#አጫጭር_የረመዷን_ፈትዋዎች 8⃣
📋#ያለምንም_ምክንያት_ረመዷንን_ያልፆመ_ሰው
☪ከዛዱልመዓድ ፈታዋ ቁ.42 ላይ የ6ኛው ጥያቄ ምላሽ
🏴ጥያቄ ፡
•
6⃣.ወንድሜ ክርስቲያን ነበረ ፤ ከሰለመ በኃላ ያለምንም ምክንያት 3 አመት በተከታታይ ረመዷንን አልፆመም። አሁን በዲኑ ጠንክሯል ፤ ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለው ፤ ቀዷእ ለማውጣት ኮንትራት ነው የሚሰራው , ስራ ይበዛበታል , ለመፆም ይከብደዋል ፤ ምን ማድረግ ነው ያለበት?
•
🏳መልስ ፡
°
🔻#ረመዷንን_መፆም_የእያንዳንዱ_ሙስሊም_ግዴታ #ነው። እስከሰለመ ድረስ ሶላት ሊሰግድ ፣ ረመዷንን ሊፆም ይገበዋል። ይህን ባለማድረጉ ሊፀፀት ፣ ጌታውን ምህረት ልጠይቅና ሊቶብት ይገባዋል። ሙስሊም ከመሆኑ ጋር , የፆምን ግዴታነት ከማወቁ ጋር ረመዷንን ያሳለፈ ሰው ቀዷእ ማውጣት ግዴታ ይሆንበታል ፤ ይህ የአብዛኃኞቹ "የጁሙሁረል ዑለማ" አስተያየት ነው።
°
🔻ጥቂት የሚባሉ የዲን ሊቃውንት በግዴለሽነት ካሳለፈው , ወቅቱ ካለፈ ቀዷእ አይወጣም ፤ ተመሳሳይ ሱንና ዒባዳ ነው እንጂ ማብዛት ያለበት ብለዋል። እያወቀ በግዴለሽነት ወቅቱን ካሳለፈው ኃላ ላይ ቀዷእ ማውጣት አይጠበቅበትም ፤ ቢያወጣም አይጥጠቀምም። ምክንያቱም እያወቀ ያለ "ኡዙር"/(ምክንያት) ወቅቱን ካሳለፈው ከዛ በኃላ ቢሰራውም ተቀባይነት የለውምና ብለዋል። #በላጩ_እንደምንም #ብሎ_ቀዷእ_ማውጣቱ_ነው ፤ አብዛኃኞቹ የዲን ሊቃውንቶች የመረጡት ጥንቃቄ የተሞላበትም አቋም የሆነው ቀዷእ ማውጣቱ ነው።
°
🔻ከላይ እንደተባለው ስራ በዝቶበት የሚከብደው ከሆነ በተከታታይ ቀዷእ አውጣ አይባልም ፤ እያረፈ ራሱን እየተንከባከበ ቀዷእ ማውጣት ይችላል። ኢማኑ ድክመት ኖሮበት ቀዷእ አውጣ ስለተባለ ከኢስላም ሊወጣ ይችላል የሚል ስጋት ካለ የተወሰኑ የዲን ሊቃውንቶች የተጠቀሙትን አስታያየት በመያዝ ነገሩን ማቅለልና ማግራራት የሚቻልበት ሁኔታ ይኖራል።
°
🔻ነገር ግን ጥያቄው ላይ እንደተባለው በዲኑ ላይ ጠንካራ ከሆነ ቀስ እያልክ መፆም ይጠበቅብሃል ብሎ ማስረዳት እና መንገር ይቻላል። ይህን የምንለው ያለፉትን አመታት ሶላትን ከመስገዱ ጋር ፣ በአላህ ከማመኑ ጋር ፣ የጾም ግዴታነት ከመቀበሉ ጋር መጾም ትቶ ከሆነ ነው። እንጂ ያለፉትን አመታት ሶላት ሙሉ በሙሉ ትቶ ከነበረ ያሳለፈው በምላሱ ሸሃዳ ቢይዘም ሙስሊም ስላልነበረ ቀዷእ ማውጣት ግዴታ አይሆንበትም።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📕ምንጭ ፦ ከኡስታዝ አሕመድ አደም የዛዱልመዐድ ፈታዋ ቁ.42 ኦዲዮ ላይ የተወሰደ.
✍️አደም
ኤዲት የተደረገው በአቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn Yahya Ahmed
📆እሮብ ረጀብ 20/1440ሂ. # መጋቢት 18/2011.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ ፦ /channel/ibnyahya7
✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya777/
#አጫጭር_የረመዷን_ፈትዋዎች 7⃣
#ያለሶላት_የተፆመ_ፆም
☪ከዛዱልመዓድ ፈታዋ ቁ.40 ላይ የ3ኛው ጥያቄ ምላሽ.
•
▪️ጥያቄ ፡
•
3⃣.እናቴ ከአራት አመት በፊት ረመዷንን ሶላት ሳትስግድ ትፆም ነበረ ፤ ሐይድ ላይም ሆና ትፆም ነበር ፤ ከአሁን በፊት በዚህ መልኩ የፆመችው እንዴት ይታያል? ምንስ ነው ማድረግ ያለብኝ? ቀዷእም ለማውጣት ልኩ አይታወቅም ፤ ቀዷእስ ማውጣት ግዴታ ከሆነባት ፆም ላይ እኔ ባግዛትና ብፆምላት እችላለሁ ወይ?
•
▪️መልስ ፡
°
🔻ይህ የተደረገው በ"ጅህልና"/(ባለማወቅ) ከሆነ በማለማወቋ "ኡዝር"/(ምክንያት) ሊስጣት ይችላል አላህ ዘንድ - ተባረክ ወትዓላ - ሳያቁ ባጠፉት ጥፋት አላህ አይቀጣም። እያወቁ በግዴለሽነት ከሆነ ሶላትን የተወችው ፣ እስከነሐይዷ ትፆም የነበረው ይሄ ከባድ ስህተት ነው , ጥፋት ነው , ወንጀል ነው።
°
🔻#ሆን_ብሎ_ሶላትን_መተው_ከእስልምና_ያወጣል። በመሆኑም ባለማወቅ ከሆነ ምንም ችግር የለባትም ፤ ካወቀችው ስዓት ጀምራ ፆምና ሶላቷን አስተካክላ መቀጠል ነው። እያወቀች በግዴለሽነት ከሆነ ስሌላት የተወችው ከዑለሞች አስተያየት "ራጂሑ"/(ከማስረጃ አንፃር አመዛኙ) ሶላትን ሆን ብሎ የተወ ሰው ይከፍራል ፤ ከእስልምና ይወጣል።
°
🔻#በኩፍር_ወቅት_ያሳለፉትን_ዒባዳ_ቀዷእ_ማውጣት_ግዴታ_አይደለም። ተውበት ከማድረግ ጋር , ሱንና ሶላት ፣ ሱንና ፆም ፣ "ኢስቲግፋር" ማብዛት ይጠበቅባታል። ሐይድ ላይ ሆኖ መፆም ከባድ ወንጀል ነው ፤ #ያለሶላት_መፆም_ዋጋ_የለውም። ቤተሰቦቻችን ልናስተምር ፤ ያወቅነውን ልናሳውቅ , ልንመክር ይገባናል።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📕ምንጭ ፦ ከኡስታዝ አሕመድ አደም የዛዱልመዐድ ፈታዋ ቁ.40 ኦዲዮ ላይ የተወሰደ.
✍️ ፈትሒያ ቢንት ሸምሱ
ኤዲት የተደረገው በአቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn Yahya Ahmed
📆ማክሰኞ ረጀብ 19/1440ሂ. # መጋቢት 17/2011.
➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ ፦ /channel/ibnyahya7
✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya777/
👆👆
▪️ከዛሬው የመንሀጅ ነክ ጥያቄና መልሶች ክፍል 28 ላይ የወጡ ጥያቄዎች
🔻1.አንድ ሰው ዐቂዳዬ ሰለፍይ ፣ መንሀጄ ኢኽዋን ፣ የአምልኮ ዘርፌ ደግሞ ሱፍይ ነኝ ማለቱ ትክክል ነውን?
ሀ.አው ትክክል ነው
ለ.ትክክል አይደለም
ሐ.በሁሉም ዘርፍ ሰለፎችን መከተል ይኖርብናል
መ.ለ እና ሐ
/channel/ibnyahya7/6653
°
🔻2.የሰለፎች አቋም ወይም የአህሉስ-ሱንናዎች ዐቂዳ ችግር አለበትን?
ሀ.አው አለበት
ለ.የለበትም
ሐ.እንደግለሰብ አህሉስ-ሱንናዎች ችግር ሊኖርባቸው ይችላል ፤ መንሀጁ ግን ችግር የለበትም
መ.ለ እና ሐ
/channel/ibnyahya7/6654
°
🔉ድምፁን ለማዳመጥ
⬇️⬇️
/channel/ibnyahya7/6651
____
©ዲን መመካከር ነው - الدين النصيحة
📆ሸዕባን 9/1442ሂ. # መጋቢት 13/2013
____
📣Join us ፦ /channel/ibnyahya7
▪️ማስታወቂያ
🔻በቀጣይ ደግሞ በአሏህ ፍቃድ በኡስታዝ አብዱልዋሲዕ የተቀራውን የ"መጃሊሱ ሸህሪ-ረመዷን" ኪታብ ሙሉ ደርስ እንለቃለን። ቻናላችንን ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ባረከሏሁፊኩም
/channel/derses7
#አጫጭር_የረመዷን_ፈትዋዎች 5⃣
📋#በፆም_ምትክ_ሰደቃ_ማብላት_የሚቻልበት_ሁኔታ
☪ከዛዱልመዓድ ፈታዋ ቁ.41 ላይ የ9ኛው ጥያቄ ምላሽ.
