين الأسر و الخلان ويبررون على فعلهم المنكر بالقول على ما لا يعلمون بأن هذا هو الدين الحق الذي كان عليه السلف الصالح ويا سبحان الله!
● التكفريون يتشبثون بعلماء السنة كابن تيمية و الالباني و ابن باز لنصر باطلهم
وهؤلاء كذلك يتشبثون بعلماء السنة
وفي الحقيقة هو كما قيل
كل يدعي وصلا بليلى وليلى لا تقر لهم بذلك

● و تجد التكفريين عندهم غرور و الإعجاب بالنفس لأنهم اعتقدوا أنهم هم المسلمون و غيرهم الكافرون
وهؤلاء تجد منهم الغرور و الإعجاب بالنفس و ادعاء العلم
حتى بعصهم قال إنه يجوز له أن يفتي في النوازل
و بعضهم يقول لم يفته أي خير فلا يريد التناصح مع أحد يعارضه في بعض المواقف
و بعضعم يدعي أنه أهل للجرح و التعديل
و من الجرح و التعديل التكفير


قال الشيخ سليمان الرحيلي حفظه الله تعالى
أصبحوا بعض الشباب مثل التكفريين 👇
አልካቲብ ፡ ሙሐመድ ከሚሴ

https://youtu.be/vc_dpnAMEgU

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

👆👆
▪️ከዛሬው የመንሀጅ ነክ ጥያቄና መልሶች ክፍል 29 ላይ የወጡ ጥያቄዎች

🔻1.ዑለማዎች በተለያዩበት ነጥብ ላይ ሁልጊዜ ገር ገር የሆነውን ነገር እየተከታተሉ ቀላሉን መያዝ ይቻላልን?

ሀ.ይቻላል
ለ.አይቻልም
/channel/ibnyahya7/6683
°
🔻2.ሸሪዓችን ያግራራውን ነገር መከተል እንዴት ይታያል?

ሀ.ይወደዳል
ለ.ይጠላል
ሐ.አይቻልም
/channel/ibnyahya7/6684
°
🔻3.አንድ ሰው ጥረት አድርጎ ማስረጃን ካመዛዘነ በኋላ ወደሌላ ገር ወደሆነ የዑለማዎች አባባል አቋሙን ቢቀይር ይወቀሳልን?

ሀ.አው ይወቀሳል
ለ.አይወቀስም
/channel/ibnyahya7/6685
°
🔉ድምፁን ለማዳመጥ
⬇️⬇️
/channel/ibnyahya7/6681
____
©ዲን መመካከር ነው - الدين النصيحة
📆ሸዕባን 16/1442ሂ. # መጋቢት 20/2013
____
📣Join us ፦ /channel/ibnyahya7

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

29.የዑለማዎችን ማግራራት መከተል ..👇👇

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

#አጫጭር_የረመዷን_ፈትዋዎች 9⃣

📋#ባለማወቅ_ግብረ-#ስጋ_ግኑኝነት_መፈፀም

☪ከዛዱልመዓድ ፈታዋ ቁ.42 ላይ የ7ኛው ጥያቄ ምላሽ.

🏴ጥያቄ ፡

7⃣.እስልምናን የተቀበልኩት ያለፈው አመት ረመዷን ላይ ነው። ወድያውኑ እስልምናን እንደተቀበልኩኝ ስለዲኔ ህግጋት ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም ፤ ባለቤቴም አዲስ ነው እስልምናን የተቀበለው ፤ ሓራም መሆኑን ሳናውቅ በረመዷን በቀኑ ክፍለ-ጊዜ ግንኙነት አደረግን። አሁን ሓራም መሆኑን እና ከፋራም እንዳለበት አወቅኩኝ ፤ ባለማወቅ ያደረግነው እንዴት ይታያል?

🏳መልስ ፡
°
🔻በቀን ክፍለ-ጊዜ የግብረ-ስጋ ግንኙነት ማድረጉ ፆም እንደሚያበላሽም ፣ ከፋራም እንዳለበት ሁለቱንም የማታውቁ ከሆነ ፆማችሁ ትክክል ነው ፤ ምንም የለባችሁም። ነገር ግን ፆም እንደሚያበላሽ ታውቁ ከነበረና የማታውቁት ከፋራ እንዳለበት ብቻ ከነበረ ፤ ፆም እንደሚያበላሽ ካወቃችሁ ከፋራ እንዳለበት ብታውቁም ባታውቁም ግንኙነቱ ፆምን ያፈርሣል። ከፋራውም አይቀርላችሁም።
°
🔻ግንኙነት ፆም እንደሚያፈርስ በማወቃችሁ ብቻ ልትርቁት እና ልትጠነቀቁት ይገባ ነበር። ነገር ግን እንደሚያፈርስም ፣ ከፋራ እንዳለበትም ምንም ካላወቃችሁ { .. ربنا لاتؤاخذنآ إن نسينآ أو أخطأنا .. } ተብሏል። [| .. ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይ ብንስት አትያዘን ፤ አትቅጣን። .. |] (በቀራህ ፥ 286).
°
🔻በመሆኑም ፆማችሁ ትክክል ነው ፤ ቀዷእም የለባችሁም ፤ ከፋራም የለባችሁም። #ከፋራ_እንዳለበት_ሳይሆን_ፆም_እንደሚያፈርስ_ብቻ_እንኳ_የምታውቁ_ከሆነ_ከፋራ_ግዴታ_ይሆንባችኋል።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📕ምንጭ ፦ ከኡስታዝ አሕመድ አደም የዛዱልመዐድ ፈታዋ ቁ.42 ኦዲዮ ላይ የተወሰደ.
✍️ ፈትሒያ ቢንት ሸምሱ
ኤዲት የተደረገው በአቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn Yahya Ahmed
📆ሐሙስ ረጀብ 21/1440ሂ. # መጋቢት 19/2011.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ ፦ /channel/ibnyahya7

✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya777/

Читать полностью…
Subscribe to a channel