ibnyahya777 | Unsorted

Telegram-канал ibnyahya777 - Ibn Yahya Ahmed

2272

የተለያዩ ዲናዊ ፅሑፎችን ብቻ የማስተላልፍበት ቻናሌ ነው።

Subscribe to a channel

Ibn Yahya Ahmed

በቁርኣን አስታውስ 2.

{ هَلْ أَتَىٰ عَلَى الْإِنسَانِ حِينٌ مِّنَ الدَّهْرِ لَمْ يَكُن شَيْئًا مَّذْكُورًا }

[| በሰው ልጅ ላይ የሚታወስ ነገር ሳይሆን ከዘመናት የተወሰነ ጊዜ በእርግጥ አልፎበታል፡፡ |]
ሰረቱል-ኢንሳን ፥ 1

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

በቁርኣን አስታውስ .. 1
{ أَيْنَمَا تَكُونُوا يُدْرِككُّمُ الْمَوْتُ وَلَوْ كُنتُمْ فِي بُرُوجٍ مُّشَيَّدَةٍ ۗ }

«የትም ስፍራ ብትሆኑ በጠነከሩ ሕንጻዎች ውስጥ ብትሆኑም እንኳ ሞት ያገኛችኋል፡፡ ..

ሱረቱ-ኒሳእ ፥ 78

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

ዛሬ ከዐስር በኋላ ኢማሙ በማይክ ባለመናገሩ ምክንያት መደበኛው ዳዕዋ በኡስታዝ ጅብሪል አክመል አማካኝነት እየተካሄደ ይገኛል። አሏህ ካለ ከዚህ በኋላ በቀጣይ
ቀናት ምን እንደሚከሰት እየተከታተልን የምናደርሳችሁ ይሆናል።
@ibnyahya7

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

አንዋር መስጂድ ላይ ከዐስር በኋላ በረንዳው ላይ ይደረግ የነበረውን ዳዕዋ ለማስቆም በማይክ ኢማሞቹ ዳዕዋ እያደረጉ እያስተጓጎሉት ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት ረመዷን ሙሉ ሳይደረግ ቀርቷል።
@ibnyahya7

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

የዘንድሮ ረመዷን ፍጥነት ይለያል ... በቃ ልንሰናበተው ነው .. በጣም ያሳዝናል ..አሏህ ከተጠቃሚዎቹ ያድርገን .. ቀጣይ አመትም ያድርሰን
@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️የዘካተልፊጥር ፈታዋ ሊንኮች

🔻በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ አደም የተሰጡ የዘካተል ፊጥር ፈትዋዎችን በቀላሉ በዩቲዩብ እና በቴሌግራም ለማዳመጥ ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ።
°
🔻ፈታዋ 1.
የዘካተልፊጥር አወጣጥ እንዴት ነው? ግዴታ የሚሆነውስ በማን ላይ ነው?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4877
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/0O53UmqajcQ
°
🔻ፈታዋ 2.
ዘካተልፊጥርን በብር ማውጣት ይቻላልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4883
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/No2g9w820n8
°
🔻ፈታዋ 3.
ዘካተልፊጥርን ከፆምንበት አከባቢ ውጭ ማውጣት ይቻላልን? የሚወጡ እህሎችስ?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4886
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/_fpK_5NyM8c
°
🔻ፈታዋ 4.
ዘካተልፊጥራችንን እንዲሰጡልን ብራችንን ወደሌላ ሀገር መላክ እንዴት ይታያል? በዚህ ስራ ላይ ለተሰማሩ ጠቃሚ ምክር ተዳሶበታል።
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4890
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/08wBfgJitpA
°
🔻ፈታዋ 5.
የዘካተል ፊጥር መስጫ ጊዜ መቼ ነው? ለማውጣት ውክልና የተቀበለ ሰው ከሌላ ብር ላይ ማውጣት እንዴት ይታያል?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4893
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/xmFB3TMqNcM
°
🔻ፈታዋ 6.
ዘካተልፊጥርን ማውጣት ካልተመቸን ቤተሰቦቻችን ቢያወጡልን ይቻላልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4898
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/GPV_dditp6o
°
🔻ፈታዋ 7.
አንድ ሰው ሳይወክከል ለሌላ ሰው ዘካተልፊጥርን ማውጣት ይችላልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4903
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/BWd1sedsCU4
°
🔻ፈታዋ 8.
ያለሱ እውቅና ዘካተልፊጥር የወጣለት ሰው ድጋሜ ማውጣት አለበትን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4908
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/5QFFNF6b9Vg
°
🔻ፈታዋ 9.
ቤተሰብ ውስጥ ዘካተልፊጥር ማውጣት የማን ግዴታ ነው?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4915
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/LPv4acHkWyA
°
🔻ፈታዋ 10.
ከራሴ ገንዘብ የቤተሰቦቼን ዘካተልፊጥር ማውጣት እችላለሁን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4918
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/h-gUQ77TbxA
°
🔻ፈታዋ 11.
ሺርክ ለሚሰሩ ቤተሰቦቻችን ዘካተልፊጥር ማውጣት ይቻላልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4924
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/x-fuiNdEao4
°
🔻ፈታዋ 12.
በስጦታ ብር ዘካተልፊጥር ማውጣት ይበቃልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4927
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/bFTgF9ZFlVw
°
🔻ፈታዋ 13.
ዘካተልፊጥራችንን ሶላት የማይሰግድ ሰው ቢያወጣልን ይቻላልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4930
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/4StgcVsmO8s
°
🔻ፈታዋ 14.
የወንድሜን እና የእህቴን ዘካተልፊጥር ማውጣት እችላለሁን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4933
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/iBSyHad6RUg
°
🔻ፈታዋ 15.
ዘካተልፊጥር የሚሰጥጠው ለማን ነው?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4936
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/MEUFvII9__k
°
🔻ፈታዋ 16.
ዘካተልፊጥርን ለቤተሰቦች(ለእናት ፣ አባት እና ልጆች) መስጠት ይቻላልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4939
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/5MQTasTn78o
°
🔻ፈታዋ 17.
ዘካተልፊጥርን ለአጎት እና ለአክስት ልጅ መስጠት ይቻላልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4942
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/XLnlRB_zjC0
°
🔻ፈታዋ 18.
ዘካተልፊጥርን ለእህትና ለወንድም መስጠት ይቻላልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4945
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/EpN5BMxgxxI
°
🔻ፈታዋ 19.
ባለማወቅ የብዙ አመት ዘካተልፊጥር ያላወጣ ሰው ምን ማድረግ አለበት?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4948
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/vbB8WQnZn9U
°
🔻ፈታዋ 20.
ዘካተልፊጥርን ከዒድ በፊት መስጠት ያልቻለ ሰው ከዒድ በኋላ ቢሰጥ ያብቃቃውልን?
በቴሌግራም ፦ /channel/ibnyahya7/4951
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/deK2ih25FPE
_
✍ጥንቅር ፡ አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን የሕያ / Ibn Yahya Ahmed
📆(እሮብ ረመዷን 27/1441ሂ. # ግንቦት 12/2012 # May 20/2020.)
__
©ዲን መመካከር ነው - الدين النصيحة
📣ጆይን ፦ /channel/ibnyahya7
✅ላይክ ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya7777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