▪️ጥያቄ ፡
•
9⃣.ጓደኛዬ በጣም ያማታል ፤ መፆም አትችልም። 30 ሚስኪን በየቀኑ ለማብላት አይመቻትም። ስለሚያማትም ሚስኪን ያለበት ቦታ ሄዳ መፈለግ አልቻለችምና ለ30 ሚስኪን የሚሰጥጠውን ለአንድ ሚስኪን ብቻ መስጠት ይቻላል ወይ?
•
▪️መልስ ፡
•
🔻#በጣም_ያመመው_ሁሉ_በፆም_ፋንታ_ሚስኪን_አያበላም ፤ በፆም ፋንታ ሚስኪን የሚያበላው ህመሙ የማይለቅ የሆነ ሰው ነው። ከፍተኛ ደም ግፊት ፣ በእድሜ መግፋት ምክንያት ከልክ በላይ መድከምና ያለ ምግብ መዋል አለመቻል ፣ እነዚህና መሰል የሆኑ ቋሚ , የማይለቁ , ያገግማል , ይድናል ተብሎ ተስፋ የማይደረግ ህመም ከሆነ ነው። እንጂ በጊዜያዊነት ወይም #ታክሞ_ሊድን_የሚችል_በሽታ_ያለበት_ሰው #በፆም_ፋንታ_ማብላት_አይፈቀድለትም።
°
🔻በመሆኑም ይቺ እህት - አላህ ከህመሟ እንዲያድናት እንጠይቀዋለን - ህመሟ ቋሚ ነው , የመዳን ተስፋ የለውም ብለው የጤና ባለሙያዎች የነገሯት አይነት ህመም ከሆነ ለእያንዳንዱን ቀን ኣንድ ኣንድ ሚስኪን ማብላት ትችላለች። ለእያንዳንዱ ቀን ኣንድ ኣንድ ሚስኪን ነው መሆን ያለበት እንጂ አንድን ሚስኪን 30 ቀን ማብላት ወይም #ለአንድ_ሚስኪን_የሰላሳውን_ቀን_መስጠት_አይቻልም።
°
🔻ባለችበት አካባቢ ሚስኪን ከሌለ ሌላ ሃገር ያሉ ዘመዶቿን , ቤተሰቦቿን አናግራ ለ30 ሚስኪን እንዲያበሉላት ማድረግ ትችላለች። ለ30 ሚስኪን ማከፋፈሉን በተመለከተ በረመዷን በእያንዳንዱ ቀን ኣንድ ኣንድ ሚስኪን ማብላትም ይቻላል ፤ አዘግይቶ ሰላሳውንም በአንድ ቀን ረመዷን ሲያልቅ መጨረሻ ላይ ማብላትም ይቻላል። #ሰላሳውንም_አስቀድሞ_ረመዷን_ሳያልቅ_ግን_ማብላት_አይቻልም።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📕ምንጭ ፦ ከኡስታዝ አሕመድ አደም የዛዱልመዐድ ፈታዋ ቁ.41 ኦዲዮ ላይ የተወሰደ.
✍️ ኡሙሙሐመድ
ኤዲት የተደረገው በአቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn Yahya Ahmed
📆እሁድ ረጀብ 17/1440ሂ. # መጋቢት 15/2011.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦/channel/ibnyahya7
✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ ፦ https://www.facebook.com/ibnyahya777/
◼️ደርስ ቁ.28
🔻በሸይኽ ሙሐመድ ዐረብ የተቀራውን የ"ኢርሻድ" ኪታብ ሙሉ ደርስ ዳውንሎድ ለማድረግ
👇👇
/channel/derses7/923
🔻ለዚህ ነው ቅድም ሁለት አይነት ርእሶች አሉ ብዬ የከፋፈልኩላችሁ ፤ ግን በሁሉም ርእሶች ላይ ኡዝር እንሰጠጥ ብሎ ተቃቅፎ ተሻሽቶ መሄዱ አያዋጣንም አላህ ዘንድም ዱንያም ላይ ማለት ነው ፤ መፍትሄም አይደለም, ለሚፈለግበት አላማ ግብ የሚያደርስ አይደለም, አላህ ዘንድም የሚያዋጣ አይሆንም። እርማት የግድ ነው #መተራረም_የግድ_ነው እውነትን የበላይ ማድረግ ማለት ነው። ለአሏህ ብሎ መውደድ ለአላህ ብሎ መጥላት ፤ #ግን_ይሄ_ሁሉ_ቅድም_እንዳልኩት_ሚዛናዊነትን_እና_ፍትሀዊነትን_የተላበሰ_ሊሆን_ይገባል_ማለት_ነው። ይሄ ርእስ ሰፊ ነው ቢሆንም ግን ኢንሻአላህ ካለን ሰአት አንፃር በዚህ ላይ እንብቃቃለን።
_______
(①).(ቲርሚዚይ ፥ 2180 ፤ አሕመድ ፥ 5/218 ፤ ኢብን አቢሸይባህ ፥ 15/101)
(②).(አት-ተውባህ ፥ 25)
(③).(አልአዕራፍ ፥ 138)
(④).(አልአዕራፍ ፥ 139-140)
__________
📕ምንጭ ፦ ኢስላማዊ ወንድማማችነት ከሚለው የኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ የድምፅ ፋይል የተወሰደ (በ2002 አ.ል የተቀዳ)
✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn yahya Ahmed
📆በዙልሒጃህ 29/1439ሂ ተፅፎ ሰኞ በረጀብ 24/1442ሂ. # የካቲት 29/2013 # March 8/2021.ማስተካከያ የተደረገበት
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦ /channel/ibnyahya777
✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/ibnyahy7
°
🔻ጉዞ ላይ ነው ሙስሊም ፤ ዳዕዋም ሲያደርግ የተለያዩ ነገሮችንም ሲያደርግ ፤ ካልሆነ ከጎን እየጎተተ የሚያስቸግረውን ጥሎት ነው የሚጓዘው። (ምን ማለት ነው) ይሄ አይነት ርእሶች ላይ አልፈልግም ምናምን ያለውን ጥሎት ነው የሚጓዘው። #ካፊር_አይለውም ኩፍራ ካልሰራ ወይም ሺርክ ካልሰራ በስተቀር ፤ እሱም ደግሞ በግለሰባዊ ደረጃ የሚሰጡ ብይኖች የሚያስፈልጓቸው መስፈርቶች ሊኖሩ ይችላሉ።
°
🔻#ሁለተኛው ፦ #ቁርአናዊ_እና_ሐዲሳዊ_መረጃዎች_ለሁሉም_ዓሊም_ግልፅ_የማይሆኑበት_ደረጃ_ላይ_ከሆነ አሏህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - በጥበቡ አንዳንድ ጊዜ ዑለማዎች እርስ በእርስ እንዲበላለጡ ጥረት እንዲያደርጉ ሁሉንም ነገር ፍንትው ያለ ግልፅ መመሪያ አያደርገውም። ያ ከሆነ ፤ ብሎም ደግሞ #ከዚህ_በፊት_የነበሩት_አበይት_ትውልዶች_የተስማሙበት_ካልሆነ በዚህ ርእስ ላይ የአንዳቸውን አቋም ቢመርጥ ተወጋዥ አይሆንም። ይሄን አይነት አቋም መርጦ እንኳን እኛ ሌላ አይነት አቋም ኖሮን ወንድማማችነታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ችግር የለውም። እንደፊቅህ መሳኢሎች ብዙ የፊቅህ ርእሶች ላይ ይህ ነገር ሱና ነው? ወይስ ዋጂብ ነው? ፤ ዑለማዎች የተለያየ አመለካከት ይኖራቸዋል። ያም ከመሆኑ ጋራ አንድ ላይ ተሳስረው ይጓዙ ነበር።
°
🔻#ሁለቱን_መለየት_የቻለ_ሰው_በዚህ_አይነት_ርእሶች ላይ ምንም አይነት ውዥንብሮች አይረቱት ይሆናል በአላህ ፍቃድ። #ሁለቱን_የቀላቀለ_ሰው_ግን የቅድሙን አይነት መርሆ ሲያርገበግብ ታዩታላችሁ። በተስማማንበት እንስማማ ባልተስማማንበት ደግሞ.. ምን ማለት ነው ባልተስማማንበት? ማንኛውም ነገር ማለት ነው። ይሄኛው ሙሽሪክ ነው ፤ እኔ የማመልከው ዐብዱልቃድር ጄይላኒን ነው ይላል ፤ ወይም ሼይኸና ሑሴንን ነው ፤ አልያም ደግሞ እከሌን ነው ፤ ወይም ያኛውን ነው የማመልከው ወይም እሳቸው ቢሞቱም ይጎዳሉ ይጠቅማሉ ይላል ፤ አይ አንተ አመለካከትህ ነው ችግር የለውም ፤ እንደው ብትተወው ብዬ ምናልባት ልመክረው እችል ይሆናል ፤ አይመክሩም ማለት እኮ አይደለም እንዲህ የሚሉ ሰዎች ፤ ሊመክሩ ይችሉ ይሆናል ግን እምቢ ሲላቸው በዛው ነው በቃ ችግር የለውም።
°