እውን የሚፈርሱት ቤቶች ህገ ወጥ ናቸውን?
~
ሰሞኑን እንደተለመደው አእላፍ ቤቶች እየፈረሱ እጅግ በርካታ ህዝብ ጎዳና ላይ እየወደቀ ነው። ምክንያቱ ሁሉም እንደሚያውቀው "ህገ ወጥ ናቸው" የሚል ነው። የሚገርመው ግን "በምንም መልኩ ህገ ወጥ ግንባታን ልንደግፍ አይገባም፣ ይፍረሱ!" የሚሉ ሙስሊሞች መኖራቸው ነው። በርግጥ ይህንን የሚሉት ሙስሊሞች ብቻ አይደሉም። ነገር ግን የሙስሊሞቹ በተለዬ ስለሚገርመኝ ምናልባት አላህን ከፈሩ ለማስታወስ ነው ይህቺን የጫጫርቁት።
በቅድሚያ መሬት የመንግስት ነው የሚለው ህግ ከሸሪዐ ውጭ እንኳ እንየው ቢባል ርህራሄ የሌለበት የጨካኞች ህግ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ 30 እና 40 ሚሊዮን በነበረ ጊዜ ህጉ ከመኖሩ ጋር በዚህ መልኩ በጥብቅ ስለማይያዝ ሰው መኖሪያ ጎጆ ለመቀለስ አይቸገርም ነበር። ዛሬ ቁጥሩ 120 ሚሊዮን ካለፈ በኋላ ግን መንግስት ጨከነ። ለዚህ ቀዳሚው ምክንያት ደግሞ መንግስት እሳት የላሰ የመሬት ነጋዴ መሆኑ ነው። ለገበሬው በካሬ ሜትር በ20 እና 30 ብር አስቦ "ካሳ" እየሰጠ እሱ ግን አንዲት ካሬ ሜትር 40 እና 50 ሺ ብር ይቸበችባል። ይህንን "ጨው" ስለቀመሰ ነው ምስኪን የኔ ብጤዎች ላይ የሚጨክነው። የዘር ፖለቲካው ውጥረት ደግሞ የራሱ ድርሻ አለው።
እንዳልኩት ለዚህ ጭካኔው ሽፋን የሚያደርገው ህጉን ነው። እንጂ እነዚህ ኑሮ ያጎበጣቸው ደካማ ዜጎችኮ የመንግስትን 100 እና 2ዐዐ እጥፍ ዋጋ አውጥተው ነው መሬቱን ከገበሬ የሚገዙት። ከዚያም በዚህ ሁሉ ነገር ዋጋው እሳት በሆነበት ጊዜ የቤት መስሪያውን ወጭ አውጥተው ይገነባሉ። ይህ አልበቃ ብሎ ለየ አካባቢው ደንቦችና የጎጥ ኃላፊዎች አእላፍ ብር ከከፈሉ በኋላ ነው የሚሰሩት። አንዳንዴ የበላው ሲዞር ሌላው እያስፈራራ ለተደጋጋሚ ብዝበዛ ይዳረጋሉ። የፈረሳ ወሬ በተናፈሰ ቁጥር እየሰበሰቡ ማብላት የተለመደ ነው። ይህም አይበቃም። ለልማት እየተባሉ በየ ጊዜው መዋጮ ይከፍላሉ።
ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ነው እንግዲህ "የመሬት ወረራ" የሚል አሸማቃቂ ቃል እየተጠቀሙ የዘመናት ጥሪታቸውን በላያቸው ላይ የሚንዱባቸው። እየወደመ ያለውን የአገር ሃብት እንተወው፣ በመሬት ንግድ ከሚገኘው ትርፍ ጋር የሚወዳደር ስላልሆነ ከቁብም የሚቆጥረው የለም። ግን ሁሉ ቢቀር ምናለ ለዚህ ኑሮ ላደቀቀው ህዝብ እንጥፍጣፊ እዝነት እንኳ ቢኖር። ይሄ ህዝብኮ እንኳን ቤት ፈርሶበት ቤት ይዞም መኖር አቅቶታል።
ልብ በሉ! ድሃው ጎጆ የሚቀልስበት አንድም ህጋዊ አማራጭ የለም። እና ይሄ ሁሉ ወገን የት ይውደቅ? ህግ የሚዘጋጀው ለሃገርና ለወገን ጥቅም ሲባል ነበር። በተቃራኒው አገርና ህዝብን የሚጎዳ ህግ ምኑ ነው እንደ ህግ የሚያስቆጥረው? እንዲህ አይነቱን መነሻ ይዘን ነው ወይ አቅመ ደካማ ወገኖች ላይ የምንፈርደው?
ህዝብኮ ጎዳና ላይ እየተሯሯጠ ካልሲ የሚቸረችረው ከደንብ አስከባሪ ጋር አባሮሽ መጫወት አምሮት አይደለም። ህዝብኮ ከመሰረተ ልማት ርቆ ጫካ መንጥሮ፣ ዳገት ደልድሎ ደሳሳ ጎጆ የሚቀልሰው ከመንግስት ጋር ትከሻ መለካካት ፈልጎ አይደለም። የልጆቹን ጉሮሮ የሚዘጋበት የ'ለት ጉርስ፣ አንገቱን የሚያሾልክበት ደሳሳ ጎጆ ለማግኘት አማራጭ ሁሉ ቢዘጋ፣ ኑሮ ቢጨልምበት ነው። በዚህ መልኩ ሁሉንም አማራጭ ከከረቸሙ በኋላ እግሩ በመራው በየብስ በባህር ተሰዶ ዐረብ አገር ወጥቶ እንዳይሰራ እነሱን ጭራቅ እያደረጉ መሳል ምን ትርጉም አለው? ከዚህ በኋላ በአራቱም አቅጣጫ ኬላዎችን እየዘጉ፣ "ህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች" እያሉ ሌላ ከባድ እርምጃ መውሰዱ ምን ትርጉም ይኖረዋል? እሺ ይሄ ህዝብ ምን ይሁን? የት ይውደቅ? በጣም ግራ የገባ ነገር እኮ ነው።
ለማንኛውም "እነሱ ለምን ህገ ወጥ ግንባታ ውስጥ ይገባሉ?" የምትሉ፣ ያላችሁበት ምቾት የወገንን ሰቆቃ እንዳታዩ የሸፈነባችሁ ወገኖቻችን ሆይ! እስኪ ለሰፊው ህዝብ የሚሆን "ህጋዊ" የምትሉትን አማራጭ ጠቁሙን። በርግጠኝነት ምርጫችሁ በረሃብ የሚያልቁ ወገኖችን "ለምን ኬክ አይበሉም?" ያለችዋ ሞልቃቃ አይነት ነው። ከዚህ በመለስ ያለው ያለ ጥርጥር ጭካኔ ወይም ጥላቻ ብቻ ነው።
በተረፈ ገበሬው የመሬቱ ባለ ሐቅ እስከሆነ ድረስ በገንዘቡ ከሱ መሬት የገዛ ሰው ከኢስላም አንፃር በመሬቱ ላይ ባለ ሙሉ ሐቅ ነው። የሸሪዐ ህግ የሚገዛችሁ ከሆነ (ሙስሊም ሆናችሁ ምስኪኖችን "ህገ ወጦች" ለምትሉ ማለቴ ነው) መሬቱን የገዙት በህጋዊ መንገድ ነው። የሸሪዐን ህግ መንግስት አይተገብረውም ማለት እኛ "ህገ ወጥ ነው" እንድንለው ይፈቀድልናል ማለት አይደለም። መንግስት ዝሙትን ይፈቅዳል። ይህን ህግ ተከትለን ለዝሙት ልንሟገት ነው? "በጋብቻ ላይ ጋብቻ" በሚል መነሻ ከአንድ በላይ ማግባትን ወንጀል የሚያደርጉ አካባቢዎች አሉ። ይህንን ህግ ተከትለን ሐራም ነው ልንል ነው? ለፖለቲካዊ አሰላለፎች ያለን ውግንና ገደል እየከተተን ስለሆነ ልንጠነቀቅና አላህን ልንፈራ ይገባል። ግፍ መናገር ከነገ በፊት ለዛሬ የሚተርፍ ዳፋ ያመጣል። የነገው ደግሞ የባሰ ነው። ዱንያ እንደሆነች የፈለገ ብትደላ መጠውለጓ አይቀርም። ከዚያ በኋላ ያለው ሃገር በደቦ ፍርድ የሚታለፍ አይደለም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 23/2015)
=
የቴሌግራም ቻናል :-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