🔻ልክ እንደምን ማለት ነው ፤ "የኢጅቲሀድ መስአላ" ላይ ማለት ነው .. ሱጁድ ለማድረግ ከላይ ስትወርዱ እጅ ብታስቀድሙ ይሻላል ብላችሁ እኔ ፤ ባታስቀድሙም የተወሰኑ ዑለማዎች የመረጡት ስለሆነ እንደውም የብዙሀኑ አባባል ነው ችግር የለውም ፤ እንደዛ ነው አመለከካከታቸውም ስልታቸውም እንደዛ ነው ማለት ነው እነሱ። እምቢ ካለ ችግር የለውም አብረው ነው የሚጓዙት። በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ እንደምትሰሟቸው ስምምነቶች ማለት ነው።
°
🔻ወይም ደግሞ አሏህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - የሚገቡትን ባህሪያት እና ስሞችን እንደፈለገ የሚቆለምም እና የሚያጣምም ሰውም ግድ የለም ወንድማማች ነን ብለው ተሳፍሮ አብረን ጥረት እናድርግ። በዚህ መልኩ አሰስ ገሰሱ ይሰባሰባል ለሆነ አላማ ብለው ማለት ነው። ሱብሓነ ረቢ(ይላል ኡስታዝ ኢልያስ በመገረም) ምን ለማድረግ? ኢስላምን የበላይ ለማድረግ ፤ ኢስላምንማ የበላይ ማድረግ ሳይሆን የበታች ማድረግ ነው። ምክንያቱም የአሏህ እርዳታ እኮ የሚታደለው ለሙእሚኖች ነው የአሏህን ህግ ላከበሩት ነው።
°
🔻የተለያየ የቢድዓ አመለካከት የሚያራምዱ ሰዎችን በሰልፍ ውስጥ ሰግስጎ መጓዝ አደጋ ነው። ይህንን ሰለፎች ስለሚያውቁ ዑመር ኢብኑ ዐብዱልዓዚዝ ለምሳሌ ምን ይላል ፦ | لا تغزو مع القدرية فإنهم لا ينصرون | ፡ |" ከቀደሪያዎች ጋራ ጂሀድ እንዳትወጡ የእናንተ ሰፍ ውስጥ ገብተው ፤ ለምን? የአላህን እርዳታ ያስቀርባቹኋል በፍፁም ይላል። "|
°
🔻አው! ግልፅ የሆነ ነገር በድሮ ጊዜ ሙናፊቆች ወጥተው አልነበር እንዴ? ልቱልኝ ይሆናል ለምሳሌ በረሱል - ﷺ - "ጀይሽ"/(ጦር) ውስጥ ፤ እና እነሱ ሙናፊቆች ናቸው ሲጀመር ሙስሊም ነን ብለው ነው የሚወጡት ደብቀውት ማለት ነው ፤ አንተ የተደበቀው አይመለከትህም ውስጥ ያለው አይመለከትህም ማለት ነው ፤ ምንድነው የምታምነው? እውነትህን ነው ወይስ ውሸትህን ነው? ይፈተሽ ቤቱ ምን አይነት ኪታብ ነው ያለው ፤ አያገባህም። ግን ሳትጠይቀው | ويأتيك بالأخبار من لم تزود | እንደተባለው ይናገራል ወይ ሌላ ሰው ይነግርሃል ስለእሱ። እንደዚህ እንደዚህ ነው .. ጭራሽ ከመናገርም አልፎ አቋሙን በተለያዩ አጋጣሚዎች ያሰራጫል ወደዚህ ጥመት ይጣራል። ይሄ አደጋ ነው ፤ አይንህ እያየ ጆሮህ እየሰማ ዝምአትልም።
°
🔻ምን ምሳሌ ልስጣችሁ ለዚ .. #ኢስላምን_የበላይ_ለማድረግ_ነው_አይደል! አላማው ፤ ረሱል - ﷺ - በሑነይን ዘመቻ ጉዞ ላይ እያሉ በአቢዋቂዲኒ ለይሲ ቲርሚዚይ እና ሌሎችም እንደዘገቡት (①) የሑነይን ዘመቻ እንግዲህ መካን ከተቆጣጠሩ በኋላ የነበረ ዘመቻ ነው ፤ 8ኛው አመት ላይ ማለት ነው። መካን እንደተቆጠጠሩ የአሏህ መልእክተኛ 10,000ሺ ጦር ይዘው ነበር መካን የተቆጣጠሩት ይሄ በኢስላም ታሪክ የመጀመሪያው ነበር ይሄን ያክል ቁጥር ሲሰባሰብ ፤ ከዛ ከመካ አዳዲስ ሙስሊሞች እና አንዳንድ ሙስሊም ያልሆኑ ያው ከነሱ ጋር እንቀላቀላለን ብለው ገቡ ዝምብለው ማለት ነው ፤ ቀጥታ ተሳታፊ ሆነው አይደለም። ምናልባት የጦር መሳሪያ ሰጡ ምናምን ... ይሄ ዝምብሎ እንደመግዛት ነው የሚቆጠረው ፤ (ከዛ) 12000ሺ ሆኑ።
°
🔻ከዚህ ጦርነት ሁለት ትምህርት መውሰድ እንችላለን ፤ ብዙ ትምህርት ይወሰዳል ግን ሁለት ነገር ነው ማጉላት የምፈልገው። 12000ሺ ሲሆኑ ፦
°
1⃣ኛ.የተወሰኑት በተለይ አዳዲሶች ዛሬማ | لن نغلب اليوم من قلة | አሉ። ብንሸነፍ ከቁጥር ማነስ አንሸነፍም አሉ ፤ ይሄ ሁሉ ቁጥር ኖሮን እንዴት እንሸነፋለን የሚል ስሜት ልባቸው ውስጥ አደረ ፤ የተወሰኑት ተናገሩ በአንደበታቸው ፤ የተወሰኑት ሶሓቦች ሲሰሙ አልወደዱትም ይሄን ነገር። ምን ነበር ውጤቱ መጀመሪያ ላይ? ልክ እንደደረሱ ለካ እነዚያ የተለያዩ ቦታዎች (ላይ) መሽገው ገደል ውስጥ እንዲገቡ አድርገዋቸዋል ፤ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የቀስት መአት አወረዱባቸው ፤ ሁሉም ሸሸ 12000ሺ አልነበር የቀረው በጣት የሚቆጠር ሰው ብቻ ነበረ ረሱል - ﷺ - እና አጠገብ ማለት ነው ፤ ሁሉም ሸሸ።
°
🔻እሳቸው ወደፊት መሄድ ጀመሩ የአላህ መልእክተኛ በመሸሽ ፋንታ ማለት ነው ፤ ሶሐቦች ተጨነቁ ፤ ከዛ በኋላ ረሱል - ﷺ - አጠገባቸው ያሉትን እንደ ዓባስ ያሉትን ድምፁ ከፍ ያለ ሰው ተጣራ .. "ያ አህለ በይዐተስ-ሰሙራ" ፣ "ያአህል ከዛ ወከዛ" እያለ ሁሉም ሲጠሩ ያንን ቃል ኪዳን ሲያስታውሱ ተመለሱ ፤ ፈረሱ አልቆም ሲለው እንኳን ፈረሱን ጥሎ መመለስ ጀመረ ፤ ሁሉም ተሰባሰበ። መጀመሪያም ከባድ ውድቀት ነበረ የገጠማቸው ከዛ አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - ደግሞ እርዳታውን ለገሳቸው።
°
#አጫጭር_የረመዷን_ፈትዋዎች 3⃣
#ይድናል_ተብሎ_ተስፋ_የማይጣልበት_ህመም
❇️ከዛዱልመዓድ ፈታዋ ቁ.39 ላይ የ2ኛው ጥያቄ ምላሽ.
•
▪️ጥያቄ ፡
•
2⃣.እናቴ የጨጓራ በሽተኛ ናት ፤ ረመዷንን መጾም አትችልም። ምን ማድረግ ነው ያለባት?
•
▪️መልስ ፡
°
🔻በሽታው እጅግ በጣም የከፋ ከሆነ እና መቼም አይለቅም , አትድንም , መፆም አትችልም የሚል ታማኝ ዶክተር መረጃ ሰጥቷት ክሆነ ለእያንዳንዱ ቀን አንዳንድ ሚስኪን ታበላለች። ታክሞ የሚድን ከሆነ እና የሚጠፋ ከሆነ ግን እስኪሻላት ጠብቃ ስትድን ያፈጠረቻቸው ቀኖችን ቀዷእ ታወጣለች ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📕ምንጭ ፦ ከኡስታዝ አሕመድ አደም የዛዱልመዐድ ፈታዋ ቁ.39 ኦዲዮ ላይ የተወሰደ.
✍️አደም
ኤዲት የተደረገው በአቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn Yahya Ahmed
📆ጁሙዓ ረጀብ 15/1440ሂ. # መጋቢት 13/2011.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦/channel/ibnyahya7
✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ ፦ https://www.facebook.com/ibnyahya777/
#አጫጭር_የረመዷን_ፈትዋዎች 2⃣
#በእርግዝና_ምክንያት_ያፈጠረች_ሴት_እና_ቀዷእ_ሳይወጡ_ቀጣዩ_ረመዷን_ቢመጣ
❇️ከዛዱልመዓድ ፈታዋ ቁ.37 ላይ የ6ኛው ጥያቄ ምላሽ.
▪️ጥያቄ ፡
•
6⃣.ያለፈው ረመዷን ነፍሰ-ጡር ስለነበርኩኝ 22 ቀን አልፆምኩም ነበር ፤ አሁን ቀዷእ እያወጣሁኝ ነው። ቀዷእ ብቻ ነው ማውጣት ያለብኝ ወይስ ተጨማሪ ከፋራ አለብኝ? አሁን እያመመኝ ነው ፣ ልጅም እያጠባሁ ነው ያለፈውን ቀዷእ ሳልከፍል ቀጣዩን ረመዷን ስጨርስ ቀዷውን ማውጣት እችላለሁ ወይ? በብርስ ከፋራ መክፈል ይቻላልን?