ምናልባትም! ...

▪️ኢማም/አሰጋጅ ሱጁድ ላይ ሆኖ የደረሰ ሰው ሩኩዕ ስላመለጠው ይህን ሱጁድ ማድረጉ ከኢማሙ ጋር ረክዓህ እንደማግኘት ባይቆጠርለትም ነገር ግን ፈጥኖ ከሱ ጋር ሱጁድ ማድረግ ይገባዋል። ይህም ነቢዩﷺ "አንዳችሁ ለሰላት ሲመጣ ኢማሙ አንድ ሁኔታ ላይ ሆኖ ከደረሰ እርሱ የሚያደርገውን ያድርግ/ እንደሱ ይሁን" ስላሉ ሲሆን  በሌላ በኩል ደግሞ -ቲርሚዚይ ሱነናቸው ላይ እንዳሰፈሩት- ምናልባትም ከዚህ ሱጁድ ሲነሳ ወንጀሎቹ ተምረው/ተሰርዘውለት ሊነሳ ይችላል!።
ብዙ ሰዎች ኢማም ሩኩዕ ላይ ሆኖ ወይም ሩኩዕ ሊወርድ ሲል ከደረሱ ብቻ ነው ፈጥነው ሰላቱን ለመቀላቀል የሚቸኩሉት። ኢማሙ ከሱጁድ እስኪነሳ ድረስ ቆመው የሚጠብቁም ብዙ ሰዎች አሉ!
▪️ብልህና አዋቂ ሰው  በደረሰበት ሰዓት ኢማሙን ተቀላቅሎ እርሱ የሚያደርገውን ያደርጋል፤ በዚህም የነቢዩንﷺ ትዕዛዝ ይፈጽማል፤ ወንጀሉን የሚማርበትንም ዕድል ያሰፋል። ሞኝ ግን ቆሞ ይቀራል!

✍️ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
  8/8/1444ዓ.ሂ @ዛዱል መዓድ

💥 በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኜት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ
🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐/channel/ahmedadem
~
🌐/channel/zad_qirat
~~~~
🔗https://www.facebook.com/yenegew/
~~~~
📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

/channel/+dem1w7cApyY2ZTdk
ለመርከዙ ግንባታ የአቅማችንን እንወጣ

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️መስጂድ ውስጥ ደርስ ማዳመጥ...

🔻[[ መስጂድ ውስጥ ደርስ የሚያዳምጥ ሰው ልቡ በጣም ይረጋጋል። መስጂድ ውስጥ ከሚሰጡ ደርሶች የሚርቅ ሰው ሶላት ቢሰግድም እንኳን መረጋጋት ከሚባለው ነገር የተወሰነ ክፍል ከቀልቡ ላይ ይነሳበታል። ]] // ኡስታዝ አቡየሕያ አብዱልዋሲዕ. ኡሱሉልኢማን ደርስ ክፍል 20 ላይ የተወሰደ.

@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

#ቁሙ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنَّ المَوْتَ فَزَعٌ، فَإِذا رَأَيْتُمُ الجَنازَةَ فَقُومُوا.﴾

“ሞት ማለት ሊደነግጡለት የሚገባ ነገር ነውና ጀናዛ በተመለከታችሁ ግዜ ቁሙ።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 960

ጆይን፦ /channel/BuhariMuslimAmharic

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️ላንቺ ይሄ ብቻ ይበቃሻል

🔻ፊትሽን ሸፍነሽ በመሄድሽ በቀላሉ ከፆታዊ ትንኳሳ ትጠበቂያለሽ። እንደውሻ ማንንም የሚላከፈው ወንድ አንቺን ሲያይ አደቡን ይይዛል። ላንቺ ይሄ ብቻ ይበቃሻል!!

@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

📚በዛዱል መዓድ የትምህርት መድረክ
በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም " رسالة الحجاب"
" ሪሳለቱል-ሒጃብ "በሚል ርዕስ ተቀርቶ ያለቀው ጠቃሚና አስፈላጊ ትምህርት የድምፅ ፋይሎች ከታች ያገኙታል።
~~
📚የኪታቡን ፒዲኤፍ ለማግኜት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ
↕️ ↕️ ↕️ ↕️
🔎 https://goo.gl/wbkVRF
🔸 🔹 🔸 🔹 🔸

☄ሪሳለቱል ሒጃብ
ክ(1)
🔎/channel/zad_qirat/755

☄ሪሳለቱል ሒጃብ
ክ/2
🔎/channel/zad_qirat/756

☄ሪሳለቱል ሒጃብ
ክ/3
🔎/channel/zad_qirat/757

☄ሪሳለቱል ሒጃብ
ክ/4
🔎/channel/zad_qirat/758

☄ሪሳለቱል ሒጃብ
ክ/5
🔎/channel/zad_qirat/759

☄ሪሳለቱል ሒጃብ
ክ/6
🔎/channel/zad_qirat/760

☄ሪሳለቱል ሒጃብ
ክ/7
🔎/channel/zad_qirat/761

☄ሪሳለቱል ሒጃብ
ክ/8
🔎/channel/zad_qirat/762

☄ሪሳለቱል ሒጃብ
ክ/9
🔎/channel/zad_qirat/763

💥ሙሉውን ትምህርት ለማግኘት
ይህን ሊንክ ይጠቀሙ
⬇️ ⬇️ ⬇️ ⬇️

🔖 /channel/zad_qirat/765

💥 በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኜት ከታች ባለው የቴሌግራም ሊንክ ይቀላቀሉ
🔸🔹🔸🔹🔸🔹