•
▪️መልስ ፡
•
🔻#ሸሪዓው_በሚያፀድቀው_በበቂ_ምክንያት_ረመዷን_ላይ_የበላ_ሰው_ሁዋላ_ላይ "#የሚወጅብበት"/(ግዴታ የሚሆንበት) #ቀዷእ_ብቻ_ማውጣት_ነው። ቀዷእም ከፋራም ግዴታ የሚሆነው በግብረ-ስጋ ግንኙነት ምክንያት ፆሙን ያፈረሰ ሰው ላይ ነው። ነፍሰ-ጡር የነበረች ፣ ታጠባ የነበረች እናት ረመዷን ላይ ከበላች ሁዋላ ላይ ግዴታ የሚሆንባት ከፋራ ብቻ ነው።
°
🔻ያለ በቂ ምክንያት ቀዷዋን ሳታወጣ ሌላ ረመዷን የገባባት እንደሆነ ከቀዷእ በተጨማሪ ከፋራ ማውጣት አለባት እንደ ቅጣት ያሉ የተወሰኑ ዑለሞች አሉ። ነገር ግን ይሄን የአላህ ባሮች ላይ ግዴታ ለማድረግ በቂ የሚባል ማስረጃ ባለመኖሩ ተውበት ከማድረግና አላህን ምህረት ከመጠየቅ ጋር ቀዷእ ብቻ ማውጣቱ በቂ ነው።
°
🔻#ቀጣዩን_ረመዷን_ስጨርስ_ቀዷውን_ማውጣት እችላለሁ ወይ? የሚለው ነጥብ መሃል ላይ መፆም የሚችሉበት ሁኔታ ሳይፈጠር ሌላኛው ረመዷን መጥቶ ከሆነ ፤ አልያ ደግሞ መሃል ላይ የነበረውን ጊዜ በህመም ከሆነ ያሳለፉት አሁንም መፆም የሚያስችል ጤና ላይ ካልሆኑ ከፊታችን ያለውን ረመዷን ፁመዉ ካጠናቀቁ ቡኋላ ቀዷእ ማውጣት ይቻላል ።
°
🔻ያለፈውን ፆም በብር ከፋራ መክፈል አይቻልም። ለሞት ሰው አልያ ደግሞ በሕይወት ቢኖርም የማይለቅ ከባድ በሽታ ኖሮበት መቼም መፆም አይችልም ለሚባል ሰው ነው ምግብ በማብላት ከፋራ የሚወጣለት። ከፋራው ምግብ ነው የተባለለት ነገር ላይ ደግሞ ገንዘብ አይሰጥም ፤ ምግብ እና እህል ነው የሚሰጠው።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📕ምንጭ ፦ ከኡስታዝ አሕመድ አደም የዛዱልመዓድ ፈታዋ ቁ.37 ኦዲዮ ላይ የተወሰደ.
✍️ኡኽት አቡበክር
ኤዲት የተደረገው በአቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn Yahya Ahmed
📆ሐሙስ ረጀብ 14/1439ሂ. # መጋቢት 12/2011.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦/channel/ibnyahya7
✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ ፦ https://www.facebook.com/ibnyahya777/
الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات
ዛሬ የወሎ ከተሞች የዒልም እና የዳዕዋ ቅፍለት ተልእኮውን ጨርሶ በመመለስ ላይ ይገኛል።
ይህ የዳዕዋ ቅፍለት በተለያዩ ከተሞችና የገጠር ከተሞች ዳዕዋ አድርጓል። በተጨማሪም በየከተሞቹ በሚገኙ ብዙ መሳጂዶች ዳዕዋ፣ አጭር ኮርስ እና ኹጥባ አድርጓል። በደሴ ከተማ ብቻ 10 መሳጂዶች ላይ ዳዕዋ፣ አጭር ኮርስ እና ኹጥባ አድርጓል። አልሀምዱሊላህ!! ዳእዋ የተደረገባቸው ከተሞች
ደሴ
ኮምቦልቻ
ገርባ
ደጋን
ኩታ በር
ቢስቲማ
ሰንበቴ
ሸዋ ሮቢት
ከሚሴ እና
ሀይቅ ናቸው።
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
☀️ሁዳ መልቲሚዲያ
ቴሌግራም 👇
t.me/huda4eth
ፌስቡክ👇
fb.com/huda4eth
ዩትዩብ👇
http://www.youtube.com/c/HudaMultimedia
ማስታወቂያ ለቢዝነስ አመራሮች
23ሺ subscriber ባለው የቴሌግራም ቻናላችን ላይ እንዲሁም 18ሺ እና 13ሺ ፎሎወር ባላቸው የፌስቡክ አካውንታችን ላይ ሐላል የቢዝነስ ስራዎቻችሁን ለማስተዋወቅ የምትፈልጉ t.me/ahmedibnyahya ላይ ወይም https://www.facebook.com/ahmed.ibnyahya
ማነጋገር የምትችሉ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።
/channel/ibnyahya7
ነሲሓ የዒልም ቅፍለት ኮርስ ቁ.5
ከጁምዓ መጋቢት 18/2013 – እሁድ መጋቢት 19/2013 ዓ.ል
በድሬዳዋና እና አካባቢዋ የሚካሄድ ልዩ የዒልም ፕሮግራም
√ ኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ
√ ኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ
√ ኡስታዝ ሱለይማን አብደላህ
√ ኡስታዝ ሙሀመድ ዓረቦ
√ ኡስታዝ ሻሚል ሙዘሚል
√ ኡስታዝ ተውፊቅ ራህመቶ
√ ኡስታዝ ጀማል ያሲን እና
በሌሎችም ኡስታዞች ትምህርት ይቀርባል
دورة قافلة النصيحة العلمية الخامسة
شعبان ١٤٤٢هے
مدينتي دريداوا وهرر - شرق إثيوبيا
T.me/merkezuna
የፆም ማብራሪያን መፅሐፍ ከአዲስ አበባ አትተውባ መክተባ በተጨማሪ በቤተል ተቅዋ መስጂድ ፊትለፊት ፣ በድሬዳዋ ከጁሙዓ እስከ እሁድ በሚቆየው የነሲሃ የኢልም ቅፍለት ጉዞ ላይ እና በቡታጅራ ከተማ በ0915666195 ላይ አሕመድ ብለው ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን። ሌሎች የክልል ከተማዎች ላይ ሲደርስ በአሏህ ፍቃድ የምናሳውቃችሁ ይሆናል። ብዛት ማከፋፈል የምትፈልጉ በቴሌግራም አድራሻችን @ahmedibnyahya ላይ ማነጋገር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
Читать полностью…▪️#መንሀጅ_ነክ_ጥያቄና_መልሶች 2️⃣8️⃣
➠ጥያቄ ፡
28.አንድ ሰው ዐቂዳዬ ሰለፍይ ፣ መንሀጄ ኢኽዋን ፣ የአምልኮ ዘርፌ ደግሞ ሱፍይ ማለቱ ትክክል ነውን?
➠መልስ ፡
🔻"መንሀጀ-ሰለፍ" ሰዎች በቃል ደረጃ የሚናገሩት ሳይሆን ሰለፎች ዘንድ የነበረው ትክክለኛው የአህሉስ-ሱንና አቋም ላይ ምንም አይነት ጉድለት የለም። እንደ-ግለሰብ አህሉስ-ሱንናዎች ጉድለት ሊኖርባቸው ይችላል። ግን እንደ-ኢጅማዕ (እንደ ሙሉ ስምምነታቸው) ወይም እንደ-አቋም ተብሎ በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ የሚነገረውን ንግግር ስንመለከት ምንም አይነት ጉድለት አያስተናግድም።
°
🔻እንደ-ግለሰብ ነብያቶች ሲቀሩ ማንም ጥቡቅ የለም። እናም ጉድለት ስለሌለው ወደሌሎች ቦታዎች መሄድ አያስፈልገውም ማለት ነው። የተሟላ መንሀጅ ነው። ቁርአን የተሟላ እንደሆነው ሁሉ የቁርአን ተከታዮችም ይህን የተሟላ ነገር ነው የሚከተሉት። ልክ አሏሁ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - { ۗ ۚ الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ } [| ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ |] እንዳለው ማለት ነው። (ማኢዳህ ፥ 3).
°
🔻ስለዚህ አንድ ሰው ሰለፎችን መከተል ከፈለገ በዐቂዳም ፣ በመንሀጅም ፣ በአካሄድም ፣ በሁሉም መስክ ላይ እነሱን መከተል ተፈላጊ ነው። በተለይ የዲን ርእስ ላይ ማለቴ ነው። እናም ይህ አባባል ከዚህ አንፃር ሲታይ እርስበርሱ የሚጋጭ መሆኑ ግልፅ ነው ማለት ነው።
__________
📕ምንጭ ፦ በ2003 ወይም 2004 አ.ል ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከነበረው ሙሐደራ ላይ የተወሰደ ጥያቄ
✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn yahya Ahmed
📆ሸዕባን 9/1442ሂ. # መጋቢት 13/2013 # March 22/2021
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦ /channel/ibnyahya777
✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/ibnyahy7
#አጫጭር_የረመዷን_ፈትዋዎች 6⃣
📋#ቀዷእ_ሳያወጡ_ቀጣዩ_ረመዷን_መጥቶ_ቢሞቱ
❇️ከዛዱልመዓድ ፈታዋ ቁ.67 ላይ የ5ኛው ጥያቄ ምላሽ
•
▪️ጥያቄ ፡
•
5⃣.አንድ አባት ካለፈው አመት ረመዷን በፊት በህመም (ምክንያት) አልፆመም ነበር ፤ ያለፈውን አመት ረመዷን ፆሟል ፤ ነገር ግን የቀድሞውን ቀዷእ ሳያወጡ በህመም ምክንያት ሞቱ። ቀዷእ ብቻ ነው ወይስ ከፋራም አለባቸው? ልጆቻቸው ማውጣት አለባቸው ወይ?