🌐/channel/ahmedadem
📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️ሰዑዲን አሏህ ያስተካክላት

🔻ቢንሰልማን አሏህ ይምራውና የሰዑዲን ህዝብ የተለያዩ ሓራም ነገሮችን እየፈቀደ አየኽላቁ እንዲበላሽ እያደረገ እንደሚገኝ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
°
🔻በሌላ በኩል ደግሞ ሰሞኑን በኳሱ አለም ታዋቂ ተጫዋች ወደሳዑዲ አስመጥተዋል። ወጣቱን እንግዲ ማንን አርኣያ አድርጎ እንደሚከተል አዳጋች አይደለም። በአሏህ የካደን ሰው መውደድ እሱን እንደአርኣያ አድርጎ መከተል ከሙስሊም የማይጠበቅ ተግባር መሆኑ ለማንም አይሰውርም። አሏህ ሁላችንምም ይምራን.

@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

አልሐምዱሊላህ ስርጭታችን ተመልሷል። ስላደረጋችሁት ድጋፍ ሁሉ በአላህ ስም እናመሰግናለን። ጀዛኩሙላሁ ኸይረን

11555 ነሲሓ ቲቪ

📡 Satellite: Nilesat
Fequency: 11555 or 11554 
Polarization: Vertical
Fec. 5/6
Symbol rate: 27500

@nesihatv

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

🔻ቤት የሚፈርስባችሁ ወንድሞቻችን አሏህ ትእግስቱን ይስጣችሁ! ታገሱ ከትእግስት ውጭ መጥፎ ቃላት ጌታችሁ ላይ አትናገሩ! ከቤታችሁም ከፈጣሪያችሁም እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ! አሏህ ይርዳችሁ

@ibnyahya7

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

🔻ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ እየተንሰራፋ ካሉ ትልቅ ጥፋቶች ውስጥ ሙስሊም ባትለዳሮች ሓያእ በጎደለው መልኩ ተቃቅፈው ምናምን ፎቶ እየተነሱ መልቀቅ ነው። እረ ተው ተመከሩ!! ሙስሊሞችንም አታሰድቡ!!

@Ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

ረመዷን ካለቀ በኋላ ሸዋል ላይም ያቆማሉ ብለን ብንጠብቅ አላቆሙም። ይባስ ብሎ ዛሬ ምክትል ኢማሙ ዳዕዋውን ተንኩሷል። ከወራት በፊት ጣሃ ዳዕዋውን ለማስቆም በተደጋጋሚ መፎከሩም አይረሳም!!
@ibnyahya7

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

ይሄ ጉዳይ ቀስ በቀስ ኢኽላሳችንን ተፈታትኖ ወደ ፊት ሐጅና ዑምራ ለሚሄዱ ተጓዦችም መጥፎ ተምሳሌት እንዳይሆን ያሰጋል። ይታሰብበት‼

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

ያለ ብዙ ልፋት ወንጀሉን አላህ እንዲያራግፍለት የሚፈልግ ሰው ካለ፦  መላኢካዎች እርሱ ላይ የሚያደርጉት ዱዓእና ኢስቲግፋር ይበዛለት ዘንድ ሰላት ከሰገደ በኋላ መስገጃው ላይ በመፅናት እድሉን ይጠቀም ።”

[“ሸርሑ አልቡኻሪ”(2/95)]


/channel/sultan_54

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

ማሳሰቢያ
አስቀድሞ ዘካተል-ፊጥር መስጠት ለሚፈልግ ሰው ከዛሬ ጀምሮ ማውጣት ይቻላል።

ዛዱል-መዓድ
/channel/ahmedadem

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

ማስረገጥ ይቀድማል
~
በአጥፊ ላይ እርምት መስጠት የሚፈልግ ሰው አንዱ የሚጠበቅበት ነጥብ ማስረገጥ ነው። አጥፍቷል የተባለው አካል በተጨባጭ ጥፋቱ ተገኝቶበታል ወይ? እውነታው በተወራው መልኩ ነው ወይ? ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ማስረገጥ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው፣ ዋጂብ። አሉባልታ ላይ ተመስርቶ ፍረጃ ውስጥ መግባት፣ ነገር ማራገብ፣ ለመልስ መቸኮል፣ ... ከተቅዋ ጋር የሚሄድ አይደለም። የማይታመንን ሰው ወይም ታማኝ ይሁን አይሁን የማይታወቅን አካል ወሬ ይዞ ሰዎችን መወንጀል አይፈቀድም። እንዲህ አይነቱ ችኩል አካሄድ ራሳችንንም ጭምር ነው የሚጎዳው። ምናልባት የሆነ ጊዜ ከተረጋጋን ያኔ ለፀፀት ያጋልጠናል። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል:-
{یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوۤا۟ إِن جَاۤءَكُمۡ فَاسِقُۢ بِنَبَإࣲ فَتَبَیَّنُوۤا۟ أَن تُصِیبُوا۟ قَوۡمَۢا بِجَهَـٰلَةࣲ فَتُصۡبِحُوا۟ عَلَىٰ مَا فَعَلۡتُمۡ نَـٰدِمِینَ}
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ሆናችሁ ህዝቦችን እንዳትጎዱና በሰራችሁት ነገር ላይ ተፀፃቾች እንዳትሆኑ አረጋግጡ።" [ሑጁራት፡ 6]
በተለይ በዚህ ዘመን አሉባልታ የበዛበት፣ ማሰራጫ መንገዱም የሰፋበት ሁኔታ ስለ በዛ ይበልጥ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። የሰማነውን፣ ያነበብነውን ሁሉ ከማራገብ መጠንቀቅ አለብን። ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "አንድ ሰው የሰማውን ሁሉ ማውራቱ ከውሸት በኩል በቂው ነው"ይላሉ። [ሙስሊም፡ 5] ይሄ አብዛኞቻችን የተለከፍንበት በሽታ ነው።
ሳያጣሩ ወከባ የሚፈጥሩ ሰዎች በብዛት በጭፍን ቡድንተኝነት የሚጓዙ፣ ጥላቻና ቂም ያሰከራቸው፣ ስህተትን በጉጉት የሚጠብቁ ምቀኞች ናቸው። እርምት ለአላህ ተብሎ በኢኽላስ የሚፈፀም ዒባዳ እንጂ የጥላቻ ሱስ ማስተንፈሻ፣ ቂም ማወራረጃ፣ መበሻሸቂያ አይደለም። እርምት መስፈርቶቹን ባሟላ መልኩ በስርአት ሲፈፀም ዲን የሚጠበቅበት ጂ..ሃ..ድ ይሆናል። ያለ ልጓም በጥላቻ፣ በችኮላ ሲፈፀም ደግሞ ሙሲባ ይሆናል። ስለዚህ ሁሌም ቢሆን እርግጠኛ ባልሆንበት ጉዳይ ላይ እርምት ለመስጠት ከመሞከር መቆጠብ ይገባናል።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me/IbnuMunewor

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

#የረመዷን_ወር_መለያዎች 1️⃣

📌የረመዷን ወር ከእስልምና ማእዘናቶች እና እስልምና ከተገነባባቸው ትላልቅ መሰረቶች ውስጥ 4ኛው ማእዘን ነው። ማስረጃውም ነብዩ - ﷺ - ተከታዩን ለማለታቸው ነው ፦[ እስልምና በአምስት ነገሮች ላይ ተገንቦታል(ተመስርቷል) ፤ ከአላህ ውጭ በእውነት የሚገዙት አምላክ የለም ሙሐመድም የአላህ ባሪያ እና መልእክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር ; ሶላትን ማቋቋም ; ዘካን መስጠት ; ረመዷንን መፆም ; በይትን ሀጅ ማድረግ ] 📒(ቡኻሪ ፥ 8 / ሙስሊም ፥ 16)
°
📌የረመዷን ወርን መፆም አላህ ግዴታ ካደረጋቸው ነገራቶች ውስጥ አንዱ ግዴታ ለመሆኑ ማንም ሰው ከሚያውቀው ሀይማኖታዊ እውቀቶች ውስጥ እና ሙስሊሞችም በሙሉ የተስማሙበት ጉዳይ ነው።
____________________________
📕ምንጭ ፦ ሙሐመድ ዓሊ ፈርኩስ (ከአልከሊመት-አሸህሪያ ላይ የተቀነጨበ ቁጥር ፥ 12 ) ይፋዊ ኢንተርኔት ድረ-ገፅ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣ጆይን ያድርጉ፦ /channel/ibnyahya7
✅ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

🥢 "አሏህ ሆይ! የወንድማችንን ነውር አታሰማን" ይላሉ አንድ የመስጂድ ኢማም፤

ሁላችንም የወንድማችንን ነውር ላለመስማት መጣር ይኖርብናል። የወንድማችንን ነውር የሰማን ዕለት ለእርሱ ያለን ክብር፣ ቦታ እና አመለካከት ከመቀየሩም ባሻገር እርሱን እንድንጠላ ያደርገናል፤ መጠላላት፣ መመቀኛኘት እና ቂም መያያዝ ደግሞ የምዕመናን ባህሪ አይደለም። ዱንያ ላይ -ወንድሞቼ- ከነውር የፀዳ አንድም ፍጡር ሊኖር እንደማይችል ከማንም አይሰወርም።
"አንድም" የሚለው ቃል ይሰመርበት፤ ሸይኽም፣ ዓሊምም፣ ኡስታዝም፣ ኢማምም፣ የዲን ተማሪም፣ ተራው ማህበረሰብም፣ ትልቁም፣ ትንሹም ማንም ከነውር የፀዳ የለም።
من ذا الذي ترضى سجاياه كلها
                .......................... 
ይላል ገጣሚው! "ማነው እርሱ ሙሉ ተፈጥሯዊ ባህሪያቶቹ ሚወደድለት?" የለም።
من ذا الذي ما ساء قط
                ومن له الحسنى فقط
"ማን ነው ከነውር ሁሉ ፀድቶ እና መልካምነት ብቻ ኖሮት ተሳስቶ እማያውቅ ?" ይላል፤ የለም።

አብዘሃኛውን ጊዜ ደግሞ ግለሰብን በተመለከተ በሰዎች መሓከል ሚሰራጩ ወሬዎች ከእውነታው የራቁ ሆነው እናገኛቸዋል። ስለዚህ -ወንድሞች- በጣም ጥንቃቄ ያስፈልገዋል፤ ተራ ስለ ሰው ወሬ ይዞብን የመጣን ሰው እንዳናስተናግድ። ከህሜት፣ የሰውን ስም ከማጥፋት፣ ሰው እና ሰውን ከማጋጨት እና ከመሳሰሉት በጣም ልንርቅ ይገባል። የሙዕሚን መገለጫም አይደለም። ጨርሻለሁ!