•
▪️መልስ ፡
°
🔻የቀድሞውን አመት ረመዷን በህመም ምክንያት ሳይፆሙ ቆይተው አስራአንዱን ወር ሙሉ በህመም አሳልፈው ፤ መኃል ላይ መፆም የሚችሉበትን ያክል ሳያገግሙ ቆይተው ቀጣዩ ረመዷን ሲመጣ ድነው ከሆነ ያ(ን) ረመዷን የፆሙት ፤ ከዚያ በፊት የነበረውን ረመዷን መፆም የሚችሉበት የጤና ሁኔታ ላይ ካልነበሩ ምንም የለባቸውም።#ነገር_ግን_መኃል_ላይ_ድነው_መፆም_ከመቻላቸው_ጋር_ሳይፆሙ ሌላኛው ረመዷን ገብቶ የቅርቡን ረመዷን ፁመው ከዚያ በፊት የነበረውን ሳይፆሙ #የሞቱ_እንደሆነ_ቀዷእ_ማውጣት_ግዴታ_ይሆናል።
°
🔻#ልጆቻቸው_ቀዷእ_ቢያወጡላቸው_የተሻለ_ነው ፤ ማውጣት የማይችሉ ከሆነ ለእያንዳንዱ ቀን ኣንድ ኣንድ ሚስኪን ማብላት ይችላሉ። አባትዬው ጥለው ከሞቱት ከራሳቸው ንብረት ወይም ገንዘብ ቢሆን የተሻለ ነው ፤ ካልሆነ (ግን) ልጆች እራሳቸው ከራሳቸው ገንዘብ "ነይተው" ማብላት ይችላሉ።
°
🔻ፆሙን ከመረጡ ማብላቱ ግዴታ አይደለም ፤ ነገር ግን በወቅቱ መፆም እየቻለ የዘገየ ሰው ከፆም በተመጨማሪ ምግብ ማብላት ያስፈልገዋል እንደ ቅጣት የሚሉ በርካታ ዑለማዎች አሉና ልጆች በፆም ከመክፈላቸው በተጨማሪ ከእያንዳንዱ ቀን ጋር ሚስኪን ቢያበሉ ፤ አልያ (ደግሞ) በነፍስ-ወከፍ የቻሉትን ያክል ሰደቃ ቢሰጡላቸው ፣ ምግብ ቢያበሉላቸው የተሻለ ነው።
°
🔻#ልጆቻቸው_አንፆምም_ካሉ_ማብላቱ_ዋጂብ_እና_ግዴታ ነው ፤ ከፆሙ ፆም ብቻ በቂ ነው። በርካታ ዑለማዎች ከፆም ጋር ማብላት ተገቢ ነው ስላሉ ከፆሙም ጋር አብረው ቢችሉ የተሻለ የሚሆንበት ሁኔታ ይኖራል። ሟች ከመሆናቸው አንፃር ሰደቃው በየትኛውም ሁኔታ ለሳቸው የሚጠቅም እና አስፈላጊ ነው።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📕ምንጭ ፦ ከኡስታዝ አሕመድ አደም የዛዱልመዐድ ፈታዋ ቁ.67 ኦዲዮ ላይ የተወሰደ.
✍️አደም
ኤዲት የተደረገው በአቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn Yahya Ahmed
📆ሰኞ ረጀብ 18/1440ሂ. # መጋቢት 16/2011.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦/channel/ibnyahya7
✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ ፦ https://www.facebook.com/ibnyahya777/
#አጫጭር_የረመዷን_ፈትዋዎች 4⃣
📋#በረመዷን_ባለማወቅ_ያልተፆሙ_ቀናቶች_የቀዷእ_አወጣጥ_ሁኔታ
❇️ከዛዱልመዓድ ፈታዋ ቁ.41 ላይ የ13ኛው ጥያቄ ምላሽ.
•
▪️ጥያቄ ፡
•
1⃣3⃣.ወንድሜ ያለፈው አመት ረመዷን ሙስሊም የሌለበት ሃገር ሄዶ 15 ቀን አልፆመም። አሁን በምን መልኩ ነው ቀዷእ ማውጣት ያለበት?
•
▪️መልስ ፡
°
🔻ሙስሊም የሌለበት ሃገር ሄዶ ብሎ መወሰን ይከብዳል። እያንዳንዱን ቤት አንኳኩቶ የጠየቀ ሰው እንጂ ይህ ሃገር ላይ ወይም እገሌ የሚባለው ሃገር ላይ ሙስሊም የለም አይባልም ፤ በሁሉም ሃገር ላይ የአላህ ባሮች ይኖራሉ። እንደዚሁ ደግሞ #መፆም_ያለንበት_ሃገር_ላይ_ሙስሊም_ከመኖር_ካለመኖር_ጋር_ግንኙነት_የለውም።
°
🔻የረመዷን ወር መግባቱን በየትኛውም መልኩ ካወቀ ለብቻውም ቢሆን መፆም ይወጅብበታል , ግዴታ ይሆንበታል። ፆም (እንደ) ሶላተል-ጀማዓ አይደለም ፤ ሁለት , ሶስት ሰው ከዛ በላይ ሆነው እንጂ አይፆምም አይባልም። ለአካለ መጠን የደረሰ ፣ ጤነኛ የሆነ ሰው ረመዷን መሆኑን ካወቀ መፆም ግዴታ ይሆንበታል።
°
🔻ይሄን ማድረግ እየቻለ ሙስሊም ሃገር አይደለም ያለሁት ብሎ #በመተዉ_ወንጀለኛ ነው ፤ መቶበት ይጠበቅበታል። ይህ ረመዷን እንዳለቀ ባለፈው አመት ረመዷን ያልፆማቸው 15 ቀናቶችን ቀዷእ ማውጣት ፣ አሏህን ምኅረት መጠየቅ ይጠበቅበታል።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📕ምንጭ ፦ ከኡስታዝ አሕመድ አደም የዛዱልመዐድ ፈታዋ ቁ.41 ኦዲዮ ላይ የተወሰደ.
✍️ ኡሙሙሐመድ
ኤዲት የተደረገው በአቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn Yahya Ahmed
📆ቅዳሜ ረጀብ 16/1440ሂ. # መጋቢት 14/2011.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦/channel/ibnyahya7
✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ ፦ https://www.facebook.com/ibnyahya777/
#ተውሒድ_ላይ_ከመጡ_ሐዲሶች 2⃣5⃣
🔻ከኢብኑዐባስ - ረዲየሏሁዐንሁማ - በተከታዩ የአሏሁ - ተዓላ - ንግግር አስመልክቶ ተይዞ እንደተወራው ፦ { وَقَالُوا لَا تَذَرُنَّ آلِهَتَكُمْ وَلَا تَذَرُنَّ وَدًّا وَلَا سُوَاعًا وَلَا يَغُوثَ وَيَعُوقَ وَنَسْرًا } [| አሉም «አምላኮቻችሁን አትተዉ፡፡ ወድንም፣ ሱዋዕንም፣ የጉሥንም፣ የዑቅንም ነስርንም አትተው፡፡ |] (ኑሕ ፥ 23). ይህን አለ ፡ እነዚህ ከኑሕ ህዝቦች ደጋግ የነበሩ ሰዎች ናቸው ፤ እነሱ በጠፉ ጊዜ ሸይጧን ወደህዝቦቻቸው እነሱ ሲቀመጡበት በነበረው የተቀረፁ የሆኑ ጣኦታትን ትከሉ ፤ በስማቸውም ሰይሙት ብሎ ነገራቸው ፤ እነሱም ሰሩ ግን አልተመለከም ነበር ፤ የተከሉት ሰዎች በጠፉ እና እውቀት በተነሳ ጊዜ ተመለከች። (ቡኻሪ ፥ 8/4920)
~~~~
📣ጆይን ፦ /channel/ibnyahya777
✅ላይክ ፦ https://m.facebook.com/ibnyahy7
🔻ምን ይላል ቁርአን ላይ ይሄን ሲጠቁም ፦ { .. ۙ وَيَوْمَ حُنَيْنٍ ۙ إِذْ أَعْجَبَتْكُمْ كَثْرَتُكُمْ فَلَمْ تُغْنِ عَنكُمْ شَيْئًا وَضَاقَتْ عَلَيْكُمُ الْأَرْضُ بِمَا رَحُبَتْ ثُمَّ وَلَّيْتُم مُّدْبِرِينَ } (②) የቁጥር ርእስ አይደለማ ፤ ቅድም ትልቁ አላማ ምን ነበር? ቁጥር ማበራከት ነዋ? ማለት አንድ ላይ እንሰባሰብና የሚለው አባባል ማለት ነው ፤ የፈለገ ጥፋት ቢያጠፋም እንሰባሰብ የሚለው አባባል ፤ አላማው ምንድን ነው? ቁጥር ማሰባሰብ ነው አይደለል? ብዛት ነው ፤ ብዛት ይፈይዳል? ብዛት ብቻውን ማለቴ ነው ፤ አንድ ሰበብ ሊሆን ይችላል የዱንያ ሰበብ ግን #ከብዛት_ይልቅ_የሚቀደመው_ጥራት_ነው።
°
🔻ምን አለ አሏህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - { ۙ إِذْ أَعْجَبَتْكُمْ كَثْرَتُكُمْ } [| ብዛታችሁ ባስደነቃችሁ ጊዜ |] ይላል ፣ { فَلَمْ تُغْنِ عَنكُمْ شَيْئًا } [| እናንተን ምንም ያህል አልፈየዳችሁም አልጠቀማችሁም |] ይላል ፤ { وَضَاقَتْ عَلَيْكُمُ الْأَرْضُ بِمَا رَحُبَتْ } [| ምድርን ከሰፊነቷ ጋራ ጠበበችባችሁ |] ይላል ፤ የዛን ቀን { ثُمَّ وَلَّيْتُم مُّدْبِرِينَ } [| ጀርባ ሰጥታችሁ ከዛ በኋላ አመለጣችሁ ሄዳችሁ |] ይላል ፤ { ثُمَّ أَنزَلَ اللَّهُ سَكِينَتَهُ عَلَىٰ رَسُولِهِ وَعَلَى الْمُؤْمِنِينَ } [| ከዛ በኋላ አሏህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - ደግሞ እርጋታውን ሰኪናውን በረሱል - ﷺ - ላይ እና በምእመናኖች ላይ አወረደ |] ፡ { وَأَنزَلَ جُنُودًا لَّمْ تَرَوْهَا } [| እናንተ የማታዩዋቸውን ሰራዊቶች አወረደ |] ፤ መላኢካዎች ወርደው ነበር የዝዛኔ ባልታየ መልኩ ማለት ነው። ይሄ አንድ ትምህርት ነው።
°
2⃣ኛው ፡ ከዚሁ ጦርነት የሚወሰደው ትምህርት በዚህ ጦርነት ታሪክ ላይ እየተጓዙ መልእክተኛው - ﷺ - ወደ ጦርነቱ አቡዋቂዲኒል-ለይሲ እንደሚያስተላልፍልን የተወሰኑት አዳዲሶቹ ምን አዩ ፤ እነዚያ ሙሽሪኮች አጋሪያን መሳሪያዎቻቸውን ዛፍ ላይ ያንጠለጥላሉ የሆነ ዛፍ ላይ(ሲድራህ). ለምን? በረካ ፈልገው መሳሪያዎቻችን ያ ዛፍ ላይ ካንጠለጠልን እርዳታን እናገኛለን ድልን እንጎናፀፋለን በሚል ግምት ማለት ነው። ይሄንን ሲያዩ ምን አሉ የተወሰኑት የአላህ መልእክተኛን ምን አሏቸው ፦ | اجعل لنا ذات أنواط كما لهم ذات أنواط | [ እኛም መሳሪያዎቻችንን የምናንጠለጥልበት አንድ ዛፍ አድርግልን እነሱ የሚያንጠለጥሉበት ዛፍ እንዳላቸው ሁሉ ] አሉ። ከባድ ጥያቄ ነው።
°
🔻መልእክተኛው ግን ቆይ እስኪ እነዚህን ሰዎች አሁን ወደጂሀድ እየሄድን ስለሆነ ሞራላቸውንም አልነካም ፤ ብሎም ደግሞ አንድነታችንን አንበታትንም በኋላ ምናልባት ቀስ ብዬ ድል ከተጎናፀፍን እና የበላይ ከሆንን በኋላ ነግራቸዋለሁ አሉ እንዴ? አይደለም! ምን አሉ ፦ [" ألله أكبر إنها السنن قلتم والذي نفسي بيده كما قالت بني إسرائيل لموسى اجعل لنا إلها كما لهم ألهه، قال إنكم قوم تجهلون "] ከዛ [ لتتبعن سنن من كان قبلكم ] አሉ መልእክተኛው። [" አሏሁ አክበር አሉ የአላህ መልእክተኛ ተቆጡ! ይሄማ መንገድ ነው አሉ ፤ ረሱል - ﷺ - ምን አሉ ፦ ከዚህ በፊት የነበሩ ሰዎች መንገድ ነው የድሮዎቹን ካፊሮች መንገድ ልትከተሉ ነው አሏቸው። አሁን ያላችሁት ንግግር ልክ በኑ ኢስራኢል የሙሳ ህዝቦች ለሙሳ እንደተናገሩት አይነት ንግግር ነው "] አሉ ፤ ምን አሉ እነሱ አሏህ ቁርአን ሱረቱል አዕራፍ ላይ ጠቅሶታል ፦ { وَجَاوَزْنَا بِبَنِي إِسْرَائِيلَ الْبَحْرَ فَأَتَوْا عَلَىٰ قَوْمٍ يَعْكُفُونَ عَلَىٰ أَصْنَامٍ لَّهُمْ ۚ قَالُوا يَا مُوسَى اجْعَل لَّنَا إِلَٰهًا كَمَا لَهُمْ آلِهَةٌ ۚ } (③)
°
🔻መንገድ ላይ ሲሄዱ ጣኦት የሚገዙ ሰዎችን አዩ ተቀምጠው ጣኦቶቻቸው አከባቢ የሚገዙ ፤ ታዲያ እነሱም እኮ አማልክት እንዳላቸው ሌላ አማልክት አድርግልን አሉ ፤ ለሙሳ እኮ ነው እንደዚህ የሚሏቸው .. አሏህን ትተው ሌላ አማልክት አድርግልን (አሉ) ደግሞ የሚገርመው ለሳቸው ጥያቄ ማቅረባቸው ነው። ያ ሁሉ ጭቅጭቅ, ያ ሁሉ ጥረት, ያ ሁሉ ጥሪ የነበረው ምን ነበር? ያንን የሙሳን ጥሪ ዋና አላማ እንደገና ረስተው ወይ ትተው ተመልሰው ታጥቦ ጭቃ እንደሚባለው ምን አሉ ፦ { اجْعَل لَّنَا إِلَٰهًا كَمَا لَهُمْ آلِهَةٌ ۚ } እነሱ አማልክት እንዳላቸው ለኛም ሌላ አማልክት አድርግልን።
°
{ قَالَ إِنَّكُمْ قَوْمٌ تَجْهَلُونَ * إِنَّ هَٰؤُلَاءِ مُتَبَّرٌ مَّا هُمْ فِيهِ وَبَاطِلٌ مَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ * قَالَ أَغَيْرَ اللَّهِ أَبْغِيكُمْ إِلَٰهًا وَهُوَ فَضَّلَكُمْ عَلَى الْعَالَمِينَ } (④)
( [| ... «እናንተ የምትሳሳቱ ህዝቦች ናችሁ» * «እነዚህ እነርሱ በውስጡ ያሉበት ነገር ጠፊ ነው፡፡ ይሰሩት የነበሩትም ብልሹ ነው» (አላቸው)፤ «ከአላህ ሌላ እርሱ ከዓለማት ያበለጣችሁ ሲሆን (የምትገዙት) አምላክን እፈልግላችኋለሁን» አለ፡፡ |] )
°
🔻ሙሳ ተቆጡዋቸው ልክ እንደዚሁ ረሱልም - ﷺ - ተቆጡዋቸው ሶሓቦችን። የት እየሄዱ ነው? ቦታውን አስተውሉ .. አው! #በዚህ_ርእስ_ላይማ_ምንም_አይነት_ድርድር_የለምና_ነው ፤ ምክንያቱም ድርድር ካለማ አላማው ምንድን ነው? ኢስላምን የበላይ ማድረግ ነው አይደለ? ታዲያ እዚህ ገና ሳትሄድ ሳትንቀሳቀስ በፊት ኢስላምን የበታች የሚያደርግ ነገር ሲፈጠር እርማቱ ከዚህ ሊጀምር አይገባም? ስለዚህ አሰስ ገሰሱን ይዞ ኢስላምን የበላይ አደርጋለሁ የሚለው ነገር አያስኬድም ፤ #መፍትሄም_አይደለም ፤ መፍትሄም ካለመሆኑ ባሻገር የድሮዎቹ ዑለማዎች ሙሉ ስምምነትን የጣሰ አዲስ የቢድዓ መርሆ ነው። አዲስ መሆኑ ብቻ ቢድዓ ያስብለዋል ማለት ነው ይሄን አባባል።
°
🔻ግን ቃሉ ላይ አይደለም የምንጠለጠለው ልብ በሉ! የነሱን ፍላጎት ስለምናቀው ነው ፤ እንጂ ይሄን አባባል አንዳንድ ዑለማዎች የሆነ ርእስ ላይ ሊጠቀሙበት ይችላሉ ፤ ያ ችግር የለውም። ምሳሌ ሼይኽ ዐብዱረሕማን አስ-ሰዕዲ "አልሙናዘራት አልፊቅሂያ" የምትል ትንሽዬ ኪታብ አለቻቸው በዚያ መግቢያ ላይ በዑለማች መካከል የተፈጠሩ በተለያዩ የፊቅህ ርእሶች ላይ "ራጂሕ"/(በላጭ አባባል) እና "መርጁሑን"/(ተበላጭ አባባል) በክርክር መልኩ ለማስቀመጥ ፈልገው ነው እና ይሄ አባባል ምነኛ ያማረ ነው ብለው የትኛውን አባባል ጠቀሱ? ^^በተስማማንበት ነገር እንስማማ ባልተስማማንበት ላይ ኡዝር እንሰጣጥ^^ አው በዚህ ርእስ ላይ ኡዝር እንሰጣጣለን።
°
▪️መንሀጅ ነክ ጥያቄና መልሶች 2️⃣7️⃣
➠ጥያቄ ፡
27.በተስማማንበት እንስማማ ባልተስማማንበት ደግሞ ምክንያት ተሰጣጥተን (ኡዝር ተሰጣጥተን) እንተላለፍ የሚለው አባባል ትክክል ነውን?