✍ Abu Uwais Nafyad
/channel/AbuUweis

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

📢መልካም ዜና ለወላጆች

▫️ለልጅዎ ንፁህ ኢስላማዊ ተርቢያ ተርበዋል?

▫️የዚህ ዘመን ከባባድ የስብዕና ጥፋት ዘመቻዎች ማዕበል በልጆዎ ላይ ሰግተዋል?

▫️ልጆች የእረፍት ቀናቶችን በምን እንደሚያሳልፉ አሳስቦታል?

✅ነሲሓ ቲቪ ከመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ጋር በመተባበር በአይነቱ ልዩ የሆነ ታዳጊዎችን በመልካም ኢስላማዊ ተርቢያ የሚቀርፁ የአራት ቀን የታዳጊዎች ኮርስ አሰናድቶ ይጠብቆታል!

▪️ኮርሱ የሚሰጠው በሁለት ደረጃዎች ተከፍሎ ሲሆን፦

ደረጃ 1፡ ዕድሜያቸው ከ10-13

የሚሰጠው ትምህርት

1.የእምነት መሰረቶች (አቂዳ)
2.መልካም ስነምግባር(አኽላቅ)
3. ሶላት

ደረጃ 2፡ ዕድሜያቸው ከ14-18

የሚሰጠው ትምህርት

1.አቂዳ
2.የአላህ ትእዛዞች የምንፈጽምበት ስርአት
3.ማህበራዊ ሚዲያና ታዳጊዎች ጥፋትና ጉዳት እንዲሁም እርምትና ልማት

ጁሙኣ:- ሴቶችን ብቻ የተመለከተ ልዩ ሙሀደራ

🗓ቀን ከሰኞ ጥር 22 - 25፣2015

🕘ጠዋት ከ2:30-6:30

🕌 አድራሻ
ለወንዶችና ሴቶች፦ከጦር ሀይሎች ከፍ ብሎ 18 ማዞሪያ አካባቢ የሚገኘው መርከዝ ኢብኑ መስኡድ ዋና ቢሮ

ለሴቶች ብቻ፦ቤተል አደባባይ ንግድ ባንክ ያለበት ፎቅ ላይ

ለተጨማሪ መረጃ

18 ማዞሪያ
ለሴቶች 0904366666
ለወንዶች 0972757575

ቤተል(ለሴቶች)
093 048 4284  ይደውሉ

⚠️ወላጆች ልጆቻችሁን በመላክ ኃላፊነታችሁን ተወጡ!

መልእክቱን ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን❗️

/channel/darulhadis18

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️ሸይኽ ዐብዱሰላም አሏህ ይጠብቃቸው

🔻ሸይኽ ዐብዱሰላም ይባላሉ። ሸህሆጀሌ መስጂድ ለረዥም አመታት በኢማምነት አገልግለዋል። ዛሬ ሀሙስ በመሆኑ ፆማቸውን የሚያፈጥሩት እዛው ነው። ከመግሪብ በኋላ ምታዩት መልኩ ተከናንበው ዚክራቸውን ሲሉ ዒሻእ ይደርሳል። ይህ የዘወትር ተግባራቸው ነው። ለረዥም አመታት ከዐስር እስከ ዒሻእ እዛው መስጂድ ውስጥ የምትመለከቱት ስፍራ ላይ ቁጭ ብለው ያስቀራሉ ዒባዳ ያደርጋሉ። ባጭሩ መስጂዱ ቤታቸው ነው ማለት ይቻላል።

🔻ፊታቸው ሁለመናቸው ሲታይ አኺራን ከሚያስታውሱ የዘመናችን ዑለማዎች እና ዓቢዶች መካከል አንዱ ናቸው። ከሸይኽ ባሲጢም ጋር ያላቸው ወዳጅነት ይሄ ነው የሚባል አልነበረም .. ጁሙዓም በብዛት የሚሰግዱት እሳቸው ጋር ነበር .. ከእለታት አንድ ቀን ሸይኽ ባሲጥ ጋር እየቀራን በሩ ተንኳክቶ ሲከፈት ሸይኽ ዐብዱሰላም ነበሩ እና ሸይኽ ባሲጥ ከደርሳቸው ባንዴ ብድግ ብለው ዘለው የተቃቀፉትን ገጠመኝ አልሳረውም!! .. አሏህ ይርሃማቸውና ሸይኽ ባሲጢ ሲሞቱ በኑዛዜያቸው መሰረት ጀናዛቸው ላይ ያሰገዱባቸውም ሸይኽ ናቸው። አሏህ ይጠብቃቸው.

@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

▪️ስሙን ሲሰማ ራሱ ..