➠መልስ ፡
🔻"በተስማማንበት እንስማማ ባልተስማማንበት ደግሞ ምክንያት ተሰጣጥተን (ኡዝር ተሰጣጥተን) እንተላለፍ" ይህ ቃል በድንገት ብልጭታዊ ምልከታ ስናየው ጥሩ መስሎ ሊታየን ይችል ይሆናል።
ግን አንደኛ ፦ የመጨረሻውን ሀረግ ስናስተውል ፤
ሁለተኛ ደግሞ ፦ የሚፈለግበትንም መልእክት ስንመለከት ያለበት ግድፈት ጎልቶ ይታያል።
°
🔻አንድነት እጅግ አስፈላጊ ነው የሙስሊሞች አንድነት ፤ ልንጥርለት ልንለፋለት የተለያዩ መስዋእትነት ልንከፍንለት የሚገባ ነገር ነው። ግን ይሄ ሲሆን ደግሞ መንገዱንም ልናውቀው ይገባል ።
°
🔻አንድ ሰው አንድን ህንፃ መገንባት እፈልጋለው ይላል ፤ ይሄን ህንፃ ለመገንባት ሁላችሁም ተባበሩ ይላቸዋል ፤ እሺ ይላል ሁሉም ሰው ይተባበራረል ይመጣል ግን ሰዎቹ መጥተው ምን እንደሚያደርጉ አያውቁም ፤ ይሄ አይነት ትብብር ይፈይዳል? ትብብር ጥሩ ነው ፤ ድር ሲያብር አንበሳ ያስር ሲባል ሰምቷል ተባበሩ ሁላችሁም ይላቸዋል ሁሉም ይመጣል ፤ 10አመት ቢያልፍ ምንም የሚፈጠር ነገር የለም ተቀናጅቶ ማን ምን መስራት እንዳለበት ሲታወቅ ካልሆነ በስተቀር።
°
🔻ይህ ብቻ ሳይሆን ከዚህበፊት ሊሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶችም ሲሟሉ መሆን ይኖርበታል። ለሶላት ሙአዚኑ አዛን ሲል ጥሪ እያደረገ ነው አይደለም? ኑ እና ስገዱ ነው ፤ ግን በውስጥ ታዋቂነት ዉዱዕ አድርጋችሁ ኑ ነው ፤ (አይደለም?) ዉዱእ ያላደረገውንም , መስገድ የማይችለውንም , ያልሰለመውንም ሁሉንም ሰብስበህ ና እና ስገድ ብትለው እና መስጂድ ብታስገባው ምን ይጠቅመዋል? ስለዚህ ለሆነ አላማ ብሎ ሙስሊሞችን ለመመልመል ሲፈለግ ሁሉንም በዚህ መልኩ መሰብሰቡ ልክ ለሶላት ዉዱእ የሌለውንም , ሙስሊም ያልሆነውንም , ሐይድ ላይ ያለችውንም , ሴቱንም , ወንዱንም ደባልቆ ወደመስጂድ መገፍተር እንደመሆን ነው የሚታሰበው። አንዳንድ ዑለማዎች ይሄን ምሳሌ ስለሰጡ ነው የጠቀስኩላችሁ።
°
🔻ታዲያ ይሄንን ይበልጥ ለማብራራት ኢንሻ አሏህ በአጭሩም ቢሆን አንድ ማወቅ ያለብን ነገር አለ ፤ እርስ በእርስ ልንተላለፍለት እና የኔ አቋሜ ነው ይሄም የአንተ አቋም ነው ብለን ያለምንም ውግዘት እና ነቀፌታ #አንድ_ላይ_ተያይዘን_ሊያስኬደን_የሚችል ርእስ ይኖራል። ከዚህ ውጭ ደግሞ አንድ ላይ ሊያስኬደን የማይችል ርእስ ይኖራል። አንተም አቋሜ እኔም አቋምህ የማንባባልበት #መተራረም_የግድ_የሚሆንበት_ርእስ ይኖራል። ይሄ እንግዲህ በሰንጠረዥ የሚዘረዘር አይደለም።
°
🔻ግን ምንድን ነው መሰረቱ ከተባለ ፦ #ዑለማዎች_የተስማሙበት_ግልጽ_ቁርአናዊ_እና_ሓዲሳዊ_አስረጂዎች_የተነባበሩበት_ጉዳይ_ከሆነ_ይህንን_ያለማመንታት_መቀበል_ይገባል። ሓዲሳዊ እና ቁርአናዊ ኣስረጂዎች የተነባበሩበት ዑለማዎችም የተስማሙበት ርእስ ከሆነ ይህንን መጣስ አደጋ ነው።
°
🔻አሏህ ቁርአን ላይ ፦ { وَمَن يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا }ይላል። (አን-ኒሳእ ፥ 115) መልእክተኛውን የሚፃረር ፤ .. መቼ? እውነት ከተገለፀለት በኋላ, መመሪያ ከተገለፀለት በኋላ ፤ ከዚያስ ፡ {وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ} ከሙእሚኖች መንገድ ውጭ ሌላ መንገድን የሚመርጥ ካለ ማለት ነው። #የሙእሚኖች_መንገድ_ማለት_የሶሐቦች_መንገድ_ነው ፤ የታቢዒዮች የታላላቅ የኢስላም ሊቃውንት መንገድ ነው። ከነሱ መንገድ ውጭ ሌላ አዲስ ፈሊጣዊ መንገድ የመረጠ ማለት ነው። ይሄ ቅድም ያልኳችሁን ያብራራል። ቁርአናዊና እና ሒዲሳዊ አስረጂዎችን የጣሰ ፤ ለምን {وَمَن يُشَاقِقِ الرَّسُولَ} ብሏል። መልእክተኛውን ደግሞ የተፃረረ ቁርአንን ተፃሯል ፡ { مَّن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ } ተለያይተው የሚታዩ ነገሮች ስላልሆኑ ማለት ነው።
°
🔻ስለዚህ ነው አሏህ ቁርአን ላይ ፦{ ... أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ } (ኒሳእ ፥ 55) የሚለው። {أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ} የሚለውን "አጢዑ"/(ታዘዙ) የሚለውን ፊዕሉን ከመድገም ጋር ነው አረፍተ-ነገሩን ያስከተለው ፤ {وَأَطِيعُوا أُولِي الْأَمْرِ} አላለም። ምን አለ ፦ { وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ } ፤ "ታቢዕ"/(ተከታይ) ነው ፤ የኛ የበላይ የሆኑ ዑለማዎች እና መሪዎች ቁርአናዊ እና ሐዲሳዊ መመሪያዎችን በገጠመ መልኩ ትእዛዝ ሲያስተላልፉ ብቻ ነው ማለት እሺ የምንለው። ግን አሏህን እና መልእክተኛው የሚለውን ቀጥታ አሏህ እንዲህ አለ መልእክተኛው እንዲህ አሉ ሲባል እጅ መስጠት ብቻ ነው መፍትሄ የለውም። ይሄ ቁርአናዊ ጥበብ ነው የአገላለፁ ስልትም ምክንያት አለው።
°
🔻ሌላው ፡ {وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ} ፡ #ኢጅማዕን መጣስ ነው ቅድም እንዳልኳችሁ። ይሄኛውን አላህ ምን ይላል ፦ {نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ} ፡ የተሾመበትን እንሾመዋለን በተሾመበት ርእስ እንሾመዋለን ፤ ወይም ደግሞ ወደዞረበት እናዞረዋለን ማለት ነው። ጥመትን መርጧል በመረጠው ጎዳና ላይ እንዲጓዝ አሏህ - ሱብሓነሁወተዓላ - መንገዱን ይከፍትለታል ፤ አያስገድደውም። { وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ } ፡ ጀሀነም እናስገባዋለን ፤ { وَسَاءَتْ مَصِيرًا } ምንኛ የከፋች መመለሻ ነች ይላል።
°
🔻ስለዚህ ዑለማዎች የተስማሙበትን አዲስ ነገር መጣስ ፤ ወይ ዑለማዎች የተስማሙበትን ነገር ጥሶ አዲስ ፈሊጦችን ማምጣት አደጋ ነው ፤ ቁርአን እና ሒዲስንም መጣስ እንደዚሁ ማለት ነው። ይህ ግልፅ ቁርአናዊ እና ሒዳሳዊ መረጃ ሲሆን ነው። #በዚህ_ርእስ_ላይ_እየተሻሹ_መሄድ_የለም። ይህንን የጣሰ ሰው አላዋቂ ከሆነ እንዲያውቅ ትምህርት ይሰጠዋል ፤ ጥፋተኛ ከሆነ አውቆ ካጠፋ ይመከራል ፤ ካልሆነ ግን ከሱ ጋራ እየተሻሹ መንገድ ላይ መጓተት የለም ፤ ጌዜ የለንምና ቀጥታ ወደፊት ነው የምናመራው።
°
🔻እረ ባክህ አንተ ና! ምናምን እያልክ ሁል ጊዜ .. መስጂድ ለምሳሌ ሶለተል ጀማዓ አንድ ሰው አልመጣም ሲልህ እሱን ለማምጣት ብለህ እየተጓተትክ ሶላተል ጀማዓ ታሳልፋለህ? አላማው ምንድን ነው ሶላተል ጀመዓ እሱን የምታመጣበት? እሱ ሶላተልጀማዓ እንዲመጣ ብለህ አብራችሁ ሁለታችሁም (እሱ ብቻ ሳይሆን ማለት ነው) ሁለታችሁም ጀማዓ ሶላት ታሳልፋላችሁ? ስለዚህ ስትጎትተው የማይመጣልህ ከሆነ ከሱ ጋራ እየተሻሸህ መንገድ ላይ እየተደባደብክ አታሳልፍም አይደል? እንደዚያ ነው ነገሩ።
🔻ታላቅ የሙሐደራ ፕሮግራም
✂️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም
✨ርዕስ፦ "በወንድማማችንት ጥላ ስር" ቁጥር2
📌በኡስታዝ ሱለይማን አብደላህ (ሐፊዘሁላህ)
📎የፊታችን እሁድ መጋቢት 05-2013 አስር ሰላት እንደተገባደደ
✂️አድራሻ፦ ሎሚ ሜዳ ኹበይብ መስጂድ
t.me/httplailahailelah
◼️ራዚቃችን አሏህ ነው
🔻ኑሮ ተወዶም ሳይወደድም የሚረዝቀን አሏህ ነው። ስጋት አይግባን .. ከኛ የሚጠበቀው ሰበብ ማድረስ ነው።
{ ۖ نَّحْنُ نَرْزُقُكَ ۗ }
[ እኛ እንረዝቅሀለን ] (ጧሃ ፥ 132)
t.me/ibnyahya777
#አጫጭር_የረመዷን_ፈትዋዎች 1⃣
📋#ለሞተ_ሰው_ቀዷእ_ማውጣት
❇️ከዛዱልመዓድ ፈታዋ ቁ.39 ላይ የ3 ኛው ጥያቄ ምላሽ.