🔻ትክክለኛ ሙስሊም የሆነ ሰው እንኳን የካ*ፊ*ሮች በዓል ላይ መሳተፍ ይቅርና ስሙን ሲሰማ ራሱ ያንገሸግሸዋል።

@ibnyahya777

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

የምስራች ለኢልም ፈላጊዎች በሙሉ
ፈትህ አልመጂድ ሸርህ ኪታብ አተውሂድ በየሳምንቱ ጁሙዓ ከመግሪብ እስከ ዒሻ በዓይሻ መስጂድ ይቀራል በቴሌግራም ቻናል በቀጥታ ኦን ላይ መቅራት ለሚትፈልጉ መከታተል የምችሉ መሆኑን እንገልፃለን





/channel/ustaztofikrahmeto

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

አንርሳቸው በ... እናስታውሳቸው!

▪️ወዳጅ ወይም ዘመድ ሲሞት ለቀናት ወይም ለሳምንታት፣ ጥቂቶቻችንም ለወራት፣ በጣም ጥቂቶችም እንደራሳቸው የዲን ጥንካሬና እንዳጡት ሰው ቅርበትና ደረጃ ለውስን አመታት ዱዓና ኢስቲግፋር እናደርጋለን።ከዛ በኋላ ግን በንግግር መሃል የሟች ስም ሲነሳ እንኳ በስርዓቱ "አላህ ይዘንለት/ላት" ማለቱን እንረሳለን!

🔸እውነተኛ ወዳጅ መቼም ቢሆን ወዳጁን አይረሳም።በተለይ ወልደው ብዙ ዋጋ ከፍለው ያሳደጉን ወላጆቻችንን፣
ጌታችንና ዲናችንን እንድናውቅ ያደረጉን አስተማሪዎቻችንን፣በችግር ጊዜ ከጎናችን የቆሙ ባለውለታዎቻችንን፣ምንም ባያደርጉልን በዲን ገመድ የተሳሰርናቸው ሙስሊም ሙታንን፣በተለይ በተለይ ደግሞ ዱኒያ ላይ ዘርና ዘመድ ኖሮ ዱዓና ኢስቲጝፋር የሚያደርግላቸው፣ ሰደቃ የሚሰጥላቸው ወገን የሌላቸው (ሰለምቴ፣ በላጤነት የሞቱና መሰል ብቸኛዎችን) አስታውሰን ለሁሉም ዱዓእ፣ ኢስቲጝፋርና እንደ አቅማችን ሰደቃ ልናደርግ ይገባል።

▪️ዛሬ ቀድመውት ወደ ኣኺራህ ለሄዱ ወገኖቹ ኣኺራህ ላይ የሚጠቅማቸውን ነገር የሚያደርግ ሰው ነገ እሱም ተራው ደርሶ ወደ ማይቀረው ኣኺራህ ሲሄድ በህይወት ካሉ ሰዎች ውስጥ አስታውሶት እዛ የሚጠቅመውን ነገር የሚያደርግለትን ሰው አላህ ያቆምለታል።

🔅ከቀደምት መልካም አርዓያዎቻችን ውስጥ ሐጅ ሳያደርጉ ለሞቱ ሐጅ የሚያደርጉ፣ ዘር ለሌላቸው ሙታንም ነይተው ሰደቃ የሚያደርጉላቸው ነበሩ።

አሁን ባለንበት ዘመንም ሐጅ ሳያደርጉ ለሞቱ የዲን ሊቃውንት በየተራ ሐጅ የሚያደርጉ ደጋግ የአላህ ባሪያዎች አሉ!

▪️እኛ ግን ብዙዎቻችን አይደለም ለሌሎች ኣኺራህ አስበንና ተጨንቀን የሚጠቅማቸውን  ነገር ማድረግ ይቅርና የራሳችንን ኣኺራም ዘንግተናል!

🔸በህይወት እያለን ስንት ነገር የምናደርግላቸውና የማይሆነውን ሁሉ የምንሆንላቸው ሰዎች ስንሞት በምን ዓይነት ፍጥነት እንደሚረሱን ብናውቅ ኖሮ ለሰዎች አንድም ደቂቃ አልሰጥም ባልን ነበር!ስለዚህ የሰዎችን ዱኒያ እያሳመርን የራሳችንን ኣኺራህ አናበላሽ!ለሌሎች ብቻ እየተሯሯጥን እራሳችንን አንጣል።በህይወት እስካለን ድረስ ለነፍሳችንም ለሌሎችም የሚጠቅም ነገር እንስራ።

አላህ አርቆ የሚያስብ ልብ ይስጠን ዱኒያና ኣኺራችንም ያሳምርልን!
ለመላው ሙስሊም ሙታን ምህረትና እዝነቱን ይለግስልን ፣በተለይም ባስታወስናቸው ቁጥር ልባችን ለሚደነግጥና ዓይናቸው ለሚናፍቀን ወላጅ፣ ዘመድና ወዳጆቻችን በሙሉ!

✍️ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
  10/6/1444ዓ.ሂ
@ዛዱል መዓድ

ኣሚን- ኣሚን

🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸

🌐/channel/ahmedadem

📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ

Читать полностью…

Ibn Yahya Ahmed

እኔ በጣም ግርም የሚለኝ ነሲሓን የመሰለ ትልቅ ተቋም በገንዘብ ምክንያት ሲቋረጥ ነው። ሀብታሙን ነጋዴ አቀናጅቶ ለሳተላይትና መሰል ክፍያዎች ብር ማግኘት እንደዚ ከባድ ሆነ ማለት ነው?? ወላሂ በጣም ያሳዝናል!!

@ibnyahya777

Читать полностью…
Subscribe to a channel