▪️ጥያቄ ፡
•
3⃣.እናቴ በህመም ምክንያት አንድ አመት ረመዷን አልጾመችም ፤ አላህ ይዘንላትና ወደ አኼራ ሄደች ፤ አሁን እኔ ምን ላድርግ?
•
▪️መልስ ፡
•
አላህ እንዲያዝናላት ፣ ወንጀሏን እንዲምራት እና ለእናንተም ትእግስት እንዲሰጣችሁ አላህን እንለምነዋለን።
°
🔻#በዛው_ህመሟ_ሳትድንና_ደህና_ሆና_መፆም_የምትችልበት_ሁኔታ_ላይ_ሳትሆን_ከሆነ_የሞተችው_ምንም የለባትም። ፆምም የለባትም ፤ የምግብ ከፋራም የለባትም። #ጤናዋ_ተስተካክሎ_መፆም_የምትችልበት_ሁኔታ_ላይ_ከመሆኗም_ጋር_ሳትፆም_ዘግይታ_የሞተች_እንደሆነ_ሁለት_አማራጭ_አለ ፡
1ኛው.ልጆቿ ወይም ቤተሰቦቿ መፆም ይችላሉ። ይህን ካላደረጉ (2ኛ).ለእያንዳንዷ ቀን አንዳንድ ሚስኪን ያበሉላታል።
°
እነሆ ነብያችን - ዐለይሂሶላቱ ወሰላም - [" من مات وعليه صيام صام عنه وليه "]
[ ፆም እያለበት የሞተ ሰው ቤተሰቦቹ ኃላፊዎቹ ይፆሙለታል። ] ብለዋል. (ቡኻሪ ፥ 1816 / ሙስሊም ፥ 1935).
°
ለእያንዳንዱ ሚስኪን 2ኪሎ ተኩል እስከ 3ኪሎ በሃገሩ ሰዎች የሚመገቡትን ምግብ መስጠት ይቻላል። 30 ቀን ከሆነ ያልፆመችው 30 ሚስኪን ፤ ከ30 ቀን በታች ከሆነም ደግሞ ባልፆመቻቸው ቀኖች ልክ ለሚስኪን መስጠት ይቻላል። መስጠት የሚከብድ ከሆነ ቤት ጠርቶ ለእያንዳንዱ ቀን አንዳንድ ሚስኪን አጥግቦ ማብላት ይቻላል። ሰላሳውንም አንድ ላይ ሰብስቦ ቢያበሉ ችግር የለውም ፤ በተወሰነ መልኩ ከፋፍለው ቢያበሉም ችግር የለውም።
°
ቤት ጠርቶ ማብላት ላይ በተወሰነ መልኩ "ኺላፍ"/(የዑለማዎች ልዩነት) አለበት። ለየቲሙ ሐቁን መስጠቱ , "ሚልኩ"/(ንብረቱ) ማድረጉ የተሻለ ነው። ማብላቱ ለሚስኪኑ ወይም ለሚያበሉ ሰዎች የሚቀልበት ሁኔታ ካለ የፈቀዱ (ወይም) ይቻላል ያሉ ሊቃውንት አሉና ምሳ ወይም ራት ቤት አጥግቦ ማብላት ይቻላል።
°
🔻የዚሁ ጥያቄ መጨረሻ ላይ "ስንት ቀን እንደፆመች ፤ ስንት ቀን እንዳልፆመች እርግጠኛ አይደለሁም" የሚል ቃል አለበት። #ሟቹ_ስንት_ቀን_አንዳልፆመ_ካልታወቀ #መገመት_ነው ፤ ምን ያክል ቀን ነው የታመመው? በሽተኛ ሆኖስ የፆመበት ቀን አለ ወይ? የሚለውን ለሱ ቅርብ ከሆኑ , ከበሽተኛው ቅርብ ከሆኑ ሰዎች ማጣራት ነው። 10 ቀን ነው 12 ቀን? የሚል ጥርጣሬ ካለ 12 በሚለው ሄዶ የ12 ቀን ፆም መፆም ፤ አልያ ደግሞ 12 ሚስኪን ማብላት ነው። 20 (ቀን) ነው 25 (ቀን)? ጥርጣሬ ካለም 25 (ቀን) ማድረግ ነው። ከግምታችን ከፍተኛውን ቁጥር በመያዝ ጥንቃቄ ከማድረግ ጋር በግምት ቀዷእ ማውጣት ይቻላል።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📕ምንጭ ፦ ከኡስታዝ አሕመድ አደም የዛዱልመዐድ ፈታዋ ቁ.39 ኦዲዮ ላይ የተወሰደ.
✍️አደም
ኤዲት የተደረገው በአቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn Yahya Ahmed
📆እሮብ ረጀብ 13/1440ሂ. # መጋቢት 11/2011.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦/channel/ibnyahya7
✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ ፦ https://www.facebook.com/ibnyahya777/
◾️#ልዩ_አጫጭር_የረመዷን_ፈትዋዎች
🔻የረመዷን ወር ሊገባ የተወሰኑ ቀናቶች ይቀሩታል። ይህን የተከበረ ወር በእውቀት ላይ ሆነን እንድንፆመው ያስችለን ዘንድ በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ከሚተላለፈው የዛዱል መዓድ ፈታዋ ላይ ረመዷንን ብቻ የሚመለከቱ ፈትዋዎችን በመምረጥ ከ2 አመት በፊት የለቀቅናቸውን 43 ፈትዋዎች በድጋሜ በአሏህ ፍቃድ ከአሁኑ ሐሙስ ጀመሮ ለሳምንት 3ቀን ማለትም ሐሙስ ፣ ጁሙዓ እና ቅዳሜ ለመልቀቅ ተዘጋጅተናል።
°
🔻ፈትዋዎቹ ለሁላችንም በሚመች መልኩ በድምፅም በፅሑፍም በፌስቡክ ፣ በቴሌግራም ፣ በዋትሳፕ እና በዩቲዩብ አድራሻዎቻችን ላይ የሚለቀቁ ይሆናሉ። ጊዜ ካገኘን ጥያቄና መልስ ለማዘጋጀትም እንሞክራለን። ፈትዋዎቹን በማንበብ እና በማዳመጥ እንደዚሁም ለሌሎች ሼር በማድረግ እንድትዘጋጁ ጥሪ እናቀርባለን።
/channel/ibnyahya7
°
🔻አድራሻዎቻችን በድጋሜ ለማስታወስ ያክል ፡
1⃣.Facebook
https://www.facebook.com/ahmed.ibnyahya https://m.facebook.com/ibnyahya7777
ወይም
https://m.facebook.com/ibnyahy7
_
2⃣Telegram
°
/channel/ibnyahya7
እና
/channel/ibnyahya777
_
3⃣.WhatsApp
ግሩፕ ቁ.6
https://chat.whatsapp.com/20ZCnHJCIkt6mH796urSLO
°
ግሩፕ ቁ.5
https://chat.whatsapp.com/CNutaQ96uoL0xmK1MBLe3Y
°
ግሩፕ ቁ.4
https://chat.whatsapp.com/4vvq5pC2j3fBGWFuHR1VCJ
_
ግሩፕ ቁ.3
https://chat.whatsapp.com/8bsijWsuGIZ0mYStCjvAG1
_
ግሩፕ ቁ.2
https://chat.whatsapp.com/AvIFk49J1B04GuDSQ07eev
_
ግሩፕ ቁ.1
https://chat.whatsapp.com/7yuu7yUnUjvIW6PEaG4THA
°
🔽4️⃣.Youtube
https://www.youtube.com/channel/UC5sNVfGTc3VvlJbvl_dUhOA
____
©ዲን መመካከር ነው - الدين النصيحة
✍አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን የሕያ @Ibn yahya ahmed
📆እሁድ ረጀብ 23/1442ሂ. # የካቲት28 /2013 # March 7/2021.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣ጆይን ያድርጉ፦/channel/ibnyahya7
✅ላይክ ያድርጉ ፦ https://www.facebook.com/ibnyahy7/
▪️የፆም ማብራሪያ ~ 2ኛ እትም
🔻የኡስታዝ አሕመድ አደም የ"መንሀጁ-ሳሊኪን" የድምፅ ፋይልን መሰረት በማድረግ በወንድም አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን የሕያ የተዘጋጀው የፆም ማብራሪያ የተሰኘው መፅሐፍ ዳግም ወደገበያ ተመልሷል።
🏴አድራሻ ፡ መርካቶ አንዋር መስጂድ አትተውባ መክተባ ላይ ያገኙታል
t.me/ibnyahya777
◼️ቢድዓ
🔽" ቢድዓ በነብያችን - ﷺ - ጊዜ የለም ፤ ግን ስለቢድዓ ሲያወሩ ፊታቸው ይለዋወጥ ነበር። ምክንያቱም ሙስሊሙን ህዝብ የሚበታትን ትልቅ ነቀርሳ ስለሆነ ነው። " (ሸይኽ ባሲጢ رحمه الله / ኡሱሉል ኢማን ክፍል 2 ደርስ ላይ የተወሰደ).
t.me/ibnyahya777